You are on page 1of 4

7ቱ ጥያቄዎችና ማብራሪያዎቻቸው

ጥያቄ 1፦ በሕገ-መንግሥት፣ በፖለቲካ ማኒፌስቶ፣ በመደበኛ ትምህርት፣ በሚዲያና መሰል


መንገዶች ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮንና ኦርቶዶክሳዊያንን ለጥቃት የሚጋልጡ መልዕክቶች
በአስቸኳይ በሕግ እንዲታገዱ ።
✓ የተዛባ ታሪካዊ ግኑኝነት የሚል ቃል የተጠቀሙት ሕገ-ምንግሥቱን ያዘጋጁ
የብሔር ፖለቲከኞች ናቸው።
✓ የብሔር ፖለቲከኞች የተዛባ የሚሉት በሕገ መንግሥት ያጸኑት ታሪክ አላቸው፤
✓ ኮሚኒስቶች ለሺ ዘመናት እሥራት ውስጥ ነበረች እንድተፈታ የቀደመውን ማጥፋት
አለብን ይላሉ፤
✓ በዚህ መሠረት ትምህርቱን፣ኪነቱን፣ ሚዲያውን፣ መዋቅሩን ተቆጣጠሩት፣
“ተዛባ” የባለው “ታሪክ” ከታሪካዊት ኦርቶዶክስ ክርስትና ክርስቲያን ማኅበረሰብ፣
ቅርሥ፣ ሀብት፣ ታሪካዊ ጀግኖች፣ መጽሐፍት፣ አስተመህሮ ጋር ተጣምሮ የማስወገድ
ዒላማ ተደረገ፤
✓ ኦርቶዶክሳዊነት ሀብት ለማደለብ፣ ለዲሞክራሲ የአስተዳደር ሥርዓት፣ ለዘመናዊ
አኗኗር፣ ለሥራ ስነ-ምግባር እንቅፋት የሆነ፣ የድኽነት ምክኒያት ናት፤ በቁስ
የደኸየ በሰማይም ተስፋ የለውም የሚል አስተምህሮ የሚያራምዱ ብዙዎችን
አሳስተው ኦርቶዶክስ-ጠል ለማድረግ ሠሩ፤ ከኮምኒስት የመደብ፣ የብሔረሰብ እና
የተጨቋኝ-ጨቋኝ የፖለቲካ ትግል ፅንሰ ሀሳብ ጀምሮ እሰክ ብልጽግ ፓርቲ
እስተሳብ ድረስ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊነትን ዒላማ አደረጉ፤ የአሁኑ ዘመን ፖለቲካም
ኦርቶዶክሳዊና አገር በቀል እሴቶችን በጀርመኑ ሉተርና በማክስ ዌበር ትምህርት
መተካት መበልጸግን እንደሚያስገኝ ይናገራሉ። ከዚያ ለውጥ ሁሉ ነባሩን
ማጥፋት ወደሚል ያዘነብላሉ
✓ በውስጥና በውጭ ይህን ዝንባሌ ተከትለው ነባር ኦረቶዶክሳዊነት ላይ የተመሠረቱ
ኢትዮጵያዊ እሴቶችንና ክርስቲያኖችን በማጥፋት የሚሳተፉ ሌሎች እምነቶችና
ባህሎችም የ[ፖለቲካውን ዝንባሌ ተከትለው ኦርቶዶክሳዊነትን በመዳከም
ጥቃቱን ይቀጥላሉ፣ ቀጥለዋል።
ጥያቄ 2፦ ኦርቶዶክሳዊያንን ለይቶ ከሥራ፣ ከመንግሥት ኃላፊነት፣ ከሀብት ማፍራት እድሎች
የሚያገል ከቀበሌ እስከ ፌደራል የተዘረጋው ሃይማኖታዊ መንግሥትና መዋቅር በአስቸኳይ
እንዲቆምና ሃይማኖታዊ ሳይሆን ሕዝባዊ መሆኑን በተግባር እንዲያረጋግጥ ።
o በርእዮት እና ደጋፊ ትርክት ላይ የተመሠረተ የኦርቶዶክሳዊነት ጥላቻን በተግባር
ለመተርጎም እንደ ምእራባዊያን የፌሚኒስት (የሴታዊት) ፖለቲካ “ካሣዊ ድረጊት
(አፊርማቲቭ አክሽን) በሚል ኦርቶዶክሳዊያንን ከአገራዊ ጥቅም ማገድ ተጀመረ፤
የገጠር መሬት፣ የከተማ የንግድ ቤቶች፣ የትምህርትና የሥራ እድል፣ የመንግሥት ቁልፍ
የሥልጣን ቦታዎች፣ የሚዲያ፣ የመረጃ፣ የፋይናንስ፣ ወዘተ መዋቅራት የኦርቶስ
ክርስቲያን ዜጋን ተሳትፎ በግልጽ በሚታይ ደረጃ ከሕዝቡ ብዛት በማይመጣጠን ደረጃ
ቀነሰ።
o የቱሪዝም ምልክቶች ለዓለም ኢግዚብሽን ሲቀርቡ የኦርቶዶክስ በዝቷል ብለው በቅዱስ
ላሉበላ ድንቅ ሕንጻዎች መትክ ቁልል እና ትክል ድንጋይ፣ ዋሊያና ዝንጀሮ ወይንም
ሉሲ አጥንት ምሥል አንዲቀርብ የሚከራከሩ የባህልና የቱሪዝም ኤክስፐርቶች
ይመደባሉ
o ሃይማኖት ማለት መጽሐፍ ቅዱስና ቁራን ላይ መመሥረት ብቻ አይደለም
o ርእዮት፣ ባህል፣ ፖለቲካ፣ --- ራሱ አምላክ ሰው ሆኖ ካስተማረው በላይ ራሱን ከፍ
የሚያደርግና ለመተካት የሚሠራ ሁሉ ሃማኖታዊ ነው
o መንግሥት ሃይማኖታዊ የሚባለው ምን ሲሆን
✓ ሕግን፣ ትምህርትን፣ ኪነትን፣ ምልክቶችን፣ ከአንድ የተወሰ አስተምህሮ ወስዶ
ሌላውን ለመተካት የሚሠራ ከሆነ
✓ የሕዝቡን ቁጥር ያላገናዘበ የሥልጣን ክፍፍል ተደርጎ የተወሰኑት ከተገፉ ---
✓ ሕዝባዊ ሲሆን መሪዎቹ የራሳቸውን እምነትና ርእዮት እንደያዙ የሚመሩትን ሕዝብ
ብዝኃ እምነት፣ ብዝኃ ባህል፣ ብዝሃ ፍላጎት ማዕከላዊ ጋርዮሻዊ ነጥብ ፈልጎና፣
o “ብልፅግና” የተባለው ከምዕረባዊያን ውሱን የፕሮቴስታንት ሴክት የተቀዳ የአሁኑ
መንግሥት መመወሪያ ሴኩላር አይደለም። ለኢትዮጵያነ ባህሎች፣እምነቶችና እሴቶች
ኤስማማም። በተለይ ኦርቶዶክስ እና ማንኛውምን ነባር እሴቶች የሚጠላና እንደ
ኮሚኒዝም በግዴታ ሕዝቡን መለወጥ የሚሞክር ርእዮተ ዓለም ነው። \ ለዚህ
ማሥረጃው፡- (1) የመደመር መፅሀፍ አጠቃላይ ይዘት፣ (2) የብልፅግና ማሰልጠኛ፣
(3) የፓርቲው ሎጎ፣ (4) የባለስልጣናቱ ማነነት ከነባር ኢትዮጵያዊ እሴት የራቁ
ሰዎች መመረጥ (ኦርቶዶክስ-ጠልነት)፣ (5) በንግግር፣ በአምልኮ ሥርዓት፣
በሚጠቀሙት ዜቤዎች ሁሉ ምዕራባዊና ወቅታዊነት፣ ብልጭልጭና ነባር-ጠልነትን
ማንፀባረቅ፣ (6) ጨካኔና ሐፍረተ-ቢስነት፡-ለሰው ልጆች ሞትና ስደት ድንታ
ማጣት፣ (7) የፓርቲው ስያሜው የብልፅግና መፅሀፍ ቅዱስ መመሪያዎች እና ስርአት
መሆን፣ (8) ድረጅታዊ መዋቅር ሳይሆን ኃይማኖታዊ መምሰሉ እና በሁሉ
እንቅስቃሴው ከኃይማኖታዊ ተቁዋማት ጋር ተፎካካሪ መምሰሉ፣ (9) በህልም እና
በትንቢት መመራት፣ (10) በኦርቶዶክሳውያን ላይ የተፈፀመው ጥፋት በቀጥታ
መርዳትና ፍትሕ መንፈግ፣ (11) በየደረጃውና በጊዜ ሂደት ሀገር አፍራሽ ሁኔታዎች
መጨመር፣ (12) ኦርቶዶክስን ለማጥፋት በኃላ ቀርነት፣ በጨቋኝነት መክሰስ፣
ቦታዋን መንጥቅ፣ በትምህርት ሥረዓትና በሕግ ደረጃ ማፈንና ማጥቃት ኦርቶዶክሳዊያን
ታሪካዊያን ለአገር አንድነትና ነፃነት የደከሙትን ስም ማጥፋት፣ ቤተ ክህነትን በብሔር
ዘውግ አንዲከፋፈል ክርስቶሳዊ ማንነትን በንዑስ ማንነት በሚለውጡ ምንደኞች ማመስ
ጥያቄ 3፦ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን በቋንቋና በተለያዩ ዘውጎች ለመከፋፈል የሚደረገው
ፖለቲካዊ ጥረት፣ በጥናትና በምርምር ስም የሚደረጉ የመከፋፈል ዘመቻዎች እና ተግባራት
እንዲታገዱ።
✓ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ አንድ ያደረገችውን የጥምቀት ልጅ በሥጋ ልጅነትና በስሑት
ርእዮት ማሳትና መበተን
✓ የተበተነውንና በንዑስ ማንነት የተሰለፈውን አንዱን ደግፎ ሌላው ነቅፎና ገፍቶ ማፋጀት
✓ መለያየቱ ዘለቄታዊና ሥር-ነቀል እንዲሆን ከውጭ ጠላት ጋር በመተባበር ሐሰተኛ
ትርክትና የፖለቲካ ትንተናዎችን መጻፍና ማሳተም፣ ድጋፍ ሰጭ ፖሊሲዎች ማውጣት፣
ኦርቶዶክስን አግለለው የሚሠሩ የቴሌዥናና ሌለቾ ሚዲዎች ማስፋፋት
✓ አገራዊ የኢኮኖሚ ችግር፣ የፖለቲካ ውጥንቅጥ፣ የማኅበረሰብ መፍረስና በፖለቲካ ሥርዓት
አስተዳደር ብልሽ ወይንም መቃናት ሊጠፉና ሊስተካከሉ የሚገቡትን ሁኔታዎች
ከኦርቶዶክስ ጋር ማገናኘት
ጥያቄ 4፡ -በኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠሩ የአካል፣ የሥነ-ልቦና፣ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣
የፖለቲካ፣ የማፈናቀል፣ ከአገራዊ ተሳትፎ የመገለልና የፍጅት ጥቃቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ።
✓ ከጂጂጋ እስከ አዲስ አባባ፣ ከባሌ እስከ ወለጋና ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ ከአጣዩ እስከ ጂማና
መቱ የተዘረጋ ምንግሥታዊ ኦርቶዶክሶችን የማፈናቀል ሂደት፣ ኦርቶዶክሶችን የማድኸየት፣
ከምንግሥት ኃላፊንተ ውጭ ማደረግ፣
✓ ጭፍጨፋና ማሳቀቅ
✓ ካህናትን መግደል
✓ ከልማት ግብአት አድልዎችና ልዩ ልዩ ቁሳዊ ትቅም ከእምንተ ማስወጣት
✓ የአገልግሎት ቦታዎችን፡- ገዳማት፣ የቤተክርስቲያን ቦታዎቸ፣ የመስቀልና የጥምቀተ ባሕር
ቦታዎችን በቀጥታ፣ ሲያስፈልግ ሌሎችን አደራጅቶ በመላክማስነጠቅ
ጥያቄ 5 ፦ እስከ አሁን የተፈጸመው ጥቃት በዝርዝር ተገልጾ አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ እና
የተጎዱት እንዲካሡ።
✓ በደርግ መውደቂያ ዋዜማ ኢሕአዴግና ኦነግ አሶሳ ሲደርሱ ከፈጸሙት ግድያ ጀምሮ
በበደኖና አርባ ጉጉ፣ በወተርና በዶዶላ፣ በቤኒሻንጉልና በወለጋ፣ በቡራዩና በአጣዬ ወዘተ
የቀጠለው ለይቶ የማጥቃት ሂደት ትኩረቱ ኦርቶዶክስ ላይ ቢሆንም ክርስቲያን ተባብሮ
እንዳይከላከል በአማራ ብሔር ስም “ነፍጠኛ” በሚል ኮድ ነው።
✓ ባለፉት 31 ዓመታት በተለይ ባለፉት 4 ዓመታት በእቅድ የተካሄደው ማፈናቀልና ግድያ
✓ እየተካሄደ ያለው ኦርቶዶክስን የመግፋት መንግሥታዊና መዋቅራዊ ትቃት በዝርዝር ታውቆ
መፍትሔ አልተሰጠውም--- ይሰጠው--- ቀጣይነቱ ይገታ
ጥያቄ 6 ፦ በመላው አገሪቱ የተፈናቀሉ ኦርቶዶክሳዊያን ወደ ቀደመ ቦታቸው እንዲመለሱ።
✓ የአገሪቱን የአሠፋፈር ስብጥር ከኦርቶዶክሳዊያን ለማጽዳት በርእዮተ ዓለምና በተለያዩ
እምነቶችና ባህሎች ጥምረት ከፍተኛ ማፈናቀልና ማሳደድ እየተካሄደ ነው። ይህ
የሚስተካከለው የተሳደዱት ወደ ነበሩበት ሲመለሱ፣ ለደረሰባቸው ጉዳት ሲካሱና
ወደተስተካከል ኑሮ፣ ማኅባረዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ሲመለሱ ብቻ ነው! ይደረግ
ጥያቄ 7 ፦ “አዲሲቷ ኢትዮጵያ” በሚል ሽፋን ኦርቶዶክሳዊ አሻራዎችን የመደለዝ ፖለቲካዊ
ሂደት በአስቸኳይ እንዲገታ እና በግልጽ ይቅርታ ተጠይቆ እርምት እንዲወሰድ።
✓ የሃይማኖት አሻራ መገለጫዎች ከቤተ መቅደስ ውች በሕዝብ ባህል፣ ጠባይ፣ ቁሳዊና
የማይዳሰሱ ቅርሶች፣ ድመፀትና ኪነጥበብ ይገለጣል። እንዲሁም የእምነቱ ተከታዮች
ያፈሯቸው የጦር ሜዳ ጀግኖች፣ የአስተዳደርና የአመራር አቅማቸው ለሰው ልጆች ነፃነት
አስተዋጽኦ ባደረጉ፣ ለአገር አንድነትና የህዝቦች ውሕደት አመራር በሰጡ፣ ውስብስብ
ፖለቲከዊና ዲፕሎማሰሳዊ ጥያቄዎችን በመለሱ ዜጎች ይወከላል።
✓ የሃይማኖት አሻራ በአስተዳደር፣ በሕግ፣ በባሕልና በማኅበራዊ የኑሮ ዘይቤም ይገለጣል።
✓ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ከላይ የተገለጡትን አሻራዎች ሁሉ ለመዋጋት ቀዳሚውን የማትለሸትና
የማውደም፣ ተቃራናዊውን የማግንና አዳዲስ የመትከል፣ የሐሰት ትርክትን የማሰራጨት፣
የመደበኛ ትምህርት ይዘትን በሐሰተኛ ትርክት የመበከል፣ ምልክቶችን የመድምሰስ ሥራ
ላይ በተጠመዱ ፖለቲከኞች ትመራለች።
✓ ይህ ሂደት ቆሞ በእውቀት፣ በማስተዋል፣ በሁሉም ዜጎች የእኩል ተሳትፎ አገር ይመራ!
ኦርቶዶክስን ማጥቃት ይቁም ነው!

You might also like