Professional Documents
Culture Documents
Family Toolkit Amharic ADA
Family Toolkit Amharic ADA
ከ 8ኛ ወደ 9ኛ ክፍል ሽግግር እና
ከዚያ በላይ የቤተሰብ መሳሪያ
April 5, 2019
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የእያንዳንዱ የተማሪ ጉዞ የማየት ግዴታ አለበት። ዘር፣ ጾታ፣ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ፣ የቋንቋ ብቃት፣
የመማር ዘዴ ወይም አካል ጉዳተኝነት ሳይለይ ሁሉም ልጅ የሚያስፈልጋቸውን ማንኛውም ነገር ማድረግ የእኛ ኃላፊነት ነው ብለን እናምናለን። ቤተሰቦች በዚህ
ሥራ ውስጥ ወሳኝ አጋሮቻችን ናቸው።
በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቤተሰቦች ተሳታፊ ማድረግ (EFIHS)የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና
ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ የጋራ ትብብር ነው።
1
About the Kinds of Supports Your School Provides AMHARIC
❖ አማካሪ
❖ ምክትል ርእሰመምህር
❖ መምህራን
❖ የወጣት ጤና ማዕከል
❖ ረዳቶች
2
Find out about important events at your child’s school AMHARIC
የስርኣተ ትምህርት ምሽት ዝግጅት እና መረጃውን በሙሉ እንዲረዱት ለማገዝ አስፈላጊ ከሆነ አስተርጓሚ እንዲኖርዎ መጠየቅ።
የልጅዎ ትምህርት ቤት እርስዎን በት/ ቤት ውስጥ ስለሚገኙ ሀብቶች እንዲያውቁ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን
እንዴት ድጋፍ መስጠት እንደሚችሉ እንዲረዳዎ ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች ይኖሯቸዋል።
3
Requesting an Interpreter and English Language Learners AMHARIC
አስተርጓሚ መጠየቅ:
For updated information go to: https://www.seattleschools.org/departments/english_language_learners
የሲያትል የህዝብ ት/ቤቶች ሁሉም ቤተሰቦች በልጃቸው ትምህርት እና የት /ቤት ዝግጅቶች ላይ እንዲሳተፉ
ያበረታታል። ይህ ስራ ያለ እርስዎ እገዛ ልንሰራው አንችልም!!
የእንግሉዝኛ ቋንቋ ተማሪዎች (ELL) እና አለምአቀፍ ፕሮግራሞች ዲፓርትሜንት በሲያትል የህዝብ ት/ ቤቶች ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች
በሙሉ በዋናዎቹ ዘጠኝ ቋንቋዎቻችን የትርጉም እና የአስቶርጓሚ አገልግለቶች ያቀራባል: አማርኛ፣ አረብኛ፣ ቻይንኛ፣ ኦሮሞኛ፣ ስፓኒሽኛ፣
ሶማሊኛ፣ ታጋሎግኛ፣ ትግሪኛ እና ቬትናምኛ
ሌሎች ቋንቋዎች በሁለት ቋንቋ ተናጋሪ የቤተሰብ አስተባባሪ በኩል በመጠየቅ ይገኛሉ።
እባክዎን በ: 206-252-0072 ይደውሉ ወይም ወደ: languages@seattleschools.org ኢሜይል ያድርጉ::
የ ASL ትርጉም ከ 504 አስተባባሪው ጋር ይገኛል::
እባክዎን ወደ: 504coordinator@seattleschools.org ኢሜይል ያድርጉ::
አስተርጓሚ የሚፈልጉ ወይም አስተርጓሚ ለመጠየቅ የሚፈልጉ ከሆነ ለማሳወቅ የልጅዎን አስተማሪ፣ አማካሪ፣ ርእሰ መምህር፣ ወይም ኬዝ
ማናጀረ ( አይኢፒ ላላቸው ተማሪዎች)ያነጋግሩ።
ቤተሰቦች ልጆቻቸው የእናታቸውን ቋንቋ ለመገንባትና ለመጠበቅ ከፍተኛ ድጋፍ ይሰጣሉ። ከአንድ በላይ ቋንቋዎች እውቀት መኖሩ ከሌሎች
በርካታ ጥቅሞች መካከል አንዱ የልጅዎን የፈጠራ አስተሳሰብ እና የችግር አፈታት ክህሎቶችን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።
በፀደይ 2011 ፣ ሲያትል የህዝብ ት /ቤቶች የቋንቋ ብቃት ለመገምገም እና ለተማሪዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ብቃት-ተኮር ክሬዲቶችን ለመስጠት
ፖሊሲ እና አካሄድ አፅድቋል።ልጅዎ ከእንግሊዝኛ ውጭ ሌላ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ የሚችል(የምትችል) ከሆነ(ከሆነች)፣ በዚህ ፕሮግራም
መሳተፍ ይችላል(ትችላለች)።ተማሪዎች ከ 1-4 የ 2 ኛ ደረጃ ትም /ቤት የዓለም ቋንቋ ክሬዲት ማግኘት ይችላሉ:: እነዚህ ክሬዲቶች የሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት የምረቃ መስፈርት እና ለ 4 ዓመት የዓለም(የውጭ አገር) ቋንቋዎች ኮሌጅ የመግቢያዎች መስፈርቶችን ለማሟላት ሊያግዙ ይችላሉ።
በአለም ቋንቋ ክሬዲት ፈተና (እስከ 4 ክሬዲቶች የሚያስገኝ ) ወይም በከፍተኛ ምደባ (AP) ወይም ዓለም አቀፍ ባካሎሬት (IB) የቋንቋ
ፈተናዎች በማለፍ የቋንቋ ክህሎታቸውን ያሳዩ ተመራቂዎች State Seal of Biliteracy ያገኛሉ። The Seal ዛሬ ባለው አለም ውስጥ
የእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ እና መጻፍ እና ቢያንስ አንድ ሌላ ቋንቋ መጠቀም ጥቅሙን ለማጉላት የታሰበ ነው።
የዓለም ቋንቋ ክሬዲት አማራጭ የሌላ ቋንቋ ዕውቀት ያላቸው ተማሪዎችን እውቅና ይሰጣል። በአፍ መፍቻ ቋንቋው ክረዲት ያገኘው አንድ
ተማሪ እንዲህ ብሏል ፣ “የዓለም ቋንቋ ክረዲት ማግኘት ቋንቋየን እና ህዝቤን ያከብራል።” አዎንታዊ ማንነት ይገነባል::
4
የሁለተኛ ደረጃ የምረቃ መስፈርቶች ዝርዝር High School Graduation Requirements Checklist AMHARIC
በ 2021 እና ከዚያ በላይ ያሉ ተማሪዎች ለመመረቅ 24 ነጥቦች ማግኘት አለባቸው:: በአንድ ሴሚስተር 6 ክፍሎች የሚወስድ አንድ ተማሪ በየሴሚስተሩ 3.0 ክሬዲቶች
ማግኘት ይችላል, ይህም ማለት በዓመት ጠቅላላ 6 ክሬዲቶች ያገኛል::ስለዚህ፣ አንድ ተማሪ በአራቱም ዓመት በየዓመት ሙሉውን ፕሮግራም ስድስት ክፍሎች ከወሰደ እና
ካለፈ፣በዚሁ በ 24 ክሬዲቶች ይመረቃል።. (እባክዎ በዚህ ሰነድ የመጨረሻ ገፅ ላይ የቃላት መግለጫዎች ይመልከቱ።)
ኮርሶች ክረዲቶች ተጠናቅቋል ለ 4-ዓመት ኮሌጅ ተጨማሪ የሁለተኛ ደረጃ መስፈርቶቾ ተጠናቅቋል
Fine Arts .50 Fine Arts-2 ለ 4 ዓመት ኮሌጅ
Fine Arts .50 credits. 1 can አነስተኛ የመመዝገብያ የሁለተኛ ደረጃ እና ከዛ በላይ እቅድ
Fine Arts .50 be personal መስፈርት ለማየት: ሰዓት የአገልግሎት ትምህርት
pathway. Ready Set Grad የተጠናቀቁ ሰዓቶች _______
Fine Arts .50
Language Arts 9A .50 Language (Washington State ተማሪዎች በክልሉ የተወሰኑ
Language Arts 9B .50 Arts - 4 Achievement ፈተናዎች ወይም የተፈቀዱ የቋንቋ
credits. Council) ኣማራጭ ፈተናዎችን እና ሂሳብ
Language Arts 10A .50 እንዲያልፉ ይጠበቅባቸዋል።
አንዳንድ ኮሌጆች
Language Arts 10B .50 ተጨማሪ መስፈርቶች ከ 2019-20 ጀመሮ የ ሳይንስ ፈተና
Language Arts 11A .50 አሏቸው. ማለፍ ይጠብቅባቸዋል።.
Language Arts 11B .50
Language Arts 12A .50
Language Arts 12B .50
Algebra1A or Integr Math .50 Mathematics 3 የሂሳብ ክሬዲቶች እና *** ተማሪዎች Algebra I ወይም Integrated
Algebra 1B or Integr Math .50 -3 credits የሲንየር ዓመት Math 1 ፣ እና Geometry ወይምIntegrated
Geom. 1Aor Integr Math2 .50 ኳንቲቴቲቨ ሒሳብ Math 2 ወይም Algebra 2 መውሰድ ወይም በ
Geom. 1Bor Integr Math2 .50 OSPI ተቀባይነት ያላቸው ተመጣጣኝ የሙያ እና
Algeb 2Aor CTE opt *** .50 የቴክኒካዊ ትምህርት ኮርሶች ክረዲት ማግኘትአለባቸው::
Algeb 2Bor CTE opt *** .50
Science with a lab .50 Science – 3 * ተማሪዎች Phys A/Chem A and Biology A
Science with a lab .50 credits. and B ማጠናቀቅ አለባቸው:: ከ 3 የሳይንስ ክሬዲቶች
Science with a lab .50 ውስጥ ቢያንስ 2 በ ላቦራቶሪ ሳይንስ ሦስተኛው ክሬዲት
Science with a lab .50 በተማሪዎች ፍላጎቶች መሰረት ይመረጣል፣ እና የ CTE
Science or CTE option* .50 ሳይንስ-ተኮር ያካተት ትምህርት ሊጨምር ይችላል::
Science or CTE option* .50
Physical Education (PE) .50 Health and የ PE ብቃት ፈተና-በክፍል ውስጥ
Physical Education .50 PE – 2 ይካሄዳል:: ተማሪው (PE) ውድቅ
Physical Education .50 credits ካልወሰደው፣ ተማሪው አሁንም
Health .50 ፈተናውን ማለፍ አለበት::
Career & Tech Ed (CTE) .50 CTE – 1 ተቀባይነት ያላቸው ኮርሶች ለማወቅ የዲስትሪክቱ
Career & Tech Ed (CTE) .50 credit ኦፊሳላዊ የኮርሶች ዝርዝር ይመልከቱ።
WA State History **** .50 (SPS) Social ****WA State አብዛኛውን ጊዜ
World History 1 .50 Studies – 3 በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው
World History 2 .50 credits. የሚወሰደው.:: ተማሪዎች በ 11 ኛ
World History 3 .50 ወይም 12 ኛ ክፍል የ OSPI
US History 11A .50 (ዋሽንግተን ስቴት) ተቀባይነት ያገኘ
የciviccs ግምገማ ማጠናቀቅ
US History 11B .50 አለባቸው::
American Govt .50
WL or Personal Path** .50 WL or 2-3 ዓመታት በአንዱ **Personal Pathway የዓለም ቋንቋ (WL) ፣ የ
WL or Personal Path** .50 Personal የዓለም ቋንቋ ሙያ እና የ ቴክኒካዊ ትምህርት (CTE) ፣ ስነ ጥበብ ፣
WL or Personal Path** .50 Pathways-2 ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ-ከስራ ግቦች ጋር የተያያዙ
WL or Personal Path** .50 credits ትምህርቶች
Electives as needed .50
(4 credits) ea
አንዳንድ የ4-ዓመት ኮሌጆች ቢያንስ 2 ነጥብ ( "C" አማካኝ) የ Grade Point Average
ጠቅላላ መስፈርቶች 24 ክሬዲቶች (GPA) ይጠይቃሉ::
እያንዳንዱ ተማሪ ኮርሶችን ማለፍ እና ከ 2 ኛ ደረጃ ት /ቤት ሊመረቅ ይችላሉ። አንዳንዶች በ 9ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎችን እንዴት እንደሚሆኑ እየተማሩ ነው።
በቤተሰቦቻቸው እና በትምህርት ቤት ሰራተኞች ድጋፍ፣ እንደ 9 ኛ ክፍል ያሉ የመማር ችሎታቸውን ማሻሻል ይችላሉ፣እናም የመመረቅ እድላቸውን ከፍ ይላል። በጣም ወቅታዊ የሆነውን መረጃ
እያዩ መሆንዎን ለማረጋገጥ የመስመር ላይ የምረቃ መረጃን ይመልከቱ: https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=18711
5
9th Grade is the most important year in high school AMHARIC
ዕውነታ
ከኮሌጅ የተመረቁ ትምህርታቸውን 3. የ9ኛ ክፍል ኮርሶችን ማለፍ ወሳኝነት አለው::
ካቋረጡት ይልቅ በአማካይ በዓመት ከ
ተማሪዎች 60% እና ከዚያ በላይ ካገኙ ትምህርታቸውን ለማለፍ እና ክሬዲቶችን ለማግኘት
12,900 ዶላር በላይ ያገኛሉ::
ይችላሉ:: ነገር ግን ኮሌጅ ለመግባት ተማሪው በተቻለ መጠን የተሻለ ውጤት ለማግኘት
የተማሪዎትን የመመረቂያ መስፈርቶች ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይጠበቅበታል:: ከ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመመረቅ በአማካይ "C " ማግኘት
ይረዱ:: በሚከተለው የወረዳው ድህረ ያስፈልጋል:: ዝቅተኛ ውጤት ያገኙ ተማሪዎች ለምረቃ ብቁ ለሚያደርጋቸው የስቴት ፈተና ወይም
ገጽ ላይ ይገኛል:: ለኮሌጅ የመግቢያ መስፈርት አልተዘጋጁም ማለት ነው::
www.seattleschools.org
ምንም እንኳ ተማሪዎች የወደቁበትን ኮርስ ከት/ሰዓት ውጭ ወይም በበጋው ወቅት
በመጀመሪያ “Students” ከዚያም ቢደግሙትም በ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለሚሰጡት ከፍተኛ ኮርሶች ያላቸው ዝግጁነት አነስተኛ
“Academics,” በመቀጠልም ስለሚሆን ይህ ደግሞ ለ 4 ዓመት የኮሌጅ ትምህርት ለማመልከት ዘቅተኛ
“Graduation Requirements.” ዝግጁነትእንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል::
በሚለው ቁልፍ ላይ ይጫኑ ወይም
የመመረቂያ መመሪያውን ለማግኘት ወላጆች እንዴት ሊረዱ ይችላሉ?
የተማሪዎትን አማካሪ ይጠይቁ::
➢ ተማሪዎት ሁልጊዜ የቤት ስራዎችን መስራቱን ያረጋግጡ::
ዕውነታ
➢ ከተማሪዎት ጋር ግቦችን በማስቀመጥ ስለ እድገታቸው ይጠይቋቸው::
ጥናቶች እንደሚያሳዩት 2ኛ ደረጃን ➢ እርዳታ ሲፈልግ አስተማሪዎቹን እንዲጠይቅ ተማሪዎትን ያበረታቱ::
ያጠናቀቁና ከኮሌጅ የጨረሱ ➢ ስለ ሁሉም የልጆችዎ አስተማሪዎች የነጥብ አሰጣጥ አሰራሮችን ማወቅዎትን ያረጋግጡ::
ተማሪዎች ካልጨረሱት ተማሪዎች
ይልቅ በህይወት ዘመናቸው በሚሊዮን ➢ A የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና ከዚያ በኋላ ያለውን እቅድ ኮፒውን ለማግኘት ት/ቤትዎትን
የሚጠጋ ዶላር የሚያገኙ ከመሆኑም ይጠይቁ::
በላይ ስራ ያለማግኘት ዕድላቸው ➢ ተማሪዎት ደጋፊ ኮርሶችን(electives) ፍላጎታቸውን ለማሰስና ከፍተኛ ትምህርቶችን
በጣም ዝቅተኛ ነው:: ለመውሰድ ይችሉ ዘንድ እንዲጠቀሙባቸው ያበረታቷቸው::
7
AMHARIC
ፀጋዎች (The source)
For the most up to date information, go to https://www.seattleschools.org/cms/One.aspx?portalId=627&pageId=16245
ሶርስ እርስዎ እና ልጅዎ አቴንዳንስ ፣በኮርሶቻቸው ላይ ያላቸው እድገት ፣ እና የጎደሉ አሳይመንቶች ለመከታተል የሚያስችል የዌብ ፀጋ ነው።
ተማሪዎች የየራሳቸው ሶርስ አካውንት ሊኖራቸው ይችላል።ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጆቻቹ ግስጋሴ ለመከታተል እና ለመደገፍ የተለያየ የሶርስ
አካውንት ሊኖራችሁ ይችላል። ወላጆች /አሳዳጊዎች እያንዳንዱ የልጆዎን መረጃ ለማየት የሚያስችል አንድ አካውንት ሊኖራችሁ ይችላል።ሶርስ
የሚከተሉትን እንዲያደርጉ ያስችልዎታል:
8
The SOURCE Account Set Up AMHARIC
በተጨማሪም ቤት ውስጥ ኮምፒዩተር ከሌለዎት፣ የሶርስን አካውንትዎ በሚከተሉት ኮምፒተር በመጠቀም መግባት ይችላሉ :
• የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ነፃ የሞባይል አፕ
• የህዝብ ቤተ-መጽሐፍት
• የልጅዎ ት / ቤት
• በኣቅራብያዎ የሚገኝ የማህበረሰብ ድርጅት
ቤተሰቦች ብዙ ጊዜ የሚጠይቁት: “ሶርስ በምንያህል ግዜ ማየት አለብኝ?”
መልስ : አብዛኞቹ መምህራን ሶርስን በየሁለት ሳምንት ያዘምኑታል፣ ነገር ግን ይህ የግድ አይደለም። አስፈላጊ ነው ብለው በሚያስቡበት
ጊዜ ሁሉ በተደገጋሚ ማየት ይችላሉ፣ነገር ግን ሶርሱን በየሁለት ሳምንቱ ከተመለከቱ ትክክለኛውን መረጃ ሊያዩ ይችላሉ። የትምህርት
ክትትልን በቅርበት መከታተል ከፈለጉ፣ በተደጋጋሚ ሶርስን መፈተሸ ይችላሉ። በ ሶርስ ላይ ያለው መረጃ እርግጠኛ ካልሆኑ የልጅዎን
አስተማሪዎች ኢሜይል ማድረግ ይችላሉ።
ስኩሎጂ: አንዳንድ መምህራን የቤት ስራዎች፣ መልእክቶች፣ ዝግጅቶችን፣ እና የቀን መቁጠሪያዎችን ለመለጠፍ ስኩሎጂ ሊጠቀሙ
ይችላሉ። በሶርስ አካውንትዎ አማካኝነት ወደ ስኩሎጂ መግባት ይችላሉ ።
9
Homework Help, page 1 AMHARIC
ወላጆች የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የቤት ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ እንዴት ሊረዱዋቸው ይችላሉ?
ጥናቶች የቤት ስራዎች ከኣንደኛ ደረጃ ወይም ከመካከለኛ ትምህርት ቤት ይልቅ በ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ይበልጥ ጥቅሞች እንዳሉት
ያሳያሉ።በቤት ሥራ ላይ የወላጅ ተሳትፎ ጠንካራ ተፅዕኖ አለው የሚሉ ጥቂት ጥያቄዎች አሉ።ወላጆች፣ወጣቶች የቤት ሥራን
ሲቃወሙ ወይም ይህን ለማድረግ የሚያስችላቸውን ክህሎቶች ሲያንሳቸው ምንም እንኳን ማጨናነቅ ባይችሉም፣የት/ ቤት ስኬት
የቤት ስራን ማጠናቀቅ ላይ ያሉትን መሰናክሎች ለማሸነፍ የወላጆች ፈቃደኛነት ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል።
ወላጆች፣ስለ የቤት ስራ አስፈላጊነት ግልጽ መልእክቶችን እና የተወሰነ የድጋፍ ስልቶችን በመስጠት የቤት ስራቸውን በማገዝ ወጣቶች
እንዲሳካላቸው ሊያደርጉይችላሉ ። ወላጆች ለልጆቻቸው የቤት ስራን በተመለከተ ሊሰጥዋቸው የሚችሉ ሶስት ቁልፍ መልዕክቶች
አሉ።
የቤት ስራ የትምህርት አስፈላጊ ክፍል ነው:: ወጣቶች የቤት ስራቸውን እንዲያጠናቅቁ እና ብግዜ እንዲያስረክቡ መጠበቅ። ወጣቶች
የቤት ስራ ኃላፊነት እንዲወስዱ እና የጊዜ አስተዳደር ችሎታ እንዲኖራቸው ማድረግ።
እንደ አስፈላጊነቱ የወላጅ ወይም የሌላ ድጋፍ ይቀርባል::: አንዳንድ ወጣቶች በትክክል በቤት ስራ በጣም ይቸገራሉ፣ ምክንያቱም በጣም
ከባድ ሆኖ ስለሚያገኙት ወይም በራሳቸው እንዴት እንደሚሠሩት ስለማያውቁ ነው። ሆኖም ግን ወላጆች ማበረታቻ ሲሰጡዋቸው
እና ሲቸገሩ እርዳታ ማግኘት እንደሚችሉ ሲያረጋግጡላቸው ወጣቶች ተስፋ የመቁረጥ ወይም የመበሳጨት እድላቸው ዝቅተኛ
ይሆናል ። ወጣቶች ያልገባቸው ወይም የተቸገሩበት የቤት ስራቸው በመለየት ላይ ለመርዳት ይችላሉ። ወጣቶች እርስዎ
ከሚሰጡዋቸው የቤት ስራ እገዛ በላይ የሚፈልጉ ከሆነ፣እነሱ ወይም እርስዎ የሚያስቸግራቸው የትምህርት ዓይነት መምህር ማነጋገር
ይችላሉ። ወይም ተጨማሪ የበለጠ እርዳታ ለማግኘት አማካሪውን ሊያነጋግሩ ይችላሉ። ልጅዎ ከአስተማሪ ጋር ለመወያየት እንዲዘጋጅ
ለማድረግ ክእርስዎ ጋር ጥያቄዎችን የመጠየቅ ልምምድ ሊያደርግ ይችላል። የተማሪ ተነሳሽነት የማይሰሩ ከሆነ ወላጆች መምህራንን
በቀጥታ እንዲያነጋግሩ ይበረታታሉ። በጣም ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎች እና ብልህ ወላጆች እንኳን ከቤት ውጭ በትምህርት ቤት ውስጥ
ከሚገኘው የቤት ሥራ ማእከል ወይም የትምህርት አስጠኚ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ወላጆች የልጆቻቸው የቤት ስራ አይሰሩም። ይህ መልዕክት የወላጅ ሚና የእነሱ ሥራ መስራት ሳይሆን እነሱን ማበረታታት እና
ስራቸውን እንዲያከናውኑ ማገዝ መሆኑን ለወጣቶች ለመንገር ነው።
10
Homework Help, page 2 AMHARIC
በየእለቱ የወጣትዎን የቤት ስራ መከታተል:: የቤት ሥራን ለማጠናቀቅ የወላጅ ድጋፍ ያላቸው ወጣቶች በቤት ስራ ላይ የበለጠ ጊዜ
እንደሚያሳልፉ ጥናቶች ያሳያሉ። ወላጆች ወጣት ልጆቻቸውን ለማበረታታት፣ትኩረት ለመስጠትና ከቤት ስራ ጋር የተያያዙ አሉታዊ
ስሜቶችን ለመዋጋት የሚያስችሉ ስትራቴጂዎች ሊሰጧቸው ይችላሉ። አንዳንድ ወጣቶች፣ በተለይም በዕድሜ እየገፉ ሲሄዱ፣ የወላጆች
እርዳታ ወይም ክትትል ይቃወማሉ፣ በትንሹ ወላጆች ስለ የቤት ስራ እና ስራውን መቼ ለማጠናቀቅ እንዳቀዱ መጠየቅ ይችላሉ:: ‘‘ምን
ማድረግ ይጠበቃል እና መቼ ነው የሚሰራው?’’ ወላጆች ወጣት ልጆቻቸው የቤት ስራ እቅድ እንዲያወጡ በሚረዱበት ጊዜ ለወላጆች
በየዕለቱ መደጋገም ይሆናል።
ግልፅ የሆነ የተለመደ የቤት ስራ እቅድ መመስረት:: ከተለመዱ ተግባራት የተያያዙ ስራዎች ለማከናወን በጣም ቀላል ነው። ወላጆች
የቤት ሥራን ለማጠናቀቅ በየቀኑ በመሥራት የቤት ስራውን በተቀላጠፈ መንገድ ማከናወን ብቻ ሳይሆን፣ ለኮሌጅ እና ሥራን ጨምሮ
ለመጪው ህይወት ተግባራዊ ሊያደርጋቸው የሚችሉበትን ስርዓት ያበረታታል። የቤት ሥራዎችን ለመስራት የሚከናወኑ ተግባራት
የሚከተሉትን ያካትታሉ፥:
• ልጅዎ ውጤታማ የሆነ የመማሪያ ቦታ እንዲፈጥር ያግዙ:: ሁሉም ተማሪዎች የሚማሩትና የሚያጠኑት በተመሳሳይ መንገድ
አይደለም:: በአጠቃላይ፣ አንድ ተማሪ ከረብሻ እና መቆራረጥ ነፃ የሆነ፣ ጥሩ ብርሃን እና ምቹ የሆነ ወንበር ባለው ቦታ ላይ
የበለጠ ተነሳሽነት እና በጥናት ላይ ማተኮር ይችላል።
• ታዳጊዎች የቤት ሥራዎቻቸውን ለመጨረስ የሚያስፈልጉት ነገሮች በሙሉ መኖራቸውም እርግጠኛ ይሁኑ። (ለምሳሌ፣
እርሳሶች፣ ማጥፊያ፣ ወረቀት፣ መዝገበ ቃላት፣ ካልኩሌተር)::
• የቤት ሥራ ለመስራት ጥሩ ጊዜን ይወስኑ (ለምሳሌ፣ ከትምህርት በኋላ፣ ከእራት በኋላ ወይም በፊት)::
• የቤት ስራን ለማጠናቀቅ እቅድ ያውጡ ( ለምሳሌ :የሚከናወኑ ተግባራትን ሁሉ ይዘርዝሩ፣ ወጣቶች እያንዳንዱን ስራ መቼ
እንደሚጀምሩ እና ስራውን ለመፈፀም ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ይገምቱ)::
• ወጣቶች የተዋቀረ ስርዓቶችን ማቋቋም እና በእቅዳቸው መቆየት እንዲችሉ መርዳት። ወጣት ልጆችዎ የመስርያ ቦታቸውን
እንዲያፀዱ እና የቤት ስራዎችን ለመከታተል የሚያስችሉ ስርዓቶችን እንዲኖራቸው ያግዙዋቸው።
11
Some Ways for Parents/Guardians to Engage with Their Students AMHARIC
TIGRIGNA
• ልጅዎ ለድርጊታቸው ተጠያቂ እንዲሆን ያድርጉ:: ይህም ማለት እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለድርጊታቸው ተጠያቂ ናቸው፣
እና እያንዳንዱን የስነምግባር ደንቦች እና የአቋም ደረጃዎች መከተል ይጠበቅበታል። ልጆቻችሁን ተጠያቂ የማድረግ
የመጀመሪያው እርምጃ እርስዎ ስለሚጠብቁት ነገር ግልጽ ማድርግ ነው።
• ልጅዎን ስለ አካዴሚያዊ ግቦች እና የሥራ ፍላጎቶች ይጠይቁት(ቋት)። ስለ ኮሌጅ እና የሥራ እድሎች የተለያዩ የመረጃ
ምንጮችን በመሰብሰብ እገዛ ያድርጉ።
• ልጅዎ ከንባብ የተገኙ ትርጉማቸው የማያውቃቸው 5 ቃላቶች እንዲመርጡ ያድርጉ እና እያንዳንዱን ቃል በአረፍተ ነገሩ
ውስጥ እንደገና እንዲያነቡት ያድርጉ። በእያንዳንዱ ዓረፍተ ነገር ውስጥ እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል መሠረት በማድረግ
ለእያንዳንዱ ቃል ያላቸውን ትርጓሜዎች ተነጋገሩ።
• የማኅበራዊ ጥናት ወይም የሳይንስ መጽሀፍ በማንበብ፣ ልጅዎ ጽሑፉን ለመረዳት አስፈላጊ የሆኑትን ቃላቶች እንዲያወጡ
ያድርጉ። የራሳቸውን የይዘት መዝገበ ቃላት ሲፈጥሩ አጫጭር መግለጫዎችን መጨመር ይችላሉ።
• ልጅዎ በዙሪያቸው ስላለው ዓለም ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ(እንድትጠይቅ) ያበረታቱ:: ጥያቄን በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ
በመመልከት፣ በማሰስ፣ በመመርመር ወይም በጥናት ላይ ተንተርሰው መልስ እንዲሰጡ ያግዟቸው።
ከ from the 2014 Seattle Public Schools’ Family Literacy, Math, & Science Toolkits
that were developed by the District’s Literacy, Math, and Science coaches and Family Engagement Office ተወስዶ የተሻሻለ
12
Most Frequently Asked Questions of School Counselors AMHARIC
ተማሪዬ ከክፍል ውስጥ በአንዱ የማያልፍ ከሆነ፣ የሰመር ትምህርት ወይም ክሬዲት መልሶ ማግኘት አስፈላጊ ነው?
መልስ: በኮርሱ ላይ ይወሰናል:: ከልጅዎ አማካሪ ጋር መነጋገር በጣም አስፈላጊ ነው።
ስለ ልጅዎ ስጋት ካለብዎ ወይም ለውጥ ካደረጉ እና ለምን ለውጥ እንዳረጉ የማያውቁ ከሆኑ --የቤተሰብዎ ዶክተር ያነጋግሩ። በተጨማሪም
የወጣቱ የጤና ማእከል፣ የትምህርት ቤቱን ነርስ፣ ወይም የልጅዎን የትምህርት ቤት አማካሪ ማግኘት ይችላሉ።
አጠቃላይ ስጋት ካለዎት እና ማንን መደወል እንዳለብዎት የማያውቁ ከሆነ፣እባክዎን ለልጅዎ የትምህርት ቤት አማካሪ ይደውሉ።
ከ Seattle Public School’s Ballard High School “Welcome to 9th Grade Parent Orientation” Packetተወስዶ የተሻሻለ
13
AMHARIC
የተማሪ ጥቅሞች
Naviance ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ የሚከተሉትን እድል በመስጠት ለሕይወታቸው የሚሆን ዕቅድ እንዲያወጡ
ያስችላቸዋል :
• የኮሌጅ ዕድሎች እና የስራ መስኮችን ማሰስ
• የ 4 ዓመት ኮርስ እቅድ ማዘጋጀት እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ምረቃ ክትትል ማድረግ
• የስኮላርሽፕ ፍለጋን ጨምሮ ለኮሌጅ የገንዘብ አማራጮችን መገንዘብ
• ተስማሚ የሆኑ ኮሌጆችን፣ የኮሌጅ መስፈርቶችን እና የሙያ መስኮችን መለየት
• የራስ መግለጫ፣ የትምህርት ማስረጃ እና የመምህራን የድጋፍ ደብዳቤን ጨምሮ ለሥራ እና ለኮሌጅ ማመልከቻዎች የሚያገለግሉ
የሰነድ መረጃዎች ማዘጋጀት
የቤተሰብ ጥቅሞች
Naviance ወላጆች ተማሪዎቻቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸው ካጠናቀቁ በኋላ የሚከተሉትን እድል በመስጠት ለሕይወታቸው
የሚሆን ዕቅድ እንዲያወጡ ያስችላቸዋል:
• የኮሌጅ ዕድሎች እና የስራ መስኮችን ከተማሪዎ ጋር ማሰስ
• ተማሪዎ ለኮሌጅ እና ለሙያ ዕቅድ ሂደት ባለቤትነት እንዲወስዱ ማድረግ
• ልጅችዎ ጥንካሬዎቻቸውን፣ ፍላጎቶቻቸውን፣ እና ግቦቻቸውን እንዲመረምር ማገዝ
• የስኮላርሽፕ ፍለጋን እና የገንዘብ ድጋፍ መረጃዎች ጨምሮ ለኮሌጅ የገንዘብ አማራጮችን መዳሰስ
• በጣም አስፈላጊ የሆኑ ቀኖችን መከታተል
14
Supporting 9th Grade Students who Receive Special Education Services AMHARIC
ከትምህርት የመቅረት መንስኤ መመልከት እና መፍታት በጣም አስፈላጊ ነው። ለብዙ ቀናት ከትምህርት ገበታ መቅረት (ከ 10% በላይ የትምህርት
ቀናት መቅረት) ወደ ኮርሱን መውደቅ ያመራል። ተማሪዎች ከትምህርት የሚቀሩበት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
• ከልጁ አካል ጉዳተኝነት ጋር የተያያዙ ቀሪዎች ናቸው?
• በ IEP ውስጥ መመዝገብ እና መታየት ያለባቸው የጤና ችግሮች አሉ?
• የመጓጓዣ ጉዳይ ነው?
• ፍርሃት ወይም ጭንቀት የመሳሰሉ ከአካል ጉዳተኝነት ጋር የተዛመዱ ፈጣን ምላሽ የሚፈልጉ ቀሪዎች።
በተቻለ መጠን፣ተማሪው እዚያ ለመገኘት እንዲችል የትምህርት ቤቱ የአየር ሁኔታን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ጨምሮ ቀሪዎችን ለማሻሻል
መፍትሔዎችን እና ስልቶችን ለማዘጋጀት ተማሪዎችን ማሳተፍ ነው።
ወላጆች/ አሳዳጊዎች በትምህርት መከታተል እና በኮርስ ማለፊያ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ የተሻሉ ዘዴዎችን ለመወያየት የ IEP
ስብሰባ (የግል የትምህርታዊ ፕሮግራም ላላቸው) ወይም ሌላ የትምህርት ቤት የቡድን ስብሰባ መጠየቅ ይችላሉ። የስብሰባ ቀጠሮ ለመያዝ
የልጅዎን አማካሪ ወይም የ IEP ኬዝ ማናጀር መጠየቅ ይችላሉ። በስብሰባው ወቅት አስተርጓሚ የሚያስፈልግዎ ከሆነ አስቀድመው ይጠይቁ።
http://www.gearup.wa.gov/file/preparing-students-disabilities-postsecondary-education-resource-guide-use-
gear-school-staff
ይህ የመገልገያ መመሪያ የሙያ እና የስራ ትምህርት ቤቶች፣ የሁለትና የአራት ዓመት ኮሌጆች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በድህረ ሁለተኛ
ደረጃ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ትምህርታቸውን ለመቀጠል የሚያስቡ የአካል ጉዳት ያለባቸው ከሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ጋር የሚሰሩ
ቤተሰቦች ለመርዳት የተዘጋጀ ነው።ምክንያቱም የ ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ተቋማት ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስለሚለያዩ ነው፣አካል ጉዳተኛ
ተማሪዎች ስኬታማ እንዲሆኑ መብቶቻቸው ፣ ኃላፊነቶቻቸው እና እራሳቸውን መቆም እንዳለባቸው ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።
15
AMHARIC
ከ6 ኛ-12 ኛ ላሉ ክፍሎች ለ ከፍተኛ ብቃት መንገዶች እና የትምህርት ቤት ምደባ በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የ
Advanced Learning 6th-12th Grade Students ገፅ ይጎብኙ። ለእርስዎ ምቾት ሲባል ፣ ከታች በተደጋጋሚ ለሚጠየቁ
ጥያቄዎች የተወሰኑ ምላሾች ቀርበዋል (FAQs):
• አንድ ተማሪ በ SPS የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤቶች በከፍተኛ ደረጃ ኮርሶች ለመመዝገብ ከፍተኛ ብቃት ላላቸው
(HC) ወይም የላቀ ትምህርት (AL) አገልግሎቶች ብቁ መሆን አለበት?
ምንም እንኳን የ HC ወይም AL ብቁነት ባይኖራቸውም፣ ሁሉም ብቃቶች፣ ከፍተኛ ምደባ፣ BI እና የእጥፍ ክረዲት ኮርሶች ለሁሉም ተማሪዎች
ክፍት ናቸው። The International Baccalaureate Accelerated (IBX) መርሀግብር በ Ingraham ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት መመዝገብ የሚፈልጉ ተማሪዎች ለ HC አገልግሎቶች ብቁ መሆን ኣለባቸው።
• አንድ ተማሪ በሁሉም የ SPS የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት የ HC Pathway Course Recommendations መውሰድ ይችላል?
አያቻልም:: ለ HC አገልግሎቶች ብቁ የሆኑ ተማሪዎች ከሦስቱ የ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአንዱ መውሰድ ይችላል። በዚህ የሽግግር ሂደት
ውስጥ፣ የተወሰኑ ኮርሶች በተማሪ ፍላጎት፣ ምዝገባ እና በሠራተኞች መሰረት በየተራ ቅደም ተከተል ሊሰጡ ይችላሉ።
• አንድ የሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት በ 2018-2019 Garfield ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ወይም Ingraham ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት ውስጥ
የተመዘገበ ከሆነ፣ለ 2019-2020 የትምህርት ዓመት ት / ቤቱን መለወጥ ያስፈልገዋል?
አያስፈልግም። በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ብቃት መርሃ ግብር በ Garfield ወይም Ingraham ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች እዛው ይቀጥላሉ።
• በ 2018-2019 ውስጥ በከፍተኛ ብቃት መርሃ ግብር በ Garfield ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመዘገበ / ች ተማሪ , ተማሪው በ 2019-
2020 ወደ Lincoln ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲቀየር መጠየቅ ይችላል?
አዎ። ምንም እንኳን በ 8ኛ ክፍል በHCC ውስጥ ትምህርት ቤት ባይኖሩም፣በ2019-20 ትምህርት ዘመን ለ 10 ክፍል HC ለመግባት ብቁ
የሆኑ ተማሪዎች፣ Garfield ካሉ ወይም Lincoln HC pathway የመማርያ አካባቢ ካሉ ወደ Lincoln ለማመልከት መምረጥ ይችላሉ።
ቤተሰቦች ክፍት የመመዝገቢያ ጊዜ ውስጥ የምርጫ ቅጹን ማስገባት አለባቸው።
ተጨማሪ ስለ ክፍት የምዝገባ ግዜ ያንብቡ።
16
• ለ HC አገልግሎቶች ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በ በራሳቸው "HC Pathway ሁሉተኛ ደርጃ " ለመሳተፍ ይጠየቃሉ?
አይጠየቁም። በአንደኛ ደረጃ ወይም መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የከፍተኛ ብቃት ያላቸው አገልግሎቶችን ለመቀበል ብቁ መሆናቸው የተለዩ
እና ኮርሳቸው HCC መሆኑን በግልፅ የተገፁ ተ ማ ሪዎች፣ለ HC ብቁ የሆኑ ተማሮዎች ፍላጎት ፣ በኮሌጅ እና የስራ ግቦች ላይ በመመርኮዝ
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ኮርሶችንመምረጥ ይችላሉ:: ባህላዊ የ HC ኬዝ ሞዴል በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አይቀጥልም; ይሁን እንጂ የ HC
እና (AL) አገልግሎቶች የሚያገኙ ተማሪዎች ወደ የላቀ ደረጃ ኮርስ የመቀጠል እድል ይኖራቸዋል።
• ሁሉም የምረቃ መስፈርቶች ከተሟሉ አንድ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ቀድሞ ሊመረቅ ይችላሉ?
አዎ፣ አንድ ተማሪ ለተወሰነ የምረቃ አመት ሁሉንም የክልሉ እና የዲስትሪክቱ የመመርቅያ መስፈርቶች ካሟላ፣ተማሪው / ዋ የመመርቅያ ክረዲት
የተጠናቀቀ መሆኑን ለማረጋገጥ እና ቀደም ብሎ ለመመረቅ ከት/ ቤት አማካሪያቸው ጋር ቀጠሮ መያዝ ይቻላል። ተማሪዎችና ቤተሰቦች
የተማሪው የታቀዱ ትምህርቶች ሁሉንም የምረቃ መስፈርቶች ያሟሉ መሆናቸውም ለማረጋገጥ የምረቃ መጽሔት ማየት እና ከትም /ቤት
አማካሪያቸው ጋር መገናኘ አለባቸው።
• አንድ ተማሪ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ብቁ የሚያደርግ በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሱን ካጠናቀቀ፣ እነዚህን
ክሬዲቶች ወደ የተማሪው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትራንስክሪፕት የማዛወር ሂደት እንዴት ነው?
ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ብቁ የሚያደርግ በመለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሱን ያጠናቀቁ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ከሁለተኛ
ደረጃ ት /ቤት አማካሪዎ የመካከለኛ ትምህርት ቤት ክሬዲት ቅጽ መጠየቅ ይችላሉ።የክረዲቱ ብቁነት ለመወሰን ተማሪዎች እና ቤተሰቦች
የተጠናቀቁ ቅጾችን ወደ አማካሪ ቢሮ መመለስ አለባቸው።
From the Seattle Public Schools Office of Student Support Services, Advanced Learning
Revised January 16, 2019
For updated information go to: https://www.seattleschools.org/cms/one.aspx?pageId=14554
(www.seattleschools.org > Academics > Advanced Learning)
17
State Testing Requirements for Graduation AMHARIC
ሁሉም የ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች የ Smarter Balanced Assessments (SBA) የእንግሊዝኛ ቋንቋ (ELA) እና የሂሳብ
ፈተናዎች መውሰድ አለባቸው።
ሁሉም የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች የ Washington Comprehensive Assessment of Science* ፈተና ጭምር
መውሰድ አለባቸው።
* ከ 2019-2020 የትምህርት አመት ጀምሮ የሳይንስ ምዘና ማለፍ የምረቃ መስፈርት ነው።
ተማሪ የ እንግሊዝኛ ቋንቋ (ELA) እና/ወይም የሂሳብ ፈተናዎችን ካላለፈ፣ከ 11 ኛ ክፍል ጀምሮ የሚከተሉት አማራጮች
ይኖራሉ።:
1. ተማሪው በ 11ኛ እና/ወይም 12ኛ ክፍል እንደአስፈላጊነቱ የ SBA ፈተናዎችን እንደገና ሊወስድ ይችላሉ (መኸር እና / ወይም ፀደይ)::
2. አንድ ተማሪ በ SAT ወይም በ ACT ፈተና የማለፍያ ውጤት ማግኘት ይችላል:: SAT ካለ ምንም ክፍያ በትምህርት ቀን ለ junior
ተማሪዎች ይሰጣል:: አንድ ተማሪ የምረቃ አማራጭ (ችን) ለመጠቀም ን SBAC መሞከር አለበት።
የ 2017-2020 ምድብ:
የምረቃ የፈተና መስፈርቶች SAT with SAT ACT with ACT (no
Essay (March 2016
(March 2016 or later) Writing Writing)
or later)
ሂሳብ 430 430 16 16
የእንግሊዝኛ ቋንቋ 410 N/A 14 N/A
3. አንድ ተማሪ በትምህርት ቤት ውስጥ በ COE (Collection of Evidence) ክፍሎች መመዝገብ ይችላል፣ በክፍል ውስጥ ክረዲት
ሊያገኝ ይችላል፣እና የማለፊያ ውጤት የሚያገኝ የስራ ተግባራትን ያቀርባል። አንዳንድ ት/ ቤቶች የምረቃ መስፈርቱን ለማሟላት አንድ
ዓመት ሙሉ የኮሌጅ መሸጋገርያ ትምህርት ሊያቀርቡ ይችላሉ።
4. አንድ ተማሪ በ ELA ወይም በሂሳብ በሁለት አማራጭ ክረዲት ማለፍ ይችላል ፣ እንደ ራኒግ ስታርት ወይም ኮሌጅ በሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት ያሉ
በትም/ቤትዎ ውስጥ የትኞቹ አማራጮች ሊቀርቡ እንደሚችሉ ለማወቅ የት/ ቤቱን አማካሪ ወይም የትምህርት ጣልቃገብነት ባለሙያን ያነጋግሩ::
18
Explanation of Terms AMHARIC
የቃላቶች መግለጫ
ACT እና SAT የኮሌጅ መግቢያ ፈተናዎች
ብዙ ኮሌጆች የ ACT ወይም የ SAT ፈተናዎች ውጤቶችን እንደ የምዝገባውን ሂደት አካል እንዲሆን ይጠይቃሉ ::
በአብዛኛው ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የመግብያ ውሳኔዎች ለማድረግ የሚጠቀሙባቸው የመግቢያ ፈተናዎች ናቸው:: የ ACT እና SAT ፈተናዎች ዓላማ
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለኮሌጅ ዝግጁ መሆናቸውን ለመለካት እና ኮሌጆችን ሁሉንም አመልካቾችን ለማነፃፀር ጥቅም ላይ ሊውል
የሚችል አንድ የጋራ መረጃ ነጥብ ነው። አብዛኞቹ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ACT ፣SAT ወይም ሁለቱም ፈተናዎች ጁኒየር ተማሪዎች በፀደይ
ወቅት፣ሲንየር ተማሪዎች ደግሞ በመከር ወቅት ይወስዳሉ። ኮሌጅ ከማመልከትዎ በፊት ውጤትዎን ከፍ ማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ ፈተናውን እንደገና
ለመውሰድ ጊዜዎ መተው በጣም አስፈላጊ ነው።
የላቀ ትምህርት ተማሪ (AL) እና ከፍተኛ ችሎታ ያላቸው( HC)መሸጋገርያ( Advanced Learner (AL) and Highly Capable (HC)
Pathway)
ተማሪዎች ተመሳሳይ ዕድመ ካላቸው የክፍል ጓደኛቻቸው በላይ ለየት ያለ የመማር እና የመረዳት ችሎታ ካሳዩ ፣ በወላጆች፣ በመምህራን፣ በሌሎች
ሰራተኞች፣ ወይም በየማኅበረሰብ አባላት ተለይተው ፣በወላጆቻቸው ብቁ መሆናቸውን በተገቢው ግምገማ ሂደት ውስጥ እንዲሳተፉ ይደረጋል። የላቀ
ትምህርት አገልግሎት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች (ሁለቴ ልዩ የሆኑ ተማርዎች)እና ልዩ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች ወይም ከሁሉም ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣
ዘር እና ባህል ሊያጠቃልል ይችላል።
የላቀ ትምህርት ተማሪ (AL) የላቀ ትምህርት ከ ኪንደርጋርተን እስክ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች የብቁነት ምድብ ነው። ጥቆማ በመጨረሻው የትምህርት
ዓመት ወይም በበጋ ወቅት ይካሄዳል። ፈታናው በየዓመቱ በመከር ወቅት ይካሄዳል።.
ከስራ ጋር የተያያዘ ትምህርት / የሙያ እና ቴክኒካዊ ትምህርት (CCL/CTE)( Career Connected Learning/Career and Technical
Education (CCL/CTE))
የ CCL/CTE)) ክፍሎች ወይም ኣንዳንድ የተፈቀዱ የ CCL/CTE)) ኮርስ ያልሆኑ በመቃኘት እና በመዘጋኘ ክረዲት ማግኘት ይቻላል።።ለተፈቀዱ
ኮርሶች ኦፊሴላዊ የዲስትሪክት የኮርስ ዝርዝርን ይመልከቱ።
ክረዲት
” ክሬዲት ምንድን ነው?” ክሬዲቶች ተማሪዎች በአጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርትን መስፈርቶች ያሟሉ መሆናቸውን ለመገምገም
ከሚጠቀሙባቸው ቀዳሚ ዘዴዎች መካከል ኣንዱ ነው ። ክሬዲቶች ኮርስ ወይም አስፈላጊ የትምህርት ቤት ፕሮግራም ሲጨርሱ እና ሲያልፉ ይሰጣሉ።
የሲያትል የህዝብ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ዲፕሎማ እንዲያገኙ ክረዲቶች ማከማቸት ያስፈልገዋል።
Naviance
Naviance ተማሪዎች ኮሌጆችንና የሙያ ጉዛቸውን እንዲመረምሩ ፣ብቃቶችን እና ችሎታን በስራና በጠባይ ተኮርነት ዳሰሳ እንዲያደርጉ እና አካዳሚያዊ
ግቦች ላይ ለመድረስ በሚያስችላቸው መንገድ ላይ ለመቆየት ያግዛሉ::
19
OSPI (የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ጽ / ቤት)
የህዝብ ትምህርት ቤቶች የበላይ ተቆጣጣሪ ጽህፈት ቤት በዋሽንግተን ክልል ውስጥ ያሉ የ k-12 ትምህርት በበላይነት የሚቆጣጠር ድርጅት ነው። OSPI
ከአንድ ሚሊዮን በላይ የህዝብ ትምህርት ቤቶችን ተማሪዎች በመወከል መሰረታዊ የትምህርት ፕሮግራሞችን ለማስተዳደር እና የትምህርት ማሻሻያ
ለማድረግ ከ 295 የትምህርት ድስትሪክቶች ጋር በመተባበር ይሰራል።
ራኒግ ስታርት
ራንግ ስታርት ቢያንስ የ 11 ኛ ክፍል በቂ ክረዲት ያገኙ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በማህበርሰብ ኮሌጅ የሚሰጥ አማራጭ ኮርስ ነው።
Seal of Biliteracy
በአለም ቋንቋ ክሬዲት ፈተና (እስከ 4 ክሬዲቶች የሚያስገኝ ) ወይም በከፍተኛ ምደባ (AP) ወይም ዓለም አቀፍ ባካሎሬት (IB) የቋንቋ ፈተናዎች በማለፍ
የቋንቋ ክህሎታቸውን ያሳዩ ተመራቂዎች State Seal of Biliteracy ያገኛሉ። The Seal ዛሬ ባለው አለም ውስጥ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መናገር፣ ማንበብ
እና መጻፍ እና ቢያንስ አንድ ሌላ ቋንቋ መጠቀም ጥቅሙን ለማጉላት የታሰበ ነው።
ስኩሎጂ (Schoology)
አንዳንድ መምህራን የቤት ስራዎች፣ መልእክቶች፣ ዝግጅቶችን፣ እና የቀን መቁጠሪያዎችን ለመለጠፍ ስኩሎጂ ሊጠቀሙ ይችላሉ።
በሶርስ አካውንትዎ አማካኝነት ወደ ስኩሎጂ መግባት ይችላሉ ።.
ለ 4 ዓመት ኮሌጅ ወይም ዩኒቨርሲቲ ለመግባት እቅድ ያላቸው ሁሉም ተማሪዎች ፣የዓለም ቋንቋዎች (እንደ ስፓኒሽ፣ ፈረንሣይኛ፣ ወዘተ )ቢያንስ ለሁለት
አመታት እንዲከታተሉ ይመከራል ።
20