You are on page 1of 116

የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የእይታና የትወና ጥበባት


የተማሪ መጽሐፍ

አንደኛ ክፍል

የ ደ ቡ ብ ብ ሔሮ ች ብ ረ ሰ ቦ ች ሕ ዝ ቦ ች ክ ል ል መን ግ ስ ት ት ምህ ር ት ቢ ሮ
I
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የእይታና የትወና ጥበባት


የተማሪ መጽሐፍ
አንደኛ ክፍል
አዘጋጆች፡-
ምንያህል በቀለ
ደግፌ ጌታቸው
ካሌብ ካሳ

ስዓሊ፡- ካሌብ ካሳ
ኖታ ቀራጭ፡- ምንያህል በቀለ
ኤዲተር ፡- አምዶም ገ/ዩሃንስ
ጥራት ተቆጣጣሪ፡- ተክለማሪያም ጥላሁን
ተዋበ ታደሰ
አፅዳቂ ፡- ሲዳሞ ሳልስ
ቅድስት ደፋር
ዋንቱሳ ጎንሳ
ይመኙሻል ዩሱፍ
ሃብታሙ ጳውሎስ

የ ደ ቡ ብ ብ ሔሮ ች ብ ረ ሰ ቦ ች ሕ ዝ ቦ ች ክ ል ል መን ግ ስ ት
ት ምህ ር ት ቢ ሮ

I
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ማውጫ
ምዕራፍ አንድ .................................................................................................................................... 1
ምልከታ .............................................................................................................................................. 1
1.1. ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በማየት እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም ድርጊቶችን መናገር .......................... 2

1.2. ከውዝዋዜ ጋር የተዛመዱ ቀላል መዝሙሮችን መስማትና መመልከት .................... 10

1.3. ምስሎችን ፣እንቅስቃሴዎችን እና መልዕክቶችን ..................................................................... 13

1.4. ወፍራም እና ቀጭን ድምጽ መለየት ..................................................................................... 21

ምዕራፍ ሁለት ................................................................................................................................... 26


ፈጠራዊ ገለጻ ..................................................................................................................................... 26
2.1.የቤተሰብ አባላትን ተግባራት አስመስሎ ...................................................................................... 27

2.2. መቸክቸክ ፣መስመር መለማመድ እና ማቅለም ......................................................................... 30

2.3.ስለ ቤተሰብ መዘመር ................................................................................................................ 44

2.4.ቀለል ባሉ ምቶች መወዛወዝ ...................................................................................................... 46

3.1.መዝሙሮች፣ቀለሞች፣ውዝዋዜዎች፣ተረቶች፣አፈ......................................................................... 51

ታሪኮች ፣እንቆቅልሾች እና ትወናዎች ................................................................................................. 51

ምዕራፍ ሦስት.................................................................................................................................... 51
ባህሎች .............................................................................................................................................. 51
3.2. በአካባቢያችን ያሉ ቀለሞች .................................................................................................. 67

ምዕራፍ አራት .................................................................................................................................... 76


ባህላዊ ክንዋኔዎችን ማድነቅ................................................................................................................ 76
4.2..አካላዊ እንቅስቃሴ .................................................................................................................. 93

ምዕራፍ አምስት .............................................................................................................................. 95


ጥበባዊ ትግበራ ማቅረብ .................................................................................................................. 95
5.1. የህብረት ጨዋታዎች ................................................................................................................ 96

5.2. በህብረት መዘመር ................................................................................................................... 97

5.3. ስለ ተፈጥሮ ሃብት እና በዙሪያችን ስላሉ የተፈጥሮ ቀለሞች ......................................................... 98

II
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ አንድ
ምልከታ

መግቢያ

ምልከታ የተለያዩ ድርጊችን ከአካባቢያችን እንዲሁም


ከተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች እንዲሁም ምስሎች
በመመልከት ፣ በማዳመጥ መልዕክቶችን የምንረዳበት
አንደኛው መንገድ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ ከተለያዩ
መልዕክት ማስተላለፊያዎች መልዕክቶችን እንረዳለን፡፡

ተማሪዎች ይሄንን ምዕራፍ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-

 የተለያዩ መዝሙሮችን ትዘምራላችሁ፡፡


 ምስሎችን ተመልክታችሁ መልዕክታቸውን መረዳት
ትችላላችሁ፡፡
 የድምጾችን ቅጥነት እና ውፍረት ትለያላችሁ፡፡

1
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.1. ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በማየት እንቅስቃሴዎችን


እንዲሁም ድርጊቶችን መናገር

በቴሌቭዥን ምስሎችን ከነ እንቅስቃሴያቸው እንዲሁም


ከድምጽ ጋር እንመለከታለን፡፡ እግር ኳስ ፣እሩጫ፣ሰዎች
ሙዚቃ ሲጫወቱ እንዲሁም ሌሎችን ተግባራትን
በቴሌቭዥን መመልከት እንችላለን፡፡

በፎቶ ፣በስዕል ደሞ ምስሎችን ብቻ ማየት እንችላለን፡፡


ፎቶ የምንለው የፎቶግራፍ መሳሪያን ተጠቅመን
የምናገኘውን ምስል ሲሆን ፣ስዕል ግን በእርሳስ በማቅለሚያ

እንዲሁም በተለያዩ ቁሳቁሶች ተጠቅመን በእጅ የሚሰራ


ነው፡፡

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ በኋላ ፡-የተለያዩ


እንቅስቃሴዎችን እና መልዕክቶችን በምስል እና በድምጽ
ትገነዘባላችሁ፡፡

 ተማሪዎች ከዚህ በፊት በቴሌቭዥን አይታችሁ


የወደዳችሁትን ነገር ለመምህራችሁ ተናገሩ?
 ከዚህ በፊት በሌሎች መጽሀፍት ስላያችሁት ስዕል
ወይም ፎቶግራፍ ተናገሩ?

2
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.1 .ልጆቹ ቴሌቭዥን ሲመለከቱ


 ልጆቹ በቴሌቭዥን ምን እየተመለከቱ ነው? ያያችሁትን
ተናገሩ፡፡

ምስል 1.2.
 ልጁ በቴሌቭዥን የሜዳ አህያ እየተመለከተ ነው፡፡
የሜዳ አህያ ባለ መስመር ጥቁር እና ነጭ የቆዳ
ቀለም እንዳለው አያችሁ ?

3
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.3.በምስሉ ልጅቷ ስታነብ እንመለከታለን

ምስል 1.4.
 እዚህ ምስል ላይ ልጆቹ ሲጫወቱ ይታያሉ እንደዚህ እጅ
ለእጅ ተያይዛችሁ የምትጫወቱት ጨዋታ አለ?
ጨዋታውስ ምን ይባላል?

4
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እንቅስቃሴ ያለባቸው ምስሎች

ምስል1.5. በስዕሉ ላይ ሰዎች ሲሮጡ እናያለን፡፡

ምስል 1.6 ልጁ ብስክሌት እየነዳ

5
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.7
 ከላይ በምትመለከቱት ምስል ላይ ልጁ ምን እያደረገ
ይታያችኋል?

ምስል 1.8

 ልጆቹ ምን ጨዋታ እየተጫወቱ ይመስላችኋል?

6
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.9
 ልጁ ምን እያደረገ ነው ?

ምስል 1.10 ሰውዬው ክራር እየተጫወተ

ክራር ባህላዊ የሀገራችን የሙዚቃ መሳሪያ ሲሆን 6


ወይም 5 ክር አለው ፡፡ ክራርን በግርፍ ወይም በድርድር
የአጨዋወት አይነት እንጫወተዋለን፡፡

 ሰዎች ምን የሙዚቃ መሳሪያ ሲጫወቱ አይታችኋል?


 የምትወዱት የሙዚቃ መሳሪያስ ምንድን ነው
ለመምህራችሁ ንገሩት

7
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እንቅስቃሴ የሌለባቸው ምስሎች

ምስል 1.11
ልጁ ቆሟል እየተንቀሳቀሰ አይደለም ፡፡

ምስል 1.12
 ውሻው ምን እያደረገ ነው ? እንቅስቃሴ አለው ?

8
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እንቅስቃሴ ያለባቸው እና የሌለባቸው ምስሎች

ምስል 1.13

ምስል 1.14

ምስል 1.15

9
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.2. ከውዝዋዜ ጋር የተዛመዱ ቀላል መዝሙሮችን


መስማትና መመልከት

ተማሪዎች በዚህ ርዕስ የተለያዩ እንቅስቃሴ ያላቸውን


መዝሙሮች በቡድን እና በግል ትዘምራላችሁ፡፡

መዝሙሮቹን በምትዘምሩበት እንዲሁም በቡድን


በምትጫወቱበት ጊዜ እርስ በእርስ በመረዳዳት መሆን
አለበት፡፡

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡-የተለያዩ መዝሙሮችን በግል


እንዲሁም በቡድን መዘመር ትችላላችሁ፡፡

 እስቲ ተማሪዎች አንድ የምታውቁትን መዝሙር


ዘምሩ?
ስምሽ ማን ነው
ስምሽ ማን ነው ሰብለ ወንጌል
የት ትማሪያለሽ? ጫሞ ትምህርት ቤት
መቼ ትመጪያለሽ ሰኞ ማታ
ምንይዤልሽ ቸኮላታ
ማርዬ ቻቻ ማርዬ ቻቻ ኦ እንጥሼ

10
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.16 ልጆ ማርዬ ቻቻ ሲጫወቱ

መሃረቤን ያያችሁ
ልጆች መሃረቤን ያያችሁ ሲጫወቱ ፡፡

ምስል 1.17
 መሃረቤን ያያችሁ ጨዋታ የምትጫወቱት በቡድን
ነው ወይስ ብቻ ለብቻ ?
11
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መዝሙር
መዝሙሩን ሰምታችሁ በህብረት ዘምሩ፡፡
እንማር
እንማር እንማር
እንመራመር
ለሀገር እንድንተርፍ
እንድንከበር

ምስል 1.18 ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ


 መዝሙሩ ምን ያስተምረናል ?
 በአካባቢያችሁ የምታውቁት መዝሙር አለ? ካለ
ለመምህራችሁ ዘምሩ?

12
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.3. ምስሎችን ፣እንቅስቃሴዎችን እና መልዕክቶችን

መረዳት
ምስሎች የተለያዩ መልዕክት ያስተላልፋሉ፡፡

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ በኋላ ፡-የተለያዩ ምልክት እና


ምስሎችን ትለያላችሁ፡፡

 እስቲ ተማሪዎች ከቤታችሁ ወደ ትምህርት ቤት


ስትመጡ መንገድ ላይ ምን ምልክት አያችሁ ?
ያያችሁትን ምልክት መምህራችሁ ሲጠይቃቹሁ
በየተራ ንገሩት፡፡

ምስል 1.19
ይሄን ምስል ስንመለከት ቆሻሻን በአግባቡ ለቆሻሻ

ማጠራቀሚያ በተዘጋጀ ቦታ ላይ ብቻ መጣል እንዳለብን

ይጠቁመናል፡፡

13
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.20
ይሄ ምስል እጃችሁን መታጠብ ንጽህናችሁን መጠበቅ
እንዳለባችሁ ያሳያል፡፡

ምስል 1.21
ምልክቱን መንገድ ላይ ተመልክታችሁ ታውቃላችሁ?

መንገዱ ላይ የተሰመረው መስመር ምን መልዕክት


ያስተላልፋል ?

14
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.22
 ይሄስ የምታዩት ምስል ምን መልዕክት ያስተላልፋል?

ምስል 1.23

 የትኛው የሴት የትኛው የወንድ ምስል እንደሆነ ለዩ፡፡


እንዴት አወቃችሁ በምን ለያችኋቸው?

ስለ ተመለከታችሁት ምስል ለአስተማሪያችሁ ተራ በተራ


ንገሩት ፡፡

15
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.24
 ልጆቷ ምን እያደረገች ይታያችኋል ?

ምስል 1.25

ዶክተሮች ህመምተኞችን ያክማሉ፣ይንከባከባሉ እንዲሁም


ምክር ይሰጣሉ፡፡

16
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.26
የህክምና ባለሙያዎች

ምስል 1.27
 ይሄስ የምን ባለሙያ ነው ?
 ሰላምታውን በማየት ሙያውን አዎቃችሁ ?
17
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.28፡ በምስሉ ላይ ባለታክሲው ሰውዬ መኪናውን


እየነዳ ይታያል፡፡

ባለታክሲ ሰዎችን ከቦታ ቦታ ያመላልሳል፡፡

 በእናንተስ አካባቢ ሰዎች ከቦታ ቦታ ለመሄድ ምን


አይነት ትራንስፖርት ነው የሚጠቀሙት?

18
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የተደበቁ ምስሎችን ማግኘት

ምስል 1.29
በስዕሉ ላይ የሚታየው ባቢ አሳ ለመያዝ እየሞከረ ነው፡፡
ግን አሳ ማግኘት አልቻለም፡፡አሳዎች ውሃ ውስጥ የሉም፡፡
አምስቱ አሳዎች የት ነው የሚገኙት?

19
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ከምስሉ ውስጥ ምን ይታያችኋል?

ምስል 1.30

ምስል 1.31
ስንት ወፎች ይታያችኋል?

20
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.4. ወፍራም እና ቀጭን ድምጽ መለየት

ድምጾች ሲሰሙ ወፍራም እና ቀጭን ሆነው


እንሰማቸዋለን፡፡ ሰዎች የተለያየ የድምጽ ቅጥነት እና
ውፍረት አላቸው ፡፡አንድ አንድ ሰዎች ድምጻቸው ወፍራም
ሲሆን የአንዳንዶች ደግሞ ቀጠን ይላል፡፡እንስሶችም
እንዲሁም አእዋፍትም የተለያየ የድምጽ ውፍረት እና
ቅጥነት አላቸው፡፡

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡-ቀጭን እና ወፍራም ድምጽ


ያላቸው እንሰሳትን እና አዕዋፋትን ትለያላችሁ፡፡

 ተማሪዎች በአካባቢያችሁ ካሉ እንሰሳት ሲጮህ


ወፍራም ድምጽ ያለው እንሰሳ ማን ነው?
ለመምህራችሁ በየተራ ንገሩት ::

ምስል 1.32.ልጁ በሬዲዮ ሙዚቃ እያዳመጠ ፡፡

21
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በሬዲዮ የተለያዩ መዝሙሮች ፣ዘፈኖች እንዲሁም የሰዎችን


ድምጽ ስንሰማ የድምጻቸውን ውፍረት እና ቅጥነትም
መለየት እንችላለን፡፡

 በሬዲዮ ለመስማት የምትፈልጉት ምንድን ነው ?


 በሬዲዮ የምን እንሰሳ ድምጽ ሰምታችሁ ታውቃላችሁ?
ድምጹስ ወፍራም ነበር ቀጭን?

ምስሉ 1.33
ብዙ ወፎች ሲዘምሩ ድምጻቸው ቀጭን ነው፡፡
ሁልጊዜ ለሊቱ ሊነጋ ሲል የወፎችን ድምጽ እንሰማለን፡፡
ንጋት ላይ ወፎች በቀጫጭን ድምጽ ሲዘምሩ እንዲሁም
የተለያየ ድምጽ ሲያወጡ መስማት የተለመደ ነው፡፡

22
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.34
የዝሆን ድምጽ ደግሞ በጣም ወፍራም ነው፡፡

ምስል 1.35 . ወፍ
 ወፎች ሲዘምሩ ሰምታችኋል ?
 የወፎች ሁሉ ዝማሬያቸው አንድ አይነት ነው ወይስ
ይለያያል?

23
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 1.36
አንበሳ ሲጮህ ወፍራም ድምጽ ነው
የሚያወጣው፡፡ሲጮህም ድምጹ ከእሩቅ መሰማት ይችላል፡፡

 ሌላ እናንተ የምታውቁት ወፍራም ድምጽ ያለው እንሰሳ


ማን ነው ?

24
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
በዚህ ምዕራፍ ተማሪዎች በተንቀሳቃሽ ምስል እንዲሁም
በምስል የተደገፉ ድርጊቶቸንና እንቅስቃሴዎችን
ተረድታችኋል፡፡
እንቅስቃሴዎችን የያዙ መዝሙሮችንም ዘምረናል፡፡
መዝሙርን ፣እንቅስቃሴን ፣ድርጊቶችን የሚያሳዩ ስዕሎች
እና ተንቀሳቃሽ ምስሎች በዚህ ምዕራፍ እየተመለከታችሁ
ለመምህራችሁ ነግራችኋል፡፡የድምጽ ውፍረትእና ቅጥነትንም
አውቃችኋል፡፡ ወፎች ሲዘምሩ ቀጭን ድምጽ እንዳላቸው
እንደ አንበሳ እና ዝሆን ያሉ እንሰሳት ደግሞ ድምጻቸው
ወፍራም እንደሆነ አውቀናል፡፡
መልመጃ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሀሰት በማለች
መልሱ፡፡
1.ውዝዋዜ በእንቅስቃሴ የሚገለጽ ድርጊት ነው፡፡
2.ምስሎች ወይም ምልክቶች መልዕክት ማስተላለፍ
ይችላሉ፡፡
3.መዝሙሮች መልዕክት የላቸውም፡፡
4.በመዝሙር መወዛወዝ ይቻላል፡፡
5. የበሬ ድምጽ ከድመት ድምጽ ይወፍራል፡፡

25
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ ሁለት
ፈጠራዊ ገለጻ

ስዕል፣ጽሁፍ ፣ትወና (ሚና መጫዎት)፣ሙዚቃ መጫዎት


፣ማቅለም እንዲሁም የተለያዩ ቅርጻ ቅርጾችን መስራት ጥበባዊ
ገለጻዎች ይባላሉ፡፡

ጥበባዊ ገለጻዎች ለልጆች የማወቅ ፍላጎትን በመጨመር ጥልቅ


ሰሜትን በማስረጽ የፈጠራ ችሎታቸውን ያሳድጋል፡፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-

 የተለያዩ ሚናዎችን በትወና ጥበብ ማሳየት ትችላላችሁ


 የተለያዩ መስመሮችን እና ቀላል ቅርጾችን መሰራት
ትቸላላችሁ
 ስለ ቤተሰብ የሚያስተምሩ መዝሙሮችን ትዘምራላችሁ
 ቀላል የውዝዋዜ እንቅስቃሴዎችን ትቻላላችሁ

26
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.1.የቤተሰብ አባላትን ተግባራት አስመስሎ

መጫወት

የቤተሰብን አባል ወይም ሌላ ተግባርን አስመስሎ መጫወት


ሚና መጫወት (ትወና )ይባላል፡፡

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡- ሚና መጫወት (ትወና)


ምን እንደሆነ የቤተሰቦቻችሁን ተግባራት በማስመሰል
ታውቃላችሁ፡፡

 ተማሪዎቸ እስኪ የቤተሰቦቻችሁን የቤት ውስጥ


ተግባራት ተናገሩ?
 እቤታችሁ ውስጥ ምግብ ማን ነው የሚያበስለው
ቤቱንስ ቀለም የሚቀባው ማን ነው ?

የቤተሰብ አባላት

እናት፣አባት፣እህት፣ወንድም፣አጎት፣አክስት፣አያት

ምስል 2.1. እናቶች ምግብ ሲያበስሉ


27
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ቤተሰቦቻችን የተለያየ ስራ በቤት ውስጥ እንዲሁም በስራ


ቦታቸው ይሰራሉ፡፡ በቤት ውስጥ ምግብ ያበስላሉ፣ቤት
ያጸዳሉ ፣ልብሶች ያጥባሉ እንዲሁም የተለያየ ሰራ
ይሰራሉ፡፡

ከቤተሰብ አባላት ተግባሮች ውስጥ ልጆችን መንከባከብ


አንዱ ተግባር ነው፡፡

ተማሪዎች ቤተሰቦቻችሁ እናንተን እንዲሁም ወንድሞቻችሁን


፣እህቶቻችሁን እንዴት እንደሚንከባከቡ አስተማሪያችሁ
በሚያሳያችሁ እና በሚነግራችሁ መሰረት አስመስላችሁ
አሳዩ፡፡

ምስል 2.2.ቤተሰቦች እናት ፣አባት እና ልጆች


28
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 2.3.አባት በእርሻ ስራ ላይ ፡፡

ምስል 2.4.እናት ልጇን ጡት እያጠባች


29
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

አባት እርሻ ያርሳል፣ልጆቹን ይንከባከባል፡፡

እናት ጥጥ ትፈትላለች፣ምግብ ታበስላለች፣ልጆቿን


ትንከባከባለች፡፡

ቤተሰብ ውስጥ የልጆች ተግባር ትምህርት ይማራሉ፣


ቤተሰቦቻቸውን በቀላል ስራዎች ላይ ማገዝ፡፡

2.2. መቸክቸክ ፣መስመር መለማመድ እና ማቅለም

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡- እጃችሁን ለማፍታታት


ችክቸካዎችን ትለማመዳላችሁ እንዲሁም የተለያዩ
መስመሮችን መስራት ትችላላችሁ፡፡ የቅርጾችን ውስጠኛ
ክፍል ማቅለም ትችላላችሁ፡፡

 ተማሪዎቸ እስኪ ወረቀት ላይ የፈለጋችሁትም ምስል


ስሩ ?

በቀለም እርሳሶች የተቸከቸኩ ምስሎች

ምስል 2.5

30
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.2.1.ሶስት አይነት ችክቸካዎችን መለማመድ


መቸክቸክ ማለት በእርሳስ እንዲሁም በሌላ መጻፊያ እጅን
ወደ ፈለጉት አቅጣጫ በማስኬድ የተለያዩ መስመር መሰል
እና እጥፋቶች መስራት ማለት ነው፡፡

ልጆች መቸክቸክ እጃችሁ በደንብ ስዕል ለመሳል ፣ለመጻፍ


እንዲፍታታ ያደርግላችኋል፡፡

 ችክቸካ ማለት ምን ማለት እንደሆነ ለመምህራችሁ


ተናገሩ?

ከዚህ በታች ያሉትን አይነት ችክቸካዎች በደብተሮቻችሁ


ላይ ተለማመዱ

I. ወደ ጎን (አግድሞሽ )መቸክቸክ

II. ወደ ታች የሚወርድ መቸክቸክ

31
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

III. ክብ መስመሮችን በሚሰራ መልኩ መቸክቸክ

ልጆች ሶስቱንም ችክቸካ ለይታችሁ ከተለማመዳችሁ በኋላ


ሶስቱንም በአንድ ላይ በማድረግ ችክቸካውን ተለማመዱ፡፡
2.2.2.. የመስመር አይነቶች
ቋሚ መስመር
ከላይ ወደ ታች የሚወርድ ቀጥ ያለ መስመር

አግድም መስመር
ከመሬት ጋር ትይዩ የሚሄድ መስመር (ከግራ ወደ ቀኝ
ወይም ከቀይ ወደ ግራ የሚሰመር ቀጥ ያለ መስመር)

32
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሰያፍ መስመር
ቀጥ ያለ ሆኖ በግማሽ የወደቀ መስመር

ታጣፊ ወይም ቆልማማ መስመር


የክብ መስመር ተቆርጦ የወጣ መሳይ መስመር

ዚግዛግ መስመር
የሰያፍ መስመሮች ስሪት ሲሆን የተቆራረጠ ውጣ
ውረድን የሚያሳይ መስመር ነው

33
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሞገዳማ መስመር
ቆልመም ባለ መታጠፊያ ከፍ ዝቅ የሚል መስመር

ሽክርክር መስመር
ደጋግሞ የሚዞር መስመር ነው፡፡

34
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ከዚህ በታች ያሉትን መስመሮች ተለማመዱ


ያልደመቁትን መስመሮች ማድመቅ፡፡ይሄንን ልምምድ በሌላ
መለማመጃ ደብተራችሁ ላይ ተለማመዱ፡፡

መስመሮችን በመጠቀም ቅርጽ መስራት

35
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መስመሮችን በተለያየ ነገር ላይ እንመለከታቸዋለን


፡፡አንድ ሰው ሲቆም ቀጥ ያለ መስመር ይሰራል፡፡

ምስል 2.7

ምስል 2.8
ሰው ሲተኛ ደሞ አግድም መስመር ይሰራል፡፡

36
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

 ከታች የምትመለከቷት ልጅ ምን አይነት መስመር ነው


የሰራችው?

ምስል 2.9

በችክቸካ እና በመስመር ስዕል መለማመድ

ምስል 2.6.በችክቸካ የተሳለ ስዕል

37
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.2.3.ቅርጾች
ልታውቋቸው የሚገቡ ቅርጾች፡፡
እኩል አራት ማዕዘን ቅርጽ
በአራቱም ጎን ያሉ መስመሮች እኩል ልኬት ይኖራቸዋል

አራት ጎን ያለው ቅርጽ


አራት ጠርዝ ያለው ቅርጽ ነው፡፡ ቋሚ እና አግዳሚው
መስመር እኩል ልኬታ የላቸውም፡፡

38
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ክብ ቅርጽ

ሞላላ ቅርጽ
እንደ እንቁላል አይነት ሞለል ያለ ክብ ቅርጽ መሳይ ነው፡፡

ሶስት ጎን ያለው ቅርጽ


ሶስት መዐዘን ቅርጽ ሶስት ጠርዞች ያሉት መስመር ነው፡፡

39
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

አምስት መዐዘን የያዘ ቅርጽ


አምስት ጠርዞች ያሉት ቅርጽ ነው፡፡

የኮከብ ቅርጽ
የከዋክብት ቅርጽ በጨለማ ከሰማይ ላይ የምናያቸው ኮከቦች
አይነት ቅርጽ ነው፡፡

የምናያቸው ነገሮች ብዙዎቹ የራሳቸው ቅርጽ አላቸው፡፡


ለምሳሌ ሳጥን አራት ማዕዘን አለው፡፡

ምስል .2.10

40
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.2.11
እንቁላል ደሞ ሞላላ ቅርጽ አለው፡፡

ምስል 2.12
ኳስ ክብ ቅርጽ አለው፡፡
ከኳስ ሌላ ክብ ቅርጽ ያላቸውን ነገሮች ለመምህራችሁ
ተናገሩ?
እንዲሁም ከሳጥን ሌላ አራት መዕዘን ያላቸውን ነገሮች
ተናገሩ?
41
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ነጥቦችን በመጠቀም ቅርጾችን እና መስመሮችን መስራት


አግድም ቀጥ ያለ መስመር አሰራር
ሁለት ነጥቦችን ማስቀመጥ፡፡ሁለቱ ነጥቦችን በመስመር
ማገናኘት

• •
• •

አራት መዐዘን አሰራር


አራት ነጥቦችን ማስቀመጥ ፡፡ነጥቦችቹን ቀጥ ባለ መስመር
ማገናኘት፡፡

• •
• •

42
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.2.4. ቅርጾችን ማቅለም


ተማሪዎች ከታች እንደምትመለከቷቸው አይነት ቅርጾችን
መሃለኛውን ክፍል ማቅለም ትለማመዳላችሁ፡፡በእርሳስ
፣በእስክርቢቶ ወይም ቀለም ባላቸው መጻፊያዎች ማቅለም
ትችላላችሁ፡፡ ተማሪዎች ማቅለም ያለባችሁ መጽሃፋችሁ
ላይ ሳይሆን ሌላ መለማመጃ ደብተራችሁ ላይ ነው፡፡

43
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

2.3.ስለ ቤተሰብ መዘመር

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡- የተለያዩ ስለ ቤተሰብ


የሚናገሩ መዝሙሮችን መዘመር ትችላላችሁ፡፡

 ተማሪዎቸ እስኪ የምታውቁትን መዝሙር


ለመምህራችሁ ተናገሩ?

ስለ አባት ፣እናት፣ እህት፣ ወንድም የተዘመሩ መዝሙሮችን


ትዘምራላችሁ፡፡

ምስል 2.13

እወዳችኋለሁ
አባ…….ቴ
እና……ቴ
ወንድሜ እህቴ
እውዳችኋለሁ ከራሴ አብልጬ

 ከላይ ያለው መዝሙር ስለ ምንድን ነው የሚነግረን?

44
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ወንድሜ ያዕቆብ

ወንድሜ ያእቆብ
ወንድሜ ያዕቆብ
ተኝተሃል ወይ
አትነሳም ወይ
ደውል ተደወለ
ደውል ተደወለ
ተነሳ ተነሳ
እህቴ የሺ
እህቴ የሺ
ተኝተሻል ወይ
አትነሺም ወይ
ደውል ተደወለ
ደውል ተደወለ
ተነሺ ተነሺ

ስለወንድሞቻችን ስለ እህቶቻችን የሚናገር መዝሙር


በመቀጠል እንዘምራለን፡፡ መምህራችሁ መዝሙሩን
ከዘመሩላችሁ በኋላ እናንተ ተከትላችሁ ዘምሩ፡፡

45
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እንዴት ነሽ
.
.
የወንድሜ የእህቴ ጓደኛ
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ንገሪኛ

እናቶች ልጆቻቸውን ሲያስተኙ አይታችኋል ዜማውንስ


ታውቁታላችሁ ?

እሹሩሩሩ
እሹሩሩሩ እሹሩሩሩ
የማሙዬ እናት ቶሎ ነይለት
ወተቱን በጉያ
ዳቦውን ባህያ
ይዘሽለት ነይ እሹሩሩሩ
2.4.ቀለል ባሉ ምቶች መወዛወዝ

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡- ቀለል ባሉ ምቶች


መንቀሳቀስ እና የተለያዩ መዝሙሮችን በውዝዋዜ መግለጽ
ትችላላችሁ፡፡

 መምህራችሁ በሚሰጣችሁ ቀላል ምቶች ከመዝሙሮች


ጋር ተወዛወዙ፡፡

46
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 2.14

እግሮቻችን እና እጆቻችን ከጓደኞቻችን እርስ በእርስ


በማነካካት የተለያየ ጨዋታ መጫወት እንችላለን፡፡
እግሮቻችንን እንዲሁም እጆቻችንን በማጋጨት ከመዝሙር
ጋር የምንጫወታቸው ጨዋታዎች አሉ፡፡

በሁለቱ እጆቼ ቸብ ቸብ ቸብ
በእግሮቼ ጣቶች ትም ትም ትም
በሁለቱ ጣቶቼ ቀጭ ቀጭ ቀጭ
በሁለቱ እግሮቼ እንጣጥ እንጣጥ እንጣጥ
እላለሁ እጫወታለሁ
እላለሁ እጫወታለሁ
እስኪ እናንተ የምታውቁት ጨዋታ ምንድን ነው?

47
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 2.15

ሸረሪቷ ቀስ በቀስ

ሸረሪት ቀስ ብላ በድሯ ላይ ወደ ላይ ስትወጣ በእጃችሁ


እንቅስቃሴ እያሳያችሁ የምትዘምሩት መዝሙር፡፡

ምስል 2.16

48
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ሸረሪቷ….ቀስ በቀስ…

ቀስ በቀስ …….

ወደ ላይ ወጣች

ንፋሱ መጥቶ……..

ወደ ቀኝ ወደ ግራ አደረጋት

ድንብሽ ለድንብሽ

ድንብሽ ለድንብሽ ድንብሽ ኖራ

ኖራ መስኮራ መስኮርኮርኪ

ኮርኪ ሰላሌ ስላሌንቦ

ሌንቦ ክፍሌ ሌንቦ

ክፍሌ ላንቃ

ምስል. 2.17.ልጆች ድንቡሽ ለድንቡሽ ሲጫወቱ

49
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መልመጃዎች
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጡ፡፡

1. ይህ መስመር ምን መስመር
ይባላል፡፡

ሀ. አግድምለ. ቀጥታሐ. ዚግዛግ

2. ከሚከተሉት ቅርጾች ውስጥ ሞላላ ቅርጽ የትኛው


ነው፡፡

ሀ. ለ. ሐ.

3. ህጻን ልጅ ለማስተኛት የማባበያ መዝሙር የትኛው


ነው?

ሀ. እሹሩሩሩ ለ.ወንድሜ ያዕቆብ ሐ.እንማር

4.ከነዚህ ቅርጾች ውስጥ ውስጡ የተቀባው የትኛው ነው

ሀ. ለ. ሐ.

50
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ ሦስት
ባህሎች

አካባቢ እና ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ጥበቦች

ባህል ማለት የህዝቦች ልማድ፣ የአመጋገብ፣የአለባበስ፣ የሙዚቃ፣


የውዝዋዜ ሰርዓት ነው፡፡ በሀገራችንም የተለያዩ ውብ ባህሎች
ይገኛሉ፡፡ የተለያዩ ባህሎችን በተረቶች፣ በአልባሳቶች፣ በውዝዋዜዎች
፣በእንቆቅልሾች መማር እንችላለን፡፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-

 የተለያዩ ተረቶችን ፣እንቆቀልሾችን እንዲሁም


አፈታሪኮቸን ታውቃላችሁ
 የተለያዩ የባህል ውዝዋዜዎችን መለየት ትችላላችሁ
 በአካባቢያችሁ ያሉ ቀለማትን መለየት ትችላላችሁ
3.1.መዝሙሮች፣ቀለሞች፣ውዝዋዜዎች፣ተረቶች፣አፈ
ታሪኮች ፣እንቆቅልሾች እና ትወናዎች
3.1.1.ተረቶች
ተረት ማለት ስለ ተለያዩ ነገሮች የሚነግረን የሚያስተምረን
ታሪክ ማለት ነው፡፡

51
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡-የተለያዩ ተረቶችን


ታውቃላችሁ፡፡

 እስቲ ተማሪዎች አንድ የምታውቁትን ተረት


ለመምህራችሁ ንገሩት?
ተረት- 1

ቀበሮ እና አውራ ዶሮ
አንድ ቀን አንድ ቀበሮ ምግብ ፍለጋ ወደ ሰዎች መኖሪያ
መንደር መጣ፡፡በመንደሩ አንድ አውራ ዶሮ አንድ ድንጋይ
ላይ ቆሞ ኩሉሉ …….እያለ ሲጮህ ቀበሮው ሰማና ወደ
አውራ ዶሮ ቀረብ ብሎ

“ሰላም ላንተ ይሁን ወንድሜ አውራ ዶሮ እንደምን ዋልክ”


አለው::

አውራ ዶሮውም“ የዶሮ አምላክ ይመስገንና ሰላም ነኝ” ሲል


መለሰ፡፡ቀበሮም ቀጠል አድርጎ፣

“ወንድሙ አውራ ዶሮ ከእሩቅ ሆኜ ድምጽህን ስሰማ ደስ


የሚል መሆኑን ተረዳሁ፡፡በእርግጥም ድምጽህ በጣም ደስ
ይላል፡፡ ወደዚህም የመጣሁት ቀረብ ብዬ ብሰማው እንዴት
ደስ እንደሚል ለማረጋገጥ ነውና ፣እስቲ እባክህ አንዴ
ቀረብ በለኝና አሰማኝ” ሲል ለመነው::

52
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል. 3.1

አውራ ዶሮውም በቀበሮው ሙገሳ እጅግ በጣም ተደሰተ


ወዲያውም ወደ ቀበሮው ቀረብ በማለት ጎንበስ ቀና አለና
አይኑን ጨፍኖ ኩኩሉሉ…ኡኡ….ብሎ ሳይጨርስ ቀበሮውም
ዘሎ የዶሮውን ክንፍ ጭምድዶ ይዞ ወደ ዋሻው ይዞት
መሮጥ ጀመረ፡፡

እረኞችም ቀበሮ ዶሮውን ይዞት ሲሮጥ አይተው ኖሮ ከኋላ


እየተከተሉ ያሳድዱት ጀመር፡፡በዚህ ጊዜ አውራ ዶሮ አንድ
መላ መጣለት፡፡

“ይህውልህ ወዳጄ ቀበሮ እረኞች ዶሯችንን ወሰደ እያሉ


እየሮጡ ነው ፡፡ተከታትለው መጥተው እንዳይደበድቡህ ፡፡
የእናንተ ዶሮ አይደለም በላቸው” ሲል ዶሮው ቀበሮውን
መከረው፡፡

53
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ቀበሮውም እውነት መስሎት ወደ እረኞቹ ዞሮ ፣

“እናንተ እረኞች ዶሮው የእናንተ አይደለም የኔ ነው” ሲል


፡፡ አውራ ዶሮውም ከቀበሮው አፍ አፈትልኮ በመሮጥ
አንድ ዛፍ ላይ ወጥቶ ቁጭ አለ፡፡ ከዛም ዶሮው ቀበሮውን
ቁልቁል እየተመለከተ

“ይሄውልህ ወዳጄ ቀበሮ በአለም ላይ አንተ ብቻ ብልጥ


የሆንክ እንዳይመስልህ፡፡ በብልጠት ማታለል የጥሩ ስነ
ምግባር ድርጊት አይደለም እሺ፡፡” ሲል ተናግሮ ከዛፉ
ላይ ዘሎ በመውረድ አመለጠ፡፡

ምስል .3.2

 አሁን ካነበባችሁት ተረት ምን ተማራችሁ?


 በተረት ውስጥ ያሉት እነማን ናቸው ?

54
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ተረት -2
አንበሳ እና አይጥ

አንድ ወቅት የእንስሶች ንጉስ የነበረ አንድ አንበሳ በጫካ


ውስጥ ይኖር ነበር፡፡

ከእለታት አንድ ቀን ይህ አንበሳ ምግቡን ፍለጋ ከጫካ


ውስጥ ሲዘዋወር አንዲት አይጥ አገኘ፡፡ አይጧንም አግኝቶ
ሊበላት ሲል “አያ አንበሳ እባክህ አትብላኝ” አለችው፡፡አያ
አንበሳም “ዛሬ እርቦኛል አንቺን ካልበላሁ ታዲያ ምን
ልብላ?” ሲል ተናገረ፡፡

አይጧም “የዛሬን ማረኝ እንጂ አንድ ቀን ውለታህን


እመልሳለሁ” አለችው፡፡ አንቺ በአካልሽ ትንሽ ነሽ እንዴት
ለእኔ ውለታ ትመልሻለሽ አላት፡፡ የዛሬን ማረኝ እንጂ አንድ
ቀን ውለታህን እመልሳለሁ አለች፡፡

ምስል .3.3

55
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

አንበሳው እየሳቀ “በይ ለዛሬ ሂጂ” ብሎ አዘነላትና


ለቀቃት፡፡አይጧም እየሮጠች ከፊቱ ሄደች፡፡ አንበሳውም
የወደቀ ስጋ አገኘና በልቶ ረሃቡን አስታገሰ፡፡

ከጥቂት ጊዚያት በኋላ አንበሳው የሚበላ ስጋ ፍለጋ


በጫካው ውስጥ ሲዘዋወር ድንገት አዳኞች የአዘጋጁት
የገመድ ወጥመድ ውስጥ ገባ ፡፡

ምስል .3.4

አንበሳው ቢታገል ቢታገል ገመዱን መፍታት አልቻለም፡፡


ያን እለት አይጥ በአጋጣሚ መንገድ ስታልፍ አንበሳ ታስሮ
አየች፡፡ ወደ አንበሳውም በመቅረብ “አያ አንበሳ አሁን
ገመዱን ቆርጬ ከገባህበት ገመድ አስወጣሃለሁ፡፡”

56
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.3.5

የአይጥ ጥርስ ጠንካራ እና ብዙ ነገር መቁረጥ የሚችል


ስለሆነ አይጧ ገመዱን በፍጥነት ቆርጣ ጣለችው፡፡
አንበሳውም ነጻ ወጣ ፡፡ አንበሳውም ውለታህን እመልሳለሁ
ያለችውን አስታውሶ በጣም ተገረመ፡፡አይጧን አመስግኗት
በሰላም ወደ ቤቱ ሄደ፡፡

ልጆች ከተረቱ መልካም ነገር ማድረግ ቆይቶ የሚጠቅመው


ለራስ እንደሆነ ተማራችሁ?

57
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እንቆቅልሽ ጨዋታ

ልጆች እንቆቅልሽ ጨዋታ በቡድን ሆናችሁ የምትጫወቱት


ጨዋታ ነው፡፡

በጨዋታው ጠያቂ እና መላሽ ይኖራል፡፡ጠያቂ እንቆቅልሽ


ብሎ ይጀምራል፡፡

መላሽ ምን አውቅልህ ብሎ ይመልሳል፡፡ ከዛ ጠያቂው


ጥያቄውን ይጠይቃል፡፡

እንቆቅልሽ

እንቆቅልሽ በጥያቄና መልስ ድብቅ ሃሳቦችን በጨዋታ


መልክ የምንማርበት ዜዴ ነው፡፡

እንቆቅልሽ ጨዋታ የሚጫወቱት ጠያቂ እና ጥያቄውን


የሚመልስ ሰው በመሆን ነው፡፡

 መጀመሪያ ጠያቂው ምን ብሎ ይጀምራል ? ከዛስ መላሽ


ምን ይላል የሚለውን ለመምህራችሁ ተናገሩ፡፡

58
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

1.የእንቆቅልሽ ጨዋታዎች

1.ትልቁ አዞ ተጠማዞ

2.አራት እግር አለው ወንዝ የማይሻገር

3.ከቁርስ በፊት የማይበላ

4.ጸጉሯን አበጥራ ገበያ የምትወጣ

5.ከመብላታችን በፊት የምንሰብረው

6.እናትየው ጥቁር ለጆቿ ነጫጭ

7.ገላዬ ብርቱካናማ ኮፍያዬ አረንጓዴ እኔ ማን ነኝ

8.ወጣት ሳለሁ እረዝማለሁ ሳረጅ አጥራለሁ እኔ ማን ነኝ

9.በራሴ አፍ የለኝም ግን ሰዎች የተናገሩትን እደግማለሁ

10.ንጹህ ሲሆን የሚጠቁር ሲቆሽሽ ነጭ የሚሆን

11.ላዩ በድን ታቹ በድን መሃሉ ነፍስ አድን

12.ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ

59
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3.1.2. ውዝዋዜዎች
በሃገራችን የተለያዩ አይነት ውዝዋዜዎች አሉ፡፡ወዝዋዜዎች
ስለ ሰዎች ባህል የምናውቅበት አንዱ ዘዴ ነው፡፡በሃገራችን
የተለያዩ ባህሎች አሉ እነዚህም ባህሎች የተለያየ የሙዚቃ
ምት እና የአጨፋፈር ስርዓት አላቸው፡፡

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡-የተለያዩ ውዝዋዜዎችን


ትመለከታላችሁ፡፡እንዲሁም ውዝዋዜዎቹን በጥቂቱ
ትወዛወዛላችሁ፡፡

 እስቲ ምታውቁትን የባህል ውዝዋዜ አሳዩ ?


 በአካባቢያችሁ ያለው ምን አይነት ውዝዋዜ ነው?

በቴሌቭዥንስ ምን አይነት ጭፈራ ወይም ውዝዋዜ


ተመልክታችኋል?

ምስል 3.6

60
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በሃገራችን ከሚገኙ ውዝዋዜዎች ውስጥ ጥቂቱን ከታች


በምስሉ ተመልከቱ፡፡ ምስሉ ላይ ከውዝዋዜው በተጨማሪ
የባህሉን አለባበስም ይዟል፡፡እንደ ባህሉ ጭፈራ የአለባበስ
ስርዓቱም እንደ አካባቢው የተለየ ነው ፡፡

ምስል 3.7 የጋሞ ማህበረሰብ ባህላዊ ጭፈራ

ምስል 3.8 የኛንጋቶም ማህበረሰብ ባህላዊ ጭፈራ


ተማሪዎች በዚህ ጭፈራ ላይ አለባበሳቸውን አያችሁ?
61
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 3.9. የኮንሶ ማህበረሰብ ጭፈራ

ምስል 3.10. የደራሼ ማህበረሰብ ጭፈራ


እንደዚህ አይነትስ ጭፈራ ተመልክታችሁ ታውቃላችሁ?

62
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 3.11 የጉራጌ ማህበረሰብ ባህላዊ ጭፈራ


 ይሄስ ጭፈራ በአካባቢያችሁ ካለው ጭፈራ ጋር
ይመሳሰላል ወይስ ይለያል?አለባበሳቸውንስ አያችሁ ?

ምስል 3.12 የሱማሌ ማህበረሰብ ጭፈራ

63
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል .3.13 ኦሮሞ ማህበረሰብ ጭፈራ

ምስል 3.14 የአማራ ማህበረሰብ ጭፈራ

ተማሪዎች መምህራችሁ በሚያሳያችሁ መሰረት የተለያዩ


ጭፈራዎችን በቡድን እንዲሁም በግል ተለማመዱ ፡፡

64
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3.1.3.መዝሙሮች
ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡-የተለያዩ መዝሙሮችን
መዘመር ትችላላችሁ፡፡

እስቲ ምታውቁትን መዝሙር ዘምራችሁ ለመምህራችሁ


አሰሙ ?

የሚከተለውን መዝሙር መምህራችሁ በሚሰጣችሁ ዜማ


መሰረት ዘምሩት ፡፡
ዝናብ ሂድልኝ
ዝናብ ሂድልኝ ነገ ተመለስልኝ
ዝናብ ሂድልኝ ዛሬ ጨዋታ አለብኝ

ምስል .3.15

65
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ቡደን ጨዋታ ከመዝሙር ጋር ፡፡

ልጅ ለመፈለግ መጥተናል ዛሬ በማለዳ


ልጅ ለመፈለግ መጥተናል ዛሬ በማለዳ
ማንን ትፈልጋላችሁ ዛሬ በማለዳ
ሚሚን እንፈልጋታለን ዛሬ በማለዳ
እሷን መጥቶ የሚወስዳት ማን ጎበዝ አላችሁ
እሷን መጥቶ የሚወስዳት አቡሻ አለና
የኛ ልጅ በርቺ በርቺ እንዳትረቺ
የኛ ልጅ በርታ በርታ እንዳትረታ

ምስል 3.16
66
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

3.2. በአካባቢያችን ያሉ ቀለሞች

አካባቢያች በተለያዩ ቀለሞች የደመቀ ነው፡፡ልብሳችን ፣የቤት


ግድግዳችን ፣የእንሰሳ ቆዳ ቀለሞች እና ሌሎችም ነገሮች
ሁሉ የራሳቸው አይነትቀለም አላቸው፡፡

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ ፡- የተለያዩ ቀለሞችን መለየት


ትችላላችሁ፡፡እንዲሁም የባንዲራ ቀለማትን የልብስ
ቀለማትን በስዕል ላይ ማቅለም ትችላላችሁ፡፡

ተማሪዎች እስቲ አጠገባችሁ የተቀመጠውን የጓደኛችሁን


የልብስ ቀለም ተናገሩ ?

ቀይቀለም ብርቱካናማ ቀለም

67
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ቡኒቀለም ሰማያዊ ቀለም

ቢጫ ቀለም

68
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ጎጆ

ምስል 3.17.ከውጪ ግድግዳው የተቀባ

ግድግዳው ላይ ምን አይነት ቀለም አያችሁ በሩ ላይስ ምን


አይነት ቀለም ይታያችኋል

ምስል .3.18

ከላይ ያለውን ምስል ግድግዳውን በቢጫ በሩን በቀይ


ጣራውን በጥቁር ቀለም አቅልሙ
69
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የአልባሳት ቀለም

ሰማያዊ ኮት

ቀይ ቁምጣ አረንጓዴ ካኒቴራ

ቢጫ ቀሚስ

ምስል .3.19
 ልጆች የለበሳችሁት ልብስ ምን አይነት ቀለም አለው?
 የአባታችሁ ፣የእናታችሁ የልብስ ቀለም ምን አይነት
ነው?

70
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል .3.20

ሱሪና ሹራባችሁ የናንተስ ምን አይነት ቀለም ነው ?እስቲ


ከታች ያለውን ሱሪ እና ሹራብ በሌላ ወረቀት ላይ
በራሳችሁ ልብስ አይነት ቀለም ቀቡ፡፡

ምስል .3.21

71
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የለበሳችሁትን የቀሚስ ቀለም አይነት በመቀባት


ተለማመዱ ፡፡

ምስል 3.22

ስንደቅ ዓላማ

ምስል.3.23

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ


ተማሪዎች የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት ምን ምን ናቸው?

72
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ከታች በተሰጠው የባንዲራ ምስል መሰረት በሌላ ወረቀት


ቀለማቱን ፡፡

ምስል .3.24

የባህል አልባሳት ቀለም

ምስል 3.25

73
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.3.26

ባህላዊ የሴቶች ቀሚስ ቀለማት

ምስል.3.27. የባህል ቀሚስ ቀለም

74
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል .3.28 የሃመር ወጣት ሴት


 ምን ምን አይነት ቀለም ከልብሷ ላይ አያችሁ?

የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሃሰት በማለት


መልሱ፡፡
1. የባህልአለባሳት የአንድን አካባቢ ባህል መግለጽ
ይችላሉ፡፡
2. በሀገራችን የተለያዩ የውዝዋዜዎች አይነቶች አሉ፡፡
3. ተረቶች መልካም ስነምግባርን ማስተላለፍ ይችላሉ፡፡
4. የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ አንድ አይነት ቀለም ብቻ
ነው ያለው፡፡

75
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ አራት
ባህላዊ ክንዋኔዎችን ማድነቅ

ሀገራችን ላይ ብዙ ድንቅ ባህሎች አሉ ፡፡ የአመጋገብ፣


የአለባበስ፣ የአጨፋፈር፣ የቋንቋ እንዲሁም ሌሎች ብዙ
ባህሎች አሉ፡፡

 ልጆች በአካባቢያችሁ ሰርግ አይታችሁ ታውቃላችሁ?


 አይታችሁ የምታውቁ ከሆነ ከሰርጉ ላይ ምን ምን
አያችሁ ?
 ሽማግሌዎች የተጣሉትን ሰዎች ሲያስታርቁ
አይታችኋል ?

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-

 የተለያዩ ባህሎችን መልካም ባህሎችን ትገነዘባላችሁ፡፡


 ባህላዊ ተግባራት ፣ ውዝዋዜን እንዲሁም ሙዚቃን
ታውቃላችሁ፡፡
 ባህላዊ የሆኑ መዝሙሮችን ትዘምራላችሁ፡፡
 በምስሎች የተለያዩ ባህሎችን የቤት አሰራር
፣አልባሳት፣ ጌጣጌጦችን መለየት ትችላላችሁ፡፡

76
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.1.ባህልን የሚገልጹ መዝሙሮቸ ፣ውዝዋዜዎች ፣ሚና


መጫዎት እና ምስል
4.1.1. ስለ ባህል የሚናገሩ መዝሙሮች
እኛ ኢትዮጵያን ከሌላው አለም የተለየ የራሳችን የሆነ ባህል
እንዳለን አይታችኋል፡፡ከዚህም ውስጥ የራሳችን የሙዚቃ
ቅኝት እና የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጥቀስ ይቻላል ፡፡

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- የተለያዩ ባህልን የሚያወድሱ


መዝሙሮችን ትዘምራላችሁ፡፡ እንዲሁም የተለያዩ የባህል
የሙዚቃ መሳሪያዎችን ታውቃላችሁ፡፡

 ስለምታውቁት የባህል የሙዚቃ መሳሪያ ለመምህራችሁ


ተናገሩ ?

የሙዚቃ መሳሪያዎቹን በምስል ተመልከቱ ፡፡

ምስል.4.1- ከበሮ

77
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.4.2. .ክራር

ምስል .4.3.ማሲንቆ

78
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.4.4. በገና

ምስል.4.5. ዋሽንት

79
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.4.5. ፊላ

እኛም አለን ሙዚቃ


እኛም አለን ሙዚቃ ስሜት የሚያነቃ
እኛም አለን ሙዚቃ ስሜት የሚያነቃ
ከበሯችን
ቡም ቡም ቡም ቡም
ክራራችን
ታታታታ
ማሲንቋችን
ላላ ላላ
በገናችን
ቦም ቦም ቦም ቦም
4.1.1.ሚና መጫዎት
ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- በአካባቢያችሁ ያሉ ባህሎችን
በሚና መጫወት ትረዳላችሁ፡፡

እስቲ ከዚህ በፊት ያያችሁትን ሚና መጫዎት ተናገሩ ?

80
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የጋሞ አባቶች የእርቅ ስርዓት

ምስል .4.6
የጋሞ ሽማግሌዎች በሃገር ሰላም እንዲፈጠር በማድረግ
ይታወቃሉ፡፡

ተማሪዎች በቡድን በመሆን መምህራችሁ በሚሰጣችሁ


የሚና ጨዋታ መሰረት ትተውናላችሁ፡፡

ሰርጎችን ፣ባህላዊ ሽምግልናዎችን እንዲሁም የተለያዩ


የሃገራችን ባህሎችን አስመስላችሁ በቡድን ተጫወቱ፡፡

81
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የኮንሶ የእርከን ስራ

ልጆች በሃገራችን ብዙ ሚደነቁ ባህሎች አሉ ከነዚህም


ውስጥ አንዱ የስራ ባህል ነው፡፡

በኮንሶ ተራራማ አካባቢ አፈር በውሃ እንዳይታጠብ የእርከን


ስራ ይሰራል፡፡

የእርከን ስራ እንዴት እንደሚሰራ ከመምህራችሁ በማየት


የእርክን ስራን አስመስላችሁ በህብረት ስሩ፡፡

የተለያዩ ባለሙያዎችን መስሎ መጫወት

ምስል.4.7.ሀኪም

82
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 4.8

ልጅቷ እንደ ትራፊክ ሆና ስትጫወት፡፡

ትራፊኮች መኪኖች በአግባቡ እንዲተላለፉ ሲያደርጉ ይሄን


አይነት ምልክት ያሳያሉ፡፡

4.1.3. ባህሎችን የሚያሳዩ ምስሎች፡

መግቢያ

በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች እንደባህላቸው የተለያዩ


ማጌጫዎች አሉአቸው ፡፡
ባህልላዊ እሴቶች በተለያየ መንገድ ይገለጻሉ፡፡ የአንድ
ማህበረሰብ አኗኗር እንዲሁም ሁኔታ ከሚያዘጋጃቸው
የባህል ጥበባዊው ጤቶች መረዳት እንችላለን፡፡
83
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በእጅ የሚሰሩ የሸክላ ውጤቶች፣ የሽመናስራዎች ብሎም


የቤት አሰራሮች እንዲሁም ጭፈራዎች የአንድን ህዝብ
ባህል፣አኗኗር እና ሁኔታ ይገልጻሉ፡፡
ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- የተለያዩ ባህሎችን
የሚያሳዩ ውብ ምስሎችን ታያላችሁ ስለባህሎችም
ታውቃላችሁ፡፡

 የሚቀጥለው ገጽ ላይ ያለውን ምስልላይ ያያችሁትን


ለመምህራችሁ ተናገሩ?ጭፈራዎቹስ ምን
ያመሳስላቸዋል?

ምስል.4.9 የኮንሶ ማህበረሰብ ጭፈራ

84
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.4.10 የሀመር ኢቫንጋዲ ጭፈራ

ምስል 4.11 የዳሰነች ማህበረሰብ ጭፈራ

85
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል 4.12 የኛንጋቶም ማህበረሰብ ጭፈራ

ባህላዊ መዋቢያዎች

ምስል.4.13

86
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.4.14

ምስል.4.15

87
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ባህላዊ የቤት አሰራሮች


በሃገራችን የተለያዩ ባህላዊ የቤት አሰራሮች ይገኛሉ፡፡
በደንጋይ ፣ በጭቃ፣ በሳር ፣ በቀርክሃ ቤቶች ይሰራሉ፡፡
በሀገራችን የባህላዊ ቤት አሰራር ብዙ ጊዜ ጣራቸው የሳር
ክዳን የሆኑ ጎጆ ቤቶች ናቸው ፡፡

ምስል.4.16 የጉራጌ ማህበረሰብ ቤት አሰራር

88
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.4.17.የጋሞ ማህበረሰብ ቤት አሰራር

ምስል 4.18. የደቡብ ኦሞ አካባቢቤት አሰራር


 በአካባቢያችሁ ቤቶች በምንድን ነው የሚሰሩት ?

89
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ባህላዊ የቡና አቀራረብ ስርዓት

ምስል.4.19

ባህላዊ የጥበብ ስራዎች

ምስል.4.20. በእጅ የሚሰራ ባህዊ ሰፌድ

90
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ባህላዊ ሽመና እና ፈትል

ምስል.4.21 ጥጥ የምትፈትል ሴት

ምስል.4.22 ሽመና የሚሰራ ሰው

91
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በባህላዊ ሽመና የተሰሩ ባህላዊ ጨርቆች

ምስል.4.23

ምስል.4.24.ባህላዊ የሀበሻ ቀሚስ

92
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.2..አካላዊ እንቅስቃሴ

የሰውነት እንቅስቃሴ የምንለው በቀላል የሙዚቃ ምቶች


ልጆች ሰውነታቸውን የሚያንቀሳቅሱበት ድርጊት ነው፡፡
ልጆች እንደ ውዝዋዜ ያለ የሰውነት ክፍሎቻቸውን ከምት
ጋር በማዛመድ በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ተግባር ነው፡፡

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- ስለ ቀላል የሰውነት


እንቅስቃሴዎች ታውቃላችሁ እንዲሁም ቀላል የሰውነት
እንቅስቃሴዎችን መተግበር ትችላላችሁ፡፡

 እስቲ ተማሪዎች የምታውቁትን አንድ ቀላል የእግር


እንቅስቃሴ ወይም ጨዋታ ለመምህራችሁ አሳዩ ?

4.2.1 .ልጁ የሰውነት እንቅስቃሴ ሲያደርግ

93
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

4.2 ልጁ እየዘለለ
የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሐሰት በማለት
መልሱ፡፡

1. በባህላችን የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ ተገቢ ተግባር


ነው፡፡
2. ሃገራችን ውስጥ ብዙ የሚደነቁ ባህሎች አሉ፡፡
3. በሃገራችን አልባሳት አንድ አይነት ብቻ ናቸው፡፡
4. በሃገራችን የተለያየ የሰርግ ስርዐቶች አሉ፡፡
5. በሃገራችን የተለያዩ የቤት አሰራሮች የሉም፡፡
6. በእጅ የሚሰሩ አልባሳት እንዲሁም የተለያዩ የእደ
ጥበብ ውጤቶች የአንድን ህዝብ ባህል እና አኗኗር
ይገልጻሉ፡፡

94
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምዕራፍ አምስት
ጥበባዊ ትግበራ ማቅረብ

ጥበባዊ ትግበራ በተለያዩ መንገድ ተማሪዎቹን አሳታፊ በማድረግ


የሙዚቃን ፣የስዕልን ፣ የትወናን ጥበብ በአንድ የምንተገብርበት
መንገድ ነው ፡፡

በዚህ ምዕራፍ በተግባር የተደገፉ መዝሙሮች፣ስዕሎችን


እንዲሁም ውዝዋዜዎችን በማቀናጀት እንማራለን፡፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ካጠናቀቃችሁ በኋላ፡-

 በመዝሙር ፣በውዝዋዜ በመታጀብ ስለ ቀለም


ታውቃላችሁ፡፡
 በቡድን ቀለል ያሉ መዝሙሮችን ትዘምራላችሁ፡፡
 አካባቢያቸውላይ ያሉ የተፈጥሮ ቀለሞች መግለጽ
ትችላላችሁ፡፡
 ቀለል ያሉ መዝሙር እና ውዝዋዜን በአንድ ላይ
ታቀርባላችሁ፡፡
 የተፈጥሮ ሃብቶችን የተመለከቱ መዝሙሮች
ትዘምራላችሁ፡፡
 የተፈጥሮ ሃብቶችን በስዕል እና በፎቶ ታውቃላችሁ፡፡
95
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

5.1. የህብረት ጨዋታዎች

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- ቀለማን የሚናገሩ


ጨዋታዎችን ታውቃላችሁ፡፡

እስቲ አንድ የምትወዱትን ጨዋታ ተጫውታችሁ


ለመምህራችሁ አሳዩ?

የቀለም የቡድን ጨዋታ


ልጆች ሶስት ወይም አራት በመሆን ትጫወታላችሁ፡፡ አንድ
ልጅ ጨዋታውን እንዲመራ ይደረጋል፡፡ ጨዋታውን የሚመራ
ልጅ ጨዋታውን አረንጓዴ፣አረንጓዴ እያለ ይዘምራል፡፡

የሚጫወቱት ልጆች አረንጓዴ ሲባል ባሉበት ዱብ ዱብ


ይላሉ፡፡ድንገት ቢጫ ሲል ይቀመጣሉ፡፡ቀይ ሲል ቀጥ
ብለው ይቆማሉ፡፡ የጫዋታውን መሪ ልጅ በመከተል
ይተገብራሉ፡፡ያልታዘዘውን ያደረገ ልጅ ጨዋታውን
ይፎርሻል፡፡ለምሳሌ ቀይ ሲባል የተቀመጠ ወይም ዱብ ዱብ
ያለ በጨዋታው ይፎርሻል፡፡

96
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ቀለሟን የነካ

አጨዋወት

በጨዋታው በግል ወይም እስከ አምስት ልጆችን በቡድን


መምረጥ ፡፡መምህሩ የአንድ ቀለም ስም ሲጠራ ተማሪዎች
በአካባቢያቸው የሚገኝን መምህሩ የጠራው ቀለም አይነት
የያዘ ቁስ በቶሎ በመንካት ታሳያላችሁ ፡፡ ቶሎ ቀለሙን
የነካ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል፡፡

5.2. በህብረት መዘመር

ይህንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- ስለ ቀለም የሚያነሱ


መዝሙሮችን ከእንቅስቃሴ ጋር በማጀብ ትዘምራላችሁ፡፡

የምታውቁትን መዝሙር ለመምህራችሁ ዘምሩ ?

ልጆች ከታች ያለውን መዝሙር መምህራችሁ በሚሰጣችሁ


ዜማ ዘምሩት፡፡መዝሙሩ በቡድን ሆናችሁ የምትዘምሩት
ነው፡፡

97
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ማን ነው ቀይ ያደረገው
ማን ነው ቀይ ያደረገው
እኔ ነኝ ቀይ ያደረግኩት
ምን ነው ቢጫ ያደረገው
እኔ ነኝ ቢጫ ያደረግኩት
ምን ነው ነጭ ያደረገው
እኔ ነኝ ነጭ ያደረግኩት
ምን ነው ጥቁር ያደረገው
እኔ ነኝ ጥቁር ያደረግኩት

5.3. ስለ ተፈጥሮ ሃብት እና በዙሪያችን ስላሉ የተፈጥሮ


ቀለሞች
በዙሪያችንያሉ ነገሮችን ተመልከቱ ዛፎችን፣ አበቦችን፣
ተራሮችን፣ እንስሶችን ፣ ወንዞችን የራሳቸው ቀለም
አላቸው፡፡

ቀለሞችን ለመቀባት ብንፈልግም ቀለሞቸን ከአካባቢያችን


ካሉ ነገሮችን እናገኛለን አረንጓዴ ብትፈልጉ ከተለያዩ
ቅጠሎች ታገኛላችሁ፡፡ቀይ ብትፈልጉ ከቀይ አፈር ከአበቦች
ማግኘት ይቻላል፡፡

98
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ይሄንን ርዕስ ካጠናቀቃችሁ :- በሚና መጫዎት የተለያዩ


እንስሳትን ድምጽ ታስመስላላችሁ እንዲሁም ቀለማቸውን
ታውቃላችሁ፡፡

 እስቲ በሬዎች እንዴት እንደሚራመዱ እንዲሁም


እንዴት እንደሚጮሁ ተናገሩ ?
 ተማሪዎች ጥቁር ቀለምን ከምን ማዘጋጀት እንችላለን
እስቲ የምታውቁትን ተናገሩ?

ምስል.5.1 በተፈጥሮ የተዋበው የአባይ ወንዝ

99
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የዛፉን ቀለም ፣የወንዙን ቀለም እና የሳሩን ቀለም


ተመልከታችሁ ያያችሁትን ቀለም ተናገሩ ፡፡

ምስል.5.2. የእንሰት ተክል

የእንሰት ተክሎችስ ቅጠላቸውና ግንዳቸው ምን አይነት


ቀለም አለው ?

ምስል.5.3 ተራራ አካባቢ የተሰራች ጎጆ


100
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

መዝሙር
ሃገሬን ጎብኝቼ

ተራሮችን አቋርጬ
እርሻ ማሳ ተመልክቼ
ከምንጮቹም ተጎንጭቼ
ሃይቆቹንም አይቼ
ኮ ር ቻ ለ ሁ
ሃ ገ ሬ ን
አ ይ ቼ

ምስል.5.4 ጫሞ ሃይቅ

101
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የወፎች ቀለም
ወፎች ሲዘምሩ ስምታችኋል በጣም የሚያምር ድምጽ
አላቸው ፡፡
ድምጻቸው ብቻ ሳይሆን የሚያምሩ የተለያዩ ቀለም
ያሏቸው ላባዎችም አሏቸው፡፡

ምስል 5.5 የተለያየ ቀለማት ያላቸው ወፎች

ምስል 5.6.አረንጓዴ ፣ቢጫ እና ቀይ ቀለም ያለው


በቀቀን ወፍ

102
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.5.7.ሰማያዊ ቀለም ያላት ወፍ

ምስል.5.8
ሰማያዊ ፣አረንጓዴ፣ቀይ እና ቡርትካናማ ቀለም ያላቸው
ወፎች
ልጆች በአካባቢያችሁ ያሉ ወፎች ምን አይነት ቀለም
አላቸው?
103
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የወፏን ቀለም ማቅለም ፡፡

ምስል.5.9

ምስል 5.10.ፒኮክ
ፒኮክ በተለያየ ቀለም ያሸበረቀ ላባ አላት፡፡

104
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

በአካባቢያችሁ ያሉ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች ቀለም

ምስል.5.11.ብርቱካን

ምስል.5.12.ካሮት

105
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.5.13.ማንጎ

ምስል.5.14.ሙዝ

106
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.5.15.አቮካዶ

ምስል5.16. ቲማቲም

107
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ተማሪዎች የአቦካዶ ቀለም ምን አይነት ነው? የቲማቲምስ?


ከዚህ በታች የተሰጧችሁን ምስሎች በትክክለኛው ቀለም
በሌላ ወረቀት ላይ አቅልሙ

ምስል.5.17
ይሄ የማንጎ ዛፍ ነው ቅጠሎቹ ምን ቀለም መሆን
አለባቸው?

ምስል.5.18.
ይሄስ ምንድን ነው ቀለሙስ ምን መሆን አለበት
108
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

ምስል.5.19
ይሄስ ምንድን ነው ቀለሙስ ምን መሆን አለበት

ምስል.5.20
ይሄ ምን አትክልት ነው ቀለሙስ ምን መሆን አለበት?

109
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

እንሰሳት እና ቀለማቸው

ምስል.5.21

ምስል.5.22
የሜዳ አህዮችን ከተመለከታችሁ ደሞ የቆዳቸው ቀለም ላይ
ነጭ እና ጥቁር ቀለም በመስመር ሆኖ ታያላችሁ፡፡

110
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የተፈጥሮ ሀብቶች
ወንዞች፣ ሃይቆች እንዲሁም ደኖች የተፈጥሮ ሃብት
ከምንላቸው ውስጥ ይመደባሉ ፡፡

ምስል.5.23. ኦሞ ወንዝ

የቃል መልመጃ
ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ስጡ
1. በአካባቢያችሁ ካሉ የተፈጥሮ ቀለማት የምትወዱት ቀለም
ምንድን ነው?
2. በትምህርት ቤታችሁ ግቢ ውስጥ በብዛት ያሉት ቀለሞች
ምንምን ናቸው ?
3. ስለ አካባቢያችሁ የሚናገር አንድ መዝሙር ዘምሩ?

111
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

የእይታና የትወና ጥበባት


የተማሪ መጽሐፍ

አንደኛ ክፍል

የ ደ ቡ ብ ብ ሔሮ ች ብ ረ ሰ ቦ ች ሕ ዝ ቦ ች ክ ል ል መን ግ ስ ት
ት ምህ ር ት ቢ ሮ
112
የእይታና የትወና ጥበባት 1ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

113

You might also like