Professional Documents
Culture Documents
የመምህር መምሪያ
4ኛ ክፍል
አዘጋጆች
አቶ አበበ ደሴ ስንቄ
አቶ ቴዎድሮስ ጥዑማይ ረዳ
ቡድን መሪ
ዶ/ር ተከተል አብርሃም
ዲዛይነር
አትርሳው ጥግይሁን ወረቀት
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 23
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
መግለጫ፦
መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎቶች የሚባሉት በእያንዳንዱ የእለት ተዕለት ተግባራችን የምናከናውናቸው ተግባሮችን ለመፈጸም
የሚያስችሉን እንቅስቃሴዎች ሲሆኑ የእለት ተእለት ተግባራትንም ሆነ ለሁሉም የስፖርት ክህሎቶች መሠረት የሆኑ እንቅስቃሴዎች
ናቸው። እነዚህም እንቅስቃሴዎች ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ፣ በቦታ ላይ በመሆንና መሳሪያ በመጠቀም የምንሰራቸው እንቅስቃሴዎች
ናቸው። ተማሪዎች ሶስቱንም መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎቶች በማቀናጀት የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ማሰራት ይጠበቃል።
ስለዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ተግባር ለተማሪዎች በመስጠት በሶስተኛ ክፍል ትምህርታቸው የነበራቸውን ቅድመ አውቀት ለመመዘንና
ትምህርቱን ከተማሪዎች አቅም፣ ችሎታና እውቀት ጋር አዛምዶ ለማቅረብ ያስችላል።
ተግባር አንድ
1. ሦስቱን መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎቶች በማቀናጀት የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩና ሦስቱን መሠረታዊ
የእንቅስቃሴ ክህሎቶች በማቀናጀት መስራት ምን ዓይነት ጠቀሜታ እንዳለው እንዲገልጹ ማድረግና ማብራሪያ መስጠት።
የክፍል አደረጃጀት
የክፍሉን ተማሪዎች ባሉት ኳሶች መሰረት እና ባለቸው የአካል ብቃትና ቁመና በቡድን መክፈል።
ተማሪዎችን በረድፍ በማሰለፍ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ከላይኛው የአካል ክፍል ወደ ታችኛው
የአካል ክፍል ማሰራት
በተደረደሩ ኮኖች ላይ መሮጥ ሰርቶ ማሳየት
ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው እና ፍጥነትን በመጨመር ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
የሁሉንም ተማሪዎች አሰራር በየቡድኑ በመሄድ መከታተልና እርምትና ማበረታቻ በመሰጠት ተማሪዎችን በሁለት ረድፍ
በማሰለፍ የሰውነት ማብረድና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራትና ከእለቱ ትምህርት ምን እንደተማሩና ምን ጠቀሜታ
እንደሰጣቸው በቃል ጥያቄ ማረጋገጥ።
በመጨረሻም የእለቱን ትምህርት አስመልክቶ አጭር ማጠቃለያ በመስጠትና በቦታና በመራመድ በአንድ እግርና በሁለት
እግር ገመድ መዝለልን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሁለት ረድፍ አሰልፎ ወደ ክፍል መመለስ።
ትምህርት አራት በቦታና በመራመድ በአንድ እግርና በሁለት እግር ገመድ መዝለል
ተማሪዎችን ከላይ በተገለጸው አደራጀጀት በማደራጀት በመስመሮች እንዴት ኳስ በእጅ በመያዝ በአራት ማዕዘን መስመር
እየዘለሉ መሄድ እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ በማድረግ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው እንዲሰሩና
መስራታቸውን በማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ በማሰራት
ስለ ኳስን በእጅ በመያዝ በአራት ማዕዘን መስመር እየዘለሉ መሄድን ማጠቃለልና ኳስን በእግር በመያዝ በመስምር ወደ
ግራና ቀኝ መዝለልን በማሰተዋወቅ በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ተግባር ሁለት
1. በመሳሪያ የሚሰሩ የእንቅስቃሴ ዓይነቶችን እንዲዘርዝሩና የዘረዘሯቸውን በመሳሪያ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን መስራት ምን
ዓይነት ጠቀሜታ እንዳለው እንዲገልጹ ማድረግና ማብራሪያ መስጠት።
ትምህርት አስራ ስድስት በመራመድ ኳስን በወገብና በእግር መካከል በእጅ ማዞር
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው ደጋግመው
እንዲሰሩና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በመራመድ ኳስን በወገብና በእግር መካከል በእጅ ማዞርን ማጠቃለልና ኳስን በኮኖች መካከል ዚግዛግ ማንጠርን
በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደክፍል መመለስ።
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 12
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
መግቢያ
የምት እንቅስቃሴዎች የሚባሉት ከተለያዩ የሙዚቃ ድምጾች ወይም የምት የሙዚቃ መሳሪያዎች ድምጽ ጋር ጊዜ ጠብቀው
በማቀናጀት የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች ናቸው። እነዚህ እንቅስቃሴዎችም አካል ብቃትን፣ ምልሰት የመስጠትን፣ አዎንታዊ ስሜትንና
የፈጠራ አቅምን የማዳበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው።
ስለዚህ ተማሪዎች በመማር ማስተማሩ ሂደት በቂ እውቀት እንዲኖራቸውና ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቀጥሎ የቀረበውን ተግባር ቀድሞ
የቤት ስራ መስጠት ያስፈልጋል።
ተግባር አንድ
1. በሙዚቃ ምት የሚሰሩ የመሳሪያ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩና የመሳሪያ እንቅስቃሴዎችን ከሙዚቃ ምት ጋር አቀናጅቶ
መስራት ምን ዓይነት ጠቀሜታ እንደሚሰጥ እንዲያብራሩ ማድረግና ግብረ መልስ መስጠት።
በፈጣን የሙዚቃ ምት በቦታ ገመድ በቀኝ እና በግራ እግር መዝለልን ማጠቃለልና እየሮጡ በሩጫ ምት ገመድ መዝለልን
በማስተዋወቅተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ተግባር ሁለት
1. ፈጠራ ምን ማለት እንደሆነና የምት እንቅስቃሴዎችን እንዴት መፍጠር እንደሚቻል እንዲገልጹ ማድረግና ለምላሻቸው
ግብረ መልስ መስጠት።
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 18
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
መግቢያ
ልዩ ልዩ ጨዋታዎች በዝቅተኛ ደረጃ የተደራጁና የራሳቸው ህግ ያላቸው ጨዋታዎች ናቸው። በዝቅተኛ ደረጃ የተደራጁ ማለት
ዳኛ፣ ተመልካች፣ አሰልጣኝ፣ ፖሊስ እና የመሳሰሉት የለላቸው በጋራ ስምምነትና መግባባት የሚከናወኑ ሲሆኑ ጨዋታዎቹ በጋራ
በመስራትና በመጫዎት አብሮ/ተባብሮ መስራትን፣ ህግን ማክበርና ለህግ ተገዢ መሆንን፣ ሌሎችን የማክበርና ለራስ ዋጋ የመስጠትን፣
ብርታትን፣ ቅልጥፍናን፣ የአካል ቅንጅትን እንዲሁም የዕለት ተዕለት ተግባራትን ለመተግበርና ጤንነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ
ጨዋታዎች መሆናቸውን በዝርዝር ማስረዳትና ሊደረጉ የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማድረግና መግለጽ የሚያስፈልግ ነው።
ስለዚህ ተማሪዎች ይህን አስተሳሰብ እንዲያዳብሩና በጨዋታው ሂደት ንቁና አዎንታዊ አስተሳሰብ ኖሯቸው መልካም ተሳታፊ
እንዲሆኑ በዝርዝር ማስረዳትና ቀጥሎ ያለውን ተግባር ቀድመው ሰርተው እንዲመጡ ማድረግ ተገቢ ነው።
ተግባር አንድ
1. ራስን ለመምራትና አዎንታዊ አስተሳሰብ የሚያዳብሩ የሚያውቋቸውን ልዩ ልዩ ጨዋታዎች እንዲዘረዝሩ ማድረግና አጭር
ማብራሪያ መስጠት።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን ጥንድ ጥንድ ማድረግ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ስፖርት ሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፡
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በጥንድ ማደራጀት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ስፖርት ሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የጓደኛን እንቅስቃሴ ተከትሎ ሁለት እንቅስቃሴዎችን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ጓደኛ የሚያሳየውን/የምታሳየውን ሁለት ተከታታይ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንዲሰሩና ጓደኛ የሚለውን/
የምትለውን እንቅስቃሴ እንዳይሰሩ መግለጽና ስራቸውን በተከታታይ በማየት ግብረ መልስ መስጠት
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ጥንዶች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋጋሚ እንዲሰሩና
መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የጓደኛን እንቅስቃሴ ተከትሎ ሁለት እንቅስቃሴዎችን መስራትን ማጠቃለልና በኬሻ ውስጥ ደርሶ መልስ ሩጫን
በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
በክብ ዙሪያ ኳስን አምስት ዙር መቀባበልን ማጠቃለልና አሳ ማጥመድ ጨዋታን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ
ክፍል መመለስ።
የክፍል አደረጃጀት
የክፍሉን ተማሪዎች በፆታ፣ በአካለ መጠንና ችሎታ ጥንድ ጥንድ ከመደቡ በኋላ ተመሳሳይ ቁጥር መስጠትና ለሁለት
ቡድን በመክፈል በተዘጋጀው ሜዳ ከመስመር ውጭ በተመሳሳይ ቦታ እንዲቆሙ ማድረግ
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፡ አራት ማዕዘን 25ሜ በ15ሜ መስመር፣ ሰባት ትንንሽ ኳሶች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ተማሪዎችን ከላይ በተገለጸው አደረጃጀት በማደራጀት ኳስን መሰብሰብ የሚለውን ጨዋታ ህግ አጭር ማብራሪያ
መስጠትና እንዴት መጫዎት እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየት እና እንዲሰሩ በማድረግ ጨዋታውን ማጫዎትና ውሳኔ መስጠት
ማለትም ተማሪዎች በአራት ማዕዘን መስመሩ ውጭ እንዲሮጡ፣ በመግቢያው ቦታ እንዲገቡ፣ ተቃራኒ የያዘውን ኳስ
መቀማት እንደማይቻል፣ ኳስን መልቀም እንጂ በኳስ ላይ መተኛት እንደማይቻልና ከተሸነፉ ያሸነፈችውን/ያሸነፈውን
ተማሪ መጨበጥና ማድነቅ እንዲችሉ እና ሁሉም ተማሪ ቁጥሩ ሲጠራ ተመሳሳይ ተግባር እንዲፈጽም ማበረታታት፣
ድጋፍና ክትትል ማድረግ
አሸናፊውን ቡድን በጭብጨባ በማበረታታት የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ በማሰራትና በማጠቃለል
ወደ ክፍል በሰልፍ መመለስ።
•• እያደረጉ ማቧደን
በክብ ውስጥ ያሉ ልጆችን ኳስ በእግር በመንዳት ማስነካትን ማጠቃለልና የአሳ ማጥመድን ጨዋታ በማስተዋወቅ
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 23
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
ªªአካል ብቃትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይረዳሉ።
ªªየአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የሚሰጡትን ጠቃሜት ያደንቃሉ።
ªªተገቢ የሆኑ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በመስራት የአካል ብቃታቸውን ያዳብራሉ።
መግቢያ
ጤና ማለት ከበሽታ ነጻ መሆን ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዱ የእለት ተእለት ተግባራት ንቁና ውጤታማ በሆነ መልኩ ማከናወንና
ከየትኛውም የህብረተሰብ ክፍልና ከአካባቢ ጋር ተስማምቶና ተግባብቶ መኖርን ይጨምራል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ደግሞ
በታቀደና በተደራጀ ሁኔታ የተለያዩ ስፖርታዊ እንስቃሴዎችን አዘውትረን በመስራት ሁሉም የአካል ክፍሎች ጤነኛ እንዲሆኑ
የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች ናቸው።
ተግባር አንድ
1. የልብ እና የአተነፋፈስ ስርዓት እንቅስቃሴዎችን መሥራት የሚሠጣቸውን ጠቀሜታዎች እንዲዘረዝሩ ማድረግና አጭር
ማብራሪያ መስጠት።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ገመድ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በፆታቸው ባሉት ገመዶች ቁጥር በቡድን ማደራጀት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በቦታ ስምንት ቁጥር ገመድ አዘላለልን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋግሚ
እንዲሰሩና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በቦታ ስምንት ቁጥር ገመድ መዝለልን ማጠቃለልና የቡድን ገመድ ዝላይን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል
መመለስ።
የቡድን ገመድ ዝላይን ማጠቃለልና የስድስት ደቂቃ ሩጫን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/በሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በቦታ ላይ በሶምሶማ ሩጫ እጅን ወደተለያዩ አቅጣጫዋች መዘርጋትና ማጠፍን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋጋሚ
እንዲሰሩና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 3ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 34
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
በቦታ ላይ በሶምሶማ ሩጫ እጅን ወደተለያዩ አቅጣጫዋች መዘርጋትና ማጠፍን ማጠቃለልና በቦታ ላይ በሶምሶማ
እንቅስቃሴ ጭንን ተራ በተራ የመንካት እንቅስቃሴን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በቦታ ላይ በሶምሶማ እንቅስቃሴ ጭንን ተራ በተራ የመንካት እንቅስቃሴን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋጋሚ
እንዲሰሩና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በቦታላይ በሶምሶማ እንቅስቃሴ ጭንን ተራ በተራ የመንካት እንቅስቃሴ መቆምን ማጠቃለልና
በቦታ ላይ በሶምሶማ እንቅስቃሴ ከኋላ ተረከዝን ተራ በተራ የመንካት እንቅስቃሴን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ
ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን እንደ ቁጥራቸው መጠን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በቦታ ላይ በሶምሶማ እንቅስቃሴ ከኋላ ተረከዝን ተራ በተራ የመንካት እንቅስቃሴን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ተግባር ሁለት
1. የጡንቻ ብርታት እንቅስቃሴዎችን መስራት ለምን እንደሚጠቅም እንዲገልጹ ማድረግና አጭር ማብራሪያ መስጠት።
ትምህርት አስራ አንድ በቦታ በመቆም በሁለቱ እግሮች ወደፊት እና ወደኋላ መዝለል
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በሁለት እግሮች ወደፊት እና ወደኋላ እንዴት መዝለል እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ትምህርት አስራ ሁለት በቦታ በመቆም በሁለቱ እግሮች ወደ አራቱም አቅጣጫዎች መዝለል
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በመቀመጥ እግርን በአየር ላይ እንዴት መዘርጋትና ማጠፍ እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየት
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩት አስመስለው እንዲሰሩ
ማድረግናና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በመቀመጥ እግርን በአየር ላይ መዘርጋትና ማጠፍን ማጠቃለልና
እግር ዘርግቶ በመቀመጥ ተራ በተራ ማንሳትን ማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎች ባላቸው የቁጥር ብዛት በሁለት/ሦስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
እግር ዘርግቶ በመቀመጥ ተራ በተራ ከመሬት እንዴት ማንሳት እና ማውረድ እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ
ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋጋሚ
እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
እግር ዘርግቶ በመቀመጥ ተራ በተራ ማንሳትን ማጠቃለልና
የመተጣጠፍ እንቅስቃሴን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ተግባር ሶስት
1. የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎችን መስራት የሚሰጣቸውን ጠቀሜታዎች እንዲዘረዝሩ ማድረግና አጭር ማጠቃለያ መስጠት።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 3ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 41
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ሁለት እጅን ወደላይ በመዘርጋት ወደቀኝና ግራ እንዴት ማዘንበል እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋጋሚ
እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ሁለት እጅን ወደላይ በመዘርጋት ወደቀኝና ግራ ማዘንበልን ማጠቃለልና
የውጭ የእግርን ጫማ መንካትን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ሁለት እግርን በመክፈትና ሁለት እጅን ወደላይ በመዘርጋት በውጭ በኩል በሁለት
ትምህርት አስራ ስምንት
እጅ ተራ በተራ የእግርን ጫማ መንካት
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የውጭ የእግርን ጫማ በሁለት እጅ እንዴት መንካት እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው በተደጋጋሚ
እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የውጭ የእግርን ጫማ መንካትን ማጠቃለልና
ወገብን ወደፊትና ወደኋላ ማሳሳብን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
እግርን እንዴት ማሳሳብ እንደሚቻል ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
ጥሩ አድርገው የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው ደጋግመው
እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት ሁለት ዓይነት ጠቀሜታዎች አሉት። እነሱም አንደኛ ጤንነታችን ለመጠበቅና በዕለት ተዕለት
ገጠመኛችን የሚገጥሙንን ማንኛውን ተግባራት በብቃት ለመወጣት ሲሆን ይህንንም ለመወጣት የሚያስችለን የልብና
የአተነፋፈስ ስርዓታችን ሲዳብር፣ የጡንቻ ብርታታችንና ጥንካሬያችን ሲሻሻል፣ የመጠጣጠፍ አቅማችን ሲዳብርና በሰውነታችን
ውስጥ ተገቢ የሆነ የስብ መጠንና የሰውነት ክብደት ሲኖረን ነው። ሁለተኛው ደግሞ በተለያዩ የስፖርት ውድድሮች ብቁ
ለመሆናና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለንን ብቃት ለማዳበር ሲሆን እነሱም ቅልጥፍና፣ ፍጥነት፣ ኃይል፣ ቅንጅት፣ ሚዛንን
መጠበቅና ምልሰት የመስጠት አቅምን ለማዳበር ያስችላል።
2. ገመድ መዝለል፣ ደረጃ መውጣትና መውረድ፣ የእግር ጉዞ ማድረግ፣ ሶምሶማ ሩጫ መሮጥ ወዘተ
3.የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎች በዋነኝነት የሚሰራው ለጡንቻ፣ ለመገጣጠሚያዎችና ለጅማቶች ሲሆን የእነዚህን የአካል ክፍሎች
የመተጣጠፍ አቅም በመጨመር የጡንቻ ህመምን፣ የመገጣጠሚያ እና የጅማት ህመሞችንና በእነዚህ የአካል ክፍሎች መጎዳት
የሚመጡ ተያያዥ ህመሞችን ለመከላከል ያስችላል።
4. ተግበራቶችን በፍጥነት ለመተግበር፣ ፈጣን የሆነ ግብረ መልስ ለመስጠት፣ ቀልጣፍ ለመሆንና ወዘተ
5. ተማሪዎች የተሰማቸውን ማንኛውንም ስሜታቸውን እንዲገልጹ መገፋፋትና የተሳሳተ ግንዛቤ ካላቸው ማስተካከል ተገቢ ነው።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 3ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 47
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ
ምዕራፍ
5 ጅምናስቲክስ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 21
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
ªªመሠረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ይረዳሉ።
ªªየመሠረታዊ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ጥበብ ያደንቃሉ።
ªªመሠረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን መስራት ይችላሉ።
መግቢያ
የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች የተለያዩ የአካል ክፍሎችን የመተጣጠፍና የመዘርጋት እንዲሁም የዕለት ተዕለት ተግባራቶችን
የመተግበር አቅምን የሚያዳብሩ፣ ራስንም ከተለያዩ አዳጋዎችና የአካል ጉዳቶች ለመከላከል የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች ናቸው።
በዚህ የክፍል ደረጃቸው የሚማሯቸው የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች በሶስተኛ ክፍል ከተማሯቸው በተወሰነ መልኩ ልዩነት ያላቸው
ስለሆኑ ከእንቅስቃሴ ክህሎታቸው በተጨማሪ እንቀስቃሴዎቹን በመስራት ሊያመጡላቸው/ሊያስገኟቸው የሚችሉትን ለውጦች
በመግለጽ ተማሪዎችን በማበረታታት በተደጋጋሚ ማሰራት ይጠበቃል። ሌላውና ወሳኙ ጉዳይ የተማሪዎችን አካል ብቃት፣ ልምድ፣
ተሰጥኦና አካለ መጠን ከግምት ውስጥ አስገብቶ ማስተማር የመማር- ማስተማሩን ሂደት ያሳልጠዋል።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በፆታቸው በመክፈል ባሉት ፍራሾች በቡድን ማደራጀት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ሁለት ለሁለት በመሆን ወደፊት መንከባለልን ከተማሪ ጋር ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
የተሻለ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው ደጋግመው እንዲሰሩ
ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው
ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በጓደኛ ጀርባ ላይ ወደፊት መንከባለል ጠቀሜታን በመግለጽ ማጠቃለልና
ፍራሽ ላይ በግንባር መቆምን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ተግባር ሦስት
1. የቁጥር ጅምናስቲክስ ምን ጠቀሜታ እንደሚሰጥ ተማሪዎችን መጠየቅና አጭር ግብረ መልስ መስጠት።
በዚህ የክፍል ደረጃቸው ቁጥራቸው ከሶስተኛ ክፍል የሚጨምር ተከታታይ የቁጥር ጅምናስቲክስሶችን በመስራት የተገለጸውን
ጠቀሜታ እንዲያመጡ ማድረግና በተለይ በትምህርት ቤት በዓላት፣ የስፖርትና የተለያዩ በዓላቶች ላይ በትዕይንት መልክ ለማቅረብ
የሚያስችል በመሆኑ እንቅስቃሴውን አሻሽሎና አሳድጎ ማቅረብ ተገቢ ነው። ተማሪዎች በመማር ማስተማሩ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ
ቀጥሎ የቀረበውን ተግባር የቤት ስራ መስጠት ይገባል።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት ረድፍ በመስመር እንዲቆሙ ማድረግ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በእጅ ተከታታይ የቁጥር ጅምናስቲክስን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በተሻለ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው
ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በእጅ ተከታታይ የቁጥር ጅምናስቲክስ መስራት ጠቀሜታን በመግለጽማጠቃለልና
የእጅና የወገብ የቁጥር ጅምናስቲክስን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት መስመር ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የእጅና የወገብ የቁጥር ጅምናስቲክስን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው
ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የእጅና የወገብ የቁጥር ጅምናስቲክስ ጠቀሜታን በመግለጽ ማጠቃለልና
በእግር የሚሰሩ የቁጥር ጂምናስቲኮችን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት መስመር ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በእግር የሚሰሩ የቁጥር ጅምናስቲኮችን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው
በተደጋጋሚ እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በእግር የሚሰሩ የቁጥር ጅምናስቲኮችጠቀሜታን በመግለጽ ማጠቃለልና
በእግርና በእጅ የሚሰሩ የቁጥር ጅምናስቲክሶችን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በሁለት/ሶስት መስመር ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደሜዳ በመውሰድ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
በእግርና በእጅ የሚሰሩ የቁጥር ጅምናስቲክሶችን ሰርቶ ማሳየትና እንዲሰሩ ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በተሻለ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች ያዩትን አስመስለው
ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ምዕራፍ
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
በዞናቸው የሚገኙ ባህላዊ ጭፈራዎችንና ጨዋታዎችን ይገነዘባሉ።
በዞናቸው የሚገኙ ባህላዊ ጭፈራዎችንና ጨዋታዎች ለጤና የሚሰጧቸውን ጠቀሜታዎች ያደንቃሉ።
በዞናቸው የሚገኙ ባህላዊ ጭፈራዎችንና ጨዋታዎችን ይጫዎታሉ።
ለተማሪዎች በሶስተኛ ክፍል ትምህርታቸው በወረዳቸው የሚገኙ ባህላው ጭፈራዎችን ማለት የሰርግ፣ የስራ፣ የበአላት የተማሩ
በመሆኑ ስለነዚህ ጭፈራዎች የሚያውቁትን እንዲገልጹና እንዲጨፍሩ ማድረግና ማበረታታት። ከዚያም በዞናቸው የሚገኙ
ባህላዊ ጭፈራዎችን ማወቅና መሳተፍ ከላይ በተገለጹት ክንዋኔዎች በንቃት ለመሳተፍና ስሜታቸውንና ደስታቸውን ለመግለጽ
የሚያስችላቸው ከመሆኑም ባሻገር ከተለያየ የህብረተሰብ አካል ጋር ለመተዋወቅና ለመግባባት የአካል ቅንጅታቸውንና ብቃታቸውን
የሚያዳብሩ መሆናቸው በተጨባጭ ምሳሌ ማስረዳት። ከዚህም በተጨማሪ ቀጥሎ የቀረበውን ተግበር ሰርተው እንዲመጡ የቤት
ስራ መስጠት።
ተግባር አንድ
1. በዞናቸው የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎችን እንዲዘረዝሩና የባህላዊ ጭፈራዎችን ጠቀሜታ እንዲያብራሩ በማድረግ እጭር
ግብረ መልስ መስጠት።
በጥሩ ሁኔታ የሰሩትን ቡድኖች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ቡድኖች ያዩትን አስመስለው ደጋግመው
እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
ቀላል የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢ እንቅስቃሴ ማሰራት
የወንዶች የበዓላት ባህላዊ ጭፈራዎችን ጠቀሜታ በመግለጽ ማጠቃለልና
የሴቶች የስራ ባህላዊ ጭፈራዎችን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።
ባህላዊ ጨዋታዎች ለአካባቢው ማህበረሰብ እንደመገናኛ፣ መዝናኛና የበዓላት ጊዜ ማሳለፊያ ከተፈጥሮ ልምድና እንቅስቃሴዎች
ጋር የተዛመዱ መሆናቸውንና እነዚህን ባህላዊ ጨዋታዎች መጫዎት ባህላዊ እሴትን ከመጠበቅና ከማቆየትም ባሻገር የተሻለ
ማህበራዊ ግንኙነትን ለማዳበርና ጤንነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ መሆኑን ለተማሪዎች ማሳወቅ ተማሪዎች አዎንታዊ ፍቅርና ፍልጎት
እንዲኖራቸው ያደርጋል።
በመሆኑም በዞናቸው የሚገኙ ባህላዊ ጨዋታዎችን ማወቅና መጫዎት እንዲችሉና በመማር- ማስተማሩ ሂደት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ
ቀድሞ ቀጥሎ የቀረበውን ተግባር በመስጠት ሰርተው እንዲመጡ ማድረግ ያስፈልጋል።
ተግባር ሁለት
1. በዞናቸው የሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታዎችን እንዲዘረዝሩና ባህላዊ ጨዋታዎችን መጫዎት የሚሰጡትን ጠቀሜታዎች
እንዲያብራሩ ማድረግና አጭር ገለፃ ማድረግ።
አስፈላጊ ቁሳቁሶች፤ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፤ ተማሪዎችን በፆታቸው በመክፈል ባሉት ፍራሾች መሰረት በቡድን በማደራጀት
በአካለ መጠናቸው በጥንድ መመደብ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ሜዳ በመውሰድ ቀላል የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የግብግብ ጨዋታ ህግን መግለጽና አጨዋዎቱን ቅድመ እውቀት ባላቸው ተማሪዎች አሰርቶ ማሳየትና እንዲጫዎቱ
ማድረግ
ልዩ ድጋፍ ለሚሹ እየተዘዋወሩ ድጋፍና ክትትል መስጠት
በተሻለ ሁኔታ የሰሩትን ተማሪዎች በመምረጥ ሰርተው እንዲያሳዩ ማድረግና ሁሉም ተማሪዎች አስመስለው ደጋግመው
እንዲሰሩ ማድረግና መስራታቸውን ማረጋገጥ
ቀላል የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
የግብግብ ጨዋታን ጠቀሜታ በመግለጽ ማጠቃለልና
የልምጭ ግልቢያን በማስተዋወቅ ተማሪዎችን በሰልፍ ወደ ክፍል መመለስ።