You are on page 1of 2

የጋብቻ ቃል ኪዳን ሥነ ሥርዓት

ከመልዕክቱ በኋላ የሚያጋባው መሪ ተነስቶ እንዲህ ይላል፤

1. የተወደዳችሁ ወንድሞች፣ እህቶች፣ እንግዶች፣ እንደምትመለከቱት በቅዱስ ጋብቻ ለመዋሃድ


አቶ____________________ እና ወ/ሪት ____________________ ተዘጋጅተው ቀርበዋል የእነርሱን መጋባት
የሚከለክል ምንም ምክንያት ሰላልተገኘ አሁን በፊታችሁ የጋብቻቸውን ቃል ኪዳን ሥነ ሥርዓት እናስፈፅማለን፡፡
2. ከዚህ በኋላ የሚያጋባው መሪ ሙሽሮቹን እንዲህ ይላቸዋል፤ ሙሽሮች በመሪው ፊት ይቆማሉ፡፡

ጋብቻ በእግዚአብሔር የታቀደ በኢየሱስ ክርስቶስ የታተመና የተቀደሰ መሆኑን ታምናላችሁ?

መልስ አዎን አምናለሁ፤ በየተራ

3. ሙሽራውን አሁን አንተ በእግዚአብሔርና በእነዚህ ምስክሮች ፊት በጎንህ ያለችውን እህት_______ ሚስትህ
አድርገህ በጤንነቷና በህመሟ እያፈቀርካትን እያፅናናሃት በምቾትና በችግር የሚያስፈልጋትንም እያቀረብክላት
እንደ ክርስቲያን ባልም በታማኝነት ሁልጊዜ ከዕርስዋ ጋር በሕይወት እስካላች ድረስ በርስዋ ብቻ ፀንተህ ትኖራለህ?
መልስ አዎን እኖራለሁ

4. ሙሽሪትን አሁን አንቺ በእግዚአብሔርና በእነዚህ ምስክሮች ፊት በጎንሽ ያለውን ወንድም_______ ባልሽ አድርገሽ
በጤንነቱና በህመሙ እያፈቀርሽውና እያፅናናሽው በምቾትና በችግር የሚያስፈልገውንም እያቀረብሽለት እንደ
ክርስቲያን ሚስት በታማኝነት ሁልጊዜ ከዕርሱ ጋር በሕይወት እስካላችሁ ድረስ በርሱ ብቻ ፀንተሽ ትኖሪያለሽ?
መልስ አዎን እኖራለሁ

የቀለበት መለዋወጥ ሥነ ሥርዓት

5. የመሪው ጥያቄ አንተ ___________ ለገባህላት ቃል ኪዳን ምልክት ይሆናት ዘንድ ይህንን ቀለበት ለ
___________ ትሰጣታለህ?

መልስ አዎን እሰጣታለሁ ለገባሁልሽ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንሽ ዘንድ ይህንን ቀለበት እሰጥሻለሁ፡፡

6. የመሪው ጥያቄ አንቺ ___________ ለገባሽለት ቃል ኪዳን ምልክት ይሆነው ዘንድ ይህንን ቀለበት ለ
___________ ትሰጪዋለሽ?

መልስ አዎን እሰጠዋለሁ ለገባሁልህ ቃል ኪዳን ምልክት ይሆንህ ዘንድ ይህንን ቀለበት እሰጥሀለሁ፡

7. ሁለቱም እጅ ለእጅ ይያያዛሉ የተያያዘውን እጃቸውን የሚያጋባው መሪ ይዞ ይፀልይላቸዋል፡፡

- የአብርሃም፣ የይስሃቅ፣ የያዕቆብ አምላክ ከእናንተ ጋር ይሁን ይህ አንድነታችሁ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ
ይባረክ፡፡
- እግዚአብሔር ያጣመረውን ሰው አይለየውም፡፡ ባልና ሚስት ሆናችሁ በሰላምና በደስታ፣ እግዚአብሔርን
በመፍራት ትዕዛዛቱንም በመጠበቅ ኑሩ፡፡ አሜን
የሻማ ሥነ ሥርዓት

8. የሻማ ሥነ ሥርዓት ከተፈፀመ በኋላ መሪው እንዲህ ይላል ሰው እናትና አባቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል
ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ፡፡
የፊርማ ሥነ ሥርዓት

ካህኑ ጋብቻውን ያውጃል

9. ከእግዚአብሔርና ከቤተክርስቲያን እንዲሁም ከአዲስ አበባ መስተዳድር በተሰጠኝ ሥልጣን መሰረት ይህንን የጋብቻ
ሥነ ሥርዓት እንደ እግዚአብሔር ቃልና እንደ ኢትዮጵያ ህግ መሰረት አስፈፅሜያለሁ፡፡
ካህኑ ቀኑን ይናገራል

10. የምስክር ወረቀት አጋቢው ይሰጣል ሌሎችም ይመጣሉ ፊርማ ምስክሮችም ይፈርማሉ

11. መዘምራን

12. በመጨረሻ ሙሽሮች ከመውጣታቸው በፊት መሪው ህዝቡን ይባርካል እግዚአብሔር ይማረን ይባርከንም የፊቱን
ብርሃን በላያችን ያብራ አሜን፡፡

13. የሐዋሪያት ፀሎት

You might also like