You are on page 1of 7

If there are images in this attachment, they will

not be displayed.
በሳይንስና ከፍተኛ ትመህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት
የአካዳሚክ ቴክኒካል ባለሙያዎች ደንብ
ማውጫ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የቴክኒክ
ባለሙያዎች ደንብ
ደንብ ቁጥር ________
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት የሚሰሩ የአካዳሚክ ቴክኒካል ባለሙያዎች ተግባርና
ኃላፊነት ለመወሰን የወጣ ደንብ
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በማስተማሪያ ሆስፒታሎች
የሚሰሩ ቴክኒካል ባለሙያዎች የሚያከናውኗቸውን ዝርዝር
ተግባራት በመለየት፣ተግባርና ኃላፊነታቸውን በመስጠት ጥቅማ
ጥቅማቸውንና የዕድገት መሰላላቸውን መወሰንና መብቶቻቸው
እንዲጠበቅ
በማስፈለጉ፣ የቴክኒካል ረዳቶች የደረጃ ዕድገት የትምህርት
ዕድል፣ጥቅማ ጥቅም፣የስራ ልምድ አያያዝ፣የስራ አፈፃጸም
የምዘና ሂደትና የውጤት አሰጣጥ ላይ ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት
መዘርጋት
በማስፈለጉ፣ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የከፍተኛ
ትምህርት ቴክኒካል
ባለሙያዎችን አሰራር፣ ጥቅማ ጥቅም፣ የትምህርት ዕድል
ለመወሰን ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡
ክፍል አንድ አጠቃላይ
1. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ስር በሚገኙ
የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ
የአካዳሚክ ቴክኒክ ባለሙያዎች ቁጥር_______/2011 ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡
1. አውጭ አካል
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው ስልጣን
መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡ ይህ ደንብ ተጠሪነቱ ለሳይንስና
ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በመሆኑ በሁሉም የመንግስት
ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የማስተማሪያ ሆስፒታል
ባላቸው የአካዳሚክ ቴክኒክ
ባለሙያዎች የስራ እንቅስቃሴ ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡
1. ትርጓሜ
የአካዳሚክ ቴክኒክ ባለሙያዎች፡- ሌላ ትርጓሜ እስካልተሰጠው
ዲረስ የቴክኒክ ባለሙያዎች ማለት በዚህ ደንብ መሰረት
የተሰጠው ትርጓሜ በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
በሚገኙ ወርክሾፖች፣ቤተ ሙከራዎች፣በማስተማሪያ
ሆስፒታሎች፣በልህቀት
ማዕከላትና ተማሪዎች የተግባር ትምህርት በሚማሩባቸው
ኢንደስቲሪዎችና መስኮች የአካዳሚክ ስራ የሚሰሩ ባለሙያዎች
ናቸው፡፡
ቤተሙከራ ማለት ለተፈጥሮ ሳይንስ፤ ማህበራዊ ሳይንስ እና
ቴክኖሎጂ ትምህርት በአንድ ክፍል የተደራጁ ሣይንሳዊ
መሳሪያዎችን እና የአሰራር ስልቶችን በመጠቀም የተግባር
ትምህርትና ሳይንሳዊ የምርምር ሙከራዎች የሚሰጥበት ክፍል
ነው፤
የመስክ ትምህርት ማለት በተፈጥሮና ማህበራዊ ሣይንስ፣
በቴክኖሎጂና ምህንድስና የትምህርት ዘርፍ በመስክ በመገኘት
የተግባር ትምህርትና ጥናት የሚካሄድበት ስርዓት ነው።
በምርምርና በማህበረሰብ አገልግሎቶች በመስክ በመገኘት
የተግባር ትምህርት በሳይንሳዊ ዘዴ ትምህርትና ጥናት
የሚካሄድበት ስርዓት ነው ፤
ወርክሾፕ ማለት፡ በቴክኖሎጂና የምህንድስና ዘርፍ የተለያዩ
መሳሪያዎችንና ማሽኖችን የያዘ ክፍል ሁኖ በቴክኖሎጂና
ምህንድስና ትምህርት ተማሪዎች የተለያዩ ፕሮቶታይፕ
ማምረት እንዲችሉ የሚማሩበት ክፍል ነው። የሳይንስ፤
ለቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በመጠቀም ተግባራዊ ትምህርት
፣ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥበት ክፍል
ነው፤
1. የፆታ አገላለፅ
በዚህ ደንብ ውስጥ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለጸ የሴት
ፆታንም ያጠቃልላል፡፡
1. የተፈፃሚነት ወሰን
ይህ ደንብ በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡
1. ዓላማ
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚኖረውን የወርክሾፖች፣ ቤተ
ሙከራዎች፣ የኢንደስትሪ ትስስሮች፣ የልህቀት ማዕከላት፣
የመስክ የተግባር ትምህርት፣ ምርምሮችና የማህበረሰብ
አገልግሎቶችን ለማሻሻል ውጤታማ ለማድረግና ከስራው ባህሪ
አንፃር የባለሙያዎችን ተጠቃሚነትና መብት ለማረጋገጥ፣
1. መርህ
- የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የካዳሚክ የቴክኒካል የቴክኒካ
ባለሙያዎች ደንብ የሚነጨው ከከፍተኛ ትምህርት አዋጅ መሆን
ይኖርበታል፡፡
- ይህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ ቴክኒካል
ባለሙያዎች ደንብ ከከፍተኛ ትምህርት አዋጅ የሚጋጭ ወይም
የሚቃረን መሆን የለበትም፡፡
- ይህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአካዳሚክ የቴክኒክ
ባለሙያዎች ደንብ ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት እና የማስተማሪያ ሆስፒታል ለመላው ሰራተኞች
ግንዛቤና የጋራ መግባባት መፈጠር አለበት፡፡
ክፍል ሁለት
2.1. መብትና ግደታ
1. . የአካዳሚክ ቴክኒካል ባለሙያዎች መብትና ግደታዎች
2.1.1. የአካዳሚክ ቴክኒካል ባለሙያዎች ግደታዎች
- የተግባር ትምህርት በሚሰጥባቸው የትምህርት ይዘቶችን
በመለየት ግብአቶችንና አደረጃጀቶችን በማመቻቸት ትምህርቱን
ባግቡ እንዲሰጥይሰጣሉያደርጋሉ፡፡
- ተግባር ተኮር ትምህርትና ስልጠና ይሰጣል።
- በጥናትና ምርምር ስራ ላይ ቀጥተኛ ሙያዊ ተሳትፎ
ያደርጋል።
- በቤተሙከራ/ወርክሾፕና በመስክ ስራ የሚሰጥ/የሚካሄድ
የተግባር ትምህርትን/ምርምርን በኃላፊነት ይመራል
ያስተባብራል።
- በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ቋማት በሚገኙ
ወርክሾፖች፣ቤተ ሙከራዎች፣ በማስተማሪያ ሆስፒታሎች፣
በልህቀት ማዕከላትና ተማሪዎች የተግባር ትምህርት
በሚማሩባቸው ኢንደስቲሪዎች፣ ጥናትና ምርምር፣ የማህበረሰብ
አገልግሎት በሚሰጡባቸው መስኮች የሚጠበቅባቸውን ተግባራት
ይፈጽማሉ፡፡
-
ለተግባርትምህርትየሚያገለግሉየተለያዩአይነትማንዋሎችንበጥራ
ትአዘጋጅቶጥቅምላይእንዲውሉያደርጋል፤
- የቴክኖሎጅእድገትናመሻሻልንበመከተልየላቦራቶሪ እና የመስክ
ትምህርትየላቀ፤ቀልጣፋናውጤታማማድረግ
ይጠበቅበታል፤
- የተለያዩ የላብራቶሪ/የመስክ ፤ የወርክሾፕ መሳሪያዎችን
መግጠም፣ የመፍታት ፣ የማደራጀት፣ ብቃቱን የማረጋገጥ
ኃላፊነት አለበት፣
- የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በቤተ-ሙከራ/በመስክ
የሚወስዱትን የተግባር /የመስክ ትምህርቶችን ዓለማቀፋዊ
ደረጃውን በጠበቀ መልክ እንዲማሩ እና እንዲመራመሩ
ያደርጋል።
- እንደ አግባብነቱ
ጥናትናምርምርለሚሰሩሰዎችሆነመረጃለሚፈልጉበሙሉየላቦራ
ቶሪ እና የመስክ ውጤቶችን በመተንተን ይሰጣል፤
-
በጥናትናምርምርዙርያየተገኙውጤቶችናመረጃዎችንስህተትናች
ግርያለባቸውንለይቶማስተካካልናትክክለኛየሆኑትንበማሻሻልናበ
ማጠናከርበጥንቃቄይይዛል፤እንደአስፈላጊነቱውጤቱንምለጥናት
ናምርምርማዕከልሪፖርትያደርጋል፤
- ተግባርና ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት የሚያስችለው
የትምህርት ዝግጅት እና ክህሎት ያለው ባለሙያ ሊሆን ይገባል፤
- ለተግባር ትምህርት የተገዙ ማቴሪያሎችን ተማሪዎች
በጥንቃቄ እንዲጠቀሙ ማድረግ፤ ማስተካካልና ትክክለኛ
ያልሆኑትን በማሻሻልና በማጠናከር በጥንቃቄ የመያዝና
እንደአስፈላጊነቱም በጥናትና ምርምር ዙርያ የተገኙ ውጤቶችና
መረጃዎችን ስህተትና ችግር ያለባቸውን ለይቶ ውጤቱንም
ለጥናትና ምርምር ማዕከል ሪፖርት ማድረግ አለበት፤
2.1.2. የአካዳሚክ ቴክኒካል ባለሙያዎች መብቶች
- ሙያውን ለማሳደግና ለማሻሻል የሚረዱ የረጂምና የአጭር
ጊዜ ስልጠናዎች ተጠቃሚ ይሆናል፤
- ተቋሙ በሚያወጣው መመሪያ መሰረት የተለያዩ ጥቅማ
ጥቅሞች ይጠበቁለታል፣
- ተቋሙ ባወጣው የዝውውር መመሪያ መሰረትና ባለሙያው
በሚያቀርበው ተጨባጭ መረጀዎችን መሰረት በማድረግ በአቻ
የስራ ሙያ ዝውውር ሊሰጠው ይችላል፣
- ለባለሙያው ደህንነት ሲባል እንደ ስራው ባህሪው የአደጋ
ተጋላጭነት አበል ይኖረዋል፣
1. የተሻሩ ህጎች ከዚህ ደንብ ጋር የማይጣጣሙ መመሪያዎች
ወይም አሰራሮች በዚህ ደንብ በተመለኬ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት
አይኖራቸውም፡፡
1. ደንቡ የሚ ጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌደራል ነጋሪ ጋዜት
ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

You might also like