Professional Documents
Culture Documents
Covid - 19
Covid - 19
የፊት ጭንብል እንዲያደርጉ ይመከራል፤ ጭንብሉን በእጅዎ አይነካኩ፤ በማንኛውም ጊዜ ወደአንገቶ አያውርዱ፤
አያውልቁ፤
የጭንብሉ ዓይነት በቤት ውስጥ በሚገኙ የሚታጠቡ ጨርቆች ወይም ፎጣ የተዘጋጁ ሊሆኑ ይችላሉ።
ወደተቋሙ ከመግባቶ በፊት የሙቀት ምርመራ እንዲደረግሎት ይተባበሩ፤
ከኮቪድ 19 ተጋላጭነት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ሲጠየቁ ማለትም የጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ
ካልዎት፣ ሳልንና የመተንፈስ ችግር ካለቦት በማሳወቅ ይተባበሩ፤
በተቋሙ ደጃፍ በተዘጋጁ የንጽህና መጠበቂያዎች (ሳሙናና ውሃ ወይም ሳኒታይዘር) እጅዎን ያጽዱ፤
የእጅ ጓንት ካደረጉ እንዲያወልቁ ይመከራል፤
የግድ ድጋፍ ካላስፈለጐት በቀር አስታማሚ አስከትለው ወደተቋሙ ባለማስገባት ይተባበሩ፤
ጤና ተቋሙ ውስጥ መጨናነቅን ለመቀነስ ተራዎ እስኪደርስ ወደ ውስጥ ባለመግባት ይተባበሩ፤
ጤና ተቋሙ ማቆያ አካባቢ አካላዊ ርቀቶን ይጠብቁ፤
በማቆያው አካባቢ በተቻለ መጠን ባያወሩ ይመከራል
ይህም ከአፍ ፍንጣቂዎችን በመቀነስ የቫይረሱን ስርጭት ይቀንሳል።
ምርመራ በሚደረግሎት ጊዜ አካላዊ ርቀት መጠበቅ ስለሚያዳግት የዓይን ሐኪም ወይም ነርሶች የፊት መከላከያና
ጭንብል ሊያደርጉ ይችላሉ፤ ሆኖም በማንኛውም ጊዜ የራስዎን ጭንብል አያውልቁ፤አይነካኩ፤
በተጨማሪም በመመርመሪያ መሣሪያዎች አካባቢ ወይም የጤና ባለሙያው/ዋ ተጠግቶ/ታ በሚመረምሮት ጊዜ የአፍ
ፍንጣቂ ለመቀነስ ምርመራው እስኪያልቅ ድረስ ባያወሩ ይመከራል፤ ከምርመራው በፊትና ምርመራው ካለቀ በኋላ
የጤና ባለሙያው/ዋ አካላዊ ርቀቱን በጠበቀበት/ችበት ጊዜ ጥያቄ ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡
በምርመራው ጊዜ ሳል ወይም ማስነጠስ ከመጣቦት ከምርመራ መሳሪያው ራቅ በማለት ፊቶን በክርንዎ ይደብቁ፣
ወዲያው እጅዎን ይታጠቡ
የበር እጀታዎችን በእጅዎ ሳይሆን በክርንዎ ይክፈቱ፤ ባጋጣሚ ከነኩ እጅዎን ይታጠቡ
አጣዳፊ ወይም ድንገተኛ ያልሆኑ የምርመራ ቀጠሮዎችና ቀዶ ጥገናዎች በዓይን ሐኪሞች ግምገማ ተለይተው
ቀጠሮአቸው ሊተላለፍ የሚችል መሆኑን ይረዱ
ወደ ዓይን ህክምና ተቋማት መምጣት በማይችሉበት ጊዜ የዓይን ጤናዎን ከቫይረሱ ለመጠበቅና ስርጭቱን
ለመከላከል ምን ማድረግ ይችላሉ?
የፊትዎን በሚገባ በመታጠብ የዓይን ንጽህናን ይጠብቁ፤ ሆኖም በቅድሚያ እጅዎን ለ 20 ሴኮንድ በሳሙናና በውሃ
ይታጠቡ፤
ዓይኖን በእጅዎ አይሹ፤ አይነካኩ፤
ዓይኖን ካሳከክዎት እጅዎን እየታጠቡ በቀዝቃዛ ውሃ ዓይኖ ላይ ቸፍ ቸፍ ያድርጉ፤
የመቆርቆርና የማቃጠል ስሜት ካልሆት የዓይን ማለስለሻ (ሰው ሰራሽ ዕንባ፣ ለምሣሌ፦ tear naturale,
hydrocil filac, rohto ice) ጠብታዎችን ያለ ሐኪም ማዘዣ ወረቀት (without prescription, over the
counter) መግዛትና መጠቀም ይችላሉ፤
ጠብታ ሲያደርጉ እጅዎን በቅድሚያ ይታጠቡ፡፡
ሆኖም ዓይንዎ ከቀላ ወደህክምና ይሂዱ፤ ቅላት ለማጥፋት በሚል ስቴሮይድ, Dexamethasone የመሳሰሉ
ጠብታዎች ተጓዳኝ ችግሮችን ሊፈጥሩ ስለሚችሉ ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ከፋርማሲ ገዝተው አይጠቀሙ::
ምንም እንኳን ተለጣፊ ሌንሶች (contact lens) ለቫይረሱ ተጋላጭነትን ስለመጨመራቸው ማስረጃ ባይኖርም፣
ዓይንን ለመነካካት ስለሚያጋልጡ ለጊዜው አይመከሩም፡፡
የዓይን መነጽሮዎን ሁልጊዜ ያድርጉ፤ አጽድተው ይጠቀሙ፤
በሐኪምዎ የታዘዙ ተከታታይ መድሃኒቶችን (ለምሳሌ፦ የግላኮማ ጠብታዎች፣ የዓይን ቁጣ (Uveitis)
መድሃኒቶች፣ ወይም ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚታዘዙ ጠብታዎችን) ሐኪሞን ሳያማክሩ አያቋርጡ፤
ከሐኪምዎት ጋር በመነጋገር ለረጅም ጊዜ የሚበቃዎትን መድሃኒት ባንድ ጊዜ እንዲታዘዝሎት ያመቻቹ፤
የዓይን ሐኪሞን ማንኛውም ጥያቄ ለመጠየቅ ወደ ጤና ተቋማቱ ይደውሉ፤
የኮቪድ-19 ምልክቶች ወይም ተመሳሳይ ጉንፋን መሳይ ምልክት ከታየቦት ወይም ከኮቪድ - 19 ታካሚ ጋር ንክኪ
ካልዎት በመጀመሪያ ወደ 8335 እና 952 ነጻ የስልክ መስመሮች ይደውሉ:: ከዚያም ወደ ዓይን ሕክምና ተቋም
በመደወል ስላለቦት ህመም ያሳውቁ፡፡ የዓይን ህመሙ ድንገተኛ ካልሆነ በስተቀር ወደ ዓይን ህክምና ተቋም
መምጣት ላይኖርቦት ይችላል። ድንገተኛ ህመም ከሆነ የዓይን ህክምናው ቡድን ተገቢውን የጥንቃቄ ዝግጅት
እንዲያደርግ ያስችላል፡፡