You are on page 1of 7

ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ

ቅጽ
የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ
I. አጠቃላይ መግለጫ
የመሥሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ደረጃ 4 ሜዲካል ላቦራቶሪ ቴክኒሺያን ሜዲካል ላቦራቶሪ
II

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ/ተጠሪነት በፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር/ቢሮ ብቻ የሚሞላ
የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
የሜዲካል ላቦራቶሪ ክፍል ሃላፊ X

መሥሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
በየደረጃው ባሉ ጤና ተቋም
II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ ውጤቶችና ተግባራት
2.1 የሥራ መደቡ ዓላማ፡
 የሽንት የሰገራ፣ የደም፣ የቆዳ ቅርፊት፣ የወንድ ብልት ፈሳሽና አክታ ምርመራ በማድረግ፣የላቦራቶሪ አደጋዎች
ተጋላጭነትን በመከላከል፤የህሙማን ደህንነትን በማስጠበቅና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ለታካሚዎች ትክክለኛ
የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታ በመስጠት ጤናቸው እንዲሻሻል ማድረግ ነው፡፡
2.2 የሥራ መደቡ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1 ናሙና መሰብሰብ፤መመዝገብ፤ማዘጋጀት፤ ማደራጀትና ማስቀመጥ
 ናሙና ከመውሰዱ በፊት ታካሚዎች አስፈላጊዉን መረጃ ማሟላታቸውን ያረጋግጣል፡፡
 ናሙና ለመሰብሰብ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ያዘጋጃል፤
 ናሙና ለሚሰጡ ማንኛውም ታካሚ ስለ ናሙና አወሳሰድ እና አቀባበል መመሪያና ምክር ይሰጣል፡፡
 የታካሚዎቹን ሙሉ መረጃ በመመዝገብ የሽንት፣ የሠገራ፣ደም (capillary blood)፣ የቆዳ ቅርፊት (skin scraping)፣
የወንድ ብልት ፈሳሽና (Urethral discharge) አክታ ናሙናዎችን ይወስዳል፡፡
 የሰበሰባቸዉን የታካሚዎችን ናሙናዎች መለያ ይሰጣል፡፡
 የናሙና አግባብነት ከመመዘኛው ጋር ማመሳከርና ደረጃቸዉንና ጥራታቸዉን ላላሟሉ ናሙናዎች ምዝገባ በማካሄድ
አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጣል፡፡
 በክፍሉ የሚዘጋጁ ስታንዳርዶችን እና ዶክምንቶችን በአግባቡ ይጠቀማል፡፡
 የተሰበሰቡ ናሙናዎችን በተቀመጠው የአሰራር ቅደም ተከተል (SOP) መሰረት ለምርመራ ያዘጋጃል፣
 ናሙናዎቹ ከመመርመራቸዉ በፊት ወይም ከተመረመሩ በኋላ እያንዳንዱ ናሙና መቀመጥ ባለባቸዉ አግባብ ያደራጃቸዋል
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ
ቅጽ
ያስቀምጣቸዋል፡፡
 የተሰበሰቡትን ናሙናዎች በክፍሉ የማይሰሩትን ወደሚሰሩበት ክፍል ወይም ተቋም በናሙና ቅብብሎሽ ስርዓቱ መሰረት
ይልካል/ያስተላልፋል፤ውጤቱን ይቀበላል፤ ይመዘግባል፡፡
 በናሙና ቅብብሎሽ ስርዓት መሰረት ወደ ላቦራቶሪው በሪፈራል የሚመጡ ናሙናወችን ይመዘግባል፤ለሚመለከተው
ክፍል ያቀርባል፤ውጤቱን መዝግቦ ወደመጣበት ተቋም ይልካል፡፡
 በመማር ማስተማር ሂደት ለተግባር ልምምድ ስራ የሚያስፈልጉ ናሙናዎችን እና እቃዎችን እንደአስፈላጊነቱ ያዘጋጃል፤
 ናሙናዎችን በቀመጠዉ መመሪያ መሰረት ከምርመራ በኋላ እንደአስፈላጊነቱ በአግባቡ ያስቀምጣል
 ናሙናዎች የምርመራ ሂደታቸዉን ከጨረሱ በኋላ እንደየናሙና አይነቶች ለይቶ በተቀመጠዉ የአወጋገድ ስርዓት መሰረት
እንዲወገዱ ያደርጋል፡፡

ዉጤት 2 የላቦራቶሪ ምርመራ ግብዓቶችን እንዲሟሉ ማድረግ፣ ማዘጋጀትና ከዓገልግሎት በኋላ እንዲወገዱ ማድረግ
 የተለያዩ የመመርመሪያ ሪኤጀንትና ኬሚካሎችን (Working solution) ከዋናው ስቶክ ያዘጋጃል -
 በክፍሉ የሚሰሩትን የላቦራቶሪ ምርምራ ግብዓቶች እንዲሟሉ ጥያቄ ያቀርባል፤ ክትትል ያደርጋል፤ በአግባቡ ስራ ላይ ያውላል፡፡
 በአቀማመጥ ወይም በማኝኛዉም የስራ ሂደት ችግር የደረሰባቸዉ እቃዎችና ንብረቶች ሲያጋጥሙ ወዲያዉ ለክፍል ሃላፊዉ ሪፓርት
ያቀርባል፡፡
 የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ኬሚካሎችና አላቂ እቃዎች እንደአስፈላጊነቱ ቆጠራ ያከናዉናል፤ ዝርዝር ያዘጋጃል፡
 የመስሪያ ጊዜአቸው ያለፈባቸው ግብአቶችን መለየትና እንዲወገዱ ዝርዝራቸውን ለክፍል ሃላፊ ያሳውቃል፡፡
 አላቂና ቋሚ የላቦራቶሪ ግብዓቶችን በአግባቡና በማኑፋክቸረሩ መመሪያ መሰረት ያስቀምጣል፡ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፡፡
ዉጤት 3 የሽንትና ፓራሳይቶሎጂ ምርመራ ማድረግና ዉጤቱን ማጸደቅ
 የሽንት ምርመራዎችን (Physical & chemical) ሰርቶ ዉጤቱን ለሚያጸድቁ ላቦራቶሪ ባለሙያዎች ያቀርባል፡፡
 ፓራሳይቶሎጅካል ምርመራዎችን (Direct stool examination and malaria RDT) ሰርቶ ዉጤቱን ለሚያጸድቁ
ላቦራቶሪ ባለሙያዎች ያቀርባል፡፡
 የጸደቁ የላቦራቶሪ ውጤቶችን በትክክል በመመዝገብ ውጤቱን ለተገልጋዩ በወቅቱ ይሰጣል፡፡
 የሙያ ማሻሻያ ስልጠና (continuous professional development) ላይ ይሳተፋል እውቀቱን ያዳብራል፤
ዉጤት-4 የላቦራቶሪ አደጋዎች ተጋላጭነትን መከላከልና መቆጣጠር፤የህሙማን ደህንነትን ማስጠበቅና እና ቆሻሻን በአግባቡ ማስወገድ
 ህሙማንና ራሱን በላቦራቶሪ ዉስጥ ሊፈጠሩ ከሚችሉ የተለያዩ አደጋዎች ለመከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ የአደጋ
መከላከያ ቁሳቁሶችንና አልባሳትን በስራ ጊዜያት ሁሉ እንደየአስፈላጊነታቸዉ ይጠቀማል፡፡
 በላቦራቶሪ ዉስጥ አደጋዎች ሲከሰቱ እንደየአደጋዉ ሁኔታ አደጋዉን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተቀመጠዉን መመሪያ
ተከትሎ ተግባራዊ ያደርጋል፤ አደጋዉን ይቆጣጠራል፡፡
 የተፈጠረዉ አደጋ ከቁጥጥር ዉጪ ከሆነ ለሚመለከተዉ ክፍል በፍጥነት ሪፓርት ያደርጋል፡፡
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ
ቅጽ

 ለላቦራቶሪ ክፍል ስራዎች የጽዳት መጠበቂያ እና የብክለት መከላከያ ኬሚካሎችን (Disinfectant) በየእለቱ ያዘጋጃል፤
 የላቦራቶሪ መስሪያ ቦታዎችን (workstation) በየቀኑ ከስራ በፊትና በኋላ በማጽዳት የስራ አካባቢውን ከተላላፊ በሽታ
ይጠብቃል፣
 መልሶ ጥቅም ላይ የሚውሉ የላቦራቶሪ መገልገያ መሳሪያዎችን ከብክለት (ከጀርም) ነጻ ለማድረግ ስተራላይዝ እና
ዲስኢንፌክት ያደርጋል፤
 በስራው ወቅት የሚፈጠሩትን ባዮሎጂካል እና ኬሚካል ቆሻሻዎች የአወጋገድ መመሪያዉን ተከትሎ በአግባቡ
እንዲወገዱ ያደርጋል፤

III. የሥራው ባህርይ መግለጫዎች


3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ሥራው ለላቦራቶሪ ምርመራ የተላኩትን ታካሚዎች የተጠየቀውን የላቦራቶሪ ምርመራ አይነት እና የታካሚውን መረጃ ትክክለኛነት
መለየትና ማረጋገጥ፤የሚወሰደውን ናሙና አይነት መወሰን፤ለታካሚዉ ስለታዘዘው ምርመራ አይነት፣ ስለናሙና አወሳሰድ፣
ናሙና ሲወሰድ ስለሚከሰቱ ችግሮች፣ የናሙናው አሰባሰብ ጥራት ለምርመራው ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ እና ሌሎች
አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ወይም የምክር አገልግሎት መስጠት፤ ናመናውን ለመውሰድ ታካሚውን
ማዘጋጀት፤በተቀመጠው የአሰራር ቅደም ተከተል መሰረት ተገቢውን ናሙና መውሰድና ለዋናው ምርመራ
ማዘጋጀት፤በምርመራ ወቅት ትክክለኛውን የምርመራ ቅደም ተከተል በመከተል የሽንት፤ሰገራና የወባ ምርመራ ( malaria
RDT) ምርመራዎችን መስራት፣የላቦራቶሪ ክፍሉንና መሳሪያዎችን ንጽህና ከብክለት ነጻ መሆኑን ማረጋገጥን የሚጠይቅ
ሲሆን፤
 በስራ ክንዉን ወቅት ትክክለኛዉን መረጃ አለማግኘት፣ የመብራት መቆራረጥ፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ብልሽት መከሰት፣ ታካሚዎቹ በሰዓቱ
ናሙናዉን ያለማምጣት፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች የጥራት መጓደል፣ ኬሚካሎች ጥራት መጓደል፣ በማይክሮስኮፕ የሚታዩ ተዋስያን በአይትና
በመጠን መቀራረባቸው ለመለየት ማስቸገር እና የተለያዩ የናሙና እና ኬሚካሎች ማስቀመጫ መሳሪያዎች የሙቀት መጠን መቀያየር፤
ስራው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ ተያያዥና ከፍተኛ ትኩረትን የሚጠይቁ ችግሮች ናቸዉ፡፡
 እነዚህንም ችግሮች ትክክለኛዉን መረጃ በመሰብሰብ፣ ሌሎች የመብራት ሀይል አማራጭ ዘዴዎችን በማፈላለግ፣ ታካሚዎች ናሙና ሳያቆዩ
በሰዓቱ እንዲያመጡ ግንዛቤ በማስጨበጥ፣ የኬሚካል ማስቀመጫ መሳሪያዎችን በተገቢዉ ቦታ በማስቀመጥ፣ ከመጀመሪያ እሰከ መጨረሻ
ባሉት የምርመራ ሂደቶች ከመመርመሪያ ዲቫይሶች ጋር አብሮ ባለ የውስጥ ጥራት ቁጥጥር (in built quality control) በመስራት
ትክክለኛ የላቦራቶሪ ውጤት እንዲወጣ በማድረግ፣ በሥራ የተገኙ የላብራቶሪ ምርመራ ተሞክሮችን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ የተለያዩ
አማራጮችን በማመንጨትና የተሸለውን አማራጭ በመምረጥ ችግሮቹን መፍታትን ይጠይቃል፡፡
3.2. ራስን ችሎ መስራት
3.2.1. ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው የላቦራቶሪ የአፈፃፀም መመሪያዎችን፣ የሙያ ስነ-ምግባሮችና (SOP) መሰረት የሚከናወን ሲሆን ያልተለመዱ
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ
ቅጽ
የናሙናና የምርመራ ግኝቶች ሲያጋጥሙ በኃላፊው በሚሰጥ ግልጽ የላብራቶሪ መመሪያ መሰርት ይፈጸማል፡፡
3.2.2. ስራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው በተሰጠ መመሪያ መሠረት ተገቢውን የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው ይታያል፡፡
3.3 ተጠያቂነት፣
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት፣
 ሥራዉ ለላቦራቶሪ ምርመራ የተላኩትን ታካሚዎች የተጠየቀውን የላቦራቶሪ ምርመራ አይነት እና የታካሚውን መረጃ ትክክለኛነት
ማረጋግጥ፤ስለታዘዘው ምርመራ አይነትና ናሙና አወሳሰድ አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ወይም የምክር አገልግሎት ለታካሚው
መስጠት፤ናሙና ሲወሰድ ለሚከሰቱ ችግሮችና የናሙናው አሰባሰብ ጥራት ለምርመራው ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ
ለታከሚው ማስረዳት፤ናመናውን ለመውሰድ ታካሚውን በትክክል ማዘጋጀት፤በተቀመጠው የአሰራር ቅደም ተከተል
መሰረት ተገቢውን ናሙና መዉሰድና ለዋናው ምርመራ ማዘጋጀት፤በምርመራ ወቅት በትክክለኛው የምርመራ ቅደም
ተከተል መሰረት በደረጃው የሚሰሩትን የሽንት፤የሰገራና የደም (malaria RDT) ምርመራዎችን መስራት፣ የኪቶች
የውስጥ ጥራት ቁጥጥር (internal quality control) መስራት፣ የላቦራቶሪ ክፍሉንና መሳሪያዎችን ንጽህና መጠበቅና
እንዲሁም ከብክለት ነጻ መሆኑን ማረጋገጥ፤የክፍሉን እና የመሳሪያዎችን የሙቀት መጠን በየእለቱ መከታተልን
የሚጠይቅ ተግባር ሲሆን እነዚህን ተግባራት በአግባቡ ባይከናወን የበሽተኛ መጉላላት ይፈጠራል፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች
ብልሽትና የኬሚካሎች ብክነት ይፈጠራል፣ የላቦራቶሪ ዉጤት መዛባት ይፈጥራል፣ ታካሚዎች ለከፍተኛ ህመምና የጤና
መቃወስ ይዳረጋሉ፣ ይህም በሙያተኛውና በህክምና አገልግሎቱ ላይ ስራ በማስተጓጎል አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላል፡፡
3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 ሥራው የታካሚዉ የምርመራ ውጤት ሚስጥራዊነቱ ባይጠበቅና ሚስጥር ቢባክን ወይም ለማይመለከተው አካል ወይም
ቦታ አሳልፎ ቢሰጥ የታካሚዉን ስነልቦናዊና ማህበራዊ ግንኙነት ያቃዉሳል፣ በታካሚዉና በተቋሙ መካከል ከፍተኛ
አለመግባባትና ቅራኔን ይፈጥራል፤
3.4 ፈጠራ
 ሥራው አዳዲስ የላብራቶሪ ምርመራ ሃሳቦችንና የአሠራር ዘዴዎችን በማመንጨት የሥራው ውጤታማነት እንዲሻሻል
ማድረግን የሚጠይቅ ነው፡፡
3.5 የሥራ ግንኙነት
3.5.1. የግንኙነቱ ዓይነትና ደረጃ
 ሥራው ከውስጥ ከቅርብ ሃላፊዉ፤ ከሀኪም፣ ከክፍሉ ሙያተኞች፣ ከነርሶች፣ ከተቋሙ ዉጪ ካሉ ላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣
ከታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸዉ ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3.5.2. የግንኙነቱ ዓላማ/አስፈላጊነት
 ስለ ስራዉ መረጃና ልምድ ለመለዋወጥ፤ናሙና ለመስጠትና ለመቀበል፤የተሻሻለ የምርመራ ዘዴዎችን በላቦራቶሪው ዉስጥ
ለማምጣት፣ ተባብሮ ለመስራት፣ መመሪያ ለመቀበል፣ ምክርና ድጋፍ ለመቀበልና ለመስጠት፣ የሙያ ማሻሻ ያ ልምድ
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ
ቅጽ

ለማድረግ፡፡

3.5.3 የግንኙነት ድግግሞሽ


 ሥራው 30% የስራ ግንኙነት ማድረግን ይጠይቃል፡፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
3.6.1.1 በሀላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለበትም፡፡
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ
 የለበትም፡፡
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ /ገንዘብ/
 የለበትም፡፡
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራውን ለማከናወን የሚያገለግሉ እንደ ማይክሮሰኮፕ (Bright Field Microscope)፤ ሴንትሪፊውጅ፣ ጠረጴዛ፤
ወንበር፤ሸልፍ፤ ኮምፒዩተር፤ ፕሪንተር፤ ፍሪጅ፤አውቶክሌቭ እና ጠቅላላ ግምታቸው እስከ 300,000 ብር (ሶስት መቶ
ሺህ ብር ብቻ) የሚሆን የላቦራቶሪ እቃዎችን በጥንቃቄ መያዝና በአግባቡ ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በጋራ የመጠቀም
ኃላፊነት አለበት፡፡
3.7 ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ሥራዉ ለላቦራቶሪ ምርመራ የተላኩትን ታካሚዎች የተጠየቀውን የላቦራቶሪ ምርመራ አይነት እና የታካሚውን መረጃ ትክክለኛነት
ማረጋግጥ፤ስለታዘዘው ምርመራ አይነትና ናሙና አወሳሰድ አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ወይም የምክር አገልግሎት ለታካሚው
መስጠት፤ናሙና ሲወሰድ ለሚከሰቱ ችግሮችና የናሙናው አሰባሰብ ጥራት ለምርመራው ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽዖ
ለታከሚው ማስረዳት፤በምርመራ ወቅት በትክክለኛው የምርመራ ቅደም ተከተል መሰረት በደረጃው የሚሰሩትን
የሽንት፣ የሠገራ፣የደም (malaria RDT)፣ የቆዳ ቅርፊት (skin scraping)፣ የወንድ ብልት ፈሳሽና (Urethral
discharge) አክታ ናሙናዎችን መሰብሰብ፣የሽንት፣ የሠገራ፣የደም (malaria RDT) ምርመራዎችን መስራት፣
ከመጀመሪያ እሰከ መጨረሻ ባሉት የምርመራ ሂደቶች ከመመርመሪያ ዲቫይሶች ጋር አብሮ ባለ የውስጥ ጥራት ቁጥጥር (in built
quality control) በመስራት፤ የክፍሉን እና የመሳሪያዎችን የሙቀት መጠን በየእለቱ በመከታተል፣ መካከለኛ የሆነ
የአዕምሮ ድካምን የሚያስከትል ሲሆን ይህም ከስራ ሰዓቱ 45% ይሆናል፡፡
3.7.2 ስነልቦናዊ ጥረት
 ሥራው በባህሪው በተለያየ ህመም ከሚሰቃዩና ጉዳት ከደረሰባቸው ታካሚዎች የተለያዩ ከሰውነት ናሙናዎች ሲወሰዱ
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ
ቅጽ
በሙያተኛው ላይ መሰደብ፣ጭቅጭቅ፣ ክርክርና አለመግባባቶች የባለሙያዉን ስሜት የሚፈታተኑ ሲሆኑ በላብራቶ
ምርመራው ላይ ያለውን የአፈፃፀም ክፍተት ለመለየት እና ክፍተቶችን ተገንዝቦ ለውጥንና ውጤትን ለማምጣት
የሚያስችል የሥነልቦና ዝግጅነትን፤ ቁርጠኝነትን፤ የሥራ ትጋትን እና ያለውን እውቀትና ክህሎት ተጠቅሞ ከሌሎች
የህክምና ባለሙያዎች ጋር በቡድን የመሥራት ጥረትን የሚጠይቅ ነው፡፡
3.7.2 የዕይታ ጥረት፣
 ሥራው የላቦራቶሪ ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት የበሽተኛዉን ናሙና ከፍተኛ ትኩረት በተሞላበት ሁኔታ በጣም
ጥቃቅን ተሃዋስያንን ለመፈለግ ከፍተኛ የሆነ የዓይን ትኩረትና መመሰጥ የሚፈልግ ሲሆን ከስራ ሰዓቱ 70% ያህል
የእይታ ጥረትን ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የአካል ጥረት
 ሥራው 60% በመቀመጥ፤ 25% በመቆም እና 15% በመንቀሳቀስ የሚከናወን ነው፡፡
3.8. የሥራ አካባቢ ሁኔታ፣
3.8.1. ሥጋትና አደጋ፣
 ሥራው በላብራቶሪ ምርመራ ወቅት በላቦራቶሪ ኬሚካሎች እና በተሰባሪና ስለታማ የላቦራቶሪ ዕቃዎች (Physical,
biological & Chemical hazards) ምክንያት በሚከሰቱ የተለያዩ በሽታዎች እና አካላዊ አደጋዎች የመጋለጥ፣ ከፍተኛ
የአሲድና ቤዝ መጠን ያላቸው ኬሚካሎች በሰዉነቱ ላይ ቢፈስ የመቃጠልና የአካል መጉደልን ያስከትላል፡፡
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ፣
 ሥራው በአብዛኛው ከህመምተኛዉ የሚሰበሰቡ የተለያዩ ናሙናዎች (ሰገራ፣ ሽንትና አክታ)ከተለያዩ ናሙናዎች ዉስጥ
በሚኖሩ የተላላፊ በሽታዎች አምጭ ተህዋስያን ከፍተኛ መጥፎ ጠረንና ተቀጣጣይ የሆኑ በትነት አደገኛ ጭስ
ከሚፈጥሩ በርካታ የላቦራቶሪ ኬሚካሎች ያሉበት የሥራ አካባቢ በመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የጤና መታወክን ያስከትላል፡፡

3.9 እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. የትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
ደረጃ 4 - በህክምና ላቦራቶሪ ቴክኖሎጅ

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር ሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
3 ዓመት በህክምና ላቦራቶሪ ቴክኒሻን ላይ የሰራ

የሥራ ዝርዝሩን ያዘጋጀው ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን


ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ሚኒቴር የሥራ ዝርዝር መግለጫ
ቅጽ

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like