You are on page 1of 6

የ4ኛ ክፍል የሒሳብ ትምህርት

4.3. ይዘትን መለካት


- ይዘትን ለመለካት የምንጠቀምባቸው የተለመዱ ምድቦች ሚሊ ሊትር (ሚ.ሊ) እና ሊትር (ሊ) ናቸው፡፡
በጣም ትንሽ የሆነን ይዘት ለመለካት የምንጠቀምበት ምድብ ሚሊ ሊትር ሲሆን፤ከፍተኛ መጠን ያለውን
ይዘት ለመለካት ሊትር እንጠቀማለን፡፡ለምሳሌ
1. በጣም ትንሽ መጠን ያለውን ይዘት ለመለካት እንደ ስሪንጅ፣ የሻይማንኪያ እና የመሳሰሉትን
መሳሪያዎችበመጠቀም በሚሊሊትር መለካት ይቻላል፡፡
2. ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ይዘቶች ለመለካት ሊትር እንጠቀማለን፡፡ ለምሳሌ ግማሽ ሊትር፣ 1ሊትር፣
2ሊትር የሚይዙ ጠርሙሶች ለመለኪያነት በመጠቀም መለካት ይቻላል፡፡
- በይዘት ምድቦች መካከል ያለ ዝምድና 1ሊትር = 1000ሚሊ ሊትር
➢ ከሊትር ወደ ሚሊሊትር (ከከፍተኛ ወደ ዝቅተኛ) ለመቀየር በሊትር የተሰጠውን መጠን በ1000
ማባዛት እና ውጤቱን በሚ.ሊ መፃፍ፡፡
➢ ከሚሊ ሊትር ወደ ሊትር (ከዝቅተኛ ወደ ከፍተኛ) ለመቀየር በሚሊ ሊትር የተሰጠውን መጠን
በ1000 ማካፈል እና ውጤቱን በሊትር መፃፍ፡፡ምሳሌ፡-
ሀ. 5ሊትር = 5  1000ሚሊ
= 5000ሚሊ
ለ. 3.06ሊ = 3.06  1000ሚሊ
= 3060ሚሊ
ሐ. 300,000ሚሊ = 300,000  1000ሊ
= 300ሊት
መ. 42675ሚሊ = 42675  1000ሊ
= 42.675ሊ
የይዘት መለኪያ ምድቦችን መደመርና መቀነስ
- በተለያዩ ምድቦች የተለኩ ይዘቶችን ለመደመር ወይም ለመቀነስ የሚመረጠው ወደ አንድ አይነት
ምድብ መቀየርና መስራቱ ነው፡፡
- በተለያዩ ምድቦች የተለኩ ይዘቶች ለማወዳደር የሚመቸው ሁሉንም ምድብ ወደአንድ አይነት
ምድብ መቀየር እና ማወዳደር ነው፡፡ምሳሌ፡-
ሀ. 7.5 ሊትር + 870 ሚ.ሊ = 7.5  1000ሚሊ +870ሚሊ(ከፍተኛውን አሀድ ወደ ዝቅተኛው መቀየር)
= 7500ሚሊ + 870ሚሊ
= 8370ሚሊ ወይም
7.5ሊትር + 870ሚሊ = 7.5ሊትር + (870  1000ሊትር)(ዝቅተኛውን አሀድ ወደ ከፍተኛ መቀየር)
= 7.5ሊትር + 0.87ሊትር
= 8.37ሊትር
ለ. 12ሊትር - 1.7ሊትር = 12.0ሊትር - 1.7ሊትር
= 10.3ሊትር
ምዕራፍ 5
የጠለል ምስሎችና ጠጣር ምስሎች
5.1. ማዕዘናዊ አንግል
- ሁለት ተቋራጭ ቀጥታ መስመሮች ሀ እና ለ በሚቋረጡበት ነጥብ ላይ አራት እኩል መጠን
ያላቸው አንግሎችን ከመሰረቱ እያንዳንዱ አንግል ማዕዘናዊ አንግል ይባላ፡፡ ማዕዘናዊ አንግል
መሆኑን ለማረጋገጥ የጎነ-ሶስት መሳያውን እንጠቀማለን፡፡ የጎነ-ሶስት መሳያ ሁለት አጭር ጎኖች
መስመሮቹ ላይ የሚያርፍ ከሆነ ማዕዘናዊ አንግል ተመስርቷል ማለት ነው፡፡
- ሁለት ጨረሮች የጋራ መነሻ ነጥብ ሲኖራቸው አንግል ይመሰርታሉ፡፡ ሁለት ቀጥታ መስመሮች
ሲቋረጡ አንግል ይመሰርታሉ፡


ጎነ ሶስት ማሳያ
- ሁለት ቀጥታ መስመሮች ሀ እና ለ ቀጤነክ ተቋራጭ መስመሮች ናቸው የሚባሉት ሲተላለፉ
ማዕዘናዊ አንግል የሚመሰርቱ ከሆነ ነው፡፡

5.2. ነጥቦች፣ ቀጥታ መስመሮችና ጠለሎች


- የጠለል ምስሎች ባለሁለት ተለኪ የጂኦሜትሪ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የጠለል ምስች ርዝመት እና
ወርድ ሲኖራቸው ከፍታ ግን የላቸውም፡፡ምሳሌ
ጎነ-ሶስቶች፣ ጎነ-አራቶች እና ክቦች የጠለል ምስሎች ናቸው፡፡

ጎነ-ሦስት ፓራሌሎ ግራም(ጎነ-አራት) ክብ

በነጥቦች፣ መስመሮችና ጠለሎች መካከል ያለ ዝምድና


- በነጥቦች ጠለል መካከል ያለውን ዝምድና ለመግለፅ፡- ነጥቦችን እና ጠለሉን በማየት ነጥቡ
በጠለሉ ላይ፣ ከጠለሉበላይ፣ ከጠለሉ ጎን ወይም ከጠለሉ በታች በማለት ይገለፃል፡፡ እንዲሁም
በቀጥታ መስመሮችና በጠለል መካከል ያለው ዝምድና ሲገለፅ በተመሳሳይ መንገድ ይገለፃል፡፡
ለምሳሌ፡- ከዚህ በታች ያለውን ምስል ተመልከቱ፡፡

- ነጥብ “ቀ” ከጠለል “ሀለመሠ” በታች ነው፡፡ ቀጥታ መስመር “ሰሸ” ከጠለል “ሀለመሠ” ጎን ነው፡፡
እርግብ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የግል ት/ቤት
ኮተቤ ከኬ.ጂ- 10ኛ ስልክ ቁ.: - 0116601935
0938606060
የወላጅ ፊርማ

ብቁ ዜጋ ማፍራት አላማችን ነው!!!


ሙሉስም _____________________________ ክፍል- 4ኛ ቀን ______________
የትም/አይነት፡-ሒሳብ የ2012 ዓ.ም የ3ኛው ሩብ ዓመት ወርክሽት 1 ሰዓት_____
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች “እውነት” ወይም “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡
1. በጣም ትንሽ የሆነን ይዘት ለመለካት የምንጠቀምበት ምድብ ሚሊ ሊትር ነው፡፡
2. ከሊትር ወደ ሚሊ ሊትር ለመቀየር በሊትር የተሠጠውን መጠን በ1000 ማባዛት እና ውጤቱን በሚሊ
ሊትር መፃፍ፡፡
3. 1000 ሚሊ ሊትር ከ1ሊትር ጋር እኩል ነው፡፡
4. 1 ቶን ከ 10 ኪሎ ግራም ጋር እኩል ነው፡፡
ለ. በ “ሀ” ስር ከተዘረዘሩት በ “ለ” ስር ከተዘረዘሩት ጋር አዛምዱ፡፡
“ሀ” “ለ”
1. የይዘት መለኪያ ሀ. ከ.ሜ ሜትር ሳ.ሜ
2. የርዝመት መለኪያ ለ. ሊትር ሚሊ ሊትር
3. የክብደት መለኪያ ሐ. ቶን፣ኩንታል ኪ.ግ
ሐ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትዕዛዙ መሠረት አስሉ፡፡
1. የሚከተሉትን አስሉና ውጤቱን በኪሎግራም አስቀምጡ፡፡
ሀ. 49.5 ኪ.ግ + 90.5 ኪ.ግ = _________ ሐ. 127 ኪ.ግ - 80 ኪ.ግ= _________
ለ. 4.7 ቶን + 700 ኪ.ግ = _________ መ. 19 ቶን -34 ኪግ = _________
2. የሚከተሉትን ጥያቄዎች የ > < ወይም= ምልክት በመጠቀም አወዳድሩ፡፡
ሀ. 72 ኪ.ግ _________ 7200 ግራም ሐ. 46ቶን _________ 4600ኪ.ግ
ለ. 8.ኪ.ግ _________ 2000 ግራም መ. 83 ኩንታል _________ 83000 ግራም
3. የሚከተሉትን ወደ ሚሊ ሊትር ቀይሩ፡፡
ሀ. 15 ሊትር = _________
ለ. 0.56 ሊትር = _________
4. ወ/ሮ አስናቁ ከነበራት 10 ሊትር ዘይት 3.5 ሊትር ተጠቅማለች፡፡ ወ/ሮ አስናቁ ያልተተቀመችበት ዘይት
ስንት ነው ____________________
5. የሚከተሉትን ሊትር ቀይሩ፡፡
ሀ. 400 ሊትር = _________ ሐ. 3710.000 ሚሊ ሊትር
ለ. 7000 ሚሊ ሊትር = _________
6. የሚከተሉትን አስሉና ውጤቱን በሚሊ ሊትር አስቀምጡ፡፡
ሀ. 6 ሊትር + 4000 ሚ.ሊ= _________ ሐ. 16 ሊትር -9000 ሚሊ = _________
ለ. 8 ሊትር + 705 ሚ.ሊ= _________ መ. 12 ሊትር - 1080 ሚ.ሊ = _________
7. የሚከተሉትን አስሉና ውጤቱን በሊትር አስቀምጡ፡፡
ሀ. 35 ሊትር + 15000 ሚ.ሊ = _________ ሐ. 40 ሊትር-25000 ሚ.ሊ= _________
ለ. 34.16 ሊትር 94ሚ.ሊ= _________ መ. 75.86 ሊትር -65000 ሚ.ሊ= _________
8. ክፍተኛ መጠን ያለው ይዘት የሚለካበት ምን ይባላል ____________________
እርግብ አፀደ ህፃናት የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የግል ት/ቤት
ኮተቤ ከኬ.ጂ- 10ኛ ስልክ ቁ.: - 0116601935
0938606060
የወላጅ ፊርማ

9. ብቁ ዜጋ ማፍራት አላማችን ነው!!!


10.
ሙሉስም _____________________________ ክፍል- 4ኛ ቀን ______________
11.
የትም/አይነት፡-ሒሳብ
12. የ2012 ዓ.ም“እውነት”
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች የ3ኛው ሩብ
ወይምዓመት ወርክሽት
“ሐሰት” 3
በማለት ሰዓት_____
መልሱ፡፡
ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትዕዛዙ መሠረት ስሩ፡፡
1. የሚከተሉትን ወደ ሳ.ሜ ቀይሩ፡፡
ሀ. 45ሜ መ. 720ሜ
ለ. 66ሜ ሠ. 15 ኪ.ሜ
2. የሚከተሉትን ወደ ሜትር ቀይሩ፡፡
ሀ. 500 ሳ.ሜ መ. 0.05 ከ.ሜ
ለ. 7ኪ.ሜ ሠ. 20.000 ሳ.ሜ
ሐ. 12ኬ.ሜ ረ. 45.24ከ.ሜ
3. የሚከተሉትን ወደ ግራም ቀይሩ፡፡
ሀ. 45 ኪ.ግ ሐ. 76.25 ኪ.ግ
ለ. 10 ኩንታል መ. 6 ኩንታል
4. የሚከተሉትን ወደ ቶን ቀይሩ፡፡
ሀ. 560 ኩንታል ለ. 2000 ኩንታል ሐ. 2000ኪ.ግ መ. 72.000 ኪ.ግ
5. የሚከተሉትን ወደ ኪ.ግ ቀይሩ፡፡
ሀ. 80.000 ግራም ሐ. 3000 ኩንታል
ለ. 25000 ግራም መ. 70 ቶን
6. የሚከተሉትን ክፍት ቦታዎች ሙሉ፡፡
ሀ. 15 ኪ.ሜ ከ600 +6ኪ.ሜ በ400ሜ = _________ኪ.ሜ
ለ. 21 ኪ.ሜ ከ800ሜ - (14 ኬ.ሜ ከ300ሜ) = _________ኬ.ሜ
ሐ. 36ኪ.ሜ ከ200ሜ - 15 ኪ.ሜ ከ700 ሜ) = _________ኬ.ሜ
7. ሰባሶስት መቶኛን ወደ አስርዮሻዊ ቁጥር ቀይራችሁ ጻፉ፡፡
95
8. 100
ወደ አስርዮሻዊ ቁጥር ሲለወጥ _________ ነው፡፡

9. 25.6 ቶን ስንት ኩንታል ይሆናል


እርግብ የመና/ሁ/ደረጃ የግል ት/ቤት
ኮተቤ ከኬ.ጂ - 10ኛ ስልክ ቁ. : - 0116601935
0938606060
የወላጅ ፊርማ

ብቁ ዜጋ ማፍራት አላማችን ነው!!!


ሙሉ ስም ___________________________ክፍል፡- 4ኛ ቀን ______
የትም/አይነት፡- ሒሳብ የ2012ዓ.ም የ3ኛው ሩብ ዓመት ወርክሽት 2 ሰዓት _____

ሀ. የሚከተሉትን እውነት ወይም ሐሰት በማለት መልሱ፡፡


1. የመፅሐፍ ሽፋን የጠለል ምስል አይደለም፡፡
2. የጠረጴዛ የላይኛው የወለል ክፍል የጠለል ምስል ነው፡፡
3. አንዳንድ የጠለል ምስሎች ርዝመት፣ወርድና ከፍታ ሊኖራቸው ይችላል፡፡
4. ፓራሌሎግራም የጠለል ምስል ነው፡፡
5. ሁለት ቀጤነክ ተቋራጭ ቀጥታ መስመሮች በሚቋረጡበት ነጥብ ላይ የሚመሠርቱት አንግል
ማእዘናዊ አንግል ይባላል፡፡
ለ. የሚከተሉትን ክፍት ቦታዎች በትክክለኛው መልስ ሙሉ፡፡
1. ከፍተኛ መጠን ያለውን ይዘት ለመለካት _____________ እንጠቀማለን፡፡
2. እጅግ በጣም ትልቅ ክብደት ያላቸውን ነገሮች ለመለካት ______ ፣ _______ እና _________
እንጠቀማለን፡፡
3. እጅግ በጣም ትንሽ ክብደት ያላቸውን ነገሮች ለመለካት _____________ እንጠቀማለን፡፡
4. በጣም ትንሽ የሆነ ይዘት ለመለካት _____________ እንጠቀማለን፡፡
ሐ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በትዕዛዙ መሰረት አስሉ፡፡(ስሩ)
1. ከዚህ በታች የተመለከተውን ምስል ተመልከቱና ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች መልሱ፡፡
ሀ. ነጥብ “ወ” ከጠለል “ተቸነፈ” በውስጥ ወይስ በውጭ በኩል ይገኛል?_____________
ለ. ውስን ቀጥታ መስመር “ረሰ” ከጠለል “ተቸነፈ” ላይ ይገኛል ወይስ አይገኝም?_____________
ሐ. ነጥብ “መ” ከጠለል “ተቸነፈ” በቀኝ ወይስ በግራ በኩል ይገኛል?__________
መ. ነጥብ ”ከ” ከጠለል “ተቸነፈ” በቀኝ ወይስ በግራ በኩል ይገኛል?__________
2. ሁለት ቀጥታ መስመሮች “ሀ” እና “ለ” ቀጤነክ ተቋራጭ መስመሮች ናቸው ማለት ምን ማለት
ነው?_________________________________________________
3. አንግል እንዴት ይመሰረታል?_________________________________________________
4. የሚከተሉትን ልኬቶች የ<፣>፣ ወይም= ምልክት በመተቀም አወዳድሩ፡፡
ሀ. 53ሊትር _____________ 5300ሚሊ
ለ. 24.09ሊ _____________ 2409ሚሊ
ሐ. 33.50ሊ _____________ 335,000ሚሊ
5. አንድ ባለሶስት 200 ሊትር ዘይት ነበረው፡፡ ለሁለት ደንበኞቹ፡- ለመጀመሪያው 55ሊትር እና
ለሁለተኛው 34ሊትር ዘይት ሸጠላቸው፡፡
ሀ. በጠቅላላው የሸጠው ዘይት ስንት ሊትር ነው ?_____________
ለ. ያልተሸጠው ዘይት ስንት ሊትር ነው ?____________
6. አንድ የውሀ ማተራቀሚያ በርሜል 500ሊትር ውሀ መያዝ ይችላል፡፡ የውሀ ማጠራቀሚያው
በውስጡ 275.5ሊትር ውሀ ቢኖረው፣ ማጠራቀሚያውን ለመሙላት ስንት ሊትር ውሀ
ያስፈልጋል?_______
7. አንዲት የወተትላም በቀን ሁለት ጊዜ ትታለባለች፡፡ጧት 5ሊትር እና ማታ 6ሊትር ትታለባለች፡፡
ሀ. ላሟ በአንድ ቀን ስንት ሊትር ወተት ትታለባለች?____________
ለ. ላሟ በአንድ ቀን ከምትታለበው 10ሊትር ወተት ቢሸጥ ቀሪው ወተት መጠን በሊትር ስንት
ነው?____________
8. አንድ ጭነት መኪና ከጭነቱ 155ኩንታል ይሆናል፡፡የጭነቱ ክብደት 35 ኩንታል ብቻ ቢሆን፣
የመኪናው ክብደት ስንት ኩንታልነው?____________
9. አንድ ነጋዴ 5ኩንታል ስኳር ነበረው፡፡ ነጋዴው ለሶስት ደንበኞቹ ለመጀመሪያው 70ኪ.ግ፣
ለሁለተኛው 55ኪ.ግ እና ለሶስተኛው 83ኪ.ግ ሸጠላቸው፡፡
ሀ. በጠቅላላ ስንት ኪ.ግ ስኳር ሸጠ?____________
ለ. ያልተሸጠው ስንት ኪ.ግ ነው?____________
10. የሚከተሉትን አስሉና ውጤቱን በሊትረ አስቀምጡ፡፡
ሀ. 18ሊትር + 2000ሚሊ = __________
ለ. 150ሊትር + 65ሊትር = __________
ሐ. 40ሊትር - 20,000ሚሊ = __________
መ. 4ሊትር + 6,000ሚሊ = __________
አዘጋጅ፡- መ/ር ፀጋው

You might also like