You are on page 1of 11

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

የቴክኖሎጅ ውድድር ቴክኒካል ኮሚቴ

እቅድ

ህዳር 2015 ዓ.ም.

አዲስ አበባ
ማውጫ ገፅ
1. መግቢያ.........................................................................................................................................2

2. የሰነዱ አስፈላጊነት..........................................................................................................................2

3. ዋና እና ዝርዝር ዓላማዎች...............................................................................................................3

3.1. ዋና ዓላማ...................................................................................................................................3

3.2. ዝርዝር ዓላማዎች........................................................................................................................3

4. የውድድሩ መርሆዎች.......................................................................................................................3

5. የሰነዱ ወሰን...................................................................................................................................3

6. ቴክኖሎጂ ለማወዳደር በቅደም ተከተል የሚከናወኑ ተግባራት እና ፈፃሚዎች..........................................3

7. የዳኞች አመራረጥና ተግባር..............................................................................................................4


7.1. ዳኞች ሊገኙ የሚችሉባቸው ተቋማት............................................................................................4
7.2. የዳኞች አመራረጥ.......................................................................................................................4

7.3. የዳኞች ተግባርና ኃላፊነት.............................................................................................................5

8. የውድድሩ ተሳታፊዎች....................................................................................................................5

9. የተወዳዳሪዎች ምዝገባ....................................................................................................................5

10. የውድድሩ የማስፈፀሚያ ስልቶች..................................................................................................5

11. የማወዳደሪያ መስፈርት...............................................................................................................6

12. የቅሬታ አቀራረብ ሂደት................................................................................................................7

13. የሽልማት አሰጣጥ.......................................................................................................................7

14. የተሳትፎ ሰርቲፊኬት...................................................................................................................8

15. ማጠቃለያ..................................................................................................................................8
1. መግቢያ

አለም በቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት በአንድ መንደር በተመሰለችበት በዚህ 21ኛው ክፍለ ዘመን ለአንድ አገር
እድገትና ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እንዲሁም ማህበራዊ ችግሮችን ለመፍታት የአገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ
መሰረት ያደረገ ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን ቀጣይነት ባለው መልኩ በመቅዳትና በማሸጋገር ፈጣን የኢኮኖሚ
ዕድገት ማምጣት የሚቻለው የልማት ፕሮግራሞች መሪ መስሪያ ቤቶችን ውጤታማነት እና ዓለም አቀፍ
ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ሲሆን ለዚህም በኢኮኖሚ የበለፀጉ ሀገራት ሳይንሳዊ ትንታኔ እና ሰፋፊ ጥናትና
ምርምርን በማካሄድ ያፈለቁትን ቴክኖሎጂዎች በተለያየ መንገድ ወደ ሀገራችን አስገብቶ በመቅዳትና
በመጠቀም የውጭ ምርትን መተካት (Import substitution) የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀይሶ ትግበራ ላይ
መሆኑ ይታወቃል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርም በአድስ መልክ ሲደራጅ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት፤
የማሻሻልና የመፍጠር አቅማቸውን በማሳደግ ለኢንተርፕራይዞች እንዳቀርቡ በማቅረብ
የኢንተርፕራይዞችን በገባያ ላይ ያለቸውን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ለሀገራችን ኢኮኖሚያ፤ ማህራዊና
ፖለቲካዊ እድገት አወንታዊ ሚና መጫወት ነው፡፡ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ እድገትና ማህበራዊ መሻሻል
ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ መቅዳት፤ ማሻሻልና ፈጠራ ጥራትንና ተወዳዳሪነትን ማእከል ያደረገ መሆን
ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ አንፃር የቴክኖሎጂ ውድድር ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረክታል፡፡
የበለጸጉ አገራት በመነሻነት የቴክኖሎጂ ውድድርን ቁልፍ መሳሪያ አድርገው ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ
በመቅዳት፤ በማሻሻልና በፈጠራ ሂደት አስደናቂ ቴክኖሎጂዎችን ያፈለቁት ለፈጠራ ስራዎች ትኩረት
በመስጠት ነው፡፡ የቴክኖሎጂ እድገት ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ባሻገር በማንኛውም የስራ
መስክ የተሰማሩ ሁሉ በዚህ ውድድር ተሳታፊ በመሆን የምርትና አገልግሎት ጥራትና ተወዳዳሪነት በከፍተኛ
ሁኔታ እንዲሻሻል አጋዥ ሆኖዋል፡፡ በተጨማሪም በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ላይ የስልጠና ጥራትን፣ የወጣቶች
የስራ ፈጠራ ተነሳሽነትንና አለም አቀፋዊ ተወደዳዳሪነትን ያጎለብታል፡፡
ይሁን እንጂ በአገራችን ለቴክኖሎጂ ውድድር የተሰጠው ትኩረት አናሳ ከመሆኑም ባሻገር በዘርፉ ያሉ
ባለሙያዎችም የቴከኖሎጂ ውድድር እንደ አንድ የቴክኖሎጂ አቅም ማጎልበቻ ተግባር ቆጥረውት እየሰሩበት
እንዳልነበረ ይታወቃል፡፡ይህንንም ዓላማ ለማሳካት ከ2011ዓ.ም ጀምሮ የአሰልጣኝ፣የሰልጣኝ እና
የአንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾችን የማወዳደሪያ ሰነድ በማዘጋጀት ማወዳር በመጀመሩ ቴክኖሎጅስቶችን
ማነቃቃት አበረታች ውጤት ተገኝቶአል፡፡
ስለሆነም ተቀድቶ ለኢንተርፕራይዝ ተሸጋግረው ሀብት ማፍራት ያስቻሉ ቴክኖሎጂዎችን በክልል፣ በክላስተር
እና በተቋማት ደረጃ በማወዳደር አሸናፊ አሰልጣኝ፣ ሰልጣኝ እና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሽ ለማበረታታት
እና በፌደራል ደረጃ የተመረጡ ቴክሎጅዎችን ወደ ምርት ለማሸጋገር እንድሁም ቴክኖሎጆችን በኢግዝቪሽን
ለህዝብ እይታ ለማቅረብ እንድቻል ከአብይ ኮሚቴው እቅድ በመነሳት ይህ የቴክኖሎጅ ቴክኒካል ኮሚቴ
የሚመራበት እቅድ ተዘጋጅቶአል፡፡
2. የሰነዱ አስፈላጊነት
በየደረጃው አሰልጣኞችን፤ ሰልጣኞችና አንቀሳቃሾችን በማወዳደር የተሸሉትን ቴክኖሎጅዎችን ወደ
ኢንድስቱሪዎች በማሸጋገር ከውጭ የሚገቡትን በመተካት የኢንተርፕራይዞችን ተወዳደሪነት ማሳደግና
ቴክኖሎጅስቶችን በማበረታታት የስራ ተነሳሽነታቸውን ለማሳደግ ነው፡፡

3. ዓላማዎች
3.1. ዋና ዓላማ
የሰነዱ ዋና ዓላማ ቴክኖሎጂን በመቅዳት እና በማሸጋገር የኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እና

በማበረታታት ለቀጣይ በአሰልጣኞች፣በሰልጣኞች እና በአንቀሳቃሹ ዘንድ የውድድር ተነሳሽነት መፍጠር እና

ቴክኖሎጂ የመቅዳት፤የማሳሳልና የመፍጠር አቅምን ማሳደግ ነው፡፡

3.2. ዝርዝር ዓላማዎች

አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዞች ቴክኖሎጂን በመቅዳት ለአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና

ማህበራዊ ዕድገት የተሻለ አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ማስቻል፣

የቴክኖሎጂ ሂደቱን ተከትሎ በማሸጋገር ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ ያደረገን ተቋም በየደረጃው

(ከተቋማት እስከ ፌደራል ድረስ) የሚያበረታታ አሰራርን መዘርጋት

ቴክኖሎጂ በመቅዳት፤በማሻሻልና የመፍጠር ሂደት ውስጥ የውድድር መንፈስ መፍጠር

አሰልጣኞች፣ሰልጣኞች እና ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች በቴክኖሎጂው ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ እውቀት

እንዲያገኙና ተነሳሽነታቸው እንዲጨምር ማድረግ፣

4. የውድድሩ መርሆዎች
 ታማኝነት
 ግልጸኝነት
 ፍትሃዊነት
 ሚስጥር ጠባቂነት
 ቅንነት
 ተጠያቂነት

5. የሰነዱ ወሰን
ይህ የማወዳደሪያ ሰነድ ቴክኖሎጂ በመቅዳት፤በማሻሻል በመፍጠር የኢንተርፕራይዞችን ተወዳዳሪነት ያረጋገጡ

የቴክኖሎጂ ባለቤቶችን በተቋም፤ በክላስተር፣በክልል እና በፌዴራል ደረጃ ለውድድር በቀረቡ አሰልጣኞች፤

ሰልጣኞች እና ኢንትርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፤ አወዳዳሪ ዳኞች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡


6. ቴክኖሎጂ ለማወዳደር በቅደም ተከተል የሚከናወኑ ተግባራት እና
ፈፃሚዎች
ተ.ቁ. ተግባራት ፈፃሚ አካላት
1. በተቋም ደረጃ አሰልጣኞች፤ ሰልጣኞችና አንቀሳቃሾቸን በቴክኖሎጅ የተቋም ቴክኒካል ኮሚቴ
እንድወዳደሩ መጋበዝ
2. በተቋም ደረጃ በአሰልጣኝ፤ በሰልጣኝ እና በአንቀሳቃሽ ከ 1-3 የወጡትን የክላስተር ቴክኒካል
በክላስተር ደረጃ ማወዳድር ኮሚቴ
3. በክላስተር ደረጃ በአሰልጣኝ፤ በሰልጣኝ እና በአንቀሳቃሽ ከ 1-3 የወጡትን የክልል ቴክኒካል ኮሚቴ
በክልል ደረጃ ማወዳድር
4. በክልል ደረጃ በአሰልጣኝ፤ በሰልጣኝ እና በአንቀሳቃሽ 1 ኛ ደረጃ የወጡትን የፌደራለ ቴክኒካል ኮሚቴ
በፌደራል ደረጃ ማወዳድር
5. ከየክልሎች የተመረጡ 120 ቴክኖሎጅዋችን በፌደራል ደረጃ ለኢግዝቪሽን የፌደራለ ቴክኒካል ኮሚቴ
ማቅረብ
6. በፌደራል ደረጃ ለኢግዝቪሽንና ለውድድር የቀረቡ ቴክኖሎጅዎችን ዝርዝር የፌደራለ ቴክኒካል ኮሚቴ
መረጃ ማጠናቀር እንድሁም ወደ ምርት የሚሸጋገሩበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር
7. የሚወዳደሩ ቴክኖሎጂዎች ሰነዶችን የማጣራት ስራ በማከናወን ሰነዱን በፌዴራል፣ በክልል፣ እና
ላቀረበው አካል ግብረ-መልስ መስጠት ክላስተር ኮሌጅ/ተቋም
8. ቴክኖሎጂዎች ከዚህ በፊት ለውድድር አለመቅረባቸውን የሚቋቋሙ ቴክኒካል
ማጣራት፣ማለትም የተቀዳ ቴክኖሎጂ የበጀት ዓመቱ ስሪት ብቻ ኮሚቴዎች
መሆኑን ማረጋገጥ
9. ለውድድር በቀረቡት የቴክኖሎጂ ዓይነቶች ላይ ዳኞችን መምረጥ፣ አቅም
መፍጠርና የማወዳደሪያ መስፈርቱን ማስረከብ
10. ለውድድር የሚቀርቡ ቴክኖሎጂዎችን የተሟላ ሰነድ በየሙያው ለተደራጁ
ዳኞች ማስረከብ
11. ለቴክኖሎጂ ውድድር እና ኢግዚቪሽን ምቹ ቦታ መገኘቱንና መሰረታዊ ቴክኒካል ኮሚቴ
ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ፡፡
12. ቴክኖሎጂ በሚወዳደርበት ቦታ በመገኘት ውድድሩን መምራት፣ በየደረጃው የተቋቋሙ
ቴክኒካል ኮሚቴዎች
13. በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት ቴክኖሎጂዎችን ማወዳደር፣ በየቴክኖሎጂ ዓይነቱ
የተደራጁ ዳኞች
14. የተቀዳውን ቴክኖሎጂ ሚስጥራዊነት መጠበቁን መከታተልና ማስጠበቅ፣ በየደረጃው የተቋቋሙ
ቴክኒካል ኮሚቴዎች
15. ቃለ-ጉባኤ በመያዝ በውድድር ወቅት የነበረውን ሂደትና የተወዳዳሪዎችን የዳኞች ጉባኤ
ውጤት የያዘ እና የተፈረመበት ሰነድ ከአስፈላጊ ማስረጃ ጋር ለሚመለከተው
የስራ ክፍል ማቅረብ፣
16. የቀረበለትን ዝርዝር መረጃ ካጣራና ከገመገመ በኋላ ለስራ ክፍሉ የበላይ አካል በየደረጃው የተቋቋሙ
አቅርቦ ማስፀደቅ፣ ቴክኒካል ኮሚቴዎች

7. የዳኞች አመራረጥና ተግባር

7.1. ዳኞች ሊገኙ የሚችሉባቸው ተቋማት


ለውድድር የሚቀርቡ ቴክኖሎጂዎች በተለያዩ ዘርፎች ምርት ማምረት እና አገልግሎት ላይ የሚውሉ በመሆናቸው

የቴክኖሎጂዎቹን ጥራትና አገልግሎት ለመፈተሽና ለማወዳደር የሚቻለው ከየዘርፉ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ


ዕውቀቱና ክህሎቱ ባላቸው ባለሙያዎች ነው፡፡ ስለዚህም ዳኞቹ ሊገኙባቸው የሚችሉ ተቋማት የሚከተሉት

ናቸው፡-

 ዩኒቨርሲቲዎች

 የምርምር ተቋማት

 ኢንዱስትሪዎች መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች

 የንግድ ዘርፍ ማህበራት

 ከዘርፍ መሪ መስሪያ ቤቶች

 ከሙያ ማህበራት

 ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች

7.2. የዳኞች አመራረጥ


የዳኞች ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት የሚታዩ ዋና ዋና መመዘኛ መስፈርቶች፡-

1) በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ/በኢንጅነሪንግ ዘርፍ ወይም ተዛማጅ የትምህርት ዝግጅት ያለው/ያላት፣


2) በከፍተኛ ኢንዱስተሪዎች ውስጥ ተዘማጅ ዘርፍ ላይ ስራ ልምድ የለው/ያላት፣
3) በተሰማራበት ሙያ ስነ ምግባር ያለው/ያላት፣
4) ከኢንዱስተሪዎች እና ከቴ/ሙ/ት/ስ/ተቋማት የሚመረጡ ዳኞች ብቃት ምዘና ውስጥ ያለፉ ቢሆን፣
5) የዳኝነት አመራር ልምድ ያለው/ያላት፣
6) የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂ ላይ የጠራ ግንዛቤ ያለው/ያላት እንዲሁም ስለ እሴት ሰንሰለት ትንተና በቂ
ግንዛቤ ያለው/ያላት ቢሆን ይመረጣል፡፡

7.3. የዳኞች ተግባርና ኃላፊነት


1) ለቴክኖሎጂ ውድድር አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች፣ሰነዶች፣ማወዳደሪያ ቼክሊስትና የሪፖርት ፎርማት
መሟላታቸውን ማረጋገጥ፣
2) ለቴክኖሎጂ ውድድር የተዘጋጀውን መስፈርት በአግባቡ መረዳትና መጠቀም
በውድድሩ ከጅምሩ እስከ መጨረሻው ያለውን ሂደት ለተወዳዳሪዎች ማሳወቅ
3) ለተወዳዳሪዎች ውጤቱን ሪከርድ በማድረግ ግብረ-መልስ በወቅቱ መስጠት
4) ከሚመለከተው የስራ ክፍል ጋር በመሆን የውድድሩን አፈጻጸም መገምገም
5) የሚወዳደረውን ቴክኖሎጂና የውድድሩን ሂደት ሚስጥራዊነት መጠበቅ
6) በውድድሩ ወቅት ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች በወቅቱ ተገቢ ምላሽ መስጠት
7) በውድድሩ ዙሪያ ያሉትን መረጃዎች በተዘጋጀው የሪፖርት ፎርማት በማጠናቀር ለሚመለከተው አካል
እንዲደርሱ ማድረግ
8. የውድድሩ ተሳታፊዎች
አስልጣኞች፣ሰልጣኞች እና የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች የውድድሩ አካላት ይሆናሉ፡፡ ሴቶችና

አካል ጉዳተኞች ይበረታታሉ፡፡

9. የተወዳዳሪዎች ምዝገባ
ማንኛውም ተወዳዳሪ በተቀመጠው የመመዝገቢያ መስፈርት መሰረት የሚከተለውን መረጃ አሟልቶ መስጠት

ይኖርበታል፡-

 የተወዳዳሪ ሙሉ ስም

 የመጡበት ተቋም/ኢንተርፕራይዝ

 የመጡበት ክልል እና ተቋም

 የሚወዳደሩበት ዘርፍ/ሙያ

 የሚወዳደሩበት ቴክኖሎጂ ስም

 ቴክኖሎጂው የተሰራበት ዓ.ም ቢቻል /የ 2014/15 በጀት ዓመቱ ቢሆን ይመረጣል፤

 ከዚህ በፊት ለውድድር ቀርቦ የማያውቅ መሆን አለበት፤

10. የውድድሩ የማስፈፀሚያ ስልቶች


የቴክኖሎጂ ውድደሩ በተደራጀ መልኩ በተቋማት፣ በክላስተሮች፣ በክልሎችና በፌዴራል ደረጃ እንዲፈጸም
የሚከተሉት የማስፈጸሚያ ስልቶች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡-

 የቴክኖሎጂ ውድድር ዕቅድን ከፌዴራል እስከ ተቋማት ለሚገኙ አደረጃጀቶች ማውረድ


 የአፈጻጸም መመሪያ ማዘጋጀትና ለፈጻሚዎች ማስተዋወቅ
 ከባላድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ጋር በቅንጅት መስራት
 የዳኞችንና የኮሚቴ አባላትን አቅም መገንባት
 በጥብቅ ዲስፕሊን የሚመራ የክትትልና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት
 መረጃዎችን በተደራጀ ሁኔታ ለውሣኔ አሰጣጥ አመቻችቶ መያዝ፤
 የእውቅናና ሽልማት ሥርዓት ማስቀመጥ
 አጠቃላይ ሂደቱን መቀመር

11. የማወዳደሪያ መስፈርት


ቴክኖሎጂዎችን ለማወዳደር የሚያገለግሉ የመመዘኛ መስፈርቶች ከስር የተገለፁት ሲሆኑ አጠቃላይ ሂደቱ
በሚከተሉት የነጥብ ገደቦች መሠረት ይሆናል፡-
1= ዝቅተኛ (ከ 65% በታች)
2= መካከለኛ (ከ 66 –75%)
3= ከፍተኛ (ከ 76 – 90%)
4= የላቀ (ከ 91 –100%)

ክብደት የተሰጠ
ተ.ቁ መስፈርት
ከ 100% ነጥብ
1 ከማህበራዊ ጠቀሜታ አንፃር 20
1.1 የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ የሚያሻሽል ስለ መሆኑ 5
1.2 የስራ ዕድል በመፍጠር ላይ ያለው አስተዋፅኦ 5
1.3 የሴቶችን የስራ ጫና የሚቀንስ ስለ መሆኑ 5
1.4 የአካል ጉዳተኞችንና አቅመ-ደካሞችን ችግር ፈቺ ስለ መሆኑ 5

2 ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንፃር 25


2.1 ከውጭ የሚገባ ምርት/አገልግሎትን የሚተካ 4

2.2 ውጭ ገበያ ዉስጥ መግባት የሚችል ምርት/አገልግሎት መሆኑ/export 4


standerd/
2.3 ከውጭ ከሚገባው ተመሳሳይ ምርት በዋጋ ያነሰ መሆኑ 4
2.4 የምግብ ዋስትና ለማረጋግጥና ድህነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያለው 5
መሆኑ
2.5 የምርት/አገልግሎት ጥራትና ምርታማነት መጨመሩ 4
2.6 የደንበኞች/ዜጎችን የመግዛት አቅምን ያገናዘበ መሆኑ 4
3 ከአካባቢ ደህንነት/አረንጓዴ ልማት አንፃር 15
3.1 የአካባቢ ብክለትን የሚቀንስ መሆኑ 3

3.2 የተፈጥሮ ሀብትን በተሻለ ሁኔታ መጠቀም ማስቻሉ 3

3.3 በአጠቃቀም ላይ የስራ ቦታ የጤናና የአካል ጉዳት የማያስከትል መሆኑ 3


(OHS)
3.4 የአካባቢውን የልማት ፀጋ መጠቀም የሚያስችል መሆኑ 4
3.5 ብሔራዊ ጥቅምና የደህንነት መረጃ ስርዓትን አደጋ የማያስከትል መሆኑ 2
4 ከቴክኖሎጂ አንፃር 40

4.1 በእሴት ሰንሰለት ትንተና ችግሮችን ለይቶ የተነሳ መሆኑ 6

4.2 የአዋጭነት ትንተና የተዘጋጀለት መሆኑ 4

4.3 አሰራር ሰነድ (ንድፍ፣ ዝርዝር ንድፍ፣ የጥሬ ዕቃ ዝርዝርና ልኬት) የያዘ 6
መሆኑ
4.4 የቴክኖሎጂ ፍብረካ ዝርዝር መግለጫ (የጥሬ ዕቃ ስም ዝርዝር፣ ልኬትና 5
ክብደት የተሰጠ
ተ.ቁ መስፈርት
ዋጋ) መቅረቡ ከ 100% ነጥብ
4.5 የአመራረት ሂደቱ ተቀምሮ የቀረበ መሆኑ 3
4.6 የአገጣጠም ሰነድ (assembling manual) 3

4.7 የናሙናና የጥራት ፍተሻ ሪፖርት መቅረቡ 5

4.8 ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል መሆኑ 4


4.9 ለአብዢ ኢንተርፕራይዞች ተሸጋግሮ ሀብት ማፍራት ማስቻሉን 4
ማረጋገጫ ሠነድ መቅረቡ
አጠቃላይ ውጤት 100

ያገኘው ደረጃ

12. የቅሬታ አቀራረብ ሂደት


ተወዳዳሪዎች በአሰራርና በውጤት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን ቅሬታን ለመፍጣት
ለተቋቋመው ቅሬታ ኮሚቴ ያቀርባል ፤ ቅሬታ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ውጤቱን ካወቁበት በሁለት
ሰዓታት ውስጥ ቀሬታቸውን ለቅሬታ ሰሚ ኮሚቴዎች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቅሬታው በቀረበ በአራት
ሰዓታት ውስጥለቅሬታ አቅራቢው ውሳኔውማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው የሰጠው ወሳኔ
የመጨረሻ ሌላ ይግባይ አይጠየቅበትም የመጨረሻ ይሆናል፡፡

13. የሽልማት አሰጣጥ


በቴክኖሎጂዎች ውድደር አሸናፊዎች በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ አስፈጻሚ አካላት በሚወስኑት መሰረት

የገንዘብ፣ የሜዳሊያ፣ የትምህርት ዕድል፣ የሰርተፍኬት፣ የውጭ እና ሀገር ውስጥ ጉብኝት እንዲሁም

ሌሎች የማበረታቻ ሽልማቶች የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡

ማስታወሻ፡-

1) ሁለት ተወዳዳሪዎቹ እኩል ውጤት ካስመዘገቡ ደራጃቸው እኩል ሆኖ ቀጣዩ ደረጃ ግን ክፍት ይሆናል፡፡ ነገር ግን
ደረጃ ሦስት ላይ አንድ አይነት ውጤት ያመጡ ሁለቱም ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡

2.) ሴቶችና አካል ጉዳተኛ ተወዳደሪዎች ከሌሎች እኩል ውጤት ካስመዘገቡ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

14. የተሳትፎ ሰርተፍኬት


ውድድሩን ያጠናቀቁ ሁሉም ተሳታፊዎች በውድድሩ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳትፎ ሰርተፍኬት የሚያገኙ

ይሆናል፡፡
15. ማጠቃለያ

ይህ የማስተግበሪያ ሰነድ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ተግባርን በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ባለው ሁኔታ

ለመፈጸም ምቹ የሚያስችል ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በትግበራ ላይ የግልጸኝነትና የአጠቃቀም ችግሮች

ሊያጋጥሙ የሚችሉ በመሆናቸው ውድድሮችን በየደረጃው የሚመሩ ቴክኒካል ኮሚቴዎች የራሳቸውን

እቅድ አዘጋጅተው መፍትሄ እያስቀመጡ ውድድሮቹን ከፍጻሜ ማድረስ የሚጠበቅባቸው ይሆናል፡፡

ከአቅም በላይ የሆነ ችግር ወይንም ለአፈጻጸም ተጨማሪ ማብራሪያዎች ቢያስፈልጉ ግን በፌደራል ደረጃ

የተቋቋመው ቴክኒካል ኮሚቴ ድጋፍ የሚሰጥ ይሆናል፡፡

አባሪ 1 በፌደራል ደረጃ ለሚዘጋጀው ኢግዝቪሽን የሚቀርብ ቴክኖሎጅ

ተ.ቁ ክልል ለውድድር የኢግዝቪሽን ድምር ምግለጫ


የሚቀርብ የሚቀርብ
ቴክኖሎጅ ቴክኖሎጅ

1 ኦሮሚያ 3 25 28

2 አማራ 3 20 23

3 አዲስ አበባ 3 30 33

4 ደቡብ 3 10 13

5 ሲዳማ 3 13 13

6 ደ/ም/ኢ 3 5 8

7 ሱማሌ 3 5 8

8 ድሬዴዋ 3 5 8

9 ሀረሪ 3 5 8

10 ቤንሻንጉል 3 3 6

11 አፋር 3 5 8

12 ጋምቤላ 2 3 5
ድምር 35 129 164

አባሪ 2 የበጀት እቅድ


ተ.ቁ የሚከናወኑ ተግባራት መለኪያ ብዛት የሚያስፈልግ
በጀት

1 ለክልሎች በመስክ ብር 10×2×20×595 238000


ቴክኒካል ድጋፍ ማድረግ

2 ለዳኞች የሙያ ክፍያ ብር 15×600 90000

3 አንደኛ ለወጡ ብር 3×300000 900000


አሸናፊዎች ሽልማት

4 ሁለተኛለወጡ ብር 3× 250000 750000


አሸናፊዎች ሽልማት

5 ሦስተኛ ለውጡ ብር 3×200000 600000


አሸናፊዎች

6 የወርቅ ሜዳሊያ ብር 9× 1000 9000

7 የምስክር ወረቀት ብር 165×200 33000

8 ድርኳን ኪራይ ብር 300000

9 ለቴክኖሎጅ ብዛት 210× 850×12 2142000


ተወዳዳሪዎችና
ኢግዝቪሽን ለሚያሳዩ
ቴክነፐሎጅስቶች አበል

ድምር 5062000

መጠባበቂያ 10 በመቶ 506200

ጠቅላላ ደድምር 5568000

You might also like