You are on page 1of 33

የማህበራዊ ሳይንስና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ

-
የአማርኛ ቋንቋ እና ስነ ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ በ 2012 ዓ.ም


አገልግሎት ላይ የዋሉ ማስታወቂያ
ፅሁፎች ቋንቋ አጠቃቀም
ትንተና


ዘመድ ፀጋየ

ጥር 2013 ዓ.ም.
ዲላ ኢትዮጵያ

'
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ ያኣ ግቢ በ 2012 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የዋሉ ማስታወቂያ ፅሁፎች ቋንቋ
አጠቃቀም

ትንተና
በዲላ ዩኒቨርሲቲ
የማህበራዊ ሳይንስና ሂውማኒቲስ ኮሌጅ
የአማርኛ ቋንቋ እና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል

ለባችለር ዲግሪ በከፊል ማሟያነት የቀረበ ጥናታዊ ጽሑፍ


ዘመድ ፀጋየ

ጥር 2013 ዓ.ም
ዲላ ኢትዩጵያ
አማካሪ
መ/ር
ኢሳያስ ይልማ
የፈተና ቦርድ አባላት

አማካሪ……………………. ቀን………………………… ፊርማ………………

ፈታኝ …………………… ቀን…………………………. ፊርማ………………


ምስጋና
በመጀመሪያ በምህረቱ እና በቸርነቱ ጠብቆ ለዚህ ላደረሰኝ ለድንግል ማርያም ልጅ ለልዑል እግዚአብሔር
ምስጋና ይድረሰው በመቀጠልም ጥናታዊ ፅሁፉ እዚህ ደረጃ እስኪደርስ የጎደለውን አሟልቶ የተጣመመውን
አቃንቶ ዘወትር የሆነውን ምክሩን እየለገሰ ጥናቱ አሁን ካለበት ደረጃ እንዲደርስ ለረዳኝ አማካሪዬ ለኢሳያስ
ይልማ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለሁ። በመቀጠልም እኔን ከፍ ለማድረግ እነሱ ዝቅ ብለው እዚህ ላደረሱኝ
ቤተሰቦቼ ምስጋናየ ከልብ ነው። በመጨረሻም በችግሬ ጊዜ ከፊቴ ሳይጠፉ መፍትሔ በመፈለግ አብረውኝ
የነበሩ ጓደኞቼን ከልብ አመሰግናለሁ።

i
ማዉጫ
ይዘት ገፅ
ምስጋና.................................................................................................................................................i
ማዉጫ...............................................................................................................................................ii
አጠቃሎ...............................................................................................................................................v
ምዕራፍ አንድ.....................................................................................................................................1
1 መግቢያ...........................................................................................................................................1
1.1 የጥናቱ ዳራ...............................................................................................................................1
1.2 የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት..................................................................................................................3
1.3 የጥናቱ አላማ...............................................................................................................................3
1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ..........................................................................................................................3
1.5 የጥናቱ ክልል እና ገደብ................................................................................................................4
1.6 የጥናቱ ዘዴ.................................................................................................................................4
1.6.1 የናሙና አመራረጥ ዘዴ............................................................................................................4
1.6.2 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ.............................................................................................................4
1.6.3 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ.............................................................................................................5
ምዕራፍ ሁለት....................................................................................................................................5
2. ክለሳ ድርሳናት.................................................................................................................................5
2.1 የማስታወቂያ ምንነት................................................................................................................5
2.2 የማስታወቂያ አጀማመር............................................................................................................6
2.3 የማስታወቂያ አይነቶች..............................................................................................................7
2.4 የማስታወቂያ አገልግሎት............................................................................................................7
2.4.1. ማሳሰብ..............................................................................................................................7
2.4.2.ማሳመን.............................................................................................................................8
2.4.3. መገፋፋት..........................................................................................................................8
2.4.4.ማስታወስ..........................................................................................................................8
2.5 የቃላት አጠቃቀም.....................................................................................................................8
2.5.1 መደበኛ የቃላት አጠቃቀም ደረጃ..........................................................................................9
2.5.2 ኢ መደበኛ የቃላት አጠቃቀም ደረጃ......................................................................................9
2.6 የቃላት ምርጫ........................................................................................................................11
2.6.1 እማሬያዊ ፍች..................................................................................................................11
2.6.2 ፍካሬያዊ ፍች..................................................................................................................11
2.7 የሰዋስው ምንነት.....................................................................................................................11
2.7.1 የቁጥር ስምምነት.............................................................................................................12
2.7.2 የጾታ ስምምነት................................................................................................................12
2.7.3 የመደብ ስምምነት............................................................................................................13
2.7.4 የጊዜ ስምምነት................................................................................................................13
2.7.5 የስርዓተ ነጥብ አገልግሎት..................................................................................................15
2.8 የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት..............................................................................................................15
ምዕራፍ ሦስት..................................................................................................................................17

ii
3. መረጃ ትንተና..............................................................................................................................17
3.1 የቃላት አጠቃቀም ችግር ትንተና......................................................................................................17
3.1.1 የጉራማይሌ ቃላት አጠቃቀም..................................................................................................17
3.1.2 የዘዬ (ቀበልቻ) ቃላት አጠቃቀም..............................................................................................18
3.1.3 የድረታ ችግር......................................................................................................................19
3.1.4 የሙያ ቃላት አጠቃቀም.........................................................................................................20
3.1.5 ድግግሞሽ...........................................................................................................................20
3.2 የሰዋሰውአጠቃቀም ስህተት ትንተና.................................................................................................21
3.2.1 የቁጥር ስምምነት..................................................................................................................21
3.2.2 የመደብ ስምምነት................................................................................................................22
3.2.3 የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም.......................................................................................................23
3.3 ምስል ከሳች እና ታዋሽነት..............................................................................................................25
ምዕራፍ አራት......................................................................................................................................26
4. ማጠቃለያና አስተያየት.......................................................................................................................26
4.1 ማጠቃለያ.................................................................................................................................26
4.2 አስተያየት.................................................................................................................................27
ዋቢ ፅሑፎች.......................................................................................................................................28
ጥቅሶች በመገኛ ቋንቋቸው.......................................................................................................................29
አባሪ 1..............................................................................................................................................30

iii
አጠቃሎ
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ አገልግሎት ላይ የዋሉ የማስታወቂያ ፅሁፎች የቋንቋ
አጠቃቀምን ተንትኖ ማሳየት ነው። ጥናቱ አመቺ የናሙ ናአመራረጥ ዘዴን በመከተል ተካሂዷል። የመረጃ
መሰብሰቢያ ዘዴዎችም ሰነድ ፍተሻ እና ያልታቀደ ምልከታ ናቸው። በተገኘው መረጃ መሠረትም የቋንቋ
አጠቃቀም፣ የቃላት ምስል ከሳችነት እና ታዋሽነት ሁኔታ እንዲሁም ሰዋሰዋዊ የቃላት አጠቃቀም
ተተንትነዋል። በዚህ ጥናት ማወቅ የተቻለው በቃላት አጠቃቀም የዘዬ (ቀበልኛ) ቃላትን ማዘውተር፣ ድረታ
እና ተደጋጋሚ ቃላትን የመጠቀም ችግር፤ ከሰዋሰው አንፃር ደግሞ የቁጥር እና የመደብ አለመስማማት
እንዲሁም ስርአተ ነጥብን በአግባቡ ያለ መጠቀም ችግር ያለበት መሆኑን ነው። እነዚህ ችግሮች ደግሞ
በማስታወቂያ አማካይነት መልዕክት ለአንባቢ በሚቀርብበት ወቅት መልዕክቱን ለማንበብ እና ለመረዳት
አዳጋች እንዳደረጉት ተደርሶባቸዋል።

iv
ምዕራፍ አንድ
1 መግቢያ
1.1 የጥናቱ ዳራ
የሠው ልጅ ሀሳቡን በፅሁፍ መግለፅ የጀመረው የዛሬ አምስት አመት ገደማ እንደነበር ይነገራል። ፅሁፍ ከመጀመሩ
ወይም ከመገኘቱ በፊትም ሠዎች ለብዙ ዘመናት ሀሳባቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ወዘተ. ሲገልፁ የኖሩት በንግግር ነበር።
ፅሁፍ የሚታዩ እና የሚዳሰሱ ልማዳዊ ወይም ስምምነታዊ ምልክቶች አማካኝነት የሚቀርብ የንግግር ቋንቋን ቀርፆ
የማቆያ ስልት ነው(አብነት፣277) ።
የመጀመሪያው ፅህፈት ተጀመረ ተብሎ የሚነገረው በሱሜሪያውያን ህዝቦች አማካኝነት ሜሶፓታሜያ ውስጥ ሲሆን
የፅሑፉ መጠሪያ ኩኒፎርም ወይም የሽብልቅ ፅሁፍ በመባል ይታወቃል። ሌሎች ደግሞ ጥንታዊ ፅሁፍ በግብፃውያን
የተፃፈው ሔሮግራፊክስ የተሠኘው ነው ይላሉ። አንዳንዶች ደግሞ የአሜሪካኖች ኮሎምቢያ የዖልሜክ እና የማያን
ህዝቦች እንደጀመሩት እና አየዳበረ እንደመጣ ይታመናል በማለት አብነት (2007፣277) ገልፆታል።
ከዚሁ ጋር አያይዞ የስርዓተ ፅሕፈት አጀማመር እና እድገትን ያጠኑ ጠበብት እንደገለፁት ለዛሬዎቹ ልዩ ልዩ የፅሁፍ
የመሠረቶች ስዕላዊ ፅህፈት፣ ቀለማዊ ፅህፈት፣ ፊደላዊ ፅህፈት የተባሉት ደረጃ በጀረጃ እያደረጉ አሁን ካለበት
እንደደረሰ ያብራራሉ (አብነት 2007፣232) ።
ፅሁፍ ስርዓትን ተከትሎ መልዕክት ለአንባቢ የሚያደርሰው ቋንቋ የሚፈቅደውን የድምፆች፣ የቃላት፣ የሀረጋት፣
የዓአረፍተ ነገሮች፣ የአንቀፅ እና የድርሰት አገባብ ስርዓትን ማወቅ ሲቻል ነው። ይህ ካልሆነ ትርጉም አልባ መሆን እና
የትርጉም መለወጥን በማስከተል ትርጉም እንዲፋለስ ያደርጋል።
በፅሁፍ አማካኝነት ሀሳብን ለማስተላለፍ ደግሞ የፅሁፍ ስርዓቶችን ማወቅ እና መጠቀም ያስፈልጋል። ይሄንን
አስመልክቶ ሳሙኤል (1999) ባዩሬኒ (1988፣1)ን በመጥቀስ የሚከተለውን ሀሳብ አስፍሯል።
ሰንፅፍ እና ስንናገር ከምናወጣቸው ድምፆች ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ማለትም ፊደሎች
(የፊደሎችን ቅንጅት) እንጠቀማለን። በአንድ በኩል ፅህፈት የንግግር ድምፆችን የሚወክሉ
ምልክቶችን የመቅዳት እና በወረቀት ላይ የማስፈር ተግባር ነው ሊባል ይችላል፤ ነገር ግን የንግግር
ድምፆችን የሚወክሉ ምልክቶችን፣ ቃላትን፣ ዓረፍተ ነገሮችን ለመመስረት በቋንቋው ስርዓት
መሰረት ተቀናብረው መዋቀር (መሰደር) አለባቸው።
ከዚህም እንደምንረዳው ፅህፈት የራሱ ስርዓት ያለው ድምፆች ቃላትን፣ ቃላት ሀረጋትን፣ ሀረጋት ዓረፍተ ነገሮችን
መገንባት እና አረፍተ ነገሮችም ርስ በዕርሳቸው ተገናኝተው የቋንቋዉን ስርዓት መጠበቅ እንዳለባቸው ነው። ዐረፍተ
ነገሮች የተዛመዱ፣ የተከታተሉ እና የተቆራኙ ከሆነ የሀሳብ አንድነት እና ጥምረት ያለው ፅሁፍ መፃፍ ይቻላል።
በአጠቃላይ ፅሁፍ በአካል መግለፅ ማለትም በንግግር መልዕክትን ማስተላለፍ በማንችልበት ሁኔታ መልዕክትን
ለማስተላለፍ፣ ሀሳብን ቀርፆ ለትውልድ ለማቆየት፣ ዘመን ተሻጋሪነትን ለማጎልበት፣ ወዘተ ያገለግላል። ለምሳሌ

1
ደብዳቤዎች፣ መልዕክቶች፣ የተለያዩ የደስታም ሆነ ሀዘን መግለጫዎች፣ ትምህርታዊ ሰነዶች፣ መፅሄቶች፣ ጋዜጦች፣
ማስታወቂያዎች እና የመሳሰሉት ሁሉ የሚቀርቡበት የሚቀርቡት በፅሁፍ ነው።
በመሆኑም የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት የሆነው በፅሁፍ ሀሳብ ከሚገለፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ የሆነው
የማስታወቂያ የቋንቋ አጠቃቀም ነው። የቀደሙ አባቶች ወይም ነገስታት ማስታወቂያ የሚውሉ የክተት ጥሪዎችን፣
የአዋጅ ነጋሪ ቃሎችን፣ የቤተክርስቲያን ደውሎችን፣ የከበሮና ፅናፅል ድምፆችን፣ ወዘተ. ሲሆን በአሁኑ ጌዜ ደግሞ
መስሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶች (ግለሰቦች) ለጨረታ፣ ለቅጥር፣ ለደንብ እና ለትዕዛዛት ገለፃ፣ ለመሸጥ፣ ለመግዛት፣
ለመለወጥ፣ የጠፋን ለመፈለግ፣ አዳዲስ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ ወዘተ. የሚጠቀሙበት ፅሁፍ ነው። በመሆኑም
ነገሮችን ለማስተላለፍ ግልፅ እና ለሰው እይታ በሚመች ቦታ ላይ በመለጠፍ፣ በጋዜጣ፣ በመፅሔት እና በመሳሰሉት ላይ
በመፃፍ እንዲሁም በዜና ማሰራጫዎች በሬድዮ፣ ቴሌቪዥን፣ በኢንተርኔት፣ ወዘተ. የሚያደርጉበት የሀሳብ መግለጫ
ነው (ባህሩ 2004፣122) ።
የማስታወቂያ መሰረተ ሀሳቦች ሲነሱ ብዙዎች የተለያዩ ትርጉም የሚሰጡ ተያያዥ ቃላት እና ሀሳባቸውን
ይሰነዝራሉ። ብዙውን (advertising) ሲነሳ የማሻሻጥ የእወቁልን እና የህዝብ ግንኙነት የሚሉትን ቃላት
በተለዋዋጭነት እንጠቀምባቸዋለን። ዳንኤል (200፣57) “እወቁልን የሚለው ሀሳብ ዕወቁ ብቻ ሳይሆን የማግባባት እና
የዕእመኑኝ ፍላጎትም አለበት። ዕወቁልኝ እነዚህ ባህሪያት ከማስታወቂያ ጋር እጅጉን ያቆራኙት እንጂ የልዩነት
ነጥቦችም አሉት፤ ዕወቁልኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ በማገልገል እጅጉን የቀረበ ነው።” በማለት ይገልፁታል።
ማስታወቂያ የአንድን ምርት፣ አገልግሎት (ሀሳብ) ለማስተዋወቅ ሲሆን ምርቶችን ለማማሻሻጥ ወይም አገልግሎትን
ለሰዎች ለማሳወቅ እና ረጅም የሚቆይ አመኔታን ለማምጣት የሚጠቅም ነው። ስለሆነም ማስታወቂያ በግል፣
በፓለቲካ ፓርቲዎችና እጩዎች፣ በማህበራዊ ተቋማት፣በጎ ፈቃደኛ ቡድኖች እና በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቅም
ላይ ይውላል (ወርልድ ቡክስ ሳይክሎፒድያ 1994፣72) ።

ማስታወቂያን በሁለት መድበን ስንመለከት የህትመትና የኤሌክትሮኒክስ ወይም የብሮድካስት በማለት ልንለየው
እንችላለን። ከዚህ አመዳደብ በመነሳት የዚህ ጥናት ትኩረት የሆነው የፅህፈት ማስታወቂያ መነሻውም ከህትመት
ወገን ከሆኑት ማስታወቂያዎች ነው። ሳራ (1992፣269) “የህትመት ማስታወቂያ ሰፋ ያለ ቅርፅ ያለው እና ሠፊውን
ሽፋን የሚይዝ ነው። ስለሆነም አስተዋዋቂዎች ለመሳብ በሚፈልጉት ታላሚ አይነት ምስሎች፣ የድምፅ ቃና፣ የቋንቋ
አጠቃቀም እና የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ዘመቻዎችን ያከናውናሉ።” በማለት ገልፃዋለች። የህትመት
ማስታወቂያ በጋዜጣ፣ በመፅሄት፣ እንዲሁም በበራሪ ወረቀቶች የሚወጡ ማስታወቂያዎችን ይመለከታል። ከነዚህም
መካከል በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ ለተለያየ አገልግሎት የሚወጡ ማስታወቂያዎችን የቋንቋ አጠቃቀም
ይመረምራል።
1.2 የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት
የዚህ ጥናት አነሳሽ ምክንያት በዋናነት ሁለት ሲሆን የመጀመሪያው አጥኚዋ በሁለት አመት ቆይታዋ የሚወጡ
ማስታወቂያዎች ላይ የተሰሩ ስህተቶችን በማየቷ ነው። ይህም ማለት በኦዳ'ያኣ ግቢ በየቦታው ተለጥፈው
2
የምንመለከታቸውና የምናነባቸው ፅሁፎች በአብዛኛው የቃላት አጠቃቀም እና ምርጫ፣ የቋንቋ ሰዋሰው አጠቃም
ችግር፣ ወዘተ. እንከኖች ይታዩበታል። በመሆኑም ይህንን ችግር በጥናት ለመመርመር መታሰቡ ነው። ሁለተኛው
ምክንያት ደግሞ በቤተ መዛግብት፣ በቤተ መፅሀፍት እና አጥኚዋ በእስካሁኑ ቆይታዋ የተለያዩ መመረቂያ ፅሁፍ
ስታነብ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ኣያ ግቢ ማስታወቂያዎች የቋንቋ አጠቃቀም ላይ የተሰራ ጥናትና ምርምር
ስላላጋጠማት ነው ። ስለዚህ እነዚህ ሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ጥናቱን ለማጥናት በር ከፍተዋል።
1.3 የጥናቱ አላማ
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ የሚዘጋጁ የማስታወቂያ ፅሑፎች የቋንቋ አጠቃቀም ላይ
ትንተና ማካሄድ ነው። በተጨማሪም ጥናቱ የሚከተሉትን ዝርዝር አላማዎች ይዟል።
 የማስታወቂያዎቹ የቃላት ምርጫ ምን እንደሚመስል መዳሰስ፤
 የማስታወቂያዎቹ ሰዋሰዋዊ የቋንቋ አጠቃቀም ሁኔታ ምን እንደሚመስል መፈተሽ፤
 የማስታወቂያ የቋንቋ አጠቃቀም ከታዋሽነት አይረሴነት አኳያ ምን እንደሚመስል መገምገም ናቸው።
1.4 የጥናቱ ጠቀሜታ
ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት ተብሎ ይታሰባል።
1. ስለ ማስታወቂያ አፃፃፍ እና ምንነት እንዲሁም ምን ምን ነገሮችን ማሟላት እንዳለበት ግንዛቤ
ያስጨብጣል።
2. የሚወጡት ማስታወቂያዎች ምን ምን ችግሮች እንዳሉባቸው ይጠቁማል።
3. ለሚያወጧቸው ማስታወቂያዎች የማስተካከል እና የማረም ብቃት እንዲኖራቸው ያግዛል።
4. ተሰንዶ ቢቀመጥ ለሌሎች ተመራማሪዎች ወይም አጥኚዎች እንደ መነሻ በመሆን ያገለግላል።
1.5 የጥናቱ ክልል እና ገደብ
ይህ ጥናት በዋናነት የሚያተኩረው በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ ውስጥ በህንፃዎች በር እና ግድግዳ ፣ በመመገቢያ
አዳራሽ በር፣ በቤተ መፅሀፍት በር እና በማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ላይ በሚወጡ የአማርኛ ማስታወቂያዎች
የቋንቋ አጠቃቀም ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። ከዚህም ውጭ ግን ተማሪዎች መታወቂያ ጠፋብን፣ መመገቢያ ካርድ
ጠፋብን፣ ሀገር የሚለውጥ፣ ትምህርት ክፍል የሚለውጥ እና የመሳሰሉትን በማለት የሚፅፉትን አያካትትም።
ምክንያቱም ሁሉንም በግቢው ውስጥ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎችን ለመቃኘት እና ለመመርመር የአቅም፣ የጊዜ
እንዲሁም የገንዘብ እጥረት ስለሚገድብ ነው። በመሆኑም በኦዳ'ያኣ ግቢ ውስጥ ከተለያዩ ቢሮዎች በሚወጡ
በአማርኛ ቋንቋ በተፃፉ ማስታወቂያዎች ላይ ብቻ በማተኮር ጥናቱ ተካሂዷል።
1.6 የጥናቱ ዘዴ
የጥናቱ ዘዴ ሲባል ጥናቱ በምን መልክ እንደሚጓዝ የሚያሳይ እና የጥናቱን ጠቅላላ ሁኔታ የሚመለከት ነው።
በመሆኑም ጥናቱ በገላጭ የምርምር ስልት ላይ የተመሰረተ ሲሆን በዚህ ክፍል ውስጥም የናሙና አመራረጥ ዘዴ፣
የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ እና የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ተብራርተዋል።
3
1.6.1 የናሙና አመራረጥ ዘዴ
ለዚህ ጥናት የተመረጠው አመቺ የናሙና አመራረጥ ዘዴ ነው። ምክንያቱም አጥኚዋ የምትማረው በኦዳ'ያኣ ግቢ
መሆኑ ለጥናቱ የሚመቸው በዚሁ ግቢ ውስጥ የሚገኙ ማስታወቂያዎች ማግኘት ስለሆነ ከጥቅምት 14 እስከ የካቲት
15/2012 ዓ.ም ድረስ የተለጠፉትን በመሰብሰብ መረጃውን ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት ተደርጓል። በኦዳ'ያኣ ግቢ
በአመቺ ናሙና ከተመረጠ በኋላ በዚህ መሰረት ለጥናቱ መሰረት ከተመረጠ ለጥናቱ መረጃ ይገኝባቸዋል ተብለው
ከታሰቡት ቦታዎች፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ በማስታወቂያ ሰሌዳዎች እና በተማሪዎች የመኖሪያ ህንፃዎች አካባቢ
የተገኙ 40 ማስታወቂያ ፅሁፎች ተሰብስበዋል። ነገር ግን ሁሉንም ለመስራት የጊዜ እና የአቅም ችግሮች ስላሉ
እንደገና በተራ የእጣ ናሙና ስልት 16 ማስታወቂያዎች ተመርጠው በዚህ ጥናት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል።
1.6.2 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ
በዚህ ጥናት አገልግሎት ላይ የዋሉት የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴዎች ምልከታ እና ሰነድ ፍተሻ ናቸው።
1.6.2.1 ምልከታ
አንድን መረጃ ትክክለኛ እና እውነተኛ እንዲሆን መረጃ ከሚገኝበት ቦታ ድረስ ዘልቆ በመግባት መረጃን ለመሰብሰብ
ከሚረዱ መሳሪያዎች ትልቁ ምልከታ ነው። ስለሆነም በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ መረጃ ለማግኘት ሲባል ባልታቀደ ምልከታ
ለአምስት ወራት ያህል በተደጋጋሚ በየማስታወቂያ መለጠፊያዎች ድረስ በመሄድ እና የተለጠፉትን ማስታወቂያዎች
በመመልከት እና ፎቶግራፍ በማንሳት መረጃን ለመሰብሰብ ተሞክሯል።
1.6.2.2 ሰነድ ፍተሻ
ሌላው የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ሰነድ ፍተሻ ነው። በመሆኑም አጥኚዋ ከርዕሱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን የተለያዩ
ሠነድና ሠነድ ነክ ፅሁፎች በማንበብ ለጥናታዊ ፅሁፍ ተሰብስቧል።
1.6.3 የመረጃ መተንተኛ ዘዴ
በዚህ ጥናት የተሰበሰበው መረጃ የሚተነተነው በአይነታዊ የመረጃ መተንተኛ ዘዴ ነው። ያለው (2004፣410) አይነታዊ
የመረጃ መተንተኛ ዘዴ በሚገባ ከተጠናከረና ተጨባጩን አለም በትክክለኛ መንገድ እንዲያሳይ ተደርጎ ከተሰራበት
ግልፅና ለአንባቢ ትርጉም ያለው ሀሳብ ለመስጠት ያስችላል ይላሉ። በዚህ ጥናት የማስታወቂያ ፅሁፎችን በመጠቀም
የተሠበሰቡት መረጃዎች በየመልካቸው ከተደራጁ በኋላ በአይነታዊ መረጃ መተንተኛ ዘዴ ከስርዓተ ነጥብ እና ከቃላት
ምርጫ እፃር ለመተንተን ተሞክሯል።

4
ምዕራፍ ሁለት
2. ክለሳ ድርሳናት
2.1 የማስታወቂያ ምንነት
በማስታዎቂያ ዙሪያ ጥናት የሚያደርጉ ባለሙያዎች በአንድ ድምጽ “ማስታወቂያ ማለት ይህ ነው” የሚል ድምዳሜ
ላይ አልደረሱም። ምክንያቱ ደግሞ የማስታወቂያ ስራ በስሌት እንደሚደርስበት የቁጥር ቀመር ሳይሆን የምርቶች እና
አገልግሎቶች የመለዋወጥ ሂደት፣ ከሙያው ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው መሆኑ እና የማስታወቂያ
ስራ በራሱ ያላቋረጠ እድገት ማሳየቱ የሚጠቀሱ ናቸው (ዳንኤል፣ 2000፣27)፡፡
ስለማስታወቂያ የተለያዩ ምሁራን ብያኔያቸውን አስቀምጠዋል። ከብያኔዎቹም መካከል የሚከተሉትን
እንመለከታለን።
ተሸገር (1996፣267) ጆንሠን (1887፣4)ን ጠቅሶ ማስታወቂያ አብዛኛውን ጊዜ የምርቱን ጠቀሜታ የሚያሳይ መረጃን
መሰረት በማድረግ ለግዢ የሚገፋፋ ለታዳሚው አመለካከት ተስማሚ ምስል በመፍጠር በእጅ አዙር የማሳመን ሂደት
ነው በማለት ገልፆታል።
በሌላም በኩል የዪናይትድ ኪንግደም ማስታወቂያ ማህበር /https://m.economic times.com /definition/
advertizing/ ማስታወቂያን ማስታወቂያ ከምርት ወይም አገልግሎት ተጠቃሚዎች ጋር የማግባቢያ መንገድ ነው።
ማስታወቂያዎች በሚያስተላልፉት መልዕክት የሚሰሙዋቸው የሚያዪዋቸው ሰዎች ላይ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ
እንዲያሳምኑ እና እንዲያሳውቁ የታሰቡ ናቸው። በማለት ገልፀዋል።
ስለ ማስታዎቂያ ምንነት ዳንኤል (2000፣28) እንደገለጸው፦
ማስታወቂያ በሚገባ የተነገረ እውነት ነው። በመሆኑም ማስታወቂያ አስደሳችነት ያለው ተሞክሮን
የሚያካፍል፣ሲያዩት የሚማርክ፣ ሲሰሙት የሚለሰልስ መሆን ይገባዋል፡፡ አድማጭና ተመልካችንም
ምነው እዚያው በታደምኩ ኑሮ፣ምነው እኔም አግንቼ የኔ ባደረግሁት ኖሮ ብሎ የሚያስቆጨው
መሆን ይጠበቅበታል። የአንድን ምርት ተጠቃሚዎች እንዲገለገሉበት የሚያግባባ፣ ክፍያ
የሚጣልበትና ግላዊነት የማይታይበት የመረጃ ቅብብሎሸ አይነት ነው።
ከዚህም የምንረዳው ከምርቶቻቸው እና አገልግሎታቸው ወይም ከሚያራምዷቸው ሀሳብ እና ከሚያከናውኗቸው
ተግባራት መካከል የተፈለገውን መልዕክት ታዳሚው ዘንድ እንዲደርስ፣ አላማው ግብ እንዲመታ እና ተቀባይነት
እንዲኖረው የማስታወቂያው መልዕክት በአዕምሮ ውስጥ ምስል በመፍጠር የሚያሳምን እና የሚያስተምር መሆን
አለበት።

2.2 የማስታወቂያ አጀማመር


የማስታወቂያ ስራ አጀማመር ታሪክን የተለያዩ ጸሀፊዎች በተለያየ መልኩ ይጻፉት እንጂ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሶስት
ሺህ ዓመተ ዓለም አካባቢ መነሻውእንደሆነ ሁሉም ይጠቅሳሉ። ደረጃውም የተሟላና ዛሬ ላይ ያለውን አይነት
ባይሆንም ማስታወቂያ ነክ ስራዎች በወቅቱ እንደነበሩ ሁሉም አጥኝዎች ይስማሙበታል። በግብጽ በ 3200 ዓ.ዓ
5
ገደማ በተሰሩ የማምለኪያ ህንጻዎች ላይ ማንኛው ንጉስ እንዳሳነጸ የሚጠቁሙ ጹሁፎች ከማስታወቂያ ወገን
ይመደባሉ። እንዲሁም በፓፒረስ ላይ በጥንታዊ ግሪክና ግብፅ ተፅፈው የተገኙ መረጃዎች የጠፉ ባሪያዎች እንደነበሩ
የሚገልፁ የጎዳና ምልክቶች እንደነበሩ አርኪኦሎጅስቶች ገልፀዋል። ለምሳሌ፣ ሼም የተባለው ባሪያ ሃፑ ከተሰኘው
አሳዳሪው ይሰወራል። ባሪያውን ለማግኘት አሳዳሪው ከዚህ በታች ያለውን ማስታወቂያ መሰል ንግግር ያስደምጣል፡፡ "ሃፑ
የቴቢስ መልካም ዜጎች ሁሉ ይህን የጠፋ ባሪያ ቢመልሱለት ይወዳል። ባሪያውም ባለ ቡናማ አይን ነው። ያለበትን
አካባቢ ዜና ላመጣ ግማሽ የወርቅ ሳንቲም ይሰጠዋል። ሼምን ወደ አሳዳሪው ለሚመልስ ደግሞ እንደፍላጎቱ ልብስ
የሚሸለም ሲሆን ሙሉ የወርቅ ሳንቲምም ይሰጠዋል" ( ዳንኤል 2000፣15) ። ይህም በጥንታዊው ግብጽ
የማስታወቂያ ይዘት ያለው አይነት ጽሁፍ መገኘቱን የሚጠቁም ምሳሌ ነው፡፡
2.3 የማስታወቂያ አይነቶች
ማስታወቂያዎች ከሚተላለፉበት ብዙሃን መገናኛ አይነት አንስቶ እስከ ታለመላቸው አላማዎች ድረስ የተለያዩ
ናቸው። በዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ያካሄዱ ባለሙያዎች ሁሉ እነዚህን እንደ አላማቸው፣ እንደየባህሪቸው፣
እንደሚተላለፍባቸው ብዙሃን መገናኛ አይነት፣ እንደምርቱና ጥቅሙ ሁኔታ፣ ወዘተ. የሚለያዩ የማስታወቂያ
አይነቶችን እንደየራሳቸው ሲከፋፍሏቸው ስም ሲሰጧቸው ይስተዋላል። አንዳንድ ባለሙያዎች የህትመትና
የብሮድካስት ማስታወቂያ በማለት ይከፍሏችዋል። አንዳንዶች ደግሞ ማስተላለፍ በተፈለገው መልዕክት ላይ
በመንተራስ መረጃ ሰጪ እና ቀስቃሽ ይሏቸዋል፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ማስታወቂያ የሚኖረውን ፋይዳ ተመልክተው
በተለያየ ጎራ ይለዩለታል። በዚህም ምክንያት ባለሙያዎችን በተቀራራቢነት ያነጋገረ እንጂ በአንድ ያስማማ ክፍፍል
አልተገኘለትም(ዳንኤል 2000፣45)።
2.4 የማስታወቂያ አገልግሎት
ማስታወቂያ የገንዘብ ወጭን የሚጠይቅ ቢሆንም የራሱ የሆነ ጠቀሜታና ውጤት አለው። በተለይ ማስታወቂያ
አስነጋሪዎች የሚጓጉላቸው ውጤቶች በመኖራቸው ለማስታወቂያ ስራው ገንዘብ ያወጣሉ። እነዚህ የሚጠበቁ
ውጤቶች ሁሉም በአንድ ጀንበር እውን ላይሆኑ ይችላሉ። ይሁን እንጅ ሁሉም ውጤቶች ከሚለቀቁ
ማስታወቂያዎች ጎልቶ የመታየት አዝማሚያ እንዳላቸው ብዙዎችን ያስማማል። ማስታወቂያ እንዲያስማማ አንድ
ሀሳብ እንዲመጣ ያደረጉትም አራት መሰረታዊ ነገሮች እንዳሉት ዳንኤል (2000፣48) እንደሚከተለው ይገልጻል፡፡

2.4.1. ማሳሰብ
ማሳሰብ ማለት ደንበኞች ለመግዛት ( ለመጠቀም ) ያላሰቡትን ነገር ምናልባትም መኖሩንም ያላወቁትን ምርት
እንዲያውቁትና እንዲሞክሩት ማድረግ ነው። የምርቱን ተፈላጊነት በማጉላትም ደንበኛን ይጨምራል። ይህ አይነቱ
ማስታወቂያ ብዙውን ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የሚታየው በገበያ አካባቢ ነው፡፡ በተለይ አዳዲስ ምርቶች ላይ ነው፡፡
2.4.2. ማሳመን
ይህ የማስታወቂያ አገልግሎት የሰዎችን ስሜት የሚነኩና ሊያሳምኑ የሚችሉ ቃላትንና ጥበባዊ ዘዴዎችን በመጠቀም
ምርቱን ወደ መግዛትና በአገልግሎቱም ወደ መጠቀም እንዲያመሩ የሚያደርግ ነው። ይህ ዘዴ ብዙውን ጊዜ ለፍቅረኛ
6
ስጦታ ማበርከትን፣ ወደሚፈለገው ሀይማኖት ሰብኮ ማስገባትን፣ በራስና በቤተሰብ ላይ ሊደርስ የሚችልን አደጋ
መከላከልን፣ በራስ መተማመንን ማጎልበትን ወዘተ. ይይዛል።

2.4.3. መገፋፋት
ማስታወቂያ ስለ ምርቱና አገልግሎቱ ጠበቅ ያለ መረጃ ሊይዝ ይገባል። ይህም ሲባል ከነበሩ ምርጫዎች መካከል
ሊያስመርጠው የሚችል ከአዲስም ሆነ ከነባሮቹ ልቆ እንዲታይ ማድረግ ሊሆን ይገባል፡፡ በዚህ ሀሳብ እንደተገለጸው
ማስታወቂያው ለእይታ በሚበቃበት ጊዜ ሰዎች ወይም ተደራሲያን አንዳች ሀይል በእዝነ ህሊናቸው አድሮ ወደ
ተገለጸው ነገር የመግባት ፍላጎታቸው ሊጨምር እንደሚችል ማሳየት ነው፡፡
2.4.4.ማስታወስ
ይህ አይነቱ ደግሞ በማስታወቂያ አማካኝነት ለማስታወስ የሚፈልገው ዋነኛው ጉዳይ የምርቱን መለዮ
ምልክት(birand) ሲሆን መለዮውም ዘወትር በደንበኞች ህሊና እንዲመላለስ ማድረግ ነው።

2.5 የቃላት አጠቃቀም


ቋንቋ መልዕክት ማስተላለፊያ መሳሪያ ነው፡፡ የአንድ ቋንቋ ተናጋሪም መልእክት የሚያስተላልፈው የቋንቋን ድምጾችን
በስርዓት አቀናጅቶ ቃላትን ከቃላት፣ ሃረጋትን ከሃረጋት እያቀናጀ ዐረፍተ ነገር መፍጠር ነው (ጌታሁን 2007፣1)፡፡
አብነት(2007፣1) በበኩሉ ስለ ቋንቋ ሲገልጽ “ይሁነኝ ተብሎ በሚፈጠሩ ትዕምርቶች አማካኝነት ሃሳብን፣ ስሜትን
እና ምኞትን እርስ በርስ ለመለዋወጥ የሚያገለግል ሙሉ በሙሉ ሰብዓዊና ኢ ደመነፍሳዊ የሆነ የመግባቢያ ስልት ነው
ይላል” በመሆኑም በመግባባት ሂደት ውስጥም ቃላት ቁልፍ ሚናን ይጫወታሉ፡፡
በተጨማሪም ደረጀ (1996፣9) ቃላትን ቋንቋን መሳሪያ በማድረግ የሰው ልጆች ሃሳባቸውን እና ስሜታቸውን
ለማስተላለፍና ለመግለጽ የሚችሉበት የነገሮች (እቃ፣ ድርጊት፣ ሁኔታ፣….) ወኪሎች ናቸው፡፡ ቃላት ትርጉም
ያላቸው የቋንቋ አካል ናቸው፡፡ ስለሆነም ከድምጾች እንደሚመሰረቱ ሁሉ እነዚህ ተቀናጅተው ሃረጋትን እንዲሁም
ትርጉም ያላቸው፣ የራሳቸው ፍች የሚሰጡ እና ሙሉ መልዕክት የሚያስተላልፉ ዓረፍተ ነገር ይሆናሉ፡፡ ቃል ሰዎች
ሃሳባችውን ከሚለዋወጡባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ሲሆን የምንፈልገውን ነገር ለመፈጸም ያስችላል፡፡
በመሆኑም በምንጽፍበትና በምንነጋገርበት ጊዜ አድማጮቻችንንና አንባቢዎቻችንንእና አንባቢዎቻችን በሚያግባባ
እና ግልጽ በሆነ መልኩ ቃላትን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ለዚህም ጉዳዮችንና ክስተቶችን ቀላልና ቀጥተኛ በሆነ ቋንቋ
ማቅረብ ይገባል፡፡ በማለት ይገልጻል፡፡
በማንኛውም ቋንቋ የመግባባት ሂደት ውስጥ ሃሳብን ወይም ስሜትን ለመግለጽ የሚያስችሉ ቃላት እጅግ በርካታ
ናቸው፡፡ ይሁንና ሁሉም ቃላት በንግግርም ይሁን በጽሁፍ እኩል አገልግሎት አይኖራቸውም፡፡ እንደ ንግግሩ ርዕሰ ጉዳይ፣
ዓላማ፣ ይዘት፣ እንደ አድማጩ ማንነት፣ እንደ ንግግሩ ቦታ፣ ወዘተ. ሃሳባችንን ለመግለጽ የምንጠቀምባቸው ቃላት
ይለያያሉ፡፡ በመሆኑም እንደምንናገረው ስለማንጽፍ ለጽሁፍ የምንጠቀምባቸው ቃላት የተመረጡ ናቸው፡፡ እነዚህም
ቃላት መደበኛ እና ኢመደበኛ ተብለው በሁለት ይከፈላሉ (ደረጀ 1996)፡፡

7
2.5.1 መደበኛ የቃላት አጠቃቀም ደረጃ
ይህ ስልት የአፍ መፍቻንም ሆነ ሁለተኛ(የውጭ)ቋንቋን በትምህርት ቤት መማርን ይመለከታል። በትምህርት ቤት
ለመማር ስርዓተ ትምህርት፣ መርሃ ትምህርት፣ የመማሪያና የማስተማሪያ ቁሳቁሶች( መጽሃፍት፣ በራሪ ወረቀቶች፣
የቴፕና የቪዲዮ ክሮች፣ ወዘተ.) መምህርና መማሪያ ቦታ፣ እንዲሁም የመማሪያ ጊዜን መመደብን ሁሉ ይጠይቃል።
በእነዚህ በተጠቀሱት ልዩ ልዩ ተግባራትና ክንዋኔዎች አማካኝነትም ለትምህርት የቀረበውን ቋንቋ ቃላት በአላማው
መሰረት ደረጃ በደረጃ የምንማራቸው ናቸው፡፡ እንዲሁም የምንጠቀምባቸው ናቸው፡፡ በመሆኑም ሰፊ እውቅና
አገልግሎት አላቸው(ደረጀ 1996፣5)።
2.5.2 ኢ መደበኛ የቃላት አጠቃቀም ደረጃ
ይህ የቃላት ማጥኛ ዘዴ ደግሞ በቋንቋው ተናጋሪ ህዝብ ውስጥ መኖር ነው። ተናጋሪው ህብረተሰብ በእየለት ውሎው
እንዳጋጠመው ለቃላት ክብደትና ቅለት ሳይጨነቅ ሃሳቡን ይገልጻል። በማህበረሰቡ ግንኙነት ውስጥም እግረ መንገዱን
የቃላት ችሎታን የምናዳብርበት ስልት ነው። ይህ ከማህበረሰቡ ጋር በመኖር የምናገኘው የእውቀት እና የቃላት
መለማመድ ዘዴ ኢመደበኛ ተብሎ ይጠራል፡፡ ኢመደበኛ የቃላት አጠቃቀም ደረጃ የሚባሉትም፣ ጉራማይሌ፣ የሙያ፣
ያራዳ፣ ዘዬ (ቀበልኛ) ቃላት ወዘተ. ናቸው፡፡ እነዚህም ውስን እውቅና አገልግሎት ያላቸው ናቸው (ደረጀ 1996 ፣5)።

2.5.2.1 ጉራማይሌ ቃላት


ሰዎች በማህበራዊ ኑሮአቸው ውስጥ ሁሉ ነገር ተሟልቶላቸው አይኖሩም። ስለዚህ ጎዶሎአቸዉን ለመሙላት ሲሉ
ሰዎች ከሰዎች ጋር መዋደድን ይመርጣሉ። ቋንቋ ደግሞ ህልውናው በሰዎች ላይ ተወስኖ የሚኖር የመግባቢያ መሳሪያ
ነው። በዚህም መሰረት የአንዱ ቋንቋ ተናጋሪ ወደ ሌላው ቋንቋ ተናጋሪ መስተጋብር ሲፈጥር የቋንቋቸው ንክኪ አብሮ
ይወሰናል። በዚህም የተነሳ የአንዱ ቋንቋ ድምጽ፣ ምእላድ፣ ቃል፣ ወዘተ. ወደ ሌላው ይሸጋገራል። በዚህም የቋንቋ
ውሰት ሊከሰት ይችላል፡፡ ሊከሰት የሚችለውም በስደት፣ በፖለቲካ፣ በወረራ፣ በአዳዲስ ነገሮች፣ በግኝቶች፣
በቴክኖሎጅ ውጤቶች እና በዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች፣ ወዘተ. ሊሆን ይችላል(ደረጀ 1996፣14)።

2.5.2.2 የሙያ ቃላት


የሙያ ቃላት የምንላቸው በአንድ ሙያ ወይም ትምህርት ዘርፍ የሰለጠኑ ሰዎች ከሙያቸው ጋር ተያያዥነት
ያላቸውን የተለያዩ ጉዳዮች ለመግለጽ የሚገለገሉባቸው ቃላት ናቸው። በሙያ ነክ ቃላት መጠቀም አንባቢው
ከሚያብራራው ሙያ ጋር ትውውቅ ያለው ካልሆነ በስተቀር ሀሳብን መጋራት ላይኖር ይችላል። ለምሳሌ፡- የጋራዥ
ሰራተኛ ከሌላ የጋራዥ ሰራተኛ፣ ሃኪም ከሌላ ሃኪም፣ አርሶ አደር ከሌላ አርሶ አደር ፣ሸማ ሰሪው ከሌላ ሸማ ሰሪ፣
ወዘተ. እርስ በርስ መግባቢያ ሙያዊ ቃላትን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ከዚህ ውጭ ግን ሃኪሙ ለገበሬው እና የጋራዥ
ሰራተኛው ለሸማ ሰሪው ቢጽፍለት በትክክል መግባባት አይኖርም። የተፈለገው መልዕክትም ሳይደርስ ሊቀር
ይችላል(ደረጀ 1996፣15)፡፡

8
በአንድ ቋንቋ ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ቃል መደበኛ ፅሁፍን ዉስጥ አይካተትም። ስለዚህ የቃላት አጠቃቀምን
ለይቶ ማወቅ ግድ ይለናል። ቃላትን ስንጠቀም የተለያዩ ችግሮች ያጋጥማሉ። እነሱም ድረታ፣ ድግግሞሽ፣ የተውሶ፣
ወዘተ. ናቸው (አብነት 2007፣45)።
የቃላት ድረታ የሚለው ጽንሰሃሳብ አንድን ነገር ለመግለጽ ወይም መልእክትን ከምንጩ ወደ ተደራሲያን ለማስተላለፍ ተመሳሳይ
ትርጉም (ፍች) ያላቸውን ቃላት መሰደር ነው። ድረታ በአገባባቸው ሙሉ ስሜት በሚያሳዩ ወይም አንድን ድርጊት በበቂ ሁኔታ
በሚገልጹ ቃላት ላይ ተመሳሳይ ፍች ወይም መልእክት የሚሰጡ ቃላትን መጨመር ነው። ይህ አይነቱ አገላለጽ ደግሞ መልእክትን
በተፈለገው መልኩ ለተፈለገው አካል ለማቅረብ መሰናክል ነው። ተመሳሳይ ድርጊትን የሚገልጹ በርካታ ቃላት መደጋገም ሃሳብን
ግልጽ ከማድረግ ይልቅ ያድበሰብሳል። አንባቢንም ወደ አልተፈለገ መደናገር ውስጥ ያስገባል ( ደረጀ 1996 ፣13) ።
ድግግሞሽ የሚባለው በፅሁፍ ውስጥ ለአፅንኦት ሲባል ቃልን ወይም ሀረግን መደጋገም ነው። ወይም የራሱ የሆነ አላማ
ያለው ሲሆን በድርሰት ውስጥ ቢገባ እንደ ስህተት ላይታይ ይችላል ነገር ከልክ ባለፈ መንገድ የሚፈፀመው ድግግሞሽ
አስፈላጊ አይደለም። አንድ ፀሀፊ ቃላትን ያለምንም ምክንያት መደጋገም እንደማይችል ማወቅ አለበት
(አብነት 2007፣45-46)፡፡

2.6 የቃላት ምርጫ


የቃላት ምርጫ ማለት በንግግርም ይሁን በጽሁፍ የመግባባት ሂደት ሃሳብን ወይም ስሜትን ወይም መልዕክትን ግልጽና
ትክክለኛ በሆነ መንገድ ለማስተላለፍ የሚያስችልን ቃል መርጦ መጠቀም ማለት ነው፡፡ ቃላት በባህሪያቸው
ተለዋዋጭ በመሆናቸው በተለያየ አገባባቸውና በቁማቸው ካላቸው ፍቺ የተለየ ሊኖራቸው ይችላል ወይም
በቁማቸው የተለያዩ ፍችዎችን ሊወክሉ ይችላሉ፡፡ ተገቢ ቃል ለመምረጥም የቃላትን ባህሪ ጠንቅቆ ማወቅ
ያስፈልጋል፡፡ በምርጫ ውስጥ እማሬያዊና ፍካሬያዊ ፍችዎችን እንመለከታለን (ደረጀ ፣1996 እና የሻው 1996፣33) ፡፡
2.6.1. እማሬያዊ ፍች
ቃላትን አብዛኛውን ጊዜ የምንጠቀማቸው በእማሬያዊ ፍቻቸው ነው። እማሬያዊ ቃላት የተደራሲያንን ስሜት
ከመንካት ይልቅ መልዕክትን ወደ ማስተላለፍ ያደላሉ። ይህ የሚሆነውም ስሜትን ከመንካት አስቀድሞ መልዕክት
መተላለፍ ስላለበት ነው። እማሬያዊ ፍች ያላቸው ቃላትን የምንጠቀምባቸው ለትምህርትና መልዕክት ለማስተላለፍ
ሲባል ለሚጻፉ ጽሁፎች ሲሆን እንደ ሳይንስ፣ ታሪክ፣ ስነ ህዝብ፣ ስነ ማህበረሰብ፣ የመሳሰሉትን እውቀቶች ለመማር
በቀጥታና በጥሬ ቃላት ፍች መጻፍ ስላለባቸው ነው(የሻው 1996፣33)፡፡
2.6.2. ፍካሬያዊ ፍች
ፍካሬያዊ ፍች ማለት በየእለቱ የምንገለገልባቸው ቃላት ልዩ ልዩ ስሜቶችን ለመከሰትና መልዕክቱን የበለጠ ጉልህ
ለማድረግ ሲባል ከነባር ፍቻቸው ሌላ አዲስ ስሜትን እንዲይዙ ይደረጋል። በዚህ አይነቱ የቃላት አጠቃቀም ቃላት
በዋሉበት ዓውድ ነጠል ያለ ባህርይ ይዘው በመቅረብ የመልዕክት አፍላቂውን ሀሳብ አጉልተውና ብርሃናማ ቀለም
ሰጥተው ያቀብላሉ። ይህ ማለት ቃላት ከተራ ትርጉማቸው ይልቅ በፍካሬያዊ መልካቸው በጥቅም ላይ ሲውሉ፣
ለስሜት ቅርብ መሆንና ሀሳብን ትኩስ አድርጎ የማሳየት ብቃት አላቸው እንድንል ያደርገናል። አብዛኛውን ጊዜም
9
አገልግሎት ላይ የሚውሉት በለበጣ ወይም ፌዝ፣ በምሳሌዊ ንግግር፣ በግጥም፣ በቅኔና በተለያዩ የልቦለድ ስራዎች ላይ
ነው ( የሻው 1996፣35)፡፡ ከዚህም የምንረዳው ማስታወቂያዎች በዚህ የቃላት ምርጫ መጻፍ እንደሌለባቸውና
በእማሬያዊ ፍቻቸው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን ነው፡፡
2.7 የሰዋስው ምንነት
ሰዋስው የአንድ ቋንቋ መዋቅራዊ ስርዓት ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮ ከሚያገኘውም ይሁን ራሱን ለመግዛት ሲል
በቀረጸው ህግና ስርዓት መሰረት ይመራል። ቋንቋም እንደ ሰው ልጅ በስርዓት ይመራል ። ይህን የቋንቋን መዋቅራዊ
ስርዓት የሚያጠና ሳይንስ ሰዋስው ይባላል። ይህም በመሆኑ የአማርኛ ቋንቋ ሰዋስው በተለያዩ የሰዋስው አመዳደብ
ተመድበው ይጠናሉ። እነዚህ መደቦችም የአማርኛ ሰዋስዋዊ መዋቅሩን (ባለቤት + ተሳቢ + ግስ) መሰረት አድርጎ
የመደብ፣ የቁጥር፣ የጾታ፣ የጊዜ ስምምነትን እንዲሁም የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀምን ይመለከታል(ባዬ፣ 2009)።
2.7.1 የቁጥር ስምምነት
ቁጥር በአንድ ስም የሚጠቀስን ነገር ምን ያህልነትን ወይም ስንትነትን የሚገልጽ ስዋሰዋዊ ባህሪ ነው፡፡
እንደየሚገልጸው ነገር አሃዛዊ መጠን (አንድ፣ ሁለት፣ ጥቂት፣ ብዙ ወይም ከመጠን በላይ) ሊሆን ይችላል፡፡ ቁጥሩ አንድ
ብቻ የሆነን ነገር የሚጠቁም ስም የነጠላ ቁጥር ስም ይባላል፡፡ መጠኑ ብዙ የሆነን ነገር የሚጠቁም ስም የብዙ ቁጥር
ስም ይባላል፡፡ በዚህ አይነት ቁጥርን በጥቅሉ ነጠላና ብዙ ብለን በሁለት እንከፍላቸዋለን፡፡ ስሞችንም እንደዚሁ
እንደሚያመለክቱት የቁጥር አይነት ነጠላ ወይም ብዙ ብለን እንለያቸዋለን፡፡ ነጠላ ስሞች ነጠላነትን የሚያመለክቱ
ምንም የተለየ ምልክት የላቸውም፡፡ ለምሳሌ፡- ልጁ፣ በግ፣ ሰው፣ ወዘተ. የነጠላ ስም ምሳሌ ናቸው። ይሁን እንጅ
ነጠላነታቸውን የሚያመለክት ምእላድ የላቸውም። ነገር ግን አንዳንድ ስሞች ነጠላነትን የሚያመለክቱበት ምእላድ
ይኖራቸዋል።
ምሳሌ፡- ወንድም ------ወንድም-እየ------- ወንድምየ
እህት---------እህት - እየ -------እህትየ
በነጠላ ስር የሚታዩት ተራ ነጠላ ነገርን ብቻ የሚያመለክቱ ሲሆኑ በንጥል ስር ያሉት ግን ተራ ነጠላነትን ሳይሆን
የተለየ ነጠላነትን (ንጥልነትን) የሚያመለክቱ ናቸው። አንድ ነገርን ብቻ ሳይሆን አንድ የተለየና የታወቀ ነገርን
ይጠቁማል። እንደነዚህ ያሉ ስሞች አንዱ ከሌሎች ተለይቶና ተነጥሎ የሚታወቅ ነገርን ስለሚጠቁሙ ንጥል ስሞች
ይባላሉ። ሌላው አስቸጋሪ የቁጥር ነገር የብዙ ቁጥር የሆኑ የግእዝ ስሞችን ወደ አማርኛው ሲገቡ እንደ ነጠላ ቁጥር
የአማርኛ ስሞች ይቆጠርና (ኦች) የሚለውጥ ምእላድ ያስከትላሉ። በዚህም ምክንያት እንደ ካህናት ያሉ ስሞችን
ምእላዱን ሲያስከትሉ ካህናት- ኦች ይሆናሉ። ይህ አይነት አጠቃቀም ደግሞ የቤተክርስቲያን አባቶችንና የግእዝ ቋንቋ
ተናጋሪዎችን እጅጉን ያስቆጣል። ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የብዙ ብዙ ምእላዶችን መጠቀም ነው (ባዬ 2009፣113-114)
፡፡

10
2.7.2 የጾታ ስምምነት
ስሞችን በወገን በወገን የምንለይበት ሰዋሰዋዊ ባህሪ ነው። ሰዋሰዋዊ ብቻ ሳይሆን፣ ተፈጥሮአዊም ሊሆን ይችላል።
በተፈጥሮአዊነቱ ስሞችን የወንድና የሴት ወገን ብለን በሁለት እንድንከፍል ይረዳናል። በተፈጥሮአቸው የወንድ
ምልክት ያላቸው የወንድ ጾታ በተፈጥሮአቸው የሴት ምልክት ያላቸው የሴት ወገን ተብለው ይለያሉ። ከሰዋሰው
አኳያም ስሞች ተባእታይ እና አንስታይ ተብለው እንደዚሁ በሁለት ይከፈላሉ። ተባዕታይነት እና አንስታይነት
ከተፈጥሮ ጾታ ማለትም ከወንድነት ወይም ከሴትነት ጋር ሊያያዝ ወይም ላይያያዝ ይችላል። በመጠናቸው ትንሽ
የሆኑ ነገሮችም በአማርኛ እንደ እንስት ስለሚቆጠሩ እነሱን የሚገልጹ ስሞች የአንስታይ ጾታ ምእላድን ያስከትላሉ።
አንስታይነት ትንሽነትን ይመለከታል ማለት ነው። ተባእታይነትም በአንጻሩ ትልቅነትን ሊያመለክት ይችላል።
ስለዚህም በተፈጥሮ ጾታው ወንዴ የሆነ እንስሳ በመጠኑ ትንሽ ከሆነ በአንስታይ ጾታ ሊጠራ ይችላል። እንዲሁም
በተፈጥሮ ጾታው እንስት (ሴቴ ) የሆነ እንስሳ በመጠኑ ትልቅ ወይም በባህሪው ወንዳወንድ ከሆነ በተባእታይ ጾታ
ሊጠራ ይችላል። ስለዚህም ወንዱን አንቺ ብለን በአንስታይ ጾታ ሴቷን ደግሞ አንተ ብለን በተባእታይ ጾታ
የምንጠራበት ጊዜ አለ። ጉዳዩ ጾታ ከወንድነትና ከሴቴነት ጋር ብቻ ሳይሆን ከመጠንና ከባህሪ ጋርም ግንኙነት ሊኖረው
እንደሚችል የሚጠቁም ነው። ቋንቋውም ይህን በምእላድ ወይም በመዋቅር ያሳያል። ከዚህም ሰዋሰዋዊ ባህርያትን
ብቻ ማሳየት ሳይሆን ማህበራዊ ግንኙነቶችንም ማንጸባረቁን ልብ ልንል ይገባል (ባዬ 2009 ፣ 120-121)።
2.7.3 የመደብ ስምምነት
በአማርኛ ቋንቋ ስርዓት የመደብ ስምምነት በነጻና በጥገኛ ተውላጠ ስሞች ይገለጻል። በቋንቋው ውስጥ የሚገኙት ነጻ
ተውላጠ ስሞች ብዙ ጊዜ የተለመዱት ናቸውና እነሱን እናያለን።

መደብ ቁጥር አክብሮት


ነጠላ ብዙ -
አንደኛ እኔ እኛ -
ሁለተኛ አንተ/አንቺ እናንተ አንቱ/እርስዎ
ሦስተኛ እሱ/እሷ እነርሱ እሳቸው

መደብን በምንጠቀምበት ጊዜ ቁጥርንም ሆነ ፆታን አብሮ እናገኘዋለን፡፡ በመሆኑ እያንዳንዳቸውን እንደሚከተለው


እንመለከታለን፡፡
2.7.4 የጊዜ ስምምነት
በዓረፍተ ነገር ውስጥ ጊዜ ወሳኝ ነው፡፡ ጊዜ የዓረፍተነገሩ ድርጊት የት ተጀምሮ የት እንዳለቀ የሚያሳይ ነው፡፡ ጊዜ
ከመቼ እስከ መቼ እንደዘለቀ የዓረፍተ ነገሩን መነሻና መድረሻ መጠቆም ይኖርበታል፡፡ ይህን ሃሳብ ደረጀ (1996)
እንዲህ በማለት ያብራራዋል፡፡ “ጊዜ ዓረፍተ ነገሩ ወደ ፊት የሚፈጸም ከሆነ ካለፈው እስከ አሁን የቀጠለ ወይም
ድርጊቱ ያለቀ /የተጠናቀቀ መሆኑን ማሳየት አለበት”፡፡ የጊዜ ስምምነት በሦስቱ የጊዜ ሂደቶች ማለትም የሃላፊ ጊዜ፤
የአሁን ጊዜ እና ወደፊት ጊዜ ተስማምተው በስርአት አረፍተ ነገሩን መግለጽ አለባቸው፡፡
11
ምሳሌ፡- ድርጅቱ የቅጥር ማስታወቂያ አውጥቶ ነበር፡፡ (ሃላፊ ጊዜ)
መስሪያ ቤቱ የቅጥር ማስታወቂያ ይለጥፋል፡፡(የወደፊት ጊዜ)
የትምህርት ቤት ግንባታ እየተካሄደ ነው፡፡(የአሁንና የወደፊት ጊዜ)
2.7.5 የስርዓተ ነጥብ አገልግሎት
የስርዓተ ነጥብ ሚና ከዓረፍተ ነገር አኳያ የሚታይ ነው፡፡ አንድ ነጥብ፤ ሁለት ነጥብ፣ ነጠብጣብ፤ አራት ነጥብ፣ ጥያቄ
ምልክት፣ ሁለት ነጥብ ከሰረዝ… እያልን ብንዘረዝር የሁሉም አገልግሎት ከአንድ ዓረፍተ ነገር አኳያ የሚነሳ ነው፡፡
አንድ ዓረፍተ ነገር የተሟላ ሃሳብ የሚያስተናግድ ነው፡፡ በመሆኑም ሃሳቡን ስርዓት አስይዞ ለማቅረብ ስርዓተ ነጥቦች
ከፍተኛ ሚና አላቸው፡፡ በሌላም በኩል ስርዓተ ነጥቦችን በምንጽፍበት ወቅት በአግባቡ መጠቀም መቻል ይኖርብናል፡፡
ከዓረፍተ ነገሮች ውጭ ስርዓተ ነጥቦች በቃላት እና በቃላት፣ በሃረጋት እና በሃረጋት መካከል ሊመጡ ይችላሉ። ይህን
ሀሳብ የሚያጠናክርልንና የስርዓተ ነጥብን አስፈላጊነት የሚያመላክትልንን የየሻውን (1996፣122) ገለጻ እንዲህ
እናነባለን ፡-
በአንድ ወቅት አስተማሪዬ የነገሩኝ ታሪክ ነበር ። ይህ ታሪክም ፈረንጆች “Comma killed the
man” የሚል ታሪክ አላቸው አሉ። ዳኛው ለህግ ፈጻሚው አንዲት ትዛዝ ይጽፋሉ ። ትዕዛዙም
“kill him, not leave him” ይላል። የመልዕክቱም ትርጉም “ግደለው፣ አትልቀቀው” የሚል ነበር
ማለት ነው ። ህግ ፈጻሚው አካል፣ ይህ ትዕዛዝ እንደደረሰው በሰውዬው ላይ የሞት ርምጃ
ወሰደበት ወይም ገደለው። በኋላ ሲጣራ፣ ዳኛው ማለት የፈለጉት “kill him not, leave him”
ማለት ኖሯል። ሊተላለፍ የፈለጉት ትዕዛዝም፣ አትግደለው፣ ተወው ወይም ልቀቀው” ነበር
ማለት ነው። በአንዲት ስርዓተ ነጥብ ስህተት ምክንያት ምስኪኑ ሰውዬ አላግባብ ሞተ። እንዲህ
ማለት የፈለግሁትም የስርዓተ ነጥብ አገልግሎት እየተረሳ ስለሆነና ትኩረት እንዲሰጠው
ስለፈለግሁ ነው።

2.8 የተዛማጅ ፅሁፍ ቅኝት


አጥኚዋ ከዚህ ጥናት ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተዛማጅነት ያላቸውን በማስታወቂያ ዙሪያ የሚዳስሱ ስራዎች
በጥቂቱ የተመለከተች ሲሆን ከዚህ ጥናት ጋር ያላቸውን ልዩነት አጥኚዋ በትኩረት አሳይታለች። ይሁን እንጂ ከዚህ
ጥናት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው የጥናት ፅሁፍ ማግኘት አልተቻለም። በዚህም መሠረት በዲላ ዩኒቨርሲቲ የተገኙ
ጥናታዊ ፅሁፎች የሚከተሉት ናቸው።
በመጀመሪያ የተዳሰሰው የበአካሉ በላይ (2004) “በ 2003 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎች
የቋንቋ አጠቃቀም ትንተና” የሚል ነው። የዚህ ጥናት ዋና ትኩረት በተጠቀሰው ጋዜጣ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎችን
ቋንቋ መመርመር ሲሆን በዚህ መሰረት ይህ ጥናት ከበአካሉ በአላማቸው ተመሳሳይ ቢሆንም ልዩነት አላቸው።
ልዩነትም የበአካሉ በላይ ፅሁፍ በህትመት ሚድያ ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህ ጥናት ሰሌዳ (መለጠፊያ) ቦታ ላይ በሚለጠፉ
ፅሁፎች ላይ ነው። በተጨማሪም የጊዜ ልዩነትም አላቸው። የበአካሉ ጥናት በ 2003 ዓ.ም በተሰራጩ
ማስታወቂያዎች ሲሆን ይህ ጥናት ደግሞ በ 2012 ዓ.ም በወጡ ማስታወቂያዎች ላይ ነው።
12
ሁለተኛው ከዚህ ጥናት ጋር ተዛማጅነት ያለው ፅሁፍ የከፍያለው (2004) “የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን የማስታወቂያ
ይዘት ትንተና” የሚል ሲሆን ጥናቱ በማስታወቂያ ዙሪያ የተሠራ መሆኑ አንድ ሲያደርጋቸው ልዩነታቸው ደግሞ
የከፍያለው ጥናት የኤሌክትሮኒክስ ሚድያ ላይ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ሲሆን ይህ ጥናት ደግሞ ህትመት ሚድያ ላይ
ያተኮረ መሆኑ ነው። በተጨማሪም የዚህ ጥናት ቋንቋ አጠቃቀም ትንተና ሲሆን የከፍያለው ጥናት ደግሞ የይዘት
ትንተና መሆኑ ያለያያቸዋል።
የመጨረሻው ከዚህ ጥናት ጋር ተዛማጅነት ያለው የኢሳያስ ኢልባሶ (2010) “ከየካቲት 2009 ዓ.ም ወዲህ በአዲስ
ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎች የቋንቋ አጠቃቀም ትንተና” ሲሆን ከዚህ ጥናት ጋር አንድ የሚያደርጋቸው
የመጀመሪያው ቋንቋ አጠቃቀም ላይ ማተኮራቸው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሠዋሰው እና የቃላት ምርጫን
የሚተነትኑ መሆናቸው ነው። የኢሳያስ ጥናት ከዚህ ጥናት የሚለየው የኢሳያስ ጥናት ማስታወቂያዎቹን ምስል እና
የመልዕክት ቁጥብነት የሚያሳይ ሲሆን ይህ ጥናት በናሙናዎቹ ስዕል ያለው ማስታወቂያ ባለመኖሩ ይህ አለማሳየቱ
ነዉ።

13
ምዕራፍ ሦስት
3. መረጃ ትንተና
የዚህ ጥናት ዋና አላማ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ በ 2012 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የዋሉ ማስታወቂያዎችን የቋንቋ
አጠቃቀም መተንተን ነው። በመሆኑም መረጃዎችን በየህንፃው እና በየማስታወቂያ መለጠፊያ የተለጠፉትን
ማስታወቂያዎች በመሰብሰብ ከክለሳ ድርሳናት እና ከንዑስ አላማ ጋር በማገናዘብ እንደሚከተለው ማብራሪያ
ተሠጥቷል።

3.1 የቃላት አጠቃቀም ችግር ትንተና

3.1.1 የጉራማይሌ ቃላት አጠቃቀም


በቋንቋዎች መካከል፣ የቋንቋ አካላትንም (የቃላት፣ የሀረጋት፣ የእርባታ ምዕላዶች ወዘተ.) ሆነ የቋንቋ ባህሪያትን
(የአገላለጽና የመዋቅር መልኮችን) መዋዋስ የነበረ፣ ዛሬም ያለ፣ ወደፊትም የሚቀጥል ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን
ማስታወቂያ መፃፍ ያለበት በመደበኛ ቋንቋ መዋስ አለ ተብሎ እንደፈለጉ እየተዋሱ ማስገባት አስፈላጊ አይደለም።
ምሳሌ 1፦ “በዩኒቨርሲቲው በሚወጣው ሁለተኛ ዙር የምርምር ፕሮፖዛል ጥሪ ከዚህ በታች
በተዘረዘሩት ትኩረት የሚሹ የምርምር ርዕሶች ላይ ፕሮፖዛል አዘጋጅታችሁ…”
በ 14/03/2012 በማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ- ሰብዕ ኮሌጅ የወጣ ማስታወቂያ ሲሆን “ፕሮፖዛል” የሚለው የእንግሊዘኛ
ቃል በአማርኛ ሰፍሮ እናገኘዋለን። ይህ ቃል “ንድፈ ጥናት” የሚል የአማርኛ አቻ እያለዉ ያለአግባብ በዘፈቀዴ
ገብቷል። በመሆኑም የራሳችንን ቋንቋ ተጠቅመን ብንፅፈው መልዕክቱ ግልፅ እንዲሆን ያደርጋል።
ምሳሌ 2፦ ፕሮፖዛል ድፌንስ(defence) የሚካሄደው ሰኞ (25/05/2010) ጧት
2:30-6:00 ሰዓት…”
ይህ ማስታወቂያ መቼ እንደወጣ አይታወቅም፤ ነገር ግን ከመልዕክቱ አንፃር በጥር ወር እንደወጣ መገንዘብ ይቻላል።
በዚህ ማስታወቂያ “ፕሮፖዛል ድፌንስ (defense)” የሚል ሀረግ እናገኛለን። ይህን ሀረግ “የንድፈ ጥናት አቅርቦት”
የሚለው ይተካዋል። በተጨማሪም “defence “የሚለው ቃል አላስፈላጊ ነው።
ምሳሌ 3፦ “…ከዚህም መካከል መፅሄት ለማሰራት የመጀመሪያ የሆነው
ፎቶ ፕሮግራም ቅድሚያ ለመስጠት ያሰብን ስለሆነ…”
ይህ ማስታወቂያ ደግሞ በተመራቂ ተማሪዎች ኮሚቴ የወጣ ሲሆን “ፕሮግራም” የሚለው ቃል እንግሊዘኛ ነው፤ አሁን
አሁን ልክ እንደ አማርኛ ቋንቋ ተቆጥሮ ስራ ላይ እየዋለ ይገኛል። በመሆኑም በአማርኛ አቻ ቃሉ “መርሀ ግብር” ተብሎ
ቢስተካከል የባዕድ ቋንቋን ከማሳደግ የራስ ቋንቋ ማሳደግ ይቻላል።

14
3.1.2 የዘዬ (ቀበልቻ) ቃላት አጠቃቀም
ዘዬ የተወሰነ ቡድን (የማህበረሰብ አባላት) የሚጠቀምበት የቋንቋ አጠቃቀም ልዩነት ነው፡፡ የቋንቋ አጠቃቀም
ልዩነቱም የሚመጣው በመልከዓ ምድራዊ ሁኔታና በማህበራዊ ሁኔታ ነው፡፡ የአንድ ቋንቋ ዘዬ ተናጋሪዎች በዘዬ ልዩነት
ሳቢያ ከመግባባት አይታገዱም፡፡ በድምጽ፣ በቃላትና በአባባሎች ልዩነት ሳቢያ ግን ግርታ ወይም የመልዕክት መደናገር
ሊፈጥር ይችላል፡ ይሁንና መልዕክቱን ሊገነዘቡት ስለሚችሉ አለመግባባት አይፈጠርም፡፡ ይሁን እንጂ ግርታን
በመፍጠሩ ለማስታወቂያ ፅሁፍ ተመራጭ አይደለም።
ምሳሌ 1፦ “በተማሪዎች መተዳደሪያ ደምብ የተጠቀሱት የዲሲፕሊን መምሪያ…”
በ 27/04/2012 ዓ.ም በተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር ወጥቶ በተማሪዎች ህብረት ህንፃ የተለጠፈ ሲሆን በዚህ
ማስታወቂያ ውስጥ መደበኛ ያልሆነ “ደምብ” የሚል ቃል እናገኛለን። ይህ ቃል በአብዛኛው ጊዜ የቋንቋ ትምህርት
ያላጠኑ ወይም የንግግር ቋንቋን በፅሁፍ የመጠቀም ልምድ ያላቸው ሰዎች እንደዚህ መፃፋቸው ግልፅ ነው። ይህ ቃል
“ደንብ” ተብሎ መፃፍ አለበት።
ምሳሌ 2፦ “…በተጨማሪም ከአቻወቻቹ ጋር መመካከር ትችላላቹ።”
ይህ ማስታወቂያ በሴቶች ህንፃ ቁጥር 512 የሚገኘው ዜሮ ፕላን አባላት የለጠፉት ሲሆን “አቻዎቻችቹ” እና
“ትችላላቹ” የሚሉት ኢ-መደበኛ ቃላት ይገኛሉ። በመሆኑም በማስታወቂያ አፃፃፍ ሂደት እንደነዚህ ያሉ ቃላት
አጠቃቀም ማስወገድ ስለሚገባ “አቻወቻቹ” የሚለው “አቻዎቻችሁ” ተብሎ እንዲሁም “ትችላላቹ” የሚለው
“ትችላላችሁ” ተብሎ መፃፍ ይገባዋል።

ምሳሌ 3፦ “…በኦዳ ያኣ ጊቢ መሆኑን አውቃችሁ እንድትዘጋጁ ት/ክፍሉ ያሳስባል።”


በዚህ ዓ. ነገር ውስጥ መደበኛ ያልሆነ ቃል “ጊቢ” የሚለው ሲሆን በአብዛኛው ጊዜ በንግግር ወቅት የሚከሰት ቃል
ሲሆን በፅሁፍ ሲቀርብ ግን “ግቢ” ተብሎ መፃፍ አለበት። ኢ-መደበኛ ቃላት ተግባቦትን ጨርሰው ያግዳሉ ማለት
ሳይሆን ግርታን በመፍጠር መግባባትን ያደናቅፋሉ ለሁሉም አንባቢ ያላቸው እውቅናም አናሳ ነው።

3.1.3 የድረታ ችግር


ቃላት ሃሳብ ናቸው፡፡ ያለአግባብ ሲባክኑ የተግባቦት ችግር ያስከትላል፡፡ ምጣኔ ቃላት ደግሞ የአንድ አረፍተ ነገር የተዋጣ
መሆን ከሚመዘንባቸው ቁም ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ይህም በምንገልጸው ሃሳብና ያንን ሃሳብ ለማቅረብ
በምንጠቀምባቸው ቃላት መጠን ይመዘናል፡፡ ለመገለጽ የምንፈልገውን ሃሳብ ወይም ስሜት እንደምንም ተጣጥረን
አንዴ ብቻ ለማለት መሞከር እንጂ ዙሪያውን እየከበብን ያዝ ለቀቅ አለማድረግ ጊዜንም አለመፍጀት ያስፈልጋል፡፡
አረፍተ ነገሮች አጭርም ረዥምም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን በአጭርም ቢሆን በረዥም ዓረፍተ ነገር ውስጥ ቃላት
ተደጋግመው ከመጡ ከሚገባው በላይ ብክነትን አሳይቷል ማለት ነው። ይህንንም ከሚከተሉት ናሙናዎች መግለፅ
እንችላለን።

15
ምሳሌ 1፦ “ለበርካታ አመታት ስትጠይቁ የነበረው ጥያቄያችሁ ምሳሽ አግኝቷል እና እያገኘም
ስላለ እንኳን ደስ አላችሁ…”
ይህ ማስታወቂያ በ 17/03/2012 በተማሪዎች መማክርት አስተባባሪ የወጣ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ቃላት በግልፅ
ባለመፃፋቸው እና የቃላት መደራረት በመኖሩ መልዕክቱን እንዲዛባ አድርጎታል። የበርካታ አመታት ጥያቄያችሁ ምላሽ
በማግኘቱ እንኳን ደስ አላችሁ ተብሎ መፃፍ ይገባዋል።
ምሳሌ 2፦ “በ 27/04/2012 ዓ.ም እና በ 29/04/2012 ዓ.ም በተካሄደ ድንገተኛ ፍተሻ ቅኝት
በኦዳ'ያኣ ግቢ ሶሻል ሳይንስ ቤተ መፅሀፍት 2 ተኛ ፈረቃ ላይ የተመደባችሁ ሰራተኞች
ስራ ባለመግባታችሁ አገልግሎቱ እንደተስተጓጎለ በሽፍት አስተባባሪው ከላይ
በተጠቀሱት ቀናት ለቤተ መፅሀፍት ዳይሮክቶሬት ሪፖርት አድርገዋል።
ስለሆነም ከላይ በስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሳችሁ የሶሻል ሳይንስ ቤተ-መፅሀፍት
ሰራተኞች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ በእናንተ መሸፈን የሚገባው ስራ
በችልተኝነት እና በግዴለሽነት ባለመሸፈኑ…”
ይህ ማስታወቂያ በ 30/04/2012 በማህበራዊ ሳይንስ ቤተ-መፅሀፍ የተለጠፈ ሲሆን የድረታ እንዲሁም የተውሶ ቃላት
ጥርቅም ነው። በመሆኑም በውስጡ ያሉት የተውሶ ቃላት መልዕክቱን አሰልቺ አድርጎታል። ይሄም
“በ 27 እና 28/04/2012 ዓ.ም በተካሄደ ድንገተኛ ቅኝት በኦዳ'ያኣ ግቢ ማህበራዊ
ሳይንስ ቤተ-መፅሀፍ 2 ተኛ ፈረቃ ላይ የተመደባችሁ ሰራተኞች በእናንተ መሸፈን
የሚገባው ስራ በችልተኝነት ባለመሸፈኑ አገልግሎቱ እንደስተጓጎለ በፈረቃ
አስተባባሪው ለቤተ-መፅሀፍት የስራ አመራር ቦርድ ሪፖርት አደርጓል። ስለሆነም
በእናተ መሽፈን የሚገባዉ ስራ…”
ተብሎ ቢስተካከል አጭር፣ ግልፅ እንዲሁም ለማንበብ የማያሰለች ይሆናል። በተጨማሪም የተውሶ ቃላትን አስወግደን
በቋንቋው ብንፅፈው መልዕክቱ ግልፅ እንዲሆን ይረዳል።

3.1.4 የሙያ ቃላት አጠቃቀም


ሙያ ነክ ቃላት የሚባሉት በአንድ ሙያ መስክ ወይም የትምህርት ዘርፍ የሰለጠኑ ሰዎች ከሙያዉ ጋር የተያያዙ
ጉዳዩች ለመግለፅ የሚገለገልባቸውቃላት ናቸው። ሙያ ነክ ቃላት አንባቢው ከሚያብራራው ሙያ ጋር ትዉዉቅ
ያለው ካልሆነ በስተቀር ሀሳብን መጋራት ላይኖር ይችላል። ይሄንንም ከሚከተለው ምሳሌ ማየት እንችላለን።
ምሳሌ 1፦ “ማስታወቂያ ከጥር 27/2012 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት የሚፈፀም የ JEG
ድልድል የስራ መደብ ምርጫ…”
ይህ ማስታወቂያ በ 25/5/2012 ለአስተዳደር ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የተለጠፈ ሲሆን “JEG” የሚለው ቃል
አብዛኛውን ጊዜ በመንግስት ሰራተኝነት ተቀጥረው የሚሰሩ ማህበረሰቦች ሲጠቀሙበት እናያለን። ይህንን ቃል
ከእነዚህ ማህበረሰብ ውጪ ያሉ አይግባቡበትም። ስለሆነም “የደረጃ እድገት” ተብሎ ቢስተካከል ጥሩ ነው።

16
ምሳሌ 2፦ “ዛሬ ማለትም በቀን 08/04/2012 የባርሴሎና እና ሪያድ ማድሪድ ጨዋታ መኖሩ
ይታወቃል።…”
ይህ ማስታወቂያ የወጣበት ቀን ባይፃፍም ከፅሁፉ በታህሳስ ወር የተለጠፈ መሆኑን ማወቅ ይቻላል። በዚህ ዓ. ነገር
ውስጥ “ባርሴሎና” እና “ሪያድ ማድሪድ” የሚሉ ሁለት ቃላት እናገኛለን። እነዚህ የእግር ኳስ ቡድን ስሞች የእግር ኳስ
ጨዋታ ዕውቀት እና ትኩረት የሌለው ሰው ላይገነዘባቸው ይችላል።

3.1.5 ድግግሞሽ
አንድን ሀሳብ አንድ ጊዜ ከገለፅን በኋላ እየተመለስን ከተገቢው በላይ ደጋግመን በምንፅፍበት ጊዜ የሚከሰት ነው።
የሚከተሉትን ምሳሌ እንመልከት

17
ምሳሌ 1፦ “የገና በዓልን አስመልክቶ በየትኛውም አካባቢ በተለይ በየትኛውም ክፍል ተቀጣጣይ
እና እሳት ሊፈጥር የሚችል ክብሪት፣ ሰንደል፣ ሻማ፣ ከሠል፣ እስቶቭ እና ሌሎች
ተቀጣጣይ ቁሶች …”
ይህ ዓ. ነገር በ 27/07/2012 ዓ.ም የተማሪዎች ህብረት ዳይሬክተር ማስታወቂያ ላይ የሠፈረ ሲሆን አንድ አይነት ፍቺ
ያላቸው ቃላት ተጠራቅመውበት እናያለን። በዚህ ዓ. ነገር ውስጥ “እሳት ሊፈጥሩ የሚችሉ ነገሮች” የሚለው በቂ
ሆኖ ሳለ ቃላት ያለ አግባብ ገብተው መልዕክቱ እንዲንዛዛ አድርገውታል። በተጨማሪም በየትኛውም አካባቢ በተለይ
በየትኛም ክፍል የሚሉ ሀረጋት እናገኛለን። ስለዚህ “በየትኛውም ቦታ” ተብሎ ቢስተካከል መልዕክቱ ሳይንዛዛ
ለተመልካች ይደርሳል።

3.2 የሰዋሰውአጠቃቀም ስህተት ትንተና


በማንኛውም የስነ ልሳን ባለሙያ እምነት በማንኛውም የክህሎት ትምህርት በስተጀርባ ሁሉም የቋንቋ ተማሪ
ሊገነዘበው የሚገባ ጥልቅና ረቂቅ የሆነ እውቀት አለ፡፡ የቋንቋ ስርዓት (ሰዋስው) በመባል የሚታወቀው ክፍል ነው፡፡ ይህ
ትምህርት የአንድን ቋንቋ ስርዓት ከድምጽ አሰካኩ እስከ ሀረግ አመሰራረቱ ድረስ የሚያሳይ ሳይንስ ነው፡፡ ዋነኛው
ዓላማው በቀጥታ የመጻፍ፣ የመናገር፣ የማንበብና የመረዳት ችሎታን የማዳበር ሳይሆን ከሚነበበውም ሆነ ከሚነገረው
ቃል፣ ሀረግ፣ አረፍተ ነገር፣ በድርሰት ጀርባ የሚገኝውን ረቂቅ ስርዓት ደረጃ በደረጃ ማሳየት ነው፡፡ ይህን በማድረግ
በክህሎት ትምህርት ውስጥ ትክክል ወይም ስህተት፣ ለምን መደበኛ ኢ- መደበኛ እንደሆነ ከስርዓቱ አንጻር እዲገነዘብ
ማስቻል ነው፡፡ በትክክል መጠቀምን ብቻ ሳይሆን ትክክለኛነት ራሱን መግለጽና በዚያ ችሎታም መሰረት ትክክለኛ
የሚባለውን አጠቃቀም መረዳትና መተግበር ነው (ባዬ 2009፣ xxi)።
በዚህም የአማርኛ ሰዋስው ስርዓት ስር፣ ባለቤት- ተሳቢ- ግስ የሚለውን ስምምነት ለመስራት ወይም ለማስኬድ
ደግሞ የቁጥር፣ የጾታ፣ የመደብ፣ የጊዜ፣ የስርዓተ ነጥብ … እያልን የምንተነትነው ይሆናል፡፡

3.2.1 የቁጥር ስምምነት


ቁጥር በአንድ ዓረፍተ ነገር ቅንብር ውስጥ የሚገኙ ቃላት የነጠላ ወይም የብዙነት ባህሪ ሊታይባቸው ይችላል። በአንድ ዓረፍተ ነገር
ውስጥ መሰረታዊ ፍችውን የሚያስገኙ ቃላት በቁጥር አመልካችነታቸው ተስማሚ ሆነው መገኘት እንዳለባቸው ማስተዋል ይገባል።
መሰረታዊ ፍቻቸዉን መያዝ አለባቸው ያልናቸው ቃላትም በርቱዕም ሆነ በኢርቱዕ መንገድ የዓረፍተነገሩ ባለቤትና ማሰሪያ አንቀጽ
ላይ ይታያሉ። እነዚህም የቁጥር ስምምነት ይኖራቸዋል ማለት ነው።
ይሁን እንጂ ከዚህ ቀጥሎ የምናያቸው ምሳሌዎች የቁጥር አለመስማማት ችግር የታየባቸው መሆኑን መረዳት
ይገባል።
ምሳሌ 1፦ “ከዚህ በታች የስም ዝርዝራችሁ የተገለፀው ተማሪዎች የተማሪዎች ዲስፕሊን ቢሮ
ስለምትፈለግ በ 20/04/2012 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ሰዓት ላይ እንድትገኙ
እናሳስባለን። “

18
ማስታወቂያው በ 17/04/2012 በተማሪዎች አገልግሎት ህንፃ ተለጥፎ የተገኘ ሲሆን በውስጡ ሁለት አይነት ስህተት
አለው። የመጀመሪያው ተሳቢ ያለ ቦታው መግባት ሲሆን ሁለተኛው የቁጥር ስምምነት ነው።ዓረፍተ ነገሩ
ከመጀመሪያ በብዙ ቁጥር ይጀምራል፤ በመካከል ነጠላ ቁጥር አለ፤ መጨረሻ ብዙ ቁጥር አለ። ይህ ዓ. ነገር
“ከዚህ በታች በስም የተዘረዘራችሁ ተማሪዎች ዲስፕሊን ቢሮ ስለምትፈለጉ
በ 20/04/2012 ከጥዋት 3:00 ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን።”
ተብሎ ቢስተካከልትክክለኛ ስርዓት ያለው ገላጭ ዓ.ነገር ነው።

3.2.2 የመደብ ስምምነት


መደብ ሰዎች በሚነጋገሩበት ወቅት ከሚኖራቸው ሚና ጋር የተገናዘበ ስማዊ ባህሪ ነው። በንግግር ወቅት
የተነጋጋሪዎች ሚና፣ ተናጋሪነት፣ ተነጋሪነት ወይም ኣድማጭነትና አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ታዛቢነት ነው። ታዛቢ ባለበት
እንነጋገር የሚባለውም ለዚህ ነው። ተናጋሪ የንግግሩ ምንጭ ስለሆነ፣ ኣንደኛ መደብ ይባላል። የሚናገረውም እኔ እያለ
ነው። ተነጋሪው ነገሩ የሚነገረው ሰው ነው። ስለዚህም ሁለተኛ መደብ ይባላል። “አንተ ስማ’’ እየተባለ ይነገረዋል ።
ከነዚህ ከሁለቱ ወጭ የሆነ ሰው ካለ ያ ሰው ሶስተኛ መደብ ይባላል። እሱ ወይም ይሄ ወዘተ እየተባለ ይጠቆማል።
እነዚህ ሶስት መደቦች በሁለት ኣይነት ቅርጽ ይከሰታሉ። ኣንደኛው በነጸ ምእላድ መልክ ሲሆን ፣ ሌላኛው በጥገኛ
ምእላድ ቅርጽ ነው። በመጀመሪያው ቅርጻቸው ሲከሰቱ መደበኛ ተውላጠ ስም ይባላሉ። እንደ ስሞች ሁሉ ለቁጥር
እና ለጾታ የተለያዩ ምዕላዶችን ሊያስከትሉ ወይም ሊያስቀከድሙ ይችላሉ (ባየ 2009፣ 135-136)፡፡ ዝርዝሩም
እንደሚከተለው ነው።

19
ምሳሌ 1፦ “ከላይ እንደተገለፀው በግል ችግር ምክንያት 04/05/2012 ዓ.ም
ጀምሮ ስለማልኖር ከራስዎ ስራ ላይ ደርበው የፈረቃ አስተባባሪን ስራ እንዲሰሩ የተወከሊሉ
መሆኑን እያሳወኩ የክፍሉ ሰራተኞች እና ግልባጭ
የተደረገላቸው ክፍሎች አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉላቸው አሳስባለሁ።”
ይህ ማስታወቂያ በ 29/04/2012 ዓ.ም በማህበራዊ ሳይንስ ቤተ-መፅሀፍ የተለጠፈ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ የመደብ
ስምምነት ችግር ይታይበታል። “የተደረገላቸው” የሚለው ሶስተኛ መደብን ሲያመለክት “እንድታደርጉላቸው”
የሚለው ደግሞ ሁለተኛ መደብን ያመለክታል። ስለዚህ የመደብ አለመስማማት ተፈጥሯል። ስለዚህ የተደረገላቸው
የሚለው “የተደረገላችሁ” ተብሎ ቢፃፍ መደቡ ተስማምቶ ትክክለኛው መልዕክት ይተላለፋል።
ምሳሌ 2፦ “የዩኒቨርስቲያችን ተማሪዎች ይሄንን አውቀው የመማር፣ የመግለፅ፣ የመከላከል
ብሎም ለሚመለከተው አካል መረጃ በመስጠት የበኩላችሁን ሀላፊነት
እንድትወጡ አሳስባለሁ።”
ይህ ዓ.ነገር በ 27/04/2012 ዓ.ም ከወጣው ማስታወቂያ የተገኘ ሲሆን “አውቀው” የሚለው ሶስተኛ መደብ
ሲያመለክት “የበኩላችሁን” እና “እንድትወጡ” የሚሉት ቃላት ሁለተኛ መደብን የሚያመለክቱ ናቸው። ስለዚህ
“አውቀው” የሚለውን ሦስተኛ መደብ ቃል “አውቃችሁ” ተብሎ ተስተካክሎ ለአንባቢ ግልፅ መሆን አለበት።
ምሳሌ 3፦ “ማንኛውም ተማሪ በህንፃ ዙሪያ እና ፍሎር ላይ እንዲሁም በመስኮት ላይ ስታጠብ
ወይም ስሸና የተገኘ ተማሪ ከባድ ርምጃ እንደምንወድ እናውቃል።”
ማስታወቂያ 28/02/2017 በወንዶች ህንፃ የተለጠፈ ሲሆን መልዕክት አስተላላፊው ለራሱ እንደፃፈው “ስሸና ወይም
ስታጠብ” እያለ ሲፅፍ እንመለከታለን። ነገር ግን መልዕክት የሚተላለፈው ለሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ ነው።
በዚህም ማስታወቂያ መልዕክት ማስተላለፍ የተፈለገው ለሦስተኛ ወገን መሆኑን ከፅሁፉ ማወቅ ይቻላል። ስለዚህ
“ሲታጠብ ወይም ሲሸና” ተብሎ መስተካከል አለበት።

3.2.3 የስርዓተ ነጥብ አጠቃቀም


የስርዓተ ነጥቦች ሚና ከዓረፍተ ነገሮች አኳያ የሚታይ ነው። የስርዓተ ነጥቦች ቁጥርም በጣም ብዙ ከመሆናቸው
የተነሳ ለአብነት ያህል አንድ ነጥብ፣ ሁለት ነጥብ፣ ነጠብጣብ፣ ነጠላ ሰረዝ፣ ድርብ ሰረዝ፣ አራት ነጥብ፣ ጥያቄ
ምልክት፣ ወዘተ. እያለን ብንዘረዝር የሁሉም አገልግሎት ከአንድ ዓረፍተ ነገር አኳያ የሚታይ ነው። አንድ ዓረፍተ ነገር
የተሟላ ሃሳብ የሚያስተናግድ ነው። ይህንን የተሟላ ሃሳብ ስርዓት አስይዞ ለማቅረብ ነው የስርዓተ ነጥቦች ኣገልግሎት
በሌላም በኩል በምንጽፋቸው ሃተታዎች ውስጥ ስርዓተ ነጥቦችን በአግባቡ መጠቀም መቻል ይኖርብናል። እናም
የስርዓተ ነጥቦች ጥናታችን በዚህ ክፍል ከዓረፍተ ነገር ትምህርቶች ጋር ተያይዞ መምጣቱ ተገቢ ነው። ጽሑፍና
ስርዓተ ነጥብ ያላቸው ወዳጂነት ወይም ግንኙነት እጅግ ላቅ ያለ ነው። ብዙዎች ቀደምት የስነጽሁፍ ምሁራን
ድርሰቶቻቸውን ይጽፉት የነበረውም ስርዓተ ነጥቦችን በአግባቡ ተጠቅመው ነበር። አሁን አሁን ግን አብዛኞቻችን
በትክክል ልንጠቀማቸው አልቻልንም። ማስታወቂያዎችን ለአብነት ስንመለከት፦

20
ምሳሌ 1፦ “ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደሞከረው ማንኛውም ተማሪ በህንፃው በላይ
በመስኮት በወንፊት እና በሌሎች በሮች …”
ይህ ማስታወቂያ በ 12/06/2012 በሴቶች ህንፃ የተለጠፈ ሲሆን ስርዓተ ነጥብን በአግባቡ አልተጠቀቀም። ነገሮችን
ወይም ስሞችን ለመዘርዘር፣ ሀረግን ከሀረግ ለመለየት፣ ምዕራፍን ከቁጥር ለመለየት ነጠላ ሰረዝ እንጠቀማለን። ነገር
ግን በዚህ ዓ.ነገር ይህ የስርዓተ ነጥብ ጉድለት አለበት። “ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረው ማንኛውም ተማሪ
በህንፃው ላይ፣ በመስኮት፣ በወንፊት እና በሌሎች በሮች …” ተብሎ መስተካከል አለበት።
ምሳሌ 2፦ “የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ካምፓስ ቤተ መፅሀፍት ባልደረባ የሆኑት በወሊድ
ምክንያት በቀን 01/05/2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት የተለዩ ሲሆን። እኛ
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መፅሀፍ ሰራተኞች…”
ይህ ማስታወቂያ ከየኒቨርሲቲው በር ላይ የተለጠፈ የሀዘን መግለጫ ሲሆን ቀን ባይኖረውም ከታች ባለው ቀን በጥር
ወር የተለጠፈ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ ማስታወቂያ ላይ አራት ነጥብ ያለቦታው ገብቷል። አራት ነጥብ የሚገባው
አንድን ሀሳብ ለመቋጨቱን ወይም መጨረሱን ለማመልከት ከማሰሪያ አንቀፅ በኋላ ነው። በዚህ ዓ.ነገር ግን “ሲሆን”
ከሚለው ቀጥሎ አራት ነጥብ እናገኛለን። “ሲሆን” የሚለው የሚያመለክተው ያልተቋጨ ወይም የሚቀጥል ሀሳብ
መኖሩን ነው ስለዚህ አራት ነጥብ ከዚህ ቦታ አያስፈልግም።
ምሳሌ 3፦ “ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ለ 2012 ዓ.ም ለጌታችን
መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን …”
ይህ ዓ.ነገር የቀረው ስርዓተ ነጥብ አለው። ይህም ስርዓተ ነጥብ ቃለ አጋኖ ነው። ምክንያቱም ለዲላ ዩኒቨርሲቲ
ተማሪዎች በሙሉ ካለ አፅንኦት ሠጥቶታል ማለት ነው። ስለዚህ ቃለ አጋኖ መጠቀም ነበረበት። “ለዲላ ዩኒቨርሲቲ
ተማሪዎች በሙሉ! እንኳን ለ 2012 ዓ.ም ለጌታችን መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
እያልን …” ተብሎ መፃፍ ነበረበት።

3.3 ምስል ከሳች እና ታዋሽነት


ምስል ከሳች እና ታዋሽነት ማለት አንድን ነገር በአዕምሯችን ቀረፀን ይዘን ያንን ነገር በምናይበት ጊዜ
እንድናስታውሰው የሚያደርገን ነው ይሄም አብዛኛውን ጊዜ የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ
ነው።
ምሳሌ፦ “…በዚህም መሰረት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ነባራዊ ሁኔታ ታህሳስ 16/2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 3:00-
7:00 ሰዓት በዋናው ግቢ ሁለገብ አዳራሽ የዲላ ዩኒቨርሲቲ እና የአካባቢው ማህበረሰብ
አባላት በተገኙበት በዓሉ በድምቀት ይከበራል። በእለቱ ልዩ የክብር እንግዶች ታዋቂው
ሰዓሊ የአካል ጉዳተኛ ብሩክ የሺጥላ እና የጆይ ኦስቲክስ ማዕከል መስራች እና ባለቤት
ወ/ሮ ዜሚ የኑስ ተገኝተው የማነቃቂያ ንግግር እና የልምድ ተሞክሯቸውን
የሚያካፍሉበት አስተማሪ መርሀ ግብር ተዘጋጅቷል።”

21
ይህ ማስታወቂያ በ 13/04/2012 ዓ.ም የተለጠፈ ሲሆን ማስታወቂያው የታዋቂ ሰዎች ስም እንዲሁም የሚያዝናኑ
እና የሚያስተምሩ መርሀ ግብሮች መኖራቸውን መግለፁ መቼ ቀኑ ደርሶ ባየሁት የሚያስብል እና ድባቡ በአእምሯችን
ውስጥ ምስል እንዲመጣ እና አይረሴ እንዲሆን አድርገውታል።

ምዕራፍ አራት

4. ማጠቃለያና አስተያየት
በዚህ ምዕራፍ ላይ የጥናቱ ማጠቃለያና ከጥናቱ ጋር የተዛመዱ በአጥኚዎቹ የተሰጡ አስተያየቶች በቅደም ተከተል
ይቀርቡበታል፡፡

4.1 ማጠቃለያ
በዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ ውስጥ በ 2012 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የዋሉ ማስታወቂያ ፅሁፎች
ላይ የቋንቋ አጠቃቀም፤ ስዋሰዋዊ ስርዓት እንዲሁም ምስል ከሳችነት እና ታዋሽነት ላይ ፍተሻ ተካሂዷል። በምዕራፍ
አንድ ላይም ለጥናቱ እንደ መነሻ የሆኑ የጥናቱ ዳራ፣ የጥናቱ አነሳሽ ምክንያት፣ የጥናቱ ዓላማ፣ የጥናቱ ጠቀሜታ፣
የጥናቱ ወሰን፣ የጥናቱ ክልል እና ገደብ፣ የጥናቱ ዘዴ፣ የናሙና አመራርጥ ዘዴ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴና መተንተኛ
ዘዴ ቀርበዋል። ለጥናቱ ትንተናም የየምሁራኑን ንድፈ ሀሳብ በማጣቀስ ተጠቅመናል፡፡ የጥናቱ ዘዴም ገላጭ ነው፡፡
ለጥናቱ መረጃ የሚሰበሰብበት ቦታ ኦዳ'ያኣ ግቢ በአመቺ ናሙና ስልት ተመርጧል፡፡ በማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳን፣
በመመገቢያ አዳራሽ በርን፣ በተማሪዎች የመኝታ ህንፃዎች፣ መግቢያ ስፍራን መሰረት በማድረግ 40 የማስታወቂያ
ፅሁፎች ተሰብስበዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥም 16 የማስታወቂያ ጽሁፎች በተራ የዕጣ ናሙና ስልት ተመርጠው ለመረጃ
ትንታኔው አገልግለዋል፡፡
በምዕራፍ ሁለት ላይም ክለሳ ድርሳናት ተከልሰዋል። በዚህ ስር የማስታወቂያ ምንነት፣ አጀማመር፣ አይነት፣
አገልግሎት እንዲሁም የቃላት ምርጫ፣ የቃላት አጠቃቀም፣ የስዋስው ምንነትንና የተዛማጅ ጽሁፍ ቅኝቶች የሚሉት
ተዳሰውበታል።
22
ምዕራፍ ሦስት የዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ዋና ክፍል ሲሆን በሰነድ ፍተሻ የተገኙ መረጃዎች በገላጭ የምርምር ስልት
ተተንትነው ቀርበዋል። ለጥናቱ ትንተናም የየምሁራኑን ንደፈ ሀሳብ በማጣቀሻነት አገልግለዋል። በቃላት ምርጫ
ረገድም እማሬያዊ እና ፍካሬያዊ ፍችዎችን በመለየት ለመመርመር ተክሞሯል፡፡ በመሆኑም ከመረጃዎች ለመረዳት
እንደተቻለው በማስታወቂያ ፅሁፎቹ ላይ ከፍካሬያዊ አገላለፆች ይልቅ እማሬያዊ የታየባቸው መሆኑን ለማረጋገጥ
ተችሏል፡፡
በቃላት አጠቃቀም ዙሪያ ደግሞ የባዕድ ቋንቋን በሰፊው የመጠቀም ችግር፣ ዘዬ (ቀበልኛ) ቃላትን የማዘውተር እና
ድረታን እና የተደጋገሙ ቃላት እና ሀረጋትን የመጠቀም ችግሮች እንዳሉ በመረጃዎቹ ተስተውሏል፡፡
በሰዋሰው ስርዓትም በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ የወጡ ማስታወቂያዎች ላይ ዐረፍተ የቁጥር እና የመደብ
አለመስማማት፣ የተሳቢ ያለቦታው መምጣት፣ ተገቢ ስርዓተ ነጥብ አለመጠቀም ችግሮች እንደሚታዩበት ለማረጋገጥ
ተችሏል።

4.2 አስተያየት
የጥናቱን ውጤት መሰረት በማድረግ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ኦዳ'ያኣ ግቢ ውስጥ የወጡ ማስታወቂያዎች የቋንቋ አጠቃቀም
ችግሮች ያሉባቸው መሆኑን ለማረጋገጥ ተችለዋል፡፡ ስለዚህም ለተገኙት ችግሮች አጥኚዎቹ የመፍትሄ ሃሳቦች
የሚሏቸውን እንደሚከተሉት አቅርበዋል፡፡
 ማስታቂያዎች ሲዘጋጁ አንባቢዎች ሊረዱት በሚችሉት በግልጽ ቋንቋ ወይም መደበኛ በሆነ የቃላት
አጠቃቀም መጠቀምና መጻፍ ቢችሉ፣
 የንግግርና የፅሕፈት የቃላት አጠቃቀምን ልዩነት የሚያውቁና የተረዱ ሰዎች ማስታዎቂያ እንዲያዘጋጁ
ማድረግ ቢቻል፣
 የስርዓተ ነጥብን ሚና እና አገልግሎት ባንተወው ( ባንዘነጋው ) ጥሩ መስራት እንደምንችል መገንዘብ ቢቻል፣
 ማስታወቂያዎችን የሚፅፉ ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ማስታወቂዎችን ከመለጠፋቸው በፊት ደጋግመው
ቢያነቡና የሚታዩ ስህተቶችንና ግድፈቶችን ለማረም ቢችሉ፣
 ማስታወቂያዎችን የሚፅፉ ሁሉ የቋንቋው ባለሙያ ናቸው ለማለት ስለማይቻልና የሚታዩትን ስህተቶች
ለማረም ይረዳ ዘንድ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቋንቋ እና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል ለአንዳንድ የስራ
ክፍሎች/ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ቢያመቻች የሚሉ ናቸው፡፡

23
ዋቢ ፅፎች
ሳሙኤል ወልደ ጊዮርጊስ (1999)። “በዲላ መሰናዶ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ 10L ክፍል ተማሪዎች
የፅህፈት ክሂል ፍተሻ።” ያልታተመ። ለመጀመሪያ ድግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ። ዲላ
ዩኒቨርሲቲ።
በአካሉ በላይ(2004)። “በ 2003 ዓ.ም በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎች የቋንቋ አጠቃቀም
ትንተና።”ያልታተመ። ለመጀመሪያ ድግሪ ማሟያ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ።
ባህሩ ዘርጋው (2000) ፡፡ ከፍተኛ መዝገበ ቃላት። አዲስ አበባ ፣ ንግድ ማተሚያ ድርጅት ።
ባዬ ይማም (2009):: የአማርኛ ሰዋሰው። አዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ቢኤ ማተሚያ ቤት፡፡
ተሻገር ሽፈራው (1996)። ማስታወቂያና መገናኛ ብዙሀን የጋዜጠኝነት ሀ.ሁ ። አዲስ አበባ፣ ሜጋ አሳታሚ ድርጅት።
አብነት ስሜ (2007) ። የቋንቋ መሰረታውያን ። አዲስ አበባ፣ ፋር ኢስት ትቴዲንግ ሃላ/የተ/የግ/ማ።
ኢሳያስ ኢልባሶ(2010)። “ከየካቲት 2009 ዓ.ም ወዲህ በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የወጡ ማስታወቂያዎች ቋንቋ አጠቃቀም
ትንተና።” ያልታተመ። ለአርት ባችለር ዲግሪ ከፊል ማሟያነት የቀረበ። ዲላ ዪኒቨርሲቲ።
ከፍያለው ዘውዴ (2004) “የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን ማስታወቂያ ይዘት ትንተና”። ያልታተመ። ለመጀመሪያ ድግሪ ማሟያ
የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ። ዲላ ዩኒቨርሲቲ።
የሻው ተሰማ (1996) ። ልሳነ ብዕር ከመልሳነ ሰብዕ ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ በብራና ማተሚያ ድርጅት ታተመ ።
ያለው እንዳወቀ (2009) ። የምርምር መሰረታዊ መርሆች እና አተገባበር ። ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፣ ተፈራ ስዩም ማተሚያ
ቤት፡፡
ደረጀ ገብሬ (1996) ። ተግባራዊ የጽህፈት መማሪያ ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ንግድ ማተሚያ ድርጅት።
ዳንኤል ብርሃኑ (2000) ፡፡ የማስታወቂያ መሰረታዊ መርሆች ። አዲስ አበባ።
ዳንኤል እና ሌሎች (1994) ። የትምህርት ጥናት እና ምርምር አተገባበር ። አዲስ አበባ ፣ሜጋ አሳታሚ
ድርጅት።
ጌታሁን አማረ (1990) ። ዘመናዊ የአማርኛ ሰዋሰው በቀላል አቀራረብ። አዲስ አበባ ፣ አልፋ አታሚዎች።
Thone, Sara (1997). Advanced English language. Hong Kong: MACMILLAN PRESS LTD.
word book encyclopedia (1994) Chicago: world book inc.
/Http://m. Economic times. Com definition/ advertising/.

24
ጥቅሶች በመገኛ ቋንቋቸው

 Print advertisement is covering a wide range of forms and products, so advertisers design
different kinds of campaign depending upon the kind of intended of audience they wish to
attract. The image, tone and language chosen will all refract the target group but in each case the
variety will be distinctive (Sara 1997,269).
 Advertising a massage designed to promote a product, a service or an idea. Is cheapest way to
inform large number of people about products or services for sale and persuade them to long
hence. Advertising is used and sponsored by social organizations, special interest group and
government( world book encyclopedia 1994,72).
 Advertising is a means of communication with the users of product or service, advertisement is
massage paid for those who Send them and are intended of inform of influence people who
receive them (/Http://m. Economic times. Com definition/ advertising/)

25

You might also like