You are on page 1of 34

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት


መረጃና መዛግብት ክፍል

የአፈጻጸም መመሪያ

በመረጃና መዛግብት ክፍል የተዘጋጀ

ሰኔ 2013 ዓ.ም

መክሥተ ዘአርእስ
መቅድም................................................................................................................................................I

መግቢያ................................................................................................................................................II

1. የሰንበት ትምህርት ቤቱ ርዕይ....................................................................................................................1

2. የክፍሉ ዓላማ....................................................................................................................................2

3. ስያሜ............................................................................................................................................3

4. መበይነ ቃላት....................................................................................................................................4
5. ተጠሪነት.........................................................................................................................................5

6. አባልነት.........................................................................................................................................6

6.1. ለክፍሉ አባልነት የሚያበቁ ሁኔታዎች....................................................................................................6


6.1.1. መደበኛ የክፍሉ አባል.............................................................................................................6
6.1.2. ተሳታፊ የክፍል አባል.............................................................................................................6
7. ለሥራ አሥፈጻሚነት የሚያበቁ ሁኔታዎች.......................................................................................................7

8. የአባልነት መብት እና ግዴታ.....................................................................................................................8

8.1. የአባላት መብት...........................................................................................................................8


8.1.1. የመደበኛ የክፍሉ አባል መብት...................................................................................................8
8.1.2. ተሳታፊ የክፍሉ አባል መብት.....................................................................................................8
8.2. የአባላት ግዴታ...........................................................................................................................8
8.2.1. መደበኛ የክፍሉ አባል ግዴታ.....................................................................................................8
9. የክፍሉ አባልነት የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች.....................................................................................................9

9.1. የመደበኛ የክፍሉ አባል...................................................................................................................9


9.2. ተሳታፊ የክፍሉ አባል.....................................................................................................................9

10. በድጋሚ አባል ስለመሆን...................................................................................................................10

11. የስብሰባና የምርጫ ሥነ-ሥርዓት..........................................................................................................11

11.1. ስብሰባ.................................................................................................................................11
11.1.1. የአጠቃላይ የክፍሉ አባላት ስብሰባ.............................................................................................11
11.1.2. የክፍሉ ሥራ አሥፈጻሚ ስብሰባ................................................................................................11
11.1.3. የንዑስ ክፍላት ስብሰባ..........................................................................................................12
11.2. ምርጫ.................................................................................................................................12
11.2.1. በምርጫ ላይ የክፍሉ ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት..........................................................................12
11.2.2. የምርጫ ሥነ ሥርዓት..........................................................................................................13
12. የክፍሉ መዋቅር፣ ተግባርና ኃላፊነት........................................................................................................14

12.1. ተግባርና ኃላፊነት......................................................................................................................14


12.1.1. የክፍሉ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት..............................................................................................14
12.1.2. አጠቃላይ የክፍሉ አባላት ተግባርና ኃላፊነት....................................................................................15
12.1.3. የክፍሉ ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት.........................................................................................15
12.1.4. የንዑስ ክፍል ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት..........................................................................................15
12.1.5. የዘርፍ ተጠሪ ተግባርና ኃላፊነት................................................................................................16
12.1.6. የክፍሉ አባል ተግባርና ኃላፊነት................................................................................................16
13. የጽሕፈት ቤትና የንዑሳን ክፍላት አወቃቀር፣ ተግባርና ኃላፊነት............................................................................17

13.1. የመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት................................................................................................17


13.1.1. ስያሜ...........................................................................................................................17
13.1.2. ተጠሪነት.......................................................................................................................17
13.1.3. መዋቅር.........................................................................................................................17
13.1.4. የመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት.....................................................................17
13.1.5. የዋና ሰብሳቢ ተግባርና ኃላፊነት................................................................................................18
13.1.6. የምክትል ሰብሳቢ ተግባር እና ኃላፊነት.........................................................................................19
13.1.7. የዋና ጸሐፊ ተግባር እና ኃላፊነት................................................................................................19
13.1.8. የምክትል ጸሐፊ ተግባር እና ኃላፊነት...........................................................................................19
13.2. የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል.....................................................................................................20
13.2.1. ስያሜ...........................................................................................................................20
13.2.2. ተጠሪነት.......................................................................................................................20
13.2.3. መዋቅር.........................................................................................................................20
13.2.4. የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት.................................................................20
13.2.5. የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተጠሪ......................................................................................20
13.2.6. የድኅረ-ገጽ መረጃ ሥርጭትና ቁጥጥር ዘርፍ...................................................................................21
13.2.7. የድኅረ-ገጽ ልማት ዘርፍ........................................................................................................21
13.3. የቤተ-መዛግብት አስተዳደር ንዑስ ክፍል...............................................................................................23
13.3.1. ስያሜ...........................................................................................................................23
13.3.2. ተጠሪነት.......................................................................................................................23
13.3.3. መዋቅር.........................................................................................................................23
13.3.4. የቤተ-መዛግብት አስተዳደር ንዑስ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት............................................................23
13.3.5. የቤተ-መዛግብት አስተዳደር ተጠሪ.............................................................................................23
13.3.6. የቤተ-መጻሕፍት አስተዳደር ዘርፍ..............................................................................................24
13.3.7. የመዛግብት አስተዳደር ዘርፍ....................................................................................................24
13.3.8. የንብረት ቁጥጥር ዘርፍ.........................................................................................................25
13.4. የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል........................................................................................................26
13.4.1. ስያሜ...........................................................................................................................26
13.4.2. ተጠሪነት.......................................................................................................................26
13.4.3. መዋቅር.........................................................................................................................26
13.4.4. የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተግባርና ኃላፊነት..............................................................................26
13.4.5. የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተጠሪ..........................................................................................27
13.4.6. የመረጃ ክምችት ዘርፍ..........................................................................................................27
13.4.7. የመረጃ ማደራጀት ዘርፍ........................................................................................................28
13.4.8. የመረጃ ሥርጭት ዘርፍ.........................................................................................................28
13.4.9. የንብረት ቁጥጥር ዘርፍ.........................................................................................................28
14. ሒሳብና ንብረትን በተመለከተ.............................................................................................................30

14.1. ሒሳብን በተመለከተ...................................................................................................................30


14.2. ንብረትን በተመለከተ...................................................................................................................30
15. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች........................................................................................................................31

15.1. የተፈጻሚነት ወሰን.....................................................................................................................31


15.2. ስለ አፈጻጸም መመሪያው መሻሻል......................................................................................................31
15.3. የአፈጻጸም መመሪያው የበላይነት.......................................................................................................31
15.4. የጾታ አገላለጽ..........................................................................................................................31
15.5. የአፈጻጸም መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ.................................................................................................31
መቅድም

እናታችን የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሕገ ልቦና፣ በሕገ ኦሪትና ሕገ ወንጌል ጸንታ
ለኖረችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እንደ አለት የጸናች የእምነት ተቋም፣ የጥበብ መገኛ፣ የሕግ መፍለቂያና
የማኅበራዊ ኑሮ መሠረት ሆና በሕዝቡና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ግንኙነት ስትመራ የኖረች ስንዱ
እመቤት መሆኗን የታሪክ ሊቃውንት ዘግበውት የሚገኝ የተገለጠ እውነት ነው፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ ለቅዱስ ጴጥሮስ በጎቼን፣ ጠቦቶቼንና
ግልገሎቼን ጠብቅ ባለው ቃል መሠረት በጎች ለተባሉ ምዕመናን ሰበካ ጉባኤን፣ ጠቦቶችና ግልገሎች ለተባሉ
ሕፃናትና ወጣቶች ደግሞ ሰንበት ትምህርት ቤትን መሥርተው መንፈሳዊ አገልግሎት ሳይታጎል እንዲቀጥል
አድርገዋል፡፡ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤትም የዚህ
መንፈሳዊ ዛፍ አንድ ፍሬ ነው፡፡

መግቢያ

i
674834749.docx
“ናሁ ሰናይ ወናሁ አዳም ሶበ ይሄልዎ አኃው ኅቡረ” “እነሆ ወንድሞች በአንድነት ቢቀመጡ መልካም
ነው እጅግም ያማረ ነው” እንዲል የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን
ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል። ቲቶ
፪፥፪-፫
ለፍቅርና ለመልካም ሥራ እንድንነቃቃ እርስ በእርሳችን እንተያይ በአንዳንዶችም ዘንድ እንደሆነው
መሰባሰባችንን አንተው እርስ በእርሳችንም እንመካከር እንጂ ይልቁንም ቀኑ ሲቃረብ እያያችሁ አብልጣችሁ
ይህን አድርጉ፡፡ ዕብ ፲፥፳፬-፳፭
የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት በ፲፱፻፶፱
ዓ.ም ለመንፈሳዊ አገልግሎት ይፋጠኑ በነበሩ አባቶች የተመሠረተ ሲሆን ባለፉት ፶፪ ዓመታት ለመንፈሳዊ
አገልግሎት የሚተጉ በሺዎች የሚቆጠሩ የቤተክርስቲያን ልጆችን ሲያፈራ ቆይቷል።
ይህ የአፈጻጸም መመሪያ በ፪፼፲ ዓ.ም የጸደቀውን የሰንበት ትምህርት ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ
መሠረት አድርጎ ሕይወት ተኮር አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ተደርጎ ለመረጃና መዛግብት ክፍል
የተዘጋጀ ነው፡፡
ደንቡ ሁለት ዓበይት ክፍሎች ያሉት ሲሆን የመጀመሪያው ዐቢይ ክፍል ስለ ጠቅላላ ደንቡ ያትታል ፣
ሁለተኛው ዐቢይ ክፍል ደግሞ በመረጃና መዛግብት ክፍል ውስጥ ስለሚኖሩት ዐበይት የአገልግሎት ክፍሎች
አወቃቀር፣ ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም በክፍሉ ውስጥ የሚገኙ አባላት መብትና ግዴታ ወዘተ የሚያብራራ
ነው፡፡

ii
674834749.docx
1. የሰንበት ትምህርት ቤቱ ርዕይ

ቅዱሳን አባቶች ጠብቀው ያስረከቡንን የቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት አክብሮና አስከብሮ
ተስፋ የምናደርገውን መንግሥተ ሰማያት ለመውረስ የሚያበቃ የጸና ሃይማኖትና ምሳሌ የሆነ ምግባር ይዞ
የሚገኝ ጥበበኛ ትውልድን የሚያፈራ ሰንበት ትምህርት ቤት ተፈጥሮ ማየት።

2. የክፍሉ ዓላማ

1
674834749.docx
 የቤተክርስቲያንንና የሰንበት ትምህርት ቤቱን የመረጃ ሀብቶች እያሰባሰበ፤ እያደራጀና እየተንከባከበ የመጠበቅ፤
ለጥናትና ምርምር እንዲሁም ለማገናዘቢያ አገልግሎት ማቅረብ

3. ስያሜ

ክፍሉ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት
መረጃና መዛግብት ክፍል ተብሎ ይጠራል፡፡

2
674834749.docx
4. መበይነ ቃላት

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ የአፈጻጸም መመሪያ ውስጥ፡-
ሀ. “ቤተ-ክርስቲያን” ማለት የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ነው።

3
674834749.docx
ለ. “ሰንበት ትምህርት ቤት” ማለት የደብረ ብሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን
ሰንበት ትምህርት ቤት ነው።

ሐ. “መረጃና መዛግብት ክፍል” ማለት የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት መረጃና መዛግብት
ክፍል ነው።

መ. “ሥልጠና” ማለት መረጃና መዛግብት ክፍል ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሥልጠና ነው።

ሠ. “የክፍል አባላት” ማለት የትምህርትና ሥልጠና ክፍል አባላት ነው።

ረ. “የሥራ አስፈጻሚ” ማለት ክፍሉን በበላይነት የሚመሩ የመረጃና መዛግብት ክፍል የጽሕፈት ቤት
አባላትና የንዑስ ክፍላት ተጠሪዎችን ነው።

ሰ. “የክፍሉ ጽሕፈት ቤት” ማለት የክፍሉን ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ፣ ጸሐፊና ምክትል ጸሐፊን
የያዘ የመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት ነው።

ሸ. “የሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት” ማለት የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ሰብሳቢ፣
ምክትል ሰብሳቢ፣ ጸሐፊና ምክትል ጽሐፊ ማለት ነው።

በ. “የክፍሉ ጠቅላላ ጉባኤ” ማለት የመረጃና መዛግብት ክፍል ጠቅላላ አባላት ጉባኤ ማለት ነው።

ተ. “የሥራ አመራር” ማለት የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የሥራ አመራር ማለት ነው።

5. ተጠሪነት

የመረጃና መዛግብት ክፍል ተጠሪነቱ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ የሥራ አመራር ነው፡፡

4
674834749.docx
6. አባልነት

6.1. ለክፍሉ አባልነት የሚያበቁ ሁኔታዎች


6.1.1. መደበኛ የክፍሉ አባል
ሀ. የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይና ዕድሜው ከ 18 ዓመት በላይ የሆነ፤
ለ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚሰጠውን ተከታታይ መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት ተከታትሎ ወደ
መደበኛ አባልነት መሸጋገሪያ የስድስት ወራት የአመክሮ ጊዜውን በአግባቡ ያጠናቀቀ፤

5
674834749.docx
ሐ. ዕድሜው ከ 16 ዓመት በላይ የሆነ እና ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚሰጠውን ተከታታይ መሠረታዊ
የሃይማኖት ትምህርት ተከታትሎ ከሕፃናት ክፍል የተዘዋወረ፤
መ. ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤቶች በበቂ ምክንያት ተዘዋውሮ የመጣ፣ ከነበረበት
ሰንበት ትምህርት ቤት መደበኛ አባል ስለመሆኑና ስለነበረው መልካም ቆይታ የሚገልጽ ከተጻፈ ፫
ወራት ያላለፈው ማስረጃ ያቀረበ፣ የተሰጠውን የአመክሮ ጊዜ በአግባቡ ያጠናቀቀ፤
ሠ. ቀደም ሲል በሰንበት ት/ቤቱ በመደበኛ አባልነት ከ 1 ዓመት በላይ የሆነ የአገልግሎት ቆይታ ኖሯቸው በቂ
በሆነ ምክንያት መደበኛ አባልነታቸው ተቋርጦ የነበረ አባላት ከነበሩበት ተመልሰው በአገልግሎት
ለመሳተፍ ሲፈልጉ ጥያቄቸውን ለሥነ-ምግባር ክፍል አቅርበው ተቀባይነት ካገኘበት ቀን ጀምሮ
እንደ መደበኛ የክፍሉ አባል ይቆጠራሉ።

6.1.2. ተሳታፊ የክፍል አባል


ሀ. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተመዝግቦ በመንፈሳዊ
አገልግሎቶች ላይ ተሳትፎ ያለው፤
ለ. በመልካም ሥነ-ምግባሩ አርአያ የሆነ፤
ሐ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ መደበኛ አባል ሳይሆን የሰንበት ትምህርት ቤቱን ዓላማ ተቀብሎ
በዕውቀቱ፣ በገንዘቡና በጉልበቱ አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሆኖ አስተዋጽኦም በመረጃና መጻግብት
ክፍሉ ጽሕፈት ቤት የተረጋገጠ፤ በጽሕፈት ቤቱ አቅራቢነት ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፍት ቤት
ቀርቦ ይሁንታ ሲያገኝ የክብር አባል ይሆናል፡፡

7. ለሥራ አሥፈጻሚነት የሚያበቁ ሁኔታዎች

ሀ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት መደበኛ አባል የሆነና አባልነቱ ያልተቋረጠ
ለ. ዕድሜው 23 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፤
ሐ. የሥራ አሥፈጻሚ ምርጫ ከመደረጉ በፊት ቢያንስ ለ፪ ዓመት በቅርበትና በትጋት በክፍሉ ያገለገለ፤
መ. በመንፈሳዊ ዕውቀት የበሰለ እና በአመራር እና በውሳኔ ሰጪነት በቂ ክሕሎት ያለው
ሠ. በንስሐ የሚመላለስና በሥነ-ምግባሩ አርዓያ መሆን የሚችል፤
ረ∙ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ውስጥ በመደበኛ አባልነት ሦስት ዓመትና ከዚያ በላይ ቆይታ ያለው፡፡
ሰ. የክፍሉን ሥራዎች ለማከናወን በቂ ጊዜ ኖሮት ኃላፊነቱን በትጋትና በብቃት ለመወጣት የሚችል፤
ሸ. በአስኳላ ትምህርት ጥሩ የትምህርት ዝግጅት ያለው።

6
674834749.docx
8. የአባልነት መብት እና ግዴታ

8.1. የአባላት መብት


8.1.1. የመደበኛ የክፍሉ አባል መብት
ሀ. ማንኛውም የክፍሉ መደበኛ አባል በክፍሉ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የመገኘት የመምረጥ፣ የመመረጥና
ስለ ክፍሉ እንቅስቃሴ መረጃ የማግኘት፤
ለ. በክፍሉ ልዩ ልዩ መዋቅሮችና አገልግሎት ውስጥ በእኩልነት የመገልገልና የማገልገል፤ መብት አለው።
8.1.2. ተሳታፊ የክፍሉ አባል መብት
ሀ. የሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥራ አመራር በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ለክብር አባላት ተለይቶ
የተቀመጡ መብቶችን የመጠቀም፤
8.2. የአባላት ግዴታ
8.2.1. መደበኛ የክፍሉ አባል ግዴታ
ሀ. የሰንበት ትምህርት ቤቱን መተዳደሪያ ደንብና የክፍሉን የአፈጻጸም መመሪያ የማክበርና የማስከበር፤
ለ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛና ልዩ መርሐ ግብራት ላይ የመገኘት፤
ሐ. በክፍሉ መደበኛና አስቸኳይ ስብሰባ ላይ የመገኘት፤
መ. ከክፍሉ የሚሰጠውን ኃላፊነት በአግባቡ የመወጣት፤

7
674834749.docx
ሠ. በክፍሉ የሚጠየቁ መረጃዎችን የመስጠትና የመተባበር፤
ረ. የክፍሉን ንብረቶች የመጠበቅና የማስጠበቅ፤
ሰ. ከቤተክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ጋር ተቃራኒ በሆኑ ድርጊቶች ተሳታፊ አለመሆን፤
ሸ. የቤተክርስቲያኒቱን ዶግማ፤ቀኖና እና ትውፊት የመጠበቅና በእነርሱም የመመራት፤
ቀ. ያለክፍሉ ፈቃድና እውቅና በክፍሉ ስም ማናቸውንም ተግባራት ያለመፈፀም፡፡

9. የክፍሉ አባልነት የሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች

9.1. የመደበኛ የክፍሉ አባል


ሀ. ሲሞት ወይም በፈቃዱ በጽሑፍ ስንብት ሲጠይቅ ፤
ለ. የታወቀ የሃይማኖት ሕጸጽ ተገኝቶበት ይህንኑ ለማረም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ በሰንበት
ትምህርት ቤቱ ሥራ አመራር ሲታገድ ወይም ሲለይ፤
ሐ. በተደጋጋሚ ከክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ውጪ የሆነ ድርጊትን በመፈጸም በተሰጠው ምክርና ተግሳጽ
ሳይመለስ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥነ-ምግባር ክፍል እገዳ ሲጣልበትና ይህም በሰንበት
ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ውሳኔ ሲሰጥ፤
መ. ያለ በቂ ምክንያትና ማስረጃ ከሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛ መርሐ-ግብርና ከክፍሉ አገልግሎት
አንድ ዓመትና ከዚያ በላይ የራቀ ከሆነ፡፡
ሠ. የሰንበት ትምህርት ቤቱን መተዳደሪያ ደንብን እንዲሁም የክፍሉን የአፈጻጸም መመሪያ
በተደጋጋሚ በመጣሱ ምክንያት ከድርጊቱ እንዲታረም የተሰጠውን ምክርና ተግሳጽ ተፈጻሚ
ሳያደርግ በድርጊቱ የቀጠለ እንደሆነ፤መደበኛ የክፍል አባልነቱ የሚቋረጥ ይሆናል።
9.2. ተሳታፊ የክፍሉ አባል
ሀ. ሲሞት ወይም በፈቃዱ በጽሑፍ ስንብት ሲጠይቅ፤
ለ. የታወቀ የሃይማኖት ሕጸጽ ተገኝቶበት ይህንኑ ለማረም ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር፤
ሐ. በተደጋጋሚ ከክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር ውጪ የሆነ ድርጊት በመፈጸሙ በምክርና ተግሣጽ
ከድርጊቱ ለመታረም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ድርጊቱ በሌሎች አባላትና ምዕመናን ላይ በጎ
ያልሆነ ተጽዕኖ የሚያሳድር ሆኖ ሲገኝና ይህም በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ውሳኔ
ሲሰጥበት ተሳታፊ የክፍል አባልነቱ ሊቋረጥ ይችላል።

8
674834749.docx
10. በድጋሚ አባል ስለመሆን

ማንኛውም የክፍል አባልነት ግዴታውን ባለመወጣት አባልነቱ እንዲቋረጥ የተደረገ ሰው በድጋሚ


የአባልነት መብቱ እንዲመለስለት ለማድረግ የሚችለው ቀደም ሲል መብቱ እንዲቋረጥ የተደረገበት ሁኔታ
መቅረቱ በሚመለከተው አካል ሲረጋገጥና የድጋሚ አባልነት ጥያቄውም በአግባቡ ተመርምሮ በሰንበት
ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ተቀባይነት ሲያገኝ ብቻ ነው።

9
674834749.docx
11. የስብሰባና የምርጫ ሥነ-ሥርዓት

11.1. ስብሰባ
11.1.1. የአጠቃላይ የክፍሉ አባላት ስብሰባ
ሀ∙ አጠቃላይ የክፍሉ መደበኛ ስብሰባ በወር አንድ ጊዜ ይሆናል፡፡
ለ. አስቸኳይ ወይም አጠቃላይ የክፍሉ ውሳኔና እውቅና የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙ
በክፍሉ ሥራ አሥፈጻሚ ወይም ከጠቅላላው መደበኛ የክፍሉ አባላት በ 1/3 ኛው ጥያቄ አቅራቢነት
ከእነዚህ በአንዳቸው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል።
ሐ. የጉባኤው ውሳኔዎች የሚተላለፉት በስምምነት ሲሆን በዚህ መልኩ ውሳኔውን ማስተላለፍ
ካልተቻለ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔው እንዲተላለፍ ይደረጋል። እኩል ድምጽ ሲኖር ሰብሳቢው
የደገፈው ሀሳብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
መ. በአጠቃላይ የክፍሉ አባላት ከመደበኛ አባላቱ ሃምሳ በመቶ /50%/ በላይ ሲገኙ ምልዐተ ጉባኤ
ይሆናል፣ ይህ ሳይሟላ ከቀረ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ሁለተኛ ጥሪ ተደርጎ በአግባቡ
ለአባላት መድረሱ ሲረጋገጥ ለስብሰባው በተያዘው አጀንዳ ላይ ብቻ በዕለቱ በተገኙ አባላት ውሳኔ
እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡
ሠ. ስብሰባው የዕለቱ ስንክሳር፣ የሥራ አፈጻጸም ዘገባ፣ የሕይወት ውይይትና በጠቅላላ ጉባኤው ውሳኔ
የሚፈልጉ አጀንዳዎች ይነሱበታል።
ረ. ስብሰባው ከ 2:00 ያልበለጠ ጊዜ የሚወስድ ይሆናል።
11.1.2. የክፍሉ ሥራ አሥፈጻሚ ስብሰባ
ሀ. የክፍሉ ሥራ አሥፈጻሚ መደበኛ ስብሰባ የሥራ አስፈጻሚው አባላት በጋራ በሚወስኑት መርሐ-
ግብር መሠረት የሚመራ ይሆናል፡፡
ለ. አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም የክፍሉ ጽሕፈት ቤት የስብሰባ ጥሪ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
ሐ. የክፍሉ ሥራ አሥፈጻሚ መደበኛ ስብሰባ ቢያንስ በወር ሁለት ጊዜ ይደረጋል፡፡
መ. የክፍሉ ሥራ አሥፈጻሚ መደበኛ ስብሰባ በክፍሉ ቢሮ ይደረጋል፡፡
ሠ. ከሥራ አሥፈጻሚ አባላቱ ከሃምሳ በመቶ (50%) በላይ የተገኙ እንደሆነ ምልዐተ ጉባኤ ይሆናል፡፡

10
674834749.docx
ረ. የስብሰባው ውሳኔዎች የሚተላለፉት በስምምነት ሲሆን በዚህ መልኩ ውሳኔውን ማስተላለፍ
ካልተቻለ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔው እንዲተላለፍ ይደረጋል። እኩል ድምጽ ሲኖር ሰብሳቢው
የደገፈው ሀሳብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ሠ. ስብሰባው የዕለቱ ስንክሳር፣ የሥራ አፈጻጸም ዘገባና ጽሕፈት ቤቱ ይዟቸው የሚመጡ አጀንዳዎች
ይኖረዋል ።
ረ. ስብሰባው ከ 1:30 ያልበለጠ ጊዜ የሚወስድ ይሆናል።
11.1.3. የንዑስ ክፍላት ስብሰባ
ሀ. የንዑስ ክፍሉ መደበኛ ስብሰባ የንዑስ ክፍሉ አባላት በጋራ በሚወስኑት መርሐ-ግብር መሠረት
የሚመራ ይሆናል፡፡
ለ. አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥም የንዑስ ክፍሉ ተጠሪ የስብሰባ ጥሪ ሊያቀርብ ይችላል፡፡
ሐ. የንዑስ ክፍሉ መደበኛ ስብሰባ ቢያንስ በወር ሁለት ጊዜ ይደረጋል፡፡
መ. የንዑስ ክፍሉ መደበኛ ስብሰባ በክፍሉ ቢሮ ይደረጋል፡፡
ሠ. ከንዑስ ክፍሉ አባላት ከሃምሳ በመቶ (50%) በላይ የተገኙ እንደሆነ ምልዐተ ጉባኤ ይሆናል፡፡
ረ. የስብሰባው ውሳኔዎች የሚተላለፉት በስምምነት ሲሆን በዚህ መልኩ ውሳኔውን ማስተላለፍ
ካልተቻለ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔው እንዲተላለፍ ይደረጋል። እኩል ድምጽ ሲኖር ሰብሳቢው
የደገፈው ሀሳብ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
11.2. ምርጫ
የክፍሉ የሥራ አስፈጻሚ (የንዑስ ክፍል ኃላፊዎች) ምርጫ አጠቃላይ በክፍሉ አባላት ጠቅላላ ጉባኤ
የሚደረግ ሲሆን ምርጫውን በበላይነት የሚመራው የክፍሉ ጽሕፈት ቤት ይሆናል።

11.2.1. በምርጫ ላይ የክፍሉ ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት


ሀ. የሥራ አስፈጻሚው የአገልግሎት ዘመን ሦስት ዓመት ሲሆን የሥራ አስፈጻሚው የሥራ ጊዜ ከመጠናቀቁ
ሦስት ወር አስቀድሞ የክፍሉ ጽሕፈት ቤት የምርጫ አፈጻጸም ዕቅድ አውጥቶ በክፍሉ ሥራ አስፈጻሚ
ስብሰባ ላይ ያጸድቃል፤

ለ. ከክፍሉ አባላት ለሥራ አስፈጻሚነት የሚኾኑ አባላትን ጥቆማ ይሰበስባል፤

ሐ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ መተዳደሪያ ደንብና በክፍሉ የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት ምርጫውን


ያስፈጽማል፤

መ. አዲስ በተመረጠውና በቀደመው ሥራ አስፈጻሚ መካከል ማናቸውንም የኃላፊነት፣ የንብረት፣ የሰነድና


የልምድ ልውውጥ እንዲካሄድ ያደርጋል፤

ሠ. ስለ ምርጫ ሂደቱ አጠቃላይ ዘገባ ለክፍሉ ጠቅላላ ጉባኤና ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፤

11
674834749.docx
ረ. የክፍሉ ጽሕፈት ቤት ከአባላቱ የሚቀርቡ እጩዎችን መርጦ ለምርጫ ለማቅረብ አመቺና አስፈላጊ
መንገዶችን ሊጠቀም ይችላል፤

ሰ. በምርጫ ሒደቱና ሥርዓቱ ላይ በክፍሉ ጠቅላላ ጉባኤ ሃምሳ (50%) በላይ ድምጽ ተቃውሞ የቀረበ
እንደኾነ የሥራ አሥፈጻሚ ድጋሚ ምርጫ ተካሒዶ ውጤቱ እስኪታወቅ ድረስ ሥራውን ነባሩ ሥራ
አሥፈጻሚ እያከናወነ ይቆያል።

11.2.2. የምርጫ ሥነ ሥርዓት


ሀ. ምርጫ ከመደረጉ አስቀድሞ የነበረው ሥራ አሥፈጻሚ ስለ ምርጫው የክፍሉ ጠቅላላ ጉባኤ መረጃ
እንዲያገኝ ያደርጋል፤

ለ. በሥራ አስፈጻሚነት የመምረጥም ኾነ የመመረጥ መብት ያለው የሰንበት ትምህርት ቤቱ መደበኛ አባልና
የመረጃና መዛግብት ክፍል አባል ብቻ ነው፤

ሐ. መራጮች ድምጽ መስጠት የሚችሉት የምርጫ አስፈጻሚው በዕለቱ ሊያስመርጥ በተዘጋጀው ቁጥር ልክ
ብቻ ነው፤

መ. በምርጫው የቀረቡ እጩዎች ባገኙት ድምጽ ልክ እንደ ቅደም ተከተላቸው ተመዝግበው እንዲይዙ
ያደርጋል።

ሠ. ለሥራ አስፈጻሚነት የሚመረጡ አባላት ለሥራ አስፈጻሚነት የሚያበቁ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ብቻ


ናቸው።

12
674834749.docx
12. የክፍሉ መዋቅር፣ ተግባርና ኃላፊነት

መረጃ ና መዛግብ ት ክፍል

የድኅረ ገጽ የቤተ -መዛግብ ት የመረጃ


አስተ ዳደር ንዑ ስ አስተ ዳደር ንዑ ስ አስተ ዳደር
ክፍል ክፍል ንዑ ስ ክፍል

12.1. ተግባርና ኃላፊነት


12.1.1. የክፍሉ ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የክፍሉን መሪ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለሰንበት ትምሕርት ቤቱ የሥራ አመራር ያጸድቃል፤ ይተገብራል
ተፈጻሚነቱን ሪፖርት ያደርጋል፡፡
ለ. የቤተክርስቲያንንና የሰንበት ትምህርት ቤቱን አጠቃላይ መረጃ በተጠናከረና በተሟላ ሁኔታ
ይሰበስባል፤ ይለያል፤ ያደራጃል፤ ይተነትናል፤ ደኅንነታቸውን ይጠብቃል፤ ለተጠቃሚዎች
ያደርሳል።
ሐ. ለቤተክርስቲያንና ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ግብዓት የሚሆኑ ማናቸውንም መረጃዎች
ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ያሰባስባል፤ ለተፈላጊው ዓላማ ያውላል።
መ. ከባለድርሻና ከተባባሪ አካላት ጋር ወቅታዊ መረጃዎችን ይለዋወጣል።
ሠ. በቤተክርስቲያን ላይ ያነጣጠሩ የአጽራረ ቤተክርስቲያንን እንቅስቃሴ ይከታተላል፤ ተጨባጭ
የሆነና በማስረጃ የተደገፈ መረጃ ሲገኝ ለሚመለከታቸው አካላት ያሳውቃል፤ ሂደቱንና
ተፈጻሚነቱን ይከታተላል።
ረ. ከባለድርሻና ከተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ማዕከላዊ የመረጃ ቋትና የቤተ-መጻሕፍት ማዕከል
እንዲቋቋም ያደርጋል።
ሰ. የመረጃ ፍሰቱንና ደኅንነቱን ወጥ፣ ዘመናዊና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያግዝ ቴክኖሎጂ
እንዲዘረጋ ያደርጋል።
ሸ. አግባብነት ያላቸው ማናቸውም መረጃዎች በተደራጅ ሁኔታ ለሚመለከታቸው አካላት በወቅቱ
እንዲደርስ ያደርጋል።

13
674834749.docx
ቀ. የሰንበት ትምህርት ቤቱን ድኅረ-ገጽ ያዘጋጃል፤ ያስተዳድራል፤ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ
የአገልግሎት ክፍሎች ሰለመረጃና መዛግብት ሥራዎች የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና እንዲያገኙ
ሁኔታዎችን ያመቻቻል።
በ. በመረጃና መዛግብት ዙሪያ ከአገልግሎት ክፍላት ጋር በመተባበር ይሠራል።
ተ. የሥራ አፈጻጸም ዘገባ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥራ አመራር ያቀርባል።
ቸ. በሥሩ ያሉትን ንብረቶች ይጠብቃል፤ ደኅንነታቸውን ይከታተላል።
ኀ. ጥናት በሚያስፈልጋቸው የክፍሉ ሥራዎች ላይ ጥናት ያደርጋል።
ነ. ለአርትኦት ክፍል ተለይተው ከተሰጡት የአርትኦት ሥራዎች በስተቀር ማንኛውንም ወደ ክፍሉ
የሚገቡ ከክፍሉም የሚወጡ ጽሑፎች ወደ አንባብያን ከመድረሳቸው በፊት የመጀመሪያ ደረጃ
የአርትኦት ሥራ ይሠራል።
12.1.2. አጠቃላይ የክፍሉ አባላት ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የክፍሉን አጠቃላይ አባላት በሚመለከቱ አገልግሎቶች ላይ መሳተፍ፤
ለ. ከክፍላት የአገልጋይ ጥያቄ ሲመጣ በአገልግሎቱ ላይ ተሳታፊ መኾን፤
ሐ. ክፍሉን ማጽዳት ማስተካከል፤
መ. ከክፍሉ አገልጋዮች ጋር በስምምነትና በመግባባት ማገልገል፤
ሠ. ዕቅዶችን በጊዜአቸው ተፈጻሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤ የማይፈጸሙበት ሁኔታ ሲፈጠር
ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ መፍትሔ መፈለግ፤
12.1.3. የክፍሉ ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ማዘጋጀት፤ መምራት፤
ለ. ክፍሉን በበላይነት መምራትና መከታተል፤
ሐ. የክፍሉ አባላት መንፈሳዊና ማኅበራዊ ሕይወታቸውን መከታተል፤ እገዛ ማድረግ፤
መ. አባላቱ በኃዘን፣ በደስታ እንዲተሳሰቡ ማድረግ፤
ሠ. ለክፍሉ አባላት የውይይትና የሥልጠና መርሐ-ግብሮችን ማዘጋጀት፤
ረ. የክፍሉን ንብረት በበላይነት መዝግቦ ይይዛል፤
ሰ. ከሌሎች ክፍላት ጋር የግንኙነት ሥራዎችን ይሠራል፤
12.1.4. የንዑስ ክፍል ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የንዑስ ክፍሉን መሪ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለክፍሉ ጽ/ቤት ያጸድቃል ይተገብራል ተፈጻሚነቱን ሪፖርት
ያደርጋል፡፡
ለ. የንዑስ ክፍሉን ስብሰባ በወር ሁለት ጊዜ ያዘጋጃል፤ ይመራል።
ሐ. አባላቱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱ ያነቃቃል፤ ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ከአገልግሎት
እንዳይርቁ ይንከባከባል፤

14
674834749.docx
መ. ከክፍሉ ጽሕፈት ቤት የሚሠጠውን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል።
ሠ. የአባላትን የአገልግሎት ሂደት ይከታተላል፤ እገዛ ያደርጋል።
12.1.5. የዘርፍ ተጠሪ ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. ከዘርፍ አገልጋዮች ጋር በመኾን ዕቅድ ያዘጋጃል፤ ያጸድቃል፤ ይተገብራል፤
ለ. የዘርፉን ስብሰባ ቀን ከዘርፉ አባላት ጋር በመወሰን አባላቱን ይሰበስባል፤
ሐ. አባላቱ በመንፈሳዊ ሕይወታቸው እንዲበረቱ ያነቃቃል፤
መ. የዘርፍ አባላትን መነፈሳዊ ሕይወት ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ ከአገልግሎት እንዳይርቁ ይንከባከባል፤
ሠ. ከንዑስ ክፍል ኃላፊና ከክፍሉ ጽሕፈት ቤት አባላት የሚሠጠውን ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል።
12.1.6. የክፍሉ አባል ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. ከእርሱ በላይ ካሉት ኃላፊዎች የሚሠጠውን ተግባር በጊዜው ያከናውናል፤

ለ. የክፍሉን መገልገያ እቃዎች በኃላፊነት ይጠብቃል፤

ሐ. ሐሳብ ያመነጫል፤ ለተፈጻሚነቱም ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር በመሆን ይሠራል፤

13. የጽሕፈት ቤትና የንዑሳን ክፍላት አወቃቀር፣ ተግባርና ኃላፊነት

13.1. የመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት


13.1.1. ስያሜ
ንዑስ ክፍሉ የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አንቀጸ ብጹዓን ሰንበት ትምህርት ቤት
የመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት ተብሎ ይጠራል፡፡

15
674834749.docx
13.1.2. ተጠሪነት
ለደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት ጽሕፈት
ቤት

13.1.3. መዋቅር

ጽሕፈት ቤት

ምክትል ምክትል
ዋና ሰብሳቢ ዋና ጸሐፊ
ሰብሳቢ ጸሐፊ
13.1.4. የመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የክፍሉን መሪ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ የሥራ አመራር ያጸድቃል፤ይተገብራል
ተፈጻሚነቱን ሪፖርት ያደርጋል፡፡
ለ. ንዑስ ክፍላት በዕቅዳቸው መሠረት እየሠሩ መኾናቸውን ይከታተላል፤ ያማክራል፤ ድጋፍ ይሰጣል።
ሐ. ገቢና ወጪ ደብዳቤዎችን ይከታተላል፤ ያስፈጽማል።
መ. ለክፍሉ የሚያስፈልጉትን ግብዓቶች ያሟላል።
ሠ. የክፍሉ አባላትን ሕይወት ይከታተላል።
ረ. ከሰንበት ትምህርት ቤቶችም ኾነ ከክፍሉ ጽሕፈት ቤት የሚመጡትን መረጃዎች ለአባላት በተገቢው ሁኔታ
ያደርሳል።
ሰ. ወደ ክፍሉ ለሚገቡ አባላት ሰለ ክፍሉ አሠራር ገለጻ ያደርጋል።
13.1.5. የዋና ሰብሳቢ ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የንዑስ ክፍላትን ኃላፊዎችና ጸሐፊዎች ከክፍሉ አባላት ጋር በመሆን ይመርጣል፣ በክፍሉ ሥራ አመራር
ያጸድቃል፤
ለ. ከንዑስ ክፍል ኃላፊዎችና ጸሐፊዎች ጋር በመሆን ክፍሎችን በበላይነት ይመራል፣
ሐ. ከሥራ አመራር ለክፍሎች የሚወርዱ መመሪያዎችን፣ ውሳኔዎችን፣ መረጃዎችን ለዋና ክፍሉ አባላት
ያሳውቃል፤
መ. የክፍሉን እንቅስቃሴ በተመለከተም ለሥራ አመራሩና ለኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍል ወቅታዊ ሪፖርት
ያቀርባል፤
ሠ. በሥራ አመራሩ የጸደቁ ዕቅዶችን፣ የሚሰጡ መመሪያዎችን ያስተገብራል፤
ረ. በክፍላቱ የሚቀርቡ የወጪና የንብረት ጥያቄ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ ይፈርማል፤

16
674834749.docx
ሰ. የክፍሉን አባላት መንከባከብ፤ በክፍል ውስጥ በሚነሱ ቅሬታዎች ላይ መፍትሔ መስጠት ይህ ሳይሆን ቢቀር

ለሥራ አመራር እንዲሁም ለሥነ-ምግባር ክትትል፣ ምክርና ተግሳጽ ክፍል ጉዳዩን በግልባጭ ያሳዉቃል፤
ሸ. በሥሩ ያሉ ንዑሳን ክፍሎችን ይመራል፡፡
ቀ. የንዑሳን ክፍሎች ኃላፊዎችን ከክፍሉ አባላት ያስመርጣል ለሥራ አመራሩ ተጠሪ አቅርቦ ያስጸድቃል፡፡

በ. የንዑሳን ክፍሎችን የአገልግሎትና የበጀት ዕቅድ በመመርመር ለሥራ አመራሩ ያቀርባል ሲጸድቅም ተግባር
ላይ ያውላል ፡፡
ተ. የንዑሳን ክፍሎችን የአገልግሎት አፈጻጸምና የበጀት እንቅስቃሴ ይገመግማል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መመሪያ
ይሰጣል ፡፡
ቸ. የአገልጋዮችን ምደባና ዝውውር በተመለከተ ከሥነ-ምግባር ክፍል ጋር በመሆን በትብብር ይሠራል፡፡
ኀ. የአገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርት በየሩብ ዓመቱና እንደ አስፈላጊነቱ የኦዲትና ኤንስፔክሽን ክፍሉ ጥያቄ
ባቀረበ ጊዜ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት በጽሑፍ ያቀርባሉ፡፡
ነ. የክፍሉን መደበኛ የሥራ አመራር ስብሰባ በየ 15 ቀኑ ያደርጋል፤ ለአባላት ጥሪ ያስተላልፋል፤ ስብሰባውን
ይመራል።
ኘ. ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ሥራ አመራር የሚሰጠውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል

13.1.6. የምክትል ሰብሳቢ ተግባር እና ኃላፊነት


ሀ. ዋና ሰብሳቢው በሌለበት ዋና ሰብሳቢውን ተክቶ ይሠራል፣
ለ. ዋና ሰብሳቢውን በሚያስፈልገው ሁሉ ያግዛል፣
ሐ. በክፍሉ ጽሕፈት ቤት የሚሰጠውን ሌሎች ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል፣
13.1.7. የዋና ጸሐፊ ተግባር እና ኃላፊነት
ሀ. የክፍሉን የስብሰባ አጀንዳ ከክፍሉ ዋና ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢና ምክትል ጸሐፊ ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣
ቃለ ጉባኤ ይይዛል፡፡
ለ. የገቢና ወጪ ማኀደር አዘጋጅቶ ደብዳቤዎችንና ተዛማጅ መረጃዎችን በአግባቡ ያስቀምጣል፣

ሐ. ንዑሳን ክፍሎች ዓመታዊ ዕቅድና በየሦስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲያዘጋጁ ያሳስባል፣
የተዘጋጁትንም አጠናቅሮ ለክፍሉ ዋና ሰብሳቢ ያቀርባል፣
መ. ከሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት የተሰጠውን የክፍሉን ዕቅድ ለንዑስ ክፍላት ኃላፊዎች አባዝቶ
ይሰጣል፣
ሠ. ከክፍሉ ሰብሳቢ የሚሰጠውን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
13.1.8. የምክትል ጸሐፊ ተግባር እና ኃላፊነት
ሀ. ዋና ጸሐፊው በሌለበት ዋና ጸሐፊውን ተክቶ ይሠራል

17
674834749.docx
ለ. ዋና ጸሐፊውን በሚያስፈልገው ሁሉ ያግዛል፣
ሐ. በክፍሉ ጽሕፈት ቤት የሚሰጠውን ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

13.2. የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል


13.2.1. ስያሜ
ንዑስ ክፍሉ የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የመረጃና መዛግብት ክፍል የድኅረ ገጽ
አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተብሎ ይጠራል፡፡

13.2.2. ተጠሪነት
ለመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት ነው።

13.2.3. መዋቅር

የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል

የድኅረ-ገጽ መረጃ ሥርጭትና የድኅረ-ገጽ ልማት


ቁጥጥር ዘርፍ ዘርፍ

13.2.4. የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት


ሀ. የንዑስ ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ አዘጋጅቶ ለክፍሉ
ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፡፡

18
674834749.docx
ለ. ድኅረ-ገጽ ማልማት፣ መረጃዎችን ማስፈር፣ ወቅታዊነታቸውን መከታተል፣ ደኅንነታቸውን መጠበቅና መከታተል።
ሐ. ሌሎች የመገናኛ ብዙኀንን ማልማት፤ መረጃዎችን ማስፈር፣ ወቅታዊነታቸውን መከታተል፣ ደኅንነታቸውን መጠበቅና
መከታተል።
መ. ለቤተክርስቲያንና ለሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚጠቅሙ መተግበሪያዎችን (Software) ማልማትና
ለተጠቃሚዎች ማድረስ
ሠ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
13.2.5. የድኅረ-ገጽ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተጠሪ
ሀ. የንዑስ ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ አዘጋጅቶ ለክፍሉ
ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡
ለ. የንዑስ ክፍሉን ስብሰባ ቢያንስ በ 15 ቀን አንዴ ያዘጋጃል፤ ይመራል።
ሐ. በንዑስ ክፍሉ ላይ የሚገኙትን የዘርፋት አባላትን ሕይወት በቅርበት ሆኖ ይከታተላል።

መ. የንዑስ ክፍሉ አባላት ሥራቸውን እንዲሠሩ ያበረታታል፣ ይከታተላል፣ እገዛ ያደርጋል።

ሠ. ንዑስ ክፍሉን ወክሎ በክፍሉ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ይገኛል፣ ለዘርፍ አባላትም ውሳኔዎችን ያሳውቃል።

ረ. በክፍሉ ጽሕፈት ቤት የተሰጡትን አዲስ አባላት ስለ ንዑስ ክፍሉ አሠራር ገለጻ ያደርጋል ወደ ዘርፎቹ በመመደብ
እንዲያገለግሉ ያደርጋል።

ሰ. የንዑስ ክፍሉ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ሥልጠና በመለየት እንዲሠለጥኑ ያደርጋል።

13.2.6. የድኅረ-ገጽ መረጃ ሥርጭትና ቁጥጥር ዘርፍ


ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. መረጃዎችን በመገናኛ ብዙኀን የሚሠራጩበትን የጊዜ ሰሌዳ ያዘጋጃል።
ሐ. ለመገናኛ ብዙኀን የሚሆኑ ግብዓቶችን ከመረጃ ክምችት ዘርፍ ይቀበላል፤ መለቀቅ የሚገባቸውን መረጃዎችን
ከክምችቶቹ ውስጥ ይለያል፤ የሚለቀቅባቸውን የመገናኛ ብዙኀን ዓይነት ይለያል።
መ. መረጃዎች መገናኛ ብዙኀን ላይ ከመለቀቃቸው አስቀድሞ በሚመለከተው አካል የአርትኦት ሥራ እንዲሠራ ያደርጋል፤
በአርትኦት ተቀባይነት ያገኙ መረጃዎችን ወቅቱን ጠብቆ መገናኛ ብዙኀን ላይ ይለቃል።
ሠ. መገናኛ ብዙኃን ላይ እየተለቀቁ ያሉትን መረጃዎች ወቅታዊነታቸውን ይከታተላል፤ ለሚመለከተው አካል ዘገባ
ያቀርባል።
ረ. ከሥርዓተ ቤተክርስቲያን ውጪ የሆኑና ከሰንበት ትምህርት ቤቱ እውቅና ውጪ የሆኑ መረጃዎች፣ ሀሳብ አስተያየቶች
ሲገኙ ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፤ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል።
ሰ. በተለቀቀው መረጃ ላይ የሚሰጡትን አስተያየቶችና የሚጠየቁትን ጥያቄዎች ይሰበስባል፤ በፈርጅ በፈርጅ ለይቶ
ያስቀምጣል፤ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ለሚመለከትው አካል ያቀርባል።

19
674834749.docx
ሸ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

13.2.7. የድኅረ-ገጽ ልማት ዘርፍ


ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዘጋጅቶ ለንዑስ
ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚጠቀምባቸው የመገናኛ ብዙኀን ጥገና በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ይጠግናል፤ ከዘመኑ ጋር
እየተራመደ መሆኑን ይከታተላል፤ ማሻሻያ ያደርጋል።
ሐ. ሰንበት ትምህርት ቤቱ እየተጠቀመባቸው ያልሆኑ ነገር ግን ሊጠቀምባቸው የሚችለው ዘመኑን የዋጁ የመገናኛ ብዙኀን
ዓይነት በመምረጥ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልግሎት የሚውልበትን መንገድ ይለያል፤ ለሚመለከተው ክፍል አቅርቦ
ያጸድቃል።
መ. የጸደቀውን የመገናኛ ብዙኀን ያለማል፤ ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር ያለውን ውጤታማነት ይመዝናል፤ ለሚመለከተው
ክፍል ዘገባ ያቀርባል።
ሠ. ሰንበት ትምህርት ቤቱ የሚጠቀምባቸው ድኅረ ገጾችን ተከታይ ለማብዛት የማስተዋወቅ ሥራ ይሠራል።
ረ. በድኅረ ገጽ አጠቃቀም ዙሪያ አባላት ሥልጠና የሚያገኙበትን መንገድ ከሚመለከታቸው ክፍላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል።
ሰ. ለሰንበት ትምህርት ቤቱ የመረጃ ማስቀመጫ ቋት (Database) ያዘጋጃል፤ ጥገና በሚያስፈልግ ጊዜ ይጠግናል።
ሸ. ሰንበት ትምህርት ቤቱ እንዲሁም ምዕመናን ሊጠቀምባቸው የሚችሉ የስልክና የኮምፒውተር መተግበሪያዎችን
(Software) ያዘጋጃል፤ ለተጠቃሚዎች ያደርሳል።
ቀ. የተሠሩት መተግበሪያዎች (Software) ከዘመኑ ጋር እየተጓዘ መሆኑን ይከታተላል፤ ማሻሻያ ያደርጋል።
በ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

 ንዑስ ክፍሉ ቢያንስ 6 አባላት ይኖሩታል።

20
674834749.docx
13.3. የቤተ-መዛግብት አስተዳደር ንዑስ ክፍል
13.3.1. ስያሜ
ንዑስ ክፍሉ የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የመረጃና መዛግብት ክፍል የቤተ-መዛግብት
አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተብሎ ይጠራል፡፡

13.3.2. ተጠሪነት
ለመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት

13.3.3. መዋቅር

የቤተ-መዛግብ ት አስተዳደር ንዑስ ክፍል

የቤተ-መጻሕፍት አስተዳደር
የመዛግብት አስተዳደር ዘርፍ የንብረት ቁጥጥር ዘርፍ
ዘርፍ

13.3.4. የቤተ-መዛግብት አስተዳደር ንዑስ ክፍል ዋና ዋና ተግባርና ኃላፊነት


ሀ. የክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል ፣ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም
ዘገባ አዘጋጅቶ ለክፍሉ ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፡፡
ለ. በምስል ወድምጽ ተዘጋጅተው በቤተ-መጻሕፍት የሚገኙ ሀብቶችን ለተጠቃሚዎች ያደርሳል።
ሐ. ቤተ-መጻሕፍቱን ዘመናዊ በሆነ መልኩ ያደራጃል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን ያካትታል፤ ይጠብቃል፤ ይንከባከባል፤
ለጠጠቃሚዎች ያደርሳል።
መ. መዝገበ መጻሕፍትንና መጽሔት ያዘጋጃል፤ ለተጠቃሚ ያደርሳል።
ሠ. የመጻሕፍት ዳሰሳና የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብር ያዘጋጃል።
ረ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል።

13.3.5. የቤተ-መዛግብት አስተዳደር ተጠሪ


ሀ. የንዑስ ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ አዘጋጅቶ ለክፍሉ
ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡
ለ. የንዑስ ክፍሉን ስብሰባ ቢያንስ በ 15 ቀን አንዴ ያዘጋጃል ይመራል።
ሐ. በንዑስ ክፍሉ ላይ የሚገኙትን የዘርፋት አባላትን ሕይወት በቅርበት ሆኖ ይከታተላል።

መ. የንዑስ ክፍሉ አባላት ሥራቸውን እንዲሠሩ ያበረታታል፣ ይከታተላል፣ እገዛ ያደርጋል።

ሠ. ንዑስ ክፍሉን ወክሎ በክፍሉ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ይገኛል፣ ለዘርፍ አባላትም ውሳኔዎችን ያሳውቃል።

21
674834749.docx
ረ. በክፍሉ ጽሕፈት ቤት የተሰጡትን አዲስ አባላት ስለ ንዑስ ክፍሉ አሠራር ገለጻ ያደርጋል ወደ ዘርፎቹ በመመደም ሥራ
እንዲሠሩ ያደርጋል።

ሰ. የንዑስ ክፍሉ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ሥልጠና በመለየት እንዲሠለጥኑ ያደርጋል።

13.3.6. የቤተ-መጻሕፍት አስተዳደር ዘርፍ


ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. ዘመናዊና ለአጠቃቀም ምቹ በሆነ አሠራር ቤተ-መጻሕፍቱን ያደራጃል።
ሐ. ለቤተ-መጻሕፍቱ የሚሆኑ መጻሕፍት፣ መጽሔትና ጋዜጦችን ያሰባስባል፤ በሚመለከተው አካል የአርትኦት
ሥራ እንዲሠራ ያደርጋል፤ መለያ በመስጠት ካሉት መጽሐፍት ጋር ደምሮ ለአጠቃቀም ዝግጁ ያደርጋል።
መ. ምዕመናን የቤተ-መጻሕፍት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ቅስቀሳ ያደርጋል፤ የአባላትን የቤተ-መጻሕፍት አጠቃቀም
ይከታተላል፤ በተደጋጋሚ ቤተ-መጻሕፍቱን የሚጠቀሙ አባላትን ያበረታታል፤ ማሻሻያ መደረግ
ያለባቸውን ነገሮች ያሻሽላል።
ሠ. የመጻሕፍት ዳሰሳ፣ የመጻሕፍት ማሰባሰብ፣ የመጻሕፍት ምረቃ ወዘተ መርሐ-ግብር ያዘጋጃል።
ረ. የንባብ ባሕልን ሊያዳብሩ የሚችሉ መርሐ-ግብሮችን ያዘጋጃል።
ሰ. የመጻሕፍት ውሰት አገልግሎት ይሰጣል፤ መጻሕፍቶቹ በጊዜው መመለሳቸውን ያረጋግጣል፤ የአገልግሎቱን ውጤታማነት
ይመዝናል፤ ማሻሻያ መደረግ ያለባቸው ነገሮች ያሻሽላል።
ሸ. በመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል የተዘጋጁ የምስል፣ የድምጽ፣ የምስል ወድምጽ መረጃዎች በቤተ-መጻሕፍት አማካኝነት
ለተጠቃሚዎች መድረስ የሚችሉ መረጃዎችን ከንዑስ ክፍሉ ይቀበላል፤ በፈርጅ በመለየት ያስቀምጣል፤
ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል።
ቀ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል።
13.3.7. የመዛግብት አስተዳደር ዘርፍ
ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. ቤተ-መጻሕፍት ውስጥ ያሉትን እንዲሁም ሌሎች የቤተ-ክርስቲያንን ዶግማ ቀኖናና ትውፊት የጠበቁ፤ በሰንበት
ትምህርት ቤቱ ተቀባይነት ያገኙ መጻሕፍቶችን በድምጽ፣ በምስል ወድምጽና በኮምፒውተር ጽሑፍ (PDF) ያዘጋጃል፤
በዓይነት ለይቶ በፈርጅ በፈርጅ ያስቀምጣል፤ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ያደርጋል።
ሐ. በሰንበት ትምህርት ቤቱ የተሰበሰቡ ጠቃሚ መረጃዎችን ዘመናዊ በሆነ መልኩ አደራጅቶ ያስቀምጣል፤
አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ለሚመለከታቸው አካላት ይልካል።
መ. የተቀመጡትን መረጃዎች የጊዜ ሰሌዳ በማውጣት ይገመግማል፤ ወቅታቸው ያለፈባቸውን መረጃዎች
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የቤተክርስቲያን ሥርዓት በሚፈቅደው መሠረት ያስወግዳል።
ሠ. በድኅረ ገጽ የሰፈሩ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ በፈርጅ በመለየት በዘመናዊ መንገድ ያስቀምጣል።

22
674834749.docx
ረ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል።
13.3.8. የንብረት ቁጥጥር ዘርፍ
ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. ንዑስ ክፍሉ ላይ ያሉትን ንብረቶች መዝግቦ ይይዛል፤ አዳዲስ ንብረቶች ወደ ንዑስ ክፍሉ ሲገቡ መዝግቦ ይረከባል፤
በጥንቃቄ ያስቀምጣል።
ሐ. ንብረቶች ያሉበትን ደረጃ ይከታተላል፤ የተጎዱ ንብረቶችን ይጠግናል።
መ. ንዑስ ክፍሉ ላይ ያሉ መወገድ የሚገባቸውን ንብረቶች ሥርዓተ ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው መሠረት ያስወግዳል።
ሠ. በወር አንድ ጊዜ ንዑስ ክፍሉ ላይ ያሉትን ንብረቶች ይቆጣጠራል፤ ከመዝገቡ ጋር ያመሳክራል፤ ለሚመለከተው አካል
ዘገባ ያቀርባል።
ረ. ንዑስ ክፍሉ ላይ ያለውን የንብረት አጠቃቀም ይገመግማል፤ ማሻሻያ መደረግ የሚገባቸውን ነገሮች ለሚመለከታቸው
አካላት ያሳውቃል፤ ዘገባ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል።
ሰ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል።

 ንዑስ ክፍሉ በውስጡ 8 አባላት ይኖሩታል።

13.4. የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል


13.4.1. ስያሜ
ንዑስ ክፍሉ የአንቀጸ ብፁዓን ሰንበት ትምህርት ቤት የመረጃና መዛግብት ክፍል የመረጃ አስተዳደር
ንዑስ ክፍል ተብሎ ይጠራል፡፡

13.4.2. ተጠሪነት
ለመረጃና መዛግብት ክፍል ጽሕፈት ቤት

13.4.3. መዋቅር

የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል

የመረጃ የመረጃ የመረጃ ንብረት


ክምችት ዘርፍ ማደራጀት ዘርፍ ሥርጭት ዘርፍ ቁጥጥር ዘርፍ

23
674834749.docx
13.4.4. የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተግባርና ኃላፊነት
ሀ. የክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ያጸድቃል፣ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘርፍ አዘጋጅቶ ለክፍሉ
ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፡፡
ለ. ማንኛውም የቤተክርስቲያንና የሰንበት ትምህርት ቤትን የመረጃ ሀብቶች በተለያዩ መንገዶች
አዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ያደርሳል።
ሐ. የተቀረጹ የተለያዩ መርሐ-ግብራትን በድምጽ፣ በምስል ወድምጽና በፎቶግራፍ አትሞ ማውጣትና
በአርትኦት ንዑስ ክፍል ፈቃድ ሲያገኝ ለተጠቃሚዎች ያደርሳል።
መ. የዜና መጽሔት ያዘጋጃል።
ሠ. የሰንበት ትምህርት ቤቱን አጠቃላይ የመረጃ ቋት (Database) ያዘጋጃል፤ መረጃዎችን ወደ መረጃ
ቋት ያስገባል፤ ይጠብቃል፤ ያበለጽጋል ለተገቢው አካል ያደርሳል።
ረ. የተለያዩ የመረጃ ማስተላለፊያ መድረኮችን ያዘጋጃል
ሰ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
13.4.5. የመረጃ አስተዳደር ንዑስ ክፍል ተጠሪ
ሀ. የንዑስ ክፍሉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ አዘጋጅቶ ለክፍሉ
ጽሕፈት ቤት ያቀርባል፡፡
ለ. የንዑስ ክፍሉን ስብሰባ ቢያንስ በ 15 ቀን አንዴ ያዘጋጃል፤ ይመራል።
ሐ. በንዑስ ክፍሉ ላይ የሚገኙትን የዘርፋት አባላትን ሕይወት በቅርበት ሆኖ ይከታተላል።

መ. የንዑስ ክፍሉ አባላት ሥራቸውን እንዲሠሩ ያበረታታል፣ ይከታተላል፣ እገዛ ያደርጋል።

ሠ. ንዑስ ክፍሉን ወክሎ በክፍሉ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ይገኛል፣ ለዘርፍ አባላትም ውሳኔዎችን ያሳውቃል።

ረ. በክፍሉ ጽሕፈት ቤት የተሰጡትን አዲስ አባላት ስለ ንዑስ ክፍሉ አሠራር ገለጻ ያደርጋል ወደ ዘርፎቹ ደብዳቤ ከክፍሉ
ጽሕፈት ቤት ሲመራለት ተግባራዊ ያደርጋል።

ሰ. የንዑስ ክፍሉ አባላት የሚያስፈልጋቸውን ሥልጠና በመለየት እንዲሠለጥኑ ያደርጋል።

13.4.6. የመረጃ ክምችት ዘርፍ


ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ
ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. በቤተክርስቲያን፣ በደብሩ፣ በሰንበት ትምህርት ቤቱና በክፍላት ዙሪያ ያሉ መረጃዎችን ከተለያዩ
ምንጮች ይሰበስባል፤ ለሚመለከተው ክፍል ይልካል።

24
674834749.docx
ሐ. በቤተክርስቲያን፣ በደብሩና በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚኖሩ መደበኛና ልዩ መርሐ ግብራትን
በድምጽ፣ በምስል ወድምጽ፣ በምስል ቅጂ ያስቀምጣል፤ ለመረጃ ማደራጀት ዘርፍ ይልካል።
መ. ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ መርሐ-ግብራት ላይ በመገኘት መረጃዎችን በምስል፣ በድምጽና በምስል
ወድምጽ ይይዛል፤ ለመረጃ ማደራጀት ዘርፍ ይልካል።
ሠ. የአጽራረ ቤተክርስቲያንን እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ለሚመለከተው አካል
በማቅረብ አፋጣኝ ምላሽ እንዲያገኙ ያደርጋል።
ረ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡

13.4.7. የመረጃ ማደራጀት ዘርፍ


ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. በመረጃ ክምችት ዘርፍ የተሰበሰቡትን መረጃዎች በዓይነት በመለየት በፈርጅ በፈርጅ ያስቀምጣል።
ሐ. በምስል፣ በድምጽ፣ በምስል ወድምጽ የተቀመጡትን መረጃዎች ለተጠቃሚ መድረስ በሚችል
መልኩ ያቀናብራል፤ በፈርጅ በፈርጅ ለይቶ ያስቀምጣል።
መ. የሰንበት ትምህርት ቤቱን የማስታወቂያ ሥራዎች ይሠራል።
ሠ. ሌሎች ዘርፉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
13.4.8. የመረጃ ሥርጭት ዘርፍ
ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡
ለ. በመረጃ ማደራጀት ዘርፍ የተደራጁትን መረጃዎች ይቀበላል፤ ለማሠራጨት ብቁ መሆናቸውን
ይመዝናል፤ የአርትኦት ሥራ እንዲሠራ ያደርጋል፤ መረጃዎቹ ለተጠቃሚ የሚደርስበትን መንገድ
ይለያል፤ ለተጠቃሚ ያደርሳል።
ሐ. የመረጃ ሥርጭቱን ውጤታማነት ይገመግማል፤ ማሻሻያዎች በሚያስፈልጉ ጊዜ ማሻሻያ ያደርጋል።
መ. ገቢ የሚያስገኙ መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች በማሳወቅ ያሰራጫል፤ ከክፍሉ ጽሕፈት ቤት ጋር
የኦዲት ሥራ ይሠራል።
ሠ. ሌሎች ዘርፉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
13.4.9. የንብረት ቁጥጥር ዘርፍ
ሀ. የዘርፉን ዓመታዊ ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ያጸድቃል፤ በየሩብ ዓመቱ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ
አዘጋጅቶ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል፡፡

25
674834749.docx
ለ. ንዑስ ክፍሉ ላይ ያሉትን ንብረቶች መዝግቦ ይይዛል፤ አዳዲስ ንብረቶች ወደ ንዑስ ክፍሉ ሲገቡ መዝግቦ ይረከባል፤
በጥንቃቄ ያስቀምጣል።
ሐ. ንብረቶች ያሉበትን ደረጃ ይከታተላል፤ የተጎዱ ንብረቶችን ይጠግናል።
መ. ንዑስ ክፍሉ ላይ ያሉ መወገድ የሚገባቸውን ንብረቶች ሥርዓተ ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው መሠረት ያስወግዳል።
ሠ. በወር አንድ ጊዜ ንዑስ ክፍሉ ላይ ያሉትን ንብረቶች ይቆጣጠራል፤ ከመዝገቡ ጋር ያመሳክራል፤ ለሚመለከተው አካል
ዘገባ ያቀርባል።
ረ. ከክፍላት የንብረት ውሰት ጥያቄ ሲመጣ በጽሕፈት ቤቱ የይሁንታ ፈቃድ ሲያገኝ በቅጽ መዝግቦ ያስረክባል፤ አገልግሎቱ
ሲጠናቀቅ በአግባቡ ይረከባል።
ሰ. ንዑስ ክፍሉ ላይ ያለውን የንብረት አጠቃቀም ይገመግማል፤ ማሻሻያ መደረግ የሚገባቸውን ነገሮች ለሚመለከታቸው
አካላት ያሳውቃል፤ ዘገባ ለንዑስ ክፍሉ ተጠሪ ያቀርባል።
ሸ. ሌሎች ክፍሉን የሚመለከቱ ተግባራትን ያከናውናል።

 ንዑስ ክፍሉ በውስጡ 12 አባላት ይኖሩታል።

26
674834749.docx
14. ሒሳብና ንብረትን በተመለከተ

14.1. ሒሳብን በተመለከተ


ሀ. የክፍሉ ጽሕፈት ቤት የሚሰጠውን በጀት የሒሳብ መዝገብ በማዘጋጀት ወጪና ገቢውን መመዝገብና በየ 3
ወር የሒሳብ ዘገባ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ማስገባት ይኖርበታል፤

ለ. በተለያየ ምክንያት ማለትም ከበጎ አድራጊዎች፤ ከአባላት ወዘተ . . . ወደ ክፍሉ የሚመጣ ገቢ ቢኖር
ከገቢው ላይ ምንም ተቀናሽ ሳይደረግ በሒሳብ ክፍል በኩል ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ገቢ ማድረግና የገቢ
ደረሰኝ መቀበል ይኖርበታል፤

ሐ. በክፍሉ ላይ የበጀት እጥረት በሚኖርበት ጊዜ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ጥያቄውን በማቅረብ


የበጀት ማሻሻያ እንዲደረግ ና አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ማድረግ ይኖርበታል፤

መ. የትኛውም የገንዘብ ገቢም ሆነ ወጪ በጊዜውና በሰዓቱ ወዲያው ወደ ሚፈለገው አገልግሎት መዋል


ይኖርበታል። በክፍል ወይም በቢሮ ውስጥ የሚቀመጥ ገንዘብ መኖር የለበትም፤

ሠ. ገቢን በተመለከተ ከሚመለከተው ከልማት ክፍል ጋር በመሆን ከሚያመጣው ገቢ ውጪ በራሱ የገቢ ምንጭ
ፈጥሮ ገቢ መሰብሰብ አይችልም፤

14.2. ንብረትን በተመለከተ


ሀ. የክፍሉ ጽሕፈት ቤት የክፍሉን ንብረት መዝግቦ የመያዝ ግዴታ አለበት፤

ለ. ክፍሉ የትኛውም ዓይነት ንብረት ለማስወገድ ሲፈልግ በቅድሚያ የሰንበት ትምሕርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት
ፈቃድ ሊያገኝ ይገባል፤

ሐ. ከክፍሉም ይሁን ከበጎ አድራጊዎች የሚሰጥ ንብረት ሲኖር በቅድሚያ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት
ቤት በደብዳቤ ማሳወቅና ወደ ሒሳብና ንብረት ክፍል ገቢ ሆኖ ተመዝግቦ በድጋሚ ወጪ መሆን
ይኖርበታል፤

መ. ማንኛውም የጎደለ ንብረት ቢኖር የክፍሉ አሥፈጻሚዎች ንብረቱን ፈልገው በቦታው የመመለስ፤
ካልሆነም የመተካት ግዴታ አለባቸው፤

ሠ. የክፍሉ ጽሕፈት ቤት በየዓመቱ በሚደረገው የንብረት ቆጠራ ላይ ክፍሉን ለቆጠራ ምቹ የማድረግና


ንብረቱን በአግባቡ የማስቆጠር ግዴታ አለበት፤

27
674834749.docx
15. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

15.1. የተፈጻሚነት ወሰን


ይህ የአፈጻጸም መመሪያና መመሪያውን መሠረት አድርገው የሚዘጋጁ ውሳኔዎችና መርሕዎች በክፍሉ አባላት
ላይ ተፈጻሚ ይኾናሉ።

15.2. ስለ አፈጻጸም መመሪያው መሻሻል


ይህ የአፈጻጸም መመሪያ አስፈላጊ ኾኖ ሲገኝ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤትና በክፍሉ አብዛኛው
አባላት ዘንድ ሲደገፍ የአፈጻጸም መመሪያው ሊሻሻል ይችላል።

15.3. የአፈጻጸም መመሪያው የበላይነት


ይህ የሰንበት ትምህርት ቤቱን መተዳደሪያ ደንብ መሠረት አድርጎ የተዘጋጀውን የአፈጻጸም መመሪያ የሚቃረኑ
ማናቸውም መመሪያዎች፣ ውሳኔውችና ልማዳዊ አሠራሮች ተፈጻሚነት አይኖራቸውም።

15.4. የጾታ አገላለጽ


በዚህ የአፈጻጸም መመሪያ ውስጥ በወንድ ጾታ የተገለጸው የሴትንም ጾታ ያካትታል።

15.5. የአፈጻጸም መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ


ይህ የአፈጻጸም መመሪያ በክፍሉ ጠቅላላ ጉባኤና በሰንበት ትምህርት ቤቱ ጽሕፈት ቤት ከጸደቀበት ከ
ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይኾናል።

28
674834749.docx

You might also like