You are on page 1of 24

ፌዴራላዊ አስተዳደር መርሆዎች እና

አተገባበር በኢትዮጵያ

ሪዋርድ የልማት ድርጅት ከጀስቲስ ፎር ኦል ፕሪዝን


ፌሎሺፕ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለም/ቤቶች የተዘጋጀ
የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ

አቅራቢ
ዶ/ር ዘሪሁን ይመር (ረ/ፕሮፌሰር)

አዳማ
ህዳር 23-24 ቀን 2014 1
መውጫ

ክፍል አንድ
ፌዴራላዊ አስተዳደር አወቃቀር

ክፍል ሁለት
ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት

ክፍል ሦስት
የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት

2
ክፍል አንድ
ፌዴራላዊ አስተዳደር አወቃቀር

3
የፌዴራሊዝም ፅንሰ-ሐሳብ
• ፌዴራል የሚል ቃል “Foedus” ከሚል የላቲን ቃል የተወረሰ ነው፡፡
• ፌዴራል ትርጉሙ ቃል-ኪዳን፣ ኮንትራት፣ ድርድር ወይም
የአብሮነትና በጋራ የመኖር ውልን ይወክላል፡፡
• ስለሆነም ፌዴራላዊ የመንግሥት አወቃቀር ማለት የራስ-
አስተዳደርንና የጋራ-አስተዳደርን ያጣመረ፣
• ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ መንግሥታት የሚፈጠሩበት፣
በቃልኪዳን የሚመሠረትና የሚመራ አጋርነት ነው፡፡
• አጋርነቱ በመካከላቸው ሊኖር የሚገባውን የሥልጣን ክፍፍልና
ዝምድናን ይወስናል፡፡
• አንዱ የሌላውን የማንነት መገለጫዎች የሆኑትን የታሪክ፣ የባህል፣
የቋንቋና የሃይማኖት እኩልነትን በማክበር ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

4
የፌዴራሊዝም አመጣጥና አመሰራረት
• የፌዴራል አወቃቀር የተጀመረው በእስራኤሎች እንደሆነ
ይጠቀሳል፡፡
• በ1291 የስዊዝ ኮንፌደሬሽን ተመሠረተ፡፡
• የስዊዝ ኮንፌደረሽን እንደገና በ1848 መሠረታዊ የሆኑ
ፌዴራላዊ መርሆዎችን ያሟላ ሥርዓት ሆኖ ተዋቀረ፡፡
• በ1789 የተመሠረተው ፌዴራል ሥርዓት የአሜሪካ ሆኖ፤
ዘመናዊ የፌዴራል ሥርዓት አወቃቀርን ተግባራዊ ያደረገ
እንደሆነ ይታመናል፡፡

5
የቀጠለ…
• ለፌዴራል የመንግሥት አወቃቀር እንደ ምክንያት የሚወሰዱ
በርካታ ቢሆኑም በብዙ ፀሃፊዎች የሚጠቀሱት የሚከተሉት
ናቸው፡-
 ፀጥታና የመስፋፋት አደጋ፡- ጠንካራ የመከላከያ ሃይል ማስፈለጉ
(ካናዳ፣ ጀርመን፣ ህንድ እና ማሌዢያ)፤
 ሰፊ የጋራ ገበያና ኢኮኖሚ የመፍጠር ፍላጎት (ካናዳ እና የአውሮፓ
ህብረት)፤
 አንድነትን ከብዝሃነት ጋር አጣምሮ ለማስቀጠል(ኢትዮጵያ)፤
 ርዕዮተ-ዓለማዊና ድህረ-ቅኝ ግዛት መፍትሄ (ኡጋንዳ እና ናይጀሪያ)፤
 ድህረ-ግጭት ፌዴራሊዝም (አሜሪካ፣ ኢትዮጵያ እና ደ/አፍሪካ)፤
 ለትልቅ የቆዳ ስፋት የሚስማማ አወቃቀር መሆኑ፤ ወዘተ ናቸው፡፡

6
የፌዴራሊዝም አወቃቀር አይነቶች

7
የፌዴራል ሥርዓቶች መሠረታዊ ባህርያት
1. የተፃፈ ህገ-መንግሥት፤
2. ከህዝባቸው ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸው ቢያንስ ሁለት
መንግሥታት፤
3. ህገ-መንግሥታዊ ዋስትና ያለው የሥልጣን ክፍፍል፤
4. ክልሎች የሚወከሉበት ሁለተኛ ምክር ቤት፤
5. ገላጋይ ተቋም እና
6. የመንግሥታት ግንኙነት ሥርዓት ናቸው፡፡

8
ክፍል ሁለት
ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት

9
የህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት ምንነት
• የቡድን ማንነት መገለጫዎች በሥርዓቱ መሠረታዊ የፖለቲካ
አስተሳሰቦችና የመንግሥት አወቃቀሮች የሚንፀባረቁበት ነው፡፡
 የቡድን ማንነት መገለጫዎች ደግሞ ብሄር፣ ብሄረሰብ፣ ባህል፣
ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ማህበራዊ መስተጋብር
ወዘተ ናቸው፡፡
• ብዝሃነትንና ህብረትን በማጣመር አንድነትን የሚያስቀጥል
ሥርዓት ነው፡፡

10
የቀጠለ …
• ብዝሃነት ማለት በአንድ ሃገር ውስጥ በተለያዩ ማንነቶች
የሚገለፁ የተለያዩ ቡድኖች/ማህበረሰቦች ግልፅ በሆነ አሰፋፈር
ወይም ታሪካዊ ምንጭ ተካተው ሲገኙ ነው፡፡
• ህብረት ማለት ብዝሃነትን በማክበርና በጋራ ጥቅምና ፍላጎት
ላይ በመመስረት አብሮ የመቀጠል ውሳኔ/ስምምነት ማለት
ነው፡፡
• ስለሆነም ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት ለመመስረት
ምክንያት ሊኖር ይገባል፡፡

11
የቀጠለ …
1) ብዝሃነትንና ህብረትን ለማስቀጠል ከብዝሃነት የሚመነጩ ነገር ግን
በህብረት የሚሟሉ ፍላጎቶች ሲኖሩ፤
2) ለጋራ ጥቅም ሲባል የተከወነ የጋራ ታሪካዊ ፍፃሜ ሲኖር፤
3) የባህል፣ የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣ የአሰፋፈር፣ የገበያና የንግድ፣ እንዲሁም
ሰፋ ያለ ማህበራዊ ትስስርና መወራረስ ሲኖሩ፤
 ስለሆነም ሕብረ-ብሄራዊ ፌዴራሊዝም በብዝሃነት ላይ የተመሰረተ
ህብረት ወይም አንድነትና ማንነቶች የሚጎለብቱበት ውህድ ነው፡፡
• የጋራ ፍላጎት፡- ሰፊ ገበያ፣ ጠንካራ የመከላከያ ሃይል፣ በዓለም አቀፍ
ግንኙነት ጠንካራ የዲፕሎማሲና የመደራደር ዓቅም እንዲሁም
ጠንካራ የንግድ ልውውጥ ዓቅም፡፡
• የጋራ ማንነት፡- የጋራ ዜግነት፣ የጋራ ሰንደቅ ዓላማ፣ የጋራ ታሪካዊ
ፍፃሜ፣ ከአብሮነት የሚመነጭ የጋራ ሀገራዊ ስሜት፣ ወዘተ ናቸው፡፡
12
የህብረ-ብሄራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓት መርሆዎች
• የቃል ኪዳን ማሰሪያ የሆነ ህገ-መንግሥት መኖርና መከበር፤
• በስምምነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ህብረት መኖር፤
• ብዝሃነትን የሚያንፀባርቅ የፖለቲካ አወቃቀር በማዕከልና
በክልሎች መከተል፤
• መከባበር፣ መቻቻል፣ መደጋገፍ (በጋራ የመኖር እሴቶችን
ማጎልበት)፤ ወዘተ ናቸው፡፡

13
የህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት መሠረታዊ ባህሪያት

• ዴሞክራሲ፤
• መድብለ-ፓርቲ ሥርዓት፤
• በመፈቃቀድ ላይ የተመሠረተ የህዝቦች ህብረት፤
• የመብቶች ጥበቃ፤
• ለቡድኖች/ማንነቶች ልዩ ትኩረት መስጠቱ፤
• ብዝሃነትና አንድነት የማይነጣጠሉበት፤
• ግንኙነቶች በመንግሥታት፣ በመንግሥታት ተቋማትና በህዝቦች
መካከል መኖር፤ ወዘተ ናቸው፡፡

14
የሕ/ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት ምሥረታ መነሻዎች
• የአንድ ብሄር መንግሥት አስተሳሰብ ብዝሃነትን ለማጥፋት
የሚወስዳቸው እርምጃዎች ውጤታማ አለመሆናቸው፤
• የህብረ-ብሄር መንግሥት ምስረታን የሚያቀነቅን አስተሳሰብ ሰፊ
ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ፤
• በተለያዩ ሃገራት የተለያዩ ቡድኖች ማንነታቸውን እያረጋገጡ
መምጣታቸው፤
• ህብረ-ብሄራዊ ሥርዓትን በመመስረት ስኬት መመዝገቡ፤
• የማንነት መብቶችን ለማረጋገጥ ሲባል ሲከሰቱ የነበሩ የተለያዩ
ግጭቶች ሊረግቡ መቻላቸው፤ ወዘተ ናቸው፡፡

15
የህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት ጠቀሜታ
• ስልጣንን ያከፋፍላል፤
• የቡድኖችን/የማንነቶችን መብቶች ያስጠብቃል፤
• ብዝሃነትን ከህብረት ጋር በማጣመር አንድነትን ያስቀጥላል፤
• ለመገንጠል ምክንያት የሚሆኑ ችግሮችን በመፍታት የመገንጠል
አደጋን ያስወግዳል፤
• ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ያመቻቻል፤
• በጎ ውድድርና ፈጠራን ያበረታታል፣ ሰፊ የኢኮኖሚ ዓቅም ይገነባል፤
• የመደማመጥ፣ መከባበርና መደጋገፍ ፖለቲካዊ ባህልን ይገነባል፤
ወዘተ ናቸው፡፡

16
ክፍል ሦስት
የኢትዮጵያ ህብረ-ብሄራዊ ፌዴራል
ሥርዓት

17
የኢትዮጵያ ህብረ- ብሄራዊ ፌዴራል ሥርዓት መነሻዎች

የማንነት ጭቆና፤
የተዛባ ግነኙነት ስለነበረ፤
የሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ዓፈና፤
የመልማት መብት መነፈግ፤
ዘላቂ ሠላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ስላልነበረ፤
የህግ የበላይነት ስላልነበረ፤
የመልካም አስተዳደር እጦት፤ ወዘተ ናቸው፡፡

18
የቀጠለ …
ስለሆነም:-
 የብሄሮች፣ የብሄረሰቦችና የህዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን
መብትን ለማረጋገጥ፤
 የተዛባውን ግነኙነት ለማረም፤
 ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን
ለማስቻል፤
 ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን፤
 በህግ የበላይነትና በፍቃድ ላይ የተመሰረተ አንድ የፖለቲካ
ማህበረሰብን በጋራ ለመገንባት፤
 መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች እንዲከበሩ ለማድረግ፤
 ባህሎችና ሃይማኖቶች ካላንዳች ልዩነት እንዲራመዱ ለማድረግ፤
ወዘተ ናቸው፡፡
19
የኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት ልዩ ባህሪያት
• የፌዴራል ሥርዓቱ አወቃቀር ዋነኛ መገለጫ ማንነቶች ናቸው፤
• ብሄሮች፣ ብሄርሰቦችና ህዝቦች ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤት ናቸው፤
• ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች የራሳቸውን ዕድል በራሳቸው
የመወሰን መብት ተጎናፅፈዋል፤
• ህገ-መንግሥትን መተርጎም የፌዴረሽን ም/ቤት ሥልጣን ነው፤
• የቡድንና የግለሰብ መብቶች እኩል የተረጋገጡበት ነው፤
• የሃይማኖት እኩልነት ልክ እንደብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እኩልነት
በኢትዮጵያ ብሄራዊ ዓርማ ተንፀባርቋል::

20
የፌዴራል ሥርዓቱ ተግዳሮቶች

• በሥርዓቱ ላይ የሚታዩ የአመለካከት ልዩነቶች፤


• የወሰንና የማንነት ግጭቶች፤
• የመልካም አስተዳደር ችግሮች፤
• ለህዝቦች ጥያቄዎች ተገቢና አፋጣኝ መልሶችን ያለመስጠት
ችግር፤
• የመንግሥታት ግንኙነት ደካማ መሆን፤ ወዘተ ናቸው፡፡

21
የወደፊት አቅጣጫዎች
• ብዝሃነትን ማክበር፤
• የጋራ ማንነት መገለጫዎችን ማጎልበት፤
• የመከባበር፣ የመደማመጥ፣ የመቻቻል፣ የመደጋገፍ እና
የመተባበር ባህልን ማጎልበት፤
• የመንግሥታትና የህዝቦች ግንኙነቶችን ማጠናከር፤
• ሥልጣንን ያለማማከል፤
• ሰፋ ያለ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፕሮግራሞችን መቀየስ፤
• መልካም አስተዳደርን ማስፈን፤
• የፓርላማን (የም/ቤቶችን) ሚና ማጎልበት፤ ወዘተ ናቸው፡፡

22
የመወያያ ጥያቄዎች
በቡድን በመከፋፈል በሚከተሉ ጥያቄዎች ላይ ውይይት አድርጉ
1.የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አስተዳደር ያስገኛቸው ጥቅሞች አሉ? ካሉ
ጥቅሞቹ ምንድን ናቸው?
2.በኢትዮጵያ የፌዴራል ሥርዓት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች ወይም ተግዳራቶች
ምንድን ናቸው? እነዚህን ተግዳራቶችስ እንዴት ማረም ይቻላል?
3.በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገ-መንግሥት ውስጥ መሻሻል ያለባቸው አንቀፆች አሉ?
አንቀፆቹስ እነማን ናቸው? ለምንስ ይሻሻላሉ? እንዴትስ ይሻሻላሉ?
4.ኢትዮጵያ ውስጥ ዘላቂ ሰላም ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍን፣
እንዲሁም ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት እንዲፋጠን ምን መደረግ አለበት
ብለው ያምናሉ? ከዚህ አንፃር የህግ አጪ ም/ቤቶች ሚናስ ምን መሆን
አለበት?

23
አመሰግናለሁ!

24

You might also like