You are on page 1of 1

ጥሪ ለቀዳሚ ወደኀሪ

ውድ የተከበራችሁ ከምንም በላይ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠራችሁ እኅትና ወንድሞቸ ለጤናችሁ እንደምን አላችሁ።የት እንደምንተዋወቅ
በባለፈ መልእክቴ የተወሰናችሁትን ለማወቅ እድሉን አገኝቻለሁ ዛሬ ግን ለታላቅ ድግስ ጥሪ ለማዘጋጀት እና ለተግባራዊ የቤትሥራ
አንድነት በዚህ ማኅበራዊ ሚዲያእኔን የምታውቁኝ ከእኔ በፊት፣ከእኔ ጋር እና ከእኔ በኋላ የተመረቃችሁና የምትመረቁ የወሎ ኮምቦልቻ
እኅትና ወንድሞቼ ለእኛም ለሌሎችም ተራፊ መሆን የሚችል ሥራ ለመስራት ስለታቀደ ኮ/ቻ ግቢ ከተመሰረተ ጀምሮ የተመረቃችሁና
የምትመረቁ የት ናችሁ?በማለት ለመልካም ኑሮ ለሀገር ለወገን ተራፊ እና ዘመን ተሻጋሪ አሻራ ታስቀምጡ ዘንድ የክብር ጥሪየን
አስተላልፋለሁ።ዛሬ ዛሬን ብቻ ሁኖ እንዳያልፍና ያሳለፍነውን ጊዜ እንዳንረግም ዛሬያችንን ነገ ነጋችንን የህልማችን የመልካም ምግባራችን
መፈጸሚያና መጻፊያ ሰሌዳ አድርገን ለትውልድ እናስቀምጥ ዘንድ እናንተ አስፈላጊ በመሆናችሁ ዛሬን የት አላችሁ?በምግባር በትምርቱ
ስትረዱን ስታስተምሩኝ የነበራችሁ አንጋፋወች ዛሬ የት ናችሁ?ያነን መረዳዳት መተሳሰብ ከግቢ ወጥተንስ ትልቅ ደረጃ ማድረስ
አይቻልምን?እሽ የት ናችሁ? ለብቻ ትግሉ የግድግዳ ግፊ አልሆነባችሁምን?ለእኔ የተወደደ የኑሮ ዘይቤ እናንተጋር የለምን?በልዩ ምክንያት
መርዳት ባለመቻላችን ያጣናቸው ወንድሞችና እኅቶች የሉምን? እሽ የት አላችሁ? ያኔ በጽዋ መርሀግብር እኔ አለሁ የመድኃኒአለም ወዳጅ
ቢያደርሰኝ ቢያደርሳችሁ ......ብላችሁ ጽዋውን ለማን ሰጣችሁት? የትስ ናቸው? እኛ ጋር የተወደደ ኑሮ ሥራ ለሌላቸው ቤተሰብ ጓደኛ
ለሌላቸው ምን ያክል ይከብድ ይሆን? እኛስ እስከመቸ በድጎማ ኑሮ ከእጅ ወደአፍ ስንመኝ እንኖራለን? ሙሉ አካል ይዘን መስራት እና
ማቀድ ለምን ግድግዳ እንደመግፋት ከበደን?እሽ እስከመቸ የደሞዝ ቀንና እስኬሉ እስከሚጨምር በምኞት እንኖራለን? ግን አላችሁ
አደል?.....በዚህ ጥሪየ አናንተን ስጠራ ሀገርንና ትውልድን በማሰብ ነውና ኑኑኑኑኑኑ!!! ብዙ እውቀት ይዛችሁ የጠፋችሁኝ ኑ!ኑ!
የያዝነውን የአለም አምድ ይዘነው መቃብር ሳንወርድ አሻራ ለትውልድ እናስቀምጥ ለዚህም የተደገሰ ድግስ ተዘጋጅቷል ሳይቀዘቅዝ
እንመገበው ዘንድ የአክብሮት ጥሪን የት ናችሁ? ብያለሁ።ጥሪውም ያለእናንተ ቢበላ አይጣፍጥምና ለቅመማው ባለሙያ ስለሆናችሁ
አሁኑኑ የት ናችሁ? ለፍቅር አምባዋ ወሎ ኮ/ቻዎች ላልተገደበው የሥራ ፍቅራችሁ መንፈሳዊ ጥሪየን አስተላልፋለሁ። ታዲያ ወሎ ኮ/ቻ
ነበሩ ወይስ ነዎት? ታዲያ ኑ እንጂ ዛሬን ሰርተን ነገን እናሳምር ይህን አታውቁ ይሆን"ጨው አልጫውን እንደሚያጣፍጠው እርስዎ
መኖርዎ መምጣትዎ ለብዞች ኑሮ ማጣፈጫ መሆንዎን?"ያውቃሉኮ ለምን ቢሉኝ ወሎ ኮ/ቻ ነዋ የተመረቁት።ስለዚህ ሳትንቁና ሳትወዛገቡ
ኑ!! እየመጡ ከሆነ የዚህን ጥሪ ማክበርዎን በላይክና ኮመንት ካደረጉ በኋላ ሙሉ ጽሑፉን ኮፒ አድርገው በፈጠሩት የማህበራዊ
ሚዲያዎት ያጋሩ እያልኩኝ ለመልስዎ የድግሱን ሆቴል በውስጥ መስመርዎ አድራሻውን የምልክላችሁ መሆኑን እገልጻለሁ።ኑ! ኑ! ኑ! ኑ!
ኑ! ብያለሁ እርስዎም ድጋፍወን በጥሪ ይመልሱልን።

ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተና ቤተሰብዎ ጋር ይሁን።

You might also like