Professional Documents
Culture Documents
Sayirq Beqirbu, Sayiderq Bertibu
Sayirq Beqirbu, Sayiderq Bertibu
ሴትዮዋ ጉድጓድ ውስጥ ትወድቅና ትጮኻለች፡፡ አንድ ሰው ይሰማትና ይመጣል፡፡ እጅሺን አምጭ ብሎ
እጇን ጎትቶ ሊያወጣት ሲሞክር እጇን ይገነጥለዋል፡፡ ሴትዮዋ ጉድጓድ ከመግባቷ ይልቅ የእጇ መገንጠል
ይብስባታል፡፡ እናም «አውጣኝ ብለው ገነጠለኝ» አለቺ ይባላል፡፡ አውጭው ከጉድጓዱ ባሰባት፡፡
አሁን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ በእምነት ተቋማት እና በእምነት መሪዎች ዘንድ እጅግ አሳዛኝ ነገሮች
እየተሰሙ ነው፡፡ የገንዘብ ዝርፊያ፣ የዘመድ አሠራር፣ ዘረኛነት፣ ጉቦ፣ የመብት ጥሰቶች፣ ማታለል፣
ለሥልጣን መታገል፣ በገንዘብ መንፈሳዊ ሥልጣንን እና ሹመትን መግዛት፣ ኢሞራላዊ የሆኑ ድርጊቶች
የዕለት ተዕለት ወሬዎች እየሆኑ ነው፡፡
እነዚህ ነገሮች አደጋቸው ለእምነት ተቋማቱ ብቻ አይደለም ሀገራዊ ጉዳትም አላቸው፡፡ ከ90 በመቶ በላይ
ሃይማኖተኛ ነኝ ብሎ የሚያምን ሕዝብ ባለባት ኢትዮጵያ ውስጥ የእምነት ተቋማት ሚና ቀላል
አይደለም፡፡ የማኅበረሰቡ የሥነ ምግባር እና የሞራል እሴቶች ምንጭ እና ጠባቂ፣ አስተማሪ እና አወራራሽ
የእምነት ተቋማት ናቸው፡፡ የሀገሪቱን ቅርሶች አና ባህሎች የሚጠብቁ እነርሱ ናቸው፡፡ ለማኅበረሰቡ የበጎ
ነገር አርአያ በመሆን የሞራል ልዕልና የሚያጎናጽፉ ናቸው፡፡
ሕዝቡ ስለ እምነት ተቋማቱ እና መሪዎቹ ክፉ ነገር እየሰማ በሄደ ቁጥር ግን እነዚህ ነገሮች ይቀራሉ፡፡
ከእምነት ተቋማቱ ብቻ ሳይሆን ከአስተምህሯቸው፣ ከሞራል እና ሥነ ምግባር እሴቶቻቸውም ይሸሻል፡፡
ተቋማቱም ማኅበረሰቡን የመቅረጽ ሚናቸው ይቀንሳል፡፡
1
dkibret@gmail.com
yÄNx@L :Y¬ãC
Daniel kibret’s Views
www.danielkibret.com
ይህ ሁኔታ የአይከን ለውጥ ያስከትላል፡፡ ለጨዋነት፣ ለትኅትና፣ ለንጽሕና፣ ለታማኝነት፣ ለድንግልና፣
ለትዕግሥት፣ ለይቅር ባይነት፣ አርአያ ያደርጋቸው የነበሩት የእምነት መሪዎቹ ከዚህ በተቃራኒ ሰ!ያገኛቸው
ሌሎች አይከኖችን ያመጣል፡፡ በአውሮፓ እና በአሜሪካ የእምነት አይከኖች ሲጠፉ ሚዲያ የፈጠራቸው
አይከኖች ናቸው የተተኩት፡፡ አርቲስቶች፣ ዘፋኞች፣ የፊልም ተዋንያን፣ የፋሽን ሰዎች፣ ኳስ ተጫዋቾች፣
ወዘተ ቦታውን ተረክበዋል፡፡ እንግሊዛውያን ከሁለት መቶ ዓመታት በፊት በየመንደሩ የመንደሩ ጠባቂ
ቅዱስ (patron Saint) የሚሉት ነገር ነበራቸው፡፡ ዛሬ የመንደሩ ጠባቂ ቅዱስ በመንደሩ ታዋቂ የእግር
ኳስ ቡድን ተተክቷል፡፡
የኛም ሀገር ዕጣ ፈንታ እንደዚህ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ ሰዎች ወደ እምነት ተቋማት ሲሄዱ ከፍ ያሉ
ሞራላዊ ነገሮችን ያስባሉ፡፡ እነርሱ በዚህ ዓለም ሊያደርጓቸው ያልቻሉትን ሊያደርጉ የቻሉ ሰዎችን
ይፈልጋሉ፡፡ አርአያ ይሻሉ፡፡ የጽናት፣ የትዕግሥት፣ የብርታት፣ የአልሸነፍ ባይነት፣ ምሳሌ ይሻሉ፡፡ እነርሱ
እንደ ሰብአ ሰገል ሲመጡ እንደ አጥቢያ ኮከብ መንገድ የሚመራቸው ይመኛሉ፡፡
ይህንን ነገር ከማግኘት ይልቅ እነርሱ ሊያሸንፉት በሚፈልጉት ነገር፣ እነርሱ በተጸየፉት ነገር፣ እነርሱ
ሊጋደሉበት በሚሰለፉበት ነገር አርአያ ያደረጓቸው አካላት ተሸንፈው ሲያገኙ ሞራላቸው ይወድቃል፡፡
ተስፋም ይቆርጣሉ፡፡ አንዳንዶቹም እያደረጉት ያለው ነገር ትክክል ነው ብለው እንዲያስቡ ይሆናል፡፡
ዘመኑ የሚዲያ በተለይም የማኅበራዊ ሚዲያ ዘመን ነው፡፡ በዓለም ጫፍ የተተነፈሰች ነገር በሰከንድ ወደ
ሌላው የዓለም ጫፍ ትደርሳለች፡፡ እንደ ትናንቱ ነገሮችን ደብቆ ይዞ መኖር አይቻልም፡፡ ሰዎች
ይሰሙታል፣ ያታል፣ ይወያዩበታልም፡፡ ከዚህም በላይ ደግሞ ችግሩ እየተባባሰ እና እየጠነከረ ሲመጣ
የፍትሕ አካላትን በር ማንኳኳቱም የማይቀር ነገር ነው፡፡
dkibret@gmail.com
yÄNx@L :Y¬ãC
Daniel kibret’s Views
www.danielkibret.com
አንድ በር ሲከፈት በመጀመርያ የሚወጣበት እንጂ በመጨረሻ የሚወጣበት አይታወቅም ይባላል፡፡ ጉዳዮች
ወደ ፍርድ ቤት መድረስ ከጀመሩ ሌሎች የችግሮቹ ተጋላጮችም መንገዱን ይቀጥሉበታል፡፡ ይኼ ደግሞ
የእምነት ተቋማቱን ሥነ ምገባራዊ እና ሞራላዊ ልዕልና ያሳጣል፡፡
በቅርቡ አንድ መነኩሴ በአንድ የ15 ዓመት አዳጊ ልጅ ላይ በፈጸሙት የግብረ ሰዶም ተግባር ልደታ
የሚገኘው ከፍተኛው ፍርድ ቤት የ14 ዓመት ጽኑ እሥራት ፈርዶባቸዋል፡፡ ልጁ ድርጊቱ የተፈጸመበት
ቤተ ክርስቲያን ለመሳለም ሲመጣ መሆኑ ደግሞ ሁኔታውን እጅግ ከባድ ያደርገዋል፡፡
ይህንን የመሰለው ኢሞራላዊ ድርጊት ከሕዝቡ አልፎ ወደ እምነት መሪዎች ዘንድ መዛመቱ፣ የእምነቱ
መሪዎችም ሥልጣናቸውን፣ አባትነታቸውን እና ተሰሚነታቸውን ተጠቅመው እየፈጸሙት መሆኑ ለማኅ
በረሰቡ እና ለተቋማቱ የመንቂያ ደውል ነው፡፡ «ጨው ለራስህ ብትል ጣፍጥ፣ ያበለዚያ ድንጋይ ነው
ብለው አውጥተው ይጥሉሃል» እንደ ተባለው የእምነት ተቋማቱ ያላቸውን ቦታ ከማጣታቸው በፊት
ለዓላማቸው ሲሉ በፍጥነት ችግሮችን መፍታት ያለባቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡
በሌላም በኩል የእምነት ተቋማቱ በልዩ ልዩ የአገልግሎት ቦታ ያሠማሯቸውን አገልጋዮች ብዛት፣ ማንነት
እና ተግባር አያውቁም፡፡ በስማቸው የሚሠራውን ነገር የሚከታተሉበት መንገድ አልዘረጉም፡፡ ማነው
ባሕታዊ? ማነው መነኩሴ? ማነው ካህን? ማነው ዲያቆን? ማነው ሰባኪ? ማነው ዘማሪ? ማነው
ፓስተር? ማነው አስመላኪ? ማነው መጋቢ? ማነው አጥማቂ? በግልጽ የሚያውቅ የለም፡፡ እነዚህ
አካላት ለሚያደርሱትስ ጥፋት ተጠያቂው ማነው? እጅግ አጠያያቂ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ አባቶች ተሰባሰቡ ሲባል «ጸለዩ፣ ጾሙ፣ ተአምር አደረጉ፣ ሃይማኖት አሰፉ፣ ሥርዓት ዐጸኑ»
የሚለውን አይደለም ሕዝቡ እየሰማ ያለው፡፡ ተደበደቡ፣ ቤታቸው ተሰበረ፣ ማስፈራሪያ ደረሳቸው፣ ሰልፍ
ተደረገ፣ አልስማማ አሉ የሚለውን ነው፡፡ እገሌ የተባት አባት ይነሡልን፣ እገሌ የተባሉት አባት
አይምጡብን የሚል ምእመን በዝቷል፡፡ ወደ የአጥቢያው ሲሄድም ሙዳየ ምጽዋት ተዘረፈ፣ ሕንፃው
dkibret@gmail.com
yÄNx@L :Y¬ãC
Daniel kibret’s Views
www.danielkibret.com
በዘመድ ተሰጠ፣ እገሌ በጉቦ ተሾመ፣ እነ እገሌ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ መሬት ገዙ፣ ቤት ሠሩ፤ ንዋያተ
ቅድሳት ጠፉ፣ ተዘረፉ የሚለውን ነው እየሰማ ያለው፡፡
አሁን አሁን በማኅበረሰባችን ዘንድ የምንሰማቸው እና የምናያቸው የሥነ ምግባር ጥፋቶች እና ኢሞራላዊ
ድርጊቶች አንዱ መነሻ የሥነ ምግባር እና የሞራል አርአያ መጥፋት ሳይሆን አይቀርም፡፡ የእምነት ተቋማቱ
ዋነኛ ሥራቸው ትተው ንግድ ወደ ማስፋፋት፣ ገንዘብ ወደ መሰብሰብ፣ ሥልጣን ወደ መቀራመት እና
ቤት ንብረት ወደ ማፍራት ስለገቡ የሕዝቡን ሞራላዊ እና ሥነ ምገባራዊ እሴቶች የሚያስጠብቅ፣ አርአያ
የሚሆን እና የሚያሰርጽ እየጠፋ ይመስለኛል፡፡
በማኅበረሰባችን ዘንድ ግብረ ሰዶማዊነት እየተስፋፋ ነው፡፡ ሕፃናትን መድፈር እየተለመደ ነው፤ ፍች
የሰዓታት ዜና እየሆነ ነው፣ በወጣቶች ዘንድ ድንግልናን መጠበቅ ነውር እየሆነ ነው፤ ከዳቦ ቤቶች ይልቅ
ጫት ቤቶች እየበዙ ነው፤ ጉቦ ማሳፈሩ ቀርቶ እየተወደሰ ነው፤ አሲድ በሰው ላይ መድፋት፣ ዓይን
ጎልጉሎ ማውጣት፣ በቢላዋ የትዳር ጓደኛን ማረድ፣ ልጅን ቆራርጦ መግደል እውነት የሃይማኖተኛ ሕዝብ
ጠባያት ናቸውን?
የሀገሪቱ ሕጎችም የሃይማኖት ተቋማት እንደ ሕጋቸው ሳይሆን እንደፈለጉ እንዲሆኑ የሚያግዙ ናቸው፡፡
ገንዘባቸው ቁጥጥር አይደረግበትም፡፡ ግብር አለመክፈል እና ቁጥጥር አለማድረግ የተለያዩ ናቸው፡፡ ገንዘብ
በተዝረከረከበት ቦታ ሁሉ ወንጀል በልጽጎ መገኘቱ ደግሞ የማይቀር ነው፡፡ አወቃቀራቸው እና አሠራራ
ቸውን ዘመናዊ እንዲያደርጉ፣ የቁጥጥር ሥርዓት እንዲዘረጉ፣ አገልጋዮቻቸውን እና አባሎቻቸውን መዝግ
በው እንዲያውቁ የሚያስገድዳቸው ነገር የለም፡፡
dkibret@gmail.com