Professional Documents
Culture Documents
የመምህር መምሪያ
2ኛ ክፍል
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ISBN ቁጥር - በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ
ዋጋ ብር -
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
የመምህር መምሪያ
2ኛ ክፍል
አዘጋጆች
አቶ መስፍን ከተማ
አቶ አዳነ እሸቱ
አርታኢዎች
አቶ አማረ መብራት
አቶ እንድርያስ ገብረአብ
ቡድን መሪ
ዶ/ር ተከተል አብርሃም
ሰዓሊ
በላይሁን ጸጋዬ
ዲዛይነር
አትርሳው ጥግይሁን
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 23
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
የመሰረታዊ እንቅስቃሴ አይነቶችን ያዉቃሉ።
መሰረታዊ እንቅስቃሴዎች በመስራት አካላቸዉን ያዳብራሉ።
የመሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎቶችን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።
መግለጫ፦
መሰረታዊ ክህሎቶች የምንላቸዉ ህጻናት በዕለት ከዕለት እንቅስቃሴዎቻቸዉ የሚያከናዉኗቸዉ ተግባራት ናቸዉ። ሶስት አይነት
መሰረታዊ እንቅስቃሴዎች አሉ። እነርሱም ፡-
ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ መሰረታዊ ክህሎቶች የሚከተሉትን እንቅስቃሴዎችን ያካትታል። እነርሱም፦ መራመድ፣ መሮጥ፣
መንጠር፣ መዝለል እና መንሸራተት የተወሰኑት ናቸዉ።
በአንድ ቦታ ቆመዉ ወይም ተቀምጠዉ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች በርካቶች ናቸዉ። ለአብነትም ፦ መታጠፍ፣ ማሳሳብ፣ መግፋት፣
ወደ ላይ ማንሳት እና መጠማዘዝ ወዘተ. ይጠቀሳሉ።
የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለመስራት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን በመጠቀም ከእንቅስቃሴዎች ጋር አቀናጅቶ መጠቀም
መሰረታዊ ክህሎትን ያሳድጋል። ከመሳሪያ ጋር ተቀናጅተዉ ከሚሰሩ እንቅስቃሴዎች ዉስጥ የሚከተሉት ይጠቀሳሉ። እነርሱም፡-
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ማስታዎሻ፦ ቀሪዎቹ ቁጥሮች አሰራራቸዉ ተመሳሳይ ስለሆነ በ3 - ቁጥር፣ በ5 - ቁጥር፣ በ7 - ቁጥር፣ በ9 - ቁጥር እና በ8 - ቁጥር
ላይ በፍጥነት እንዲሰሩ ማድረግ። ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ ተማሪዎች እንደየሁኔታዉ ተግባረትን አዘጋጅቶና አመቻችቶ እንዲተገበሩ
ማድረግ።
ማስታወሻ፦ በ “በ“ - ፊደል፣ በ “ሠ“ ፊደል፣ በ “ጠ“ -ፊደል፣ በ “ረ“ ፊደል ላይ በፍጥነት የመሮጥ ተግባራትን በተመሳሳይ ሂደት
ለእያንዳንዱ በማደራጀት መተግበር። ልዩ ፍላጎት ላላቸዉ ተማሪዎች እንደየሁኔታዉ ተግባራትን አዘጋጅቶና አመቻችሎ እንዲሰሩ
ማድረግ።
ማስታወሻ፦ በሶስት ጎን ቅርፅ፣ በመሶብ -ወርቅ ቅርፅ ላይ የፍጥነት ሩጫ ተግባራትን በተመሳሳይ ሂደት ለእያንዳንዱ የመነሻ ቦታዎቹን
በመወሰን እንዲተገብሩ ማድረግ።
ክትትል እና ግምገማ፡-
አቅጣጫን እየቀያየሩ በሚሰሩ የእንቅስቃሴ ተግባራት ወቅት በምልከታ መከታተልና ስህተቶችን ቀስ በቀስ በማስተካከል
ወደሚፈለገዉ ዉጤት ተማሪዎቹን ማምጣት።
ልጆች መስራት የሚችሉትን የጊዜ እርዝማኔ ከመጀመሪያ ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት ያመጡትን መሻሻል መመዝገብና
የሚያሳዩትን ለውጥ መገምገም።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 2ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 3
ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት
ሀ. በሩጫ የምንፈልግበት ቦታ በፍጥነት ለመድረስ፣ ስራዎችን በፍጥነት ለማከናወን፣ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች በፍጥነት ለመተጣጠፍ፣
ሰዉነታችን ቀልጣፋ እንዲሆን ወዘተ… ።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ቀጥ ባለ መስመር በተደረደሩት ቀለበቶች መካከል ከ1 - 1.5 ሜትር ርቀት እንዲኖር አድርጎ ተማሪዎቹ ይዘዉ እንዲቆሙ
ማድረግ፣
ተረኛዉ ተማሪ አጎንብሶ መሬት ለመሬት በመዳህ በቀለበቱ ዉስጥ ማለፍና ቀለበቶቹን አልፎ ሲጨርስ ፊት በመሆን እንደ
ጎደኞቹ ቀለበቱን መያዝ፣
ፊት ቀለበቱን ይዞ የነበረዉ ቀለበቱን የሚይዝለት ተማሪ እንደመጣ በፍጥነት ወደ ኋላ በመሮጥ በቀለበቶቹ ዉስጥ ማለፍ፣
ሁሉም ተማሪዎች እድሉን እንዲያገኙ ማድረግ፣
ከ 6 - 8 ጊዜ እረፍት በመስጠት ደጋግሞ ማሰራት ።
ኳሶች
የክፍል አደረጃጀት፦ ከ2 - 4 መስመር በማሰለፍ ማደራጀት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፦
ቀጥ ባለ መስመር በየቡድኑ እኩል ተማሪዎች አድርጎ ማደራጀት፣
ተደራጅተዉ በተሰለፉ ተማሪዎች በመካካል ከ1 – 1.5 ሜትር እርቀት እንዲኖር ማድረግ፣
ተደራጅተዉ የተሰለፉት ተማሪዎች በመጠኑ እግራቸዉን እንዲከፍቱ ማድረግ፣
ኳሱን ከመሬት ጋር አገናኝቶ በመያዝ በሁለት እግሮች መካከል መሬት ለመሬት በማንከባለል ወደ ኋላ ላለዉ ተማሪ እንዲደርስ
በማድረግ ቀሪዎቹ ተማሪዎች በተመሳሳይ መልኩ እንዲሰሩ ማድረግ፣
በፍጥነት የጨረሰዉ ቡድንን አሸናፊ ማድረግ፣
በመካከሉ እረፍት እየሰጡ ጨዋታዉን ከ6 - 8 ጊዜ ደጋግሞ ማሰራት።
ከ2 - 5 ሜትር ርቀት እየዘለሉ እንዲሄድና የተወሰነላቸዉን እርቀት እንደጨረሱ ከማዳበሪያዎቹ /ከጆንያ / ዉስጥ ወጥተዉ
ማዳበሪያዉን ይዘዉ እየሮጡ እንዲመለሱ ማድረግ፣
በፍጥነት የጨረሰዉን ቡድን አሸናፊ በማድረግ እንዲያጫበጭቡላቸዉ ማድረግ፣
ጨዋታዉን ከ6 - 8 ጊዜ ደጋግሞ ማሰራት።
ክትትል እና ግምገማ፡-
ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ በሚሰሩ እንቅስቃሴዎች ልምምድ ወቅት ሁሉም ተማሪዎች በተገቢው መንገድ እየሰሩ መሆናቸውን
በምልከታ መከታተልና ቀስ በቀስ እርማት በመስጠት አቅማቸዉን ማሻሻል።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ክትትልና ግምገማ፦
በልምምዱ ሁሉም እየተሳተፉ ስለመሆናቸው በምልከታ መከታተልና ሰርተዉ እዲያሳዩ በማድረግ ስለ አሰራራቸው አስተያየት
መስጠት።
በቦታ ላይ በመሆን የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲገልጹ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ መረዳታቸውን ማረጋገጥ።
ንዑስ ርዕስ፦ 1.4. ከወገብ በታች ከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች (12- ክ/ጊዜ)
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ተግባር፦ ሀ. በሲባጎ / በክር / የታሰረ ኳስን በእጅ በማንጠልጠል በፊት እግር እየመቱ
መሄድ
ተግባር፦ ለ. በሲባጎ /በክር/ የታሰረ ኳስን በእጅ በማንጠልጠል በዉስጥና በዉጪ እግር
እየመቱ መሄድ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፦
በሲባጎ / በክር / የተንጠለጠለ ኳስ
በሲባጎ የተንጠለጠለን ኳስ በእጅ ወደ ፊት ገፋ በማድረግ በእግር በዉጪኛዉና በዉስጠኛዉ ክፍል ወደ ጎን ከ10 - 15 ሜትር
እየመቱ መሄድ፣
ባልሰራዉ እግር ተመሳሳይ ተግባር መስራት፣
ይህንን ተግባር ከ6 - 8 ጊዜ ደጋግሞ ማሰራት።
ክትትል እና ግምገማ፦
ከወገብ በታች ከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲሰሩ በማድረግ በምልከታ መከታተልና ሰርተዉ እንዲያሳዩ
በማድረግ።
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 12
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
ተከታታይ እና ቀጣይነት ያላቸዉ ሪትሚካዊ / ምት / እንቅስቃሴዎችን ያዉቃሉ።
ተከታታይ እና ቀጣይነት ያላቸዉ ሪትሚካዊ / ምት / እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ከሙዚቃ ሪትሚካዊ / ምት / ጋር ተቀናጅተዉ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች ያደንቃሉ።
የላይኛዉንና የታችኛዉን የሰዉነት ክፍሎች ሊያሳትፉ ከሚችሉ የሙዚቃ ሪትሚካዊ / ምት / ካላቸዉ እንቅስቃሴዎች
ጋር አቀናጅቶ የመስራት ክህሎት ያሳድጋሉ።
መግለጫ
ሪትሚካዊ / ምት / ድምጾችን ወይም ሙዚቃዎችን ከመሰረታዊ እንቅስቃሴዎች ጋር በማቀናጀት መተግበር የተማሪዎችን አእምሮ
በመሰብሰብ በትኩረት ስራዎችን አቀናጅተዉ የመስራት ክህሎትን ያዳብራል። በዚህ ክፍለ ትምህርት ቀላል ተከታታይ ወይም
የተለያዩ ሪትሚካዊ / ምት / ክህሎት እና ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለዉ ሪትሚካዊ / ምት / ክህሎት እናያለን።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
የሁለተኛ የፊሽካ / የቁጥር / ድምጽ ሲሰማ ግራ እጅን ወደ ላይ በማንሳት ከግራ እግር ጋር ወደ ግራ አቅጣጫ ማዞርና ወደ
ቦታ መመለስ፣
የሶስተኛ የፊሽካ / የቁጥር / ድምጽ ሲሰማ እጅን ወደ ጎን በመዘርጋት ግራ እግርን ሸብረክ አድርጎ ወደ ግራ መንሸራተት፣
የአራተኛ የፊሽካ / የቁጥር / ድምጽ ሲሰማ እጅን ወደ ጎን በመዘርጋት ወደ ቦታ በመመለስ ቀኝ እግርን ሸብረክ አድርጎ ወደ
ቀኝ መንሸራተት፣
ከላይ ያለዉን ተግባር ፍሰቱን ጠብቆ ወዳልሰራዉ አቅጣጫ መስራት፣
በመካከል ዕረፍት በመስጠት በቅደም ተከተሉ ከ4 - 6 ጊዜ ማሰራት።
ክትትል እና ግምገማ፦
ቀላል ተከታታይ እና ከድምፅ ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲሰሩ በማድረግ በምልከታ መከታተል።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
የክፍል አደረጃጀት፦ በ4/5 - በረድፍ ሰልፍ ማሰለፍ፣ በ4/5 - ግማሽ ክብ ቅርፅ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፦
በጎን በኩል እግርን አጥፎና በሁለት እጅ አቅፎ መቀመጥ፣
የቀኝ እግርን ወደ ፊት የግራ እግርን ወደ ኋላ አጥፎ በአንድ እጅ መሬት ተደግፎ እስከ አንድ ደቂቃ መቆየት፣
የግራ እግርን ወደ ፊት የቀኝ እግርን ወደ ኋላ አጥፎ በአንድ እጅ መሬት ከ30 - 40 ሴኮንድ መቆየት፣
በመካከል ዕረፍት በመስጠት በቅደም ተከተሉ መሰረት ከ6 - 8 ጊዜ እንዲሰሩ ማድረግ።
ተግባር፦ ረ. እግር ከፍቶ የኋላ እግር በጣት መቆምና እጅ ወደ ጎን መዘርጋት፣ በጎን በኩል
እጅ ዘርግቶ አንድ እግርን ወደ ኋላ ማንሳት፣ አንድ እግርን ወደ ፊት በማንሳት ሁለት እጅ
ከራስ በላይ ማድረግ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፦
ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፦ በ4/5 - በረድፍ ሰልፍ ማሰለፍ፣ በ4/5 - ግማሽ ክብ ቅርዕ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፦
ቁጭ በማለት ሁለት እግርን አጥፎ የእግርን ጫፍ በእጅ መያዝ፣
እግርን ዘርግቶ መሬት በመቀመጥ ትንሽ ጎንበስ በማለት በሁለት እጅ እግርን መያዝ፣
መሬት እግርን ዘርግቶ መቀመጥና የተዘረጋዉን እግር ወደ ጎን በማጠፍ እጅ በተቃራኒ ቦታ መሬትን መደገፍ፣
በመካከል ዕረፍት በመስጠት በቅደም ተከተሉ መሰረት ከ6 - 8 ጊዜ እንዲሰሩ ማድረግ።
• ፊሽካ
የክፍል አደረጃጀት፦ በ4/5 - በእረድፍ ሰልፍ ማሰለፍ፣ በ4/5 - ግማሽ ክብ ቅርፅ ማሰለፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፦
እግርን በማጣመር እጅን ወደ ጎን መዘርጋት፣
እግርን ፊትና ኋላ በማድረግ እጅን ወደ ጎን መዘርጋት፣
አንድ እግርን ወደ ኋላ በማንሳት በአንድ እግር እጅን ዘርግቶ ሚዛን መጠበቅ፣
በመካከል ዕረፍት በመስጠት በቅደም ተከተሉ መሰረት ከ6 - 8 ጊዜ ደጋግሞ እንዲሰሩ ማድረግ።
ክትትል እና ግምገማ፡-
ውስብስብ እና ተከታታይ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን ከድምፅ / ከቁጥር / ጋር አቀናጅተው እንዲሰሩ በማድረግ በምልከታ
መከታተልና ስለ አሰራራቸው አስተያየት መስጠት።
ከድምፅ / ከምት / ጋር በማዋሀድ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በተግባር እንዲሰሩ በማድረግ በምልከታ መረዳታቸውን
ማረጋገጥ።
ሀ. አቀናጅቶ የመስራት አቅምን ይጨምራል፣ ለሰማነዉ፣ ላየነዉ፣ ለቀመስነዉ፣ ለዳሰስነዉ ነገር ፈጣን ምላሽ የመስጠት ክህሎትን
ማዳበር ወዘተ……።
ምዕራፍ
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ያውቃሉ።
ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ያደንቃሉ።
ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
የሰዉን ችግር እንደራሳቸዉ አድርገዉ ከግምት ዉስጥ በማስገባት ይገነዘባሉ።
መግለጫ
ጨዋታዎች እና ዉድድሮች የተማሪዎችን ማህበራዊ መስተጋብር ለማጎልበት ያላቸዉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነዉ። በጨዋታዎችና
በስፖርታዊ ዉድድሮች ጊዜ የመናደድ፣ የመቆጣት፣ አንዱ የሌላዉን ስሜት ከመረዳት ይልቅ የራስን ፍላጎት ብቻ መከተል ይታያል።
እነዚህ ያልተገቡ ስሜቶችን በጨዋታዎችና በስፖርታዊ ዉድድሮች ህግ በማስተካከል መግባባትን ማሳደግ ይቻላል።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ክትትል እና ግምገማ፦
የራስን ሚና በማወቅ እንቅስቃሴዎችን በጋር ተቀናጅተው ሲሰሩ በምልከታ መከታተልና አሰራራቸው ላይ አስተያየት
መስጠት።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ዝርዝር ዓላማዎች፦
• ስዕሎች /ፖስተሮች /
ተግባር፦ ሐ. ነካሁኝ
ክትትል እና ግምገማ
ማህበራዊ መስተጋብርን በሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆናቸውን በምልከታ መከታተል።
ዉሳኔ የመስጠት ክህሎትን የሚያሻሽሉ ጨዋታዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያደርጉትን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ።
ለ. የአማርኛ፣ የሂሳብ፣ የሙዚቃ፣ የስነ- ጥበብ አና ሌሎች የትምህርት ይዘቶችን እያዝናኑ አይረሴ አድርጎ ለማስተማር ያስችላል።
ምዕራፍ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 23
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
ጤናና የአካል ብቃትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ያውቃሉ።
ጤናና የአካል ብቃትን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።
ጤናና የአካል ብቃትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሳሴዎችን ይሰራሉ።
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በመስራት መሰረታዊ ክሎትን ያዳብራሉ።
ጤናና የአካል ብቃትን የሚያዳብሩ እንቀቅስቃሴዎችን ለመስራት ይነሳሳሉ።
መግቢያ
ልብ፣ ሳንባ፣ የአየርና የደም ቧንቧዎች መደበኛ ተፈጥሯዊ ተግባራቸዉን ድካምን እየተቋቋሙ መስራት እንዲችሉ መሰረታዊ
እቅስቃሴዎችን በአግባቡና በመደበኛነት መስራት ይገባል።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ተግባር፦ ቀ. በቦታ ላይ ሩጫ
ክትትል እና ግምገማ፦
የልብና የሳንባ ብርታትን በሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ በንቃት እየተሣተፉ መሆናቸውን በምልከታ መከታተል።
የልብና የሳንባ ብርታት ችሎታን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን እንዲናገሩ በቃል መጠየቅ።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ተግባር፦ ሸ. እግርን በጎን በኩል ፊትና ኋላ አድርጎ በሁለት እጅ የፊት እግርን መንካት
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
አንድ እጅና እግር መጀመሪያ ወደ ፊት እየሄደ ቀሪዉ እየተከተለ እንደ እንቁራሪት አስመስሎ ወደ ፊት ከ5 – 10 ሜትር መሄድ፣
ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ከ6 - 8 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት።
ክትትል እና ግምገማ፡-
የጡንቻ ብርታትን በሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ በንቃት እየተሳተፉ መሆናቸውን በምልከታ መከታተል።
የጡንቻ ብርታት ችሎታን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን እንዲናገሩ በቃል መጠየቅ።
ሀ. እቃዎችን ለማንሳትና ለመያዝ፣ ዳገትን በቀላሉ ለመዉጣት፣ ጡንቻዎቻችን ተግባራትን በሚሰሩበት ጊዜ ቶሎ አንዳይደክሙ
ወዘተ… ይጠቅማሉ።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ክትትል እና ግምገማ፡-
የመሳሳብና የመተጣጠፍ ተግባራትን በሚሰሩበት ጊዜ በንቃት መሳተፋቸውን በምልከታ መከታተል።
የመተጣጠፍ ችሎታን የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን እንዲናገሩ በቃል መጠየቅ።
ምዕራፍ
5 ጅምናስቲክስ
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 21
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
መሰረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ያዉቃሉ።
መሰረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
መሰረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ፍላጎት ያሳያሉ።
መግቢያ
የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ሰዉነታችንን ቀልጣፋ በማድረግ በቀላሉ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ተንቀሳቅሶ የመስራት አቅምን
ይጨምራሉ።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ተግባር፦ ለ. ወገብ በመያዝ በተመሳሳይ እግር መሪነት በቀጥታ መስመር እንደ ፈረስ
አስመስሎ መጋለብ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕሎች / ፖስተሮች /፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ክትትል እና ግምገማ፡-
በምልከታ እያንዳንዱን ተግባር ላይ ያላቸዉን ተግባራዊ ተሳትፎና ችሎታ መመልከት
ወዘተ… ናቸዉ።
ምዕራፍ
አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፦
በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎችን ያዉቃሉ።
በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎችን በተግባር ይጫወታሉ።
በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች ለጤናቸዉ የሚሰጠዉን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።
መግለጫ
አንድ ማህበረሰብ ማንነቱን ከሚገልፅባቸዉ መንገዶች ዉስጥ ባህላዊ ጭፈራዎችና ባህላዊ ጨዋታዎቸ አንዱ መንገድ ናቸዉ።
ንዑስ ርዕስ፦ 6.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎች (10- ክ/ጊዜ)
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ማስታወሻ፦ በቀረበዉ ምሳሌ መሰረት በሠፈራቸዉ እና በአካባቢያቸዉ የሚዘወተሩ የሴቶች ባህላዊ ጭፈራዎችን እዲያመጡ
በማድረግ ያመጡትን ባህላዊ ጭፈራዎች እንደየዘፈኖቹ ባህሪያት ከልዩ ልዩ የሰዉነት ክፍሎች ጋር አቀናጅተዉ በእንቅስቃሴዎች
እንዲሰሩ ማድረግ።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 2ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 62
ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች
ተግባር-1
ለ. በአካባቢያቸዉ የወንዶች ባህላዊ ጭፈራዎችን ይለያሉ፣ ከሰዉነት ክፍሎቻቸዉ ጋር አቀናጅተዉ በመስራት ጤንነታቸዉን
ይጠብቃሉ።
ሀ. ሴቶችና ወንዶች በጋራ ተቀናጅተዉ ስራዎችን ቢሰሩ ዉጤታማ እንደሚሆኑ ይረዳሉ፣ እርስበርስ የምዳዳት ባህላቸዉን ያጎለብታሉ፣
ከልዩ ልዩ የሰዉነትታቸዉ ክፍል ጋር አቀናጅተዉ በመስራት ጤንነታቸዉን ይጠብቃሉ።
ዝርዝር ዓላማዎች፦
ለ.የአካባቢያዉን ጨዋታዎች ይለያሉ፣ ከሰዉነት ክፍሎቻቸዉ ጋር አቀናጅተዉ በመስራት አካላቸዉን ያዳብራሉ፣ ጤንነታቸዉን
ይጠብቃሉ ….።
ሀ. በአካባቢያቸዉ ሴቶችና ወንዶች የሚጫወቷቸዉን ባህላዊ ጨዋታዎችን ይለያሉ ፤ ጨዋታዎቹን ከእንቅስቃሴዎች ጋር በማቀናጀት
ጤናንና የአካል ብቃታቸዉን ያሻስላሉ ። ከበርካታ ባህላዊ ጨዋታ አንድ ምሳሌ ፡-
ተግባር፦ ሀ. አያጅቦ - ጅቦ
ተማሪዎች : አያ ጅቦ - አለህ ?
ጅብ ፡ አዎ አለሁ
ተማሪዎች : ምን እየሰራህ ?
ጅብ ፡ እየተራመድኩ
ተማሪዎች : አያ ጅቦ - አለህ ?
ጅብ ፡ አዎ አለሁ
ተማሪዎች : ምን እየሰራህ ?
ጅብ ፡ እናንተን ልበላ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ስዕል /ፖስተሮች/፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ
ተግባር፦ ለ. እንጫወት ዛሬ
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 2ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 65
ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች
ማስታወሻ፦ ጉልበቴ በርታ በርታ፣ እንሂድ በጫካ፣ ልጅ ለመፈለግ መጥተናል፣ አንድ ጊዜ፣ ቀዩ ወፍ እና ሌሎች በሰፈራቸዉና
በአካባቢያቸዉ ተዘዉትረዉ የሚጫወቷቸዉን እንዲያመጡ በማድረግ ከሰዉነት ክፍሎች ጋር አቀናጅተዉ በተግባር አንዲጫወቷቸዉ
ማድረግ።
ክትትል እና ግምገማ፡-
ባህላዊ ጭፈራዎችንና ባህላዊ ጨዋታዎችን ከእንቅስቃሴ ጋር ያላቸዉን አዛምዶ የመተግበር ክህሎታቸዉን መመልከት።