You are on page 1of 9

ለሬዲዮ የሚተላለፍ

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ እ.ኤ.አ በ 2001 አካል ጉዳተኝነትና ጤና በሚል ባዘጋጀው ፅሁፍ

ላይ የጤና ክፍሎችን ተግባርና አካል ጉዳተኝነት ፅንሰ-ሃሳብ የያዘ የአካል ጉዳተኝነት

መስፈርቶችን ያዘጋጀ ቢሆንም፤ የአካል ጉዳት ምን ማለት እንደሆነ የሚያሣይ ዓለም

አቀፋዊና ወጥ የሆነ የጋራ ስምምነት የተደረሰበት ትር Ù ሜ የለም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው

አካል ጉዳተኝነት በየጊዜው እየተሻሻለ የሚሄድ ሰፊ ፅንሰ ሀሣብ በመሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም

ለዚህ ማስፈፀሚያ መመሪያ ዓላማ ሲባል “አካል ጉዳተኛ ማለት የተለያዩ መሰናክሎች

ከሚያስከትላ D ቸው ተጽእኖዎች የተነሳ ከሌሎች አቻዎቹ ጋር በእኩል ደረጃ በማኅበረሰቡ

ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዳያደርግ ሊገድቡ ከሚችሉ የረዥም ጊዜ

አካላዊ፣ አእምሮአዊ፣ ሥነ አእምሮአዊ ወይም የስሜት ህዋሳት እክሎች ያለበት ሰው

ነው፡፡ (የተመድ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ጥበቃ ኮንቬንሽን/UN CRPDs/፣ አንቀጽ 1)፡፡

በዓለማችን ከሚገኘው የሕዝብ ብዛት 15% ወይም አንድ ቢሊዮን የሚሆኑት በአእምሮ፣

በአካልና በስሜት ሕዋሳት ላይ በሚደርስ ጉዳት ሳቢያ አካል ጉዳተኞች እንደሆኑ እ.ኤ.አ.

በ 2011 የዓለም የጤና ድርጅትና የዓለም ባንክ በጋራ ያወጡት ሪፖርት ይጠቁማል፡፡

በተመሳሳይ በማደግ ላይ ባሉ ሀገሮች የአካል ጉዳተኞች ቁጥር ከጠቅላላው ህዝብ ብዛት

ከ 15-20% እንደሚደርስ በተለይም በሀገራችን 17.6% አካል ጉዳተኞች እንደሆኑ ሪፖርቱ

ያስረዳል፡፡

እ.አ.አ. በ 1984፣ በ 1994 እና በ 2007 በተካሄዱት ብሔራዊ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ

ሪፖርት መሰረት የሀገሪቱ አካል ጉዳተኞች ብዛት እንደ ቅደም ተከተላቸው 3.6%፣

1.9% እና 1.2% እንደሆነ ያሳያል፡፡ በዚሁ መሰረት በማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ

እ.ኤ.አ. በ 2007 በተደረገው የህዝብና ቤት ቆጠራ መሠረት የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት

73,750,932 ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 864,218 /1.17% /አካል ጉዳተኞች ናቸው፡፡ ከነዚህ

አካል ጉዳተኞች ውስጥ 464,202 ወንዶች ሲሆኑ 400,016 ሴቶች ናቸው፡፡ እ.ኤ.አ.
በ 2007 ጀምሮ ባለው አጠቃላይ የህዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት እ.አ.አ. በ 2012

በተደረገው ቆጠራ ከ 80 ሚሊዩን በላይ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ ከዚህ ውስጥ ከአንድ

ሚሊዮን በላይ የሚደርሰው የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች እንደሚሆኑ ይገመታል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ 1994 እና በ 2007 በማዕከላዊ ስታትስቲክስ

ኤጀንሲ አማካኝነት በተካሄደው ብሔራዊ የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት

እንደሚያሳየው በወቅቱ ከነበረው ነዋሪ (2,112,737 እና 2,739,551) ህዝብ ብዛት መካከል

እንደቅደም ተከተላቸው 45,936 እና 36,940 አካል ጉዳተኞች ወንድ (አካል ጉዳተኞች

የነበሩ ሲሆን 20,657 (2.39) እና 16,283 (1.88) ሴት አካል ጉዳተኞች እንደነበሩ ለማወቅ

ተችላ D ል፡፡ ቁጥሩ ሊያንስ የቻለው በዋናነት ህብረተሰቡ ስለአካል ጉዳተኞችም ሆነ

ስለቆጠራው ጠቀሜታ በቂ ግንዛቤ የሌለው በመሆኑ አካል ጉዳተኞችን የማያስቆጥሩ

ቤተሰቦች ስለሚኖሩ ነው፡፡

የመዲናችን አካል ጉዳተኞች በተለይም ሴቶችና ህፃናት ከማህበረሰቡ ተገልለው

እንደሚኖሩ የአደባባይ ሚስጥር ነው፡፡ እነዚህም አካል ጉዳተኞች ዜጎች ከማህበረሰብ

ተሳትፎ እየተገለሉ ያሉት በአካል ጉዳተኝነታቸው ምክንያት የሚያበረክቱት አንዳችም

ነገር ስለሌለ ወይም ምንም አይነት ተግባር መፈፀም ስለማይችሉ ሳይሆን በዋነኝነት

በማህበረሰቡ ባለው የተዛባ አመለካከት ችግር ነው፡፡

አካል ጉዳተኞች የትምህርትና የሙያ ስልጠና፣ የህክምና፣ የስራ ስምሪት፣ የተደራሽነት

(ተደራሽነት ከመንገድ፣ ከመጓጓዣ አውታሮች እና ከመረጃ) ተስማሚ የሰው ሰራሽ


አካልና የአካል ድጋፍ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ

ባለመፈጠሩ የተነሳ ከሌላው ጉዳት አልባ የህብረተሰብ ክፍል እኩል በሀገሪቱ የማህበራዊ፣
ፖለቲካዊ፣ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በሚፈለገው መልኩ ባለመሳተፋቸው

የአገሪቱም እድገት ፍሬ ተ s ዳሽ አልሆኑም፡፡

አካል ጉዳተኛ ህፃናትና ሴቶች ከማህበረሰቡ ከሚገለሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ

ሲሆኑ እነርሱም የጤና፣ የህግ፣ የስነ-ልቦናዊ ማህበራዊ አገልግሎቶች የማግኘት

እድላቸው የጠበበ የማህበረሰብ ክፍሎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ በተጨማሪም በእነዚህ

ውስብስብ በሆነው የማህበረሰብ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ምክንያት አካል ጉዳተኛ

ህፃናትና ሴቶች ከእይታ የተደበቁ፣ የትምህርትና ሌሎች መሰረታዊ አገልግሎቶች

የማግኘት እድል የተነፈጋቸው ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

ብዙ አካል ጉዳተኞችም ክብራቸውንና መብቶቻቸውን ጠንቅቀው ስለማያውቁ

የሚደርሰባቸው በደል አውጥተው መናገር እና መብታቸውን ለማስጠበቅ አስፈላጊውን

እንቅስቃሴ ሲያደርጉ አይታዩም፡፡ በደላቸውን በአደባባይ መናገር የቻሉትም ጉዳያቸው

ብዙውን ጊዜ ከቁብ አይቆጠርም ወይም በአግባቡ አይስተናገድላቸውም፡፡ ይህም

በማህበረሰቡ ተገቢውን ቦታና ትኩረት እንዲያጡ እና ለፆታዊ ጥቃቶች ይበልጥ

ተጋላጭ የሆኑ አድር Ù ቸዋል፡፡ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ከሴትነታቸው ባሻገር በአካል

ጉዳተኝነታቸው ድርብ መገለል ይደርስባቸዋል፡፡

የአካል ጉዳተኛ ሴቶች ከጉዳት አልባ ሴቶችና ከአካል ጉዳተኛ ወንዶች ጋር ሲነፃፀር

በአመዛኙ ያልተማሩና የስራ እድል ያላገኙ ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡ በአሉታዊ መልኩ

በመታየታቸውና መፈረጃቸው ምክንያት አንደ አቻ ወንድ Ù ደኞቻቸው ከቤት ውጭ

የመንቀሳቀስ እድል አያገኙም፡፡ ብዙውን ጊዜ ከማህበረሰቡ እይታ የራቁ ከህዝባዊ

አገልግሎቶች ተጠቃሚ ያልሆኑ ናቸው፡፡ በተደጋጋሚ ለወሲባዊ ጥቃት የተጋለጡ

ሆነው እያለ በአንፃሩ የህክምና አገልግሎትና በተለይም የስነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት

ተጠቃሚ አይደሉም፡፡ በአሉታዊ መልኩ መታየታቸውም ክህሎታቸውን፣


እውቀታቸውንና በራስ መተማመናቸውን በማዳከም ያላቸውን አቅም አውጥተው

እንዳይጠቀሙ ያደርጋቸዋል፡፡

አካል ጉዳተኞች በማህበረሰቡ ውስጥ በመንግሥትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች

የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለመጠቀም በርካታ እንቅፋቶች ስለሚያጋጥ à ቸው በአስቸጋሪ

ሁኔታ ኑሮአቸውን ለመምራት ተገደዋል፡፡ እነዚህን መሰናክሎች ለመቅረፍ የሚያስችሉ

የህግና የአሰራር ድጋፎች ያሉ ቢሆንም በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ የተሰሩ የግንዛቤ

ማስጨበጫ ስራዎች እንቅስቃሴ አናሳ በመሆኑ፣ አገልግሎት ሰጪ አካላትም ተገቢውን

ትኩረት ባለመስጠታቸው፣ ራሳቸው አካል ጉዳተኞችም ስለሚሰጡ አገልግሎቶች በቂ

እውቀትና ግንዛቤ ባለማግኘታቸውና ግንዛቤውም ያላቸው ቢሆኑ ተደራጅተው መብትና

ጥቅሞቻቸውን ከማስጠበቅ አንፃር ደካማ በመሆኑ ምክንያት በተዘረጉ አገልግሎቶች

ተጠቃሚ ሲሆኑ አይታዩም፡፡

በተጨማሪም በአገራችን ብሎም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ አካል ጉዳተኞች

በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እንደነበሩ በእለት ተእለት ኑ b ቸው ከሚያጋጥ à ቸው

እጅግ ብዙ መሰናክሎች መመልከት (መረዳት) ይቻላል፡፡ ከእነዚህ መሰናክሎች መካከል

ድህነት፣ የራሱ የአካል ጉዳተኛው ግንዛቤ እጥረትና አመለካከት፣ ህብረተሰቡ አካል

ጉዳተኞችን በተመለከተ ያለው ዝቅተኛ ግንዛቤና አሉታዊ አመለካከት ይገኙበታል፡፡

ድህነት ሰዎችን ለአካል ጉዳት የበለጠ ተጋላጭ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ አካል ጉዳት ደግሞ

ድህነት የበለጠ ጠንካራና ጥልቅ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ይህም በአካል ጉዳትና በድህነት መካከል ጠንካራ ግንኙነት አንዳለ ያመለክታል፡፡

አንዳንድ የቤተሰብ አባል (ግለሰብ) የአካል ጉዳት ከደረሰበት ወይም የደረሰበት መሆኑ

ከታወቀበት ቅፅበት ጀምሮ ለአድልዎና መገለል ይጋለጣል፡፡ ይህ ሂደት እየቀጠለ ከመጣ

አካል ጉዳትና ድህነት ተከታታይ ወደ ሆነ ድርብርብ መገለል የመለወጥ ሀይል አለው፡፡


በዚህ መሰረት በከተማው ውስጥ ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ አካል ጉዳተኞች ቁጥር

ከፍተኛ መሆኑን መገመት ይቻላል፡፡

በእርግጥ ድህነት አካል ጉዳተኞች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍና የተመቻቹ ሁኔታዎችን

ለመፍጠር በራሳቸው ብቻ ያለ-ሦስተኛ ወገን እርዳታ ለማግኘት የሚያደርጉትን ጥረት

በእጅጉ ይገድባል፡፡ በአጭሩ ነባራዊ ሁኔታ አካል ጉዳትን ከምፅዋትና ከህክምና ጉዳይ

እንዲሁም ከቤተሰብ የገንዘብ (የኢኮኖሚ) አቅም ጋር አያይዞ በመመልከት የአካል

ጉዳተኛው ግለሰብ ፍላጎት ከፍ ባለ የቴክኒክ እገዛ ካልሆነ በቀር ሊ à ላ የማይችል

ፍላጎት ተደርጎ ስለሚቆጠር አብዛኛውን ጊዜ አካል ጉዳተኞች የሚያገኙት ድጋፍ

በቤተሰብና በ Ù ደኛ ላይ ብቻ ተመስርቶ በቤት ውስጥ በሚከናወኑ የቀን ተቀን

ተግባራት ተወስኖ ቆይ a ል፡፡

በከተማችን ድህነትን በማጥፋት ጥረት ውስጥ አካል ጉዳተኞችንና ሌሎች የተገለሉ

ወገኖችን መብትና ፍላጎቶች ከግምት ውስጥ ሳያስገባ እውን ሊሆን አይችልም፡፡ አካል

ጉዳተኞችን በፍትሃዊነትና በእኩልነት ያላካተተ ፕሮግራም ውጤታማ አይሆንም፡፡

አካል ጉዳተኝነትን በሚሊኒየም የልማት ግቦች ውስጥ ለማካተት የሚሰራ የተባበሩት

ባለሙያዎች ቡድን እንዳስቀመጠው “ፖሊሲዎች፣ ፕሮግራሞች፣ የአፈፃፀምና ክትትል

ግምገማዎች አካል ጉዳተኞችን ካላካተቱ የምዕተ ዓመቱ ግብ እውን አይሆንም” ሲል

በግልፅ ያስቀምጣል፡፡

ይህ ፖሊሲ አውጪዎችና በልማት ላይ የተሰማሩ አካላት አሁን ያላ D ቸውን

ፖሊሲዎች፣ የስራ አካሄዶች፣ የድርጅቶቻቸውን አወቃቀር መፈተሽና አካል ጉዳተኞችን

ያላካተተ ከሆነ አካታች የልማት አካሄድ እንዲከተሉ የሚያስገነዝብና አድቮኬት

የሚያደርግ ነው፡፡ ለልማቱ እድገት ሂደት ዘላቂ በሆነ መልኩ አካል ጉዳተኞች
በየድርጅቶች፣ በየስራ ዘርፎችና በሁሉም የልማት ስራዎች ላይ በቀጥታ እንዲሳተፉ

ማድረግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

1.1 አካል ጉዳተኞችን የተመለከቱት ሀገራዊ ፖሊሲዎችና ህጎች

አካል ጉዳተኛ ዜጎች ሰብአዊ ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ እንደማንኛውም ጉዳት

አልባ ዜጎች ህብረተሰብ በሚያደርጋቸው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ

እንቅስቃሴዎች ውስጥ በእኩል ደረጃ ተሳታፊ እንዲሆኑና ስለአካል ጉዳተኞች ያለውን

የተዛባ ግንዛቤ እና አመለካከትን ለመቀየር፣ በማናቸውም መልኩ የሚያጋጥማቸው

መሰናክሎች ተወግደዋል፤ የእንቅስቃሴ እና የመረጃ ተደራሽነታቸው የተ à ላ እንዲሆን


መንግስትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላትን

የሚያበረታታ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ የአካል ጉዳተኞችን

ልዮ ፍላጎቶች እውቅና የሚሰጡ የተለያዩ ሀገራዊ ፖሊሲዎች፣ ህጎችንና ፕሮግራሞች

መዘርጋትን ያጠቃልላል፤ እነርሱም፡-

 በ 1987 ዓ.ም የወጣው የሀገሪቱ የበላይ የሆነው የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 41/5

መንግስት የአካልና የአእምሮ ጉዳተኞችን ለማ ss ምና ለመርዳት የሀገሪቱ አቅም

በፈቀደ መጠን ደረጃ እንክብካቤ እንደሚያደርግ መደንገጉ፣

 የሀገሪቱ የበላይ ሕግ የሆነው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ህገ መንግስት አጠቃላይ የሆኑ እኩልነትና

አለማዳላትን የሚያመለክቱ መርሆዎች ከመያዙ በተጨማሪ አካል ጉዳተኞች

የተሃድሶና ድጋፍ አገልግሎት የሚያስፈልጋቸው መሆኑን የሚደነግግ አንቀፅ

ማካተቱ፣

 እ.ኤ.አ 2006 በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀደቀውን የአካል ጉዳተኞች

መብቶች ጥበቃ ኮንቬንሽንን ሀገራችን ተቀብላ በአዋጅ ቁጥር 676/2000 በማጽደቅ

የአገሪቱ ህግ አካል እንዲሆን ማድረ Ù፣

 በ 1989 ዓ.ም በወጣው የማህበራዊ ደህንነት ልማት ፖሊሲ ልዩ ትኩረት ከሰጣቸው

ሰባት በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል አካል

ጉዳተኞች እንዲካተቱ መደረጉ፣

 በ 2007 ዓ.ም በፀደቀው ብሄራዊ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ትኩረት ከተሰጣቸው

የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ ለችግር የተጋለጡ አካል ጉዳተኞች መሆናቸው፣

 የአካል ጉዳተኞች ከስራ ስምሪት ጋር በተያያዘ የሚገጥማቸውን ችግሮች ለመቅረፍ

እንዲቻል የአካል ጉዳተኞች ስራ ስምሪት መብት አዋጅ ቁጥር 568/2000

ለማስፈፀም የወጣ መመሪያ መዘጋጀቱ፣

 የኢትዮጵያ የህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001፣ ደንብና መመሪያው በሀገሪቱ የሚገነቡ

ህንፃዎች የአካል ጉዳተኞችን ከግምት ውስጥ ያስገባ እና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ


እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል መዘጋጀቱ እና ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ

መሆናቸው፣

 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እ.ኤ.አ ከ 2004-2013 ተፈጻሚ

የሚሆን ብሄራዊ የአካል ጉዳተኞች የድርጊት መርሀ ግብር ማዘጋጀቱ፡፡ ይህ መርሀ

ግብርም አስራ ሦስት የትኩረት አቅጣጫዎችን የያዘ ሲሆን የሚመለከታቸው

የመንግሥት አስፋፃሚ አካላት በቅንጅት እና በትብብር በመስራት የአካል

ጉዳተኞችን መሰረታዊ ችግሮች በሂደት ለመፍታት የሚያስችል መሆኑ፣

 በ 2003 የተዘጋጀው ብሄራዊ ተሀድሶ ስትራቴጂ ሰነድ አካል ጉዳተኞችን በህብረተሰቡ

ውስጥ ለማሳተፍ ተደራሽ፣ ውጤታማ፣ ጥራት ያለው፣ አቅምን ያገናዘበና ዘላቂ

አካላዊ ተሀድሶ አገልግሎት የማቅረብ ግብን ለማሳካት የሚረዳ ሁሉን አቀፍ

ብሄራዊ የአካላዊ ተሀድሶ ስትራቴጂ ተቀርፆ ስራ ላይ መዋሉ፡፡

 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ሲቪል ሰርቪስ አዋጅ ቁጥር 515/2004 ምንም እንካ D ን ተፈፃሚነቱ

በመንግስት ሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ላይ ብቻ ቢሆንም በውስጡ አካል ጉዳተኞች

በሰራ ላይ ያላቸውን የተሳትፎ እድል የሚያስፋ የህግ ድንጋጌ መዘጋጀቱ፣

 የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 የአካል ጉዳተኞችን የስራ ዕድል ሁኔታ

የሚያመለክት ልዩ ድንጋጌ ባይኖረው ከላይ ከተገለፁ አዋጆች ጋር ተመሳሳይ በሆኑ

የስራ መስክ ላይ ያለማዳላት መርሆዎች አካ a ል፡፡ በተለይ በአዋጅ አንቀጽ 29

ንዑስ አንቀፅ 3 ስር አሰሪዎች የሰራተኞችን ቅነሳ በሚያደርጉበት ወቅት ለአካል

ጉዳተኛ ሰራተኞች የስራ ዋስትና ጥበቃ መስጠት እንዳለባቸው መደንገጉ፣

 በተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/2002 አዋጅ በአንቀጾቹ ውስጥ ከ 60%

በላይ የሆኑ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚያቀርባ D ቸው

ዕቃዎችና አገልግሎቶች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከመክፈል ነፃ እንዲሆን የሚያደርግ

ድንጋጌ ሲሆን ማንኛውም አሰሪ ድርጅት አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ እንዲያሰራ

ለማድረግ ያበረታታል፣
 የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የታሪፍ ሰነድ አካል ጉዳተኞች ከግብር ነፃ

በሆነ (አነስተኛ) መጠን ያለው ታሪፍ በመክፈል ዕቃዎችን ወደ አገር ውስጥ

እንዲያስገቡ እድል መስጠቱ፣

 ስለ አካል ጉዳተኞች የልዩ ፍላጎት ተጠቃሚነት መብት እ.ኤ.አ በ 2009 የተዘጋጀ

የቴክኒክ፣ የቮኬሽናልና የስልጠና አፈጻጸም መዋቅራዊ አደረጃጀት መኖሩ፣

 አካል ጉዳተኞችን የልዩ መብት ተጠቃሚ ያደረገው የቫት ህግን ለማስፈጸም

የወጣው የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 79/95 መኖሩ፣

 የአምስት አመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በምዕራፍ ስምነት ላይ የአካል

ጉዳተኞች ጉዳይ ልዩ ትኩረት ከሚሹ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ውስጥ እንዲካተት

መደረጉ እና የአካል ጉዳተኞች መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውንና ውስብስብ

ችግሮቻቸውን በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል ሁሉም የሴክተር መስሪያ ቤቶች

በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ማስቀመጡ፣

በአጠቃላይ መንግሥት በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ከላይ ከተገለጹትና ሌሎች የህግና

የአሰራር ማዕቀፎች እንዲዘረጉ ከማድረግ ጀምሮ የተለያዮ ተግባራትን እያከናወነ

ይገኛል፡፡ በፌዴራልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ በተለይም በሠራተኛና

ማኅበራዊ ጉዳይ ሴክተር በየደረጃው ባሉ አስፈፃሚ አካላት የተለያዩ አካል ጉዳተኝነትን

የመከላከልና የተሃድሶ አገልግሎቶች ሲከናወኑ ቆይ a ል፡፡

You might also like