You are on page 1of 38

ቪጅን ሥነ-መለኮት ኮሌጅ

Vision Bible College

ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት

Ethics and Stewardship

Canada

Diploma Program
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ማውጫ
ክፍል አንድ: - ክርስትያናዊ ስነ-ምግባር (Biblical Ethics)
I. የስነ-ምግባር ታሪክ
II. ስነ-ምግባርና ማህበረሰብ
III. የስነ - ምግባር አማራጮች
IV. ክርስትያን ከባህል ጋር ያለው ግንኙነት
V. የክርስትያናዊ የስነምግባር መሠረቶች
VI. የስነምግባር ጉዳዮች (Ethical Issues)
VII. ክርስትያንና ፓለቲካ
VIII. የስራ ባህል
IX. መዝናኛና ስነ ምግባር
X. ጋብቻ (Marriage)
XI. ክርስትያንና ተፈጥሮ (Christians & Nature)
ክፍል :- ክርስትያናዊ ባለአደራነት
I. የባለአደራነት ትርጉም
II. ባለአደራነት በመጽሓፍ ቅዱስ እይታ
III. የባለአደራ ሐላፊነት
IV. የባለአደራነት መሥፈርት

V. ባላደራነት ኃላፍነት

Page 2
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ክፍል አንድ
ክርስትያናዊ ስነ-ምግባር (Biblical Ethics)
I. የስነ - ምግባር ታሪክ
ስነ-ምግባር የሚል ቃል ኢቲክ ከሚል የግሪክ ቃል ጋር እኩል ትርጉም ያለው ሲሆን ስለሰው
ባህርይና ፀባይ፣ ስለ ውስጣዊ ማንነት የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል ነዉ፡፡ ስነምግባር ፍፁምና
ልማድ እንዲሁም የአኗኗር ዘይቤ የሚቀረፅ መለኪያ ሲሆን ከግብረገብ ፈጽሞ የተለየ ትርጉም
ያለው ነው፡፡ ስነምግባር የእውነት ገጽታ ጋር የሚዛመድ ሲሆን በተለያየ ጊዜ በተለያዩ
አስተምህሮዎችና ፍልስፍናዎች ጫና ደርሶበት ያደገና አሁንም ያለ ትምህርት ነው፡፡

1.1. የቀደሙት የግሪክ ፈላስፎች


በዚህ ጊዜ የነበሩት ፈላስፋዎች ፕላቶና አርስቶትል ሲሆኑ ፕላቶ የሰው ትልቁ የመልካምነት
ስነምግባር መሆን የሚገባው “ደስታ” ሊያገኝበት በሚችል ጥበብ ውስጥ ሆኖ በግለሰቡ
ምክንያታዊነት መስራት የራሱን ድርጊት ሲፈጽም ነው ብሎ ሲናገር አርስቶትል ደግሞ የሰው
መልካምነት ግቡ ላይ መድረስ ሲሆን የሰው ግብ ደግሞ መልበካምነት ሲሆን ሰው ደስታን
የማግኘቱ ደረጃ እያደገ ሲሄድ “ራስን ወደማወቅ” ይደርሳል ብሎ ይናገራል፡፡

1.2. የመካከለኛወ ዘመን ፈላስፎች


በዚህ ዘመን ከነበሩ ምሁራን ደግሞ ቅዱስ አውግስትንና ቶማስ አክይንስ ሲሆኑ አውግስተን
የሰው የስነምግባር ትኩረት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆን እንዳለበትና ሰው በራሱ ጥረት ወደ
መልካምነት መድረስ እንደማይችል ይልቈንም የእግዚአብሔር ፀጋ እንደሚያስፈልገው የተናገረ
ሲሆን ቶማስ ከኪያንስ ደግመ ሕግንና ህብረተሰቡ በአንድ ላይ መልካምነት ማምጣት

Page 3
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

እንደሚችሉ ተናግሯል፡፡ ሕግ ኃጢአት ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ሰውን ወደ መልካም


ለማምጣት እና ትክክለኛ ቅርጽ እንዲይዝ ያደርጋል ይላል፡፡

1.3. ዘመናዊ ፈላስፎች


በዚህ ጊዜ የነበሩ ደግሞ ዴቨነሃምና አማኑኤል ከንት ሲሆኑ ሃሞ የሰው አይምሮ መፈራት
የስሜት ብስለት ከመሆን ስለሚያልፍ ልጠገብ የሚሆን ሰው በሚመጣው “መንስኤና ውጤት
ብቻ” መሆን እንዳለበትና የሚሰማውን ሲደረግ ነው ብሎ ሲናገር ካንት ደግሞ የሰው
መልካምነት በድርጊት ምክንያታዊነትና የሐላፊነት ስሜት ለመውሰደ ሲደረግና ድርጊቱ
ከተፈጥሮ ህግ ጋር እኩል ሲሆን ነው ብሎ ያስተምራል፡፡

II. ስነ-ምግባርና ማህበረሰብ


በዚህ ባለንበት ዘመን ማህበረሰባችን ፅንስ ለማስወረድ፣ ዘረኝነት፣ ሱሰኝነት፣ ቁማርተኝነትና
ሌሎች የስነ ምግባር ጥያቄዊች ላይ ግራ በማጋባት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከቴክኖሎጂ ዕድገትና
ማህበረሰባዊ ለውጥ ጋር ተያይዞ የስነ ምግባር ውድቀት የማይካድ እውነት ሆኗል፡፡
➢ ክርስቲያናዊ ንፅረተ አለም
ሁሉም የየራሱ የሆነ ግንዛቤ ቢኖረውም እንኳ እያንዳንዱ ሰው ግን ግንዛቤው መሰረት ማድረግ
የሚገባው መጽሐፍ ቅዱሳዊ በሆነ መመሪያ መሆን አለበት፡፡
➢ ፍፁም እውነት፡-
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስነምግባር ፍፁም በሆነ እውነት አለ በማለት የሚጀምር እንጂ መለኪያው
በግለሰቡ ነባራዊ ሁኔታ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡

Page 4
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

የስነ ምግባር ትምህርት የምናጠናበት ምክንያቶች ሦስት አሉ፡፡


1. ምዕራባውያን የባህል ለውጥና ተፅዕኖ እያደገ መምጣቱ
2. የሰዎች የተሳሳተ የስነምግባር ተግባራቶች እየሰፋ መምጣቱ
3. የስነምግባር ጉዳዩች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በመዋሃድ አካሄዱን ለማስተካከል

III. የስነ - ምግባር አማራጮች


ምንም እንኳ የተለያዩ አመለካከቶች ስነ ምግባር በንጽጽር መተያየት አለበት ብለው
ቢያስተምሩም ፍፁም የሆነና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያደረገ የስነምግባር አስተምህሮ
ማራመድ ተገቢ ነው፡፡

1. የባህል አንፃራዊነት (Cultural Relativism)


ይህ አመለካከት ሁሉ የሚደረግ የተለያየ የድርጊት ስራዎች በሚያደርጉት ህብረተሰብ
ተቀባይነት ያለውና በራሳቸው ባህል መሰረት ያፀደቁት እስከሆነ ድረስ ትክክል ነው በማለት
ማንኛውም የገብረገብ ተመክሮ ማውገዝ አንችልም፤ የግብረገብ መሰኪያም ማግኘት አንችልም፤
የግብረገብ አስተምህሮ ሁሉ በየህብረተሰቡ እውነት ነው በማለት ያስተምራሉ፡፡

2. ሁለንተናዊ ስነምግባር (Situational Ethics)


ይህ የስነምግባር ትምህርት በጆሴፍ ፋሊቸር የተስፋፋ ሲሆን ፍፁም የሆነ የግብረገብ
መሪሆዎች በማስወገድ የአንድን የስነምግባር መለኪያ ወይም ተቀባይነት ከድርጊቱ በኋላ ባለው
ውጤት ነው በማለት ያስተምራል፡፡

Page 5
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

2. ባህሪያዊ (Behaviorism)
ይህ አመለካከት ደግሞ ግብረገብነት ወይም የስነ ምግባር አስተምህሮ ወይም መለኪያ ለግለሰቡ
ተጠያቂነት ሊያደርገው እንደማይችል፣ ግለሰቡ የሚያደርገው ድርጊት በማህበረሰቡ ተፅዕኖ
የአካባቢው ወይም የዘር ውጤት እንጂ የራሱ አይደለም፡፡
ፍፁም የሆኑ የስነ ምግባር ገፅታ
ይህ አመለካከት ለማንኛውም የግብረገብና መልካምነት ስነምግባር ፍፁም መለክያ አለ በማለት
መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ እግዚአብሔር ያስቀመጠው መለክያ የሚያስቀምጡ ናቸው፡፡ ከነዚህም
የመጽሐፍ ቅዲስ እውነቶች፤
1. እግዚአብሔር በቃሉ የገለጠው ግብረገብ የባህሪው ነፀብራቅ፡፡
2. የእግዚአብሔር የግብረገብ መመሪያዎች በውጫዊ ድጋፍ ላይ ከመስራት ይልቅ በውስጥ
ተነሳሽነት ፣ በግል አስተሳሰብ ላይ ይመሰረታል፡፡
3. የእግዚአብሔር የሰዎች እሴት የሚወሰንበት ፍፁም መለኪያ ሰጥቷል፡፡

IV. ክርስትያን ከባህል ጋር ያለው ግንኙነት


ክርስቲያኖች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የዓለም ተፅዕኖ ሊደረስባቸውና ችግር ውስጥ ሊገጥማቸው
ይችላል፣ ነገር ግን ከዓለም ጋር አብረን በመኖር ወንጌል መመስከር እንዳለብን መጽሐፍ
ቅዱሳዊ ነው፡፡ እነዚህ የሚታረቁበት የተለያዩ መጽሐፍ ቅዱሳዉ ሞዴሎች አሉ፡፡

1. የመለየት ሞዴል /‘’Separation Model’’/


ክርስቲያን ከዓለም ካለው ማንኛውም ግንኙነት መለየት እንዳለበት የሚናገር ሲሆን የአብርሃምና
የሙሴ እንዲሁም የኖህ መርህ የሚከተል አስተምህሮ ነው፡፡

Page 6
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

2. የመመሳሰል ሞዴል /‘’Identification Model’’/


ይህ አመለካከት ደግሞ ክርስትያን በዚች አለም እስከኖረ ድረስ በዓለም ባህል፣ ፓለቲካ፣ ንግድ፣
ኪነጥበብ ወዘተ… በመመሳሰል መስራት እንዳለበትና የዮሴፍ፣ የዳንኤልና የጳውሎስ ፈለግ
በመከተል የሚያስተምር ነው፡፡

3. የመለወጥ ሞዴል /‘’Changing Model’’/


ይህ አመለካከት ደግሞ ክርስትያን በዓለም ውስጥ ሆኖ ዓለምን መለወጥ እንዳለበትና
የሚለውጥ የወንጌል ኃይል በማቅረብ የእግዚአብሔር ኃይል በማወቅና በመገንዘብ መኖር
እንዳለባቸው የሚያስተምር ነው፡፡

4. የተሳግዎ ሞዴል /‘’Incarnational Model’’/


ይህ ደግሞ የክርስቶስ ፈለግ የሚከተል ሲሆን ሰው ከዓለም ክፉ ከሆኑ ነገሮች በመራቅ
ከማህበረሰቡ ግን ራሱን በማዛመድ የህብረተሰቡ ቦህልና ስርዓት የመለወጥ መንገድ
ያስተምራል፡፡

V. የክርስትያናዊ የስነምግባር መሠረቶች


የክርስትያን ስነምግባር የሚያልፈው በተለያዩ የመፅሐፍ ቅዱስ መርሆዎች ላይ ነው፡፡
1. ፍቅር፡- ክርስትያን የግብረ ገብነት ባህሪ ሊኖረው የሚገባ ቢሆንም እንኳ መሰረቱ ግን
በፍቅር የተመሰረተ መሆን እንዳለበትና ይህ ፍቅር ደግሞ እግዚአብሔር ሰዎችን
በወደደበት በመለኮታዊ ፍቅር መሆን እንዳለበት ያስተምራል፡፡

Page 7
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

2. ፍትህ፡- ፍትህ የሚለው ቃል በመፅሐፍ ቅዱስ ከ 100 ጊዜ በላይ የተፃፈ ሲሆን


ከዋነኛዎቹ የክርስትያን ስነምግባሮች አንዱ እንደሆነና የእግዚአብሔር የፅድቅና
የእግዚአብሔር ሐሳብ የምንፈፅምበት ባህሪ ነው፡፡
3. ታማኝነት፡- ታማኝነት የክርስትያን ስነምግባር ሆኖ የምንሰራው ስራ ለጌታ
እንደምንሠራው በማመን ስንሰራ ነው፡፡
4. ቅንነት፡- ደግሞ የምንሰራው ነገር ሁሉ በየዋህነትና በገርነት መስራት ያለብንን ነገር
የሚያሳይ ነው፡፡

VI. የስነምግባር ጉዳዮች (Ethical Issues)


ፅንስ ማስወረድ (Abortion)
ፅንስ ማስወረድ በጣም አከራካሪ ከሆኑ ስነምግባሮች አንዱ ሆኖ በጥንቱም ዓልም ጀምሮ የነበረ
ሲሆነ ለእስራኤላዉያን በቀድሞ የቤተክርስትያን ታሪክ ተቃውሞ የነበረው ነው፡፡ በ1870ዎቹ
የፅንስ ማስወረድ የተቃውሞ ሕጎች የወጡ ሲሆኑ ነገር ግን በ1970 በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ
ፅንስ ማስወረድን ፈቀዱ፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፅንስ ማስወረድ የራሱ የሆነ መመሪያ በግልፅ ባያስቀምጥም እንኳ ከልደት
በፊት ያለ ህይወት ልክ እንደተወለደ ህፃን ተቀባይነት ያለው በመሆነ፣ ፅንስ የእግዚአብሔር
ሉዓላዊ ኃይል የሚገለጥበት በመሆኑ ማህፀንን የሚዘጋና የሚከፍት እግዚአብሔር ብቻ
በመሆኑ እንደ ነውርና እንማደይፈቀድ ያስተምራል፡፡ ሌሎች ከመፅሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ ውጪ
የሆኑ የፅንስ ማስወረድን የሚቃወሙ ሀሳቦች ቢኖሩም የቤተክርስትያን ሞላሽ መሆን ያለበት
እንደ የህይወት መታደግ፣ ስለ ሌሎች መፀለይ፣ ለሌሎች መደገፉ የመሳሰሉት ነው፡፡

Page 8
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

በእስራኤላውያን ዘንድ ጽንስ ማስወረድ የማይታሰብ እና ከባድ ድርጊት ተደርነጐ ይወሰድ ነበር፡፡
ምክንያቱም፡ -
1. ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ መሆናቸው ስለሚታወቅ - መዝ 127፥3
2. ማህፀን የሚከፍትና የሚዘጋ እግዚአብሔር ስለሆነ - ዘፍ 29፥ 31 1ሳሙ 1፥14-20
3. ልጅ ማጣት እንደ እርግማን ይቆጠር ስለነበር - ዘዳ 25፥6 ሩት 4፥5

ግብረ - ሰዶማዊነት
ምንም እንኳ ግብረ ሰዶማዊነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢመጣም መጽሐፍ ቅዲስ
እንደሚያስተምረን ግን ግብረ ሰዶማዊነት የእግዚአብሔር ሓሳብና ፈቀድ አለመሆኑ ፣
እግዚብሔር ከሰዎች ለጋብቻ ውስጥ መጣመር ያለባቸው በተቃራኒ ፆታ ብቻ መሆን
እንዳለባቸው፣ ወንድ አባቱንና እናቱን እንደሚለው፣ አንድ ስጋ እንደሚሆኑና እንደሚጣበቁ
ይናገራል፡፡ በጋብቻ ውስጥ የሚደረግ ግብረ ወሲብ ተቀባይነት ያለው ፣ በግብረሰዶማዊነት
የእግዝአብሔር የድቅ ፍርድ እንደሚመጣና ከመፅሐፍ ቅዱሳዊ ንፁህ ትምህርት እንደሚቃረን
ይናገራል፡፡

ምንም እንኳ በምዕራባውያን ውስጥ ያሉ አብያተክርስቲያናት በአንዳንድ ላይ ግብረሰዶማዊነት


ቢቀበሉም እውነተኛዋ ቤተክርስትያን ገና ለግብረሰዶማዊያን በፍቅርና በትዕግስት በማየት
ግብረሰዶማዊነት ግን መፃረር አለባት፡፡ ቤተክርስትያን ማድረግ ያለባት በግብረሰዶማውያን ላይ
ያላት ዕይታ ሲሆን ልክ እንደ ማንኛውም ሐጢያት እንደ ኃጢያት በማየት ለኃጢያት ደግሞ
ይቅር የምትልና የምትሸፍን ለመሆን ይህን ሊያሸንፍ የሚችለው የእግዚአብሔር ይልና ፀጋ
ለመቀበል መፀለይ አለባት፡፡

Page 9
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ምስለ ወሲብ (Phonography)


ምስለ ወሲብ ማለት ወስባዊ ስሜትን የሚያነሳሳ ወሲብ ነክ ዕይታ ሲሆን በተያዩ ማንገዶች
በመሰራጨት የተለያዩ ችግሮች የሚያመጣ ነው፡፡ ከነዚበህ ችግሮች ስነልቦናዊ ችግሮች፣ በሱስ
የመያዝ ችግርና ወዘተ ናቸው፡፡ ምስለ ወሲብ የሚያመጣባቸው ችግሮች ብዙዎች ቢሆንም
እንኳ ወላጆች ለልጆቻቸው መፅሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት በማስተማር፣ ከወሲባዊ ዕይታዎች
መራቅ፣ መጋቢዎች ትክክለኛ የወሲብ ትምህርት በማስተማር፣ ምዕመኑንና ማህበረሰቡን
በመከታተል ከችግር ማላቀቅ አለብን፡፡

VII. ክርስትያንና ፓለቲካ


ልክ እንደ ሌሎች የፓለቲካ ጉዳይም በክርስትና አከራካሪ ጉዳይ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ነገር ግን
መጽሐፍ ቅዲስ በቂ በየሆነ ግንዛቤ ይሰጣል፡፡ ክርስቲየን ለአገሩ ኃላፊነት እንዳለበት (ማር
12፡13-17) ፣ ለአገር መንግስት መገዛት እንዳለብን፣ በመንግስት ጉዳዮች እግዚአብሔር
በመፍራት ፀጥና ዝግ ብለን መኖር እንዳለብን ይናገራል፡፡
ስለዚህ መጽሐፍ አራት የክርስትያን ግዴታዎች እናያለን፡፡ እነርሱም፡-
1. አማኝ መንግሥትን ማክበር አለበት (ሮሜ 13፥7)
2. አማኝ በአገሩ ለሚወጡ ህጎች መታዘዝ ይጠበቅበታል (ቲቶ 3፥1 1ጴጥ 2፡13-17 ፣
ሮሜ 13፡1-7)
3. አማኝ ታክስ (ግብር) መክፈል አለበት (ማቴ 22፡15-22)
4. አማኝ በስልጣን ላይ መፀለይ አለበት (ሐዋ 2፡1)

Page 10
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ክርስትያን ለፓለቲክ ውስጥ የፅድቅ ተፅዕኖ ለማሳደር ህይወት ክቡር መሆኑ ታሳቢ ለማድረግ፣
ለሃይማኖታዊ ዕጩ የሚቃወም ስርዓት በመቃወም ፍትህና ቅድስና (ፅድቅ) በማስፈን
ታደኝነት፣ ትዕግሥት፣ ተጠያቂነት የመሳሰሉትን በማስፋፋትና በመተግባር ድርሻው መውጣት
አለበት፡፡

IIX. የስራ ባህል


መጽሐፍ ቅዱስ የስራ የሆነ ዕይታ ያለው ሲሆን ስራ ከእግዝአብሔር ዘንድ የተሰጠ ስጦታ
እንደሆነ ሰው በኃላፊነትና በመቀበል በመስራት እንዳለበት ያስተምራል፡፡ የስራ ስጦታ ሰው
ከመውደቁ በፊትም ጀምሮ እንደተሰጠና የሰው ልጅ ልዩ ስጦታ እንደሆነ ያስተምራል፡፡ ስራ
ከሦስት የስራ ስነምግባር መርሆዎች እንዳሉ ይነናገራሉ፡፡ እነርሱም ታማኝነት፣ የክርስቶስ
ጌትነት እና የእግዚአብሔር የብድራት ክፍያ ናቸው፡፡

ከዚህ የተነሳ መፅሐፍ ቅዱስ ሁሉ ሰው ስራ መስራት እንዳለበት፣ ለስራ ታዛዥና አክብሮት


መስጠት እንዳለበት፣ ማንኛወም ስራ ሕጋዊና መፅሐፍ ቅዱሳዊ እስከሆነ ድረስ መስራት
እንደሚቻል በስራ ውጤት (እንዲደረግ) ወንጌል መመስከር፣ ስራ ራሱ የአምልኮ መንገድ
እንደሆነ ያሰተምራል፡፡

IX. መዝናኛና ስነ ምግባር


መዝናኛዎች መልካም ነገር እንዳለባቸው ሁሉ ጎጂ ነገርም ሊኖራቸው ግድ ነውና በአሜሪካ
በተደረገው ጥናት ሰዎች ብዙ ጊዜያቸውን በማግሰን ላይ ትልቅ ጉዳት እንደሚያደርስ
ያመለክታሉ፡፡ በተለይ ለብዙ ጊዜ ቴሌቭዥንን በመመልከት በጭንቅላት ላይ የሚያመጣው
ጠጭንቅላት ሞገድ (Braihlwave) በተጨማሪ ጊዜያችንን በማባከን፣ ባህሪያችን በመወሰን፣

Page 11
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

እውነታውን የመገንዘብ ጥቅም ለማባዛት፣ ለግብረ ገብ ያለንን ጥንቃቄ ለማጥፋትና ትርጉም


ያለውን የቤተሰብ ህይወት በማዛባት ትልቅ ጉዳት አለበት፡፡

አንድ ክርስትያን ማድረግ ያለበት የመፅሐፍ ቅዱስ መርሆዎች ማለት የጊዜ ባለአደራነት
መርህ፣ ራስን የመግዛት መርህ፣ የሞራላዊነትና ንፅህና መርህ፣ የማነፅ መርህና የእግዚአብሔር
ክቡር መሰረት ለማድረግ መሆን አለበት፣ ስለዚ ሰው መዝናኛ የማድረግ ሞርጨ በማድረግ ላይ
ንቁ በመሆን፣ የቤተሰብ መዝናኛዎች በመሞረድ፣ ዝርዝር ፕሮግራሞች በጥንቃቄ ማንበብ፣
የገንዘብ የመዝናኛ ወጪ ማስላት፣ ቴሌቭዥን ማጥራት መለማመድ ወዘተ ማድረግ አለበት፡፡

X. ጋብቻ (Marriage)
በክርስትያኖች መካከል ለክርስትያናዊ ጋብቻ መካከል ባለው መረዳት የተለያየ ሲሆን ለጋብቻ
ጋብቻ ሊያደርገው የሚችል ጉዳይ የጋብቻ መፍረስ ጉዳይ ለጋብቻ የቤተክርስትያን ኃላፊነት
መሆን ያለበት ምንድነው ለሚሉ ዙነያ ላይ የተለያየ አመለካከት አለባቸው፡፡ ጋብቻ ለአንድ
ወንድና ሴት መካከል የሚደረግ ዘላቂነት ያለው የህይወት ዘመን ትስስር ነው፡፡ ስለዚ
የእግዚአብሔር ኃሳብ እግዚአብሔር ራሱ ያጣመረውን ማንም አይፈታው ከሚል ጋር
ስለሚቃረን ፍቺ የእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ እንዳይደለ እንረዳለን፡፡ በተለያየ ግዜያት
የተለያዩ ሙሁራኖች የተለያየ አመለካከታቸውን አስፍረዋል፡፡

በካቶሊክ ቤተክርስትያን ጋብቻ ምስጥር እንደ ሆነና የጋብቻ መፍረስ የማይቻል አጀንዳ እንደ
ሆነ ስታስተምር የነበረች ስትሆን የተሃድሶ አራማጆች የሆኑት ግን በአንፃሩ ጋብቻ ምስጥር

Page 12
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

መሆኑና መፍረስ አይችልም ለሚል ሐሳብ እንደማይቀበሉት ተናግረዋል፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ


ዕይታ ጋብቻ ልንረዳው የሚገባን እንደ ኪዳን ነው፡፡ ኪዳን የግንኙነት ማብራሪያ ሲሆን በተስፋ
ላይ የሚመሰረት መሠጠት በእህዛብ የሚታወቅ የሚያድግ ነው፡፡ ጋብቻ ለኪዳን ዓይን ሲታይ
ጠንካራ፣ ተቀባይነት ያለውና የሚያድግ ግንኙነት ያደርገዋል፡፡ መፅሐፍ ቅዱሳዊ የጋብቻ
ባህሪያት ስንመለከት በታራኒ ፆታ መካከል የሚደረግ፣ በህዝብ ፊት ዕውቅና ያለው፣ ዘላቂ፣
የስጋ ግንኙነት ያካተተ ነው፡፡

XI. ክርስትያንና ተፈጥሮ (Christians & Nature)


እግዚአብሔር ፍጥረታትን ስፈጥር የሰው ልጅ በተገቢና በትክክለኛ መንገድ እንዲንከባከበውና
የተስተካከለ ዕይታ ኖራት ጤናማ ግንኙነት ለመመስረት ሲሆን ነገር ግን የሰው ልጅ የተለያየ
አመለካከት ከመኖሩ የተነሳ የተለያዩ ጉዳዮች እየታዩ ይገኛሉ፡፡ አንዳንድ ምሁራኖች ሁሉም
ፍጥረት እኩል ናቸው የሚል አመለካከት ያላቸው ሲሆኑ ከመፅሐፍ ቅዱሳዊ ዕይታ የሚቃረን
ሐሳብ የያዙ ናቸው፡፡

ሌሎች ደግሞ ሁሉም እግዚአብሔር ነው እግዝአብሔርም ሁሉን ነው የሚል አመለካከት


ያላቸው ሲሆኑ ምንም አይነት ፍጥረት መጥፋት የለበትም በለት ይከራከራሉ፣ አንዳንዶችም
ቁሳዊ ፍጥረት ሁሉ ለመንፈሳዊዉ አለም ክፉና የሚያስፈልግ ነው ከሚል ሐሳባቸው የተነሳ
ቁሳዊ ነገሮች ሁላቸው ማጥፋት እንደተገቢ ነገር ይቆጥራሉ፡፡

ነገር ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ ክርስትያናዊ መሰረት ያደረገ ዕይታ ሲኖረን ማስተካከል የሚችል
ሐሳብ እስከሆነ ድረስ ስለ እግዚአብሔር ስለ ፍጥረት ሚዛናዊና መፅሐፍ ቅዱሳዊ አለካከት
ሊኖረን እንዲሁም ስለፍጥረትና ሰውልጅ ግንሀኑነት ትክክለርመረዳት አለብን፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ

Page 13
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

እንደሚያስተምረው የሰውልጅ ለመልካም ባለአደራነት በመነሳት በአካባቢው ለሚከሰቱ ችግሮች


መፍትሔ ማምጣት ለመቻል በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ትክክለኛ ግንኙነት መፍጠር ፣
አለበት፡፡

የዘመኑ የስልጣኔ አካሄድ በአካባቢው የመሮት መለወጥና የመስፈሪያ ውድመት እንዲሁም


የዝሪያ መጥፋት ዋና ምክንያት በመሆን የተፈጥሮ ቅርፅ የባህል መዛባት እያስከተለ የሚገኝ
ከባድ ሸክም ከመሆኑ የተነሳ የሰው ልጅ ሁሉ ትክክለኛና የእግዝአብሔር ዓላማ መሪ ያደረገ
በመያዝ ከአካባቢው ጋር ያለው ግንኙነት ማስተካከል አለበት፡፡

ክፍል

ክርስትያናዊ ባለአደራነት

Page 14
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

መግቢያ

በዓለምም ይሁን በጌታ ቤት ባለአደራ ሰዉ ይፈለጋል፡፡ ባለንበት ዘመን በጥንቃቄ ስንመለከት


ብዙ አማኞች በምድር ላይ የአንግድነትን ሕይወት አየረሱ መምጣታቸዉ የባለአደራነት
ሕይወትን እየረሱ እንዲመጡ አድርጓቸዋል፡፡ ባለአደራነትን ማወቅ እንደ ክርስቲያን በምድር
ላይ የሚኖረንን ሕይወት ከልቅነት ሰብሰብ ወዳለ ማንነት እንድንመጣ ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ
ተጠያቂነት መኖሩን እያሰበን በጥንቃቄ እንድንመላለስ ያስችለናል፡፡ ብዙ ጊዜ በክርስትና
ሕይወት ማወቅ ያለመፈለግና እዉቀት የማጣት ችግር ብዙ ነገር እንድናበላሽ ያደርገናል ፡፡
ከዚህ አንጻር የባለአደራነትን ትርጉም አለማወቅ ግን ያላዋቂ እጥፊ እንድንሆን አድርጎናል ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አሁን ባለችዉ ቤተክርስቲያን ዉስጥ አልፎ አልፎ እንደምናየዉ


እግዚአብሔርን አለመፍራት ፣ እንደልብ መመላለስ ፣ ገደብ የለሸ ኑሮ ዉስጥ መግባት ፣
አገልጋይ ሆነን ከምናገለልላቸዉ ምዕመናና አኮኖሚ ወጣ ያለ አኮኖሚያዊ አቅም ዉስጥ
መግባት ፣ ለእገዚአብሔር ቤት ገንዘብ ታማኝ አለመሆን ምልክቶች የባለአደራነትን መንፈስ
የማጣት ዉጤት ነዉ፡፡

የባለአደራነት ሕይወት ተረስቶ እዉነተኛ አገልጋይነት ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ብድራትን


የሚያሰጥ አገልጋይ ይኮናል ብሎ ማሰብ በጣም ሞኝነት ነዉ፡፡ በርግጥ አሁን በአንዳንዶች ዘንድ
የሚታየዉ የአገልግሎት ሒደት ብድራትን እንደሙሴ ከመመልከት ይልቅ እና ለባለአደራነት
ሕይወት ዋጋ ከመስጠት ይልቅ በየትም መንገድ ይሁን የምንፈልገዉን ማግኘት የአገልግሎትና
የሕይወት ስኬት መለኪያ እየሆነ መምጣቱ በግልጥ የሚታይ ነገር ነዉ፡፡ የባለአደራነት
ሕይወት ወሳኝ ግቡ ለተረዳ ሰዉ ባለአደራነት ቀንበር የሚጨምር እንጂ የሚያዝናና አይደለም፡፡
ባለአደራ ከሚኖረዉ ሕይወት ጀምሮ እስከሚገለግለዉ አገልግሎት ድረስ የሚያደርገዉን ሁሉ
በጥንቃቄ ለጌታ ክብር ያደርገዋል፡፡
Page 15
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

I. የባለአደራነት ትርጉም

ክርሰቲያናዊ ባለአደራነት የሚጀምረዉ ህይወት ራሱ የእግገዚአብሔር ስጦታ መሆኑን ከማወቅና


እግዚአብሐር ደግ ሰጪ መሆኑን ከማወቅ ይጀምራል፡፡ ይህ መረዳት ሲኖረን ሁሉ ነገር ስጦታ
መሆኑን እንረዳለን፡፡ እኛና የእኛ የሆነ ነገር ሁሉ ማለትም ኑሮአችን ፣ ክህሎታችን ፣ የፈጠራ
ችሎታችን እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸዉ፡፡

ከዚህም የተነሳ እኛ ለምናደርገዉና ለምንሰራዉ ሥራ ምላሽ የምንሰጥና ሐላፊነት ያለብን


ሰዎች ነን፡፡1 የማንኛዉም ነገር ትርጉም መዛባት የሕይወት ዋጋ አሰጣጣችንን የኑሮ
ዘይቤያችንን የሕይወትና የአገልግሎት ፍልስፍናችንን ሙሉ በሙሉ ይጎዳዋል ተጽዕኖም
ያደርጋል፡፡

ስለ ባለአደራነት ወደ ዝርዝር ትርጉም ሐሰብ ከመሄዳችን በፊት ቃሉን በጥንቃቄ ማወቅ


ያስፈልጋል፡፡ ባለአደራነት የሚለዉ የአዲስ ኪዳን ቃል መሰረቱ ግሪክ ስሆን ”oikonomia,”
ኦይኮኖሚያ ከሚለዉ ቃል የወጣ ነዉ፡፡ ይህ ቃል ኢኮኖሚ ለሚለዉ ቃል መሰረት ነዉ፡፡
ባለአደራ የሚለዉ ቃል በቤት ዉስጥ ያለዉን በሐላፊነት የሚቆጣጠር በባለቤቱ ዘንድ
የሚታወቅ ሐለፊነት የተሰጠዉ ሰዉ ማለት ነዉ፡፡

ባለአደራነት ቃሉን ስንመለከት የማስተዳደር ሐለፊነትን የሚያመለክት ሲሆን ፤ ባለአደራ ሙሉ


በሙሉ ለጌታዉ ተጠያቂ እና ተጠሪ እንደሆነ በትክክል የገባዉ ሰዉ ማለት ነዉ፡፡ ዘፍጥ 39 ፡

1
--------- Christian stewardship as a way of life. Retrieved from, http://WWW.stewardship.diosohio.org
at 10/9/2016.

Page 16
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

4-6 በሌላ መልኩ ጌታችን ኢየሱስ በምሳሌ እንደተናገረዉ የጌታዉን ሃብት እንዲስተዳድር
ጌታዉ ታማኝ አድርጎ የቆጠረዉ ሰዉ ነው፡፡ ሉቃ 16 ፡1-13

ባለአደራ ኑሮው ፣ ሕይወቱ እና የዋጋ አሰጣጡ በአጠቃላይ ከባለአደራነት ጋር የተያያዘ ነዉ፡፡


አልፎ አልፎ እንደምንመለከተዉ የእግዚአብሔር ጸጋ በሙላት የተገለጠባቸዉ ፣ እግዚአብሔር
ለራሱ አላማ የባረካቸዉ እና የተለያየ ስጦታና ችሎታ በዉስጣቸዉ ለራሱ ዓለማ
ያስቀመጠባቸዉ ሰዎች የባለአደራነት ትርጉም ስለጠፋባቸዉ ስህተት ዉስጥ ሲገቡ ይስተዋላሉ፡፡
የትርጉም ስህተት ሙሉ ስሕተት ዉስጥ ሊመራ ይችላል፡፡

ከሰዉ አንጻር ባለአደራ በጊዜ ብዛት ታማኝነቱ የተፈተነ የባለቤቱ ተወካይ ሆኖ እንዲሰራ
በባለቤቱ እምነት የተጣለበት አገልጋይ ነዉ፡፡ ባለአደራ ሐለፊነት የሚሰማዉ አገልጋይ እንጂ
አለቃ ነኝ ባይ ፣ አትንኩኝ ባይ ፣ ማንም ሊጠይቀኝ አይችልም ባይ አይደለም፡፡ ባለአደራ
የባለቤት ሙሉ ተወካይ እንጂ ባለቤት ሊሆን ፈጽሞ አይችልም፡፡

ባለአደራ የተሰጠዉን ሓላፊነት በብቃት እንዲፈጽም የሚጠበቅበት ሰዉ ነዉ፡፡ ይህ ማለት


ባለአደራ ሥራ መሥራቱን ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅበትን መሥራቱን ትኩረት ሰጥቶ ሊያስብበት
ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መሞቱ አካባቢ በእግዚአብሔር አብ ሊሠራ የተገባዉን ስራ
ሁሉ አጠናቆ እንደሰራ እንመለከታለን (ዮሐ 17 ፡ 4-5):: ባለአደራ እንደ ተቀጣሪ ሥራ
መስራቱን ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንገድ ወይም አደራ በተሰጠዉ መስመር ሥራ
መስራቱን ያስተዉላል ፡፡

ባለአደራ ስራን ፣ ስጦታን ፣ እቃዎችንና በአደራ የተሰጡትን ነገሮች ከሙሉ ስልጣን ጋር


የተሰጠዉ የባለቤቱን ልብ ማሳረፍ የሚችል ተአማኒነትን ያተረፈ ሰዉ መሆን አለበት፡፡
ስልጣንን በተመለከተ ባለአደራና በለአደራ ያልሆነ ሰዉ እኩል አመለካከት ይኖረዋል ተብሎ

Page 17
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

አይታሰብም፡፡ ባለአደራ ስልጣንን እንደ ኃይል ማሳያ ሲመለከት ባለአደራ ግን ሥልጣንን


የእግዚአብሔርን ጉዳይ ማስፈጸሚያ መሣሪያ አድርጎ ይመለከታል፡፡

ባለአደራ የትም ይቀመጥ የት በምንም መለኩ የባለቤትነት ስሜት የማይሰማዉ ሰዉ ነዉ፡፡


አንዳንዴ የባለአደራ ዉስጥ ስሜቱ ”ባለቤት ነህ" የሚል መልዕክት ቢያስተላልፍም ሰዎች
ስሙን እና ዝናዉን ቢያዉጁለትም ባለአደራ መሆኑን እንጂ ባለቤት መሆኑን በምንም መልኩ
አይቀበልም፡፡ ዛሬ ዛሬ ጸጋ ስጦታዎችና ቤተክርስቲያን በግለሰብ ስም ሲጠሩ በድርጊት
ስንመለከት ፣ በቤተክርስቲያን ዉስጥ በባለራዕይ የሚባለዉ ሰዉ ፈላጭ ቆራጭ ሁኖ ወደ
አምላክነት ሲለወጥ ፣ የክርስቶስን የቤተክርስቲያን ራስነት በሰዉ ሲተካ ምን ያህል ባለአደራነት
ከቤተክርስቲያን እየጠፋ እንዳለ ምልከቶች ናቸዉ፡፡

እዉነተኛ ባለአደራ እግዚአብሔር ባሰቀመጠዉ ስፍራ ሳያጉረመርም ደግሞም ሳይዝናና


ሥራዉን እና አገልግሎቱን ከእግዚአብሔር ጋር እያያዘ በጥንቃቄ የሚመላለስ አገልጋይ ነዉ፡፡
ባለ አደራ ሥራ መስራቱን ወይም ሥራ መሰራቱን ብቻ ሳይሆን ጌታዉ በፈለገዉ መስመር ስራ
መስራቱን በጥንቃቄ ይመለከታል፡፡ ከዝህም የተነሳ ባለአደራ ደስታዉ የጌታዉ ደስታ ሆኖ
እናገኛለን፡፡ ዘፍጥ 24 ፡ 1-27

ባለአደራ በሐላፊነት በተሰጠዉ ማንኛዉም በማይታዩ ፣ በሚታይ ነገሮች እና ንብረት ላይ


በአግባቡ ቁጥጥር የሚያደርግ እና ከልቅ ማንንት ራሱንም የሚጠብቅ ልቅ ማንነትን በሰዎች
ሲያይ የሚቃወም ሰዉ ሊሆን ይገባል፡፡ ግልጥ የሒሳብ አሰራርንና ግልጥ ቁጥጥርን በራሱም
እግዚአብሔር ባስቀመጠዉ ስፍራ እንዲሆን ያደርጋል፡፡ ያልኖርነበት ነገር ተጽዕኖ የማድረግ
ብቃትን ያሳጣናል፡፡ ባለአደራ ጌታዉ ቁጥጥር እንደሚያደርገዉ ስለሚያወቅ ጠንቃቃ ነዉ፡፡ ማቴ
25 ፡ 14 ተጠያቂነት እንዳለ በምንም መለኩ አይረሳዉም፡፡ ባለአደራ በርሱ ሥር ባለዉ ነገር
ላይ ተቆጣጣሪ ቢሆንም በርሱ ላይ ተቆጣጣሪ እንዳለ ግን አይዘነጋም፡፡ 1ኛ ጴጥ 5 ፡ 4
Page 18
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ስለሆነም ባለአደራነት፡-

➢ በእግዚአብሔር ለሰው የተሰጠ ተጠያቂነት ያለበት የመግዛት፣ የመብዛት፣ ምድርን


የመሙላትና የመጠበቅ የማስተዳደር•ኃላፊነት ነው፡፡

➢ ባለአደራነት የሌላውን ንብረት በታማኝነት የመያዝ፣ የመጠበቅና የማስተዳደር


በመጨረሻም ተጠያቂነት ያለበት ሊያሸልም ወይም ሊያስቀጣ የሚችል ኃላፊነት ነው፤

➢ በታሪክም እንደሚታወቀው ባለአደራነት አንድ ንጉሥ ግዛቱን ለቅቆ ራቅ ወዳለ ሥፍራ


ሲሄድ መንግሥቱን በኃላፊነት ተረክቦ መምራትን ማስተዳደርን የሚያካትት ተግባር
ወይንም መንግስትን ተረክቦ ለመምራት እድሜው ያልደረሰ አልጋ ወራሽ ሲኖር
መንግስቱን ተረክቦ እስኪመራ ድረስ በምትኩ ሆኖ የመምራትና የማስተዳደር ኃላፊነትን
ያመላክታል፡፡

➢ ባለአደራነት ከሥራ ወይም ከማንኛውም ዓይነት ኃላፊነት በሚገኘው ጊዜያዊ ጥቅም


ሳይሸነገል የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በማከናወን ብቻ የሚገኘውን ደስታና ሙሉ
እርካታ ለመቀበል ሲል እያንዳንዱ ሰው ሊያከብረውና ሊታዘዘው የሚገባ ከእግዚአብሔር
የተሰጠ ተጠያቂነት ያለበት ትልቅ ኃላፊነት ነው፤

➢ እግዚአብሔር ይህንን የባለአደራነት•ኃላፊነት የሰጠው እርሱ በምድር ላይ ለሰየማቸው


ሶስቱ ተቋማት ለቤተሰብ፣ ለመንግሥትና ለቤተ ክርስቲያን ሲሆን ይህንን አደራ
የሰጠውም ሰውን እንዲያገለግሉ፣ አካባቢን እንዲጠብቁ፣ ተፈጥሮን እንዲንከባከቡና
እግዚአብሔርንም እንዲያከብሩ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተቋም ኃላፊነቱን አውቆ በአግባቡ
ሲወጣ ከላይ የተገለጠው ውጤት የሚደረስበትና የሚጨበጥም ይሆናል፡፡

Page 19
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

➢ ፒተር ብሎክ የሚባለው ጸሐፊ እንደተረጎመው “ባለአደራነት ድርጅቶቻችንን


ስናስተዳድርና ስንመራ መሰረታዊ ለውጦችን ለማግኘት የሚያስቸሉንን ተስፋ ሰጪ
መንገዶች የሚያመላክተን ዋና ሐሳብ ነው::” በማለት ይገልጸዋል፡፡ ይህም አባባል
ባለአደራነት ከመንፈሳዊያን ሰዎች ብቻ የሚጠበቅ የኃላፊነት ድርሻ ሳይሆን በማንኛውም
ተግባር ላይ ከተሰማራው የሰው ዘር ሁሉ መሆኑንም ያስመዘግበናል፡፡

II. ባለአደራነት በመጽሐፍ ቅዱስ እይታ

ባለአደራነት በመጽሓፍ ቅዱስ ዉስጥ ጎልቶ የሚታይ ርዕስ ነዉ፡፡ ባለአደራነት በመጽሓፍ ቅዱስ
እይታ ትልቅ ስፍራ የሚኖረዉ በምድር ላይ የመኖራችንን ሁሉን ነገር ሊነካ የሚችል ጉዳይ
ስለሆነ ነዉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያዉቅ ሰዉ ባለአደራነት አይጠፋበትም፡፡ ከፍጥረት
መጀመረያ ጀምሮ እስከ ቤተክርስቲያን መነጠቅ ድረስ የባለአደራነት ነገር ጎልቶ ይታያል ፡፡

አዳም የመጀመሪያዉ ባለአደራ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አዳምን ገነትን እንዲንከባከብ በአደራ


እንደሰጠዉ እናያለን፡፡ በሐጢአት እሰከወደቀበት ጊዜ ድረስ ስራዉን በታማኝነት ስርቶ ነበር፡፡
ዘፍ 2 ፡ 15

ኖህ የባለአደራነት ስራዉን በጥንቃቄ እንደተወጣ እናያለን፡፡ ስለዚህም የመርከቡ ባለቤት


እግዚአብሔር ስለሆን በሩን የዘጋዉ ራሱ እግዚአብሔር ነበር፡፡ ኖህ ባለአደራ ስለነበር የፈለገዉን
ሳይሆን እግዚአብሔር የፈለገዉን ነበር የሠራዉ፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር የፈቀደዉን
የእንስሳ ዓይነትና የሰዉን ቁጥር ያስገባዉ፡፡ ዘፍጥ 6 ፡ 13-22

ሙሴ የማደሪዉን ድንኳን ሲሠራ ባለአደራ እንጂ ባለቤት ስላልነበር በጥንቃቄ ነበር የሠራዉ ፡፡
ሙሴ የማደሪያዉን ድንኳን ሲሰራ ባለአደራ ስለነበር እርሱ በሚፈልገዉ መንገድ ሳይሆን

Page 20
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ ነበር የሰራዉ፡፡ ዘጸ 37-40 ያም ብቻ ሳይሆን በምድረበዳ ጉዞ


የማደሪያዉ ድንኳን በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ከእስራኤል ነገድ ማን ቀዳሚ ማን ቀጣይ እንደሆነ
በእግዚአብሔር እንደ ተደነገገዉ መሰረት ሲያካሔድ እንደነበር እናያለን፡፡

ነገስታት ሲሾሙ ዋና ስራቸዉ የነበረዉ ባለአደራ ሆነዉ የእግዚአብሔርን ሐሳብ


እንዲያሰፈጽሙ እንጂ ለሌላ ዓለማ አልነበረም ፡፡ ከአንዳንዶቹ በስተቀር ባለአደራነታቸዉን
እያወጁ በታማኝነት አገልግለዉ አልፈዋል፡፡ እግዚአብሔር እንደልቤ የሆነዉን የእሴይ ልጅ
አገኘሁ ሲል ሐሳቤን የሚያስፈጽም ንጉስ አገኘሁ ማለቱ ነበር፡፡ ሐዋ 13 ፡ 22

በነቢያትም ሕይወት የምንመለከተዉ አገልግሎታቸዉን ሲወጡ የነበረዉ በባለአደራነት መንፈስ


እንደሆነ እና እግዚአብሔር ያላቸዉን ብለዉ ማንኛዉንም ዋጋ ለመክፈል በእግዚአብሔር ጎን
የቆሙ የአቋም ሰዎች ነበሩ፡፡ ነቢያት መንፈሳዊ ነጻነታቸዉን ጠብቀዉ እንዲያገለገሉ
ያደረጋቸዉ በባለአደራነት መንፈስ ማገልገላቸዉ ነበር ፡፡ ስለዚህም ክብር ፣ ዝና እና ዝሙት
በዘመናችን እንደምናየዉ ብዙዎች አገልጋዮችን ያንበረከከ ፈተና አነርሱን ሳይበግራቸዉ
ተቋቁመዉ የተወጡት ለባለአደራነት ስፍራና አክብሮት በመስጠታቸዉ ነበር፡፡ ስጦታህ ላንተ
ይሁን /ዳንኤል ዳን 5 ፡ 17/ ሚኪያስ /ሕያዉ እግዚአብሔርን አምላኬ የሚለዉን እርሱን
እናገራለሁ አለ ፡፡/2ኛ ዜና 18 ፡ 13/ ናታን / ያ ሰዉ አንተ ነህ ፡፡/2ኛ ሳሙ 12 ፡ 1-6/

ወደ አዲስ ኪዳን አገልጋዮች ደግሞ ስንመጣ ከክርሰቶስ አገልግሎትና አስተምሮ ጀመሮ እሰከ
ሐዋሪያት አገልግሎት የባለአደራነት ጉዳይ ትኩረት የተሰጠዉ ጉዳይ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ
ከአብ የተቀበለዉን አደራ ለሐዋሪያት ሲያስረክባቸዉ እንመለከታለን፡፡ ዮሐ 17 ፡ 17

ሐዋሪያትም ከጌታ የተቀበሉትን የባለአደራነት ጉዳይ ትኩረት ሰጥተዉ ዋጋ እየከፈሉ


ለቤተክርስቲያን አባቶች አስረክበዉ አልፈዋል፡፡ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ ሰዎች እንደ ባለአደራ

Page 21
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ይቁጠሩን ብሎ በተጨማሪ ለልጁ ለጢሞጢዎስ ሲጽፍ ለታመኑት አደራ ስጥ ብሉ ተናግሯል፡፡


1ኛ ቆሮ 4 ፡ 1-4 2ኛ ጢሞ 2 ፡ 1-2 በተለይ በጥንቷ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ዉስጥ
ይገለጥ የነበረዉ ስለ ወንጌል ዋጋ እየከፈሉ በታማኝነት ከጌታ የተቀበሉትን ተልዕኮ ተወጡ
እንጂ እንደኛ ዘመን በወንጌል አልተጠቀሙም፡፡ በወንጌል የሌሎቸንን ጭለማ የሌሎችን ድሕነት
አስወገዱ እንጂ በምንም መልኩ ራሳቸዉን አላበለጸጉም፡፡

አዉነተኛ ባለአደራ ደስታዉ አትኩሮቱ ተልእኮዉን በብቃት መፈጸሙ ላይ እንጂ ተልኮዉ


ዉስጥ የሚገኘዉ ጥቅም ላይ አይደለም፡፡ ባለአደራ የዋጋ አሰጣጡ ከጌታዉ የዋጋ አሰጣጥ ጋር
በምንም መልኩ አይጣረስም፡፡

እንግዲህ ልመርበት የሚገባው የሰው ባለአደራነት ከእግዚአብሔር የተሰጠ ኃላፊነት ነው


(Man’s Stewardship – God-given Responsibility). ይኸውም፡-

✓ ከውድቀት በፊት የነበረ ኃላፊነት (Pre-Fall Mandate):- ዘፍ. 1፡26-28 ብዙ፣


ተባዙ፣ምድርን ሙሉአት፣ ግዙአትም፣ጠብቋት የሚል ነው፡፡ በእግዚአብሔር አምሳል
የተፈጠረው ሰው መልኩን መያዝ ብቻ ሳይሆን የመግዛት ውክልናም ነበር
የተቀበለው፤ እንደ እግዚአብሔር እንደራሴ በፍጥረቱ ላይ የማስተዳደር ሙሉ
ኃላፊነት ተሰጥቶታል፤

✓ ሥራም በኤደን ገነት ውስጥ የተጀመረው ከዚህ ውክልና የተነሳ ነበር፤ ሰው እንደ
አምላኩ አዳዲስ ነገሮችን የመፍጠርና አምላኩን ደስ የማሰኘት ዕድል ነበረው፡፡ ሥራ
ከውድቀት በፊት የተሰጠ ልዩ ስጦታ ነው፣ አልተወሰደብንም፤

Page 22
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

✓ ከውድቀት በኋላ የተሰጠ ኃላፊነት (Post-Fall Mandate):- ዘፍ. 3: 1-24. ሰው


በምርጫው የተሰጠውን ትዕዛዝ በመተላለፍ በአምላኩ ህግ ላይ ስላመጸ
ከተቀመጠበት ሥፍራና ከተሰጠው ትልቅ ኃላፊነት ተነስቶ ከገነትም ወጥቶ
በተገኘበት ምድር ላይ እንዲኖርና እንዲሠራ ተደረገ፤ ያለመታዘዙ ውጤት ሞትን፣
በወሊድ ጊዜ ሥቃይን፣ በሥራ መድከምን፣ የምድር መረገምን አስከተለ፤ ሰው በላቡ
ወዝ በድካም የምድርን ፍሬ እንዲበላ አዲስ ትዕዛዝ ዋጣ፤ የተባረከው ስጦታ ሥራ
አድካሚና አስቸጋሪ ሆነ፤

✓ ምድር ከመረገሙዋ የተነሳ እሾህና አሜከላ በማብቀሏ ሥራ የሚያደክም


የሚያስቸግር የሚከብድ አንዳንዴም የሚያታክት ሆነብን፤ ሆኖም ሥራን ያበላሸው
ሰው ስለሆነ ለሥራ አስቸጋሪነትና አድካሚነት ከራሱ ከሰው በቀር ማንም
አይጠየቅም፤

✓ በክርስቶስ በኩል በዳግም ምጽአቱ ፍጥረት ሁሉ እንደገና ሲታደስና እርግማን


ሲወገድ ያኔ ማንኛውም ተግባር አድካሚነቱ ቀርቶ አስደሳችና እርካታን የሚሰጥ
ይሆንልናል፡፡ እስከዚያም ድረስ ባላደራነታችንን እንዴት መወጣት እንዳለብን
መጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ትምህርቶችንና መመሪያዎችን ይሰጠናል፡፡

III. የባለአደራ ሐላፊነት


ባለአደራነት ለገባዉ ሰዉ ትልቅ ሐላፊነት ያለበት ጉዳይ ነዉ፡፡ ከእግዚአብሔር በአደራ
ለተቀበልነዉ ስጦታ እና ልዩ ልዩ ነገር ሁሉ በእግዚአብሐር ፊት ተጠያቂዎች ነን፡፡ የባለአደራ
ሐላፊነት አግዚአብሔር በሕይወታችን የሚያስቀምጠዉ ነገር ሁሉ ከእርሱ ማንነት የተነሳ እንጂ
Page 23
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ከኛ ከምንም ነገር ጋር ተያያዥነት እንደሌለዉ ከማወቅ ይጀምራል ፡፡ ባለአደራ ባለቤትነትንና


ሐላፊነትን በደንብ ለይቶ ያዉቃል፡፡

1. የተቀበልነዉን ነገር ለተፈለገዉ ጉዳይ ብቻ የማዋል ሐላፊነት

የባለአደራ አንዱ ሐላፊነት ከጌታ የተቀበላቸዉን ቁሳቁስና ስጦታዎች በአግባቡ እግዚአብሔር


ለሚፈልገዉ ዓላማ ብቻ የማዋል ሐላፊነት አለበት፡፡ የብዙዎች ባለአደራዎች ችግር ይህ
ይመስለኛል፡፡ አንዳንድ ሰዉ እግዚአብሔር የሰጠዉን ስጦታ እግዚአብሔር በአደራ የሰጠዉን
ነገር በሰዉ ግፊት ይሁን ራስን ካለመግዛት ፈተና ባልተፈለገ መንገድ በመጠቀም ስሕተት
ዉስጥ ይገባል ፡፡

እግዚአብሔር በአደራ የሰጠንን ማንኛዉንም ነገር አግዚአብሔር ላልሰጠን ዓላማ ማወል


በእግዚአብሔር ዘንድ ተጠያቂ ያደርገናል፡፡ ሳዖል እግዚአብሔር የሰጠዉን ስልጣን እግዚአብሔር
ለፈለገዉ ጉዳይ ማዋል በለመቻሉ ከንጉሥነት እንዲሻር አድርጎታል፡፡ 1ኛ ሳሙ 15 ፡ 17-13
መንፈሳዊነት በፈለጉት መንገድ መንፈሳዊ ሥራን መስራት ሳይሆን እግዚአብሔር በሚፈልገዉ
መሠረት መንፈሳዊ ስራን መሥራት ነዉ፡፡ ስልጣንና ስጦታ በሕይወታችን በጨመረ ቁጥር
ተጠያቂነትም አየጨመረ ይሔዳል፡፡

2. በተቀበልነዉ ነገር በትጋት የመስራት እና የማገልገል ሐላፊነት

በለአደራ አንዱ መታወቂያዉ በምድር ላይ የሚኖረዉ ቆይታ ዉስን መሆኑን አዉቆ


እግዚአብሄር በሰጠዉ ዕድሜ በትጋት መስራቱ ነዉ፡፡ ሉቃ 12 ፡ 37 ትጋት አንዱ

Page 24
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

የባለአደራነት መታወቂያ ነዉ፡፡ ብዙ አገልጋዮችና ክርስቲያኖች በዉስጣቸዉ እግዚአብሔር


ያስቀመጠዉ ጸጋ ሊደፈንና ሊጠፋ ዋና ምክኒያት የሚሆነዉ ያለመትጋት ችግር ነዉ፡፡ ዉስን
እድሜ እንዳለዉ የገባዉ ሰዉ በጊዜ አይቀልድም የተሰጠዉን ተልዕኮ በብቃት ይፈጽመዋል፡፡
ባለአደራ እግዚአብሔር በሰጠዉ ዕድሜ የእግዚአብሔርን ሓሳብ እንደ ዳዊት አገልግሎ ያልፋል
ሐዋ 13 ፡ 36 ፡፡ ስንፍና የመንፈሰዊ ስኬት እንቅፋት ነገር ነዉ፡፡ ይህ መንፈሳዊ በሽታ
በትጋት እንጂ በጸሎት የማይወገድ ጉዳይ ነዉ፡፡ አዉነተኛ ትጋት ታይታን መሰረት ያደረገ
ሳይሆን እግዚአብሔርን በመፍራት ብቻ የሚገለጥ ነዉ፡፡

3. በተቀበልነዉ ነገር አማካኝነት የሚመጡትን ክብርና ዝና የመሸሽ ብቃት

ለአንድ ባለአደራ ትልቅ ነገር የተቀበለዉን አደራ በብቃት መወጣት እንጂ ለክብርና ለዝና
መሮጥ አይደለም፡፡ አንዳንዴ ያለአሰብናቸዉ ያልጠበቅናቸዉ ደግምም ያልገመትናቸዉ ብዙ
ክብርና ዝና በዉስጣችን ከተቀመጠዉ ስጦታና ነገር የተነሳ ይመጣሉ ፡፡ የሚመጡ ክብሮችንና
ዝናን እንዴት እንደምናስተናግዳቸዉ ካላወቅን ስጦታንና ልዩ ልዩ ነገሮችን በአደራ ከሰጠን
ከእግዚአብሔር ጋር ሊያጣሉን ይችላሉ፡፡

አግዚአብሔር በዉስጣችን ባሰቀመጠዉ ነገር ስማችን ሲነሳ ትህትናችንና ቅንነታችን በብዛት


ሊጨምር ይገባል፡፡ የሐዋሪያዉ ጳዉሎስ እና የባልንጀራዉ አገልግሎት ጥሩ ምሳሌ ሊሆነን
ይገባል ፡፡ ሐዋ 14 ፡ 8-18 ክበር ሲመጣላቸዉ ሸሹ እንጂ ይገባናል ብለዉ ራሳቸዉን
ሲያሞካሹ አልተገኙም ፡፡ ለራሳቸዉም ሌላ ስም አልሰጡም ሰዎች ስም ሲሰጧቸዉም ዝም
አላሉም፡፡ ክብርን ለራስ መፈለግ በሕይወታችን ባይታይም ሰዎች የማይገባዉን ክብር ሲሰጡን
ዝም ብሎ መቀበል ተገቢ አይደለም፡፡ ዮሐንስ አገልግሎቱ ለጌታችን መንገድን መጥረግ ነበር ፡፡
ከዚህም የተነሳ እርሱ ሊልቅ እኔ ላንስ ይገባኛል ነበር ያለዉ፡፡ ዮሐ 3 ፡ 30 ማንኛዉም ብቃት
መቻልን ይጠይቃል፡፡
Page 25
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

4. በአደራ የተቀበልነዉን ነገር ላልተፈለገ አገልግሎትም ሆነ ቦታ ያለማዋል ሐላፊነት

ባለአደራ ከጌታ የተቀበለዉ ስጦታም ይሁን ልዩ ልዩ ነገሮች ባለአደራ እንጂ ባለቤት ስላልሆነ
ለፈለገዉ ጉዳይ ሊያዉለዉ አይችልም፡፡ ለቤተክርስቲያን መታነጽ የተሰጠዉን የጸጋ ስጦታዎች
ለግል ጥቅም ማግኛ አድርገን የምንጠቀም ከሆነ ትልቅ ስሕተት ነዉ፡፡ እግዚአብሔር
የምናደርገዉን ነገር ወይም ስራ ሳይሆን ስራዉን የምንሰራበትን መነሻ ሓሰብ ሳይቀር ንጹህ
ሊሆን ይገባል ፡፡ እግዚአብሔር እንደሰዉ ሥራችንና የምንፈጥረዉን ግርግር ሳይሆን ሥራዉን
ወይም አገልግሎቱን የጀመርንበትን መነሻ ሐሳብ ሳይቀር ያዉቃል፡፡

ባለአደራ የበዛ ጥንቃቄ የሚያደርገዉ አደራ በሰጠዉ በእግዚአብሔር ፊት እንጂ በሰዉ ፊት


ላለዉ መሆን የለበትም፡፡ አይደለም የእግዚአብሔር ስጦታ የእኛ እንደሆነ የምናስበዉ ገንዘብ እና
አካላችነ እንኳ ባለአደራ እንጂ ባለቤት ስላልሆንን እንደፈለግን ልናደርግ አንችልም፡፡ እሰቲፈን
principle centered leadership /መመሪያ ተኮር መሪነት በሚለዉ መጽሃፍ ዉስጥ ሰዎች
በቅድመያ በምንም ነገር ዉስጥ ምን አገኛለሁ የሚሉ ከሆነ የባለአደራነት ስሜት የላቸዉም
ደግሞም ተወካይነት ሰሜት ለሚገባ መመሪያ ለዓለማ የላቸዉም ማለት ነዉ፡፡2

IV. የባለአደራነት መስፈርት


ምንም ነገር መስፈርትና መለያ ከሌለዉ ድንበር አይኖረዉም ፡፡ ባለአደራነት የራሱ መስፈርትና
መለያ መለኪያ አለዉ፡፡ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ ለልጁ ለጢሞቲዎስ ሲመክረዉ ለአደራ የሚበቁ
ሰዎችን መስፈርት አስቀምጦላቸዉ እንጂ ላገኘኸዉ ሁሉ አደራ ስጥ አላለዉም፡፡ 2ኛ ጢሞ 2 ፡

2
Stephen R. Covey, Principle-Centered leadership. Simon & Schuster UK Ltd, 1992. PP 53
Page 26
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

2 ዮቶር ሙሴን ሥራ ለሰዎች እንዲያከፋፍል ሲመክረዉ ከእስራኤል ላገኘኸዉ ሁሉ ሃላፊነት


ስጠዉ ብሎ አልመከረዉም ነገር ግን መስፈርት ሲያወጣ እንመለከታለን፡፡ ዘጸ 18 ፡ 21

ዛሬ ዛሬ ስንመለከት መለኪያ ስለሌለን ብዙ አገልግሎቶች ለአደራ በማይበቁ የባለአደራነት


መንፈስ በማይሰማቸዉ ሰዎች ትከሻ ላይ አሰቀምጠን ብዙ ነገሮች መበላሸት ችለዋል፡፡
እግዚአብሔር ያደረገለን እና በዉስጣችን ያስቀመጠዉ ጸጋ በርሱ ዘንድ መስፈርት የሚያሟላ
ማንነት ስላለን ሳይሆን እንዲያዉ በምህረቱ ብዛት እንደሆነ እናዉቃለን ፡፡ ሆኖም ግን
በዉስጣችን ከተቀመጠዉ የከበረ ነገር የተነሳ ባለአደራነት የሚጠይቀዉን ማንኛዉንም ደረጃዉን
የጠበቀ ሕይወት መኖር ይጠበቅብናል፡፡

ሀ. ታማኝ መሆን አለበት 1ኛ ቆሮ

በክርስትና ታማኝነት በብዙ አቅጣጫ ይገለጣል፡፡ ታማኝነት ከራስ ይጀምርና ለእግዚአብሔርና


ለሌሎች ይቀጥላል፡፡ ታማኝነት በጊዜና በሒደት ተፈትኖ የሚታወቅ እንጂ ሰዉን በማየት ብቻ
ማወቅ አይታሰብም፡፡ ታማኝነት የሚፈተን ነገር ነዉ፡፡ ለቤተሰቡ ታማኝ ያለሆነ ሰዉ ቤተሰቡን
ምሳሌነት ባለዉ ሕይወት ያለመራ ሰዉ ታማን ነዉ ብሎ መደምደም አይታሰብም፡፡ ለትዳር
ጓደኛዉ ለልጆች ከሚናገረዉ ቃል እስከሚኖረዉ ኑሮ ታማኝ ያለሆነ ሰዉ ለእግዚአብሔር
ታማኝ ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ሓዋሪዉ ጳዉሎስ ከብዙ አገልጋዮች ጋር አገልግሏል ፡፡
ስለታማኝነታቸዉ የመሰከረላቸዉ የተወሰኑ አገልጋዮች ነበር፡፡ ኤጳፍራ ቆላ 1 ፡ 7 ቲኪቆስ
ቆላስ 4 ፡ 7 ፡፡ ባለአደራነትንና ታማኝነትን ነጣጥሎ ማየት አይቻልም፡፡

እግዚአብሔር ታማኝነታችንን በመከልከል አይለካም፡፡ ነገር ግን ሁሉን ነገር አሳልፎ በመስጠት


ይለካናል፡፡ ማቴ 25 ፡ 21 /ለእያንዳንዱ እነደ አቅሙ/ እዚህ ክፍል ላይ እንደምንመለከተዉ

Page 27
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ጌታቸዉ ስለሰጣቸዉ ነበር ሊቆጣጠራቸዉ የመጣዉ፡፡ እግዚአብሔር ባልሰጠን ነገር ላይ


ሊመዝነን እፈልግም፡፡ ታማኝ ተብልዉ የተመሰከረላቸዉ አገልጋዮች በተሰጣቸዉ መክሊት
መጠን በማትረፋቸዉ እነጂ በብዛቱ አይደለም፡፡ ስለዚህ ታማኝነት እግዚአብሔር በሰጠን ጸጋና
ነገር መጠን እንጂ በብዛት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የሚጠብቅብኝ በሰጠን መጠን ነዉ፡፡ ሉቃስ
12 ፡ 18 /ብዙ ከተሰጠዉ ሰዉ ሁሉ ብዙ ይጠበቅበታል/

ባለ አደራ ታማኝ በሆነ መጠን የጌታዉን ልብ ያሳርፋል፡፡ ዳንኤል በምረኮ ምድር ዉስጥ
ተቀምጦ በታማኝነቱ የተመሰከረለት ባለአደራ ነበር፡፡ ዳን 6 ፡ 4 /ነገር ግን የታመነ ነበርና፡፡/
ዳንኤል እነደባለአደራ በታማኝነቱ ንጉሱን ያሳረፈ ሰዉ ነበር፡፡

ለ. መንፈሳዊ ስርዓት ያለዉና ራሱን የሚገዛ መሆን ይተበቅበታል

ማንኛዉም ስርዓት ድንገት ወደ ሕይወታችን ድንገት የሚመጣ ነገር ሳይሆን በሒደት


የምንለማመደዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ስርዓት በፍቅር ብቻ የምንማረዉ ሳይሆን አንዳንዴ በጠንካራ
የእግዚአብሔር አመራርና በሚያስጨንቅ መንገድ የምናገኘዉ ትምሕርት ነዉ፡፡ የሥርዓት
መማሪያ መንገድን የሚጠላ ሰዉ ለቅ ማንነት ላለመልቀቅ የፈለገ ሰዉ ብቻ ነዉ፡፡ ሙሉ
ወታደር ለመሆን በወታደራዊ ስርዓት ዉስጥ ማለፍ የግዴታ ይሆናል /መዝሙ 118 ፡ 71/፡፡

ባለአደራ አንዱ የሚጠበቅበት ነገር ወይም መስፈርት በነገር ሁሉ ራሱን በየትኛዉም ማለትም
በደስታም በሐዘንም ራሱን የሚገዛና ለባለአደራነት ሥርዓት ራሱን ያስገዛ ሊሆን ይገባዋል፡፡
ራሱን የማይገዛ ሰዉ የባለአደራነትን ተልዕኮ በብቃት መወጣት አይችልም፡፡

ምናልባት መንገድ ላይ የሚያገኘዉ ልዩ ልዩ ፈተና ሃሰቡን ሳይቀር ሊያስለዉጠዉ እና ከግብ


እንዳይደርስ ሊያደርገዉ ይችላል፡፡ የባለአደራነትን ስራ ለመፈጸም መንፈሳዊ ስርዓት ወሳኝ ነገር

Page 28
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ነዉ፡፡ ልቅ ማንነት ያለዉ ሰዉ ባለድል እና ስኬታማ ይሆናል ብለን አናስብም፡፡ በባለአደራ


መንገድ ላይ ተልዕኮዉን በብቃት እንዳይፈጽም የሚያደርጋቸዉ ፈተናዎች ይገጥሙታል ፡፡
እነዚሀን ፈተናዎች ማለፍ የሚችለዉ ስርዓት ባለዉ ሕይወት ራሱን የመራ እንደሆነ ብቻ
ነዉ፡፡

ብዙ ጊዜ ራስን መግዛት የሚያስፈልግዉ በአንዳንድ ሐጢአቶች ላይ ብቻ እንደሆነ እናስባለን ፡፡


ሰይጣን ከገነት ጀምሮ እሰከ እሱስ ድረስ ራስን የመግዛት ፈተና ያቀረበዉ ሰዎች የሚጠሉትን
ነገር በማቅረብ ሳይሆን የሚፈተኑበትን የሚወዱትን ነገር በማቅረብ ነዉ፡፡ ራሳችንን መገዛታችን
የሚታወቀዉ ከምንወደዉ ነገር ጋር ፊት ለፊት ስንገናኝ ብቻ ነዉ፡፡

ባለአደራ ሕይወቱ በጠቅላላ በእግዚአብሔር ስርዓት የሚመራ መሆን አለበት፡፡ ስርዓት


ዝርክርክነትን ከመንፈሳዊ ሰዎች ላይ የሚያስወግድ መድሓኒት ነዉ፡፡ ሥርዓት እስራት
የሚመስላቸዉ ክርስቲያኖች አሉ፡፡ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ ለልጁ ለጢሞ ስለ ስርዓት አስፈላጊነት
ይነግረዋል፡፡ 1ኛ ጢሞ 1 ፡ 15 እንኳን ባለአደራነት በእግዚአብሐር ቤት መኖር በሥርዓት
መመላለስን የሚጠይቅ ነገር ነዉ፡፡

ሐ. ዘወትር የሚጸልይ የእግዚአብሔርን አመራር መከተል አለበት

ዶክተር ማየለስ ስለጸሎት በጻፉት መጽሐፋቸዉ “ጸሎት ለአማኝ አማራጭ ሊሆን አይችልም፡፡
የእግዚአብሔርን ዓላማ በእያንዳንዳችን ሕይወት በምድር ላይ ለማስፈጸም ጠቃሚ ነገር ነዉ፡፡”3
መንፈሳዊ ሐላፊነተን ያለ ጸሎት መወጣት በምንም መልኩ አይታሰብም፡፡ ሐዋሪያዉ ጳዉሎስ
ከጌታ የተቀበለዉን አደራ እንደሚገባ መወጣት ይችል ዘንድ ከራሱ አልፎ ለኤፌሶን ቅዱሳን

3
Myles Munroe , Understanding the Purpose and Power of Prayer. Whitaker house: Nassau Bahamas. 2002 .PP
41
Page 29
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ጸልዩልኝ በማለት የጸሎት ርዕስ ይሰጣል፡፡ ኤፌ 6 ፡ 20 ከክርስቶስ ሕይወት የምንማረዉ


ይህንኑ ልምምድ ነዉ ፡፡ ከአብ የተቀበለዉን ስራ ለመከወን ሁል ጊዜ ልማዱ አድርጎ ሌሊቱን
ሙሉ ይጸልይ ነበር፡፡ ማቴ 14 ፡ 23 ሉቃ 6 ፡ 14 ክርሰቲያናዊ ባለአደራነትና ጸሎት
የማይለያዩ ነገሮች ናቸዉ፡፡ ክርስቲያን ባለአደራነት ተልዕኮዉን ለመወጣት ስልታዊ አቅድ
አስፈላጊ ቢሆንም ጸሎት ግን ሊረሳ የማችል ነገር ነዉ፡፡

ማንኛዉም መንፈሳዊ ነገር ለማከናወን ጸሎት ዋና ነገር ነዉ፡፡ በየትኛዉም መስክ ባለአደራ
ጸሎትን ልማዱ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ዳንኤል በምርኮ አገር በተመደበበት በመሪነትና በሒሳብ ስራ
ላይ ዉጤታማ ነበር ፡፡ በምርኮ ምድር የተሳካለት ፣ የባለአደራነትን ስራ በብቃት የሰራ
ሠራተኛ እና እግዚአብሔርን አስከብሮ ያለፈ ሰዉ ነበር ፡፡ በሕይወቱ በጠላቶቹ ዘንድ እንኳ
ሳቀር ስንመለከት በቀን ሶስት ጊዜ በጌታ ፊት የመጸለይ ጠንካራ ልምምድ ነበረዉ፡፡ ዳን 6 ፡
1-3 ¸ 10 ብዙ ሰባኪዎች ስለዳንኤል ስኬት ይነግሩናለ እንጂ የጸሎት ሕይወቱን እና ትጋቱን
አይነግሩንም፡፡ ጸሎት ለባለአደራ በዉስጡ የተቀበለዉን ስጦታም ይሁን አደራ በብቃት
እንዲፈጽም ከማድረጉ በላይ ጽናትንና ጥንካሬን የሚሰጥ ኃይለኛ ነገር ነዉ፡፡

V. ባላደራነት ኃላፍነት
እንግዲህ ከሙሉ ኃላፊነት ጋር የተጠራ አንድ ባለአደራ የጥርውን አውጣጫ ለይቶ ማወቅ
የግድ ይላል፡፡ ጠቅለል ባለ መልኩ ግን ልናውቀው የሚገባው ነገር አማኞች እንደ ባላአደራ
የተጠራነው የሚከተሉትን ተግባራት እንዲንፈጽመው እንደሆነም ልናውቅ ይገባል፡፡ እነዚህም፡-

1. የተፈጥሮን እምቅ ሀብት ለማልማት ተጠርተናል፡፡

Page 30
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ይህንን ደግሞ በሥራ ሳንጠመድ ተግባራዊ ማድረግ አንችልም፤ ያለሥራ ተሳትፎ


ባለአደራነታችንን ልንወጣም አንችልም፡፡ ሰው ሲፈጠር በእግዚአብሔር መልክ ብቻ
አይደለም ነገር ግን የእግዚአብሔር ጥበብም ተሰጥቶት ነበር የተፈጠረው፡፡
ይህም ጥበብ እጅግ ጥልቅና ትልቅም ነው፤ እግዚአብሔር የፈጠረውን ማዕድን፣ ልዩ
ልዩ የተፈጥሮ ሀብትና በመጠቀም አዳዲስ መገልገያዎችን መስራት ማምረት ይችላል፡፡
ይህም ጥበብ በሰው ዘር ታሪክ ውስጥ ሰባተኛው ትውልድ የሆነው ላሜህ ከሴላ
የወለደው የአዳም ስምንተኛው ትውልድ የሆነው ቱባልቃየን ከናስና ከብረት የሚቀጠቀጥ
ዕቃን የሚሠራ ባለሙያ ሆነ፡፡
እንግዲህ ያን ጊዜ የተጀመረው የብረታ ብረት ሥራ (metal work – metallurgy) ዛሬ
እጅግ የተራቀቀ ደረጃ ላይ ደረሶ የሠለጠነው የሰው ልጅ ከምድር ማዕድናት መንኮራኩር
ሠርቶ ሕዋህን ሰንጥቆ በመጓዝ ወደ ሌሎች ዓለማት እየሄደ ነው፡፡ ከባለአደራነት ጋር
እውቀትንና ጥበብን ከፈጣሪው የተቀበለው የሰው ልጅ ከተሰጠው እውቀትና ጥበብ አንድ
አምስተኛውንም እንዳልተጠቀመበት ጠቢባኑ ይነግሩናል፡፡
ይህ መረጃ ትክክል ከሆነ የስው ልጅ እስከ አሁን ከሰራቸው የሚበልጡ አስደናቂ
ነገሮችን እንደሚሠራ አያጠያይቅም፡፡ ታዲያ በሰው ልጅ የሥልጣኔ ጉዞ ውስጥ
የእግዜአብሔር እጅ እንዳለችና ዳንኤልም 12፡4 ላይ "ብዙ ሰዎች ይመራመራሉ
ዕውቀትም ይበዛል፤" ሲል የተነበየውን ማሰቡም ተገቢ ነው፡፡

2. የሰዎችን ሕይወት ለማሻሻልና ለማሳመር ተጠርተናል፡፡


✓ ይህ ደግሞ የሰውን ሕይወትና ኑሮ ለመለወጥ የሚሠራውን ማንኛውንም ዓይነት ሥራ
የሚያካትት ነው፤ የመንፈሳዊ አገልግሎት ሥራ፣ የቤት ውስጥ ሥራ፣ የምግብ
ዝግጅት፣ የመኖሪያ ቤት ሥራ፣ የንግድ ሥራ፣ የልብስ ስፌት ሥራ፣ የትምህርት

Page 31
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

አገልግሎት፣ የጤና አገልግሎት፣ የምርምር ሥራ፣ የጥገና ሥራ፣ የቁንጅና ሥራ፣


የትራንስፖረት አገልግሎት ሥራ የመሳሰሉትን ሁሉ ይጨምራል፤ (ሌስ ኔውቢጅን
የተባሉ ደራሲ “ለእግዚአብሔር እውነተኛ የፍቅርና የመታዘዝ መስዋእትነት የሚከፈለው
በዓለም ውስጥ በሚሰጠው አገልግሎት ነው፡፡” ሲሉ ጽፏል (2ጢሞ. 3፡ 16)፡፡

3. በምድር ላይ ማህበረሰብን ለመገንባት ተጠርተናል፡፡


➢ ከሰዎች ጋር አብረን ለመኖር በሚያስችል መልኩ ስለተፈጠርን ማህበረሰብን
እንመሰርታለን፤ ለሰዎች ጥቅም የሚያመጣ አገልግሎትንም እንፈጽማለን፡፡ ስለዚህም
ማንኛውም ማህበረሰብአዊ አገልግሎት የሰውን ልጅ አእምሮአዊ፣ አካላዊ፣ መንፈሳዊ፣
ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰባዊ ፍላጎት ለማሟላት የሚደረገው አገልግሎት ለሰው ጥቅምና
ዘላቂ ልማትን እስካስገኘ ድረስ ሁላችንምእንደ ታማኝ ባለአደራ ተግተን ልንፈጽመው
የሚገባን ተግባር ነው፡፡
4. በዋነኝነት ደግሞ ወንጌልን በመመስከርና የጌታን መንግስት በመስፋት የእምነት
ማህበረሰብ ለመመስረት ስለተጠራን አማኞች ለተጠራንበት ወንጊል እንደሚገባ
በመኖር እግዚአብሔር መልካም የሚለውን ሥራ ሁሉ ተግተን ልንሠራው
ይገባናል፡፡
✓ ይህ ማህበረሰብ በሳምነት አንድ ቀን ለሶስት ሰዓት የሚገናኝ ሳይሆን ሳምነቱን ሁሉ
የሚገናኝ የሚጠያየቅና የሚደጋገፍ፤ ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የተጠራ ማህበረሰብ
ነው፡፡ በአምልኮ፣ በሥራ፣ በንግድ፣ በደስታና በሐዘን ቦታ ሁሉ የሚገናኝና ሁሉን በጋራ
የሚካፈል ማህበረስብ ነው (ሮሜ.12፡ 15)፡፡

Page 32
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

5. ዓለምን ለማበልጠግና ለሕብረት ተጠርተናል፡፡


➢ የእግዚአብሔር ጥሪ ምድርን የሚሞላ ዓለም አቀፍ ጥሪ ነው፤ የትኛውም መልካም
የሥራ ዓይነት ይህንን ጥሪ ለመስፈጸም ትልቅ እገዛ ያደርጋል (መዘ. 133፡1-3፣ 2ቆሮ.
6፡10፣)፡፡ሕብረትን የመሰረተና የሚወደው እግዚአብሔር በፍጹም ሕብረት ስለሚኖር
በጎውን ለመሥራትና የምንኖርበትን ሥፍራ በመለወጥ ዓለምን ስናበለጽግ ደስ ይለዋል፡፡

6. ሀብትን ለማፍራትና ድህነትን ለማስወገድ ተጠርተናል፡፡


ሥራ ድህነትን ለማስወገድ ትልቅ ሚና አለው አዲስ ሀብትን ለመፍጠር ያስችላል
የሰውን ምድራዊ ህልውና በተሻለ መልኩ ይቀይራል (2ቆሮ. 9፡ 9-15) ፡፡ እግዚአብሔር
የበረከት አምላክ ስለሆነ ሥራችንን ሊባርክልንና ከድህነትም ቀንበር ሊያወጣን ሙሉ
ፈቃዱ ነው፡፡
እኛ አማኞች በተሰጠን አደራ ልክ ሥራ በመስራት እራሳችንንና አካባቢያችንን ብሎም
አገራችንን ብንለውጥ ለእግዚአብሔር ክብር ለእኛም ደስታ ሰለሚሆን እግዚአብሔር
አብሮን ይደሰታል እንጂ የብልጽግናችን ጠላት አይሆንም፡፡
ልታወቅ የሚገባው ነገር ጌታ የድህነታችን ጠላት እንጂ የብልጽግና ባላጋራ አይደለም፡፡
አስቀድሞም ሰው ሲፈጠር ለበረከት እንጂ ለውርደትና ለጉስቁልና አይደለም፤
ድህነትንም ጉስቁልናንም በራሱ ላይ ያመጣው ሰው እራሱ ነው፡፡ ስው ተግቶ ከሰራ
አምላኩ የድካሙን ፍሬ ይባርክለታል፡፡ ጠቢቡ ለሰው የከበረ ሀብት ትጋት ነው ስለሚል
ሰው ተግቶ ከሠራ ሀብትን የማያፈራበትና ደህነትን የማያስወግድበት ምክንያት
አይኖረውም፡፡ ስለዚህ ሀብትን ለማፍራት መንገዱ በሃቅ ተግቶ መሥራት ነው፡፡

7. በሰማይ መዝገብ ሀብት እንድናኖር ተጠርተናል፡፡

Page 33
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

➢ በምድር ላይ የምንሰራው መልካም ሥራ በሰማያዊው መንግሥት ቀጣይ ሥራን በበለጠ


መልኩ እንደምንሠራ ያመላክተናል፤ ወደ እግዚአብሄር መንግስት የምንገባው
ለመዘመርና ለመተኛት አይደለም (ማቴ. 6፡ 19-21)፡፡ በዚያም አዲስ ሕይወትና
መልካም ሥራ ይጠብቀናል ማለት ነው፡፡
➢ በምድር ላይ ለተቸገሩትና አቅም ለሌላቸው ሰዎች የሚሰራው መልካም ሥራ ሁሉ
በሰማይም መልካም ብድራትን እንደሚያስገኝ ጌታ ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ላይ
በምዕራፍ 25 ግልጽ አድርጎ አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም "ሰው የሚዘራውን ሁሉ
ያንኔ ደግሞ የጫዳልኛና፤... መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት፡፡ ... ለሰው ሁሉ
ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ፡፡" በማለት አማኞችን አስገንዘቧል
(ገላትያ 6፡7-10)፡፡
➢ የመጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ትምህርት በፍርድ ቀን ዓለም ትጠፋለች ሳይሆን ዓለም
ትለወጣለች (Transformed) የሚለው መርህ ነው፡፡ ወርቅ በእሳት እንደሚቀልጥና
በውስጡ ያለው ቆሻሻ እንደሚወገድ ከዚያም በኋላ ደምቆ ለውበት እንደሚያገለግል ሁሉ
ዓለምም በውስጥዋ ያለው ቆሻሻና አመጽ በእግዚአብሔር እሳት ተቃጥሎ ከጸዳ በኋላ
ለእግዚአብሔር ክብርና ለዳኑ ሰዎችም ምቹ የመኖሪያ ሥፍራ ትሆናለች፡፡ ጌታ
‹መንግሥትህ ትምጣ› ብለን እንደንጸልይ ሲያስተምረንም የእርሱ መንግሥት በዚህ
ምድር ላይ እንድተሰለጥንና እኛም መንግሥቱን ወርሰን ለእግዚአብሔር ክብር
የሚሆነውን ሥራ ብቻ እየሠራን ለዘላዓለም ከእርሱ ጋር እንድንኖር ነው፡፡

8. በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪካቸው በሰፊው የተጻፈላቸው የእምነት አባቶች በእነዚህ


የጥሪ አይነቶች ውስጥ አልፈዋል፤ እነዚህ ጥሪዎች ዛሬም በዚህ ዘመን ባሉት
አማኞች ሕይወት ውሰጥ ይሰራሉ፡፡ ዮሴፍ፣ነህምያ፣ ዳንኤል፣ አስቴር፣

Page 34
ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ባለ አደራነት 2019

ጵርስቅላና አቂላ፣ ልዲያና በኢዮጴ የነበረው ቁርበት ፋቂው ስምዖን በመልካም


ሥራቸውና በታማኝነታቸው ሁሌ የሚተሰቡ ጥሩ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ለእነርሱ
ሥራ ጥሪ ነበር!

በማጠቃለልም ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ሊያደርጉ የተጠሩ አማኞች ሁሉ የጌታን ሥራ


ለመሥራት በየተሰጣቸው ዝንባሌ የሥራ ጥሪ ሲደርሳቸው በተጠሩበት መጠራታቸው
በመመላለስ የጌታን ሐሳብ በማገልገልና ለሕብረተሰብ በረከት በመሆን እግዚአብሔርን
በሥራቸው ካስከበሩ ከእግዚአብሔር ለተሰጣቸው ጥሪ ታማኞች መሆናቸውን
የሚያስመሰክሩበት እርሱንም የሚያስከብሩበት መንገድ ነው፡፡
በመሆኑም አንድ ባለአደራ ሥራ ጥሪ ነው? ለሚለው ጥያቄም ትክክለኛው ምላሽ ‹‹አዎን ሥራ
የከበረ ጥሪ ነው! ›› የሚል ነው፡፡ በማቴዎስ ወንጌል 5፡16 "መልካሙን ሥራችሁን አይተው
በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡" ብሎ
ያስተማረው ጌታ በልጆቹ ሥራ አባቱ እንዲከበር ትውልድም ሁሉ እንዲባረክ ይፈልጋል፡፡
ሥራን ክቡር ያሰኘው ጀማሪውና ፈጣሪው እግዚአብሔር ነው፡፡ በልጆቹ መልካም ሥራም እርሱ
እንደገና ይከበራል፡፡

Page 35

You might also like