You are on page 1of 45

የከይዘን ልማት ቡድን

(ከልቡ)

የኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት


2010 ዓ.ም
1
የስልጠናው ይዘት
1. የጥራት ቁጥጥር ቡድን

2. የከይዘን የልማት ቡድን

2.1 የከይዘን የልማት ቡድን ትርጉም

2.2 የከይዘን የልማት ቡድን ዓይነቶች

3. የከይዘን የልማት ቡድን አደረጃጀት


የጥራት ቁጥጥር
I. የጥራት ቁጥጥር ማለት ምንድን ነው?

 የጥራት ቁጥጥር ማለት ምርት እና አገልግሎትን ለማሳደግ፣ ደንበኛውን


ለማርካት በጥራት አስፈላጊነት ዙርያ አጠቃላይ የአመራር ትኩረት
መስጠት ነው፡፡
1.1 የጥራት ቁጥጥር ቡድኖች ፅንሰ ሀሳብ
 የጥራት ቁጥጥር ቡድን ፍልስፍና የሚመነጨው ሰዎች ካላቸው
ሰብዓዊ መብት እና ተሳታፊነት ላይ የተመሰረተ ሲሆን

 ይህም “ሰዎች የአንድ ተቋም ከፍተኛው ሀብት መሆናቸው ” እና


በተቋም ውስጥ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ እድል ሊሰጣቸው ይገባል
1.2 የጥራት ቁጥጥር ቡድን አመሠራረት
 የጥራት ቁጥጥር ቡድን ለመጀመሪያ ግዜ የተቋቋመው
በ1962 በጃፓን የሳይንቲስቶች እና መሀንዲሶች ማህበር
(JUSE) ሲሆን በ ዶ/ር ኩሩ ኢሽካዋ መሪነትና አነሳሽነት
ነው፡፡
ልማዳዊ የአመራር ፍልስፍና
እና
ከይዘናዊ የአመራር ፍልስፍና
ልማዳዊ የአመራር ፍልስፍና
ሰራተኞች እንደ ሮቦት
የሚታዩበት

7
ከይዘናዊ የአመራር ፍልስፍና

• ሁሉም ሰራተኞች እንደ ሰው የሚታዩበት እና ያላቸውንም


እውቀት እና አቅም አውጥተው እንዲጠቀሙ የሚያስችል
የአመራር ፍልስፍና ነው፡፡

8
2. የከይዘን የልማት ቡድን
2.1 የከይዘን የልማት ቡድኖች ትርጉም
 በአንድ የስራ ቦታ ላይ ያሉ ሰራተኞች ብዛታቸው ከ3-10 የሆኑ
ከስራው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው ቡድን የሚፈጥሩበት ነው፡፡

10
የከይዘን የልማት ቡድኖች ዓላማ

በስራ ቦታ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን መፍታት

የስራ አካባቢን ወጥ /የተደራጀ ማድረግ

የራሳቸውን አቅም መገነባባት

11
የከይዘን ልማት ቡድን ዝርዝር መርኅዎች
 ቀጣይና የማያቋርጥ የተሻለ ለውጥ ማምጣት፣
 ከሁሉ በላይ የሰው ሀብት ወሳኝ መሆኑን መገንዘብ፣
 የዕውቀት ሽግግርን ማመቻቸት፣
 ከመዝረክረክ የጸዳ አሠራር መፍጠር፣
 በላቀ እውቀት ላይ የተመሰረተ አሠራርና የአሠራር ማሻሻያ በመኖሩ፣
 የቡድን አሠራርን ማስፈን፣
 የባለቤትነት ስሜት ማዳበር።

12
(የቀጠለ…)
የከይዘን ልማት ቡድን አስፈላጊነት

1. የከይዘን የልማት ቡድን ፍልስፍና የሚመነጨው ሰዎች በተፈጥሮአቸው


ካላቸው ፍላጐት ነው፡፡ ይህም ማለት ሰዎች

 ነጻና ከማነቆ ለመላቀቅ


 የተሻለና የተለየ ነገር ለመሥራት እና
 ለማደግ የመፈለግ ተፈጥሮአዊ ስሜት አላቸው፡፡

2. ሰዎች በተለመደው አሠራር ውስጥ ተሟሙቀው እንዳይኖሩ፣


እውቀታቸውን እንዲያሻሽሉ እንዲሁም ሥራዎቻቸውን በራስ መተማመን
ስሜት እንዲያከናውኑ ያስችላቸዋል።

14
2.2 የከይዘን ልማት ቡድን አይነቶች
1. ንዑስ ቡድኖች
 በአንድ የስራ ቦታ ላይ ያሉ ሰራተኞች ብዛታቸው 10 በላይ ሲሆን ንዑስ ቡድን
ይፈጥራሉ/ይመሰረታሉ፡፡
2. ጥምር ቡድኖች፡-
 ከአንድ የሥራ ክፍል የዘለለና የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን የሚያገናኝ ችግር እና ስራ

ሲፈጠር ጥምር የከይዘን ልማት ቡድን ይፈጠራሉ፡፡

 ጥምር ቡድኖችም በጋራ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ያደርጋሉ


3. አንድን ችግር ለመፍታት የሚደራጅ ቡድን

 አንድ ተቋማዊ ችግር በአንድ ልማት ቡድን መፈታት ሳይቻል ሲቀር

በሌሎች የስራ ክፍሎች በተወጣጡ አባላት ይመሰረታል፡፡

 ቡድኑም ኃላፊነቱን ከተወጣ በኋላ የሚበተን ይሆናል፡፡


3. የከይዘን ልማት ቡድኖች አደራጃጀት
ፕሬዝዳንት

ዓብይ የከይዘን ልማት


ቡድን
የከይዘን ቢሮ

የየክፍሉ አስተባባሪ የየክፍሉ አስተባባሪ የየክፍሉ አስተባባሪ


ቡድን ቡድን ቡድን

የልማት ቡድን የልማት ቡድን የልማት ቡድን

ቡድን መሪ ቡድን መሪ ቡድን መሪ

አባላት አባላት አባላት


የዓብይ የልማት ቡድን ሚና
ዓብይ የልማት ቡድን በተቋሙ ኃላፊ የሚመራና ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ
መካከለኛ አመራር አባላትን ያቀፈ ሆኖ የሚከተሉት ዋና ዋና ተግባራት
ይኖሩታል

 የተቋሙን የከይዘን ልማት ቡድኖች አመራር መስጠት፣

 ግልጽ የሆነ የከይዘን ልማት ቡድኖች ፖሊስና ግብ ማዘጋጀት፣

 ለተሻለ አፈጻጸም የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት


የየክፍሉ አስተባባሪ ቡድን ሚና
የከይዘን ልማት ቡድን አስተባባሪ ከሥራ አመራር አባላት መካከል የሚመደብ ሲሆን
ሥራውም፡-

 ከሥራ አመራር አባላት ጋር በመመካከር ለከይዘን ልማት ቡድኖች ድጋፍ መስጠት፣

 ለቡድኖቹ የሥልጠና መርሀ-ግብር ማዘጋጀትና መተግበር፣

 ችግሮች ሲከሰቱ ማቃለል፣

 የከይዘን ትግበራ ውጤትን መገምገምና ሪፖርት ማቅረብ፣

 ቀና የሆነ የውድድር መንፈስ ይፈጥራል

 ምርጥ ተሞክሮች መቀመር እና ለሌሎች የስራ ክፍሎች ማሳያ መፍጠር

 ለከይዘን ቡድኖች ግብሃቶችን እና በጀቶችን ማዘጋጀት


የቡድን መሪ ሚና
የከይዘን ልማት ቡድን መሪ ከከይዘን ልማት ቡድን የሚመረጥ ሲሆን ሥራውም፡-

 ሁሉም አባላት ተገቢውን ሚና እንዲጫወቱ አመራር መስጠት

 በአባላት መካከል የቡድን አሠራር ባህል እንዲሰፍን ማስቻልና እንደ አንድ የቡድን አባል
ሀላፊነትን መወጣት

 መልካም የስራ አካባቢን በመፍጠር እያንዳንዱ የቡድን አባላት ሀሳባቸውን የሚገልጹበት


ሁኔታን ማመቻቸት፣ ማገዝና መርዳት፣

 ቀልጣፋና ውጤታማ የስብሰባ ሥነ ሥርዓት መፍጠር

 መልካም የስብሰባ ሥነ ምግባርን ማስፈንና ተተኪ አመራር ማፍራት

 የቡድን አባላትን ስለ ጥራት ቁጥጥር የማስፈጸሚያ ቴክኒኮች ማሰልጠንና አቅጣጫ ማሳየት


የጥሩ እና ስኬታማ መሪ ባሕርይ ምንድነው?
 ዘርፈ ብዙ አስተሳሰብ እና ክኅሎትን የሚያዳብር

 በመልካም ስነ-ምግባር እና ግብረገብ የተቃኘ

 ተከታዮቹን የሚያከብር እና የሚያበረታታ

 በእጅጉ ባለራዕይ የሆነ (አርቆ አሳቢ) ከዚህ በተጨማሪ


 ማዳመጥ…..አባላቱን
በሚገባ ማድመጥ
 መግለጽ ・・・ለአባሉ በሚገባ መግለጽ
 መርዳት・・・・.የአባላትን እንቅስቃሴ ማገዝ
 መወያየት ・・・ሁሌ ከአባላት ጋር መወያየት
 መገምገም ・・・ፍትሀዊ በሆነ መንገድ ውጤትን መገምገም
 ምላሽ መስጠት ・・・ለውጤቱ ተገቢውን ምላሽ መስጠት
23
የአባላት ሚና
 በቀና አመለካከት ራስን መገንባት

 በቡድን ስብሰባ በጊዜው በመገኘት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ፣

 ችግሮችን መለየትና የመፍትሄ ሃሣብም ማመንጨት፣

 ከቡድን መሪ ጋርና ከሌሎች አባላት ጋር መተባበርና የሚሰጠውን ተግባርና


ሀላፊነት መወጣት፣

 ቀላል የማስፈጸሚያ ቴክኒኮችን ማወቅ፣

 ቀጣይነት ያለው የማሻሻያ ሥራዎችን መተግበር፣

 የስራ ቦታ ህግና ስነ ምግባርን መከተል


የከይዘን የልማት ቡድኖች ስብሰባዎች
የስብሰባ ጊዜ
 ስብሰባዎች መከናወን ያለባቸው መደበኛ ሥራን በማይጎዳ ሁኔታ
መሆን አለበት።
 ይህም፦ከ20-30 ደቂቃ በሳምንት አንድ ጊዜ የስብሰባ ጊዜ ሆኖ ቢበዛ
ከአንድ ሰዓት መሆን አለበት።
የስብሰባ ሰዓቶቹም ቢቻል
በምሳ ሰዓት አብሮ እየበሉ
በሻይ ሰዓት አብሮ እየጠጡ
በሥራ ሰዓት ሥራ ሳይቆም፣ወዘተ የስራ ሁኔታን ስለማሻሻል
የመወያየት ባህል ሊዳብር ይገባዋል፤
26
የስብሰባ ቦታ
 ስብሰባው የሚከናወነው በስራ ቦታ አመቺ የሆነ ቦታ በማዘጋጀት ነው

 ከተለመደው የስብሰባ ሥርዓትና በተለየ መልኩ ችግሩ/ማነቆው


በተከሰተበት ቦታ በመሆን ስለጉዳዩ ብቻ ትኩረት በመስጠት ለመወያየት
ያስችላል

27
የስብሰባ አጀንዳ
 ከስብሰባ ቀን በፊት የስብሰባው አጀንዳና ከአባላት ምን እንደሚጠበቅ
አመቺ በሆነ መንገድ እንዲያውቁት ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

 ይህም አባላት ጉዳዩን አውቀውት በቅድሚያ ተዘጋጅተው እንዲመጡ


ያደርጋቸዋል፡፡

 ለእያንዳንዱ አጀንዳም ጊዜ ገደብ ሊሰጠው ይገባል

28
የከይዘን የልማት ቡድኖች በፍጹም የማይወያዩባቸው ጉዳዮች

 ስለ ሕብረት ሥራ ስምምነት
 ስለ ስነምግባር ችግር
 ስለ ግል ጉዳይ
 ስለ ደምወዝ እና ማበረታቻ ክፍያ (ቦነስ)
 ስለ በጀት
 ስለ ቅጥር ፣ ዝውውርና እድገት

29
የስብሰባ ሂደት
 የከይዘን ልማት ቡድን ስብሰባ በተቻለ አቅም ስብሰባው አሳታፊ
እንዲሆን ይፈለጋል፡፡

 በቀረቡት አጀንዳዎች/የመነጋገሪያ ሃሣቦች ላይ አባላት አስተያየታቸውን


እንዲሰጡ ይደረጋል፡፡

አባላት ሪፖርታቸውን እንዲያቀርቡ በመጋበዝ ውይይት እንዲደረግበት


ይደረጋል፡፡

30
ስብሰባዎች የቀጠለ…

 በተቻለ አቅም ውሣኔዎች በመግባባት ላይ የተመሠረቱ እንዲሆን ማድረግ


የተሻለ ሲሆን ካልሆነም በድምጽ ብልጫ እንዲያልፉ ይደረጋል፡፡

 ለቀጣዩ ስብሰባ ሥራን በመከፋፈልና የስብሰባ ጊዜን በመወሰን ስብሰባው


ይጠቃለላል፡፡

 በየስብሰባ መጨረሻ ላይ የስብሰባ ሂደቱን መገምገም አስፈላጊ ነው፡፡

31
የስብሰባ ቃለ-ጉባዔ
በእያንዳንዱ ስብሰባ ወቅት፦

 የቀረበውን መወያያ ሃሣብ፣

 የተላለፈውን ውሣኔ፣

 የተሰጠው የሥራ ድርሻ፣

 ፈጻሚ አካልና የጊዜ ገደብ የያዘ ቃለጉባኤ በቡድኑ ጸሓፊ ይያዛል፡፡


 በቀጣይ ስብሰባ ላይ አፈጻጸማቸው በቃለ ጉባዔው መሰረት ሊገመገም
ይገባል፡፡
32
በከይዘን የልማት ቡድን ውስጥ ቅሬታዎች እና አቀራረባቸው
የከይዘን ሥራ የራስ ተነሳሽነትንና ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ ብሎም እያንዳንዱ
አባል ሠርቶ ውጤቱን የሚያየውና የሚደሰትበት ነው፤ ሆኖም፦
 አንድ አባል ወይም የቡድን መሪ በማንኛውም ሁኔታ በቡድኑ አሠራር ቅር
ሲሰኝ በውይይት ሊፈታ ይገባል፡፡
 ቅሬታም በመረጃና ማስረጃ ተደግፎ ሊቀርብ ይገባል፡፡
 በቡድኑ ውሣኔ ያልረካ መሪ ወይም አባል ለዓቢይ የልማት
ቡድን/አስተባባሪ ቡድን ሊያቀርብ ይችላል፡፡

33
የከይዘን ልማት ቡድን የማስጀመሪያ ሂደት

2. በየክፍሉን የከይዘን
1. ዓብይ የከይዘን ልማት ቡድን
ልማት ኮሚቴ እና ማደራጀት
የየክፍሉ አስተባባሪ
ኮሚቴ መመስረት
በተመሳሳይ ወቅት
ሱፐርቫይዘሮችን
ማሰልጠን

5.የቡድኖቹን የስራ አፈጻጸም


ስብሰባ በማደራጀት 3. የከልቡ
ክንውናቸውን 4. ቡድኖቹን
እንዲያቀርቡ በማድረግ ወደ ስራ ቡድን
የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ
ማስገባት መሪዎችን
ቡድኖች እውቅና
መስጠት ማሰልጠን
የከልቡ የችግር አፈታት ሂደት

1. ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባውን ችግር መለየትና መምረጥ

2. መረጃ በመሰብሰብ አሁን ያለበትን ሁኔታ መረዳት/ማጥናት፣

3. ትንተና ማከናወን፣

4. ግብ ማስቀመጥ(set target)

5. የዝርዝር መርሀ-ግብር ማዘጋጀት፣

6. አማራጭ የመፍትሄ ሃሣቦችን ማመንጨትና መተግበር፣

7. ውጤቱን ከተቀመጠው ግብ አንጻር መገምገም፣

8. ለተሻለው አሠራር ደረጃ ማውጣት፣


ቀጣይ የማሻሻያ ስራዎች /PDCA/
የከይዘን ልማት ቡድኖች በማያሰልስ ሁኔታ በቀጣይነት ጥራትና
ምርታማነትን ለማሻሻል
 ምርታማነትን ለመጨመር፣
 አቅርቦትን ለማፋጠን ፣
 የሥራ ላይ ደህንነትን ለመጠበቅ፣
 ተሳትፎን ለማጐልበትና ጥራት የተላበሰ የሥራ አካባቢ ለመፍጠር
ዋናው መሣሪያ የማቀድ፣ የመተግበር፣ የማረጋገጥ የማስቀጠል ኡደት
/PDCA cycle/ ነው፡፡
የቀጠለ…
ማረም

ውጤቱ አጥጋቢ ካልሆነ

ማቀድ መተግበር ማረጋገጥ

ውጤቱ አጥጋቢ ከሆነ

ማስቀጠል
(IMPLEMENT)
የከይዘን የልማት ቡድን አባላት በግል የሚሰጣቸውን ስራዎች እንዴት
ይሥሩ?
ይህ የከይዘን ልማት ቡድን አባላት በግል የሚሰሩትን ሰዎች
የሚከፋፈሉበት /ድርሻ የሚወስዱበት ነው
ለአባላት የሚሰጡ የግል ሥራዎች ማከፋፈያ ቅጽን በመጠቀም
ሥራዎችን ይከፋፈላሉ
 ይህ የሥራ ክፍፍል፣ ሥራዎች ሳይሠሩ ባለቤት አጥተው
ተንጠልጥለው እንዳይቀሩ እንዲሁም በሚፈለገው መጠን፣ ጊዜ እና
ጥራት እንዲተገበሩ ለማድረግ ነው።

40
መሪዎች የሚጠቀሙባቸው ቅጾች

 የቃለ ጉባዔ ቅጾች.docx

 የሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ.docx

 ለአባላት የሚሰጡ የግል ሥራዎች ማከፋፈያ ቅፅ

41
ለአባላት የሚሰጡ የግል ሥራዎች ማከፋፈያ ቅፅ
ተ.ቁ የስራው ዓይነት ስራው የሚያልቀበት ቀን ስራውን እንዲሰራ የተመደበ ሰው የሚጠበቀው ውጤት
ማስቀጠል
 ይህ ፈታኙ የከይዘን ፍልስፍና
ምዕራፍ ነው።

 ይህ ትግበራውን የጀመሩ ተቋማት

የወደፊት መለኪያ ነው።

 ሙያዊ የሆነ የትግበራ ሂደትን እንደ


ቅድመ-ሁኔታ የሚጠይቅ ነው።

43
በህብረት መስራት ሁሌም አሸናፊ
ያደርጋል
ሁላችንም የስራ ባህላችንን አሻሽለን ለለውጥ እጅለእጅ ተያይዘን
እንነሳ
እናመሰግናለን

You might also like