Professional Documents
Culture Documents
Kes Berhan Medhanit
Kes Berhan Medhanit
ሀገረሰባዊ ህክምና ጤና ነክ ድርጊቶችን፣ የአቀራረብ መንገድችን፣ ዕውቀትንና እምነቶችን፣ እፀዋትን፣ እንሰሳትን፣ ማዕድናትን፣
መንፈሳዊ ቁሶችንና መንፈሳዊ ክዋኔዎችን መሰረት በማድረግ ህመሞችን የማወቅ፣ የመከላከልና የመፈወስ ስርዓት እንደሆነ
ይታያል ሲቀጥልም ይታሰባል፡፡
በማህበረሰቡ በሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ የጤና ችግሮች መፍትሄ የማግኘት በሚል የማህበረሰቡ አባላት የሚከውናቸው
አጠቃላይ ድርጊቶች በሀገረሰባዊ ህክምና ውስጥ የሚጠኑ ጉዳዮች እንደሆኑ ይታያል፤ይታሰባል፡፡ እነዚህ ድርጊቶችም
ማህበረሰቡ ስለ ህመምና ጤና ያለው እሳቤ፣ ስለ ህመምተኛው ያለው አመለካከት፣ ስለ ህክምና ባለሙያዎቹ ያለው
አመለካከት፣ አንድን የህመም አይነት ለመለየት የሚጠቀምበት ዘዴ፣ ለበሽታዎቹ መከላከያ ወይም ማጥፊያ የሚሆኑ
መድኃኒቶችን ከምን ከምን እንደሚያዘጋጅ፣ እንዴት እንደሚያዘጋጅ፣ መቼ እና የት እንደያሚዘጋጅ፣ የመደኃኒቶቹ የአወሳሰድ
ስርዓት እና ለህክምናው የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች የመሳሰለትን ነጥቦች ሁሉ እሳቤ ውስጥ ይገባሉ፤ ይታያሉ።
በአጠቃላይ የባህል ሕክምና እውቀት የማህበረሰብን አካባቢያዊ እውቀት፣ እምነት፣ ደንብ፣ ሥርዓት፣ ተግባርና ሙያን ታሳቢ
ያደረገ፤ጥበባዊ ድርጊትን ያካተተ፤ የተለያዩ የበሽታ መንስኤዎችን፣ አውዲዊ ሥርዓቶችን፣ የጤና መጠበቂያና በሽታ
መከላከያ ዘዴዎችን መሰረት ያደረገ ነው፡፡ (ብርቱካን 2012፣ 6)
2/ሀገረሰባዊ ህክምና መድኃኒት ከመንፈሳዊ ሃይማኖት አንጻር ምን ማለት ነው? ምን አይነት እሳቤ አለ?
ሀገረሰባዊ ህክምና መድኃኒት ከመንፈሳዊ ሃይማኖት አንጻር በጣም ተገቢ እና ተመራጭ እንዲሁም ተመካሪ የሆነ መደሃኒት
ነው፡፡ ምክንያቱም መድኃኒቱን የሚያዘጋጁት በመንፈሳዊ ሃይማኖት የበለጸጉ፡ የበሰሉ አባቶች ናቸውና፡፡ ለዚህም ማስረጃ
መጽሐፈ ሲራክ 38፡1 ላይ እንዲህ ሲል ይገኛል”እሱን እግዚአብሔር ስለመረጠው ጌትነቱ እንደ እጁ ሥራ ነውና ባለ
መድኃኒትን አክብረው”ይላል፡፡አሁንም ከዛው ምእራፍ ቁጥር 3 ላይ እንዲህ የሚል ምስክር ይገኛል”ባለ መድኃኒትን
በጥበቡ ያከብሩታል በመኳንንትም ዘንድ ይመሰገናል” ይላል፡፡ Assefa (1992; P.4)፤ "የኢትዮጵያ ሃይማኖትና አምልኮ
የውጭ አገር ተፅዕኖ አለበት" ይላሉ፡፡ የባህል ሕክምና ዕውቀት ከሃይማኖት፣ ከእምነትና ከአምልኮ ሥርዓትና ተግባር ጋር
እንደሚገናኝ ጠቁመው፤ የኢትዮጵያ ሃይማኖት፣ አምልኮና እምነት ከጎረቤት አገሮች ጋር የተወራረሰ በመሆኑ፤ የውጭ አገር
ሃይማኖትና ልማድ ተፅዕኖ እንዳለበት ገልፀዋል፡፡ በተለይ ከግብፅ፣ ከዐረብና ከሱዳን በነበረን፤ የንግድና የሃይማኖት ግንኙነት
የባህል ሕክምና ዕውቀትና ሥርዓት፣ አምልኮና ጥበብ ወደ ኢትዮጵያ እንደገባ (እንደተዛመተ) አትተዋል፡፡
3/ሀገረሰባዊ መደኃኒት መቸ እንደተጀመረ ከመንፈሳዊ አስተሳሰብ ከክርስትና(መጽሐፍ ቅዱስ ገድላት እና ሌሎች አዋልድ
መጽሐፍት አንጻር )
የባህል ሕክምና እውቀት፣ ልማድና አተገባበር ሥርዓት መቼ ተጀመረ? እንዴት? እና እነማን ጀመሩት? የሚል ጥያቄዎችን በቂ
ምላሽ፣ መረጃና ማስረጃ ማግኘት እንደሚያስቸግር፤ በመስኩ ጥናት ያደረጉ ተመራማሪዎች (አሰፋ፣2008፤ Pankhurst,1996;
Alemayehu,1984) ጠቁመዋል፡፡
Alemayehu (1984) የባህል ህክምና አጀማመር አስመልክተው ሲገልጹ “የሰው ልጅ በሽታን መከላከል፣ መድኃኒትን
መጠቀምና መፈወስ የጀመረው ከጥንተ-ክርስቶስ ልደት 25,000 ዓ.ዓ በፊት ነው” ይላሉ፡፡ በሌላ በኩል (Desta ,2004) እና
(Pankhurst ,2005) በኢትዮጵያ የባህል ሕክምና ታሪክ አጀማመር በቂ የታሪክ ማስረጃ እንደሌለ ገልጸው፤
ስለኢትዮጵያውያን የባህል መድኃኒት አጠቃቀም እውቀት የመጀመሪያ ደረጃና መረጃ የሚሉት የ”Alessandro Zorzi እና
የ Francisco Alvares”ን ዘገባ ነው፡፡
ሃገረሰባዊ መደኃኒት መቼ ተጀመረ ለሚለው ከመንፈሳዊ አስተሳሰብ አንጻር እና ከክርስትና ፤ከመጽሐፍ ቅዱስ፤ከገድላት
እንዲሁም ከአዋልድ መጽሃፍት ተመልክተን ጠቅለል ያለ ሃሳብ ስናቀረብ ገድላት በራሳቸው መድሃኒት ናቸው፡፡ምክንያቱም
እግዚአብሔር ገድሉ የተጻፈለትን ቅዱስ በስምህ ላመነ፤ለተማጽነ፤ለለመነ ፤ባንተ ስም ነደያንን ላበላ ላጠጣ ደዌ ሥጋ ደዌ
ነብስ አያገኘውም ብሎ ቃል ገብቶለታልና አማኞች ይህን አምነው ብያደርጉ ይድናሉ፡፡መጽሃፍ ቅዱስም ይህን ሐሳብ እንዲህ
ሲል (ማቴ 10፡40_42) ያጠነክረዋል፡፡
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ
ያገኛል፤ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቅን ዋጋ ያገኛል። ስለዚህ እውነት እላችኋለሁ፣ ማንም ሰው ከእነዚህ
ከታናናሾች ለአንዱ ደቀ መዝሙሬ በመሆኑ አንድ ጽዋ ቀዝቃዛ ውሃ ቢሰጠው ዋጋውን አያጣም።”
እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና
እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡} ዩኑስ 52
መንስኤው እንዲህ ነው ባይባልም እግዚአብሔር ግን ሳያውቀው ድንገተኛ ችግር ሆን በሽታ በአጋጣሚ አያመጣም፡፡ነገር
ግንእግዚአብሔር ለሰው ልጅ ሲያዝን ለእርግማት ወይም ለቅጣት በሽታን ሊልክ ይችላል ይባላል፡፡ለዚህ መሰል በሽታ
ፈውስ የሚገኘው ደግሞ በእምነት ላይ በተመሰረተ ህክምና ነው፡፡ለዚሕ ተጠቃሽ ጸበል ነው፡፡መጽህፍ ቅዱስ ላይም
ተጠቅሷል፡፡በቤተ ሳይዳ የነበረው መጠመቂያ ውሃ የእግዚአብሔር መልአክ ሲያንቀሳቅሰው በሽተኞች እየገቡ ይፈወሱ ነበር
ይላል፡፡(ዮሐ 5፤41) በሐገራችንም ሜሮን (ቅብዓ ቅዱስ)ቤተክርስቲያን የምታሰጠው መድኃኒት ነው፡፡ይህም በመጽሐፍ
ቅዱስ ማር 6፡13 ” ብዙ አጋንንትም አስወጡ፤እንዲሁም ብዙ ሕመምተኞችን ዘይት እየቀቡ ፈወሱ።”ይላል፡፡ሌላው
ፈውስ ማግኛ ጸሎት ነው፡፡ለዚህም መጽሃፍ ቅዱስ ማስረጃ አለው፡፡ሐዋ 9፡40_41
በእስልምናም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ፈውስ ከፈጣሪ እንደሚገኝ ያምናል፡፡ተአምራዊ ፈውስ የሚል እስላማዊ የህክምና
መጽሃፍ ላይ እንደተጻፈው”ሙስሊም የሆነ ሰው ሁሉ ይህን የአላህ ቃል አምኖ መቀበል እና በአላህ ፈዋሽነትም በመመካት
መለኮታዊ እና ተአምራዊ ኃይል በሆነዉ ተአምራዊ መደሃኒት መጠቀም ብልሃትነት ነዉ ይላል፡፡”
እምነት (ሰሎሞን 2007፣ 179) ስነልቦናዊ ሁነት( psychological state) ሲሆን አንድ ሰው እምነትነው ብሎ የሚቀበለውና
አማኙም የሚያምንበት ነገር የራሱን ምክንያት ወይም ማብራርያ የሚያቀርብበት ስርዓት ነው። እነዚህን ምክንያቶች ወይም
ማብራሪያዎች በዕምነቱ ዙርያ ያለ ማስረጃዎች፣ መመሪያዎች፣ ህጎች፣ ደንቦች፣ ሰርዓቶች ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። ስነልቦናዊ
ሁነት የሆነው ዕምነት አዕምሮአዊ ውክልና የመስጠት ሂደት ነው። አዕምሮዓዊ ውክልናዉም እምነቱን በሚቀበለው
ማህበረሰብ ወይም በወካዩ(object of belief) መካከል ያለው መንፈሳዊ መስተጋብር ነው።
እምነት ማለት “ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው፡፡ ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል
እንደተዘጋጁ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን (ዕብ 11፡1-3)፡፡” ለምሳሌ መንግስተ
ሰማያትን (የዘላለም ሕይወትን) ተስፋ እናደርጋለን፡፡እምነትም ይህንን ተስፋ ያረጋግጥልናል፡፡ የእግዚአብሔርን (የሰማዩን)
መንግስት አላየነውም፡፡ እምነት ይህንን ያላየነውን ነገር ያስረዳናል፡፡ ሳይንስ ይህንን ሊያደርግ አይቻለውም። እምነት በፍጹም
እውነት (absolute truth) ላይ እንጂ እንደ ሳይንስ በአንጻራዊ እውነት (relative truth) ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡
የመፅሃፌ ቅደስ መዜገበ ቃሊት ዯግሞ ሇቃለ