You are on page 1of 2

የተከበሩ

የተከበሩ
ውድ የዕለቱ ተመራቂዎች እና የተመራቂዎች ቤተሰቦች
የማሕበረሰብ ተወካዮች
ተጋባዥ እንግዶች
እንዲሁም የኮሌጁ ሃላፊዎችና ሠራተኞች
ውድ ተመራቂዎች የምረቃ በዓል ላይ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁልን በተመራቂዎችና በቤተሰቦቻቸው ስም
ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ሁላችሁንም እንኳን ደህና መጣችሁልን እላለሁ፡፡

ከሁሉ አስቀድሜ ቀድሞ የከተማ ልማት ሠራተኞች ተቋም ተብሎ ይታወቅ የነበረውና ከአሁን ጀምሮ ግን “ብርሃን
ሶሻል ዲቨሎፕመንት ኮሌጅ “በብርሃን ሶሻል ዲቨሎፕመንት ትሬይኒንግ ኤንድ ኮነሰልቴሽን ሴንተር” ስር መቋቋሙን
ይፋ እያደረግኩ ኮሌጁ በአሁኑ ጊዜ በኮሚኒቲ ሰርቪስ ወርከ ከደረጃ 1-4 ያሰለጥናል፡፡
ውድ ተመራቂዎች የምረቃ በዓል ላይ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስለተገኛችሁልን በተመራቂዎችና በቤተሰቦቻቸው ስም
ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ ሁላችሁንም እንኳን ደህና መጣችሁልን እያልሁ በዘርፉ የሚሰጠውን የሥልጠና መርሀ
ግብር ከብዙ አድካሚ ጉዞ በኋላ አጠናቃችሁ የዛሬው ፍሬያማ ውጤት በመብቃታችሁ የተሰማኝን ልባዊ ደስታና እርካታ
በሥራ ጓደኞቼና በራሴም ስም እየገለጽኩ ተመራቂዎችንና የተመራቂዎችን ቤተሰቦች እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት
እወዳለሁ፡፡
ሀገራችን ከድህነት ለመውጣት በመታደርገው ትግል ውስጥ ተሳታፊ በመሆን የበኩላቸሁን አስዋጽኦ አንደምታደርጉ
ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡
ከአሁን በፊት በሙሉ በተቀነባበረ ዘዴ የከተማ ልማት ፕሮጀክት ላለፉት 25 ዓመታት ደህንትን በመቀነስ ዙርያ ጥረት
ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ይም ፕሮጅት ቀጠይነት አንዲነረው የተገኑትን ልምዶች ተግባራው ለማደረግ የ
ትምሀርትና ስልጠና ኮሌጅ ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑን በገንዘብ ነበር ይህ ኮሌጅ የተቋቋመው፡፡
ኮሌጃን የበተቀነባበረ ዘዴ የከተማ ልማት ፕሮጀክት ተግባር መነሻ በማድረግ እና ወደ ንድፈ ሀሳቡ ከተግባር ጋር
አጣምረው በመማር በሌሎች ተመሳሳይ የድህነት ችግር ባለባቸው አካባቢዎች እንዲገለገሉበት ለማሰቻል የትምህርት
ፕሮግራም ዘርግቶ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ብርሃን ሶሻል ዲቨሎፕመንት ኮሌጅ በዚሁ አቅጣጫ
በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፣
ኮሌጃቸን እስካሁንም ለስምንት ባለፉት ዓመታት ለ 8 ኛ ጊዘ ያሰመረቀ ሲሆን በዚህ ዕለት ለ 9 ኛ በተለያዩ ደረጃ
የሰለጠኖትን ሰልጣኖች በማሰመረቅ ላይይገኛል፡፡የአሁን የኮሚኒተ ሰርቪስ ወርክ ትምርት ተማራቂዎች 33 ሲሆኑ
ባለፉት ዓመታት በበመሰረታዊ ኮመፒተር በሶሻል ደቬከሎመንት ጭመር እስከአሁን ድራስ 398 ተማሪዎችን አሰልጥኖ
አስመርቋል፡፡

ይህንን ኮሌጅ ሰልጣኖችን በንድፍ ሀሳብ ብቻ ሰይሆን ወደ ተላያዩ ግበርሰናይ ደርጅቶች በመላክ የመስክ ጉብኝትና
የትብብር ስልጣና የስራ ዓላም ጋር አጣምሮ ዕውቀትና ክህሎት ለማስጨበጥ ይጥራል፡፡

ይህ ማሰልጠኛ ኮሌጅ አሁን አለበት ደረጃ የደረሰው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ ድርሻ ባላቸው መንግሥታዊና
መንግሥታዊ ባልሆኑ አካላት ያላቋረጠ ድጋፍና ትብብር፣ እንዲሁም በተለያዩ ዕርዳታ ለጋሾች የገንዘብ ድጋፍ መሆኑን
በዚሁ አጋጣሚ እየገለጽሁ በእናንተ ፊት በማዕከሉና በዕለቱ ተመራቂዎች ስም ልባዊ ምሥጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡

የዕለት ተዕለት ሥራችንን በምናከናውንበት ወቅት ትክክለኛውን አቅጣጫ በማሳየትና ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት በኩል
የአዲስ አበባ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ጽ/ቤት
የተጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ይህ ድጋፋቸውና ክትትላቸው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተስፋ እያደረግሁ
እስካሁን ለሰጡንና ወደፊትም ለሚያደርጉልን ዕገዛ ከወዲሁ ምሥጋናዬን አቀርባለሁ፡፡

ይህ ኮሌጅ ባለፉት ጥቂት አመታት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በብሔራዊ ደረጃ በሚደረገው ምዘና ወይም COC ከ 6
ጊዜ በላይ አሰመዘኖ በአማካይ ከ 90 በመቶ በላይ በማለፋቸው ውጤቱ እጅግ አበረታች ሆኖ ተገኝቷል፡፡
በተጨማሪም እአስካአሁን ባለው መራጃ መሰረት ከተመረቁት ከ 90 በመቶ ተመራቂዎች ተቀጥረው በስራ ዓለም
ላይ የሚገኑ መሆኑን ሁላቸን ደስ ሊለን ይገባል፡፡ አንድአንድ ጊዜም ሰልጣኞችን ለመቅጠር የሚፈልጉት ደርጅቶች በቂ
ሰልጣኞን ማግነት ያልቻሉ መሆናቸውን እናስታውሳለን፡፡ ወደፊትም ከድርጅቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠርና የተሻለ
ጥረት በማድረግ ይህ የተጀመረውን አበረታች ሁኔታ የምንጠቀበት መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለማሳወቅ እወዳለሁ፡፡
ደርጅታቸን አ.ኤ፣አ ከ 2013 ጀምሮ በኢትዮጵያ ነዋሪዎች በጎ አድራጎት ማህበርነት እነዲመዘገብና ፍቃድ አግኝቶ
እንዲቀጥል ላቀረብነው ጥያቄ ድጋፍና እገዛ ላደረጉልን ለሚከተሉት ተቋማትና ግለሰቦች በዚህ አጋጣሚ ልባዊ
ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለሁ፡፡

1) የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ኤጄንሲ


2) የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጄንሲ
3) ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ
4) ለፋይንና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ

ውድ ተመራቂዎች፣
እንኳን ለዛሬው ዕለት አደረሳችሁ በማለት የተሰማኝን ደሰታ በድጋሚ እየገለጽኩ ሁላችሁም ከሥልጠናው ባገኛችሁት
ዕውቀትና ክህሎት በመታገዝ በምትሰማሩበት ሥራ ውስጥ የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት እንደምታውሉት ያለኝን
ጽኑ እምነት እገልጻለሁ፡፡ በተጨማሪም ለዚህ እንድትበቁና ጥረታችሁና ድካማችሁ ውጤታማ እንዲሆን ከጎናችሁ
ሳይለዩ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ሲረዷችሁ የቆዩትን መምህራን፣ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በዚሁ አጋጣሚ
ለማመስገን እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም በሥራ ዓለም በምትሰማሩበት ወቅት ከተሞክሮዎቻችሁ እየተማራችሁ በስልጠናው ወቅት ያገኛችሁትን
ዕውቀትና ክህሎት ይበልጥ እያዳበራችሁ ራሳችሁንና ህብረተሰቡን የምትጠቅሙ ዜጎች እንድትሆኑ ያለኝን ልባዊ ምኞት
እየገለጽኩ ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳችሁ እላለሁ፡፡

You might also like