Professional Documents
Culture Documents
Hand Wash Amharic
Hand Wash Amharic
እጅን በሚገባ መታጠብ እንደ ኢንፍሎዌንዛ እና ጉንፋን የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎችን ራስን ለመከላከል
ያስችላል፡፡ እጅዎን መታጠብዎ ጤንነትን ለመጠበቅ ብቻ ሳይሆን ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለሌሎች
እንዳያስተላልፉ ይረዳዎታል፡፡
ምንም እንኳን እጅዎ ንፁህ መስሎ ቢታይዎትም ጀርሞችን ሊሸከም ይችላል፡፡ ምክንያቱም እጅ በአይን
ሊታዩ የማይችሉ ጀርሞች በተለያዩ አጋጣሚዎች ይያዛል፡፡
1. ተቀማጥንና አንጀት ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ይቀንሳል፡፡ እጅን መታጠብ በተቅማጥ የመያዝ እድልንና
የአንጀት መመረዝን ይቀንሳል፡፡ ይህን በተለይ ለህፃናት ጠቃሚ ነው፡፡ የተቅማጥ በሽታ በአለም ላይ
የሚገኙ እድሚያቸው ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ህፃናትን ለሞት የሚዳርግ በሽታ ነው፡፡ በሽታው
በንክኪ ሲከሰት እጅን በሳሙና በመታጠብ መከላከል ይቻላል፡፣ እጅን መታጠብ ከአንጀት ትል ጋር
የተየያዘ ችግር ይከላከላል፡፡
2. የአይን ኢንፌክሽን ይከላከላል
የአይን ኢንፌክሽን በሽታ ለምሳሌ ትራኮማ (የአይን ማዝ) የእጅን ሁልጊዜ በመታጠብ መቀነስ ይቻላል፡፡
እጅዎን መታጠብዎ የመታመም እድልዎን በሚገባ ይቀንሳል፡፡
እጅዎን መቼ መታጠብ አለብዎ
- ምግብ ከማዘጋጀትዎ በፊት፣ በሚያዘጋጁበት ጊዜ እና በኋላ
- ምግብ ከመመገብዎ በፊት
- በሽተኛ የሆነን ሰው ከመርዳትዋዎ በፊትና ከረዱ በኋላ
- ለልጅዎች ዳይፐር ከቀየሩ ወይም ሽንት ቤት የተጠቀመ ልጅዎን ካጠቡ በኋላ
- የተቆረጠን ወይም ቁስልን ከከካሙ (ከነቡ) በኋላ
- ሽንት ቤት ከተጠቀሙ በኋላ፡፡
- አፍንጨዎን ከነኩ፣ ካሳሉና ካስነጠሱ በኋላ፡፡
- እንስሶችን ከነኩ፣ ከመገቡ ወይም የእንስሶችን ቆሻሻ ከነኩ በኋላ
ምንም እንኳን እጅ መታጠብ ቀላል ሥራ ቢመስልም እጅዎን ከጀመርም ለማፅዳት የሚከተሉትን ቅደም
ተብሎች መከተል ይገባዎታል፡፡