You are on page 1of 4

ከብዕረኞቹ የተላከው ደብዳቤ 16/10/2015

የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ አንድነት ገዳም መነኮሳት ፦

አደራ በእመቤት በመዳኒዓለም ይዣቸዋለሁ እስከ መጨረሻው ያንቡትና ለሌላው ያጋሩት።

ይህ የማይደገም ከቅዱሳኑ የተላከ ከበርሃ የመጣ ፈቃደ እግዚአብሔር ያለበት ማንም ሰው መስጠት ብቻ አይደለም

ለሚሰጡት ቅን ልቦች ያደርስ ዘንድ share share ማድረግ ያለበት የበረከት ስራ ።

እመኑኝ ይህ የኢትዮጰያ ትንሳኤ የማብሰሪያ ዋዜማ የሆነ የእኛንም ሕይወት የሚቀይር ከእግዚአብሔር መልስ

የምናገኝበት የማይደገም ዕድል ነው የፈለገ ሳይሆን የተፈቀደለት እርሱ ከእዚህ በረከት ይቀበላል እርሱ ይፈቅድልን

ዘንድ ስለ እዚህ ነገር እንፀልይ።

በሕይወታችሁ ሰማታችሁት የማታውቁት ገዳማት ናቸው ገዳማቱ በዳውንት አውራጃ የሚገኙ ሲሆን በእግር ከ 3

እስከ 8 ሰዓታት በእግር የሚያስኬድ መንገድ ያላቸው ጭው ያለ በርሃ ውስጥ ይገኛሉ።

በነብር ፤በዘንዶ የሚጠበቁ በደመና የተከበቡ ቅዱሳን መላዕክት እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው

የሚታዩበት መካነ ቅዱሳን ናቸው አንዳንዶቹ ለማመን የሚከብድ አስደናቂ ተአምራት የተፈፀመባቸው እስከ አሁን

በአለማወቃችን እንድንፀፀት እንድንቆጭ የሚያደር ታሪክ አላቸው።

ሁሉም ጥንታዊያ ገዳማት ናቸው ብዛታቸው ደግሞ 87 ገዳማት ናቸው ብዙ ቅዱሳን ተሰውረውበታል ስጋ ለበስ

የሆኑ ቁጥራቸው ከመላዕክት የተደመሩ በአንበሳ ላይ የተቀመጡ ደመናን ጠቅሰው የተሳፈሩ ባህር ከፍለው የተሻገሩ

አጥናፈ ዓለማትን የዞሩ ቅዱሳን ገዳሞቹን ገድመውታል።

የሁሉንም ገዳሞች ታሪክ ለመተረክ ጊዜ አይበቃም እንጂ ባወራው ብፅፈው እጅን በአፍ የሚያስጭን አግርሞት

የሚጭር አጀይብ የሚያሰኝ ድንቅ አስገራሚ ነገር አሳያችሁ ነበር ሁሉን እንዳንተርክ ጊዜ ያስጥርብናል እንዳለ

ቅዱስ ጳውሎስ።

በእነዚህ ገዳሞች ኢትዮጰያን አይደለም ዓለምን የሚያስምር የፀሎት አይል ያላቸው መነኮሳት ይበዙበታል ዳዋ

ጥሰው አመድ ነስንሰው ዲንጋይ ተተርሰው ግርማ ሌሊቱን ድምፀ አራዊቱን ታግሰው ለእኛ ለልጆቻቸው በዋሻ

በገደል በሰርጥ በጢሻ ውስጥ ወድቀው ይለምናሉ።

ሆዳቸው ከጀርባቸው ተጣብቆ አጥንታቸው አንድ ሁለት ተብሎ ተቆጥሮ ጭብጥ ቆሎ ቆርጥመው የቆሸሸ

የደፈረሰ ውሃ ተጎንጭተው የሚለብስቱ አጥተው ድሪቶ ደርበው አመድ ላይ ተከባለው ለራሳቸው ሳይሆን

ለሕዝባቸው ይፀልያሉ።
የከተማው መነኩሴ ጃቦ በጨበጠበት ቦርጭ ባወጣበት ካባ በደረበበት ላይ ደርበን ደራርበን እንሰጣለን ቤት መኪና

አላቸው ድግስ ደግሰን ያማረ የጣመ እናበላቸዋለን ግን እንደ በርሃ እንዳሉት መነኮሳት ለእኛ አይፀልዩልንም

አያነቡም አያለቅሱልንም ።

ያለምንም ክፍያ ርሀብ እየፈጃቸው የፀሐይ ሐሩር እያቃጠላቸው ብርዱ እየወጋቸው ምንም ያላደረግንላቸውን

እኛን በመንፈሳዊ መነፅር ተመልክተውን አብዝተው ይፀልዩልናል እኛ ግን ለእነርሱ ምን አደርግንላቸው ? ምንስ

ሰጠናቸው ? ምንም።

ዛሬ ግን ፊት ለፊታችን ቆመው ይለምኑናል በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት ሕዝቡ በጦርነት በርሃብ ተቀጥቶ የሚበላው

የሚጠጣው አጥቶ በመቸገሩ ገዳማት ረዳት በማሳጣት እንዲዘጋ ተደርገዋል።

ክረምት በመጣ ቁጥር የደም ግብር የለመደው ዲያብሎስ ዛሬም ሕዝቡን በችግርና በስጋት እንዲኖር አድርጎታል

በርካታ ገዳማት ወድመዋል መነኮሳት ተገለዋል ገዳማት ተፈተዋል የምንሰማ የምናየው ሁሉ ጨርቅ አስጥሎ

ያሳብዳል።

በእዚህ የተነሳ በሰሜን ወሎ በዳውንት አውራጃ የሚገኙ እንኳን ለመዘጋት አይደለም አንድ ቀንም ቢሆን ስብሀተ

እግዚአብሔር የማይስተጓጎሉባቸው ገዳማት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ተዘግተዋል።

ይህ የሆነው 4 መሰረታዊ ችግሮች ባለሟሟላታቸው ነው እነርሱም

1ኛ ጧፍ

2ኛ እጣን

3ኛ ዘቢብ

4ኛ ሻማ ብቻ ነው የሚፈልጉት።

እኛ ለጉባዬ ማድመቂያ ለቀረፃ ፤ለለቅሶ ፤እንዲው ዝም ብለን የምናበራውን ጧፍ የገጠሪቱ ገዳማት አጥተውት

ተቸግረው ገዳማቸው እንዲዘጋ ሆኗል እኛ መጫወቻ ያደረግነው ጧፍ በርሃ ያለት ገዳማት ግን የወርቅ ያህል

ተወዶባቸው ተቸግረዋል።

በከተማ ያሉት አቢያተ ክርስቲያናት በሰለት የሚገቡት ጧፍ እጣን ዘቢብ ሻማው መልሰው በጫረታ ለነጋዴ

ከሚሸጡት ምን አለ ቀንሰው ለገጠር አቢያተ ክርስቲያናት ቢልኩ ብዬ ተመኘው እኛም አንለምንም ነበር ሆድ

ይፍጀው ዝም ማለት ይሻላል።

እግዚአብሔር ሰው አለው እንደ አገልጋዮቹ አፊኒና ፊናስ ያሉ ምናምቴ መቅደሱ ውስጥ ቢኖሩም እንደ ሳሙኤል

ያለም እግዚአብሔር ሰው አለው ደብቆም ቢሆን በመቅደሱ ያሳድጋል።


የሰማይ ቤታችን እግዚአብሔር እንዲያዘጋጅልን ፤በወርቅ መዝገብ የሚፃፍ ደግሞም የኢትዮጰያን ትንሳኤ እናይ

ዘንድ ከታሰርንበት እስራት እርሱ ይፈታን ዘንድ ከሰማይ አምላክ የመጣችሁን ትዕዛዝ እንፈፅም ።

ማንም ኦርቶዶክስ የሆነ አማኝ ይህን በረከት እንዳያልፈው ስል በትህትና እጠይቃለሁ እግዚአብሔር በገንዘብ ላይ

የሾማችሁ ሳሰስቱ ስጡት በተረፈ የአቅማችሁን ያህል መርዳት በምትችሉት ሁሉ እርዱ እርሱ ዋጋችሁን

ይሰጣችዋልና።

87 ገዳማት ተዘግተዋል እነዚህ ገዳማት የወር አይደለም የዓመት የሚያስፈልጋቸው እጣን፣ ጧፍ ፤ዘቢብ ፤ሻማ

በመግዛት እናስከፍታለን ገዳማት አይዘጉም ማርያም እኛ እያለን በፍፁም አይደረግም።

የማሰባሰብ ዘመቻው ተጀምሯል በመላው ዓለም ያሉት ሁሉ ይሳተፉ ዘንድ ለሁላችሁ ዕድሉን አመቻችተናል

በደንብ አንብቡት መመሪያውን ፦

ሕጋዊ ፈቃዱን አውጥተናል የገዳማት ዝርዝ በፎቶ ላይ መመልከት ትችላላችሁ

ይህ ያስፈፅሙ ዘንድ የተቋቋሙት ኮሚቴ

1 ኛ ፅዮን ተካበ ፦ 09 12 68 5157

2 ኛ ፍሬ ፦ 09 91 45 66 77

3 ኛ ፦ ሲሳይ በቀለ ፦ 09 11 38 09 46

4 ኛ ፦ ተስፉ ፦ 09 62 19 51 62

5 ኛ ፦ ዳዊት ፦ 09 32 10 38 51 ናቸው ።

እጣን ፤ ጧፍ ፤ ዘቢብ ፥ሻማ መሸጫ ሱቆች ።

መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን፦

1 ኛ ታክሲ ተራ ጋር የመጀመሪያው ሱቅ ዳንኤል ንዋይተ ቅዱሳን መሸጫ።

2 ኛ ፦ የራጉኤል ትምህርት ቤት አንደኛ ፎቅ

09 13 02 04 12 ሳሚ ንዋይተ ቅዱሳን መሸጫ ።

ሳህሊተ ምሕረት ቤተክርስቲያ ፦

ፍሬ ሕይወት ንዋይተ ቅዱሳን መሸጫ 09 42 00 00 13 ደውሉ።

ለሙ መዳኒዓለም ጋርመት ጀሞዎች አካባቢው ፦

ለሙ መዳኒዓለም ሰንበት ትምህርት ቤት ንዋይተ ቅዱሳን መሸጫ

09 00 56 66 01 ሀና እንዲሁም 09 14 46 43 01 ገብሩ ።
በተመቾት በአቅራቢያ ስለ ቅዱሳኑ ለገዳማቱ ስትሉ የሚያስፈልጉትን ገዝተው አሳስረው ከስመ ክርስት ጋር በሱቁ

ይኑሩልን።

በአካውንት በገንዘብ መስጠት እንፈልጋለን ካላችሁ የተቋቋመው ኮሚቴ ታማኝ ቅን ልጆች እንኳን

የእግዚአብሔርን ሊነኩ ራሳቸው እንኳን በበጎ ስራ የሚሳተፉ ብርቄ እህቶቻችን አካውንት ከፍተዋል።

አካውንት 10005530 51952 ንግድ ባንክ።

የአካውንቱ ስም ፍሬ ወይኒ ጌታሁን እና ፅዮን ተካበ በሚለው ይላኩ።

በፈለጉት መንገድ መጠቀም ይችላሉ በጣም ፈጣን የበረከት ስራ ነው ገዳማዊያኑ አዲስ አበባ ናቸው በፍጥነት

ስጡንና ይዘን እንሂድ ብለዋል ክረምት ነው በዛ ላይ የማይቀር ጦርነት አለና ቀድመን ከዋሻችን ብለዋል ፍጠኑ።

ጥብቅ ማሳሰቢያ ፦ ማንኛውም ሰው በፈለገው መንገድ ከረዳ በኃላ ስመ ክርስትናውን በብጣሽ ቢፅፍ አንቀበልም

በስርዓት አንድ ሉክ ገዝታችሁ ከነ ቤተሰባችሁ በስርዓት ፅፋቹ ከገዛችሁት ዕቃ ጋር አስቀምጡልን ።

2 ኛ በባንክ የምታስገቡ በቴሌ ግራም ከነ ሙሉ ቤተሰባችሁ ስመ ክርስትና ላኩልን በላይ በተጠቀው ስልክ ግዴታ

ደውላችሁ አልያም በቴሌ ግራም ያሳውቁ።

የእያንዳንዳችሁ ስመ ክርስትና ተባዝቶ ለ 87 ቱ ገዳማት የሚሰጥ ስለሆነ በጥንቃቄ እንዲነበብ አድርጋችሁ ፃፉ ።

በአጠቃላይ ያረውን መረጃ ለማወቅ ፦

ለእኔ ደካማ ወንድማችሁ ላኩልኝ

አክሊሉ ተፈሪ 09 13 70 49 68

Aklilu Teferi 09 13 70 49 68 በቴሌ ግራም በኢሞ በቀጥታም አስተናግዳችዋለሁ።

በእኛ ትውልድ ማንም ያልፃፈው ሰማያዊ ስራ በእጆቻችን ፅፈን ለልጆቻችን እናወርሳቸዋለን።

ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ የሆነ ባለማዕተብ ታዋቂ ፔጆች የማህበራዊ አንቂዎች በሙሉ ለሁሉ ታደርሱ ዘንድ በቅዱሳኑ

መነኮሳቱ ስም እንለምናቸዋለን ።

መልካም ዕድል የቅዱሳኑ አምላክ ያስፈፅመን።

You might also like