Professional Documents
Culture Documents
Brochure NMIE SETCD
Brochure NMIE SETCD
እንደየአገራት የዕድገት ደረጃና ተጨባጭ ሁኔታዎች ለሳይንስ መሳሪያ የሚሰጠው ትርጓሜ በይዘት ወሰን የተለያዩ
ቢመስሉም ኢንስቲትዩቱን ለማቋቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባወጣው ደንብ ቁጥር 194/2003 ወስጥ “ የሳይንስ
መሳሪያ ማለት ለምርምርና ሥርፀት፣ ለትምህርትና ሥልጠና፣ ለጥራትና ቁጥጥርና ፍተሻ፣ ለሥነ-ልክ፣ ለሰው ወይም
ለእንስሳት ህክምና አገልግሎቶች ሥራ ላይ የሚውል መሳሪያ ነው” ተብሎ ተብራርቶ ይገኛል፡፡
ምርምሮችን በማከሄድና በምልስ ምህንድስና አግባብ የሳይንስ መሳሪያዎችን በአገር ምርት መተካት
የሳይንስ መሳሪያዎችን በብቃት ለመጠቀም የሚያስችሉ አገራዊ የአቅም ግንባታ ተግባር ተኮር የስልጠና
ፕሮግራሞችን ማካሄድ
ጥገናና ተያያዥ የቴክኒክ አገልግሎቶቸን በመስጠትና በማስፋት በተቋማት የሚሰጡ ሳይንሳዊ አገልገሎቶች
እንዳይደናቀፉና ቀጣይነት እንዲኖራቸው ማድረግ
የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተሰማሚነት(ከቴክኖሎጂ፣ ከማህበራዊ፣ ከኢኮኖሚዊ፣ ከሥነ-ምግባራዊና ከአካባቢ
ሁኔታዎች አንጻር) መዳሰስና መረጃዎችን ማሰራጨት
በሳይንስ መሳሪያዎች ዙሪያ የማማከር አገልግሎቶችን በመስጠት ሳይንሳዊ ተግባራትን የሚከናውኑ ተቋማትን
በመደገፍ ክፍተቶችን መሙላት ናቸው።
አደረጃጀት
በሳይንስ መሳሪያዎች ዘርፍ በጥቅሉና በንዑሳን ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለመምራት ሁለት ዋና ዋና የሥራ
ሂደቶች ማለትም የሳይንስ መሳሪያዎች ሥልጠናና ምክር ዳይሬክቶሬት እና የሳይንስ መሳሪያዎች ምህንድስናና ቴክኒክ
ዳይሬክቶሬት በኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ሥር ተዋቅረዋል፡፡ እያንዳንዳቸውም ከላይ በተመለከቱት የሳይንስ መሳሪያ
ንዑሳን ዘርፎች አግባብ የተዋቀሩ ሰምንት ቡድኖች ከነፋሲሊቲዎቻቸው ሲኖራቸው
የሳይንስ መሳሪያዎች ምህንድስናና ቴክኒክ ዳሬክቶሬት በሥሩ በአራቱም ንዑሳን ዘርፎቹ በተዋቀሩት ቡድኖችና
ወርክሾፖች በመታገዝ በዋናነት ከተቋማት ዓቅም በላይ የሆኑና በደንበኛው ጥያቄ መሰረት የሚስተናገድ የተከላ፣
የጥገና፣ የኮሞሺኒንግ፣ የማስወገድና ተያያዥ አገልግሎቶችን ሲያከናውን በእነዚሁ አገልግሎቶች ለመስጠት በግል የንግድ
ተቋምነት የሚቋቋሙ ድርጅቶችን ብቃትንም በመገምገም ያረጋግጣል፡፡
በተጨማሪም ለአራቱም ቡድኖች በጥገናና ተዛማጅ የቴክኒክ
ስራዎች ሂደቶች ውሰጥ በቀላሉ በአገር ውስጥ ገበያ ለማይገኙ
ሜካኒካልና ጠርሙስነክ መለዋወጫዎችንና ተፈላጊ አካለትን
ዲዛይን በማድረግና በመስራት የሚያቀርብ ቡድን ከሜካኒካልና
ግላስብሎዊነግ ወርክሾፖች ጋር ተደራጀቷል፡፡
የሥልጠና አገልግሎት፡
ኢንሰቲትዩቱ በመንግሰትም ሆነ በግል ተቋማት በሳይንስ
መሳሪያዎች ቴክኒካል ተግባራትን በማከናወን ላይ ለሚገኙና
ወደ ስራ ለሚገቡ መሀንዲሶችና ቴክኒሻኖች ዕውቀትና
ክህሎትን የሚያሳደግ በዲዛይን፣ ጥገና አንዲሁም በሳይንስ
መሳሪያዎች ስራ አመራር ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባር ተኮር
ስልጠናዎች ይሰጣል። ስልጠናዎቹ በግሩፕ የሚሰጡ ሲሆኑ
ለዚሁ በተዘጋጁ የስልጠና ላቦራቶሪዎች ወስጥ ነው።
በእያንዳንዱ ስልጠና የሚጠበቀው ትንሹ የሰልጣኝ ቁጥር 10
ሲሆን የሚወስዱት ጊዜም ከአንድ አስከ ሁለት ሳምንት ነው።
በስልጠናው ላይ ከ 80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የስልጠና
ይዘት ለሸፈኑ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ይሰጣል።
የምክር አገልግሎት
በሰይንስ መሳሪያዎች ህይወት ዑደት ማለትም ከመምረጥ፣ ከመግዛት፣ ከመጠቀም እስከ ማስወገድ ድረስ ባሉ ሂደቶች
በርካታ ችግሮች፣ ክፈተቶችና ተግዳሮቶች በየተቋማቱ ይታያሉ። ኢንስቲትዩቱ ተቋማት ተግባራቶቻቸውን በብቃት
አንዲወጡ ለማስቻል በሳይንስ መሳሪያዎች ዙሪያ ከሚሰጣቸው የቴክኒክ አና የስልጠና አገልግሎቶች በተጨማሪም
የሳይንስ መሳሪያዎች ከመምረጥ፣ ከመግዛት፣ ከመጠቀም ወይም ማስወገድ ጋር በተያያዘ የማማከር አገልግሎት
ይሰጣል። አገልግሎቱን ለማግኘት ጥያቄ ማቅረብና የምክር አገልግሎቱ ውጤት እንደቀረበ ክፍያ በመፈፀም
ይጠናቀቃል።
ኢንስቲትዩቱ የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ተደራሽነት ለማስፋትና የመጠቀም (የመትከል፣ የመፈሸ፣ የመጠገን
ወይም/እና የማስወገድ) ዓቅምን ለማሳደግ የሳይንስ መሳሪያዎች ተጠቃሚ ተቋማት የራሳቸውን የተክኒካል
አገልግሎቶች የሚሰጥ ክፍል ለማቋቋም በሚያደርጉት ጥረት ውስጥም በሚደረጉ ሰምምነቶች ቀጥተኛ የሆነ ድጋፍ
ይሰጣል።
ለበለጠ መረጃ እና የተከላ፣ የጥገና፣ የኮሞሺኒንግ፣ የማስወገድና ተያያዥ አገልግሎት እና የብቃት ማረጋገጥ አገልግሎት
ለማግኘት፡-
የሳይንስ መሳሪያዎች ምህንድስናና ቴክኒክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጽ/ቤትን በስልክ ቁጥር +251-116
462783 እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎትን +251-116 457648 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
የሳይንስ መሳሪያዎች ሥልጠናና ምክር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ጽ/ቤትን በስልክ ቁጥር +251 116 463031
በመደወል ማግኘት ይቻላል።