You are on page 1of 5

ጉባኤ ከሇባት!

ከዱ/ን ሙለጌታ ወሌዯገብርኤሌ

(ወዯ ዋና ርዕሴ ከመዝሇቄ በፊት በተሇምድ እንዱሁም በስማ በሇው ስሇሚተረጎሙ ቃሊትና ስሇሚነገሩ
የቃሊት ፍቺዎች ከዚህም አሌፎ ቃሊቶቹ ታሪካዊና ስነ መሇኮታዊ መሰረተ ሃሳባቸው ሇቀው ላሊ ትርጓሜና
አንዴምታ ይዘው ስሇሚገኙ አንዲንዴ የቤተ-ክርስቲያን ቋንቋዎች በጥቂቱ እንመሇከታሇን። በተጨማሪም
በቤተ-ክርስቲያናችን ታሪክ ጉባኤ ከሇባት (የውሾች ጉባኤ) በመባሌ ስሇሚታወቀው የመሇካውያን ጉባኤ
የርዕሳችን ሰፊው ክፍሌ የሚይዝ ይሆናሌ። በስተመጨረሻም አጫጭርና ጠንካራ ማሳሰቢያዎችን
ተካተዋሌ። መሌካም ንባብ!)
ወቅቱ ከምን ጊዜ በሊይ የሃይማኖት መሪዎች በመንፈሳዊ ስሌጣን ስም ያሻቸውን ሲያዯርጉና ሲፈጽሙ
እንዱሁም ኢ-ክርስቲያናዊ በሆነ የስነ- ምግባር ጉዴሇት ተዘፍቀው ዴሃውን ሲበዴለና ጻዱቁን ሲያጎሳቁለ
ማየቱ የዕሇተ ዕሇት ተግባራቸው ከሆነ ረጅም ዘመን አስቆጥሯሌ። ስሇሆነም ጸሏፊው እንዯ ኢትዮጵያ
ኦርቶድክስ ተዋህድ ቤተ-ክርስቲያን ስርዓትና አስተምህሮ መሰረት መንፈሳዊ ስሌጣን በተመሇከተ
የአንዲንዴ ቃሊቶች ፍቺ በማብራራት ሇመንዯርዯር ተገዶሌ። ይኸውም ሲኖድስ ማሇት ስርወ ቃለ ከግሪክ
ቋንቋ የተገኘ ሲሆን ትርጓሜውም “ጉባኤ” ማሇት ነው። 1 እዚህ ሊይ በዋናነት የቃለ ትርጓሜ ማስፈር
ያስፈሇገበት ምክንያትም ብዙሏኑ የቤተ-ክርስቲያናችን ተከታዮች ምእመናን ከየዋህነት የተነሳ ስሇ ቃለ
ያሊቸው የተሳሳተ ትርጓሜ ሇማስተካከሌና ትክክሇኛ የቃለ ፍቺና መንፈሱም ሇማስጨበጥ ታስቦ ነው።
ሲኖድስ ማሇት የማይሳሳት፣ የማይከሰስ፣ የማይጨበጥና የማይዲሰስ፣ ስህተት የማያውቃቸው የሌዩ
ፍጥረታት ስብስብ ማሇት አይዯሇም። ምንም እንኳን በሏዋሪያት ዘመን ሲኖድስ ማሇት ፈቃዲቸው/ሁሇ
መናቸው ሇመንፈስ ቅደስ ያስገዙ ቅደሳን ስብስብ ማሇት ቢሆንም በውሳኔዎቻቸውም ፍፁማን ቢሆኑ
በቤተ-ክርስቲያን ታሪክ ግን ይህን ሏቅ የሚያዯበዝዙ ክስተቶች ቆጥረን ሇመዝሇቅም አይቻሇንም።
ሲኖድስ ማሇት ክንፍ ያሊቸው የሰው ወፎች ስብስብ ማሇትም አይዯሇም። ሲኖድስ በመጽሏፍ
የሰፈረው አምሊካዊ ቃሌ የሚጠብቅና የሚያስጠብቅ ክፍሌ ነው።
ሲኖድስ የመጽሏፍ ቅደስ ቃሌ ሽሮ በምትኩ ላሊ የሚያበጃጅ የተሇየ ስሌጣን ያሇው አካሌም
አይዯሇም። ሲኖድስ ማሇት ከሁለም በሊይ ከሆነው ከመጽሏፍ ቅደስ በታች ነው።
እውነተኛ ሲኖድስ መሰረቱ በመጽሏፍ ቅደስ ሊይ የተጣሇ ነው። ተሰብሳቢዎቹም በመንፈስ ቅደስ
ምሪት ጉባኤቸውን ያካሂዲለ ሲባሌ አንዴ ሌብና አንዴ ሃሳብ ሆነው በአንዴ ቃሌ የሚያጸዴቁትም ሆነ
የሚሽሩትን ሇእግዚአብሔር ክብር መጽሏፍ ቅደስን ያማከሇ ሲሆን ብቻ ነው!!
በሏዋሪያት ዘመን ሲኖድስ የእግዚአብሔርን ክብር ሌባቸውና መንፈሳቸው ሇተሰበረ ሕዝብ ሲገሌጥ
እንዱሁም ምእመናን ከስህተት ትምህርት ሲጠብቅና ቤተ-ክርስቲያንን ሇመሌካም ነገር ሲያንጽ፣ ሲያዘጋጅ
በአንጻሩ ዯግሞ በበተያዩ ዘመናት የተነሱ ሃያሊን ነገስታት ጥም ሇማርካትና ፓሇቲካዊ አጀንዲ አስፈጻሚዎች
በመሆንም “ሲኖድስ” ሲያጠፋ፣ ሲቆርጥ፣ ሲፈሌጥ፣ ሲያሳዴዴ፣ ሲፈጅ፣ ሲያርዴና ቅደሳንን በወጡበት
ሲያስቀር የመጣና ያሇ ፈሪሃ እግዚአብሔር የማያውቃቸው መንፈሳዊ ካባ ያጠሇቁ የስመ መንፈሳዊያን
ስብስብም እንዯሆነ ሌብ ማሇት ያስፈሌጋሌ። እርግጥ ይህን ዓይነቱ እውነት ከሰንበተ ክርስቲያን (የእሁዴ
ተሳሊሚ) ሌብ አይገኝም ታሪክን ሇማወቅ ከሰባኪ ሳይሆን ከጉባኤ ነውና።
በመግቢያዬ እንዯገሇጽኩት አሁን ዯግሞ ስሇ ጉባኤ ከሇባት ጥንተ ነገር በግርዴፉ ሌተርክሊችሁ። “ጉባኤ
ከሇባት” የሚሇው ሃይሇ ቃሌ ከግእዝ ቋንቋ የተገኘ ሲሆን በቁሙ ሲተረጎም “የውሾች ጉባኤ” ማሇት ነው።
ሌብ ይበለ! የሃይሇ ቃለ ተናጋሪዎች ሉቃነ ጳጳሳት ሲሆኑ ተቀባዮችም እንዱሁ ሉቃነ ጳጳሳት ናቸው።
ዘመኑ 451 እ.ኤ.አ. ሲሆን በወቅቱ መርቅያን የተባሇ ንጉስ ሮምን ይገዛበት የነበረ ዘመን ነው። ታዴያ በዚህ
ዘመን ሌዩ/እንግዲ ነገር የተከሰተበት ዘመን አሌነበረም። ሌክ እንዯ ቀዴሞ ዘመናት አሇመግባባትን እንዱሁ
በተመሳሳይ ተስተናግዶሌ። የተሇየ/እንግዲ ነገር ተከሰተ ቢባሌ እንኳ ንትርኩና ሽኩቻው ሳይሆን ንትርኩ
ያስከተሇው ጦስ ቀዴሞ ከተካሄደ ጉባኤያት ሇየት ያዯርገዋሌ። በዚህ ጉባኤ 650 ኤጲስ ቆጶሳት የተገኙ
ሲሆን ጉባኤውም የተሰየመው ኬሌቄድን በተባሇች ከተማ ነበር።
1 የካርዱናልች ጉባኤም ሆነ ፖፑ አይሳሳትም፣ አይከሰስም ከመጽሏፍ ቅደስም ይሌቅ ፖፑ የበሊይ ባሇ
ስሌጣን ነው የሚሇው ትምህርት የኦርቶድክስ ቤተ-ክርስቲያን ትምህርት ሳይሆን የሮማ ካቶሉክ
ፕሮፖጋንዲ ነው። በዚህ ጉባኤ ምንም እንኳን ቀዴሞ ሲብሊሊ የነበረው የአውጣኪ ትምህርት ያወገዘ
ቢሆንም በዋናነት ጉባኤው ጎሌቶ የሚታወቅበት ግን ኢየሱስን በማስመሌከት ከወዯ ሮም አከባቢ ቀዲማዊ
ሌዮን የተባሇው የሮማ ሉቀ ጳጳሳት በመሌዕክተኞች በኩሌ የተሊከው ደብዲ ዯብዲቤ ነው። ዯብዲቤው
ከዚህ ቀዯም ምንም ዓይነት ጉባኤ ተዘርግቶበት የማይውቅ ርዕሰ ጉዲይ ያዘሇ ከመሆኑ በተጨማሪ
በዯብዲቤ ውስጥ የተገሇጸውን ትምህርት ጉባኤው ያሇ አንዲች ማቅማማት አሜን ብል እንዱቀበሌ
የሚያስገዴዴም ነበር።
ከዚህም የተነሳ ጉባኤው ከፍተኛ የሆነ ግጭትና ብጥብጥ ከማስነሳቱ በተጨማሪ ቀዯም ብል ሇሦስት ጊዜት
ጉባኤ ዘርግተው አንዴ ሌብና አንዴ ቃሌም ሆነው ላሊው ሲያወግዙ፣ ሲሇዩና በግዞት ሲያኖሩ የመጡ
ሉቃነ ጳጳሳት እርስ በርሳቸው ተወጋግዘውና ተፋጅተው ያሇ ፍሬ መሇያየታቸው ጉባኤው በቤተ-ክርስቲያን
ታሪክ የተሇየ ያዯርገዋሌ።
2 ይህ የኬሌቄድን ጉባኤ በመባሌ የሚታወቀው 4ኛ ጉባኤ በቤተ-ክርስቲያናችን (በኦርቶድክ አብያተ
ክርስቲያናት) ዘንዴ ተቀባይነት የላሇውና የማይቆጠርም ሲሆን ጉባኤ ከሇባት የሚሇውን ስያሜ ሉያገኝ
የቻሇውም ከዚህ የተነሳ ነው።
ውግዘት በቤተ-ክርስቲያን ታሪክና በመጽሏፍ ቅደስ እይታ:
ማውገዝ ከህብረት መሇየት ማግሇሌ ማስናበት ማሇት ሲሆን ቃለ ራሱ ከፍተኛ ስነ መሇኮታዊ እሴት ያሇው
ነው። ቀዯም ስንሌ እንዯተመሇከትነው የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች ከመሊ ጎዯሌ ሏዋሪያዊ አስተምህሮዋን
ሇመጠበቅ ከመጽሏፍ ቅደስ ያፈነገጡ ትምህርቶችን አሁንም በከፊሌ መጽሏፍ ቅደስ ማዕከሌ ያዯረገ
እርምጃዎች እየወሰደ መጥተዋሌ። ይህ የአባቶቻችን መጽሏፍ ቅደስ መሰረት ያዯረገ አካሄዴ መካከሌ
አንደና አንኳር ነጥብ የተመሇከትን እንዯሆነ በተሇይ ቀዴመው የተካሄደትን ሦስቱ ጉባኤት ያሳይዋቸው
መጽሏፍ ቅደሳዊ ስነ ምግባር ተጠቃሽ ነው። በእነዚህ ጉባኤት የተሊሇፉ ውግዘቶች ራሱን የቻሇ የጎሊ ስነ
መሇኮታዊ ስህተቶች ቢኖሩትም የአንዴም ተከራካሪ ግሇሰብ መጽሏፍ ቅደሳዊና መሰረታዊ መብቱ ግን
አሌከሇከለም (አሌገዯቡም ማሇት ግን አይዯሇም)።
እነዚህ የኒቅያ፣ የቁስጥንጥንያና የኤፌሶን ጉባኤ በመባሌ የሚታወቁ ጉባኤት (ጉባኤዎቹ በመዘርጋት ረገዴ
ራሱ የቻሇ ፖሇቲካዊ አንዴምታ ቢኖረውም) ከየቅጣጫው የተገኙ የቤተ-ክርስቲያን መሪዎች በተገኙበት
ተወጋዦቹ ምንም መጨረሻቸው ውግዘት ቢሆንም “መጽሏፍ ቅደስ የሚሇው ይህንኑ ነው ሲለ” በጉባኤ
ፊት ቀርበው እንዯ መረዲታቸው ስፋትና ጥሌቀት ከቅዴሳት መፃህፍትን እያጣቀሱ ሽንጣቸውን ገትረው
ሞግተው ተሟግተው እምነታቸው በይፋ በመግሇጽ ነበር። በእነዚህ ጉባኤት ታሪክ አንዴም የቤተ-
ክርስቲያን ሉቅ በላሇበት እንዱህ ታስተምራሇህ ተብል በስሚ ስሚ ወይንም ዯግሞ ባሊንጣዎችሁ
በሚቀርቡት ክስ የተነሳ የተወገዘ የሇም። በኢትዮጵያ መዱና በአዱስ አበባ ከተማ መቀመጫው ያዯረገ
ሲኖድስ ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ሲባሌም ይህን እውነት መሰረት ያዯረገ ነው።
ላሊው ውግዘትን በተመሇክተ መጽሏፍ ቅደስ ምን ይሊሌ? ማሇታችን አይቀርም። መጽሏፍ ቅደስ መሰረት
የላሇው ክርስቲያናዊ ትምህርት የሇምና ጥያቄው መነሳቱ ተገቢ ነው። አሁንም መጽሏፍ ቅደስ አንዴን
ሰው ከሕብረት/ከጉባኤ ስሇ መሇየት በተመሇከተ ግሌጽ የሆነ ትምህርት ነው ያሇው። ከጌታ ትምህርቶች
መካከሌ የተነሳን እንዯሆነም “ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንደ እንዱጠፋ በሰማያት ያሇው አባታችሁ ፈቃዴ
አይዯሇም። ወንዴምህም ቢበዴሌህ፥ ሄዯህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው ቢሰማህ፥
ወንዴምህን ገንዘብ አዯረግኸው፤ ባይሰማህ ግን፥ በሁሇት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁለ እንዱጸና፥
ዲግመኛ አንዴ ወይም ሁሇት ከአንተ ጋር ውሰዴ፤ እነርሱንም ባይሰማ፥ ሇቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ዯግሞም
ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንዯ አረመኔና እንዯ ቀራጭ ይሁንሌህ።” (ማቴ. 18÷ 15) ሌብ ይበለ!
የተዘረጉ ጉባኤት (በተሇይ ቀዯምቶቹ) ጉባኤዎቹ በከፍተኛ ወጪ ከመዘርጋቸው በፊት የተሇየ ትምህርት
እያሰራጩ ነው ተብሇው ስማቸው የተሰማ የቤተ-ክርስቲያን መሪዎችና መምህራን ሉቃውንት አስቀዴሞ
በወዲጆቻቸውና በቅርበት በሚያውቋቸው ግሇሰቦች አማካኝነት በኩሌ “ተው! እንዱህማ አይዯሇም
እየሳትክ ነው” ተብሇው ሲያበቁ “የሇም! ትክክሌ ነኝ!” ሲለ ትምህርታቸውን እየገፉበት በመምጣታቸው
ነበር ጉባኤ ራሱ መዘርጋት ያስፈሇገበት ምክንያት። ውግዘቶቹም የተሊሇፉት ተወጋዦቹ “ብዙሏኑ
በተስማሙበትና በሚስማሙበት ትምህርት ሳይሆን ከዚህ ቀዯም ባሌኩትና አሁንም ዯግሜ በዚህ ጉባኤ
ፊት ባረጋገጥኩት ቃላ ጸንቻሇሁ! የምሇውጠው ቃሌም ሆነ የምቀይረው ሃሳብ የሇኝም ” በማሇታቸው
ነበር። ታዴያ ሇመጽሏፍ ቅደስ ቃሌ (ማቴ. 18÷ 15) ጆሮ ያሌሰጠና ጆሮም የላሇው የአዱስ አበባው
ሲኖድስ የሰዎች ሰብዓዊ መብት ቢጥስ ምን ይዯንቃሌ? አበው የኬሌቀድን ጉባኤን ጉባኤ ከሇባት/የውሾች
ስብሰባ ሲለ የሰየሙትን ደብዲ እንግዱህ ይህን ይመስሊሌ። በተመሳሳይ አሁንም ቢሆን የበሌዓምን
የስህተት መንገዴ ተከትል የሚዯረገውን ማንኛውም ዓይነት ትሌቅም ትንሽም ሕገ ወጥ ጉባኤ ጉባኤ
ከሇባት/የውሾች ጉባኤ ይባሊሌ። ፈጽሞም ተሰሚነት/ተቀባይነት የሇውም ሇወዯፊቱም ተቀባይነት
አይኖረውምም!!
2 እስከዚህ ዘመን ዴረስ አንዱት ሃይማኖት አንዱት ቤተ-ክርስቲያን እንዯነበረች ሲሆን ስምዋም
ሏዋሪያዊት ቤተ-ክርስቲያን በመባሌ ትታወቅ እንዯነበረች የታሪክ መዛግብት ያስረዲለ።
3 ከፊሌ የተሊሇፉ ውግዘቶች ተወጋዦቹ (አንዲንድቹ) ከነበራቸው ምጡቅና ረቂቅ እውቀት፣ የክህነትና
የቤተ-ክርስቲያን ስሌጣን፣ ከአንዯበተ ርቱዑነታቸውና ከመንፈሳዊ ብስሇታቸውም የተነሳ ቀዯም ብሇው
ካፈራቻቸው ተከታዮች/ዯጋፊዎች፣ በእኩያዋቻቸውም ከነበራቸው አክብሮት ተዲምሮ ገና በቀሊለ ሉፈቱ
ይችለ የነበሩ ችግሮች ገና ሇገና ባይስማሙስ ተብል በፖሇቲካዊ ጣሌቃ ገብነት የተፈጸሙም አለ ተብል
ስሇሚታመን ነው።
ሇኢትዮጵያ ኦርቶድክስ ተዋህድ ቤተ-ክርስቲያን የእምነት ተከታዮች በሙለ:
“አንተ ግን፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ ከዚህ ሽሽ፤ ጽዴቅንና እግዚአብሔርን መምሰሌ እምነትንም
ፍቅርንም መጽናትንም የዋህነትንም ተከታተሌ” (1ኛ ጢሞ. 6፣ 11) ሇምን? ቢለ የሀገሬ ሰው የዝንጀሮ
መንጋ ቢከተለት ገዯሌ ያሇው እንዲይዯርስብህ እንሇዋሇን።
ሇመገናኛ ብዙሏን:
ጉዲዩ አባ ጳውልስን የሚያንኮታኩትና የሚያዲክም ፍሬ ነገር ቢኖረው ኖሮ ይሄኔ ስንሻው ተገኘ እየተባሇ
በተገኘችው ትንሽ ቀዲዲ እያሰፋና እንዯ ሊስኪትም እየወጠረ የማያፏጭ ፍጥረት አይኖርም ነበር። ሇመሆኑ
“ፍትሕ ተጓዯሇ ዴሃ ተበዯሇ! ፍትሕ እንሻሇን! ፍትሕ! ፍትሕ! ዲኝነት!” እየተባሇ ብዙ የሚጮክሇት ምን
ዓይነቱ ፍትሕ ይሆን? ሰው ሳይዯመጥ፣ ቀርቦም የእምነትም ሆነ የክህዯት ቃለን ሳይሰጥ፣ ስርዓተ ቤተ-
ክርስቲያን ተጥሶ የአንዴ ወገን ዴምጽ ብቻ ተሰምቶ ሇዛውም የከሳሽ አቤቱታ ሰው ባሌዋሇበት ጥፋተኛ ነህ
ተብል ሲገፋ ሇአሊስፈሊጊ የህይወት ውጣ ውረዴም ሲዲረግ እንዳት አስቻሊችሁ? እንግዱህ ወዯዴንም
ጠሊንም እነዚህ ወገኖችም እኩሌ እንዯላሊው የፍትህ ያሇህ! ጭኸት የሚሻቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ስሇ ላሊው እምነት የፍትህ ጉዲይ ሲጮክ ስሇ እነዚህም ሽፋን ተሰጥቶት “የፍትህ ያሇህ! የዲኛ ያሇህ!”
ተብል መጮክ በተገባ ነበር ዲሩ ግን ፖሇቲካዊ ትርፉ ሲሰሊ ሚዛን የማይዯፋ ሆኖ በመገኘቱ ይቅር ርዕሰ
ዓንቀጽ ተሰርቶ ሉጮክሊቸው ቀርቶ ጽሐፎቻችን እንኳን ሊሇማስተናገዴ ያሇምንም ምክንያት በሮቻችሁ
ዘግታችኋሌ።
ጠቢቡ “አባቱን የሚረግም እናቱንም የማይባርክ ትውሌዴ አሇ” ሲሌ እንዱህ ያሇ ነገር ገጥሞት ይሆን?
ራሱን ስዯተኛ ሲሌ ሇሚጠራ ሲኖድስ:
እናንተ የስዯታችን ምክንያት “ስርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ተጣሰ፣ ፈረሰ!” ነው ባዮችስ ወዳት ናችሁ? ምን
አሊችሁ? ምን ነው? ባሌገባችሁ፣ በማይገባችሁ፣ በማያገባችሁና በማይመሇከታችሁ ጉዲይ ከበሮ ስትዯሌቁና
ስታሳብቁ በየአዯባባዩም ተጽፎ የተሰጣችሁን ስታነበንቡና ይህን ይበለሌን ተብሊችሁ አፋችሁ እንዯ
ተከፈተ መቃብር ስትከፍቱ፣ መስቀሌ ተሸክማችሁ ጥሊም ዘርግታችሁ አሊህ ወአክበር ስትለና ስታስብለ
ያሊሳፈራችሁ በእምነት የሚመስሎችሁ፣ በገዛ ሌጆቻችሁና ወንዴሞቻችሁ በጠራራ ጸሏይ በአዯባባይ ፍትህ
ሲጓዯሌባቸው ሲበዯለና አሇ አገባብ ሲገፉ ዝም ያሊችሁ? ወይስ መጽሏፍ “መዝገብህ ባሇበት ሌብህ ዯግሞ
በዚያ ይሆናሌና” (ማቴ 6፥21) እንዱሌ ሌባችሁ በሰዎች እጅ ሆነችና አይታችሁ እንዲሊያችሁ ሰምታችሁም
እንዲሌሰማችሁ በመሆን የዴሃውን ጭኸት እንዲትጮኹ ቆሌፈው አስቀመጧችሁ?
ሇማንኛውም መሌሰን እስክንገናኝ ዴረስ በዚች አጭር ግጥም ሌሇያችሁ።
ኧረ ምን ዓይነት ነው የሃይማኖት ደብዲ:
የባሪያቱን አስወዴድ የጭዋይቱን ሌጅ ሚያስከዲ።
ኧረ ምን ይሻሊሌ ጳጳሳቱ አበደ:
መስቀሌ አንጠሌጥሇው ሲያበቁ ክርስቶስን ከነ ወንጌለ የካደ።
ኧረ ሰዎቹ (ሉቃነ ጳጳሳቱ) ሞኞች ናቸው:
እንዲባዘኑ በጎች ጋጣ እንዯ ጠፋባቸው:
በአባቱ ቀኝ የተቀመጠውን ሉቀ ካህን ማጣታቸው።
የዝንጀሮ መንጋ ቢከተለት ገዯሌ
እስቲ ጨምሩበት በበዯሌ ሊይ በዯሌ!
ከዱ/ን ሙለጌታ ወሌዯገብርኤሌ
yetdgnayalehe@gmail.com
Unated States of__america

You might also like