You are on page 1of 1

1 ፓስተር ክሪስ

እውነቱን አምናችሁ ተግብሩት

እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል (ዮሐ 8፡32)።


አንድ ቀን፣ የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ያለበት አንድ ሰው ሊያየኝ መጣ። የደረት ሕመም ነበረበት፣ እናም በሚያስልበት ወቅት ደም ይወጣው
ነበር ። በጣም ከባድ ነበር። ለኔ ለማሳየት የምርመራውን ሰነዶች አወጣ። ከዚያም እኔ “ክርስቶስ በአንተ ወስጥ እንደሚኖር ታምናለህን?”
አልኩት። እሱም “አዎ” አለ። ስለዚህ፣ “ያ ማለት በአንተ ውስጥ ያለው የክርስቶስ ሕይወት ለህመም፣ ለበሽታ፣ ወይም ለማንኛውም ዓይነት
ኢንፌክሽን የማይጋለጥ ስለሆነ የሳንባ ነቀርሳ ልትያዝ አትችልም ማለት ነው” አልኩት።
ወደ ዶክተሮች ሲመለስ፣ የሳንባ ነቀርሳ የሌለበት መሆኑን አረጋገጡ. ሃሌሉያ! ሰውየው በጣም ተደነቀ ። ጥያቄው ግን ፣ ሰዎች ለምን
በበሽታ ይጠቃሉ ነው? ምክንያቱ ምድነው ኢየሱስን ስለማያውቁ፤ እውነቱን አያውቁም። ስለ መለኮታዊ ጤንነት እውነተኛውን ወንጌል
ሰምተው በሕመም ወይም በበሽታ የሚጠቁ ሰዎችስ? የሰሙትን በትክክል እንደማያምኑ በቀላሉ ያሳያል። ስታምኑት፣ ሕይወታችሁን
ይለውጠዋል!
በመግቢያ ጥቅሳችን ላይ እንዳነበብው፣ ኢየሱስ “እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል” ብሏል። ኢየሱስ ማንንም
አልዋሸም፤ በጭራሽ! ለምሳሌ “ሳንባ ነቀርሳ አለብኝ” ስትሉ በምን አውቃችሁ ነው? ምናልባት ለቀናት ማሳል፣ ደም ወይም አክታ ማሳል፣
የደረት ህመም፣ ወዘተ የመሳሰሉ ምልክቶች እና ስሜቶች ተሰምተዋችሁ ይሆናል። ይህም ሳንባ ነቀርሳ እንዳለባችሁ አሳምኗችኋል። ግን ለምን
እግዚአብሔር ስለ አናንተ ያለውንስ ለማወቅ አትሞክሩም? በህይወታችሁ ውስጥ የእግዚአብሔር መገኘት ምልክቶች ምንድን ናቸው?
የማንን ዘገባ ታምናላችሁ? የእግዚአብሔርን ወይስ የዶክተሮቹን? ምላሽ የምትሰጡት ላመናችሁበት ነው። የሕመም ምልክቶችን እና
ስሜቶችን ስታምኑ ታማሚ እና በሽተኛ ትሆናላቹህ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ብተታመኑ፣ ለውጥ ይሆናል፤ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ
ስላለ ደማችሁ እንደነጻ ትገነዘባላችሁ፤ በሰውነታችሁ ውስጥ ምንም አይነት በሽታ ወይም ህመም ሊንሰራፋ አይችልም። ክብር ለእግዚአብሔር
ይሁን !

የእምነት ዓዋጅ

ከተራ ሰው ከፍ ያለ የማይጠፋ ህይወት አግኝቻለሁ። አዲሱ ሕይወቴ የመጣው ንጹህ ከሆነው ከእግዚአብሔር ቃል ነው ፤ እንዲሁም
ዘላለማዊ ነው፣ ምክንያቱም ሰውነቴን የተቆጣጠረው መንፈስ ቅዱስ፣ በመለኮታዊ ሕይወት ስለሞላውና፣ ሕመምን ሁሉ ከእኔ ስለሚያራግፍ
ነው። ለበሽታ የተጋለጠው አሮጌው ሕይወቴ በእግዚአብሔር ሕይወት ተተክቷል። ይህንን እውነት አምናለሁ፣ እናም በዚህ እኖራለሁ! ክብር
ለእግዚአብሔር ይሁን።

ለተጨማሪ ጥናት
ኢሳይያስ 53:1
1 ኛ ጴጥሮስ 1:23
ሮሜ 8፡10-11

You might also like