You are on page 1of 38

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ

የማህበራዊ ሳይንስ እና ሰባዊነት ኮሌጅ

የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች)ና ስነ ጽሑፍ: አማርኛ ትምህርት ክፍል

የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ የህይወት አኗኗር ይዘት ትንተና

ጤና የኔአጋዥ

ለመጀመሪያ ዲግሪ በከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ

ነሃሴ 2014 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ
በምስራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ከተማ አስተዳደር በ 01 ቀበሌ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ
ክርስቲያን የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት አኗኗር ይዘት ትንተና

የማህበራዊ ሳይንስና ሰባዊነት ኮሌጅ የኢትዮጵያ ቋንቋ(ዎች)

እና ስነ ጽሑፍ:አማርኛ ትምህርት ክፍል

ጤና የኔአጋዥ

ለአማካሪ ድርቧ ደበበ(ደ/ር)

ለመጀመሪያ ዲግሪ በከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥናታዊ ጽሁፍ

ነሃሴ 2014 ዓ.ም

ደብረ ማርቆስ
,

ማውጫ

ይዘት ገጽ
ማውጫ...........................................................................................................................................................i
ምስጋና...........................................................................................................................................................iv
አጠቃሎ..........................................................................................................................................................v
ምዕራፍ አንድ:- መግቢያ 1...................................................................................................................................1
1.1. ጥናቱ ዳራ.............................................................................................................................................1
1.2. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት.............................................................................................................................2
1.3. የጥናቱ ዓላማ.........................................................................................................................................2
1.4. ጥናቱ የሚመልሳቸዉ ጥቄዎች.....................................................................................................................2
1.5 የጥናቱ ጠቀሜታ......................................................................................................................................2
1.6. የጥናቱ ወሰን..........................................................................................................................................3
1.7.በትናቱ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ እርምጃዎች......................................................................................3
1.7.1. በጥናቱ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች...........................................................................................................3

1.7.2. ላጋጠሙ ችግሮች የተወሰዱ መፍትሔዎች................................................................................................3

ምዕራፍ ሁለት:-ክለሳ ድርሳን.................................................................................................................................4


2.1. ፅንስ ሀሳባዊ ቅኝት...................................................................................................................................4
2.1.1.የቆሎ ተማሪዎች ስያሜ ምንነት...............................................................................................................4

2.2. የቆሎ ተማሪዎች አኗኗር.............................................................................................................................5


2.3.የቀደሙ ጥናቶች ቅኝት...............................................................................................................................7
ምዕራፍ ሦስት:- የጥናቱ ዘዴ...............................................................................................................................12
3.1. የናሙና አመራረጥ ዘዴ...........................................................................................................................12
3.2.የመረጃ መሰባሰቢያ ዘዴ...........................................................................................................................12
3.2.1. ምልከታ.......................................................................................................................................12

3.2.2. ቃለ መጠይቅ................................................................................................................................13

3.1.3. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ.....................................................................................................................13

ምዕራፍ አራት:- አካባቢያዊ ዳራ...........................................................................................................................15


ምዕራፍ አምስት፡- የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት መገለጫዎች..................................................................................16
5.1. ጉዞ.....................................................................................................................................................16
5.2. ልመና.................................................................................................................................................16

i
,

5.2.1. የመለመኛ ሰዓት..............................................................................................................................17

5.2.2. የመንደር ድልድል...........................................................................................................................17

5.2.3. የመለመኛ ቁሳቁሶች..........................................................................................................................17

5.2.4. ማህበረሰቡ ለልመና ያለው አመለካከት..................................................................................................18

5.3. ስም ቅየራ............................................................................................................................................19
5.3.1. ከቤተሰብ ለመደበቅ..........................................................................................................................20

5.3.2. ከመጸሐፍ ቅዱስ በመነሳት.................................................................................................................20

5.4. የትምህርት ወቅት..................................................................................................................................21


5.4.1. ዓብይ ጾም.....................................................................................................................................21

5.4.2. ክረምት.......................................................................................................................................22

5.5. የቆሎ ተማሪ ተረቶች...............................................................................................................................23


5.5.1. ያጡትን ማግኛ ተረቶች......................................................................................................................23

5.5.2. ማንነታቸውን ለማሳወቅ የሚጠቀሙት ተረት...........................................................................................23

5.5.3. ትዝብትና ተቃውሞን መግለጫ ተረት.......................................................................................................24


5.7. መረጃ ትንተና.......................................................................................................................................25
5.7.1.ማህበራዊ ዘርፍን በተመለከተ..............................................................................................................25

5.7.2. መሰረተ ልማትን በተመለከተ.............................................................................................................25

5.7.3. የከተማዋ የኢንቨስትመንት አማራጮች..................................................................................................25

5.7.4. የከተማዋ ዋና ዋና ተቋማት................................................................................................................25

5.7.5.ሃይማኖታዊ ተቋማትን በተመለከተ.......................................................................................................26

5.7.6. ታሪካዊናመንፈሳዊ የሃይማኖት ቦታዎች.................................................................................................26

5.7.7.የቆሎ ተማሪ ጉባኤን በተመለከተ..........................................................................................................26

5.8. መረዳዳት......................................................................................................................................27

5.8.1.የእርስ በርስ መማማር.......................................................................................................................27

5.8.2. ለአካል ጉዳተኛ ተማሪ የሚደረግ ድጋፍ..................................................................................................28

5.8.3. የአዲስ ተማሪ አቀባበል.....................................................................................................................28

ምዕራፍ ስድስት:ማጠቃለያ እና የመፍትሔ ሃሳብ.......................................................................................................29

ii
,

6.1. ማጠቃለያ...........................................................................................................................................29
6.2. የይሁንታ ሀሳብ.........................................................................................................................................30
አባሪዎች........................................................................................................................................................31
መረጃ አቀባዮች...............................................................................................................................................33
ዋቢ ጽሁፎች..................................................................................................................................................34

ምስጋና
ከሁሉ አስቀድሜ እዚህ እንድደርስ የረዳኝን ልዑል እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ ። ከዚህ በመቀጠልም ሙሉ
ጊዜዋን ሳሰስት ያለ ምንም መሰልቸት የተዋጣለት ስራ እንዳቀርብ የደገፈችኝን አማካርዬ (ዶ/ር) ድርቧ ደበብ
ምስጋየን ማቅረብ እፈልጋለሁ።እንዲሁም ጥናታዊ ጽሑፊን ስሰራ በገንዘብም ሆነ በሀሳብ ድጋፍ እየሰጡ ከጎኔ
ላልተለዩኝ ጓደኞቼ ÷ቤተሰቦች እና መረጃ በመስጠት ለተባበሩኝ ለሞጣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ አቨው

iii
,

ካህናት÷ዲያቆናት እና መዘምራን በተለይ ለቄስ ሐይማኖት አጋዥና ለዲያቆን ዘላለም አዱኛዉ


በእግዚአብሔር ስም ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ።

አጠቃሎ
የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት አኗኗር በሞጣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ” በሚል ርዕስ
የተካሄደው ጥናት ዋና ዓላማ አድርጎ የተነሳው የቆሎ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ህይወት ምን እንደሚመስል
ማሳየት ነው፡፡ ይህ አላማ ግቡን ይመታ ዘንድ ለጥናቱ ግብአት የሆኑ መረጃዎች በምልከታና በቃለ መጠይቅ
ተሰብስበዋል፡፡ ይህ ጥናት በቆሎ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ጊዜ ተደጋግመው የሚከሰቱና የተማሪ
መገለጫ የሆኑትን እንደ ጉዞ ፣ ስም ቅየራ ፣ ልመና ፣ መረዳዳት የትምህርት ወቅትና የእርስ በርስ መማማር
የመሳሰሉ ጉዳዮች ተዳሰው ቀርበውበታል፡፡ ከጥናቱ መረዳት እንደተቻለው ተማሪዎች የሚፈፅሟቸው እንደ
ጉዞ ፣ ስም ቅየራ፣ ልመና ያሉ ጉዳዮች በተማሪዎች ዘንድ ሀይማኖታዊ ፣ ስነ-ልቦናዊና ፣ ማህበራዊ
ምክንያቶችን የያዙ ናቸው፡፡ እንዲሁም ማህበረሰቡ ለተማሪዎችና ለልመና ያለው አመለካከት ሁለት አይነት

iv
,

እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በህብረተሰቡ ዘንድ ተማሪዎች በአዎንታዊና በአሉታዊ መንገድ እንደሚታዩ ማወቅ
ተችሏል፡፡ ከጥናቱ መረዳት እንደ ተቻለው በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ ክረምትና አብይ ፆም ሀሳባቸውን
ሰብስበው ለመማርና አዲስ ነገር ለመፍጠር ስለሚያግዟቸው በጉጉት የሚጠበቁ የትምህርት ወቅቶች ናቸው ፡፡
በተጨማሪም በተማሪዎች ዘንድ በዕውቀት በልጦ መገኘት በሚማሩበት ትምህርት ቤትም ሆነ በቀሪው
ማህበረሰብ ዘንድ ያላቸው ደረጃና ቦታ ከፍ እንደሚያደርግ ጥናቱ አሳይቷል፡፡ በመጨረሻ የቆሎ ተማሪዎች
በዋና ገፀ ባህሪነት የተሳሉባቸው ተረቶች ይዘታቸው ከተማሪ ህይወት ጋር በቀጥታ እንደሚቆራኝ ማወቅ
ተችሏል፡፡ ተረቶቹም ተማሪዎች በማህበረሰቡ ዘንድ የታዘቡትን ነገር የሚቃወሙባቸው፣ የራሳቸውን ማንነት
የሚገልፁባቸው፣ ያጡትን የሚያገኙባቸው ፣ ትዝብትና ተቃውሟቸውን የሚገልፁባቸው እንደሆኑ ጥናቱ
ያሳያል፡፡በተጨማሪም የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ የህይወት አኗኗር በተመለከተ ከሀይማኖት ይዘታቸዉ
በተጨማሪ ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮችናእሴቶች የያዙ ስለሆነ የሚመለከታቸዉ አካላት በስፋትና በትኩረት
ሰጥተዉ ቢያጠኑት አለማቀፋዊ እዉቅና እንደሚያገኝ ጥናቱ ይገልጻል፡፡

v
,

ምዕራፍ አንድ:- መግቢያ 1


1.1. ጥናቱ ዳራ
ኢትዮጵያ ብሉይ ኪዳንንም ሆነ አዲስ ኪዳንን ቀድማ በመቀበል የታወቀች ሀገር ናት÷በመሆኑም በ 4 ኛው
ክፍለ ዘመን ክርስትናን ከተቀበለች በኋላ ሀይማኖታዊ ትምህርት በተለያዩ መንገድ ስትሰጥ ቆይታለች፡፡
ክርስትናን ከመቀበሏ ጋር ተያይዞ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ሊቃውንትን ለማፍራት ሀይማኖታዊ ትምህርት
በሰፊው ይሰጥ ነበር፡፡Pankhurst (1966, 27), ብዙውን ጊዜ ሀይማኖታዊ ትምህርት ይሰጥ የነበረው
በቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂነት ነው፡፡ ከክርስትና ሀይማኖት መስፋፋት ጋር በተያያዘም በተለያየ መልኩ
በተለይም ለወጣቶች ሰፋ ያለ እና በአቀራረቡ የጠነከረ ትምህርት ይሰጥ ነበር፡፡ሀይለማርያም(1963፣42)፡፡
ይህንን ሀይማኖታዊ ትምህርት ከሚከታተሉት ወጣቶች መካከል ደግሞ በተለምዶ የቆሎ ተማሪዎች ተብለው
የሚታወቁት ተቀዳሚ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የቆሎ ተማሪዎች ለቤተክርስቲያነ አገልጋይ ለመሆን በቤተክርስቲያን ሃላፊነት መምህር ተዘጋጅቶላቸው
የሚማሩ ናቸው፡ ምንም እንኳን በኢትዮጵያ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት መቼ እና የት ጉባኤ ዘርግተው
ማስተማር እንደጀመሩ በውል ባይታወቅም ከ 19 ኛው ከፍለ ዘመን ጀምሮ ግን በተደራጀ መልኩ
በየቤተክርስቲያኑ የተጠናከረ ትምህርት ይሰጥ እንደነበር የሚያስረዱ መረጃዎች
ይገኛሉ Pankhurst( 1966,28):: የቆሎ ተማሪዎች ይህንን ሀይማኖታዊ ትምህርት በቤተክርስቲያን ዙሪያ
ተሰባስበው ሲከታተሉ የእራሳቸው የሆነየትምህርት፣ ስርዓት፣ የአኗኗር ብልሃትና የህይወት መገለጫዎች
አሏቸው፡፡ የትምህርት ሰርዓታቸውም በአራት ዋና ዋና ምዕራፎች የተከፈለ ነው፡፡ እነዚህም የንባብ ቤት፣
የዜማ ቤት፣ የቅኔ ቤትና የመጽሐፍ ቤት በመባል ይታወቃሉ፡፡ በሌላ በኩል በትምህርት ቤት ህይወታቸው የእኛ
የሚሏቸውና ከቀሪው ማህበረሰብ ጋር የሚጋሯቸው የሕይወት መገለጫዎች አሏቸው፡፡ ይህ ጥናትም የቆሎ
ትማሪዎች የትምህርት ቤት ህይወት ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ነው፡፡
የቆሎተማሪዎች ጎጆ ቀልሰው ሲኖሩ የሚጋሯቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ማለትም በት/ት ሰዓት፣በልመና ጊዜ
በሰሞንተኛ ጊዜ፣በአገልግሎት ሰዓት፣በቅፀላ ሰዓት የአብሮነት ህይወታቸው የጠበቀ ነው፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች
የራሳቸው የሆነ የፍልስፍና መንገድ አሏቸው፡- አዲስ ገብ ተማሪዎችን የሚያስፈሩ ጨዋታዎች ለምሳሌ፡-
የአቢ ክብራ በአፋቸው፣በእጃቸው፣በእግራቸው ፣በጀሯቸው ፍም እሳት በመያዝ መብራቱን በማጥፋትና
በማስፍራራት ይከዎናል፡፡

1.2. የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት


ይህንን ጥናት ለማጥናት ካነሳሱኝ ምከንያቶች መካከል በቅድሚያ የሚጠቀሰው የቆሎ ተማሪዎችን ህይወት
በሰፊው የዳሰሱ ጥናቶችባለማግኘቴ ነው፡፡ ምክንያቱም በዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ለተለያዩ ኮርሶች ማሟያ የተሰሩ
የተለያዩ ጥናታዊ ወረቀቶችን እስከቻልኩ ድረስ የማንበብ ዕድሉ ገጥሞኝ ስለነበር የቆሎ ተማሪዎችን ህይወት
በሰፊው የዳሰሰ ጥናት አላጋጠመኝም፡፡በተጨማሪም በአደግሁበት በሞጣ ከተማ በ 01 ቀበሌ በቅዱስ ጊዮርጊስ
ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ለቆሎ ተማሪዎች ቅርበት ስለነበረኝ በትምህርት ቤት ህይወታቸው ተደጋግመው

1
,

ከሚከሰቱ ሁኔታዎች በመነሳት ህይወታቸው ምን እንደሚመስል ለመፈተሽ ያለኝ ጉጉት እና፣እንዲሁም


በተለምዶ ተሜ እየተባሉ የቆሎ ተማሪዎች የሚሳሉባቸው ተረቶች ይዘታቸው ምን ይሆን? ከህይወታቸው
ጋር ያላቸው ግንኙነትስ እንዴት ተገልጾ ይሆን? ለሚለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ያለኝ ፍላጎት ነው፡፡

1.3. የጥናቱ ዓላማ


የዚህ ጥናት ዋና ዓላማ በሞጣ ከተማ 01 ቀበሌ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የሚገኙ የቆሎ
ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት አኗኗር ምን እንደሚመስል ማሳየት ነው፡፡ በውስጡም የሚከተሉትን ንዑሳን
ዓላማዎች አካቷል፡፡
በቆሎ ተማሪዎች ህይወት ተደጋግመው የሚከሰቱ የህይወት መገለጫዎች ምን ምን እንደሆኑ መጠቆም፣
የቆሎ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቆይታቸው የሚያልፉባቸውን ደረጃዎች ማሳየት ÷የቆሎ ተማሪዎች ስለ
ማህበረሰቡ ቀሪው ማህበረሰብ ደግሞ ስለ እነሱ ያለውን አመለካከት መግለጽ ናቸው።

1.4. ጥናቱ የሚመልሳቸዉ ጥቄዎች


የሞጣ ከተማ የቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የቆሎ ተማሪዎች ህይወት ምን ይመስላል?
የቆሎ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቆይታቸዉ የሚልፏቸዉ ደረጃዎች ምን ምን ናቸዉ?
የቆሎ ተማሪዎች ለማ/ሰቡና ማ/ሰቡ ለቆሎ ተማሪዎች ያላቸዉ አመለካከት እንዴት ይገለል?

1.5 የጥናቱ ጠቀሜታ


ይህ ጥናት የሚከተሉትን ጠቀሜታዎች ይኖሩታል።ጥናቱ የቆሎ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ህይወት ምን
እንደሚመስል ለማህበረሰቡ ለማሳወቅ ይጠቅማል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ይህ ጥናት የቆሎ ተማሪዎችን
የተለያዩ ጉዳዮች ለምሳሌ ሰነቃሎቻቸውን፣ የትምህርት አሰጣጡን፣ እያንዳንዱን የክፍል ደረጃ፣ ወዘተ.
ከፋፍሎ ማጥናት ለሚፈልግ ተመራማሪ ጥቅል የሆነ የመነሻ ሀሳብ ይሰጣል፡፡ በመጨረሻም የእነዚህን
ተማሪዎች ህልውና ለማስቀጠል ለሚንቀሳቀሱ÷ለምሳሌ: እንደ ማህበረ ቅዱሳን ላሉ ሀይማኖታዊ
ድርጅቶች÷ተማሪዎቹበምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ መረጃ ይሰጣል ተብሎ ይታሰባል፤እና ሌሎች፡፡

1.6. የጥናቱ ወሰን


ይህ ጥናት ይዞት የተነሳው ዓላማ ይሳካ ዘንድ የእራሱ የሆነ የጥናት ወሰን ይኖረዋል፡፡ ይህ ጥናትም ከቦታ አንፃር
በሞጣ ከተማ 01 ቀበሌ በቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በሚገኙ የቆሎ ትምህርት ቤቶች ላይ ተወሰኗል፡፡ ከይዘት
አንፃር ደግሞ ሁለት የቅኔ ቤት ጉባኤዎች፡ አንድ የዜማ ቤት ጉባኤና አንድ የንባብ ቤት ጉባኤ ብቻበናሙናነት
ተወስደዋል፡ጥናቱም እነዚህን ዓላማዎች ይዞ ተነስቷል:የቆሎ ተማሪዎች ያሏቸውን የህይወት ደረጃዎች
መመርመር ÷የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት እይታቸውን ማሳየት እና የቆሎ ተማሪዎች ስለ ማህበረሰቡ
÷ማህበረሰቡ ደግሞ ሰለ እነሱ ያላቸውን አመለካከት መዳሰስ
ይህ ጥናትም በዚህ ቦታ ላይ የተወሰነበት ምክንያት በሞጣ ከተማ ዉስጥ ከሚገኙ የቆሎ ትምህርት ቤቶች
ውስጥ በተማሪዎች ቁጥርና በመምህራን ታዋቂነት ከሌሎች ስለሚሻሉ ነው። ሌላው ከይዘት አንፃር ደግሞ
ለቆሎ ተማሪዎች ፈታኝ የሚባሉት ትምህርቶች ቅኔ ቤት ÷ዜማ ቤት እና ንባብ ቤት ስለሆኑ ነው።

2
,

1.7.1. በጥናቱ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች


 በመረጃ ሰጭዎች በቀተሮዉ ቦታ እና ሰዓት አለመገኘት፡፡
 ከወቅቱ አንፃር መረጃ ከሚሰጡኝ ሰዎች ጋር በቶሎዉ መግባባት አመቻል፡፡
 መረጃ ሰጭዎች መረጃዉን በዘፈቀደ መስጠት፡፡
 አብዛኛዉን መረጃዉን የሚሰጡኝ ሰዎች በቃላቸዉ ስለሆነ ለማደራጀት ጊዜ መዉሰዱ፡፡
1.7.2. ላጋጠሙ ችግሮች የተወሰዱ መፍትሔዎች
 መረጃ ሰጭዎች ለሚመቻቸዉ ቦታ እና ሰዓት እንዲገኙልኝ ማድረግ፡፡
 በመረጃ ሰጭዎች ዘንድ አመኔታን ለማግኘት ከየት እና የማን እናደሆንኩ ገለፃ በማድረግ የሄድኩበትን ምክንያት
ማስረዳት፡፡
 መረጃ ሰጭዎች መረጃን ሲሰጡኝ በቅደም ተከተል እንዲገልፁ ማድረግ፡፡
 አብዛኛዉን መረጃዎች በቃል ሲሰጡኝ በቅደም ተከተል እንዲነግሩኝ ማደረግ፡፡

ምዕራፍ ሁለት:-ክለሳ ድርሳን

2.1. ፅንስ ሀሳባዊ ቅኝት


ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ ውስጥ ስለ ቆሎ ተማሪዎች ስያሜ፣ስለ ህይወት አኗኗራቸው፣የትምህርት ቤት ህይወታቸው እና የቀደሙ ጥናቶች
በሰፊው ተዳሰው ቀርበዋል፡፡

2.1.1.የቆሎ ተማሪዎች ስያሜ ምንነት


በቤተክርስቲያን ስር ተጠቃለው የሚማሩ ተማሪዎች በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራሉ፤ ከእነዚህም መካከል
የአብነት ተማሪዎች፣ “የቄስ ተማሪዎች” እና የቆሉ ተማሪዎች” የሚሉት ይጠቀሳሉ፡፡ ነገር ግን ለዚህ ጥናት
“የቆሎ ተማሪዎች” የሚለው ስያሜ ተመራጭ ሆኗል፡፡ ሁለቱ ስያሜዎች ያልተመረጡበትን ምክንያት
ስንመለከት “የአብነት ተማሪዎች” የሚለው መጠሪያ በዚህ ጥናት ያልተመረጠበት ምክንያት የዚህ ጥናት
ተተኳሪ ተማሪዎች በሚገኙበት አካባቢ ያልተለመደ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ መጠሪያ ከቅርብ ጊዜ በተለይም
“ማህበረ ቅዱሳን” የሚለው ሀይማኖታዊ ድርጅት የሚጠቀምበት መጠሪያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች
ጥናትና ምርምር ማዕከል ያዘጋጀው መዝገበ ቃላት “አብነት” የሚለውን ቃል ምሳሌ ፤ አርአያ፣ የጠለቀ
ትምህርት ያለው እና እውቅ መምህር በማለት ይተረጉመዋል፡፡ ይህ ስያሜ አንድም የትምህርት መጀመሪያ
መሆናቸውን ለመጠቆምና በሌላ በኩል በእውቀት የበለፀጉ መሆናቸውን ለመጠቆም የተሰጠ ስያሜ መሆኑን
መረዳት ይቻላል፡፡ ነገር ግን ይህ ስያሜ የቅርብ ጊዜ በመሆኑ እና በተለይም ይህ ጥናት በተካሄደበት አካባቢ
የተለመደ ስላልሆነ ለተማሪዎች መጠሪያነት አልዋለም፡፡ በሌላ በኩል “የቄስ ተማሪዎች” የሚለውን ስያሜ
ስንመለከት ስያሜውን ያገኙት ከትምህርት በኋላ ከሚሰማሩበት ሙያ በአንዱ ላይ ብቻ በመመስረት ነው፡፡
ይህ ስያሜ የተማሪዎችን ማንነት ሙሉ በሙሉ አይገልፅም፤ ምክንያቱም “ቄስ” የሚለው ቃል “ቀስ” አገለገለ

3
,

ከሚለው የግዕዝ ቋንቋ የመጣ መሆኑን ኪዳነማርያም (198 ዐ፣ 81)ይገልፃል፡፡ስለዚህ ይህ ስያሜ ተማሪዎች
ከትምህርት በኋላ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የተማሪዎች ጥቅል መጠሪያ ሊሆን
አልቻለም፡፡

“የቆሎ ተማሪዎች” የሚለው መጠሪያ በሁለት ምከንያቶች በዚህ ጥናት ለተማሪዎች መጠሪያ ሆኖ
ተመርጧል፡፡ በመጀመያ ይህ ጥናት ልማዳዊ ጥናት እንደመሆኑ መጠን አካባቢያዊ ስያሜ ትልቅ ድርሻ
ይሰጠዋል፡፡ ለጥናት ከተመረጠው አካባቢ ከሁለቱ ስያሜዎች ይልቅ “የቆሎ ተማሪዎች” የሚለው መጠሪያ
በሰፊው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ እንዲሁም ተማሪዎች እራሳቸውን የሚጠሩበት መጠሪያ ስለሆነ ሊመረጥ
ችሏል፡፡ በሌላ በኩል ስያሜው የተማሪዎችን ትክክለኛ ህይወት የሚያሳይ በመሆኑ ነው፡፡ በኢትዮጵያ
ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል በተዘጋጀው የአማርኛ መዝገበ ቃላት መሰረት “የቆሎ ተማሪ” ማለት
ከየመንደሩ የሚያገኘውን ቁራሽ እንጀራ እንዲሁም ጥራጥሬውን በቆሎ መልክ እያዘጋጀ በመመገብ እንደ
ንባብ፣ ዜማ፣ ቅኔ፣ ወዘተ.ያሉትን የትምህርት አይነቶች የሚቀጽል የቤተክህነት ተማሪ ነው”ይህ ስያሜ
በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች የሚገኙ ተማሪዎች ጥቅል መጠሪያ መሆኑ እና ስያሜውም የትምህርት ቤት
ህይወታቸውን የሚገልፅ መሆኑን መረዳት ይቻላል፡፡ ኪዳነማርያም ጌታሁን “ጥንታዊ የቆሎ ተማሪ” በሚለው
መጽሐፋ የቆሎ ተማሪ ማለት ጥሬ ቆርጥሞ፣ ውሃ ጠጥቶ በችግርና በረሃብ የሚማር መሆኑን ገልጿል
(198 ዐ፣ 6)፡፡ ከላይ የተነሱት ሁለቱም ስያሜዎች እንደገለፁት የቆሎ ተማሪ የሚለው መጠሪያ ህይወታቸውን
መሰረት አድርጎ የተሰጠ መጠሪያ ነው፡፡ በነዚህ ምክንያቶችም ስያሜው ለዚህ ጥናት የተማሪዎች ጥቅል
መጠሪያ ስያሜ በመሆን አገልግሏል፡፡

2.2. የቆሎ ተማሪዎች አኗኗር


የቆሎ ተማሪዎች የራሳቸው የሆነ የአኗኗር ስርአት አላቸው፡፡ ሀብተማርያም ወርቅነህ “ጥንታዊ የኢትዮጵያ
ትምህርት” በሚለው መጽሐፋ በሀገራችን የሚገኙ የቆሎ ተማሪዎች ህይወት የራሱ የሆነ ወግና ስርዓት
እንዳለው ገልጸዋል (1963፣ 288)፡፡ ኑሯቸውንም የሚመሩት በቤተክርስቲያን አቅራቢያና በመምህራቸው ቤት
ዙሪያ በህብረት በሚቀልሷቸው ጐጆዎች ውስጥ ነው፡፡ የቆሎ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቆይታቸው
የሚያልፋባቸው አራት ዋና ዋና የትምህርት ደረጃዎች አሉ፡፡ እነሱም ንባብ ቤት ፣ ዜማ ቤት፣ ቅኔ ቤትና
መፃሕፍት ቤት ናቸው (እምባቆም 197 ዐ፣3፤ ሀብተማሪያም 1963፣39፤ Pankhurst 1968:32-33)፡፡
እያንዳንዳቸው ደረጃዎች በውስጣቸው ብዙ ንዑሳን ክፍሎች ቢኖሯቸውም አራቱ ደረጃዎች ግን ጎልተው
የሚታወቁት ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ትምህርት የተለያየ መልክ ስላለው በተለይም የትምህርት አሰጣጡ እራሱን
ችሎ ሊጠና እንደሚችል ሀብተማሪያም (1963፣15) ይገልፃል፡፡

በገጠሯ ኢትዮጵያ በእያንዳንዱ የገጠር ቀበሌ የእራሱ ቤተክርስቲያንና ትምህርት ቤት አለው፡፡ ትምህርት ቤቶቹም ብዙውን ጊዜ
በቤተክርስቲያን አቅራቢያ የሚሰሩ ናቸው፡፡ ይህን ሃሳብ ለማጠናከር የሪቻርድ ፖንክረስትን ሃሳብ ማቅረቡ ተገቢ ይሆናል፡፡

4
,

በየቤተክርስቲያኑ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የቆሎ ተማሪዎች እንደየደረጃቸው ገብተው ይማራሉ፡፡


የተማሪዎች መማሪያ ቦታ ከቤተክርስቲያን አለመራቁ ትምህርት ቤቶቹ በቤተክርስቲያን ሃላፊነት እንደሚመሩ
ይጠቁማል፡፡ ለትምህርት የሚነሱ የቆሎ ተማሪዎችም ከቤተሰቦቻቸው ርቀው በመሄድ እና የእራሳቸውን ጎጆ
በመቀለስ ለምነው በሚያገኙት ቁራሽ እንጀራ የእራሳቸውን ህይወት መኖር ይጀምራሉ፡፡

ተማሪዎች ሃይማኖታዊ ትምህርትን ዋና ዓላማ አድርገው ቢነሱም በትምህርት ቤት ቆይታቸው እንደ ታሪክ፣
ግጥም፣ ሙዚቃ፣ ፍልስፍናና መድሃኒት ቅመማ፣ ወዘተ. የመሳሰሉትን የትምህርት አይነቶችን ሁሉ
እንደሚማሩ ሪቻርድ ፖንክረስት ያስረዳል Pankhurst (1966፣28)፡፡ ከሪቻርድ ፖንክረስት መረዳት
እንደሚቻለው ዛሬ ላይ የዘመናዊ ትምህርት ትኩረት የሆኑት የትምህርት ዘርፎች ቀደም ብሎም በኢተዮጵያ
የቆሎ ትምህርት ቤቶች ይሰጡ ነበር፡፡ በተጨማሪም እነዚህ ትምህርት ቤቶች በሀገራችን ለሚሰጠው ዘመናዊ
ትምህርት መሰረት መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል፡፡ እነዚህን ተማሪዎች የሚያስተምሯቸው መምህራን
በእውቀት የበለፀጉ እና በአውሮፖ “ኘሮፌሰር” ከሚባሉትምሁራን ጋር እንደሚስተካከሉ ሪቻርድ ፖንክስት
Lady Harber ን በመጥቀስ የመምህራኖቹን አዋቂነት ይገልጻል (1968፣29):: የቆሎ ተማሪዎች በትምህርት
ቤት ህይወታቸው በበዙ የእውቀት መስኮች የበለጸጉ ቢሆኑም የትምህርት ቤት ህይወታቸው ግን በችግርና
በስቃይ የተሞላ ነው፡፡ ችግራቸው የሚጀምረውም ገና ከመነሻው ቤተሰቦቻቸውን ጥለው በመሰደድ
በሚያደርጉት መስዋእትነት ነው፡፡ ይህን የተማሪዎችን ችግር ሀብተማሪያም እንደገለፀው በኢትዮጵያ ህዝቦች
ዘንድ ትምህርት ይወደድ ነበር፡፡ ህዝቡም በህብረት ትምህርት ቤት ይሰራና መምህራን ይቀጥር ነበር፡፡ ነገር ግን
በተማሪዎች ላይ ብዙ ችግር ይደርስባቸው ነበር፡፡ (1963፤29)፡፡

የቆሎ ተማሪዎች ለትምህርት ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ሲሰደዱ ምንም ተስፋ የሚያደርጉት ነገር የለም፡፡
ከቤተሰቦቻቸው ፈቃድ ስለማያገኙ ቤተሰቦቻቸውን አማክረው ስንቅ ተሰንቆላቸው ከመሄድ ይልቅ በድብቅ
አስቸጋሪውን ህይወት ይጀምራሉ፡፡ ሪቻርድ ፖንክረስት እንደሚለው እውቀትን ተጠምቶ የሚሰደድ ተማሪ
ብቸኛ ሀብቱ የቁራሽ እንጀራ መለመኛ የምትሆንው “አክፋዳው”ብቻ ናት፡፡ ህይወቱንም በልመና በሚያገኘው
እንጀራ እንደሚመራ ተሰፋ በማድረግ ብቻ ነው ቤተሰቦቹን ጥሎ የሚሰደደው Pankhurst (1966፡29)፡፡ የቆሎ
ተማሪዎች እውቀትን ፍለጋ ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ከተሰደዱ በኋላ በየትምህርት ቤቱ ሲገናኙ ኑሯአቸው
በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተ የጋርዮሽ ኑሮ ነው፡፡ እምባቆም ቃለወልድ “ Tradasional Ethiopian church
school” በሚለው መጽሐፋ ተማሪዎች በጋራ ጎጆ ይቀልሳሉ ፣በጋራ ይሰራሉ፣ በጋራ ይማራሉ እንዲሁም
በጋራ ይመገባሉ በማለትማህበራዊ ህይወታቻው የጠነከረ መሆኑን ያስረዳል እምባቆም (197 ዐ 16፡19)፡፡
ህይወተቻው በጋርዮሽ ላይ የተመሰረተ መሆኑ እነዚህ ተማሪዎች እንደ አንድ ቡድን ተቆጥረው
ጥቅልህይወታቸውም ይጠናል፡፡

5
,

የቆሎ ተማሪዎችም በትምህርት ቤት ህይወታቸው የተለያዩ የህይወት ደረጃዎችን ያልፋሉ፡፡ ለትምህርት


ቤተሰቦቻቸው ጥለው ይሰደዳሉ፤ ከስደት መልስም በአካባቢው የተከበሩ የሃይማኖት መሪዎች ይሆናሉ፡፡
ይህንን የተማሪዎችን ወግ ማዕረግ በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል፡፡ አንዱም Martin and
Martine(2 ዐዐ 5፣11 ዐ) እንደሚሉት ወግ ማዕረግ የሚባለው ነገር የግለሰቡ ህይወት ላይ ትልቅ አሻራ አሳርፎ
የሚያልፍ ነው፡፡ የቆሎ ተማሪዎች ከተማሪነት ከስደትና ከችግር ወደ መሪነት የሚሸጋገሩበት ደረጃ
በህይወታቸው ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡ በሌላ መልኩ የቆሎ ተማሪዎች ለወግ ማዕረግ የሚያደርጉት ጉዞ
ከስሜታዊ ጉዞ ጋር ሊዛመድ ይችላል፡፡ ቴዎድሮስ ገብሬ (2001፡ 45) እንደገለጸው ማንኛውም ተጋዳሊ ለገድል
ሲጠራ የሚያልፍባቸው ሶሶት ምዕራፎች አሉ፡፡ ከወገን መለየት፣ ወደ ጥብቅ ስፍራ መዝለቅና ከስፍራው
አንዳች በረከት ይዞ መመለስ ናቸው፡፡ እነዚህ ምእራፎች በቆሎ ተማሪዎች ህይወት ውስጥ ተደጋግመው
የሚከሰቱ ናቸው፡፡ ከእነዚህ ከመለየት ፣ ከመዝለቅና በረከት ይዞ ከመመለሰ ጋር ተያይዘው ከሚነሱ ጭብጦች
መካከል አንዱ ፍለጋ ነውቴዎድሮስ (2 ዐዐ 1፣ 45)፡፡

የቆሎ ተማሪዎችም ለጉዟቸው ምክንያት የሚሆናቸው ፍለጋ ነው፡፡ የቆሎ ተማሪዎች ከቤተሰብ ተነጥለው
ጋራ ሸንተረሩን አቆራርጠው እውቀትና ጥበበ ፍለጋ እጅግ አድካሚ ጉዞ ያደርጋሉ፡፡ቴዎድሮስ(2001፣60)
እንደገለጸው የሚፈልጉትን ነገር ለማግኘት የሚደረገው ጉዞ ዓለማዊም ሃይማኖታዊም መሰረት ሊኖረው
ይችላል የቆሎ ተማሪዎች ጉዞም ሁለቱን ነገሮች አጣምሮ የያዘ ነው፡፡

2.3.የቀደሙ ጥናቶች ቅኝት


ከቆሎ ተማሪዎች ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ጥናቶች ካደረጉት ተመራማሪዎች መካከል አለማየሁ ሞገስ
በ 1971 እ.ኤ.አ “Traditional church Education” በሚል ርዕስ የአደረገው ጥናት ይጠቀሳል፡፡ የአለማየሁ
ጥናት ዋና አላማው በባህላዊ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ዕውቀት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ተንትኖ
ማሳየት ነው፡፡ በውጤቱም የኢትዮጵያ ባህል የሚጠበቅና እውቀትም ከትውልድ ትውልድ የሚተላለፈው ቤተ-
ክርስቲያን በምትሰጠው ትምህርት አማካኝነት መሆኑን አሳይቷል፡፡ ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ ከአለማየሁ ጋር
የሚመሳሰለው ሁለቱም ትምህርቶች የሚሰጡት በቤተ-ክርስቲያን አማካኝነት በመሆኑ እና የተማሪዎች
ህይወት በትምህርት ቤት ቆይታቸው ምን እንደሚመስል በማሳየቱ ነው፡፡

ልዩ የሚደርጋቸው ለዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ የተሰበሰቡት መረጃዎች በፎቶ የተደገፈ ሲሆን ሌላው ልዩነት
የአለማየሁ ርዕስ Traditional Church Education መሆኑና ይህ ደግሞ የቆሎ ተማሪዎች ህይወት ላይ
መስራቱ ነው፡፡

ሌላው ምልከታ የተካሄደበት ጥናታዊ ጽሑፍ በላይነህ ደሴ በ 1999 ዓ.ም.“የቅኔ ቆጠራ ነገራና ዘረፋ በተመረጡ
የጎጃም ጉባኤዎች” በሚል ርዕስ ያደረገው ጥናት ነው፡፡ ይህ ሥራ ለኢትዮጵያ ሥነ ጽሁፍና ፎክሎር ድህረ
ምረቃ መርሃ ግብር ለሁለተኛ ድግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናት ነው፡፡

6
,

አጥኚዋ የሪቻርድ ዶርሰንን ሀሳብ በመያዘ ሀይማኖታዊክንውኖችን ከልማዳዊ ጥናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት
እንደሚኖራቸው ገልጿል፡፡ እነዚህ ባህላዊ ትምህርት ቤቶችም ሪቻርድ ዶርሰን በሚለው የፎከሎር ዘርፍ
ይጠቃለላሉ በማለት ባህላዊ የቅኔ ትምህርት አሰጣጥ በሀገረሰባዊ ልማድ ስር እንደሚጠቃለል ገልጿል፡፡

የበላይነህ ደሴ ጥናት ዋና አላማው ሀይማኖታዊ ክንውኖች ከልማዳዊ ጥናትቀጥተኛ ግንኙነት


እንደሚኖራቸው መግለፅ ነው፡፡ከዚህ ጥናት ጋር የሚመሳሰለው ሁለቱም ጥናቶች በቄስ ተማሪዎች ትምህርት
ቤት ውስጥ የሚሰጡ ትምህርቶችን ማንሳታቸው እና ሁለቱም አንድ አይነት የመረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ
መጠቀማቸው ነው፡፡ ልዩ የሚያደርጋቸው ጉዳይ ከቦታ አንፃር ስንመለከት ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ በጅሁር ከተማ
የሚገኙ የቆሎ ተማሪዎችን ህይወት የሚያሳይ ሲሆን የበላነህ ደሴ ግን የቅኔ ቆጠራና ነገራ በተመረጡ የጎጃም
ጉባኤዎች ውስጥ የተጠና ጥናት በመሆኑ ሊለይ ችሏል፡፡

“የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት አሰጣጥ”፡፡ በሚል ርዕስ ምስጢረ ሰዋሰው በ 1974 ዓ.ም.; ያደረገው ጥናት ሌላው
ተዛማጅ ጥናት ነው፡፡ ይህ ጥናት ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ቢሆንም በጥናቱ ከተነሱ ጉዳዮች አንፃር
ግን ጥልቅ ምርምር የተካሄደበት ሥራ ነው፡፡ ጥናቱ ስለ ግዕዝ ቋንቋ አመጣጥ ታሪካዊ ዳሰሳ ካደረገ በኋላ
አባቶች በግዕዝ ቋንቋ ብዙ ፅፈዋል፡፡ እጅግ ብዙ ተመራምረዋል በማለት ይህንን እውቀት ከየት አመጡት
እንዴትስ ተማሩ የሚሉ መጠይቆችን ለመመለስ ጥናቱን ማካሄዱን ገልጿል፡፡ ይህ ቀጥተኛ ፅሁፍ ስለ ግዕዝ
ቋንቋ አመጣጥ መግለጽ በመሆኑም የግዕዝን ቋንቋ በዋነኝነት የሚጠቀሙት ደግሞ የቆሎ ተማሪዎች ናቸው፤
በዚህ የተነሳ እንዲመሳሰሉ አድርጓቸዋል፡፡ መረጃውን የሰበሰበውም ይህንን ትምህርት ከተማሩት አባቶች ጋር
በቀጥታ በመገናኘት ማለትም በምልክት በመሆኑ ተመሳስለዋል፡፡የሚለያዩበት ሚስጢረ ስለትምህርት አሰጣጡ
ያጠና ሲሆን ይህ ጥናት ደግሞ ህይወታቸው ምን እንደሚመስል፣ ምን ምን ነገሮችን በህይወታቸው ውስጥ
ያሳልፋሉ የሚለውን የሚገልፅ በመሆኑ ነው፡፡

ሌላው ልዩነታቸው ሚስጢረ ሁለት የታወቁ የቅኔ ጉባኤዎች በማነፃፀር ያቀረበ በመሆኑ ነው፡፡ በተጨማሪም
የቆሎ ተማሪዎች የለተያዩ አጋጣሚዎች ሲያጋጥማቸው እንደት ራሳቸውን እንደሚያሳውቁና ምን አይነት
የመፍትሔ ሀሳቦችን እንደሚያመነጩ ባለማሳየቱ ይህ ጥናት ደግሞ እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ማሳየቱ
ይለያያቸዋል፡፡

ምስጢረ በማጠቃለያው ባህላዊ ትምህርት ቤቶች ኋላ ቀርና የማይለወጡ ሳይሆኑ ብዙ የህይወት ልምዶች
የሚገኙባቸው የእውቀት ማዕከላት መሆናቸውን በአፅንኦት ገልጿል፡፡ በአጠቃላይ ይህ ሥራ የተማሪዎችን
ህይወትም በጥልቀት ለመመርመር ባደረገው ጥረት ከዚህ ስራ ጋር ሲመሳሰል ማህበረሰቡ ለተማሪዎች ያለውን
አመለካከት ባለመግለፁ እና በስነቃሎቻቸው ህይወታቸው እንዴት እንደሚገለፅ ባለማየቱ ከዚህ ጥናት ጋር
እንዲለያይ አድርጎታል፡፡

7
,

አምሀ ኢየሱስ አስፋ በ 1994 ዓ.ም.“መንፈሳዊ ትምህርት ቤት /ቄስ ትምህር ቤት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ
ያደረገው ጥናት ምልከታ ተካሂዶበታል፡፡ ጥናቱ በያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ
የቀረበ ስራ ነው፡፡ አጥኚው ገና ከመነሻው በቄስ ትምህርት ቤቶች ላይ እና በሚያነሷቸው ጉዳዮች ላይ የቀረበ
ጥናት ባለማግኘቱ ይህንን ጥናት ለማካሄድ መነሳቱን ገልጿል፡፡ አጥኚው የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ
እንደመሆኑ መጠን ትኩረት ያደረገው ከቄስ ትምህር ቤት ደረጃዎች መካከል በ “ዜማ ቤት” ላይ ነው፡፡ ጥናቱ
በዜማ ቤት ላይ ቢያተኩርም በመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶች ጉድለትምከንያራት ስራውን በትክክል መግለፅ
አልቻለም፡፡ ገና ከርዕሱ ቄስ ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ ብሎ ርዕሱን ሰፊ ቢያደርገውም የተጠቀመባቸው
የመረጃ መሰብሰቢያ መንገዶች ግን ከሥራው ጋር አብረው የማይሄዱ ናቸው፡፡ ምክንያቱም ጥናቱ የተካሄደው
በእድሜ ገፋ ያሉ ቄሶችን ብቻ ቃለ መጠይቅ በማድረግ መሆኑ በጥናቱ ተገልጿልና ነው፡፡

አጥኚው የዜማ ትምህርት አሰጣጥን ለማንሳት በኢትዮጵያ የቄስ ትምህርት ቤት እንዴት እና መቼ


እንደተጀመረ ታሪካዊ ዳሰሳ አድርጓል፡፡ በጥናቱ እንደተገለፀው እነዚህ ትምህርት ቤቶች መቼ እንደተጀመሩ
በውል ማወቅ ባይቻልም ለዘመናዊ ትምህርት መነሻ መሆናቸው ግን አያጠያይቅም በማለት የቄስ ትምህርት
ቤቶች ያላቸውን ፋይዳ ለማሳየት ጥረት አድርጓል፡፡ ትምህርት ቤቶች በቤተክርስቲያን ስር መታቀፋቸውና
መምህራኑ በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸው ከፍተኛ ተቀባይነት ብቸኛ የትምህርት ማዕከል ሆነው ለብዙ አመታት
እንዲኖሩ አስችሏቸዋል በማለት በጥናቱ ለማሳየት ሞክሯል፡፡ ነገር ግን ጥናቱን በመረጃ ከማስደገፍ ይልቅ የግል
አስተያየት በሚመስል ሁኔታ አቅርቦታል፡፡ በጥናቱ እንደተገለፀው ዜማ ቤት መሰረቱ ያሬዳዊ ዜማ መሆኑን
ከመግለፅ አልፎ ቁርኝታቸውን በመረጃ አስደግፎ ለማሳየት ምንም የደተረገ ጥረት በጥናቱ አልታየም፡፡

የአምሀ ኢየሱስ ጥናት ዋና አላማው የቄስ ትምህርት ቤት በኢትዮጵያ እንዴት እና መቼ እንደተጀመረ ታሪካዊ
አመጣጡን ማሳየት ነው፡፡ በውጤቱም እነዚህ ትምህርት ቤቶች መቼ እንደተጀመሩ በውል ማውቅ ባይቻልም
ለዘመናዊ ትምህርት መነሻ መሆናቸውን ግን አሳይቷል፡፡

የአምሀኢየሱስ ጥናት ከዚህ ጥናት ጋር የሚመሳሰለው የቄስ ትምህርት ቤት እና የአብነት ትምህርት ቤት


ተመሳሳይ በመሆናቸው ነው፡፡ ልዩነታቸው ይህ ጥናት የሚያነሳው ርዕስሰ ጉዳይ ትምህርቱ መቼ እና እንዴት
እንደተጀመረ የሚያሳይ አለመሆኑ ነው፡፡ ሌላው ይህ ጥናት የቆሎ ተማሪዎችን ህይወት ስነ-ቃሎችንና
ተረቶችን በማንሳቱ እንዲለያዩ አድርጓቸዋል፡፡ በተጨማሪም አምሀ ከቆሎ ተማሪዎች የትምህርት ደረጃ
ውስጥ አንዱን ብቻ ማለትም የቅኔ ቤት ትምህርትን በማጥናቱ ነው፡፡ይህ ማለት ደግሞ በተዘዋዋሪ ያጠናው
ስለትምህርት አሰጣጡ በመሆኑ ነው፡፡

ሌላው ቅኝት የተደረገበት ሥራ ገዛኸኝ ጌታቸው የአብነት ትምህርት ቤቶች ለዘመናዊ ትምህርት እድገትና
ለሀገሪቱ አስተዳደር ያደረጉት አስተዋፅኦ /አመተ ምህረት ያልተጠቀሰ/ በሚል ርዕስ ያቀረበው ጥናታዊ ጽሁፍ
ነው፡፡ ጥናቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ከሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ

8
,

ማህበረ ቅዱሳን ባላቸው ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት ላይ የቀረበ ሥራ ነው፡፡ ይህ ጥናት የምርምር ጥያቄዎችን
በማንሳት በጥናቱ መልስ ለማግኘት ሞክሯል፡፡ በጥናቱ እንደተገለፀው በቤተክርስቲያን ትምህርት
የሚሰጥባቸው ማዕከላት በተለምዶ የቆሎ ትምህርት ቤት ይባላል፡፡ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ዓላማ
የቤተክርስቲያን ሊቃውንትን ማፍራት ቢሆንም አያሌ ሀገራዊ ተግባራትን ለኢትዮጵያ ሲያበረክቱ
መቆየታቸውን መረጃ እያጣቀሰ ማሳየት ችሏል፡፡ ሀገራችን ታሪኳ ተመዝግቦና ተጠብቆ የኖረው ከቆሎ
ትምህርት ቤቶች ተምረው በሚመጡ ተማራዎች እንደነበር ማሳየትችሏል፡፡ በሀገራችን ሕግ አውጭም ሆነ
ሕግ አስከባሪ አካላት የሚመጡት ከእነዚህ የትምህርት ማዕከላት እንደነበር በአፅንኦት ገልጿል፡፡

ገዛኽኝ ከዚህ በፊት በእነዚህ ትምህርት ቤቶች ላይ ጥናት ያካሄዱ ተመራማሪዎች የትምህርት ቤቱን ጠንካራ
ጎን ከመመልከት ይልቅ ለሀገራችን ድህነትና ኋላቀርነት ተጠያቂ ሲያደርጓቸው መቆየታቸውን አንስቷል፡፡
ይህም ሳይንሳዊ ምርምር ሳያደርጉ ከግል ስሜት የመነጫ ሃሳብ ነው በማለትአጥኝዎችን ይነቅፋል፡፡ ይልቁንስ
እነዚህን ትምህርት ቤቶች የታሪክ የባህልና የፖለቲካ ተመራማሪዎች በጥልቀትና በገለልተኛነት ሰሜት
ሊመረምሯቸው ይገባል በማለትየግልአስተያየቱን አስቀምጧል፡፡ አጥኝው በማጠቃለል እንደገለፀው ሀገር
በቀል እውቀት ለአንድ ሀገር እድገት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው፡፡ የቆሎ ትምህርት ቤቶችም ሲያደርጉ
የኖሩት ይህንን ነው በማለት የነበራቸውን ሀገራዊ ፋይዳ አንፀባርቋል፡፡ አያይዞም የሙዚቃ፣ የሰነ ፅሁፍ፣ የስነ
ልቦናና የፍልስፍና ትምህርት ከፍሎች ከነዚህ ትምህርት ቤቶች ጋር የሚገናኙበት ሁኔታ ስላለ ትኩረት ሰጥተው
ቢመረምሯቸው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጿል፡፡ የቆሎ ትምህርት ቤቶች የብዙ ነገር መገኛ መሆናቸውንም
ለማንፀባረቅ ሞክሯል፡፡ ከዚህ አኪያ ጥናቱ ይዞት ከተነሳው ርዕስና የምርምር ጥያቄ አንፃር ግቡን መቷል ማለት
ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ጥናት አድራጊ ቅኝት የተደረገባቸው ስራዎች ለተለያየ ዓላማ የተደረጉ ጥናቶች ቢሆንም
በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ መልክ ከቆሎ ተማሪዎች ጋር የሚገናኙ ጉዳዮችን ስለሚያነሱ ከዚህ ጥናት ጋር
ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ጥናቶቹ ከስነ ትምህርት ፣ ከታሪክና ከሙዚቃ ጋር በተያያዘ የተጠኑ ቢሆኑም ሁሉም
የቆሎ ትምህርት ቤቶች የብዙ ነገር መገኛ መሆናቸውን መመስከር ችለዋል፡፡ እያንዳንዱ ሥራ የራሱ ደካማና
ጠንካራ ጎን እንዳለ ሆኖ የተማሪዎችን ህይወት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በማንሳታቸው ከዚህ ጥናት ጋር
ተመሳሳይነት ፈጥረዋል፡፡ በአንፃሩ ሁሉም የተማሪዎችን ህይወት ሲያነሱ ሰነቃሎቻቸወን ሳይመለከቱ
በመቅረታቸው ከዚህ ጥናት ጋር ይለያያሉ፡፡

9
,

ምዕራፍ ሦስት:- የጥናቱ ዘዴ


ይህ ጥናት የፎክሎር ጥናት እንደመሆኑ መጠን የጥናቱ ዜዴ የቆሎ ተማሪዎችን ልማዳዊ ህይወት
አኗኗር ይዘት ትንተና አላማ ተኮር የናሙና አመራረጥ ዘዴን የተከተለ ሲሆን የመረጃ መሰብሰብያ
ዘዴውም ምልከታና ቃለ መጠይቅ በመሆን ቀርበዋል ።

3.1. የናሙና አመራረጥ ዘዴ


ጥናቱ የሚካሄደዉ በሞጣ ከተማ በ 01 ቀበሌ በቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሲሆን መረጃዎች
የተሰበሰቡት በዋናነት በአከባቢው ውስጥ ከሚገኙት ተማሪዎች ነው፡፡ እነዚህም የተመረጡት በአላማ
ተኮር ናሙና አመራረጥ ዘዴ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሌላ ማህበረሰብ ይልቅ ከእነሱ የበለጠ ለጥናቱ
የሚጠቅም መረጃ ማግኘት ይቻላል ተብሎ ስለሚታመን ነው፡፡ ይህ ቦታ የተመረጠው በአመቺ የናሙና
ዘዴ ነው፡፡ ምክንያቱም አጥኚዋ በምትኖርበት አከባቢ በአቅራቢያ የምትፈልገውን መረጃ በቀላሉ
ማግኘት ስለምትችል ነው፡፡

3.2.የመረጃ መሰባሰቢያ ዘዴ
ጥናታዊ ስራን ለማቅረብ መሠረታዊ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ነው፡በዚህ ጥናታዊ
ፅሁፍ ውስጥ ካሉት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ውስጥ ሁለት አይነት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች
አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ እነሱም ምልከታእና ቃለ መጠይቅ ናቸው፡፡

3.2.1. ምልከታ
አጥኚዋ ለዚህ ጥናት ለ 5 ጊዜ ያህል ዓላማን መሰረት ያደረገ ምልከታ በማድረግ መረጃን መሰብሰብ
ችላለች፡፡ምክንያቱም ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት ዓላማ በማዘጋጀት ና በመንደፍ አመቺ ሁኖ በመገኘቱ
ነዉ፡፡የአጥኚዋ ምልከታም የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት ምን እንደሚመስል ÷የአኗኗር
ዘይቤያቸውን ÷የትምህርት ስዓታቸውንእና የአመጋገብ ስርዓታቸውን በአይነ ህሌናዋ በማየት
ነው።ምልከታው የተካሄደውም ተማሪዎች በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ነው። ምክንያቱም አጥኚዋ
በአካል ተገኝታ ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ነው። መረጃው የተሰበሰበበት
መንገድም የቆሎ ተማሪዎች የሚያደርጉትን ተግባራት በመቃኘት ነው።በምልከታ ወቅትም የተገኘ
መረጃ የቆሎ ተማሪዎች በትምህርት ወቅት ሲኖሩ አንዱ ከአንዱ ጋር በመተባበር ማለትም ከራሳቸዉ
ይልቅ ለሌላ ቅድሚያ በመስጠት ፣በተለይ ለአዲስ ገብ ተማሪዎች የተለየ ክብር መስጠት፣ለልመና
ሲወጡ ማታ የተማሩትን ሲጠያየቁ፣ምግብ ለመመገብ ሲቀርቡ በጋራ ጸሎት አድርገዉ ሲመገቡ
ተመልክቻለሁ፡፡ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የትምህርት ስርዓታቸዉ ጀማሪና ነባር ተማሪዎች አብረዉ
በአንድ ላይ ሲማሩ ተመልክቻለሁ፡፡ምልከታ የተካሄደዉ ተማሪዎች በተገኙበት አጥኚዋ በአካል በመገኘት

10
,

ለጥናቱ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በመሰብሰብ ነዉ፡፡ይህ መረጃም የተሰበሰበበት መንገድ የቆሎ
ተማሪዎች የሚያደርጉትን ተግባር በማየት ነዉ፡፡

3.2.2. ቃለ መጠይቅ
አጥኚዋ ያዘጋጀው መጠይቅ ልቅ ቃለ መጠይቅ ነው። ለዚህ ጥናትም ተጠያቂ የሚሆኑ ስዎች
ለቆሎተማሪዎች ቅርበት ያላቸው ስዎች ናቸው።
እነዚህም መርጌታዎች÷ቄሳውስቶች÷መዘምራን እና ተማሪዎች ናቸው፡፡አጥኚዋ ይህንን ጥናት ስታጠና
ለሁለት መርጌታ፣ለሁለት ቄስ፣ለአንድ መዘምር እና ለሁለት ዲያቆን በጠቅላላ ለሰባት ሰዎች ቃለ
መጠይቅ በማዘጋጀት መረጃዎችን ሰብስባለች፡፡የቆሎ ተማሪዎች በብዛት አካባቢያቸዉን ለቀዉ ሂደዉ
ስማቸዉን ቀይረዉ የሚማሩበት ምክንያት የተማሪ ወላጆች የቆሎ ተማሪ እንዲሆኑ ፍቃደኛ
ካለመሆናቸዉ የተነሳና እሽ ብለዉ ስለማያስተምሯቸዉ መሆኑን በቃለ መጠይቅ አረጋግጣለች(ቄስ
ሐይማኖት አጋዥ፣ጥር፣2014 ዓ.ም)፡፡
የቆሎ ተማሪዎች በሚማሩበት ወቅት እንጀራ ሆነ የተገኘዉን ነገር ይለምናሉ ይህ የቆሎ ተማሪዎች
ስርዓት ነዉ፡፡ስረኣቱን ማፍረስና አለምንም ማለት አይቻልም፡፡ሁሉም ተማሪ በጎጥ በጎጥ በመደልደል
ስዓቱን ጠብቆ ያገኘዉን ነገር ይዞ መመለስ አለበት፡፡የመጣዉም ነገር በጋራ ጸሎት ተደርጎ በጋራ ይበላል
(ዲያቆን ዘላለም አዱኛዉ፣መጋቢት፣2014 ዓ.ም)፡፡
በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ በትምህርት ቆይታቸዉ የተለየ የትምህርት ወቅት ተብሎ የሚታሰበዉ
በክረምት ና በአብይ ጾም ወቅት ነዉ፡፡ምክንያቱም በእነዚህ ወቅቶች በክረምት ከተፈጥሮ ክስተቶች
ጋር በማያያዝ አዳዲስ ነገሮችን እየፈጠሩ እንዲማሩ ጾም ደግሞ በጾም ና በጸሎት ተግተዉና
በርትተዉ ሲማሩ ትምህርት ይገባቸዋል ተብሎ ስለሚታሰብ ነዉ(መዘምር እዝራ
ማህሪዉ፣የካቲት፣2014 ዓ.ም)፡፡
አዳዲስ የቆሎ ተማሪዎች ሲመጡ የተለያዩ አቀባበሎች ይደርግላቸዋል፡፡ማለትም ለትምህርቱ አዲስ
የሆኑ እንዲሁም የትምህርት እድገት ለማሻሻል ብለዉ የመጡ ተማሪዎችን ልክ እንደ አብሮ አደግ
ጓደኛ በመንከባከብና በማላመድ ከነሹ ህይወት አኗኗር ጋር አብረዉ እንዲሳተፉ ያደርጋሉ (መርጌታ
ዐይነ ኩሉ ደባስ፣የካቲት፣2014 ዓ.ም)፡፡

3.1.3. የመረጃ መተንተኛ ዘዴ


አጥኚዋ ያልተደራጀ መረጃ ትርጉም በሚሰጥ መልክ ተደራጅተው፣ ተጠቃሎ፣ ተተንትኖና፣ ተተርጉሞ
ካልቀረበ ለአንባቢውም ሆነ ለራሱ ለተመራማሪው የሚያስተላልፈው መልክት ግልጽ አይደለም፡፡
የተደራጀውን መረጃ አጠቃሎ ለማቅረብ እና ትርጉም ለመስጠት ደግሞ በተገቢ መንገድ ሊተነተን

11
,

ይገባል፡፡ መረጃዎች እንደጥናቱ አይነት መጠናዊ ወይም አይነታዊ ሊሆኑ ይችላሉ ያለውእንዳወቅ ሙሉ
(2004፣ 243)፡፡

ይህ ጥናት ትኩረት ከተሰጠዉ ርዕስ በመነሳት ዓይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴን ማለትም ምልከትና
ቃለ መጠይቅ ተጠቅሞ የተሰበሰበዉን መረጃ በመተንተነና በማብራራት ገለጻና ሀተታ የሚጠይቅ
በመሆኑ ነዉ፡፡ስለሆነም ስለ ቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ የህይወት እይታ አስመልክቶ የመረጃ ምንጮች
የሰጡትን ሃሳብና የተሰበሰበዉን መረጃ ሀተታዊ ስለሆነ አጥኚዋ ለመተንተን ዓይነታዊ የመረጃ
መተንተኛ ዘዴን ተግባራዊ አድርጋለች፡፡

ከዚህ በመነሳት በቃለ መጠይቅና በምልከታ የተሰበሰቡት መረጃዎች በገላጭ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ
ተተንትነዋል።

ምዕራፍ አራት:- አካባቢያዊ ዳራ

12
,

4.1 የሞጣ ከተማ አስተዳደር ገጽታ

ሞጣ ከተማ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙት ከተማ አስተዳደሮች ዉስጥ

አንዷ ስትሆን፤የተመሰረተችዉም በ 1747 ዓ.ም በወለተ እስራኤል አማካኝነት እንደሆነ አበዉ ይናገራሉ፡፡ሞጣ

ከሌሎች ከተማ አስተዳደሮች ልዩ የሚያደርጋት ዋ ለካ ያ ሰባቱ ዋርካ እየተባለ የሚዜምላት ድንቅ ከተማ

በመሆኗ ነዉ፡፡እነዚህ ሰባቱ ዋርካ ከተማዋ ስትቆረቆር ጀምረዉ አብረዉ የበቀሉ እንደሆሉ ይናገራሉ፡፡ከተማዋ

በስድስት(6) ቀበሌዎች የተዋቀረች ናት፡፡ለመኖር ምቹ (ተስማሚ) የአየር ንብረት ያላት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ

የኢንዳስትሪ ፋብካዎች የተገነቡበት ና አገልግሎት እየሰጡ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ከተማዋ የተለያዩ እምነቶች

ያሉባት ቢሆንም ሁሉም እምነቶች በመቻቻል፣በመተሳሰብና በመፈቃቀር የሚኖሩባት ዉብ ከተማ ናት፡፡

መልካ ምድራዊ አቀማመጠዋ ደልዳላ ዉጣ ዉረድ የሌለባት በ 10 ሺ(አስር ሺ) ሄከታር መሬት ላይ

የተንጣለለች ከተማ ናት፡፡

በከተማዋ ዉስጥ የሚኖሩ ህዝቦች በአብዛዉ በንግድ ስራ ፣በመንግስት ስራ እና እንዲሁም በተወሰነ ደረጃ ደግሞ በእደ
ጥበብ ዉጤቶች ፣በከብት እርባታ ይተዳደራሉ፡፡በዚች ከተማ አስር የሚደርሱ ቤተ ክርስቲያን ና አስራ ሁለት መስጊዶች
ይገኛሉ፡፡ከተማዋ በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ የተከበበች ስትሆን በሰሜን መክሊት፣በደቡብ ድመት ገደል፣በምስራቅ ምን
ታዝግባና በምዕራብ ወብ ማርያም ከበሌዎች ያዋስኗታል፡፡የትራንስፖርት አገልግሎት በመኪና ከዞን ከተማ 192 ኪ.ሜ ርቀት
ላይ ስትገኝ ከክልል ከተማ ደግሞ 120 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡ሞጣ ከተማ ከደብረ ማርቆስ ከተማ ይልቅ ለባህር ዳር
ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ የምትገኝ ዉብና ማራኪ ከተማ ናት፡፡በእምነት የተለያዩ ህዝቦች የሚኖሩባት ከተማ ብትሆንም
በደስታና በመከራ ጊዜ የሙስሊምና የክርስቲያን አማኞች የተለየ መዋደድና ፍቅር አላቸዉ፡፡ማለትም በሰርግ ስነ ስርዓት ላይ
የክርስቲያን ከሆነ ከሙስሊሞች ሴቶች ተመርጠዉ ድግሱን ያዘጋጃሉ፤የክርስቲያን ሲሆንም እነዲሁ ያዘጋጁና አብሮነታቸዉን
ሲያዳብሩ የኖሩ ታላቅ ህዝቦች ናቸዉ፡፡በተጨማሪም በሀዘን ስርዓት ላይም በአንድ ላይ የሃዘን ተካፋይ በመሆን አብረዉ
በህበረት በመኖር ባህላዊ እሴታቸዉን እያዳበሩ የሚኖሩ ህዝቦች ናቸዉ፡፡

ምዕራፍ አምስት፡- የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ ህይወት መገለጫዎች

ይህ ምእራፍ የቆሎ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ቆይታቸው የሚያከናውኗቸው ተግባራት ይቀርቡበታል።

በመስክ ምልከታ የተሰበሰቡ መረጃዎች ትንተና ተደርጎባቸው እንደ አስፈላጊነቱ ቀርበዋል።

5.1. ጉዞ
በቆሎ ተማሪዎች ህይወት ውሰጥ ጉዞ የመጀመሪያው ክስተት ነው። ከንባብ ቤት ተማሪዎች በስተቀር

በሁሉም ደረጃዎች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት አድካሚና እልህ አስጨራሽ ጉዞ

13
,

ስነልቦናዊ ወይም ሃይማኖታዊ ዳራ አለው። ጉዞ ከሚያደርጉባቸው መካከልም እንደ ምክንያት የሚያነሷቸው

ከቤተሰብ ጋር እየተኖረ ትምህርት አይገባም በሚል የተነሳ፤በግብርና ስራ ባይጠመዱ ሙሉ ጊዜያቸውን

በትምህርት ለማሳለፍ ይታገላሉ፡፡ተሜ ሁል ጊዜ እንደተንከራተተ ነው የሚኖረው ከሃገር ሃገር ከመምህር

መምህር ሳይቀያየር ምኑን ተማሪ ሆነው፤ በእናት እጅ እየጎረሱና ሆድ ሙሉ እየበሉ ትምህርት የለም።

ፈጣሪም እናንተ ልፉ እኔ እጨምርላችኋለሁ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ ተማሪ አብዛኛውን ህይወቱን በራሱ ፍቃድ

የተሰደደ ስደተኛ ሆኖ ይኖራል። አሁን እዚህ እኛ ዘንድ ያሉት ተማሪዎች ከተለያ የ ቦታ የመጡ ናቸዉ የሚሉ

መረጃዎችን አጥኚዋ በቃለ መጠይቅ አግኝታለች(ቄስ ሐይማኖተ አጋዥ፣ጥር፣2014 ዓም)፡፡

ከላይ በምክንያትነት ከቀረቡት ሃሳቦች መረዳት የሚቻለው በተማሪዎች ስነልቦና ትምህርት መሰዋእትነትን

መፈተንን እና መቸገርን ይጠይቃል።ተደላድሎ በምቾት በመኖር ትምህርት አይገባም ብለው ያስባሉ።

አላማን ለማሳካት እና ተሽሎ ለመገኘት መፈተንና መቸገር አለብን ብለው ስለሚያምኑ ቤተሰቦቻቸውን

ትተው ጉዞ ይጀምራሉ። እውቀትን ተርበው ቤተሰቦቻቸውን ትተው የሚያደርጉትን ጉዞ እንደ መሰዋእትነት

ይቆጥሩታል።

5.2. ልመና
የቆሎ ተማሪዎች ተለይተው የሚታወቁበት አንዱልመና ነው። በትምህርት ቤት የሚያሳልፉትን

ህይወትየሚማሩት (በእንተ ስሟ ለማርያም) ብለው በሚያገኙት ቁራሽ እንጀራ ነው። በቆሎ ተማሪዎች

ዘንድልመና እራሱን የቻለ ስርአት ነው።

5.2.1. የመለመኛ ሰዓት


ከመሪጌታ ዐይነ ኩሉ በተገኘው መረጃ መሠረት ማንም ተማሪ በፈለገው ሰአት ወጥቶ መለመን አይችልም ።

ለልመና የሚወጡበት ሰዓትበአማካኝ ከዘጠኝ ሰዓትበኋላ ነው። ይህም የሆነበት ሁለት ምክንያቶች አሉት።

አንደኛውምክንያት ከሚለምኑት ማህበረሰብ የስራ ባህል ጋር የተያያዘ ነው። ይህጥናት በተካሄደበት አካባቢ

በየስራው ተሰማርተዉ የሚውሉ ሰዎች ወደ ቤቱ የሚመለሰው ከአስር ሰዓት በኋላ በመሆኑ ነው።

ተማሪዎች ከዚህ በፊት ለልመና ቢነሱ በየቤቱ ሰው ስለማያገኙ ነው። እና በቤት ውስጥ የሚያገኙት ህጻናትን

ብቻ በመሆኑ ነው። ስለዚህ ለልመና ወጥተው ባዶ እጃቸውን እንዳይመለሱ የገበሬዎችን የመመለሻ ሰዓት

ጠብቀው ለልመና ይወጣሉሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከትምህርት ሰዓታቸው ጋር የሚገናኝ ነው። እስከ

ስምንት እና ዘጠኝ ሰዓት ያለው ሰዓት በአበዛኛው የትምህርት ሰዓታቸው ስለሆነ ከዛ በኋላ ለልመና

ይንቀሳቀሳሉ(ቃለ መጠይቅ)

14
,

5.2.2. የመንደር ድልድል


በሚማሩበት ጉባዔ ስር የሚጠቃለሉ የ 01 ቀበሌዎች በሙሉ በእጣ ተደልድለው በተማሪዎች ይከፋፈላሉ።

ድልድሉም የሚካሄደው በእጣ ነው። እያንዳንዱ ተማሪ በእጣ የደረሰው መንደር ብቻ በመሄድ መለመን

ይኖርበታል።ድልድሉን የሚያካሂዱት በጉባዔው የተመረጡ ተማሪዎች ናቸው።ሲመረጡም እንደ መስፈርት

የሚወሰደው እድሜ፤ባህርይ፤ የእውቀት ደረጃቸውና የመሳሰሉት ናቸው።ስርአቱም በየሳምንቱ

ይካሄዳል።በየሳምንቱ የሚካሄድበትምክንያት አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ ሊሆን ስለሚችል በየሳምንቱ

እየተቀያየሩ ሁሉም ተማሪዎች ሁሉንም መንደር የማግኘት እድል እንዲኖራቸው ሲባል ነው።

5.2.3. የመለመኛ ቁሳቁሶች


ተማሪዎች ለልመና ሲነሱ የሚይዟቸው ቁሳቁሶች አኮፋዳና ረጂም በትር ነው።አኮፋዳው ከማዳበሪያ (ከቆዳ)

የተሰራ ሲሆን የሚለምኑትን ቁራሽ እንጀራ ከመያዝ ባለፈ ትልቅ ትምህርት አለው። ይህም ከሃይማኖታቸው

ጋር የተያያዘ ነው። ተማሪዎች እንደሚሉት መንፈስቅዱስ ከእመቤታችን አድሮ ኢየሱስክርስቶስ እንደተወለደ

ሁሉ ለልመና ሲነሱ አቆፋዳው የለመኑትን ቁራሽ

እንጀራ ከመያዝ በተጨማሪ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ማደሪያ ነው ብለው ያምናሉ።በዚህም መሰረት

ለልመና ከጎጇቸ ውወጥተው ዞረው እስኪመለሱ እመቤታችን አብራትከተለናለች፤አጥተንም አንመለስም

ያገኝናትም ትንሽ ነገር በረከት ይኖራል በተጨማሪም የዕለት ጉርሳችውን የምታዘጋጅላቸውም ሆነ ከክፉ ነገር

የምትጠብቃችው “ድንግልማርያም” ናት፡፡ስለዚህም ለልመና ሲነሱከነርሱ ጋር መሆኗን ያምናሉ። ይህንን

እምነታቸውን ለመግለጽ ማንም ተማሪ ለልመና ወጥቶ በመንገድ ላይእያለ አቆፋዳው ውስጥ ያለውን ቁራሽ

እንጀራ መብላትአይችልም።ምክንያቱም ከአቆፋዳው አብራቸው ስትንከራተት የነበራቸው

“ድንግልማርያምአለች። ስለዚህ በሰላም ወደጎጇቸው ገብተውድንግል ማርያምን መሸኘት አለባቸው።

የመሽኘት ስርአቱም እራሱን የቻለ ደንብ አለው። አንድ ተማሪ ዛሬ ላይ የመለሰችው ድንግል ማርያም ነገ
ሰአቱ ደርሶ እስክትመትጣ በሰላም መሸኘት አለበት። ከልመና የመጣ ተማሪ የያዘውን አቆፋዳ እንደያዘ ወደ
ጎጆው አይገባም። በአካባቢው ላሉ ተማሪዎች ከአቆፋዳው እያወጣ(የማርያም መሸኛ)በማለት ያቃምሳል።
ይህንን ካደረገ በኋላ በነጻነት መመገብ ይቻላል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በመንገድ ላይ ሰው እንኳን ሳያያው የቀመሰ
ተማሪ ካለ ሰይጣን አሳሳተኝ ብሎ ለጓደኞቹ ይናዘዛል እንጂ ዝም ብሎ አይቀመጥም።
ሁለተኛ የመለመኛ ቁሳቁስ በትር ነው። አገልግሎቱ ውሻ በሚመጣበት ጊዜ እራሱን የሚከለክልበት ብቸኛ
መሳሪያ ነው።ረጂም የሚሆንበት ምክንያት ውሻውም ከርቀት ለመመለስ እንዲያመቸው ነው። አንድ ተማሪ
በሚለምንበት ወቅት ውሻው ከርቀት የቱንም ያህል ቢያስቸግረው እራሱን መከላከል እንጂ ውሻውን
መደብደብ አይችልም።የማይደበድብበት ምክንያት ውሻውን ከደበደበ የሚለምነውን ሰውዬ (የውሻው ባለቤት)
15
,

እንደናቀ ስለመቆጠር ነው።ከውሻው ጋር ታግሎ ካልለመነና ውሻ በምፍራት የተመደበበትን መንደር


አለመለመን ወይም በውሻ ተነክሶ መምጣት በተማሪዎች ዘንድ እንደ ውርደት ይቆጠራል። እራሱን ከውሻ
ያልጠበቀ ምኑን ተማሪ ሆነ ተብሎ ይሳቅበታል።

5.2.4. ማህበረሰቡ ለልመና ያለው አመለካከት


ማህበረሰቡ ለልመና ሁለት አይነት አመለካከቶች አሉት።እነርሱም አውንታዊና አሉታዊ አመለካከት ናቸው።

5.2.4.1.አወንታዊ አመለካከት
የቆሎ ተማሪዎች ከቤታቸው የሚወጡት ጥበብን ፍለጋ ነው።የድንግል ማርያምንስም ጠርተው የሚኖሩ
የፈቃደኛ ስደተኛችመሆናቸውአምኖ የሚቀበል ማህበረሰብም ይህን አስቸጋሪ የሆ ነውን ህይወት አልፎ
በአለም የቤተክርቲያን አገልጋይዮች በመሆን እነሱን ከፈጣሪያቸው ጋር የሚያገናኙና የመሸጋገሪያ ድልድይ
መሆናችውን ስለሚያምኑ ልመናቸውን በደስታ ይቀበላሉ፡፡እንዲኖሩም ከፍታኛ ጉጉት አላቸው፡፡የዛሬዎቹ
ተማሪዎች ነገ የእግዚአብሔር አይኖች ናቸው፡፡ስለሆነም ሲለምኑ መስጠት እንደ ጽድቅ ሳይለምኑ መቅረት
ደግሞ በረከት እንደማጣት ይቆጠራል፡፡ነገ የሚደርሱበትን በማሰብለልመና በበራቸውለሚቆም ተማሪ ትልቅ
ክብር ይሰጣሉ፡፡ይህንን በማሰብተማሪ ካለመነ ምነው ረድኤት ተለየንፈጣሪእራቀን ብለው ያምናሉ፡፡ ይህንን
ለማረጋገጥ ተማሪዎችን በልመና ለይተው ከሚተዳደርሸ ሌሎች ሰዎችለይተው የሚመለከቱበት እይታቸው
ነው፡፡ ለምሳሌበአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች በተገኘ መረጃ መሰረት ሌሎች ለማኞች ሲቆሙ”ለማኝ
ቆሟል”ሲሉ ተማሪ ለልመና ሲቆም“ተማሪ ቆሟል” ይላሉ፡፡ስለዚህ ተማሪዎች አጥተው ወይም መስራት
ሳይችሉ ቀርተው ሳይሆን ለትምህርት ሲሉ የወጡ መሆናቸውን አውቀዋል ማለት ነው፡፡ወይም ደግሞ ተማሪ
እግረ እርጥብ ነው በረከት ይዞ ይመጣል በማለት ለሚሰጡት ቁራሽ እንጀራ አንዳች ቅሬታ አያድርባቸውም፡፡
ተማሪ ከበራቸው ላይ ካልቆመ እምነታችንን ተጠራጥሮታል ወይም እግዚአብሔር እርቆኛል ብለው ያምናሉ፡፡
በእንተ ስሟ ለማርያም ብሎ የሚለምን ተማሪበበራቸው ቢቆም ግን ፈጣሪ ታርቆኛል በቤቴ በረከት ሊገባ ነው
የሚል ተስፋ በውስጣቸው ያድራል፡፡

5.2.4.2.አሉታዊ አመለካከት
ይህ አሉታዊ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ተማሪዎችን የሚመለከቱበት አተያይ በተለያየ ምክንያት ፍርሀት
ያለባቸው ናቸው፡፡ ፍርሀታቸውን ተማሪዎች ተንኮለኛ፣ድግምትና ጥንቆላ ያደርሳሉ ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡
ስለዚህ ሳንሰጣቸው ቢመለሱ በልጆቻችንና በንብረታችን ላይ ድግምት ሊያደርሱብን ይችላሉ የሚል
አመለካከት አላቸው፡፡ ከወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ ጋር በተደረገ ውይይት ‹‹ የበሰለ ነገር ባይኖር እንኳ ጥሬ ቢሆን
አፍሰን እንሰጣቸዋለን፡፡ ምጣድም አልጣድን ብለን ብንመልሳቸው ተንኮል ያስቡብናል በማለት ስጋታቸውን
ገልጸዋል፡፡''ይህ አመለካከት የሚሳያን የተማሪዎችን አዋቂነት ከማህበረሰቡ የተሻለ ሁሉንም የማድረግ ችሎታ
እንዳላቸው መገንዘብ ይቻላል፡፡

16
,

5.3. ስም ቅየራ
በቆሎ ተማሪዎች ህይወት ውስጥ ከሚመጡ ክስተቶች መካከል ስም ቅየራ አንዱ ነው።አብዛኞቹ የቆሎ
ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸው ያወጡላቸውን ስም ትተው በሌላ ስም ይጠራሉ።ከተማሪዎች በተገኘ መረጃ
መሰረትም ስማችውን የሚቀይሩበት የራሳቸው ምክንያት አሏቸው፡፡

5.3.1. ከቤተሰብ ለመደበቅ


ይህ ቀደም ብሎ ከተነሳው ጉዞ ጋር የተያያዘ ነው። ተማሪዎች ጉዞ ሲያደርጉ ከቤተሰቦቻቸው ፍቃድ
አያገኙም። ከተማሪዎች በተገኝ መረጃ መሰረት ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት ፈቅደው
ቢልኳቸውም የቤተሰብ ዓላማ በአካባቢያቸው በሚገኙ የንባብ ቤቶች ፊደል ቆጥረውና ዳዊት ደግመው
እንዲያበቁ ነው።ስለዚህ ከዚህ ከፍ የሚለውን ደረጃመማርየሚፈልግ ተማሪከወላጁ ፍቃድአያገኝም። በዚህ
መሰረት ጉዞውን የሚያደርገው ከቤተሰቦቹ በመደበቅ ነው፡፡ ቤተሰቦቹም ልጆቻቸውን በየጉባዔው ሰው እየላኩ
ማፈላለግ ይይዛሉ።ቤተሰብ ለልጁ ባወጣለት ስም እየጠራ ቢፈልግም ልጁ ወደ ጉባዔው ሲቀላቀል ስሙን
ስለሚቀይር አየሁየሚል ሰው አያገኝም።ወላጆች ልጆቻቸው እነሱን ጥለው እንዳይሄዱ የሚፈልጉበት
ምክንያት አላቸው።አንደኛው ለልጆቻቸው ካላቸውፍቅር የተነሳ በማያውቁት ሃገር ሄደው ለምነው
እየበሉእንዲኖሩ አይፈቅዱላቸውም።እንዲርቋቸውም አይፈልጉም፡ተማሪዎች ሩቅ ሃገር አቆራርጠው
ስለሚሄዱ መርቀው አይሸኟቸውም።
ሁለተኛውም ምክንያት ደግሞ ልጆቻቸው ከእነርሱ ጋር ሆነው ስራ እያገዟቸው እንዲኖሩ
ይፈልጋሉ።ስለዚህተማሪዎቹከወላጆቻቸውጠፍተው ስለሚዎጡናወላጆቻቸው እንደሚፈልጓቸው
ስለሚያውቁ አፈላልገው እንዳያገኝዋቸው ስማቸውን ይቀይራሉ።

(ጥር፣17፣2014 ዓ.ም በቅዱስ ጊዮርጊስ ከሚማሩ የዜማ ተማሪዎች ውስጥ ተማሪ በቃሉ ይርጋ እንዳለዉ ወደ
አዲሱ ጉባዔ (ትምህርት ቤት)የሚቀላቀል ተማሪ በምንም መንገድ ትክክለኛ ስሙን አይናገርም።በጣም
የሚቀራረቡና አብሮ አደግ ጓደኛሞች ቢኖሩም እንኳን ትክክለኛ ስማቸውን ላይጠራሩ ይማማላሉ።

5.3.2. ከመጸሐፍ ቅዱስ በመነሳት


ተማሪዎች ስማቸውን መለወጥ ከሃይማኖታቸውና ከሥብእናቸው መለወጥጋር ይይያዛል።አለማዊ ህይወት
ትተው ወደ መንፈሳዊ ህይወት መግባታቸውን መሰረት በማድረግ ቤተሰብ ያዋጣላቸውን አለማዊ ስም
ይቀይራሉ፡፡ከስብእና እና ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ ስም ቅየራ መጻሀፍ ቅዱሳዊ መሆኑን ይናገራሉ።ኢየሱስ
ክርስቶስ ተከታዮቹን ሲመርጥ ስማቸውን እንደለወጠው ሁሉ እነሱም ለመምህራቸው እራሳቸውን እንደ
ደቀመዝሙር ስለሚቆጠሩ ስማቸውንይቀይራሉ።ስማቸውን ሲቀይሩ በዘፈቀደ አይደለም። አዲስ ስማቸውንየሚቀይሩትስማቸው
የወደፊት ፍላጎታቸውን፤ምኞታቸውን እና አድናቆታቸውን የሚጠቁም ይሆናል።ስም ሲቀየር የሚለውጠው ሰም በራሱ ወይም
ከአባታቸው ስም ጋር ሆኖ አንድ አይነት ፍቺ መስጠት አለበት።ስሙ ትርጉም እንዲሰጥ ተደርጎ መለወጡም በራሱ
በሃይማኖታዊ መሰረት አለው።ለምሳሌ፡-የሉቃስ ወንጌል”ሲነጋም ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ

17
,

ጠራቸው።ከውስጣቸውም አስራሁለቱን መረጠ፤ ሐዋሪያት ብሎም ሰየማቸው(ሉቃ 6፡13)፡፡ሌላው በማርቆስ


ወንጌል እንደተገለጸው ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጠው የስም ለውጥ ከአንዳች ፍቺ ጋር የተያያዘ
ነው።”የዘብዲዎስ ልጅ ያዕቆብንና የያዕቆብን ወንድም ዮሐንስንም ‹ቦኤርኔጌስ› ብሎ
ሰየማቸው፤ትርጉሙ”(የነጎድጓድ ልጆች)ማለት ነው።(ማርቆስ 3፡13) (ቃለ መጠይቅ

5.4. የትምህርት ወቅት


መሪጌታ ኤፍሬም ይህንን አስመልክተው የቆሎ ተማሪዎች የትምህርት ወቅቶች የሚባሉት በአመት
ሁለት ወቅቶች ናቸው፡፡ እነርሱም የአብይጾም እና ክረምት ናቸው። በነዚህ የትምህርት ወቅቶችም
ተማሪዎች ከአንዱ ጉባኤ ወደ ሌላ ጉባኤ አይንቀሳቀሱም፤እነዚህ ሁለት ወቅቶች የተመረጡባቸው
የራሳቸው የሆነ ምክንያት አላቸው።

5.4.1. ዓብይ ጾም
በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ የዓብይ ጾም በአማካይ ወደ ሁለት ወር የሚጠጋ ነው፤
ይህ ወቅት ጉባኤዎችከሌላው ጊዜ በተለያየ መልኩ በተማሪዎች የሚደምቁበት ጊዜ ነው።
ተማሪዎችም እንደዋና የትምህርት ወቅት በጉጉት ይጠብቁታል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አንደኛ
ተማሪዎቹ በጾምና በጸሎት ተግተን ስንማር ትምህርት ይገባናል ብለው ስለሚያምኑ ነው፡፡በጾም ወቅት
ረጅምመንገድ በእግር መጓዝ ስለማይፈቀድ ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስመማር ስለሚችሉ ነው።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በዚህ ወቅት የጾም ወቅት ስለሆነ በሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ ምንም አይነት
ድግስ አይደገስም።ድግስ አለመደገሱ ደግሞ ተማሪዎች ድግስ ፍለጋ ከቦታ ቦታ እንዳይዞሩና በትምህርታቸው
እንዳይዘናጉ ይጠቅማቸዋል።ምክንያቱም የተለያዩ ድግሶች የሚኖሩ ከሆነ መምህሩ በጥሪ ተማሪዎች ደግሞ
ለልመና ስለሚሄዱ በጉባኤ ላይ ላይገኙ ይችላሉ።ስለዚህ በጾም ወቅት መምህራኖች ወዴትም
ስለማይንቀሳቀሱ መምህሩ እና ተማሪዎች እንደልብ የመገናኘት እድላቸው ከፍተኛ ነው። በተጨማሪም በጾም
ወቅት በሚከናወን ቅዳሴ የዜማተማሪ፣ በአብይ ጾም ወቅት በሚከናወን ቅኔ ተማሪ ደግሞ በሚከናወነው ቅኔ
በተግባር የመማር እድልን ያገኛሉ።በቅዳሴ ወቅት በሰሙት መሰረት የራሳቸውን ችሎታ ተጠቅመው አዲስ ቅኔ
ይፈጥራሉ።መምህራኖቹም ቢሆኑ የሃሳብ ነጻነትን ይሰጧቸዋል፡፡ የራሳቸውን ፈጠራ ሲፈጥሩም ለረጅም ጊዜ
በተመስጦ ውስጥ ይሆናሉ።ይህን ለማድረግም ከመማሪያ ቦታቸው ራቅ ብለው ሰው ወደ ማይበዛበት ቦታ
በመሄድ ወደ ውስጣቸው ይመለከታል።አዲስ ነገር ለመፍጠርም የተለያዩ እንቅስቃሴያቸው
ያሳያሉ።ተሸፋፍነው ይተኛሉ፤ዛፍ ላይ ይወጣሉ፤ወደሰማይ ይመለከታሉ፡፡

5.4.2. ክረምት
በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ ዋና የትምህርት ወቅት ተደርጎ የሚታወቀው የክረምት ወቅት ነው፡፡ ከዓመቱ አራት
ወቅቶች መካከል ክረምት ተማሪዎች ሃሳባቸውን ሁሉ ሰብስበው ለትምህርት እራሳቸውን የሚዘጋጁበት ጊዜ

18
,

ነው ከተማሪዎች በተገኘ መረጃ መሰረት ክረምት ለትምህር ዋና ወቅት ተደርጎ የተመረጠበት ምክንያት
ከተፈጥሮ ክስተቶች ጋር በተያያዘ ነው፡፡ በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ የንባብ ቤትን ያለፈ ተማሪ የአስተሳብ ነጻነት
ተሰጥቶት በራሱ አዲስ ፈጠራ እየታገዘ ትምህርቱን ይቀጥላል፡፡አዲስ ነገር ለመፍጠር ደግሞ የተፈጥሮ
ክስተቶችን እንደ ግብአት ይጠቀማል፡፡ ክረምት ከሌሎች ወቅቶች በተለየ መልኩ ብዙ ነገሮች የሚከሰቱበት እና
የሚለዋወጡበት ጊዜ ነው፡፡ የነገሮች መለዋወጥና በነበሩበት አለመቆየታው ደግሞ ለዜማና ለቅኔ ተማሪዎች
የፈጠራ ልምዳቸውን ያዳብራል፡፡ በክረምት ደመና በሰማይ ላይ የሚያንዣብብበት፣ጉም ወርዶ ወርዶ
የሚረገረግበት ፣መብረቅና ነጎድጓድ ከወዲያ ወዲህ የሚሰማበት፣ወንዞች ሞልተው ከልካቸው በላይ
የሚፈሱበት፣ዝናብ ያለማቋረጥ የሚዘንብበት ጊዜ ነው፡፡ በአጠቃላይ መሬቱ በልምላሜ የሚሞላበትና ለአይን
የሚታክቱ ተፈጥሮአዊ ክስተቶች የሚቀያየሩበት ወቅት ነው፡፡ የቅኔም ሆነ የዜማ ተማሪ በዚህ ተፈጥሮአዊ
ክስተት ታግዘው አዲስ ነገር ይፈጥራሉ፡፡ የዜማ ተማሪውም ከነፋሱ ሽውታ፣ ወንዞች ሲሞሉ ከሚያሰሙት
ድምፅና እንቅስቃሴ ጋር ዜማውን ያዋህዳል፡፡ የቅኔ ተማሪም አይኑን እስከሚታክተው ድረስ ከሚመለከተው
ነገር በመነሳት አዲስ ቅኔ ይፈጥራል፡፡

በአጠቃላይየክረምት ወቅት ይዞት በሚመጣው ክስተት ምክንያት ለፈጠራ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ስለሆነም
በዚህ ወቅት ተማሪ ከቦታ ቦታ አይንቀሳቀስም፡፡ ከጉባኤ ወጥቶ ወደ ሌላ ጉባኤ አይዞርም፤ ከዚህ ይልቅ ሙሉ
ትኩረቱን ለትምህርቱ ያደርጋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ክረምት ለትምህርት የሚመረጥበት ሌላው ምክንያት ከላይ እንደተገለፀው በክረምት
ወንዞች ይሞላሉ፣ መንገድ ሁሉ በጭቃ ይዋጣል፣ በሠላም የተሻገሩት ወንዝ ሲመለሱ ሞልቶ ሊጠብቅ
ይችላል፡፡ እነዚህ ሁሉ ክስተቶች ከቦታ ቦታ እንዳይዟዟሩ ወይም መምህር እንዳያማርጡ ያደርጋቸዋል፡፡
ስለሆነም በዚህ ወቅት በጋ ላይ ለክረምት ብለው ያዘጋጁትን ድርቆሽ ባሉበት በመያዝ በአንድ ጉባኤ ረግተው
እንዲማሩ ያደርጋቸዋል፡፡

5.5. የቆሎ ተማሪ ተረቶች


የቆሎ ተማሪዎች ተረታቸውን ለተለያዩ ነገር ይጠቀሙባቸዋል፡፡ ማለትም ያጡትን ለማግኛ ፤ትዝብትና
ተቃውሞን ለመግለጽ እና ማንነታቸውን ለማሳወቅይጠቀሙበታል፡፡

5.5.1. ያጡትን ማግኛ ተረቶች


የቆሎ ተማሪዎች ለልመና በተለያየወቅት በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ የተለያየ ገጠመኝ ይኖራቸዋል፡፡ለምሳሌ
፦የአንዱን ሚስት ሌላው ሲያማግጥ ነውርየሚባል ነገር ሲፈጽሙ የመሳሰሉትን ድርጊቶች ሊመለከቱ
ይችላሉ፡፡

19
,

ከእለታት አንድ ቀን ተሜ በአቆፋዳው ተልባ ይዞ ከመንደር መንደር እየለመነና ተልባውን የምትቆላለት ምጣድ
የጣደች ሴት ይፈልጋል፡፡በመንደር እየዞረም ባለበት ጊዜም ድንገት ምጣድ የጣደችሴት ያገኛል፡፡እሜቴ እባኮትን
ይህችን ተልባ ባሰሙት ምጣዱ ያምሱልኝ ብሎ ሲጠይቅ አንድሰው ወደ ጓዳ ዘሎ ሲገባ ያያል፡፡ሴትየዋም
ወዲህ በል ብላ ሰትቆላ ተልባው እየተፈናጠረ ያስቸግራል ልትከድነው ስትሞክር ተሜ በሜዳው ላይ ያሞሌ
ጨውና ዳቦ ስላየ የሰውየው እንደሆነ ስለገመተ እሜቴ አይክደኑት የተረፈው ይበቃኛልይላታል፡፡ተልባው
አብዛኛው እየተፈናጠረ ፈስሶ አለቀ እሷም የተረፈውን በአቁፋዳህላድርግልህ ሂድትለዋለች፡፡እርሱም
መዘግየት ስለፈለገ የእመቤቴን ስም የጠራሁበትን ትቼ አልሄድም ይልና የፈሰሰውን መልቀምይጀምራል፡፡
መልቀምእንደጀመረምባል ከሄደበት ከተፍ ይላል፡፡ባልአሞሌ ጨውንና የዳቦውን ክምር ተመልክቶም የማን
እንደሆነ ይጠይቃል፡፡ሚስትም የተማሪው እንደሆነ ትነግረዋለች፡፡ተሜም ይችን አጋጣሚ ተጠቅሞ እሜቴ
የነፍስ ዋጋ ይሁንሎት ብሎ ዳቦውንና አሞሌውን ይዞ ሊሄድ ሲል ያቅተውና አይ እሜቴ ከድካሞት
አይበልጥምና ያሸክሙኝ ይላታል፡፡እርሷም በአይኗ ገላምጣ ወደ ጓዳ ትገባለች ፡፡ ባልም አሸክሚውና
ምርቃትሽን ጨርሺ ይላታል፡፡ሚስትም ካሸከመችውበኃላ ተከትላው ትወጣና እባክህን ዳቦውን ወስደህ
አሞሌ ጨውን ላው ትለዋለች፡፡ እርሱም እግዚአብሔር የሰጠኝን ላንቺ አልሰጥም ብሏት ዳቦውንና አሞሌ
ጨውንም ይዞ እብስ አለ ይባላል፡፡

5.5.2. ማንነታቸውን ለማሳወቅ የሚጠቀሙት ተረት


ከእለታት በአንድ ቀን ተማሪና የሚማርበት ደብተራ ቄስ በአንድ ላይ ለህዳር ሚካኤል ዝክር ይሄዳሉ ፡፡ከዝክሩ
ቦታ እንደደረሱ ቄሱ ተሜን በል ደጅ ተቀመጥ ብለው ወደ ቤት ይገባሉ፡፡ከገቡ በኋላምለዝክር የመጣው ሰው
ተነስቶ በክብር ተቀበላቸው፡፡ቄሱም ዝክሩን አስጀመሩና ወዲያው የተደገሰውን መብላት መጠጣት
ይጀምራሉ፡፡ተሜ ግን በኋላ ትርፍራፊ ይሰጠዋል ብለው ዝም ይሉታል፡፡ቄሱም ስጡት እንኳን ሳይሉ
እስከመምጣቱ እረስተውታል፡፡የተሰበሰበው ሰውም አባታችን ዛሬ ቀኑ ሚካኤል ምን ያደረገበት ቀን ነው
ብለው ይጠይቋቸዋል፡፡ቄሱ ታሪኩን ስለማያውቁት ወደ ሽንት ቤት ደርሼልምጣ በማለት ወደ ተሜ ሄደው
ይጠይቁታል፡፡ አንጀቱ እርር ድብን ያለው ተማሪም ሚካኤል የሞተበት ቀን ነው በማለት ይመልስላቸዋል፡፡
ቄሱም እንግዲህ ዛሬ የዘከርነው የሚካኤል ዝክር የሞተበትን ቀን ነው ይላሉ፡፡በዚህን ጊዜ ተማሪው እ ሪ ብሎ
እየጮኸ ዛሬ ሚካኤል የሞተበት ቀን አይደለም ብሎ ትክክለኛውን ታሪክ በመናገር በመጨረሻም መላዕክት
አይሞቱም ብሎ ቄሱን ያዋርዳቸዋል፡፡ቄሱም ክብራቸውን ተገፈው ያለ አጃቢ ተመለሱይባላል፡፡

5.5.3. ትዝብትና ተቃውሞን መግለጫ ተረት


ተማሪ መቼም በአካባቢው በሚገኘ ትምህርት ቤት የመማር ልምድ የለውምና ራቅ ወዳለ ቦታ ሲሄድ ይውልና
ወደ አንድ ቤት በመሄድ የእግዚብሔር እንግዳ ነኝ አሳድሩኝ በማለት ይጠይቃል፡፡ባለቤቶቹ ቤት የእንግዳ ነው
በማለትእንዲያድር ይፈቅዱለታል፡፡እመቤቲቱም ወጣ ገባ ሲሉ ተሜንሲመለከቱት የሚስብ ነው፡፡ ልጃቸውን
ይጠሩና ለብ ያለውሃ ለተሜ አምጭለት ብለው አዘዙ፤ተሜም እግዚአብሔር ይባርክልኝ ብሎ ልብሱን ከፍ

20
,

አድርጎ መታጠብ ይጀምራል፡፡ሴትየዋም ትኩር ብለው ሲያዩትተሜ ቀልብ ይስባል፡፡በልና ከፍ ብለህ ተቀመጥ
ምግብም ብላ ጠጣ እያሉ ሲንከባከቡት ያመሻሉ፡፡ተሜም ስለተደረገለት ግብዣ ሁሉየነፍስ ዋጋ ያድርግልኝ
በማለት መርቆ እዛው መደብላይ ሊተኛ ሲል በልና ከዚህ ካልጋው ጠጋ ብለህ ተኛ በኔ ልታስፈርድ ነው
ይሉታል፡፡ግድ የለም እዚሁ እተኛለሁ ብሎ እምቢ ይላል፡፡ሴትየዋም ጠጋ ብለው እንደ ማባበል ሲቃጣችው
ተሜ ነገሩ ገባውና እሜቴ አይሆንም አይሆንም እንዲያውም ሞቶብኛል ደግሞም ተማሪ ነኝ
ሲላቸውሴትየዋምየዋዛ አልነበሩምና እኔስ ምን አልኩ አምጣና ቅበረው ነውያልኩት ይሉታል፡፡የሴትየዋ
ድፍረት ያስገረመው ተሜም አይ እሜቴ ቢቀበርም የሚቀበረው በሃገሩ በወገኑበደንቡ መሰረት ብሎ
አሳፈራቸው ይባላል፡፡

5.7. መረጃ ትንተና


5.7.1.ማህበራዊ ዘርፍን በተመለከተ
ትምህርት:-ከተማዋ በትምህርት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ አንደኛ ደረጃን በተመለከተ 6 አፀደ

ህፃናት÷4 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ÷4 አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ÷4 ሁለተኛ ደረጃ እና 1 ቴክኒክናሙያ

በድምሩ 19 እና የግል ኮሌጆች የትምህርት ተቋማት አሏት።

ጤና:በከተማዋ 1 ጤና ጣብያዎች ÷6 ጤና ኬላዎች ÷1 ሆስፒታል እና የግል ክኒሊኮችናመድሃኒት ቤቶች

ለወረዳው አገልግሎት በመስጠት ይገኛሉ ።

5.7.2. መሰረተ ልማትን በተመለከተ


መብራት:በከተማዋ የመብራት መቆራረጥ ችግር በአብዛኛዉ አይታይም፡፡ምክንያቱም በከተማዋ የመብራትሃይል

ስለሚገኝ ነዉ፡፡

ስልክ:የከተማዋ ማህበረሰብ የተንቀሳቃሽ ስልክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን በ 3 የኔትወርክ ታወር

ተገንብቶ ቀበሌዎችን የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ሆነዋል።

መንገድ: የሞጣ ከተማ ከቀበሌዎችም አልፎ ተርፎ የተለያዩ ከተማዎችን የሚያገናኝ መንገድ አለ፡፡ ከቀበሌ

እስከ ፌደራል የሚያገናኝ የመንገድ አገልግሎት ይሰጣል።

ውሃ:በከተማዋ በአብዛኛው ቀበሌ የቧንቧ ውሃ ተጠቃሚ ናቸዉ ።

5.7.3. የከተማዋ የኢንቨስትመንት አማራጮች


ሞጣ ከተማ ዙሪያዉን በትናንሽ ወንዞች የተከበበች ቢሆንም አገልግሎት እየሰጠ አይገኝም፡፡ጠንካራ የህዝብ

ባለቤት በመሆኗ በከተማዋ ዉስጥ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ቢሰማሩ ትርፋማ ሊያደርጉ የሚችሉ ዘርፎች አሉ፡፡

21
,

እነዚህም:~በአሽዋ ምርት÷በድንጋይናበቡለኬት ምርት ለመሰማራት በቂ ሃብትናአቅርቦት መኖር፤ ለእንሰሳት

ማድለብና ለንብ እርባታ ምቹ፤ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ለመስራት ለም መሬትና ግብዓት መኖሩ

የከተማዋን አሳድጓል፡፡

5.7.4. የከተማዋ ዋና ዋና ተቋማት


 ሆቴል

 ዳቦቤት

 ሰጋ ቤት

 ምግብ ቤት

 ቡና ቤት

 አነስተኛና መካከለኛ ሪስቶራንት

 ፎቶቤትና ሱፐር ማርኬት

 የሴቶችናየወንዶች የውበት ሳሎን

 የተለያዩ ባንክ

 አብቁተ ተቋማት ይገኛሉ ።

5.7.5.ሃይማኖታዊ ተቋማትን በተመለከተ


ሞጣ ከተማ የኦርቶዶክስ እምነት፣የእስልምናእምነት ፣የወንጌል አማኞች ይገኛሉ፡፡በአብዛኛዉ ግን

የኦርቶዶክስና የእስልምና እምነት ተከታዮች ከተማዋን ሸፍነዉ ይገኛሉ፡፤ሲኖሩም እርስ በርሳቸዉ

በመቻቻልና በመተሳሰብ ነዉ፡፡10 የኦርቶዶክስ ተከታዮች 1 የወንጌል አማኞች ና 12 የእስልምና ተከታዮች

በከተማዋ ይገኛሉ፡፡

5.7.6. ታሪካዊናመንፈሳዊ የሃይማኖት ቦታዎች


በሞጣ ከተማ ዉስጥ ከሚገኙ አቢያተ ክርስቲያናት ዉስጥ ቅዱስ ጊዎርጊሰ ቤተክርስቲያን ከወረዳም አልፎ ተርፎ በክልል እንዲሁም
በሌሎች ህዝቦች ዘንድ እንዲታወቅ ከሚያደርጉት ዉስጥ የቅኔ ባላባት ፣ የድጓዉ መቀበያ ፣ የቅኔዉ፣የዜማዉ የአብነቱ መምህር መሪ ጌታ
አይነኩሉ ሲሆን በዞንንና በአጎራባች ወረዳወች ከሚታወቁት ቦታወች ዉስጥ ችጋ ፀበል (በአታ ለማርያም ) ገዳም በከተማዋ ዉስጥ
ይገኛል ፡፡

22
,

5.7.7.የቆሎ ተማሪ ጉባኤን በተመለከተ

በሞጣ ከተማ በቅዱስ ጊዮርጊሰ ቤተ ክርሰቲያን ጉባየ ዘርግቶ ማስተማር አዲስ ባይሆንም ለ ዘርግቶ

ማስተማር አዲስ ባይሆንም ልዩ የሚያደርጉት ቅኔ ቤት÷ዜማ ቤት÷ድጓ ቤት ÷ንባብ ቤት መጽሐፍ ቤት እና

አብነት ትምህርት ቤት በአንድ ላይ መስጠት መቻሉ ነው። እንዲሁም የድጓ ቤት መምህር ÷የንባብ ቤት

መምህር÷የዜማ ቤት መምህር ÷የመጽሐፍ ቤት መምህር ÷የቅኔ ቤትመምህር እናየአብነት መምህር

የምስክርነት ወረቀትን በመስጠትና በርካታ ተማሪዎችንበማስተናገድ የሚታወቅ ጉባኤ ሲሆን አሁን በቅርቡም

የኢትዮጵያ የቅኔ ዮኒቨርስቲ በመባል መስረት ተቀምጦ በመሰራት ላይ የሚገኝ ትልቅ ቦታ ነው።

5.8. መረዳዳት
እያንዳንዱ ተማሪ የራሱ የሆነ ጎጆ ቢኖረውም የሚኖሩት፤የሚመገቡትና የሚለምኑት በጋራ ነው።በቆሎ
ተማሪዎች ዘንድ ለራሱ ሳይሆን ለሌላ ቅድሚያ መስጠት እርስ በርስ መከባበር የመሳሰሉት በጉልህ
የሚንጸባረቁ ባህርያት ናቸው።ከነዚህም መካከል ለዓካል ጉዳተኛና አዲስ ለሚመጡ ተማሪዎች የሚደረጉ
ድጋፎች ይጠቀሳሉ።

5.8.1.የእርስ በርስ መማማር


በቆሎ ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኘው አንድ መምህር ብቻ ነው።አንድ ብቻ ከመሆኑ ጋር በተያያዘም

ብዙውን ጊዜ በአውቀቱ የተሻለ ተማሪ እየተመረጠ መምሀሩን በመቀበል ለሌሎች ተማሪዎች

ያስተላልፋል።ከተማሪ አስረዲና በተገኘ መረጃ መሰረት መምህሩ አቅማቸው ደከም የለምከሆነ የተመረጠውን

ተማሪ እንደ አፍ ማጉያ ይጠቀሙበታል።ተማሪውም ያለምንም መሰልቸት ከመምህሩ በመቀበል ድምጹን ከፍ

በማድረግ ለጓደኞቹ ያስተላልፋል።በዚህም መሰረት አንድ ተማሪ ሲማር ፤ዳዊት ሲደግም፤ዜማ ሲያወርድ

ወይም ቅኔ ሲዘርፍና ሲናገር ሌሎች ተቀምጠው ያዳምጣሉ፤ ይመለከታሉ፡፡ይህምየሚሆነው በእያንዳንዱ

ጉባኤ ላይ ጀማሪዎችም ሆኑ ነባር ተማሪዎች በአንድ ላይ ስለሚማሩነው።በቅኔ ቤት

ቅኔዘራፊቅኔ(ሀ)ብሎየመጀመሪያው ተማሪቅኔሲናገር መፍራት አይጠበቅበትም ።አንዱ ከአንዱ ይማራብለው

ያምናሉ።ጀማሪ ተማሪዎች ከእነሱ በእውቀት የሚበልጧቸውን ቁጭ ብለው መከታተላቸው ያላቸውን

መከባባር የሚያሳይ ነው።ምልከታን እንደ አንድ የማስተማሪያ ዘዴ ይጠቀሙበታል።ምልከታው

እውቀታቸውን ለማጠናከር ተራቸው ደርሶ እነሱም አንድ ተማሪ በትምህርት እኩል ደረጃ ላይ ያለውን

ተማሪሲመለከት እርሱም በመንፈሳዊ ቅናት ተነሳስቶ የተሻለ ሆኖ ለመገኘት ይጥራል።ወይም ደግሞ አንድ

23
,

ተማሪ በእውቀት ከሱበታች የሆኑትን አልፎት የመጣንትምህርት ሲመለከት ያለፈውን ክፍተቱን ለመሙላትና

አዲስ ካለም እራሱን ለመገንባት ይረዳዋል።

የመምህሩ ስራ የሚሆነው ተማሪዎቹ እርስ በርሳቸው ሲማማሩ ያልተግባቡትን እርማት መስጠት

ይሆናል።ከላይ እንደተጠቀሰው በማህበረ ቅኔ የተሻለ እውቀት ያለው ተማሪ በግዕዝ የተነገረውን በአማርኛ

እየፈታ ይናገራል።ቅኔ ተቀባዩም ቅኔውን እየተቀበለ ለጉባኤው ይናገራል።ሁሉም ተማሪዎች ያልገባቸውን

በቅኔ ተቀባዩ በኩል ይጠይቃሉ።ይከራከራሉ፡፡ ቅኔ ተናጋሪውን ተማሪ ሲከራከሩት ከቆዩ በኋላ ጉባኤው በጋራ

ድምጽ(ይበል ነው)በማለት ያበረታቱታል።ቅኔ የሚናገረው ጥሩ ነገር ባያቀርብና ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ

የማበረታቻ ሃሳብ በማቅረብ ጉባኤው ይበተናል።ከዚህ በመነሳት እርስ በእርስ የመማማር ልምዳቸውን

መረዳት ይቻላል።

5.8.2. ለአካል ጉዳተኛ ተማሪ የሚደረግ ድጋፍ


የአካል ጉዳተኛ እንደሌሎች ተማሪዎች ከሃገር ሃገር አይዘዋወሩም።አንድ ጊዜ በአረፉበት
ለረጅምጊዜስለሚቆዩና በጉባኤው በደንብ ስለሚታወቁ ሁሉም ተማሪዎች ይንከባከቧቸዋል።ጉዳታቸው ከባድ
(ለመንቀሳቀስ) የሚያስቸግራችው ከሆነ ውሃ ከወንዝ በመቅዳትና ለምኖ ምግብ በመስጠት
ያግዟቸዋል።ጉዳታቸው ቀለል ያለና በእንተ ስማ ለማርያም ብለው ለምነው መምጣት ከቻሉ በመንደር
ድልድሉ ጊዜ ቀረብ ያለ ቦታ ይሰጣቸዋል።የጥገኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው በጋራ ጎጆ ይቀይሱላቸዋል።

የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የቱንም ያህል ቢሆኑም በጉባኤ ላይ የመገኘት ግዴታ አለባቸው በዚህን ጊዜም
ቢሆን የተለየ እገዛ ይደረግላቸዋል።በጉባኤው ላይም የሚመቻቸውን ቦታ በማዘጋጀት ሲመጡ ቦታ በመልቀቅ
ይንክባከቧቸዋል።

5.8.3. የአዲስ ተማሪ አቀባበል


ከመሪጌታ ነብዩ በተገኘ መረጃ መሰረት ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያት ከአንድ ጉባኤ ወደ ሌላ ጉባኤ ሊዘዋወሩ
ይችላሉ።አድካሚ የእግር ጉዞ በማድረግ ከጉባኤ ወደ ጉባኤ ቤት ይዘዋወራሉ።አንዱን ጉባኤ ትተው
የሚሄዱበት ምክንያት አንዱን የትምህርት ደረጃ ጨርሰው ወደ ሌላ ሲተላለፉ ነው።የንባብ ቤትን ትምህርት
የጨረሰ ተማሪ የዜማ መምህር ፍለጋ፤የዜማን ትምህርት ያጠናቀቀ የቅኔ መምህር ፍለጋ ጉባኤ ይቀይራል።ይህ
ጊዜበህይወታቸው ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ምክንያቱም ከደረጃ ደረጃ የሚዘዋወሩበት (የሚያድጉበት) ስለሆነ
ነው፡፡

ሁለተኛው ምክንያት በራሳቸውበተማሪዎቹ በግል ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡አንድ ተማሪ ከቅኔ ቤት ወደ ቅኔ


ቤት ወይም ከዜማ ቤት ወደ ዜማ ቤት ሊዘዋወር ይችላል፡፡ ይህንን የጉባኤለውጥ የሚያደርጉት የተሻለ
መምህር ፍለጋ ሲሉ የሚያደርጉት ዝውውር ነው፡፡ይህንንም ሲያደርጉ የተለያዩ ምክንያቶችን ይጠቅሳሉ።

24
,

ምዕራፍ ስድስት:ማጠቃለያ እና የመፍትሔ ሃሳብ


6.1. ማጠቃለያ
በሀገራችን የቆሎ ተማሪዎች ታሪክ ብዙ ዘመን ያስቆጠረ ነገር ግን የእድሜውን ያህል ብዙ ጥናት ያልተደረገበት
ነው፡፡ ከዚህ በመነሳትም በሞጣ ከተማ በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የሚገኙ የቆሎ ተማሪዎች ሕይወት
ምን እንደሚመስል ለማሳየት ይህ ጥናት ተካሂዷል፡፡ ለጥናቱ ግብዓት የሆኑ መረጃዎችም በምልከታና በቃለ
መጠይቅ ተሰብስበው በገላጭና ትንተናዊ በሆነ መልኩ ተዳስሰው ቀርበዋል፡፡

ይህ ጥናት እንደሚያመለክተው የቆሎ ተማሪዎች ተለይተው የሚታወቁባቸው እና የእነሱ መገለጫዎች የሆኑ


አያሌ የሕይወት ተሞክሮ አሏቸው፡፡ ማንኛውም የቆሎ ተማሪ የንባብ ቤት ትምህርቱን ካጠናቀቀና ወደ ሌላ
ደረጃ መሄድ ከፈለገ የግድ አድካሚና እልህ አስጨራሽ ጉዞን እንሚያደርግ ጥናቱ ያሳያል፡፡ ይህንን የሚደርጉትም
የራሳቸው የሆነ ምክንያት ስላላቸው ነው፡፡ ከቤተሰብ ርቀው ሙሉ ሰዓታቸውን ለትምህርት ለማዋል፤
ከቤተሰብ ጋር በምቾት እየተኖረ ትምህርት በቀላሉ አይገባም ብሎ ከማመን የተነሳ እንደሆነ ጥናቱ አሳይቷል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ማንኛውም ተማሪ ከቤተሰቦቹ ተነጥሎ ከሄደ በኋላ በመጀመሪያ የሚወስደው እርምጃ
ስሙን መቀየር ነው፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት ከቤተሰብ ለመደበቅ፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ በመነሳት፣ አለማዊ
ስማቸውን ከአለማዊ ግብራቸው ጋር መተዋቸውን ለማመልከት መሆኑን ይህ ጥናት አሳይቷል፡፡

በዚህ ጥናት እንደተገለፀው በተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ጊዜ ልመና ተለይተው የሚታወቁበት


ተግባራቸው ነው፡፡ ልመናቸውም የራሱ የሆነ ደንብና ስርዓት አለው፡፡ ይህ የልመና ደንብና ስርዓታቸውም
ከሌሎች በልመና ከሚተዳደሩ ሰዎች ተለይተው እንዲታወቁ አድርጓቸዋል፡፡ የልመና ስርዓታቸውም ዘፈቀዳዊ
ሳይሆን ከዕምነት ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ማህበረሰቡ ለልመና እና ለተማሪዎች ያለው አመለካከት ሁለት አይነት
መሆኑን ይህ ጥናት ያሳያል፡፡ በአንድ በኩል ያሉት ወገኖች ተማሪ ሲለምን መስጠት የፅድቅ ምልክት ነው፡፡
ተማሪዎች መለመናቸውም ለማህበረሰቡ በረከት ያስገኛል ብለው አምነው የተቀበሉ የማህበረሰብ ክፍሎች
ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ ለተማሪዎች የሚሰጡት ከፍርሀት ጋር በተያያዘ እንጂ ተማሪዎች የፅድቅ ምልክቶች
ሳይሆኑ ክፉ ነገር የሚያደርጉና ሰይጣናዊ ስራ የሚሰሩ አድርገው የሚቆጥሯቸው አሉ፡፡

ሌላው የቆሎ ተማሪዎች በተለያዩ ቦታዎች በሚዘዋወሩበት ጊዜ የተለያየ ገጠመኝ አላቸው፡፡ ይህንን
ገጠመኛቸውን እንዴት እንደሚገልጹ በዚህ ጥናት ታይቷል፡፡

25
,

6.2. የይሁንታ ሀሳብ


ይህ የቆሎ ተማሪዎች ልማዳዊ የህይወት እይታ ከሐይማኖታዊ ይዘትነቱ ባሻገር በውስጡ ልዩ ልዩ ማህበራዊ
ጉዳዮችንና እሴቶችን የያዘ ነው፡፡ በመሆኑም ከሚቀርብበት አውድና ሁኔታ ሥራ ጥናት ቢደረግበት መልካም
ነበር፡፡ እስካሁንም በተወሰኑ አካባቢዎች ብቻ የሚከነውነውን በስፋት እንዲሰራበት ልዩ ልዩ አካላት የራሳቸውን
አስተዋፅኦ ቢያደርጉ መልካም ነው፡፡ በተጨማሪም ቀደም በስፋት ይከናወን የነበረው የቆሎ ተማሪ የህይወት
እይታን በልዩ ልዩ ምክንያቶች እየተዳከመ መጥቷል በመሆኑም የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው
ተጠናክሮ የሚቀጥልበት መንገድ ቢመቻች ጥሩ ነው፡፡ የቀሎ ተማሪ ህይወት ከህይወቱ በስተጀርባ ያሉ በጥናቱ
ውስጥ የተዳሰሱትም ይሁን ያልተዳሰሱት በልዩ ልዩ አካባቢዎች ያሉትን በስራው ጥናት ተደርጎባቸው
አለማቀፋዊ ዕውቅና ተሰጥቷቸው ሁሉም አካላት እንዲያውቁት ቢደረግ መልካም ነው እላለሁ፡፡

አባሪዎች
አባሪ አንድ

አንድ ተማሪ ቅኔ ለመቁጠር ሁልጊዜ የሚሄድበት ዘወር ያለ ስፍራ ነበር፡፡ነገር ግን ውሃ ለመጠጣት ወይም ሽንት
ቤት ለመጠቀም ሲነሳ አንዲት ጦጣ ወረቀቱን እየቀደደች እሱ ሲያደርግ የተመለከተቸውን ሁሉ ለማድረግ
እያለች ትረብሸው ነበር፡፡ ይህንን የተመለከተው ተማሪ አንድ ቀን ቢላዋ ይዞ ይመጣል ቁጭ ብሎ ይቆይና ውሃ
ለመጠጣት ዕቃውን አስቀምጦ ሲሄድ ቢላዋውን ያነሳና በደንደሱ በኩል አንገቱን የሚቆርጥ መስሎ ይገዘግዛል፡

26
,

፤ይህንን ስትመለከት የቆየች ጦጣም ቢላዋውን ታነሳና በስለቱ በኩል የገዛ አንገቷን ቆርጣ እዛው ላይ ሞታ
አገኛት” ተማሪ ጦጣንም በለጠ ተብሎ ይወራል፡፡

አባሪ ሁለት

አንድ የንስሃ አባቱን ሚስት እሁድ እሁድ እየጠበቀ የለመደ ተማሪ ነበር፡፡የንስሀ አባቱም እሁድ እሁድ
ከቤተክርስቲያን ቀርተው አያውቁም ተሜም እሁድን እየጠበቀ የልቡን ያደርሳል፡፡አንድ ቀን ሰውው ከመንገድ
የህመም ስሜት ተሰምቷቸው ይመለሳሉ፡፡እነተሜም ሳያስቡት ሲደረስባቸው ደንግጠው ተማሪው ከአልጋ ስር
ይገባል፡፡ባልና ሚስትም ገንፎ አገንፍተው ሲበሉ ሚስት ለአዋዩ እያለች ወደ አልጋ ስር ትወረውራለች በዚህ
ጊዜ የወረወረችው ትኩስ ገንፎ በተማሪው መቀመጫ ላይ ይለጠፋል ትኩስ ገንፎ ያቃጠለው ተማሪም
አልጋውን ከነሰውየው ገልብጦ ወጥቶ ይሮጣል ሚስትም በስመ አብ በሉ መምሩ ሰይጣን እኮ ነው አለች
ይባላል፡፡
አባሪ ሶስት

ከዕለታት አንድ ቀን የቆሎ ተማሪ የእግዜር እንግዳ ብሎ ወደ አንድ መንደር ጎራ ይላል እነሱም ቤት
የእግዚአብሔር ነው ግባ ብለው ይቀበሉታል፡፡ ነገር ግን እራታቸውን ዶሮ ወጥ ሰርተው ነበርና ተሜ እንዳይበላ
ሰስተው ሽሮ ይሰጡትና እነሱም ቀማምሰው ይተኛሉ፡፡ተሜም ሽሮውን ይበላና ይተኛል፡፡ሰዎቹም አንድ ቀበኛ
ጥጃ ስላለች ልብስህን እንዳትበላብህ ብለው ደህና ልምጭ ይሰጡትና በዚህ በላት ይሉታል፡፡ ተሜም የዶሮ
ወጡ ሽታ እንቅልፍ ሲያሳጣው ከተኙ በኋላ ቀስ ብሎ ተነስቶ ጥስቅ አርጎ ይበላና ተመልሶ ይተኛል፡፡
ባለቤቶቹም ተሜ ተኝቷል ብለው ሲነሱ ድስቱ ባዶውን ቀርቷል በዚህ ጊዜ ሴትዮዋ ቆይ ተሜ በልቶት ይሆናል
ብላ አፉን ልታሸት ጎንበስ ስትል ጌታው ኧረ ያሏት ጥጃ መጣች በማለት ሴትዮዋን በያዘው ልምጭ ለምጦ
መለሳት ይባላል፡፡

አባሪ አራት

ከዕለታት አንድ ቀን ተሜ ለልመና ይሄድና አንድ ቤት ሲደርስ በእንተ ስማ ለማርያም ይላል፡፤በዚህን ጊዜ የቤቱ
ባለቤት ትወጣና እቤት ውስጥ ምንም ነገር የለም ቁጭ ብዬ ብቻ ነው ያለው ቁጭ ብዬ ልስጥህ ትለዋለች ቁጭ
ብዬ የእህል አይነት ነው፡፡ ተሜም እመቤቴ ካሉስ ተኝተው ቢሰጡኝ ይሻላል አለ ይባላል፡፡
አባሪ አምስት

አንድ የቆሎ ተማሪ ለልመና ይወጣል ከአንድ ቤት ደረሰም በእንተ ስማ ለማርያም ብሎ ሲለምን የቤቱ ባለቤት
እንጀራ በአኩፊዳው እየከተተች ሀገርህ ወዴት ነው ስትለው እሱም ከእነማይ ይላታል፡፡ እሷም ከሰማይ ብላ
ትጠይቀዋለች ተሜም ምን ለማለት እነደፈለገች ለማወቅ ፈልጎ ነገሩን ገልበጥ አድርጎ አዎ ይላታል፡፡እሷም
እናትና አባቷ ሞተው ስለነበር ተሜ አባቴን አግኝተሀቸዋል ብላ ትጠይቀዋለች እሱም ደህና ናቸው
የሚለብሱት አልቆባቸዋል ይላታል፡፤እሷም በጣም እያዘነች የባሏን ልብሽ ለአባቷ የእሷን ልብስ ለእናቷ
በጨርቅ ቋጥራ ሰጠችው፡፡ ተሜ ይህን ተሸክሞ እብስ ይላል፡፡ ከቆይታ በኋላ ባሏ ከስራ ይመጣና ልብስ ሲቀይር

27
,

ሲሞከረው ልብሶቹ የሉም፡፡ የት ሄደ ልብሱ ብሎ ሲጠማቀት ሁሉንም ትነግረዋለች፡፡ ባልም በሁኔታው ተናዶ
የቆሎውን ጭኑ እየጋለበ ተማሪውን ፍለጋ ይሄዳል፡፡ ትንሽ ሄድ እንዳለም ተማሪውን ያገኘዋል፡፡ ተማሪም ከሩቅ
አይቶት ኖሮ ከረጢቱን ወደ አጥር ስር መወረወርና መንገዱን ይቀጥላል፡፡ ሰውየውም አሁን በዚጅ በኩል አንድ
ተማሪ ሲያልፍ አየህ ብሎ ይጠይቀዋል፡፡ ተማሪውም አዎን ጌታዬ አሁን እየሮጠ አለፈ ነገር ግን ቁልቁለት
ስለሆነ በቅሎዎ እሺ አትለውትም ይላል፡፡ ሰውየውም እባክህ ጠብቅልኝ ብሎት በእግር መሮጥ ጀመረ፡፡
ተማሪው እሽ ብሎ በቅሎዋን ይቀበልና ስምህ ማነው ሲባል የአሁኑ ይባስ ብሎት በበቅሎው እየጋለበ ሄደ
ይባላል፡፡

መረጃ አቀባዮች

ስም ጾታ ዕድሜ ሙያ መረጃው መረጃው የተሰበሰበበት ቀን

ቄስ/ሐይማኖት አጋዥ ወ 42 ለ 10 ዓመታት ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ጥር 12፣13 እና 16/2014 ዓ/ም


በቅዳሴ ያገለገሉ ክርስቲያን

መሬጌታ ዐይነ ኩሉ ወ 53 የደብሩ መርጌታ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ይካቲት 7 እና 8/2014 ዓ/ም


ደባስ ክርስቲያን

መዘምር እዝራ ወ 46 መዘምር ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ይካቲት 11 እና 12/2014 ዓ/ም


ማህሪዉ ክርስቲያን

መዘምር ህሩይ ማኔ ወ 45 መዘምር ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ታህሳስ 19፣23/2014 ዓ/ም


ክርስቲያን
ዲያቆን ዘላላም ወ 25 የዜማ ተማሪ ቅዱስ ገብርኤል መጋቢት 24 እና 25/2014 ዓ/ም
አዱኛዉ ቤተ ክርስቲያን

ዲያቆን ተመስገን ወ 28 የቅኔ ተማሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዚያ 30 2014 ዓ/ም

28
,

በላቸዉ ቤተ ክርስቲያን

አቶ ሐብቱ ተዘራ ወ 40 ነጋዴ ቅዱስ ጊዮርጊስ ማያዚያ 12፣16 እና 17


ቤተ ክርስቲያን /2014 ዓ/ም

ዋቢ ጽሁፎች
ሀብተ ማርያም ወርቅነህ፡፡ (1963)፡፡ ጥንታዊ የኢትዮጵያ ትምህርት፡፡ አዲስ አበባ ፣

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፡፡

ሚስጥር ሰዋሰው፡፡ (1974)፡፡"ጥንታዊ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት"፡፡ የዲግሪ ማሟያ

ጽሁፍ፡፡ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፡፡

በላይነህ ደሴ፡፡ (1999)፡፡"የቅኔ ቆጠራ ነገራና ዘረፋ በተመረጡ የጎጃም ጉባኤዎች"፡፡

የዲግሪማሟያ ጥናታዊ ጽሁፍ፡፡ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ፡፡

ቴወድሮስ ገብሬ፡፡(2011)፡፡በይነ ዲሲፕሊናዊ የስነ ፁሁፍ ንባብ፡፡አዲስ አበባ ፕሬስ፡፡

አምሃ ኢየሱስ አሰፋ፡፡(1994)፡፡"መንፈሳዊ ትምህርት ቤት (ቄስ ትምህርት ቤት )"፡፡የድግሪማሙያ ጽሁፍ ፡፡


ያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት ፡፡

ኪዳነ ማርያም ጌታሁን፡፡(1980)፡፡ጥንታዊ የቆሎ ተማሪ፡፡አዲስ አበባ ፣ትንሳኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት፡፡

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር፡፡(2000)፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ የብሉይና የአዲስ ኪዳን

መፅሐፍት፡፡ አዲስ አባባ ፣ የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማህበር፡፡

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል፡፡(1992)፡፡ የአማርኛ መዝገበ ቃላት፡፡

አዲስ አበባ ዩነቨርሲቲ፡፡

29
,

ገዛኸኝ ጌታቸው፡፡" የአብነት ትምህርት ቤቶች በዘመናዊ ትምህርት እድገትና በሀገር


አስተዳደር ያደረጉት አስተዋጽኦ"በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የሰንበት
ትምህርት ቤቶች ማደራጃና መምሪያ ባዘጋጀው አውደ ጥናት ላይ የቀረበ፡፡ (አመተ
ምህረት ያልጠቀሰ)፡፡
ፈቃደ አዘዘ፡፡(1991)፡፡ ስነ ቃል መምሪያ፡፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ማተሚያ ድርጅት፡፡

Almayhu Moges.(1971) .“ the traditional church education”. Addis Ababa. Hile Selassie

University.

Ben Amas Dan. “ To words a definition of fulklurs in context”. Journal of American folklore.

Embakom Kale weled.Translatedby mengistu lemma. (1970). Traditional Ethiopian

education. New York Colombia university.

Finnegan, Ruth. (1972). Oral tradition and the verbal arts a guide to research practices.

London, Rutledge.

Pankhursk, Richard. (1966).Ethiopian church, state and education in Africa. Scanlon

David G. New York teachers college press.

30
,

የቆሎ ተማሪዎች የህይወት ዕይታበሚለው ርዕስ ለሚደርገው ጥናት የቀረበ ቃለመጠይቅ

1. የቆሎ ተማሪ በብዛት አካባቢው ለቆ በሌላ የሚማርበት ምክንያት ምንድን ነው፡፡ በአካባቢያችሁ
ሆናችሁ ብትማሩ ምን ችግር አለው?
2. ስማችሁን የምትቀይሩበት ምክንያት ምንድነው?
3. በምትማሩበት ወቅት ትለምናላችሁ ባትለምኑስ ሳትለምኑ መማር አትችሉም?
4. እርስ በርሳችሁ በምን በምን ነገሮች ትረዳዳላችሁ?
5. አካል ጉዳተኛ ተማሪ በመካከላችሁ ቢኖር ምን አይነት ድጋፍና እንክብካቤ ታደርጉለታላችሁ?
6. በትምህርት ቤት ቆይታችሁ ለየ የትምህርት ወቅት አለ ካለስ የተመጣበት የራሱ የሆነ ምክንያት
ይኖረው ይሁን?
7. አዲስ ለሚመጣ ተማሪ የሚደረግ አቀባበል በምን ምልኩ ነው?

31

You might also like