You are on page 1of 47

የሐዋርያት ስራ እና የጳውሎስ መልዕክቶች

እንዳለ ተፈራ

ለናዝሬት መሰረተ ክርስቶስ ኮሌጅ

መጋቢት 19-2011
Contents
ክፍል አንድ.........................................................................................................................................................................6

1. አጠቃላይ መግቢያ.....................................................................................................................................................6

1.3. የጳውሎስ መለወጥ................................................................................................................................................7

1.4. ታሪኩን ማደራጀት...............................................................................................................................................8


1.5. የጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ.........................................................................................................................................9
1.6. አዲሱ እይታ.........................................................................................................................................................9

2. የሐዋርያት ስራ........................................................................................................................................................10

2.1. መግቢያ..............................................................................................................................................................10

2.1.1. ፀሐፊ............................................................................................................................................................10

2.1.2. የተጻፈበት ቀን................................................................................................................................................11

2.1.3. ዓላማ............................................................................................................................................................11

2.1.4. ተቀባይ..........................................................................................................................................................12

2.2. ሀቲት.................................................................................................................................................................12

2.3. ነገረ መለኮት.......................................................................................................................................................16


የእግዚአብሄር ዕቅድ...........................................................................................................................................................16
የፍጻሜ ዘመን..................................................................................................................................................................16
ድነት...............................................................................................................................................................................16
የእግዚአብሄር ቃል.............................................................................................................................................................16
መንፈስ ቅዱስ.................................................................................................................................................................16
የእግዚአብሄር ህዝብ..........................................................................................................................................................17

መወያያ ጥያቄ..................................................................................................................................................................17

ክፍል ሦስት-በሚሲዮናዊ ጉዞ የተጻፉ..................................................................................................................................17

ሮሜ...............................................................................................................................................................................17

1. መግቢያ..................................................................................................................................................................17

1.1 ፀሐፊ.................................................................................................................................................................17

1.2 የተጻፈበት ቀን....................................................................................................................................................17

1.3 ዓላማ.................................................................................................................................................................17

2. የሮሜ ጭብጥ.........................................................................................................................................................17

3. ነገረ መለኮት............................................................................................................................................................20
4. መወያያ ጥያቄ.........................................................................................................................................................22

1 እና 2 ቆሮንቶስ..............................................................................................................................................................22

መግቢያ...........................................................................................................................................................................22

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................22

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................22

ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................23

1 ቆሮንቶስ ጭብጥ...........................................................................................................................................................23

2 ቆሮንቶስ ጭብጥ...........................................................................................................................................................26

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................27

መወያያ ጥያቄ..................................................................................................................................................................30

ገላተያ.............................................................................................................................................................................30

መግቢያ...........................................................................................................................................................................30

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................30

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................30

ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................30

የገላተያ ጭብጥ................................................................................................................................................................30

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................31
1 እና 2 ተሰሎንቄ.............................................................................................................................................................33

መግቢያ...........................................................................................................................................................................33

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................33

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................33

ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................33

መ. ጭብጥ......................................................................................................................................................................34

ሀቲት..............................................................................................................................................................................34

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................35

መወያያ ጥያቄ..................................................................................................................................................................37

ክፍል አራት-የእስር ቤት መልዕክቶች...................................................................................................................................38

ኤፌሶን...........................................................................................................................................................................38

መግቢያ...........................................................................................................................................................................38

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................38

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................38
ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................38

ጭብጥ............................................................................................................................................................................38

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................39

መወያያ ጥያቄ..................................................................................................................................................................40
ፊሊጲስየስ......................................................................................................................................................................40

መግቢያ...........................................................................................................................................................................40

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................40

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................40

ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................40

ጭብጥ............................................................................................................................................................................41

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................41

መወያያ ጥያቄ..................................................................................................................................................................43
ቆላሲስ............................................................................................................................................................................43

መግቢያ...........................................................................................................................................................................43

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................43

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................43

ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................43

ጭብጥ............................................................................................................................................................................43

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................44
ፊልሞን...........................................................................................................................................................................44

መግቢያ...........................................................................................................................................................................44

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................44

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................44

ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................44

ጭብጥ............................................................................................................................................................................45

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................45

መወያያ ጥያቄ..................................................................................................................................................................46

ክፍል አምስት...................................................................................................................................................................46

የመጋቢያን መልዕክት........................................................................................................................................................46

መግቢያ...........................................................................................................................................................................46

ሀ. ፀሐፊ..........................................................................................................................................................................46

ለ. የተጻፈበት ቀን.............................................................................................................................................................46
ሐ. ዓላማ.........................................................................................................................................................................46

ጭብጥ............................................................................................................................................................................47
1 ጢሞቲዎስ...................................................................................................................................................................47
2 ጢሞቲዎስ...................................................................................................................................................................47
ቲቶ................................................................................................................................................................................48

ነገረ መለኮት....................................................................................................................................................................48
ክፍል አንድ
1. አጠቃላይ መግቢያ
1.1. የጳውሎስ ፅሁፎች

በአጠቃላይ ከሃያ ሰባቱ የአዲስ ኪዳን መጸሐፍት ውስጥ የጳውሎስ የሚባሉት አሥራ ሶስት የሚያክሉት ሲሆኑ ይህም ከአዲስ ኪዳን
መጸሐፍት ውስጥ አብዛኛው እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡መጸሐፍቶቹ እጅግ ጠቃሚ ሊባሉ የሚችሉ ናቸው፡፡ይህም በተለያየ ምክንያት
ነው፡፡ትረንስ ጠቃሚ ጥቅሞቹን ሲጠቅስ አንድም የቀደመችው ክርስቲያናዊ እንቅስቃሴን ወካዮች መሆናቸው ላይ ነው፡፡ይህም
አንዳንዶቹ እውነተኛ ታሪኮችን የሚያትቱ እውነተኛ ደብዳቤዎች ናችው፡፡ይህም አንዳንድ ጌዜ በጣም ግላዊ ደብዳቤዎች ሲሆኑ
እነዚያም የፀሐፊውን ፍላጎት፤ስሜት ሀሳብ እንዲሁም ማንነቱን ሁሉ በግልፅ የሚያሳዩ ናቸው፡፡

ፀሐፊው አብይ ወካይ ስለሆነ ያንን ዘመን ለማየት እንደ መስኮት ሊያገለግል ይችላል፡፡የወካይነት ሚና ብቻ ወይም መስኮት ከፋች
ብቻ ሳይሆኑ ሁለተኛው ጥቅማቸው የሰውን ህይወት ነኪ መሆናቸው ይለያቸዋል፡፡ ይህም የመጀመሪያ አንባቢዎቹን ብቻ ሳይሆን
በየዘመናቱ (በዚህ ዘመን ቢሆንም) ያሉትን ሁሉ የሚነኩ ፅሁፎች ናቸው፡፡ይህም እንደ ቅዱስ አውጎስጢኖስ መለወጥ (ሮሜ 13፡13-
14 ሲያነብ)፤ ከሮሜ መልዕክት ለማዘጋጀት በሚያደርገው ጥረት ሉተር ጻድቅ በእምነቱ በህይወት ይኖራል (1፡17) በማንበብ
መለወጡን እንዲሁም ጆን ዊስሌ የሉተርን የሮሜን መቅድም ሲነነብ በመስማቱ ልቡ ሲቀጣጠል ስናይ የጳውሎስ መልዕክቶች ለዋጭ
ናቸው የሚል ግንዛቤ እንድኒዝ ሊያደርገን ይችላል፡፡1

ምንም እንኳን ጥቅማቸው ብዙ ቢሆንም የጳውሎስ መልዕክቶች ግን ከባድ አይደሉም ብሎ ማለት አይቻልም፡፡ይህንንንም ጴጥሮስ
ቀድሞ አጢኖት የጳውሎስ መልዕከቶች ለመረዳት ከባድ ናቸው በማለት ተናግሮ ነበር (2 ጴጥ 3፡16)፡፡ትረንስ የጳውሎስን መልዕክቶች
ክብደት ሲያብራራ በአውድ ውስጥ የተገለፀ ንግግር ነው ይለናል፡፡ይሀም የስልኩን የወዲያኛውን ድምፅ ተናጋሪ እንዳለመስማት
እንደሆነ ይነግረናል፡፡2ለዚህም ተጠቃሽ የሚሆነው የታወቀ ወንድም (2 ቆሮ 8፡17) እንዲሁም በገላተያ የሚያውኳችሁ የተባለው
አባባል (ገላ 5፡12) ግልፅ አይደለም፡፡ከሁሉ በላይ እነማን ናቸው ያደረጉትን ያደረጉበት መነሻ ምክንያት (motive) ምንድነው? ብለን
ብንል መልስ የለንም፡፡

ሊቃውንት የጳውሎስን መልዕክቶች በሶስት ትልልቅ ክፍሎች ይከፍሏቸዋል፡፡እነዚህም አንደኛ በሚሲዮናዊ ጉዞ ላይ እያለ የጻፋቸው
ናቸው፡፡ይህም ሦስት ሚሲዮናዊ ጉዞ ባደረገባቸው አስር ዓመታት ጊዜ ውስጥ የተጻፉ ናቸው (ከ 48-58)፡፡3 የመጀመሪያው ሚሲዮናዊ
ጉዞ ወቅት ገላተያን (ገላተያ አጨቃጫቂ ነው)4 ፤ሁለተኛው ላይ 1 ኛ እና 2 ኛ ተሰሎንቄን እንዲሁም ሶስተኛው ላይ 1 ኛ እና 2 ኛ
ቆሮንቶስን እና ሮሜን ፅፏል፡፡5በሁለተኛ ተራ ውስጥ የሚካተቱት የእስር ቤተ መልዕክቶች ሲሆኑ እነርሱም
ኤፌሶን፤ቆላሲስ፤ፊሊጲሲየስ እና ፊልሞን ናቸው፡፡ሦስተኛ የመጋቢያን መጸሐፍት የሚባሉት ናቸው፡፡እነዚህም ውስጥ ሊካተቱ
የሚችሉት 1 ኛ እና 2 ኛ ጢሞቴዎስ እና ቲቶ ናቸው፡፡

1.2. የጳውሎስ ታሪክ

ጳውሎስ ለረጅም ዓመታት የጠርሲሱ ጳዉሎስ በመባል ይታወቅ ነበር፡፡በጠርሴስ ኪልቅያ ከአይሁድ ቤተሰቦች እንደተወለደ ታሪኩ
ይዘግባል፡፡ በእርግጥ አይሁዳዊ ብቻ ሳይሆን ፈሪሳዊ እና የፈሪሳዊ ልጅ፤ ከዕብራዊ ዕብራዊ (ዕብራይስጥ ወይም አራማይክ ተናጋሪ)፤
ከቢንያም ወገን የነበረ፤ በልጅነቱ ድንኳን መስፋትን የተማረ እንደነበረ ከራሱ የህይወት ምስክርነተ መረዳት ይቻላል (የሐዋ 23:6;
ፊሊ 3:4-5;የሐዋ 18:3).በልጅነት ወደ ኢየሩሳሌም በመጓዝ በሂላል ትምህርት ቤት መምህር ከነበረው ከገማልያል እግር ስር የተማረ
እንደነበር መፀሀፍ ቅዱስ ያረጋግጥልናል (የሐዋ 22:3)::በትምህርቱም በወቅቱ ከነበሩት ቀናተኛ አይሁድ በበረታ ሁኔታ ለአባቶች ወግ
የሚቀና ነበር(ገላ 1:14)፡፡

1
Terence L. Donaldon, “Introduction to the Pauline Corpus” in The Pauline Epistle ed. John Muddiman and John Barton (New York:
Oxford university press, 2001.
2
Terence L. Donaldon, 29.
3
David K Lowery “a theology of Pau’s Missionary Epistel” in A Biblical Theology of the New Testament, (Chicago : Moody Press, 1994) 244.
4
See David K Lowery “a theology of Pau’s Missionary Epistel” in A Biblical Theology of the New Testament, 244.ደቡብ ገላተያ ከሆነ
(አንጾኪያ፤ኢቆኒየን ልስጥራን እና ደርቤ) በመጀመሪያው ሚሲዮናዊ ጉዞ (የሐዋ 13-14)፡፡ነገር ግን ሰሜን ከሆነ ሁለተኛው ሚሲዮናዊ ጉዞ ላይ (16፡6) ሲሆን ዳግመኛ
ወደዚህ ወደ ሰሜን ገላተያ በሶስተኛው ጉዞ ስለተመለሰ (የሐዋ 18፡23) 1 ቆሮ ከመጻፉ በፊት ከኤፌሶን ወይም በቆርንቶስ ሆኖ ሮሜን ከጻፉ በፊት ሊሆን ይችላል፡፡
5
David K Lowery “a theology of Pau’s Missionary Epistel” in A Biblical Theology of the New Testament, (Chicago : Moody Press, 1994) 244.
ይህም ቅናቱ ቤተ ክርስትያንን ያለ ልክ እንዲያሳድድ ያበቃው ሲሆን እንደወጣት ፈሪሳዊነቱም እስጢፋኖስ ሲወገር እና ሲገደል
ተባብሮ ነበር (Acts 7:58-83):: በክርስትያኖች ላይ ያደረገው ዘመቻ በህጋዊ ደብዳቤ የታገዘ ክርስትያን አህቶችን እና ወንድሞችን
የማሰር የክርስቶስ ቤተክርስትያን ለኪሳራ የዳረገ ነበር (የሐዋ 26:10-11; የሐዋ 1:13):: ከእንደዘህ አይነት ዘመቻዎች በአንዱ
ማለትም ወደ ደማስቆ በሚያደርገው ጉዞ ነዉ ለመለወጥ የበቃው፡፡

ጳውሎስ የግሪክ ባህል አሻራ ያረፈበት ሲሆን በትክክልም የግሪክ ትምሀርት የተቀበለ እንደነበረ ማወቅ ይቻላል ( የሐዋ 17:28፤ ቲቶ
1:12)እጅግ የዳበረ የግሪክ ባህል ያረፈበት ከመሆኑም በላይ የእነርሱ አስተሳሰብ ይንፀባረቅበት ነበር፡፡ እንግዲህ በዚህ ሁሉ ባህል እና
አስተሳሰብ ውስጥ ማደር ማለት የዘመኑን አባባሎች እና ፀሀፍት እንግዳ አለመሆኑን ማየት ይቻላል፡፡በተጨማሪ ጳውሎስ በመወለድ
ያገኘው ሮማዊ ዜግነት ያለው ሰው ነበር (Acts 22me:28)::ከዚህ የተነሳ ወደ ቄሳር ይግባኝ ማለት አስችሎታል (የሐ 16:37-39)፡፡
ከዚህ የተነሣ ጳውሎስ ለአህዛብ ሐዋርያ ለመሆን ብቃት እንዳለው ማየት ይቻላል፡፡ስለዚህ በቀላሉ እንዲህ ብሎ ማለት ይቻለዋል እኔ
በሁሉ ነገር ሁሉንም ሆነኩኝ አንዳንዶችን አድን እንደሆነ ብዬ (1 የሐዋ 9:22)፡፡ 6

የሐዋርያት ስራን እንደ ጳውሎስ የታሪክ ዘገባ ምንጭነት መጠቀም ከጥያቄ ነጻ ነው አያስብልም፡፡ አንድም ለምንድነው ፀሐፊው
(ሉቃስ) የጳውሎስን በጥድፊያና በሀዘን የተሞላ የቆሮንቶስ ጉብኝት (2 ቆሮ 2፡1)፤ የተለያዩ መከራዎቹን (በተለይም መርከብ መሰበር
2 ቆሮ 11፡23-27) ያልዘገበው?ሁለተኛ ጥያቄ የሚጭረው ጉዳይ የገላ 1፡18 እና የሐዋ 9፡26-30 መጣረሳቸው ጉዳይ ነው፡፡ይህም
ከተለወጠ በኃላ በሐዋርያት ስራ ላይ ትልቅ ግምት የተሰጠው ጉብኝት ሲሆን ያም በርናባስ እስኪያሳምናቸው ድረስ የጳውሎስን
ማመን መቀበል ከብዷቸው ነበር፡፡ነገር ግን በገላተያ ላይ የጳውሎስ ወደ ኢየሩሳሌም የመውጣቱ ጉዳይ ብዙ ትኩረት እንዳይስብ
ተደርጓል፡፡እንዲሁም ወደ ኢየሩሳሌም የመሄዱ ጉዳይ ኬፋን ለማየት ቢሆንም ከያዕቆብ በስተቀር ማንንም ማየት እንዳልቻለ
ይነግረናል፡፡እንዲሁም አብዛኞቹ በዓይን አይተውት እንደማያውቁ እና ድሮ አሳዳጅ የነበረ እንደተለወጠ ብቻ እንደሰሙ ይናገራል፡፡፡ 7

ወደ ውስጥ ገብተን ስንመለከት ልዩነት ቢኖርም የሚያመሳስላቸው ጉዳይ ግን ብዙ ነው፡፡ለምሳሌ ደማስቆ ላይ እንደተቀየረ (ገላ 1፡
15-17፤ የሐዋ 9፡9-19) ተከትሎ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ (ገላ 1፡18፤ የሐዋ 9፡26) በቂልቂያ ጠርሴስ መቆየቱ (ገላ 1፡21 የሐዋ 9፡30)
ከዚያ ወደ ሶሪያ እንፆኪያ መሄዱ (ገላ 1፡21 የሐዋ 11፡25-26)፡፡

1.3. የጳውሎስ መለወጥ


ጳውሎስን የኢየሱስ ክርስቶስን ቤተ ክርስትያን ያለ መጠን እያሳደደ በነበረበት ጊዜ በደማስቆ መንገድ ላይ በክብር የተሞላው ጌታ
እንደተገናኘው መፀሐፍ ቅዱስ ይተርክልናል፡፡ይህ ደግሞ ተአምራዊ ለውጥ በህይወቱ እንዲከሰት ምክንያተ ሆኗል፡፡ተረንስ ጳውሎስ
የቀድሞ የጳውሎስ ምልከታን በሞገተበት ፅሁፉ ጳውሎስ የይሁዲ እምነት የጎደለው አንዳች ነገር እንዳለ የተገነዘበ መሆኑ እና ይህም
መዳን በስራ የሚለውን መዳን በእምነት ከሚለው ጋር አነጻጽሮ ነው እያሉ ቀደምት የጳውሎስ ምልከታ አራማጆች ይነግሩናል
ይላል፡፡8ለውጥ ቅፅበታዊ ስለሆነ ይህ ትክክል ሊሆን አይችልም፡፡

ጳውሎስ ኢየሱስ የእግዚአብሄር ልጅ እና መሲህ ነው ብለው የሚያስቡትነ የክርስትያኖነችን አመለካከት የሚክድ ነበር፡፡እንዲሁም
እስጢፋኖስ ስለክርስቶስ መነሳት እንዲህ በማለት የሰጠውን ምስክርነት አነሆ ሰማይ ተከፍቶ የሰውም ልጅ በእግዚአብሔር ቆሞ
አየዋለው ሲል ከተቃወሙት ቀንደኛው ነበር (የሐዋ 7:56):: ውሸታም በማለት እስጢፋኖስ ላይ በመጮህ እንደ ወገሩት የሐዋርያት
ስራ ፀሐፊ ይዘግብልናል. ሳኦልም በእስጢፋኖስ መገዳል ተስማምቶ ነበር፡፡ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳኦልን በደማስቆ መንገድ ላይ
በተናገረው ጊዜ እስጢፋኖስ ትክክል እርሱ ግን ተሳስቶ እንደነበረ ተገንዝቧል፡፡ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ ሲረዳ ወዲያው በደማስቆ
መኩራብ ኢየሱስ ህያው መሆኑን እና ከመሞት እንደተነሳ ለማወጅ አልቸገረውም፡፡

ምንም እንኳን በደማስቆ መንገድ ላይ ያጋጠመው ልምምድ ድንገተኛ እና ተአምራዊ ቢሆንም የተለወጠው ግን ለዘለቄታው ነበር፡፡
የለውጡ ተፅህኖ ስነልቦናው እና በእውቀት አድማሱ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አሳድሮበታል፡፡ ይሄ ደግሞ እንደሚገባ የተብራራው
ኢየሩሳሌምን ከመጎብኘቱ በፊት በአረብያ እና ደማስቆ ምድር ለአስራ አራት ዓመታት መሆኑ ልብ ማለት ይቻላል(ገላ 1:16-19)፡፡9

6
Hampton Keathley, Concise New Testemant survry, (Michigan: Grand Rapid, 1977) no page.
7
Terence L. Donaldon, 29.
8
Terence L. Donaldon, 29.
9
Hampton Keathley, Concise New Testemant survry, (Michigan: Grand Rapid, 1977) no page.
1.4. ታሪኩን ማደራጀት
ሀ. ከገላተያ 1-2 እና የሐዋ 9-11 ተንተርሰን የጳውሎስን ሚሲዮናዊ ታሪክ ማደራጀት እንችላለን፡፡ከተለወጠ በኃላ ለጥቂት ጊዜ
ደማስቆ ከተማ ውስጥ ተቀምጧል (የሐዋ 9፡19) ይህም የሆነው ወደ አረበያ በረሀ ከመሄዱ በፊት ነው (ገላ 1፡17)፡፡በዚህ ጊዜ ኮስተር
ያለ አገልግሎት ውስጥ ገብቶ ነበር (2 ቆሮ 11:32)፡፡

ለ. ከተወሰነ ጊዜ በኃላ ወደ ደማስቆ ተመልሷል (ገላ 1:17; የሐዋ 9:20–22?), ይህ አገልግሎት ጊዜ በአይሁድ እና በንጉስ አርቴስ
የሞት ዛቻ ምክንያት የአገልግሎቱ ጊዜው አጭር ነበር (2 ቆሮ 11:32; የሐዋ 9:23–24)፡፡እንግዲህ እንደ ሐዋርያት ስራ ሳይሆን በዚህ
በሁለተኛው የደማስቆ ጉብኝቱ ነው በመስኮት በቅርጫት ከቅጥር ላይ የወረደው (2 ቆሮ 11:33; የሐዋ 9:25-ካርሰን-363),

ሐ.ከዚህ ጊዜ በኃላ ነው እንግዲህ ባርናባስ ጳውሎስን ለአገልግሎት አብሮት እንዲሄድ የጋብዘው (የሐዋ 11፡25-26)፡፡ምናልባትም
በዚህ ጊዜ ነው ለረሀብ እርዳታ የተደረገው (የሐዋ 11፡25-26)፡፡ምናልባትም ጳውሎስ በአንፆኪያ የተገኘው ከዳነ ከ 12 ወይም 13
ዓመት በኃላ ነው፡፡ምናልባትም በዚህ ጊዜ ነው ሐዋርያት ስራ ያልዘገባቸው ጉዳዮች የተከናወኑት (1 ቆሮ 11፡22-27)፡፡

ሀ ለ
መለወጥ
(Gal. 1:15–16 = Acts 9:1–19)
3 yrs 3 yrs.
First Jerusalem visit
(Gal. 1:18 = Acts 9:26–30)
14 yrs 14 yrs.
Second Jerusalem visit
(Gal. 2:1–10 = Acts 11:27–30) 14 years Total time
17 years

1.5. የጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ


የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉዞውን ሉቃስ ሲያስተዋውቅ እንመለከታለን (የሐዋ 13፡1-3)፡፡ይህ ምናልባትም ምንም ዓይነት ግንኙነት
ከእርሱ በፊት ካለው ታሪክ ጋር ዝምድና የሌለው ይመስላል፡፡ነገር ግን ታሪኩን ቀድሞ አንፆኪያ ጋር ከነበረው ታሪክ ጋር ዝምድና
ይኖረዋል (ሐዋ 11፡19-30)፡፡በዚህ ጉዞ የተካፈሉት በርናባስ፤ዮሐንስ የተባለው ማርቆስ እና ጳውሎስ ራሱ ሲሆኑ ያካለሉት ስፍራ
በደቡብ ገላተያ የሚገኙትን ሀገራት ነው፡፡እነዚህም ጲስዲያን፤አንጺዮክ፤ኢቆኒየን፤ልስጥራ እና ደርቤ ናቸው (የሐዋ 13፡4-14፡26-
Carson-364)፡፡.

ከመጀመሪያው ጉዞ በኃላ ጳውሎስ እና ባርናባስ በአንፆኪያ ለረጅም ጊዜ አሳልፈዋል (የሐዋ 14፤28-ገላ፡2፡11-14- Carson-364).)
ይህም ወደ ኢየሩሳሌም ጉባኤ ሳይሄዱ በፊት ነው (የሐዋ 15፡29)፡፡ነገር ግን ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ ካደረጉ በኃላ ወደ እንጾኪያ
ተመልሰው ለጥቂት ጊዜ ተቀምጠዋል (የሐዋ 15፡30-33) በዚህ ጊዜ ነው ዮሐንስ የተባለው ማርቆስ ለሐዋርያዊ ጉዞ ይመጥናል
አይመጥንም በሚል ከተከራከሩ በኃላ በመካከላቸው መከፋፋት ተከስቶ ለየብቻቸው እንደሄዱ ይናገራል(የሐዋ 15፡36-41)፡፡.

ሁለተኛው የጳውሎስ ሚሲዮናዊ ጉዞ ወደ ደቡብ ገላተያ የተደረገ ሲሆን ያም በትንሹ ኤሼያ የተደረገ እና መቄዶንያን ፊሊጲሲዮስን
(1 ተሰ 2፡2) እንዲሁም ተሰሎንቄ ቤሪያ (የሐዋ 17፡10-15) አካያን አቴንስን (1 ተሰ 2፡2 ፊሊ 4፡15-16) እና ቆሮንቶስን (2 ቆሮ 11፡7-
9) ያካለለ ነበር፡፡ጳውሎስ ወደ ቆሮንቶስ በመጣ ጊዜ ለስምንት ወራት ቁጭ ብሎ እንዳስተማረ ሉቃስ ማብራሪያ ሰጥቷል (የሐዋ 18፡
11)፡፡

ሶስተኛው የጳውሎስ ሐዋርያዊ ጉዞ የጀመረው ከአንፆኪያ ሲሆን በሁለተኛው ሚሲዮናዊ ጎዞ እንዳደረገው ገላተያን ጲርጊያን ደርቤን
ልስጥራን ኢቆንዮንን ጲስዲያን ዳግመኛ ጎብኝቷል፡፡ከዚያ ወደ ኤፌሶን አቅንቶ በዚያ ጵርስቅላንና አቄላን አግኝቷቸዋል (የሐዋ 18፡
23-19፡41- page 317-Gundry)፡፡
1.6. አዲሱ እይታ
መቼም ጳውሎስ ለይሁዲ እምነት ያለው አተያይ ምንድነው የሚለውን የ 16 ኛው ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን አዳሾች የሰጡት
ምላሽ ተፅእኖ ፈጣሪ አተያይ ነው፡፡እንግዲህ ሉተርም ሆኑ ካልቪን በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክር ውስጥ መዳን ህግ በመጠበቅ ነው
የሚለውን አተያይ ይሁዲም እንደዚያው እንደሆነ ተረድተውት ነበር፡፡ይህንንም ህግ ጠባቂነት ጳውሎስ በገላተያ መጸሐፍ
ተቃውመውታል ብለው ሙግት ገጥመው ነበር፡፡የቤተ ክርስቲያን አዳሾች በጳውሎስ ጊዜ የነበሩት አይሁድ ለመጸደቅ ህግን መጠበቅ
የሚል መዳን በስራ የሚል አተያይ ስለነበራቸው ጳውሎስ የነቀፈው ያንን አተያይ ነው በማለት ሀሳብ አቅርበው ነበር፡፡

ታዲያ ጳውሎስ ይህን ለመዳን ህግ መጠበቅ የሚለውን አተያይ በመንቀፍ ለመጸደቅ ማመን ነው ይህም ደግሞ የሰውን ስራ ፈጽም
የማይቀበል ነው በማለት የ 16 ኛው ክፍለ ዘመን አዳሾች አምነው ሞግተዋል፡፡ከዚህ የተነሳ የጳውሎስን መጎናጸፊያ ለብሰው
ለመጸደቅ ማመን ነው በማለት ሞገቱ (Carson-375)፡፡በ 16 ኛው ክፍለ ዘመን የተነሱት የቤተ ክርስቲያን አዳሾች ጳውሎስም ሆነ
ኢየሱስ የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ይሁዲነት ልክ ህግ ተኮር (legalistic) እንደሆነ አድርገው ይቃወሙት እንደነበረ አድርገው
ተረድተው ነበር፡፡ይህም የአዲስ ኪዳን አስተምህሮ ይሁዲነትን በዚህ መልክ ተረድተው እንደነበር ግልፅ ነው (Carson 376)፡፡

ነገር ግን በ 1977 ኢፒ ሳንደር የሚባል ሰው ጳውሎስ እና ፓላስቲኒያን ጁዳይዝም የሚባል መጸሐፍ አሳተመ፡፡ይህም የቤተ ክርስቲያን
አዳሾች ጳውሎስ ይሁዲነትን ከተረዱበት አረዳድ የተለየ እና በይሁዲነት አረዳድ ላይ ሌላ ዕይታ የፈነጠቀ የልዩነት ነጥብ ሆኗል፡፡
የሳንደርስ የመከራከሪያ ነጥብ “ይሁዲነት ህጋዊነት (legalistic) ነው” የሚለው ምልከታ ስህተት ነው የሚል ነው፡፡ብዙ ሰነዶችን
ካገላበጠ በኃላ ሳንደርስ ይሁዲነት ድነት በቃል ኪዳን ውስጥ ለመኖር የሚደረግ ህግ ጥበቃ (“covenantal nomism) እንጂ ድርቅ ያለ
ህግ ጥበቃ (legalistic) አይደለም የሚል ነው፡፡ስለዚህ ድነት ለእስራኤል እግዚአብሄር በቃል ውስጥ እንዲኖሩ ከሰጠው ቃል ኪዳን
የሚመነጭ ነው፡፡እግዚአብሄር እስራኤልን መረጠ ያም ምርጫ የድነት መሰረት ነው ብሎ ሳንደርስ ሞገተ፡፡ስለዚህ ህግ መኖሪያ (በቃል
ኪዳኑ ውስጥ) እንጂ መግቢያ አይደለም (Carson376)፡፡

ትልቅ ተቀባይነት ያገኘው ምላሽ ግን በጄምስ ደን የተሰጠው ነው (Carson-377)፡፡ይህም ጳውሎስ የተቃወመው ወግ አጥባቂነት
(legalism) ሳይሆን ድነት በእነርሱ ዘር ብቻ ታጥሮ እንዲቀመጥ መፈለጉ ነው፡፡ታዲያ ይህ አዲስ የጳውሎስ ይሁዲነት ዕይታ
ከመጸሐፈቅ ቅዱስ ጋር ምን ያስተሳስረዋል?ጥያቄው ታዲያ ጳውሎስ ከይሁዲነት ምንድነው የተቃወመው? የሚል ጥያቄ ይነሳል፡፡
ሳንደርስ ሲመልስ ጳውሎስ ለመዳን በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን የሚለው ሀሳቡ እጅግ አግላይ አድርጎት ስለነበር ይሁዲነት በቃል ኪዳን
ውስጥ ህግን በመጠበቅ መኖር (covenantal nomism) የሚለውን ከነአካቴው ተቃውሞታል ብሎ ለመሞገት ጥረት አደረገ፡፡

ይህ መልስ ግን ብዙ ሊቃውንትን አላረካቸውም(Carson 376)፡፡ጳውሎስ ታዲያ ምንን ነው የተቃወመው ለሚለው ምላሽ


እንዲሆን ብዙ ምላሾች ተሰጥተዋል፡፡ፅንፍ የረገጠው ምልከታ መካከል ጭራሽ ጳውሎስ ጭራሽ ይሁዲነትን (ልማዶች እና
ለምምዶች) አልተቃወመም እና አይሁዶች በራሰቸው ቃል ኪዳኑ ውስጥ ድነትን ማግኘት ይችላሉ በማለት ምላሽ ለመስጠት ጥረት
ተደርጓል፡፡እናም አህዛብ ብቻ ናቸው ክርስቶስን እንደ አዳኝ የወሰዱት የሚለውን እጅግ ፅንፍ የረገጠ ምልከታ ነው፡፡

ወይም በድነት ጉዳይ የብሄር አግላይነትን ነው (Carson-377) በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡በጄምስ ደን እና በቀደምት ተርጓሚዎች
መካከል ሮሜ 3፡20 (ሮሜ 3፡28፤ ገላ 2፡16 3፤2 5፤10) ፍቺ ላይ አለመስማማታቸው ነው፡፡የልየነት ነጥቡም የህግ ስራ የሚለው ቃል
ነው፡፡የቤተ ክርስቲያን አዳሾች (አብዛኛው ኢቫንጄሊካል) ጳውሎስ የህግ ስራ ሲል በህግ መጽደቅን ማለቱ ነው ብለው ይረዱታል፡፡
እንደ ሳንደርስ አረዳድ ከሆነ ማንም ይሁዳዊ (ጳውሎስም ቢሆን) ይሁዲነትን እንደ ደረቅ ህግ ተከታይ (legalism) አድርጎ ሊሞግት
አይችልም፡፡ለዚህ ነው ጄምስ ደን ጳውሎስ የተቃወመው የብሄር አግላይነትን (ethnic exclusivism) ነው በማለት ምላሽ የሰጠው፡፡
ቀደምት ተርጓሚዎች እንደተረዱት ህግን መጠበቅ ብለው በጭራሽ አይደለም ብሎ ደን ተከራክሯል፡፡ህግ ቶራ ማለት ሲሆን ይህም
ይሁዲዎችን ይሁዲዎች እንዲሆን ያደረጋቸው እና ከሌሎች አህዛብ ራሳቸው ለይተው እንዲኖሩ ያደረጋቸው ጉዳይ ነው ብሎ
ተከራከረ (Carson-377)፡፡

ስለዚህ አይሁዶች ሲኖሩ ከሌሎች አህዛብ ተለይተው እንዲኖሩ ያደረጋቸው የአመጋገብ ህግጋት መገረዝ እና ሰንበት ናቸው በማለት
ለማብራራት ጥረት አድርጓል ደን (Carso-378)፡፡

ነገር ግን እንደ ሽራይነር ከሆነ የህግ ስራ የሚለውን ይሁዲነትን በአህዛብ ላይ ከመጫን ጋር ተያይዞ የተነገረ አይደለም፡፡ይልቅ ጳውሎስ
የህግ ስራ ሲል ለጽደቅ የሚደረግ ስራ ነው ይለናል ሽራይነር (ሮሜ 3፡24 ገላ 2፡16)፡፡ጽድቅ በህግ በኩል ቢሆን ኖሮ በክርስቶስ በኩል
የተገለጠው ጸጋ ከንቱ ይሆን ነበር (ገላ 2፡21)ከዚህ ተነስተን ጸጋ እና ስራ እርስ በእርስ የሚቃረኑ ጉዳዮች ናቸው፡፡ድነት በስራ ቢሆን
ኖሮ ልክ እንደ ደሞዝ የተገባን በሆነ ነበር (ሮሜ 4፡4)፡በተቃራኒው ጳውሎስ ድነት የተሰጠው ለማመሰሩት ነው ብሏል (ሮሜ 4፡4
ሮሜ. 4:5Thomas R. Schriener-348)፡፡መመረጥ ራሱ እንደ ጸጋ እንጂ እንደ ስራ ሊሆን አይችልም (ሮሜ 11፡6)፡፡ጽድቅ በስራ
ቢሆን ኖሮ ድነት ለኀጢያተኞ ባልተሰጠ ነበር (ሮሜ 4፡13-16-Thomas R. Schriener-348)፡፡
ክፍል ሁለት

2. የሐዋርያት ስራ
2.1. መግቢያ
2.1.1. ፀሐፊ
ሉቃስ እና የሐዋርያት ስራ በጥሞና ከተመለከትነው ተመሳሳይነት ያላቸው መጸሐፍት ናቸው፡፡መግቢያው ራሱ ተመሳሳይነት አለው፡፡
ያም ፀሐፊው የተማረ (ሉቃ 1፡1-4 ምርጥ ግሪክን ቋንቋን ተጠቅሟል) እንደሆነ መረዳት ይቻላል፡፡ከመጀመሪያው ሐዋርያት መካከል
አልነበረም፡፡ምክንያቱ ከመጀመሪያው የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን በማለት ስለሚናገር እርሱ ከመጀመሪያዎቹ
አገልጋዮች መካክል እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ያ ብቻ ሳይሆን በመካከላችን በሆነው ነገር የሚለው የድርጊቱ ተካፋይ እንደሆነ ግልፅ ነው
(290 ካርሰን እና ሙ)፡፡ሌላው እኛ የሚሉት (እስከ 16፡ 8-10 ድረስ ሄዶ ከዚያ ደግሞ ከ 20፡5-15 21፡1-18፤ እና 27፤1-28፡16 ሲቀጥል
ይታያል) እነዚህ ዓረፍተ ነገሮች የሚነግሩን ጸሐፊው የድርጉቱ አካል ሆኖ ክስተቱን እንደ ዘገበ ነው፡፡

ነገሩ እንዲህ ከሆነ ፀሐፊው ጳውሎስ ከጥራዎስ ተነስቶ ወደ ፊሊጲሲየስ ሚሲዮናዊ ጉዞ ሲያደርጉ አብሮት ነበር (290 ካርሰን እና
ሙ)፡፡በኃላ ላይ ከጳውሎስ ጋር ፊሊጲስየስ ሦስተኛ ሚሲዮናዊ ጉዞ ሲያደርግ በሚሊጢ ተገናኝተዋል ከዚያ ከሚሊጢን ወደ
ኢየሩሳሌም ጉዞ አድርገዋል (20፡5-15፤ 21፡1-18)፡፡በመጨረሻ ከጳውሎስ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ አድርገዋል (27፡1-28፡16-290
ካርሰን እና ሙ)፡፡

ታዲያ ጸሐፊዎ ከጳውሎስ ጋር በሮም ታስሮ ስለነበር ያንን ስም በዚያን ወቅት (በሮም ለሁለት ዓመት በታሰረ ጊዜ) በጻፋቸው
ፅሁፎች የጠቀሳቸው መካከል መሆን አለበት እነዚህም ማርቆስ ጀስቱስ ኢጳፍራ ዴማስ ሉቃስ ቲኪቆስ ቲሞጢዮስ አርስትራኮስ
ናቸው (እነዚህ ሰዎች በፊልሞን ቆላሲስ ኤፌሶች እና ፊሊጲሲየስ መጸሐፈፎች- 291 ካርሰን እና ሙ)፡፡

ሉቃስ ሀኪም ነው (ቆላ 4፤14) ስለሚል እና ሉቃስ በወንጌሉም ሆነ በሐዋርያት ስራ የህክምና ቃላት ስለሚጠቀም ጸሐፊው ሉቃስ
ነው የሚል ማብራሪያ በቅርቡ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ 10እንዲህም ሆኖ ግን ባርክሌይ ሉቃስ በደመ ነፍስ የህክምና ቃላት ይጠቀማል
በማለት ሀሳብ ሰንዝሯል፡፡

ከመጸሐፍ ቅዱስ ውጪ ያሉትን መረጃዎች ስናይ ደግሞ ሞራቶሪያን ቀኖና (180-200) ኢራኒየስ ጸረ ማርሶናይት መቅድም፤
ክሊመንት ዘአሌክሳንደርያ ቱርቱልያን ኢዩዚበስ ሁሉም ሉቃስ ጸሐፊው እንደሆነ ይሰማማሉ (291 ካርሰን እና ሙ)፡፡

2.1.2. የተጻፈበት ቀን
አብዛኛው የመጸሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት የሐዋርያት ስራን በሶስት ዘመናት ውስጥ ይመድቡታል ያም ከ 62-70፤ 80-95 እና 115-130
ዓ.ም መካከል ነው (296 carson)፡፡ሌሎች ደግሞ ከ 62 ብዙም ጊዜው አይርቅም ብለው ይናገራሉ፡፡ምክንያቱም 1. ሉቃስ ግልፅ ባለ
ሁኔታ የጳውሎስን መልዕክቶች አልጠቀሳቸውም ወይም ቸል ብሏቸዋል፡፡2. በኃላ በ 66 ዓ.ም አካባቢ በድንገት የተቀየረው
የይሁዲነትን ህጋዊ ሃይማኖትነት ሲታሰብ ፅሁፉ ከ 66. ዓ.ም በፊት እንደተጻፈ አመልካች ነው፡፡3. የሉቃስ የኒሮን ስደት አለመጥቀሱ
(ስደቱ ተከናውኑ ቢሆን ኖሮ በሆነ መንገድ ፅሁፉ ላይ ተፅህኖ ማሳረፉ አይቀርም ነበር)፡፡4. ግልፅ ባለ ሁኔታ የመርከብ መሰበር ትርክቱን
ሲያቀርብ የቅርብ ጊዜ ጉዳይ እንደሆነ ያሳያል (27፡1-28፡16 ካርሰን 300)፡፡

2.1.3. ዓላማ
አንደኛ አብዛኞቹ ሊቃውንት እንደሚያስቡት በሉቃስ 1፡1-4 ላይ የተጠቀሰው ዓላማ ማለት ስለሰማህው ቃል እርግጡን እንድታውቅ
እፅፍልሃለሁ የሚለውን ሀሳብ የዚህ የሁለተኛውም ክፍል ዓላማ አድርጎ መውሰድ ይቻላል (ካርሰን 301)፡፡

ሌላኛው ዓለማ ሊሆን የሚችለው እንዴት አድርጎ ወንጌል እንደተስፋፋ ታሪካዊ ዘገባ ለማቅረብ ነው ያም ከኢየሩሳሌም ጀምሮ
የምድር ጫፍ እስከ ምትባለዋ ሮም ደረስ ለማሳየት ነው፡፡እንደ ዶናልድ ጉተሬ ከሆነ ሉቃስ ታሪክን የታሪክን ክስተት በቅደም ተከተል
እንደሚዘግብ ዘጋቢ አልነበርም፡፡ወይም እንደ ታሪክ ምሁር አልዘገበም፡፡11 አንዳንድ ታሪኮችንም ቸል ብሏቸዋል ለምሳሌ ጳውሎስ
ከተለወጠ በኃላ ወደ አረቢያ በረሀ እንደሄድ እንዳልሄደ፡፡ 12

10
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World, ( Leicester: Inter-Varsity Press, 1994) 23.

11
Donald Gutherie, New Testamenet Introduction, () 261.
12
Donald Gutherie, New Testamenet Introduction, () 261.
ሦስተኛ ሉቃስ ነገረ መለኮታዊ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፡፡ይህም የእግዚአብሄር ዘለዓለማዊ ዕቅድ መሆኑ ያም ኢየሱስ መቋቋም
በማይቻልበት ሀይል ቤተ ክርስቲያኑን እንደገነባ ለማሳየት ነው (ማቴ 16፡18)፡፡ይህም የአምላክ በሰው ልጆች መካከል መስራት ሲሆን
ይህም አይሁድ እውነተኛ መሲያቸውን ሲተው ጉዳዩ እንዴት አድርጎ ወደ ሌላ (አህዛብ) እንደ ዞረ ለማሳየት ነው፡፡ዶናልድ ጉተሬ
ሲያብራራ ከኢየሩሳሌም ወደ ሮም የተደረገው እንቅስቃሴ እና የግሪክን ባህል መውረሱ ነገረ መለኮታዊ እንድምታ አለው ይለናል፡፡ 13

አራተኛ ሉቃስ የአቃቢ እምነት ዓለማ ያለው መሆኑ ይታያል፡፡እንደ ዶናልድ ጉተሬ ከሆነ ይህ አቃቢ እምነት አኪያሄድ አንድም
ከአይሁድ እና ከሮም አንጻር ነው፡፡14 ለአይሁድ ክርስትና የአይሁድ ተቀናቃኝ አይደለም የሚል፡፡ያም አንዳንድ ጊዜ ሐዋርያት
ስርዓቶችን ሲያደርጉ ያሳያል፡፡ሌላኛው ደግሞ ከሮም አንጻር ነው፡፡ይህም አብዛኛዎቹ የሮም መኳንንት ከክርስትና ጋር ያላቸውን
ግንኙነት በመጥቀስ ክርስትና በእምነቱም ሆነ በልምምዱ ምንም ዓይነት ችግር የማያመጣ መሆኑን ለማሳየት ጥረት አድርጓል፡፡ 15
ይህም ህግን የሚከትል መሆኑን ብዙ የህግ ስርዓቶችን እንዳከበረ ለማሳየት ይሞክራል፡፡

አምስተኛ ሊሆን የሚችለው እንደ ዶናልድ ጉተሬ ከሆነ የመንፈስ ወንጌል መሆኑን ነው፡፡ 16በሌላ አባባል ወንጌል ከኃላው መለኮታዊ
እጅ ያለበት ነው፡፡ከሰው ወይም በሰው የመጣ አይደለም፡፡ለዚህ ነው ቤተ ክርስቲያን የተወለደቸው በመንፈስ ጥምቀት ነው (2፡38)፤
በመንፈስ መሞላት ለእውነተኛ ክርስትና ምልክት ነው (2፡4፤6፡3፤8፡17፤10፡44፤19፡6)፡፡የመንፈስ ምሪት በሚሲዮን ስራ አስፈላጊነት
(13፡2፤16፡17፤)፡፡በስሙ ፈውስ መምጣቱ (3፡6፤ 4፡10)፡፡

2.1.4. ተቀባይ
ሉቃስ ልክ እንደ ሉቃስ ወንጌል ሁሉ ተቀባዩ ቴዎፍሎስ የሚባል ሰው እንደሆን ግልፅ ለማድረግ ጥረት አድርጓል፡፡ምናልባትም ይህ ሰው
የሉቃስ ወዳጅ እና የሚረዳው ሳይሆን አይቀርም፡፡ምናልባትም በገንዘብ ይደግፈው የነበረ ሰው ሊሆን ይችላል (ሉቃ 1፡1-301
ካርሰን)፡፡

2.2. ሀቲት
መጸሐፉ በሁለት ከፍለን ማየት ይቻላል፡፡አንደኛ ከምዕራፍ 1-12 ድረስ እንዲሁም ከምዕራፍ 13-28 ያለውን ማለት ነው፡፡ይህም
በሁለቱ አብይ ሐዋርያት ታሪክ ላይ ተንተርሰን የምንከፍለው ክፍፍል ነው፡፡ሉቃስ እያንዳንዱን ክፍል ሲዘጋ ወደ ተለየ ስፍራ
ከመሸጋገሩ በፊት አንድ ተመሳሳይ የቃላት አጠቃቀም ይጠቀም ነበር፡፡ ያም የጌታ ቃል እጅግ ያሸንፍ እና ይበዛ ነበር ይለናል (6፡7፣ 9፡
31፣12፡24፣ 16፡5፣ 19፡20 (1:8 carson-286)፡፡

የቤተ ክርስቲያን እና የተልዕኮዋ ጅማሬ (1:1–2:41)፡፡ሉቃስ ቤተ ክርስቲያንን እና ተልዕኮዋን ከኢየሱስ ቃላት እና ድርጊት ጋር
ያያይዛል፡፡ሐዋርያቱን ለሚመጣው መንፈስ ያዘጋጃቸው (1:4–5) እና ለአለም አቀፍ አገልግሎት ተልዕኮውን የሰጣቸው ከሞት
የተነሳው ኢየሱስ ነው17(1:8)፡፡ስቶት የሀዋርያቱን የአገልግሎት መሰረቶች መመረጥ፤ራሱን መግለጡ፤መመሪያ መስጠቱ እና
የመንፈስ ተስፋ መስጠቱ ነው በማለት ጥሩ አድርጎ አብራርቶታል፡፡18 እርገቱ የአገልግሎቱ ማብቂያ (1:9–11; ሉቃ 24:50–51) ነው፡፡

ምስክሮቼ የሚለው ትልቅ ቦታ የተሰጠው ጉዳይ ነው (1፡8)፡፡የመንግስቱ ጥያቄ ጉዳይ ተገልብጧል ያም መንግስቱ ውስጣዊ፤ዓለም
አቀፍዊ ሲሆን ቀስ በቀስ የሚስፋፋ ነው (1፡6-8)፡፡የዕርገቱ ታሪክ የሉቃስ ወንጌልን እና ሐዋርያት ስራን የሚያያይዝ ነው፡፡ዕርገቱ
የፋሲካ ቀን ወይስ ከ 40 ቀን በኃላ? (ሉቃ. 24:51), (የሐዋ 1፤9)፡፡19 40 ቀኑን መጥቀስ ያን ያክል አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፡፡እርገት
ታሪካዊነቱን የሚጠይቁ ሰዎች አሉ ግን ሉቃስ በአይን ምስክሮች ፊት የተደረገ ነው ማረጋገጫውን ይናገራል፡፡ 20የመላዕክቱ መልዕክት
ጥቅም ምንድነው? ይመጣል እና ወደ ስራ እንደሚመለሱ ሊሆን ይችላል፡፡ ማትያስ ይሁዳን ተክቶ ስለመመረጡ (1:12–
26),በጴንጤቆስጤ ቀን መንፈስ ቅዱስ መውረዱን በሶስት ክስተት ይነግረናል እነዚህም ድምጽ፤እሳት እና ልሳን ነው (2:1–13)፡፡
ታዲያ የልሳን ጥቅሙ ምንድነው?ዘርን ብሄርን ቋንቋን ያለፈ የመንፈስ አንድነት መሆኑን አመልካች ሊሆን ይችላል፡፡መንፈስ

13
Donald Gutherie, New Testamenet Introduction, () 262.
14
Donald Gutherie, New Testamenet Introduction, () 261.
15
Bailey, Mark ; Constable, Tom ; Swindoll, Charles R. ; Zuck, Roy B.: Nelson's New Testament Survey : Discover the Background, Theology and
Meaning of Every Book in the New Testament. Nashville : Word, 1999, S. 196
16
Donald Gutherie, New Testamenet Introduction, () 261.
17
See Thomas L. Constable, Notes on Acts, 31 የትንሳኤ ትርክት ጠቀሜታ አንደኛ፣ ዕርገት የኢየሱስ መክበሩ እና ጌትነቱ ማረጋገጫ ምልክት ነው፡፡ሁለተኛ
የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ቀጣይነት አመልካች ነው፡፡ሦስት የመንፈስ መምጣት አመልካች ነው፡፡አራት የትንሳኤ ፍጻሜ ነው አምስት የክርስትና ሚሽን ጅማሬ ነው፡፡
ስድስት፤ ለኢየሱስ መምጣት አመላካች ነው፡፡
18
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World, 82-86.
19
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World, 45.
20
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World,48.
ለመውረዱ ምልክትም ነው፡፡የመጀመሪያውን ሚሲዮናዊ ስብከት ይተርክልናል (2:14–41-ካርሰን 286)፡፡የኢየኤል ትንቢት ሙሉ
ለሙሉ ተፈፅሟል?ያ ግን አይደለም በሁለቱ በክርስቶስ ምጻቶች መካከል ያለው ጊዜ የመንፈስ ጊዜ በመባል ይታወቃል፡፡21

የኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን (2:42–6:7)


የቀድመዋ የኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ባህሪ ፍንጭ ይሰጠናል (2:42–47)፡፡ጆን ስቶት ይህን ሲዘረዝረው
ለትምህርት፤ለኀብረት፤ለአምልኮ እና ወንጌል ለማሰራጨት የምትተጋ ነበረች ይለናል፡፡ 22ጴጥሮስ የሚታወቅ ሽባ ሰውን ስለፈወሰ
ሳናርዲንን ለውሳኔ እንዲቸገር አድርጎታል (3:1–10)፡፡ይህም ጴጥሮስን ሌላ ስብከት እንዲያቀርብ አስችሎታል (3:13–26)፡፡ጴጥሮስ
እና ዮሐንስ በኢየሱስ ስም አትስበኩ ተብለው ቢባሉም እነርሱ ግን በፅናት ተቃውመውታል (4:1–22)፡፡እዚህ ጋ ለዘብተኞች ሉቃስ
በሌለበት እንዴት የሚስጥር ንግግራቸውን አወቀ? ብለው ለመሞገት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ነገር ግን ስቶት ጳውሎስ ወይም ገማለያል
ኖረው እና ተናግሮ ቢሆንስ ይለናል፡፡23ስደቱን በመፍራት ቤተክርስቲያን ቃሉን በግልጥነት ለመናገር እንድትችል ስትፀልይ በመንፈስ
እንደተሞላች ሉቃስ ይተርክልናል (4:23–31)፡፡

ሐዋርያት ቀላል ህይወት ይኖሩ ነበር፤አንድ ልብ ነበራቸው፤የጋራ ኑሮ (4፡32-37)፡፡ በዚህ መሐል ሁሉት ባለትዳሮች በፍቃድ ላይ
በተመሰረተ መካፈል ውስጥ ቤተክርስቲያንን ሲዋሹ ታይተዋል (4፡32-37)፡፡ለመሆኑ የነዚህ ሰዎች ኀጢያት ምንድነው? ግብዝነት
ነው፡፡ይህም የሰይጣን ተግባር ነው፡፡ኀጢያቱ መንፈስ ቅዱስን፤ቤተ ክርስትያንን ሲሆን ቅድስናንም አመልካች ነው፡፡ስቶት ይህን
ክስተት ከውግዘት ጋር አያይዞ ይናገራል፡፡ኀጢያታቸውም ፈጣን የሆነ ፍርድን አስከትሏል (5፡12-16)፡፡በህዝቡ መካከል የተደረገ ፈውስ
(5፡17-42) ዳግመኛ ተቃውሞን ሲቀሰቅስ እና ሐዋርያቱንም ለስደት ዳረገ (5፡12-16)፡፡የገማልያል ምክር ሐዋርያቱን ከእስር
እንዲፈቱ አድርጓቸዋል፡፡ሐዋርያቱ ሲወጡ በደስታ ነበር የወጡት፡፡ሌላ ችግር ተከሰተ ያም በምግብ እደላ ላይ አድሎ ነው፡፡መፍትሄው
ለቃሉ ለጸሎት እንዲተጉ፤ከራሳቸው ወገን የሆኑ ምግብ እንዲያድሉ (6፡1-6)፡፡ውጤቱም የሚገርም ሆነ ያም ቃሉ ተስፋፋ፡፡ስቶት
ለማህበረሰብ ስራ የሚተጋ በዚያ እንዲሰማራ ለቃሉ እና ለጸሎት የሚተጋ በዚያ እንዲሰማራ ጥሪ ያቀርባል፡፡

የአገልግሎት ወሰን ማስፋት፤ እስጢፋኖስ፤ሰማርያ እና ሳኦል (6:8–9:31).


አብዛኞቹ አማኞች ታማኝ የሆኑ አይሁዶች ነበሩ፡፡ከዚህ ነጥብ በኃላ ቤተክስቲያን ከአይሁድ አጥር ወጥታ የአገልግሎት ወሰኗን
አስፍታለች፡፡በዚህ ጉዳይ አብይ ሚና የተወጣው እስጢፋኖስ ነው፡፡ይህ ሰው በመቅደሱ እና በህጉ ላይ ከፉ ነገር ተናግሯል ተብሎ
የተከሰሰው በሀሰት ነው (6፡8-15)፡፡በአብርሃም (በሜሶፖቶሚያ)፤በዮሴፍ (በግብፅ ባሪያ ሆኖ)፤ሙሴ (በምድያም በቁጥቋጦ ውስጥ)፤
በዳዊት እና ሰለሞን ዘመን የእግዚአብሄር መገለጥ በአንድ ስፍራ አልተወሰነም በማለት ምላሽ ሰጥቷል (7፡1-53)፡፡በኃላ ለድፍረቱ
በድንጋይ ወግረውታል (7፡54-60-ካርሰን 287)፡፡አሟሟቱ ከክርስቶስ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡የእስጢፋኖስ ደፋር የሆነ አቋም ስደትን
አስከተለ ያም ከሐዋርያት በስተቀር ለስደት ዳረጋቸው (8፡1-3)፡፡

ከተሰደዱት መካከል አንዱ ፊሊጶስ ሲሆን እርሱም ወንጌል ለሰማራውያን አድርሷል፡፡ሰማራውያን ሲለወጡ ጴጥሮስ እና ዮሃንስ ወደ
እግዚአብሄር መንግስት እንዲቀላቀሉ በመንፈስ እንዲሞሉ ፀልየውላቸዋል (8፡4-25)፡፡ፊሊጶስ አሁንም በእግዚአብሄር መላአክ ተነድቶ
ወደ ለኢትዮጲያዊ መልዕክት አድርሶለታል (8፡26-40)፡፡ከዚያ ዋናው የአህዛብ ሐዋርያ የሆነውን የጳውሎስ መለወጥን ይተርክልናል
(9፡1-30)፡፡አንዳንዶች መለወጡን ሳይኮሎጂ ሲያጣጥሉት ሃሉሲኔሽን ነው ይላሉ፡፡የሰማው ድምጽ ትክክለኛ ነበር (9፡10-25)፡፡
ጳውሎስ በለውጡ አንደኛ አክብሮተ እግዚአብሄር ጨምሯል (ሲፀልይ ታገኘዋለህ)፤ከቤተ ክር ጋር ኀብረት ማድረጉ፤ (እውነተኛ
ለውጥ ከቤተ/ክር አያርቅም)፡፡የሳኦል የአገልግሎት ጅማሬ ክርስቶስ ተኮር፤በመንፈስ የሆነ፤ድፍረት የሞላው፤ ዋጋ የሚያስከፍል
ነበር(9፡26-31)፡፡ በኃላ ሉቃስ ታሪኩን ሲደመድመው ቤተክርስቲያን በረታች፤በጌታ ፍርሃት ገነነ እና በቁጥርም ትበዛ ነበር ይለናል (9፡
31-ካርሰን 287)፡፡

ጴጥሮስ እና የመጀመሪያው አህዛብ መለወጥ (9:32–12:24)


የሳኦል እና ቆርኖሊዮስ መለወጥ ክርስትና የአይሁድ ልብሱን እንዲጥል አደርጎታል፡፡ይህ ክፍል ትኩረት የሚያዳርገው በጴጥሮስ
አገልግሎት ላይ ነው፡፡ያም አህዛብ እንዴት አደርገው በእርሱ አማካኝነት እንደተለወጡ ነው፡፡ጴጥሮስ በሊዲያ ኢዮጴ ከኢየሩሳሌም
በሰሜናዊ ምዕራብ በአሉ አንዳንድ ከተሞች ላይ ወንጌልን ሰብኳል (9፡32-43)፡፡ጴጥሮስ ቆርኖሊዮስ ወደ እምነት እንዲመጣ
21
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World,73.
22
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World,73.
23
Stott, John R. W,The Message of Acts : The Spirit, the Church & the World,98.
ምክንያት ሆኗል (10፡1-23)፡፡በቆርኖሊዮስ ቤት በጴጥሮስ ስብከት መሃል መንፈስ ቅዱስ በጉባኤተኞቹ ላይ ሲወርድ ያም እግዚአብሄር
አህዛብን በመንፈስ ለማጥመቁ እንደ ምልክት ተደርጎ ሲወሰድ ይታያል (10፡24-48-ካርሰን 287)፡፡ሉቃስ ሊነግረን የፈለገው የአህዛብ
እና የአይሁድ ድብልቅ ቤተ ክርስቲያን እንደተጀመረች ነው (ካር 287)፡፡ክርስቲያን የሚል ስም ለአማኞች ተሰጥቷቸዋል (11፡19-0)፡፡
ይህ ክፍል የሚያበቃው ጴጥሮስ በተአምራት ከእስር ቤት እንደተፈታ በመተረክ ነው (12፡1-19)፡፡ይህም ታሪክ በዚሁ ሰበብ ሄሮድስ
አግሪጳ እንደሞት ይነግረናል፡፡ አሁንም ሉቃስ ተደጋጋሚ የመደምደሚያ ቃላቱን ሲናገር ይታያል፡፡ያም የጌታ ቃ እጅግ ይበዛ እና
ያሸንፍ ጀመረ በማለት ነው (ካርሰን -288)፡፡

የጳውሎስ የአህዛብ አገልግሎት (12:25–16:5)

የጳውሎስ አገልግሎት ዋናው ሀሳብ እንዴት ወንጌል ወደ አህዛብ እንደገባ እንዲሁም ከኢየሩሳሌምም ተነስቶ እስከ ምድር ዳርቻ
እንደደረሰ እና ወንጌልም ሆነ ክርስትና ለሮም ግዛት ስጋት አለመሆኑን ለማሳየት ተናግሮታል፡፡

ጳውሎስ በርናባስ እና ዮሐንስ ማርቆስን ወደ የመጀመሪያ ሚሲዮናዊ ጉዞ እንዲያደርጉ ተላኩ(12፡25-13፡3)፡፡ጉዞው መጀመሪያ ወደ


ሲፒረስ የተደረገ ሲሆን (13፡4-12)፡፡ከዚያም ወደ ትንሹ ኢሲያ ደቡባዊ ዳርቻ የተደረገ ጉዞ ሲሆን ከዚያም ፒሲዲያ የምትባል ከተማ
እንደደሩሰ ይዘግብልናል፡፡በዚያም ስፍራ ወንጌል ተኮር የሆነ መልዕክት ጳውሎስ አቀረበ (13፡13-14)፡፡በዚህ ስፍራ ተመሳሳይ የሆነ
የክስተት ውደት ይታያል፡፡ ያም የአይሁዶች ወንጌልን መቃወም፤ የወንጌል መልዕክት ውደ አእዛብ መዞሩ ከዚያ አይሁዶች ስደት
ማስነሳታቸው እና እነ ጳውሎስ ከዚያ ስፍራ ለቀው መውጣታቸው ነው (13:44-52)፡፡ጳውሎስ እና የስራ አጋሮቹ ወደ ኢቆኒየን
ሲሄዱ ሄደዋል (14፡21-28)፤ ጳውሎስ ወደ ተወገረበት ልስጥራ (14፡8-20) ወደ ደርቤ ደቀ መዛሙርትን እያበረቱ ተመለሱ(14፡21-
28)፡፡ወደ አንፆኪያ ሲመለሱ ለአህዛብ ወንጌልን በማድረስ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ተግዳሮት ገጥሟቸው ነበር፡፡ይህ ህግ የለሽ የሆነ
ወንጌል ለአህዛብ እንዳስተማሩ ተደርጎ ተወስዶ ነበር ከብዙ ክርክር በኃላ ዋና ሊባል የሚችል ውሳኔ ተወሰነ ያም ወንጌል እንዲያድግ
ምክንያት ሆነ፡፡

ጳውሎስ እና በርናባስ ሊያደርጉ በነበረው በሁለተኛው ሚሲዮናዊ ጉዞ ግጭት ተከስቶ ነበር፡፡ ያም ጳውሎስ ማርቆስን በሚሲዮናዊው
ጉዞ ይዞት መሄድ አልፈለገም ነገር ግን በርናባስ ይዞት መሄድ ፈለገ፡፡ስለዚህ በርናባስ ማርቆስን ይዞ ወደ ሲጲሪየስ ሲሄድ ጳውሎስ
ደግሞ ሲላስን ይዞ ወደ ሲሪያ ኪልቂያ ቤተ ክርስቲያናት ሄዷል (15፡30-41)፡፡በዚህ ወቀት ጳውሎስ ራሱ ጢሞቲዮስን ይዞት ሄዷል
(16፡1-4)፡፡በዚህ በመጨረሻ ጊዜም ሉቃስ ቤተ ክርስቲያን በረታች እንዲሁም እጅግ ትበዛ ነበር ብሎ ሲደመድም ይታያል (16፡5)፡፡

ወደ አህዛብ ዓለም በጥልቀት መግባት (16:6–19:20).

ጳውሎስ ወደ መቄዶንያ ቀስ በቀስ ሲጠጋ ይተያል (16፡6-10)፡፡የመጀመሪያው መዳረሻ ፊሊጲሲየስ ሲሆን ያም የሮማ ኮሎኒ ሆና
የመቄዶነያ ዋና ከተማ ነበረች፡፡በዚያ ከተማ ጳውሎስ እና ሲላስን እስር ቤት ተጥለዋል (ካርሰን 288)፡፡ጌታ ከእስር ቤት ሲያስፈታው
እና የሮማ ዜግነቱ ሲያተርፈው ይታያል፡፡ከዚያ ወደ ቤሪያ ሄደ (17፡10-15-ካርሰን 289)፡፡

ጳውሎን ሁለተኛ ስብከቱን ብዙ ጥበብ ያለበት ጥርጣሬ በገነነበት በአህዛብ ዓለም በአቴንስ አቀረበ (17፡16-34)፡፡ውጤቱ እጅግ ትንሽ
ነው፡፡ጳውሎስ ጠባብ ወደሆነችው (ልክ እንደ አንገት የሆነች ሀገር) ቆሮንቶስ መጥቷል፡፡በዚያም አንድ ዓመት ከግማሽ በመስበክ ራሱን
ጋሊሊዮ ፊት በመከላከል እንዲሁም ከአቂላ እና ጵርስቅላ ጋር ወንጌልን ሲሰራ ቆይቷል (18፡1-17)፡፡ሶስቱም ወደ ኤፌሶን ከሄዱ በኃላ
ጳውሎስ ሁለቱን ትቶ እሱ ወደ ቂሳርያ አንፆኪያ ከዚያም ወደ ትንሹ ኢሲያ ደቡባዊ ሲሄድ ይታያል (18፡18-23)፡፡በኤፌሶን ጵርስቅላ
እና አቂላ የአጵሎስን እምነት በተሻለ አስረድተውታል( 18፡24-28)፡፡ከዚያም ኤፌሶን ለሁለት ዓመት ከግማሽ ያክል ኖሯል፡፡በዚህ
ስፍራ አንዳንድ መጥምቁ ዮሐንስን ደቀ መዛሙርት ላውጧል (19፡1-7)፡፡ስብከቱንም ራሱ ባለበት ቦታ እንዲሁ ሲሰብክ ቆይቷል (19፡
8-10)፤ ተአምራት እያደረገ (19፡11-12) የአጋንንት አሰራርን እያባረረ (19፡13-19)፡፡በዚህ መንገድ የእግዚአብሄር ቃል እጅግ ያድግና
ያሸንፍ ነበር (19፡20)፡፡

ጳውሎስ ኤፌሶንን በመጣው የስደት ነውጥ ምክንያት ለቀቀ (19፡23-41)፡፡ግሪክን እና መቄዶንያን ደግመኛ ሲጎበኝ ከዚያም ወደ
ይሁዳ ጉዞ አድርጓል (20፡1-6)፡፡ሲመለስ በጢራኦስ ሊሰብክ ቆሟል፡ (20፡7-37)፡፡ዳግመኛ በሚሊጢን የቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎችን
ለመጎብኘት ቆሟል (20፡7-38)፡፡በጢሮስ እና በቂሳርያ በኢየሩሳሌም ስለሚገጥመው መከራ መልዕክት ቢሰማም ተነስቶ ሄዷል፡፡
ማስጠንቀቂያው ዕውን ሆኗል (ካርሰን-289)፡፡

በኃላ ለአይሁድ ክርስቲያኖች ብሎ አይሁዳዊ ባንዲራን ያም የመንጻት እና ስለት ማድረጉ ተመልሶ ለስደት ዳርጎታል (21፡17-26)፡፡
አንዳንድ አይሁዶች ጳውሎስ ወደ መቅደስ አንዳንድ አህዛብን ይዞ እንደገባ ሰሙ ያም ከፍተኛ ነውጥ እንዲነሳ እና ያም በሮማውያን
ጣልቃ ገብነት እስኪረገብ ከፍተኛ ስደት ተነስቷል (21፡27-36)፡፡ጳውሎስ ተያዘ ግን ለህዝቡ ንግግር እንዲያደርግ ተፈቀደለት (21፡37-
22፡22)፡፡አሁንም አይሁዳዊ ዜግነቱ እንዲጠበቅ ሲያደርገው ጉዳዩን ደግሞ በሳናርዲን (በአይሁድ ሸንጎ) ፊት እንዲቆም አድርጎታል
(20፡30-23፡10-ካርሰን 289)፡፡

ምንም እንኳን አይሁድ ሊገድሉት ቢያሴሩም (23:12-15) ጳውሎስ ወደ ቂሳሪያ ሄደ በዚያም ራሱን በህግ ፊት በሮማዊው ሀገረ ገዢ
ፊልከስ ፊት ራሱን ተከላከለ (23፡16-24፡27)፡፡ከዚያም ለሁለት ዓመታት በቂሳሪያ ካሳለፈ በኃላ ወደ ቄሳር ይግባኝ አለ (25፡1-12)፡፡
በኃላ በፊስጠስ እና በእንግዳው ንጉ አግሪጳ ሁለተኛ እና ሚስቱ በርኒቄ ፊት ራሱን ተከላከለ (25፡13-26፡32)፡፡በኃላ ወደ ሮም ተላከ
በመንገዱ ላይ ከባድ የሆነ ወጀብ በሚሊጢን ደሴት እንዲዘገዩ አደረጋቸው (27፡1-28፡10)፡፡ሮም ደረሰ እዚያም በገዛ ቤቱ በጠባቂዎች
እየተጠበቀ እንዲኖር እና ወንጌልን እንዲያስተምር ተፈቀደለት (28፡11-31-ካርሰን 290)፡፡

2.3. ነገረ መለኮት


የእግዚአብሄር ዕቅድ
የእግዚአብሄር ዘለዓለማዊ ዕቅድ ለእስራኤል ሲፈፀም ይታያል (1፡32-33፣ 54-55፣ 68-79)፡፡ይህ ዕቅድ በክርስቶስ አገልግሎት ሞት
ትንሳኤ በመጨረሻ በእግዚአብሄር ህዝብ ተፈፅሟል፡፡ይህም እቅድ እስከ ምድር ጫፍ በሚለው ውስጥ ሲታይ ያም በቤተ ክርስቲያን
መስፋፋት ታይቷል፡፡ይህም አምላክ የፈለገው ጉዳይ (1:16, 21; 3:12; 4:21; 9:16; 14:21; 17:3; 19:21; 23:11; 27:24) በራዕይ
(10:10–16; 16:9; 18:9; 22:17–21) የቃሉ መተግበር ((1:20; 2:16–21, 25–28, 34–35; 3:22–23; 4:11, 25–26; 7:48–49;
8:31– 35; 13:33–37, 40–41, 47; 15:15–18; 17:2–3; 26:22–23; 28:25–27) ፡፡የእግዚአብሄር ዕቅዱ በዋናነት የፀናው በኢየሱስ
ሞት (2:23; 13:27)እና በአህዛብ መካተት ውስጥ ነው (10:1–16; 13:47; 15:15–18)፡፡

የፍጻሜ ዘመን
ኢየሱስ በመምጣቱ መንፈስ ቅዱስ በመውረዱ የመጨረሻው ዘመን እንደመጣ ግልጥ ነው፡፡ይህ ዘመን በነቢያት መጸሐፍ ውስጥ
ካየነው እግዚአብሄር ህዝቡን የሚያድንበት እና ጠላቱን የሚበቀልበት ዘመን ነው፡፡ሉቃስ በግልፅ እንዳስቀመጠው ይህ የፍጻሜ ዘመን
ጉዳይ ነው (3፡21፤ 10፡32)፡፡ቀደምት ቤተ ክርስቲያን በመጨረሻው ዘመን ወስጥ እንደ አለች በመረዳት ውስጥ ኖራለች በተለይም
ደግሞ በልሳን መናገር የመጨረሻው ዘመን ምልክት ተደርጎ ተወስዷል (2፡16-17-ካርሰን 323 )፡፡

ድነት
ድነት በሉቃስም ሆነ በሐዋርያት ስራ መጸሐፍ አብይ ነገረ መለኮታዊ ሀሳብ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ (ሉቃ 2፡21፤ ኢዮ 2፡32፤ 2፡
47፤ 4፡12 5፡31፤ 13፡ 23፤ 13፡26፤ 16፡31፤ 28፡28)፡፡

የእግዚአብሄር ቃል
በተለይም የእግዚአብሄር ሃይል ቸል የተባለ ዋና ነገረ መለኮታዊ ጭብጥ ሆኖ ይታያል፡፡ይህም የቤተ ክርስቲያን እድግት ከእግዞአብሄር
ቃል ሀይል ጋር በእጅጉ ተሳስሮ ይታያል፡፡በዋናነት ሐዋርያት በሄዱበት ሁሉ ያደርጉ የነበረው ቃሉን መስበክ ነበር፡፡ቃሉን ተቀበሉ
የሚለው አባባል እንደ ዛሬ ጊዜ ጌታን ተቀበሉ ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነበር (11፡1)፡፡የጌታ ቃል በዛ አደገ ሰፋ የሚለው የተለመደ
የሉቃስ የመዝጊያ ንግግር ነበር (6፡7፤ 12፤24፤ 13፡49 19፡20)፡፡ለሉቃስ የጌታ ቃል ማለት የእግዚአብሄር በተለየ ሁኔታ በክርስቶስ
አማካኝነት የሚያደርገው ትድግና ነው፡፡ቃሉን በታማኝነት በመስበካቸው ሂደት ውስጥ ነው መንፈሳዊ ለውጥ ይከሰት የነበረው
(ካርሰን- 324)፡፡

መንፈስ ቅዱስ
በዋናነት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው የመንፈስ ስራ ሉቃስን እና የሐዋርያት ስራን ያጣመረ ጭብጥ ነው፡፡ኢየሱስ በሉቃስ ላይ
እንደተቀባ ቤተ ክርስቲያንም ተቀብታለች ጌታ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሀይል ተአምራት እና ድንቅ ያደርግ እንደነበረ እንዲሁ
ሐዋርያት በመንፈስ ሀይል ይፈውሱ ነበር፡፡መንፈስ በወንጌላት ውስጥ ምሪት ይሰጥ እንደነበር እንዲሁም በሐዋርያት ስራ ውስጥ
ያንን ተግባሩን ሲያከናውን ይታያል፡፡በሉቃስ ላይ መንፈስ ነቢያዊ ስራ ሲሰራ ይታያል፡፡ይህም ክርስቲያኖች እንዲመሰክሩ
ሲያደርጋቸው (4:8, 31; 7:55; 13:9) እንዲሁም ሐዋርያዊ አግልግሎትን ሲመራ (8:29, 39; 11:12; 13:2; 16:6, 7; 20:22-ካርሰን
324)፡፡ኢዮኤል ሴቶች እና ወንዶች ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ሲል ይህ አገልግሎት ትልቅ ግምት የተሰጠው ሆኖ ይታያል፡፡

ሌላኛው የመንፈስ ስራ ደግሞ ለወንጌል ምላሽ የሰጡ ሰዎች በመንፈስ እንደተሞሉ ሲሆን ይህም በጴንጤቆስጤ ቀን (2፡38)
ሳማርያ 8፡15-17) ቆርኖሊዮስ እና ቤተ ሰዎቹ (10፡44)፡፡መንፈስን ማግኘት ማለት በግልጥ ሰውየው የእግዚአብሄር ቤተሰብ አካል
እንደሆነ የሚገልፅ ነው (11:15–17; 15:8–9)፡፡
የእግዚአብሄር ህዝብ
እኛ ማነን ለሚለው ጥያቄ ሉቃስ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ያም አይሁዶች ብቻ ቢሆኑ ኖሮ ይህ የተፈጠረው የአይሁድ የተለየ ክንፍ ተደርጎ
ሊወሰድ ይችል ነበር፡፡ነገር ግን ወዲያው ሰማርያውያን እና አህዛብ መቀላቀል ሲጀምሩ ነገሩ መልኩን አየቀየረ መጣ፡፡ሉቃስ የሚነግረን
ከህጉ እና ከመቅደሱ ጋር ያለን ትስስር እንደተፋታ እና ክርስቲያን የሚል አዲስ ስም እንደተፈጠረ ያም የክርስቶስ ተከታዮች እንደሆኑ
ግልፅ ያደርግልናል (11፡26)፡፡

መወያያ ጥያቄ
ክፍል ሦስት-በሚሲዮናዊ ጉዞ የተጻፉ
ሮሜ
1. መግቢያ
የሮሜ መልዕክት ከጳውሎስ መልዕክቶች ሁሉ ረጅሙ እና ነገረ መለኮታዊ ጠቀሜታውም የላቀ ነው፡፡ሉተር ንፁህ ወንጌል ብሎታል፡፡
ገና ከጅማሬው (1፡1-17) እስከ መዝጊያው (15፡14-16፡27) የነገረ መለኮት ሰነድ ሆኖ ያገለገለ ነው፡፡ዋናው ጭብጥ ወንጌል እንደ
የእግዚአብሄር ፅድቅ መገለጥን የሚናገር ሲሆን ያም ፅድቅ በእምነት የሚገኝ ነው (1፡16-17-ካርሰን 391)፡፡
1.1 ፀሐፊ
የሮሜ መጸሐፍ ራሱ የተጸፈው በጳውሎስ እንደሆነ ይናገራል (1፡1)፡፡በዚህ ቃል ላይ እጅግም ተቃውሞ አልገጠመም፡፡ጠርጢዮስ
ምናልባት 16፡22) ፅሁፉን የጻፈ (ሴክሬተሪ) ሊሆን ይችላል፡፡ምንም እንኳን አንዳንዶች ከጳውሎስ ሌላ የተወሰነውን ክፍል የሆነ ሰው
ፅፎት ጨምሮታል ብለው ቢሉም ያን ያክል ግን ተቃውሞ አልገጠመውም፡፡

1.2 የተጻፈበት ቀን
ዶናልድ ጎተሬም ሆነ ካርሰን እና ሙ የሮሜ መልዕክት የተጻፈበትን ጊዜ ወደ 57 ዓ.ም እንደሚጠጋ ይሰማማሉ፡፡ምክንያቱም ጳውሎስ
ከኢየሩሳሌም እስከ አውላሪቆስ ወንጌልን ፈፅሞ የሰበከ እና አዲስ ድንግል መሬት (ለወንጌል) ወደ ስፔን ለመሄድ የተነሳበት ወቀት
እንደሆነ ይገልፅልናል (15፡19-28)፡፡ይህም ማለት ወደ ሶስተኛው ሚሲዮናዊ ጉዞ አካባቢ ነው ማለት ነው፡፡

1.3 ዓላማ
አንደኛ ጳውሎስ ወደ አስጳኒያ ሚሲዮናዊ ጉዞ እቅድ እንዳለው ግልፅ አድርጎልናል፡፡በሂደቱም እንዲረዱት ተሰፋ አድርጓል፡፡ ሁለተኛ
ከዚህ የተነሳ የሚሰብከውን ወንጌል ምንነት ሊያሳውቃቸው እና ለሚሲዮናዊ ጉዞው ዕርዳታ መሰብሰብ እንደፈለገ ማየት ይቻላል
(ካርሰን 403)፡፡ጉንደሬ ሌሎች ተጨማሪ የሮሜ መልዕክትን ለማሳየት ጥረት አደርጓል፡፡ሦስተኛ ይህም የሮም አማኞችን
በእምነታቸው ሊያበረታ (1፡11፤15)፡፡አራተኛ ምናልባትም አህዛብ ክርስቲያን በአይሁድ ክርስቲያኖች ላይ የሚያሳይቱን የእምነት
የበላይነት ለማረም ሳያስብ እልቀረም (11፡17-32)፡፡እንዲሁም እነዚህ አህዛብ አማኞች አሁንም አይሁድ እያሳዩ ያሉትን ስርዓቶችን
በንቀት ሳያዩ አልቀረም ይህንንም ለማስተካክል ፅፉል (14፡1-23) በማለት ለማሳየት ጥረት ያደርጋል፡፡አምስተኛ

2. የሮሜ ጭብጥ
2.1. መግቢያ (1፡1-17)
በመግቢያው ላይ ዋናው የመጸሐፉ ጭብጥ የተንጸባረቀበት ነው፡፡ያም ወደ አምስት የሚደርሱ እውነቶች ናቸው፡፡እነዚህም 1.
የእግዚአብሄር ወንጌል 2.በቅዱሳት መጸሐፍት የተመሰከረለት 3. ኢየሱስን በተመለከተ የእግዚአብሄርም የዳዊትም ልጅ የሆነ 4.
በትንሳኤው አዲስን የመጨረሻ ዘመንን ብስራት ያበሰረ 5.ጌትነቱ የተመሰከረለት 6. የሮም አማኞች እንደተመረጡ እንዲቆጥሩ
የታሰበበት ነው (ጄምስ ደን-601)፡፡ይህን ከገለጸ በኃላ ጳውሎስ ስለ ወንጌል ያብራራል ያም የእግዚአብሄር ሀይል እንደሆነ ሲሆን
አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰዎች ነው፡፡

2.2. የሰው ልጅ ኀጢያተኛ ስለሆነ ወንጌል ያስፈልገዋል (1:18–3፡20)


ጳውሎስ በቅድሚያ እንዴት ሰው ሁሉ በኀጢያት እንደተያዘ ይናገራል፡፡ሰዎች ስግብግብ፤ነውረኝነት እና መጥፎ ሕይወት ኖረዋል፡፡
ከዚህ ኀጢያት የተነሳ የእግዚአበሄር ቁጣ ተገልጧል (1፡18-19)፡፡በመጀመሪያ በአህዛብ ላይ ተቆጥቷል ይህም በማድረጉ ሊኮነን
አይችልም፡፡ምክንያቱም ራሱን በተፈጥሮ ገልጧል (1፡18-19)፡፡

አይሁድንም በባሰ ሁኔታ ተቆጥቷል ምክንያቱም ፍቃዱን በህጉ ውስጥ በተብራራ ሁኔታ ሰጥቷቸው ነበርና፡፡ነገር ግን ህግ አላቸው
ማለት ህግን ፈፅመዋል ማለት አይደለም፡፡አህዛብን ይኮንናሉ ነገር ግን ዋናው ሌቦች እነርሱ ነበሩ፡፡ለኪዳኑ እንደ ምልክት የተሰጣቸው
መገረዝ ሊታደጋቸው አይችልም (2፡1-3፡8)፡፡መዳን በፀጋ ነው ካልን እንዴት ሰው በስራ የዘለዓለም ህይወት ሊወርስ ይችላል? (2፡6-
11)፡፡24

የተገረዘውንም ያልተገረዘውንም እንደ ኀጢያተኛ ዞር በል ካለው ታዲያ የተመረጠ ህዝብ አካል መሆን ምን ፋይዳ አለው?(3፡1-8)፡፡
እግዚአብሄር ለህዝቡ ያለው ታማኝነት ቀጣይ ነው፡፡ይህንንም በሮሜ 9-11 በተብራራ ሁኔታ ይመለስበታል፡፡ታዲያ አይሁድም ሆኑ
አህዛብ የኀጢያት ባሪያ ናቸው (3፡9-20-ካርሰን)፡፡ይህን አስከፊ ሁኔታ መለወጥ የሚችል እግዚአብሄር ብቻ ነው ያም ልጁን መስዋዕት
አድርጎ በማቅረብ ነው(3፡21-26)፡፡

2.3. ውንጌል ምላሽ ነው (3፡21-5፡21)


ለዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ምላሽ ሊሰጥ የሚችለው የክርስቶስ ሞት ነው (3፡21-25)፡፡ይህ ሞት ያስፈለገው የብሉይ ኪዳን የምትክነት
የመስዋት ስርዓት ተንተርሶ ነው (ጄ ደን 603)፡፡ክርስቶስ ለድነት ብሎ የሞተው ሞት ለምንም ዓይነት መመካት ቦታ አይሰጥም (3፡
27-31)፡፡ጸጋ ለግል ለስኬት (achievement) የሚሰጠው ምንም ዓይነት ቦታ የለውም፡፡ታዲያ መመካት በምን ህግ ነው የተወገደው?
በስራ?በጭራሽ፡፡በእምነት ህግ ነወ፡፡አብርሃም የጸደቀው እህዛብ በነበረበት ጊዜ እንጂ በተገረዘ ጊዜ አልነበረም (4፡1-25-ካርሰን 391)፡፡
ይህ ያለው መልዕክት ምንድነው? ብንል እምነት እንጂ መገረዝ አለመገረዝ ወሳኝ አለመሆኑን ነው፡፡

ይህ ፅድቅ ለአሁንም ሆነ ለሚመጣው ዘመን ያለውን ፋይዳ በዚህ በሁለተኛው ክፍል ውስጥ ያብራራልናል፡፡መጽደቅ፤መታረቅ ወይም
ከእግዚአብሄ ጋር ሰላምን መያዝ ከሚመጣው ፍርድ እንድናመልጥ እንደሚያደርገን ይነግረናል (5፡1-11)፡፡ለአማኝ ለዚህ ተስፋ
የሚሆነው ጉዳይ ከክርስቶስ ጋር ያለው ግንኙነት ነው፡፡ይህም ከአዳም የኀጢያት ተፅዕኖ አላቆን ለእርሱ ለሆኑት የዘለዓለም ህይወት
ይሰጣቸዋል (5፡12-21)፡፡

2.4. ወንጌል የቅድስና ሕይወት እብድንኖር ይረዳናል (6:1–8:39)


አሁንም ግን አማኝ በትግል ውስጥ አለ፡፡ይህም ከኀጢያት፤ ከህግ ከሞት እና ከስጋ ጋር ሳያቋርጥ ይዋጋል፡፡ስንዋጋ ግን ፍፁም በሆነ
የድል ስሜት ነው፡፡ምንያቱም ኢየሱስ ከእነዚህ ሀይላት ቀንበር ነጻ አውጥቶናል፡፡ኀጢያት በእኛ ላይ አይሰለጥንም (6፡1,14)
እግዚብሄር ነው ጌታችን፡፡ይህ ድል ዕውን የሚሆነው በመተባበር (identification) ነው፡፡መተባበሪያ መሳሪያው ጥምቀት ሲሆን
መንተባበረው ከሞቱ ትንሳኤው ጋር ነው፡፡በተመሳሳይ ከኀጢያት የተነሳ የሰዎችን ሁኔታ ያባባሰው ህግም ከዚህ በሃላ አያጎብጠንም
(7፡1-25)፡፡ለመሆኑ የጳውሎስ የህግ ምልከታ ምንድነው?25ህግ በራሱ ችግር አይደለም ችግሩ የስጋ መድከም ነው፡፡ምዕራፍ 7 ምሳሌ
ነው ወይስ ስለ ራሱ ነው የጻፈው ብለው ሰዎች ይጠይቃሉ?26ነገር ግን ጆን ስቶት ጳውሎስ ስለ ቅድስና ሊያስተምር አልጻፈውም (7)
ይልቅ የህግ ስፍራው የት እንደሆነ ለማመልከት ነው ይላል፡፡ምናልባት አይሁድ ክርስቲያን ህግ ጠል ናቸው ብለው ከሰው ይሆናል፡፡ 27
በእግዚአብሄር መንፈስ አማካኝነት አማኝ በኀጢያት እና በሞት ላይ ድልን ይቀዳጃል (8፡1-13)፡፡ያው መንፈስ ልጆቹ አድርጎናል፡፡
የተጀመረው የእግዚአብሄር ስራ በድል እንደሚጠናቀቅ ማረጋገጫ ይሰጠናል፡፡ያጸድቀናል ወደ ክብርም ይመራናል (8፡18-39-ካርሰን
392)፡፡

2.5. ወንጌል እና እስራኤል (9:1–11:36)

24
ይህ አከራካሪ ነው፡፡አንዳንድ ሊቃውንት መዳን በጸጋ ፍርድ ግን በስራ ነው ይላሉ፡፡(see Cottrell, Jack: Romans : Volume 1. Joplin, Mo. : College Press Pub.
Co., 1996-c1998 (College Press NIV Commentary), S. Ro 2:7)ሌሎች ደግሞ ሰውየው ማመን አለማመኑ መለያው (marker) ስራ ነው ይላሉ በእርግጥ ይህው
ስራ ለማያምን ሲሆን በህግ ለመዳን የሚናፍቅ (legalist) ያደርገዋል፤ታዲያ መጠበቅ ያለብን እያንዳንዷን ህግ ነው?አይ የሚፈልጉ ስለሚል የአመለካከት ጉዳይ ነው
ይለናል ሊዮ ሞሪስ (Morris, Leon: The Epistle to the Romans. Grand Rapids, Mich.; Leicester, England : W.B. Eerdmans; Inter-Varsity Press, 1988, S.
116)፡፡እንዲያውም ስቶት ሲናገር የሚያድን እምነት ይኑር አይኑር የሚገለጠው መልካም ነገር ለማድረግ ባለን ፍላጎት ነው ይለናል (Stott, John R. W,The Message
of Romans : God's Good News for the World, (Leicester, England; Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2001) 84.
25
ይህ ወሳኝ እና አጨቃጫቂ ጥያቄ ነው፡፡ደን ህግ በሶስት መልክ ያየዋል 1. በቀደምት ዕይታ አራማጆች የሚታየው እንደ ሞት እና ኀጢያት በተቃርኖ የተቀመጠ ኃይል
ተደርጎ ነው (ሮሜ 5፡20 እና 7፤5)፡፡(የኤቫንጀሊካልን ከታች ተመልከት)፡፡2. ዝብርቅርቅ ነው ሳንደርስ እና ሬስናን ጳውሎስ በህግ ጉዳይ ላይ ዘባራቂ ወይም ወጥነት
የሚጎድለው ነው ይላሉ፡፡3.ጳውሎስ የተቃወመው ህግ እንደ መታደል መቆጠሩ-ደን ትክክለኛው ይህ ነው ይላል፡፡ለደን ትክክለኛው ህግ ግዝረትም የምግብ ስርዓትም
(አይሁድን ከአህዛብ ስለለየው የልዩነት ባጅ) አይደሉም (2፡25-29፤4፡9-12፤9፡10-13፡14፡1-12)፡፡ሰው ሊከተለው የሚገባው ጎረቤትን እንደ ራስ መውደድ ወይም የፍቅር
ህግን ነው ይላል (13፡8-10፤ 14፡13-15፡16)፡፡(see James Dunn, “Romans”in dictionary of Paul and His letters,602).
26
አንዳንዶች ጳውሎስ ስለ ማንነቱ እየተናገረ አይደለም ይላሉ፡፡ይህን የሚሉት 1.የተሸጥሁ ጎስቋላ የሚለው ክርስትናን አይገልጽም፡፡ 2.በሮሜ 8 ከሚያስተምረው
ጋር አይመሳሰለም፡፡3.ድነት ከባርነት ያወጣናል እንጂ ባርነት አይከተንም 4.ስለ ህግ የሰጠው ምስክርነት ክርስቲያን ያልሆነ ሰው የሚያደርገው ነው፡፡ሌሎች ደግሞ
1.የግል ትግላችን 2. እኔ የሚለው ተውላጠ ስም 3.በአሁን ጊዜ ግስ ስለ ተቀመጠ ስለ ራሱ ይናገራል ይላሉ፡፡
27
በህግ ጉዳይ ኢቫንጀሊካል ህግ ተኮር (legalist) አይደሉም፡፡እነዚህ ክህግ በታች ናቸው፡፡ህገ ጠል (antinominist) አይደሉም፡፡ህግን ለመፈጸም ነጻ ህዝቦች-ይህ
ነጻነት ማለት ከህግ ነጻ መሆን ሳይሆን ለመጽደቅም ለመቀደስም ከህግ ነጻ ናቸው ማለት ነው፡፡የእግዚአብሄር ፍቃድ የተገለጠበት ስለሆነ ይደሰታሉ (7፡22) ግን ያንን
ፍቃድ ለመፈጸም የሚያስችለው ሀይል በመንፈስ ውስጥ እንጂ ህግ ውስጥ የለም( Stott, John R. W, The Message of Romans, 191).
በዚህ ክፍል ጳውሎስ ዋና ጭብጥ አድርጎ መልስ ሊሰጥ የሚፈልገው የአይሁድ ተስፋ ምንድነው? በእግዚአበሄር ዕቅድ ምን ድርሻ
አላቸው?ከእነርሱ ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናቆ ወደ ቤተ ክርስቲያን ዞር ብሏል? አይሁድም አህዛብም የሚድኑት በክርስቶስ
በማመን ከሆነ አይሁዳዊ መሆን ምን ታሪካዊ ጥቅም አለው?እግዚአብሄር ለአይሁዶች የሰጣቸው የብሉይ ኪዳን የተስፋ ቃሎችስ?
ከእንግዲስ በስጋ አህዛብ ለሆኑት አያገለግሉም ማለት ነው? የሚሉ ሲሆኑ የተለያዩ ሊቃውንት የጳውሎስን ትኩረት በተመለከተ
የተለያየ ነገር ብለዋል፡፡28

አይሁድ እና አህዛብ የሚለው ሶተኛው የሮሜ መጸሐፍ ጭብጥ ነው፡፡እግዚአብሄር ኪዳኑን ከእስራኤል ወደ ቤተ ክርስቲያን ዞር
ማድረጉ ህዝቡን ትቷቸዋል ያሰኘናል (9:1–6a)? በጭራሽ፡፡ጳውሎስ ሲመልስ አንደኛ ድነት እስራኤል ሆኖ በስጋ ስለተወለደ ብቻ
የሚሰጥ አይደለም፡፡ወይም እስራኤል ሆኖ ስለተወለደ ለድነት ዋስተና አይሰጠውም (9:6b–29)፡፡ ሁለተኛ በክርስቶስ የተገለጠውን
ፅድቅ እንዳያገኙ ሊከሰሱ የሚገባቸው ራሳቸው እስራኤላውያን ናቸው (9:30–10:21)፡፡ በተጨማሪ አንዳንድ እስራኤላውያን
(ጳውሎስን ጨምሮ) የመዳን ዕድል ስላገኙ እግዚአብሄ ህዝቡን አልተዋቸውም እንዲሁም ተስፋውን ፈፅሟል (11፡1-10)፡፡በሙግቱ
መጨረሻ አንዳንድ እስራኤልን ይንቁ ለነበሩ እብሪተኛ አህዛብ ድነት በእስራኤል በኩል እንደመጣ ወደፊት በሙላት እስራኤል
እንደምትድን (እስራኤል ሁሉ ይድናል የሚለውን ልብ ይሏል) ይነግራቸዋል (11፡12-36-ካርሰን 392)፡፡

2.6. ህይወት ለዋጭ የሆነው ወንጌል (12:1–15:13).


የመጨረሻው የጳውሎስ መልዕክት ላይ እግዚአብሄር እንዴት በወንጌል በኩል ተግባራዊ በሆነ ህይወት እንደሰራ ሲያስረዳቸው
እናያለን፡፡ጸጋው መስዋዕታዊ ህይወት እንዲኖሩ እንደሚያደርጋቸው ያሳስባቸዋል (12፡1-2)፡፡ይህ አገልግሎት ብዙ ዓይነት ቅርፆች
አሉት ያም እግዚአብሄር ለህዝቡ በሰጣቸው ስጦታዎች አማካኝነት የሚገለጥ ነው (12፡3-8)፡፡ይህ አገልግሎት መደረግ ያለበት በፍቅር
ነው (12፡9-12))፡፡እግዚአብሄርን ማገልገል ለባለስልጣናት ያለንን ግዴታ መዘንጋት ማለት አይደለም (13፡1-7)፡፡ምንም እንኳን ከህግ ነጻ
የወጣን ቢሆንም ህግን ሁሉ በሚጠቀልለው ወንድምን መውደድ ቸል ልንል አይገባም (13፡8-10)፡፡ማገልገል ያለብን የድነት ጨረር
የፈነጠቀ መሆኑን በመረዳት እና ያም ብርሃንን በማንጸባረቅ ነው (13፡8-10)፡፡በመጨረሻም ምንም እንኳን አንዳንዶች የብሉይ ኪዳን
ስርዓቶችን ቢያደርጉም አማኞች ግን በመናናቅ መተያየት እንደሌለባቸው ያሳስባቸዋል (ካርሰን 393)፡፡

ደብዳቤውን የሚዘጋው (15፡14-16፡27) ጳውሎስ ያለበትን ሁኔታ እና የጉዞ ዕቅዱን በመዘርዘር ነው፡፡ የጸሎት ጥያቄ በማቅረብ (15፡
30-33) እንዲሁም ረጅም ሰላምታ በማቅረብ ነው (16፡1-16)፡፡

3. ነገረ መለኮት
ቅድመ እውቀት
ሽራይነር የቀደመ እውቀት ማለት እግዚአብሄር በቀደመ እውቀቱ የልጁን መልክ ይመስሉ ዘንድ ወስኗል ማለት ነው ይለናል፡፡
እግዚአብሄር አስቀድሞ ማን የክርስቶስ እንደሚሆን ያውቃል (የሐዋ 26፡5፣ 2 ጴጥ 3፡17-ሽራይነር 399)፡፡ሌላው ከብሉይ ኪዳን
አንጻር አሁንም ሽራይነር አስቀድሞ ማወቅ ማለት ምርጫ ነው ይለናል (አሞፅ 3፡2)፡፡ይህም አስቀድሞ ያወቃቸውን ህዝብ
አልተወም ስለሚል (ሮሜ 11፡2) ከምርጫ ጋር ይሄዳል እንደማለት ነው (ሽራይነር-339)፡፡ይህ ግን እውነት አይደለም ይለናል
ዊዝንግተን ምክንያቱም ማወቅ አንዳንድ ጊዜ ከምርጫ ሌላ ጊዜ ደግሞ ከፍቅር ጋር ሄዷል (The problem with Evangelical
theology-59)፡፡ለአብዛኛው ካልቪስት ምልከታ ላላቸው (ሽራይነርን ጨምሮ) ቅድመ እውቀት ማለት ቅድመ ውሳኔ
(forordination or predestination) ነው፡፡ማወቅ እና መወሰን አንድ ከሆኑ እግዚአብሄር ክፋትን እና ኀጢያትን አስቀድሞ ወስኗል
ማለት ነው (Dave Hunt What love is this: 113)፡፡
የእግዚአብሄር ፍቅር እና ምርጫ

የእግዚአበሄር ፍቅር ከምርጫው ጋር ተያይዞ ተነግሯል (1፡7-ሽራይነር-341)፡፡ይህም ያዕቆብን ወደድኩ ኤሳውን ጠላሁ ባለው ንግግር
ውስጥ ግልፅ ብሏል ይለናል ሽራይነር (ሮሜ 9፡13)፡፡ይህም ሚልኪያስ 1፡2-3 የተጠቀስ ጥቅስ ነው (ሚል 1፡2-3)፡፡የአህዛብ መመረጥ
እንደውዴታ ተጠቅሷል (ሆሴ 2፡23፤ ሮሜ 11፡28- ሽራይነር 341)፡፡ምህረትም እንደ ምርጫ ተጠቅሷል በማለት ሙግቱን ያቀርባል
(ዘፀ 33፡19 ሮሜ 9፡11-14 ሽራይነር-343)፡፡ታዲያ ወደደ ማለት መረጠ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ግን ጥያቄው እንደ ዊዝንግተን ከሆነ
ምርጫ ምን አይነት ነው? ግለሰባዊ ወይስ ማህበራዊ? (The problem with Evangelical theology-59)፡፡
28
ብዙ ሊቃውንት ጳውሎስ ምን ላይ ነው ያተኮረው የሚለውን መስማማት አልቻሉም፡፡አንዳንዶች የእግዚአብሄር ሉአላዊ ምርጫ ከእስራኤል እና አህዛብ አንጻር
(ሮበርት ሃልደን) ሌሎች ደግሞ የአህዛብ መካተት እና የአይሁድ ገለል መደረግ (ቻርለስ ሆጅ) ትንቢቱ ፍጻሜ እንዲያገኝ የቤተ ክርስቲያን ተተክቶ መግባት
(ኢቫንጀሊካል ሊቃውንት)፤ በእግዚአብሄር ቤተሰብ ውስጥ የአይሁድ አህዛብ ትብብር (ክሪስተር ስታንድል) በእምነት መጽደቅ እግዚአብሄር ለእስራኤል ከሰጠው ተስፋ
ጋር ይጣጣማል ወይስ ልዩነት አለው የሚለውን ለማየት (አንድረስ ኔግሬን ጆን ዘይስተለር) አአህዛብን በክርስቲያን ሚሺን መድረስ እና ይህ አይሁዶችንም ያካትታል
(see Stott, John R. W, The Message of Romans, 261)፡፡
ምርጫ

ሽራይነር ከእስማኤል ይልቅ ይስሐቅ ከኤሳው ይልቅ ያዕቆብ ተመረጠ በማለት ክርክሩን ለማቅረብ ጥረት ያደርጋል (ሮሜ 9፡10-13)፡፡
ምርጫው በመልካምነቱ ላይ የተመሰረተ አይደለም ይለናል ሽራይነር፡፡ታዲያ ይህን ውሳኔ ሲያደርግ እግዚአብሄርን ፍርደ ገምድል
አያደርገውም? ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ እርሱ እንደ ሸክላ ሰራተኛ ነው የፈለገውን ማድረግ ይችላል በማለት ይሞግታል (Schreiner
-346)፡፡ጥያቄው ግን በአዲስ ኪዳን ምርጫ የሚባል የለምን የሚል ነው? ምርጫማ አለ፡፡እንደ ዊዝንግተን ከሆነ (አስቀድመን
እንዳነሳነው) ምርጫው ማህበራዊ ነው (The problem with Evangelical theology-59) ፡፡ምርጫ የሚለው ሀሳብ በነጠላ
ሳይሆን በብዙ ጥቅም ላይ ውሎ የምናየው ለዚህ ነው (The problem with Evangelical theology-59) ፡፡ጀምስ ደን እንደውም
በጣም እስራኤል አስቀድማ ብትመረጥም የተመረጠችው እንደ ህዝብ በአህዛብ መካከል ብርሃን እንድትሆን ነው (Dunn-in
dictionary of Paul-605)፡፡

ፀጋ

ፀጋ ማለት ነጻ ስጦታ ማለት ነው፡፡ያም በስራ የማይገኝ ነው፡፡ ነገር ግን ኀጢያተኛውን በሚያፀድቅ በክርስቶስ ለሚያመን ፅድቁ ሆኖ
እንዲቆጠርለት የሚያደርግ ሂደት ነው፡፡ይህ ሁሉ ሆኖ ኢፒ ሳንደርስ ይሁዲነትም የፀጋ እምነት ነው፡፡ህግ ለአይሁድ በኪዳኑ ውስጥ
መኖሪያ መርዕ ነው፡ በማለት ሞግቷል፡፡ስለዚህ የጳውሎስ ሙግት ህግ ፀጋ ዓይነት ሙግት አይደለም ይለናል፡፡ነገር ግን የፀጋ ህግ ሙግት
የጳውሎስ ሀሳብ እንደሆነ ሽራይነር ይሞግታል (Schreiner-349)፡፡ይህም በ ቲቶ 3፡5-6 ታይቷል ይለናል፡፡የአይሁድ ሃይማኖት ህግ
ተኮር አይደለም ብሎ ማለት አይቻልም፡፡

ጥሪ

እንደ ሽራይነር ከሆነ በሮሜ 8፡29-30 ላይ የተጠቀሱት ቃላቶች በተርታ የተቀመቱ ናቸው፡፡እና የሚጠሩት የተወሰኑት ናቸው፡፡ታዲያ
እነዚህ የተጠሩት ናቸው የጸደቁት (ሮሜ 5፡1 (Schreiner -350)፡፡ካልቪንስቶች ጥሪን ሲናገሩ ዝም ብለው እግዚአብሄር የሰው ዘርን
ሁሉ ጠራ የሚለው ሀሳብ አይስማማቸውም፡፡ምክንያቱም የተጠሩት ምላሽ ሊሰጡ የሚችሉት ብቻ ናቸው፡፡የሚጠቀሙበት ቃል
ውጤታማ ጥሪ (effectual calling)፡፡ጥሪ እንደ ዊዝንግተን ከሆነ ግብዣ ነው፡ (The problem with Evangelical-66)፡፡

አስቀድሞ መወሰን

ሌላኛው ሀሳብ እንግዲህ አስቀድሞ መወሰን ነው፡፡ይህ ቃል በሮሜ በኢቫንጀሊካል ነገረ መለኮት ውስጥ ቁልፍ ቃል ሲሆን፡፡ሰው ምንም
ይሁን ምን እግዚአብሄር አስቀድሞ ከወሰነው ወሰነው ነው በማለት ለመከራከር ጥረት ይደረጋል፡፡እንደ ዊዝንግተን ከሆነ እግዚአብሄር
የወሰነው ማን እንደሚድን ወይም ማን እንደማይድን ሳይሆን ይልቅ እግዚአብሄር ክፉም ሆነ ደግ ነገር በአማኞች ላይ እንዲከሰት
አስቀድሞ እንደወሰነ እና ያም ክፉ ሆነ ደግ ሲከሰት የሰዎችን ባህሪ ሰርቶ ያልፋል (The problem with Evangelical-66)፡፡ስለዚህ
ቁጥር 28 ከ 29 ጋር መነበብ አለበት፡፡

መጽደቅ

ሌላኛው በሮሜ 8፡30 ላይ የተጠቀሰው ሀሳብ አጸደቃቸው የሚለው ቃል ነው፡፡በሌላ አባባል መጸደቅ (justification) ማለት ነው፡፡
መጸደቅ ከሚመጣው ፍርድ መትረፍ ማለት ነው (Schreiner-351)፡፡ዳኛ በደለኛውን በደለኛ ሲል ንፅሁን ንፁህ ይለዋል (ዘዳ 25፡1
2 ሳመ 15፡4 1 ነገ 8፡31-32 ኢሳ 5፡23 Thomas R. Schreiner-352)፡፡ጻድቅ ከሆኑ እግዚአብሄር ጻድቅ ናችሁ ይላቸዋል (ሮሜ
2፤13)፡፡ኬስማን እና ሽልማቸር የእግዚአብሄር ጽድቅ ለዋጭ መሆን አለበት ብለው ተናገረዋል፡፡ምክንያቱም ጽድቁ ተገልጧል
ሲለሚል (ሮሜ 1፡17)፡፡ይህም ማለት በደለኛ አይደለህም ብሎ ከማወጅ (ከመፍረድ) በላይ ነው፡፡የእግዚአብሄር ጸድቅ ተገለጠ ሲሉ
እግዚአብሄር በዓለም ታሪክ ገባ ማለት ነው ብለው ይሞግታሉ፡፡የእግዚአብሄር ጽድቅ ድነት የታከለበት የማዳን ተግባር ነው፡፡ነገር ግን
ሁለቱም ነው ብሎ ማለት ይቻላል፡፡በአንድ ጎኑ ማጸደቅ በሌላ ደግሞ መለወጥ (Schreiner-355)፡፡

ድነት

በሮሜ 8፡30 ላይ የሚናገረው መክበር መዳን ነው፡፡መዳን መታረቅ መዋጀት እና መቀደስ የድነት ቀንቋዎች ናቸው (Schreiner 362)፡፡
መዳን ከሚመጣው ቁጣ ነው (1 ተሰ 1፡10)፡፡ታዲያ ዛሬ የጸደቁት ከፍርድ ያመልጣሉ (ሮሜ 5፡9 ሮሜ. 7:24 Schreiner-362)፡፡

መደምደሚያ
ሽራይነር ብዙ ወንጌላውያን አማኞች ከሮሜ መጸሐፍ ውስጥ እግዚአብሄር አስቀድሞ ጥቂቶችን ይመርጣል እነዚህም ሊድኑ ያሉ
ናቸው በማለት ያምናሉ፡፡ታዲያ እነዚያ ሊድኑ ያሉት በውጤታማ ጥሪ ይጠራሉ በመጨረሻም ወደ ክብር ይገባሉ ብለው ይላሉ (ሮሜ
8፡29,30)፡፡ሌሎች ደግሞ ነገሩ እንዲህ አይደለም ብለው ይከራከራሉ፡፡ 29በተመሳሳይ መንገድ እግዚአብሄር አንዳንድ ሰዎችን ልባቸውን
ያደነድናቸዋል ብለው ይናገራሉ፡፡ለዚህ እንደ ምሳሌ የሚወስዱት ፈርኦንን ነው፡ (ሮሜ 9፡18፤ 11፡7-10፤ 25፤2፡5)፡፡30 ይህ የእነ
ኦገስቲን እና ካልቪን ምልከታ ነው፡፡31 ስለዚህ ድነት ለሁሉ አይደለም፡፡እንደውም ክርስቶስ የሞተው ለጥቂቶች ነው ብለው ለመሞገት
ጥረት ያደርጋሉ፡፡32 የሚያምኑት የተመረጡ እና እግዚአብሄር በሚስጥር በልባቸው የሚሰራባቸው ናቸው ይላሉ፡፡33

ማርሻል ይህን በፅኑ ይሞግታል፡፡አንደኛ በሮሜም ሆነ በሌሎች ላይ በግልፅ እንደምናየው የጌታ ሞት ለሁሉም ነው (ሮሜ 5፡18፤ 11፡
32)፡፡34 ሁለተኛ እግዚአብሄርን ኢፍታዊ ያደርገዋል፡፡ታዲያ እርሱ ሁሉን የማድረግ ያልተገደ ነጻነት አለው (ሮሜ 9፡15)፡፡ይህ ግን
እግዚአብሄርን እንዲምረን እኛ መጫን አንችልም ለማለት የተነገረ እንጂ እግዚአብሄር በፍትሁ ምክንያትያዊ አይደለም ለማለት
አይለም፡፡35 ሦስተኛ አስቀድሞ መወሰን ዓላማውን ከማድረግ አንጻር ወይም ለራሱ የሆነ ህዝብ ለመፍጠር እንጂ ጥቂቶችን መርጦ
ለማዳን ሌሎችን ለመግፋት አይደለም፡፡36 አራተኛ እስራኤል እንዲድኑ (እንዲያምኑ) ፀልዮአል፡፡ታዲያ እግዚአብሄር የሰውን ፍጻሜ
ሁሉ ከወሰነ ለምን መጸለይ አስፈለገው?4141 አምስት ኀጢያተኛን ራሱ የሚያደነድነው ከሆነ ለምን የእስራኤል መደንደን ያሳዝነዋል
(ሮሜ 11፡23፤ 11፡14)፡፡37 ሰዎች የሚያደርጉትን የሚያደርጉት በፍቃዳቸው ነው (1 ተሰ 2፡18፤ ሮሜ 16፡25)፡፡38 ሰው ለሚሰራው ነገር
ሁሉ የራሱ ችግር እንደሆነም ተደርጎ ከሮሜ 9፡30 ጀምሮ ተነግሯል፡፡39

1 እና 2 ቆሮንቶስ
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
በሁለቱም የቆሮንጦስ መልዕክቶች ላይ ጳውሎስ ፀሐፊ እንደሆነ ግልፅ ያደርግልናል፡፡ይህንን የሞገቱ በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ወደ
2 ቆሮንቶስ መልዕክት ስንመጣ ብዙ የመከፋፈል ንድፈ ሀሳብ መጥቷል፡፡በእነዚህ ንድፈ ሀሳቦች በአመዛኙ ክፍሎች ጳውሎስ
አልጻፈውም ወደሚል ድምዳሜ ተደርሷል፡፡በዋናነት 2 ቆር 6፡14-7፡1 ከጳውሎስ ውጪ ያለ ሰው ፅፎታል ብሎ ይሞግታሉ (Carson
419)፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
አይሁዶች በጳውሎስ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ያደረሱበት ጊዜ ከሆነ (የሐዋ 18፡12) ይህ ወቅት ጋሊሊዮ ዘመን ስለነበር ይህ ጊዜውን ወደ
51 ዓ.ም ይወስደዋል፡፡ምክንያቱም የፍርድ ውሳኔ ከተሰጠ በኃላ ጳውሎስ በቆንጦስ ለጥቂት ጊዜ ቆይቷል (የሐዋ 18፡18)፡፡ከዚያም ወደ
ሶሪያ በ 52 ዓ.ም በመርከብ ተጉዟል፡፡ጳውሎስ በኤፌሶን ለሁለት ዓመት ከግማሽ ስለቆየ ቀኑን ወደ 55 ዓ.ም ይወስደዋል፡፡ስለዚህ
ጳውሎስ 1 ቆሮ ሲፅፍ በኤፌሶን ነበር ይህም ከጴንጤቆስጤ ባህል በፊት መሆኑ ነው (16፡8)፡፡ምናልባትም ሁለተኛ ቆሮንቶስን
በሚቀጥለው ዓመት/ዓመታት ጨርሶታል፡፡በዚያን ጊዜ መቄዶኒያ ነበር (2 ቆሮ 2፡12-13፤ 7፡5፤ 8፡1-5 9፡2 ካርሰን-448)፡፡

ሐ. ዓላማ
በኤፌሶን በነበረው አገልግሎቱ ጳውሎስ ስለ ቤተ ክርስቲያኗ ወሬ ሰምቷል፡፡እነዚያም ሰዎች እስጢፋኖስ ፈርዶናጥስ አካይቆስ ናቸው
(1 ቆሮ 16፡17)፡፡ይህም ፈጣን መልክዕክት ቤተ ክርስቲያኗ እንደተከፋፈለች (1 ቆሮ 1፡11) የጳውሎስ ሐዋርያዊ ስልጣን መጠየቁ

29
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 331
30
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 331.
31
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 332.
32
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 332.
33
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 332.
34
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 332.
35
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 333.
36
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 333.
4141
This presupposes that God can influence people to believe in response to prayer. But Paul does not say, and never says, “God’s purpose is
that X should be saved, but in order that this should happen he instigates me to pray for X so that he can ‘answer’ the prayer which he has put
into my heart to pray.”
37
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 333.
38
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 334.
39
Marshall, I. Howard: New Testament Theology, 334.
(1 ቆሮ 4፡3)፡፡ታዲያ ጳውሎስ እነዚህ ቅሬታዎችን ጉዳይ ለመፍታት ጉብኝት አቅዶ ነበር (1 ቆሮ 4፡19)፡፡ከአለበት ቦታ ወደ ቆሮንቶስ
ለመሄድ ትንሽ ይከብድ ስለነበር ለመጻፍ ወስነ (Encountering-273)፡፡

መ. ጳውሎስ ለቆሮንቶስ የጻፋቸው ጽሑፎች

አንደኛ፤ ይህ ማለት ከ 1 ቆሮንቶስ በፊት የጻፈው ጽሑፍ ነው (1 ቆሮ 5፡9)፡፡ይዘቱም ግብረ ገባዊ ሕይወት ከሌላቸው ሰዎች ጋር
መተባበር እንደሌላቸው ነው፡፡ይህንን እነርሱ የተረዱት በኀጢያት ልምምድ ውስጥ ከአሉ ጋር እንደሆነ አድርገው ነው፡፡እንዲህ ከሆነ
እንዴት አድርገው ወደ ንሰሀ ሊያመጧቸው ይችላሉ?ስለዚህ ጳውሎስ የጻፈው በክርስቲያናዊ ግብረ ገብ ከማይኖሩ አማኞች ጋር
ነው፡፡

ሁለተኛ፤ጳውሎስ ከሰዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን መከፋፈል ከሰማ እና እንዲሁም በደብዳቤ ያለባቸውን አንዳንድ ጥያቄ ካቀረቡ በኃላ
እርሱን ለማብራራት ሁለተኛ ፅሁፍ ጻፈላቸው፡፡ይህም አንደኛ የቆሮንቶስ መልዕክት በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ጳውሎስ አጵሎስ
ተመልሶ ችግሩቹን እንዲፈታ ቢጠይቀውም ፍቃደኛ አልሆነም (1 ቆሮ 16፡12)፡፡ስለዚህ በቀሎዔ ቤተ ሰዎች አማካኝነት ደብዳቤውን
ላከላቸው፡፡

ሦስተኛ-ጳውሎስ መልዕክቱን ከጻፈ በኃላ አንዳንድ ችግሮች እርሱ በፈለገበት መንገድ ሳይሄደሉለት የቀሩ ይመስላል፡፡ስለሆነም
ጳውሎስ ለአጭር ጊዜ ጉብኝት ወደ ቆሮንቶስ ሄደ፡፡ይህንን ጉብኝት የስቃይ ጉብኝት ብሎታል (2 ቆሮ 2፡1)፡፡ወደ ኤፌሶን ከተመለሰ
በኃላ የኃዘን ደብዳቤ የተባለ ሌላ መልዕክት ጽፎ በቲቶ በኩል ሰደደ (2 ኛ ቆሮ 2፡4፤7፡8-9)፡፡አንዳንድ ምሁራን ይህ 1 ቆሮ መልዕክት
ያመለክታል ይላሉ፡፡ሌሎች ግን በዚህ መልዕክት ውስጥ ብዙ ኃዘን እንደሌለለ በመግለጽ ጳውሎስ አሁን በእጃችን ስለሌለ መልዕክት
እየተናገረ ሳይሆን አይቀርም ይላሉ፡፡

አራተኛ-ጳውሎስ የኤፌሶን አገልግሎቱን ከፈጸመ በኃላ ወደ ቆሮንቶስና ኢየሩሳሌም አመራ፡፡ይህንንም ያደረገው በሁለተኛው
የወንጌል መልዕክተኝነት ጉዞው የመሰረታቸውን አብያተ ክርስቲያናት በእግር እየተጓዘ በመጎብኘት በመቄዶንያ በኩል ለማለፍ ነበር፡፡
በተጨማሪም አብያተ ክርስቲያናት በኢየሩሳሌም ለሚገኙ ደሆች ክርስቲያኖች አንዲሰጥ ያዋጡትን ገንዘብ ሰብስቧል፡፡ጳውሎስ
በመቄዶንያ ሳለ ቲቶ ከቆሮንቶስ ተመልሶ ስለ ቆሮንቶስ ክርስቲያኖች መለወጥ ገለጸለት (2 ቆሮ 7፡5-7)፡፡ጳወሎስም በአመስጋኝነቱ
በመጸሐፉ ውስጥ የሚገኘውን የሁለተኛ ቆሮንቶስን መልዕክት ጻፈ፡፡40

1 ቆሮንቶስ ጭብጥ
1.1 ሠላምታ እና ምስጋና (1:4–9)

ከሁሉ አስቀድሞ ለቆሮንቶስ አማኞች ሰላምታ ያቀርባል (1:1–3)፡፡ይህ ሰላምታ ጸሐፊ (ጳውሎስ እና ሶስቴኒዮስ) ተቀባይ
የቆሮንቶስ አማኞች እንደሆኑ በጥንት የደብዳቤ አጻጻፍን መሰረት አድርጎ ይጽፋል፡፡ እና እግዚአብሄር በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን
እያደረገው ያለውን ነገር ምስጋና ካቀረበ ሲያቀርብ ይታያል(1:4–9)፡፡

1.2. በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ችግሮች (1፡10-6፡20)

ጳውሎስ ወደ ዋናው የመጸሐፉ ክፍፍል ሲገባ ይታያል (1:10–4:21)፡፡ከቀሉዔ ቤተ ሰዎች እንደሰማው ሪፖርት (1:11),
ቆሮንቶሳውያን ራሳቸውን ከታዋቂ መሪዎች ጋር በማስተሳሰር የፓርቲ ክፍፍል ውስጥ እንደገቡ ተረድቷል ይህም የመሪዎቹን የጥበብ
ችሎታ መሰረት አድርጎ የተፈጠረ ነው (1:10– 17)፡፡ ጳውሎስ ይህን ጥበብ ይንቀዋል፡፡ሁለት ዓይነት ጥበብ ተጠቅሷል፡፡ከዓለም ጥበብ
አንጻር ወንጌል ራሱ እንደ ሞኝነት ተቆጥሯል (1:18–25)፡፡ያ ብቻ ሳይሆን ክርስቲያን መሆን ሞኝነት ሆኗል (1:26–31)፡፡

ወንጌልን በሰው ላይ ጫና ለመፍጠሪያ ወይም የራስን ብቃት ማሳያ አይደለም፡፡ይልቅ እውነትን እና ሀይልን የሚገልጥ ሲሆን
የሞተውን የተነሳው ኢየሱስ የመልዕክቱ ማጠንጠኛ ነው (2:1–5)፡፡በተቃራኒው የእግዚአብሄር ሞኝነት ከዓለም ጥበብ የሚጠበብ
ከሆነ እግዚአብሄርም የዓለምን ሞኝ ነገር በመምረጥ የዓለምን ጥበብ የሚያሳፍር ከሆነ ቆሮንቶሳውያን የዓለምን ጥበብ መስበካቸው
ከክርስቲያን እምነታቸው እና ልምምዳቸው ጋር የሚቃረን ነው (ካርሰን 415)፡፡

የእግዚአብሄር ጥበብ በክርስቶስ የአደባባይ ሞት ብቻ የተገለጠ ሳይሆን በግልም መንፈስ ቅዱስ ሰዎችን በማሳመን ሂደት የተገለጠ
ነው አለበለዚያ ሰዎች ሊያምኑ አይችሉም ነበር (2፡6-16)፡፡ጥበብ ለበሰሉት ነው ብሎ ይናገራል (2፡6)፡፡ የበሰሉት እነማናቸው?41እንደ

40
ቲም ፌሎስ፤ አዲስ ኪዳን የጥናት መመሪያና ማብራሪያ 104፡፡
መንፈሳዊ ሰዎች አላናገራቸውም ምክንያቱም ቢያንስ እንደ ጥሪያቸው መጠን እንኳን ሊኖሩ ያልቻሉ ሰዎች ናቸው (2፡6-16)፡፡
በታዋቂ መሪዎቻቸው ስም የሚከፋፈሉ (3፡1-4) ጨቅላዎች ነበሩ፡፡ከዚህ የተነሳ ክርስቲያናዊ መሪነትን ሲያብራራ ይታያል፡፡

በሚቀጥሉት ምዕራፎች በክርስቲያን መሪዎች ላይ የተፈጠረ የተሳሳተ ግንዛቤን (ፐ የእኔ መሪ የሚል ግንዛቤ) ለማስወገድ ጥረት
ሲያደርግ ይታያል ይህንንም ለማብራራት የህንጻውን እና የእርሻውን ምሳሌ ተጠቀመ (3፡9-15)፡፡ይህም በክርስቲያን አመራር ውስጥ
ያለን መደጋገፍ እና ለእግዚአብሄርም ያለን ተጠያቂነትን ለማሳየት ጥረት አድርጓል፡፡ያም ቤተ ክርስቲያንን ሊያፈርሱ የተነሱትን ሁሉ
ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው ይታያል (3፡16-17-ካርሰን 416)፡፡

ተመልሶ በጥበብ እና በሞኝነት መካከል ያለውን ተቃርኖ ሲያብራረ እና በክርስትና መሪነት ውስጥ ሊፈጠር የሚችል የግንዛቤ
እጥረትን ሲቃወም ይታያል፡፡ይህም ቆርንቶሳውያን የመለያየት ነገር እንደ ጥበብ ከቆጠሩት ራሳቸውን የሚያታልሉ ሲሆን መጸሐፉ
ትህትናን እውነተኛ ክርስቲያናዊ ብስለትን የክርስትና እሴት እንደሆነ ዝንግተው ማለት ነው (3፡18-23)፡፡

ክርስቲያኖች መረዳት ያለባቸው ጉዳይ እግዚአብሄር ብቻ የሰዎችን ብቃት የሚለካ መሆኑን እና እርሱ ብቻ መዛኝ መሆኑን ነው
(4:1–7)፡፡ታዲያ ይህን ጉዳይ ሐዋርያው የራሱን ሁኔታ ያም ምን ያክል መጫወቻ፤ውራ እንዳዳረጋቸው በማሳየት የእነርሱን ትዕቢት
ሊያርም ሲጣጣር ይታያል (4:8–13)፡፡ስለዚህ በክርስቶስ ለወለዳቸው አባት ራሳቸውን እንዲሰጡ ያሳስባቸዋል (4፡14-17)፡፡ስለዚህ
ጉብኝቱን ማዘግየቱ የመጨረሻ ማሳሰቢያ ሊሰጣቸው (በምን ልምጣባችሁ በበትር) እና ስጋትም የሚፈጥረ ሆኗል (4፡14-17)፡፡

ጳውሎስ በምዕራፍ 5-6 ላይ ሶስት ጉዳዮች በእነዚህ ክፍሎች ላይ ትልቅ ቦታ ይዘው ይታያሉ፡፡አንደኛው በዘመድ መካከል የሚደረግ
ወሲብ (የእንጀራ እናቱን ያገባ) (5፡1-18) እና በዚሁ አያይዞ በአለፉት ምዕራፎች የተናገረውን ጉዳይ ያብራራበት (5፡9-13)፡፡
ሁለተኛው በወንድሞች መካከል ስለሚደረግ የፍርድ ቤት ጉዳይ (6፡1-11)፡፡ጳውሎስ አማኞች ወደ ፍርድ ቤት መሄዳቸውን
ተቃውሟል? ሦስተኛ ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ወሲባዊ ጥምረትን (ስጋ ለምግብ ነው) ፡፡ያም መንፈሳዊነትን አጣመው መረዳታቸው
ነው (6፡12-20-ካርሰን 416)፡፡

1.3. ለእነርሱ ጥያቄ የተሰጠ ምላሽ

አንደኛ ጥያቄ-ጋብቻ እና ተያያዥ ጉዳዮች (7) ሌላው ቆሮንቶሳውያን ከጠየቁት ተነስቶ ያብራራቸዋል (7፡1)፡፡ያንን የጥያቄ ደብዳቤ
እስጢፋኖስ ወይም አካይቆስ አምጥቶት ሊሆን ይችላል (16፡17)፡፡ጋብቻ እና ተያያዝ ጉዳዮችን ሊያይ ሞክሯል (7፡1-40)፡፡

ሁለተኛ ጥያቄ-ለጣኦት የተሰዋ ስጋ መብላት (8-11፡1)-ፍቅር መርዕ ሊሆነኝ ይገባል ለጣኦት የተሰዋን መብላት አለብኝ ወይም
የለብኝም የሚለውን መፈታት ያለበት ሰው ከራስ ወዳድነት በጸዳ ፍቅር ነው (ወንድሜን ስጋ… 8፡1-13- ካርሰን 417)፡፡ይህ ጉዳይ
የእውቀት ጫፍ መርገጥን የሚጠይቅ አይደለም፡፡መብት ቢኖረኝም አላደርገውም- (9) በዚህ ውስጥ መብቱ ቢኖረውም ያንን መብት
መተውን ሲያሳይ ያንን ያደረገበት ምክንያት ብዙዎችን ለክርስቶስ ለመማረክ ነው፡፡ይህ ራሱን የመካድ እና ራሱን የመግዛት ጉዳይ
የሁሉም መመሪያ ሊሆን ይገባዋል (9፡24-27)፡፡ለተነሳው ጉዳይ ምሳሌ-(10)የእስራኤል መጥፎው ምሳሌ ቆሮንቶሳውያን ላሉበት
ሁኔታ ጠቃሜታ ያለው ሆኗል፡፡በመልካም መጀመር ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሄር ፍርድ ስር እንዳንወድቅ መጨረስ ወሳኝ ነገር ነው
(10፡1-13)፡፡ጣኦት አምልኮ መወገድ ካለበት ክርስቲያኖች የአረማውያን ቤተ መቅደስ ውስጥ ተካፋይ መሆን የለባቸውም (10፡14-22-
ካርሰን 417)፡፡ከዚያም ለሌላው ክርስቲያን ለሌላው ክርስቲያን ከመኖር አንጻር ከምግብ ለመታቀብ ወይም ምግብ ለመብላት
ልለሚኖረው ነጸነት ጳውሎ የሰጣቸው ዝርዝር መመሪያዎች (1 ቆሮ 10፡23-11፡1)፡፡

ሶስተኛ-ወንዶች እና ሴቶች በአምልኮ ስብሰባ ላይ ምን አይነት ልብስ መልበስ ይኖርባቸዋል፡፡ይሀም ሴቶች በጉባኤ ሲገኙ ምን አይነት
አለባበስ ሊኖራቸው ይገባል? የሚልን ጉዳይ ነው (11፡2-16)፡፡ይህን ለማስረዳት ጳውሎስ ብዙ ግልፅ ያልሆኑ እና አጨቃጫቂ ሀሳቦች
አንስቷል፡፡42

41
ለአንዳንዶች የበሰሉት ማለት ፍጹም የሆኑ መንፈሳዊ ሰዎች ናቸው ሲል ሌላው ከፍ ያለ ደረጃ ላይ የደረሱ ሰዎች፤ለየት ያለ ጥበብ የተቀመጠ ከአለ ከተሰበከው
ከኢየሱስ ለየት ያለ መሆን አለበት ብለው ያስቀምጣሉ፡፡ ታዲያ ፍጥረታዊ የተባሉት (መንፈሳዊ የተባሉት ሰዎች ቁ 14) ዝቅ ያሉ መንፈሳዊነት ያላቸው ናቸው ወይስ
ለመስቀሉ መልዕክት እና ለመንፈስ ቅዱስ ሀይል ራሳቸውን ያላስገዙ (see Thiselton, Anthony C, The First Epistle to the Corinthians : A Commentary on the
Greek Text, (Grand Rapids, Mich:W.B. Eerdmans, 2000) 233.
42
አንዱ አነታራኪ ርዕስ ወንድ የሴት ራስ ነው የሚለው ነው፡፡አንዳንዶች የስልጣን ተዋረደን (Higheraricical ) ያመለክታል ብለው ሲረዱት ሊሌች አቻ
(hegaliterial_) አይነት ምልከታ አላቸው፡፡የኃለኞቹ ምንጭ (source) ያመለክታል፡፡ይህ ቃል ከነማብራሪያው እጅግ አሳቻ ነው፡፡ለምሳሌ የስልጣን ተዋረድ የሚሉት
በአብ እና በወልድስ መካከል የስልጣን ተዋረድ አለ?ለሚለው መልስ የላቸውም፡፡ሁለትኞቹ ምንጭ የሚሉት ግሩደም ባጠናው ጥናት በመጸሐፍ ቅዱስ ውስጥ በምንም
አይነት መንገድ ራስ የሚለው ምንጭ በሚለው ሳይሆን የበላይ በሚል እንደሚታይ አብራርቷል፡፡ያም ትክክል ሊሆን ይችላል፡፡ቴስልተን መከባበር የሚለው ትክክል ነው
በማለት ትንታኔ ይሰጣል (see Thiselton, Anthony C, The First Epistle to the Corinthians : A Commentary on the Greek Text, (Grand Rapids, Mich. :
W.B. Eerdmans, 2000,) 820-823.)
አራተኛ- ደግሞ የጌታን እራት በተነቀፈ ሁኔታ ማከናወንን በተመለከተ (11፡17-34)፡፡ይህም ሰው በጌታ እራት ላይ ተገቢው
አመለካከት ምንድነው የሚል ነው፡፡

አምስት-የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን እና ልምምድን የተመለከተ (12፡1-14፡40)፡፡ ትንቢት እና ልሳን ስጦታ በንጽጽር ቀርቧል (14፡1-
25)፡፡በዚህ ክፍል ጳውሎስ በልዩ ሁኔታ የትንቢት እና የልሳን ጥቅም ፅፎላቸዋል (14፡1-25)፡፡በልዩነት ውስጥ ስላለ አንድነት
አብራርቶላቸዋል (12) እንዲሁም ስለ ፍቅር ዘለዓለማዊነት ያም ምርጥ መንገድ በአግባብ እና በስርዓት ጉባኤዎችን ማድረግ
እንዳለብን ግልፅ አድርጎላቸዋል (14፡26-40)፡፡ ከዚያም ስለ አማኞች ትንሳኤ ነገረ መለኮታዊ ዕውነታዎችን ሲያብራራ ይታያል፡፡
በዚያም አማኞች በትንሳኤ ውስጥ ያለውን ድል አሻቅበው እንዲያዩ ያሳስባቸዋል (15)፡፡ከዚያም ገንዘብን ስለመሰብሰብ ያለባቸውን
ግርታ ሊያጠራ የሚችል መመሪያ ሲሰጥ እናያለን (16፡1-11)፡፡እና ሰለ አጵሎስ መምጣት ያብራራል፡፡ሐዋርያው እጅግ ጠቃሚ የሆኑ
መመሪያዎችን ሲሰጥ ይታያል ከዚያም መጸሐፉን በሰላምታ ይዘጋል (16፡13-18-ካርሰን 418)፡፡

2 ቆሮንቶስ ጭብጥ
2.1 ሰላምታ እና ምስጋና (1፡1-11)

በሁለተኛው የሃዋርያው ጳውሎስ መልዕክት የመጀመሪያው ሰላምታ በመስጠት ይጀምራል (1፡1-2) ከዚያ ለጥቆ ረጅም ምስጋና
ያቀርባል (1፡3-11)፡፡የምስጋናው ክፍል ስሜታዊነት ያዘነበለ እና በእርሱ( በጳውሎስ) ሕይወት ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡ይህም ከዚህ ቀደም
ያቀርብ የነበረውን ዓይነት የምስጋና አይነት ሳይሆን ከመከራ ጋር አያይዞ ምስጋናውን አሳይቷል (1፡10 ካርሰን 417)፡፡

2.3 የጉዞ ዕቅዱን መከለሱ ያብራራል

የጉዞ ዕቅዱን መሰረዙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷቸዋል (1፡12-2፡13)፡፡ልክ እንደ አለማዊ ሁኔታ ሀሳቡን የሚለዋውጥ እንዳልሆነ
ያብራራል(1፡12-14-ካርሰን 417)፡፡የጉዞ ዕቅዱን ከከለሰ በኃላ (1፡15-22) ለምን የጉዞውን ዕቅድ እንደቀየረ ማብራሪያ ይሰጣል፡፡ይህም
በዋናነት ቆሮንቶሳውያን በመጀመሪያው ጉዞ ወቅት እንዳደረሰባቸው ሀዘን እንዳያደርስባቸው በማሰብ እንደሆነ ግልፅ ያደርጋል (1፡
12-14-ካርሰን 417)፡፡

ተከትሎም አንድን ከዚህ በፊት ቤተ ክርስቲያን ገስፃው የነበረን ሰው እንዴት ይቅር ማለት እና ማፅናናት እንዳለባቸው
ያብራራል (2፡5-11)፡፡ይህን ደብዳቤ የጸፈበትን ጊዜ ግልፅ ያደርጋል ይህም ቲቶን በቆሮንቶስ ያለውን ሁኔታ ሪፖርት ይዞ
በጥራኦስ ሊያገኘው ሞክሮ እንዳልተሳካለት ያስረዳል፡፡ስለዚህ ወደ መቄዶኒያ ሄዶ ምን እየተከናወነ ማየት ፈልጓል (2፡12-
13)፡፡ከዚያ ወደ ምስጋና ሲዞር ይታያል (2፡14-17)፡፡

2.4 ሐዋርያዊ አገልግሎቱን ይከላከላል (2፡14-7፡1)

በአገልግሎቱ የእግዚብሄር የማስቻል ሀይል-2፡14-3፡18 ከዚያም ክርስቲያናዊ አገልግሎትን ያብራራል (2፡14-7፡4)፡፡ ጳውሎስ በዚህ
በረጅም ክፍል ውስጥ እግዚብሄር ራሱ ለአገልግሎቱ ብቃት እንደሰጠው ይናገራል፡፡ከእርሱ አገልግሎት የተነሳ ሰዎች በሁለት
ተከፍለዋል፡፡እነዚህም የሚድኑት እና የሚጠፉት ናቸው (2፡14-3፡6)፡፡ድሉን ለመግለፅ የሮማን ጀኔራል ምሳሌ ይጠቀማል፡፡ትልቁ ጥያቄ
ምርኮኞቹ እነማን ናቸው? ወይም ድሉን አክባሪ ማነው? የሚለው ነው፡፡ታዲያ ምሁራን ይህን በሁለት መልክ ይረዱታል43በሁለቱ
ኪዳናት ውስጥ ያለውን አገልግሎት ወደ ማወዳደር ይሄዳል (3፡7-18)፡፡

የክርስቶስ ሀይል በጳውሎስ አገልግሎት-4፡1-12 ጳውሎስ አገልግሎቱን በእግዚአብሄር ምህረት እንደተቀበለው ይናገራል፡፡በሂደቱም
ታማኝነቱን ለማሳየት ይሞክራል (4፡1-6)፡፡በዚህ አገልግሎት ውስጥ መዝገቡ ክርስቶስ እንደሆነ ይገልፃል ያንን መዝገብ የያዘው
ሸክላው ጳውሎስ ራሱ ነው (4፡7-18)፡፡

ጳውሎስ ዘለዓለማዊ ሽልማት እያሰበ ይሰራል-4፡13-5፡10 ሸክላው ምንም እንኳን ፈራሽ ቢሆንም ጳውሎስ ሁል ጊዜ ደካማ ነው
ማለት አይደለም፡፡ይህም የጳውሎስ ደካማ ማንነት ሰማያዊው ድንኳን መለወጡ አይቀርም (5፡1-10)፡፡

43
ይህ ታሪክ አንድ የሮም ጄኔራል ምርኮኞቹን ይዞ ድል አድርጎ ወደ ከተማ ሲገባ የሚያደርገውን የሰልፍ ስነ ስርዓት የሚያሳይ ነው፡፡በዚህ ምሳሌ ሁለት ዓይነት
አተረጓጎም ሊቃውንት ይከተላሉ፡፡አንዱ ጄኔራሉ ጌታ ኢየሱስ ሲሆን ወታደሮቹ እውቁቱን የሚያውዱት አገልጋዮቹ (እነ ጳውሎስ) ናቸው የሚል ነው፡፡ሁለተኛው
ራሱ ምርኮኛው ጳውሎስ ነው የሚል ነው፡፡በዚያም የራሱን መከራ ሊያሳይ ይሞክራል ብለው ብዙዎች ይሞግታሉ፡፡በዚህም ጳውሎስን ማረከው ከዚያ ዝናውን
እንዲየወጣ አደረገው ለማለት ነው፡፡ለዚህ ለሁለተኛው ትርጉም ለክርክር ከሚቀርቡ ጥቅሶች 1 ቆሮ 4፡8-13 2 ቆሮ 1፡5-10፤ 2፡14-16፤ 4፡7-12፤ 6፡4-10፤ 11፡23-28
(see Kistemaker, Simon J. and Hendriksen, William, New Testament Commentary : Exposition of the Second Epistle to the Corinthians, (Grand
Rapids : Baker Book House, 1953-2001) 89.
ጳውሎስ የክርስቶስ አምባሳደር-5፡11-6፡2 በዚህም ክርስቶስን እንጂ የሚያገለግላቸውን እንደማያስደስት ተረድቷል፡፡ሰሚዎቹ ምላሽ
ባይሰጡትም የክርስቶስ ፍቅር ብቻ በዚህ አገልግሎት ውስጥ እንዲቆይ እንዳስቻለው ይገልጻል፡፡ይህም እርቅን እንዲያውጅ እና
በክርስቶስ የተጀመረውን አዲስ ጅማሬ ሲገልጥ ይታያል (5፡16-21)፡፡ስለዚህ ጳውሎስ ቆርንቶሳውያን ልባቸውን ለእግዚአብሄር እና
ለእሱ እንዲከፍቱለት ይጠይቃቸዋል ጸጋውን በከንቱ እንዳይቀበሉ ግልፅ ያደርጋል (6፡1-13)፡፡

ለእግዚአብሄር በንፅህና መኖር ምላሹ ሌሎች ነገሮችን ባለመስማት በህይወታቸው ብቸኛው መሆን ያለበት አግዚአብሄር መሆን
አለበት (6፡14-7፡1)፡፡ስለዚህ ልመናውን ያቀርባል (7፡2-4,ካርሰን 418)፡፡

2.5. የቆሮንቶስ ለውጥ እና የጳውሎስ ደስታ-7፡2-26

ልክ እዚህ ክፍል ላይ ጳውሎስ ቲቶ የሚያስደስት ዜና ይዞ በመምጣቱ መደሰቱን በመግለፅ የጀመረውን ታሪክ ሲገልፅ ይታያል (7፡5-
16)፡፡ቀድሞ አቅርቦት ለነበረው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ በመስማቱ እጅግ ተደስቷል፡፡
2.6. ለኢየሩሳሌም የሚደረግ መዋጮ 8-9

የስጦታው ዓላማ እና እንዴት ይደረግ-8፡1-9፡5 ታዲያ በዚህ ጊዜ ስለ እርሱ ማሰባቸውን ይህም ለኢየሩሳሌም መደረግ ስላለበት
መዋጮ ማንሳት አስፈላጊ ሆኗል (8፡1-9፡15)፡፡የመቄዶኒያ ክርስቲያኖች በመስጠት ታላቅ የሆነ ምሳሌነትን አሳይተዋል ይህም
ቆርንቶሳውያን የጀመሩትን የገንዘብ ስጦታ ወደ ፍጻሜ አንዲያመጡት አበረታቷቸዋል (8፡7-15)፡፡የቲቶ ተልዕኮ የተጀመረውን
አገልግሎት (የመስጠት) ማበረታታት ነው (8፡16-24)፡፡

በመስጠት ላይ ሊኖረን የሚገባ አመለካከት-9፡6-15 ጳውሎስ እና የመቄዶንያ ክርስቲያኖች አንድ ላይ ለጉብኝት ወደ ቆሮንቶስ
ስለሚመጡ ይህን ለማመቻቸት ስራን ለመስራትም ሊሆን ይችላል (9፡1-5)፡፡መስጠትን ነገረ መለኮታዊ ዕይታ ፈንጥቆበታል (9፡6-15
ካርሰን 418)፡፡

2.7. እውነተኛ ለሐዋርያነቱ ማረጋገጫ

በ 1-9 እና 10-13 መካከል ያለው ግንኙነት ግልፅ አይደለም፡፡ነገር ግን በጳውሎስ እና በቆሮንቶስ መካከል አዲስ የሆነ ሽኩቻ
እንደተጀመረ ግልፅ ነው፡፡ስለዚህ ጳውሎስ ከእምነት የመነጨ መታዘዝን ሲጠይቅ ይታያል (10፡1-6)፡፡ስለ ትምክህት እንዲናገር
ምክንያት የሆነ ጉዳይ ውስጥ ከቶታል (10፡7-18)፡፡ሀሰተኛ ሐዋርያትን ሲነቅፍ እና የስህተት መስፈርቶችን ሲነቅፍ ይታያል (11፡1-
15)፡፡

በሞኝነታቸው ልክ ምላሽ ለመስጠት ይህም ትምክህትን በመግለጥ ተቃውሞዋቸውን ሲሞግት ይታያል (11፡18-33)፡፡እዚህ ጋ
ክርስቲያን መመካት አለበት ወይ የሚለው ነው? በእርግጥ የተመካው በድካሙ ነው፡፡ምክንያቱም ድካሙ የእግዚአብሄር ሀይል
እንዲገለጥ ዕድል ይሰጠዋል (12፡1-10)፡፡ቆሮንቶሳውያን ተቃዋሚዎችን አለመኮነናው ተግሳፅ ደርሶባቸዋል (12፡11,21)፡፡ለሶስተኛ
ጊዜ ሲመጣ ይህን ጉዳይ አጢነው ምላሽ መስጥ ካልቻሉ አጸፋው ከባድ ሊሆን እንደሚችል ያስጠነቅቃቸዋል፡፡መጸሐፉ በሰላምታ እና
በፀጋ ቃላት ይጨርሳል (ካርሰን 418)፡፡

ነገረ መለኮት
ወንጌል

ጳውሎስ በተደጋጋሚ የተቀበለውን መልዕክት እንዳስተላለፈ እና እነዚህያም መልዕክቶስ (ሰነዶች) ስልጣን ያላቸው እንደሆኑ ግልፅ
ያደርጋል፡፡44 የክርስቶስ ትንሳኤን እውነት ከሌሎች እንደተቀበለና ለቤተ ክርስቲያን እንዳስተላለፈ ይናገራል (1 ቆሮ. 15፡1-5)፡፡45ይህ
ምንባብ (1 ቆሮ. 15፡1-5) እጅግ ፋይዳ ያለው ነው፡፡አንደኛ ተቀበልኩ አስተላለፍኩኝ በሚለው ውስጥ ቀደምት አስተምህሮች ለእርሱ
እና ለአንባቢዎቹ ስልጣን ያላቸው መሆናቸውን ያሳያል፡፡46 ሁለተኛ ጳውሎስ የወንጌልን ዋና ዋና ሀሳቦች በእጣሬ መልክ አሳይቶናል
ይህም ወደ ድነት የሚያደርስ ነው፡፡ይህንንም ከሌሎች የተቀበለው እርሱ ራሱ ሲሰብክ ከነበረው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ 47
ሶስተኛ ዋናው የወንጌል መልዕክት መጸሐፍ እንደሚል ኢየሱስ ስለ ኀጢያታችን ሞተ እና ደግሞ ተነሳ የሚል ነው፡፡ 48አራተኛ ሌላኛው
ሞቱ እና ትንሳኤው መጸሐፍ እንደሚል በሚል የሚለው ሀሳብ አስፈላጊ ነው፡፡ይህም የተከናወነው መጸሐፍ እንደሚል ነው የሚለው
ሀሳብ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡49

44
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel 265.
45
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 266.
46
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 266.
47
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 266.
48
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 266.
49
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 266.
መስቀል

ለጳውሎስ ዋናው የቤተ ክርስቲያን ሀላፊነት የመስቀሉን ቃል ማወጅ ነው፡፡ይህም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል
ለማስተካከል ሲል ይህን ብሎታል፡፡50
አገልጋዮች
ጳውሎስ የአገልጋይ ሚናን እና ቦታ (status) ግልፅ አድርጎ ይናገራል 1 ቆሮ 3፡5-4፡5)፡፡51 በእግዚአብሄር ስራ ውስጥ ተካፋዮች ናቸው፡፡
እውነተኛ ፍሬ የሚሰጠው እግዚአብሄር መሆኑ እና መሰረቱ እግዚአብሄር እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ይህም ሆኖ ጳውሎስ ራሱን እና ያለውን
ስልጣን ለማሳየት ጥረት ሲያደርግ ይታያል (1 ቆሮ.9)፡፡52

መለኮት

ኢየሱስ አሁን ያለበትን ቦታ ያለምንም ጥርጥር ይናገራል፡፡ ይህም እርሱ በድካም ቢሰቀልም በሀይል እና በህያውነቱ አለ (2 ቆሮ 13፡
4)፡፡ያ ብቻ ሳይሆን እርሱ ጌታ ነው፡፡53ጳውሎስ የክርሰቶስን ጌትነት ሊያሳይ የሚሞክረው በቤተ ክርስቲያን ላይ ያለወን ስልጣን
ሊያሳይ ሲፈልግ ነው (1 ቆሮ.7፡10 9፡14)፡፡54 ከላይ ከላይ ስንመለከተው ጳውሎስ የእግዚአብሄር ፀጋ ለአንባቢዎቹ እንደተሰጠ
ያብራራል፡፡55 የተለያዩ ስጦታዎችን ሲዘረዘር ይታያል ያም የእውቀት ስጦታ እና የመናገር ስጦታዎ በምዕመናን ላይ የፈሰሰው
የካሪዝማ ስጦታ እንደሆነ ያትታል (1 ቆሮ. 1፡5-7)፡፡56

የማህበረ ምዕመን ህይወት


ጳውሎስ አማኞች የክርስቶስ አካል ናቸው በማለት ያብራራል፡፡ይህም በ 1 ቆሮ 6፡15 ላይ እያንዳንዱ ግለሰብ የክርስቶስ አካል እንደሆነ
አብራርቶታል፡፡57 ተመሳሳይ አይነት አገላለፅ በ 1 ቆሮ 10፡17 ላይ ለማሳየት ጥረት አድርጓል ይህም ከጌታ እራት ጋር አያይዞ ነው፡፡
ይህም አማኝ አንድ ናቸው፡፡ይህም ከአንድ ዳቦ ለሁሉም መካፈል ማለት አንድ መሆን ማለት ነው፡፡ 58 ማህበረ ምዕመኑ አማኞች
ወይም ቅዱሳን በሚል ተጠቅሰዋል (1 ቆሮ 2፡5፡ 14፡22-23 15፡11፣ 14፣17፣ 16፡13)፡፡59

ትንሳኤ

እንደ 1 ቆሮንቶስ መልዕክት ትንሳኤን በበቂ ሁኔታ ያብራራ መልዕክት የለም፡፡ይህ ሀሳብ ከዝሙት ጋር ተያይዞ ቀደም ብሎ ቀርቧል
(1 ቆሮ 6፡14)፡፡60የጳውሎስ ዋና ሀሳብ ሙታን ይነሳሉ ወይስ አይነሱም የሚል ጥያቄ እንጂ ያን ያክል ስለ አካላዊ ትንሳኤ ዋናው ሀሳብ
አድርጎ ሲናገር አይታይም (1 ቆሮ 15፡1-34)፡፡61
2 ቆሮንቶስ ነገረ መለኮት

የመፅናናት አምላክ

በነገረ እግዚአበሄር መጀመር ትክክለኛ ምልከታ ነው፡፡ በጳውሎስ ነገረ መለኮት ውስጥ አንዱ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነገረ
እግዚብሄር ነው፡፡በዚህ ነገረ መለኮት ምልከታ መጀመሩ ፋይዳው ብዙ ነው፡፡ይህም አምላክ የሐዋርያዊ ስልጣን ምንጭ ነው (1፡1)፡፡
እግዚአብሄር የቤተ ክርስቲያን ራስ፤ የሰላም እና የፀጋ ምንጭ ነው(1፡2)፡፡ጳውሎስ እያለፈበት ባለው መከራ እግዚአብሄርን የመፅናናት

50
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 267.
51
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 270.
52
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 270.
53
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 271.
54
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 271.
55
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 272.
56
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.272.
57
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 274.
58
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.274.
59
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 275.
60
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.277.
61
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel 278.
እና የርህራሄ አምላክ በማለት ይጠረዋል (1፡3)፡፡የሞት ድምፅን እየሰማም ቢሆን እግዚአብሄር ሙታንን የማስነሳት አቅም እንዳለው
ይናገራል፡፡62

እግዚአብሄር መፅናናትን ተስፋን እና እምነትን የሚያመጣ አምላክ ነው፡፡ኢየሱስን ከሞት አስነስቶታል፡፡በሞት ውስጥ ህይወትን
የሚለግስ ነው፡፡የፀጋ እና የርህራሄ አምላክ ሲሆን ያም ሰዎችን የሚጎበኝ ነው፡፡ሌላው ሀይሉን እና ፍቅሩን ለማሳየት ጥረት አድርጓል
(2 Cor 1:18; cf. 1 Cor 1:9; 10:13; 1 Thess 5:24; 2 Thess 3:3; 2 Tim 2:13)፡፡ 63
ኢየሱስ ክርስቶስ
ሕይወትን ሰጪ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን በትንሳኤ በማስነሳቱ ታይቷል፡፡በዚህ መሰረት ላይ ቆሞ አማኞችም ይነሳሉ ብሎ
ይናገራል (2 ቆሮ 4፡14)፡፡64 የእግዚአብሄር ፀጋ ክርስቶስ ሌለች ባለፀጋ እንዲሆኑ ራሱ በመድየት የታየ ታላቅ በረከት ነው (2 ቆሮ
8:9);65

አዲስ ፍጥረትት

ጳውሎስ ክርስቶስ ለእኛ ሞተ ማለት እኛ ከዚያ በኃላ ለእርሱ እንድንኖር አድርጎናል፡፡ 66ከክርስቶስ ጋር አንድ የሆኑ (በእምነት
አማካኝነት) ከሞቱ እና ከትንሳኤው ጋር አንድ ሆኗል (ገላ 2፡20)፡፡67 ይህ ሰዎችን ከአሮጌው የራስ ወዳድነት ማለትም ከኀጢያት እና
ከአመፅ ህይወት ነጻ ያወጣል፡፡68ሰዎችን በስጋዊ ዕይታ ማየት አብቅቶ በክርስቶስ ውስጥ ማየት እንጀምራለን፡፡በአሮጌው እይታ ከሆነ
ኢየሱስን እንደ መሲሕ እና የእግዚአብሄር የአዲስ ፍጥረት ወኪል ትሆናልህ፡፡ 69

ዕርቅ

ጳውሎስ ራሱን ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር የሚያስታርቅ አምባሳደር አድርጎ ይመለከታል፡፡ይህ የእርቅ ልመና በዋናነት ኀጢያተኞችን
እና የማያምኑትን ነው፡፡ይህን ግን ያለው በማህበረ ምዕመኑ ውስጥ እና ከራሱ ጋር ዕርቅ ከማድረግ አንጻር የተነገረ ጉዳይ ነው፡፡ 70ዕርቅ
ሁለት ዓይነት ገፀታ ያለው ሕይወት ነው፡፡በአንድ እጅ ከራሱ ጋር በክርስቶስ ሆኖ ሲያስታርቅ ያንን አገልግሎት ደግሞ ለእኛ ሰጠን፡፡ 71

ሞት ፍርድ እና መለወጥ
የማያቋርጥ ለውጥ መጨረሻ ወደሚያንጸባርቅ በክብር የተሞላ ህይወት ያደርሳል፡፡ሊገለጥ ያለው ክብር ሲተያይ የዚህ ዘመን ስቃይ
ምንም አይደለም (2 ቆሮ 5፡1-10)፡፡ይህ ክፍል እጅግ አወዛጋቢ ነው፡፡72

አንደኛ ጊዚያዊው ምድራዊ ድንኳን በዘለዓለማዊው ይተካል፡፡ይህ እንግዲህ ምንም አይነት ምጸአት ንጥቀት ሳይኖር ቀጥታ አካላዊ
ሞትን የሚያመለክት ነው (1 ተሰ 4)፡፡73 ሁለተኛ ሙታን ራቁታቸውን አይሆኑም የሚለው ዘይቢያዊው ንግግር የነፍስ ያለ ምንም
ዓይንት አካል ሳትለብስ ልትሆን የምትችልበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡ይህ አባባል የሚጣረሰው ከ 2 ቆሮ 4፡16 ጋር ነው፡፡ያም ወጪያዊ
አካላችን ቢበሰብስ እንኳን ውስጣዊው ይታደሳል ስለሚል ነው፡፡ምናልባት ጳውሎስ ያንን ይሆናል ይታደሳል የሚለው፡፡ 74ሶስተኛ
መንፈስ እንደ መያዣነት ሲሰጠን ያ ምናልባት አዲሱን ውስጣዊውን ሊያድስ ይሆናል፡፡75

62
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 291.
63
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.291.
64
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 291.
65
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.291.
66
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 294.
67
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.294.
68
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.294.
69
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 294.
70
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 294.
71
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 294
72
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 298.
73
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 298.
74
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 299.
75
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.299.
ዋናው ችግር የሚለው ጥያቄ ግን መቼ እና እንዴት ነው ይህ ክስተት የሚሆነው የሚለው ነው፡፡እንደ 1 ቆሮ 15 መሰረት
የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ይውጣል ያም ክርስቶስ ሲመጣ ነው (1 ቆሮ 15፡50፡55)፡፡ይህ ከ 1 ተሰ 4 ጋር ይጣጣማል፡፡ነገር ግን
እንደ ፊሊ 1፡20-26 መሞት ከጌታ ጋር መገኘት ነው፡፡76

በጌታ ሆኖ ማንቀላፋት (1 ተሰ 4፡14-15) ማለት በጌታ ዘንድ መገኘት ማለት ሲሆን ሙታንም ያንን ሁኔታ (ከጌታ ጋር መሆናቸውን)
ያውቁታል፡፡ይህም ሲሞቱ ከጌታ ጋር ወደ ዘለዓለማዊ ቤታቸው ይሄዳሉ (2 ቆሮ 5፡8)፡፡77

መመካት
2 ቆሮ ብዙ የሚጣመሩ ጉዳዮች ያለበት መጸሐፍ ነው፡፡ጳውሎስ እግዚአብሄር በቆሮንቶስ አማኞች ውስጥ የሚሰራውን ስራ
ተመልክቶ ነው የተመካው (2 ቆሮ 7፡4)፡፡ስለ እነርሱ በሌሎች ዘንድ ይመካሉ (2 ቆሮ 8፡24፤ 9፡2-3)፡፡78 በሰዎች ደረጃ መተማመን እና
መኩራት የሚያሳይ ሀሳብ ነው (2 ቆሮ 11፡18)፡፡ሰዎችን ሊመኩ የሚችሉበትን ዝርዝር ሀሳብ እየሰጠ አይደለም፡፡79
መወያያ ጥያቄ
ገላተያ
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
መጸሐፉ በሐዋርያው ጳውሎስ እንደተጻፈ ይናገራል (1፡1)፡፡ጸሐፊው በአዲስ አማኞች መካከል ለተከሰተው የስህተት ትምህርት ግድ
የሚለው መጋቢ ወይም ወንጌላዊ እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡ገላተያ ታማኝ የሆነ እንደሆነ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም፡፡አከራካሪው ጉዳይ
ጳውሎስ ራሱን እንዴት ነበር ያየው እንደ ክርስቲያን አይሁድ ይህን ደብዳቤ ሲፅፍ ነው፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን

ሐ. ዓላማ
ጳውሎስ ለገላተያ አማኞች ጥሪ እያቀረበ ነው (1:2)፡፡ያም እውነተኛውን ወንጌል ቸል በማለታቸው ነው(1፡7)፡፡ይህ እውነተኛ ወንጌል
ጳውሎስ ራሱ የሰበከው እና እነርሱ ቀጥታ የተቀበሉት ነው፡፡ይህም በኢየሱስ ክርስቶስ መገለጥ ለጳውሎው የተሰጠ ነው (1:12)፡፡ይህ
ወንጌል በሌሎች የተሰበከ ነው (2:7–9)፡፡ የተበረዘ ወይም የተለወጠ ወንጌል በጭራሽ ተቀባይነት የለውም፡፡የትኛውም ልዩ ወንጌል
ከጳውሎስ ወይም ከመላዕክት እንኳን ቢመጣ ከቀደመው እምነታቸው እንዲያፈነግጡ ሊያደርጋቸው እንደሆነ ግልፅ ነው (1:8-
En.280)፡፡

ጭብጥ
1. መግቢያ 1፡1-10
የጳውሎስ በዚህ መልዕክት ውስጥ የተጠቀሰው ሰላምታ በአመዛኙ ከሐዋርያዊ ስልጣኑ ጋር ተያይዞ የቀረበ ሲሆን ያም በምዕራፉ
ውስጥ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ነው ፡፡በእግዚአብሄር የተላከ እንደሆነ ተናግሯል እና ጌታ ራሱን የሰጠው ለአሁኑ ክፉ ዓለም እንደሆነ
ይናገራል (1:1–5-Carson-456 )፡፡እንደተለመደው የምስጋና ጉዳይ ሳያነሳ በቀጥታ አስቀድሞ የተሰበከላቸውን ወንጌል መተዋቸውን
በአግራሞት ይጠይቃል፡፡የተዉት ወንጌልን ብቻ ሳይሆን ክርስቶስን ጭምር እንደሆነ ይናገራል (1፡6)፡፡ለገላተያ የተሰበከው ወንጌል
ወይም በሐዋርያትም ሆነ በመላዕክት ሊለወጥ የማይችል ነው (1፡6-10)፡፡
2. ጳውሎስ የሚሰብከው ወንጌል
ወንጌሉን ከክርስቶ ከራሱ በመገለጥ እንዳገኘው ይናገራል፡፡ሌላው እንዴት ተሰዶ እንደነበር ያትታል፡፡እንዲሁም ከአንዳንድ ሐዋርያት
ጋር እንደተገናኙ ይፅፋል፡፡ይህንንም የሚያብራራው ሐዋርያት በተናገሩት ብቻ ሳይሆን ከክርስቶስ በመገለጥ እንዳገኘው ለመናገር
ነው፡፡አህዛብ የአይሁድን የመገረዝ እና የምግብ ስርዓቶች በማድረግ አይሁድ እንዲሆኑ ከሚያስገድዱት የኢየሩሳሌም መሪዎች በተለየ
ሁኔታ ቲቶ እንዲገረዝ አላደረገውም (2፡1-5)፡፡

76
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 300.
77
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 301.
78
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 302.
79
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 302.
ጳውሎስ እና የኢየሩሳሌም መሪዎች በስራ ክፍፍል ጉዳይ ላይ ማለትም ጰጥሮስን ለአይሁድ ጳውሎስ ደግሞ ለአህዛብ የውንጌል
አደራ እንደተሰጣቸው እና በዚያም ጉዳይ ላይ ከስምምነት መድረሳቸውን ሊያሳይ ጥረት ያደርጋል፡፡ይህን ሊያሳይ የሞከረው አህዛብ
እንደ ሙሴ ህግ መገረዝ የለባቸውም የሚለውን እውነት ለማሳየት ነው (2፡6-10)፡፡
3. ድነትን የሚያደናቅፍ ልምምድን ነቀፈ (2፡11-21)
በኃላ ጴጥሮስ ከአህዛብ ጋር ከመብላት ሲያፈገፍግ ሲመለከት ያ የሆነው ከኢየሩሳሌም የመጡትን አይሁዶች ጫና ፈርቶ እንደሆነ
ያብራራል፡፡ይህ ግን ትክክል እንዳልሆነ ሲያስረዳ ምክንያቱም አይሁድ ራሱ የዳኑት በህግ ስራ እንዳልሆነ ይገልፃል (2፡11-14)፡፡
ይህንንም ደግሞ ጴጥሮስ ራሱ ያመንበት የነበረ ጉዳይ ነው (የሐዋ 10፡-11፡18)፡፡በክርስቶስ የጸደቁ ኀጢያተኞች ለህግ ሞተው
በእግዚአብሄር ልጅ ላይ በአለ እምነት ይኖራሉ (2፡15-21)፡፡ጳውሎስ ይህን እውነት የሚቀናቀን ከዚህ እውነት ያፈነገጠ ነገረ መለኮት
አስቆጥቶታል፡፡ይህ ሁሉ ካልሆነ ክርስቶስ የሞተው በከንቱ ነው ማለት ነው (2:21-Carson-456)፡፡
4. በእምነት የሚገኘው ድነት
በጣም ሴሜታዊ በሆነ ሁኔታ ጳውሎስ መንፈስ ተሰጥቷቸው የነበረው ህግን በመጠበቃቸው ሳይሆን በክርስቶሰ ላይ በነበራቸው
እምነት እንደሆነ ይነግራቸዋል faith in Christ (3:1–5)፡፡

ይህ ጉዳይ እንግዳ አይደለም ምክንያቱም አብርሃም ራሱ የጸደቀው በእምነት ነው (3፡6-9) ያ ብቻ ሳይሆን በዘሩ አማካኝነት አህዛብ
እንደሚባረኩ ተስፋ እንደተሰጠው ይናገራል፡፡የሙሴ ህግ በተለየ ሁኔታ ነው እየሰራ ያለው፡፡ያም ኀጢያተኞ ላይ እርግማን ሲያመጣ
ያንን እርግማን ክርስቶስ ተሸክሞታል (3:10–14)፡፡ህግ በምንም ዓይነት ለአብርሃም የተነገረውን ኪዳን ሊተካው ወይም ሊለውጠው
አይችልም፡፡ህግ በብዙ መንገድ ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ እንደሞግዚት ሆኖ አገልግሏል (3:15–25)፡፡ህግ ኀጢያትን ወደ በደል
(በትዕዛዝ ምክንያት) በመለወጥ ሰዎችን በሞግዚትነት ይዞ ነበር ያም ወደ እርሱ አመልካች ወደሆነው ክርስቶስ እስኪመጣ ድረስ
ነው፡፡የእምነት የበላይነት ማለት ያለምንም የዘር ልዩነት ገደብን ሁሉ አስወግዷል፡፡እግዚአብሄር አንድ ህዝብ ብቻ ነው ያለው (3:26–
29)፡፡አህዛብ ባሮች አይደለም ይልቅ ልጆች ናቸው (4:1–7-Carson-457)፡፡

የሲናይን ህግ በመጠበቅ ገላቲያውያን ወደ ቀድሞ ባርነት ሊመለሱ እንዳላቸው ያስረዳቸዋል፡፡ጳውሎስ ትምህርቱን እንዳይቃወሙ
ያሳስባቸዋል (4:8–20)፡፡አብርሃም ሁለት ልጆቸን እንደ ምሳሌ በመውሰድ ስለሁለቱ ኪዳናት ይናገራል፡፡ህግን በመጠበቅ ገላታውያን
ወደ ብሉይ ኪዳን እንደሚመለሱ ያስረዳቸዋል (4፡21-31)፡፡

5. የእምነት ህይወትን ያብራራል


ክርስቶስ ያቀዳጃቸውን አርነት መጠበቅ እንጂ በግርዘት ወደዚያ ባርነት እንዳይመለሱ ያን ባርነት ያሳስባቸዋል (5፡1-12)፡፡ጳውሎስ
ህይወትን በመንፈስ መኖር በስጋ ከመኖር ጋር እርስ በእርሱ እንደሚቀዋመም ያስረዳል (6፡1-10)፡፡በመጨረሻ መገረዘም ሆነ
አለመገረዝ ምንም ቁብ የሚሰጥ ነገር እንዳልሆነ ይልቅ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን ዋና ነገር እንደሆነ ይናገራል (6:11–18-
Carson-457)፡፡

ነገረ መለኮት
የድነት ታሪክ እና ወንጌል

ወንጌል ማለት የሚሰበክ እንደሆነ ማየት ይቻላል (ገላ 1፡11)፡፡ይህም ማለት ሰዎች ምላሽ የሚሰጡበት ቃል ነው (ገላ. 1፡9)፡፡ይህም
ኢየሱስ ስለ ኀጢያታችን ሞቷል ብሎ መመስከር መቻል ነው (ገላ 2፡20)፡፡ታዲያ ክርስትና የሚታወጅ ድነት ነው፡፡80 ስለዚህ ወንጌል
ማለት የሆነውን መተርጓም መቻል ነው (ገላ 3፡1)፡፡አንድ የሆነ ሰው በመስቀል ላይ ሞቷል የሚለው በእውን ምን ሆነ የሚለው ጉዳይ
የሚያሳይ ሲሆን ፡፡ያ ግን ግማሽ እውነት ብቻ ነው፡፡ኢየሱስ ስለ ኀጢያታችን ራሱን በመስቀል ላይ ሰጠ የሚለው ትርጓሜው ነው
ወንጌልን ወንጌል የሚያሰኘው (ገላ.1፡3-4)፡፡81የኢየሱስ ሞት ማለት ከኀጢያት ፈጽሞ ያድናል ማለት ሲሆን አሁን የሰው ልጆች
ካሉበት ሁኔታ ያድናቸዋል ማለት ነው፡፡82

መጽደቅ

80
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 220.
81
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 220.
82
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 223.
ጳውሎስ ከአይሁዶች ጋር በነበረበት ሙግት አንድ ቃል ተጠቅሟል ያም መጽደቅ ወይም ዱካዮሱኔ የሚል ነው፡፡ይህም መጽደቅ
ማለት ነው፡፡መጽደቅ ጸድቅ የመሆን ክስተት ነው፡፡ዋናው ቃል በግሪክ ዲካዮ ትክክል ወይም ጻድቅ ማለት ነው፡፡83

የጳውሎስ መልዕክት እና ህግ
ግልፅ በአለ ሁኔታ ጳውሎስ ህግን በመፈጸም እና በክርስቶስ ማመን ያላቸውን ተቃርኖ ለማሳየት ጥረት አደርጓል፡፡የገላተያ አማኞች
በህግ ለመጽደቅ ፍላጎት እንዳላቸው ይነግራቸዋል (ገላ 5፡4) ያም “ሰው በህግ ስራ መጽደቅ አይችልም“ የሚለው ኀረፍተ ነገር ነው
(ገላ.2፡16)፡፡የእግዚአብሄርም በረከት የመጣው ህግን በመጠበቅ ሳይሆን በእምነት ነው፡፡84እንግዲህ እነዚህን አገላለጾች ልብ እንበል ያም
“ህግን መጠበቅ”፤“በህግ ስራ”፤“ህግ የሚጠብቅብንን መፈጸም”85 የሚሉት ኀረፍተ ነገሮች በሙሉ ተመሳሳይ ናቸው፡፡ከዚህ ሀሳብ
ሙሉ በልዩነት የሚቆሙ አሉ፡፡86

ለምንድነው ግን ሰው ህግን በመጠበቅ ሊጸድቅ የማይችለው? ህግ ህይወትን መስጠት አይችልም ወይም ያንን አይልም (ገላ 3:21)፡፡
ነገር ግን ህግ ህይወትን ይሰጣል ብለው ሰዎች ለምን ይናገራሉ?ህግ ለሚጠብቁት ህይወት እንደሚለግሳቸው ይናገራል (ገላ 3:12,
የጠቀሰው ከዘሌ 18:5 ሲሆን ሮሜ 10:5 ጠቅሶታል)፡፡ጳውሎስ ህግን ከእምነት ጋር ጎን ለጎን ያስቀምጣል፡፡ስለ እምነት ሲናገር ጻድቅ
በእምነት በህይወት ይኖራል በማለት ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ነገር ግን ህግ ህይወት መስጠት አይችልም፡፡ህይወትን መስጠት የሚችለው
መንፈስ ነው(2 ቆሮ. 3፡6)፡፡በህግ እና በመንፈስ መካከል ያለው መሰረታዊ ልዩነት ህግ መጠበቁ (demand) ሲሆን መንፈስ ግን ኃይል
ማጎናጸፉ ነው፡፡87 ምንም እንኳን ሰዎች በቃል ኪዳን ውስጥ በህግ መኖር (ኮቭናንታል ኖሚዘም) ቢያምኑም ነገር ግን አይሁድ 4040
ከቃል ኪዳኑ አፈንግጠው የነበሩበት እና ከእግዚአብሄር ጋር ጉዳያቸውን የሚያስተካክሉት ህግን በመጠበቅ እንደነበር ያም አንዳንድ
የህግ መምህራንን በመከተል እንደሆነ ልባ ማለት ይቻላል፡፡ስለዚህ ቀጥተኛው አስተምህሮ የነበረው ህግን መጠበቅ መጽደቅ ማለት
ነው ተብሎ ይታሰባል፡፡88ህግን አለመጠበቅ ማለት በእርግማን ስር መሆን ማለት ነው (ገላ.3፡21፤ ዘዳ 27፡26)፡፡ህግ ወደ ህይወት
ያደርሳል ተብሎ አይታሰብም (ገላ 3:21).89

መንፈስ
በገላተያ መጸሐፍ የመንፈስ ሚና ምንድነው ብለን ልንዳስስ ይገባናል፡መስቀል ከ 1-3 ድረሰ አብይ ስፍራ ይዟል ብለን የምንል ከሆነ
መንፈስ ደግሞ ከ 4-6 ትልቁን ሚና ሲጫወት እናያለን፡፡እርግጥ ነው በመጀመሪያው ክፍል ውስጥ ስለ መንፈስ የተጠቀሰው በ 3፡1-
5፣14 ላይ ብቻ ነው፡፡ጳውሎስ በዚህ ስፍራ ዋናው የመከራከሪያ ነጥቡን አማኞች መንፈስን ስራ ከተለማመዱ በኃላ የይሁዲነት
እምነት አቀንቃኞ ሲመጡ ወደ ህግ እንዴት እንደዞሩ በማሳየት ነው፡፡በማህበረ ምዕመናን መካከል እግዚአብሄር የመንፈስን ግልጠት
(manifestations) የሰጠው ህግን ስለፈፀሙ አልነበረም፡፡የመንፈስ መሰጠት የአብርሃም በረከት ውጤት ነው፡፡የአብርሃም በረከት
በክርስቶስ በኩል የመንፈስ መሰጠት ማለት ነው፡፡90

ለጳውሎስ በህግ ስር በህግ ጥላ ስር መሆን በባርነት እንደመኖር ማለት ሲሆን በጻጋ ስር መሆን ማለት ደግሞ የእግዚአብሄር ልጆች
መሆን ማለት ነው፡፡ይህ በክርስቶስ ያገኘነው አዲስ ስፍራ የሁለት መንስኤዎች ውጤት እንደሆነ ይነግረናል፡፡ልጆች የተሆነው
በእምነት ነው (Gal 3.26)፡፡ይህም እምነት በጥምቀት ድርጊት የተፈጸመ ነው፡፡ያም ጥምቀት በክርስቶስ ውስጥ መካተቻ እና
ከእግዚአብሄር ጋር አዲስ ግንኙነት መጀመሪያ እና ክርስቶስን መልበሻ እንደሆነ ተገልጧል፡፡ ሁለተኛው መንሰኤ እግዚአብሄር የልጁን
መንፈስ ወደ አማኞች መላኩ ነው፡፡መንፈስ የተላከው ለእምነት ምላሽ ሆኖ ነው፡፡ያ መንፈስም የልጅነትን ስልጣን እንድንቀናጅ
አድርጎናል፡፡ይህም አማኞችን አባቴ ለማለት ያበቃል፡፡91

83
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 222.
84
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. 227.
85
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 227
86
ይህም አስቀድመን እንዳልነው ጳውሎስ የተቃወመው የህግ ስራ እስራኤል በልዩነት እንድትታይ የሚያደርጓት መለዮ ሲሆን እነርሱም የምግብ ስርዓት፤ግርዘት
የመሳሰሉትን ነው፡፡
87
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 227
4040
This is the phrase used by E. P. Sanders, Paul, the Law and the Jewish People (Philadelphia: Fortress, 1983), to characterize his
understanding of Judaism (pp. 444–50).
88
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 228
89
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 230
90
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 232
91
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 233
ገላተያ 5፡16-25 ስለ መንፈስ የሚናገር ዋናው እና እጅግ ጠቃሚ የሆነ ክፍል ነው፡፡መንፈስ አንዳንድ አስፈላጊ የሆኑ ባህሪያትን
ማፍራት እንድንችል ያስችለናል፡፡ያ መንፈስ ህይወት ሰጪ ዘዋሪ ሲሆን ይህም ፍሬ እንድናፈራ ያስችለናል፡፡ይህም የፍቅር ደስታ
ሰላም እና የመሳሰሉት መገለጥ ነው፡፡አማኝ መንፈስ እነዚህ ነገሮች እንዲያደርግ ልንፈቅድ ይገባናል፡፡ 92

1 እና 2 ተሰሎንቄ

መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
ጸሐፊ ማነው የሚለውን ጥያቄ ካርሰን በሶስት መልክ ለማየት ጥረት ያደርጋል(ካርሰን 532)፡፡አንድም ተባባሪ ጸሐፊ ሌላው አንደኛ
ተሰሎንቄን የተረጎመው እና የጳውሎስ የራሱ ጸሐፊነት ማለት ነው (ካርሰን 532)፡፡አንዳንዶች ጭማሪ ክፍሎች አሉ ብለው ይህ
ጭማሪ በሌሎች ተጽፏል ብለው ይላሉ፡፡ ሁለቱም መልዕክቶች ደራሲውን ጳውሎስ ሲላስ እና ጢሞቲዮስ ጸሐፊዎች እንደሆኑ
ይናገራል፡፡ነገር ግን ትውፊት ጸሐፊው ጳውሎስ ነው ይላል፡፡

ይህ ትክክል ነው ወይ?ከሌሎች የጳውሎስ መልዕክቶች በተለየ ሁኔታ በሁለተኛ መደብ ብዙ (እኛ) የተገለፁ ናቸው፡፡ይህ ይሁን እንጂ
አንደኛ መደብ ነጠላ ግን ተጠቅሷል (1 ተሰ 2፡18፤3፡5፤5፡27 እና 2 ተሰ.2፡5፤ 3፡17)፡፡በኀብረት ተፅፏል ብለን ብንል እንኳን ይህ ግን
ያልተለመደ ነው፡፡ስለዚህ የመጀመሪያ መደብ ነጠላ መጠቀሙ የስነ ፅሁን ዘዴ ሊሆን ይችላል ብሎ ካርሰን ይከራከራል (ካርሰን 536)፡፡

ወደ ሁለተኛ ተሰሎንቄ ስንመጣ ግር የሚል ነገር ያጋጥመናል፡፡መጸሐፉ በጳውሎስ አልተጻፈም የሚለው ሀሳብ በብዙዎች ምሁራን
ዘንድ ተቀባይነት አግኝቷል (ካርሰን 537)፡፡ምንም እንኳን በሁለቱ መጸሐፉች መካከል የፅሁፍ ድግምግሞሽ ያለ ቢመስልም ያ ግን
መጸሐፉ ሲጀምር እና ሲያልቅ ስለሆነ ያን ያክል የሚያስኬድ አይደለም፡፡ለምሳሌ ስለ አገልግሎቱ በሚናገረው ክፍል (1 ተሰ 2፡1-3፡13)
ምንም አይነት ዝምድና ከ 2 ተሰ ጋር የለውም፡፡ስለዚህ ይህን ስናይ ጳውሎስ ሁለቱንም መጸሐፉች ፅፎታል የሚለው አሳማኝ ነው
(ካርሰን 545)፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
1 እና 2 ኛ ተሰሎንቄ የተጻፈው በ 50 እና 51 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡

ሐ. ዓላማ
ጳውሎስ መጸሐፍቱን የጻፈበት ሶስት መሰረታዊ አላማዎች አሉት፡፡አንደኛ በጥድፊያ ከተሰሎንቄ የወጣበትን ሀሳብ ለማብራራት
ነው (1-3)፡፡ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር የሚያመጣውን ፋይዳ ለማሳየት (4፡1-12) ሌላው በሟች ዘመዶቻቸው ምክንያት ያዘኑ
ወገኖችን ለማጽናናት ጽፏታል (4፡13-5፡11-Carson-544)፡፡

መ. የመጸሐፉቶቹ ቅደም ተከተል


የትኛው ከየትኛው ቀድሞ ተጸፈ የሚለው በዚህ ዘመን ያሉ የተሰሎንቄን መጸሐፍ የሚያጠኑ ምሁራን አብይ ጥያቄ ነው፡፡
አንዳንዶች ሁለተኛ ተሰሎንቄ ሲሉ ሌሎች አንደኛ ተሰሎንቄ ቀዳሚ ነው ስለዚህ በትውፊት የተላለፈልን የመጸሐፍቶቹ ቅደም
ተከተል ትክክል ነው ብለው ይሞግታሉ፡፡ይህ ምን ይፈይድልናል ለሚል ምናልባት ወደ ፊት ጠጋ ብሎ ማጥናት ለሚፈልግ እንግዳ
እንዳይሆንበት ታስቦ የቀረበ ነው፡፡
1. ሁለተኛ ተሰሎንቄ ይቀድማል
አንደኛ-ስደቱ በአንደኛ ተሰሎንቄ የአለፈ ጉዳይ ሲሆን በሁለተኛው ግን እንደ አዲስ ይታይ ነበር፡፡ይህም 2 ተሰሎንቄ 1፡4-7 በአሁን
ጊዜ ይናገራል፡፡ስደቱን እየታገሳችሁ (4) መከራ እየተቀበላችሁ (5) ለሚያስጨንቋችሁ (6) እየተቸገራችሁ ያላችሁ (7)

ሁለተኛ-1 ተሰ ስደት ትዝታ ነው፡፡ያም 1 ተሰ 2፡14 እና 3፡4 ከገዛ ወገናችሁ ተሰቃይታችኃል፡፡


ሦስተኛ-የጢሞቲዎስ መላክ እና የ 2 ተሰሎንቄ መጸሐፍ ዓላማ ተመሳሳይ ነው፡፡ይህም ጢሞቲዎስን መላኩ በእምነታቸው
እንዲያበረታቸው እና እንዲያፅናናቸው ነበር (1 ተሰ 3፡2) ያም 2 ተሰሎንቄ እግዚአብሄር እንዲያበረታችሁ በማለት ይነግራቸዋል
(2 ተሰ 2፡17)፡፡ጢሞቴዎስ ወደዚያ የሄደው ማንም ሰው በመከራው እንዳይናወጥ ነው (1 ተሰ 3፡3)፡፡ስለዚህ አስቀድሞ 2 ተሰሎንቄን
ይዞት ሄዶ ነበር፡፡
2. 2 ተሰሎንቄ ይቀድማል
አንደኛ -1 ተሰሎንቄ ራሱ እየተጻፈ በነበረበት ጊዜ መከራ ላይ ነበሩ፡፡ወይም አንዳንድ ክፍሎች እንዳለፈ ትዝታ መከራን ማሰብ
ትክክል አይደለም፡፡ወይም እነዚህ ቁጥሮች መከራን እንዳለፈ ጉዳይ የሚያዩት (1፡6፤ 2፡14፤ 3፡2-4) የሚያወሩት ወንጌልን ሲቀበሉ

92
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 233
ያለውን ታሪክ ነው፡፡መከራው ያለፈ ጉዳይ አይደለም 1 ተሰሎንቄ ሲጻፍ፡፡ ያን የምናየው በጌታ በርትታችኃል (1 ተሰ 3፡8፤ፊሊ 1፡27
2 ተሰ 2፡15) የሚለው አሁን በመከራ ውስጥ ማለት ነው፡፡1 ተሰ 3፡2 ይህ መከራ የሚለው ያሉበትን ጊዜ ነው፡፡
ሁለተኛ-ጢሞቴዎስ ወደ ተሰሎንቄ በሄደ ጊዜ (1 ተሰ 3፡1-5) ሁለተኛ ተሰሎንቄን (እንደ መጀመሪያ መጸሐፍ) ይዞት ሄዷል የሚል
ምንም አይነት መረጃ የለንም፡፡
ሦስተኛ ጢሞቴዎስ መሄዱ (1 ተሰ 3፡3፤ 2 ተሰ 2፡17) እና ሁለቱም እንርሱ እንዲበረቱ መነገሩ በዕውን 2 ተሰሎንቄን ይዞት ሄዷል
ማለት ይቻላል?
ሦስተኛ-አስቀድመን እንደነገርናችሁ ያለ ስርዓት የሚሄዱ (1 ተሰ 4፡11) የሚለው ሀረግ ምናልባትም ይህ አይነት አስተምህሮ በቃል
የተላለፈ ይሆናል እንጂ ሁለተኛውን ተሰሎንቄ ላይሆን ይችላል፡፡
አራተኛ ስለ ጊዜ እና ሰዓት ልንነግራች አያስፈልግም ያለው (1 ተሰ 5፡1) ቀድሞ በሁለተኛ ተሰሎንቄ (እንደ አንደኛ መጸሐፍ
ቆጥረው) እንዳወቁ ያመለክታል ይላሉ፡፡ይህ ግን በቤተ ክርስቲያን በአፍ ሲነገር የቆየ ጉዳይ ነው፡፡
አምስት ማብራሪያ ለመስጠት (1 ተሰ 4፡9-10 እና 2 ተሰ 3፡6-15 1 ተሰ 4፡13 እና 2 ተሰ 2፡1-12 ተሰ 5፡1 እና 2 ተሰ 2፡1-12) ግን ይህ
ተብራራ የተባለውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲናገር የነበረ ሊሆን ይችላል፡፡93

መ. ጭብጥ
1 ተሰሎንቄ

1. እምነታቸውን ያነሳል 1-3

መጸሐፉ ለየት ባለ ሰላምታ ይጀምራል (1፡1-3) ይህም ጳውሎስን ሲላስን እና ጢሞቲየስን እንደ መጸሐፉ ላኪ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
የተሰሎንቄ አማኞች በሙሉ ልብ ለወንጌል ያሳዩትን መሰጠት በማስታወስ ሲያመሰግናቸው ይታያል (1፡4-10)፡፡የመጸሐፉ አካል
ሁለት ዓይነት ክፍሎች አሉት አንዱ 2፡1-3፡13 ሲሆን ያም ሐዋርያው ከተሰሎንቄ ወገኖች ጋር ያለውን መስተጋብር የሚያነሳ ነው፡፡
ሁለተኛው ጳውሎስ ለተሰሎንቄ አማኞች መመሪያ ሲሰጣቸው ይታያል (4፡1-5፡11)፡፡

ጳውሎስ በተሰሎንቄ የነበረውን አገልግሎት በማውሳት ይጀምራል (2፡1-12)፡፡እንዴት አድርጎ እንደ ሰበከ ከሚያትተው ሀሳቡ እንዴት
እድርጎ እንደ ተቀበሉ ይናገራል፡፡እንዴት አድርጎ እንደ ተቀበሉ በማሰብ ያመሰግናቸዋል፡፡ለወንጌል የከፈሉት መስዋትነት ለወንጌል
መሰጠታቸውን እንደሚያመለክት (ካርሰን-533) ይናገራቸዋል (2:14–16)፡፡ተመሳሳይ ስደት የጳውሎስን የተሰሎንቄ ቆይታ ያሳጠረ
እና ምናልባትም ይጸኑ ይሆን የሚል ፍርሃትን ያሳደረበት ነው (2:17– 3:5)፡፡ነገር ግን ጢሞቲዮስ ሁሉ ሰላም እንደሆነ ይናገራል (3፡6-
13-Carson-533)፡፡

2. እንዴት መመላለስ እንደሚገባቸው 4-5

ጳውሎስ የተሰሎንቄ አማኞች በሶስት መንገድ ቢኖሩ እግዚአብሄርን እንደሚያስደስቱ ያሳያቸዋል (4፡1) ያም ሴሰኝነትን
በማስወገድ፤እርስ በእርስ በመዋደድ እና ጠንክረው በመስራት ነው (4፡3-12)፡፡ከዚያ የተሰሎንቄ አማኞች ያሳዘናቸውን ጉዳይ ያነሳል
ያም የአንዳንድ ወገኖች ሞት ነው፡፡ነገር ግን በጌታ የሆኑ ሙታን የታደሉ ናቸው (4፡13-18)፡፡የምሳሌነት ህይወት እንዲኖሩ
ያሳስባቸዋል 5፡1-11)፡፡መጸሐፉን ሲዘጋ ግልፅ ያለ መመሪያዎችን የጸሎት ጥያቄዎችን እና ሰላምታን በመስጠት ነው (5፡12-28-
ካርሰን-533)፡፡

2 ተሰሎንቄ

1. ፍርድ ለማያምኑ በምፅአቱ (1)


ጳውሎስ ሲላስን እና ጢሞቲዮስን አብሮ ሰራተኛ እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል (1፡1-2)፡፡የምስጋናው ክፍል (1፡3-12) ከጨረሰ በኃላ
ወዲያው በስደት ውስጥ በፅናት ሰለመቆም ይናገራል፡፡

2. የክርስቶስ ዳግም ምፅአት ምልክት (2)

93
Green, Gene L.: The Letters to the Thessalonians. Grand Rapids, Mich.; Leicester, England : W.B. Eerdmans Pub.; Apollos, 2002 (The Pillar New
Testament Commentary), S. 64
ምናልባትም ይህ ስደት የኢየሱስ አመጣጥ በተሳሳተ መንገድ እንዲረዱ አደርጓቸዋል 94 ያንን ነው ጳውሎስ ሊያስተካክላቸው ሲሞክር
የሚታየው (2፡1-12)፡፡ጳውሎስ ከዚያ በእምነታቸው ፀንተው እንዲቆሙ ሲያሳስባቸው ይታይል እና ለመበረታታት እንዲጸልዩ
ያሳስባቸዋል (2፡13-17)፡፡
3. እስከ ምፅአቱ በትጋት ማገልገል (3)
ለራሱም እንዲጸልዩለት ያሳስባቸዋል የጸሎቱም ሀሳብ በአገልግሎታቸው መታመን እንዲሆንላቸው እና ከስደት መጠበቅ እንዲችሉ
ነው (3፡1-5)፡፡ሌላው ደግሞ በ 1 ተሰሎንቄ ውስጥ ተጠቅሶ የነበረው በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ስለተነሳው ስራ ፈትነት ነው (1 ተሰ 4፡
11-12)፡፡ይህ ጉዳይ እጅግ ከፍቶ ይታያል፡፡በዚህ ላይ ጳውሎስ ሰፋ ያለ መመሪያ ሲያስተላልፍ ይታያል፡፡ከዚያ አጠር ያለ ጸሎት
በማቅረብ እና መጸሐፉ በራሱ እንደ ተጻፈ አድርጎ ይደመድማል (3:16–18-Carson-534)፡፡

ነገረ መለኮት

1 ተሰሎንቄ

ሐዋርያነት

ሐዋርያት እነማን ናቸው? ማርሻል ሚሲዮናውያን ናቸው ይለናል፡፡ሐዋርያት ሰዎች ኢየሱስን እንዲቀበሉ የሚያበረታቱ
ከእግዚአብሄር የተላኩ ናቸው፡፡95እውነተኛ ሐዋርያት በስብከት ስራ የተጠመዱ ናቸው፡፡በእርግጥ ጳውሎስ የእውነተኛ ሐዋርያት
መገለጫዎች ይነግረናል (2 ቆሮ 12፡12)፡፡ነገር ግን ንግግር ብቻ ሳይሆን ተአምራትም አንዱ የአገልግሎታቸው መገለጫ ነው (ገላ 3፡
5)፡፡በተሰሎንቄ መልዕክት ጳውሎስ ወንጌል በንግግር ብቻ አልመጣም በሀይልም ጭምር እንጂ ሲል ተአምራዊ ምልክቶችን እያለ
ሊሆን ይችላል፡፡96በወንጌል ስራ ውስጥ የመንፈስ ቅዱስን ሚና ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፤ ነገር ግን ወንጌል በቃላትም መምጣት አለበት፤
ያ ማለት ዝም ብሎ የሰው ጥበብ ማለት አይደለም (1 ቆሮ.2፡4-5)፡፡97

ወንጌል
ዋናው የወንጌል ይዘት በዚህ መልዕክት ውስጥ ግልፅ ብሎ ተቀምጧል (1 ተሰ 1:5; 2:2, 4, 8–9; 3:2)፡፡ ወንጌል ማለት መልካም
የምስራች ነው፡፡ይህም ዋናውን የክርስቲያን መልዕክት የሚያሳይ ነው፡፡ይህም በ 1 ቆሮ 15፡3-5 ላይ ተቀምጧል፡፡ይህም በኢየሱስ ሞት
እና ትንሳኤ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ሞቱ በቆሮንቶስ ላይ ለእኛ እንደሆነ ሲናገር በተሰሎንቄም ውስጥም ለእኛ እንደሆነ ይናገራል፡፡
ከእግዚአብሄር ቁጣ የዳንበት እንደሆነ ግልፅ ነው (1 ተሰ 5፡9-10)፡፡በተሰሎንቄ ሞቱ እና ትንሳኤ ለወደፊት ተስፋ እንደ መሰረት ሆኖ
አገልግሏል (1 ተሰ 4፡14፤5፡9-10) በ 1 ቆሮ ወንጌል በሞቱ እና በትንሳኤውን ያማከለ ነው፡፡ወንጌል ሞቱን እና ትንሳኤውን መሰረት
ቢያደርግም ነገር ግን ይዘቱ ምፅአቱንም ያሳያል፡፡98

በሁለተኛ ደረጃ ከጳውሎስ መልዕክት የምንረዳው ሰሚዎቹ እንዴት አደርገው ለወንጌል መልዕክት ምላሽ እንደሰጡ ነው (1 ተሰ.1፡9-
10)፡፡የሰሙት ስለ እውነተኛ አምላክ እና ስለ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው(1 ቆሮ 8፡5-6)፡፡እንዲሁም ከሞት ስለመነሳቱ (1 ቆሮ 15፡3-5)
አዳኙ ከሚመጣው ቁጣ እንደሚያድን (ሮሜ 5፡9)፡፡ክርስቶስ እንደሞተ እና ከሞት እንደተነሳ ይህም ደግሞ የድነታችን ምንጭ
እንደሆነ መረዳት ይገባል (1 ተሰ.5፡9) የሞተው ለአማኞች ሲሆን ያም በመጨረሻ ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ ነው (1 ተሰ.5፡10)፡፡ከዚህ
የምንረዳው ለተሰሎንቄ አማኞች የተሰበከው ወንጌል በሁሉም የጳውሎስ ጽሁፎች ውስጥ ከተጠቀሰው ጋር አንድ እንደሆነ ልብ
ማለት ይቻላል፡፡99

መለወጥ
ለወንጌል የተሰጠው ምላሽ ወደ እግዚአብሄር ዘወር ማለት ተብሎ ቀርቧል፡፡ይህ ሀሳብ ጣኦትን ያመልኩ ለነበሩ አህዛብ የተነገረ
አገላለፅ ነው፡፡ነገር ግን ትክክለኛው ቃል እምነት የሚባለው ነው፡፡እምነት ማለት ልጁ ኢየሱስን እና እግዚአብሄርን መታመን መሰጠት
እና መታዘዝ ነው፡፡ይህ እንግዲህ ክርስቲያኖች ከእግዚብሄር ጋር ላላቸው ግንኙነት ወሳኝ የልዩነት ነጥብ ነው፡፡ይህ በብለይ ኪዳን የነበረ
ሲሆን በሌሎች ሃይማኖቶች የማይታወቅ ጉዳይ አልነበረም፡፡ለዚህ ነው አማኞች የሚለው አገላለፅ ለተከታዮቹ ውሎ
የምንመለከተው፡፡100
94
ይህ ምልክትን እንዲናገር ያደርገዋል በዚህም አንድ የጥፋት ልጅ የአመፅ ሰው መምጣቱ ሲሆን ሌላው ደግሞ እሰከዚያ ድረስ የሚከለክል መኖሩ ነው፡፡ይህን
በሁለተኛው ተሰሎንቄ ነገረ መለኮት ውስጥ ማየት ይቻላል፡፡
95
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel, 239.
96
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel, 239.
97
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel, 239.
98
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel, 240.
99
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel, 240.
100
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel,240.
መለወጥ (conversion) በሰው ቀንቋ ሲገለፅ ነው፡፡ሐዋርያው እግዚአብሄር ለአማኞች ምን እንዳደረገ ይነግራቸዋል በዚህ ጉዳይ
እምነት እንዲኖራቸው ያደፋፍራቸዋል፡፡ሰዎች ለዚህ መልዕክት ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ይህንን ምላሽ ሲሰጡ በእምት ነው፡፡ያ እንግዲህ
ከእግዚአብሄር ጋር ለሚኖራቸው ግንኙነት እንደ መነሻ ነጥብ ሆኖ ይገለጻል፡፡ታዲያ እንደ እግዚአብሄር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል
አልተቀበላችሁም ሲል ይህንን እውነታ ይለውጠዋል ማለት አይደለም፡፡መልዕክቱ ሲተላለፍ የመንፈስ እርዳታ ይኖረዋል እንዲሁም
መልዕክቱን ሲቀበሉ በደስታ እንዲሆን በተቀባዮቹ ውስጥ እንዲሰራ ያደርገዋል፡፡መመረጥ የሚለው መታየት ያለበት ወንጌል መጣ
እንርሱ ተቀበሉት ከሚል አቅጣጫ ብቻ ነው፡፡101

ከሰሚዎቹ (ከመጀመሪያ አንባቢዎቹ) ጀርባ የእግዚአብሄር አንቀሳቃሽነት አለ ይህም ሲጠራችሁ የሚል ቃል አለበት (1 ተሰ. 2፡12፤ 4፡
7፤ 5፡24)፡፡ጳውሎስ ምርጫ የሚል ቃል ይጠቀማል (1 ተሰ. 1፡4) ያም አንባቢዎቹ የእግዚአብሄር ቤተሰብ (ወገን መሆናቸውን
ለማመልከት ነው) ናቸው የሚለውን ለማብራራት ነው፡፡ምርጫን ለድነት ነው የሚል የተለመደ አባባል አለ ነገር ግን ይህ ቃል የዋለው
ቀድሞም የእግዚአብሄር ህዝብ አካል ለሆኑ ሰዎች ነው፡፡ይህ ማለት በንጽጽር የተቀመጠ ሀሳብ አይለም፡፡ወንጌል ሲሰበካቸው
መቀበላቸው እንደ ተመረጡ ተደርገው ተቆጥረዋል እንጂ ቀድሞ ስለተወሰኑ ተደርገው አይመስልም፡፡ 102
ታማኝነት
ጳውሎስ የሰይጣንን ክፉ ስራ እንደሚያውቅ ግልፅ ያደርግልናል (1 ተሰ 3፡5) ያም ሁኔታዎችን ክፉ ሀሳቡን ለመፈጸም
እንደሚያውለው ግልፅ እንደሚያውቅ ግልፅ ያደርግልናል (1 ተሰ 2፡18)፡፡ሰይጣን አሁንም ሰዎችን ለመፈተን ነጻ እንደሆነ ይናገራል ግን
ለምን እግዚአብሄር ሰይጣንን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አያጠፋውም ለሚለው ጥያቄ ምላሽ አይሰጠም (1 ተሰ 2፡18)፡፡ግን
በእግዚአብሄር ሀይል ተደፍጥጦ ያለ ሀይል ነው፡፡አንድ ቀን ሰይጣንን እግዚአብሄር እንደሚያጠፋው እና ያንንም ሙሉ ለሙሉ አንድ
ቀን እንደሚያደርገው ይናገራል፡፡103
ያለው ግር የሚል እውነታ የቅዱሳን እስከ መጨረሻ መጽናት የሚወሰነው በእግዚአብሄር ነው ወይስ በራሳቸው የሚለው ጉዳይ ነው፡፡
ያም በጌታ ፅኑ የሚለውን ሀሳብ ስናይ ነው (1 ተሰ 3፡8)፡፡ይህ ሀረግ የሚያመለክተው የእነርሱ ፅናት የሚመጣው ከሰውኛ አቅጣጫ
ብቻ አይደለም፡፡የራሳቸው መታመን ወይም በጌታ ላይ ያላቸው መደገፍ ወሳኝ ሲሆን ጌታ እስከ መጨረሻ ሊያቆማቸው የሚችል
ጉዳይ ነው፡፡104

በጌታ (“in the Lord”) የሚለው አገላለፅ በመልዕክቱ ውስጥ ብዙ ጊዜ ተንፀባርቋል (1 ተሰ 1፡1 2 ተሰ 1፡1 ቈላ 3፡3)፡፡በእርሱ (“in
him”) ከሚለው አገላለፅ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ከዚህ ገለጻ የምንረዳው ልክ እንደ ተውሳከ ግስ አይነት ሲሆን ያም ግሱን ለመግለፅ
(ለመርዳት) እንደገባ ነው፡፡ያም የአማኞች ህይወት በሞተው እና ከሙታን በተነሳው ጌታ የሚወሰን እንደሆነ እና ከዚህ ጌታ ጋር
ያላቸውን ግንኙነት የሚያትት ነው (1 ተሰ 4፡1፤ 5፡12፣18)፡፡በቅፅል መልክም የገባበት ሁኔታ አለ፡፡ይህም የሆነ መንፈሳዊ ትስስር
በክርስቶስ እና በአንባቢዎቹ መካከል ያለ ይመስላል፡፡ይህም የአማኞች ፅኑ አቋም (መታመን የሚወስን) ነው፡፡ግን ዋናው ቁም ነገር
የእግዚአብሄር ታማኝነት ነው (1 ተሰ 5፡24 2 ተሰ 3፡3)፡፡105

ቅድስና
ቅድስና ሌላኛው በዚህ መልዕክት ውስጥ የምናገኘው ጭብጥ ነው (1 ተሰ 4፡1)፡፡ይህ ቃል የሚያመለክተው ቅዱሳን የእግዚአብሄር
ልጆች ሲሆኑ የሚያገኙትን ባህሪ ሲሆን ያም ባህሪ በእምነታቸው ሲያድጉ እና እየጎለመሱ ሲመጡ የሚገለጥ ህይወት ነው (1 ተሰ 4፡
1-12)፡፡የወታደር ዩኒፎርም ያደረገ ሁሉ ወታደር ሊሆን ይችላል አንዳንዶች ግን አዲስ ምልምል ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ እጅግ የሰለጠኑ
ናቸው ከላይ ሲታዩ በዩኒፎርም ወታደር መምሰል ብቻ ሳይሆን በሂደት ወደተፈለገው ብቃት ማደግ አለባቸው፡፡የቅድስና መጎልበት
የሚያመለክተው እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን ለአንባቢዎቹ መለገሱን ነው፡፡106
ቅድስና የሚለው ሀሳብ ከጳውሎስ መጸሐፍት ሁሉ በ 1 ተሰሎንቄ ውስጥ አብይ ጉዳይ ሆኖ ይታያል (1 ተሰ 3፡13፤ 4፡3-4፤7፤ 5፡23
2 ተሰ 2፡13)፡፡በጌታ ቀን ያለ ነውር ከመሆን ጋር ተያይዞ ቀርቧል (1 ተሰ 3፡13፤ 5፡23)፡፡ከወሲባዊ ንፅህና ጋር ተያይዞ ቀርቧል ያም ቅጥ
ከአጣ ሴሰኝነት ንፁህ መሆን እና ለጋብቻ ታማኝ ከመሆን ጋር ተያይዞ ቀርቧል (1 ተሰ 4፡3-8)፡፡107

የቅድስና መልክ ተደርገው ሊወሰዱ ከሚችሉት መለያዎች መካከል እምነት ፍቅር እና ተስፋ ናቸው (1 ተሰ 1፡3 5፡8)፡፡ይህም አማኝ
ከእግዚአብሄር ጋር ከአማኞች ጋር እና ከወደፊቱ ጋር ያለው ነገር የተሳሰረ መሆኑን አመልካች ነው፡፡ በጥልቀት ለመናገር ያክል 1 ተሰ
1-3 ስለ እምነት የሚያወራ ነው፡፡1 ተሰ 4፡1-12 ስለ ፍቅር ግንኙነት የሚያወሳ ሲሆን 1 ተሰ 4፡13-5፡11 ደግሞ ስለ ተስፋ የሚናገር
ነው፡፡

101
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 241
102
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 242
103
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 242
104
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 242
105
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 242
106
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 243
107
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 243
እምነት ማለት የእግዚአብሄርን ህላዌ እውነተኝነት መቀበል እና ራሱን ሙሉ ለሙሉ ለዚያ እውነት መስጠት ሲሆን ያም የመለወጥ
(conversion) ማህተም ነው (1 ተሰ 1፡8)፡፡የእምነት ሌላው ገፅታ ደግሞ ቀጣይ መሆኑ ሲሆን ያም በቀጣይነት የጌታ የኢየሱስ
መሞት እና መነሳትን መታመን (1 ተሰ 4፡14) ሲሆን አማኝ የሚለው ቃል ለክርስቲያኖች ተገቢ የሆነ ቃል ነው (1 ተሰ 1፡7፤ 2፡
10፤13)፡፡የእምነታቸው ቀጣይነት የጳውሎስ ትልቅ ትኩረት ሆኖ ይታያል (1 ተሰ 3፡2፤5፤ 6-7)፡፡ አስቀድሞ ለማየት እንደተሞከረው
እምነት ከፍቅር ጋር ተያያዥነት አለው (1 ተሰ 3፡6፤ 5፡8)፡፡ፍቅር ግን በራሱ የሚቆም አንዱ የክርስቲያኖች ባህሪ ነው (1 ተሰ 4፡9-
10)፡፡የእግዚአብሄርም ባህሪ ሊታመን የሚችል መሆኖ ተጠቅሷል (1 ተሰ 5፡24)፡፡108

ትንሳኤ እና ምፅአት
ከሁሉም የጳውሎስ መልዕክቶች 1 ኛ እና 2 ኛ ተሰሎንቄ ስለ ወደፊቱ አብይ ቦታ ሰጥተው የሚናገሩ መጸሐፍት ናቸው፡፡መለወጥ
አማኞች አሁን እግዚብሄርን ያገለግላሉ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ከሰማይ የሚገለጠውን ልጁን ይጠባበቃሉ ማለትንም ያካትታል (1 ተሰ
1፡9-10)፡፡ጌታ ሲመጣ የሰሩት ሚሲዮናዊ ስራ ያስመሰግናቸዋል (1 ተሰ 2፡19-20)፡፡ሲመጣ ቅዱሳን እና ያለነውር እንዲሆን ይጠበቃል
(1 ተሰ 3፡13፤ 5፡23)፡፡ጳውሎስ ሰፋ ያለ ክፍል ሰጥቶ ይህን ጭብጥ ያትታል (1 ተሰ 4፡13-5፡11)፡፡ቀኑ የደስታ የሽልማት ሲሆን
በተመሳሳይ መንገድ ጥፋት እና ፍርድ ነው፡፡109

ሁለት ቁም ነገሮች የጳውሎስን ውይይት ይዞታል፡፡የመጀመሪያው ጌታ ሳይመጣ በፊት የሞቱት ቅዱሳን ጌታ ሲመጣ ስለማይኖሩ
በምጻቱ አይካፈሉም የሚል ሀሳብ ቅዱሳን ይዘው ነበር፡፡ለዚህ ጳውሎስ የሰጠው መልስ እንደሁም በህይወት ያሉ ቅዱሳን የሚመጡት
ሁለተኛ ነው፡፡ምክንያቱም መጀመሪያ የሚነሱት በጌታ የሞቱት ሙታን ናቸው ከዚያ በኀብረት አንድ ላይ ጌታን ይቀበላሉ፡፡ሁሉ ነገር
የሚታይ ነው የሚመስለው ያም ንጥቀት 110 እርሱን መገናኘት የሚለው ግልፅ ነው፡፡ ሁለተኛው የጳውሎስ ሀሳብ የጌዜ ጉዳይ እና
ለዚያ የሚደረግ ዝግጅትን የሚያካትት ነው፡፡ምጻአት ድንገተ የሚሆን ነው፡፡ስለዚህ መንፈሳዊ ዝግጅት አስፈላጊ እንደሆነ ነው፡፡111

ሁለተኛ ተሰሎንቄ ነገረ መለኮት

የአመፅ ሰው (The Man of Lawlessness)


በተሃድሶ ዘመን የቤተ ክርስቲያን አዳሽ ይህ ሰው የካቶሊክ ጳጳስ ነው የሚል መረዳት ነበረቸው፡፡አሁን ግን ይህ
እንብዛም የታየዘ ጉዳይ አይለም፡፡ሌሎች ጳውሎስ የሮም ነገስታትን (በተለይም ካሊጎላን እና ኔሮን) ማለቱ ነው
ብለው ያስቡ ነበር፡፡እርግጥ ነው ነገስታቱ ቤተ ክርስቲያንን ይቃወሙ ነበር ራሳቸውን አምላክ አድርገው
ይቆጥሩ ነበር፡፡
ካሊጉላ የራሱን ምስል በኢየሩሳሌም መቅደስ ውስጥ የማስቀመጥ ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው፡፡ይህ ከማድረግ ግን
ሞት ከልክሎታል (41 ዓ.ም ማቴ 24፡15፤ ዳን 9፡27 11፡31፤ 12፡11)፡፡በየትኛውም መስፈርት ግን ምስሉን
ማስቀመጥ እና ራሱ መቀመጥ አንድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡በተጨማሪ ጳውሎስ የተናገረው በምፃት ሊመጣ ስላለ
ሰው (eschatological figure) እንጂ በወቅቱ ስለነበረ ሰው እየተናገረ አይደለም፡፡

የሚሰራው ወይም የሚናገረው ለመፍታት አሁንም ቢሆን አከራካሪ ነው፡፡ለምሳሌ ራሱን ያልቃል፤አምላክ ብሎ
ከተጠራው ሁሉ በላይ ራሱን ይጠራል የሚለው እንደተጠበቀ ሆኖ በቤተ መቅደስ ውስጥ እስኪቀመጥ ድረስ
የሚለው ሐረግ አከራካሪ ነው፡፡አንዳዶች አሁንም ድረስ የእስራኤል ቤተ መቅደስ ይሰራል ይህም ሰው ራሱን
እዚያ ያኖራል ብለው ይናገራሉ፡፡ስቶት ይህን ሲሞግት በመቅደስ (2፡4) መቀመጥ የሚለውን የዕብሪት እና
የእግዚአብሄርን ስም ማወረድ ምልክት (a symbol of arrogance and even blasphemy) ብለን ምናልባት
በትክክል ከፈታነው የጳውሎስ ሀሳብ ልዑል አቀፍ፤አመፀኛ (global rather than local) ፤የክርስቶስ ተቃዋሚ
እና በዘመናችን ያለ ሰው ከማለት ይልቅ በመጨረሻ ዘመን የሚገለጥ (eschatological than a contemporary
figure) በማለት ሊሞግት ጥረት ያደርጋል፡፡112

108
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.243.
109
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.244.
110
ይህ የምፃት ጉዳይ እጅግ አከራካሪ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ሰዎች ከዚህ ጋር በሚመለከት ሁለት አይነት ትልልቅ ምልከታ ይዘዋል ያም ይመጣል እንኖራለን (አልቦ
ሚሊኒየም) ሎሎች ደግሞ ሚሊኒየም በመባል ይታወቃሉ፡፡ሁለትኞቹ በሶስት ከፍለው ያዮቸዋል በአጭሩ ከመከራ በፊት በመከራ ውስጥ እና ከመከራ በኃላ ሚሊኒየም
ወይም ሺህ አመት ይጀመራል በማለት ነው፡፡
111
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel.245.
ሌሎች ደግሞ በስጋ የተገለጠ ሰይጣን እንደሆነ ወይም ደግሞ ሀሰተኛው መሲህ እንደሆነ አድርገው ይረዱታል፡፡
ይህ ሁሉ ቢሆንም እርግጡን ለመናገር አያስችልም፡፡የምናውቀው ነገር ምንም አይሁን ምን ክፋት ሰው ሆኖ
(embodiment of evil) በመጨረሻ ዘመን ሊገለጥ እንዳለ ግልፅ ነው፡፡
አጋጅ ሀይል (ከልካይ)

ይህን ከልካይ ሀይል የተሰሎንቄ አማኞች እንደሚያውቁት ጳውሎስ ይናገራል፡፡እና በገዛ ራሱ ጊዜ ሊገለጥ
እንዳለው ያስረግጥላቸዋል (2 ተሰ 2፡6)፡፡ችገር የሚያደርገው የሚያግድ (6) የሚለው ቃል የተቀመጠው በግዑዝ
ፆታ መሆኑ ነው፡፡በቁጥር 7 ግን በበወንዴ ጾታ ተቀምጧል፡፡ታዲያ በግዑዝ ሲቀመጥ ሮማን ነው ሲባል ወይም
መወንዴ ሲቀመጥ ደግሞ የሮም ነገስታት ናቸው በሚል ለመከራከር ጥረት ተደርጓል፡፡ለምሳሌ ኔሮ እንደ አመጽ
ሰው ታይቷል፡፡ሊባል የተፈለገው አንዱ ሳይወገድ (አንድ ከልካይ ንጉስ) ሌላኛው (የአመጽ ሰው የሆነው ንጉስ)
ሊመጣ አይችልም የሚል ነው፡፡ጳውሎስ ይህን ሊል ነው፡፡ይህ ግን እንዳልሆነ የምናውቀው ሮም ሆኑ ንጉሶቿ
ለዘለዓለም ስለተወገዱ እና ክርስቶስም (የመጨረሻ ዘመንም) ስላልመጣ ያ ሊሆን አይችልም፡፡

ጳውሎስ ራሱ አጋጅ ሀይል ነው በማለት ሰዎች ለመናገር ይሞክራሉ፡፡አንዳንዶች መለአክ ነው ያም አሁን


በስልጣን ላይ ያለ ነው ብሎ ይናገራል፡፡ይህም ሆኖ ጳውሎስ መለአክ ነው የሚለውን መቀበል ይከብደዋል፡፡እነ
ቢቢ ዋትፊልድ በመቅደስ የሚቀመጠውን የአመፅ ልጅ የሚለውን ሀሳብ ኢየሱስ የክፋት እርኩሰት (ማቴ 24፡15)
ጋይ አያይዞ ለመናገር ጥረት አድርጓል፡፡እናም የጥፋት ልጅ ሮም ከልካዩ ያዕቆብ ነው ማቱ ትንሽ ጉዳዩን
አደናጋሪ አድርጎታል፡፡

አንዳንዶች ደግሞ ቤተ ክርስቲያን እና መንፈስ ቅዱስ አጋጅ የተባሉት ብለው ይናገራሉ፡፡ያም ሆኖ ምንም
አይነት ማረጋገጫ የለንም (ቢያንስ በሌሎች መጸሐፍ ቅዱስ ክፍሎች)፡፡ደግሞም መንፈስ ቅዱስ ለምን
ይወሰዳል ለሚለው ጥያቄ ምላሽ ላይሆን ይችላል፡፡

እንደ ሊዮ ሞሪስ ከሆነ ክፉ (የክፋት አሰራር ሁሉ ሲሆን -principle of order) በወንዱ ጾታ የተቀመጠው ደግሞ
የዚያ ክፋት በሰው አምሳል (personification) መገለጥ ሊሆን ይችላል፡፡በሮማ ከየነው ይላል ሊዮ ሞሪስ ሮም
የክፋት አሰራር ስትሆን መገለጫዎቿ ደግሞ ነገስታቶቿ ናቸው፡፡በሌሎች ህግጋቶችም ተመሳሳይ ሊሆን
ይችላል፡፡የአመጽ ልጅ ስራ የሚጀምረው ህግ መስራት ሲየቆም ነው በማለት ለመሞገት ጥረት ያደርጋል፡፡ይህም
መጨረሻ እየባሰ እንደሚሄድ እና መጨረሻውም እንደሚመጣ ለማየት ጥረት ያደርጋል፡፡ 113

ክፍል አራት-የእስር ቤት መልዕክቶች


ኤፌሶን
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
ጳውሎስ ፅፎታል የሚሉ ከሚያነሷቸው ሀሳቦች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡አንደኛ መጸሐፉ በጳውሎስ ተፅፌያለሁ ይላል
(1፡1 እና 3፡1)፡፡እንዲሁም እስረኛ እንደሆነ ይናገራል (3፡1፤ 4፡1)፡፡ሁለተኛ ከፍተኛ ዝውውር ያደርግ የነበረ መጸሐፍ ነው፡፡ሌላው
በአብዛኛው ብዙ አባቶች ይደግፉታል፡፡ሶስተኛ የጳውሎስ አወቃቀር፤የጳውሎስ ቋንቋዎች በግልፅ ተንጸባርቀውበታል ብለው ይላሉ
(ካርሰን 481)፡፡አራተኛ ከቈላሲስ አንጻር ካየነው ሁለት መጸሐፎችን (ቈላሲስ እና ኤፌሶን) በአንድ ሰው ባይጻፉ ኖሮ በዚህ አይነት
ተመሳስሎ ሊጻፍ አይችልም ብለው ይላሉ (ኤፌ 6፡21-22 እና ቈላሲስ 4፡7-8)፡፡

ልዩነትም አለው ለምሳሌ በኤፌሶን ምስጢር የአይሁድ እና የአህዛብ አንድነት ሲሆን (ኤፌ 3፡3-6) በቈላሲስ ደግሞ ክርስቶስ ራሱ
ምስጢር ነው፡፡ሁለት አህምሮ አንድን ስራ አስተሳስሮም ለየብቻም እንዲቆሙ አድርጎ መጻፍ አይቻልም በማለት ከአንድ ሰው ያም
ከጳውሎስ የወጣ ነው የሚል ሀሳብ አቅርበዋል፡፡የቈላሲስ ግልባጭም አይደለም፡፡በዚያ ዘመን በሰው ስም መጻፍ ያን ያክል የተለመደ
ጉዳይ አልነበርም፡፡በመጨረሻ ጳውሎስ እስረኛ ነበር (3፡1፤ 4፡1) ይህን ፅሁፍ ሲፅፍ፡፡በእርሱ ስም እንዲህ አይነት ፅሁፍ ሊፅፍ የሚችል
ማንም የለም (482)፡፡
112
Stott, John R. W.: The Message of Thessalonians : The Gospel & the End of Time. Leicester, England; Downers Grove, Ill., U.S.A. : Inter-Varsity
Press, 1994 (The Bible Speaks Today), S. 164
113
Morris Leon “Man of Lawlesness Restraning power” in Dictionary of Paul and His Letters. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 1993, S.
593
ጳውሎስ አልጻፈውም የሚል ከሚቀርበው ሀሳብ-አንደኛ ከጳውሎስ ነገረ መለኮት አንጻር ያዩታል፡፡ለምሳሌ በኤፌሶን ላይ የቤተ
ክርስቲያን መሰረት ሐዋርያት እና ነቢያት ሲሆኑ (2፡20) በሌሎች ደግሞ መሰረቱ ክርስቶስ ራሱ ነው (1 ቆሮ 3፡11)፡፡ቤተ ክርስቲያን
አለም አቀፋዊት ስትሆን በሌሎች መልዕክቶች ሀገራዊ (local) ነች፡፡ኤፌሶን ጋብቻን በክርስቶስ እና በቤተ ክርስቲያን መካከል ላለ
ግንኙነት እንደ ምሳሌ ሲወስድ (5፡23-33) የቆሮንቶሱ ጳውሎስ ግን ይህን ሊያደርግ አይችልም (ካርሰን-484)፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
ጳውሎስ መጸሐፉን ሲፅፍ በእስር ቤት እንደነበረ ግልፅ ነው (3፡1፤ 4፡1)፡፡ይህ በአመዛኙ በሮም በዕድሜው ወደ መጨረሻ ያለውን
የእስር ጊዜ የሚያመለክት አድርገው ብዙ ሰዎች ይወስዱታል፡፡ይህ ከሆነ ወደ 60 ዓ.ም ግድም ተፅፎ ሊሆን ይችላል፡፡

ሐ. ዓላማ
የኤፌሶን መልዕክት እንዲጻፍ የሆነበት የተለየ ክስተት በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ መለየት አይቻልም፡፡ይህም ሆኖ አንዳንዶች በአይሁድ
እና አህዛብ መካክለ የተከሰተ ውጥረት ለፅሁፉ መነሻ ነው ሲሉ ሌለች አህዛብ ያላቸውን ቦታ ለማሳየት ነው በማለት ይናገራሉ፡፡
ካርሰን የኤፌሶን መልእክት ተቀባዮች አህዛብ ሊሆን ናቸው እና የጳውሎስም ጭብጥ አንድነት እንዲኖር ጥሪ ያቀርባል እና ስነ
ምግባርን መጠበቅ አስፈላጊ ስለመሆኑ ይናገራል፡፡ሰማይ ከክርስቶስ ጋር ያደረውን ዕርቅ ትኩረት ሰጥቶ ይናገራል (ካርሰን 492)፡፡

ጭብጥ

1. አማኞች ማናቸው 1-3


ሰላምታ ካቀረበ በኃላ (1፡1-2) እግዚአብሄር በከርስቶስ ስላደረገው የመዋጀት ስራ ያብራራል (1፡3-14) ሁሉ የሆነው በእግዚአብሄር ፀጋ
እንደሆነ ይናገራል፡፡አብ በመንፈሳዊ በረከት ባረከን ያም መመረጥ ሲሆን ምርጫውም ዓለም ሳይፈጠር በፍቅር የተደረገ ነው (1፡3-5)
፡፡በመንፈስ ታትመናል፡፡ጳውሎስ ምስጋና እና ፀሎት ለአማኞች ያቀርባል (1፡15-23-ካርሰን 479)፡፡
ምዕራፍ 2 ኀጢያተኝነታቸውን ያሳስባቸዋል114 እና እንዲሁም ድነት በጸጋ መሆኑን ለጥቆም መልካም ስራ እንዲያደርጉ ያሳስባቸዋል
(2፡1-10) ከዚያም እንዴት እግዚአብሄር አይሁድም ሆነ አህዛብም ያልሆነ በክርስቶስ ሰለም በማምጣት አንድን እዝብ እንደፈጠረ
ግልፅ ያደርጋል (2፡11-22)፡፡

ጳውሎስ የአህዛብ ወደ አካሉ መግባትን በገለፀበት ሀተታ አህዛብ የገቡት ወደ ጥንቱ የእግዚአብሄር ህዝብ ወደ ሆኑት እስራኤላውያን
ሲሆን ያም ሁለቱ አንደ አንድ ህዝብ እንዲቆጠሩ አድርጓቸዋል (3፡1፡-6)፡፡ያም እግዚአብሄር በክርስቶስ አስቀድሞ ያደረገው ነው (3፡7-
13)፡፡ይህም ወደ ጸሎት ሲመራው እና ክርስቶስ በልባቸው እንደሚኖር እና ወሰን የሌለውን ፍቅር ሲያስታውሳቸው ማየት ይቻላል
(3፡14-21-ካርሰን 479)፡፡

2. ለወንጌል እንደሚገባ መኖር 4-6


የመንፈስን አንድነት ስለ መጠበቅ ትኩረት ተሰጥቶታል (4፡1-6)፤ ያም ከእግዚአብሄር ዘንድ የቤተ ክርስቲያን ከተሰጥ ስጦታ
የሚመነጭ መሆኑን ይነግራቸዋል፡፡ይህም ስጦታ ደግሞ ሊያሳድጋቸው የሚችል እንደሆነ ተነግሯል (4፡7-16)፡፡ሐዋርያት በዚህ ዘመን
አሉ ወይም የሉም ለሚለው ስቶት የሉም የሚል መልስ ሰጥቷል፡፡115 እርግጥ ነው ይህ ጥቅስ በየዘመናቱ ስለሚነሱት የሚናገር ነው?116

እንደ ብርሃን ልጆች እንዲመላለሱ አሳስቧቸዋል (4፡17-5፡21) ይህ የተሰጣቸው መመሪያ (እንደ ብርሃን ልጆች እንዲኖሩ) ከነገረ
መለኮታዊ እውነት አንጻር ለማሳየት ተሞክሯል፡፡ይህም የእግዚአብሄርን ምሳሌነት እንዲከተሉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል (5፡1) እንዲሁም

114
አንዳንዶች ሙታን ነበርን የሚለውን ሀሳብ ዘይቢያዊ ንግግር ነው ይህም ጠፍቶ እንደነበረው ልጅ እና ሲመለስ አባቱ ይህ ልጄ ሞቶ ነበር የሚለወን በማንሳት
ለመሞገት ጥረት ያደርጋሉ፡፡ሌሎች እንደ ጆን ስቶት አይነቶቹ ትክክለና የነበርንበት ሁኔታ ነው ብሎው ይከራከራሉ ((see-Stott, John R. W.: God's New Society :
The Message of Ephesians. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 1979, 1980, S. 71)

115
ሐዋርያ የሚለው ሦስት ትርጉም ያለው ሀሳብ ነው፡፡ያም ዮሐ 13፡16 ለሁሉም-ለሆነ ስራ ከቤተ ክርስቲያን የተላኩ-2 ቆሮ 8፡23 ፊሊ 2፡25-እና 12 ናቸው፡፡በዚህ
ስፍራ ሐዋርያት ሲል ሦስትኞችን ማለቱ ነው ያም አስቀድሞ ሐዋርያትን በማለት (First)1 ቆሮ 12፡28 በማለት ስቶት ይከራከራል (Stott, John R. W.: God's
New Society : The Message of Ephesians. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 1979, 1980, S. 160)፡፡
116
ጆን ስቶት ለዚህ ጥያቄ ምላሽ ይሰጣል፡፡ይህም ልክ እንደ ጴጥሮስ ጳውሎስ ያሉ የሉም ግን ነገሩን ክፍት ሲያደርገው ሐዋርያዊ አገልግሎት ግን አለ ይላል እነዚያም
ፈር ቀዳጅ ሚሲዮናዊ ስራ የሰሩ፤ቤተ ክርስቲያን የተከሉ ከስፍራ ስፍራ የሚዞሩ የሚያገለግሉ ወይም የሚመሩ በማለት ስቶት ሀሳቡን ይከራከራል፡፡
የክርስቶስን ፍቅር እንዲከተሉ ምሳሌነት ተሰጥቷቸዋል (5፡2) በጋብቻ ውስጥም የክርስቶስ እና የቤተ ክርስቲያን ትስስር እንደ
ምሳሌነት ተጠቅሷል (ካርሰን 479)፡፡ለልጆች ወላጆች ግንኙነት (6፡1-4) ለባሮች እና ጌቶችን (6፡5-9) በተመለከት መመሪያ ሰጥቷል

በመጨረሻ የእግዚአብሄርን ዕቃ ጦር እንዲለብሱ ያሳስባቸዋል (6፡10-18) የጸሎትን ሀይል እንዲጠቀሙ መመሪያ ይሰጣቸዋል (6፡19-
20)፡፡በመጨረሻ ሰላምታ ደብዳቤውን ይዘጋል (6፡21-24 ካርሰን 479)፡፡
ነገረ መለኮት
ቀድሞ መወሰን

አስቀድመን በሮሜ መጸሐፍለ ላይ ለማየት ጥረት እንዳደረግነው ሁለት የማይታረቁ የሚመስሉ ሀሳቦች በብዙ
መጸሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት እንደሚንጸባረቁ ግልፅ ነው፡፡ለምሳሌ ጆን ስቶት ስለዚህ ዶግማ (doctrine) ሲናገር
በግል እንደተመረጥን ያም እንጠፋለን ብለን መስጋት እንደሌለብን ለማስረገጥ ይሞክራል፡፡ 117ይህን ሀሳብ
ሲያብራራው ስለመመረጥ የሚናገረው አስተምህሮ ማወቃችን ለቅድስና እንደ ተጨማሪ መነሳሻ ምክንያት
ይሆነናል ( he doctrine of election is an incentive to holiness, not an excuse for sin) እንጂ ለኀጢያት
እንደ ማመካኛ ልንጠቀምበት አይገባም በማለት ይናገራል፡፡118 ሲሄ አርኖልድ (ቀጥታ የዚህ ሰው ነገረ መለኮት
ምን እንደሆነ ግልፅ ባይሆንም) እግዚአብሄር የመረጠው ህዝብ ነው ያንንም ህዝብ ከእስራት ነጻ አወጣቸው
ይቅር አላቸው በማለት ይናገራል፡፡119

Stott, John R. W.: God's New Society : The Message of Ephesians. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 1979,
1980, S. 38

ጸሎት እና አምልኮ

ምንም እንኳን የራሱን ጸሎት ጰውሎስ የዘረዘረ ቢሆንም ይህ የሚያመለክተው የጸሎትን በቅዱሳን ውስጥ ያለውን አስፈላጊነት
ነው፡፡ጳውሎስ ብዙ ቦታ እንዲጸልዩለት ሲማጠናቸው እንመለከታለን፡፡ 120 (ጸሎት የሚያስፈልገን ለምን ይሆን?)፡፡

አይሁድ እና አህዛብ

አብይ የያዘው ጉዳይ አይሁድ እና አህዛብ በኢየሱስ ሞት አንድ ህዝብ አንድም መቅደስ እንደሆኑ እና ያም እግዚአብሄር የሚኖርበት
እንደሆነ ይነግራቸዋል፡፡121ይህም ዕውን የሆነው ለሐዋርያቱ እና ለነቢያቱ በተገለጠው መሰረት ሲሆን ይህን መልዕክት ጳውሎስ
ለአህዛብ እንዲያዳርስ እንደተላከ ያብራራል፡፡122 በኤፌሶን መልዕክት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ሀሳብ ዩኒቨርሳል እንጂ አንዲትን
አጥቢያ የሚያመላክት አይደለም፡፡123አጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ፍቅር ነጸብራቅ ነች (ኤፌ 5፡25፤ 29)፡፡አካሉም
እንደሆነች ተቀጥራለች (ኤፌ 1፡22፤ 5፡23)፡፡ስለዚህ ዩኒቨርሳል ማንነት (cosmic entity) ተገልጻለች፡፡ስለዚህ ከቤተ ክርስቲያን ጋር
በተያያዘ ይህ ደብዳቤ ጉዳዩን አንድ ደረጃ ወደፊት ከፍ አድርጎታል፡፡124

አንዳንድ ሊቃውንት ይህን ዩኒቨርሳል ማንነት (cosmic entity) የሚለውን በየዘመናቱ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ነው ብለው
ይናገራሉ፡፡125

117
Stott, John R. W.: God's New Society : The Message of Ephesians. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 1979, 1980, S. 38
118
Stott, John R. W.: God's New Society : The Message of Ephesians. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 1979, 1980, S. 38
119
CA Arnold,”Ephesian letter to” in Dictionary of Paul and His letters, 200.
120
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 390
121
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 390
122
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 390
123
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 391
124
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 392
125
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 392
ሀይላት ስልጣናት እና የክርስቶስ ጌትነት

ሌላው ጭብጥ ሀይላት ስልጣናት ሲሆኑ እነዚህ ማንነቶች ዓለምን እንደቆጣጠሩ እና አማኙን እንደሚዋጉ ተደርጎ ተጠቅሷል፡ምንም
እንኳን እንደተማረኩ (ተጥቅ እንደፈቱ) እና እንደተሸነፉ ተደርጎ የተጠቀሰ ቢሆንም (ቈላሲስ 2፡15) ይህ ጉዳይ በኤፌሶችን
አልተጠቀሰም፡፡ነገር ግን የክርስቶስ የበላይነት ብቻ ተንፀባርቋል፡፡ነገር ግን እነዚህ ሀይላት በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ (active)
እንደሆኑ ተጠቅሷል እና አማኞች ሊቃወሙት የሚገባ ነው፡፡126

መንፈስ ቅዱስ

አብዝቶ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን እያንዳንዱ አማኞችን እንደሞላ በሚናገር ሰንድ ውስጥ ለመንፈስ ቅዱስ ቦታ ያለ አይመስልም፡፡
ነገር ግን የመንፈስ ቅዱስ ሁኔታ ከቈላሲስ ይልቅ አብዝቶ ተጠቅሷል፡፡127ለሐዋርያቱ እና ለነቢያቱ የተሰጠው መገለጥ በመንፈስ
ቅዱስ አማካኝነት ነው (ኤፌ 3፡5)፡፡መንፈስ ቅዱስ ማህተም እንደሆነ (ኤፌ 1፡13) ቅዱሰን የሚበረቱት በመንፈስ ቅዱስ እንደሆነ
(ኤፌ 3፡16) የመንፈስ ቅዱስን ሙላት እንዲፈልጉ ተነግሯቸዋል (5፡18)፡፡መንፈስ ቅዱስ አንድነትን በማምጣት ትልቅ ስራ
እንደሚሰራ ተነግሯል (2፡18፤ 4፤3-4)፡፡ከጥበብ እና ከእውቀት ጋር ተያይዞ ተነግሯል (1፡17)፡፡በአጭሩ መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ስራ
አስፈጻሚ (divine agent) እንደሆነ ይታያል፡፡ይህም በጸሎት ሲቀርቡ (2፡18) ስጦታ ሲሰጥ እና ክፉ ሀይላትን ለመቃወም ጉልበት
እንደሆነ ተነግሯል፡፡128

መወያያ ጥያቄ
ፊሊጲስየስ
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
መጸሐፉ በጳውሎስ እንደተጻፈ ራሱ ይነግረናል፡፡ይህንን አቋም የሚሞግት ጠንከር ያለ ተቃውሞ አልገጠመም፡፡የአጻጻፍ
ዘይቤው፤እንዲሁም ክስተቱ የጳውሎስ እንደሆነ ማየት ይቻላል፡፡ይህ ሆኖ እንደ መዝሙር የሚቆጠረው ፊሊጲሲየስ 2፡5-11 ከየት
እንደመጣ ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ ነው፡፡ቃላቶቹ እንግዳ ናቸው ለምሳሌ መልክ (2፡6፤7) መቀማት (ቁጥር 6) ከፍ ከፍ አደረገው
(ቁጥር 9) የጳውሎስ አይደሉም (ካርሰን-499)፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
ይህ መጸሐፍ የተጻፈበት ጊዜን ለማወቅ ጳውሎስ መቼ ነበር የታሰረው የሚለውን መመለስ ይገባል፡፡በሮም በቁም እስር ላይ በነበረ
ጊዜ ከሆነ ጊዜው 61-62 ሊሆን ይችላል፡፡የቂሳሪያ ሲመጣ ከሆነ 59-60 ሊሆን ይችላል ከኤፌሶን ወይም ከቆሮንቶስ ከተጻፈ
ምናልባትም ቀደም ብሎ ተጽፎ ሊሆን ይችላል፡፡ስለዚህ የጊዜ ወሰን ስናስቀምጥ የተጻፈው ከ 50-60 አካባቢ ሊሆን ይችላል(ካርሰን-
499)፡፡

ሐ. ዓላማ
አንደኛ የአፍሮዲጡን ሁኔታ እንዲያውቁ ነው፡፡ይህም የአፍሮዲጡ መታመመን ሁኔታ መረጃ ለመስጠት ነው፡፡የጳውሎስን እስር
ሰምተው አንዲጠይቀው እና ገንዘብ እንዲሰጠው አፍሮዲጡን ላኩት (4፡10-18)፤ጳውሎስ ጥሩ ሁኔታ ላይ ስላለነበረ (ተጎሳቅሎስ
ስለነበር) አፍሮዲጡ ተጨማሪ ገንዘብ እንዲልኩለት ጥያቄ አቀረበ (ፊሊ 2፡25-30)፤አፍሮዲጡ ራሱ ታመመ ቤተ ክርስቲያን ይህንን
በሰማች ጊዜ ለአፍሮዲጡ ሰጋች (ፊሊ 2፡26-27፤30) መታመሙን መስማታቸውን በሰማ ጊዜ ተጨነቀ (2፡26) ይህን ደብዳቤ አስይዞ
ሊልከው ወሰነ፡፡በተጨማሪ ጢሞቲዎስ እና እሱም ራሱ ከተፈታ ሊጎበኛቸው እንደሚችል መልዕክት መላክ ፈለገ፡፡

ሁለተኛ ጳውሎስን የሚቃወሙ ሰዎች እና ሀሰት የሚያስተምሩ ሰዎች እና በአንድነት የማይኖሩ ሰዎች ነበሩ፡፡አንዳንዶች እስሩን
ለማክበድ የሚሰብኩ፡፡የሀሰት ትምህርት የሚያስተምሩ (ከገላተያ ጋር ይመሳሰል ይሆናል-ክፉ ሰራተኞች (ፊሊ 3፡2)-የመስቀሉ
ጠላቶች (3፡18)፡፡በራስ ወዳድነት የተነሳ በሁለት ሴቶች አማካኝነት መከፋፈል ተከስቷል ያንን ለማረቅ (4፡2)፡፡

ሦስተኛ ስለተደረገለት የግንዘብ ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ፡፡ይህም ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ ተሞልቻለሁ የሚለው እና ያን ያክል እናንተን
እንጂ ያላችሁን አልፈልግም የሚልበት ክፍል ነው (ቲም ፌሎስ 290-292)፡፡

126
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 393
127
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 394
128
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 394
ጭብጥ
1. መግቢያ
የተለመደ ሰላምታውን ካቀረበ በኃላ (1፡1-2) እግዚአብሄርን ስለ ፊሊጲሲየስ ያመሰግናል እንዲሁም ይጸልይላቸዋል (1፡3-11)፡፡
2. የጳውሎስ እስራት 1፡12-26
መታሰሩ ወንጌልን እንዲያደግ እንዳደረገ ይነግራቸዋል (1፡12-18) በእነርሱ ጸሎት ከእስራት ነጻ ሊወጣ እንደሚችል ተስፋ አድርጓል
(1፡19-26)፡፡መከራ መቀበል እንኳን ቢሆን እንደ አማኝ አንደሚገባ እንዲኖሩ ያሳስባቸዋል (1፡27-30)፡፡ክርስቲያን ለመከራም
ተጠርቷል፡፡
3. ለክርስቶስ መኖር 1፡27-2፡18
የመልዕክቱን አንባቢዎች ትሁት እንዲሆኑ እና የክርስቶስን ምሳሌ እንዲከተሉ ያሳስባቸዋል፡፡ክርስቶስ ከማንነቱ አምላክ ሆኖ ሳለ
የመስቀልን መከራ እንደታገሰ ሁሉ ማለት ነው፡፡እግዚአብሄርም ከፍ ከፍ እንዳደረገው (2፡1-11) እንዲሁም እነርሱም እግዚአብሄርን
በታማኝነት እንዲያገለግሉ ያሳስባቸዋል (2፡12-18-ካርሰን 498)፡፡
4. ግላዊ መረጃ ስለ አፍሮዲጡ
በዚህም አፍሮዲጡን እና ጢሞቲዎስን እንዲሰዳቸው ተስፋ አድርጓል (2፡19-24፤ 2፡25-30)፡፡
5. ክርስቲያናዊ ኑሮ 3፡1-4፡19
መገረዝን የሚሰብኩትን ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፡፡እንደ ይሁዲነቱ ትልቅ የሆነ ትምክት ነበረው ነገር ግን ይህን ስለ ክርስቶስ
ሲል እንደ ጉድፍ ቆጥሮታል፡፡ይህም ክርስቶስን ለማወቅ ካለው ረሀብ የተነሳ ነው (3፡1-11)፡፡ፍጹምነት ደረጃ እንዳልደረሰ ያብራራል
ነገር ግን ወደ ግቡ እየተዘረጋ እንዳለ ይነግራቸዋል፡፡የፊሊጲሲየስ ሰዎችን የሚነግራቸው የክርስቶስን መመለስ እንዲጠባበቁ እንጂ
የክርስቶስ መስቀል ጠላቶችን እንዳይመለከቱ ነው (3፡12-4፡1-ካርሰን-498)፡፡

የመጸሐፉን ዋና ክፍል ከጨረሰ በኃላ አብረውት የሰሩትን ሰዎች ሰላምታ ያቀርብላቸዋል (4፡2-3)፤እንዲሁም በጌታ ደስ ሊሰኙ እንጂ
ሊጨነቁ እንደማይገባ የእግዚአብሄር ሰላም እንደሚጠብቃቸው ይነግራቸዋል (4፡4-7)፡፡ክርስቲያናዊ ባህሪን ሊያሳዩ እንደሚገባ
ይነግራቸዋል (4፡8-9)፡፡
6. ስለ ስጦታው አመሰገነ 4፡10-20
ስለላኩለት ገንዘብ ምስጋና (4፡10-20) አቅርቦ ሰላምና ጸጋ እንዲበዛላቸው በማሳሰብ ያጠናቅቃል (4፡21-23-ካርሰን-498)፡፡
ነገረ መለኮት
የክርስቶስ መክበር እና መዋረደ

በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተከስቶ ስለነበረው እና የመከፋፈል ምክንያት ስለሆነ ጥላቻ ሲያነሳ ጳውሎስ የተለያዩ መከራከሪያ ነጥቦችን
ያስቀምጣል (ፊሊ 2፡1-4) ከሁሉ የሚበልጠው ግን የክርስቶስን ሀሳብ (ምልከታ) የያዘው ክፍል ነው፡፡129 ያም በእግዚአብሄር መልክ
የነበረ መቀማትን ያልቆጠረ መሆኑን አፅንኦት ይሰጣል (ፊሊ 2፡5-8)፡፡130ይህ አገላለፅ ክርስቶስን ከአብ ጋር በተመሳሳይ ስልጣን
ያስቀምጠዋል (2፡11)፡፡131የክርስቶስን የህይወት ሂደት ይናገራል (ፊሊ 2:6–11)132 ዋናው ሀሳቡ ያው ተመሳሳይ የሕይወት ውደት
በአማኞችም ውስጥ እንዲደገም ነው (ፊሊ 3፡1-21)፡፡ሂደቱም ቪ ቅርፅ ዓይነት ነው፡፡ይህም ከእግዚአብሄር ወደ ምድር ከዚያም ወደ
እግዚአብሄር፡፡ክርስቶስ አሁንም ሰውነቱን ሳይለቅ ሁሉን ቻይነቱንም ይዞ አሁን እንዳለ ያሳያል (ፊሊ 3፡20)፡፡133

መንፈስ ቅዱስ
129
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 355
130
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 355
131
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 355
132
ኬኖሲስ Kenosis:ይህ ንድፈ ሀሳብ በፊሊ 2፡7 ላይ ራሱን ባዶ አደረ የሚለውን ቃል (κενοῦν,)” መሰረት ያደረገ ነው፡፡ይህም ወደ 17 ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ
የመጀረ ሲሆን ብዙዎች ይህን ምልከታ ተቀብለው ያራግቡታል፡፡በቅርብ ጊዜ በኢትዮጲያ የአንድ ቤተ እምነት ዶክተር የመመረቂያ ፅሁፉን በዚህ ቃል ላይ መሰረት
አድርጎ ክርስቶስ ራሱን ባዶ አደረገ ማለት መለኮታዊ ባህሪውን ትቷል ብሎ ለመሞገት ጥረት አድርጓል፡፡ይህ አስተሳሰብ ክርስቶስ በንፅፅር መለኮታዊ ባህሪያቱን ያም
ሁሉን ማወቁ በሁሉ ስፍራ መገኘቱ ሁሉን ቻይነቱን ትቶ በምድር ተከስቷል ብሎ ይላል፡፡ነገር ግን እንደ ቅድስና ፍቅር ጽድቅ የመሳሰሉትን አለቀቀም ብሎ ለመሞገት
ይሞክራል፡፡ይህ ግን ትክክል አይደለም ምክንያቱም ጄራልድ ሲሞግት አንደኛ አንድ ጥቅስ ላይ ሆነን ይህን አይነት አስተምህሮ ማበጀት አንችልም፡፡ባዶ አደረገ ማለት
ትቶ መጣ ከማለት ይልቅ ያልነበረውን ጨመረ የሚል ነው፡፡ስለዚህ ይላል ጄራልድ በተሰግዖ ክርስቶስ ከአምላክ አነሰ ሳይሆን ጨመረ በማለት ይከራከራል (see
Hawthorne, Gerald F.: Word Biblical Commentary : Philippians. Dallas : Word, Incorporated, 2004 (Word Biblical Commentary 43), S. 121)፡፡
ሌላው ግሩደም ይህ ጉዳይ ከባህሪ አንጻር የገባ ነው ብሎ ይላል፡፡ ነገር ግን አውዱ ራሱን ዝቅ አደረገ ለመስቀል ሞት ታዛዥ ሆነ የሚለው ሀሳብ የሚነግረን ስለ ትህትና
እንጂ መለኮታዊ ባህሪያትን ስለመተው አይደለም፡፡የጳውሎስም ዓላማ ትህትናን ለማስተማር ነው (ፊሊ 2፡1)፡፡ ትሁት ለመሆን የፊሊጲሲያስ አማኞች ከተፈጥሮ
ችሎታቸው አንዳች መተው አያስፈልጋቸውም ነበር፡፡ሌላው በፊሊጲስየስ 2፡7 ላይ የተጠቀሰው ራሱን ባዶ አደረገ የሚለው አመለካከት የማይፈለግበት ምክንያት
ሌሎች የአዲስ ኪዳን ምንባባት ምንም አይነት ፍንጭ ስለዚህ ጉዳይ ስለማይሰጡ ነው፡፡የኬኖሲስ አስተሳሰብ እንዲህ ጉዳይ የሆነበት ምክንያት ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ
በአንድ ጊዜ አምላከም ሰውም ነው የሚለው ለአህምሮ ስለማይመች ነው( ተመልከት ዌይን ግሩደም፤የመጸሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መግቢያ፡ስልታዊ ነገረ መለኮት ቅፅ
1(አዲስ አበባ፡ኤስ አይ ኤም፣2008)613)፡፡
133
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 357
በአንድነት እንዲቆሙ የተነገራቸው አንድ መንፈስ (1፡27) ተመሳሳይ መንፈስ መካፈላቸው (2፡1) ያን ያክል ግር የሚያሰኝ አባባል
አይደለም፡፡ምክንያቱም ያ አብሮነትን የሚያበዛ እንዲሁም የአብሮነትን ትስስር የሚያጠናክር የመንፈስ ቅዱስ በረከት ነው፡፡ይህም
በክርስቶስ መካፈልን ስናስብ እንዴት አድርጎ ተመሳሳይ ቃላትን እንደተጠቀመ ማየት ይቻላል (1 ቆሮ 1፡9)አምላኮ ራሱ በመንፈስ
ቅዱስ አማካኝነት እንደሚደረግ (through the agency of the Spirit) ግልፅ ያደርጋል (ፊሊ 3፡3)፡፡134

እግዚአብሄር አብ

ከማንኛውም ክስተት በስተጀርባ ያለው እግዚአብሄር እንደሆነ እና በአማኞች ውስጥ እየሰራ እንደሆነ ይነግረናል (ፊሊ 2፡13፤ 3፡15)
እንደሚጠብቃቸው እና ህይወታቸውን እንደሚገዛ ግልፅ ያደርጋል (2፡27)፡፡ለዚህ ነው ምስጋና ልማነ ሁሉ ወደ እርሱ የሚቀርበው
(ፊሊ 4፡6-1፡3)፡፡135

በክርስቶስ አዲስ ህይወት

አንደኛ ይህ ጉዳይ በፀሎት ሪፖርት ውስጥ የተንፀባረቀ ነው፡፡ያም በፍቅር በእውቀት በንፅህና እና በጽድቅ እንዲጎለበቱ በሚናገረው
ክፍል ውስጥ ማለት ነው (ፊሊ 1፡9-11)፡፡136ይህን ጉዳይ ስናይ በክርስቶስ መጸደቅ (justification) እና ዕርቅ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ
ግርታ ይኖር ይሆን ብለን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ይህም አማኞች በዚያን ቀን ያለ ምንም አይነት ፍርሃት በእግዚአብሄር ፊት ሊቆሙ
እንደሚችሉ ግልፅ ተደርጎ ተቀምጧል (ሮሜ 5፡1-11)፡፡137 ነገር ግን ጳውሎስ ግልፅ የሚያደርግልን እግዚአብሄር ነቀፋ እና ነውር የሌለን
እንድንሆን ሳያቋርጥ እንደሚሰራ ለማሳየት ነው (ፊሊ 1፡6)፡፡138

ሁለተኛ ይህ ሕይወት በሰው ደረጃ እንኳን ካየነው ጳውሎስ እና አብረውት የሚሰሩት ሰራተኞች በአብሮ ሰራተኝነት ደረጃ ብቻ ያሉ
እንዳልሆኑ ለማሳየት ነው፡፡ይህም ግንኙነታቸው እውነተኛ ወዳጆች እና በፍቅር የሆነ እንደሆነ የሚያመለክት ነው፡፡ምክንያቱም
ሁሉም አማኞች ናቸው እነዚህ ሁለት ግንኙነቶ በአንድ ተቀላቅለው ሊታዩ የሚችሉ ናቸው፡፡ 139ይህም ኀብረት (ኮይኖኒያ) ማለት
ሲሆን በዋናነት የሚታየው በመንፈስ ቅዱስ የሆነ የእግዚአብሄር በረከት መሆኑን ነው (ፊሊ 1፡7፤ 2፡1)፡፡ይህን ልክ በወንጌል
እንደተገለጠው ማለት ነው (1፡5) ይህም እርስ በእርስ እና ከጳውሎስ ጋር ያለውን ትስስር የሚሳይ ነው (4፡14-15)፡፡ይህም መካፈል
የሚያካትተው በክርስቶስ መከራ መካፈል (ፊሊ 3፡10) ሲያድግም በትንሳኤው ወደ መካፈል ይመጣል፡፡140

ሦስተኛ ሌላኛው ህይወት ተጨባጭ በሆነ ሁኔታ በጳውሎስ ህይውት መካፈል ያመለክታል፡፡ይህም በገንዘብ የሚመነዘር ነው፡፡ሌላው
የጳውሎስን ሰራተኛ በመላክ አብሮ እንዲሰራ ማድረግ፤ሌላኛው ጸሎት ማድረግ ሲሆን ያለዚያ ጸሎት ስራው ሊቀጥል እንደማይችል
ይነግረዋል፡፡አንድ ላይ ለወንጌል በመትመም ዓለማዊነትን በመጣል እንዲበረቱ ያደርጋቸዋል (ፊሊ 2፡16)፡፡141

ድነት ፊሊ 2፡12?

በዚህ ስፍራ ላይ የራሳችሁን መዳን ፈፅሙ ሲል ምን ማለቱ ነው?ይህም ጥቅስ የክርክር ምክንያት ሆኗል፡፡ጥያቄው ድነት ዋስትና
(Eternal security) የሌለው ጉዳይ ነው? የሚል ጥያቄ አለው፡፡

ድነት ማህበረሰባዊ ጤና አውተን ጄራልድ ሙግቱን የሚጀምረው ከመጸሐፍ ቅዱስ ትርጉም (Translation) ነው፡፡ለዚህ ነው
ትርጉም ነገረ መለኮታዊ እንድምታ ይኖረዋል የሚባለው፡፡መጀመሪያ የራሳችሁን መዳን ፈፅሙ በማለት ኬጂቪ ፤ኒው አር ኤስ ቪ፤ኤን
አይ ቪ እና አር ኤስ ቪ ተርጉመውታል፡፡ነገር ግን እርሱ ሲተረጉመው ጤናችሁ [መንፈሳዊ]ላይ ስሩ (“work
at achieving
[spiritual] health.” ) ብሎ ተረጎመው ለዚህም መከራከሪያ ማቅረብ ጀመረ፡፡ ጳውሎስ የእያንዳንዱ ሰው 142

ድነት ለማንሳት ፈልጎ አይደለም በማለት ለማሳየት ጥረት ማድረግ ጀመረ፡፡ይህም የማህበረሰቡ ጤናን

134
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 358
135
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 358
136
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 358
137
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 358
138
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 359
139
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 359
140
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 359
141
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 360
142
Hawthorne, Gerald F.: Word Biblical Commentary : Philippians. Dallas : Word, Incorporated, 2004 (Word Biblical Commentary 43), S. 139
የሚመለከት ነው ብሎ አለ፡፡ይህም ጳውሎስ ሰው ራስ ወዳድ መሆናቸው አሳስቦታል (ፊሊ 2፡4)፡፡ይህን ብሎ
ሲያበቃ ጳውሎስ መዳንን ከነፍስ ድነት ጋር አያይዞት ሊያነሳ አይችልም በማለት ሙግቱን ያቀርባል፡፡የራሳችሁን
የሚለው ማህበረሰባዊ እንጂ ግላዊ ድነትን አያመለክትም፡፡ድነት በተለያየ ስፍራ ጤናን ይመለከታል፡፡ስለዚህ
ጳውሎ ግድ ያለው የማህበረሰቡ መንፈሳዊ ጤና ጉዳይ ነው ብሎ ይሞግታል፡፡ 143 ይህም ድነት ማህበረሰባዊ
እንጂ ነገረ መለኮታዊ አይደለም እንደማለት ነው፡፡

ድነት ነገረ መለኮታዊ

ፒተር ኦ ብረያን ጳውሎስ ድነት σωτηρία የሚለውን ቃል የተጠቀመው በፊሊጲሲየስ ውስጥ ማህበራዊ ሳይሆነ ነገረ
መለኮታዊ ነው በማለት ምክንያቱን ያቀርባል፡፡አንደኛ ይህ ቃል (ድነት) በ 1፡19 ሆነ 1፡28 ላይ ከነፍስ ድነት ጋር ተያይዞ
ተቀምጧል፡፡የራሳችሁ የሚለው የክርስቲያን ማህበረሰቡን ጤና ለመናገር ሳይሆን ሁሉን በዚህ አስተሳሰብ ዕይታ ውስጥ
ለማየት ነው፡፡ድነት የዚህ እና የአሁን ጉዳይ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ይህም ያመኑትን በተግባር (1፡27) ማሳየት ነው ይላል፡፡
ይህ ማለት ድነት የእኛ እና የእኛ መፈፀም ብቻ ነው ማለት አይደለም እርሱ በህይወታችን ሳያቋርጥ ይሰራል (2 ጴጥ 1፡
10)፡፡ በጳውሎስ መረዳት ቀኑ ሲቀርብ ጨምረን ማድረግ ያለብንን እንድናደርግ ይነግረናል (ሮሜ 13፡11)፡፡በመፍራት እና
በመንቀጥቀጥ የሚለው የሚዛመደው (fit) ዘለዓለማዊ ድነት ጋር ነው፡፡ስለዚህ ድነት የግል ሲሆን ያም በማህበረሰብ
ሕይወት የሚታይ ነው በማለት ይከራከራል፡፡144

መወያያ ጥያቄ
ቆላሲስ
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
ጸሐፊው ማነው የሚለው ጥያቄ መነጋገሪያ ነጥብ ነው፡፡እስከ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ያን ያክል ማን ፅፎታል የሚለው ጉዳይ
ጥያቄ አልነበረም፡፡ይህም ሆኖ በጣም ጥቂት የሆኑ ሊቃውንት ናቸው የጳውሎስን ጸሐፊነት የሚጠራጠሩት፡፡ለምሳሌ ቡልትማን
አንዱ ነው፡፡የጳውሎስ ጭማሪ መጸሐፍ እንደሆነ ቆጥሯል (“deutero-Pauline,”)፡፡ምናልባት ጳውሎስ ከማለት ይልቅ ተከታዮቹ
ፅፈውታል የሚለው የሚያስኬድ በማለት ለመሞገት ጥረት ተደርጓል፡፡ሌሎች ለምሳሌ ኩመል ሞል ብሩስ ኦ ብራያን እና ጋርላንድ
ፀሐፊው ጳውሎስ ነው ብለው ይሞግታሉ፡፡

መጸሐፉ ጳውሎስ ፅፎኛል በማለት ይናገራል (1፡1) እንዲሁም እኔ ጳውሎስ የሚለው (1፡23) በራሴ በጳውሎስ እጅ ፅፌዋለሁ
የሚለው (4፡18) ይህም በየደብዳቤዎቹ መለያ ነው (2 ተሰ 3፡17) ጳውሎስ ለመጻፉ ምስከር ነው፡፡ይህም ሆኖ ክርክር የሚቀርብበት
ምክያት ቋንቋ ነገረ መለኮት እና ከኤፌሶን ጋር ያለው ዝምድና (ግንኙነት) ነው (ካርሰን-517)፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
የተጻፈበት ቀን ግልፅ አይደለም፡፡ይህም ሆኖ ጳውሎስ የት ነበር የታሰረው የሚለው ምናልባት ጥሩ አመላካች ይሆናል፡፡ሮም ካልን በ 60
ዓ.ም ሊሆን ይችላል፡፡ከሮም ሌላ ቦታ ፅፎታል የምንል ከሆነ ወደ 50 ዓ.ም አካባቢ ሊሆን ይችላል (ካርሰን-522)፡፡

ሐ. ዓላማ
ጭብጥ
1. መግቢያ
መክፈቻው ሰላምታ (1፡1-2) ለጥቆ የቈላሲስ ክርስቲያኖች ስላላቸው እምነት እና ፍቅር ምስጋና ያቀርባል ፡፡
2. ክርስቶስ በላጭ ነው

143
Hawthorne, Gerald F.: Word Biblical Commentary : Philippians. Dallas : Word, Incorporated, 2004 (Word Biblical Commentary 43), S. 139
144
O'Brien, Peter Thomas: The Epistle to the Philippians : A Commentary on the Greek Text. Grand Rapids, Mich. : Eerdmans, 1991, S. 280
ከዚያም ስለ ክርስቶስ ልዕቀት ይናገራል (1፡15-20) ያም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው ብሎ ይናገራል፡፡በፍጥረት ውስጥም ንቁ
ተሳታፊ (active ) እንደሆነ ይናገራል፡፡ከዚያም የክርስቶስ የደረገው የመቤዠት (reconciling) ስራ ያነሳል (1፡21-23)፡፡ይህም ጉዳይ
ራሱ ለክርስቶስ ሲሰራ ያጋጠመውን መከራ እንዲያነሳ ያደርገዋል (1፡24-2፡5 ካርሰን-516)፡፡

ተራ እና ከንቱ በሆነ ፍልስፍና እንዳይወሰዱ ይናገራቸዋል (2፡6-8)፡፡ከዚያም ወደ ክርስቶስ ትልቅነት ይመጣል የመለኮት ሙላት
በሰውነቱ ተገልጦ እንደሚኖር ያነሳል እና ድነታቸውን እንደሰራ ያነሳላቸዋል (2፡9-15)፡፡ለሃይማኖታዊ ባህላት ለምግብ ህግጋት
እንዳይማረኩ ጥሪ ያቀርባል (2፡16-23)፡፡

3. ለክርስቶስ መኖር
ከክርስቶስ ጋር ስለተነሱ ማድረግ ያለባቸውን እና የሌለባቸውን ግልፅ ማሳሰቢያ ይሰጣቸዋል (3፡1-17)፡፡145እንደ ክርስቲያን ቤተሰብ
እንዴት መኖር እንዳለባቸው ለሚስቶች፤ለባሎች፤ለልጆች፤ለአባቶች፤ለባሮች እና ለጌቶች መመሪያ ይሰጣል (3፡18-4፡1)፡፡በውጭ
ባሉት ዘንድ በጥበብ መኖር እንዳለባቸው እና እንዲጸልዩለት ጥሪ ያቀርባል (4፡2-6-ካርሰን-516)፡፡ቲቂኮስ ከእነርሱ ዘንድ ዜና
እንደሚያመጣላቸው ይነግራቸዋል፡፡
4. ማጠቃለያ
ከዚያም ብዙ የሆኑ አማኝ ጓደኞቹን ሰላምታ ያቀርባል(4፡7-15)፡፡ፅሁፉ እየተዘዋወረ እንዲነበብ መመሪያ ይሰጣል (4፡16-17)
የጳውሎስን የሚመስል ሰላምታ ያቀርባል (4፡18-ካርሰን-517)፡፡

ነገረ መለኮት
ነገረ ክርስቶስ

በሶስቱም የጳውሎስ የእስር ቤት መልዕክቶ (ፊሊጲሲየስ ቈላሲስ እና ኤፌሶን) በጣም የዳበረ የነገረ ክርስቶስ ሀሳብ ቀርቧል፡፡ያም
ቅድመ ህላዌ፤በአሁን እና በሚመጣው ዘመን በተፈጥሮ ሁሉ ላይ ያለውን ልዕቀት ይናገራል፡፡ 146በጣም አስፈላጊው ነገር ክርስቶስ ሰው
ሆኖ መገኘቱ ነው (2፡9)፡፡ይህም በአሁን ጊዜ ግስ የተቀመጠ ሲሆን ያም አሁን ክርስቶስ በከበረ ቦታ በዚህ ሁኔታ እንዳለ አመልካች
ሲሆን በተጨማሪ በሀላፊ ጊዜ መቀመጡ ደግሞ የቀድሞ በምድር ያለውን ሁኔታ ያሳያል (ቈላ 2፡9)፡፡147የመለኮት ሙላት በሰውነቱ
ተገልጦ ይኖራል የሚለው አዲስ የጎለበተ ሲሆን (1፡19፤ 2፡9) አማኞችም በክርስቶስ በተመሳሳይ ሁኔታ ይሞላሉ፡፡148

ዕርቅ

በአንድ ጎን ሰው ኀጢያተኛ ነው የሚለው አስተሳሰብ በመልዕክቱ ውስጥ አለ (1፡21) ከእግዚአብሄር ዘወር ያሉ (የራቁ) መሆናቸው እና
የእርሱ ጠላቶች መሆናቸው (ቈላ 1፡21) እንዲሁም በዚህ በጨለማ ዓለም ውስጥ መሆናቸው (1፡13) ከዚያም ራሳቸውን ማዳን
የማይችሉ መሆናቸው ተግልፆል፡፡የክርስቶስ መምጣት የማዳን ዘመቻ እንደሆነ ይናገራል፡፡መዋጀት የኀጢያት ይቅርታ በሚል ሀረግ
ተገልፆል (1፡14፤ 2፡13)፡፡ቀድሞ የኀጢያት ይቅርታ ከማለት ይልቅ መፅደቅ (justification) ቃል ይጠቀም ነበር (ሮሜ 4፡7)፡፡ሮሜ 6
ደግሞ የመጸደቅን ልምምድ ሲናገር ቈላ 3-4 ደግሞ ጥልቅ የሆነ ተግባራዊ ህይወትን ያሳያል፡፡ይህ ለክርስቶስ መሞት እና መኖር ምን
ማለት እንደሆነ ለማሳየት ጥረት ያደርጋል፡፡የዚህ ዓላማ ለእግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ለመፍጠር ነው (1፡12)፡፡149

ቤተ ክርስቲያን

ቤተ ክርስቲያን በተለያየ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሏል ያም አንደኛ ስብሰባ (4፡16)፡ሁለተኛ የቤት ለቤት ቤተ ክርስቲያን ሌላኛው ደግሞ
(4፡15) በቆላሲስ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከዚያም ከፍ ያለ ትርጓሜ ይዞ ይታያል ያም ዩኒቨርሳል ዕይታ ነው ክርስቶስ የቤተ ክርስቲያን
ራስ ነው ይላል (1፡18)፡፡ቁጥር 18 የሚነግረን ሰማያዊ ልዕለ መለኮታዊ ተቋምን እንጂ ስብሰባ ወይም የቤት ለቤት ቤተ ክርስቲያንን
አይደለም፡፡
145
ፒተር ኦ ብራያን ከክርስቶስ ጋር (σὺν Χριστῷ) የሚለውን ቃል (2፡12፤20 3፡3፤4) ጠቅሶታል፡፡ይልና ይህም ያላቸውን ግንኙነት አመልካች ነው በማለት
ለመናገር ይሚክራል፡፡
146
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 375
147
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 375
148
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 376
149
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 377
ጥምቀት 2፡12-13?

ፊልሞን
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
ጳውሎስ ጸሐፊው እንደሆነ ግልፅ ነው (ካርሰን-589)፡፡ጸሐፊው በማህበረሰብ ውስጥ የሚነሱ ችግሮችን የመፍታት ጥበብ ያለው ሰው
እንደሆነ ግልፅ ነው፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
የፊልሞን መጸሐፍ ከቆላሲስ መጸሐፍ ጋር ተያያዥ ነው፡፡ሁለቱም ጢሞቲዎስን እንደ ተባባሪ የመልዕክቱ ላኪ አድርገው
ይጠቅሱታል፤ሁለቱም ኤጳፍራን ያነሳሉ (ቆላ 1፡7፤ ፊል 23) አርኪዮጳስን ይጠቅሳሉ (ቆላ 4፡17፤ ፊል 2) ሁለቱም
ማርቆስን፤አሪስጣስን፤ዴማስ ሉቃስን እና የጳውሎስ ወዳጆች ይጠቅሳሉ (ቆላ 4፡10 እና 14 ፊል 24) ቆላሲዮስ አናሲሞስን
ይጠቅሳሉ (4፡9)፡፡አናሲሞስ የቆላሲስ ነዋሪ እንደሆነ ተጠቅሷል ስለዚህ ፊልሞንም የቆላሲስ ነዋሪ ነው ብንል ትክክል ነን(ቆላ 4፡9)፡፡
ይህ የሚያመለክተው ሁለቱም መልዕክቶች በአንድ ወቅት ተፅፈዋል የሚልን ሀሳብ ነው፡፡ታዲያ የተጻፈው ከየት ነው የሚለው
አወዛጋቢ ነው፡፡ከኤፌሶን ከሆነ (55 ወይም 56) ቂሳርያ ከሆነ (57-59 የሐዋ 34፡23-36፡32) ሮም ከሆነ (60-62) ሊሆን ይችላል፡፡ግን
ኤፌሶን የሚለው አዘንብሏል (ካርሰን-593)፡፡

ሐ. ዓላማ
አንደኛ-ፊልሞና የኮበለለ ባርያውን አናሲሞስን እንዲቀበል ለማግባባት ነው፡፡አናሲሞስ ወደ ሮም የመጣው ለመደበቅ ይሆናል፡፡አንድ
ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርባት ከተማ ለመደበቅ፡፡ቢያዝ ሞት ወይም በጋለ ብረት መተኮስ ዕጣው ነበር፡፡የያዘው ሰው መመለስ ግዴታ
ነበረበት፡፡ጳውሎስ በራሱ ፈቃድ ውይም በህግ አስገዳጅነት ለመመለስ ፈልጎ ሊሆን ይችላል፡፡ከሚለው ይልቅ አብልጦ ሊያደርግ
እንደሚችል ሲያግባባው ምናልባት ከባርነት ነጻ እንዲያወጣው እየጠየቀው ሊሆን ይችላል፡፡ሁለተኛ-ጳውሎስ በቅርቡ ተፈትቶ ወደ
ቆላስይስ እንደሚመጣ ለመግለፅ ነው፡፡ይህም የእንግዳ ቤት ለማግኘት ሊሆን ይችላል፡፡ሦስተኛ-ምናልባትም የባሪያ አሳዳሪዎች
ተመሳሳይ ባህሪ እንዲያሳዩ ሊሆን ይችላል፡፡አራተኛ-ማህበረሰቡ ላገለላቸው ሰዎች መራራት እንዳለበት ለማሳየት ነው (ቲም ፌሎስ
443-444)፡፡ምንም እንኳን ይህ ቀደምት የሆነ ምልከታ ቢሆንም በዚህ ዘመን ግን ሙግት ገጥሞታል፡፡ዋናው ጥያቄ አናሲሞስ እንዴት
ነፍሱን ለማዳን ጌታውን ወደሚያውቅ እስረኛ ሊሄድ ቻለ? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡አንዱ የተሰጠው ንድፈ ሀሳብ-ያን ያክል የኮበለለ
ባሪያ ሳይሆን ትንሽ የገንዘብ አጠቃቀም ችግር የደረሰበት እና ያንን ለማስተካከል ለመሸምገል የሞከረ ነው፡፡ይህ ግን የማያስኬደው
ይህን ያክል ርቀት (ወደ ሮም) እንዴት ሽምግልና ፍለጋ ሄደ የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለመቻሉ ነው (ካርሰን-591)፡፡

ጭብጥ
ጳውሎስ ብቻውን ሳይሆን ከጢሞቲዎስ ጋር በኀብረት እንደጻፉት ይገልፃል (1)፡፡የጻፈው ለፊልሞን አቭያ እና አርኪጳዎስ ፅፎላቸዋል
(2)፡፡

ምስጋናን ያቀረበበት ክፍል የፊልሞንን ምሳሌያዊ ህይወት ላይ ያተኮረበት ነው (4-5፤ 7)፡፡እምነቱን ለሰዎች እንዲያካፍል
ይጸልይለታል (6)፡፡የቁጥር 7 መጨረሻ ጳውሎስ ዋናውን ሀሳብ ያቀርባል፡፡የሰዎችን ልብ ስለምታሳርፍ ይለውና ቁጥር 20 ደግሞ
የእኔንም ልብ አሳርፍልኝ ይለዋለል (ካርሰን-588)፡፡

ዋናውን ክፍል በአራት ከፍለን ማየት እንችላለን፡፡ያም አንደኛ (ቁጥር 8-11) ሲሆን በዚህ ክፍል ዋናውን የደብዳቤውን ሀሳብ
ያስታውቃል፡፡ያም ስለ ልጄ ነው ይለዋል (10)፡፡ይህም በእስር በወንጌል የወለደው ልጁ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ሊያዘው ሲችል ማድረግ
ያለበትን በፍቅር እንዲያደርገው ጥሪ ያቀርብለታል (11)፡፡በዚያም ከስሙ ተነስቶ መልዕክት ያስተላልፋል፡፡

ሁለተኛ (12-16) ሲሆን አናሲሞስን መላክ እንደፈለገ ደግሞ ለወንጌል በጣም ጠቃሚው ስለሆነ መልሶ ይልክለት እንደሆነ ይህንንም
በግድ ሳይሆን በፍቅር እንዲያዳርግ ያሳስበዋል (14)፡፡ነገር ግን ፊልሞን ዕርቅ እንዲያወርድ ይለምነዋል ያም አንደ ወንድም እንጂ እንደ
ባሪያ እንዳያየው ሲሆን ያም አዲስ ስፍራ ነው (ቁ 16)፡፡

ሦስተኛው ክፍል ላይ አሁንም ጳውሎስ ደግሞ እንደ አማኝ ወንድም እንዲያየው ጥሪ ያቀርባል (17) ይህም በአናሲሞስ የተነሳ
የከሰረው ነገር ቢኖር ራሱ ጳውሎስ እንደሚተካው ይነግረዋል (18-19)፡፡በመጨረሻ ልመና ይህንን ክፍል ይዘጋዋል (20)፡፡ይህን
አስቀድመን እንዳነሳነው የቁጥር 7 ቋንቋ በማንሳት ነው፡፡
ከዚያ በላይ ሊያደርግ እንደምትችል አውቃለሁ የሚለውን ወስደው አንዳንዶች ፊልሞን አናሲሞስን ለጳውሎስ መመለስ ብቻ
ሳይሆን ምናልባትም ነጻነቱን (ከባርነት ነጻ ማድረግ) እንደሚችል ያብራራለታል (20-21፡፡የጉዞ ዕቅድ በመጥቀስ፤ጓደኞቹን በመሰናበት
አና የጸጋ ምኞት በመመኘት ያበቃል (25-ካርሰን 589)፡፡

ነገረ መለኮት
የጳውሎስ ልመና መሰረት ያደረገው ወንጌልን እና ክርስቲያናዊ ኀብረትን ነው፡፡የምንዳርገው በጎ ነገር ሁሉ መሰረቱ የክርስትና ኀብረት
መሆን አለበት (ቆላሲስ 1፡4)፡፡ይህም ምንጩ አንድ እምነት መካፈላቸው ነው፡፡ያም የፊልሞን ፍቅር ወደ ሌሎች የሚሻገር ነው፡፡
ሁሉም በጋራ ከአላቸው እምነት አንጻር የሞተውን የተነሳውን ኢየሱሱን ማሰብ እንደሚገባ ከዚያም አንጻር ጳውሎስ ፊልሞንን
ሲያዘው ይታያል፡፡ የባሪያ ጌታ ግንኙነት ወይም ከባሪያ ጌታ ነጻ የሆነ ግንኙነት ምጡቅ በሆነው ግንኙነት የተተካ ነው፡፡ይህ ጉዳይ
በጌታም ቢሆን በስጋ እውን የሆነ ነው፡፡150

መወያያ ጥያቄ

ክፍል አምስት

የመጋቢያን መልዕክት
መግቢያ
ሀ. ፀሐፊ
መጸሐፍቶቹ የተጻፉት በጳውሎስ መሆኑን ምስክርነት ይሰጣሉ (1 ጠሞ 1፡1፤2 ጠሞ 2፡1፤ቲቶ 1፡1)፡፡አንዳንዶች (ዶናልድ ጉተሬ-434)
መጸሐፉን በጳውሎስ ስም ሌላ ሰው ፅፎታል የሚሉ ሰዎች እንዳሉ ይናገራል፡፡ በመልዕክቶቹ መካከል ከፍተኛ የሆነ የቋንቋ
ተመሳሳይነት አለ፡፡ውጪያዊ መስረጃዎች ለምሳሌ ሙራቶሪያን ቀኖና ፀሐፊው ጳውሎስ ነው ይላል፡፡

አልጻፈውም የሚሉ እንዲህ ዓይነት የቤተ ክርስቲያን አደረጃጀት በጳውሎስ ዘመን ሊሆን አይችልም (it is too advanced for
Paul)፤አዲስ አማኝ አትሹም የሚለው በጳውሎስ ዘመን ሊሆን አይችልም፡፡ሌላው በውስጥ የተነሳው የስህተት ትምህርት የዚያ
ዘመን (ግኖስቲሲዝምን የሚመስል) ሊሆን አይችልም (ጉተሬ 441)፡፡ይህም የብህትና ህይወትን መደገፉ፤ወይም ቅጥ ያጣ ህይወት
ልምድን መደገፉ የክርስቶስን ትንሳኤ መቃወሙ የሁለተኛው ክፍለ ዘመን ዓይነት ነው፡፡ሌሎች ይህ አያስኬድም ብለው ይላሉ
ምክንያቱም ግኖስቲሲዝም እስከ ጳውሎስ ዘመን ድረስ የተዘረጋ የቆየ ፍልስፍና ስለሆነ በማለት ይሞግታሉ (ጉተሬ 442)፡፡

ለ. የተጻፈበት ቀን
ሐ. ዓላማ
የ 1 ጢሞቴዎስ-ምናልባትም የጢሞቲዎስ ተቀባይነት እንዲጨምር ስልጣን እንዲኖረው ለማስቻል ተጽፎ ሊሆን ይችላል፡፡ሌላው
ግንስቲክን የሚመስል የስህተት ትምህርት ገብቶ ነበር (1 ጢሞ 1፡3-20)፡፡ አስተምህሮው ስጋን እንዲጨቁኑ እና ከአንዳንድ ነገር
እንዲርቁ ያስተምሩ ነበር (1 ጢሞ 1፡4-6፤ 6፡3-8፤ 20-21)፡፡ሦስተኛው ቤተ ክር እንዴት እንደሚያስተዳድር መመሪያ ለመስጠት ነው
(1 ጢሞ 3፡1-13)፡

ጠሞቴዎስ ጳውሎስ ሉቃስ ሲቀር ሁሉም ስደት በመፍራት ትተውት ነበር፡፡ዴማስ (2 ጢሞ 4፡10፤ 11)፡፡ምናልባት ጢሞቴዎስም
በእምነቱ ጉዳይ ፈርቶ አፈግፍጎ ይሆናል እና ስደት እንዳይፈራ ለማጀገን የተጻፈ ይሆናል (2 ጢሞ 1፡8)፡፡ሁለተኛ በስደት፤በስህተት
ትምህርት የምትናጥ ቤተ ክርስ ሰዎች የወንጌልን እውነት አጥብቆ እንዲይዝ (2 ጢሞ 1፡14፤ 4፡2)፡፡በመጨረሻ ቃሉ ላይ አገልግሎቱን
እንዲመሰርት ነው (2 ጢሞ 2፡15-ቲም ፌሎስ 406)፡፡

ቲቶ-በቀርጤስ ቤተ ክርስቲያን እንዴት እንደሚያደራጅ ለመግለፅ፡፡ቀርጤስ አስቸጋሪ ቦታ ነበር ያም ህዝቡ ሰነፎች እና በላተኞች
ነበሩ፡፡የባህሪ ለውጥ እንዲያመጣ ያሳስበዋል፡፡ሁለተኛ የቀርጤስ ሰዎች እንዴት መመላለስ እንዳለባቸው ለማሳሰብ ነው፡፡ሦስተኛ
ጠንካራ ቤተ ክርስቲያን እንዴት ማደራጀት እንደሚቻል ሊያሳይ ይችላል ያም ሁሉንም የዕድሜ ክልሎች ማየት ይጠይቃል፡፡አራተኛ
የስህተት ትምህርትን ለመጋፈጥ (ቲቶ 1፡1)፡፡ስህተቱ የመጣው ከተገረዙት ወገን ሲሆን ህግን የመጠበቅ አስፈላጊነት አጽንኦት
ይሰጣሉ፡፡ጳውሎስ እግዚአብሄርን እንደሚያውቁ ይናገራሉ ግን አያውቁትም በማለት የሞግታቸዋል (ቲቶ 1፡10-16)፡፡

150
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 362
ጭብጥ
1 ጢሞቲዎስ
ግላዊ ምክር-ሰላምታ (1፡1-2) ከዚያ ለጥቆ ስለ ህግ የሚያስተምሩ የስህተት አስተማሪዎችን ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል (1፡3-13)፡፡
የእግዚአብሄር ፀጋ እና ምህረት ስለበዛለት ምስጋና ያቀርባል፡፡ራሱ እንዴት ምህረት እንደበዛለት ማብራሪያ ይሰጣል (1፡12-17)፡፡ይህ
መልዕክት በዋናነት መሰረት ያደረገው ጢሞቴዎስ መልካሙን ገድል እንዲጋደል ማበረታታት ላይ ነው፡፡ይህም ጢሞቴዎስ ራሱ
ተጠልፎ እንዳይወደቅ የግል ሕይወቱን ንፅህና እንዲጠብቅ ያሳስበዋል (1፡18-21)፡፡

ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር-ለባለስልጣናት እንዲጸለይ ይነግራቸዋል፡፡ይህም የቤተ.ክር መሪ ምዕመኑ የሚጸልይ እንዲሆኑ ማሳየት


አለበት (2፡1-8)፡፡ወዲያው ሴቶች እንዴት ምሳሊያዊ ህይወት መምራት እንዳለባቸው ማሳየት አለበት፡፡ይህም ከአለባበስ እንጻር ነው
(2፡8-15)፡፡ጢሞቴዎስ መሪዎች በመምረጥ ሂደት ውስጥ ጥንቃቄ እንዲኖር አብይ ሚናውን እንዲወጣ ያሳስበዋል፡፡ይህም መደረግ
ያለበት በመስፈርት እንደሆነ ለኤጲስ ቆጶሳት (3፡1-7) ለዲያቆናት (3፡8-10፤ 12-13) እንዲሁም ስለ ሴቶች ዲያቆናት (3፡11)
መስፈርት መመሪያ ይሰጠዋል፡፡ወንጌልን ይጠብቃል፡፡ይህም ከስህተት ትምህርት ነው (4፡1-5)፡፡የወንጌል እውነትን በመጠበቅ ሂደት
ስጦታውን ቸል እንዳይል ያሳስበዋል (4፡6-16)፡፡ጢሞዎስ ለሁሉም የዕድሜ ክልል የሚሆን አገልግሎት (ባህሪ) እንዲያቀርብ ያሳስበዋል
(5፡1-16)፡፡ስለ ሽማግሌዎች ለየት ያለ ትዕዛዝ ይሰጠዋል (5፡17-20)፡፡ጢሞቴዎስ ከሁሉም የክርስቲያን ማህበረሰብ (ባሮች እና
ጌቶች) ጋር ያለውን ግንኙነት የተስተካከለ እንዲሆን ያሳስበዋል (1 ጢሞ 6፡1-2)፡፡

የመጨረሻ ግላዊ ምክር-ከሀሰት መምህራን ጋር የማያስፈልግ ንትርክ ውስጥ መግባት እንደሌለበት እና ራሱን ከገንዘብ ፍቅር ማራቅ
እንደሚያስፈልገው ይነግረዋል (6፡3-10)፡፡ከዚህ ተነስቶ ሀብታሞች ገንዘባቸውን የት ማከማቸት እንዳለባቸው መመሪያ ይሰጣል (6፡
17-19)፡፡ጳውሎስ ደብዳቤዎን የሚዘጋው በእምነት እንዲበረታ በማሳሰብ ነው (6፡20-21)፡፡በኃላ ጳውሎስ የጸጋ ምኞቸቱን በመግለፅ
ያጠናቅቃል (6፡21-ካርሰን-572)፡፡

2 ጢሞቲዎስ
በጌታ መቆም ይገባል-(ሞቱን እያሰበ የጻፈው ነው (4፡6-8)፡፡ሲጀምር ሰላምታ በመስጠት ነው (1፡1-2)፡፡ከዚያም ምስጋና እና
ማብረታታት ያቀርባል (1፡3-7)፡፡ቀጥሎ ጳውሎስ በወንጌል ስላላፈረ እርሱም በጳውሎስ (ምናልባት ጳውሎስ ራሱን በሰጠው
በወንጌል) እንዳያፍር ያሳስበዋል (1፡8-14)፡፡ትንሽ ስለመተዉ ነገር ግን ሄኔሲፎሩ ያደረገውን ነገር ካስታወሰው (1፡15-18) በጌታ ፀጋ
እንዲበረታ ያሳስበዋል (2፡1-7) እናም የወንጌልን አስፈላጊነት ያብራራለታል (2፡8-13)፡፡ከዚያም ስለ ሀሰት መምህራን ግልፅ ነገር
ይነግረዋል (2፡14-26)፡፡
ለሀሰት ትምህርት ምላሽ ስጥ- በመጨረሻ ዘመን መጥፎ ዘመን ሊመጣ እንደሚችል ትንቢታዊ መልዕክት ያስተላልፍለታል (3፡1-
9)ከዚያም እግዚአብሄር በመከራው ሁሉ እንዳዳነው በመናገር ምስጋና ያቀርባል፡፡ከልጅነቱ ጀምሮ ያምንበት የነበረውን ትምህርት
እንዲቀጥል ያሳስበዋል፡፡ያም መጸሐፍት በህይወቱ ድነት ጉዳይ ላይ የላቸውን ሚና ይናገራል (3፡14-17)፡፡
የመጨረሻ ንግግር-በዚህ ሁሉ ቃሉን እዲሰብክ መመሪያ ይሰጠዋል (4፡1-5)፡፡ሞቱ እየመጣ እንደሆነ እና ለዚያም የሚያስፈልግ
ዝግጅት እንዲያደርግ ማሳሰቢያ ይሰጠዋል (4፡6-8)፡፡ከዚያ ስለ አንዳንድ ግለሰቦች ተከታታይ ንግግር ያደርጋል (4፡9-15)፡፡በሰላምታ እና
በጸጋ ምኞት ይደመድማል (4፡9-15-ካርሰን-578)፡፡
ቲቶ
መሪ ስለመሾም-ጳውሎስ እንደተለመደው በሰላምታ ይጀምራል (1፡1-4)፡፡ሰላምታው ትንሽ ከተመለደው ረዘም ያለ ሲሆን
እግዚአብሄር የዘለዓለም ህይወትን አስቀድሞ እንደወሰነ ይናገራል፡፡በቀርጤስ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያዋቅር እንደተወው
ያስታውሰዋል፡፡በእያንዳንዱ ከተማ ሽማግሌዎችን እንዲሾም መመሪያ ይሰጠዋል፡፡ይህም የሚሾመው ሰው ለዚህ ስራ የሚመጥን
መሆን እንዳለበት ያሳስበዋል (1፡5-9)፡፡
የሀሰት ትምህርት መከላከል-ሌላው በቀርጤስ አመጸኛ ሰዎች እንዳሉ ያስታውሰዋል፡፡ይህም ጳውሎ ቲቶን እንዲያስጠነቅቃቸው
መመሪያ ይሰጠዋል (1፡10-16)፡፡ይህም ሽማግሌውን ምን ማስተማር እንዳለበት (2፡2) ቆነጃጅትን (2፡3-5) ጎበዛዝት (2፡6-8) ባሮችን
(2፡9-10) ግልፅ ያደርግለታል፡፡
የፀጋው ወንጌል-ሰዎች ሁሉ ለወንጌል መኖር ይጠበቅባቸዋል፡፡ያም የጌታን መገለጠ በመጠባበቅ ጉዳይ ላይ ነው (2፡11-15)፡፡በሰልጣን
ላይ ያሉት ሰዎች መታዘዝ አለባቸው፡፡ወደ ጌታ ከመምጣተቸው በፊት ያለው ጊዜ እና ከመጡ በኃላ ያለው ጊዜ ልዩነት እንዳለ
ይነግራቸዋል (3፡3-8)፡፡ክፍፍልን ማስወገድ ይገባል (3፡9-11)፡፡ከዚያም አንዳንድ መመሪያዎችን ይሰጣቸዋል እና በሰላምታ ይዘጋል (3፡
12-15-582-ካርሰን 582)፡፡
ነገረ መለኮት
ኢየሱስ እና እግዚአብሄር

ነገረ ክርስቶስ
መገለጥ በሚለው ሀሳብ ዙሪያ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ይህ መገለጥ የተባለውን ቃል ከምፅአት ጋር አያይዞ ጳውሎስ በ 2 ተሰሎንቄ 2፡8
ይነግረናል፡፡እና ያንኑ ቃል በዚህ ስፍራ ይጠቀማል (ቲቶ 2፡13፤ 2 ጢሞ 4፡1፤8)፡፡ከዚያም አልፎ የጌታን ምድራዊ ህይወት የሚያሳይ
ነው (2 ጢሞ 1፡10)፡፡151ይህ ቃል የሚነግረን የተገለጠው ሰማያዊ አካል መሆኑን ነው፡፡ይህም 1 ጢሞ 3፡16 ላይ በስጋ የተገለጠ
በመንፈስ የጸደቀ የታየ ቃል ነው፡፡ወደ ዓለም መምጣቱ በሚለው ላይ ያለው አገላለፅ ልክ ዮሐንስ የተጠቀመው ሲሆን የተሰግዖ ቃል
ነው (1 ጢሞ 1፡15)፡፡152
ሌላ አስቸጋሪ ሀሳብ በ 2 ጢሞ 1፡9-10 ላይ ተገልፆ ይታያል፡፡ዓለም ሳይጀመር በፊት ፀጋ ተሰጠን የሚለው ሀረግ ነው፡፡ይህም ቢሆን
ክርስቶስ በምድር ከመምጣቱ በፊት በሚል ሊታይ ይችላል፡፡ 153በየትኛው አዲስ ኪዳን መጸሐፍት ላይ የድነት ጉዳይ የሚታየው
ኢየሱስ ወደ ምድር ከመጣ ጋር ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የመንፈስ መውረድ የሐዋርያት ምስክርነት ጋር ይያያዛል፡፡ተመሳሳይ ሀሳብ
1 ጢሞ 2፡5-6 ተንጸባርቆ እናያለን ያም ኢየሱስ ራሱን መስጠቱ ከሐዋርያት ምስክርነት ጋር ይያያዛል (2 ቆሮ 5፡18-21) ማስታረቁ
ከእርቅ ዕወጃው ጋር ተያያዥ ነው፡፡154
የአማኝ ህይወት

የክርስቲያን ሕይወት ምን መምሰል አለበት የሚለው ጉዳይ አንድ አብይ ጥያቄ ነው፡፡ቀደምት የሆነ አመለካከት በዚህ ጉዳይ ላይ አለ፡፡
ያም ከእግዚአብሄር አዳኝነት የተነሳ አንድ ሰው የእግዚብሄር ቤተሰብ አካል ይሆናል (2 ጢሞ 1፡15፤ 2፡4 4፡16 2 ጢሞ 1፡9፤ ቲቶ 3፡5
1 ጢሞ 2፡15 2 ጢሞ 4፡18)፡፡155 የሰው ልጅ በሙሉ ክፉ ከንቱ እንደሆነ አመልካች ነው (ቲቶ 2፡11፤ 14፤ 3፡3)፡፡ድነት ታዲያ ከዚህ ክፉ
የሕይወት ልምምድ መታደግ ነው፡፡ይህም ህይወት ወይም የዘለዓለም ሕይወት የሚል ሀሳብ ተንፀባርቆበታል (1 ጢሞ 1፡16፤ 6፡12,
19; 2 ጢሞ 1:1, 10; ቲቶ 1:2; 3:7); ይህም በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ የማቋርጥ ሕይወት ማለት ነው (2 ጢሞ 4፡18) አሁን
እና እዚህም ግን ጥራት ያለው ሕይወትም መኖር ማለት ነው (1 ጢሞ 4፡8)፡፡ምንም እንኳን ጥቂት ነገር ቢባልም ስለ ፍርድ ቀንም
ተነግሯል (1 ጢሞ 5፡24)፡፡በዚያን ቀን ምህርት የሚያይ እንዳለ ይናገራል (2 ጢሞ 1፡18፤ 4፡8)፡፡ይህ የሚያሳየው የዳኑ ኀጢያተኞችን
ነው፡፡156

መዳን መዋጀት መሆኑን ግልፅ ያደርግልናል ይህም ቤዛነትን ያመለክታል እናም የኢየሱስን ንግግር ያስታውሰናል (ማር 10፡45-1 ጢሞ
2፡5፤ ቲቶ 2፡14)፡፡ይህም ትድግና ከኀጢያት ሁሉ እና ከዚያም ውጤት ነው፡፡ይህም መጽደቅ ብሎ ጳውሎስ የሚናገረው ነው (ቲቶ 3፡

151
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 408
152
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 409
153
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 409
154
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 409
155
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 411

156
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 411
7)፡፡መታደስ እና ልደት የሚሉ ቃላትም ይጠቀማል፡፡ይህም መሰረታዊ ለውጥን ወይም መቀየርን ለማመልከት ሲሆን ያንንም
የሚሰራው መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡157

157
Marshall, I. Howard: New Testament Theology : Many Witnesses, One Gospel. Downers Grove, Ill. : InterVarsity Press, 2004, S. 411

You might also like