You are on page 1of 2

በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!

በዛሬ ፅሁፍ ላይ ተማሪዎች መጪውን የፈተና ወቅት በተረጋጋ ሁኔታ እዲጀምሩ ለማስቻል ሲሆን በዚህ ጊዜያት ሊገጥማቸው
የሚችለውን ውጥረት ለመቆጣጠር እገዛ የሚያረጉ የተወሰኑ ነጥቦች በዝርዝር ቀርበዋል። ፈተና የመፈተኛ ጊዜ ሲቃረብ ሁላችንም
በመጠኑ መጨነቅ እና ከወትሮው ከፍ ባለ መጠን ውጥረት ውስጥ መግባታችን የተለመደ ነገር ነው ። ይህም ጤናማ ፍርሀት ለፈተና
እንድንተጋ ስለሚረዳን በተሻለ ለመዘጋጀት እንዲሁም ጥሩ ትኩረት ለመድረግ ያስችለናል። ሆኖም ግን ይህ ጭንቀት ወይም ቴንሽን
መጠነኛ ካልሆነ ወደ መደናገር እና ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት ይዳርገናል ። በዚህም የተነሳ ፈተናችንን በጥሩ እንዳናስኬድ እና ተገቢውን
ትኩረት እንዳንሰጥ ያረገናል ። ከዚህም ሀሳብ ጋር በተያያዘ ለዚህ አይነቱ ጭንቀት እና ውጥረት ውስጥ እንድንገባ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ
ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ:

• አሉታዊ ሀሳቦች ወደ አዕምሮ በመምጣት ሀሳባችን በሙሉ ስለ ፈተናው አስከፊነት እና ስለውጤት መበላሸት አብዝተን ስናስብ ።

• በቂ እና ምክንያታዊ ያልሆነ ግመታ እና ድምዳሜ አጠቃሎ ስለፈተናው ማሰብ ።

• የውጫዊ ተፅእኖ እንደ ቤተሰብ ፣ መምህራን እና ጓደኛ የሚመጡ ጫናዎች አስተሳሰባችን ላይ ይህ መሆን አለበት ወይም መሆን
የለበትም የሚል አቋም መያዝ ስህተትን እንዳንቀበል እና መሳሳትን እንድንፈራ ስለሚያረግ በፈተና መዳረሻ ከፍተኛ ለሆነ ውጥረት
ይዳርገናል ።

• ሙሉ ሀሳብን ወደ ፈተናው ይዘት እና ሁኔታ ከማተኮር ይልቅ ወደ ውጤት እና ነጥብ ብቻ ላይ ማተኮር እና ማስላት። እነዚህ ዋና
ዋናዎቹ በፈተና ወቅት ውጥረትን እና ጭንቀትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች ናቸው። ስለዚህ ተፈታኞች የተወሰነ ዘዴን በመጠቀም ይህን
አይነቱን ከፍተኛ ውጥረት መቆጣጠር የምትችሉበትን መንገድ አንድ በአንድ እንመልከት፤

ከፈተና በፊት ማድረግ የሚገባን ዜዴዎች፤ -

• ፈተና ሲመጣ መጠነኛ ውጥረት እና ጭንቀት ተፈጥሮአዊ እና ሁሉም ተፈታኝ ተማሪ እንደሚያጋጥመው መረዳት።

• ለፈተና ስንዘጋጅ አዎንታዊ እና በጎ ሀሳቦችን ማሰብ፡፡ ይህ ማለት ስለፈተናው ክብደት እና አስከፊነት ከማሰብ በተቃራኒው በአይነ
ህሊና (visualization) ዘና ብለን ስንፈተን እና ፈተናውን በተገቢ መንገድ ስንፈተን በአእምሮችን መሳል ። ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዚህ
ቀደም በክፍል ውስጥ በብቃት የሰራናቸውን ፈተናዎች እና የገኘነውን ጥሩ ውጤቶች ማሰብ። እናም ምን አይነት ፈተና ሊመጣ ይችላል
ብለን አብዝተን አለመጨነቅ ይልቅ የሚመጣው ፈተና ከዚህ በፊት ከተማርነው የተለየ አለመሆኑን መረዳት እና መጪውም ፈተና
በተመሳሳይ እንደምንሰራው ማሰብ።

• ፈተና ማለት ከዚህ ቀደም ከተማርነው ነገር የተረዳነውን እና የቀሰምነውን እውቀት የምንለካበት መመዘኛ እንጂ የኛ የህይወት ምዕራፍ
ማብቂያ ወይም አጠቃላይ ችሎታችንን የሚያመላክት አይደለም ። ምክንያቱም ከላይ እንደ ምክንያት ለተቀመጡት ነጥቦች ከዚህ ሀሳብ
በተያያዘ አንድ ተማሪ በፈተና ጥሩ ውጤት ባያገኝ እና ቢሳሳት ቀድሞውኑ ወደ ጭንቅላቱ የሚመጣው አለማወቁ ዋጋ እንደሚያስከፍለው
እና ቤተሰቦቹም ሆነ መምህራን እንደ ሰነፍ እና ዋጋ እንደሌለው ስለሚገመት ስህተትን አስተካክሎ ለቀጣይ ለማሻሻል እና ለመማር
መሰናክል ይፈጥራል። ስለዚህ ማወቅ ያለብን አንድ ነገር ቢኖር መሳሳትን አለመፍራት እና ሁሌም ለማወቅ እና ራስን ለማሻሻል ዝግጅ
መሆንን ነው ። እንዲሁም አሁን የምንፈተነው ፈተና እንዳሰብነው እንኳን ውጤቱ ባያስደስት ለቀጣይ ማስተካከል እና ማሻሻል
እንደሚቻል ማመን።

• ከጓደኞቻችን ጋር ያጠናነውን ነገር በጋራ ሆነን መጠያየቅ እና እርስ በርስ ያወቅነውን ነገር መለዋወጥ፡፡ ይህ ዘዴ ይበልጥ የማስታወስ
ብቃታችንን እንደሚጨምር እና የተጠያየቅነው ነገር እንዳይረሳን ያረጋል ። ከዚህም በተጨማሪ የተሳሳትነውን ነገር ድጋሚ እንድንከልስ
እና እርማት እንድናረግ ያግዘናል።

• የፈተና ቀን ሲቃረብ እንደ ወትሮው ዘና ማለት እና በቂ እረፍትና በቂ እንቅልፍ መተኛት ። ይህም ጭንቀትን ይቀንስልናል፣ እንዲሁም
ተረጋግተን ያጠናነውን ነገር አስበን እንድንሰራ ይረዳናል። ፈተና ከጀመርን በኋላ መድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤

• ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት።
• አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ።

• ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን
እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ።

• በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ
ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ።

ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር፡፡ ለምሳሌ "አሁን ደህና ነኝ" ፥ "ጥሩ ሆኛለሁ "
ወይም በምናምነው ሀይማኖት ጊዜ የማይወስድብንን አጭር ፀሎት በልባችን መፀለይ። ከዛም መልሰን በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን
መጀመር።

• ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን
በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ •

በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ
የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ።

• ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም
ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ።

• በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። ይልቅ በጣም ሳንንቀራፈፍ ተረጋግተን
ፈተናውን መስራት እና ፈተናውን ከጨረስን በኋላ ተመልሰን የሰራነውን ጥያቄ አጠቃላይ ማየት።

ለሁሉም ተፈታኞች መልካም የፈተና ጊዜ!

የየካ ክፍለ ከተማ ት/ተ ጽ/ቤት|

ምንጭ፡- Addis express media

You might also like