Professional Documents
Culture Documents
Social Studies II (Modified) Normal
Social Studies II (Modified) Normal
መጠነግብር 4/6
አዘጋጆች
ታህሳስ 2007
ጎንደር
መጠነግብር 4/6
አዘጋጆች
መግቢያ........................................................................................................... 18
ምዕራፍ ሦስት..................................................................................................... 65
መግቢያ........................................................................................................... 65
የሞጁል መግቢያ
የማህበራዊ ጥናት ትምህርት የማህበራዊ ሳይንሶች ዉህድ ነዉ፡፡ ተፈጥሮአዊና ሰዉ ሰራሽ እዉነታዎችንና
ክስተቶችን ለመረዳት፣ ለመንከባከብና በአግባቡ ለመጠቀም ይረዳል፡፡ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ
ግንዛቤዎችን ለማዳበርና ተገቢ የዜግነት ድርሻን ለመወጣት ያስችላል፡፡
ይህ ኮርስ / SoSt - 222 / በ 10+3 የዲፕሎማ ፕሮገራም ለሚከታተሉ የዉህድ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች
የተዘጋጀ ሲሆን ስድስት የግንኙነት ሰዓት ተመድቦለት የሚሰጥ ኮርስ ነዉ፡፡
በኮርሱ ዉስጥ የተካተቱት ክፍለ ትምህርቶች ምእራፍ አንድ፡- የከፍታ ልዩነት በካርታ፣ ምእራፍ ሁለት፡-
የአለምና የኢትዮጵያ ፊዚካዊ አካባቢ፤ ምእራፍ ሶስት፡- የአለም ህዝብ፣የኢኮኖሚ ስርዓትና ልማት፣ ምእራፍ
አራት፡- ኢትዮጵያና የአፍሪካ ቀንድ እኤእ ከ 1855-1991፣ምእራፍ አምስት፡- የአፍሪካ ታሪክ እኤእ
በ 1880 ዎቹ፣ ምእራፍ ስድስት፡- የዘመናዊዉና የአሁኑ አለም ታሪክ እኤአ ከ 1815 -1945 የሚሉት ዋና ዋና
ክፍለ ትምህርት ሲሆኑ በየክፍለ ትምህርቱ መጀመሪያ የትምህርት አላማዎች ተገልጸዋል፡፡ እንዲሁም በየክፍለ
ትምህርቱ መጨረሻ ማጠቃለያና የክለሳ ጥያቄዎች ተካተዋል፡፡
ምዕራፍ አንድ
ዓላማ
ሰልጣኞች ይህን ምዕራፍ ካጠናቀቃችሁ በሁላ፦
የገፀ ምድርን ከፍታና የከፍታ ልዩነት ለመግለፅ የሚያስችሉ ባህላዊ ዘዴዎችን ትገልፃላችሁ።
የስምርቅጦችን ባህሪያት ታብራራላችሁ።
የውስን ከፍታ ማሳያ ዘዴዎችን ትለያላችሁ።
የቆለቆል ዓይነቶችን በስዕላዊ መግለጫ ታሳያላችሁ።
በቆለቆሎችና በድፈቶች መካከል ያለውን ዝምድና ታስረዳላችሁ።
ተግባር 1.1
በማንኛዉም የመሬት መዋቅር (ክፍል) ማዕከል ያለ ቦታ ከባህር ወለል በላይ ያለው የጉባጉብ ልዩነት ከፍታ
ይባላል።
የተለያዩ የመሬት ገጽታዎች የከፍታ ልዩነት በካርታ ላይ በተለያዩ መንገዶች ተወክሎ ይገለጻል።
ተግባር 1.2
የተለያዩ የመሬት ገጽታዎችን የከፍታ ልዩነት ካርታ ላይ ለማንበብም ሆነ ለመረዳት በመጀመሪያ የካርታ
ባለሙያዎች የመሬትን ጉባጉብ (ወጣ ገባ) በዝርግ ወረቀት (ካርታ) ላይ የሚወክሉባቸውን መንገዶች ማወቅ
ይገባል። የመሬትን ወጣ ገባ የከፍታ ልዩነት ለመግለጽ የሚያስችሉ ሁለት ዋና ዋና የተለያዩ ዘዴዎች አሉ።
እነሱም ባህላዊ ዘዴዎች (Traditional methods) እና ስምርቅጦች (Contour lines) ናቸው።
ትኩረት
ጥፍተ ምድራዊ ስምር ንድፍ ዘዴ ጥንታዊ የካርታ ስራ ሙከራ ሲሆን ከላይ በተገለጹት ጉድለቶች
ምክንያት በአሁኑ ጊዜ ጠቀሜታሙ ዝቅተኛ ነዉ።
ተግባር 1.3
ለ. ሽምጥ (Hachures)
ሽምጥ (hachures) ቆለቆሎችን (slopes) በካርታ ላይ ለማሳየት የምንጠቀምባቸው አጫጭር መስመሮች
ናቸው። የሽምጥ መስመሮች የሚሰመሩት የውሃን ፍሰት አቅጣጫ ተከትለው ሲሆን ዋና አገልግሎታቸው
የቆለቆሎችን ድፈት (gradient) ለማሳየት ነው። ነገር ግን ሽምጥ (hachures) መስመሮችን በመጀመሪያ
ጥንታዊ የካርታ ስራ ባለሙያዎች ተራሮችንና ሸለቆዎችን ዝርግ ወረቀት ላይ በቀላሉ ለመንደፍ ይጠቀሙበት
ነበር።
ሽምጥ መስመሮች ጭልጤ ድፈት ቆለቆሎችን (steeper slopes) የሚወክሉ ከሆኑ አጫጭርና ተጠጋግተው
ሲቀመጡ፤ ድኩም ድፈት ቆለቆሎችን (gentle slopes) ሲወክሉ ደግሞ ረጃጅምና ተራርቀው ይቀመጣሉ።
በዚህ ዘመን የሽምጥ መስመሮችን ለብቻቸው ካርታ ላይ መጠቀም እየቀረ ነው። ከዚያ ይልቅ ሽምጥ
መስመሮች የተወሰኑ የገጸ ምድር አይነቶችን ማለትም ዘብጣዘብጥ(escarpment)፣ ገሞራ ቆሬ(crater) እና
ስጥመትን(depression) ለመወከል ከስምርቅጦች ጋር በማቀናጀት ጥቅም ላይ ይውላሉ።
ሐ. ጉባጥለት (Hill-shading)
ጉባጥለት ሌላኛው ካርታ ላይ የከፍታ ልዩነት ወካይ ዘዴ ነው። ጉባጥለት ኮረብታን ወይም ጉባጉብን በካርታ ላይ
የሚያሳየው ከሀሳባዊ የመብራት ምንጭ ነው። የሀሳባዊ መብራት ምንጩ ከካርታው ሰሜን ምዕራብ ማዕዘን
እንደሆነ ይታመናል። ከዚህ አንጻር በካርታው ደቡብ ምስራቅ ላይ የሚገኙ ቆለቆሎች ከሰሜን መዕራብ
ቆለቆሎች ይልቅ የጠቆሩና የተከለሉ ሆነው ይታያሉ።
ስዕል 4. (ለ) የተመሳሳይ ኮረብታ ቦታ ከላይ ሲታይ (Top-view of the same hilly area)
ትኩረት
በጣም ዝቅተኛው የከፍታ ንብር በአረንጓዴ ቀለም ሲቀለም ከዝቅተኛው ቦታ ቀጥሎ ያለው ከፍታ
በቢጫ ቀለም ሆኖ ከፍተኛው ቦታ በቡናማ ቀለም ይቀለማል። በጣም ከፍተኛ ከፍታ ያላቸው
ቦታዎች ደግሞ ጥቁር፣ቀይ፣ሀምራዊ ወይም ነጭ ቀለም በመጠቀም የንብብር ቅልመት ሊሰራ
ይችላል።
2. ጥልቅ ንብብር ቅልመት/ንቅሰት በከፍተኛ መስፈርት ካርታ ላይ ሌሎችን የገጸ ምድር አይነቶች
የማደብዘዝ ወይም የመሸፈን እድሉ ከፍተኛ ነው። ለአነስተኛ መስፈርት ካርታ ግን ጠቀሜታው የጎላ
ነው።
3. ጥቂት የቀለም አይነቶች ለካርታ አንባቢው የተሳሳተ ግንዛቤን ሊፈጥሩ ይችላሉ። ምሳሌ፦ የአረንጓዴ
ቀለም የቦታውን ለምነት ወይም የደን ሽፋን እንዳለው ግንዛቤ ሊፈጥር ይችላል።
4. ቀለማት የቦታውን የከፍታ ልዩነት እንጅ ሌላ ዝርዝር መግለጫ መስጠት አይችልም።
5. የንብብር ቅልመት/ንቅሰት ካርታዎች ህትመት ውድ መሆናቸው።
6. ስምርቅጦች ቀጤ ቃጥላ (vetical cliff) ወይም ፏፏቴ (water fall) በሚወክሉበት ጊዜ ካልሆነ
በስተቀር ርስበርሳቸው አይገናኙም፣አይጠላለፉም።
ትኩረት
ካርታውን ተጠቅመን የነጥብ ‘A’ን ከፍታ ለማግኘት የምንከተላቸውን ደንቦች በጥንቃቄ ተመልከቱ።
ሀ. በነጥብ ‘A’ ላይ የሚያልፍ አጭር አቋራጭ ቀጥተኛ መስመር በማስመር ሁለቱን ስምርቅጦች
ማገናኘት
ለ. ያሰመራችሁትን የመስመር ርዝመት መለካት (ምሳሌ 20 ሳ.ሜ)
ሐ. ከታችኛው ስምርቅጥ እስከ ነጥብ ‘A’ ያለውን ርዝመት መለካት (ምሳሌ 15 ሳ.ሜ)
መ. በሁለቱ ስምርቅጦች መካከል ያለውን ስምርቅጥ ፋታ መለየት (የስምርቅጥ ፋታ = 100 ሜ)
ሠ. የነጥብ ‘A’ን ከፍታ እንደሚከተለው መወሰን
600+(15*100)/20 = 675 ሜ ወይም
700+(5*100)/20 =675 ሜ
ተግባር 1.4
ተግባር 1.5
ስምርቅጦች ተጠጋግተው የተሰመሩ ከሆነ ቆለቆሉ ጭልጤ ድፈት መሆኑን፤ተራርቀው የተሰመሩ ከሆነ ደግሞ
ቆለቆሉ ድኩም ድፈት መሆኑን በማየት መለየት ይቻላል። የቆለቆሉን የድፈት መጠን ምን ያህል እንደሆነ
ለማወቅ ስንፈልግ በድፈት ስሌት ቀመር ማግኘት ይቻላል።
ተግባር 1.6
ድፈት አንድ በተወሰነ ገጸ ምድር ወይም በወንዞችና በመንገዶች ላይ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለው ርቀት
ቆለቆሉ በምን ያህል ዲግሪ ዥው ያለ(ያጋደለ) መሆኑን የምንገልጽበት የስሌት ዘዴ ነው። ይህም በሁለቱ
ነጥቦች መካከል ያለውን የከፍታ ልዩነት እና ርቀት ግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
ትኩረት
በሁለት ነጥቦች መካከል ያለውን ድፈት ለማስላት የሚከተለውን ቀመር መጠቀም ይኖርብናል።
ድፈት ንጥጥ = በሁለት ነጥቦች መካከል ያለው የከፍታ ልዩነት ሲካፈል በተመሳሳይ ነጥቦች
መካከል
ያለው የርቀት ልኬት
ድፈት መቶኛ = ድፈት ንጥጥ * 100
ድፈት ዲግሪ = ድፈት ንጥጥ * 600
ተግባር 1.7
ከዚህ በታች ያለውን ካርታ በማጥናት ድፈትን እንዴት ማስላት እንደሚቻል ሂደቶችን አሳዩ።
ከተራራው መነሻ እስከ ተራራው ጫፍ ድረስ እኩል (አንድ አይነት) ድፈት ያለው ቆለቆል ትክክል ቆለቆል
ይባላል። ስምርቅጦች በዚህ ቆለቆል ጊዜ አንዱ ከሌላኛው በእኩል ርቀት ተሰምረው የተቀመጡ ናቸው።
ከተራራው መነሻ ጭልጤ ድፈት ሆኖ ወደ ተራራው ጫፍ ድኩም ድፈት ያለው ቆለቆል ጉብብ ቆለቆል
ይባላል። ጉብብ ቆለቆል የሚወክሉ ስምርቅጦች ከተራራው መነሻ በጣም ተጠጋግተው፤ ወደ ተራራው ጫፍ
ደግሞ ተራርቀው እናገኛቸዋለን።
ከጉብብ ቆለቆል በተቃራኒ ስርጉድ ቆለቆል ተራራው ጫፍ ጭልጤ ድፈት ሆኖ ከተራራው መነሻ ድኩም ድፈት
ያለው ቆለቆል ስርጉድ ቆለቆል ይባላል። ስለዚህ ስርጉድ ቆለቆል ስምርቅጦች ከተራራው መነሻ ተራርቀው
ሲቀመጡ ወደ ተራራው ጫፍ ደግሞ በጣም ተጋግተው እናገኛቸዋለን።
ማጠቃለያ
በማንኛውም የመሬት መዋቅር ወይም ክፍል ማዕከል ያለ ቦታ ከባህር ወለል በላይ ያለው የጉባጉብ ልዩነት ከፍታ ይባላል።
የመሬትን ወጣ ገባ የከፍታ ልዩነት ባህላዊ ዘዴዎችን እና ስምርቅጦችን በመጠቀም መግለፅ ይቻላል። ባህላዊ ዘዴዎች
የምንላቸው ጥፍተ ምድራዊ ስምር ንድፍ፣ ሽምጥ፣ ጉባጥለትና ቅርፅ መስመሮች ናቸው። አሁን አሁን ብዙ ጊዜ ከፍታንና
የከፍታን ልዩነት ለማሳየት የምንጠቀምባቸው የሃሳብ መስመሮች ስምርቅጦች ይባላሉ። ነገር ግን ስምርቅጦችን በመጠቀም
ውስን ከፍታዎችን (specific heights) ማለትም የተራራ ጫፎችን፣ የኮረብታ ጫፎችን፣ የሸለቆ ወለሎችን፣ የማማዎችን፣
የከተሞችን ወዘተ ከፍታ በተለየ ሁኔታ ሊያሳዩ አይችሉም። ለእነዚህና መሰል የተለያዩ የመሬት ገጽታ ከፍታዎችን በካርታ ላይ
ለማሳየት ወይም ለመወከል እውቅ ፍታ፣ ትሪግኖሜትሪካል ነጥቦች፣ ማጣቀሻ እና የከፍታ ስሌት ዘዴዎችን በመጠቀም ማሳየት
ይቻላል። ድፈት አንድ በተወሰነ ገጸ ምድር ወይም በወንዞችና በመንገዶች ላይ በሁለት ነጥቦች መካከል ያለው ርቀት ቆለቆሉ
በምን ያህል ዲግሪ ዥው ያለ(ያጋደለ) መሆኑን የምንገልጽበት የስሌት ዘዴ ነው።
1. የገፀ ምድርን ከፍታና የከፍታ ልዩነት ለመግለፅ የሚያስችሉ ባህላዊ ዘዴዎች ጥቀሱ።
2. የስምርቅጦችን ባህሪያት አብራሩ።
3. የውስን ከፍታ ማሳያ ዘዴዎችን በመግለፅ ለእያንዳንዳቸው ተጨባጭ ምሳሌ አቅርቡ።
4. የቆለቆል ዓይነቶችን በስዕላዊ መግለጫ አሳዩ።
5. በቆለቆሎችና በድፈቶች መካከል ያለውን ዝምድና አስረዱ።
ከዚህ በታች በቀረበው ካርታ መሰረት የሚከተሉትን ጥያቄዎች ስሩ።
ምእራፍ ሁለት
መግቢያ
በዚህ ምእራፍ ዉስጥ የስነመሬታዊ ጊዜ ሚዛን፣ የኢትዩጵያ ስነመሬታዊ ድርጊቶች፣ የአየር ቅጥ፣ የአለም
የአየር ቅጥ ክፍፍል፣ የኢትዮጵያ አየርቅጥ፣ የአየር ቅጥ ለዉጥና ሊያስከትል የሚችለዉ ጉዳት እና ስርዓተ
ምህዳር የሚሉ ይዘቶች ተካተዋል፡፡ በተጨማሪም እንደ ርእሱ ሁኔታ ተማሪዎችን ሊያሳትፉ የሚችሉ የተለያዩ
የተግባር ስራዎች የተቀረጹ ሲሆን አሰልጣኝ መምህራን እነዚህን ጥያቄዎች በማዳበር ተማሪዎች እንዲሰሩት
ይጠበቃል፡፡
ስነመሬታዊ ጊዜ በአራት የጊዜ እርከን ደረጃዎች ይከፈላል፡፡ እነሱም ዘመን /Eon / ክፍለ ዘመን / Era /
ወቅትና/ period/ ክፍለ ወቅት /Epoch/ ናቸዉ፡፡
ዘመን ክፍለ ዘመን ወቅት ክፍለ ወቅት እነዚህ በአንድ ላይ ስነመሬታዊ የጊዜ ሚዛንን
ይመሰርታሉ፡፡
ዘመን / Eon /፡- የመቶ ሚሊዮን አመታት የጊዜ ርዘመት ያለዉ የመጀመሪያዉና በጣም ረዥሙ የስነ መሬታዊ
ጊዜ ክፍፍል ነዉ፡፡ ስነመሬታዊ ጊዜ በአራት ዘመናት ይከፈላል፡፡ እነሱም ትእይንተ ህይወት / phanerozoic /፣
ፕሮትሮይዚክ / protriozoic /፣ አርኪያን / Archean / እና ሀዲያን /Hadean/ ናቸዉ፡፡ እያንዳንዱ ዘመን
እንደገና በክፍለ ዘመናት የተከፋፈለ ነዉ፡፡ ለምሳሌ የስነ መሬታዊ የጊዜ ሚዛንን በሚያሳየዉ ሰንጠረዥ ላይ
እንደምትመለከቱት የትእይንተ ህይወት ዘመን በሶስት ክፍለ ዘመናት የተከፋፈለ ነዉ፡፡ እነሱም የሰብአ፣
የማእከላዊና የዘመነ ጥንተ ህይወት ናቸዉ፡፡
ክፍለ ዘመን / Era / ፡- ይህ ደግሞ ሁለተኛዉ የሰነመሬታዊ ጊዜ ክፍፍል ነዉ፡፡
ወቅት / period /:- ሶስተኛዉ የስነመሬታዊ ጊዜ ክፍፍል ነዉ፡፡
ክፍለ ወቅት / Epoch / ፡- አራተኛዉና ትንሹ የስነመሬታዊ ጊዜ ክፍፍል ነዉ፡፡
በስነምድር ተመራማሪዎች ጥናት መሰረት የመሬት እድሜ ከ 4.5 - 4.6 ቢሊዮን አመት ይሆናል ተብሎ
ይገመታል፡፡ በዚህ ረዥሙ የመሬት እድሜ ዉስጥ ብዙ የተለያዩ ስነመሬታዊና ስነ-ህይወታዊ ድርጊቶች በመሬት
ላይ ተከናዉነዋል፡፡ እነዚህን ድርጊታዊ ክንዋኔዎች በጥልቀትና በዝርዝር ለማጥናት ያመች ዘንድ የስነምድር
ተመራማሪዎች የመሬትን የህይወት ታሪክ በአራት ክፍለ ዘመናት ከፍለዉታል፡፡ እነሱም፡-
ሀ.የቅድመ ካምብራዊ ዘመን/ከ 4.5 ቢሊዮን - 600 ሚሊዮን አመት/
ለ.የዘመነ ጥንተ ህይወት /ከ 600 – 250 ሚሊዮን አመት/
ሐ.የማእከላዊ ዘመን /ከ 250 ሚሊዮን--- 70 ሚሊዮን አመት/ እና
መ.የሰብኣ ዘመን /ከ 70 ሚሊዮን --- አሁን/ ናቸዉ፡፡
እያንዳንዱ ክፍለ ዘመን በወቅቶች የተከፋፈለ ሲሆን ወቅቶች ደግሞ በተለያዩ ክፍለ ወቅቶች የተከፋፈሉ
ናቸዉ፡፡ በእያንዳንዱ ዘመን ክፍፍል የተለያዩ ስነምድራዊና ስነ-ህይወታዊ ድርጊቶች ተካሂደዋል፡፡ እነዘህም
ድርጊቶች የአህጉራትና ዉኃማ አካለት ቅርጽና መገኛ መለዋወጥ፣ የተለያዩ መልክአ ምድሮችና የአለቶች
ስሪት፣ የተለያዩ እንስሳትና እጽዋት ዝግመተ ለዉጥና የተለያዩ የአየር ቅጥ መከሰትን ያካተቱ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም እነዚህ ድርጊቶች አንዱን ዘመን ከሌላዉ ለመለየት የሚያስችሉ መነሻ ደንበር ተደርገዉ ይወሰዳሉ፡፡
ህይወ
ት
/
የማእከላዊ ክሬታሸስ/cretaceous/
ዘመን 144
/Mesozoic ጁራሲክ 208
era/ ትሪያሲክ 225
ዘመነጥንተህይ ፔሪሚያን 270
ወት ካርቦኒፈረስ 360
/Paleozoic ድቮኒያን 408
phaneorozoic/
/Precambrian
4550
era/
/Hadean/
ሀዲያን
ተግባር 2.1
1.የመሬት ዉጫዊ ገጽታ በየጊዜዉ እንዲለዋወጥ የሚያደርጉ ዉስጣዊና ዉጫዊ ሀይሎች ምን ምን ናቸዉ፡፡
2.የመሬት እድሜ የሚለካባቸዉ መንገዶች ምን ምን እንደሆኑ መጽሀፍ አንብባችሁ ወይም ሰዎችን ጠይቃችሁ ሪፖርት
አቅርቡ፡፡
3.አንዱ ክፍለ ዘመን ከሌላዉ በምን ይለያል?
ይህ ዘመን መሬት ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አለፉት 600 ሚሊዮን አመታት ያለዉን ጊዜ ይሸፍናል፡፡
ቅድመ ካምብራዊ ዘመን 88 ከመቶ የሚሆነዉን ስነመሬታዊ ጊዜ ይሸፍናል፡፡ በመሆኑም ቅድመ ካምብራዊ
ዘመን በመሬት የህይወት ታሪክ ዉስጥ እጅግ በጣም ሩቁና የጥንት ዘመን ነዉ፡፡
ስለመሬት ታሪክ ግንዛቤ የምናገኝበት ዋናዉ ዘዴ በተለያዩ ዘመናት በመሬት ላይ በተፈጠሩት አለቶችና ቅሪት
አካላት ላይ ጥናትና ምርምር በማድረግ ነዉ፡፡ በቅድመ ካምብራዊ ዘመን ስለተከናወኑት ድርጊቶች ለማጥናት
መሰረታዊ ችግር የሆነዉ በዚያ ዘመን የተሰሩት አብዛኛዎቹ አለቶች በአሁኑ ጊዜ በአፈር መሸርሸር
መከላታቸዉና ወደ ሌላ አለት በመለወጣቸዉ ምክንያት በቂ መረጃ ማግኘት አለመቻሉ ነዉ፡፡ ይህም በቅድመ
ካምብራዊ ዘመን ስለተከናወኑት ድርጊቶች ያለን እዉቀት ዉስን እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ይሁን እንጅ አንዳንድ
ዛሬ እየተካሄዱ ያሉ ስነምድራዊ ሂደቶች በቅድመ ካምብራዊ ዘመንም ስለመካሄዳቸዉ የሚጠቁሙ መረጃዎች
አሉ፡፡ ለምሳሌ የገሞራዊነት/Volcanism/፣ የአፍር መሽርሸር፣ የአፈር ክምችትና የተራራ ግንባታ ሂደቶች
በቅድመ ካምብራዊ ዘመንም ተካሂደዋል፡፡
መሬት የተሰራችባቸዉ የመጀመሪያዎቹና ጥንታዊ አለቶች ስሪት የተካሄደዉ በቅድመ ካምብራዊ ዘመን ነበር፡፡
በቅድመ ካምብራዊ ዘመን የተሰሩት አለቶች በሌሎች ዘመናት ከተሰሩት አለቶች የሚለዩበት ዋና መለያ ባህሪ
የእንስሳት ቅሪት አካል በዉስጣቸዉ አለመኖሩ ነዉ፡፡ ለዚህም ሁለት መሰረታዊ ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛዉ
ምክንያት አብዛኛዎቹ የቅድመ ካምብራዊ ዘመን አለቶች ገሞራዊና ልዉጤ አለቶች ነበሩ፡፡ ሁለተኛዉ
ምክንያት ደግሞ በቅድመ ካምብራዊ ዘመን የነበሩት እንስሳት በስስ ቆዳ የተሸፈኑ ስለነበር ለአለቶች ስሪት
የሚሆንና እንደቅሪት አካል ሆኖ በአለቶች ዉስጥ ሊቆይ የሚችል ጠንካራ ቆዳና አጽም አልነበራቸዉም፡፡
በቅድመ ካምብራዊ ዘመን ከተፈጠሩት ጥንታዊ አለቶች መካከከል አብዛኛዎቹ ከነሱ በኋላ በተሰሩ አለቶች
ስለተቀበሩ ልዉጥና ቧልጭታማ አለቶች /metamorphaized and crystalline rocks/ ሆነዋል፡፡
ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ስነመሬታዊ ድርጊቶች በተጨማሪ እንደ አሜባና ዝልግልግ አሳ /jelly fish/ የመሳሰሉ
ትንንሽ ጥንታዊ ህይወት ያላቸዉ ነገሮች በቅድመ ካምብራዊ ዘመን እንደተፈጠሩ ይታመናል፡፡
ዘመነ ጥንተ ህይወት ከዘመነ ቅድመ ህይወት በመቀጠል በእድሜ ሁለተኛዉ ረዥም ጥንታዊ ዘመን ሲሆን
የጀርባ አጥንት የሌላቸዉ የህይወት ዘመን እየተባለ ይጠራል፡፡ የዘመነ ጥንተ ህይወት ዘመን ለ 375 ሚሊዮን
አመት ያህል የቆየ ነዉ፡፡ ይህ ዘመን ብዙ ስነመሬታዊ ድርጊቶች የተከናወኑበት በመሆኑ በስድስት ወቅቶች
ተከፍሏል፡፡ በእያንዳንዱ ወቅትም የተለያዩ ስነመሬታዊና ስነ-ህይወታዊ ድርጊቶች ተከናዉነዋል፡፡ ለምሳሌ
በዘመነ ጥንተ ህይወት መጨረሻ በፕሌት ቴክቶኒክ ግፊት ምክንያት ሁሉም አህጉራት ተዋህደዉ አንድ አህጉር
መስርተዉ ነበር፡፡ ይህ አህጉር ቅድመ ክፍፍል አህጉር /ዉህድ- አህጉር/ (pangea) ተብሎ ይጠራል፡፡
በመጀመሪያዉ ዘመነ ጥንተ ህይወት ወቅት ህይወት ያላቸዉ ነገሮች የሚገኙት በዉቅያኖሶች ዉስጥና
በዳርቻቸዉ ብቻ ነበር፡፡ በኋላ ግን ህይወት ላላቸዉ ነገሮች አስፈላጊ የሆኑ የከባቢ አየር ይዘቶች ማለትም
የኦክስጅን፣ የናይትሮጅንና የካርቦንዳይኦክሳይድ መጠን እየጨመረ ሲመጣ ትልልቅ እንስሳትና እጽዋት በየብስ
ላይ እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ ተፈጠረላቸዉ፡፡ ዘመነ ጥንተ ህይወት የሚታወቀዉ ብዙ ህይወት ያላቸዉ ነገሮች
የተፈጠሩበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን ብዙ ህይወት ያላቸዉ ነገሮች ከምድር የጠፉበት ዘመን በመሆኑ ጭምር ነዉ፡፡
ለምሳሌ በኦረዶቪሲያን፣ በዲቮኒያንና በፐርሚያን ወቅቶች ብዙ ህይወት ያላቸዉ ነገሮች ከምድር ጠፍተዋል፡፡
ይህ ከፍተኛ የህይወት እልቂት ምናልባት በአየር ለዉጥና በእሳተገሞራ ፍንዳታ ምክንያት ሣይሆን አይቀርም
ተብሎ ይገመታል፡፡
የማእከላዊ ዘመን ሶስተኛዉ የስነመሬታዊ ዘመን ሲሆን 180 ሚሊዮን አመት ቆይቷል፡፡ ይህ ስነመሬታዊ ዘመን
በሶስት ስነመሬታዊ ወቅቶች ማለትም በትሪያሲክ፣ በጁራሲክና በክሪታሼየስ ወቅቶች በቅደም ተከተል
የተከፈለ ነዉ፡፡ በእያንዳንዱ ወቅትም ብዙ ስነመሬታዊና ስነ ህይወታዊ ድርጊቶች ተከስተዋል፡፡ ለምሳሌ
በትራሲክ ወቅት መጨረሻ ከፍተኛ የፕሌት ቴክቶኒክ እንቅስቀሴ ስለነበር ቅድመ ክፍፍል አህጉር/ዉህድ-
አህጉር/(pangea) ወደ ሁለት አህጉራት ተከፍሎ ነበር፡፡ እነሱም የጎንደዋናላንድ /ደቡባዊ የዉህድ አህጉር ክፍል/
እና ላዉሮዥያ /ሰሜናዊ የዉህድ አህጉር ክፍል/ ተብለዉ ይጠራሉ፡፡ እነዚህ አህጉራት በክሪታሼስ ወቅት
መጨረሻ ተከፋፍለዉ አሁን የምናዉቃቸዉን ሰባት አህጉራት መስርተዋል፡፡ ስእል 2.1 ን ተመልከቱ፡፡
በማእከላዊ ዘመን ዳይኖሰርስና መሰል ተሳቢ እንስሳት በቁጥር ከሌሎች እንስሳት ይበልጡ ስለነበር የማእከላዊ
ዘመን አንዳንድ ጊዜ የተራማጅና የተሣቢ እንስሳት የህይወት ዘመን እየተባለ ይጠራል፡፡ በማእከላዊ ዘመን
የመጨረሻዉ ወቅት ሌላ ሁለት ታላላቅ የስነ-ህይወታዊ ድርጊቶች ተከስተዋል፡፡ እነሱም፡-
የዳይኖሰርስ ከምድር መጥፋትና
የአጥቢ እንስሳት፣የአእዋፍና የአበባማ እጽዋት መፈጠር ናቸዉ፡፡
የሰብአ ክፍለ ዘመን አንዳንድ ጊዜ የጡት አጥቢ እንስሳት የህይወት ዘመን እየተባለ ይጠራል፡፡ ይህ የስነመሬታዊ
ዘመን በመሬት ታሪክ ውስጥ እጅግ በጣም የቅርብና የአሁን ዘመን ነው፡፡ የሰብአ ክፍለ ዘመን በሁለት
ስነመሬታዊ ወቅቶች የተከፈለ ሲሁን እነሱም ሶስተኛና አራተኛ ወቅቶች ተብለዉ ይጠራሉ፡፡ ሶስተኛ ወቅት
ከዘሬ 70 ሚሊዮን አስከ 1.6 ሚሊዮን አመታት ያለዉን ጊዜ ሲሽፍን አራተኛ ወቅት ደግሞ ከዛሬ 1.6 ሚሊዮን
እስከ አሁን ድረስ ያለዉን ጊዜ ይሸፍናል፡፡ ልክ እንደሌሎች ወቅቶች በነዚህ ወቅቶችም የተለያዩ ስነመሬታዊ
ድርጊቶች ተካሂደዋል፡፡ ለምሳሌ በሶስተኛ ወቅት በእሳተ ገሞራ የታጀበ የፕሌት ቴክቶኒክ እንቅስቃሴ ተካሒዶ
ዛሬ በመሬት ላይ የምናያቸዉን መልክዓምድሮች እንዲፈጠሩ አድርጓል፡፡ እንዲሁም የትልልቅ ተራራዎች
ግንባታ ሂደት በሰሜን አሜሪካ፣ በእስያና በአዉሮፓ ተካሂዷል፡፡ ለምሳሌ በአዉሮፓ የአልጵስ የተራራ ሰንሰለት፣
በሰሜን አሜሪካ የሮኪ ተራራ፣ በደቡብ አሜሪካ የኤንደስ ተራራ የተፈጠሩት በሰብአ ዘመን በሶስተኛዉ ወቅት
ነበር፡፡
በኳተርናሪ ወቅት ደግሞ በወራጅ ዉሀ፣ በበረዶና በነፋስ አማካኝነት በሶስተኛ ወቅት በተፈጠሩት
መልክአምድሮች ላይ ግጥግጦሽ /denudation/ ተካኂዷል፡፡ እንዲሁም የአየር ቅጥ በከፍተኛ ሁኔታ ቀዝቅዞ
ስለነበር አንድ አራተኛዉ የብሱ የመሬት ክፍል በበረዶ ተሸፍኖ ነበር፡፡ የአሁኑ የሰዉ ልጅ ዝርያ ሆሞሳፒንስ
/Homo Sapiens/ የተፈጠረዉ በአራተኛዉ ወቅት ከዛሬ 500,000 አመታት በፊት ነበር፡፡
ተግባር 2.2
1. በዘመነ ጥንተ ህይወት፣ በማእከላዊና በሰብ ክፍለ ዘመን የተካሄዱ ዋና ዋና ስነመሬታዊ ድርጊቶች ምን
ምን ናቸዉ?
2. የሚከተለዉን ሰንጠረዥ በመመልከት የጎደለዉን ዘመን፣ ክፍለ ዘመን፣ ወቅትና ክፍለ ወቅት
ሙላ/ሙይ
ዘመን /Econ/ ክፍለ ዘመን /Era/ ወቅት/period/ ክፍለ ወቅት ጊዜ በሚሊን
/Epoch/ አመት
የሰብአ ዘመን አራተኛ/Quaternary/ ሆሎሰን 0.01
/Cenozoic era/ ---------- 1.6
ፕሌዮሴን 5.3
---------------- ማዮሲን 23.7
ኦሊጎሲን 36.6
-------------- -------- 57.8
ፖሊዮሲን 66.4
ክሬታሸስ/cretaceous/
--------------- 144
ጁራሲክ 208
ትሪያሲክ 225
ዘመነጥንተህይወት ፔሪሚያን 270
/ Paleozoic era/ ካርቦኒፈረስ 360
---------- 408
ሱሉሪያን 438
----------- 505
ካምብሪያን 570
ፕሮተሮዞይክ ቅድመ ካምብራዊ 2500
/proterozoic/ ዘመን
/Precambrian era/ 3900
------------
4550
-------------
ይህ ዘመን በኢትዮጵ ላይ በተደጋገሚ የተራራ ግንባታና በጎመራዊ ተግባራት የሚታወቅ ነው፡፡ በቅድመ
ካምብራዊ ዘመን የኢትዮጵያ መሬት ገጽታ በአጐጥጓጭ ላይ ተግባር (intrusive igneous activity) የታጀበ
ከፍተኛ የመሬት መታጠፍ የታየበት ወቅት ነበር፡፡ በግንባታ ተራራ መካከልና ከግንባታ ተራራ በኋላም ቢሆን
ለረዥም ጊዜ የቆየ የግጥ ግጦሽ (denudation) ወቅት ተከስቷል፡፡ ይህ ለረዥም ጊዜያት የቆየ የግጥግጦሽ
ወቅት ከግጥግጦሽ በፊት የተገነቡትን ተራሮች በማጠብ ወደ ሜዳነት ወይም ውስድ ስቶታነት (peneplain)
እንዲቀየሩ አድርጓቸዋል፡
በቅድመ ካምብራዊ ዘመን የተሰሩ አለቶች /ድንጋዮች/ በስነመሬት ተመራማሪዎች የተለያየ ስያሜዎች
ተሰጥቷቸዋል፡፡ እነዚህም የተለያዩ ስሞች ስርጌ ስብጥርጥር /basement complex/፣ ባልጩትና ስርጌ
/crystalline basement / ወይም ስርጌ አለቶች /basement rocks / የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ አለቶች
ከእነርሱ በኋላ ለተፈጠሩ አለቶች የመሰረት አለቶች በመሆናቸው እስከ አሁን ከተሰሩት አለቶች ሁሉ ረዥም
እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው፡፡ የቅድመ ካምብራዊ ዘመን አለቶች በቅርብ ዘመን በተሰሩ አለቶች ውስጥ ተቀብረው
የሚገኙ ቢሆንም በላያቸው ላይ ባሉ አለቶች ሽርሽር /እጥበት ምክንያት/ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች
ማለትም በሰሜንና በመካከለኛው ትግራይ፣ በመተከል አሶሳ፣ በከፊል የኤሊባቡርና የአባይ ጭልጢት ሸለቆ፣
በመካከለኛው ሲዳሞ፣ በደቡብ ኦሞ እና በተወሰኑ የባሌና የምስራቃዊ ሐረርጌ ቦታዎች ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡
በአጠቃላይ በቅድመ ካምብራዊ ዘመን በኢትዮጵያ የሚከተሉት ዋና ዋና ስነመሬታዊ ድርጊቶች የተካሄዱበት
ዘመን ነው፡፡
በከፍተኛ የመሬት እንቅስቃሴ ምክንያት የትልልቅ ተራራዎች ግንባታ
ገመራዊ ተግባራት በተለይ ገሞራዊ አጐጥጓጭ ግይ/volcanic intrusion /
የአለቶች ልውጠት /metamorphism/ እና
ተከታታይ የሆነ የግጥግጦሽ ሂደቶች ናቸዉ፡፡
ለ. በዘመነ ጥንት ህይወት በኢትዮጵያ የተካሄዱ ስነመሬታዊ ድርጊቶች
በዘመነ ጥንት ህይወት ምንም አይነት ግንባታ ተራራ ያልተካሄደበት ዘመን ሲሆን ዋና የስነመሬታዊ ሂደት
የነበረው ተከታታይነት ያለው ግጥግጦሽ /continuous denudation/ ነበር፡፡ በዚህም የተነሣ በቅድመ ካምብራዊ
ዘመን የተሰሩት ትልልቅ ቅልብሽ ተራሮች /huge fold mountains/ ለከፍተኛና ለረዥም ጊዜያት ለቆየ
ግጥግጣሽና ለውሰድ ስቶታነት ተዳርገዋል፡፡ እንዲሁም የእነዚህ ቅልብሽ ተራራ ሰንሰለቶች ወደ ውስድ ሰቶታ
ወይም ቅድመ ካምብሪያዊ አለት ወለል ተመልሰዋል፡፡ በዘመነ ጥንት ህይወት በተካሄደው ተከታታይነት ያለው
ግጥግጦሽ ምክንያት የተፈጠሩት ደለሎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ለአለቶች ምስረታ የሚሆን የደለል ክምችት
ሳይቀር ከምስራቅ አፍሪካ /ከአፍሪካ ቀንድ/ ወደ ደቡብና ምስራቅ አቅጣጫ ተወስደው የደቡባዊ አፍሪካንና
የመካከለኛው ምስራቅን ባህርማና አህጉራዊ ደለል ፈጥረዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በዘመነ ጥንት ህይወት
በኢትዮጵያ የአለት ምስረታ ሄደት አልተካሄደም፡፡
በማእከለዊ ዘመን ጊዜ የአሁኑ የአፍሪካ ቀንድና የአረብ የመሬት ክፍል ተፈራራቂና ዘገምተኛ በሆነ የመሬት
ስርገትና መነሳት /የመሬት ከፍ ዝቅ/ ሂደት የታየበት ዘመን ነበር፡፡ በተመሣሣይ ሁኔታ ያለምንም የመሬት
መታጠፍና መሰንጠቅ በግንባታ ተራራ የታጀበ ከደቡብ ምስራቅ ወደ ሰሜን ምእራብ ያጋደለ የመሬት
አቀማመጥ ሁኔታ የተንፀባረቀበት ወቅት ነበር፡፡ ይህ የመሬት እርፋታ /subsidence / በአፍሪካ ቀንድ የጀመረው
በቀዳማዊ የማእከለ ዘመን ክፍለ ወቅት የዛሬ 225 ሚሊዮን አመት ገደማ አካባቢ ነበር፡፡ የደቡብ ምስራቅ
አካባቢ ቀስ በቀስ ሲሰምጥም የባህር ሞገድ ከሶማልያና ኦጋዴን አካባቢ ጀምሮ ቀስ በቀስ ወደ ሰሜን ምእራብ
በውሀማ አካል ተጥለቀለቀ፡፡ ይህ በምድር ዝቅ /ስጥመት/ የተጀመረዉና ከደቡብ ምስራቅ ወደ ሰሜን ምእራብ
የተደረገ እልፈት ባህር /transgration of sea / እስከ ሁለተኛው የማእከለ ዘመን ወቅት /Jurassic period /
ቀጥሏል፡፡ በዚያን ጊዜ የባህሩ ወሀ ወደ መሬታማው አካል እየተስፋፋ ሲሄድ ከውቅያኖሱ ወደ መሬት አካል
የተወሰደዉ አሸዋማ አፈር ቅድመ ካምፔራዊ አለቶች/ ስርጌ ስብጥርጥር አለቶችን/ በደለል አለበሳቸው፡፡
በተጨማሪም ከጊዜ ቆይታ በኋላ የውሃው ጥልቀት እየጨመረ ሲመጣ በቀድሞ አሸዋ ላይ ተጨማሪ ብሃ
/ድንጋይ/ (shale)፣ ጀሶ( gypsum) እና ኖራ (lime) በላዩ ላይ ሊደረብበት ችሏል፡፡ በጊዜ ብዛት የተደራረቡት
አሻዋና ኖራ እርስ በርሳቸው በመጠባበቅ አሸዋ ድንጋይ (sandstone) እና ኖራ ድንጋይ በቅደም ተከተል ከስር
ወደ ላይ በመሆን ሊፈጠሩ ችለዋል፡፡ እነዚህን የቆዩ የውሃማ ዝቃጭ (ደለል) ንጣፍ መጀመሪያ ላይ በተገኙበት
የቦታ ስም መነሻ በማድረግ በቅደም ተከተል የአድግራት አሸዋማ ድንጋይና የሂንታሉ የኖራ ድንጋይ ተብለው
ይጠራሉ፡፡
በመጨረሻው የማእከላዊ ዘመን ወቅት (cretaceous period) የአፍሪካ ቀንድ መሬት ወደ ላይ በመነሳቱ
ምክንያት የአብዛኛው መሬት ከባህር ወለል በላይ ከፍታ ጨምሯል፡፡ ይህ ሁኔታ ከሰሜን ምእራብ ወደ ደቡብ
ምስራቅ የባህር ሽሽ (sea regrasstion) ክስተትን አስከትሏል፡፡ በዚህ የባህር ሽሽ ሌላ የጀሶ፣ የበሃ (shale) እና
የአሸዋ በሂንታሎ የኖራ ድንጋይ ላይ ተደርበዋል፡፡
ይህ የላይኛው የመጨረሻ የማእከለ ዘመን የደለል (ዝቅጠት) አለት የላይኛዉ አሸዋማ ድንጋይ /upper
sandstone/ እየተባለ ይጠራል፡፡
በስተመጨረሻ የማእከለዊ ዘመን የብሱ የመሬት ክፍል ከውኃማዉ አካል ወደ ላይ ሲወጣ 3 ዋና ዋና ደለል
አለቶች በቅድመ ካምብራዊ አለቶች /ስርጌ ስብጥርጥር/ ላይ ተደርበው ሊፈጠሩ ችለዋል፡፡እነዚህ የጥንት
ባህርማ የደለል አለቶች
የመሬታማው አካል ከአልፋተ ባህርና ባህርሽሽ ቀድሞ በማገደሉ ምክንያትና ከዚያ በኋላ በተካሄደው የእልፈተ
ባህርና ባህረ ሽሽ አቅጣጫ ሂደት የአሸዋማ አለቶች እድሜና ውፍረት ከደቡብ ምስራቅ እስከ ሰሜን ምእራብ
ይለያያል፡፡
የአድግራት አሸዋማ ድንጋይ በእድሜውና በውፍረቱ በደቡብ ምስራቅ ትልቅ ሲሆን ወደ ሰሜን
ምእራብ አቅጣጫ ስንጓዝ እድሜውና ውፍረቱ እየቀነሰ ይመጣል፡፡
የላይኛው አሸዋማ ድንጋይ በደቡብ ምስራቅ ወፍራምና በእድሜው ትንሽ ሲሆን በሰሜን ምእራብ
ደግሞ በእድሜው ትልቅና በውፍረቱ ደግሞ ስስ ነው፡፡
የእልፈተ ባህር ክስተትና የማእከለ ዘመን ደለል አለቶች አብዛኛዉን የኢትዮጵያ ክፍል ያካተቱ (የሸፈኑ) ሲሆን
እስከ ማእከላዊ ትግራይና የምእራባዊ ከፍተኛ ቦታዎች ምእራባዊ ግድለት(slope) የከለሉ ነበር፡፡ አብዛኛወቹ
የማእከላዊ ዘመን ደለሌ አለቶች በስብአ ዘመን አለቶች ስር ተቀብረው ይገኛሉ፡፡ ሆኖም ግን የማእከዊ ዘመን
ቀደምት ባህርማ ደለሌ አለቶች በደቡብ ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች (ኦጋዴንና ሶማሊያ) በስፋት በመሬት ገጽ
ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌሎች ቦታዎችም ለምሳሌ በማከላዊ ትግራይ፣ በአባይ ጭልጠት (Gorges of Abay) እና በዋቢ
ሸበሌ ተጋልጠው ይገኛሉ፡፡
የማእከላዊ ዘመን የደለሌ አለቶች ስሪት በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የተካሄደበት ክፍለ ዘመን ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ መሬት ከቅድመ ካምብራዊ ዘመን ጀምሮ ለተለያዩ የውጫዊና ውስጣዊ ሃይሎች ተጋልጧል፡፡ ይህ
ቀጣይነት የነበረው የመሬት ግልጦሽ የኢትዮጵያን የመሬት አካል እንዲሰነጠቅ አድርጓታል፡፡ በነዚህ ትልልቅ ሰፊ
የመሬት ስንጥቆች በርካታ መጠን ያለው ትፍ (lava) ከመሬት ውስጥ ወደ ውጭ እንዲፈስ አስቻለው፡፡ በመሬት
ውጫዊ ክፍል የፈሰሰው ትፍ ተደራራቢ የሆኑ አለቶችን ፈጥሯል፡፡ እነዚህ ተደራራቢ አለቶች ክምሬ ረድፎች
ትፍ ወይም ገች አለት (Trappean series of lava or trap rock ) ወይም ኮተቤ (bassal) እየተባሉ ይጠራሉ፡፡
እነዚህ አለቶች በማአከለዊ ዘመን የተፈጠሩትን ውሃማ (ባህርማ) ደለል አለቶች በማልበስ የኢትዮጵያ ገብቶን
(plateau) ፈጠሩ፡፡
እነዚህ ዝቅጠቶች በሚገኙበት ቦታና በአፈጣጠራቸዉ ሂደት መሰረት በሚከተሉት ምድቦች ይከፈላሉ፡፡
እነዚህም፡-
ወንዛዊ ዝቅጠቶች / fluvial deposits /፡- በወንዝ ዳርቻ የሚገኙ ደለሎች
ሀይቃማ ደለሎች / lacustrine deposites/:- በሀይቅ ተሸፍኖ በነበረ ቦታ ላይ የሚፈጠሩ ደለሎች
ነፋሳዊ ክምቹ / aeolaine deposits /፡- በነፋስ አማካኝነት በዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የሚፈጠሩ
ደለሎች
የበረዶ ዝቅጠቶች / glacial deposit /፡- የበረዶ ክምችት
ባህርማ ደለሎች /marine deposits/፡- በባህር ተሸፍኖ በነበረ ቦታ ላይ የሚገኙ ደለሎች ይባላሉ፡፡
የኳታርነር ወቅት በመካካለኛውና በከፍተኛ ኬክሮስ ክልል ውስጥ የመጨረሻዉ የበሮደ ዘመን እየተባለ ሲጠራ
በሞቃታማው (ሃሩር) ክልል ደግሞ የዘመነ ዝናብ (Pluvial period) እየተባለ ይጠራል፡፡
225 ሚ
ዘመነ ጥንተ
ህይወት
ዘመን
ተግባር 2.3
1.በቅድመ ካምብራዊ ዘመን፣ በዘመነ ጥነተ ዘመን፣ በማእከላዊና በሰብአ ክፈለ ዘመን በኢትዮጵያ የተካሄዱ ስነመሬታዊ
ድርጊቶችን ዘርዝሩ፡፡
2.የስምጥ ሸለቆ አፈጣጠር ሂደትን አስረዱ፡፡
3.የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ያልተረጋጋዉ የኢትዮጵያ ክፍል ለምን ተባለ?
4.የኢትዮጵያን ስምጥ ሸለቆ የሚያሣይ ካርታ ሰርታችሁ ለአሰልጣኝ መምህራችሁ አሳዮ፡፡
አየር ቅጥ፡- አየር ቅጥ ማለት በአንድ አካባቢ ለብዙጊዜ ተደጋግሞ የሚከሰት አየር ጠባይ ነዉ፡ የአየር ጠባይ
ለረዥም ጊዜ ሲጠናቀር አየር ቅጥ በመባል ይታወቃል፡፡ አብዛኛዉን ጊዜ የአንድ አካባቢ የአየር ቅጥ የሚገለጸዉ
ለረዥም ጊዜ የተመዘገበን የአየር ሙቀት፣ የዝናብ መጠን፣ የአየር ርጥበት፣ የነፋስ ፍጥነት፣ ወዘተ መረጃን
ስታስቲካዊ ባህሪ ለምሳሌ ( አማካይ ዉጤት) በማስላት ነዉ፡፡
በዓለም ላይ ብዙ አይነት የአየር ቅጦች ይገኛሉ፡፡ እነዚህ የተለያዩ የአየር ቅጥ ሁኔታዎች የሚፈጠሩት
በየአካባቢዉ በሚለዋወጡ የአየር ቅጥ እና የአየር ጠባይ ይዘቶች ነዉ፡፡ የአየር ቅጥ እና የአየር ጠባይ ይዘቶች
የአንድን የተወሰነ ቦታ የካባቢ የአየር ቅጥ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ክስተቶች ናቸዉ፡፡ እነሱም ልከ ሙቀት፣
ዝናብ፣ የአየር ግፊት፣ ነፋስና የፀሀይ ብርሀን ናቸዉ፡፡ በሌላ በኩል እነዚህን የአየር ቅጥ ይዘቶች በተለያዩ ቦታዎች
ልዩነት እንዲኖራቸዉ የሚያደርጉ የአየር ቅጥ ተቆጣጣሪዎች አሉ፡፡ እነሱም የመሬት ከፍታ፣ የኬክሮስ ልዩነት፣
ከባህር መራቅ ወይም መቅረብ፣ የአየር ግፊት መለያየት፣ የዉቅያኖስ ሞገድ ወዘተ… ናቸዉ፡፡
ተግባር- 2.4
1.በአየር ቅጥና በአየር ጠባይ መካከል ያለዉን አንድነትና ልዩነት አስረዱ፡፡
2.እያንዳንዱ የአየር ቅጥ ተቆጣጣሪ በአየር ቅጥ የሚያሳድረዉን ተጽእኖ ምሳሌ በመስጠት አብራሩ፡፡
3.የእያንዳንዱን የአየር ቅጥ ይዘት ምንነት ግለጹ፡፡
4.የአየር ቅጥ በሰዉ ልጅ ኑሮ ላይ እንዴት ተጽእኖ እንደሚያሳድር አብራሩ፡፡
በአጠቃላይ የአየር ቅጥን በተለያዩ ምድቦች መከፋፈል ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከከል ጥቂቶቹን
ቀጥለን እንመለከታለን፡፡
ዉስብስብ የአየር ቅጥ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ ለመጠቀምና በእያንዳንዱ የአየር ቅጥ አይነት
ላይ የምናካሂደዉን የጥናት ሂደት ለማፋጠንና ለማቅለል ይረዳል
በአለም ላይ የሚገኙ የአፈር አይነቶችን፣የመልክአምድሮችን፣ የእጽዋትን፣ የእንስሳትንና የምጣኔ
ሀብታዊ እንቅስቃሴዎችን ስርጭት ለመለየትና ለማጥናት ይጠቅማል፡፡ እንዲሁም
የጥንታዊ ግሪኮች የአየር ቅጥ ክፍፍል ዘዴ ደካማ ጎኑ የዝናብ መጠንን እንደ መስፈርት ስለማይጠቀም
የክረምትና በጋ ወቅቶችን በትክክል ለመለየት አያስችልም፡፡
በአሁኑ ጊዜ የኮፐን የአየርቅጥ ክፍፍል ዘዴ ክልላዊ የአየር ቅጦችን ለማጥናት ከሁሉም የአየር ቅጥ ክፍፍል
ዘዴዎች የበለጠ በሰፊዉ ተቀባይነትን አግኝቷል፡፡ ይህም ሊሆን የቻለዉ የተጠቀመበት ዘዴ ቀላልና ግልጽ
ከመሆኑ በተጨማሪ በቀላሉ ሊገኙ የሚችሉ መረጃዎችን ማለትም ወርሀዊና አመታዊ አማካይ ልከ ሙቀትንና
የዝናብ መጠንን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ነዉ፡፡
የአምስቱ ዋናዋና የአየርቅጥ ክልሎች ምልክትና መግለጫ ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡
1.ገሞጂማ ርጥብ አየር ቅጥ /Tropical Moist Climate /A/
በዚህ የአየር ቅጥ ክልል የሁሉም ወሮች አማካይ ልከ ሙቀት መጠን ከ 18 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በላይ ነዉ፡፡
የሁሉም ወሮች ልከ ሙቀት ሞቃት ከመሆኑ የተነሳ እዉነተኛ የበረድ ወቅት /real winter season/ የለም፡፡ ይህ
የአየር ቅጥ ክልል በሶስት ንዑስ የአየር ቅጥ ክልሎች ይከፈላል፡፡ እነሱም፡
የገሞጂማ ስግር አየር ቅጥ /Tropical monsoon climate /Am/፣
ተግባር-2.5
1.በጥንታዊ ግሪኮች የአየር ቅጥ ክልሎች መካከከል ምን መሰረታዊ ልዩነት ተገነዘባችሁ?
2.እናንተ የምትኖሩት በየትኛዉ የአየርቅጥ ክልል ነዉ?
3.የእያንዳንዱን የኮፐን ንዑስ የአየር ቅጥ አይነቶችን የልከ ሙቀትና የዝናብ ሁኔታ አስረዱ፡፡
4.የጥንታዊ ግሪኮችና የኮፐን የአየርቅጥ ክፍፍል ዘዴ ልዩነት ምንድን ነዉ?
1.ኬክሮስ /latitude/:- ኢትዮጵያ የምትገኘዉ በ 30 ሰሜንና 150 ሰሜን ሞቃታማዉ ክልል ዉስጥ ነዉ፡፡
በዚህ ክልል ዉስጥ ፀሀይ በአናት ላይ ስለምትገኝ ሁሉም ቦታዎች ከፍተኛዉን የፀሀይ ጨረር ያገኛሉ፡፡ ይህ
ሁኔታ በኢትዮጵያ የሚከተሉት የአየር ቅጥ ሁኔታዎች እንዲከሰቱ አድርጓል፡፡
ከፍተኛ ልከ ሙቀት
ከፍተኛ የቀን ልከ ሙቀት ልዩነት
ዝቅተኛ አማካይ ወርሀዊና አመታዊ ልከ ሙቀት ልዩነት
ከሞላ ጎደል እኩል የቀንና ሌሊት ርዝመት ናቸዉ፡፡
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች የሚገኙት በአገሪቱ ማእከላዊ ክፍል ሲሆን ዝቅተኛ ቦታዎች ደግሞ በጠረፍ
አካባቢ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም አንድ ሰዉ ከጠረፉ የሀገሪቱ ክፍል ወደ ማእከላዊ ክፍል ሲጓዝ ሙቀት ይቀንሳል
የዝናብ መጠን ግን ይጨምራል፡፡ ይህም በኢትዮጵያ የልከ ሙቀትና ዝናብ መጠን ከቦታቦታ በከፍታ ምክንያት
ይለያያል ማለት ነዉ፡፡ በጥቅሉ ሲታይ ዝቅተኛ ቦታዎች ከፍተኛ ልከ ሙቀትና ዝቅተኛ ዝናብ መጠን
ሲኖራቸዉ ከፍተኛ ቦታዎች ደግሞ ዝቅተኛ ልከ ሙቀትና ከፍተኛ የዝናብ መጠን አላቸዉ፡፡
ምንም እንኳ ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ቦታዎች በተመሳሳይ ኬክሮስ ቢገኙም በከፍታ ልዩነት ምክንያት
የተለያየ መጠን ያለዉ ልከ ሙቀትና ዝናብ ሊያስመዘግቡ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በተመሳሳይ ከፍታ ነገር ግን
በተለያየ የኬክሮስ መስመር የሚገኙ ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ተመሳሳይ የሆነ ልከ ሙቀት ሊኖራቸዉ ይችላል፡፡
ከዚህ የምንረዳዉ ከፍታ ዋናዉ የኢትዮጵያ የአየር ቅጥ ተቆጣጣሪ መሆኑን ነዉ፡፡
3.የአየር ጠባይ ስርዓት (Weather system) / ወቅታዊ ነፋሶችና የከባቢ አየር ግፊት/
ፀሀይ በካንሰርና በካፕሪኮርን መስመሮች መካከል የምታደርገዉ አንጻራዊ እንቅስቃሴ ኢንተር ትሮፒካል
ግንኙነት ሰቅ /ITCZ/ ከምድር ሰቅ ወደ ሰሜንና ደቡብ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ በኢትዮጵያ የተለያዩ ነፋሶች
በተለያዩ ወቅቶች እንዲነፍሱ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ እነዚህ የአየር ጠባይ ስርአቶች በኢትዮጵያ የአየርግፊት፣
የልከ ሙቀትና የዝናብ መጠንን ልዩነት ያስከትላሉ፡፡
በኢትዮጵያ የአየር ቅጥ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚያሳድሩ ዋናዋና የአየር ጠባይ ስርአቶች፡-
የሰሜን ምስራቅ ምስራቄ ነፋሶች(North east trade winds) / በታህሳስ፣ በጥርና በየካቲት ወደ
ኢትዮጵ የሚነፍሱ ነፋሶች/
መሬት ሰቃዊ ምእራብጌ (Equatorial westerlies) /በሰኔ፣ በሀምሌና በነሀሴ ወደ ኢትዮጵያ የሚነፍሱ
ነፋሶች/
የኢትዮጵያ ልከ ሙቀት በዋናነት የሚወሰነዉ በከፍታና በኬክሮስ መገኛ ሲሆን የደመና ሽፋንም የራሱ
አስተዋጽኦ አለዉ፡፡ ከላይ እንደተገለጸዉ ኢትዮጵያ የምትገኘዉ ከፍተኛ ገቢ ጸሀይማ ጨረርና እያንዳንዱ ቦታ
በአመት ሁለት ጊዜ ቀጤ የጸሀይ ጨረር በሚያገኝበት የገሞጂማ ክልል ነዉ፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኛዉ የኢትዮጵያ
ክፍል ከፍተኛ ቦታ በመሆኑ ከፍታዉ የገሞጂማ ልከ ሙቀት ሁኔታ እንዳይኖረዉ ተጽእኖ አሳድሮበታል፡፡
በኢትዮጵያ የገሞጂማ ልከ ሙቀት ሁኔታ የሚከሰተዉ በአገሪቱ ዳርቻ /ድንበር/ አካባቢ ነዉ፡፡ በመሆኑም
ከኢትዮጵያ ዳርቻ ወደ ማእከላዊ ክፍል ስንጓዝ ከፍታ ስለሚጨምር ልከ ሙቀት ይቀንሳል፡፡ ከዚህ የምንረዳዉ
ኢትዮጵያ ሞቃትና ቀዝቃዛ ልከ ሙቀት የሚከሰትባት አገር መሆኗን ነዉ፡፡
ከፍታ በልከ ሙቀት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ ስላለዉ ኢትዮጵያን በተለያዩ የስነ-ምህዳር /ልከ ሙቀት/ ክልሎች
ለመከፋፈል ዋና መስፈርት ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በመሆኑም የከፍታና ልከ ሙቀትን ግንኙነት መሰረት በማድረግ
ኢትዮጵያ በአምስት የልከ ሙቀት /ስነ ምህዳር ክልሎች/ ትከፈላለች፡፡ እነሱም በረሀ፣ ቆላ፣ ወይናደጋ፣ ደጋና
ዉርጭ/ ቁር/ ናቸዉ፡፡
ዉርጭ ፡- የአልፓይን የአየር ቅጥ አይነት ነዉ፡፡ አመታዊ አማካይ የልከ ሙቀት መጠን ከ 100 ሴንቲግሬድ በታች
ነዉ፡፡ አመታዊ የዝናብ መጠን ደግሞ ከ 800 - 2000 ሚሊሜትር ይደርሳል፡፡ ይህ የአየር ቅጥ
ከፍታቸዉ ከ 3,300 ሜትር ከባህር ወለል በላይ በሆኑ ቦታዎች ይገኛል፡፡ ለምሳሌ የሰሜን፣ የባሌ፣
የጉና፣ የአማራሳይንትና የጮቄ ተራሮች በዉርጭ ልከ ሙቀት ክልል ይመደባሉ፡፡
ደጋ፡- ደጋ ከወይኖጌ አየር ቅጥ ጋር ተመሳሳይ ነዉ፡፡ ይህ የአየር ቅጥ ከፍታቸዉ ከባህር ወለል በላይ ከ 2,300 -
3,300 ሜትር በሆኑ ቦታዎች ይገኛል፡፡ አመታዊ የዝናብ መጠኑ ከ 1000 -2000 ሚሊሜተር ይደርሳል፡፡
የደጋ ክልል አካባቢዎች ለብዙ አመታት ህዝብ ሰፍሮ የቆየባቸዉ በመሆኑ የተነሳ በአፈር መሸርሸር፣
በንር ግጦሽና በደን መጨፍጨፍ ምክንያት መሬታቸዉ በከፍተኛ ሁኔታ የተጎዳ ነዉ፡፡
ወይና ደጋ፡- ከባህር ወለል በላይ ከ 1,500 -2,300 ሜትር ከፍታ ባለቸዉ ቦታዎች ይገኛል፡፡ አመታዊ አማካይ ልከ
ሙቀት በ 15 ና 20 ዲግሪሴንቲግሬድ መካከከል ሲሆን አመታዊ የዝናብ መጠን ደግሞ እስከ 1200
ሚሊሜትር ይደርሳል፡፡ የወይና ደጋ አካባቢዎች አብዛኛዉን የአገሪቱን የእርሻ መሬት የያዙ
በመሆናቸዉ ዋና የእህል /ጥራጠሬ/ ምርት አምራቾች ናቸዉ፡፡
ቆላ፡- ከፊል ክችሌ የአየር ቅጥ /semi arid climate/ አለዉ፡፡ ቆላ ከፍታቸዉ ከ 500 -1500 ሜትር ከባህር ወለል
በላይ በሆኑ ቦታዎች የሚገኝ የአየር ቅጥ ነዉ፡፡ አመታዊ አማካይ ልከ ሙቀት ከ 20-30
ዲግሪሴንቲግሬድ ነዉ፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን በ 410 ና 820 ሚሊሜትር መካከከል
ቢሆንም በምእራብ የጋምቤላ ቦታዎች እስከ 1600 ሚሊሜትር ይደርሳል፡፡ የዝናቡ መጠን ከአመት
አመት ከፍተኛ ልዩነት ያሳያል፡፡
በረሀ፡- በረሀ ማለት ጠራራና ክችሌ /hot and arid climate/ የአየር ቅጥ ነዉ፡፡ይህ የአየር ቅጥ ከፍታቸዉ
ከ 500 ሜትር በታች በሆኑ ዝቅተኛ ቦታዎች ይገኛል፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ከ 500
ሚሊሜትር በታች ሲሆን አመታዊ አማካይ ልከ ሙቀት ደግሞ ከ 30 ዲግሪሴንቲግሬድ በላይ ነዉ፡፡
በርሀ ብዙ ጊዜ የሚታወቀዉ በሀይለኛ ነፋስ፣ በከፍተኛ ልከ ሙቅት፣ በአነስተኛ ርጥበትና በትንሽ
የደመና ሽፋን ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ ልከ ሙቀት ስርጭት ከቦታ ቦታ እንዲለያይ ተጽእኖ ከሚያሳድሩ ተቆጣጣሪዎች አንዱ የደመና
ሽፋን ነዉ፡፡ የደመና ሽፋን መኖር ለመሬት የሙቀት መጋረጃ /መከላከያ/ ሆኖ ያገለግላል፡፡ ይህም ሲባል ቀን
ከፀሀይ ወደ መሬት የሚመጣዉ ሙቀት ሙሉ በሙሉ መሬት ላይ እንዳይደርስ ይከላከላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ
ሌሌት በሰማይ ላይ ደመና ካለ መሬት ቀን ከጸሀይ ያገኘችዉ ሙቀት ከመሬት ርቆ ወደ ከባቢ አየር እንዳይሄድ
ይከላከላል፡፡ ስለዚህ የደመና ሽፋን መኖር ወይም አለመኖር የኢትዮጵያ የልከ ሙቀት መጠን ከቦታ ቦታ ልዩነት
እንዲኖረዉ ያደርጋል ማለት ነዉ፡፡
የደመና ሽፋን በክረምት ወቅት / ከሰኔ እስከ ነሀሴ/ በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ልከ ሙቀት ሁኔታ ላይ ከፍተኛ
ተጽእኖ ያሳድራል፡፡ ምንም እኳን በክረምት ወቅት ኢትዮጵያ ቀጤ የፀሀይ ጨረር የምታገኝበት ወቅት ቢሆንም
የጸሀይ ጨረር በደመና ተዉጦ ስለሚቀር የከፍተኛ ቦታዎች የልከ ሙቀት መጠን አነስተኛ ነዉ፡፡ ሌላዉ
ኢትዮጵያ ቀጤ የፀሀይ ጨረር የምታገኝበት ወቅት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ነዉ፡፡ በዚህ
ወቅት በኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች የደመና ሽፋን ስለሌለ የልከ ሙቀት መጠን ከፍተኛ ነዉ፡፡ የኢትዮጵያ
ሰሜን ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች ዝቅተኛ ቦታዎች በመሆናቸዉና ንጹህ ሰማይ ስላላቸዉ
ልከ ሙቀታቸዉ ከሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች ጋር ሲወዳደር ከፍተኛ ነዉ፡፡
ተግባር- 2.6
1.ከፍታ የኢትዮጵያ የአየር ቅጥ ዋና ተቆጣጣሪ ለምን ተባለ?
2.እናንተ የምትኖሩበት ቀበሌ ከላይ ከተጠቀሱት የልከ ሙቀት ክልሎች ከየትኛዉ ይመደባል?
3.እናንተ የምትገኙበትን የልከ ሙቀት ክልል የአየር ቅጥሁኔታ፣የእጽዋትና የዱር እንስሳትን አይነት የሚገልጽ
የኢትዮጵያ የቀን አማካይ ልከ ሙቀት፡- የኢትዮጵያ የቀን አማካይ የልከ ሙቀት መጠን ከአመታዊ አማካይ
የልከ ሙቀት መጠን በእጅጉ ይበልጣል፡፡ የሙቀት ስርጭቱም ከቦታ ቦታ ከፍተኛ ልዩነት አለዉ፡፡ ለምሳሌ የቀኑ
ከፍተኛ የልከ ሙቀት መጠን በደቡብ ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች ከ 370 ሴንቲግሬድ በላይ
ሲሆን በከፍተኛ ቦታዎች ደግሞ ከ 10 -150 ሴንቲግሬድ ነዉ፡፡
የቀን ልከ ሙቀት መጠን ከወር ወርም ይለያያል፡፡ ለምሳሌ መጋቢት፣ሚያዚያና ግንቦት በሁሉም የአገሪቱ
ክፍሎች ከፍተኛ ልከ ሙቀት የሚመዘገብባቸዉ ወሮች ናቸዉ፡፡
ወርሀዊ አማካይ ልከ ሙቀት፡- የኢትዮጵያ ወርሀዊ አማካይ የልከ ሙቀት መጠን ከወር ወርና ከቦታ ቦታ ልዩነት አለዉ፡፡
በአብዛኛዎቹ ከፍተኛ ቦታዎች እስከ 00 ሴንቲግሬድ የሚደርስ ዝቅተኛ ወርሀዊ አማካይ ልከ ሙቀት ከህዳር እስከ
ጥር ወር ይመዘገባል፡፡ በጣም ዝቅተኛዉ ወርሀዊ አማካይ ልከ ሙቀት /00 ሴንቲግሬድ ወይም በታች/ በሰሜን ምእራብ
/በጎንደርና ጎጃም/፣በማእከላዊ /በሸዋ/ እና በደቡብ ምስራቅ/ በአሩሲና ባሌ/ ከፍተኛ ቦታዎች በጥር ወር ይመዘገባል፡፡
ከፍተኛዉ ወርሀዊ አማካይ የልከ ሙቀት መጠን ደግሞ ከ 300 ሴንቲግሬድ በላይ ሲሆን በምእራብ፣ በሰሜን
ምስራቅና በደቡብ ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች ከመጋቢት እስከ ሰኔ ይመዘገባል፡፡
አመታዊ አማካይ ልከ ሙቀት፡- በኢትዮጵያ አመታዊ አማካይ የልከ ሙቀት መጠን ከቦታ ቦታ ይለያያል፡፡
ዝቅተኛዉ አመታዊ አማካይ የልከ ሙቀት መጠን (ከ 100 ሴንቲግሬድ በታች) በሰሜን ምእራብ፣ በማእከላዊና
በደቡብ ምስራቅ ከፍተኛ ቦታዎች ይመዘገባል፡፡ ከፍተኛዉ አመታዊ አማካይ የልከ ሙቀት መጠን (ከ 350
ሴንቲግሬድ በላይ) ደግሞ በአገሪቱ የሰሜን ምስራቅ ዳርቻ /በዳሎል ዋድያቶ/ ይመዘገባል፡፡ የዳሎል /ዳናክል/
ዋዲያቶ በኢትዮጵያ በጣም ሞቃታማዉ ቦታ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ የቀን ልከ ሙቀት ልዩነት /daily range of temperature/ ፡-ታህሳስ፣ ጥርና የካቲት ጸሀይ
በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ አናት ላይ ስለምትሆን በኢትዮጵያ የበጋ ወቅት ነዉ፡፡ በዚህ ጊዜ ሙቀትን አፍኖ የሚይዝ
በቂ የደመና ሽፋን በሰማይ ላይ አይኖርም፡፡ በዚህ ምክንያት ከጸሀይ ወደ መሬት የሚደርሰዉ የሙቀት መጠን
ከፍተኛ ነዉ፡፡ ሌሊት ደግሞ ከመሬት ተንጸባርቆ የሚመለሰዉን ሙቀት አፍኖ የሚያስቀር የደመና ሽፋን
ስለማይኖር የገጸምድር የሙቀት መጠን ይቀንሳል፡፡ በዚህ የተነሳ በበጋ ወቅት የኢትዮጵያ የቀኑ ልከ ሙቀት
ልዩነት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ነዉ፡፡
አመታዊ የሙቀት ልዩነት፡- በኢትዮጵያ ከፍተኛዉ አመታዊ የሙቀት ልዩነት የሚከሰተዉ በዝቅተኛ ቦታዎች
ነዉ፡፡ ነገር ግን ከፍታ ሲጨምር የሙቀት ልዩነት ይቀንሳል፡፡
ተግባር- 2.7
1.አንተ / አንች በምትኖርበት/ በምትኖሪበት አካባቢ በጣም ከፍተኛና ዝቅተኛ ልከ ሙቀት የሚከሰትባቸዉን
ወሮች ተናገር/ተናገሪ፡፡
በኢትዮጵያ አራት ወቅቶች አሉ፡፡ አንዱ ወቅት ከሌላዉ የሚለየዉ በአመታዊ የዝናብ ስርጭትና በአየር ጠባይ
ስርዓት ነዉ፡፡ እነዚህ ወቅቶች፡-
በጋ /የደረቅ ወቅት/
በልግ /የአነስተኛ ዝናብ ወቅት/
ክረምት /የከፍተኛ ዝናብ ወቅት/ እና
ጸደይ / እንደ በልግ የአነስተኛ ዝናብ ወቅት/ ናቸዉ፡፡
1. በጋ፡- ከታህሳስ አስከ የካቲት የሚከሰት ደረቅ ወቅት ነዉ፡፡ በዚህ ወቅት ፀሀይ ከምድር ወገብ በስተሰሜን
አናት ላይ ትሆናለች፡፡ በበጋ ወቅት ከፍተኛ የአየር ግፊት በደቡብ ምእራብ እስያ ሲፈጠር ዝቅተኛ የአየር
ግፊት ደግሞ በማእከላዊ አፍሪካ ይፈጠራል፡፡ እንዲሁም ኢንተርትሮፒካል ግንኙነት ሰቅ ወደ ደቡብ
ይዛወራል፡፡ በዚህ ወቅት የሰሜን ምስራቅ ምስራቄ ነፋሶች (North east trade winds/ ከእስያ ደረቅ
መሬት ተነስተዉ ወደ ኢትዮጵያ ይነፍሳሉ፡፡ አነዚህ ነፋሶች ርጥበት አዘል ባለመሆናቸዉ በኢትዮጵያ
ደረቅ የአየር ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ በጋ በአብዛኛዉ የኢትዮጵያ ክፍል ደረቅ ወቅት ይሆናል፡፡
2.በልግ፡- ይህ ወቅት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ያለዉን ጊዜ ይሸፍናል፡፡ በኢትዮጵያ ከፍተኛዉ ልከ ሙቀት
የሚመዘገበዉ በዚህ ወቅት ነዉ፡፡ በዚህ ወቅት የሚፈጠረዉ ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ በጊዜና ቦታ
ይለያያል፡፡ በበልግ ወቅት ኢንተርትሮፒካል ግንኑነት ሰቅ በምድርሰቅ አካባቢ ይሆናል፡፡ በዚህ የተነሳ
ከህንድ ዉቅያኖስ የሚነሱ መሬት ሰቃዊ ምስራቄ ነፋሶች (Equatorial Easterlies) ወደ ኢትዮጵያ
ስለሚነፍሱ የደቡብ ምስራቅ ከፍተኛና ዝቅተኛ ቦታዎች ዝናብ እንዲያገኙ ያስችሏቸዋል፡፡
3. ክረምት ፡- ይህ ከሰኔ - መስከረም የሚከሰት የኢትዮጵያ ዋናዉ የዝናብ ወቅት ነዉ፡፡ በዚህ ወቅት ፀሀይ
ከምድር ወገብ በስተሰሜን አናት ላይ ትሆናለች፡፡ በመሆኑም ዝቅተኛ የአየር ግፊት በደቡብ ምስራቅ
እስያ ይፈጠራል፡፡ ከፍተኛ የአየር ግፊት ደግሞ በካፕሪኮርን መስመር አካባቢ በህንድና በአትላንቲክ
ዉቅያኖስ ላይ ይፈጠራል፡፡ በተጨማሪም ኢንተርትሮፒካል ግንኙነት ሰቅ ከኢትዮጵያ በስተሰሜንና
በሰሜን ምስራቅ በቀይ ባህርና በኤደን የባህር ወሽመጥ ላይ ይሆናል፡፡ በዚህ ምክንያት ዝናብ ጥል
ከሆኑት ከደቡብ ምሰራቅና ሰሜን ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች በስተቀር አብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ
ክፍሎች ከአትላንቲክ ዉቅያኖስ በሚነሱ መሬት ሰቃዊ ምእራብጌ ነፋሶች (Equatorial westerlies)
አማካኝነት ዝናብ ያገኛሉ፡፡
4.ጸደይ፡-ይህ ወቅት ከመስከረም እስከ ህዳር ያለዉን ጊዜ የሚሸፍን የአነስተኛ ዝናብ ወቅት ነዉ፡፡ በዚህ ወቅት
ከህንድ ዉቅያኖስ የሚነሱ መሬት ሰቃዊ ምስራቄ ነፋሶች (Equatorial Easterlies) ወደ ኢትዮጵያ
ስለሚነፍሱ የደቡብ ምስራቅ ከፍተኛና ዝቅተኛ ቦታዎች ለሁለተኛ ጊዜ ዝናብ ያገኛሉ፡፡
በጥቅሉ የኢትዮጵያ ዝናብ ስርጭት ሁኔታ ሲታይ ከፍተኛ አመታዊ የዝናብ መጠን እስከ 2700 ሚሊሜትር
የሚደርስ የሚመዘገበዉ በሀገሪቱ የደቡብ ምእራብ ከፍተኛ ቦታዎች ነዉ፡፡ ነገርግን ወደ ሰሜን፣ ሰሜን
ምስራቅና ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ስንጓዝ እየቀነሰ ይመጣል፡፡ ስእል 2.2 ትን ይመልከቱ፡
ተግባር- 2.8
1.ተራራ ዝል ዝናብ የኢትዮጵያ ዋና የዝና አይነት ለምን ሊሆን ቻለ?
2.በኢትዮጵያ አመታዊ የዝናብ መጠን ልዩነት መኖሩ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ ጉዳይና በተፈጥሯዊ አካባቢ
ላይ እያስከተለ ያለዉ ተጽእኖ ምንድን ነዉ?
3.ከፍተኛ የዝናብ መጠን የሚያገኘዉ የትኛዉ የኢትዮጵያ ክፍል ነዉ? ለምን ከፍተኛ የዝናብ መጠን ሊያገኝ
ቻለ?
4.አነስተኛ የዝናብ መጠን የሚያገኘዉ የትኛዉ የኢትዮጵያ ክፍል የትኛዉ ነዉ? ለምን አነስተኛ ዝናብ መጠን
ሊያገኝ ቻለ?
5.የኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ከዝቅተኛ ቦታዎች የበለጠ ዝናብ ለምን ሊያገኙ ቻሉ?
ይህ ክልል የሰሜን ምእራብ ከፍተኛ ቦታዎችንና የምእራብ ዝቅተኛ ቦታዎችን ያቀፈ ሲሆን በሀገሪቱ ትልቁ
የዝናብ ክልል ነዉ፡፡ ክልሉ ዝናብ የሚያገኘዉ ከአትላንቲክ ዉቅያኖስ ተነስተዉ ወደ ኢትዮጵያ በሚነፍሱ መሬት
ሰቃዊ ምእራብጌ ነፋሶች (Equatorial westerlies) አማካኝነት ነዉ፡፡
3.በጸደይና በልግ ዝናብ የሚያገኙ / autumn and Spring Rainfall regions/
እነዚህ አካባቢዎች የደቡብ ምስራቅ ከፍተኛና ዝቅተኛ ቦታዎች ናቸዉ፡፡ የክልሉ ዝናብ አምጭ ነፋሶች መሬት
ሰቃዊ ምስራቄ ነፋሶች (Equatorial Easterlies/ ኛቸዉ፡፡ አማካይ የዝናብ መጠኑ ከ 500 -1000 ሚሊሜተር
ይደርሳል፡፡ የደቡብ ምስራቅ ዝቅተኛ ቦታዎች በአመት ሁለት ጊዜ ዝናብ ስለሚያገኙ በአመት ሁለት ጊዜ
የዝናብ መገኛ ክልል / Duble rainfall region/ ይባላሉ፡፡ ስእል 2.3 ትን ይመልከቱ፡፡
ተግባር- 2.9
1.አንተ/ች የምትኖርበት / የምትኖሪበት ቀበሌ ወይም ወረዳ ከላይ ከተዘረዘሩት የዝናብ ክልሎች ከየትኛዉ
ይመደባል?
2. የምትኖርበት/የምትኖሪበት ቀበሌ/ወረዳ ዝናብ እንዲያገኝ የሚያስችለዉን የነፋስ አይነት ተናገሩ፡፡
3. እናንተ በምትኖሩበት አካባቢ ዝናብ አዘል ነፋስ እንዲነፍስ ያደረገዉ ምክንያት ምንድን ነዉ ትላላችሁ?
በጎሞጅማ ክልል የልከ ሙቀት መጠን ከፍተኛ ነዉ፡፡ በዚህ የተነሳ የአመቱ ወቅቶች የሚከፈሉት በዝናብ መጠን
በሚፈጠር ልዩነት መሰረት ነዉ፡፡ ስለዚህ በጎሞጅማ ክልል ሁለት ወቅቶች ብቻ ይኖራሉ ማለት ነዉ፡፡ እነርሱም
ርጥብ ዝናባማና ደረቅ ወቅቶች ናቸዉ፡፡ በኢትዮጵያም በበጋና በክረምት ወቅቶች መካከል ብዙም የሙቀት
መጠን ልዩነት በማይታይባቸዉ ስፍራዎች ተመሳሳይ አከፋፈል ይታያል፡፡ ጠቅለል ብሎ ሲታይ በኢትዮጵያ
በአመት አራት ወቅቶች አሉ፡፡ እነሱም ክረምት፣ ጸደይ፣ በጋና በልግ ናቸዉ፡፡
በዚህ የአየር ቅጥ ክልል በከፍታ ምክንያት የሞቃታማዉ ወር አማካይ የልከ ሙቀት መጠን ከ 10 ዲግሪ
ሴንቲግሬድ በታች ነዉ፡፡ አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠን ደግሞ በ 800 ና 2000 ሚሊሜትር መካከከል ነዉ፡፡
በከፍተኛ ቦታ የአየር ቅጥ ክልል የበጋ ወራቶች ደረቅ ናቸዉ፡፡ ይህ የአየር ቅጥ ክልል ከፍታቸዉ ከ 3500 ሜትር
በላይ በሆኑ ቦታዎች ለምሳሌ በሰሜን፣ በባሌና በአሩሲ ከፍተኛ ቦታዎች ይገኛል፡፡
ተግባር- 2.10
1.ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን የኢትዮጵያ የአየር ቅጥ ክልሎችን የዝናብና የልከ ሙቀት ሁኔታ አስረዱ፡፡
2.የኢትዮጵያን የአየር ቅጥ ክልሎች የሚያሳየዉን ካርታ በመመልከት የሚከተሉትን ቦታዎች ዋና የአየር
ቅጥ አይነት ግለጽ/ጭ፡፡
ሀ.የሰሜን ምስራቅና ደቡብ ዝቅተኛ ቦታዎች አየር ቅጥ ___________________
ለ.የደቡብ ምእራብ ከፍተኛ ቦታዎች አየር ቅጥ__________________
ሐ.የማእከላዊ፣ደቡባዊና ደቡብ ምስራቅ ከፍተኛ ቦታዎች አየር ቅጥ______________
መ.የኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ አየር ቅጥ_________________
የአየር ቅጥ ለዉጥ (climate change) ስንል ግን አማካይ የአየር ቅጥ ይዘቶች ማለትም የአየር ሙቀት፣ የዝናብ
መጠን፣ የአየር ርጥበት፣ የነፋስ ፍጥነት፣ ወዘተ በቀጣይነት መጨመርን ወይም መቀነስን ማለት ነዉ፡፡ ለምሳሌ
የምድራችን አማካይ አመታዊ የአየር ሙቀት በአለፉት መቶ አመታት ጊዜ ዉስጥ እየጨመረ መጥቷል፡፡
የመሬት አየር ቅጥ በተፈጥሯዊ ሂደት ሁልጊዜም ተለዋዋጭ ነዉ፡፡ ዛሬ አለምን በከፍተኛ ሁኔታ እያስሰበ ያለዉ
በሰዉልጅ ድርጊት አማካኝነት የአየር ቅጥ ለዉጥ በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱ ነዉ፡፡ በሁሉም
የአለም ክፍል እየታየ ያለዉ የአየር ቅጥ ለዉጥ በሳይንቲስቶች ተጠንቶ መንስኤዉን ለማወቅ ተሞክሯል፡፡
በጥናቱ ዉጤት መሰረት የአየር ቅጥ ለዉጥ መንስኤዎች በሁለት ይመደባሉ፡፡ እነሱም ሰዉ ሰራሽና ተፈጥሯዊ
ምክንያቶች ናቸዉ፡፡
1.ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች
የአየር ቅጥ ለዉጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ በርካታ ተፈጥሯዊ ደንቢዎች አሉ፡፡ ከነዚህ መካከከል ዋና ዋናዎቹ
አህጉራዊ ሽርተታ (continental drift)፣ ገሞራ (volcano)፣ የዉቅያኖስ ሞገድ (ocean currents)፣ ወዘተ…
ናቸዉ፡፡
ሀ. አህጉራዊ ሽርተታ
ዛሬ የምናዉቃቸዉ አህጉራት የተመሰረቱት አንድ አህጉር ብቻ ከነበረዉ ዉህድ አህጉር /pangea/ መከፋፈል
ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነዉ፡፡ ዉህድ አህጉር ወደተለያዩ እህጉራት መከፋፈል የጀመረዉ ከሚሊዮኖች አመታት
በፊት ነዉ፡፡ ይህ የአህጉራት መከፋፈል የመሬትን ገጽታ በመለዋወጥና የአህጉራትንና የዉኃማ አካላትን መገኛ
/አቀማመጥ/ በመቀየር በአየር ቅጥ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አሳድሯል፡፡ በተጨማሪም የአህጉራት ክፋፍል የነፋስና
የወቅያኖስ ሞገዶችን አቅጣጫ በማስቀየር ለአየር ቅጥ መለወጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡
ለ. ገሞራ
እሳተገሞራ ሲፈነዳ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የሰልፈር ዳይአክሳይድ (so2 )፣ ወሀ ላቮት (water vapour)፣ የአቧራ
ብናኝና አመድ ወደ ከባቢ አየር ይገባል፡፡ ምንም እንኳ የገሞራ ፍንዳታ ለትንሽ ቀናት የሚቆይ ቢሆንም በአንድ
ጊዜ ወደ ከባቢ አየር የሚገባዉ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ጋዝና አመድ ለብዙ አመታት በአየር ቅጥ ላይ ተጽእኖ
ያሳድራል፡፡ በተለይምጋዞችና የአቧራ ብናኞች በአናቶስፊር (stratosphere) ዉስጥ በመከማቸትና ከፀሀይ ወደ
መሬት የሚመጣዉን የጨረር ሐይል በማገድ በመሬት ላይ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እንዲከሰት ያደርጋሉ፡፡
ሐ. የዉቅያኖስ ሞገድ
የዉቅያኖስ ሞግድ የአየር ቅጥ ስርአት ዋና አካል ነዉ፡፡ የዉቅያኖስ ሞገድ ልከ ሙቀትን ከቦታ ቦታ በማንቀሳቀስ
የአየር ቅጥ ለዉጥ ያስከትላል፡፡ አብዛኛዉ የዉቅያኖስ ሙቀት በዉሀ ላቮት መልክ ወደ ከባቢ አየር በመሄድ
አፍላሽ ጋዝ (Green house gas) ይሆናል:: በተጨማሪም ከወቅያኖስ ወደ ከባቢ አየር የሚገባዉ የዉሀ ላቮት
ለደመና ስሪት አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ደመናዉ ደግሞ ከፀሀይ የሚመጣዉን የሙቀት ጨረር መሬት ላይ
እንዳይደረስ በማድረግ በመሬት ላይ ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታን ያስከትላል፡፡
ከፀሀይ የሚመነጨዉና ወደ መሬት የሚመጣዉ አብዛኛዉ ባለአጭር ሞገድ ጨረር (short wave solar
radation) በከባቢ አየር ዉስጥ ዘልቆ በማለፍ የመሬትን ገጽ እንዲሞቅ ያደርጋል፡፡ መሬትም በበኩሏ የራሷን
ባለረዥም ሞገድ ጨረር (long wave radation) በማመንጨት ወደ ከባቢ አየርና ወደ ህዋ መልሳ ትረጫለች፡፡
በከባቢ አየር የሚገኙ አንዳንድ ጋዞች ከመሬት የሚመነጨዉን የረዥም ሞገድ ጨረር ዉጦ በማስቀረትና መልሶ
በመርጨት የመሬትን ገጽና አቅራቢያዉ የሚገኘዉን አየር ከፍ ያለ ሙቀት እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ይህ ተፈጥሯዊ
ክስተት የአፍላሽ ጋዞች ተጽእኖ /ዉጤት/ በመባል ይታወቃል፡፡ ስእል 2.4 ትን ተመልከቱ፡፡
ምንም እንኳ ከባቢ አየር በአብዛኛዉ (99 በመቶ) የናይትሮጅን እና ኦክስጅን ድብልቅ ቢሆንም ከመሬት
የሚመነጨዉን ባለረዥም ሞገድ የጨረር ሀይል በይበልጥ ዉጦ የማስቀረት ባህሪ ያላቸዉና ለተፈጥሯዊዉ
የአፍላሽ ጋዞች ዉጤት አስተዋጽኦ የሚያደርጉት በአነስተኛ መጠን የሚገኙት የዉሀ ተን፣ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ፣
ሚቴን፣ ናይትረስ አክሳይድ፣ኦዞን፣ ወዘተ ሲሆኑ እነዚህ ጋዞች አፍላሽ ጋዞች /Green house gases/ በመባል
ይታወቃሉ፡፡
ለ. ሰዉ ሰራሽ የአፍላሽ ጋዝ ክምችትና ዉጤት
ከህዝብ ቁጥር ማደግና ከኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀዉ የአፍላሽ ጋዝ
መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ነዉ፡፡ለምሳሌ ከኢንዱስትሪዉ አብዮት በፊት ከነበረዉ ጋር
ሲነጻጸር በአሁኑ ጊዜ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ፣ ሚቴንና ናይትረስ ኦክሳይድ በከፍተኛ መጠን ጨምረዉ ይገኛሉ፡፡
ፍሎሮክሎሮካርቦንስ (CFC)፣ ፐርፍሎሪኔትድካርቦን (PFCS)፣ ሀይድሮፈለሮ ካርቦን እና
ሰልፈርሄክሳይፈሎራይድ (SF6 ) በመባል የሚታወቁ ጋዞች ከሰባ አመታት በፊት ፈጽሞ በከባቢ አየር ዉስጥ
ያልነበሩና ሙሉ በሙሉ ሰዉ ሰራሽ የኢንዱስትሪ ኬሚካሎች ናቸዉ፡፡
የአፍላሽ ጋዞች ክምችት በከባቢ አየር ዉስጥ እየጨመረ መምጣት የአፍላሽ ጋዞች ዉጤት እንዲጠናከር ወይም
እንዲጎለብት በማድረግ የአለማችንን መሞቅና የአየር ቅጥ ለዉጥ ሊያስከትል እንደሚችል ይታመናል፡፡
የአፍላሽ ጋዝ ምንጮች
የአፍላሽ ጋዞች በከባቢ አየር ዉስጥ አንዴ ከገቡ ለብዙ አመታት የመቆየት ባህሪ አላቸዉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
ከመሬት የሚመነጨዉ ረዥም ሞገድ የጨረር ሀይልን ዉጦ የማስቀረት ችሎታቸዉ የተለያየ ነዉ፡፡ የአፍላሽ
ጋዝ ምንጭ የሆኑ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ብዙና የተለያዩ ናቸዉ፡፡ ከዚህ ቀጥሎ በዋናናት የሚታወቁት
የሶስቱን አፍላሽ ጋዞች ማለትም ካርቦንዳይኦክሳይድ፣ ሚቴንና ናይትረስ ኦክሳይድ ምንጮችን ለማብራራት
ተሞክሯል፡፡
ሀ.ካርቦንዳይኦክሳይድ
የተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች የሀይል ፍላጎትን ለማሟላት ሲባል የቅሬተ አካል ነዳጅ
ማለትም የከሰል ደንጋይን፣ ዘይትን፣ የተፈጥሮ ጋዝን መጠቀም ዋናዉ የካርቦንዳይኦክሳይድ ምንጭ ነዉ፡፡
የኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጫ ጣቢያዎች፣ ኢንዱስትሪዎች፣ መኪኖች፣ አዉሮፕላኖች፣ ባቡሮችና መርከቦች፣
ቤት ዉስጥ፣ የንግድና የመንግስት ተቋማት የሀይል ፍላጎታቸዉን የሚያሟሉት የቅሪተ አካል ነዳጅን
በመጠቀም ነዉ፡፡ የደን መጨፍጨፍ ሌላዉ አይነተኛ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ምንጭ ነዉ፡፡
ከኢንዱስትሪዉ አብዮት ጀምሮ የቅሪተ አካል ፍጆታ በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ላይ ነዉ፡፡
ለ.ሚቴን (CH4)
ሰዉ ሰራሽ ሚቴን ወደ ከባቢ አየር የሚገባዉ ከቆሻሻ አያያዝ፣ ከእርሻ እንቅስቃሴና ከቅሪተ አካል ነዳጅ
የአመራረት አጠቃቀምና የስርጭት ሂደት ነዉ፡፡
ካርቦን አዘል ቁስ አካል ኦክስጅን በሌለበት ሁኔታ በባክተሪያ አማካኝነት ሲበሰብስ ወይም ሲፈራርስ ሚቴን
ይፈጥራል፡፡ ለምሳሌ ደረቅ ቆሻሻ የሚጠራቀምባቸዉ ጉድጓዶች በሚቴን አመንጭነታቸዉ ይጣወቃሉ፡፡
ከኢንዱስትሪና ከቤት ዉስጥ የሚወጣ ፍሳሽ ቆሻሻ፣ የሴፕቲክታንክና የጉድጓድ ሽንት ቤቶች የሚቴን ምንጭ
ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ የተፈጥሮ ጋዝ አመራረት፣አጠቃቀምና የስርጭት ሂደት ሚቴንን ያመነጫል፡፡
የተረጋጋ የአየር ቅጥ ዘላቂነት ላለዉ ልማት አንዱ ቅድመ ሁኔታ ነዉ፡፡ ባለፉት 10 ሽህ አመታት የመሬት
አማካይ አመታዊ የአየር ሙቀት ብዙ ለዉጥ ያልታየበትና የተረጋጋ እንደነበረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ከላይ እንደተገለጸዉ በአፍላሽ ጋዞች መጨመር ምክንያት ሊከሰት የሚችለዉ የአየር ቅጥ ለዉጥ የተለያዩ
ክስተቶችን ያስከትላል፡፡ ከነዚህ መካከል ዋናዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
ሀ. የአለም አማካይ የሙቀት መጠን መጨመር /Global warming/፡- የአለም የሙቀት መጠን መጨመር
ሲባል የገጸምድር አማካይ የሙቀት መጠን መጭመር ማለት ነዉ፡፡ በ 2007 በበየነመንግስታቱ የአየር ቅጥ
ለዉጥ ፓኔል / Intergovernmental panel on climate change / የተዘጋጀዉ አራተኛዉ የአየር ቅጥ ለዉጥ
ግምገማ ሪፖርት እንደሚያሳየዉ በ 20 ኛዉ ክፍለ ዘመን የገጸ-ምድር አማካይ የሙቀት መጠን በ 0.74
ዲግሪ ሴልሸስ ጨምሯል፡፡ ይህ በ 20 ኛዉ ክፍለ ዘመን አጋማሽ የተከሰተዉ የአለም አማካይ የሙቀት
መጠን መጨመር ዋና መንስኤዉ በከባቢ አየር ዉስጥ የአፍላሽ ጋዞች ክምችት መጨመር ነዉ፡፡ ይህም
በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የሚያስከትለዉ ጉዳት እንዲሁ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡
ለ. የበረሀማነት መስፋፋት፡- በአየር ቅጥ ለዉጥ ምክንያት የሰፈራ ቦታዎች፣ የእርሻ ቦታዎች፣ የሳር ምድሮች፣
ርጥብ መሬት፣በደን የተሸፈኑ ቦታዎች፣ወዘተ ወደ በረሀማ አካባቢ ሊለወጡ ይችላሉ፡፡
ሐ. ድርቅ፡- የአየር ቅጥ ለዉጥ ድርቅ በተደጋጋሚ እንዲከሰት ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ ለድርቅ ተጋላጭ
በሆኑ አካባቢዎች ድርቅ በ 3 እና 8 አመታት መሀል እንደገና ይከሰታል
መ. የባህር ወለል ከፍ ማለት፡- ዉሀ ሲሞቅ ስለሚለጠጥ የበለጠ ቦታ ይዛል፡፡ ይህ ደግሞ ዉቅያኖስ ሲሞቅ
የባህር ወለል ከፍ እንደሚል ያስረዳል፡፡ በዚህ ክፍለ ዘመን መጨረሻ በአየር ቅጥ ለዉጥ የተነሳ አለምአቀፍ
አማካይ የባህር ወለል ከ 18 -59 ሴንቲሜተር ከፍ እንደሚል ይጠበቃል፡፡ የባህር ወለል ከፍ ማለት ትንንሽ
ደሴቶችንና በባህር ዳርቻ የሚገኙ ከተሞችን በጎርፍ እንዲጥለቀለቁ ሊያደርግ ይችላል፡፡
ሠ. የገሞጅማ ሰቅ መገኛ መስፋፋት፡- በአየር ቅጥ ለዉጥ የተነሳ የገሞጅማ ሰቅ ከትክክለኛ መገኛዉ ከአንድ
ዲግሪ ባላነሰ መጠን ወደ ሰሜናዊና ደቡባዊ ንፍቀ ክበቦች ሊሰፋ እነደሚችል ይጠበቃል፡፡
ረ. የአለም አቀፍ ነፋሶች አቅጣጫ መቀየር፡- የአለም አቀፍ ሙቀት መጠን ከጨመረ ጀት-ስትሪምስ /Jet
streams/ ይዳከማሉ፣ አለም አቀፍ ነፋሶችም መደበኛ አቅጣጫቸዉን እንዲቀይሩ ይገደዳሉ፡፡ ይህ ክስተት
መደበኛዉን ወቅታዊ የዝናብ ስርጭት ያናጋል፡፡
ሰ. የብዘኅ ህይዎት መጥፋት፡- የአለም አቀፍ ሙቀት መጠን መጨመር አንዳንድ ህይዎት ያላቸዉን ነገሮች
ከምድር እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ የአለም አቀፍ አማካይ የሙቀት መጠን አሁን ከአለዉ መጠን በሁለት ዲግሪ
ሴልሸስ ከጨመረ ሁሉም ህይዎት ያላቸዉ ነገሮች ወደ መጥፋት ደረጃ የሚያደርስ አደጋ /ስጋት/ ላይ
ይወድቃሉ ተብሎ ይገመታል፡፡
ተግባር- 2.11
1. በአካባቢያችሁ የአየር ቅጥ ለዉጥ መከሰቱን ታዉቃላችሁ? ታዉቁ ከሆን ምን አይነት የአየር ቅጥ ለዉጥ
ተከስቷል?
2. በአካባቢያችሁ የአየር ቅጥ ለዉጥ በተፈጥሮ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ያስከተላቸዉን ጉዳቶች ዘርዝሩ
3. በአካባቢያችሁ የአሁኑ የዝናብና የሙቀት መጠን ከቀደምት አመታት ጋር ሲነጻጸር ልዩነት አለዉ?
ወላጆቻችሁን ወይም ሌሎች ታላላቅ ሰዎችን ጠይቃችሁ ሪፖርት አቅርቡ፡፡
4. በአካባቢያችሁ በአየር ቅጥ ለዉጥ ምክንያት የዉሀ መጠናቸዉ የቀነሰ ወይም የደረቁ ወንዞች፣ሀይቆችና
ረግረጋማ ቦታዎች አሉ? መልሳችሁ አዎ ከሆነ ስለሁኔታዉ ሪፖርት ጽፋችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ
አቅርቡ፡፡
ተግባር- 2.12
1. በአካባቢያችሁ የአየር ቅጥን ለዉጥ ለመከላከል በህብረተሰቡና በመንግስት የተሰሩ
ስራዎችን ዘርዝሩ፡
2. የአየር ቅጥ ለዉጥን ለመከላከል የእናንተ ድረሻ ምን መሆን አለበት ብላችሁ ታስባላችሁ?
3. የአየር ቅጥ ለዉጥን ለመከላከል የአደጉ አገሮች ምን ማድረግ አለባቸዉ ብላችሁ ታስባላችሁ?
ታዳጊ አገሮችስ?
ስርዓተ ምኅዳር የሚለዉን ቃል መጀመሪያ ያፈለቀዉ እንግለዛዊ የሰነ ምዳር ተመራማሪ A.G Tansley እ.ኤ.አ
በ 1935 ሲሆን ትርጉሙንም እንዲህ ሲል ገልጾታል “ስርአተ ምህዳር በአንድ ተፈጥሯዊ አካባቢ እጽዋት፣
እንስሳት፣ ሌሎችም ህይወት ያላቸዉና ህይወት የሌላቸዉ ነገሮች የህይወት ዑደት ተሳስሮ የሚገኝበት
ተፈጥሯዊ ስርዓት ነዉ፡፡” በአንድ አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ህይወት ያላቸዉና ህይዎት የሌላቸዉ ነገሮች
እርስበርሳቸዉ ግንኙነት / መስተጋብር/ ያደርጋሉ፡፡ ግንኙነታቸዉም ተደጋግፈዉ እንዲቆዩ ይረዳቸዋል፡፡
ስርዓተ ምኅዳሮች በስፋታቸዉ ይለያያሉ፡፡ አንዳንዶቹ ትንሽ ቦታ የሸፈኑ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ደግሞ በጣም ሰፊ
ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ የአፍሪካ የበረሀ ስርዓተ ምህዳርና የበራዚል ዶፍማ ደን (rainforest) ስፊ ቦታ ስለያዙ በጣም
ሰፊ ስርዓተ-ምህዳሮች ናቸዉ፡፡
የስርዓተ ምኅዳር አካላት ህይወት ያላቸዉና ህይወት የሌላቸዉ ተብለዉ በሁለት ይመደባሉ፡፡ ህይወት የሌላቸዉ
የስርዓተ ምኅዳር አካለት ዉሀ፣ ማእድናት፣ የፀሀይ ብርሀን፣ አየር፣ አየር ቅጥና አፈር ሲሆኑ ህይወት ያላቸዉ
የስርዓተ ምኅዳር አካላት ደግሞ በተፈጥሯዊ መጠለያ የሚኖሩ ሁሉንም ህይወት ያላቸዉን ነገሮች
ያጠቃልላል፡፡ ህይወት ያላቸዉ አካላት ምግባቸዉን ለማግኘት በሚጠቀሙበት መንገድ መሰረት በሶስት ዋና ዋና
ምድቦች ይመደባሉ፡፡ እነሱም አምራቾች (producers)፣ ተመጋቢዎች (consumers) እና አፈራራሾች
(decomposers) ናቸዉ፡፡
አምራቾች፡- እነዚህ በብርሀን ዝግጅ /ብርሀን ቅመም/ (photosynthesis) ሂደት የራሳቸዉን ምግብ የሚያዘጋጁ
አረንጓዴ ተክሎችና ትንንሽ ዉሀ አቅላሚዎች/ Algae/ ናቸዉ፡፡
ተመጋቢዎች፡- እነዚህ ደግሞ የራሳቸዉን ምግብ ማዘጋጀት የማይችሉና የሚፈልጉትን ምግብ ለማግኘት
በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የአምራቾች ጥገኛ ሆነዉ የሚኖሩ ናቸዉ፡፡ በአምራቾች የተዘጋጁ ቁሳዊ ነገሮችን
እየተመገቡና አየተጠቀሙ የሚኖሩ ናቸዉ፡፡ ተመጋቢዎች በአመጋገባቸዉ ልማድ መሰረት በሶስት ይከፈላሉ፡፡
እነሱም እጸ በል (Herbivorous)፣ ስጋ በል (carnivorous ) እና ሁሉን በል /ስጋና እጽዋት/ (omnivorous)
ናቸዉ ፡፡
አፈራራሾች / decomposers /:- እነዚህ ደግሞ የሞቱና የበሰበሱ ቅሪት አካላትን የሚመገቡና ህያዉ ቁስ-አካልን
/organic matter/ ወደ ህይወት የሌለዉ ቁስ-አካል /inorganic matter/ የሚቀይሩ ህይወት ያላቸዉ ነገሮች
ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ ባክተሪያዎች የሞቱ ቁስ አካላትን አፈራራሾች ናቸዉ፡፡
ተግባር-2.13
በአካባቢያችሁ ከሚገኙ እንስሳት መካከል እጸ በል፣ ስጋ በልና ሁሉን በል የሆኑትን ለይታችሁ ዘርዝሩ፡፡
የስርዓተ- ምኅዳር አካላት ከፍተኛ መደጋገፍ ወይም ቁርኝት አላቸዉ፡፡ ለምሳሌ እጽዋት በአግባቡ የሚያድጉት
ለም አፈር ሲኖር ነዉ፡፡ የእጽዋት ቅጠል ሲረግፍ መሬት ላይ ወድቆ በመበስበስ የአፈሩን ለምነት ይጨምራል፡፡
እንስሳት ለህይወታቸዉ መቀጠል እጽዋት ያስፈልጋቸዋል፡፡ የእንስሳት ቅሪት አካላት ደግሞ ለአፈር ለምነት
በእጅጉ አስፈላጊ ናቸዉ፡፡ የስጋ በል እስሳት ህልዉና የተመሰረተዉ በቅጠልና ሳር በል በሆኑ እንስሳት ህልዉና ላይ
ነዉ፡፡ ሳር በልና ስጋ በል እንስሳት ህልዉናቸዉ የተመሰረተዉ በአካባቢዉ በሚገኙ እጽዋትና እንስሳት ላይ ነዉ፡፡
ስለዚህ በአንድ ስርዓተ-ምህዳር ዉስጥ የሚገኙ የተለያዩ አካላት መካከል ከፍተኛ የመደጋገፍና የቁርኝት ስርአት
በመኖሩ የአንዱ ህልዉና ወይም ጉዳት በሌላዉ ላይ ቀጥተኛ ወይንም ቀጥተኛ ያልሆነ ተጽእኖ ያስከትላል፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአለማችን በተለያዩ ምክንያት እጽዋት እየወደሙና እየተጨፈጨፉ ይገኛሉ፡፡ ማእድናት በብዛት
ይወጣሉ፡፡ መሬትም በከፍተኛ ደረጃ ይታረሳል፡፡ ዉሀም ለተለያዩ አገልግሎቶች ይዉላል፡፡ የሰዉ ልጅ ፍላጎትና
የአኗኗር ዘይቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተለወጠና እያደገ በመምጣቱ በስርዓተ ምህዳር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ
አየፈጠረ ነዉ፡፡
የስርዓተ ምህዳርን ዓይነት የሚወስኑ ዋና ዋና ደንቢዎች ልከ ሙቀት፣ ዝናብ፣ የአፍር አይነት፣ የኬክሮስ መገኛና
ከፍታ ናቸዉ፡፡ ከነዚህ ደንቢዎች መካከከል የሰርዓተ ምህዳርን አይነት በመወሰን ረገድ አየር ቅጥ የሚጫወተዉ
ሚና በእጅጉ ከፍተኛ ነዉ፡፡ እነዚህ ደንቢዎች በአካባቢያቸዉ ከሚገኙ ህይዎት ያላቸዉ ነገሮች ጋር
የሚያደርጉት መስተጋብር ለተለያዩ የተፈጥሮ ስርዓተ ምህዳሮች መኖር ምክንያት ሆኗል፡፡
የተፈጥሮ ስርተ ምህዳሮች ከሚገኙበት የመሬት ክፍል አኳያ ሲታዩ የዉሀ ዉስጥ ስርዓተ ምህዳሮችና ምድራዊ
ስረዓተ ምህዳሮች ተብለዉ በሁለት ይመደባሉ፡፡ በዉሀ ዉስጥ የሚገኙ ስርዓተ ምህዳሮች የዉሀ ዉስጥ ስርዓተ
ምህዳሮች ተብለዉ ይጠራሉ፡፡ ዉቅያኖሶች፣ ሀይቆች፣ወንዞችና ኩሬዎች የዉሀ ዉስጥ ስርዓተ ምህዳር
ምሳሌዎች ናቸዉ፡፡
በየብስ ላይ የሚገኙ ስርዓተ ምህዳሮች ደግሞ ምድራዊ ስርዓተ ምህዳሮች ይባላሉ፡፡ እነዚህ ስርዓተ ምህዳሮች
ህይወት ያላቸዉና ህይዎት የሌላቸዉ የስርዓተ ምህዳር አካላት በሚያደርጉት መስተጋብር መሰረት በስድስት
ዋናዋና የስርዓተ ምህዳር ክልሎች ይመደባሉ፡፡ እነሱም በርሀ / desert /፣ ጮቄ/ tundra/፣ የሳር ምድር/
grassland /፣ ቅጠል አርጋፊ ደን /deciduous forest /፣ የታይጋ ደን / taiga or coniferious forest / አና
ጎሞጅማ ዶፍ ጫካ / tropical rain forest / ናቸዉ፡፡
እያንዳንዱ ስርዓተ ምህዳር የራሱ የሆነ የአየር ቅጥ፣ የአፈር፣ የእጽዋትና የዱር እንስሳት አይነት አለዉ፡፡
እንዲሁም እያንዳነዱ ስርዓተ ምህዳር በተለያዩ የአለም ክፍሎች ሊገኝ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የበረሀ ሥርዓተ
ምህዳር በሰሜን አሜሪካ፣ በአፍሪካ፣ በደቡብ አሜሪካ፣ በእስያና በአዉስትራሊያ ይገኛል፡፡
ሀ.በረሀ
አንድን ቦታ በረሀ የሚያስብለዉ ዋናዉ ነገር የዝናብ እጥረት ነዉ፡፡ በረሀ ስንል አመታዊ አማካይ የዝናብ መጠኑ
ከ 25 ሴንቲሜትር በታች የሆነን ማንኛዉንም ቦታ ማለት ነዉ፡፡ ልከ ሙቀቱም በቀን ከ 25-40 ዲግሪ
ሴንቲግሬድና በላይ ሲሆን በሌሊት ደግሞ ከ 0 ዲ.ሴ በታች ይቀዘቅዛል፡፡ በበረሀማ ቦታዎች ብዙ የእጽዋትና
የእንስሳት ዝርያዎች ቢኖሩም የእያንዳንዱ ዝርያ ብዛት ግን አነስተኛ ነዉ፡፡ የእጽዋት ዝርያዎቹም ደረቅ፣
በጣም ሞቃትና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታን መቋቋም የሚችሉ ናቸዉ፡፡ በሞቃት በረሀማ ቦታዎች የእርጥበትና
የእጽዋት ሽፋን እጥረት ስላለ የአፈር ስሪት ሂደቱ ደካማ ነዉ፡፡ በመሆኑም የበረሀ መሬት በአሸዋ፣ በጠጠርና
በአለቶች የተሸፈነ ነዉ፡፡ እንደ እባብ፣ እንሽላሊት፣ ቀበሮ የመሳሰሉት እንስሳት በአካባቢዉ የተለመዱ ናቸዉ፡፡
ተግባር- 2.14
1.ሶስቱን ዋና ዋና የበረሀ አይነቶች ዘርዝሩ፡፡
2.አንዱ የበረሀ አይነት ከሌላዉ በምን ይለያል?
3.የበረሀ እጽዋትና እንስሳት ሙቀትንና የዉሀ እጥረትን የሚቋቋሙበትን ዘዴ አስረዱ፡፡
ለ. ጮቄ
ይህ ክልል በዋልቴ የበረዶ ቁልልና በቅንምብብማ ጫካዎች መካከል የሚገኝ ነዉ፡፡ የከፍተኛ ኬክሮስ ቀዝቃዛ
የአየር ቅጥ በዋልታዎች አካባቢ እጽዋት እንዳይበቅሉ ስለሚያግድ ጮቄ በጣም ቀዝቃዛና ዛፍ የለሽ ስርዓተ-
ምህዳር እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በጮቄ ስስዓተ ምህዳር የፀሀይ ጨረር በጣም ያጋደለ በመሆኑ በ 3 ወይም 4
ወሮች ብቻ ከ 0 ዲግሪሴንቲግሬድ በለይ ልከ ሙቀት ይመዘገባል፡፡ አመታዊ አማካኝ የዝናብ መጠኑ ከ 250
ሚ.ሚ በታች ነዉ፡፡
እጽዋት ለመብቀልና ለማደግ በቂ ሙቀት ስለሚያስፈልጋቸዉ በዚህ ስርዓተ ምድር ብዙ እጽዋት አይበቅሉም፡፡
ይሁን እንጅ መጠነኛ ሙቀት ባላቸዉ አካባቢዎች እንደ በሌሎቶችና በሌሴቶች ያሉ ትንንሽ የእጽዋት
ዝርያዎች ይበቅላሉ፡፡
ይህን ስርዓተ ምኅዳር ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታን ለመቋቋም የሚያስችል ጠንካራ ቆዳና ጸጉር ያላቸዉ እንደ ድብና
የአርክቲክ ቀበሮ መሰል እንስሳት ለግጦሽና ለመጠለያነት ይጠቀሙበታል፡፡
በጮቄ ስርዓተ ምኅዳር መሬት ላይ የተከማቸዉ ግግር በረዶ ዉሀ ወደ ዉስጥ እንዳይሰርግ ስለሚያግድ ታች
አፈር/ sub soil/ ሁልጊዜ በረድ ሲሆን የላይኛዉ አፈር ደግሞ ዉሀ አዘል ነዉ፡፡ በዉሀ አዘል አፈር ዉስጥ
የአክስጅን እጥረት ስላለ የባክተሪያዎችን ቅሪት አካላትን የማፈራረስ ተግባር ይገድበዋል፡፡ ይህም የጮቄ ምድር
በከፊል በፈራረሱ የእጽዋት አካላት እንዲሸፈን አድርጎታል፡፡
አነስተኛ የህዝብ ብዛት በሚገኝባቸዉ የሳር ምድር አካባቢዎች ልዩ ልዩ እጸበልና ስጋ በል እንስሳት ይገኛሉ፡፡
ከእጸበል እንስሳት መካከል እንደ ዝሆን፣ የሜዳ አህያ፣ ድኩላ፣ የሚዳ ፍየል የመሳሰሉት ትልልቅ እንስሳት
ይገኛሉ፡፡ ከስጋበል እንስሳት መካከከል ደግሞ አንበሳ፣ነብር፣አቦሸማኔ ፣ተኩላና ጅብ ወዘተ የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡
ተግባር- 2.15
1.ሶስቱን ዋና ዋና የሳር ምድር አይነቶች ዘርዝሩ፡፡
2. አንዱ የሳር ምድር ዓይነት ከሌላዉ በምን ይለያል?
3.በሳር ምድር ተጽእኖ ከሚያሳድሩ የሰዉ ልጅ ድርጊቶች መካከል ቢያንስ አራቱን ጥቀሱ፡፡
መ. ቅጠል አርጋፊ ደን
ቅጠል አርጋፊ ደን የዉሀ ብክነትን ለመከላከል ሲባል ቅጠላቸዉን በየአመቱ የሚያረግፉ ዛፎች የሚገኙበት የደን
ስርዓተ ምህዳር ነዉ፡፡ ከዛፎቹ መካከከል የጠንካራ እንጨት ዝርያዎች እንደ ማፕል፣ልምጭ፣ኦአክ፣ የመሳሰሉት
ይገኙበታል፡፡ በተጨማሪም ብዙ አበባማ እጽዋት በበልግ ወቀት ይበቅላሉ፡፡ዛፎቹ የዉሀ ብክነትን ለመከላከል
በጸደይ ወቅት ቅጠላቸዉን ያረግፋሉ፡፡ ቅጠሉም በባክተሪያዎች አማካኝነት ስለሚፈራርስ አፈሩ ለምነት
እንዲኖረዉ ይረዳል፡፡
ይህ ክልል በአንጻራዊ መልኩ የተስተካከለ ስርጭት ያለዉ ከ 75-100 ሴ.ሜ የሚሆን አመታዊ አማካይ የዝናብ
መጠን ያገኛል፡፡
ስርዓተ- ምድሩ ለብዙ የተለያዩ ተባዮችና ለትንንሽና ትልልቅ አጥቢ እንስሳት መጠለያ ነዉ፡፡ ከአጥቢ እንስሳት
መካከከል አይጥ፣ ድብ፣ ሞል፣ ቀበሮ፣ ባጀረስ /badgers/ አቁስጣ /weasel /፣ ወዘተ የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡
በታይጋ ደን ዉስጥ እጸበልና ስጋበል የሆኑ ልዩልዩ እንስሳት ይገኛሉ፡፡ ከስጋበል እንስሳት መካከከል ተኩላ፣ አይጥ
የሚመስሉ ትንንሽ እስሳት/ voles/፣ አጋዘን ወዘተ… የመሳሰሉት ይገኛሉ፡፡ እንዲሁም በሞቄ ወቅት ተባዮችን
የሚመገቡ ወፎች ከሌሎች ክልሎች ወደ ታይጋ ክልል ይመጣሉ፡፡ የበረድ ወቅት ሲጀምር ወደ መጡበት
ተመልሰዉ ይሄዳሉ፡፡
ረ. የገሞጂማ ዶፍ ጫካ ደን
ይህ ክልል የሚገኘዉ በ 60 ሰሜንና በ 60 ደቡብ በምድር ሰቅ አካባቢ ነዉ፡፡ የዶፍ ጫካ ደን ክልል የአማዞንና የዛየር
ወንዝ ተፋሰሶችን፣ የኮሎንቢያን የባህር ዳርቻ፣ በምስራቅ አፍሪካ ታንዛኒያና የደቡብ ምስራቅ እስያ ደሴቶችን
ይሸፍናል፡፡
በዚህ ክልል በየቀኑ የቀትር ፀሀይ በአናት ላይ ትገኛለች፡፡ የአመቱ አማካይ የሙቀት መጠን 27 ደ.ሴ ይሆናል፡፡
ዝናብ በየቀኑ ከሰዓት በኋላ ይጥላል፡፡ አመታዊ የዝናብ መጠን ከ 1500 -2500 ሚ.ሚ ይሆናል፡፡ ዝናብ
የማይጥልበት ወር የለም፡፡ የክልሉ የዝናብ ዓነት ኮንቬንሽናል ነዉ፡፡
ተስማሚ የዝናብና የሙቀት መጠን በክልሉ የሚገኙትን ተክሎች እድገትና አይነት አዳብሮታል፡፡ ይህ አካባቢ
በአለም ከሚገኙ ሌሎች ስፍራዎች በበለጠ ሁኔታ ዉበት በሚሰጡ ተክሎች ተዥጎርጉሮ ይታያል፡፡ በዚህ ክልል
ከሚገኙ ዛፎች መካከል የጠንካራ እንጨት ዝርያዎች እንደ ሮዝ ዉድ፣ ጥቁር እንጨት፣ ማሆጋኒና የመሳሰሉት
ይገኙበታል፡፡
ያሳድራል፡፡ ዝናብ በስርዓተ-ምህዳር ላይ ሊያደርስ የሚችለዉ የጉዳት መጠን በዝናቡ መጠን፣ አጣጣልና
ወቅታዊ የዝናብ ስርጭት ሁኔታ ይወሰናል፡፡
ልከ ሙቀት በስርዓተ-ምኅዳር ላይ ተጽእኖ የሚያሳድር ሌላዉ ዋና ደንቢ ነዉ፡፡ የልከ ሙቀት መጠን በተለያዩ
የአለም ክፍሎች መካከል የማይናቅ ልዩነት አለዉ፡፡ ለምሳሌ በገሞጂማ ክልል የሚገኙ አብዛኛዎቹ ቦታዎች
አመቱን ሙሉ የማይለዋወጥ ከፍተኛ ልከ ሙቀት ሲኖራቸዉ ዋልታዎች ደግሞ ረዥም ቀዝቃዛ የበረድ ወቅት
/long and cold winter/ እና አጭርና ቀዝቃዛ የሞቄ ወቅት/ short and cool summer / አላቸዉ፡፡ የሌሎች
አካባቢዎች የልከ ሙቀት መጠን ደግሞ በገሞጂማና በዋልታዎች የልከ ሙቀት መጠን መካከል ነዉ፡፡ ይህ የልከ
ሙቀት ልዩነት የስርዓተ-ምህዳር አካላት አይነት ከቦታ ቦታ የተለያዩ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡
ከላይ እንደተገለጸዉ ልከ ሙቀትና ርጥበት በአንድ ስርዓተ-ምህዳር ዉስጥ ሊኖሩ የሚችሉ የእጽዋት አይነቶችን
በመወሰን ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ፡፡ ለምሳሌ አነስተኛ ርጥበትና ልከ ሙቀት ያላቸዉ አካባቢዎች የጮቄ
እጽዋት /Tundra vegetation/ አላቸዉ፡፡ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ርጥበትና ቀዝቃዛ ልከ ሙቀት ያላቸዉ
አካባቢዎች የቅምብ ቀጥ ደኖች /coniferous forests/ መገኛ ናቸዉ፡፡ ደረቅና ሞቃታማ አካባቢዎች ደግሞ
የበረሀ እጽዋት አላቸዉ፡፡ መካከለኛ የዝናብ መጠን ወይም ወቅታዊ ዝናብ የሚያገኙ ቦታዎች በገሶ /savanna/
አጽዋት የተሸፈኑ ናቸዉ፡፡ ከፍተኛ የዝናብና ልከ ሙቀት መጠን ያላቸዉ አካባቢዎች ደግሞ ለገሞጂማ ዶፍ
ጫካ / Tropical rainforest / እጽዋት ተስማሚ ናቸዉ፡፡
ከፍታ በጨመረ ቁጥር አየር ቅጥ ይቀዘቅዛል፡፡ ለምሳሌ ከኢትዮጵያ ዳርቻ ዝቅተኛ ቦታዎች ተነስተን ወደ
ሰሜን ምእራብና ደቡብ ምስራቅ ከፍተኛ ቦታዎች ስንጓዝ ከፍታ አየጨመረ የአየር ቅጥግን እየቀዘቀዘ
ይመጣል፡፡ በገሞጂማ ክልልም ቢሆን አንደ ክሊናማንጃሮ መሰል ትልልቅ ተራራዎች ጫፍ ላይ በረዶ ሊፈጠር
ይችላል፡፡ ስለዚህ የእጽዋት ስርጭት ከአየር ቅጥ ስርጭት ጋር ግንኙነት ስላለዉ ወደ ከፍተኛ ቦታዎች ስንጓዝ
በአየር ቅጥ ላይ የምናየዉ ለዉጥ በተመሳሳይ ሁኔታ በእጽዋት ስርጭትም ሊታይ ይችላል፡፡
ማጠቃለያ
ስነ-መሬታዊ ጊዜ በአራት የጊዜ እርከን ደረጃዎች ይከፈላል፡፡ እነሱም ዘመን /Eon / ክፍለ ዘመን/
Era / ወቅትና/ period/ ክፍለ ወቅት /Epoch/ ናቸዉ፡፡
በስነምድር ተመራማሪዎች ጥናት መሰረት የመሬት እድሜ ከ 4.5 - 4.6 ቢሊዮን አመት ይሆናል
ተብሎ ይታመናል፡፡
የስነምድ ተመራማሪዎች የመሬትን የህይወት ታሪክ በአራት ክፍለ ዘመናት ከፍለዉታል፡፡ እነሱም
የዘመነ ቅድመ ህይወት፣ የዘመነ ጥንተ ህይወት የማእከላዊ ዘመን እና የሰብዓ ዘመን ናቸዉ፡፡
በእያንዳንዱ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያ የተለያዩ ስነ-ምድራዊ ድርጊቶች ተከናዉነዋል፡፡
አየርቅጥ ማለት በአንድ አካባቢ ለብዙጊዜ ተደጋግሞ የሚከሰት የአየር ጠባይ ነዉ፡፡ የአየር ጠባይ
ለረዥም ጊዜ ሲጠናቀር የአየር ቅጥ በመባል ይታወቃል፡፡
ዋልድሚር ኩፐን የአለምን የአየርቅጥ በአምስት የአየርቅጥ አይነቶች/ክልሎች/ ከፍሎታል፡፡ እነሱም
ገሞጂማ አየር ቅጥ /A/፣ ደረቅ አየር ቅጥ /B /፣ ዉሀ አዘል ማእከላዊ ኬክሮስ አየር ቅጥ / C/፣ ዉሀ
አዘል በጣም ቀዝቃዛ ማእከላዊ ኬክሮስ አየር ቅጥ/ D/ እና ዋልቴ አየር ቅጥ /E /ናቸዉ፡፡
በኢትዮጵያ የአየር ቅጥ እንዲለዋወጡ የሚያደርጉ ብዙ ተቆጣጣሪዎች አሉ፡፡ከነዚህ መካከል ኬክሮስ፣
ከፍታና የአየር ፀባይ ስርዓት በግንባር ቀደምነት ይጠቀሳሉ፡፡
በኢትዮጵያ ዝናብ ከቦታ ወደ ቦታና ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲለያይ ከሚያደርጉት ተቆጣጣሪዎች መካከል
ዋናዋናዎቹ ከፍታና የአየር ጠባይ ስርአት ናቸዉ፡፡
በኢትዮጵያ በአመት አራት ወቅቶች አሉ፡፡ እነሱም ክረምት፣ ጸደይ፣ በጋና በልግ ናቸዉ፡፡
የአየር ቅጥ ለዉጥ ስንል አማካይ የአየር ቅጥ ይዘቶች ማለትም የአየር ሙቀት፣የዝናብ መጠን፣ የአየር
እርጥበት፣ የነፋስ ፍጥነት፣ ወዘተ በቀጣይነት መጨመርን ወይም መቀነስን ማለት ነዉ፡፡
የአየር ቅጥ ለዉጥ ሊያስከትሉ የሚችሉ ተፈጥሯዊ ደንቢዎች አህጉራዊ ሽርተታ፣ገሞራ፣ የዉቅያኖስ
ሞገድ፣ ወዘተ ሲሆኑ ሰዉ ሰራሽ ምክንያት ደግሞ በከባቢ አየር ዉስጥ የአፍላሽ ጋዞች ክምችት ነዉ፡፡
የአየር ቅጥ ለዉጥ የሚያስከትላቸዉ ዋናዋና ክስተቶች የአለም አማካይ የሙቀት መጠን መጨመር፣
የበረሀማነት መስፋፋት፣ ድርቅ፣ የባህር ወለል ከፍ ማለት፣የገሞጅማ ሰቅ መገኛ መስፋት፣ የአለም
አቀፍ ነፋሶች አቅጣጫ መቀየር እና የብዙሀ ህይዎት መጥፋት ናቸዉ፡፡
የመሬት የብሱ ክፍል በስድስት ዋናዋና የስርዓተ- ምዳር ክልሎች ይከፈላል ፡፡እነሱም በርሀ ፣ጮቄ
፣የሳርምድር ፣ቅጠል አርጋፊ ደን፣የታይጋ ደን አና ገሞጂማ ዶፍ ጫካ ናቸዉ፡፡
የክለሳ ጥያቄዎች
1.አራቱን የመሬት ህይወት ታሪክ ክፍለ ዘመናት ከሩቅ ወደ ቅርብ በቅደም ተከተል ዘርዝሩ፡፡2.በኢትዮጵያ
በሰብዓ ዘመን የተሰሩትን የደለሌ አለቶች ዘርዝሩ፡፡
3.ከኮፐን የአየር ቅጥ ክልሎች መካከል በኢትዮጵያ የሚገኙትን ዘርዝሩ፡፡
4. ኢትዮጵያ የከፍተኛ ቦታ አገር ባትሆን ኖሮ ምን አይነት የአየር ቅጥ ይኖራት ነበር?
5.የኢትዮጵያን አየር ቅጥ ዋናዋና ተቆጣጣሪዎች ዘርዝሩ፡፡
6. የአየር ቅጥ ለዉጥና የአየር ቅጥ ተለዋዋጭነትን ልዮነት አበራሩ፡፡
7.የአፍላሽ ጋዞች በአየር ቅጥ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽእኖ አብራሩ፡፡
8. ኢትዮጵያን በክረምት ወቅት ዝናብ እንድታገኝ ያደረጋት ምክንያት ምንድን ነዉ?
9. ስርዓተ-ምህዳር ምን ማለት ነዉ?
10. የስርዓተ ምህዳር አካላትን መስተጋብር አብራሩ፡፡
ምዕራፍ ሦስት
መግቢያ
ውድ ሰልጣኞች በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የአለም ህዝብ ብዛትና እድገት ሁኔታ፣ በህዝብ ስርጭት ላይ ተፅዕኖ
የሚያሳድሩ ነገሮች፣ የህዝብ ዝፈትና ውቅር፣ የኢትዮጵያ ህዝብና የስነህዝብ ፖሊሲ፣ የአለም ኢኮኖሚ ስርዓት
አይነቶች፣ የዘላቂ ልማትና እድገት መለኪያዎች እና የኢኮኖሚ ድርጅቶች የሚሉ ርዕሶች ተካተዋል።
በመሆኑም በዚህ ክፍለ ትምህርት ስለህዝብ ነክ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ትውውቅ ይደረጋል።
ዓላማ
ከዚህ ምዕራፍ መጠናቀቅ በሁላ ሰልጣኞች፦
በህዝብ ስርጭት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ነገሮችን ታስረዳላችሁ።
የስነህዝብ መረጃ ምንጮችን ትገልፃላችሁ።
የኢትዮጵያ ሦስት ተከታታይ የቤትና ህዝብ ቆጠራ ውጤቶች ትተነትናላችሁ።
የኢትዮጵያን ብሄራዊ ስነህዝብ ፖሊሲና ስልቶች ታስረዳላችሁ።
የስነህዝብ ፖሊሲን ትርጉም ትገልፃላችሁ።
የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ አይነቶችን ትለያላችሁ።
የዘላቂ ልማት ፅንሰ ሀሳብ ምንነት ትገልፃላችሁ።
ወዘተ... ባህርያት ያላቸውን ቡድኖች ወይም ክፍሎች ያቅፋል። እነዚህ ቡድኖች ወይም ክፍሎች ደግሞ የዚያን
ህዝብ ጥንቅርና አጠቃላይ ባህርያት ይወስናሉ።
በተለያዩ ጊዜያት ስለአለም ህዝብ ብዛትና እድገት እንዲሁ ምስርጭት ጥናቶች ተካሂደዋል። ለምሳሌ የሰው
ልጅ በፍራፍሬ ለቀማና በእንስሳት አደን ይተዳደር በነበረበት ዘመን ከ 10,000 ዓ.ዓ በፊት የአለም ህዝብ ብዛት
4 ሚሊዮን እንደነበር ተገምቷል። ይህ አህዝ ከኢንዱስትሪ አብዮት በኋላ በፍትነት ማደግ ጀመረ።
ከኢንዱስትሪ አብዮት ዋዜማ (1750 ዎች) የአለም ህዝብ ብዛት 1 ቢሊዮን እንደደረሰና በየአመቱ በ 2.6
ሚሊዮን እድገት ያሳይ እንደነበር ከተለያዩ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። በአሁኑ ዘመን የአለም ህዝብ ከ 7
ቢሊዮን በላይ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ህዝብ ነክ መረጃ ይገልፃል። ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ የአለም
ህዝብ ብዛት ከአውሮፓውያን የኢንዱስትሪ አብዮት በኋላ ከፍተኛ እድገት አሳይቷል።
ተግባር 3.1
የዓለም ህዝብ ቁጥር በተለይ ከአውሮፓውያን የኢንዱስትሪ አብዮት ወዲህ በፍጥነት እየጨመረ
መጥቷል፡፡ ለዚህ ፈጣን የሕዝብ ቁጥር እድገት በምክንያትነት ሊጠቀሱ የሚችሉት ሁኔታዎች
ምንድን ናቸው?
የሚከተለው ሠንጠረዥ የአለም ህዝብ ቁጥር እድገት በምን አይነት ሁኔታ እየጨመረ እንደመጣ ያሳየናል፡፡
ሠንጠረዥ 3.1፡ የዓለም ሕዝብ ቁጥር እድገትና ዓመታዊ ጭማሪ (10000 ዓ.ዓ. -2100 ዓ.ም)
አመት (እ.ኤ.አ) የሕዝብ ብዛት አመታዊ ጭማሬ
በመቶኛ
10000 ዓ.ዓ 100,000-10,000,000 -
5000 5,000,000- 20,000,000 -
1 ዓ.ም 256,000,000 -
1300 400,000,000 -
1650 0.5 ቢሊዮን 0.1
1800 1.2 “ 0.5
1900 1.6 “ 0.6
1950 2.5 “ 1.10
1980 4.4 “ 1.7
2000 6.2 “ 1.4
2025 8.1 “ 0.8
2050 9.5 “ 0.4
የሰው ልጅ በዱር ፍራፍሬ ለቀማና በእንስሳት አደን በሚተዳደርበት በጥንት ዘመን የአለም የህዝብ ቁጥር እጅግ
በጣም ዝቅተኛ ነበር። ይሁን እንጂ የሰው ልጅ የግብርና ስራን ከጀመረና አንድ ቦታ ላይ በቋሚነት መስፈር
ከጀመረ በኋላ ቁጥሩ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መጣ። በመቀጠልም ከኢንዱስትሪው አብዮት መከሰት ጋር
ተያይዞ የአለም የህዝብ ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ሊመጣ ችሏል። በዚህ መሰረት በ 1650 ዓ.ም አካባቢ
የአለም ህዝብ ብዛት 0.5 ቢሊዮን እንደነበርና አመታዊ እድገቱም 0.1% ሲሆን በ 2025 ዓ.ም 8.1 ቢሊዮንና
አመታዊ እድገቱም 0.8% እንደሚደርስ ይገመታል።
በአለማችን ፈጣን የህዝብ እድገት የሚታየው በተለይ በታዳጊ አገሮች ሲሆን በበለፀጉት አገሮች ግን የህዝብ
ቁጥር ጭማሬው አነስተኛና አዝጋሚ እንደሆነ ከሚቀጥለው ሠንጠረዥ መረዳት ይቻላል፡፡
ሠንጠረዥ 3.2፡ የአለም ሕዝብ ቁጥር እድገት(በቢሊዮን) እና አመታዊ ጭማሬ (በመቶኛ) በበለፀጉና በታዳጊ
አገሮች (1980 – 2100 እ.ኤ.አ.)
ክልል 1980 2000 2050 2100
ዓለም 4.4 6.2 9.5 10.2
(1.7) (1.4) (0.36) (0.10)
የበለፀጉ አገሮች 1.1 1.3 1.4 1.4
(0.68) (0.04) (0.07 (0.02)
ታዳጊ አገሮች 3.3 4.8 8.1 8.8
(2.04) (1.64) (0.41) (0.11)
አፍሪካ 0.5 0.9 2.2 2.6
(3.0) (2.77) (0.84) (0.31)
ደ. አሜሪካ 0.4 0.6 1.1 1.2
(2.38) (1.92) (0.52) (0.20)
ሰ.አሜሪካ 0.25 0.3 0.4 0.4
(1.04) (0.62) (0.22) (0.06)
ምሥ. እስያ (1.2) 1.5 1.8 1.8
(0.89) (0.03) (-0.04)
ደ. እስያ (1.4) 2.1 3.2 3.3
(2.14) (1.53) (0.30) (0.01)
አውሮፓ 0.5 0.5 0.5 0.5
(0.3) (0.15) (- 0. 08) (0.00)
ኦሺንያ 0.02 0.03 0.04 0.04
(1.44) (0.92 (0.19) (0.07)
ሩሲያ 0.3 0.3 0.4 0.4
( 0.93) (0.60) (0.16) (0.00)
ማስታወሻ፡- በቅንፍ ውስጥ የሚታዩት አሃዞች የሚያመለክቱት አማካይ አመታዊ የህዝብ ቁጥር ጭማሬን
በመቶኛ ነው፡፡
ተግባር 3.2
1. በታዳጊ አገሮች የህዝቡ ቁጥርና አመታዊ ጭማሬው ከፍተኛ ሊሆኑ የቻሉበትን ዋና ዋና ምክንያቶች
ዘርዝሩ፡፡
2. ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት የሚያሳድረውን ተፅእኖ በዝርዝር አብራሩ፡፡
3. ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገትን ለመግታት ምን መደረግ አለበት ትላላችሁ?
4. ከሚከተሉት ውስጥ በሀሳቡ የምትሰማሙበትን አንዱን በመምረጥ ደግፋችሁ ሌላኛውን በመቃወም
የመከራከሪያ ሀሳብ አቅርቡ፡-
ሀ) የህዝብ ቁጥር መጨመር ችግር ይፈጥራል፡፡
ለ) የህዝብ ቁጥር መጨመር ችግር አይፈጥርም (ጠቃሚ ነው) ፡፡
ተግባር 3.3
የአለም ህዝብ አሠፋፈር በሁሉም የአለም አካባቢዎች ተመሣሣይ አይደለም፡፡ ለምሣሌ፡- ከጠቅላላው የአለም
ህዝብ 2/3 የሚሆነው ሠፍሮ የሚገኘው 1/7 በሚሆነው የመሬት ክፍል ላይ ብቻ ነው፡፡በሌላ በኩል 90%
የሚሆነው የአለም ህዝብ በሰሜን ንፍቀ ክበብ፣ 10% ደግሞ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ ይገኛል፡፡ የአለም ህዝብ
ስርጭት በአህጉር ደረጃ ምን እንደሚመስል ደግሞ ከሚቀጥለው ሠንጠረዥ ማየት ይቻላል፡፡
ተግባር 3.4
ተግባር 3.5
አብዛኛው የአለም ህዝብ በየትኛው ንፍቀ ክበብ ሠፍሮ ይገኛል ? በሁለቱ ንፍቀ ክበቦችና በተለያዩ
ኬክሮሶች መካከል የሚታየው የህዝብ ክምችት ልዩነት ከምን የመነጨ ይመስላችኃል?
ተግባር 3.6
በህዝብ ስርጭት ላይ ተፅዕኖ የሚያትሉ በርካታ ነገሮች አሉ። እነዚህ ነገሮች በሶስት ዋና ዋና ምድቦች
ይከፈላሉ። እነዚህም፦
1. ተፈጥሮዓዊ ነገሮች
2. ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች
3. ታሪካዊ ጉዳዮች ናቸው።
1. ተፈጥሮዓዊ ነገሮች
በህዝብ ስርጭት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ዋና ዋና ተፈጥሮዓዊ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው።
የቦታው ለትራንስፖርትና መገናኛ ያለው ቅርበት
የመልክዓምድር ሁኔታ
የአየር ንብረት
የውሃ አቅርቦት
የማዕድናት ክምችት
የአፈር ሁኔታ
የእፅዋት ሽፋን ናቸው።
ተግባር 3.7
ተግባር 3.8
3.ታሪካዊ ጉዳዮች
የአለም ህዝብ ስርጭት የቅርብ ጊዜ ምክንያቶች ውጤት ብቻ ሳይሆን የጥንታዊ ታሪኮች ምክንያት ውጤት
ጭምር ነው። ለምሳሌ፦ የአፍሪካ ህዝብ ስርጭት በ 19 ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የአውሮፓዊያን ቅኝ ገዥዎች
በማዕድን፣ በወደብና በአስተዳደር ከተሞች አካባቢ የነበራቸውን ትኩረት የሚያንፀባርቅ ነው። እንዲሁም
ጦርነት፣ የባሪያ ንግድ፣ ጥንታዊ የንግድ መስመሮች ወዘተ በአለም ህዝብ ስርጭት ላይ ተፅዕኖ የነበራቸ ታሪካዊ
ምክንያቶች ናቸው።
ይህ የሚያስረዳው 104 የገጠር ነዋሪዎች በአማካኝ 1 ካሬ ኪሎ ሜትር የእርሻ መሬት እንደሚጠቀሙ ነው።
የአንድን ህዝብ የእድሜና የፆታ ስብጥር (ውቅር) የምንተነትንበት ሥእላዊ መግለጫ የህዝብ ፒራሚድ በመባል
ይታወቃል፡፡ የህዝብ ፒራሚድ የአንድ አካባቢን ህዝብ የእድሜና የፆታ ስብጥር ከማሳየቱም በላይ በህዝቡ
ውስጥ ያለውን የውልደትና የሞት ሁኔታ፤ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አመልካች ነው፡፡ የተለያየ
ዲሞግራፊያዊ(ህዝበ ነክ) ባህርያት (የውልደት፣ የሞት የእድሜ ወዘተ. ሁኔታዎች) ያላቸው ህዝቦች የተለያየ
የፒራሚድ ቅርፆች ይኖሯቸዋል፡፡ ለምሣሌ፡- የታዳጊ አገሮችንና የበለፀጉ አገሮችን ህዝቦች ዲሞግራፊያዊ ገፅታ
የሚወክሉ ፒራሚዶች በቅርፅ የተለያዩ ናቸው፡፡
ተግባር 3.9
1. የታዳጊና የበለፀጉ አገሮች ህዝቦችን መዋቅሮች የሚወክሉ ሁለት ናሙና ፒራሚዶችን ከተለያዩ
የፅሁፍ መረጃዎችና መፃህፍት ላይ ካሰባሰባችሁ በኋላ በፒራሚዶች መካከል ያለውን የቅርፅ ልዩነት፣
የቅርፅ ልዩነቱን መንሥኤና እያንዳንዱ ፒራሚድ የሚያስተላልፈውን መልእክት ወይም
የሚወክላቸውን ህዝበ ነክ ባህርያት በገለፃ አቅርቡ፡፡
2. በሁለቱ ፒራሚዶች መካከል ያለውን ልዩነት፡-
ሀ) ከውልደት
ለ) ከሞት
ሐ) ከእድሜ ስብጥር
መ) ከህዝብ ቁጥር እድገት እና
ሠ) ከማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ ሁኔታዎች አንፃር አብራሩ፡፡
በ 1984 እ.ኤ.አ በተካሄደው የመጀመሪያ ቤትና ህዝብ ቆጠራ የኢትዮጵያ ህዝብ ጠቅላላ ብዛት 39.8 ሚሊዮን
ነው። በሁለተኛው (1994 እ.ኤ.አ) ቆጠራ ወደ 53.4 ሚሊዮን የጨመረ ሲሆን በሦስተኛው ቆጠራ (2007
እ.ኤ.አ) ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ወደ 73.9 ሚሊዮን አሻቅቧል። የኢትዮጵያ ህዝብ እ.ኤ.አ በ 2010 እና
በ 2025 94 ሚሊዮን እና 132 ሚሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ተገምቷል።
ትርጓሜ
የስነህዝብ ፖሊሲ ማለት የአንድ ህዝብ አብይ ዲሞግራፊያዊ ባህርያት (ማለትም የውልደት፣ የሞትና ፣
የፍልሠት ሁኔታዎች) ለአካባቢያዊ ፣ ኤኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወዘተ. እድገቶች አዎንታዊ
አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ የሚችሉበትን መልክ እና አቅጣጫ እንዲይዙ ለማድረግ አንድ መንግስት የሚወስደው
ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ወይም የሚቀይሰው አስተዳደራዊ መርሃ ግብር ነው ማለት ይቻላል፡፡
በኢትዮጵያ ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገትን ለመግታት ይቻል ዘንድ የስነ ህዝብ ፖሊሲ ተቀርፆ የተለያዩ
እስትራተጅዎች ተነድፈዋል። የዚህ ፖሊሲ ዋነኛ አላማም የአገሪቱ ፈጣን የህዝብ ቁጥር ጭማሬ ከምጣኔ
ሀብታዊ እድገቱና ከተፈጥሮ ሃብቱ የመሸከም አቅም ጋር ማመጣጠን ነው። ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ
የተቀየሱ እስትራተጂዎችም የሚከተሉት ናቸው።
በህዝብ ቁጥርና በምርታማነት መካከል ያለውን ክፍተት ማጥበብ
ከገጠር ወደ ከተሞች የሚደረገውን ፍልሰት መቀነስ
የአካባቢ እንክብካቤን በማሳደግ የተፈጥር አካባቢን የመሸከም አቅም ማሳደግ
የሴቶችን ማህበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ አቅም ማጎልበት
የውልደት መጠንን መቀነስ
ተግባር 3.10
የሠው ልጅ ከጥንት ጀምሮ ለመኖር የሚያስፈልጉትን መሠረታዊና ሁለተኛ ደረጃ ፍላጎቶች ለማሟላት
በተለያዩ ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡ የሠው ልጅ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች
ተግባር 3.11
1. መሠረታዊ ፍላጎቶችና ሁለተኛ ደረጃ ፍላጎቶች (human needs & Human Wants ) የሚባሉት
ምንድን ናቸው ? ልዩነታቸውን አብራሩ፡፡
2. የሰው ልጅ ፍላጎቶች በምጣኔ ሀብታዊ ዕድገትና ሥልጣኔ ምክንያት ሊለዋወጡ እንደሚችሉ
ይታመናል ፡፡ ሆኖም ከሁለተኛ ደረጃ ፍላጎት ይልቅ መሠረታዊ ፍላጎቶች በዘመን ልዩነትም ሆነ
በኢኮኖሚ ዕድገት ብዙም ለውጥ አያሣዩም፡፡ ከላይ የተገለፀው አባባል ምን ማለት እንደሆነ
አብራሩ፡፡
3. ሦስቱ ዋና ዋና የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች አይነቶች እነማን ናቸው?
4. የእያንዳንዱ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ ባህርይ ምንድን ነው ? በእያንዳንዱ የምጣኔ ሃብት
እንቅስቃሴ ውስጥ ሊመደቡ የሚችሉ ክፍላተ ኢኮኖሚዎችን ዘርዝሩ፡፡
5. በጥንት ሠዎችና በአሁኑ ወቅት ደግሞ በጣም ኋላ ቀር በሆኑ አካባቢዎች መሠረታዊ ፍላጎቶችን
ለማሟላት የሚከናወኑ ምጣኔ ሀብታዊ ተግባራት ምንድን ናቸው? የጠቀሳችኋቸው ተግባራት
በየትኛው የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ ውስጥ ይመድባሉ?
ልማት የሚለውን ፅንሰ ሀሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሙት የምጣኔ ሀብት ምሁራን እና ፖለቲከኞች በ 20 ኛው ክፍለ
ዘመን ነው። ይሁን እንጅ መቸ፣ እንዴትና በማን የሚለው በውል አይታወቅም። ነገር ግን የልማት ፅንሰ ሀሳብ በአብዛኛው
ከካፒታሊዝም ስርዓት ማቆጥቆጥ ጋር ተያይዞ እናገኘዋለን።
ተግባር 3.12
ልማት በጣም ሰፊ ፅንሰ ሃሳብ ነው። ልማት ሰፊ ፅንሰ ሃሳብ በመሆኑ የሰው ልጆች የእውቀት፣ ቁሳዊ፣ እና መንፈሳዊ ፍላጎቶች
መሟላት (Sustenance) ጋር ይዛመዳል። ልማት የፖለቲካ ልማት (Political Development)፣ የማህበራዊ ልማት
(Social Development)፣ እና የኢኮኖሚ ልማት (Economic Development) ተብሎ በየፈርጁ ይታያል። ነገር ግን
በዚህ ንዑስ ርዕስ ልማትን ከኢኮኖሚ ገፅታ አንፃር ለማየት ይሞከራል። ልማትና የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ትስስር/ግንኙነት
አላቸው። የኢኮኖሚ እድገት ማለት አንድ አገር በአንድ አመት ያመረተችው አጠቃላይ የሀብት መጠን ሆኖ የግብርና፣ የጥሬ
እቃ፣ የኢዱስትሪ ምርቶችን እና የአገልግሎት አሰጣጥን ያካተተ ነው።
በአንድ አገር ውስጥ የዜጎች ቁሳዊና መንፈሳዊ ፍላጎት ተሟልቶ ሲገኝ ልማት(Development) እንዳለ ይነገራል። ይህ ማለት
በቂ መጠለያ፣ ልብስ፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ ትራንስፖርትና መገናኛ፣ የጤናና የትምህርት ተቋማት፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ፣
መብራት፣ ስልክ፣ ፖስታ፣ የነፍስ ወከፍ መጨመር፣ የተሻለ የኑሮ ደረጃ፣ ወዘተ እና አጠቃላይ የዜጎች መንፈሳዊ ፍላጎት
መሟላት የአንድን አገር ልማት ሊመሰክሩ የሚችሉ ጉዳዮች ናቸው።
ዘላቂ ልማት (Sustainable Development) ማለት ቀጣይነት ያለው ተከታታይ የሆነ እድገት ማለት ነው። ዘላቂ ልማት
የአሁኑን ትውልድና የመጭውን ትውልድ ፍላጎት መሟላትን ታሳቢ የሚያደርግ ፅንሰ ሀሳብ ነው። አሁን ያለው ትውልድ
የመጭውን ትውልድ ፍላጎት መሟላት በማይጎዳ ወይም በማያዛባ ሁኔታ ፍላጎቱንና የሚያስፈልጉትን ነገሮች ማሟላት ሲችልና
ቀጣይነት ያለው እድገት ሲያስመዘግብ ዘላቂ ልማት ይባላል።
በአንድ አገር ዘላቂ ልማትና እድገት መኖር ወይም አለመኖር ከላይ በተገለፁት ጉዳዮች ማለትም በቂ መጠለያ፣
ልብስ፣ የተመጣጠነ ምግብ፣ ትራንስፖርትና መገናኛ፣ የጤናና የትምህርት ተቋማት፣ ንፁህ የመጠጥ ውሃ፣ መብራት፣ ስልክ፣
ፖስታ፣ የነፍስ ወከፍ ገቢ መጨመር እና ከአጠቃላይ የዜጎች የኑሮ ደረጃ እና መንፈሳዊ ፍላጎት መሟላት አንፃር መግለፅ
የሚቻል ቢሆንም በሚከተሉት ሦስት ተያያዥ የእድገት ሁኔታች ይገለፃል። እነሱም፦
1. የኢኮኖሚ እድገት ፦ በሸቀጦች ምርትና አገልግሎት አሰጣጥ ተከታታይ የሆነ እድገት በማስመዝገብ የመንግስትን
ስራ በአግባቡ በመምርት የውጭ ብድርን መቆጣጠር ሲችልና በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና እና
በኢንዱስትሪ መካከል የተመጣጠነ እድገት ሲኖር ነው።
2. አካባቢያዊ እድገት፦ እድገቱ በአካባቢ ልማት ላይ ጉዳት የማያስከትልና የአካባቢውን የሃብት ምንጮች በአግባቡ
የሚጠቀም፤ አካባቢን ከብክነትና ከጥፋት የሚጠብቅ ማለትም የብዙሃ ህይወትን፤ የአካባቢ አየርን እና የስነ
ምህዳሩን ደህንነት መጠበቅ የሚችል ልማት ሲኖር ነው።
3. ማህበራዊ እድገት፦ እድገቱ ፍትሀዊ ስርጭት ሲኖረው፣ በቂ ማህበራዊ አገልግሎቶችን ምሳሌ ጤና፣ ትምህርት፣
መንገድ፣ እና የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ሲያቀርብ፤ የፆታ እኩልነትን፣ የፖለቲካ ተሳትፎንና ተጠያቂነትን በዘላቂነት
ማዳበር የሚችል ልማት ነው።
አለምአቀፋዊ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ከሚባሉት መካከል ለምሳሌ ያህል የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል።
የአለም ባንክ (World Bank)
አለምአቀፍ የገንዘብ ድርጅት (International Monetary Fund)
አለምአቀፍ የሰራተኞች ድርጅት (International Labour Organization)
አለምአቀፍ የንግድ ድርጅት (International Trade Organization) እና ሌሎችም
አህጉራዊ ከሚባሉት የኢኮኖሚ ድርጅቶች ደግሞ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ
የአውሮፓ ህብረት (European Union)
የሰሜን አሜሪካ ነፃ የንግድ ስምምነት (North American Free Trade Agreement) ወዘተ ናቸው።
ተግባር 3.13
ማጠቃለያ
ከኢንዱስትሪ አብዮት ዋዜማ (1750 ዎች) የአለም ህዝብ ብዛት 1 ቢሊዮን እንደደረሰና በየአመቱ በ 2.6
ሚሊዮን እድገት ያሳይ እንደነበር ከተለያዩ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። በአሁኑ ዘመን የአለም ህዝብ ከ 7
ቢሊዮን በላይ እንደሆነ የተባበሩት መንግስታት ህዝብ ነክ መረጃ ይገልፃል። በአለማችን ፈጣን የህዝብ እድገት
የሚታየው በተለይ በታዳጊ አገሮች ሲሆን በበለፀጉት አገሮች ግን የህዝብ ቁጥር ጭማሬው አነስተኛና አዝጋሚ
ነው። የአለም ህዝብ አሠፋፈር በሁሉም የአለም አካባቢዎች ተመሣሣይ አይደለም፡፡ በህዝብ ስርጭት ላይ
ተፅዕኖ የሚያሳድሩ በርካታ ነገሮች አሉ። እነዚህ ነገሮች በሶስት ዋና ዋና ምድቦች ይከፈላሉ። እነዚህም፦
ተፈጥሮዓዊ ነገሮች፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ታሪካዊ ጉዳዮች ናቸው። የአንድን ህዝብ የእድሜና
የፆታ ስብጥር (ውቅር) የምንተነትንበት ሥእላዊ መግለጫ የህዝብ ፒራሚድ በመባል ይታወቃል፡፡ የህዝብ
ፒራሚድ የአንድ አካባቢን ህዝብ የእድሜና የፆታ ስብጥር ከማሳየቱም በላይ በህዝቡ ውስጥ ያለውን
የውልደትና የሞት ሁኔታ፤ እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አመልካች ነው፡፡ የስነህዝብ መረጃ
ፖሊሲዎችን፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እቅዶችን ለመንደፍ መሰረታዊ ጠቀሜታ አለው። የስነ ህዝብ መረጃ
አሰባሰብ የአንድ አገር ከሌላው ስለሚለይ በአገሮች መካከል ያለውን የስነ ህዝብ መረጃ ማወዳደር አስቸጋሪ
ነው። ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ የስነህዝብ መረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይመደባሉ።
እነሱም ሙሉ ቆጠራ (Census)፣ የናሙና ቆጠራ (Sampling method) እና የአብይ ምዝገባ (Vital
registration) ናቸው። በኢትዮጵያ ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገትን ለመግታት ይቻል ዘንድ የስነ ህዝብ ፖሊሲ
ተቀርፆ የተለያዩ እስትራተጅዎች ተነድፈዋል። የዚህ ፖሊሲ ዋነኛ አላማም የአገሪቱ ፈጣን የህዝብ ቁጥር
ጭማሬ ከምጣኔ ሀብታዊ እድገቱና ከተፈጥሮ ሃብቱ የመሸከም አቅም ጋር ማመጣጠን ነው።
ምዕራፍ አራት
መግቢያ፡-
የዘመናዊ የተማከለ የአፄ ግዛት ምስረታ በኢትዩጵያ የተጀመረውና የተጠናቀቀው በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ
ነው ፡፡ ይህ የተማከለ የአፄ ግዛት ምስረታ በዋናነት የተጀመረው በአፄ ቴወድሮስ 2 ኛ ከ 1855 ዓ.ም ጀምሮ ነበር፡፡ አፄ
ቴዎድሮስ ኢትዩጵያ በተማከለ የአፄ ግዛት እንድትመራና የዘመነ መሳፍንት ዘመን መከፋፈል እንዲቀር ትልቅ ስራ ሰርተዋል፡፡
ይህ ፖሊሲያቸውም ከእርሳቸው ቀጥሎ በተነሱት ነገስታት ተቀባይነት አግኝቶ ሊቀጥል ችሏል፡፡
ከእሳቸው ቀጥሎ የተነሱት ነገስታት ማዕከላዊነትን ለመመስረት የተከተሏቸው ዘዴዎች መካከል ጥቂቶቹ “የፌዴራል” መሰል
አስተዳደር፣ የግዛት ማስፋፋትና ማግባባት ዘዴዎች ይጠቀሳሉ፡፡ በ 20 ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ይህ የማዕከላዊ መንግስት
ምስረታ መጠናቀቅ ችሏል፡፡ ይህ የተማከለ የአፄ ግዛት ምሰረታ በቀላሉ የተገኘ ሳይሆን ብዙ መስዋትነት አስከፍሏል፡፡
ለምሳሌ ብንወስድ በጣም ብዙ የሰው ደም ፈሷል፣ ብዙ ንብረት ወድሟል የባህል መጨፍለቅ አስከትሏል፣ የብሄር ጭቆናና
ማህበራዊ ቀውስ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የማዕከላዊ መንግስት ምስረታውን ፈታኝ ካደረጉት ነገሮች አንዱ ደግሞ የውጭ ወረራ
ሙከራ ስጋት ነበር ፡፡ ስለሆነም ሀገርን ከውጭ ወረራ የመከላከል ጦርነቶች ከግብፆች፣ ከማህዲስቶችና ከጣሊያኖች ጋር
ተደርጓል፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ባጭሩ በዚህ የተማከለ የአፄ መንግስት ምስረታ አስተዋፅኦ ያደረጉ ነገስታትን እናያለን፡፡
ተግባር፡- 4.1
- ለተማከለ የዘመናዊ የአፄ መንግስት ምስረታ አስተዋፅኦ ያደረጉ ነገስታትን ዘርዝሩ
አፄ ቴዎድሮስ 2 ኛ
በ 1852 እንደገና በማመጽ ከራስ አሊ ጋር ወደ ማይቀረው ጦርነት መሄዳቸው አልቀረም፡፡አንድ በአንድ የዘመኑ
ማለትም የዘመነ መሳፍንት አጋፍሪ የሆኑ መሳፍንቶችን ድል በማድረግ ኢትዩጵያን ወደ አንድነት መመለስ
ተግባርን ተወጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት ፡
በህዳር 1852 የጎጃሙን ደጃች ጎሹን በጉራምባ ጦር ሜዳ
በሚያዝያ 1853 ብሩ አሊጋዝና ሌሎች የራስ አሊ መሳፍንትን በጎርጎራ ብችን ጦር ሜዳ
በሰኔ በ 1853 ራስ አሊን በአይሻል ጦር ሜዳ
በመጨረሻም የትግራዩን ራስ ዉቤን በደረስጌ ጦር ሜዳ ድል በማድረግ አፄ ቴዎድሮስ 2 ኛ በመባል
በደረስጌ ማሪያም የንግስናቸው ስነ-ስርዓት ተፈፅሟል፡፡
አፄ ቴዎድሮስ አንድ ማዕከላዊ መንግስት ለመመስረት የተለያዩና ከባድ ጦርነቶችን አካሂዷል፡፡ የመጀመሪያ
ዘመቻቸውን ያደረጉት ወደ ወሎ ሲሆን ሂደቱም የተሳካ አልነበረም፡፡ ከወሎ ቀጥሎ ወደ ሽዋ ዘምተዋል ፡፡
በዚህም መሰረት በ 1855 በረከት በተባለው ጦር ግንባር የሸዋውን ሐይለ መለኮት በማሸነፍ ሽዋን በቁጥጥር ስር
ማድረግ ችለዋል፡፡ የአፄ ቴዎድሮስ ህልም በዘመኑ ጥልቅ እንደነበር ብዙ ምሁራን ፅፈዋል፡፡ ኢትዩጵያን አንድ
ማድረግ ብቻ ሳይሆን እየሩሳሌምን ከቱርክ ነፃ አደርጋለሁ የሚል ሀሳብ እንደነበራቸው ይነገራል፡፡
2. ዘመናዊነት፤- አፄ ቴዎድሮስ ዘመናዊ ቴክኖሎጅዎችና የጦር መሳሪያዎች
ለሀገራቸው መግባት ወይም መስራት እንዳልባቸው ያምኑ ነበር፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በዘመኑ ያልተሞከሩ
የተሻሻሉ አሰራሮችንም ለማስተዋወቅ ጥረት አድርገዋል፡፡ ከነዚህም መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት
ይገጥባቸዋል፡፡
ንጉሱም የውስጥና የውጭ ጠላቶች ዕረፍት ነስተዋቸዋል፡፡ በተለይም ሀገሪቱን አንድ የማድረግ ተግባራቸው
በተለያዩ የአካባቢያዊ ገዥዎች አልተወደዱም ተድላ ጓሉ በጎጃም ፣ ጢሶ ጎበዜ በወልቃይት፤ ዋግሹም ጎበዜ
በላስታ፤ ንጉሴና ተሰማ በስሜን ፣ካሳ ምርጫ በትግራይ ፣ሐይለ መለኮት በሽዋ ተነስተዉባቸዋል፡፡ ንጉሱም
የስልጣን ዘመናቸውን በሙሉ ማለት በሚቻል በየአካባቢው በጦርነት ቢንከራተቱ በመኖራቸው ከላይ
የተጠቀሱት ማሻሻያ ሀሳባቸውነን ሙሉ በሙሉ መተግበር ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ በተለይ ጨከን ያሉ
እርምጃዎችን እንዲወስዱና ንጉሱ ከለውጥ አርያነታቸው ይልቅ ጭካኔያቸው እንዲታወቅ አስተዋፅኦም
አበርክቷል፡፡
ጦር መሳሪያና ዲሲኘሊን የነበረው የእንግሊዝ ሰራዊት የንጉሱን ጦር ድል አደረገ፡፡ በዚሁ ቀንም አፄ ቴወድሮስ
ለጠላት ጦር ላለመማረክ ሲሉ ራሳቸውን በሽጉጥ ገደሉ፡፡ የእንግሊዝ ጦርም ብዙ የኢትዩጵያ ቅርሶችን
በመዝረፍ ምርከኞችን በማስፈታት ተመልሶ ሄደ፡፡
ከአፄ ቴዎድሮስ ሞት በኃላ በሀገሪቱ ስልጣን ለመያዝ የተለመደው ውዝግብ ቀጥሏል፡፡ ለአጭር ጊዜም ቢሆን
ስልጣኑን የተረከቡት የላስታው ዋግሹም ጎበዜ ናቸው፡፡ የንግስና ስማቸውንም ተክለ ጉዩርጊስ በማለት
ሰይመዋል፡፡ በወቅቱ ተገዳዳሪ የነበሩት መኳንንት ዋግሹም ጎበዜ /ላስታ/ ፤ካሳ ሞጫ /ትግራይ/ እና የሽዋው
ሚኒሊክ ነበሩ፡፡ ዋግሹም ጎበዜ ንግስናውን ቢረከቡም በተለይ ትግራይንና ሽዋን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡
ትግራይን ለመቆጣጠር ባደረጉት ውጊያ አሳም በተባለ ቦታ በጥር 1872 በካሳ ሀይሉ በመሸነፋቸው አጭሩ
የስልጣን ዘመናቸዉ ተጠናቋል፡፡
አፄ ዮሀንስ 4 ኛ
አፄ ዮሀንስ 4 ኛ በመካከል ካሳ ሞጫ በጥር 1872 ንጉሰ ነገስትነቱን ተረከቡት፡፡ አፄ ዩሀንስ የአፄ ቴዎድሮስን
ማዕከላዊ መንግስት ምስረተ ሀሳብ ቢረከቡም የተከተሉት ስልት ግን የተለየ ነበር፡፡ ከአፄ ቴዎድሮስ በተለየ
መልኩ የአካባቢያዊ መሪዎችን ስልጣን ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡ የተከተሉትም ስልት “የፌዴራላዊ” አስተዳደር
መልክን የተከተለ ነበር፡፡ ከረጃጅም ጦርነቶች ይልቅ ስምምነቶችን ለማድረግ ሞክረዋል፡፡ ለምሳሌ ብንወስድ
ከጎጃሙ አዳል ተሰማ ጋር በመስማማት ተክለ ሀይማኖት በሚል ስያሜ የጎጃም ንጉስ እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡
ለረዥም ጊዜ የርሳቸውን ንጉሰ ነገስትነትን ካልተቀበሉት ከአፄ ሚኒሊክ ጋርም ትልቅ ትዕግስት በማሳየት
በመጨረሻ በ 1878 ዓ.ም ላይ በተደረገ ስምምነት የሚከተለውን ቃለ ተግባብተዋል፡፡
ሚኒሊክ ለአፄ ዩሀንስ ግብር ሊገብሩ
አፄ ዩሀንስ ሀይማኖት ላይ የነበራቸው አቋም ከፖለቲካ አቅማቸው ጋር ፈፅሞ ተቃራኒ ማለት ይቻላል ፡፡
በሌሎች ሀይማኖቶች ላይም ፅኑ ቅጣቶችን ፈፅመዋል፡፡ በ 1878 በቦሩ ሜዳው ጉባኤ መሰረት በተለይ የወሎ
ሙስሊሞች በግዳጅ ወደ ክርስትና መለወጥ እንዳለባቸው ካልተለወጡ ግን ንብረታቸውና መሬታቸው
እንዲወረስ እንዲሁም ፅኑ ቅጣት ማድረሳቸው ፖሊሲያቸው ከባድ እንደነበር ያመላክታል፡፡
የአፄ ዩሀንስ ሀገርን ከውጭ ወረራ የመከላከል ተግባር እጅግ ውጤታማ ነበር፡፡ በዘመናቸዉ በዋናነት የኢትዩጵያ
ሉዓላዊ ድንበርን ጥሶ የገባው ጠላት ግብፅ ነበረች፡፡ የግብፅ መሪ የነበረው ሙሀመድ አሊ ዋና አላማ የነበረው
የአባይ ተፋሰስን እስከ ኢትዩጵያ መቆጣጠር ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ግብፅ በ 1865 አስብን በመቆጣጠር
በሶስት አቅጣጫ ወደ ኢትዩጵያ የመስፋፋት ሙከራ አደረገች፡፡ በዚህም መሰረት እቅዱን ያዘጋጀው
የሲውዘርላንድ ተወላጅ የነበረው ቅጥረኛ ወርነር ሙንዚንገር ነበር፡፡ በምስራቅ በመሀመድ ራቲብ ፓሻ
የሚመራው ጦር ሀረርን ተቆጣጠር፡፡ በጅቡቲ (ታጁራ)በኩል በሙንዚንገር የሚመራው ጦር አፋርን
ለመቆጣጠር ተንቀሳቀሰ፡፡ ሶስተኛው ከምፅዋ የተነሳው ጦር በኮረኔል አረንድሩፕ የሚመራው ሲሆን ወደ ሰሜን
ኢትዩጵያ ተንቀሳቀሰ፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ ሚኒሊክና ተክለሀይማኖት በአፄ ዩሀንስ ላይ ያመጹበት ጊዜ ሲሆን አፄ
ዩሀንስ ግን የውጭ ወራሪን ማጥፋት ላይ ትኩረት በማድረግ በግብፆች ላይ ዘምተዋል የመጀመሪያ
ፖሊሲያቸዉ ጦርነት ሳይሆን ዲኘሎማሲ ነበር፡፡ ስለሆነም ለግብፁ መሪ ደብዳቤ ቢልኩም መልስ ማግኘት
አልቻሉም፡፡ ቀጥለዉ ለአውሮፖ ሀገራት ማለትም ለእንግሊዝ ፈረንሳይና ሩሲያ አቤት ብለዋል፡፡ ነገር ግን
ምላሽ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ይህም ወደ አይቀሬው ጦርነት አመራ፡፡ በጥቅምት 23/1875 ጦራቸውን
በማንቀሳቀስ ጉንደትና ጉራ በተባሉ ጦር ግንባሮች ግብፆችን ድል አድርገዋል፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን በመጋቢት
1889 መተማ ላይ ከማህዲስቶች ጋር በተደረገው ጦርነት ሀገራቸውን ለመጠበቅ መስዋዕት ሆነዋል፡፡
አፄ ሚኒሊክ 2 ኛ
የመጀመሪያ ምዕራፍ /1878-1889/
በዚህ ምዕራፍ ለሸዋ ቅርበት ያላቸው ቦታዎች ማለትም ጉራጌ፣ አርሲ ፣ሀረርና ስልጤ ወደ ግዛት ተቀላዋል፡፡
በዚህ ምዕራፍ እንደ ሀረር ፣ አርሲና ስልጤ ጉራጌ ያሉ ቦታዎች በጦርነት የተለያዙ ናቸው፡፡ ሌሎች ቦታዎች
ማለትም በሰላም እንገባለን ያሉ እንደ ጉራጌ ፣ ጅማ እና ጌራ በሰላም የተቀላቀሉ ናቸው
የሁለተኛው ምዕራፍ /1889 – 1896/- ይህ ዘመን ክፉ ቀን /1889-1891/ የተባለው የረሀብ ጊዜ
የነበረበት በመሆኑ አፄ ሚኒሊክ በ 1894 ወደ ወላይታ በመዝመት ንጉሱን ካዎ ጦናን ድል አድርገው
ብዙ ሀብት ይዘው ተመልሰዋል፡፡ በረሀቡ ምክንያት ብዙ ቦታዎች መያዝ አልተቻለም፡፡
የሶስተኛው ምዕራፍ /1896-1900/ - በዚህ ዘመን የአፄ ሚኒሊክ ትኩረት የነበረው የድንበር
አካባቢዎችን መቆጣጠር ነበር፡፡ ይህም የሆነበት ዋናው ምክንያት በዘመኑ የነበሩ ቅኝኘ ገዥ ሀይሎችን
ለመግታት ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ከፋ፣ አፋር፣ ኦጋዴን፣ ጋንቤላ፣ ቤንሻጉል፣ እና ቦረና ወደ ግዛታቸው
ተቀላቅለዋል፡፡ ከዚህ በኋላ በአካባቢው ካሉ የቅጥ ግዛት ሀይሎች ጋር ንጉሰ ነገስቱ የድንበር ስምምነት
ከ 1897-1908 ድረስ ባለው ጊዜ ተፈራርመዋል፡፡
በአፄ ሚኒሊክ ዘመን ከተከናወኑት ተግባራት አንዱ ከጣሊያኖች ጋር የጀመሩት ወዳጅነት ነበር፡፡ ይህ
ወዳጅነት የተጀመረው በ 1876 ሲሆን በ 1889 የውጫሌ ስምምነት ድረስ ሰላማዊ ነበር፡፡ ለሁለቱ
ወገኖች ጠብ መንስኤ የሆነው በዋናነት የውጫሌ ስምምነት አንቀፅ 17 ነው፡፡ የአማርኛ ትርጉሙ
ኢትዩጵያ ከፈለገች በጣሊያን በኩል ከሌሎች ሀገራት ጋር መገናኘት እንደምትችል ሲያመላክት
የጣሊያኑ ትርጉም ግን ኢትዬጵያ የግድ የውጭ ግንኙነት ማድረግ ያለበት በጣሊያን በኩል ብቻ
እንደሆነ ነዉ፡፡ ይህም የጣሊያንን የቅኝ ግዛት ፍላጎት በግልፅ ያመላከተ ሲሆን አፄ ሚኒሊክ ጉዳዩን
በድርድር ለመጨረስ ሙከራ አድርገው ባለመሳካቱ በማርች 1/1896 የኢትዩጵያ ድል ሊጠናቀቅ
ችሏል፡፡ ይህ የአድዋ ድል ለኢትዩጵያን ብቻ ሳይሆን ለመላው የአለም ጥቁር ህዝቦች ኩራትና የነፃነት
ቀንዲል ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ተግባር፡ 4.4
መፃህፍትን በማገላበጥና ምሁራንን በማማከር ስለአድዋ ጦርነት አጀማመር፣ ሂደትና ውጤት
ጥናት ካደረጋችሁ በኋላ ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ፡፡
በሀገሪቱ የስልጣን ሽኩቻዉ መፋፋም የጀመረው ከአፄ ሚኒሊክ ህመም መጀመር ማለትም በ 1906 ነበር፡፡
በዚህ አመት በተለይ ከላይ የተጠቀሱት ሶስቱ ቅኝ ገዥ ሀገሮች ማለትም እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ጣሊያን
የሶስትዬሽ ስምምነት (Tripartite Treaty) ተዋውለዋል፡፡ ሀገሪቱ ከአፄ ሚኒሊክ ሞት በኋላ በስልጣን ሽኩቻ
ስትተራመስ የራሳችንን ፍላጎት እናሟላለን ብለው አስበው ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ፈረንሳይ የባቡር ሀዲድ
ያረፈበትን አካባቢ ለመውሰድ፣ እንግሊዝ የአባይ ሸለቆንና ምንጩን አካባቢ ለመቆጣጠር እንዲሁም ጣሊያን
ሁለቱን ቅኝ ግዛቶችን ማለትም ኤርትራና የጣሊያን ሶማሊላንድን የሚያገናኝ የባቡር መስመር እንድትሰራ
ተስማሙ፡፡ በህመም ላይ ያሉት አፄ ሚኒሊክ እነዚህን ሁለት ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን ለመቋቋም
ያሰቡትን ከማድረግ አልቦዘኑም፡፡ በመሆኑም ሁለት ነገሮችን አደረጉ፡፡ የመንግስት እንቅስቃሴው በሰላማዊ
መንገድ እንዲቀጥልና ፖለቲካዊ መረጋጋት እንዲመጣ በጥቅምት 1907 የመጀመሪያውን የሚንስትሮች
ም/ቤት አቋቋሙ፡፡ በመቀጠልም በግንቦት 1909 አልጋ ወራሻቸው እንዲሆን የልጅ ልጃቸውን ልጅ እያሱን
ሾሙ፡፡ በ 1913 ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
ከአአፄ ሚኒሊክ ሞት በኃላ ልጅ እያሱ ከእንደራሴያቸው ራስ ተሰማ ናደው ጋር ሀገሪቱን ለማስተዳደር ሙከራ
ቢያደርጉም ከፍተኛ ተቃውሞ ከእትጌ ጣይቱና ከሽዋ መኳንንት በኩል ተጋርጠባቸዋል፡፡ በተለይ ለእስልምና
ሀይማኖት ድጋፍ አድርጓል እንዲሁም ሙስሊም ሴቶችን አግብቷል በሚል ሰበብ የሽዋ መሳፍንት ስልጣኑን ወደ
ሽዋ ለመመለስ ከነበራቸው ፍላጎት አንፃር ከፍተኛ ተቋውሞ ደርሶባቸዋል፡፡ በመሆኑም መስከረም 27/1916
በተደረገ መፈንቅለ መንግስት ከስልጣናቸው ተባረዋል፡፡
የራስ ተፈሪን ወደ ስልጣን የመገስገስ ሂደት በዋናነት ያፋጠኑ ዋና ዋና ክስተቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
በ 1918 በስልጣን በመባለግና በጉቦ ምክንያት የሚኒስትሮች ም/ቤት አባላት ከንግስት ዘውዲቱ
ከስልጣን መባረር
በ 1921 የእጅ እያሱ መያዝ
በ 1923 የኢትዩጵያ ወደ ሊግ ኦፍ ኔሽንስ /የመንግስታቱ ማህበር/ አባልነት መግባትና በ 1924 ራስ
ተፈሪ በተለያዩ አውሮፖ ሀገራት፤ ት/ቤቶችና ሆስፒታሎች ያደረጉት ጉብኝት
በ 1924 ራስ ተፈራ ዋና ተቃዋሚዎች የሆኑትን ደጅ አዝማች ባልቻ ሳፎን ድል ማድረጋቸው
በ 1926 የፊት አውራሪ ጊወርጊስና ሊቀ ጰጰስ አቡነ ማቲወስ መሞት
በ 1928 የክብር ዘበኛ አዛዥ የነበሩት የደጅ አዝማች አባ ውቃው ሽንፈትና እስር
በ 1928 የራስ ተፈሪ ንግስና /ንጉስ ተፈሪ መባል/
በመጨረሻም በ 1930 የንጉስ ተፈሪ ራስ ጉግሳ ወሌን ማሸነፍን የራስ ጉግሳ ሞት ፡፡ ከዚህ ክስተት
ሁለት ቀን በኃላም የንግስት ዘውዲቱ ሞት ናቸው፡፡
ስለሆነም በህዳር 2፤1930 ተፈሪ ንጉሰ ነገስት ሐይለ ስላሴ 1 ኛ በሚል ስያሜ የኢትዩጵያ ብቸኛ ገዥ ሆኑ፡፡
ከዚህ ክስተት በኃላ ሐይለ ስላሴ ፍፀማዊ ዘውዳዊ ስርዓትን ማስፈን ጀመሩ፡፡ አካባቢያዊ ገዥዎች
ስልጣናቸውን ቀስ በቀስ ማጣት ጀመሩ፡፡ ይህ የማማከል ሂደት ያፋጠኑ ዋና ዋና ክስተቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
በ 1931 የመጀመሪያው የተፃፈ ህገ መንግስት መውጣትና ስልጣኑን ጠቅሎ ለንጉሰ ነገስቱ መስጠት
ከዚህ በፊት በትውልድ ቅብብሎሽ ሲተዳደሩ የነበሩ ግዛቶች ለምሳሌ ጎጃም ፣ ጅማ በቀጥታ
በማዕከላዊ መንግስት ስር መተዳደር መጀመራቸው
የፋይናንስና በቀረጥ ስርዓት አስተዳደር በቀጥታ በማዕከላዊ መንግስት ስር መሆን
ጦር ሰራዊቱን የማዘመን ሂደት መጠናከር ናቸው፡፡
ጣሊያን ኢትዩጵያን በመውረር ድብቅ አላማዋን ለማስፈፀም በ 1934 የወልወል ግጭትን እንደሰበብ
ተጠቅማለች፡፡ በዚህ አመት የጣሊያን ጦር የኢትዩጵያ ድንበር አልፎ ሲገባ ከኢትዩጵያ ጦር ጋር ተጋጭቶ
በሁለቱም ወገኖች ወታደሮች ቆስለዋል፣ ሞተዋልም፡፡ ንጉሰ ነገስት ሐይለ ስላሴ ነገሩን በድርድር ለመፍታት
ለሊግ ኦፋኔሽንስ /የመንግስታቱ ድርጅት/ አቤቱታ ቢያሰሙም በወቅቱ ሀያል የነበሩት እንግሊዝና ፈረንሳይ
የጣሊያን ወዳጅ በመሆናቸው መፍትሄ ሊያገኙ አልቻሉም፡፡
በኢትዩጵያ በኩል በዘመኑ የነበረውን ዘመናዊ የጣሊያን ጦር የሚስተካከል ምንም ዝግጅት ያልነበረ ሲሆን
ጣሊያኖች ግን ከአድዋ ሽንፈት ጀምሮ ሲዘጋጁ እንደነበር ይታመናል፡፡፡
የጣሊያን ወረራ በሁለት አቅጣጫ (በደቡብና በስሜን) የተቃጣ ነበር ፡፡ ጦርነቱም የሚደራጀው ኤርትራ እና
የጣሊያን ሶማሊላንድ ላይ ነበር፡፡ የጦርነቱ ሂደት በአጭሩ የሚከተለውን ይመስላል፡፡ በጥቅምት 3፤1935
የጣሊያን ወታደሮች መረብ ወንዝን በማቋራጥ ወደ ትግራይ ገሰገሱ፡፡ የዚህ ጦር መሪ የነበረው ኢሚሊዩ ዲ ቦኖ
ነበር፡፡ በደቡብ ደግሞ በጀኔራል ግራዚያኒ የሚመራ ጦር ወደ መሀል ተንቀሳቀሰ፡፡ በጥቅምት ሙሉና በህዳር ወር
የደቡብ ግንባር
ከላይ እንደተገለፀው በዚህ ግንባር ያለው የጣሊያን ጦር የሚመራው በጀኔራል ግራዝያኒ ሲሆን የኢትዩጵያ ጦር
ደግሞ በሁለት ክፍሎች ማለትም በደቡብ በራስ ደስታ ዳምጠው የሚመራ ሲሆን በደቡብ ምስራቅ ደግሞ
በደጀዝማች ነሲቡ ዘአማኑኤል የሚመራ ነው፡፡ ከሰሜን ግንባር በተቃራኒ በዚህ ግንባር ያለው የኢትዩጵያ ጦር
በአንፃሩ ዘመናዊና በወጣት አዛዣች የሚመራ ነበር ፡፡ ሁሉም አዛዦችና በስራቸው ያሉ የአባላት አዛዦች
ጣሊያንን በጀግንነት ቢዋጉም አሸናፊነት ዞሮ ዞሮ ለጠላት ሆነ፡፡ በመጋቢት 26 የራስ ደስታ ዳምጠው ጦር
ተሸንፎ ራሱም በመሸሸታቸው ጠላት ዶሎ ኦደን ተቆጣጠረ ፡፡ ከሳምንት በኃላ ጣሊያን ነገሌ ቦረናን
ተቆጣጠረ፡፡
በመጨረሻም በግንቦት 5፤1936 የጠላት ጦር አዲስ አበባን ተቆጣጠረ
ተግባር 4.4
የጣሊያን ሰራዊት የኢትዩጵያን ጦር ድል ያደረገበትን ዋና ዋና ምክንያቶች ዘረዝሩ ?
የኢትዩጵያ ጦር ከተሸነፈ በኃላ ጣሊያኖች የቅኝ ግዛት አስተዳደር መስርተዋል፡፡ እነዚህን
ግዛቶች መፃህፍትን በማንበብ ለክፍል ተማሪዎች ሪፖርት አቅርቡ ?
የኢትዩጵያ አርበኞች እንቅስቃሴና የጣሊያን ተሸንፎ ከሀገር መውጣትን የሚተነትን
ጥናታዊ ፅሁፍ በማዘጋጀት ለክፍል ተማሪዎች አቅርቡ ? /የሴቶች ሚና ምን ነበር/ ?
ከነፃነት በኃላ ንጉስ ነገስት ሐይለ ስላሴ ትኩረት በመስጠት የሸሟቸውና ስልጣን የሰጧቸው አብረዋቸው
ተሰደው ለነበርና እንዲሁም ከጣሊያን ጋር ለተባበሩ /ባንዳዎች/ ነበር፡፡ ይህም በእርሳቸው ወደ እንግሊዝ ሀገር
መሰደድ ለተበሳጩት አርበኞችና ለመሳፍንት ዘሮች ከፍተኛ ቅሬታ አስከትሏል፡፡ እንደ በላይ ዘለቀ፤ነጋሽ በዛብህ
እና ታከለ ወልደ ሐዋርያት ያሉ አርበኞች ንጉሱን በፀና ተቃውመዋል፡፡ በውጤቱም በላይ ዘለቀና ሌሎቹ በሞት
ተቀጥተዋል፡፡
የንጉሰ ነገስታዊውን ስርዓት የተቃወሙት ከላይ የተጠቀሱት አርበኞች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎችም የህ/ሰብ
ክፍሎች ማለትም ገበሬዎች፣ ጦር ሀይሉ፣ ተማሪዎች ወዘተ ነበሩ፡፡
እስኪ ዋና ዋናዎችን ተቃውሞዎች እንመልከት ከጦር ሀይሉ የተነሳዉ ተቃውሞ በታህሳስ 13፤1960 በዋናነት
በሁለት ወንድማማቾች የተቀናበረው መፈንቅለ መንግስት ተሞክሯል፡፡ የክቡር ዘበኛ ሀላፊ የነበሩት ጀኔራል
መንግስቱ ነዋይና ወንድማቸው ግማርሜ ንዋይና ሌሎችንም የፖሊስና የፀጥታ ሀላፊዎችን በማስተባበር
ንጉሳዊ ስርዓቱን በማስወገድ ስልጣኑ በህገ መንግስት የተወሰነ ንጉስ ለማስቀመጥ ቢሞክሩም ከቤተ
ክርስቲያንና ከጦር ሀይል እንዲሁም ከአየር ሀይል ድጋፍ ባለማግኘታቸው መስራው ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
በተጨማሪም ህዝቡን ቀድመው ማንቃትና ማስተባበር አልቻሉም ነበር፡፡ ምንም እንኳ የመፈንቅለ መንግስት
ሙከራው ሊከሽፍም ቀጣይ ለተነሳው የተሳካው የወታደሩ መፈንቅለ መንግስት እንዲትልቅ ግብዓት እንደነበር
ይነገራል፡፡
የገበሬዎች ተቃውሞ፡- በዋናነት ተቃውሞው የተነሳው በትግራይ፤ በጎጃምና በባሌ ገበሬዎች ሲሆን የንጉሳዊ
/ዘውዳዊ/ አስተዳደሩን አቅም ፈትኖ አልፏል፡፡
ተግባር ፡- 4.6
- ገበሬዎች ያመፁባቸው ዋና ዋና ምክንያት ምን ምን ነበሩ
- ይህ የገበሬዎች አመፅ በምን መንገድ እንደተከናወነና ውጤቱ ምን እንደሆነ መፅሀፍትን በማንበብ በቡድን
ዘገባ አቅርቡ ፡፡
የወያኔ አመፅ ከ 1942-1943፡- ይህ በትግራይ የተጀመረ ሲሆን በዋናነት በምስራቅ ትግራይ በራያና አዘቦ አካባቢ
ነው፡፡ የአመፁ መሪ ብላታ ሐይለ ማርያም ረዳ ሲሆኑ የአመፁ መነሻ ተብሎ የሚወሰደው የልማት ጥያቄ ፣
ጉቦን መቃወም ፣ የብሄርተኝነት ስሜትና ራስን በራስ የማስተደደር ፍላጎት መሆኑ ይታመናል፡፡ ንጉሳዊ
አስተዳደሩ በወሰደው ጨከን ያለ እርምጃ በጥቅምት 14፤1943 ተቃውሞው በሀይል ሊቆም ችሏል፡፡
የጎጃም ገበሬዎች አመፅ /1968/፡- የዚህ አመፅ አንዱ ምክንያት ተብሎ የሚወሰደው የደጅአዝማች ፀሀይ
እንቅስቃሴ አስተዳደር ብልሽነትና ውስን በተጨማሪም በ 1967 የተደረገው የቀረጥ ጭማሪ እንደመነሻ
ይወሰዳል፡፡ አመፁ በዋናነት ያተኮረው በሞጣና በደጋ ዳሞት ወረዳዎች ሲሆን ንጉሳዊ ስርዓቱ በወሰደው
እርምጃ በሀይል ሊቆም ችሏል፡፡
የባሌ ገበሬዎች አመት /1963 – 1970/ ፡- የዚህ አመፅ ምክንያቶች ተብለው የሚጠቀሱት
- የመልካም አስተዳደር ችግር
- የመሬት መነጠቅ
- የብሄራዊ ጭቆና
- የሀይማኖት አድሎ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
በተለይ የመሬት መነጠቅና በብዙ ስፍራዎች በተለይ ከሽዋ በመምጣት በባሌ መስፈራቸው ነዋሪው ሙስሊም
ማህበረሰብ በሂደት ባህሉን የማጣት ስጋት ፈጥሮበት ነበር፡፡ አመፁም በመጀመሪያው አመታት በተለይ
በኢልኬሬ አካባቢ የመራው ካሂን አብዲ ቢሆንም በኃላ ግን ዋቆ ጉቱ በዋናነት መርቶታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ
ማዕከላዊ መንግስት በወሰደው እርምጃ በ 1970 አመፁ ሊገታ ችሏል፡፡
የተማሪዎች እንቅስቃሴ፤ በተለይ ከ 1950 ዎቹ ጀምሮ የቀድሞው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች
የሀገራቸው ኋላ መቅረት በአንፃሩ ደግሞ ገና ነፃ ከወጡ ጥቂት ጊዜ የሆናቸው የአፍሪካ ሀገሮች በመመልከት
ንጉሳዊ አስተዳደሩን መቃወም ጀምረዋል ፡፡ የራሳቸውንም ማህበር ማለትም የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
ተማሪዎች ህብረት ወይም በእንግሊዘኛ USUAA /Universty Students Uniun of Addis Abeba/ በሀገር
ውስጥ፤ በውጭም የስሜን አሜሪካ የኢትዩጵያ ተማሪዎች ህብረት /ESUNA/ Ethiopian Students Union
in North American እንዲሁም በአውሮፖ(USUE) The Ethiopian Unviersty Sudents Union In Europe
በማ ss ም ንጉሳዊ አስተዳደሩን ተቃውመዋል፡፡ በተለያዩ መጣጥፎችም ማለትም እንደ “ታገል”፣ “ታጠቅ”
የመሳሰሉ በማሳተም የፖለቲካ እንቅስቃሴ ዉስጥ በሂደት ገብተዋል
በተለይ በ 1965 ከፖርላማዉ ፊት የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣት መሬት ላራሹ /Land to the Tillers/
የሚል መፈክር አስምተዋል፡፡ ቀስ በቀስም ትግሉ ወደ መክረር ሄደ፡፡ ከ 1969 ጀምሮ የራስን እድል በራስ መወሰን
እስከ መገንጠል የሚለውን አጀንዳ በመያዝ ተንቀሳቅሰዋል፡፡ ንጉሳዊ አስተዳደሩም ይህን በመቃወም
የ USUAA መሪ የነበረውን ጥላሁን ግዛው ገሏል፡፡ በ 1970 መጀመሪያዎች ወራት የተማሪዎች አመ å
የተባባሰበትና የ DC-3 የመንገዶች አውሮኘላን እስከመጥለፍ የደረሰበት ጊዜ ነበር፡፡ በተለይ በወሎና በትግራይ
ከ 1972-1974 የነበረው ረሀብና ድርቅን በመቃወም ተማሪዎቹ አመፃቸውን ያፋፋሙበት የንጉሳዊ ስርዓቱም
ውድቀት እየተፋጠነ የመጣበት ጊዜ ነበር፡፡
ደርግ የመጀመሪያ ተግባሩ ውስጥ የሚካተተው ሀገሪቱ ውስጥ ምንም አይነት ሰላማዊ ሰልፎችና ተቃውሞዎች
እንዳየረደረጉ ማድረግ ነበር፡፡ በተጨማሪም ሌሎች ስር ነቀል የሚባሉ አዋጆች ማለትም መሬት ላራሹ
ቢያውጅም በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ሊፈጠር አልቻለም፡፡ በተለይ ከኢትዩጵያ ህዝቦች አብዩታዊ ፖርቲ
(EPRP) ጋር በነበረው ግጭት ብዙ ወገኖች ከሁሉቱም ቡድኖች ሊገደሉ ችለዋል፡፡ በሀገሪቱ ተጨባጭ
የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ባለመረጋገጣቸው፤ሌሎች ተቃዋሚዎችም በሰላማዊ መንገድ እንዲታገሉ
ባለመፈቀዱ ከ 17 በላይ የታጠቁ ድርጅቶች ደርግን በመቃወም ተነስተዋል፡፡ በዋናነት በትግራይ የተነሳው
የትግራይ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር (TPLF) ነበር፡፡ በሂደትም አራቱ ድርጅቶች ማለትም የኢትዩጵያ ህዝቦች
ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (EPDM) (የአሁኑ ብኤዴን) ፣ የአሮም ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ድርጅት (OPDO) ፤
የትግራይ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር (TPLF) እና የኢትዩጵያ የዲሞክራሲያዊ መኮንኖች አብዩታዊ ንቅናቄ
(EDORM) በጋራ በመሆን የኢትዩጵያ ህዝቦች አብዩታዊ ዲሞክራሲያዊ ግንባር /ኢህአዴግ/ መሰረቱ፡፡
በግንቦት 28፤1991 ኢህአዴግ አዲስ አበባን በመቆጣጠሩ የደርግ መጨረሻ ውድቀት ሆነ፡፡
የክለሳ ጥያቄዎች
1. ለዘመናዊ የተማከለ የአጼ ግዛጽ ምስረታ አስተዋጽኦ ያደረጉ ነገስታት እነማን ናቸዉ? ዋና ዋና
ተግባሮቻቸዉን ዘርዝሩ፡፡
2. የሁለትዮሽ አስተዳደር ምን ገጽታች ነበሩት? ለተፈሪ መኮነን ገሮ መዉጣት ዋና ዋና ምክንያቶች ምን
ምን ነበሩ?
3. የፍጹማ ዘዉዳዊ ስርአቱ መለያ ባህርያት የምትሏቸዉን በመዘርዘር በእያንዳነዱ ሀሳቦች ዙሪያ
ተወያዩ፡፡
4. ጣልያን በ 1935 ኢትዮጽያን ለምን ወረረች? የጦርነቱ ዋና ዋና ግንባሮችን ዘርዝሩ፡፡
5. የዘዉዳዊ ስርአቱን በመቃዎም የተደርጉ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎችን ዘርዝሩ፡
ምዕራፍ አምስት
በዚህም ምክንያት በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አጋማሽ ፈረንሳይ የንግድና የባህር ሀይል ጣቢያ
በሴኔጋል፣ ጊኒ፣ አይቮሪኮስት /ኮቲዲቫር/፣ ዳሆሚ፣ ጋቦን እና ማዳጋስካር አቋቋመች፡፡ ጀርመንም ከእንግሊዝ ጋር
በመፎካከር ከውህደቷ በኃላ ወደ አፍሪካ ፊቷን መልሳለች ፡፡
የአውሮፖውያን አፍሪካን ለመቀራመት የተደረገ እንቅስቃሴ በዋናነነት የሚመነጨው የአፍሪካን ተፈጥሮ
ሀብቶች እና ጥሬ ዕቃዎች ለመቀራመትና የኢንዱስትሪ ምርቶቻቸውን ወደ አፍሪካ ለመላክ ነበር፡፡ ዋና
ዋናዎቹ የአፍሪካ ምርቶች የነበሩት የምዕራብ አፍሪካ የቅጠላ ቅጠል ዘይት፣ የዝሆን ጥርስ፣ ጎማ፣ ወርቅ
ማዕድን ይገኙበታል፡፡
የበርሊኑ ጉባኤ
ከላይ እንደተገለፀው እንግሊዝ በብቸኝነት የአፍሪካን ጥሬ ሀብት የመቀራመት ተግባር ሊቀጥል የቻለው እስከ
1860 ዎቹና በ 1870 ች ብቻ ነበር፡፡ የእንግሊዝ ፍላጎት የሌሎች አውሮፖ ሀገሮች ፍላጎትን መግታት ቢሆንም
በቀላሉ ሊሳካ አልቻለም፡፡ስለሆነም አውሮፓውያን እርስ በርስ ሳይጋጩና ሳይዋጉ አፍሪካን ለመቀራመት ዘዴ
መፈለግ ጀመሩ ፡፡
የአዲሷ ጀርመን ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት አቶ ቮን ቢስማርክ የእንግሊዝን የብቸኛ የአፍሪካ ተጠቃሚነት
ከሚቃወሙ ዋነኛው ነበሩ ፡፡ በሳቸው አነሳሽነትም የአውሮፖ ሀገራትን በጀርመን ዋና ከተማ በርሊን ስብሰባ
ጠሩ፡፡ ይህ የበርሊኑ ጉባኤ በመባል የሚታወቀው ከ 1884 – 1885 የተካሄደ ነው፡፡
ተግባር፡-5.2
- የበርሊኑ ጉባኤ ዋና ዋና አጀንዳዎች ምን ነበሩ ?
- የበርሊኑ ጉባኤ ውጤት ምን ነበር ?
- የስብሰባ ተሳታፊ ሀገራት እነማን ነበሩ ?
ስብሰባውን የተሳተፉ ሀገራት እንግሊዝ ፣ ጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ አውስትራሊያ ፣ ሀንጋሪ ፣ ሩሲያ ፣ ቤልጅየም ፣
ሆላንድ ፣ ስፔየን ፣ ፖሩቹጋል ፣ ጣሊያን ፣ ዴንማርክ ፣ ስዊድንና የአቶማን ቱርክ ነበሩ፡፡ አሜሪካም ወደ
ስብሰባው ተጋብዛለች፡፡ አንድም የአፍሪካ ሀገር በዚህ ስለ አፍሪካ በሚወያየው ጉባኤ ላይ አልተጋበዘም፡፡
በጉባኤው በዋናነት የተነሱ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ከአፍሪካ ጋር ስለሚደረግ ንግድ
- በአፍሪካ ወንዞች ስለሚደረገው ነፃ የጉዞ ጉዳይ
- ስለ አፍሪካ ህዝቦች ደህንነት ሁኔታ
- አውሮፖውያን አፍሪካን ቅኝ በሚገዙበት ጊዜ እርስ በርስ እንዳይጋጩ ስለመግታት ጉዳይ ሲሆኑ
የስብሰባው ተሳታፊዎች የበርሊን ስምምነት (General Act of Berlin) ተፈራርመዋል፡፡ በዚህም መሰረት
አንድ የአውሮፖ አገር በአፍሪካ ግዛት መያዝ የፈለገውን ቦታ ለሌሎች ማሳወቅ (Notification) እንዲሁም
ብቁ አስተዳደራዊ መዋቅር (Effective admnistration) መመስረት ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም ምክንያት
ከበርሊኑ ጉባኤ በኃላ የአፍሪካ መቀራመት በመፍጠኑ በ 1900 ከኢትዩጵያና ላይቤሪያ በስተቀር ሁሉም
የአፍሪካ ሀገሮች በቅኝ ግዛት አስተዳደር ስር ወደቁ ፡፡
ሁለተኛውና ጠንካራው ተቃውሞ የተደረገው በሳሞሪ ቱሪ ሲሆን የተካሄደውም በማዲንካ ግዛት ነው፡፡ ሳሞሪ
ከ 1870 ዎቹ ጀምሮ ከኒጀር ወንዝ ምንጭ እስከ የላይኛው ቮልታ ሸለቆ ድረስ ያለውን ህዝብ አስተባብሮ
መምራት ችሎ ነበር ፡፡ በስሩም ወደ 30‚000 የሚጠጋ ሰራዊት ነበረው ፡፡ በተለይም የሚዲንካ ብሄርተኝነትን
በመጠቀም የጥንቷን ማሊ ዝና በመጠቀም ህዝቡን ማስተባበር ችሎ ነበር፡፡ በ 1887 ከፈረንሳዩች ጋር
ስምምነት ቢያደርግም እንደተለመደው ፈረንሳዩች ቃላቸውን በማጠፍ በ 1891 ግዛቱን ወረውበታል ፡፡
በመጨረሻም በ 1898 የሳሞሪ ጦር ሙሉ በሙሉ ሊሸነፍ ችሏል፡፡ በአጠቃላይ በምዕራብ አፍሪካ የተደረገው
የፀረ ግኝ ግዛት ትግል ውድቀት መሰረታዊ ምክንያቶች የፀረ ቅኝ አገዛዝ ትባሉ ህብረት አለመኖርና
የአውሮፖውያን የመሳሪያ የበላይነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
ተግባር፡-5.4
- ምዕራብ አፍሪካ ከቅኝ ግዛት በፊት በምን ይታወቅ ነበር ?
- እንግሊዝ ምዕራብ አፍሪካን ለመቆጣጠር የተቀጠመችባቸው መንገዶች ምን ምን ናቸው ?
ከላይ እንደተገለፀው እንግሊዝ የናይጀሪያን አብዛኛውን ግዛት ከ 1892-1902 መቆጣጠር ችለዋል፡፡ የዩሩባላንድ
አብዛኛው ክፍልም ከ 1892-1893 ባሉት አመታት በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ፈረንሳዩች እንደጋጠማቸው ሁሉ
እንግሊዞችም ከፍተኛ ተቃውሞና ጦርነት በናይጀሪያ አገጥሟቸዋል፡፡
እንግሊዞች ግብፅን ከተቆጣጠሩ በኃላም የቅኝ የግዛት ማስፋፋታቸውን ወደ ሱዳን አዙረዋል፡፡ ከ 1877 እስከ
1879 ሳሙኤል ቤከር የሱዳን ጠቅላይ ገዥ ተደርጎ ተሹሟል፡፡ 1879 በጀኔራል ጎርደን ተተክቷል፡፡ በሱዳንም
በተመሳሳይ መልኩ በሙሀመድ አህመድ ኢብን አብደላ /አል ማህዲ/ የሚሰራ ፀረ ቅኝ ግዛት ትግል
አጋጥሟቸዋል፡፡ በተለምዶ የማህዲስት እንቅስቃሴ በመባል ይታወቃል፡፡ ነገርግን በ 1898 አምዱር ማን
እንግሊዞች ድል በማድረግ ሱዳንን መቆጣጠር ችለዋል፡፡
የቤልጅየሙ ንጉስ የነበረው ሊዩፖልድ 2 ኛ በ 19 ኛው ክፍለ ዘመን ሁለተኛው አጋማሽ በአፍሪካ የግሉ ቅኝ
ግዛት ለመመስረት ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው፡፡ ስለሆነም መእከላዊ አፍሪካናን ለማሰልጠን በሚል ሰበብ የኮንጎ
ሸለቆን የሚሰልል ስታንለይ የተባለ ግለሰብ 1879 ወደ ኮንጎ ላከ፡፡ በመቀጠልም ከፍተኛ ወታደራዊ ዘመቻ
በማድረግ ኮንጎን /የድሮዋን ዛየር/ መቆጣጠር ቻለ፡፡ ጀርመንም በ 1874 ደቡብ ምዕራብ አፍሪካን /ናሚቢያን/
በመቆጣጠር ዜጎቿን ማስፈር ችላለች፡፡ በ 1885 ጀርመን የጀርመን ምዕራብ አፍሪካ ግዛቷን የቶጎላንድንና
ካሜሮንን በመያዝ አውጃለች፡፡ በምስራቅ አፍሪካም ሰፊ መሬት በመያዝ የታንጋኒካ ቅኝ ግዛትን መስርታለች፡፡
ከደቡብ ምዕራብ አፍሪካ በተለይ ጀርመኖች በምዕራብ አፍሪካና በታንጋኒክ ቅኝ ግዛት በዋናነት የመሰረቱት
በተከታታይ ስምምነቶች ከባህላዊ መሪዎች ጋር በማድረግ ነበር፡፡ እንደ ፈረንሳይና እንግሊዝ ጀርመኖች
በተለያየ ቦታ ከፍተኛ የፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ተጋፍጠዋል፡፡ ከዚህ ውስጥ በዋናነት የሚገለፀው የማጅ ማጅ
አመፅ ነበር፡፡
ተግባር፡- 5.5
-ማጅ ማጅ የሚለው ሀሳብ ምን ማለት ነው ?
-የማጅ ማጅ አመፅ የትና በምን ምክንያት ተደረገ ? ውጤቱስ ምን ነበር ?
ይህ 1905 የተመሰረው አመፅ በጀርመኖች ከፍተኛ ጭካኔ ቢቀለበስም የራሱ ውጤቶች ነበሩት፡፡ አንደኛው
ውጤት ጀርመኖች የቅኝ ግዛት ፖሊሲያቸውን እንዲያሻሽሉ ሲያስገድድ ሁለተኛው ደግሞ ለቀጣይ የታንጋኒክ
ህዝቦች ትግል የራሱን አሻራ አኑሮ አልፏል፡፡
ወደ ስሜን አፍሪካ ስናተኩር ከላይ እንደተጠቀሰው ግብፅ በ 1879 በእንግሊዝ ቁጥጥር ስር ከዋለች በኃላ
በቀጣይ አመታትም ሱዳንን መቆጣጠር ችላለች ፡፡ ቱኒዥያና ሞሮኮም በፈረንሳይ እጅ ሊወድቁ ችለዋል፡፡
ጣሊያንም በ 1911 ሊቢያን መቆጣጠር ችላለች፡፡
ፖርቹጋሎችም የራሳቸውን ቅኝ ግዛት የመሰረቱ ሲሆን ለማጠቃለል ያክል በዋናነት የእንግሊዝ ፣ ፈረንሳይና
የፖርቱጋል ቅኝ ግዛቶችን በሚከተለሙ መልኩ ቀርበዋል
የእንግሊዝ ቅኝ ግዛቶች
- ናይጀሪያ - ደቡብና ሰሜን ሮዲዥያ
- ጎልድኮስት /ጋና/ - ንያሳላንድ
- ሴራሊዩን - የእንግሊዝ ቤቹአናላንድ
- ጋምቢያ - የእንግሊዝ ሶማሊላንድ
- ኡጋንዳ - ዛንዚባርና ፔምባ
- ኬንያ
የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች
- ሴኔጋል - ጋቦን
- አይቬሪኮስት - ኮንጎ
- ጊኒ - ኢባንጊሻሪ (የአሁን ማኢከላዊ አፍሪካ
- ዳሆሚ ሪፐብሊክ)
- ሱዳን - ቻድ
- ማሊ - ማዳካስከር
- ስሜናዊ ቮልታ - ኮሞሮስ ደሴት
- የፈረንሳይ ሶማሊ ላንድ
የፖርቹጋል ቅኝ ግዛቶች
- አንጎላ - የቤልጅየም ኮንጎ በቤልጅየም
- ሞዛንቢክ - የኢጣሊያ ሶማሊላንድ
- ጊኒ ሲሆኑ - የጣሊያን ኤርትራ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
- ሳኦ ቶሜ /ስፔየን/
ተግባር ፡- 5.6
- ፖን አፍሪካን ንቅናቄ የትና እንዴት በማን ተመሰረተ ?
- መፃህፍትን በማገላበጥ የፖን አፍሪካን የተለያዩ ጉባኤዎችን አጀንዳዎቻቸውን ዘርዝሩ ?
- የፖን አፍሪካን ታዋቂ መሪዎች እነማን ነበሩ ?
በሁለተኛው የአለም ጦርነት ተዋግተው የተመለሱ የአፍሪካ ወታደሮች ከጦርነት መልስ በነጮች ለመገዛት
ዝግጁ አልነበሩም፡፡ ህዝቡንም ስለ ነፃነት ማነሳሳት ችለዋል የአፍሪካ ምሁራንም ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ምንም እንኳ በቅኝ ገዥዎቻቸው የሰለጠኑና የነሱን ቢሮክራሲ ለማስተዳደር የተመደቡ ቢሆንም ቀስ በቀስ ግን
የአፍሪካን የነፃነት ትግል በመምራት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በጋና /ጎልድኮስት/ የተባበሩት የጎልድ ኮስት
ኮንቬክሽን (United Goldcoast convention) የተባለውን ድርጅት በመልቀቅ በ 1949 ክዋሜ ንኩርማህ
ኮንቪክሽን ፒውፒልስ ፓርቲ (convention people’s party) በመመስረት በ 1960 ጎልድኮስትን ነጻ ለማውጣት
ችሏል፡፡ ቀስ በቀስም ሴራሊዩን በ 1961፤ ጋምቢያ በ 1970 ነፃ ወጥተዋል፡፡
ግብፅ በ 1956 ነፃነቷን ተቀዳጅታለች፡፡ በኬንያም በጆሞ ኬንያታ የሚመራው የነፃነት ትግል ፍሬ አፍርቶ
በ 1963 ኬንያ ነፃነቷን ማግኘት ችላለች፡፡
የፈረንሳይ ቅኝ ግዛቶች ነፃ መውጣት እንቅስቃሴ ከ 1950 ዎቹ ጀምሮ በሰላማዊ መንገድና በጦርነት መከናወን
ችሏል፡፡ ስለሆነም ቱኒዥያ በሀቢብ ቡርጊባ መሪነት በ 1956 ነፃ ስትወጣ አልጀሪያ ደግሞ በአህመድ ቤን ቤላ
መሪነት በ 1962 ነፃ ወጥታለች፡፡ የሁለቱ ሀገሮች ነፃነት በዋናነት የተከናወነው በረጅምና በከባድ ጦርነት በማለፍ
ነበር፡፡ በተለይም በ 1960 ዎቹ የአፍሪካ አመት (Year of africa) በመባል ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም አብዛኛው
ሀገሮች ማለትም እንደ ካሜሮን፣ ቻድ፣ የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወዘተ ነፃ መውጣት ችለዋል፡፡ በርግጥ
ከ 1960 ዎቹ በኃላ ዘግየት ብለው ነፃ የወጡ ሀገሮች መካከል አንጎላ በ 1975 ትገኝበታለች፡፡ ደቡብ አፍሪካም
ከአፖርታይድ ስርዓት ማክተም በኃላ በ 1994 አዲሱን ጥቁር ኘሬዜዳንት ኔልሰን ማንዴላ ኘሬዜዳንት በመሆኑ
ከአፖርታይድ ስርዓት ነፃ ወጥታለች፡፡
በፖለቲካው ረገድም ከፍተኛ ጉዳት እንዳስከተለ ይታመናል፡፡ በተለይ በዘፈቀደ የተሰማሩት የአፍሪካ ደንበሮች
ከነፃነት በኃላ በብዙ ሀገሮች ለርስ በርስ ጦርነት ዋነኛ መንስኤ ለመሆን በቅተዋል፡፡
በባህልም ረገድ የአፍሪካ ባህል የመነመነበትና በአንዳንድ ቦታዎችም ፈፅሞ የጠፋበት ሁኔታ ነበር፡፡
ተግባር፡- 5.7
-የቅኝ ግዛት በጎ ጎኖች ከሚባሉት ውስጥ ጥቂቶችን ዘርዝሩ ?
-ከላይ ከተቀሱት በተጨማሪ የቅኝ ግዛት ማህበራዊ ፣ ባህላዊ ፖለቲካዊ ተፅዕናዎችን ዘርዝሩ?
-በቅኝ ግዛት ሰበብ ከነፃነት በኃላ የተከሰቱ የድንበር ጦርነቶችን ዘርዝሩ ?
በዚህ ከፋፋይ ስርዓት ምክንያት በተለያየ ሰበብ በቀን እስከ 1000 ጥቁሮች በእስር ለመዳረግ በቅተዋል፡፡
ቤተክርስቲያናት ሳይቀሩ የጥቁርና የነጭ በመባል ተከፍለዋል፡፡ በየቦታው ለውሾትና ለጥቁሮች የተከለከለ የሚሉ
ባነሮች የተለመዱ ሆነዋል፡፡ ሌሎች ብዙ ከፋፋይ ህጎችም ተደንግገዋል፡፡ ክፋቱ መከፋፈል ብቻ አይደለም
ይልቁንም ጥቁሮችን በራሳቸው ሀገር ተረግጠው ተንቀውና ተጨቁነው እንዲኖሩ ማድረጋቸው የስርዓቱን
አስከፊነት ያመላክታል፡፡
ተግባር፡- 5.8
-ስለ አፖርታይድ የምታውቁትን ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር በመወያየትለመምህራቸሁ ተናገሩ ?
-አፖርታይድን በዋናነት የተዋጉ መሪ ማን ነበሩ ? ትግላቸውስ ምን ይመስላል?
የመጀመሪያው የጥቁሮች ፖርቲ የሆነው የአፍሪካ ናሽናል ኮንግረስ (ANC) የተመሰረተው በ 1912 ሲሆን
ከምስረታው ጀምሮ አፓርታይድን በፅናት ተዋግቷል፡፡ የ ANC ትግል ውጤታማ የሆነው በኔልሰን ማንዴላ
ሲሆን ስርዓቱን በመቃወም ለ 27 ዓመታት ለእስር ተዳርገው ነፃ ከወጡ ከ 1994 በኃላ የጥቁር አፍሪካ
የመጀመሪያው ኘሬዜዳንት ሲሆኑ የስርዓቱ ማብቃት ተበስሯል፡፡
በ 1945 በእንግሊዝ አገር ማንቸስተር ከተማ በተካሄደው 5 ኛው የመላው አፍሪካ ጉባኤ ከአፍሪካ ምድር
ተወክለው በሄዱ ወጣት ምሁራን የበዙበትና ከቀደሙት ጉባኤዎች ጋር ሲነፃፀር ንቅናቄውን አንድ ወደ ፊት
በማራመድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተነት ነበር ለማለት ይቻላል፡፡
የጉባኤው ዋነኛ አጀንዳ የብሄራዊ ነፃነት ትግል ነበር፡፡ ስብሰባውን ተካፍለው ወደየአገራቸው የተመለሱ
የወደፊቷ ነፃይቱ የአፍሪካ መሪዎች በአዕምሮአቸው ሰንቀውና ወስነው የመጡት በማንኛውም መንገድ
አገራቸውን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት ለመታገል ነበር፡፡ የመላው አፍሪካ ሐሳብንም ወደ አፍሪካ ምድር
አመጡ፡፡ ይህ ማለት ወደ አፍሪካ አንድነት ድርጅት የተደረገው ረጅም ጉዞ የመጀመሪያው እርምጃ
የተጀመረበት ነው፡፡
አአድ ከመመስረቱ በፊት ማለት ከ 1958-1961 ዓ.ም ድረስ በወቅቱ ነፃ የነበሩ የአፍሪካ መንግስታት አራት
ተከታታይ ጉባኤዎችን አካሂደዋል፡፡
እነሱም፡-
1. የመጀመሪያው ጉባኤ በአክራ /ጋና/ በ 1958 የተካሄደ
2. ሁለተኛው በአዲስ አበባ በተመሳሳይ በ 1958 ዓ.ም
3. ሶስተኛው በሊዩፖልድቪል /ኮንጎ/ በ 1961 ዓ.ም የተካሄዱት ናቸው፡፡
ስምንት የአፍሪካ ነፃ መንግስታት ማለትም ኢትዩጵያ ፣ ላይቤሪያ ፣ ጋና ፣ጊኒ ፣ ግብፅ ፣ ሞሮኮ ፣ ሊቢያና
ቱኒዚያ በሚያዝያ 1958 ዓ.ም በጋና ዋና ከተማ አክራ የመጀመሪያውን የአፍሪካ መንግስታት መሪዎች ስብሰባ
አደረጉ፡፡ በቀጣዩቹ ሶስት ጉባኤዎች አዲስ ነፃ የሚወጡ አገሮች የተሳታፊ መንግስታትን ቁጥር እያሳደገው
ሄዷል፡፡ በእነዚህ ጉባኤዎች የአፍሪካ መንግስታት የፀረ-ቅኝ አገዛዙን ትግል ለማሳለጥና የነፃነት ሂደቱን
ለማፋጠን እጅግ ተቀራርበው መስራት የጀመሩበት ነበር፡፡ ለነፃነት በመታገል ላይ የነበሩ ህዝቦችን ጥረት
በመደገፍ የኘሮፖጋንዳ ፣ ዲኘሎማሲና የፋይናንስ ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡ ይህም የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ
ሂደትን አንድ ተጨማሪ እርምጃ ወደፊት ወስዶታል፡፡
ሌላው ለአ.አ.ድ ምስረታ ከረዱ ሁኔታዎች አንዱ የመላው አፍሪካ ህዝቦች ጉባኤ ነው፡፡ ይህ ጉባኤም የፀረ ቅኝ
አገዛዝ ትግሉን ለማጠናከር ረድቷል፡፡ እ.አ.አ ከ 1958-1961 ዓ.ም ድረስ ሶስት የመላው አፍሪካ ህዝቦች
ጉባኤዎች ተደርገዋል፡፡
እነሱም፡-
1. የመጀመሪያው የመላው አፍሪካ ህዝቦች ጉባኤ በታህሳስ ወር 1958 በአክራ /ጋና/ ተካሄደ
2. ሁለኛው ጉባኤ በጥር 1960 በቱኒስ /ቱኒሲያ/ ተሰበሰበ ፡፡
3. ሶስተኛው በመጋቢት 1961 በካይሮ /ግብፅ/ ተደረገ፡፡
ለ/ በብዙ የአፍሪካ አገሮች ህጋዊ መንግስታትን በመፈንቅለ መንግስት ከስልጣን ሲያስወግዱ ምንም
ማድረግአለመቻሉ፡፡
ሐ/ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን በአፍሪካ ያሉ የኢኮኖሚ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የገንዘብ
አቅምየሌለው መሆኑ ፡፡
መ/ አአድ በአፍሪካ መንግስታት መካከል የሚነሱ ግጭቶችን የሚፈታበት ፍ/ቤት የሌለው መሆኑ ናቸው፡፡
በቅኝ ግዛት ዘመንና በቅኝ ግዛት ማግስት አፍሪካን ላጋጠማት የአውሮፖውያን ጫና ለመቀነስና ለመቋቋም
ታስበው ከተደራጁት አያሌ ክፍለ አህጉራዊ ትስስሮች መካከል አንዱ የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ
ማህበረሰብ ወይም በአጭሩ ኢኮዋስ እየተባለ የሚጠራው ክፍለ-አህጉራዊ ድርጅት ነው፡፡
እ.አ.አ በ 1975 ዓ.ም በናይጀሪያ ሌጎስ ከተማ ላይ በተደረገው የመሪዎች ስብሰባ በተደረሰው ስምምነት
ተመስርቶ እ.አ.አ ከ 1977 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ስራ ጀመረ ፡፡ አስራ ስድስት አባል መንግስታትን በአባልነት ያቀፈ
ትልቅ ማህበረሰብ ነው፡፡ እነሱም ቤኒን ፣ ቡርኪናፋሶ ፣ ኬኘቨርዴ ፣ ኮትዲቫር ፣ ጋምቢያ ፣ ጋና ፣ ጊኒ ቢሳው ፣
ላይበሪያ ፣ ማሊ ፣ ሞርታኒያ ፣ ኒጀር ፣ ናይጀሪያ ፣ ሴኔጋል ፣ ሴራሊዩንና ቶጎ ናቸው ፡፡
ኢኮዋስ የእራሱ ፍርድ ቤትና አምስት የተለያዩ ኮሚሽኖች አሉት ፡፡ እነሱም
1. የንግድ ፣ የቀረጥ ፣ የስደተኞች ፣ የገንዘብና የክፍያ ጉዳይ ኮሚሽን
2. የኢንዱስትሪ ፣ እርሻና የተፈጥሮ ሀብት ጉዳይ ኮሚሽን
3. የትራንስፖርት ፣ መገናኛና ኢነርጅ ጉዳይ ኮሚሽን
4. የማህበራዊና ባህላዊ ጉዳይ ኮሚሽን
5. የአስተዳደርና ፋይናንስ ጉዳይ ኮሚሽን ናቸው፡፡
የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ ሳድክ /Southern Africa Development Community SADC/
በቅኝ ግዛት ዘመን የደቡባዊ አፍሪካ አገሮች ከሌላው የአፍሪካ ክፍለ-አህጉራት በተለየ ሁኔታ በፖለቲካና
በኢኮኖሚ የተሳሰሩ ነበሩ፡፡ ለደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ወርቅና አልማዝ ማእድናት ፣ ለስሜን ሮዴዢያ /ዛምቢያ/
የመደብ ማዕድን ፣ በደቡብ ሮዴዢያ /ዚምባቡዌ/ ለተመሰረተው ግዙፍ የትምባሆ እርሻ የሚበቃ ሰራተኛ
ከየአገራቱ በበቂ መጠን ማግኘት ስለማይቻል የተፈጠረውን የሰው ሀይል እጥረት ለመሸፈን ቅኝ ገዥዎች
ከጎረቤት ቅኝ ግዛቶቻቸው ሰው በመውሰድ ይጠቀሙ ነበር፡፡
ተግባር፡-5.9
-ተማሪዎች በደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ ዋነኛዋ ቅኝ ገዥ አገር ማን ነበረች ?
በአካባቢው የሚካሄደው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ፣ የጉልበት ሰራተኛ ምልመላና የሰው ከቦታ ቦታ ዝውውሩ
እንዲሁም የሰራተኞች ክፍያ ሁኔታ በአካባቢው የነበሩትን ቅኝ ግዛቶች በኢኮኖሚና በፖለቲካ እንዲተሳሰሩ
አደረገ፡፡ ይህ ቀደም ያለ የትብብር ተሞክሮ ዘላቂ የሆነ የትብብር ባህልን በአካባቢው ፈጠረ፡፡ አንፃራዊ የሆነ
የትራንስፖርት ትስስር /በዋናነት የባቡር ግንኙነት/ መኖር የኢኮኖሚ ትስስር በክፍለ አህጉሩ ቀድሞ
እንዲመሰረት ከረዱ ምከንያቶች አንዱ ነበር፡፡
በቅኝ ግዛት ዘመን የነበረው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ትስስር ከነፃነት በኃላ በተመሰረተው ኢኮኖሚያዊ ትብብር
/ትስስር/ መሰረት ሆኖ አገልግሏል፡፡ ከአአድ ስኬቶች መካከል የሚጠቀሰው የኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ
ትብብሮች በየክፍለ አህጉሩ እንዲመሰረቱ ማድረጉ ነው፡፡ ውጤታማ ከሆኑ ክፍለ-አህጉራዊ /ከባቢያዋ/
የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች አንዱና ዋነኛው የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማህበሰረሰብ /ሳድክ/ ነው፡፡
ሳድክ የድሮ ስሙ የደቡባዊ አፍሪካ ልማት አስተባባሪ ኮሚቴ Southern African Development coordination
committee- SADCC/ ነበር፡፡ ሳድክክ የደቡባዊ አፍሪካ አገሮችን ከአፖርታይድ ደቡብ አፍሪካ ኢኮኖሚ
ጥገኝነት ለማላቀቅና ለአካባቢው ተስማሚ የሆነ /ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ በስተቀር/ የአካባቢውን አገሮች
በአባልነት አቅፎ በመካከላቸው የልማት ትብብር ለመፍጠር ታስቦ የተቋቋመ ኢኮኖሚያዊ ክፍለ-አህጉራዊ
ድርጅት ነበር፡፡ የመጀመሪያው ሳድክክ ጉባኤ የተካሄደው በአሩሻ ታንዛኒያ እ.አ.አ በ 1979 ዓ.ም ሲሆን አንጎላ ፣
ቦትስዋና ፣ ሞዛምቢክ ፣ ታንዛኒና ዛምቢያ እንዲሁም ከእርዳታ ሰጭ መንግስታትና ዓለማቀፍ እርዳታ ሰጭ
ተቋማት ወኪሎች በተገኙበት ነበር፡፡ ሌሎች ፣ ስዊዘርላንድ ማላዊና ዚምባቡዌ እ.አ.አ በ 1980 ዓ.ም ሲቀላቀሉ
ናሚቢያ ደግሞ በ 1900 ዓ.ም አባል ሆናለች፡፡
እ.አ.አ በ 1990 ዎቹ መጀመሪያ የሳድክክ አባል መንግስታት ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ውህደት ለመምጣት እንዲሰሩ
ተስማሙ፡፡ ዘመኑ አረመኔውና ዘረኛው የአፖርታይድ ስርአት የተንኮታኮተበትና በምትኩ ነፃዋ ደቡብ አፍሪካ
ሪፐብሊክ በዝነኛው ፀረ- አፖርታይድ ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ መሪነት የተወለደችበት ጊዜ ነበር፡፡ ስለሆነም
ከአፖርታይድ የተላቀቀችውና በአፍሪካ የግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ለአካባቢው የተሻለ
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ሁኔታ ልትፈጥር የምትችልበት እድል ተፈጠረ፡፡ ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ ወደ
ድርጅቱ ከመግባቷ በፊት የሌሎች አባል መንግስታት ጥቅም እንዳይነካ መጠበቅ የሚያስችል ዝግጅት ማድረግ
ነበረባቸው፡፡
ተግባር፡- 5.10
ተማሪዎች ደቡብ አፍሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚውን ይዛ ያለ ቅድመ ዝግጅት ወደ ሳድክክ ድርጅት አባልነት
ብትቀላቀል በሌሎች አባል መንግስታት ላይ ሊፈጥር የሚችለው ስጋት ምንድን ነው፡፡
እ.አ.አ በ 1992 ዓ.ም ዊንድ ሆክ /ናሚቢያ/ በተደረገው ስብሰባ የወቅቱ የሳድክክ አባል መንግስታት ሳድክክን
በማፍረስ በምትኩ የደቡባዊ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብን - ሳድክ /Southern Africa Development
Community – SADC/ መሰረቱ፡፡ የሳድክክ አላማ የነበረው የአካባቢውን አገሮች ኢኮኖሚ እርስ በርሱ
በማስተሳሰር ከደቡብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ጥገኝነት ነፃ ለመውጣት ሲሆን የሳድክ አላማ ግን የክፍለ-አህጉሩን
ኢኮኖሚ ቀስ በቀስ ግን በዘላቂነት በማዋሀድ የጋራ ልማት ለማምጣት ነው፡፡ የሳድክ የእረጅም ጊዜ እቅድ እንደ
አውሮፖ ያለ የኢኮኖሚ ህብረት በአካባቢው መመስረት ነው፡፡
የምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን ኢጋድ /Inter Governmental Authority on
Development IGAD/
የበይነ መንግስታቱ ባለስልጣን የተቋቋመው እ.አ.አ በ 1986 ዓ.ም በጣም ጠባብ በሆኑ የድርቅና በርሀማነትን
በክፍለ አህጉሩ መስፋፋትና በጋራ ለመከላከል ታስቦ ነበር፡፡ ከምስረታው ጀምሮ በተለይም እ.አ.አ ከ 1990 ዎቹ
ወዲህ ኢጋድ ስለአካባቢው አገሮች የፀጥታና የፖለቲካ ችግሮች አስፈላጊ የመወያያ መድረክ እየሆነ መጣ፡፡
ኢጋድ ዋና መቀመጫውን ጅቡቲ አድርጎ ኤርትራ ፣ ኢትዩጵያን፣ ጅቡቲን፣ ሶማሊያን፣ ኬንያን ሱዳንና
ኡጋንዳን በአባልነት አቅፏል፡፡
የኢጋድ መስራቾች እ.አ.አ በ 1990 ዎቹ አጋማሽ ላይ ኢጋድ ወደ ተሟላ ክፍለ አህጉራዊ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ
ልማት፣ የንግድና ፀጥታ ስራዎችን የሚሰራ ልክ እንደ ሳድክና ኢኮዋስ የሆነ ጠንካራ ድርጅት እንዲሆን ወሰኑ፡፡
ኢጋድ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ ካነሳሱት ምክንያቶች አንዱ የድርጅቱ መወቅራዊና ድርጅታዊ አቅም
ዓላማውንና መርሆዎቹን ለመፈፀም የሚያስችል ስላልነበሩ ነበር፡፡ እ.አ.አ በ 1996 ዓ.ም በናይሮቢ በተካሄደው
ሁለተኛው የኢጋድ አባል አገሮች አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ አዲስ ቻርተር በማፅደቅ፣ መዋቅርና አዲስ ስም
በመስጠት የልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን ሆኖ ተቋቋመ፡፡ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሶስት
ቅድሚያ የሚሰጣቸው የትብብር መስኮችን ለየ፡፡
እነሱም፡-
1. ግጭትን መከላከል፣ ግጭትን መቆጣጠርና መፍታት
2. የሰብአዊ መብት ጉዳዩችን ማስከበር
3. የመሰረተ ልማት /በተለይ ትራንስፖርትና መገናኛ/ ማስፋፋት
4. የምግብ ዋስትናና በቀጠናው ማረጋገጥና የአካባቢ ጥበቃ ማድረግ ናቸው፡፡
ኢጋድ ክፍለ አህጉራዊ ደህንነትና ቀጣይ የኢኮኖሚ ልማት በአካባቢው ማበረታታት ፍላጎት ነው፡፡ ስለዚህ
የኢጋድ ዓላማዎች ሰላምና መረጋጋትን ማስፈንና በአገሮች ውስጥ ወይመ በመካከላቸው የሚከሰቱ ግጭቶችን
ለመከላከል፣ መዳኘትና በሰላማዊ መንገድ መፍታት ነው፡፡ ኢጋድ ከመፈጠሩ ጀምሮ በሶማሊያና በሱዳን ሰላም
ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
ምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ /ኮሜሳ/ (Common Market for eastern ans southern Africa
(COMESA)
የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገቢያ ወይም በእንግሊዘኛው አህፅሮተ ቃል ኮሜሳ የተመሰረተው በመላው
አፍሪካ ራእይ መሰረት የአህጉሩን አንድነት ለመፍጠር ከክፍለ አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ህብረት ለመጀመር
ተወስኖ እ.አ.አ በ 1994 ዓ.ም ነበር፡፡ ኮሜሳ የመጀመያውን ድርጅት ማለትም የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ
አመቺ የንግድ ቀጠና /ፒቲኤ/ (Pereferential trade area for eastern and southern Africa) (PTA) ይባል
የነበረውን ድርጅት በመተካት ነው፡፡ ኮሜሳ በነፃና ሉአላዊ አገሮች መካከል የተፈጥሮ የሰው ሀይል ሀብታቸውን
ለጋራ ህዝባቸው ጥቅም ተባብረው ለማልማት በስምምነት ያቋቋሙት ድርጅት ነው፡፡ ከኮሜሳ አላማዎች
መካከል አንዱ በአባል አገሮች መካከል የሚታየውን መዋቅራዊና ተቋማዊ ድክመቶች በማስወገድ ቀጣይነት
ያለው የጋራ ልማት ለማረጋገጥ ነው፡፡ ነገር ግን በኮሜሳ የኃላ ታሪክ በመነሳት አሁን ማድረግ የሚችለው ሰፋ
ያለ የኢኮኖሚና የንግድ ቀጠና በማቋቋም የእያንዳንዱን መንግስት ውስጣዊ ድክመቶች እንደችግሩ
ለማስተናገድና ለመፍታት መሞከር ነው፡፡
የአአድን ድክመቶች ግምት ውስጥ በማስገባት የአፍሪካ ዜጎች መሪዎቻቸውን አአድን ወደ ተሻለ ጠንካራ
ድርጅትነት የሚለወጡትን ሁኔታ በጥብቅ እንዲያጠኑ መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ስለሆነም በአፍሪካ የሚገኙ ወደ 54
የሚሆኑ ነፃ ብሄራዊ መንግስታትን ህብረት ፈጥሮ ለጠንካራ ሁለንተናዊ ትብብር የሚያበቃና የአፍሪካን
ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ባህላዊ ችግሮች መፍታት በሚያስችለው አቋምና ችሎታ እንዲደራጅ
ፈለጉ፡፡ አንዳንድ ሰዎች አአድ ፈርሶ በምትኩ እንደ አውሮፖ ህብረት ያለ ጠንካራ ድርጅት በአፍሪካ መመስረት
አለበት ብለው ጠየቁ፡፡ የአውሮፖ ህብረት እ.አ.አ በ 1990 ዎቹ ትብብርና ህብረትን በአውሮፖ አገሮች መካከል
በማፋጠን ውጤታማነቱን ያስመሰከረ አህጉራዊ ድርጅት ነው፡፡
እ.አ.አ በ 2001 ዓ.ም በሊቢያ የተሰበሰው የአአድ የመሪዎች ጉባኤ በአአድ ምትክ አፍሪካ ህብረትን ለማቋቋም
በሚያስችል ሐሳብ ላይ አትኩረው ተወያዩ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ህብረት ታሪካዊ ምስረታ የሚጀመረው
በ 1960 ዎቹ በክዋሜ ንክሩማህ በህብረቱ አባል መንግስታት መካከል ቅድሚያ ኮንፌዴሬሽን በሂደት የአፍሪካ
ህብረትን ለመፍጠር አአድን እ.አ.አ ግንቦት 25 ቀን 1963 ዓ.ም በአዲስ አበባና የአፍሪካ ኢኮኖሚ ማህበረሰብን
እ.አ.አ በ 1981 ዓ.ም የተደረጉት ጥረት አካል ነው፡፡
የአፍሪካ ህብረትን በመመስረት አሳብ መጀመሪያ የተነሳው በ 1990 ዎቹ አጋማሽ በቀድሞው የሊቢያ መሪ
የነበሩት ኮሎኔል ሙሀመድ አል-ቃዳፊ አነሳሽነት ነበር፡፡ የአአድ የመንግሰታት መሪዎች ሲርጥ /ሊቢያ/
ተሰብስበው የሲርጥ አዋጅ የተባለውን እ.አ.አ መስከረም 9 ቀን 1992 ዓ.ም ለአፍሪካ ህብረት ምስረታ ጥሪ
የሚደረገውን ሰነድ አፀደቁ፡፡ ስለሆነም ቅድመ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቶ የአፍሪካ ህብረት ደርባ /ደቡብ አፍሪካ/
ውስጥ እ.አ.አ በሀምሌ 9 ቀን 2002 ዓ.ም የመጀመሪያውን የምስረታ ስብሰባ የደቡብ አፍሪካ የወቅቱ
ኘሬዜዳንት በነበሩት ታቦ ምቤኪ ሊቀ መንበርነት ስራውን ጀመረ፡፡
የአፍሪካ ህብረት አባል ያለሆነ ብቸኛ አፍሪካዊነት አገር ሞሮኮ ብቻ ናት ፡፡ ምክንያቱም ሞሮኮ ከአፍሪካ ህብረት
በፊት የነበረውን አአድን እ.አ.አ በ 1984 ዓ.ም የምዕራብ ሰሀራ ብሄራዊ ፖሊሳርዩ ግንባርን መደገፋንና
በድርጅቱ የታዛቢነት ወንበር መፍቀዱን በመቃወም ነበር፡፡ ሆኖም ግን ሞሮኮ የድርጅቱ አባል ባትሆንም ቀድሞ
በአአድ አሁን ደግሞ በአፍሪካ ህብረት ጥቅሟን የሚያስጠብቅ ታዛቢ ያላት ሲሆን የአፍሪካ ህብረት አባል
አገሮች ከድርጅቱ የሚያገኙትን ጥቅም ሁሉ ማለትም እንደ የአፍሪካ ልማት ባንክ ካሉት ተቋማት እኩል
ታገኛለች፡፡
የአፍሪካ ህብረት መጀመያ በአባል አገር ወታደር በማስማራት ጣልቃ የገባው እ.አ.አ የግንቦት ወር 2003 ዓ.ም
በቡርንዲ የተደረጉ የተለያዩ የሰላም ስምምነቶችን ለመታዘብና ሰላም ለማስከበር ከደቡብ አፍሪካ ፣
ከኢትዩጵያ ፣ ከሞዛንቢክ የተወጣጣ የሰላም አስከባሪ ሰራዊት ነበር፡፡ በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት ሰራዊት
በላይቤሪያ ፣ ሩዋንዳ ፣ ሴራሊዩን ፣ ሱዳን ፣ ሶማሊያና ማሊ በመሳሰሉ አገሮች ሰላም ለማስፈን በተደረገው
ጥረት ከፍተኛ እርዳታ አድርጓል አሁንም ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያሰማራቸው ወታደሮች በተጠቀሱት
የአፍሪካ አገሮች ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የአፍሪካ ህብረት ብዙ በአህጉራዊ ደረጃ የሚተገበሩ አዳዲስ ጠቃሚ ሰነዶችን በማዘጋጀት ድርጅቱ ሲመሰረት
የተቋቋመበትንና በስራ ላይ ያሉትን አሰራሮችና ህጎች የሚደግፉና ክፍተት የሚሞላ አድርጎ በማዘጋጀት በስራ
ላይ አውሏል፡፡ ከእነዚህ መካከል
ሀ/ እ.አ.አ በ 2003 ዓ.ም የፀደቀው ሙስናን ለመከላከልና ለመዋጋት የሚያስችለው ስምምነት
ለ/ እ.አ.አ በ 2007 ዓ.ም የፀደቀው በዲሞክራሲ ፣ ምርጫና መልካም አስተዳደር ላይ የተዘጋጀው የአፍሪካ
ቻርተር
ሐ/ ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት የሚባለው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
የአፍሪካ ህብረት የሚከተሉት ውሳኔ ሰጪና አስተዳደራዊ አካላት አሉት፡፡ እነሱም
ሀ/ የህብረቱ ጠቅላላ ጉባኤ ሠ/ የአፍሪካ ፍርድ ቤት
ለ/ የህብረቱ ስራ አስፈፃሚ ረ/ ቋሚ የተወካዩች ኮሚቴ
ሐ/ የመላው አፍሪካ ፖርላማ ሰ/ የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ተቋማትና
መ/ የህብረቱ ኮሚሽን ሸ/ ልዩ ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ናቸው፡፡
የክለሳ ጥያቄዎች
1. የኢንዱስተሪዉ አብዮት ለአፍሪቃ በቅኝ ግዛት መያዝ የነበረዉን አስተዋጽኦ ተወያየበት
2. የበርሊኑ ጉባኤ ለምን ተካሄደ? ዋና ዋና ዉሳኔዎቹን ጥቀሱ፡፡
3. በእንግሊዝ፣በፈረንሳይና በሌሎች ሀገራት ቅኝ ግዛት የተያዙ የአፍሪካ ሀገራትን ዘርዝሩ፡፡
4. የአፍሪካዉያን ቀደምት ፀረ ቅኝ ግዛት ትግል ስኬታማ ያልነበረዉ ለምንድን ነዉ?
5. የአፓርታይድ ስርአት መገረጫዎችን ዘርዝሩ፡፡
6. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ዋና ስኬቶችና ድክመቶችን ዘርዝሩ፡፡
7. የአፍሪካ ክፍለ አህጉራዊ ድርጅቶች የሚባሉትን ዘርዝሩ፡፡
ምእራፍ ስድስት
የኢንዱስትሪ አብዩት ከሞላ ጎደል ከ 1750 ዓ.ም ጀምሮ በማምረት ስልት የተካሄዱ ለውጦችን የሚዳሰስ ነው፡፡
እነዚህም አዝጋሚና ውድ ከነበረው በእጅ ማምረት ፈጣንና ርካሽ ወደ ሆነው በማሽን የማምረት ሂደት
መሸጋገርና እንዲሁም በቤት ውስጥ በተለምዶ ከማምረት ተላቆ በሚገባ በተደራጀው ፋብሪካ ደረጃ ማምረት
መጀመሩን ያመለክታል፡፡
የኢንዱስትሪ አብዩት ሰፋ ባለ ሁኔታ ሲተነተን በዘመናዊ ማምረቻ መሳሪያ መጠቀምን፤ በአጠቃላይ በሰው ልጅ
የአኗኗር ሁኔታ ላይ ያስከተለውን ጠቀሜታና ለውጥ የሚቃኝ ነው፡፡ ከታዩ የስራ ውጤቶችና ከጊዜ አንፃር
የኢንዱስትሪ አብዩትን በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች መመደብ ይቻላል፡፡ እነርሱም፡-
የአሮጌው ወይም የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ አብዩት መለያ ባህርያትና በዚህ ዘመን የታዩት መሰረታዊ
ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ/ የመጀመሪያዎቹ የተወሳሰቡ ማሽኖች የተስፋፈበትና ቀደምት ፋብሪካዎች የተገነቡበት ዘመን ነው፡፡
ለ/ እንፋሎት የሀይል ምንጭ የሆነበትና ይህ ሀይል ለምርትና ለመጓጓዣ አገልግሎት መስጠት የጀመረበት ጊዜ
ነው፡፡
ሐ/ የከሰል ፣ የብረትና የአረርብረት ምርቶች በብዛት መመረት የታየበት ወቅት ነው ፡፡
መ/ አዲስ የመጓጓዣና የመገናኛ ዘዴዎች መጠቀም መሰረት የተጣለበት ዘመን ነው፡፡
አዲሱ የኢንዱስትሪ አብዩት ከ 1870 ጀምሮ እስከአሁን ድረስ በኢንዱስትሪ መስክ የተከሰቱትን ለውጦችን
የሚዳስስ ነው፡፡ በዚህ ዘመን የሰው ልጅ ፈጠራና ግኝት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፡፡ ይህ ግኝትና ፈጠራ
በኢንዱስትሪና በሰው ልጅ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ለውጥን አስከትሏል፡፡ ይህ አብዩት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡
በዚህ ዘመን የተከሰቱ መሰረታዊ ለውጦች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ሀ/ የኤሌክትሪክ፤ የነዳጅና የአቶሚክ ጉልበት በሀይል ምንጭነት ማገልገል መጀመራቸውና አዳዲስ
ኢንዱስትሪዎችን ለመጠቀም እገዛ ማድረጋቸው፡፡
ለ/ ሳይንስ ለኢንዱስትሪ ግንባታ ማገልገሉና እንደኘላስቲክ ናይለን ወዘተ የመሳሰሉት ሰው ሰራሽ ምርቶች
በብዛት ስራ ላይ መዋል፡፡
ሐ/ እንደ አውሮኘላን ፣ ሬድዩ ፣ ቴሌ{ዥን የመሳሰሉት አዳዲስና ፈጣን የመጓጓዣና የመገናኛ መሳሪያዎች
መፈልሰፍና ስራ ላይ ማዋል፡፡
መ/ በኮምፒዉተር የሚሰሩና በአጠቃላይ በኤሌክትሮኒክስ ጥበብ የሚደገፋ መሳሪያዎች /ማሽኖች/ መፈልሰፍ፣
ሠ/ በመሬት ዙሪያ የሚሽከረከሩና ወደ ሌሎች ኘላኔቶች በየጊዜው የሚላኩትን መንኮራኩሮች ስራ
የሚያጠቃልል ዘመን ነው፡፡
ተግባር 6.1
1. የኢንዱስትሪ አብዮት ለምን እንግሊዝ አገር ተጀመረ?
2. የኢንዱስትሪ አቢዮት አዎንታዊና አሉታዊ ገጽታዎች ከኢኮኖሚ፣ከባህል፣ከፖለቲካ እና
ከማህበራዊ አንፃራዊ በዝርዝር አብራሩ?
3. የኢንዱስትሪ አቢዮት በፋብሪካ ላይ የነበረው ውጤት አብራሩ?
4. የኢንዱስትሪ አቢዮት ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው ማለት ምን ማለት ነው ?
5. በመጀመሪያውና በሁለተኛው የኢንድስትሪ አቢዮት ክፍሎች የታየ ጉልህ ልዩነቶችን
በመዘርዘር ግለፁ?
6. የኢንዱስትሪ አቢዮት በአፍሪካ ለምን ዘገየ?
በኦውስትሪያ የተጣራው የአውሮፓ አገሮች ጉባኤ አላማው ከ 23 ቱ ዓመት የናፖሊዎን ጦርነት ማብቃት ጋር
ተያይዞ የአውሮፓ አገሮች የፖለቲካ ካርታ ለመወሰን እና በአውሮፓ ሰላምና ደህንነትን ለማስፈን የሚል እሳቤ
ቢኖረውም የተወሰኑ የአዉሮፓ ሀገራት ጠትቅም ማሰክበሪያ መሆኑ አልቀርም ፡፡ ለምሳሌ ከጉባኤው በጣም
ተጠቃሚ ከነበሩት መካከል አንዷ ኦውስትሪያ ነበረች ፡፡
በቬና ጉባኤ የኢጣልያ ግዛቶች እንደሚከተው ተከፋፍለዋል
ሀ. ሎምባርዲ እና ቬኒሲያ (በሰሜን ኢጣልያ የሚገኙ ግዛቶች ) በቀጥታ በኦስትሪያ ግዛት ውስጥ እዲካተቱ
ተደርጓል፡፡
ለ. ፓርማ ፣ሞዴና፤ቱስካኒ (ማዕከላዊ ግዛቶች )እንዲሁም ኔፕልስ በራሳቸው የሚተዳደሩ
ቢሆኑም በኦስትሪያ ተፅዕኖ ውስጥ መውደቃቸው አይቀሬ ሆኗል፡፡
ሐ. የፓፓል ግዛቶች (Papal States) ሮምን በመጨመር በሮም ሊቀ ጳጳስ (pope) ቁጥጥር ስርእንዲሆኑ
ተደርጓል ፡፡
መ. ሳርዲኒያናፔድሞንት የሚባሉ ሁለት ግዛቶች በሰሜን ምዕራብ ኢጣልያ የሚገኙ ሲሆን
ከውጭ ቁጥጥር ወይም ተፅዕኖ ነፃ የነበሩት ራስ ገዝ ግዛቶች ሆነዋል ፡፡ በመሆኑም
የውህደት ንቅናቄው ዋና ፊታውራሪ በመሆን ይታወቃሉ ፡፡
2. የኦስትሪያ መንግስት ተቃውሞ፡
የኦስትሪያ መሪዎች በጣልያን ህዝቦች ላይ የነበራቸው ተፅዕኖና የበላይነት እንዲቀጥል ወይም ጥቅማቸውን
ለማስከበር የውህደቱን ንቅናቄ በጥብቅ ተቃውመዋል ብሎም ጸረ-ውህደት ንቅናቄ ማራመድ ችለዋል፡፡
በመሆኑም የውህደት ንቅናቄ ሂደቱ ሊጓተት ችሏል፡፡
3. የካቶሊክ ቤተክርሲቲያን መሪዎች ተቃውሞ
ሊቀጳጳሱና ሌሎች ቀሳውስት አንድ የተዋህዶች ጠንካር ኢጣሊያ እንድትመሰረት ፈቃደኛ አልነበሩም
ምክንያቱም ደግሞ በፓፓል ግዛቶች የነበራቸውን ስልጣንና ጥቅማጥቅም ለማስቀጠል ወይም ላለማጣት ነበር
፡፡
4. በንቅናቄ መሪዎች መካከል የዓላማ ልዩነት መኖር
ምንም እንኳ የኢጣልያ ውህደት እውን መሆን የመሪዎች የጋራ ዓላማ ቢሆንም በንቅናቄ መሪዎች መካከል
ወደፊት የሚፈጠረው የመንግስት አደረጃጀት እና መዋቅር የተለያየ አመለካከት መኖር ውህደቱን ካጓተቱት
ምክንቶች አንዱ ነበር ፡፡
ለምሳሌ፡- ጁሴፔ ማዚኒና ጁሴፔ ጋሪባልዲ የሚባሉ የውህደት ንቅናቄ መሪዎች የሚመሰረተው መንግስት
ዲሞክራሲያዊ ሪፕብሊክ እንዲሆን ይፈልጉ ነበር ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ካውንት ካሚሎ ዲ. ካቮር የተባለው መሪ
የለዘብተኛ (ሊብራል)መንግስት ስርዓት ምስረታ እንዲኖር ይፈለግ ነበር ፡፡
ጅኦባርቲ የተባለው ንቅናቄ መሪ ቡድን ደግሞ በሊቀጳጳሱ መሪነት የፌዴሬሽን መንግስት እዲመሰረት
ይፈለግ ነበር ፡፡ በነዚህ የተለያዩ አመለካከቶች መኖር ምክንያት ውህደት ከተፈለገው ጊዜ በፊት
እዳይፈፀም ሆኗል፡፡
ተግባር፡-6.2
1. የኦስትሪያ መንግስት የኢጣልያ ውህደት ንቅናቄ ለምን ተቃወመ?
2. ሊቀጳጳሱ አገዛዝ ስር የነበሩ የኢጣልያ ግዛቶችን ስም ዘርዝሩ?
3. የቬና ጉባኤ ለኢጣልያ ውህደት ንቅናቄ የነበረውን አሉታዊ ተፅዕኖ በግልፅ አብራሩ ?
4. ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ማለት ምን ማለት ነው?
የኢጣልያ ህዝቦች በተለይ ከናፖሊዎን ጦርነት በኃላ የአንድነትና ጠንካራ የሀገር ፍቅር ስሜታቸው መጨመሩ
ለውህደቱ እንደ አንድ አበረታች ምክንያት ሆኗል፡፡ ብሎም የጥንታዊ ሮምን ዝናና ክብር እዲሁም ኃያልነት
ለመመለስ ተነሳስተዋል ፡፡ በተጨማሪ ኢጣልያ የተሓድሶ (renaissance) ንቅናቄ መስራችና መናኸሪያ መሆኗ
ማነቃቂያ ሆኗታል፡፡
2. ቁርጠኛና መንፈሰ ጠንካራ አገር ወዳድ ዜጎች ብቅ ማለት
ተመዘገበ፡፡ ከጦርነቱ ማግስት በተደረጉ ስምምነቶች መሰረት ኒስይና ሳቮይ ለፈረንሳይ ተሰጡ፡፡ ኦስትሪያ
ሎምባርዲን ለኢጣሊያ አስረከበች፡፡
በሚቀጥሉት አመታት ለውህደቱ ስኬት መገለጫ የሚሆኑ ተግባራት ተካሂደዋል፡፡ በ 1860 ዓ.ም ጋሪባልዲ
ከሽዎች ጋር /Thousands or red shirts/ ከሰሜን ወደ ደቡብ በመዝመት ሲሲሊንናኔኘልስን ነፃ አወጣ፡፡
በመቀጠል ወደ ሰሜን ያደረገው ግስጋሴ በካቮር እምቢተኝነት ተገታ፡፡ በተመሳሳይ አመት የፓፓል ግዛቶች
ከሮም በስተቀር እና ሌሎች የመካከለኛው የኢጣሊያን ክፍል ግዛቶች ወደ ሰሜን የኢጣሊያን ክፍል ተቀላቀሉ፡፡
ስለዚህ ውህደቱ የላይኛውና የታችኛው የኢጣሊያ ክፍሎች የጋራ ትግል ነበር ማለት ይቻላል፡፡ በሌላ በኩል
ደግሞ ውህደቱ የላይኛው ህብረተሰብ ክፍልና የታችኛው የህብረተሰብ ክፍል አንድነት ትግል ውጤት ነበር፡፡
በ 1861 ዓ.ም ከሮምናቬኒሲያ በስተቀር ሌሎች ግዛቶች በውህደቱ ውስጥ በመቀላቀል የኢጣሊያ ግዛት
/The kingdom of ltaly / ታወጀ፡፡ ቪክተር አማኑኤል የኢጣሊያን ንጉስ ሆኖ ተሾመ፡፡ በ 1866 ዓ.ም
በተደረገው የኘሩሽያና የኦስትሪያ ጦርነት /የሳድዋ ጦርነት/ ኦስትሪያ ስትሸነፍ ኢጣሊያ ለኘሩሽያ
በማገዟ ከጦርነቱ ማግስት በተደረገው ስምምነት ቬንስያን አገኘች፡ መጨረሻዋ የኢጣሊያ ግዛት ሮም
ወደ ውህደቱ የገባቸው ደግሞ የፈረንሳይና ኘሮሽያ ጦርነት ተከትሎ ነበር፡፡ ፈረንሳይ ሮም ላይ
አስፍረው የነበረውን ሰራዊት ከኘሮሽያ ጋር በምታደርገው ጦርነት ስታስወጣ ሮም ነፃ ወጣች ፡፡
የኢጣሊያ ዋና ከተማ ሆና ተመረጠች ውህደቱም በ 1870 ዓ.ም ተጠናቀቀ፡፡
ተግባር፡-6.3
1.የኢጣልያ ውህደት ንቅናቄ ለምን ለረጅም ጊዜ ተካሄደ? ምክንያቶችን መዘርዘር በግልፅ አብራሩ ?
2.ከኢጣሊያ ውህደት ንቅናቄ ወቅት ዲሞክራሲ ሪፐብሊክ እንዲመሰረት የሚፈልጉ መሪዎች እነማን
ነበሩ ?
3.በኢጣሊያ ውህደት ንቅናቄ ወቅት የመሪነት ሚና የነበራት ግዛት ማን ነበረች ?
4.ለኢጣሊያ ውህደት መሳካት ምክንያት የነበሩት ጉዳዩችን በመዘርዘር አብራሩ ?
የጀርመን መዋሀድ በአውሮፖም ሆነ በአለም ታሪክ እና ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲታይ ሆኗል ወይም
እንደትልቅ ምዕራፍ ይቆጠራል፡፡
ተግባር፡6.4
ተማሪዎች የጀርመን ውህደት አውን መሆን በአውሮፖም ሆነ በአለም ታሪክ እንደ ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ
የሚወሰደው ለምን ይመስላችል?
ለጀርመን ውህደት ንቅናቄ አዎንታዊ ምክንያቶች ና እንቅፋቶች ዘርዝሩ
በምንም አጋጣሚ ኦስትሪያና ፈረንሳይ በአውሮፓ ምድር ጠንካራና የተዋሀደች ጀርመንን ማየት አፈልጉም
ነበር ፡፡ ይልቁንም የተበታተነች አቅም የሌላት ጀርመን ሆና እድትቀጥል ይፈልጉ ነበር ፡
ተግባር 6.5
ተማሪዎች ኦውስትሪያም ሆነች ፈረንሳይ የጀርመንን ውህደት ለምን ተቃወሙ? ምክንያቶችን በግልፅ
አብራሩ፡፡
ታናናሽ መንግስታት ውህደቱን በበጎ ጎኑ ያለማየታቸው ምክንያት ከብዙ አቅጣጫ ሊታይ ይችላል፡፡ በአንድ
በኩል ውህደቱን የእነሱን ህልውና እና ውክልና እዲሁም ጥቅም የሚያሳጣ መስሎ ስለታያቸው በሌላ በኩል
ደግሞ የታላላቅ መንግስታት ተፅዕኖ በማፍራት ለውህደቱ ፍቃደኛ አለመሆን አዝማሚያና በነበረው ሂደት
የመቀጠል ፍላጎት ነበራቸው፡፡
3.የጀርመን ህዝቦች በሃይማኖት ፣ በባህል እና በኢኮኖሚ መለያየት
ለምሳሌ፡- በኢኮኖሚ ረገድ የሰሜን ጀርመን መንግስታት ህዝቦች በንግድና አነስተኛ ኢንዱስትሪ የሚተዳደሩ
ሲሆኑ በስልጣኔም ከደቡብ መንግስታት የተሻለ ደረጃ ነበራቸው፡፡ በተቃራኒው የደቡብ ህዝቦች በእርሻ
የሚተዳደሩ መሆኑ ለውህደቱ እንደ ልዩነቱ መፍጠሪያ መንገድ በመሆን ሂደቱን አጓቶታል፡፡ በሃይማኖት ዘርፍ
ደግሞ የሰሜናዊ ጀርመን ህዝቦች በብዛት የፕሮቴስታንት ዕምነት ተከታይ ሲሆኑ የደቡቦች ደግሞ የካቶሊክ
ዕምነት ተከታይ ነበሩ፡፡ ስለሆነም የሃይማኖት ልዩነት ሌላ መሰናክል በመሆን የውህደቱ ሂደት በማዘግየት የራሱ
ሚና ነበረዉ፡፡
ጠንካራ የብሄራዊ ስሜት በህዝቦች ዘንድ እንዲኖር የተለያዩ ምሁራን ፣ የታሪክ ሰዎች
፣መፅሐፍት ፣ፍላስፋዎች ወዘተ..ታላቅ ሚና ተጫውተዋል ፡፡
ተግባር 6.6
ጠንካራ ብሄራዊ ስሜት ማለት ምን ነው ? እዴትስ ይመጣል ?
ተግባር 6.7
የኢኮኖሚ ውህደት ለፖለቲካ ውህደት ያለውን አስተዋጽዖ ግለጹ
የጀርመንን ውህደት በፊታውራሪነት ትመራ የነበረች ፕሩሽያ ስትሆን ውህደቱ ግብ እንዲሚታ ከፍተኛ
መስዋት ያደረጉ መሪዎችም የመጡት ከዚሁ ነበር ፡፡ ለምሳሌ ያህል ዊሊያም አንደኛና ኦቶ ቮን ቢስማርክን
በቀዳሚነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በ 1862 ዓ.ም ቢስማርክ ለፕሩሽያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኖ መመረጡ ለጀርመን
ውህደት ትልቁ ምዕራፍ ወይም ወሳኝ ወቅት ተደርጎ ይወሰዳል ፡፡
የቢስማርክ ሹመትን ተከትሎ በፕሩሽያ ፓርላማ ውስጥ የነበረውን ውዝግብና አለመግባባት በኃይልም ቢሆን
በመፍትሄ አግኝቷል፡፡ የቢስማርክ የመጀመሪያው እርምጃው የወታደር ግንባታ ሆኗል፡፡ ለወታደር ግንባታውም
ገንዘብ ወሳኝ መሆኑን ያለፓርላማው ፍቃድ የወታደሩን በጀት በመጨመር ጠንካራ ሰራዊት መመስረት ችሏል፡፡
ለፓርላማው ባደረገው ንግግርም የጀርመን ውህደት የሚሳካው በጩኸት ወይም በድምፅ ብልጫ ሳይሆን
በሃይል እና በደም (blood and lron policy) እንደሆነ በግልፅ አስረድቷል፡፡
የቢስማርክ ጠላትን በተናጠል የማጥቃት ስልት ኦስትሪያ ተጠናክሮ ቀጠለ ፡፡ ኦስትሪያ ቁጥር አንድ የጀርመን
ውህደት ጠላት መሆኑን በመረዳት ሁለተኛ ጦርነት ከኦስትሪያ ጋር በ 1866 ዓ.ም ተደረገ ፡፡ ይህም ጦርነት
የሳድዋ ጦርነት ወይም የሰባት ስምንት ጦርነት ይባላል፡፡ በዚህ ጦርነት ፕሩሽያ ለኢጣልያ ጋር በመተባበር
ኦስትሪያ ድል አደረገች፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ የተመዘገበው ድል ለፕሩሽያ ውህደት ትልቅ ስኬት ነበር ፡፡ ከጦርነት
በኋላ በተደረገ ስምምነት መሰረት ፡
ቬኒሲያ ለኢጣልያ ተሰጠች
ሆልስቲን የኦስትሪያ አካል ሆነች
በጀርመን ኮንፌዴሬሽን የኦስትሪያን የበላይነት አከተመ
በ 1867 ዓ.ም የሰሜን ጀርመን ኮንፌዴሬሽን በፕሩሽያ የበላይነት የተመሰረተ፡፡
ነገር ግን የደቡብ ጀርመን መንግስታት እስካሁን ድረስ የውህደቱ አካል አልሆኑም ፡፡ ሆኖም የጀርመን
ውህደት በስኬት ጎዳና ለሆኑን ማወቅ ይቻላል ፡፡ለጀርመን ውህደት የመጨረሻው እና ወሳኝ ጦርነት
የሰዳን ጦርነት ነበር፡፡ የተኬሄደውን ከ 1870 እስከ 1871 ዓ.ም ነበር::
ተግባር 6.8
- ኮንፌደሬሽን ማለት ምን ማለት ነው ? የጀርመን ኮንፌደሬሽን ለመጀመሪያ ጊዜ መቼ ተመሰረተ?
የሰዳን ጦርነት የተከሄደው በጀርመንና በፈረንሳይ መካከል ሲሆን የጦርነቱ ውጤትም በጀርመን የበላይነት
ተጠናቋል፡፡ በዚህ ጦርነት ወቅት የደቡብ ጀርመን መንግስታት ከሰሜን ጀርመን ጋር በመቀላቀል የጋራ
ጠላታቸውን (በፈረንሳይ) ማሸነፍ ችለዋል ፡፡ በናፖሊወን 3 ኛ የሚመራው የፈረንሳይ ሰራዊት ተሸነፈ
ቀጥሎም የፍራንክፈርት ስምምነት ተደረገ፡፡
ስለዚህ የጀርመን ውህደት በ 1871 ዓ.ም በድል ተጠናቀቀ፡፡ ለውህደቱ መጠናቀቅ የሰሜኑ የጀርመን ክፍል
ትልቁን ድርሻ ወይንም አስተዋፅኦ ይወስዳል፡፡ ዊሊያም 1 ኛ የጀርመን ንጉስ ነገስት ሲሆን ቢስማርክ ደግሞ
መርዓተ መንግስት (chancellor) ሆኗል፡፡
የደቡብ አሜሪካ መንግስታት የኢኮኖሚ መሰረታቸው እርሻ ሲሆን የባሪያ ጉልበት ደግሞ ዋነኛው የጉልበት
ምንጭ ነበር፡፡ የእርሻ ዘዴው ዘመናዊ ሳይሆን ሰፊ የሰው ጉልበትን መሰረት ያደረገበት ሲሆን በተቃራኒው
የሰሜን አሜሪካ መንግስታት ደግሞ ኢኮኖሚያቸው የተመሰረተው በንግድና ኢንዱስትሪ ሲሆን ባርነትን
ወይም የባሪያ ጉልበትን ይቃወሙ ነበር፡ በሌላ በኩል ደግሞ የደቡብ አሜሪካ ግዛቶች ወደ አገር የሚገቡ
ሸቀጦች ዝቅተኛ ቀረጥ እንዲጣልባቸው ሲፈልጉ ሰሜኖች ደግሞ ከፍተኛ ቀረጥ እንዲጣልባቸው ይፈልጉ
ነበር፡፡ የሰሜኖቹ ዋና አላማ የአገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ውጤትን ለማበረታት እና ኢንዱብትሪያቸው
እንዲያድግ በማሰብ ነበር፡፡
ተግባር፡- 6.9
- ተማሪዎች ከውጭ ሀገሮች በሚገቡ ሸቀጦች ላይ ወይም ዕቃዎች ላይ ከፍተኛ ቀረጥ መጣል ምን አገራዊ
ፋይዳ አለው? ክፍል ውስጥ በቡድን በመሆን ተወያዩበት፡፡
2.ፖለቲካዊ ምክንያት
የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች ፌደራላዊ መንግስትን ሲደግፍ የደቡብ አሜሪካ ግዛቶች ኮንፌዴሬሽን እንዲመሰረት
ይፈለጉ ነበር፡፡ በዚህም አግባብ ሰሜኖች የጋራ የሆነ ህገ-መንግስታዊ መብት መከበርን ሲደግፉ ደቡቦች ደግሞ
እያንዳንዱ መንግስት የግል መብት መከበር ላይ ትኩረት ያደርጉ ነበር፡፡
3.ማህበራዊ ምክያት
የባርነት ጉዳይ በሁለቱ የአሜሪዊ ህዝቦች ዘንድ የጥላቻ ወይም ቅራኔ መፈጠር ዋነኛ ምክንያት ነበር፡፡ ይህም
ማለት የሰሜን አሜሪካ ህዝቦች የባሪያ ጉልበት መጠቀምን ሲቃወሙ የደቡብ አሜሪካ ህዝቦች ደግሞ የባሪያ
ጉልበት ዋና ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ የሰሜን አሜሪካ ህዝቦች ባርነት እንዲጠፋ በይፋ ባያዉጁም ወደ
ሌሎች ግዛቶች እንዲስፋፋ አይፈልጉም ነበር፡፡ የደቡብ አሜሪካ ህዝቦች የሰሜኖችን ጥቃት በመፍራት
መገንጠልን እንዳዋና መፍትሄ ለመውሰዳቸው ለእርስ በርስ ጦርነቱ መጀመር ዋነኛ ምክንያት ሊሆን ችሏል፡፡
ተግባር፡- 6.10
የባርነትና የባሪያ ንግድ ልዩነት ምንድን ነው ?
ከላይ የጠቀስናቸውን ዋና ዋና ምክንያቶች እንዳሉ ሆነው በሰሜንና በደቡብ አሜሪካ ግዛቶች መካከል ቅራኔ
እንዲጨምር ያደረጉ ወይም እንዲፈጠር ያደረጉ ምክንያቶች አልጠፉም፡፡ ለምሳሌ በ 1850 ዎቹ የደቡብ
አገሮች የዲሞክራቲን ፖርቲው የምክር ቤት ውክልና በሰሜን የሪፐኘሊካን ፖርቲው ብልጫ ሲወሰድባቸው
የደቡቦች የመገንጠል ሀሳብ እንዲጠናከር አድርጓል፡፡ ምክንያቱም በደቡቦች ህዝቦች ዘንድ የሰሜኖች የፖለቲካ
ስልጣን የበላይነት መብቱ ለባርነት መጥፋት ስጋት ነው ብለው ያስቡ ስለነበር ነው፡፡ በእርግጥ ከጥንት ጀምሮ
የደቡብና የሰሜን አሜሪካ ግዛቶች የም/ቤት ውክልና ልዩነት ውዝገብ ሲያስነሳ የቆየ ጉዳይ ነበር፡፡ ነገር ግን
ለመገንጠል የሚያደርስ አልነበረም፡፡ በመደራደርና በመግባባት ልዩነታቸውን ሲፈቱ ቆይተዋል፡፡ የሪፐብሊካኑ
ፖርቲ በ 1854 ዓ.ም ከተመሰረተ በኃላ የብዙ አሜሪካንን ቀልብ መማረክ መጀመሩ ብሎም የቀድሞ ታዋቂ
ሰዎችና የዲሞክራቲክ ፖርቲ አባላትን ድጋፍ ማግኘቱ ለደቡብ አሜሪካዉያን የራስ ምታት መሆኑ አልቀረም፡፡
ስለዚህ የደቡብ አሜሪካ ህዝቦች መገንጠል አማራጭ የሌለው መፍትሄ አድርገው ተነሱ፡፡ በ 1859 ዓ.ም
በጆንብራውንስ አማካኝነት የተሞከረ የፀረ-ባርነት አመፅ የደቡቦች ልብ እንዲሸፍት በማድረግ ብሎም አብሮ
የመኖርን ተስፋ በማጨለም የመገንጠልን ጥያቄ የበለጠ አጠናክሯል፡፡ ብራውንስ የሞከረው እንቅስቃሴ
መጨረሻው ተይዞ በአገር መክዳት ወንጀል ተፈርጆ የሞት ቅጣትም ተፈረደበት፡፡ ይህ ያልተሳካ ሙከራ የደቡብ
አሜሪካ ህዝቦች የሰሜን ህዝቦች በተመሳሳይ አይን እንዲያዩዋቸዉ አድርጓል ማለትም ሁሉም የሰሜን
አሜሪካ ህዝቦች የፀረ-ባርነት አቋም እንዳላቸው በማሰብ በመገንጠልም እንደመፍትሄ ተወስዷል፡፡
በ 1860 ዓ.ም የአብርሀም ሊንከን ሪፐብሊካን ፖርቲውን በመወከል የአሜሪካ ኘሬዘዳንት ሆኖ መመረጥ
ሌላኛዉ የመገንጠልን ጥያቄ ያባባሰ ምክንያት ነበር፡ ምክንያቱም በደቡብ ህዝቦች ዘንድ አብርሀም ሊንከን
የፀረ-ባርነት አቋም እንዳለው በማሰብ ስልጣን በመያዙ የመጀመሪያው እርምጃ ባርነትን ማጥፋት ይሆናል
ማለታቸው አልቀረም፡፡ በእርግጥ አብርሀም ሊንከን ከመመረጡ በፊት 7 የደቡብ አገሮች /በባሪያ ጉልበት
የሚተዳደሩ/ በይፋ መገንጠላቸውን አሳውቀዋል፡፡ በአብርሀም ሊንከን መመረጥ በኃላ የሌሎች አራት አገሮች
ተጨምረው በአጠቃላይ የተገንጠሉ አገሮችን ብዛት 11 አደረጋቸው፡፡ እነዚህ አገሮች አንድ ላይ በመሆን
የራሳቸውን ኮንፌዴሬሽን መሰረቱ፡፡ ኮንፌዴሬሸኑ በጀፈርሰን ዴቪስ ይመራ ነበር፡፡ በእርግጥ ሁሉም በባሪያ
ጉልበት የሚተባዳደሩ መንግስታት ወደ ኮንፌዴሬሸኑ ተቀላቅለው ማለት አይቻልም፡፡ ለምሳሌ በደቡብና ሰሜን
አሜሪካ ድንበር አካባቢ የነበሩ አራት በባርነት የሚተዳደሩ (slave states) መገንጠልን በመተው ከውህደት ጋር
መቆየትን መርጠዋል፡፡ አገሮችም ሚሶሪ ፣ ዴላዌር ፣ ሜሪላንድ እና ኬንቱኪ ነበሩ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ቨርጂኒይ
ለሁለት ተከፈለች፡፡ ሰሜን ምዕራብ ቬርጂኒያ ውህደቱን ስትደግፍ ደቡብ ቬርጂኒያ ደግሞ በመገንጠል
ኮንፌዴሬሽኑን ተቀላቅላለች፡፡ ከዚህም አልፎ የኮንፌዴሬሽኑ መቀመጫ ከተማ /ሬችሙንድ/ ከቪርጅንያ
ከተማሪዎች አንዷ ነበረች፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሁለቱም ወገን /በሰሜንና በደቡብ/ የተቀላቀለ አመለካከት
የነበራቸው ህዝቦች መኖራቸው አልቀረም፡፡ለምሳሌ የካሊፎርኒይ /በውህደቱ ውስጥ የነበረች/ 20 ፐርሰንት
የሚሆኑ ህዝቦች የደቡብ ዲሞክራቲክ ፖርቲ ተወካይ ለነበረው ዕጩ ድምፃቸውን ሰጥተዋል፡፡
ሚያዝያ 12፤1861 ዓ.ም የደቡብ ወታደሮች በፌዴራሉ /የሰሜን/ ወታደር ላይ የመጀመሪያውን ተኩስ
ሲከፍቱ የጦርነቱ አይቀሬነት ይፋ ሆነ፡፡ ይህን ድርጊት ተከትሎ አብርሀም ሊከን የመገንጠልን ጥያቄ
ውድቅ በማድረግ ሁሉም የሰሜን ግዛቶች ሰራዊት እንዲልኩ አዘዙ፡፡ የእርስ በእርስ ጦርነቱም በ 11
የደቡብ ግዛቶች (confederate states of America led by Jefferson Davis) እና በ 23 የስሜን ግዛቶች
(Unionists led by Abraham lincoin) መካከል በይፋ ተጀመረ፡፡
ተግባር 6.11
ተማሪዎች የአሜሪካ የእርስ በእርስ ጦርነት አላማ ምንድን ነው ? ከተወያያችሁ በኃላ መልሱን ሪፖርት አድርጉ
?
በዚህ ምክንያቶች የማታ ማታ በሰሜን አሜሪካ የበላይነት ጦርነቱ ተጠናቋል፡፡ ምንም እንኳ ደቡብ
አሜሪካውያን በጦርነቱ ወቅት እንግሊዝና ፈረንሳይ ያግዙናል ብለው ቢገምቱም ያሰቡት ሳይሆን ቀርቶ
በፍፁም የበላይነት በበሜኖች ተሸንፈው እጅ ሰጡ፡፡
ተግባር 6.12
ደቡብ አሜሪካዉያን ለምን የእንግሊዝና ፈረንሳይን እርዳታ ተስፋ አደረጉ? ተማሪዎች እስኪ ምክንያቱን
መፅሀፍ በማንበብ ወይም የታሪክ ሰዎችን መጠየቅ መልሱን ለክፍል ሪፖርት አድርጉ
የጦርነቱ ውጤቶች
ከአራት አመታት በላይ የፈጀው የእርስ በእርስ ጦርነት በ 1865 ዓ.ም ሲጠናቀቅ በርካታ ማህበራዊ ፣
ኢኮኖሚይዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ውጤቶች ነበሩት፡፡
ተግባር 6.13
ተማሪዎች አንደኛው የአለም ጦርነት በባህሪው ምን አይነት ጦርነት እንደነበር ታውቃላችሁ
የአንደኛው አለም ጦርነት ኢምፔሪያሊስቶች ፍላጎታቸውንና አላማቸውን ለማሳካት ያካሄዱት ጦርነት ነው፡፡
ለነፃነት፣ ለሰላም ፣ ለዲሞክራሲ ወዘተ የተደረገ ጦርነት አልነበረም፡፡ ስለዚህ አንደኛው የአለም ጦርነት
በባህሪው የኢምፔሪያሊዝም ጦርነት ነው ለማለት ያስችላል፡፡ በዘመኑ የነበሩ የአውሮፖ ኃያላን መንግስታት
መካከል ቅኝ ግዛቶች፣ የተፅዕኖ አካባቢዎች ወዘተ በድጋሜ ለመቃረጥ የተካሄደ ጦርነት ነው፡፡
ኢምፔሪያሊስት ደረጃ በደረሱት የአውሮፖ ሀያላን መንግስታት መካከል አፍሪካን በቅኝ ግዛት
ለመያዝና የኢኮኖሚ የበላይነት ለማግኘት የታየን ከፍተኛ ፍክክር ነው፡፡ ኢምፔሪያሊዝም ብለን
የምንጠራው ለምሳሌ ከ 1 ኛው የአለም ጦርነት በፊት ከታዩት ከፍተኛ ፋክክሮች የሚከተሉት
ይገኙበታል ፡፡
ፈረንሳይና ጀርመን ሞሮኮን ለመቀራመት ባደረጉት ፋክክር ሁለት ጊዜ በ 1905 እና በ 1911 ከጦርነት
ጫፍ ደርሰዉ ተመልሰዋል፡፡
ፈረሳይና ጣሊያን ቱኒዥያን በቅኝ ግዛት ለመይዝ /በ 1881/ ተፎካክረው ነበር፡፡
ሩሲያና አውስትሪያ-ሃንጋሪ የባልካን ሀገሮችን ለመቆጣጠር በከፍተኛ ደረጃ ይፎካከሩ ነበር፡፡
እንግሊዝና ጀርመን በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ቅኝ ግዛት ለመያዝና ገቢያ ለማግኘት
ትንቅንቅ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
2. ብሔርተኝነት /Nationalism/
ተግባር፡6.16
ተማሪዎች ብሄርተኝነት እንዴት የአንደኛው የአለም ጦርነት መንስኤ እንደሆነ በቡድን ተወያዩ፡፡
ለአንደኛው የአለም ጦርነት መካሄድ በተለያዩ ሀገሮች የብሄርተኝነት ስሜት መቀስቀስ ምክንያት ነበር፡፡
ለምሳሌ ብንጠቅስ
የጀርመን ብሄርተኝነት (German nationalism)
ከ 1870-71 በጀርመንናፈረንሳይ መካከል በተደረገው ጦርነት ፈረንሳይ በመሸነፏ፤ ጀርመን የፈረንሳይን ሁለት
ግዛቶች ማለትም አልሳስናሎሬንን ነጥቃለች፡፡ስለዚህ ፈረንሳይ እነዚህን ግዛቶች ለማስመለስና ለመበቀል
አጋጣሚ በመጠቀም ላይ ነበረች ፡፡
የባልካን ብሄርተኝነት (Balkan Nationalism)
በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ የሚገኙት የባልካን አገሮች ከቱርክ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት የብሄርተኝነት ስሜት
ተቀጣጥሎባቸው ነበር፡፡ በተለይ በሰርቢያ ሕዝብ ዘንድ ታላቋን ሰርቢያ ለመመስረት ከፍተኛ ፍላጎት ነበር፡፡
ስለሆነም የሰርቢያ መንግስት በአውስትሪያ- ሀንጋሪ ግዛት የሚኖሩት ሰርቦች ገንጥሎ ወደ ሰርቢያ ለመቀላቀል
ትልቅ ምኞት ነበረው፡፡ በዚህ የተነሳ የሰርቢያና የአውስትሪያ- ሀንጋሪ መንግስታት ከፍተኛ ፍጥጫ ወይም ቅራኔ
ውስጥ ገብተው ነበር፡፡
3. ጦርኝነት (militarism)
ተግባር 6.17
የአውሮፓ ኃያላን መንግስታት በመካከላቸዉ በነበረው ከፍተኛ ፉክክር የተነሳ የወታደራዊ አቅማቸውን
ለማጠናከር ሩጫ ውስጥ ገብተው ነበር፡፡ እንግሊዝና ጀርመንም እንዱ አንዱን ለመቅደም የባህር ሀይል
ግንባታቸውን ተያያዙት፡፡
የአንደኛ የአለም ጦርነት ከመጀመሩ ቀደም ብሎ አውሮፓ በሁለት ወታደራዊ ካምፕ ወይም ቡድን ተካፍላ
ነበር፡፡ እነሱም ፡-ትሪፕል አሊያንስ እና ትሪፕል ኢንተንት በመባል ይታወቃሉ ፡፡በመቀጠል አንድ ባንድ
እንመለከታቸዋለን ፡፡
1.ትሪፕል አሊያንስ (የጀርመን ፣የአውስትሪያ- ሃንጋሪና የኢጣልያ ህብረት )
በ 1879 የአውሮፓ መአከላዊ ሃያላን የነበሩት ጀርመንና ኦውስትሪያ-ሃንጋሪ በህብረት ጠላትን የመከላከል
ወታደራዊ ስምምነት ተፈራረሙ ፡፡ ከሶስት አመታት በኋላ በ 1882 ዓ.ም ኢጣልያ ህብረቱን ተቀላቀለች
፡፡ በዚህም የጀርመን፤ የኦውስትሪያ- ሃንጋሪና የኢጣልያ ንብረት ተከናወነ ፡፡
ተግባር ፡6.18
ተማሪዎች ለጀርመን፤አውስትሪያ
ሃንጋሪና ኢጣልያ ህብረት መፈጠር ምክንያቶችን መጽሀፍ በማንበብ ወይም የታሪክ መምህራንን በመጠየቅ
ተረዱ ፡፡
ተግባር ፡-6.20
ተማሪዎች በአለንት ዘመን በሀገሮች መካካል አለመግባባት ሲፈጥር የሚሸመግላቸው አለም አቀፍ
ድርጀት ማን እደሆነ ታውቃላችሁ?
ከአንደኛው የአለም ጦርነት በፊት በሃገሮች መካካል አለመግባባት ቢፈጠር ወደ ጦርነት ከመሸጋገራቸው በፊት
የሚሸመግል ጠንካራ አለማቀፋዊ ድርጀት አልነበረም ፡፡ በ 1899 በሄግ ከተማ የተቋቋመው የአለም ፍርድ
ቤትም (hague tribunal) በአቅም ማነስ የተነሳ ሀገሮችን አስገድዶ የመዳኘት ሀይል እና የሰጠውን ውሳኔ
ተፈፃሚ የማድረግ ጥንካሬ አልነበረውም ፡፡ስለዚህ ሥርዓት አልበኝነት ሰፍኖ ነበር ለማለት ይቻላል፡፡
የጦርነቱ ፍንዳታ (outbreak of WWI)
ተግባር፡ 6.21
ተማሪዎች ለአንደኛው የአለም ጦርነት መፈንዳት የቅርብ መንስኤ (Immediate cause) ምንድን ነው?
ለአንደኛው የአለም ጦርነት መፈንዳት ሰበብ የሆነው የአውስትሪያ-ሀንጋሪ መስፍንና አልጋወራሽ የነበሩት
ፍራንሲስ ፈንዲናንድና ባለቤታቸው ሶፍያ በቦሲኒያ ዋና ከተማ ሳራጅቮ በጉብኝት ላይ እንዳሉ በሰኔ 28 1914
ዓ.ም መገደላቸው ነው፡፡ ግድያውን የፈፀመው የሰርቢያ ተወላጅ የሆነው ጋቭሪሎ ፕሪንሲፕ በመሆኑ
አውስትሪያ-ሀንጋሪ በሰርቢያ ላይ በሐምሌ 28 ቀን 1914 ዓ.ም ጦርነት አወጀች፡፡
ሩሲያ ወዳጇን ሰርቪያን ለመርዳት ጦሯን አንቀሳቀሰች፡፡ ጀርመንም የሩስያን እንቅስቃሴ በመቃወም በነሀሴ 2
ቀን በሩሲያ ላይ በነሀሴ 3 ቀን በፈረንሳይ ላይ የጦር አዋጅ አስተላለፈች፡፡ ጀርመን ፈረንሳይን ለመውጋት
ገለልተኛ ቤልጀየምን እንደመሸጋገሪያ ድልድይ ተጠቅማለች፡፡ እንግሊዝ ጀርመንን ለመውጋት ከጦርነቱ
መግባቷን አስታወቀች፡፡
ይህ ጦርነት ቀስ በቀስ ሌሎች መንግስታትንም እየጨመረ ወደ አለም ጦርነት እየተስፋፋ መጣ፡፡
ቱርክና ቡልጋሪያ ጀርመንና አውስትሪያ - ሀንጋሪን (ማዕከላዊ ሀይሎችን) በመደገፍ በጦርነቱ ገቡ፡፡
የፈረንሳይ ፣ የሩስያንና የእንግሊዝን ቡድን በመደገፍ ደግሞ ወደ ሰላሳ የሚደርሱ ሀገሮች በጦርነቱ
ተሰለፋ፡፡ ከእነዚም መካከል ዋና ዋናዎቹ ጃፖን ፣ ኢጣልያና ፣ አሜሪካ ናቸው፡፡ እነርሱም የተባበሩት
ኃይሎች (Alliied powers) በመባል በታሪክ ይታወቃሉ፡፡
ተግባር፡- 6.22
ተማሪዎች ኢጣሊያ ከትፊኘል ኢልያንስ ወጥታ ወደ ትሊኘል ኢንተንት የገባችበት ምክንያት ምንድን ነው?
አሜሪካ ወደ ጦርነቱ የገባችበት ምክንያትስ ምንድን ነው?
የአሜሪካ በጦርነቱ መሳተፍ ያመጣው ለውጥ ምንድን ነው?
የመጀመሪያው የአለም ጦርነት አሸናፊዎች ዋና አላማ አንዱ አለምን ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት
የሰፈነባት ለማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ጀርመን ዲሞክራሲያዊ ህገ-መንግስት ስትመሰርት ሌሎችን
በተመሳሳይ መልኩ መሄድ ጀምረዋል፡፡
ነገር ግን በ 1920 ዎቹ በጣሊያን የፋሽስት ስርዓት መሰንፋራት ጀመረ፡፡ በ 1922 የፋሽስት ፖርቲ በቤኒቶ
ሞሰለኒ ተመሰረተ፡፡ አላማውም ጣሊያንን ወደ ሮማ የአፄ ዘመን ግዛት ክብር ለመመለስ እንዲሁም የጣሊያንን
ብሄርተኝነት ለማጉላት ነበር፡፡ የአስተዳደር ስርዓቱ ሌላ መገለጫ ወታደራዊ አንባገነንነትና ስልጣንን ጠቅሎ
መያዝ ይገኙበታል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ አዶልፍ ሂትለር በጀርመን የናዚ ፖርቲን በመመስረት ስለጀርመን ብሄር የበላይነት ብቻ
በመስበክ ህዝቡን ወደሱ ማሰባሰብ ጀምሯል፡፡ ሂትለር ለጀርመን ህዝብ የቨርሳይለሱን ስምምነትን
እንደሚሽርና ለጀርመናውያንም ተጨማሪ መኖሪያ መሬት /ከጎረቤት ሀገሮች/ እንደሚያመቻች ገለጠ፡፡
በጃፓንም የነበረው አዝማሚያ ተመሳሳይ ነው፡፡ ስልጣንን ጠቅሎ የያዘ መንግስት በመመስረት በተለይ
ወደቻይና የመስፋፋት ህልም ነበረው፡፡ በዚህም መሰረት ከ 1932 ጀምሮ ማንቹሪያንና ሌሎች የቻይና
መደቦችን መቆጣጠር ቻለ፡፡
ተግባር 6.24
- ለሁለተኛው የአለም ጦርነት መጀመር ተጠያቂ ሀገራት እነማን ናቸዉ?ለምን?
- በሁለተኛው የአለም ጦርነት በሁለት ጎራ የተዋጉ ቡድኖች ማንና ማን ናቸዉ?
በሂደት ከላይ የጠቀስናቸው ሶስቱ ሀገራት በፍላጎታቸው በመሳሳብ የሶስትዩሽ ህብረት የሆነውን የአክሲስ
ጥምረት ወይም የሮም- ቶክዮ-በርሊን ህብረት በመመስረት በአለም ስጋት መሆን ጀመሩ፡፡ በዚህም መሰረት
ጀርመን ወደ አውሮፖ መስፋፋት በመጀመር በመጋቢት 1938 ኦስትሪያንን ወረረች፡፡ በመስከረም 1939
የቸኮዝላቪኪያን የተወሰነ ክፍል፤ ከስድስት ወር በኃላ ማለትም በመጋቢት 1939 የቀረውን ክፍል ተቆጣጠረች፡፡
በዚህ ብቻ ሳይበቃ በመስከረም 1/1939 የጀርመን ጦር ፖላንድን ለመያዝ ተንቀሳቀሰ፡፡ ለረዥም ጊዜ
ከጥቅማቸው አንፃር ምንም እርምጃ ሳይወስዱ የነበሩት የወቅቱ ሀያላን ፈረንሳይእንግሊዝ በመስከረም
3/1939 ላይ ጦርነት አወጁ፡፡
ባጠቃላይ ለሁለተኛዉ የአለም ጦርነት መጀመር ያበቁ ክስተቶች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸዉ፡፡
በጀርመን በኩል
በ 1935 የግዴታ የወታደርነት አገልግሎት መጀመር፤
ፈረንሳይን ከጥቃት ለመካከል እንዲረዳ ከወታደራዊ ቀጠና ውጭ እንዲሆን የተደረገው የራይን ግዛት
በጀርመን መያዝ፤
ጀርመን ከመንግታቱ ድርጅት በ 1933 መውጣቷ፤
የጀርመንን የህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት በማድረግ ለህዝቦች ተጨማሪ መኖሪያ በማለት ጀርመን
በ 1938 ኦስትሪያን መውረር
ሱዳንትላን የተባለው የቼኮዝላቪያ ክፍልን ጀርመን 3 ሚሊየን ጀርመናውያን ይኖሩበታል በሚል ሰበብ
ይገባኛል ማቅረቧ፤
የሙኒክ ስምምነት- የእንግሊዙ ኒቫይል ቸምበርሌይን (Neville chamberlain) የጣሊያኑ ሞሶለኒ፤
የጀርመኑ ሂትለር እና የፈረንሳዩ ዳላዲር(Daladier) ሱዳንትላንድን ለጀርመን እንዲሰጥ ወሰኑ፤
በዋናነት ከላይ እንተጠቀሰው የጀርመን ፖላንድን መውረር ለጦርነት መጀመር ምክንያት ሆኗል፤
በጣሊይን በኩል፡- ጣሊያን በ 1935 ኢትዩትጵያን ወረረች፡፡ ኢትዩትጵያም ለመንግስታቱ ማህበር አቤት
ብትልም ሰሚ አላገኝችም፡፡
በጃፖን በኩል፡- በ 1931 ጃፖን የቻይና ግዛት የሆነችውን ማንቹሪያን በመውረሯ ከመንግስታቱ ማህበር ቅሬታ
ሲነሳበት ከማህበሩ አባልነት ራሷን አገለለች፡፡
ከላይ እንደተገለፀው እነዚህ ሶስት ሀገራት ከ 1936 – 1937 የወታደራዊ ግንባር በመጀመሪያ የበርሊን ሮም
አክሲስ በመቀጠልም የበርሊን ሮም ቶክዮ ትሪአንግልን መሰረቱ፤
የጦርነቱ ሂደት
ጦርነቱ የተጀመረው ጀርመን በመስከረም 1/1939 ፖላንድን በመውረሯ ሲሆን ከሁለት ቀን በኃላ እንግሊዝና
ፈረንሳይ በጀርመን ላይ ጦርነት አወጁ፡፡ ይሁን እንጅ እንግሊዝና ፈረንሳይ የፖላንድን ህዝቦች ለመርዳት
ጦራቸውን አላኩም፡፡ ይህ ዝም ብሎ የማየት ፖሊሲ (watch and see policy) ፎኒ ዋር (phoney war) ወይም
‘’sitting war’’ በመባል ይጠራል፡፡
ሶብየት ህብረት የጀርመን መስፋፋትን በመፍራት የፖላንድን ምዕራባዊ ክፍል ተቆጣጠረች፡፡ ከ 1920 ጀምሮ
በፖላንድ ስር የነበሩት ምዕራብ ቤላሩስና ምዕራብ ዩክሬን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ሆኑ፡፡ በሰኔ 1940 የባልቲክ
ሪፐብሊክ የሆኑት ሉቲኒያና፤ ላቲቪያና ኢስቶንያ ወደ ሩሲያ ተቀላቀሉ፡፡
በፊንላንድ በኩል የሚደርሰውን የጀርመን ወረራ እሰጋለሁ በሚል ግጭት ተነስቶ ህዳር 1939 የተጀመረው
ጦርነት በየካቲት 1940 በፊላንድ ሽንፈት ተጠናቀቀ፡፡ በ 1940 በሳርቢያ የተባለውን ግዛት ለሩስያ አስረከበች፡፡
ጀርመን ፖላንድ ካሸነፈች በኃላ ወደ ሌሎች የአውሮፖ ሀገራት ፊቷን አዞረች ፡፡ ስለሆነም በሚያዝያ 9/1940
ዴንማርክና ኖርዌይን ወረረች፡፡ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኃላ የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቸምበርሌይን
በዊንስተን ቸርችል ተተኩ፡፡ እንግሊዝ እነዚህን ሀገራት ለውርደት ያደረገችው ጥረት አልተሳካም፡፡ በ 1940
ተመሳሳይ እጣ ለቤልጅየምና ሆላንድ ደረሳቸው፡፡ ከአንደኛው የአለም ጦርነት በተሻለ ቤልጅየሞች ሊዋዝም
ድሉ ለጀርመኖች ከመሆን አልዘለለም፡፡ ፈረንሳይ በጀርመን እጅ ልትወድቅ ጫፍ ላይ በነበረችበት ወቅት በሰኔ
10፤1940 ሞሰለኒ በፈረንሳይ ላይ ጦርነት አወጀ፡፡ ከእንግሊዝና ፈረንሳይ ዕቅድ በተቃራኒው ጠራቸውን
ያንቀሳቀሱት የጀርመን ሀይሎች በኒዘርላንድና በቤልጀየም በኩል የፈረንሳይና እንግሊዝ ጥምር ጦርን አሸነፋ፡፡
በሰኔ 22፤1940 በሂትለር ፊት አውራሪነት የፈረንሳይ ዕጅ መስጠትን የሚገልፅ ስምምነት ተፈረመ፡፡
ከፈረንሳይ ሽንፈት በኃላ የጀርመን ኢላማ እንግሊዝ ሆነች ፡፡ የእንግሊዝን ጦርን ከማዳከምም ጀርመኖች
ለንደንና ሌሎች ከተሞችን በአውሮኘላን ቦንብ ደበደቡ፡፡ በጦርነቱ ሂደትም ጀርመን፣ጣሊያንና፣ጃፖን ከጦርነቱ
በኃላ አለምን ለመከፋፈል እንዲሁም አዲስ ስርዓት ለመፍጠር የሶስትዩሽ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡ ከ 1940 –
1941 ሀንጋሪ ፣ ሩሲያ ቡልጋሪያና ችኮዝላቫኪያ ስምምነቱን ሲቀላቀሉ ዩጎዝላቪያ ስምምነቱን አልቀበልም
ብላለች፡፡ ስለሆነም በ 1941 በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ አሜሪካ በጦርነቱ መጀመሪያ ላይ ባትሳተፍም ኮንግረሱ
በየካቲት 1941 ማንኛውም ጀርመንና ጣልያንን ለሚወጋ ሀገር ጦር መሳሪያ ለመርዳት በኮንግረሶ ወስናለች ፡፡
በሰኔ 22፤ 1941 ሰብየት ህብረት (ሩሲያ)በጀርመንና ጣልያን ተወረረች ፡፡ ፈለንድ፣ሃንጋሪ እና ሩማንያ ከጀርመን
ጋር በማበር በሩሲያ ጦርነት አውጀዋል ፡፡ በዚሁ ቀን ዊንስተን ቸርቸል፣ ከሁለት ቀን በኋላ ደግሞ ፕሬዜዳንት
ሩዝቨልት (Roosevelt) ለሩሲያ ድጋፍ እደሚሰጡ አወጁ፡፡ ቀጥሎም የሶብየት፤ እንግሊዝ እና ሶብየት- አሜሪካ
ህብረት ተመሰረተ ፡፡
በነሀሴ 1941 ፕሬዚደንት ሩዝቨልት ኣና ጠ/ሚኒስተር ዊንስተን ቸርቸል በእንግሊዝ የጦር መርከብ ላይ ውይይት
አደረጉ፡፡ ይህም አትላንቲክ ቻርተር (Atlantic charter- 1941) የሚባለው ስሆን የስብዓዊ መብቶች
በህዳር 7 1941 የጃፓን ጦር በሃዋይ ደሴት የሚገኘውን ፒርል ሀርበር (pear harbor) በሚባለው የአሜሪካ ጦር
ካምፕ እዲሁም ሲንጋርፓር በሚገኘው የእንግሊዝ ጦር ላይ
የአውሮፕላን ጥቃት ስነዘረ፡፡ በመቀጠልም በግንቦት 1942 ማለያ፣በርማ፣ ፊሊፒንስ፣ ኢንዶኒዥያ ኣና
ሌሎችም የአሜሪካና የእንግሊዝ ግዛቶች በጃፓኖች ተያዙ፡፡ በጥር 1 ቀን 1942 በአሜሪካዋ ከተማ ዋሽግተን
26 ሀገራትን ማለትም ሩሲያ ፣ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ፖላንድ፣ ዮጉዝላቪያ፣ወ.ዘ.ተ የአክሲስ ሀገራትን በፅናት
ለመዋጋት ህብረት መሰረቱ የሁለተኛ የአለም ጦርነት በአውሮፓና በእስያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካም ተካሂዷል፡፡
ጣልያኖች የእንግሊዝና የፈረንሳይ ሶማሊላንዳድን በአጭር ጊዜ ተቋጣጥረው ነበር ፡፡ ኢትዮጵያን ወረዋል፡፡
ምንም እንኳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጀርመንና የጣልያን ጦር በአፍሪካ ቢከማችም እንግሊዞችን ከአሸናፊነት
አለቆማቸውም፡፡ በተለያዩ ቦታዎች ማለትም በትርፓሊ ፣አልጀሪያ፣ ወዘተ እንግሊዞች ድል መቀናጀት ችለዋል
፡፡ ከኢትዮጵያ ጦር ጋራ በመሆን እንግሊዝ ጣልያንን ከኢትዮጵያ አስወጥተዋል፡፡ (በግንቦት 1941)
ከአፍሪካ ድል በኋላ የተባበሩት ሀይላት (allied forces) የአውሮፓ ሀገራትን ነጻ ለማዉጣት ተንቀሳቅሰዋል ፡፡
በዋናነት ፈረንሳይና ምእራብ አዉሮፓ ሀገራት ነጻ ወጥተዋል፡፡የአክሲስ ደጋፊ (pro-axis) ሀገራት የሆኑት
ፊላንድ ፣ሃንጋሪ ፣ሩማንያ ጀርመንን ለመርዳት ተንቀሳቅሰዋዋል፡፡ በፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ሞሶሎኒ በ 1942
በህዝብ ተገደለ፡፡ ጣልያን በመስከረም 8፤1944 እጃን ሰጠች ፡፡ ከአንድ ወር በኋላ የባዶግሊዮ መንግስት ጀርመን
ላይ ጦርነት አወጀ፡፡ ሶብየቶችም ጀርመኖችን ድል ማድረግ ላይ ነበሩ፡፡ በተለይ በ 1943 የስታሊንግራድ ጦርነት
ጀርመኖች ከፍተኛ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፡፡ ወደ 900,000 የሚጠጋ የሂትለር ምርጥ ጦር በሩሲያ ተሸንፏል፡፡
ይህም የጀርመን የመጀመሪያው ትልቁ ሽንፈት ነበር፡፡
በመስከረም 6፤1944 የእንግሊዝና አሜሪካ ጦር በስሜን የፈረንሳይ ጠረፍ ሰፈረ፡፡ ኖርማንዲ የተባለችውን
ግዛት ተቆጣጠረ፡፡ በዚህ አመት ሰኔ ወር የሩስያ ቀዩ ጦር ቤላሩስን ነፃ አወጣ፡፡ በመቀጠልም የባልቲክና የዩክሬን
ግዛቶችን ተቆጣጠረ፡፡ በመስከረም 5፤1944 የሩሲያ ጦር በቡልጋሪያ በኩል በማለፍ ሀንጋሪን ተቆጣጠረ፡፡ በቲቶ
የምትመሪው ዩጐዝላቪያ ቀዩን ጦር በመደገፉ የጀርመን ስልጣን በዚች ሀገር ላይ ተጠናቀቀ፡፡ በጥር 17፤1945
የሩስያ ቀዩ ጦር ጀርመኖችን ከፖላንድ ምድር አስለቀቀ፡፡ በተመሳሳይም በሚይዝያ 1945 የሶብየት ጦር በድል
ወደ ቸኮዝላቫኪያና ኦስትሪያ ገባ፡፡
በየካቲት 1945 የያልታ ጉባኤ /yalta conference/ ተደረገ፡፡ በዚህ ጉባኤ ሩስያ ፣ አሜሪካና እንግሊዝ በክሪምያ
ግዛት ያልታ ጦርነቱን በሚጠናቀቁበት ሂደት ላይ ተወያዩ፡፡ ከጦርነቱ በኃላም ነፃ በሚወጡ ሀገራት
ዲሞክራሲያዊ መንግስታት በሚመሰረትበት ሂደትና የኢኮኖሚ ድጋፍ ለማድረግ ተስማሙ፡፡ በዚህ ጉባኤ
የመንግስታቱ ማህበር በአዲስ ጠንካራ አለማቀፍ ድርጅት መተካት እንዳለበትም ተስማሙ፡፡
በቀጣይም በጉባኤው ስምምነት መሰረት በሚያዝያ 16፤1945 ሩሲያ የጠላት ጦርን መውጋት ጀመረች፡፡
ጀርመኖችም የተባበሩት ሀያላትን ጦር መቋቋም ባለመቻላቸው እጅ ለመስጠት ተገደዱ፡፡ ሂትለርና ጎበልስ
ራሳቸውን ሲያጠፋ ሌሎች ከፍተኛ የጦር ሹማምንት የጀርመንን መሸነፍ በግንቦት 6፤1945 ፈረሙ፡፡
ተግባር 6.25
- ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በኃላ በጀርመን፣በጣልያን እንዲሁም በመላዉ አለም የተከሰቱ ዋና ዋና
ክስተቶችን ዘርዝሩ
ስለሆነም በነሀሴ 14፤1945 ጃፖን እጇን ሰጥታለች፡፡ በሂሮሽማ ወደ 160,000 ሰዎች እንዲሁም በናጋሳኪ ወደ
120,000 ሰዎች እንደሞቱ ይገመታል፡፡
በአውሮፖ ከፍተኛ የሰውና የኢኮኖሚ ቀውስ ተከስቷል፡፡ ወደ 40 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች እንደሞቱ ሲታመን
ከነዚህ ውስጥ ሁለት ሶስተኛዎቹ ሲቢሎች እንደሆኑ ይታመናል፡፡ በጣም ብዙ ከተሞች ወደ ፍርስራሽነት
ተለውጠዋል፡፡ በተለያዩ ሀገራት ጀርመንና ጣሊያንን ጨምሮ የመንግስት ለውጥ ተደርጓል፡፡
ሌላው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኃላ የተከሰተው ክስተት የኮሙኒስት ፖርቲዎች ተደማጭነት መጨመር
ነበር፡፡ ለምሳሌ በፈረንሳይና በጣልያን የኮሙኒስት ፖርቲ አባላት ቁጥር በእጅጉ ጨምሯል፡፡ ቀስ በቀስ ግን
የአባላት ቁጥሩ ለመቀነስ ችሏል፡፡ ሀገራት በኢኮኖሚና በፖለቲካ በማገገም ላይ ባሉበት ጊዜ በጀርመን የጦር
ወንጀለኞችን በመዳኘት ላይ ነበሩ፡፡ በተለይ በ 1945 እና በ 1946 በኑሬምበርግ የተቋቋመው 23 አባላት ያሉት
የአለምአቀፍ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የጦር ወንጀለኞችን ጉዳይ በመመርመር ላይ ነበር፡፡ በመጀመሪያዎቹ ክሶች
22 የናዚ መሪዎች ጦርነትን በማስነሳት ወንጀል /waging a war of aggression/ ተፈርዶባቸዋል፡፡
በተጨማሪም የሰው ዘርን በመጉዳት /crimes againet homanity/ ተከሰዋል፡፡ በዚህም ለ 11 ሚሊየን ሰዎች
ሞት ተጠያቂ ሆነዋል፡፡በዋናነት በተለይ በናዚ ጸረ አይሁዳዊ ፖሊሲ ምክንያት ጀርመንን ጨምሮ በሌሎች
ሀገራት የተገደሉ በሚሊየን የሚቆጠሩ አይሁዳውያን ሞትም ተጠያቂ ሆነዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጀትን ለመመስረት ፀረ-ፋሽስት የሆኑት የቃል ኪዳን አባል ሀገሮች መንግስታት
አብይ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተለይም በወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት የነበሩት ፋራንክሊን ሮዝቬልት የድርጀቱ
መሰራች ናቸው ብንል ማጋነን አይደለም፡፡ ይህንን ድርጀት ለመመስረት የተለያዩ ጉባኤዎች ተካሄደዋል ፡፡
ከእነዚህ መካካል ፡-
የአሜሪካ፤ የእንግሊዝ እና የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በሞስኮ ከተማ ባደረጉት ጉባኤ የዓለምን ሰላምና
ደህንነት ለማረጋገጥ የአለም አቀፍ ድርጅት መመስረትን አስፈላጊነት ተቀብለዋል ፡፡
3.የደምበርተን ኦክስ ጉባኤ /1944/
በዚህ ጉባኤ የአሜሪካ ፣ የእንግሊዝ ፣የሩሲያና የቻይና ተወካዮች ተካፍለዋል ፡፡ አዲስ ለሚመሰረተውም አለም
አቀፍ ድርጅት ረቂቅ ቻርተር አዘጋጅተዋል ፡፡
4.የያልታ ኮርፈረንስ /የካቲት 1945/
በዚህ ኮንፈረንስ ሶስት ታላላቅ መሪዎች ተካፍለዋል ፡፡ እነሱም ፡- አሜሪካዉ ፕሬዚደንት ሩዝቨልት፤እንግሊዙ
ጠ/ሚኒስትር ቸርችል እና የሩሲያዉ መሪ ስታሊን ናቸዉ፡፡በዚህ ጉባኤ፡
በመንግስታቱ ድርጅት በፀጥታው ምክር ቤት ድምፅ አሰጣጥን በተመለከተ ሊኖር የሚገባው አካሄድ
ወስነዋል፡፡
ሀገሮች ተወካዮቻቸውን ለሚቀጥለው የሳንፈራርሲስኮ ጉባኤ እንዲልኩ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን አላማዎች ግባቸውን እንዲመቱ ሀገሮችን በማስተባበር ድርጅቱ በማዕከልነት ያገለግላል፡፡
ሆኖም ግን የሚወስዳቸውን እርምጃዎች ከማስፈፀም በስተቀር በማንኛውም ሀገር የውስጥ ጣልቃ አይገባም፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 6 አካላት አሉት፡፡ እነሱም፡-
የጠቅላላ ጉባኤ (General Assembly)
ፀጥታው ም/ቤት (Security council)
የድርጅቱ ጽ/ቤት (The secretariat)
የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ ም/ቤት (Economic and social cuncil)
የሞግዚት አስተዳደር ም/ቤት እና (Trusteeship council)
1.የአለም አቀፍ ፍ/ቤት (International court of justice) ናቸው፡፡
በኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳም ም/ቤት አስተባባሪነት የሚሰሩ የተለያዩ በርካታ ድርጅቶች እንደ ዩኔስኮ፣
ዩኒሴፍ፣ የአለም ጤና ድርጅት፣ የአለም የምግብና እርሻ ድርጅት ወዘተ ተቋቁመዋል፡፡
ተግባር፡ 6.27
ተማሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የተመሰረተው ከ 50 አመት በላይ ሆኗታል፡፡ በእነዚህ ጊዜያት
ባከናወናቸው በርካታ ተግባራት መካከል አንዳንዶቹ አዋቂ ሰው በማነጋገር ክፍል ውስጥ ሪፖርት አቅርቡ?
ተግባር፡- 6.28
ቀዝቃዛው ጦርነት ሊከሰት የቻለበት ምክንያት ምን ይመስላችኋል ?
በዚህ ቀዝቃዛ ጦርነት በአሜሪካና በሩሲያ መካከል ጦርነት ባይከሰትም በነሱ በሚደገፋ ቡድኖች ግን ለተለያዩ
ቦታቸው ጦርነቶች ተከስተዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ጥቂቶቸን ዘርዝሩ፡፡
የቀዝቃዛው ጦርነት በዋናነት በተለይ ሀያላን ሀገራት መካከል የተከናወነው የኘሮፖጋንዳ /የማጥላላት
ዘመቻ/ ፣ በዲኘሎማሲና በኢኮኖሚያዊ ውድድር ፣ በጦር መሳሪያ እሽቅድድም በስላላ እንዲሁም
በሀገራት ጣልቃ በመግባት በውስጣዊ ጦርነት ነበር፡፡ ይህ ጦርነት ተጠናቀቀ የሚባለው በ 1990
የሚካኤል ጎርባቶቨ በሩሲያ ወደ ስልጣን መምጣትና እርሱን ተከትሎ በተፈረመ ውል ነው፡፡
ተግባር፡- 6.29
ለቀዝቃዛው ጦርነት መጀመር ተጠያቂ ነው የምትሉት ማንን ነው ? እንዴት?
አሜሪካ የቀዝቃዛው ጦርነት የመራችበትን ሁለት ታላላቅ ፖሊሲዎችን ግለፁ፡፡
ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በኃላ (በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅትና በኃላ) ከተከናወኑ ክስተቶች ጥቂቶችን
እንመልከት፡፡
ኮሙኒስቶችም ድጋፍ ነበረው፡፡ ሰን ያት ሰን ኮመኒስቶችን የተቀበለ ሲሆን የቻይና ኮመኒስት ፓርቲ (ccp)
በ 1921 በሻንጋይ ተመስርቷል፡፡በ 1923 ከላይ የጠቀስ ናቸው ሁለቱም ፓርቲኮች በመዋሀድ የቻይና የጦር
አበጋዞችንና ኢምፔሪያሊቶችን ለማስወገድ ተስማምተዋል፡፡ የሁለቱ ፓሪቲዎች ጥምረት ለሶስት አመታት
የዘለቀ ሲሆን የራሳቸው ወታደሮችም አሰልጥነዋል፡፡ ከሰን ያት ሰን ሞት በኋላ የ KMT መሪነቱን ስልጣን
የተረከበው ችአንግ ካይ ሽክ (chiang kai shek) ነበር፡፡
በ 1926 ወደ ሰሜን በመዝመት ከቻንግ ጅአንግ ደቡብ ያለውን የቻይና ግዛት ለመቆጣጠር ወሰነ፡፡ በዚህ መሀል
ናሽናሊስቶችና ኮሙኒስቶች ግጭት ጀመሩ፡፡ ለዚህም እንደ ምክንያት የሚቆጣጠረው ችአንግ ካይ ሸክ
ኮሚኒስቶችን የሚደግፍ ይምሰል እንጅ በተግባር ግን በ 1927 በሽዎች የሚቆጠሩ ኮሚኒስቶችን የሻንጋይ ግድያ
(shan gai massacre) በሚባለው መጨረሱ ነው፡፡ ከዚህ በኋላ የናሽናሊስቶችና የኮሚኒስቶች ህብረት
ተቋረጠ፡፡ በ 1928 ሽአንግ ካይ ሽክ በናንጅንጅ አዲስ ሪፐብሊክ መሰረት፡፡ ሀገሪቱን ለማዋሀድ ጥረት አድርጓል፡፡
በዚህ ሂደት ግን ኮሚኒስቶችን ጠላቶቹ እደሆኑ እነሱን ማሳደድ አላቆመም፡፡ በዚህ የተነሳ የኮሚኒስት መሪዎች
በሻንጋይ መደበቅ ጀመሩ፡፡በ 1933 የችአንግ ካይ ሸክ ጦን ኮሚኒስቶችን በጅአንግዚ ከበባ አደረገባቸው፡፡ በዚህ
ጊዜ ማኦ የጦሩ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን በመገንዘብ ጦሩን ማለትም የህዝቦችን ነፃ አዉጭ ጦር(peoples
liberation army) የናሽናሊስት ድንበርን በመጣስ ወደ ሰሜን መእራብ ቻይና እንደጓዝ በማዘዝ ጦሩን መራ ፡፡
ከ 600 ማይል ጉዞ በኋላ የመጨረሻ መደበቂ ቤዝ መሰረተ፡፡ በታሪክ ይህ ጉዞ ታላቁ ጉዞ (the long march)
በመባል ይታወቃል፡፡ ጉዞው አንድ አመት ፈጅቷል ፡፡ በጉዞው ወደ 90,000 የሚጠጉ ወታደሮች በጥቂት ምግብ
፣በቀዝቃዛ አየር እና በጉዞ ላይ ጦርነት በማሳለፋቸው ጉዞውን ያጠናቀቁ 9,000 ወታደሮች ብቻ እደሆኑ
ይታመናል፡፡ በዚህ ረጅም ጉዞ ማኦ ወደር የለሽ መሪ መሆኑን አስመሰከረ፡፡ በዚህ ምክንያት የኮሚኒስቶች
ንቅናቄውን ከከተማ ላብአደሩ ጋር በመሆን አጠናከሩ፡፡ ጥቂት የኮሚኒስት መሪዎችም ከችአንግ ጂአንግ
በሰተደቡብ ወደ ጂአንግዚ ግዛት ሂደዋል፡፡ መሪያቸው ማኦ ዜ ዱንግ (mao ze dong) ነበር፡፡ ማኦ የቻይና
አብዮት መጀመር ያለበት በገጠር አርሶ አደሮች እንጅ በከተማ ላብአደሮች አይደለም ብሎም ያምናል፡፡
1.የ KMT ተዋጊዎች ቁጥጥር ከ CCP የበለጠ ነበር፡፡ የዚህ ቀመር 3፡1 ነበር፡፡
2.አሜሪካ ችአንግ ካይ ሽክና ፓርቲውን KMT ን ትደግፍ ነበር፡፡
3.ሩሲያን ጨምሮ የተባበሩት ሀይላት KMT ን እንደ ብቸኛ ህጋዊ አካል ይደግፉ ነበር፡፡ ነገ ግን እነዚህ
የናሽናሊስት ሃይሎች የህዝብን ድጋፍ ለማድረግ ያደረጉት እንቅስቃሴ ዝቅተኛ ነበር፡፡
ከ 1946 የእርስ በእርስ ጦርነት በኃላ አብዛኛው የቻይና ስሜናዊ ክፍል በ KMT ቁጥጥር ስር ሆነ፡፡ ነገር ግን
ገጠሩ ክፍል በኮሙኒስቶች ስር ነበር፡፡ በጊዜ ሂደት ግን በ KMT ስር የነበረው ግዛት የኢኮኖሚ ችግር ውስጥ
መውደቅ ፣ በዋጋ ንረት፣ በሙስናና በወታደራዊ ታክቲክ ችግር ምክንያት በጥር 1949 ኮሙኒስቶች በማሸነፍ
ቤጅንግን በመቆጣጠር የቻይና ኮሙኒስት ሪፐብሊክን መሰረቱ፡፡ ችአንግ ካይ ሸክም ወደ ታይዋን በመሸሽ
ብሄራዊ መንግስት በታይፔይ መሰረተ፡፡
ይህ አዲሱ የኮሙኒስት መንግስት በቻይና ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ አገኘ፡፡ በመቀጠልም አለማቀፍ ድጋፍ በተለይ
ከሩስያ ማግኘት ችሏል፡፡ በዚህም ከፍተኛ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ድጋፍ ከሩሲያ አገኘ፡፡ ማኦ የቻይናን ኢኮኖሚ
ለማሳደግ ኢንዱስትሪውን ፣ ንግዱንና እርሻውን ለማሳደግ የሚረዱ ብዙ የለውጥ ፖሊሲዎችን አውጥቷል፡፡
የግል ኩባንያዎችን ወደ መንግስት አዛውሯል፡፡ በ 1953 ማኦ የአምስት አመት እቅድ በማቀድ በዋናነት
ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ወስኗል፡፡ በ 1957 የቻይና የድንጋይ ከሰልና ሲሚንቶ፣ ብረት እና ኤሌክትሪሲቲ
ምርት በፍጥነት አድጓል፡፡ ከዚህ በኃላም ሌሎች ተከታታይ የአምስት አመት ዕቅዶች በቻይና ተተግብረዋል፡፡
ተግባር 6.30
ተከታታይ የአምስት አመት ዕቅዶች በቻይና መተግበራቸዉ በሀገሪቱ ምን ለዉጥ አስከተለ ?
አዲሱ የኮሙኒስት መንግስት በቻይና ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ለምን አገኘ?
ተግባር፡- 6.31
የቀዝቃዛው ጦርነት ሂደት በኮርያ ምን ተፅዕኖ አስከተለ?
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና ኢትዩጵያ በምን መልኩ ከኮሪያ ጦርነት ጋር ያዛምዷቸዋላችሁ?
በየካቲት 1946 ጊዜያዊ ህዝባዊ ኮሚቴ በሰሜን ኮሪያ ተቋቋመ ፡፡ ይህም በዋናነት የተደገፈው በሶብየት ህብረት
ሲሆን ብዙ የማሻሻያ ህጎችን አወጣ፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
በነሀሴ 1946 የኮሪያ ኮሙኒስት ፖርቲና አዲሱ የህዝቦች ፖርቲ (New peoples party)በመዋሀድ የኮርያ
የሰራተኛ ፖርቲ (Korean party of labor) በስሜን ኮሪያ መሰረቱ፡፡ ሊቀ መንበሩም 2 ኛ ኪምሱንግ (Kim II
sung) ሆነው ተመረጡ፡፡ በደቡብ ኮሪያ ሲግማን ሪ(Syngman Rhee) የደቡብ ኮሪያ መሪ ሆነው በግንቦት 1948
ተመረጡ፡፡
በነሀሴ 1948 በመላ ሀገሪቱ ባደረገው የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤቶች (Supreme peoples assembly) የኮሪያ
ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ (Korean democratic republic) መንግስት ተመሰረተ፡፡ ምክር ቤቱም
የሶብየት ህብረትና የአሜሪካ ወታደሮች ከኮሪያ እንዲወጡ ጠየቀ፡፡ ይህን ተከትሎ ሁለቱም ሀገራት ከኮሪያ
ምድር ወጡ፡፡ ሰሜን ኮሪያም ደቡብ ኮሪያን በመቆጣጠር አንድ ወጥ መንግስት መሰረተች፡፡ ይህን በመቃወም
ደቡብ ኮሪያ አቤቱታዋን ለተባበሩት መንግስት ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት አቀረበች፡፡ የፀጥታው መ/ቤትም
ሶብየት ህብረት በሌለችበት በሰሜን ኮሪያ ላይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት አወጀ፡፡ በሰኔ 1950 የአሜሪካ
ወታደሮች የሲግማን ሪንመንግስት በመደገፍ ሰሜን ኮሪያን ወረረች፡፡ በዚህ የተጀመረው ጦርነት የተባበሩት
መንግስታት ድርጅት ደቡቡን በመደገፍ ጦር ልኳል፡፡ ኢትዬጵያም የተባበሩት መንግስታት ደርጅትን በጦር ከረዱ
ሀገሮች አንዷ ነበረች፡ ይህ አንዱም ጎራ ያላሸነፈበት ጦርነት በመጨረሻ በተኩስ አቁም ስምምነት ሲጠናቀቅ
ኮሪያ ከሁለት ተከፍላ እንድትቀር አድርጓል፡፡
ከዚህ በኋላ ሀገሩ ነፃነት እደሚጠብቃት ቢያምንም ፈረንሳይ ግን የጥንት ግዛቷን እደገና ለማግኘት ጥረት
ታደርግ ነበር፡፡
በዚህ ሳብያ የቬትናም ብሄርተኞችና ኮሚኒስቶች የፈረንሳይን ጦር ለመዉጋት ህብረት ፈጠሩ ፡፡
ፈረንሳይ አብዛኛውን የከተማ ክፍል ስትቆጣጠር ቪትሚንህ ደግሞ ገጠሩን ክፍል ለመያዝ በቃ፡፡ ዋና
የጦርነት ስልታቸውም የደፈጣ ዉጊያ ነበር፡፡ በግንቦት 14/ 1954 ዴን ቤን ፉ(dien bien phu) ላይ
ፈረንሳይ ከፍተኛ ሽንፈት ገጠማት ፡፡ ስለሆነም ለሆ እጅ ሰጡ፡፡ አሜሪካ በቬትናም የተጀመረዉ
ኮምኒዝምን የመቀበል ነገር በሌሎች የኢሲያ ሃገራት እንዳይስፋፋ ለማድረግ የፈረንሳይ ደጋፊ ነበረች
፡፡ ስለሆነም ከፈረንሳይ ሽንፈት በኋላ በጀኔቫ በተደረገው አለምአቀፍ የሰላም ጉባኤ ላይ ቬትናም በ 17
ዲግሪ ሰሜን ላቲቲዉድ ላይ ከሁለት እንድትከፈል ተወሰነ፡፡ ከዚህ መስመር በስተ ሰሜን የሆች ሚንህ
ኮሚኒስት አስተዳደር ሲመሰረት በደቡብ ደግሞ አሜሪካና ፈረንሳይ በንጎ ዲንህ ዴም(ngo dinh
diem)የሚመራ ፀረ-ኮሚኒስት መንግስት አቋቋሙ፡፡ ዴም ደቡብ ቬትናምናኝ በአንባገነንነት መርቷል፡፡
ተግባር 6.32
ቀዝቃዛው ጦርነት በቬትናም ያስከተለውን ችግር ተወያዩ?
የቬትናም በዚህ መልኩ መከፈል ምን ችግር ያስከተለ ይመስላችኋል ?
በዴም አንባገነን መንግስት ላይ ከፍተኛ ተቋሙሞ ሊነሳ ችሏል፡፡ የኮሙኒስት ደፈጣ ተወጊ የሆነው ቬትኮንግ
ቀስ በቀስ በደቡብ መስፋፋት ጀመረ፡፡ በርግጥ ሌሎች የሰለጠኑ በሰሜን በኩል ቢሆንም አብዛኛዎቹ ግን ከደቡብ
የመነጩ ነበሩ፡፡ ቀስ በቀስም ቬትኮንጎች ሰፊ የገጠር ግዛቶች ተቆጣጠሩ፡፡ በ 1963 ዴም በጀነራሎቹ ተገደለ፡፡
ከሱ በኋላ የመጡ መሪዎች የርሱን ያህል ተቀባይነት አልነበራቸውም፡፡ ስለሆነም የደቡብ ቬትናም በቬትኮንግ
ስር መዉደቅ አይቀሬ ሆነ፡፡ ይህን የኮሚኒስቶች ድል አይቀሬነት በመወቅ አሜሪካ ጣልቃ ገብነቷን ለማሰረፋት
ወሰነች፡፡ በርግጥ ከ 1950 ዎች ጀምሮ ጥቂት የአሜሪካ መኮንኖች ለደቡብ ቬትናም በአማካሪነት ሲሰሩ የቆዩ
ቢሆንም ቀስ በቀስ ቁጥራቸው ማደግ ጀመረ፡፡ በተጨማሪም ለደቡብ የሚደረገው የአይሮፕላንና የጦር መሳሪያ
ድጋፍ ማደግ ጀመረ፡፡
በነሀሴ 1964 የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ልይንዶን ጀንስተን /Lyndon Johnston/ለኮንግረሱ ባስተላለፋት
መልክት የሰሜን ቬትናም ቀኝ መርከብ ሁለት የአሜሪካ መርከቦችን በቶንኪን ስርጥ /gulf of Tonkin/
ማውደሙን ገለፁ፡፡ ይህን ተከትሎ ኮንግሬሱ ፕሬዜዳንቱ ጦራቸውን ወደ ቬትናም እንዲዘምቱ ፈቀዱላቸው፡፡
በ 1965 በመጨረሻ አካባቢ ወደ 185,000 የሚጠጉ የአሜሪካ ወታደሮች በቬትናም በጦርነት ላይ ነበሩ፡፡
የአሜሪካ የጦር አዉሮፕላኖችም ሰሜን ቬትናምን ደብድበዋል፡፡ በ 1968 ከግማሽ ሚሊዩን የሚበልጡ
የአሜሪካ ወታደሮች በቬትናም ጦርነት ላይ ነበሩ፡፡
አሜሪካ በጣም ዘመናዊ የጦር መሳሪያና የሰለጠነ ወታደር ቢኖራትም የሚከተሉት ችግሮች ነበሩባት፡፡
1.የአሜሪካ ወታደሮች በማያዉቁት ቦታና ደን ውስጥ የደፈጣ ዉጊያ ላይ ተዳርገዋል፡፡
6.2.7 ኩባ (cuba)
በታሀሳስ 1956 የኩባ አርበኞችና አብዮተኞች በፊደል ካስትሮ (fidel Castro) መሪነት በኩባ ደቡብ ምስራቃዊ
ክፍል ከባቲስታ (Batista) መንግስት ጋር ትግል አደረጉ፡፡ ከ 82 ቱ ታጋዮች በህይት የተረፉት 12 ብቻ ሲሆኑ ወደ
ሴራ ሜስትራ (sierra mastera) በማቅናት ትግላቸውን ቀጠሉ፡፡
የኩባ መንግስት ከአሜሪካ እርዳታ ቢያገኝም አማጽያንን በቀላሉ ማሸነፍ አልቻለም፡፡ የአብዮተኞችን ማሸነፍ
የተገነዘበዉ ባቲስታ በጥር 7፣1959 ወደ ዶሚኒካን ሪፕብሊክ ተሰደደ፡፡ ፊደል ካስሮም ህዝባዊ መንግስት
(people’s gorelnment) መሰረተ፡፡ የካስትሮ መንግስት ብዙ ማሻሻያዎችን አውጇል፡፡ ጥቂቶቹ የሚከተሉት
ይገኙበታል፡፡
በግንቦት 1960 ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች ወደ መንግስት ንብረትነት ተዛዉረዋል፡፡
ከ 1960-1961 ኢንዱስሪዎች ወደ መንግስት ይዞታነት ተዛዉረዋል፡፡
የከተማ ትርፍ መኖሪያ ቤቶችን በመንጠቅ ለላብአደሩ ተከፋፍሏል፡፡
1961 የትምህርት ዓመት /literacy year/ ተብሎ ተሰይሞ ማህይምነትን ለማጥፋት ዘመን ታውጇል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ሌሎች ሶቫሊስተ ሀገሮች የኩባን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ድግፍ አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል ግን
አሜሪካ ለውጦችን በመቃወም የኩባ ስኳርን መግዛት አቆመች፡፡ ይህም የአሜሪካ ንብረት የሆነ የስኳርና የነዳጅ
ማጥሪያዎች ፣የማዕድን ማዉጫዎች፣ የብረታ ብረት ፋብሪካዎችን በኩባ መንግስት መወረስን በመቃወም
ነው፡፡ በዚህ ጊዜ የኩባ ስኳር ወደ ሩሲያ መላክ የግድ ነበር፡፡
በተለይ በ 1961 ፕሬዜዳንት ኬኔዲ ወደ ስልጣን ሲመጡ የኩባ እና የአሜሪካ ግንኙነት በእጅጉ ሻከረ፡፡ ይህም
አሜሪካ ኩባን ትወራለች በሚለው ስጋት የተባባሰ ነበር፡፡ ይህም እዉን ሆኖ ኩባን ለመያዝ ወደ 1500 ሰው
በካርዶና መሪነት ተንቀሳቅሷል፡፡ በዋናነት ህዝቡ ኩባንያ በሚይዙበት ጊዜ በካስትሮ ላይ ያምፃል በሚል እሳቤ
ነበር የታቀደው፡፡ ነገር ግን የተሳበው ሳይሆን ህዝቡ በካስትሮ ላይ አላመፀም፡፡ በተለይ በ 1962 ኩባ የአለም
አቀፍ ውዝግብ ማዕከል ሆነች፡፡ ይህም የሆነው አሜሪካውያን በኩባ የሚሳይል ጣቢያ በሩሲያ ማቋቋሙን
ከደረሱበት በኋላ ነው፡፡ ይህም ጣቢያ ከአሜሪካ ከ 200 ማይል (ከፍሎሪዳ ጠረፍ) ብቻ የሚርቅ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ
ፕሬዜዳንት ኬኔዲ ወደ ኩባ የሚደረጉ ማናቸዉም የሚሳይል መሳሪያዎች በባህር ሃይሉ እንዲታገድ ትዕዛዝ
አወጡ፡፡ ይህ እገዳ እንዲነሳ ኩባ ላይ ያሉ ሚሳይሎች እንዲነሱ አዘዙ፡፡ ለጥቂት ቀናትም አለም በኒኩሊየር
ጦርነት ጫፍ ላይ ቆየች፡፡ በዚህ ጊዜ የሩሲያ ፕሪዜዳንት የነበሩት ክሩስቸቭ (khruschev) ሚሳይሎችን
ለማንሳት በመስማማታቸው አሜሪካ ኩባን ላለመዉረር ቃል ገባች፡፡ ውዝግቡም ሊቆም ችሏል፡፡
ተግባር-6.33
ከላይ በካስትሮ የተደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በኢትዮፕያ በደርግ ዘመን ከተደረጉ ማሻሻዮዎች ጋር
በማገናዘብ ተወያዩ?
አሜሪካ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች በሻገር ከኩባ ጋር ያጋጫች ሌሎች ምክንያቶች ምን ይመስሎችኋል ?
ተወያዩባቸው ?
የኩባ የዚህ ዘመን ሁኔታ ከቀዝቃዛው ጦርነት ጋር ይዛመዳል ብላችሁ ታስባላችሁ? እንዴት?
የክለሳ ጥያቄዎች
የኢንዱስትሪዉ አብዮት ማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዉጤቶችን ዘርዝሩ፡፡
1. ለጣልያንና ለጀርመን ዉህደት ደጋፊና አደናቃፊ የነበሩ ምክንያቶችን ዘርዝሩ፡፡
3.የአሜሪካ ርስ በርስ ጦርነት መነሳት ዋና ምክንት ምን ነበር? የጦርነቱ ዋና ዋና ዉጤቶችን ዘርዝሩ፡፡
4.ለአንደኛዉ የአለም መነሳ ዋና ዋና ምክንያቶችን ዘርዝሩለ፡፡
5.የሁለተኛዉ የአለም ጦርነትን በማስነሳት የሚጠቀሱ ሀገራት እነማን ናቸዉ?
6.ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በኃላ በአለማችን የተከናዎኑ ዋና ዋና ክስተቶችን ዘርዝሩ፡፡
የቁልፍ ቃላት ፍች
መሬት ሰቃዊ ምስራቄ ነፋሶች - ከመሬት ሰቅ አካባቢ በአጠቃላይ ከምስራቅ ወደ ምእራብ የሚነፍሱ
ነፋሶች፡፡
ጥዱፍ ዉርድ - ከከባቢ አየር ወደ መሬት የሚወርድ የፈሳሽሳ ወይም የጥጥር ዉሀ ዝቅጠት፡፡
የአየር ቅጥ ለዉጥ - በአንድ አካባቢ የሚገኝ አየር ቅጥ ተፈጥሮአዊና ሰዉ ሰራሽ በሆኑ ምክንያቶች
ቀደሞ የነበረዉ ጤናማ ሁኔታ ሲለወጥ፡፡
ብዘኅ ህይወት - በአንድ አካባቢ የሚኖሩ በአይን የማይታዩ ረቂቅ ተዋስያን እንዲሁም ግዙፍ እንስሳትና
እጽዋት አይነትና ብዛታቸዉ፣ በመሐከላቸዉ ያለዉም ትስስርና መደጋገፍ፡፡
ዋቢ መጻህፍት
University
Burns, Edward meniall (1958). Western Civilization, W.W. noron & co.
MoE (2006).History Student Text Grades 11&12