You are on page 1of 80

የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የተማሪዎች መፅሐፍ

2ኛ ክፍል

አዘጋጆች፡
ሐብታሙ ስዩም (M.Sc.)
መብራቱ ቸሩ (M.Sc.)
ፈይሣ ተረፉ (M.Ed.)
አርታኢዎች
ለታ ታደሠ (M.Ed.)
ይታገሱ ደመቀ (MSc.)
ገምጋሚዎች
ብርሃኑ ደበላ (M.Ed)
ኢሳያስ ተፈራ (MSc.)
ሙላቱ ጉድሳ (M.Ed)፧
ወደ አማርኛ የተረጎሙ
መብራቱ ቸሩ
እንዳለ አየለ
ለታ ታደሰ
ጌተቸው ዘውዴ ውቤ (M. Ed )
ግራፊክስ
ሰለሞን አለማየሁ ጉተማ (MA)

I I የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

©ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ 2014/2022

ይህ መጽሐፍ በኦሮሚያ ትምህርት ቢሮና በነቀምቴ መምህራን


ትምህር ኮሌጅ የጋራ ስምምነት በ2014/2022 ዓ.ም ተዘጋጅቶ
ታተመ፡፡ የዚህ መጽሐፍ የባለቤትነት መብት በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ከኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ፈቃድ ውጪ በሙሉም ሆነ በከፊል


ማሳተምም ሆነ አባዝቶ ማከፋፈል በሕግ ያስጠይቃል፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ II


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ማውጫ
ምዕራፍ አንድ..........................................................................................1

መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታ.................................................................1

1.1 ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠራ መሰረታዊ የእንቅስቃሴ

ችሎታዎች........................................................................................2

1.2 አንድ ቦታ በመቆም የሚሠሩ የእንቅስቃሴዎች......................................8

1.3. መሳሪያን በመጠቀም የሚሠሩ የእንቅስቃሴ ችሎታዎች.....................13

ምዕራፍ ሁለት.......................................................................................21

የቅደም ተከተል እንቅስቃሴ......................................................................21

2.1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ቅደም ተከተል.............................................22

2.2 ከምት ጋር እየተቀያየረ የሚሄድ የእንቅስቃሴ ብቃት..........................26

ምህራፍ ሶስት........................................................................................29

ማህበራዊነትንና ውስጣዊ ስሜትን መማር................................................29

3.1 ራስን ማወቅና የመቆጣጠር ችሎታን የሚያሳድጉ ጨዋታዎች እና እንቅስ

ቃሴዎች.........................................................................................30

3.2 በጨዋታና እንቅስቃሴ ውስጥ የማህበረሰባዊ ግንዛቤን የሚያሳድጉ.........33


3.3. በጨዋታና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ግንኙነት ማሳደግ.........................35

ምዕራፍ አራት.......................................................................................39
የአካል ብቃት.........................................................................................39

4.1 የልብና የሳምባን እንቅስቃሴዎች.......................................................40

4.2 የጡንቻ ብርታት..............................................................................43

4.3 መተጣጠፍ......................................................................................47

4.4 ቅልጥፍና.........................................................................................50

ምዕራፍ አምስት....................................................................................54

III III የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ጂምናስቲክስ...........................................................................................54

5.1 ቀላል ጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች.....................................................55

5.2 ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ እና አሰፈላጊነት.......................................60

5.3 መሠረታዊ ጂምናስቲክስ...................................................................67

ምዕራፍ ስድስት.....................................................................................71

ተማሪዎቹ በሚኖሩበት አካባቢ ያሉ ባህላዊ ጭፈራዎች እና ባህላዊ

ጨዋታዎች............................................................................................71

6.1 በተማሪዎች መኖርያ አከባቢ ያሉ ታዋቂ የባህል ውዝዋዜ......................72

6.2 ተማሪዎች በሚኖሩበት አካባቢ ያሉ ባህላዊ ጨዋታዎች......................73

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ IV


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ አንድ
መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታ
ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች

ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-


• መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታዎች ቅደምተከተልን
በመጠበቅ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች መዞርን
ታዳብራላችሁ።
• አንድ ቦታ በመቆም ከእንቅስቃሴ ጋር
የሚሠራ መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታዎችን
ታዳብራላችሁ።
• የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴ ችሎታዎችን ከመሳሪያ
ጋር ትሠራላችሁ።

መግቢያ
መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታ መኖር ለህጻናት እጅግ
አስፈላጊ ነው። ምክንያቱም ህጻናት እንቅስቃሴ ውስጥ
በንቃት በመሳተፍ ብዙ ጠቃሜታ ያገኛሉ። ለምሳሌ የሰውነት
ሚዛን መጠበቅ፣ የሰውነት ጤናና ጥንካሬ ለመገንባት፣
ተግባቦትና ጥሩ አመለካከት ለመገንባት እና እንዲሁም
ለልብና ሳምባ ጥንካሬ፣ ፍጥነትና ቶሎ አቅጣጫ የመቀያየር
ችሎታ ለማሳደግ ይረዳችኋል።.

1 1 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

በአጠቃላይ በዚህ ምእራፍ ውስጥ የተካተቱ ይዘቶች ከቦታ


ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠሩ የእንቅስቃሴ ችሎታ፣
አንድ ቦታ በመቆም የሚሠራ የእንቅስቃሴ ችሎታ እና
በመሳሪያ የሚሠራ የእንቅስቃሴ ችሎታን በቅደም ተከተል
ትማራላችሁ።

1.1 ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠራ


መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታዎች

ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት፡


ተማሪዎች ከዚህ የትምህርት ክፍለ ጊዜ በኋላ፡
• ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠራ የእንቅስቃሴ
ችሎታን ትዘረዝራላችሁ፡፡

• ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠራ የእንቅስቃሴ


ችሎታ ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡

• ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠራ የእንቅስቃሴ


ችሎታን ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር1.1

1. ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሠሩ የእንቅስቃሴ


ችሎታዎች ምን ምን ናቸው?

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 2


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሀ. ወደ ኃላ መራመድ

ወደ ኋላ መራመድ ማለት ከመሰረታዊ የእንቅስቃሴ ችሎታ


ውስጥ አንዱ ሆኖ ወደፊት ከመራመድ ጋር ተቀራኒ
እንቅስቃሴ የሚፈልግ ሲሆን ቀደም ብለን በእግር ጣት
መሬት መንካትና ቀጥሎም በተረከዝ መሬት በመንካት
የሚሠራ የእንቅስቃሴ ችሎታ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• መስመር ይዞ መቆም፡፡
• መጫወቻ ሜዳን አደጋ ከሚያደርሱ ነጻ ማድረግ፡፡
• የመምህሩን / መምህርቷን ትእዛዝ በመጠበቅ
ሁለት ሁለት እርምጃ ወደኋላ መራመድ፡፡
• ደጋግሞ መለማመድ፡፡

ምስል 1.1. ወደ ኋላ መራመድ

3 3 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ለ. ወደ ጎን መሸራተት
ይህንን እንቅስቃሴ ለመሥራት መጀመሪያ ትክክለኛ አቋቋም ከያዝን
በኋላ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ በመንሸራተት ወይም በመሄድ
የሚሠራ የእንቅስቃሴ ችሎታ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• እጃችን ወደ ቀኝና ወደ ግራ በመዘርጋት በትክክል
መቆም፡፡
• በእግር ወደ ግራና ወደ ቀኝ በመንሸራተት ወይም
በመሄድ ልምምድ መሥራት፡፡
• ፍጥነት በመጨመር በሁለቱም ጎን በተደጋጋሚ
መሥራት፡፡

ምስል 1.2. ወደ ጎን የመንሸራተት እነቅስቃሴ

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 4


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሐ. በእርምጃ እየዘለሉ መሄድ

በእርምጃ እየዘለሉ መሄድ እርምጃና በአንድ እግር እየዘለሉ


መሄድን ያጣመረ ነው። በመቀጠል የተቃራኒ እግር እርምጃና
ዝላይ ይቀጥላል። ይህም ጉልበት ወደ ላይ በማንሳት ጉልበት
አየር ላይ ሲሆን በሌላኛው እግር ደግሞ ወደ ላይ መዝለል
ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡

• ቀጥ ብሎ መቆም ወይም ትክክለኛ አቋቋም መያዝ።

• አንድ እግር ወደ ፊት መውሰድ የቀረውን እግር ወደ


ፊት አስተካክለን ማረፍ፡፡

• ጉልበት በማንሳትና አየር ላይ በማድረግ በቀሪው እግር


መዝለልን መለማመድ፡፡

• ዘለን ስናርፍ በፊተኛው የእግር መዳፍ ማረፍ።

• ለዝላይ ስንዘጋጅ ጉልበታችንን በትክክል ማጠፍ፡፡

• በፊተኛው እግር ማረፍና እጅን በተቀራኒ


በማንቀሳቀስ በተደጋጋሚ መለማመድ፡፡

5 5 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.3. በእርምጃ የመዝለል እንቅስቃሴን

መ. መሰናክል በመጠቀም በፍጥነት መሮጥ

ይህ ሩጫ ሰውነታችን ከወገብ በላይ ወደ ፊት ዘንበል


በማድረግ እጆችን በደረት ልክ በመያዝ እግራችን ከመሬት
በማንሳት መሰናክል ላይ በማለፍ መሮጥ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• ከመሰናክል በስተኋላ አስፈላጊውን መስመርን ጠብቆ
መቆም፡፡
• ከመስመር ኋላ በአንድ እግር በመንበርከክ በአንዱ
የእግር ጣት መሬት መንካት፡፡
• ሁለቱንም እጅ በትከሻ ስፋት ልክ መሬት በመያዝ
መዘጋጀት፡፡
• የሚሰጠውን ትእዛዝ በማዳመጥ ከ50-60 ሜትር
2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 6
የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ያለውን ርቀት መሰናክል ላይ በማለፍ መሮጥ፡፡

• በመደጋገም መለማመድ፡፡

ምስል 1.4. የመሰናክል ሩጫ

ሠ. የጥምር እንቅስቃሴ ብቃት

ይህ እንቅስቃሴ በአንድ ጊዜ ሁለትና ከዛ በላይ እንቅስቃሴዎችን


ከመሳሪያ ጋር በማቀናጀት የሚሰራ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• በቡድን መቆም፡፡
• እግርን ከጉልበት በማጠፍ እና በመዝለል መስመር
ውስጥ መቀመጥ፡፡
• በመስመር ውስጥ እግር ሲከፈት ሁለቱን እጆች አንድ
ላይ መሰብሰብ።
• የእጅና የእግር እንቅስቃሴ በተቀራኒ በማድረግ

7 7 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

እንቅስቃሴውን መቀጠል።
• የእንቅስቃሴ ድግግሞሽ በአንድ ዙር ከ3-4 መብለጥ
የለበትም፡፡
• በመደጋገም መለማመድ፡፡

ምስል 1.5. እንቅስቃሴዎችን በመቀላቀል መስራት

1.2 አንድ ቦታ በመቆም የሚሠሩ እንቅስቃሴዎች

ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት፡


ተማሪዎች ከዚህ ትምህርት ክፍለ ጊዜ በኋላ።
• አንድ ቦታ በመቆም የሚሠሩ የእንቅስቃሴ ችሎታ
ምንነትን ትገልጻላችሁ፡፡
• አንድ ቦታ በመቆም የሚሠሩ የእንቅስቃሴ ችሎታ
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡
• አንድ ቦታ በመቆም የሚሠሩ የእንቅስቃሴ ችሎታን
ታደንቃላችሁ፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 8


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ተግባር 1.2

1. አንድ ቦታ በመቆም የሚሰራ እንቅስቃሴ ምን


ምን ነው?

ሀ. ገመድ ላይ በመቀመጥ ሰውነት ወደፊትና ወደ ኃላ


ማወዛወዝ

ገመድ ላይ በመቀመጥ ወደ ፊትና ወደ ኋላ ሰውነትን


የማወዛወዝ እንቅስቃሴን መስራት ዓዕምሮአችንን በማዝናናትና
እርስ በእርስ መተሳሰብ እንዲዳብር የምናዳብርበት ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• አግዳሚ እንጨት ላይ የታሰረ ገመድ አጠገብ በሰልፍ
መቆም፡፡
• ሁለት ሁለት በመሆን አንድ ተማሪ ሌላውን በመግፋት
ተራ በተራ እንዲጫወቱ ማድረግ፡፡
• የመምህሩ/መምህርቷ ትዕዛዝ በመጠበቅ ተራ በተራ
ገምድ ላይ መቀመጥ።
• አንድ ተማሪ ሲገፈትር ሌላኛው ገመዱ ላይ በመቀመጥ
መለማመድ።
• በመደጋገም መስራት፡፡

9 9 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.6. ገመድ ላይ በመቀመጥ ሰውነትን ወደ ፊትና ወደ ኋላ መግፈት

ለ. እግርን ከጉልበት በማጠፍ ወደ ደረት ከፍ ማድረግ

እግርን ከጉልበት በማጠፍ አንድ ቦታ በመቆም ተራ በተራ


ጉልበትን ከተቃራኒ እጅ ጋር በማንሳት የሚሰራ የእንቅስቃሴ
ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡

• አንድ ቦታ በመቆም ቀኝ እግር ከጉልበት በማጠጠፍ


ወደ ግራ እጅ ክንድ ወደ ላይ ማንሳት ፡፡

• ግራ እግርን ወደ ቀኝ እጅ ክንድ ማንሳት ፡፡

• ከ4-5 በመደጋገም መስራት፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 10


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.7. እግር በማጠፍ ወደ ደረት የማንሳት

ሐ. በአንድ እግር መቆም

በአንድ እግር መቆም አንድ እግርን ከመሬት በማንሳት


በቀረው እግር ደግሞ የሰውነትን ሚዛን በመጠበቅ የመቆም
ብቃት ነው፡፡

የልምምድ ዘዴዎች

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• በትክክለኛ አቋቋም በመቆም እጅ ወደ ጎን ዘርግቶ
አንድ እግርን ወደ ጉልበት ማምጣት፡፡
• እጅ በትከሻ ልክ ወደ ጎን በመዘርጋት አንድ እግርን
በማጠፍ ጉልበት ላይ ማሳረፍ፡፡
• በቆሙበት ቦታ የሰውነትን ሚዛን በመጠበቅ ከ3-5
ሴኮንድ መቆየት፡፡
• በመደጋገም መስራት።

11 11 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.8. በአንድ አግር መቆም

መ. ወደ ግራና ቀኝ ሰውነትን መጠምዘዝ

ይህንን የእንቅስቃሴ ችሎታን ለመስራት ቅድሚያ አንድ


ቦታ በመቆም ከወገብ በላይ ያለውን ሰውነት ወደ ግራ እና
ወደ ቀኝ በማጠማዘዝ የሚሰራ የእንቅስቃሴ ችሎታ ነው፡፡

ምስል 1.9. ሰውነትን ማጠማዘዝ እንቅስቃሴ

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 12


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሠ. የሰውነት ሚዛን በመጠበቅ አግዳሚ እንጨት ላይ


መራመድ

ምስል 1.10. አግዳሚ እንጨት ላይ ሚዛንን በመጠበቅ መራመድ

1.3. መሳሪያን በመጠቀም የሚሠሩ የእንቅስቃሴ


ችሎታዎች

ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት፡


ተማሪዎች ከዚህ ትምህርት ክፍለ ጊዜ በኋላ፡-
• መሳሪያን በመጠቀም እንዴት የአካል ብቃት
እንቅስቃሴ እንደሚሰራ ትገልጻላችሁ፡፡
• መሳሪያን በመጠቀም የሚስራ የእንቅስቃሴ
ልምምድ ዘዴዎችን ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡
• መሳሪያን በመጠቀም የሚስራ የእንቅስቃሴ
ችሎታን ታደንቃላችሁ፡፡

13 13 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ተግባር 1.4

1. መሳርያን በመጠቀም በአካባብያችሁ የሚጫወቱ


ጨዋታን ተናገሩ።

1. በመሳሪያ የሚሰሩ የእንቅስቃሴዎች

በመሳሪያ የሚሰራ እንቅስቃሴዎች ማለት የተለያዩ


መሳሪያዎችን በመጠቀም የሚሰሩ የእንቅስቃሴ ማለት
ነው፡፡ አነሱም፡-

ሀ. ኳስ መወርወርና የመያዝ ችሎታ

ኳስ መወርወርና የመያዝ ችሎታ በአንድ ጊዜ የሚካሄድ


እንቅስቃሴ ሆኖ ኳስ ወደ ተለያየ አቅጣጫ በመወርወርና
በመያዝ የሚተገበር እንቅስቃሴ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴዎች

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• ከመነሻ ቦታ ላይ ኳስ በእጅ መያዝ፡፡
• በተለያየ አቅጣጫ ከጭንቅላት በላይ በሁለት እጅ
መወርወርና መያዝ፡፡
• በመቀጠል ኳስ በአንድ እጅ መወርወርና መያዝን
መለማመድ፡፡
• በመደጋገም መለማመድ፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 14


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.11. ለ. ኳስ መወርወርና መያዝ

ለ. ኳስ እያነጠሩ መሄድ

የልምምድ ዘዴዎች

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡

• በተርታ ወይም በሰልፍ መቆም፡፡

• ከወገብ ዝቅ በማለት ጉልበታችንን በማጠፍ ኳስ


በማንጠር ወደ ፊት መሄድ፡፡

• እይታችንን ኳስ ላይ ሳናደርግ ኳስን እየተቆጣጠርን


እያነጠርን መራመድ፡፡

• በመደጋገም መለማመድ፡፡

15 15 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.12. ኳስ በማንጠር መሄድን

ሐ. ኳስ በእግር ማንከባለልና ማሳለፍ

ኳስ በእግር ማንከባለልና የማሳለፍ ችሎታ ማለት ኳስን


በእግር ወደ ተለያዩ አቅጣጫ ማንከባለልና በማሳለፍ
የሚተገበር የእንቅስቃሴ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• መነሻ ቦታ ላይ ኳስ በመያዝ ተዘጋጅቶ መቆም፡፡
• ከቆምንበት ኳስ በእግር በማንከባል መቀባበል ፡፡
• በተደረደረው መሳሪያ (ኮን) መኃል ኳስን በአንድ
እግር ማንከባለል፡፡
• በቀጣይ ባልሰራው እግር ደግሞ መስራት።
2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 16
የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.13. ኳስ በማንከባለል ማሳለፍ

መ. ኳስ መለጋት

ኳስ መለጋት ኳሷን መሬት ላይ በማንከባለል ወደ


ተፈለገበት አቅጣጫ ለጓደኛ ማቀበል ነው።

17 17 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴዎች

• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• በሰልፍ መቆም።
• ከወገብ ዝቅ ብሎ ጉልበትን አጠፍ በማድረግ በእግር
ኳስ ወደ ፊት ማንከባለል፡፡
• በዓይን ኳሷን በመቆጣጠር ደጋግሞ መለማመድ።

ምስል 1.14. ኳስ መሬት ላይ መለጋት

2. ጥምር እንቅስቃሴ

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• ኳስ በመያዝ መቆም፡፡
• ከቆምንበት በኳሷ እንቅስቃሴ ማድረግ።
• ኳስ እየወረወሩ መሄድ።
• በመደጋገም መስራት፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 18


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 1.15. ጥምር እንቅስቃሴ

የምዕራፉ ማጠቃለያ

መሠረታዊ የእንቅስቃሴ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎች


በመጠቀም የሚተገበር ሆኖ ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ፣
አንድ ቦታ በመቆም፣ በመሳሪያ እና የለመሳርያ የሚሰራ
የእንቅስቃሴ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ ሩጫ፣ እርምጃ፣ ዝላይ፣ ኳስ
መቀባበል እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የምዕራፉ መልመጃ

I. ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ


“እውነት” ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት
መልስ፡፡
1. መራመድ ከቦታ ወደ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰራችሎ
ነው፡፡

19 19 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

2. በአንድ እግር በመቆም መንቀሳቀስ እና የሰውነት


ሚዛን መጠበቅ አስፈላጊ አይደለም።

II. የሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ


የያዘውን ፊደል ምረጡ
3. አንድ ቦታ በመቆም የሚሰራው እንቅስቃሴ
የትኛው ነው?

ሀ) መራመድ ሐ) ቁጢጥ ብሎ መቀመጥ


ለ) ሩጫ መ) ኳስ መጫወት

4. ከሚከተሉት አንንዱ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ከሚሰራ


እንቅስቃሴ ቀዳሚው የቱ ነው?

ሀ) ምቹ ቦታ ሐ) እየዘለሉ መሄድ
ለ) ኳስ መምታት መ) ኳስ መቀባበል

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 20


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ ሁለት
የቅደም ተከተል እንቅስቃሴ

ከዚህ ምዕራፍ የሚጠበቁ ውጤቶች


ተማሪዎች ይህን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-
• የቅደም ተከተል እንቅስቃሴን ከምት(ሪት)ጋር
ታቀናጃላችሁ።
• በሚሰጠው የሙዚቃ ምት ምልክት ተጠቅማችሁ
የተለያዩ የአካል እንቅስቃሴ ሂደቶችን ትለያላችሁ፡፡
• ምልክቶችን በመጠቀም የተለያዩ የአካል ቅንጀት
ችሎታን ታዳብራላችሁ፡፡
• በተለያዩ ምት በመታገዝ የተለያዩ የሰውነት እንቅስቀሴ
ቅንጅትን ተዳብራላችሁ።

መግቢያ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እንቅስቃሴ ከተለያየ


ምት ጋር ግንኙነት አለው፡፡ ይህም የአካል እንቅስቃሴ
ሰውነትን ከምት ጋር በማቀናጀት መስራት ይቻላል።
በዝህ ምእራፍ ወስጥ እየተቀያየረ ከሚሄድ የምት ቅደም
ተከተል ጋር እየተቀያየረ ከሚሄድ የሰውነት እንቅስቃሴን
ትማራላችሁ።

21 21 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

2.1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ቅደም ተከተል


ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት፡
ተማሪዎች ከዚህ ትምህርት ክፍለ ጊዜ በኋላ፡-
• ከምት ጋር እየተቀያየረ የሚሄድ የእንቅስቃሴ ቅደም
ተከተል ምንነት ትናገራላችሁ።
• የተቀናጀ መደበኛ የእንቅስቃሴ ችሎታ ሂደትን
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡
• የተቀናጀ የእንቅስቃሴ ችሎታ ከሙዚቃ ምት ጋር
ሰርታችሁ ያዳበራችሁትን ክህሎት ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር 2 1
1. የተጣመረ መሰረታዊ የቅደም ተከተል እንቅስቃሴ
ምንድነው?

የተጣመረ መሰረታዊ የቅደም ተከተል እንቅስቃሴ የተለያዩ


ድምፅ/ምት በመጠቀም ይሰራል።

ሀ. መደበኛ ቅደም ተከተል የአካል እንቅስቃሴ

መደበኛ ቅደም ተከተል እንቅስቃሴ ቅደም ተከተል በመጠበቅ


በየቀኑ የሚሰራ የአካል እንቅስቃሴ ነው፡፡

ለ.ምትን(ሪትም) በመከተል የሚሰራ የአካል እንቅስቃሴ

የሙዚቃ ድምጽ /ምት በመከተል የሚሰራ የተለያየ የአካል


እንቅስቃሴ ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 22


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• ተማሪዎች በቡድን በቡድን በመከፋፈል ማቆም፡፡
• በቆማበት እግርን በማንቀሳቀስ በተመሳሳይ ሁኔታ
ማጨብጨብ፡፡
• የእጅና እግር እንቅስቃሴ ፍጥነት እየጨመሩ
መለማመድ።
• በመደጋገም መለማመድ።

ሐ. የስፖርት ስፖርትመዝሙር መዝሙር

• ስፖርት ሰፖርት ስፖርት


• ስፖርት ለሠላም
• ስፖርት ለፍቅር
• ስፖርት ለአንድነት
አዝማች
• ስፖርት ሰፖርት ስፖርት
• ስፖርት ለእድገት
• ስፖርት ለጤንነት
• ስፖርት ለሀብት

መ.ወደ ላይ በመዝለል በእጅን ጭብጨባ ፍሰት መንቀሳቀስ

ይህ እንቅስቃሴ አንድ ቦታ በመቆም ወደ ላይ በመዝለል


ከእጆቻችን ምት ጋር የአካል እንቅስቃሴዎችን በማጣጣም
የሚተገበር ነው፡፡

23 23 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴዎችዘ
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• ትክክለኛ አቋቋም መቆም፡፡
• አንድ ሲባል እግርን መክፈት እጆችን ወደ ጎን
መዘርጋት
• ሁለት ሲባል በመዝለል በሁለት እጅ ከራስ በላይ
ማጨብጨብ
• ሦስት ሲባል ወደ ፍት በመዝለል በሁለት እጅ ከራስ
በላይ ማጨብጨብ
• አራት ሲባል ወደ ኋላ በመዞር እጅ ከራስ በላይ
ማጨብጨብ
• ቀስ በቀስ ፍጥነትን በመጨመር መለማመድ፡፡
• በመደጋገም መለማመድ፡፡

ምስል 2.1. ወደላይ በመዝለል እጆችን ማጨብጨብ

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 24


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሠ. ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ መዝለል

ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ መዝለል እግራችን አንድ ላይ ከመሬት


በማንሳት ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ ቀስ በቀስ እየጨመረ
በመሄድ የሚተገበር ነው።

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• በትክክል መቆም
• እግር በመክፈት እጆችን ወደ ደረት ማምጣት፡፡
• ቀስ በቀስ ፍጥነትን በመጨመር ወደ ግራ እና ወደ
ቀኝ መዝለል፡፡
• በመደጋገም መለማመድ፡፡

ምስል 2.2. ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ መዝለል

25 25 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

2.2. ከምት ጋር እየተቀያየረ የሚሄድ የእንቅስቃሴ


ብቃት
እጅን በማጨብጨብ ወይም የተለያዩ መሳሪያዎችን
በመምታት ከእጅ ምት ወይም የመሳሪያ ድምጽ ጋር
እንቅስቃሴን በማቀናጀት የሚሰራ የአካል እንቅስቃሴ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• ትክክለኛ አቋቋም መቆም፡፡
• አንድ የሚታወቅ እንቅስቃሴ መምረጥ፡፡
• ምት በመጠበቅ እግር ማንቀሳቀስ፡፡
• ሁለቱም እጆች ወደ ጎን በመዘርጋት አንድላይ
ማንቀሳቀስ፡፡
• ቀስ በቀስ ፍጥነት በመጨመር መለማመድ፡፡

ምስል 2.3. ከእጅ ምት ጋር የሚሠሩ እንቅስቃሴዎች

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 26


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የምዕራፉ ማጠቃለያ

• መደበኛ የቅደም ተከተል እንቅስቃሴ ማለት፦ የተለያዩ


የሰውነት ክፍሎችን ከሙዚቃ ድምፅ/ምት ጋር
በማስማማት የሰውነትን እንቅስቃሴ በተለያየ ደረጃ
ውስጥ እቀያየሩ በመሄድ መሰራት መቻል ነው። ቀስ
በቀሰ እየተቀያየረ የሚሄድ የምት እንቅስቃሴ ደግሞ
የሰውነት ክፍል ከተለ ያየ ምት/ሪትም ጋር በማቀነጀት
የሚሰራ እና ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ነው።

መልመጃ

I. ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ


“እውነት” ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት
መልሱ፡፡

1. የአካል እንቅስቃሴን ከሙዚቃ ምት ጋር መስራት


ትልቅ መነቃቃት ይሰጣል።

2. የአካል እንቅስቃሴ ከተለያዩ ምት /ሪትም ጋር


ከተቀነጀ አዕምሮን ያዝናናል፡፡

27 27 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ


የያዘውን ፊደል ምረጡ፡፡

3. ከሚከተሉት የአካል እንቅስቃሴዎች ውስጥ


ከሙዚቃ ምት ጋር የምሄድ የቱ ነው

ሀ) መቆም ለ) እጅ ማጨብጨብ
ሐ) መቀመጥ መ) መወርወር

4. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ ከሙዚቃምት ጋር


የሚሠራ እንቅስቃሴ ነው።

ሀ. ወደ ለይ በመዝለል እጅን ማጨብጨብ


ለ. ወደቀኝና ግራ የመዝለል እንቅሰቃሴ
ሐ. ወደጎን የመዝለል እንቅስቃሴ
መ. ሁሉም

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 28


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምህራፍ ሶስት
ማህበራዊነትንና ውስጣዊ ስሜትን መማር
ከዚህ ምዕራፍ የሚጠበቁ ውጤቶችሰ
ይህን ምዕራፍ ከተማራችሁ በኋላ፡-
• የሰውን ችግር ከግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ለተሰጠው
መፍትሔ ጥሩ እይታ ይኖራችኋል።
• በሚሰራው የሰውነት እንቅስቃሴ ውስጥ ስሜታችሁን
በመቆጣጠር ታሳያላችሁ።
• በተለያዩ የአካል እንቅስቃሴ ውስጥ በመልካም
ግንኙነትን ትሳተፋላችሁ።

መግቢያ

ማህበራዊ እድገት እና ውስጣዊ ስሜትን መቆጣጠር በአካል


እንቅስቃሴ የሚገኙ ናቸው። በቡድን የሚሰሩ ጨዋታዎች
በተማሪዎች መካከል ጥሩ ግንኙነትን ለመፍጠርና ውስጣዊ
ስሜትን የሚያሳድጉ ስለሆኑ በእንደነዚህ ጨዋታዎች ውስጥ
መሳተፍ አስፈላጊ ነው፡፡
በዚህ ምህራፍ ውስጥ ማህበራዊ እድገትና የውስጥ ስሜትን
መማር፣ ራስን የማወቅ ችሎታን የሚያሳድጉ እንቅስቃሴዎች፣
የማህበረሰቡን የግንዛቤ እና የግንኙነት ችሎታን የሚያዳብሩ
እንዲሁም የተለያዩ የባህል ግንኙነትን የሚያዳብሩ የአካል
እንቅስቃሴዎችን የሚትማሩ ይሆናል፡፡
29 29 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል
የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

3.1. ራስን ማወቅና የመቆጣጠር ችሎታን የሚያሳድጉ


ጨዋታዎች እና እንቅስቃሴዎች
ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት፡
ይህን ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦

• ራስን የማወቅና እርስ በእርስ የመረዳዳት ችሎታን


የሚያሳድጉ የአካል እንቅስቃሴዎችን ትገልጻላችሁ፡፡
• ራስን የማወቅና እርስ በእርስ የመረዳዳት ችሎታን
የሚያሳድጉ የአካል እንቅስቃሴዎችን ሰርታችሁ
ታሳያላችሁ፡፡
• ራስን የማወቅና እርስ በእርስ የመረዳዳት ችሎታን
የሚያሳድጉ የአካል እንቅስቃሴዎችን ታደንቃላችው፡፡

ተግባር 3.1
ራስን የማወቅ ችሎታ ምንድነው?

ሀ. ራስን መመዘን
ራስን መመዘን ማለት የራስን ድክመት ለይቶ ማወቅ ነው።
ያለንን ጥንካሬ ማበረታታት እና ድክመን በማሻሻል እራስን
መመዘን አስፈላጊ ነው። እራስን ለመመዘን የሚያግዙ/
የሚያሳድጉ እንቅስቃሴዎች እንደ ኳስ መምታትና መለጋት
የመሳሰሉት ናቸው። ኳስ መለጋት፣ ኳስ መምታትና
የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ራሳችን መመዘንን የሚያሳድጉ
የእንቅስቃሴ ችሎታዎች ናቸው፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 30


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• ኳስ ከፊት በማድረግ ኳስ የማይመታ እግርን ከኳስ
ጎን ማድረግ፡፡
• ከወገብ በላይ ያለውን ሰውነት ትንሽ ወደ ፊት ዝቅ
በማድረግ በዓይናችን ኳስ ላይ በማተኮር በውስጥ
እግር ኳስ መምታት፡፡
• በመደጋገም መለማመድ፡፡

ምስል 3.1. ኳስ መምታት

ለ. ራስን ማበረታታት
ራስን ማበረታታት ማለት ፦ ችግር በአጋጠመን ጊዜ ለችግሩ
እጅ አለመስጠትና ተስፋ ሳንቆርጥ ለሌላ ስራ እራሳችንን
ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በኮርቦ ( ቀለበት) ውስጥ
መዝለል ስንለማመድ ከተሳሳትን ተስፋ ሳንቆርጥ ደግሞ
መለማመድ።

31 31 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴዎች
• ሰውነትን በትክክል ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡
• መነሻ ቦታ ላይ መገኘት፡፡
• ባለ አንድ ኮርቦ (ቀለበት) ውስጥ ሁለት እግር
ማሳረፍና ሁለቱን እጆች ወደታች ማድረግ።
• በባለ ሁለት ኮርቦ (ቀለበት) ውስጥ እያንዳንዱን
እግር ማሳረፍና ሁለቱንም እጆች በትከሻ ስፋት ልክ
ወደ ፊት መክፈት፡፡
• 4-5 ጊዜ በመደጋገም መስራት፡፡
• ሰውነትን በማቀዝቀዝ ማጠናቃቅ፡፡

ምስል 3.2. ኮርቦ /ክብ ውስጥ መዝለል

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 32


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

3.2 በጨዋታና እንቅስቃሴ ውስጥ የማህበረሰባዊ ግንዛቤን


የሚያሳድጉ
ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት፡
ይህን ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦
• በጨዋታዎች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ የማህበረሰባዊ
ግንዛቤን ማሳደግን ትገልፃላችሁ፡፡

• በጨዋታዎች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ የማህበረሰባዊ


ግንዛቤን ግንኙነትን የሚያሳድጉ የአካል እንቅስቃሴዎችን
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡

• የማህበረሰቡን ግንዛቤና የግንኙነት ችሎታን የሚያሳድጉ


የአካል እንቅስቃሴዎችን ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር 3.2

1. የማህበረሰብ ግንዛቤና ግንኙነትን የሚያሳድጉ


ጨዋታዎች እና እንቅስቃስዎች ምን ምን ናቸው?

ሀ. ልዩነትን ማክበር

ልዩነት ማክበር ማለት፦ በጨዋታና በአካል እንቅስቃሴ


ውስጥ ያለ አንዳች አድሎ ለተለያዩ ሰዎች እኩል እድል
በመስጠት ማሳተፍ ማለት ነው፡፡ ለምሰሌ፡ ወንድና ሴት
ተማሪዎችወዘተ።

33 33 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 3.3. ወንድና ሴት ተሳትፎ

ምስል 3.4. ልዩነቶችን ማክበር

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 34


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ለ. ሌሎችን ሰዎችን ማክበር

በጨዋታም ሆነ በሌላ ቦታ የሌላ ሰው ሀሳብ፣ እምነት፣


ቋንቋ፣ በህል እና ማንነትን ማክበር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ምስል 3.5. በመከባበር አብሮ መጫወት

3.3. በጨዋታና እንቅስቃሴዎች ውስጥ ግንኙነት


ማሳደግ
ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር
ብቃት ይህን ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦

• በጨዋታና እንቅስቃሴዎች ውስጥ የማህበራዊ


ግንዛቤ እና ግንኙነትን ብቃትን የሚያሳድጉትን
እንቅስቃሴዎች ትገልፃላችሁ፡፡
• በጨዋታና እንቅስቃሴዎች ውስጥ የማህበራዊ
ግንዛቤ እና የግንኙነት ብቃትን የሚያሳድጉትን
እንቅስቃሴ ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡

35 35 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• በጨዋታና እንቅስቃሴዎች ውስጥ የማህበራዊ


ግንዛቤ እና የግንኙነት ብቃትን የሚያሳድጉትን
እንቅስቃሴ ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር 3.3
1. ሌላ ሰዎችን ማበረታታት ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ማበረታታት


ማንኛውም ሰው ተመሳሳይ ችሎታ የለውም። ስለዝህ
እንቅስቃሴ ውስጥም ሆነ ከእንቅስቃሴ ውጪ የዚያን ሰው
ስህተት በማረም ማበረታታት ሊበረታታ የሚገባ ባህል ነው።

ለ. የተለያዩ ባህሎችና እና ማህበረሰባዊ ግንኙነት


የሀገራችን ብሄር ብሄረሰቦች የተለያዩ ባህል እዳላቸው
የሚታወቅ ነው፡፡ የሌላውን ብሔር ባህል እንደ ራሳችን
ባህል ማክበር ማህበረሰባዊ ግንኘነትን ለማጠንከር አስፈላጊና
ወሳኝ ድርግት ነው፡፡

ምስል 3.6 የኦሮሞ ባህላዊ ውዝዋዜ

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 36


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የምዕራፉ ማጠቃለያ

ሰው ችሎታውን እና ድክመቱን የሚየውቅ ከሆነ ስሜቱን


በመቆጣጠር ወደ ቀና ሁኔታ መምጣት የችላል። ለዚህ
ደግሞ የሰውነት እንቅስቃሴ የማህበረሰብ ግንዛቤ እና
ግንኙነት ብቃትን በማጠንከር በፍቅር አብሮ ለመኖር
ይጠቅማል።የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች የተለያየ
ባህል፣እምነት ፣ማንነት አላቸው። የሌላውነ ማህበረሰብ ባህል
እንደ ራስ ባህል በማክበር ማህበራዊ ልዩነትን ማጠንከር
አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው።

የምዕራፉ መልመጃዎች

I. ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ጥያቄዎች ትክክል ከሆኑ


“እውነት” ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት
መልሱ፡፡
1. የአካል እንቅስቃሴ በትምህርት ቤት ውስጥ ብቻ
ይሰራል፡፡

2. ጨዋታን በቡድን መጫወት ጓደኛን ለማፍራት


ይረዳል፡፡

37 37 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

II. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ


የያዘውን ሆሄ ምረጥ
1. ተማሪዎች የመከባበር ባህል እንድያጠነክሩ
የማድረግ ስራ የማን ድርሻ ነው?

ሀ. የቤቴሰብ ሐ. የአካባቢ ሰዎች


ለ. የጓደኛ መ. ሁሉም መልስ ናቸው

2. ከዚህ በታች ካሉት ውስጥ አንዱ ማህበራዊ


ግንኙነት የሚያሳድግ አይደለም፡፡

ሀ. ስርአትን መጠበቅ ሐ. መከባበር


ለ. የእርስ በርስ ፍቅር መኖር መ. መጣላት

III. ለሚከተለው ጥያቄ አጭር መልስ ጻፉ፡፡

1. ከትምህርት ቤት ውጪ መስራት የሚትወዱት


የአካል እንቅስቃሴ ውስጥ ሁለቱን ጻፉ፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 38


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ አራት
የአካል ብቃት
ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች
• የአካል ብቃትን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን
ትገነዘባላችሁ።

• ከእድሜ ጋር የሚሄዱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን


በመስራት የአካል ብቃትን ታጎለብታላችሁ፡፡

• የተለያዩ የአካል ልምምዶች እንቅስቃሴ ውስጥ


በመሳተፍ ጥሩ አመለካከት ታሳያላችሁ፡፡

በማንኛውም ስራ ውስጥ የአካል ብቃት መኖር በስራ


ወጤታማነት ላይ ትልቅ ቦታ አለው። ስለዝህ ከልጆች
ጀምሮ የተለያየ የሰውነት እንቅስቃሴ ውስጥ መሳተፍ ትልቅ
ውጤት አለው።

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የምትማሩት የሰውነት ብርታት፣


የልብና የሳምባ ስራ፣የጡንቻ ጥንካሬ፣ መተጣጠፍ እና
ብቃትን ትማራላችሁ።

39 39 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

4.1 የልብና የሳምባን እንቅስቃሴዎች

ተማሪዎች ቢያንስ መጎነፀፍ ያለባቸው የመማር


ብቃት
ይህን ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦
• የልብና የሳምባ ስራ ምንነት ትናገራላችሁ ፡፡
• የልብና የሳምባ ስራ ብርታት የሚያጎለብቱ
እንቅስቃሴዎችን ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡
• በአካል እንቅስቃሴ የተጎናፀፋችሁትን የልብና
ሳምባ ብርታት ችሎታን ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር 4.1

የልብና ሳምባ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን


ጥቀሱ፡፡

ሀ. በግል ገመድ መዝለል

ገመድ ዝላይ በሚዞር ገመድ ላይ አንድ ቦታ በመሆን


ወይም ከቦተ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰራ እንቅስቃሴ ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት


• ገመድ በመያዝ ትክክለኛ አቋቋም መቆም
• በሁለት እግር በመዝለል ገመዱን ከራስ በላይ
በማዞር በሁለቱ እግር ስር ማሳለፍ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 40


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• ከ 3_4 ድግግሞሽ መስራት።


• በስተመጨረሻ ሰውነትን ማቀዝቀዝ።

ምስል 4.1. ገመድ መዝለል

ለ ከቆምንበት ጉልበት ወደ ላይ ማንሳት

ከቆሙበት እግርን ጉልበት ላይ በመጠፍ ወደ ደረት


በማንሳት የሚሰራ እንቅስቃሴ ነው።

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡
• እጅ ወደ ታች በማውረድ ትክክለኛ አቋቋም መቆም፡፡
• ሁለት እግር እኩል በማስተካከል መቆም እና
አንደኛዉን እግር ከመሬት ወደ ላይ ማንሳት፡፡
• ተራውን በመጠበቅ ሁለተኛውን እግር እንድሁ
ማነሳት።
• ፍጥነት በመጨመር ደጋግሞ መስራት።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

41 41 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 4.2. ጉልበትን ወደ ላይ ማንሳት

ሐ. ተረከዝ ወደ ላይ በማንሳት መቆም

በቆሙበት ቦታ ላይ ተረከዝን ወደ ላይ በማንሳትና


በመመለስ የሚሰራ ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡


• ትክክለኛ አቋቋም መቆም።
• ሁለቱን እግር ከተረከዝ ወደ ላይ ማንሳትና
መመለስ።
• አንዱን እግር ከተረከዝ ወደ ላይ ማንሳትና
መመለስ።
• ወደቀኝ እና ወደግራ ለመሄድ ደጋግሞ መለማመድ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 42


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• ፍጥነት በመጨመር ደጋግሞ መለማመድ።


• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 4.3. ተረከዝን ወደ ላይ ማንሳት

4.2 የጡንቻ ብርታት

ተማሪዎች ቢያንስ መጎነፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት


ይህን ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦

• ሰለ ጡንቻ ብርታት ምንነት ትናገራላችሁ።


• የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ።
• የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን
ታደንቃላችሁ።

43 43 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ተግባር 4.2
1. የጡንቻ ብርታት ምንድነው?
2. የጡንቻ ብርታትን የሚያሳድጉ እንቅስቃሴዎች
ምን ምን ናቸው?

ሀ. እጅን ወደ ጎን ማንሳትና መዘርጋት


እጅን ወደ ጎን በትከሻ ስፋት ልክ በመዘርጋት የሚሰራ
እንቅስቃሴ ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡


• ትክክለኛ አቋቋም መቆም።
• ሁለት እጆችን ወደ ጎን በመዘርጋት የእጅ መዳፍን
ተራ በተራ ወደ ላይ እና ወደ ታች ማድረግ።
• እጅን ተራ በተራ በፍጥነት በማመሳቀል መስራት።
• ፍጥነት እየጨመሩ 1-2 ደቂቃ በማቆየት መስራት።
• ከ5-7ጊዜ በመደጋገም መስራት።
• በስተመጨረሻ ሰውነትን በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 44


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 4.4. እጅን ወደ ጎን በማንሳት መዘርጋት

ለ. እጅን በማስተላለፍ እግር መንካት


እጅን በማስተላለፍ እግር መንካት ከቆሙበት ቦታ ጎንበስ
በማለት በእጅ መንካት ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡


• እግር ከፈት አድርጎ መቆም።
• ጎንበስ በማለት በቀኝ እጅ የግራ እግር ተረከዝ
መንካት ግራ እጅን ወደ ላይ ማንሳት።
• እጅን በማፈራረቅ ደጋግሞ መስራት።
• በስተመጨረሻ ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናኀቀቅ።

45 45 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 4.5. እጅን በማስተላለፍ እግር መንካት

ሐ. በጀርባ መሬት ላይ መተኛትና ወደ ጉልበት መነሳት

በጀርባ መሬት ላይ ከተኙበት ቦታ በጉልበት ልክ ቀና


በማለት የሚተገበር እንቅስቃሴ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡
• ሁለት እግር መዘርጋት እና እጅን ወደ እግር
አቅጣጫ በማድረግ በጀርባ መሬት ላይ መተኛት፡፡
• እግርን ጉልበት ላይ በማጠፍ በእግር መዳፍ በደንብ
መሬት መያዝ።
• ከደረት ቀና በማለት ጉልበትን ነክቶ ወደ መሬት
መመልስ።
• ከ2-3 ደጋግሞ መለማመድ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 46


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 4.6. በጀርባ መሬት ላይ መተኛትና መነሳት

4.3 መተጣጠፍ
1 መተጣጠፍ ምንድነው ?
2 መተጣጠፍን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን
ተናገሩ?

ይህ እንቅስቃሴ ከወገብ ወደ ቀኝና ግራ በማጠፍ የሚሰራ


ነው።
ሀ ከወገብ ወደ ጎን ማዘንበል
እንቅስቃሴው ከወገብ በላይ ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ
በማዘንበል የሚሰራ ተግባር ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡

47 47 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• በትክክለኛና አቋቋም ላይ በመሆን ሁለት እጅ ወደ


ላይ ማንሳት።
• ቀስ በማለት ወደ ግራ እና ቀኝ ማዘንበል።
• በተደጋጋሚ መለማመድ።
• በስተመጨረሻ ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 4.7. ከወገብ ወደ ጎን ማዘንበል

ለ. በመቀመጥ የእግርን ጣት መንካት

በመቀመጥ እግርን ወደ ፊት በመዘርጋት በእጅ የእግርን


ጣት መንካት ማለት ነው ፡፡

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡

• መሬት ላይ በመቀመጥ ሁለት እግርን ወደ ፊት


መዘርጋት።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 48


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• ከወገብ ጎንበስ በማለት በሁለት እጅ የእግርን ጣት


መንካት።
• ለ 4-5 ሴከንድ ማቆየት።
• በተደጋጋሚ መስራት።

ምስል 4.8. በመቀመጥ የእግር ጣት መንካት

ሐ በጀርባ ተኝቶ እግርን ማንሳት

በጀርባ በመተኛት እጅን መሬት ላይ በጎን በኩል በማድረግ


ቀስ በቀስ እግርን ወደ ላይ የማንሳት እንቅስቃሴ ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡
• እግርን በመዘርጋት በጀርባ መሬት ላይ መተኛት።
• እግርን ቀስ በቀስ ከመሬት በማንሳት ወደ ላይ
ማቆም እና 2-3 ሰከንድ መቆየት።
• በተደጋጋሚ መለማመድ።

49 49 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምስል 4.9. በጀርባ ተኝቶ እግርን ማንሳት

4.4 ቅልጥፍና
ተማሪዎች ቢያንስ መጎነፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት
ይህን ርዕስ ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦
• ሰለ ቅልጥፍና እንቅስቃሴ ትናገራላችሁ።
• ሰለ ቅልጥፍና እንቅስቃሴ ሰርታችሁ ታሳያላችሁ።
• የተጎናፀፋችሁትን የቅልጥፍና ብቃት
ታደንቃላችሁ።

ተግባር 4.4

1. ቅልጥፍና ምንድነው?

ቅልጥፍና አንድን ስራ በፍጥነት እና ወደ ተለያዩ አቅጣጫ


በመቀያየር መስራት ብቃት ነው ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 50


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሀ. በመሮጥ የተጠራውን ቀለም መንካት

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት፡፡
• ልምምድ ቦታ ላይ መገኘት።
• የተለያዩ ቀለማትን በሰርክል ማስቀመጥ።
• የመምህሩን/ርቷን ተእዛዝ በደንብ ማዳመጥ።
• የተጠራውን የቀለም ዓይነት በሩጫ ሄዶ መንካት።
• በመደጋገም መለማመድ።
• በመጨረሻ ሰውነትን በማቀዝቀዝ ማጠቃለል።

ምስል 4.10. በጀርባ ተኝቶ እግርን ማንሳት

51 51 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የምዕራፍ ማጠቃለያ

አካል ብቃት ማለት አንድ ሰው ያለ ምንም ድካም እቅስቃሴ


እንዲሰራ የሚያስችል ችሎታ ማለት ነው፡፡ የአካል ብቃት
ያለው ሰው ጥሩ ጤንነት ይኖረዋል;፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የልብና ሳንባ ብርታት ማለት ልብና


ሳንባ ያለድካም ለረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ ላይ የመቆየትን
ችሎታ ያመለክታል፡፡ በተጨማሪ የጡንቻ ብርታት ጡንቻን
ያለድካም ለረጅም ጊዜ እንቅስቃሴ ላይ የመቆየትን ችሎታን
የምያመለክት ነው፡፡

መተጣጣፍ ማለት ሰውነታችን በመገጣጠሚያ አካባቢ


የመታጠፍ ችሎታን የሚያሳይ እንቅስቃሴን ነው፡፡

የምዕራፉ መልመጃ

|. ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ “እውነት”


ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡

1. በአካል እንቅስቃሴ ውስጥ የሚሳተፉ ልጀች ጥሩ ብቃት


ይኖራቸዋል፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 52


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

||. ከ “ሀ” ስር ያሉትን ቃላቶች ከ “ለ” ስር ካሉት እና


ከሚመሳሰሉት ቃላት ጋር አዛምዱ

“ሀ” “ለ”
1. ወደ ጎን ማዘንበል ሀ መተጣጣፍ
2. ገመድ መዝለል ለ. የልብ እና የሳምባ ብርታት
እንቅስቃሴ

III. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ የያዘውን


ፊደል ምረጡ፡፡
1. የልብና ሳምባ ስራ ብርታት የሚያዳብር እንቅስቃሴ
የቱ ነው?
ሀ) ከወገብ በላይ ወደ አንድ ጎን ማዘንባል
ለ) ገመድ መዝለል
ሐ) በመቀመጥ በእጅ የእግርን ጣት መንካት
መ) ሁሉም

2. የሰውነት መገጣጠሚያን የሚያጎለብት እቅስቃሴ


ምን ይባላል ?
ሀ) የጡንቻ ብርታት
ለ) ሩጫ
ሐ) መተጣጠፍ
መ) የልብና ሳንባ ብርታት

53 53 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ አምስት
ጂምናስቲክስ
የምዕራፉ ዓላማዎች፡
ይህንን ምዕራፍ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡
• መሰረታዊ የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን
ትገነዘባላችሁ፡፡
• በመሰረታዊ የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች
ትዝናናላችሁ፡፡
• መሰረታዊ የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡

መግቢያ

ጂምናስቲክስ በመሳሪያ እና ያለ መሳሪያ እገዛ የሚሰራ


ሰፖርታዊ አንቅስቃሴ ነው፡፡ የመሳሪያ ጅምናስትክስ
የሚባሉት እንደ ፍራሽ፣ አግዳሚ እንጨት እና አግዳም
ሳጥንን በመጠቀም የሚሰሩ ሲሆን ከመሳሪያ ውጪ የሚሰሩ
ጂምናስቲክስ ደግሞ መሳሪያ ሳንጠቀም በሰውነታችን ብቻ
የሚሰሩ ናቸው፡፡

በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ቀላል መሰረታዊ የጂምናስቲክስ


እንቅስቃሴዎችን አሰፈላጊነትና ወስን የሰውነት
እንቅስቃሴን ትማራላችሁ፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 54


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

5.1 ቀላል ጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች


ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት
ይህንን ርዕስ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ
• ቀላል የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ምንነት
ትናገራላችሁ፡፡
• ቀላል የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች አሰራር
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ፡፡
• በቀላል የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ያዳበራችሁትን
ችሎታ ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር 5.1

1. ቀላል ጂምናስቲክስ ምንድነው?

ቀላልየጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች በመሳሪያ እና


ያለመሳሪያ በቀላሉ መሰራት የሚቻል የጂምናስቲክስ
እንቅስቃሴዎች ናቸው፡፡

ሀ. ወፍራም ምንጣፍ ላይ መገልበጥ

ይህ አንቅስቃሴ በጀርባ በመተኛት እጅን ወደ ኋላ ከዘረጋህ


በኋላ ምንጣፍ ላይ ወደ ጎን መገልበጥ ነው።

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።

55 55 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• በትክክል መቆም።
• ምንጣፍ በማዘጋጀት ከአንድ ምንጣፍ ኋላ የተወሰኑ
ተማሪዎችን ማሰለፍ።
• በቅደም ተከተል ያሉ ተማሪወች ምንጣፋ ላይ
በጀርባ መተኛት።
• ወደ ጎን በመገልበጥ መለማመድ።
• ወደ መጀመሪያው ቦታ በመመለስ ለመቀመጥ
መሞከር፡፡
• በመደጋገም መለማመድ።
• መጨረሻ ላይ ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.1 ፍራሽ ላይ መገልበጥ

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 56


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ለ. ወደላይ በመዝለል በሁለት እግር ማረፍ

ይህ እንቅስቃሴ ሁለት እግርን አንድ ላይ ወደላይ በማንሳት


ወደፊት በመዝለል የምሰራ እንቅስቃሴ ነው፡፡

የልምምድ ዜደ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።


• በትክክለኛ ቦታ ላይ መቆም።
• እጃችንን በትከሻ ስፋት ልክ ወደ ፊት በመዘርጋት
ጉልበታችንን አጠፍ ማድረግ፡፡
• አጠፍ ካለው ጉልበታችን ወደላይ በመዝለል ከዚያም
በሁለት እግራችን ማረፍ፡፡
• ወደ መጀመሪያው ቦታ በመመለስ ደግመን
መለማመድ፡፡
• ከ 3-5 ጊዜ በመደጋገም መለማመድ፡፡
ወደላይ በመዝለል በሁለት እግር ማረፍ

ምስል 5.2

57 57 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሐ. የሰውነት ሚዛን መጠበቅ

የሰውነት ሚዛን እንቅስቃሴ ሲሰራ በደንብ ተንቀሳቅሰን


እነድንሰራ ያግዘናል።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።


• አግዳሚ እቃ/አንጨት ላይ እጃችንን ወደ ጎን
በመዘርጋት መቆም።
• ሚዛን በመጠበቅ እስከ ጫፍ ለመሄድ መሞከር።
• በጥንቃቄ ደጋግሞ መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.3

መ. በእርዳታ እንደ እንቁራሪት መዝለል

ሁለት እጃችንን በሁለት እግራችን መሀከል በማድረግ


ቁጢጥ በማለት መቀመጥ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 58


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት


• በቆምንበት ቦታ ቁጢጥ በማለት ሁለት እጃችንን
በሁለት እግራችን መሀከል በማድረግ መሬት መያዝ
• የሰውነት ሚዛናችንን ጠብቀን በእጃችን መሬት
ሳንለቅ እግራችንን በማንሳት መዝለል፡፡
• በጥንቃቄ እየደጋገሙ መለማመድ፡፡
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.4 በእርዳታ እንደ እንቁራሪት መቀመጥ

59 59 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

5.2 ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ እና አሰፈላጊነት

ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት


ይህንን ርዕስ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ
• ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ እና አሰፈላጊነት
ተናገራላችሁ።
• ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ እና አሰፈላጊነት
ሰርታችሁ ታሳያላችሁ።
• ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ እና አሰፈላጊነት
ታደንቃላችሁ።

ተግባር 5.2

ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ ማለት ምን ማለት ነው?

ውስን የሰውነት እንቅስቃሴ ማለት ከአጠቃላይ የሰውነት


አካላት መኃል በተወሰኑት የሰውነት ክፍል ላይ ያነጣጠረ
ነው።

ሀ. ወደ ፊት መግፋት

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት


• ትክክለኛ አቋቋም መቆም።
• የሰውነት ሚዛን በመጠቀም ከጓደኛ ጋር በእጅ
መያያዝ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 60


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• ተራ በተራ እጅ በማጠፍ መገፋፋት።


• በጥንቃቄ ደጋግሞ መሰራት።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.5

ለ. ነጠላ ዘንግ ላይ እንቅስቃሴ ማድረግ

ነጠላ ዘንግ ላይ ሰውነትን ለማፍታታት ጡንቻን


ለማጠንከር የሚጠቅም እንቅስቃሴ ነው።

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።


• ትክክለኛ አቋቋም መቆም።
• ወደ ላይ በመዝለል ነጠላ ዘንግን መያዝ።
• ሰውነትን ወደ ፊት ወደ ኋላ ማወዛወዝ።
• ነጠላ ዘንጉን በመልቀቅ ወርዶ መሬት መቆም።
• ከ2-3 በመደጋገም መለማመድ።

61 61 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.6
ሐ. ወደ ላይ መሳብ

ወደ ላይ መሳብ ሰውነትን ለማፍታታት እና የእጅና


የትከሻ ጡንቻን ለማጠንከር የሚጠቅም እንቅስቃሴ ነው።
2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 62
የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።


• ነጠላ ዘንጉ መኃል ጠጋ ብሎ መቆም።
• ወደ ላይ በመዝለል ነጠላ ዘንጉን መያዝ።
• ሰውነትን ወደ ላይ መሳብና መመለስ።
• ዘንጉን በመልቀቅ ወርዶ በሁለት እግር መቆም።
• በመደጋገም መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.7

መ. መሄድ እና መጋለብ

መሄድ እና መጋለብ፦ ከመሄድ ወደ መጋለብ የሚደረግ


እንቅስቃሴ ነው።

63 63 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።


• ከተቆመበት ቦታ ከ20-25 ሜትር ከተሄደ በኋላ
እንቅስቃሴውን ወደ ሩጫ በመቀየር መሮጥ።
• በዝሁ መሰረት መሄድ____መጋለብ_____
መሄድ_____መጋለብ መስራት።
• በመደጋገም መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.8

ሠ. ወደ ላይ በመዝለል ጉልበት በማጠፍ ወደ


ደረት ማንሳት

ወደላይ በመዝለል ጉልበታችንን በማጠፍ ወደ ደረታችን


ማምጣት ወደ ቦታ በመመለስ የሚሰራ እነቅስቃሴ ነዉ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 64


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት


• ትክክለኛ የሆነ አቋቋም መቆም፡፡
• ሁለት እግርን በትከሻ ስፋት ልክ መክፈት፡፡
• እጃችንን ወደ ኋላ በማድረግ ጉልበታችንን ወደፊት
ማጠፍ፡፡
• ከቆምንበት ቦታ ላይ ወደ ላይ በመዝለል
ጉልበታችንን ወደ ደረታቸን በማምጣት ተመልሰን
መረፍ፡፡
• እየደጋገሙ መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.9 በሁለት እግር ወደላይ በመዝለል ጉልበታችንን በማጠፍ ወደ ደረታችን


ማምጣት

65 65 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ረ. በመዝለል ሁለት እግርን ወደፊት በመዘርጋት በእጃችን


የእግር ጣታችንን መንካት

ይህ እንቅስቃሴ በመዝለል ሁለት እግራችንን ወደፊት


በመዘርጋት በእጃችን የእግር ጣታችንን ለመንካት
መሞከር ነው፡፡

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት
• በምንሰራበት ቦታ ላይ መገኘት፡፡
• በቆምንበት እጃችንን ወደ ኋላ በመያዝ ጉልበታችንን
ወደፊት ማጠፍ፡፡
• ከቆምንበት ቦታ ላይ ወደ ላይ በመዝለል እግርችንን
ወደፊት በመዘርጋት በእጃችን የእግር ጣታችንን
መንካት፡፡
• እየደጋገሙ መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

ምስል 5.10 በመዝለል ሁለት እግራችንን ወደፊት በመዘርጋት በእጃችን


የእግር ጣታችንን መንካት፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 66


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

5.3 መሠረታዊ ጂምናስቲክስ


ተማሪዎች ቢያንስ መጎናፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት
ይህንን ርዕስ ተምራችሁ ስታጠናቅቁ፡፡
• መሠረታዊ ጂምናስቲክስ ምን እንደሆነ ትናገራላችሁ፡
• መሠረታዊ ጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ሰርታችሁ
ታሳያላችሁ፡፡
• መሠረታዊ ጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ተምራችሁ
የተጎናፀፋችሁትን ችሎታ ታደንቃላችሁ፡፡

ተግባር 5.3
1.መሠረታዊ ጅምናስቲክስ ምንድን ነው?

መሠረታዊጂምናስቲክስ ማለት በመሳሪያ እና የለመሳሪያ


የሚሰራ እንቅስቃ ነው፡፡

ሀ. ምንጣፍ ላይ መሮጥ
ምንጣፍ ላይ በመሮጥ የሚሰራ የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴ
ነው፡፡
የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት
• ከመነሻ ቦታ ላይ መገኘት
• የሰውነት ሚዛንን በመጠበቅ ዝግዛግ እየሰሩ ወደ
ፊት መሮጥ፡፡
• እየደጋገሙ መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።
67 67 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል
የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ለ. ምንጣፍ ላይ መቀመጥ እና መነሳት

ይህ እንቅስቃሴ መሬት ላይ በተነጠፈ ምንጣፍ ላይ


በመቀመጥ እና በመነሳት የሚሰራ ነው።

የልምምድ ዘዴ
• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።
• በሰልፍ ምንጣፍ ላይ መቆም።
• ምንጣፉ ላይ መቀመጥ መነሳት።
• እየደጋገሙ መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 68


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ሐ. በሙሉ አካል ምንጣፍ ላይ መገልበጥ

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማፍታታት።


• በሙሉ አካልምንጣፍ ላይ መተኛት።
• ወደጓን መገልበጥ።
• እየደጋገሙ መለማመድ።
• ሰውነት በማቀዝቀዝ ማጠናቀቅ።

69 69 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የምዕራፉ ማጠቃለያ

ጂምናስቲክስ ከሰውነት እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ


ሆኖ በመሳሪያ እና ያለመሳሪያ የሚሰራ ነው፡፡ ቀላል
ጂምናስቲክስ ያለመሳሪያ የሚሰራ ነው፡፡ ውስን የሰውነት
እንቅስቃሴ ማለት ከአጠቃላይ የሰውነት እንቅስቃሴ
በተወሰኑት ላይ ቢቻ ያተኮረ ነወ።

የምዕራፉ መልመጃ

|. ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ “እውነት”


ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡
1. ጂምናስቲክስ የሰውነት ሚዛን እና ቅንጅትን
የሚፈልግ እንቅስቃሴ ነው፡፡
2. ጂምናስቲክስ በመሳሪያ ብቻ የሚሰራ እንቅስቃሴ
ነው፡፡
||. ከዚህ በታች ላሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ
የያዘ ፊደል ምረጥ፡፡
1.በመሄድ እና መጋለብ ስር የሚመደብ የትኛው ነው?
ሀ. ሩጫ ለ. መሄድ ሐ. ዝላይ መ. ሁሉም

|||. ከዚህ በታች ላሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡

1. ጂምናስቲክስ ማለት ምን ማለት ነው?


2. በአንድ እግር መቆም በምን ዓይነት ጂምናስቲክስ
ስር ይመደባል።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 70


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ ስድስት
ተማሪዎቹ በሚኖሩበት አካባቢ ያሉ ባህላዊ ጭፈራዎች
እና ባህላዊ ጨዋታዎች
ከምዕራፉ የሚጠበቁ ውጤቶች
ተማሪዎች ከዚህ ምዕራፍ በኋላ፡-
• በአከባቢያችሁ የሚታወቁ የባህል ውዝዋዜ እና
ጨዋታን ትረዳላችሁ፡፡
• በህላዊ ውዝዋዜ እና ጨዋታ በጤና ላይ ያለውን
ድርሻ ታዳንቃላችሁ፡፡
• ሰውነትን ለማጎልበት የሚጠቅሙ ታዋቂ የባህል
ውዝዋዜ እና ጨዋታዎችን ትሰራላችሁ፡፡

መግቢያ

ባህላዊ ውዝዋዜ፦ በአንድ አከባቢ የሚገኘውን የባህል ዘፈን


በተለያየ መልክ ስውነትን በማወዛወዝ የሚከናወን ነው፡፡
ባህላዊ ጨዋታ የምንለው በአካባቢ የሚገኘውን መሳሪያ
በመጠቀም በመጫወት የአካባቢውን ባህል እና ልማድ
የሚያንፀባርቁበት ነዉ። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ባህላዊ
ውዝዋዜና በአካባቢያችሁ ያሉ ታዋቅ ባህላዊ ጨዋታዎችን
ትማራላችሁ፡፡

71 71 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

6.1 በተማሪዎች መኖርያ አከባቢ ያሉ ታዋቂ የባህል


ውዝዋዜ

ተማሪዎች ቢያንስ መጎነፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት


ተማሪዎች ርዕሱን ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-
• በምትኖሩበት አካባቢ የሚታወቁ የባህል
ውዝዋዜዎችን ትዘረዝራላች፡፡

• በምትኀኖሩበት አካባቢ የሚታወቁ የባህል


ውዝዋዜዎችን ሰርታችሁ ታሳያላች።

• በምትኖሩበት አካባቢ የሚታወቁ የባህል ውዝዋዜን


በሙዚቃ የሰማችሁትን ታደንቃላችሁ።

ተግባር 6.1

ጭፈራ እና ባህል ምን እንደ ሆነ ግለፁ።

ጭፈራ ከሙዚቃ ድምፅና ምት ጋር አብሮ የሚተገበር ሆኖ


የአንድን ማህበረሰብ ማንነት የሚገልፅ ነው።

ተግባር 6.2

1. በምትኖሩበት አካባቢ ያሉ ባህላዊ ጭፈራን አጥንታችሁ


ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ።

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 72


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

6.2 ተማሪዎች በሚኖሩበት አካባቢ ያሉ ባህላዊ ጨዋታዎች

ተማሪዎች ቢያንስ መጎነፀፍ ያለባቸው የመማር ብቃት


ተማሪዎች ርዕሱን ተምራችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፦
• በአካባቢያችሁ ያሉ ታዋቂ ባህላዊ ጨዋታዎችን
ትናገራላችሁ።

• በአካባቢያችሁ ያሉ ታዋቂ ባህላዊ ጨዋታዎችን


ተደንቃላችሁ።

ተግባር 6.3

1. በአካባቢያችሁ ያሉ ታዋቂ ባህላዊ ጨዋታዎችን


በመጫወት አሳዩ።

ባህላዊ ጨዋታ የአንድ ማህበረሰብ ማንነት እና ባህሉ


የሚገለፅበት ነዉ።

ለምሳሌ ትግል፣ ኮርቦ፣ ገበጣ የመሳሰሉት ናቸው።

ሀ. የኮርቦ ጨዋታ

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• ከእንጨት የተሰራ ክብና ክቡን የሚነዳበት ቆልማማ
እንጨት ማዘጋጀት፡፡
• ክቡን መሬት ላይ በመወርወር በቆልማማ እንጨት
እየገፉ ወይም እየነዱ መሮጥ፡፡

73 73 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• የሰውነት ሚዛን በመጠበቅ ፍጥነት እየጨመሩ መሄድ፡፡


• ክቡ ሳይወድቅ መንዳት
• ተራ በተራ መለማመድ፡፡

ምስል 6.1 ክብ ፒላስትክ /ጎማ ነገር ማሽከርከር

ለ. ‘‘በዚህ ልውጣ’’ አላስወጣም ጨዋታ

የልምምድ ዘዴ

• ሰውነትን በደንብ ማሟሟቅና ማሳሳብ፡፡


• ተማሪዎች እጅ ለእጅ በመያያዝና ክብ በመስራት
መቆም፡፡
• አንድ ተማሪ በመምረጥ መሀል ማስገባት፡፡
• መሀል የሚገባ/የምትገባው ተማሪ ‘‘በዚህ አስወጡኝ’’
ስል/ስትል ለሎች ተማሪዎች ‘‘አናስወጣም’’ በማለት
ይመልሳሉ፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 74


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

• መሀል ያለው/ያለችው ተማሪ የተማሪዎች እጅ


በማላቀቅ ወጥቶ መሮጥ፡፡
• ሁሉም ተማሪዎች እያባረሩ ለመያዝ መሞከር፡፡

ምስል 6.2. ‘‘በዚህ ልውጣ አናስወጣም’’ ጨዋታ

የምዕራፉ ማጠቃለያ

ባህላዊ ውዝዋዜ የተለየዩ አይነት የዘፈንና የውዝዋዜ


እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት ሆኖ ለአንድ ብሔር አክብሮት፣
እውቅና እና እሴትን ለመስጠት ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ ባህላዊ
ጨዋታዎች የአንድን ብሔር ማንነትና ባህሉን የሚገለፅበት
ጨዋታ ነው፡፡

75 75 የተማሪ መጽሐፍ 2ኛ ክፍል


የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የምዕራፉ መልመጃ
|. ከዚህ በታች ለተዘረዘሩ ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ “እውነት”
ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡

1. ባህላዊም ውዝዋዜ ለተማሪዎች የአካል ጥንካሬን


ይሰጣል፡፡
2. ባህላዊ ጨዋታዎች ለባህላዊ ስፖርት እንቅስቃሴ
አይጠቅምም፡፡

||. ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1. ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ውስጥ የባህላዊ ውዝዋዜ


ጥቅም የሆነው የቱ ነው?
ሀ. ለአብሮነት

ለ. የራስን ማንነትን ለመግለፅ

ሐ. እውቅና ለማግኘት

መ. ሁሉም መልስ ናቸው።

|||. ከዚህ በታች ላለው ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡

1. በአከባቢያችሁ ከሚጫወቱት ጨዋታዎች ውስጥ


ሁለቱን ጥቀሱ፡፡

2ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ 76

You might also like