You are on page 1of 68

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የመምህር መምሪያ
1ኛ ክፍል

አዘጋጆች
አቶ አዳነ እሸቱ (Msc)

አቶ መስፍን ከተማ (Msc)


አርታኢዎች
አቶ እንድርያስ ገብረአብ (Msc)

አቶ አማረ መብራት (Msc)


ቡድን መሪ
ዶ/ር ተከተል አብርሃም
ዲዛይነር
አትርሳው ጥግይሁን

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ


ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተመደበ በጀት
በአብክመ ትምህርት ቢሮና በምሁራን መማክርት ጉባዔ ትብብር ነው።

የመጽሐፉ ሕጋዊ የቅጂ ባለቤት © 2015 ዓ.ም. አብክመ ትምህርት ቢሮ ነው።

ምሁራን መማክርት ጉባዔ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ


ማውጫ
ምዕራፍ 1
መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት
1.1. ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች.....................................1
1.1.1 የእግር ጉዞ......................................................................................................1
1.1.2 ሩጫ...............................................................................................................5
1.1.3 ዝላይ..............................................................................................................6
1.1.4 መንጠር..........................................................................................................9
1.1.5. መንሸራተት.................................................................................................10
1.2. በቦታ ላይ በመሆን ከወገብ በላይ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች.......................11
1.2.1 የመሳሳብና የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎች..........................................................11
1.2.2 በቦታ ላይ በመሆን ከኳስ ጋር ከወገብ በላይ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች..................13
1.2.3. ማንጠር.......................................................................................................15
1.3. ከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች..................................................................15
1.3.1. ኳስ በእግር መምታት .................................................................................15
ምዕራፍ 2
ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት
2.1.ቀላል ተከታታይ ወይም የተለያዩ ሪትሚካዊ / የምት / እንቅስቃሴዎች............... 18
2.2. ውስብስብ ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው ሪትሚካዊ / የምት /የእንቅስቃሴ ክህሎት.21
ምዕራፍ 3
ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
3.1. ራስን የማወቅና የመቆጣጠር ክህሎትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች.........................25
3.2. ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያዳብሩ ጨዋታዎች ...................................................27
3.3. ዉሳኔ ሰጭነትን የሚያዳብሩ ጨዋታዎች..............................................................30
ምዕራፍ 4
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ
4.1 የልብና ስርዓተ ትንፈሳ ብርታትን የሚያዳብሩ እቅስቃሴዎች....................................34
4.2 የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች..........................................................39
4.3. መሳሳብና መተጣጠፍን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች................................................42

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ iii


ምዕራፍ 5
ጅምናስቲክስ
5.1. መሰረታዊ የጅምናስቲክስ እቅስቃሴዎች.................................................................47
5.2. ሚዛን መጠበቅ...................................................................................................51
5.3. ከወገብ በላይ የሚሰሩ የካለስተነቲክስ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች.........................56
ምዕራፍ 6
የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች
6.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎች..............................................60
6.1.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶች ባህላዊ ጭፈራዎች............................60
6.1.2. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የወንዶች ባህላዊ ጭፈራዎች.........................60
6.1.3. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶችና የወንዶች ባህላዊ ጭፈራዎች...........61
6.2. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታዎች..............................................61
6.2.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶች ባህላዊ ጨዋታዎች...........................61
6.2.2. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የወንዶች ባህላዊ ጨዋታዎች.........................62
6.2.3. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶችና የወንዶች ባህላዊ ጨዋታዎች...........62

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ iv


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

ምዕራፍ

1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 23

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-


ƒƒ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን የአሰራር ቅደም ተከተላቸውን ያውቃሉ።
ƒƒ በአንድ ቦታ ሆኖ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በመስራት መሰረታዊ የእንቅስቃሴ ብቃታቸውን ያሳድጋሉ።
ƒƒ ከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ስሜታዊ እና ማህበራዊ ክህሎቶችን ያዳብራሉ።
ƒƒ የመሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎቶችን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

መግለጫ፡-
ይህ ምዕራፍ በዋናነት ከቦታ ቦታበመንቀሳቀስ፣ በአንድ ቦታ በመሆንና ከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በውስጡ
የያዘ ነው።

1.1. ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች (6 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች የአሰራር ቅደም ተከተልን ይዘረዝራሉ።
ªªከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች በተግባር ይሰራሉ።
ªªከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች ያላቸውን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

1.1.1 የእግር ጉዞ

ተግባር፦ ሀ. በጥንድ እጅ ለእጅ በመያያዝ ወደ ፊት መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 1


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በመሆን እጅ ለእጅ በመያያዝ ደርሰው እንደሚመለሱ ማሰረዳት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የድምጽ ምልክት ሲሰጥ በጥንድ እጅ ለእጅ በመያያዝ ከ20—30 ሜትር በመራመድ ደርሶ መመለስ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት በተደጋጋሚ እንዲሰሩት ማደረግ አስፈላጊ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ጥንድ ለጥንድ እጅ ለእጅ በመያያዝ በትክክል ሲራመዱ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ ጥንድ ለጥንድ እጅ ለእጅ በመያያዝ የመራመድን ጥቅም በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ለ. እጅ ለእጅ በመያያዝ በቡድን ወደ ፊት መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ 4 ተማሪዎች በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የትምህርቱን ርዕስና ዝርዝር ዓላማዎችን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ አራት አራት በመሆን እጅ ለእጅ በመያያዝ መዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ መራመድ የሚል የትዕዛዝ በቃል ሲያሰማ ተማሪዎች ወደ ፊት እስከ 20 ሜትር ተራምደው መመለስ፣
ƒƒ በጉዞ ውቅት መጀመሪያ የእግር መዳፍ መሬትን ከነካ በኋላ የእግር ተረከዝ መንካት ይኖርበታል፣ የሰውነት ክብደት ከፊተኛው
እግር ላይ ይውላል። በዚህ ሁኔታ በመያያዝ ወደፊት መጓዝ ይችላሉ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም ለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት በተደጋጋሚ እንዲሰሩት ማደረግ፣
ƒƒ በመጨረሻም ሰውነታቸውን እንዲያቀዘቅዙ ማድረግ ተገቢ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ለእጅ በመያያዝ ወደ ፊት በትክክል ሲራመዱ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ሲሰሩ ምንያህል እንዳስደሰታቸው በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ሐ. በቀጥታ መስመር መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አፈር፣ አመድ፣ ኖራ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 2


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ እስከ 5 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ቀጥ ብሎ በተሰመረው ቀጥታ መስመር ከኋላ ይቆማሉ፣
ƒƒ አንደኛውን እግር ቀጥ ባለው መስመር ላይ በማሳረፍ ሌላኛውን እግር ማስከተል፣
ƒƒ ሰውነታቸውን ቀጥ በማድረግ መስመሩን ሳይለቁወደፊት መጓዝ፣
ƒƒ በመጨረሻም የእንቅስቃሴ ድግግሞሹን ከ3—5 ጊዜ በማድረግን በየዙሩ መካከል40 ሴኮንድ በማሳረፍ ማሰራት አስፈላጊ
ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቀጥታ መስመር ለመራመድ ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በቀጥታ መስመር እንዲራመዱ በቃል መጠየቅ እና መመልከት፣

ተግባር፦ መ. በአራት ማዕዘን ላይ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አፈር፣ አመድ፣ ኖራ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ1—2 ተማሪዎችን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ በማስከተል ቀጥ ብሎ በመቆም በተሰመረው አራት ማዕዘን ለመራመድ ከአንዱ ጫፍ ከኋላ በመቆም ራስን ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ምልክት ሲሰጥ የአራት ማዕዘን ሳይለቁ የሰውነት ሚዛንን በመጠበቅ ሰውነታቸውን ቀጥ በማድረግ ወደ ፊት
እንዲራመዱና ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም 30 ሴኮንድ እረፍት እንዲያደርጉ በማድረግ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በአራት ማዕዘን ላይ መራመድ ለምን እንዳስፈለገ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ሠ. በክብ መስመር ላይ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አፈር፣ አመድ፣ ኖራ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ1—3 ተማሪዎችን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ በመቀጠል ቀጥ ብሎ በመቆም በተሰመረው ክብ መስመር ለመራመድ ራስን ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ የክቡን መስመር ሳይለቁ የሰውነት ሚዛንን በመጠበቅ ሰውነታችን ቀጥ በማድረግ ወደፊት መጓዝ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 3


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

ƒƒ ከ3—5 ጊዜ እንቅስቃሴውን በመደጋገም እንዲሰሩ በማድረግ በየዙሩ መካከል 40 ሴኮንድ ማሳረፍ ያስፈልጋል።
ƒƒ በመጨረሻም ሰውነታቸውን እንዲያቀዘቅዙ ማድረግ ተገቢ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በክብ መስመር ላይ በትክክል ሲራመዱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. በዝግዛግ መስመር ላይ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አፈር፣ አመድ፣ ኖራ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ተራቸውን በመጠበቅ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ በቅድሚያ ቀጥ ብሎ በመቆም በተሰመረው ዝግዛግ መስመር ለመራመድ ከአንዱ ጫፍ ከኋላ በመቆም ራስን ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል መልክት ሲሰጥ የዝግዛጉን መስመር ሳይለቁ የሰውነት ሚዛንን በመጠበቅ ሰውነታቸውን ቀጥ በማድረግ ወደፊት
መጓዝ፣
ƒƒ በመጨረሻም ሰውነታቸውን እንዲያቀዘቅዙ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በዝግዛግ መስመር ላይ ለመራመድ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፡-ሰ.ኳስ በእጅ ማንከባለል

አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-


ƒƒ ትንንሽ ኳሶች፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—8 ተማሪዎችን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ በማስከተል ኳስ በእጅ በመያዝ መዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ምልክት ሲሰጥ ፊት ለፊት ላለው ጓደኛ በመሬት በማንከባለል መስጠት፤ ይህን ጨዋታ ከ5—7 ጊዜ በመደጋገም
እስከ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት እንዲሰሩት ማድረግ ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ኳስ በእጅ በትክክል ሲያንከባልሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 4


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

1.1.2 ሩጫ

ተግባር፦ ሀ. በቦታ ላይ ሩጫ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ ግራ እጅን ከክንድ በማጠፍ ከቀኝ እግር ጋር በማጣመር መዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ቀይሩ ሲል ቀኝ እጅን ከክንድ በማጠፍ ከግራ እግር ጋር ማጣመር፣
ƒƒ ስሩ የሚል የድምፅ ምልክት ሲያሰማ ተማሪዎችበቦታ ላይ ሩጫውን ይሰራሉ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ለ1 ደቂቃ እረፍት እየወሰዱ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ፤ በመጨረሻም ሰውነታቸውን
የማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቦታ ላይ ሩጫ ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በቦታ ላይ ሩጫ መስራት ከሚሰጣቸው ጥቅሞች ውስጥሶስቱን እንዲዘረዝሩ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ለ. እጃችንን እንደ ንስር ክንፍ በማድረግ መብረርን ማስመሰል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ የንስር ስዕል የሚመስል ስዕላዊ መግለጫ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ3—5 ተማሪዎችን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎች እጃቸውንእንደ ንስር ክንፍ በማድረግ መብረርን ለማስመሰል በመዘርጋት ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ እጃቸውን እንደ ንስር ክንፍ በማድረግ መብረርን በማስመሰል ከ10—15 ሜትር ደርሰው እንዲመለሱ
ማድረግ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ እንቅስቃሴውን ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማለማመድ፤ በእንቅስቃሴው መካከል እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት
ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጃቸውን እንደ ንስር ክንፍ በማድረግ መብረርን ለማስመሰል ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ እጃቸውን እንደ ንስር ክንፍ በማድረግ መብረርን ለማስመሰል እንዲሰሩ በቃል መጠየቅና ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 5


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

ተግባር፦ ሐ. በቡድን የሶምሶማ ሩጫ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ተማሪዎችን በቡድን በማድረግ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በእያንዳንዱ ቡድን ከ5—10 ተማሪዎችን የያዘ አባላት በቡድን ማደራጀት፣
ƒƒ የቀኝ እጅን ከክርን በማጠፍ እና ግራ እግር ከጉልበት በማጠፍ መዘጋጀት፣
ƒƒ በ20 ሜትር ርቀት ላይ ምልክት ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ የፊሽካ ድምጽ ሲያሰማ በቡድን የሶምሶማ ሩጫ ከምልክቱ ደርሰው እንዲመለሱ ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ለ1 ደቂቃ እረፍት እየወሰዱ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ የሶምሶማ ሩጫ ለመስራት ሲነሳሱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው ተስማሚ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

1.1.3 ዝላይ

ተግባር፦ ሀ. እንደ ካንጋሮ በሁለት እግር አስመስሎ እየዘለሉ መሄድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ተያያዥነት ያላቸው ስዕሎች፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎችበሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ ሁለት እግር በመግጠም ወይም በመክፈት እጅ ወደ ኋላ በመዘርጋት ከጉልበት ሸብረክ በማለት ክርን ላይ በማጠፍ ማዘጋጀት፣
ƒƒ በመምህሩ ትዕዛዝ በሁለት እግር በመነሳት እንደ ካንጋሮ በሁለት እግር ወደ ላይ የመዝለል እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ5—7 ጊዜ በመደጋገም1 ደቂቃእረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንደ ካንጋሮ በሁለት እግር ወደ ላይ በመዝለል ማስመሰል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. ፊት ለፊት በመሆንበጥንድ በሁለት እግር መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 6
ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ በመሆን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና እንዲያሳስቡ ማድረግ፣
ƒƒ ተማሪዎችንጥንድ እየሆኑ ፊት ለፊት በማቆም ማዘጋጀት፣
ƒƒ በመካከላቸው የ 1.5 ሜትርርቀት እንዲኖራቸው ማድረግ፣
ƒƒ እጃቸውን ከክንዳቸውና እግራቸውን ከጉልበታቸው በማጠፍ ለእንቅስቃሴው ራስን ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ በሁለት እግር እየዘለሉ ማረፍ ይጀምራሉ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—5ጊዜ በመደጋገም1 ደቂቃእረፍት በመስጠት በጥንድ ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በጥንድ ፊት ለፊት በመሆን በሁለት እግር በሚዘሉበት ጊዜ ሲደሰቱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. ሶስት ለሶስት ሆኖ በነጻነት ወደ ላይ መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በቡድን ሶስት ሶስት ተማሪዎች ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በእያንዳንዱ ቡድን ሶስት ተማሪ በመሆን ወደ ላይ እስከቻሉ ድረስ እየዘለሉ እንዲያርፉ ማድረግ፤ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—5
ጊዜ በመደጋገም ለ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት በጋራ ማስራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሶስት ሆኖ በነጻነት ወደ ላይ በትክክል ሲዘሉ መደሰታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. በቡድን ሆኖ በነፃነት ወደ ላይ መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ በሁለት እግር ለመዝለል በሚያስችል በቂ ቦታ ላይ እራሳቸውን ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ከመምህሩ ሲሰጣቸው በአንድ ጊዜ ተማሪዎች ወደ ላይ በሁለት እግር እየዘለሉ እንዲያርፉ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገምና እረፍት በመስጠት ተማሪዎች በሙሉ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቡድን ሆኖ ወደ ላይ ሲዘሉ የአነሳስና የአስተራረፍዘዴዎችን በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 7


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

ተግባር፦ ሠ. ዝላይ አንድ-ሁለት-አንድ-ሁለት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ከሽቦ፣ ከፕላስቲክ ወይም ከሌላ ነገር የተሰራ ቀለበት፣ ተዛማችስዕሎች፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስና ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6ተማሪዎችን በየቡድኑ ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ ሰውነታቸውን አሟሙቀውከቀለበቱ ውጭእንዲቆሙማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ አንድ ቁጥር ሲል ሁለት እግርን በአንድ ቀለበት ውስጥ ማስገባት ሁለት ቁጥር ሲል በአንድ ጊዜ ቀኝ እግርን ከአንዱ
ቀለበት ግራ እግርን ደግሞ ከሌላኛው ቀለበት ውስጥ እንዲያሳርፉ ማድረግ
ƒƒ በዚህ ሁኔታ ዝላዩን አንድ-ሁለት-አንድ-ሁለት በሚል ትዕዛዝ እየሰጠ እንዲተገብሩ በማድረግ ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ለ1
ደቂቃ እረፍት በመስጠት ማሰራት ተገቢ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በሁለት እግር በመነሳት በሁለት እግር ቀለበት ውስጥ በትክክል ሲያርፉ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በሁለት እግር በመነሳት በሁለት እግር ቀለበት ውስጥ ማረፍ የሚሰጠውን ጠቀሜታ እንዲገልጹ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ረ. ዝግዛግ በተቀመጠ ቀለበት ውስጥ በሁለት እግር መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ከሽቦ ወይም ከፕላስቲክ የተሰራ ቀለበት፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ እስከ 6 ተማሪዎችን በአንድ ቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ተማሪዎች በአንድ ቡድን እስከ 6 ተማሪዎችን በማደራጀት ማዘጋጀት፣
ƒƒ ቀለበት ከ40-----50 ሴንቲ ሜትር ልዩነትበዝግዛግ መስመር በማስቀመጥ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ከመምህሩ ሲሰጥ ተማሪዎች እየዘለሉ ከቀለበቱ ውስጥ በሁለት እግር በማረፍ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት እየሰጡ ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ዝግዛግ በተቀመጠ ቀለበት ውስጥ በሁለት እግር ለመዝለል ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ ዝግዛግ በተቀመጠ ቀለበት ውስጥ በሁለት እግር ሲያርፉ በዋናነት የሚሰማቸው የትኛው የሰውነት ክፍል እንደሆኑ በቃል
መጠየቅ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደ ሁኔታው የሚመጥን ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ተገቢ ነው።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 8


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

1.1.4 መንጠር

ተግባር፦ሀ. በአንድ እግር መንጠር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ2—4 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ በቀኝ እግር በመቆም መዘጋጀት፣
ƒƒ ግራ እግርን በማንሳት ከጉልበት ማጠፍ፣
ƒƒ በቆሙበት እግር ወደላይ በመዘለልእየደጋገሙ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ባልሰራው እግር ከላይ በተገለፀው የአሰራር ቅደም ተከተል መሠረት ደጋግመው ማሰራት፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚ በየዙሩ ለ1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ማሰራት ተገቢ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በአንድ እግር ለመንጠር ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. በአንድ እግር ዘሎ መሀረብን መንካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች /ማቴራያሎች /፡-
ƒƒ መሀረብ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎችን ከሁለት በመክፈል


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ መምህሩ በቀኝናበግራ እጆቹ መሀረብ ይዞ በመቆምይዘጋጃል፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲያሰማከየቡደኑ አንዳንድ ተማሪዎችን በየተራ እየሄዱ በአንድ እግር ዘለው መሀረቡን
እንዲነኩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በሌላኛው እግር ማሰራት፣
ƒƒ ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ እንቅስቃሴውን በመስራት ለ1 ደቂቃ እረፍት መስጠት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በአንድ እግር ዘሎ መሀረቡን በትክክል ለመንካት ሲሞክሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. በአንድ እግር እየነጠሩ በሁለት እግር ማረፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አመድ፣ ኖራ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 9


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ በግልተራቸውን በመጠበቅ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ አመድ ወይም ኖራ በመጠቀም ከተማሪው መማሪያ መጸሐፍት ያለውን ስዕል መሬት ላይ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ተማሪውን/ዋን ከመስመሩ ኋላ ማቆም፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ በአንድ እግር ሶስት ጊዜ በተከታታይ መዝለል፣
ƒƒ ከዚያም በሁለት እግር ማረፍ፤እንደገና በአንድ እግር በመዝለል፤ከዚያም በሁለት እግር ማረፍ፤ እንደገና በአንድ እግር
በመዝለል መጨረስና እንዲመለሱ ማድረግ፤ ከላይ በተቀመጠው የአሰራር ቅደም ተከተል መሰረት ባልሰራው እግር ማሰራት፤
ይህን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚለ1 ደቂቃ እረፍት እየሰጡ ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በአንድ እግር እየነጠሩ በሁለት እግር ሲያርፉ ያለውን ጠቀሜታ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ መ. በአንድ እግር እየነጠሩ ክብ ዉስጥ ማረፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ከጎማ ወይም ከሽቦ የተሰራ ቀለበት፣ አመድ፣ ኖራ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—7 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ መምህሩ አመድ ወይም ኖራ በመጠቀም ክብ መስመር ማስመር ወይም ከጎማ ወይም ከሽቦ የተሰራ ከ5—6
ቀለበት መሬት ላያ በመደርደር መዘጋጀት፣
ƒƒ ተማሪዎች ከቀለበቱ ውጭ በመሆን ቁመው እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
ƒƒ ትዕዛዝ ከመምህሩ ሲሰጥ በአንድ እግር እየነጠሩ ወደፊት በቀለበቶች መሄድ፣
ƒƒ ያልሰራውን እግር ከላይ በተገለፀው የአሰራር ቅደም ተከተል መሠረት ደጋግመው እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ከ4—6 ጊዜ በተደጋጋሚ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በአንድ እግር በክብ ውስጥ እየነጠሩ ሲሄዱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው የሚመጥን ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

1.1.5. መንሸራተት

ተግባር፦ ሀ. ወደግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ መንሸራተት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 10


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ አንድ እግር ወደ ጎንበመዘርጋት ማዘጋጀት፣
ƒƒ እንቅስቃሴ ወደቀኝ ወይም ወደግራ አቅጣጫ በተከታታይ ከ2—3 ጊዜ እንዲሸራተቱ ማድረግ፣
ƒƒ ባልሰራው አቅጣጫ ማሰራት፣ ይህን እንቅስቃሴው ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ በየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት
ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ በትክክል ሲንሸራተቱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

1.2. በቦታ ላይ በመሆን ከወገብ በላይ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎች (5 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªበቦታ ላይ በመሆን ከወገብ በላይ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎችንይገልጻሉ።
ªªበቦታ ላይ በመሆን ከወገብ በላይ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎችንበተግባር ይሰራሉ።
ªªበቦታ ላይ በመሆን ከወገብ በላይ የሚሰሩ መሠረታዊ እንቅስቃሴዎችንለመስራት ፍላጎት ያሳያሉ።

1.2.1 የመሳሳብና የመተጣጠፍ እንቅስቃሴዎች

ተግባር፦ ሀ. ወደ ፊት በማጎንበስ የእግር ጣት መንካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ እግራቸውን ገጥመው እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲያሰማ እጅን ወደ ላይ በማንሳት ከወገብ በማጎንበስ የእግር ጣት መንካት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በዙር ከ3—5 ጊዜ በተከታታይ እንዲሰሩ በማድረግ በየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት
ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደ ፊት በማጎንበስ የእግር ጣት መንካት በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. ወደ ፊት፣ ወደ ኋላ፣ ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ መታጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 11


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ በአንድ ቡድን ከ4—5 ተማሪዎች ይኖሩታል፣


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ርዕሱንና አላማውን ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ በመጀመሪያ ሁሉም ተማሪዎች ቀጥ ብለው እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፡
ƒƒ መምህሩ አንድ ቁጥር ሲል በማጎንበስ የእግር ጣት በእጅመያዝ፤ ሁለት ቁጥር ሲል ወደ ነበሩበት መመለስ፤ ሶስት ቁጥር ሲል
የላይኛውን የሰውነት ክፍል ወደ ኋላያዘነብላሉ፤ አራት ቁጥር ሲል ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመልሱ ማድረግ፣
ƒƒ አምስት ቁጥር ሲል ከወገብ በላይ ያለው የሰውነት ክፍል ወደ ግራ አቅጣጫ ይታጠፋሉ፣
ƒƒ ስድስት ቁጥር ሲል ወደ ነበረበት አቅጣጫ ይመለሳሉ፤ ሰባት ቁጥር ሲል ወደ ቀኝ አቅጣጫ ያጎነብሳሉ፤ ስምንት ቁጥር ሲል
ወደ ነበሩበት ቦታ ይመለሳሉ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ከ4—6 ጊዜ በተደጋጋሚ በማሰራት በየዙሩ ለ1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት እንዲሰሩ ማድረግ ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደቀኝ እና ወደ ግራ አቅጣጫ ሲታጠፉ ትክክል መሆናቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. ወደፊት በማጎንበስ በእጅ መዳፍ መሬት መንካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን በትክሻ ስፋት ልክ ከፍተው እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲያሰማ በማጎንበስ በእጅ መዳፍ መሬት መንካት፣
ƒƒ እንደገና ወደ ነበሩበት ቦታ መመለስ፤ በእንቅስቀሴው መካከል በየዙሩ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—4 ጊዜ በተደጋጋሚ
ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደፊት በማጎንበስ በእጅ መዳፍ መሬት በትክክል ለመንካት ሲሞክሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. በሆድ በመተኛት አንድ እጅ እያፈራረቁ ወደ ላይ ማንሳት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁለት እግርን ገጥሞ የእግር ጣቶችን ወደኋላ በማድረግበሆድ መተኛት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ከመምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ እጅ ወደላይ እያፈራረቁ ማሰራት፤ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—6 ጊዜ በየዙሩ ለ40
ሴኮንድ እረፍት በመስጠት በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 12
ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በመተኛት እጅ ወደ ላይ ማንሳት የሚሰጠውን ጠቀሜታ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ሠ. ሁለት እጆችን ወደ ላይ አጣምሮ ማሳሰብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት፣ ፊትና ኋላ በማድረግ ወይም በመግጠም መቆም፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ እጅ በአንድ ላይ በማጣመር መዳፍ ወደ ላይ መሳብ፣
ƒƒ እንደገና ወደ ነበሩበት መመለስ፤ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚበየዙሩ 30 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት
ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሁለት እጆችን ወደ ላይ አጣምሮ በትክክል ሲያሳስቡ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. በመቀመጥ እግርን በመዘርጋት ወደ ፊት መሳብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ መሬት ላይ በመቀመጥ ሁለት እግራቸውን ገጥመው እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲያሰማ ሁለትእጅ ወደላይ በማንሳት በአቅማቸው ልክጣታቸውን መንካት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በየዙሩ 30 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ እየደጋገሙ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ በመቀመጥ እግርን በመዘርጋት ወደ ፊት ሲሳቡ የትኛውን የሰውነት ክፍል እንደሚሰማቸው በቃል መጠየቅ፣
ƒƒ በመቀመጥ እግርን በመዘርጋት ወደ ፊት ለመሳብ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

1.2.2 በቦታ ላይ በመሆን ከኳስ ጋር ከወገብ በላይ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች

ተግባር፦ ሀ. በክብ በመቆም ኳስ ከግራ ወደቀኝ ወይም ከቀኝ ወደግራ ለጓደኛ ማቀበል
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 13


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—8 ቡድን መመደብ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በክብ ተማሪዎች እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ አንዱ ተማሪ ኳስ በመያዝ በቀኝ ወይም በግራ በኩል ኳስ ለጓደኛ እየወረወሩ እንዲያቀብሉ ትዕዛዝ መስጠት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ባልሰራው አቅጣጫ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ኳስን ለጓደኛማቀበል ከ3—5ጊዜ በመደጋገም በማሰራት በየዙሩ ለ1 ደቂቃ እረፍት እንዲያደርጉ ማድረግ ያስፈልጋል።

ማስታዎሻ፡- በክብ በመቆም ኳስን ለጓደኛ መወርወር የሚለውን እንቅስቃሴ በክብ በማስቀመጥ ማሰራት ይቻላል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በክብ በመቆም ኳስ ለጓደኛ በትክክል ሲያቀብሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. በቦታ ላይ ኳስ ከራስ በላይ ወርዉሮ መያዝ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—7 ተማሪዎች በቡድን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ኳስ በሁለት እጅ በመያዝ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ወርውሩ የሚል መምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ በቦታ ላይ ሁኖ ኳስ ከራስ በላይ እየወረወሩ መያዝን እንዲሰሩ ማድረግ፤ በየዙሩ 40
ሴኮንድ እረፍት እየሰጡ ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ ተገቢ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቦታ ላይ ኳስ ከራስ በላይ ወርዉሮ በትክክል ለመያዝ ሲነሳሱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. ወደ ታች፣ ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ኳስ መውሰድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በግል


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን በመግጠም ወይም በመክፈት ኳስ በሁለት እጅ በመያዝ መዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የመምህሩ ቃልሲሰማ በቦታ ላይ ሁኖ ወደ ታች፣ ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ኳስ መውሰድ
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ለ40 ሴኮንድ በየዙሩ እረፍት በመስጠት ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደ ታች፣ ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ኳስ ሲውስዱ የሚያሳዩትን መነሳሳት በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 14


ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

1.2.3. ማንጠር

ተግባር፦ ሀ. ትንንሽ ኳሶችን በቦታ ላይ ማንጠር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በቡድን ከ6—7 ተማሪዎችን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች በቡድን ሁነው በቦታ ላይ ኳስ በአንድ እጅ በየተራ እንዲያነጥሩ
ƒƒ / እንዲለማመዱ / ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ባልሰራው እጅ ማሰራት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ባልሰራው እጅ ከ5—7 ጊዜ በመደጋገምበየዙሩ ለ1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ትንንሽ ኳሶችን በቦታ ላይ በትክክል ሲያነጥሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በሚያነጥሩበት ወቅት ለመስራት ፍላጎት ሲያሳዩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

1.3. ከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች (12 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በመስራታቸው ይደሰታሉ።
ªªከመሳሪያ ጋር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።

1.3.1. ኳስ በእግር መምታት

ተግባር፦ ሀ. በመቆም ኳስ መምታት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ትንሽ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በቡድን ከ5—6 ተማሪዎችን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ኳስን ከእግር ፊት በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ በአንድ እግራቸው ኳስ እንዲመቱ ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ባልሰሩበት እግር እንዲመቱ በማድረግማለማመድ፣
ƒƒ ከ3—5 ጊዜበመደጋገም በየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት እየሰጡእንዲሰሩት ማድረግ ተገቢ ነው።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 15
ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በመቆም ኳስ በትክክል ሲመቱ በምልከታማረጋገጥ፣
ƒƒ በመቆም ኳስ በሚመቱበት ጊዜ ሲደሰቱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. ከአንድ ወይም ከሁለት እርምጃ በኋላኳስ መምታት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ትንንሽ ኳሶች፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—6 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ሚዛናቸውን ጠብቀው በመሰረታዊ አቋቋም እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ ከአንድ ወይም ከሁለት እርምጃ በኋላ ኳስ መምታት እንዲለማመዱ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን ተግባር ከተለማመዱ በኋላ በመንደርደር ኳስ እንዲመቱ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በሌላኛው እግርበየዙሩለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ5—7 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ
ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ከአንድ ወይም ከሁለት እርምጃ በኋላ ኳስ ሲመቱ በምልከታ መረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. ኳስ ለጓደኛ ማቀበል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ትንንሽ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—5 ተማሪዎች በቡድን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች ከተማሪው መጽሐፍ ላይ በተቀመጠው ስዕል መሰረት እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ አንደኛው ተማሪ ኳስ በእግሩ በመምታት ለጓደኛው እንዲያቀብል ማድረግ፣
ƒƒ ባልሰራበት እግር እንዲመታ ማድረግ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታኳስ ለጓደኛ በመምታት ማቀበሉንእንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—6 ጊዜ በመደጋገም በየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ኳስ ለጓደኛ በትክክል ሲያቀብሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. ኳስ ማቀበልና መቀበል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ትንሽ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 16
ምዕራፍ 1 መሠረታዊ የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—6 ተማሪዎች


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎችን በቡድን በመከፋፈል ፊት ለፊት በ5 ሜትር ልዩነት እንዲሰለፉማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ከፊት ያለው ተማሪ ኳስ ፊት ለፊት ላለው ተማሪ በመምታት በማቀበል ከኋላ መሰለፍና ሌላኛው
ተማሪ ኳስ ተቀብሎ በመምታት ከራሱ ቡድን ከኋላ ማሰለፍ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ ጨዋታው ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም በየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት እንዲያገኙ በማድረግ ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ኳስ ማቀበልና መቀበል በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ የቃል ጥያቄ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው የሚመች ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

የመልመጃ መልስ ተግባር፡-1


ƒƒ የእንቅስቃሴ ክህሎታቸውን ያሳድጋሉ፣ እርስ በርስ የመግባባት አቅማቸውን ያሻሽላሉ፣ የአካል ብቃታቸውን ለመጨመር
ይጠቅማል እና ሌሎችን መጥቀስ ይቻላል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 17


ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

ምዕራፍ

2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ


ክህሎት

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 12

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ የሰዉነት እንቅስቃሴዎችን ቀላል ተከታታይ ወይም የተለያዩ የምት/ ሪትሚካዊ / እንቅስቃሴዎች ከሙዚቃ ምት ጋር
በማዛመድ ይተገብራሉ።
ƒƒ ከባድ ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው የምት / ሪትሚካዊ / እንቅስቃሴዎችን ቅደም ተከተል ይገነዘባሉ።
ƒƒ ምትንተከትለው እንቅስቃሴዎችን በመስራት መሰረታዊ ክህሎታቸዉን ያዳብራሉ።
ƒƒ የአካል እንቅስቃሴ ከሙዚቃ ምት ጋር ያለዉን ቅንጅት ያደንቃሉ።።

መግለጫ፡-
ተማሪዎች የሰዉነት እንቅስቃሴዎችን በመጠቀም ከሚዘወተሩ የሙዚቃ ምት ጋር አቀናጅተው በመስራት መሰረታዊ የእንቅስቃሴ
ክህሎታቸዉን ይጨምራል።

2.1.ቀላል ተከታታይ ወይም የተለያዩ ሪትሚካዊ / የምት / እንቅስቃሴዎች (6 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªቀላል ተከታታይ ወይም የተለያዩ ሪትሚካዊ / የምት / እንቅስቃሴዎችንይዘረዝራሉ።
ªªቀላል ተከታታይ ወይም የተለያዩ ሪትሚካዊ / የምት / እንቅስቃሴዎችንበተግባር ያሳያሉ።
ªªቀላል ተከታታይ ወይም የተለያዩ ሪትሚካዊ / የምት / እንቅስቃሴዎችን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

ተግባር፦ ሀ.1,2,3,4 ቁጥሮችን ተከትሎ በቀኝና በግራ መዳፍ ተነካክቶ ከራስ በላይ
ማጨብጨብ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 18


ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ3—5 ተማሪዎችን በአንድ ቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ከ3---5በመሆን ፊት ለፊት በመቀመጥ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩጀምሩ የሚል የትዕዛዝ ድምፅ ሲሰጥ በእጅ መዳፋቸውአንድ፣ ሁለት፣ ሶስት ብለው በመነካካት በአራተኛ ከራስ በላይ
እንዲያጨበጭቡ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—5ጊዜ በመደጋገምበዙር 30 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማስራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ሲሰሩ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. መሬት በመቀመጥ 1,2,3,4 ቁጥሮችን በመጥራት በእጆች መዳፍ መሬትን


በመምታት ከራስ በላይ ማጨብጨብ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በከፊል በክብ መስመር ማስቀመጥ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎችን ክብ ቅርጽ ይዘው ቁጭ እንዲሉ በማድረግ የእጆቻቸውን መዳፍ መሬት በማስቀመጥ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ በተከታታይ ሶስት ጊዜ መሬቱን በእጃቸው መዳፍ በመምታት በአራተኛው ከራስ በላይ
ማጨብጨብ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ5—9 ጊዜ በመደጋገምለ1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ለመስራት ያላቸውን ፍላጎትእና ችሎታ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. እጅ ለእጅ በመያያዝ ፊት ለፊት ማጠፍና መዘርጋት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ በመሆን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን በትክሻ ስፋት ልክ ወይም በመግጠም ፊት ለፊት በመቆምእጅ ለእጅ በመያያዝ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ እጃቸውን በማጠፍና በመዘርጋት እንቅስቃሴውን ማሰራት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በዙርእስከ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ5—8 ጊዜ በመደጋገምእንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ለእጅ በመያያዝ ፊት ለፊት ማጠፍና መዘርጋት በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 19


ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

ተግባር፦ መ. በቦታ ላይ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎችን በሰልፍ ወይም በክብ ማሰለፍ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች ቀጥ ብለው እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ የፊሽካ ድምፅ ሲያሰማ ባሉበት ቦታ እጅ እና እግር በተቃራኒ አቅጣጫ በማቀናጀት እንዲንቀሳቀሱማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—7 ጊዜ በመደጋገምበዙር ለ30 ሴኮንድእረፍት በመስጠት ማስራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቦታ ላይ መራመድ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በቃል መጠየቅ።

ተግባር፦ ሠ. እግርን ከእግር ጋር ማነካካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ጥንድ ለጥንድ በማድረግ ፊት ለፊት እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ ተቃራኒ እግራቸውን እንዲያነካኩት ማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የፊሽካ ድምፅ ወይም ትዕዛዝ ሲያሰማ ባሉበት ቦታ እግራቸውን በተቃራኒ አቅጣጫ እንዲነካካ በማድረግ
እንቅስቃሴውን እንዲቀጥል ማድረግ፣
ƒƒ በእንቅስቃሴው መካከል በቂ እረፍት መስጠት ከ5—7 ጊዜ በመደጋገም ለ30 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማስራት ይቻላል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እግርን ከእግር ጋር በትክክል ሲያነካኩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው የሚስማማ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 20


ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

2.2. ውስብስብ ተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው ሪትሚካዊ / የምት /


(6 ክ/ጊዜ)
የእንቅስቃሴ ክህሎት

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው የምት / ሪትሚካዊ /የእንቅስቃሴዎች ምንነት ያብራራሉ።
ªªተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው የምት / ሪትሚካዊ / እንቅስቃሴዎች በተግባር ይሰራሉ።
ªªተከታታይ እና ቀጣይነት ያለው ሪትሚካዊ / የምት / እንቅስቃሴዎች ያላቸውን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

ተግባር፦ ሀ. እግርና እጅ ወደጎን መዘርጋት እና ወደነበረበት መመለስ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና ዝርዝር አላማዎች ማሰተዋወቅ፣
ƒƒ የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎች እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ፊት ለፊት በመሆንበትክክለኛ አቋቋም ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚልትዕዛዝ መምህሩ ሲያሰማ ተማሪዎች እግርና እጅን መክፈትና መዘርጋት በማቀናጀት ማሰራትና መመለስ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም በየዙሩለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት፣
ƒƒ ሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቀሴዎችን ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ለመስራት ፍላጎት ሲያሳዩ እና ትግበራቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. በእጅ ወገብ መያዝ እና ወደጎን መዘርጋት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት በማቆም ማዘጋጀት፤ በእጅ ወገብ መያዝ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ መምህሩ ሲያሰማ ተማሪዎች እጃቸውን ወደ ጎን መዘርጋት፣
ƒƒ እንደገና ወደነበሩበት መመለስ እና ፈጠን እያሉ እንደገና መስራት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ3—6 ጊዜ በመደጋገም በየዙሩለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 21


ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

ƒƒ በቃል ጥያቄ፣ በምልከታና በሌሎች የምዘና ስልቶች መገምገም

ተግባር፦ ሐ. ወደ ተለያዩ አቅጣጫ መጠማዘዝ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች /ማቴሪያሎች/፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ሰውነታቸውን በሚገባ የማሟሟቅና የማሳሳብ እንቅስቃሴዎችን ማሰራት፣
ƒƒ እግራቸውን በትከሻ ስፋት ልክ ከፍተው እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የፊሽካን ድምፅ መምህሩ ሲያሰማ ተማሪዎች ወደቀኝ አቅጣጫ እንዲዞሩ ማድረግ፣
ƒƒ ከዚያ ወደነበሩበት አቅጣጫ እንዲመለሱ ማድረግ፤ ወደግራ አቅጣጫ በመዞር ማሰራት፤ እንደገና ወደነበረበት መመለስ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በዙር ለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን በትክክል ሲያከናውኑ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. መቆምና ቁጭ ብሎ እግር መያዝ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ ተማሪዎች እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ መምህሩ ሲሰጥ ተማሪዎች ተቀምጠው እግራቸውን እንዲይዙት ማድረግ፣
ƒƒ መነሳት ሲል ከተቀመጡበት እንዲነሳ ማድረግ እና በድምፅ ትዕዛዝ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—6ጊዜ በተደጋጋሚ በማሰራት በየዙሩ 30 ሴኮንድ እረፍት መስጠት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በመቆምና ቁጭ ብሎ እግር መያዝ ለምን እንደሚጠቅም በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ሠ.በሁለት እግር መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ3—5 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 22
ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት እንዲቆሙ ማድረግ፣


ƒƒ እጅ በመዘርጋት ወደ ኋላ እና ወደ ፊት እያደረጉ መዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ መምህሩ ሲያሰማ በሁለት እግር ወደ ላይ እንዲዘሉ በማድረግ ወደ ፊት እንዲሄዱ ማድረግ፣
ƒƒ በሁለት እግር በሚያርፉበት ወቅት ከጉልበት ሸብረክ በማለት ማረፍና ሚዛን መጠበቅ፣
ƒƒ በእንቅስቃሴው መካከል እስከ 1 ደቂቃ እረፍት እንዲያገኙ በማድረግ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በሁለት እግር ሲዘሉየሚያሳዩትን ፍላጎትና አሰራሩንበምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. ቀጥ ባለ መስመር ላይ በሁለት እግር ወደፊትና ወደኋላ መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ አመድ፣ ኖራ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ መምህሩ ቀጥ ያለ መስመር ኖራ ወይም አመድ በመጠቀም ቀጥ ያለ መስመር በማስመር ማዘጋጀት፣
ƒƒ ተማሪዎች እግር ገጥመውእንዲቆሙ በማድረግማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የፊሽካን ድምፅ ወይም ትዛዝመምህሩ ሲያሰማ በሁለት እግር ወደ ፊትና ወደ ኋላ በመዝለል መሰራት፣
ƒƒ በእንቅስቃሴው መካከል እስከ 1 ደቂቃ እረፍት እንዲያገኙ በማድረግ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ማሳሰቢያ፡- ተግባር “ሰ”ን በሁለት እግር ወደ ፊትና ወደ ኋላ መዝለል የሚለውን እንቅስቃሴ

ክብ መስመር በመስራት ከላይኛው ጋር በተመሳሳይ እንዲሰሩት ማድረግ ይቻላል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በሁለት እግር ወደ ፊትና ወደ ኋላ መዝለል የሚሰጠውን ጠቀሜታ በቃል ጥያቄ መጠየቅ፣

ተግባር፡-ሸ. ሁለት እግር ገጥሞ ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ መዝለል

አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-


ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ሁለት እግር በመግጠም እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የፊሽካ ድምፅ መምህሩ ሲያሰማ በሁለት እግር ገጥሞ ከድምፅ ጋር በማቀናጀት ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ
በመዝለል እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ በእንቅስቃሴው መካከል ለ1 ደቂቃ እረፍት እንዲያገኙ በማድረግ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 23
ምዕራፍ 2 ሪትሚካዊ / የምት / የእንቅስቃሴ ክህሎት

ƒƒ እንቅስቃሴውን በተግባር ሲሰሩ በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው የሚስማማ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ተገቢ ነው።

የመልመጃ መልስ ተግባር፡-1


ƒƒ በሁለት እግር መዝለል፣ ወገብን በመያዝ እጅን ወደ ጎን፣ ወደ ላይ፣ ወደ ፊት መዘርጋት እና ከሙዚቃ ወይም ከድምፅ ጋር
ተቀናጅተው የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች መጥቀስ ይቻላል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 24


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ምዕራፍ

3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት


በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 18

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜትን በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን ያውቃሉ።
ƒƒ ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜትን በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ƒƒ ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜትን በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የሚያጎለብቱ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ለመስራት
ፍላጎት ያሳያሉ።

መግለጫ፡-
ይህ ምዕራፍ በውስጡ ለሶስት አላማ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ይዟል። እነርሱም፡-ራስን የማወቅና የመቆጣጠር ክህሎትን የሚያዳብሩ
እንቅስቃሴዎች፣ ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያዳብሩ እና ዉሳኔ ሰጭነትን የሚያዳብሩ ጨዋታዎች ናቸው።

3.1. ራስን የማወቅና የመቆጣጠር ክህሎትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (6 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªራስን የማወቅና የመቆጣጠር ክህሎትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።
ªªራስን የማወቅና የመቆጣጠር ክህሎትን የሚያዳብሩእንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªራስን የማወቅና የመቆጣጠር ክህሎትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በመስራታቸው ይደሰታሉ።

ተግባር፦ ሀ. በሁለት ረድፍ በመሆን ኳስ መቀባበል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6 ተማሪዎችን በቡድን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ርዕሱንና አላማውን ለተማሪዎች ማስተዋወቅ፣
ƒƒ በቅድሚያ ፊት ለፊት በረድፍ እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 25


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ በመስመር ከተሰለፉት ተማሪዎች መካከል ከፊት የቆመው ተማሪ ኳስ እንዲይዝ ማድረግ፣


ƒƒ ጀምሩየሚል ትዕዛዝመምህሩ ሲያሰማ ኳስ ለጓደኛ ማቀበል ከዚያ በኋላ እንዲሰለፉ ማድረግ፤ በዚህ ሁኔታ ጨዋታው በየዙሩ
እስከ 50 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ በማሰራት እንዲቀጥል ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በሁለት ረድፍ ሆነው በትክክል ኳስ ሲቀባበሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. ኳስ ከላይና ከታች መወርወርና መቅለብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ3—5 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ከ3—5 ተማሪዎች በ1.5 ሜትር ልዩነት በማሰለፍ እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ አንደኛው ተማሪ ኳስ በመያዝ ለሌላኛው ተማሪ በላይ በኩል ይወረውርለታል፤
ƒƒ የመካከለኛው ለመያዝ ይሞክራል፣
ƒƒ ሌላኛው ተማሪ በመቀበል በእግሩ መካከል ይወረውራል፣
ƒƒ በዚህ የአጨዋወት ስልት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እየተቀያየሩ ጨዋታውን በማሰራትበየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት መስጠት
ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ኳስ ከላይና ከታች መወርወርና መቅለብ ያለውን ጠቀሜታ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ሐ. የመስመር ማሳለፍ ጨዋታ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ትንንሽ ኳስ፣ ኖራ፣ አመድ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6 ቡድን ይሆናሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ አመድ ወይም ኖራ በመጠቀም ቀጥ ያለ መስመር ማስመር፣
ƒƒ ተማሪዎች እንዲሰለፉ ማድረግ፣
ƒƒ የተሰመረው መስመር ርቀት ከተማሪዎች 5 ሜትር አድርጎ ማስመር፣
ƒƒ ትንሽ ኳስ በመስጠት እየወረወሩ መስመሩን እንዲያሳልፉ ማድረግ፣
ƒƒ ከየቡድኑ አሸናፊዎች እርስ በርሳቸው ርቀቱን እየጨመሩ ማጫወት እና መጨረሻ የቀረው/ችው ተማሪ የጨዋታው አሸናፊ
ይሆናል /ትሆናለች /።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 26


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ የሚወረውሩትን ኳስ ከተሰመረው መስመር በትክክል ሲያሳልፉት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. ወጣ ገባ ሩጫ (ዝግዛግ ሩጫ)


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6 ቡድን በማሰራት ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማ ማሰተዋወቅ፣
ƒƒ ከ6---8ተማሪዎችን በየ1 ሜትርልዩነት በማስቀመጥ ወይም እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ሌሎች የክፍሉ ተማሪዎች በየቡድናቸው እንዲሰለፉ ማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝመምህሩ ሲያሰማ የተደረደሩ ተማሪዎች በመጠቀም ዝግዛግ እየሮጡ እንዲሄዱናለተረኞች እንዲቆሙ
ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በየዙሩ እስከ 40 ሴኮንድ እረፍት እየሰጡ ከ4—6 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወጣ ገባ ሩጫ ሲሰሩ መደሰታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

3.2. ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያዳብሩ ጨዋታዎች (6 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያዳብሩ ጨዋታዎችን ይለያሉ።
ªªማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያዳብሩ ጨዋታዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያዳብሩ ጨዋታዎችን ለመስራት ፍላጎት ያሳያሉ።

ተግባር፦ ሀ. ሰኞ -ማክሰኞ ጨዋታ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ጠፍጣፋ ድንጋይ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ በቡድን ከ3—4 ተማሪዎች


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ጠፍጣፋ ድንጋይ በተሰመሩ መስመሮች መካከል ወርውሮ መጣል፣
ƒƒ ድንጋዩን ያለበትን ሳይረግጡ ድንጋዩን በእጅ ይዞ ዘሎ መመለስ፣
ƒƒ ወይም በአንድ እግር አንክሶ ድንጋይ ያለበትን ስፍራ ረግጦ መስመሩን ሳይነኩ በእግር ጣት ድንጋዩን ከሜዳው መስመር ውጭ
አስፈንጥሮ ማስወጣት ነው፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 27


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ ቁመቱ 2 ሜትር ስፍቱ 1 ሜትር የሆነ አራት ማአዘን ያለው መስመር በሜዳው ላይ አስምሮ ከስድስት ቦታ በመክፈል ማዘጋጀት፣
ƒƒ የመጨረሻዎቹንና ሶስተኛውን ከላይ ወደታች በቁመት ለሁለት ከፍሎ ማዘጋጀት፣ ከዚያም ጠፍጣፋውን ድንጋይ ከመጀመሪያ
ቤት ይወረውርና ድንጋዩ ያረፈበትን ቦታ ሳይረግጥ ዘሎ በማለፍ በሌሎች መስመሮች ውስጥ በማንከስ ቆሞና በሁለት
በተከፈሉት መስመሮች ላይ በሁለት እግሩ በመርገጥ ከመጨረሻው ደርሶ ይመለስና ድንጋዩ ያለበትን ቦታ ሳይረግጥ ጉንበስ
ብሎ ድንጋዩን በማንሳት ዘሎ ይወጣል፣
ƒƒ ወይም ድንጋዩ ባረፈበት ቦታ አንክሶ በመቆም በእግር ጣቶቹ ድንጋዩን ገፍቶ ወይም አስፈንጥሮ ከሜዳው ማስወጣትና ዘሎ
መውጣት አለበት፣
ƒƒ ድንጋዩን በመስመር ሳያስነካ ወይም መስመር ላይ ሳያርፍ መስመሩን ሳይረግጥ ድንጋዩን ይዞ ዘሎ ከሜዳ ውጭ ከወጣና
የታጠረ ቤት ወይም ምልክት የተደረገበት ቤት እንዳለ ካልረገጠ የመጫወት እድሉ ይቀጥላል፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ እስከ ስድሰተኛው ቤት ያለመሳሳትና ከዚያም ከስድሰተኛው ወደ አንደኛው ቤት ጨርሶ የተመለሰ ከስድስቱ
አንደኛውን የራሱ ቤት በማደረግ በምልክት ያጥረዋል፣
ƒƒ ሌላው ተማሪ በታጠረው ቤት ወይም ምልክት የተደረገበት ቤት ላይ ማረፍ አይችልም፣
ƒƒ ድንጋዩን በመስመር ሳያስነካ ወይም መስመር ላይ ሳያርፍ መስመሩን ሳይረግጥ ድንጋዩን ከጨዋታው ሜዳ በአንድ ጊዜ
ያስወጣል ወይም ድንጋዩን ይዞ ዘልሎ ከሜዳ ውጭ ከወጣና የታጠረ ቤት እንዳለ ካልረገጠ የመጫወት እድሉ ይቀጥላል።
ƒƒ ብዙ ቤት በምልክት ያጠረ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሰኞ -ማክሰኞ ጨዋታ በተግባር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. አኩኩሉ አልነጋም ጨዋታ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ አንዱን ተማሪ አይኑን በመጨፈን ከወንበር ውስጥወይም በመቀመጥእንዲሸፈን ማድረግ፣
ƒƒ አይኑን ጨፍኖ ግንባሩን ደፍቶ እንዳጎነበሰ አኩኩሉአኩኩሉአኩኩሉ------ይላል፣
ƒƒ ሌሎችተማሪዎችመደበቃቸው እስኪረጋገጥ ድረስአልነጋም በማለት ይመልሳሉ፣
ƒƒ በመጨረሻም ነጋ ሲባል የተጨፈነው ተማሪ ተነስቶ የተደበቁትን ይፈልጋል ለመያዝም ያሯሩጣል፣
ƒƒ የተያዘው ተማሪ በተራው አይኑን በመጨፈን ጨዋታውን ከላይ በተቀመጠው የአሰራር ቅደም ተከተል መሰረት ይጫወቱታል፣
ƒƒ እንቅስቃሴውንሁሉም የቡድኑ ልጆች እስኪደርሳቸው በመደጋገምእንዲሰሩት ማድረግነው፡

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ስለአኩኩሉ አልነጋም ጨዋታ አሰራር የሚያውቁትን በቃል መጠየቅ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 28


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ተግባር፦ ሐ. እጅ ከፍንጅ ጨዋታ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ትንንሽ ኳስ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች በክብ እንዲቆሙ ማድረግ፤ አንዱ ተማሪ ትንሽ ኳስ በእጁ እንዲይዝ ማድረግ፤ ጀምር የሚል ድምጽ ሲሰማ ኳሱን
በአንድ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ አቅጣጫ ለሚቀጥለው ተማሪ መስጠት ነው፣
ƒƒ ኳሱን እርስበርስ በመቀባበል ጨዋታውን እንዲቀጥል ማድረግ፣
ƒƒ በቃ የሚል ድምጽ ከመምህሩ ሲሰጥ ኳስ በእጁ ላይ የተገኘበት ተማሪ እጅ ከፈንጅ ተያዘ ይባላል፤ የተያዘው ተማሪ ከጨዋታ
ውጭ ይሆናል፣
ƒƒ በዚህ የአጨዋወት ስልት ጨዋታው ይቀጥልና መጨረሻ የቀረው አሸናፊ ይሆናል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ከፍንጅ ጨዋታ ሲጫወቱ መደሰታቸውን ህግ ማክበራቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. ቆርኪ / ጠጠር/ ኳስ / መልቀም


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ቆርኪ፣ ጠጠር፣ ትንሽ ኳስ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በቡድን ከ4—6 ተማሪዎች ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎች እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ሁለት ቡድኖች ከእያንዳንዳቸውከ4—6 ተማሪዎች ያሉበት በሁለት ትይዩ ረድፍ ማሰለፍ፣
ƒƒ እስከ 10ኮርኪ ወይም ጠጠር ወይም ትንንሽ ኳስ ማስቀመጥ፣
ƒƒ እያንዳንዳቸው የተሰለፉት ቡድኖች ከኮርኪ ወይም ከጠጠር ወይም ከትንንሽ ኳስ 5 ሜትር ርቀት መሆን አለባቸው፣
ƒƒ መምህሩ ጀምርየሚል ቃል ሲያሰማ በሁለቱ ቡድኖች የመጀመሪያ የተሰለፉት ተማሪዎች ኮርኪ ወይም ጠጠር ወይም ትንንሽ
ኳስ በመሰብሰብ ጨዋታው ይካሄዳል፣
ƒƒ ብዛት ኮርኪ ወይም ጠጠር ወይም ትንንሽ ኳስ መሰብሰብ የቻለ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል፤ በዚህ ሁኔታ ጨዋታው በዙር
እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በማድረግ ከ3—4 ጊዜ በመደጋገም ይጫወቱታል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ቆርኪ / ጠጠር/ ኳስ / በትክክል ለመልቀም ፍላጎት ሲያሳዩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 29


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ተግባር፦ ሠ. መሀረብ ንጥቂያ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ መሀረብ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በቡድን ከ3—6ተማሪዎችን ማደራጀት፣


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች ከቁጥራቸው አንጻር በተለያየ ቡድን በመመደብ እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
ƒƒ ሁለት ቡድኖች መሀረብ ከያዘው መምህር ወይም ተማሪከ7—10 ሜትርልዩነት ማሰለፍ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ቃል ሲያሰማ ከሁለቱ ቡድን አንዳንድ ሰው በመሮጥ መሀረብ ለመንጠቅ ይሮጣሉ፣
ƒƒ ቀድሞ መንጠቅ የቻለው ተማሪ አሸናፊ ይሆናል፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ ጨዋታው ከ2—4 ጊዜ በመደጋገምበየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍትበመስጠት እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቃል ጥያቄ፣ ሲሰሩ በምልከታ

3.3. ዉሳኔ ሰጭነትን የሚያዳብሩ ጨዋታዎች (6 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªሀላፊነት ያለው ዉሳኔ ሰጭነትን የሚያዳብሩ ጨዋታዎችን ያውቃሉ።
ªªሀላፊነት ያለው ዉሳኔ ሰጭነትን የሚያዳብሩ ጨዋታዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªሀላፊነት ያለው ዉሳኔ ሰጭነትን የሚያዳብሩ ጨዋታዎች ያላቸውን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

ተግባር፦ ሀ. አይጥና ድመት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ7—10 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ተማሪዎች በክብ እጅ ለእጅ በመያያዝ ይቆማሉ፣
ƒƒ በክብ ቁመው የተያያዙት ድመትእንደሚባሉ ማስረዳት፣
ƒƒ በክብ ከተያያዙት ውጭ ያሉት ደግሞአይጥ እንደሚባሉ መናገር፣
ƒƒ መምህሩበር ይከፈት ሲልድመቶች እጃቸውን ይላቀቃሉ፣
ƒƒ በር በሚከፍቱበት ወይም እጃቸውን በሚላቀቁበት ጊዜ አይጦች ወደ ውስጥ በመግባትና ቶሎ ብለው ወደ ወጭ በመውጣት
ጨዋታውን ያካሂዳሉ፣
ƒƒ በር ይዘጋ ሲባልድመቶች እጅ ለእጅ ይያያዛሉ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 30


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

ƒƒ በር ሲዘጋ ከውስጥ የተያዙት አይጦች በድመቶች እንደተያዙ ተደርጎ ከጨዋታ ውጭ ይሆናሉ፣


ƒƒ በዚህ የአጨዋወት ስልት ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም በየዙሩ ለ40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት እንዲሰሩት ማድረግ፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ስለ አይጥና ድመት ጨዋታ መጫወት የሚሰጠውን ጠቀሜታ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ለ. መሀረቤን አያችሁ ?


የመጫዎቻ መዝሙር፡- ማሀረቤን ያያችሁ (3×)
አላየንም ባካችሁ (3x)
ይቺ ምንድን ናት (3x)
የዉርዬ ኳስ ናት (3x)
አይጥ አይጤ (3x)
ግቢ ድመቴ (3x)
ማየት የለም —- መዳሰስ የለም
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ መሀረብ / ጨርቅ /፣ ምልክት ማደረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6 ተማሪዎችን በየቡድኑ ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በክብ ዙሪያ ተማሪዎች እንዲቀመጡ ማድረግ፣
ƒƒ አንድ ተማሪ መሀረብ ይዞ ጨዋታዉን የሚያጫዉት መምረጥ፣
ƒƒ መሀረቤን ያያችሁ? እያለ ክቡን ሲዞር አላየንም እባካችሁ እያሉ እያጨበጨቡ ይመልሳሉ። በዚህ መሰረት እየተቀባበሉ ከላይ
ያለዉን ዘፈን ይጫወታሉ፣
ƒƒ ማሀረቡን ከጀርባው የተቀመጠበትተማሪ ማሀረቡን በመያዝና በፍጥነት በመሮጥ ለማስነካት ያስቀመጠዉ ደግሞ ላለመነካትና
የተነሳዉ ተማሪ ቦታ ላይ ለመቀመጥ ይሮጣሉ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ ጨዋታዉን በዙሩከ5—7 ጊዜ በመደጋገም እንዲጫወቱት ማድረግ ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ማሀረቤን ያያችሁ? የሚለውን ጨዋታ ለመጫወት ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. ቤት የለሽ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አመድ፣ ኖራ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 31


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ6—10 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ አመድ ወይም ኖራ በመጠቀም በ50 ሴንቲ ሜትር ልዩነት ክብ መስራት፣
ƒƒ በጨዋታው የሚሳተፉ የተማሪዎች ቁጥር ከክቡ ቁጥር በአንድ ወይም በሁለት መብለጥ አለባቸው፣
ƒƒ መምህሩ አንድ ቁጥር ሲጠራ በክቡ ዙሪያ ተማሪዎች ይሮጣሉ፣
ƒƒ በቤታችሁሲላቸው ደግሞ ተሽቀዳድመው በተዘጋጀው ባዶ ቤት ይይዛሉ፣
ƒƒ ቤትያልያዘው ተማሪ ደግሞ ከጨዋታ ውጭ ይሆናል፣
ƒƒ ከዚያ በኋላ አንዱን ቤት በማጥፋት ወይም በመቀነስ ጨዋታው ይቀጥላል፣
ƒƒ በዚህ የአጨዋወት ስልት አንድ ተማሪ እስኪቀር ድረስ ጨዋታው ይቀጥልና መጨረሻ የቀረው ተማሪ አሸናፊ ይሆናል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን በተግባር በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ የቃል ጥያቄ፣

ተግባር፦ መ. ያዕቆብ ጨዋታ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ6—10 ተማሪዎች በአንድ ቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የክፍሉተማሪዎች በቡድን ከ6—10 ተማሪዎች የያዘ አባላት ይኖሩታል፣
ƒƒ መምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ ለምሳሌ፡-“ያዕቆብ”
ƒƒ ፀጉርህን/ሽን አበጥር/ሪ፣
ƒƒ ጥርስህን/ሽን ቦርሽ፣
ƒƒ እግርህን/ሽን ታጠብ/ታጠቢ፣
ƒƒ ቁርስህን/ሽን ብላ/ብይ፣ ወ.ዘ.ተ በማለት ጨዋታውን ማጫወት።
ƒƒ እንቅስቃሴውን በሚሰሩበት ጊዜ ትዕዛዝ ያልፈጸመ ከጨዋታ ውጭ ይሆናል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ያዕቆብ ጨዋታ በጋራ ሲሰሩ የታዘዙትን ስራ በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ ለምን እንደሚጠቅም የቃል ጥያቄ፣

ተግባር፦ ሠ. የክብ መዞር ጨዋታ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ 1 ቁጥር፣ 2 ቁጥር እና 3 ቁጥር የያዘ ሶስት ፍለሽ ካርድ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 32


ምዕራፍ 3 ማህበራዊ መስተጋብርና ስሜታዊነት በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የአንድ ቡድን አባለት ከ10—15 ተማሪዎች ይኖሩታል።
ƒƒ መምህሩ እንዴት ጨዋታው እንደሚከናወን ገለፃ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ 1 ቁጥር ሲል ተማሪዎች በክቡ ዙሪያ ይሮጣሉ፣ 2 ቁጥር ሲል በክቡ ዙሪያ ይቆማሉ፣ 3 ቁጥር ሲል በክቡ ዙሪያ
ይቀመጣሉ፣
ƒƒ ሳይሳሳት እስከጨዋታው ፍጻሜ የቆየ ተማሪ የጨዋታው አሸናፊ ይሆናል፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ የክብ መዞር ጨዋታ ሲጫወቱ መደሰታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

የመልመጃ መልስ ተግባር፡-1

እርስ በርስ ያላቸው የመግባባት ችሎታ ማሳደግ፣ የጨዋታውን ህግና ደንብ ለማክበር ይጠቅማል፣ አእምሮ የማሰብ ችሎታ ያሳድጋል
እና ሌሎችን መጥቀስ ይቻላል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 33


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ምዕራፍ

4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 23

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ ጤናንና የካልብቃትን የሚያዳብሩ የእንቅስቃሴ አይነቶችን ያዉቃሉ።
ƒƒ ልዩ ልዩ የሰዉነት ክፍሎችን አቅም የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
ƒƒ የሰዉነት ክፍሎችን በማዳበርና ጤናቸዉን በመጠበቅ አስተዋጽኦ ያላቸዉን እንቅስቃሴዎች ለመስራት ፍላጎት
ያሳያሉ።

መግለጫ፡-
የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን በመስራት ልዩ ልዩ የሰዉነት ክፍሎች ተፈጥሯዊ የመስራት አቅምን በማሻሻልና ጤናችንን በመጠበቅ
ጠንካራና አምራች ማህበረሰብ ማፍራት ያስችላል። ባጠቃላይ ለዚህ ክፍል ደረጃ የተወሰኑ ጤና ተኮር የአካል ብቃት ዘርፎች
እንደሚከተለው ቀርበዋል።

4.1 የልብና ስርዓተ ትንፈሳ ብርታትን የሚያዳብሩ እቅስቃሴዎች (12 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªየልብናስርዓተ ትንፈሳ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይዘረዝራሉ።
ªªየልብናስርዓተ ትንፈሳ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªየልብናስርዓተ ትንፈሳ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ፍላጎት ያሳያሉ።

ተግባር፦ ሀ. በግል ገመድ ዝላይ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገመድ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በግል


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ገመዱን በሁለት እጅ ከኋላ በኩል አድርጎ በመያዝ መዘጋጀት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 34


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ƒƒ አንድ ጊዜ ወደ ላይ በመዝለል ከኋላ ያለዉን ገመድ በፊት በኩል እያሽከረከሩበሁለት እግሮች ስር ማሳለፍ፣
ƒƒ ገመድ ዝላዩን ሁለት ጊዜ፣ አራት ጊዜ፣ ስድስት ጊዜእያደጋገሙ ማሰራት፤ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ መካከል አስከ 1 ደቂቃ
እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ በግል ገመድ ዝላይ በትክክል ሲዘሉ ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነትበምልከታማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. እጅን እያፈራረቁ መዘርጋት እና መመለስ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ተማሪዎች እግራቸውን በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት ወይም በመግጠም እንዲቆሙናእንዲዘጋጁ ማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ከመምህሩ ሲሰጥ ግራ እጃቸውን እስከቻሉት ድረስ ወደ ጎን እንዲዘረጉት ማድረግ፣
ƒƒ ቀይሩ ሲል ቀኝ እጃቸውን እስከቻሉት መጠን ወደ ጎን እንዲዘረጉት ማድረግ፣
ƒƒ መጨረሻ ላይ ደግሞ ሁለት እጃቸውን በቻሉት መጠን ወደ ጎን እንዲዘረጉት ማድረግ፤ በዚህ የአሰራር ቅደም ተከተል መሰረት
በየዙሩ እስከ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ4—7 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅን እያፈራረቁ በሚዘረጉበት ጊዜ ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ.ሁለት እጅ ወደላይ በማንሳት ማሽከርከር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን በተወሰነ መልኩ ከፈት በማድረግ እጅን ወደ ታች በመዘርጋት መዘጋጀት፣
ƒƒ እጅን ወደ ላይ ቀጥ አድርጎ በመዘርጋት ማዘጋጀት፣
ƒƒ ሶስት ጊዜ ወደ ላይ የተዘረጋዉን እጅ ወደ ኋላ በማዞርወደ ታች መመለስ፣
ƒƒ በአንድ ላይ እጅን ወደ ላይ በማድረግ ወደ ኋላ በማዞር አራት ጊዜ ማሽከርከር፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ2–5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሁለት እጅ ወደ ላይ በማንሳት ማሽከርከር ምን ያህል እንዳስደሰታቸው በቃል መጠየቅ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 35


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ተግባር፦ መ. ሁለት እጅን በመግጠም፣ በመክፈትና ወደ ጎን በመዘርጋት ማሽከርከር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች በመካከላቸው በ3 ሜትር ልዩነት በረድፍ እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ ሲል ወደ ላይ ዘርግቶ እጅን በመግጠም ሶስት ጊዜ በማሽከርከር እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ እንደገና ወደ ላይ ዘርግቶ እጅን በመክፈት ሶስት ጊዜ ማሽከርከር እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ በመጨረሻም እጅን ወደ ጎን ዘርግቶ ሶስት ጊዜ ማሽከርከር እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ሁለት እጅን በመግጠም፣ በመክፈትና ወደ ጎን በመዘርጋት ማሽከርከር የሚለውን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም
እረፍት እየሰጡ እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ሲሰሩ በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሠ. በትንንሽ ክቦች ዙሪያ መሮጥ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ አመድ፣ ኖራ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ6—8 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ አመድ ወይም ኖራ በመጠቀም ከ6—8 ተማሪዎች የሚያስሮጥ ክብ መስመር ማዘጋጀት፣
ƒƒ በእያንዳንዱ ቡድን ከ8 ያልበለጡ ተማሪዎችን በማደራጀት በተዘጋጀው ክብ መስመር እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ሁሉም ተማሪዎች በየቡድናቸው የክቡን ዙሪያ እንዲሮጡ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም በየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት እየሰጡ እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ወይም በቃል በመጠየቅ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. ኳስ ወደ ፊት እየመቱ መሮጥ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—6 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የተማሪዎችን ብዛት መሰረት አድርጎቡድን ማደራጀት፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 36
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ƒƒ ለእያንዳንዱ ቡድን አንድኳስ በመስጠት በ30 ሜትር ክልል ዉስጥ ኳሱን በመምታት እንዲሮጡ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 2 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ2—5ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ተማሪዎችኳስ ወደ ፊት እየመቱ በሚሮጡበት ጊዜ እንቅስቃሴውን በትክክል መስራታቸውን በምልከታማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሸ. እግርን በእጅ እያፈራረቁ መንካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ከፍቶና እጅን ወደ ጎን ዘርግቶ በማቆም ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ አንድ ቁጥር ሲል በቀኝ እጃቸው ቀኝ እግራቸውን መንካት፣
ƒƒ ሁለት ቁጥር ሲል በግራ እጃቸው ግራ እግራቸውን መንካት፣
ƒƒ ሶስት ቁጥር ሲል በሁለት እጃቸው ወገባቸውን መያዝ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ3—5ጊዜ በመደጋገም ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እግር በእጅ እያፈራረቁ በትክክል ሲነኩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ቀ. እጅ ወደ ጎን እና ወደፊት መዘርጋት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር ገጥሞና እጅ ወደ ጎን ዘርግቶ በማቆም ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር ሲባል አንድ ጊዜ እጅን ወደ ፊት አምጥቶ መግጠምና መልሶ ወደ ጎን መዘርጋ፣
ƒƒ ሁለት፣ አራት እንዲሁም ስድስት ጊዜ በመካከሉ መጠነኛ እረፍት በመስጠት ወደ ጎን መዘርጋትና ወደ ፊት አምጥቶ መግጠምን
እንቅስቃሴ ማሰራት፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ3—5ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ወደጎን እና ወደፊት መዘርጋትን ሲሰሩበምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 37


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ተግባር፦ በ. እግርና እጅ በማፈራረቅ መግጠምና መዘርጋት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ከፍቶ እጅን ወደ ላይ ዘርግቶ በመቆም ማዘጋጀት፣
ƒƒ እግር ሲገጠም እጅ ወደ ታች እንደሚወርድ ማሰረዳት፣
ƒƒ አንድ ጊዜ የተከፈተዉን እጅና እግር መግጠም፣
ƒƒ ሁለት ጊዜ፣ አራት ጊዜ እና ስድስት ጊዜ በመካከሉ መጠነኛ ክፍተት በመስጠት እጅና እግርን መክፈትና መግጠምን ማለማመድ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—5ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ተገቢ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እግርና እጅ በማፈራረቅ መግጠምና መዘርጋት እንቅስቃሴ ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፡-ተ. ኳስ ማቀበልና መቀበል

አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-


ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—8 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እንደ ተማሪዎቹ ብዛትበአነስተኛ ቡድኖች ተማሪዎቹን መክፈል፣
ƒƒ አንዱን ተማሪ መሀል በማድረግ ቡድኖቹ ክብ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ መሀል ያለዉ ተማሪ በእጁ ፈጠን እያለ በመወርወር ለሁሉም ተማሪዎች ማዳረስ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ2—5ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፡- ቸ. የሶምሶማ ሩጫ

አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-


ƒƒ ኮን ወይም ለምልክት የሚያገለግል ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—8 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቡድን ከ5—7 አባላት ያላቸውን ተማሪዎች ማደራጀት፣
ƒƒ በ10 ሜትር ልዩነት ኮኖችን ወይም ለምልክት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ማስቀመጥ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 38
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ከመምህሩ ሲሰጥ ተማሪዎች በሶምሶማ እየሮጡ ከኋላ ይሰለፋሉ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በየዙሩ እስከ 2 ደቂቃ እረፍት እየሰጡ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው ተስማሚ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

4.2 የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (6 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªየጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።
ªªየጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªየጡንቻ ብርታትን የሚያሻሽሉ እንቅስቃሴዎችን ለመስራትፍላጎት ያሳያሉ።

ተግባር፦ ሀ. ወገብ ይዞ ወደላይ መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ትንሽ ከፍቶ ወገብን በሁለት እጅ ይዞ በማስቆም ማዘጋጀት፣
ƒƒ ወገብ እንደተያዘ አንድ ጊዜ ወደ ላይ ዘሎ ማረፍ፣
ƒƒ ሁለት ጊዜ፣ ሶስት ጊዜ፣ አራት ጊዜ በመካከሉ መጠነኛ እረፍት በመስጠት ማሰራት፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ በየዙሩ 1 ደቂቃእረፍት በመስጠት ከ2—5ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወገብ ይዞ ወደላይ በትክክል ሲዘሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. እጅ ወደጎን መዘርጋትና ማጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ከፍቶ እጅን ወደ ጎን ዘርግቶ መቆም፣
ƒƒ ወደ ጎን የተዘረጋን እጅ ወደ ታች ማጠፍ፣
ƒƒ የተዘረጋን እጅ ሁለት ጊዜ፣ አራት ጊዜ፣ ስድስት ጊዜ በመካከሉ መጠነኛ እረፍት በመስጠት ማሰራት፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ3—6ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 39
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅንበትክክል ወደጎን ሲዘረጉና ሲያጥፉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ.እጅ ለእጅ በመያያዝ እግር ገጥሞ ወደ ላይ መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ በማድረግ ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ፊት ለፊት እግርን ገጥሞ እጅ ለእጅ በመያያዝ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ ወደ ላይ እንዲዘሉ ማድረግ፣
ƒƒ ሁለት ጊዜ፣ ሶስት ጊዜ እና አራት ጊዜ እረፍት በመስጠት ማሰራት፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ለእጅ በመያያዝ እግር ገጥሞ ወደ ላይ ሲዘሉ ያላቸውን ፍላጎትበምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ.በሁለት እጅ ተያይዞ በአንድ እግር በመቆም ሌላኛውን እግር ወደኋላ መዘርጋት
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እጅን ወደ ላይ ዘርግቶ እርስ በእርስ በመያያዝ ማዘጋጀት፣
ƒƒ አንድ እግራቸውን ወደ ኋላ እንዲዘረጉት ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ ሲል ወደ ላይ እየዘለሉ ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ባልሰራው እግር እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ2 – 4 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በሁለት እጅ ተያይዞ በአንድ እግር በመቆም ሌላኛው እግር ወደ ኋላ በትክክል ሲዘረጉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሠ. እጅ በማጣመር ወደጎን መዘርጋትና መመለስ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች /ማቴራያሎች/፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 40


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እጅን አጣምሮ እንዲቆሙ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ከዚያ በኋላ ሰውነታቸውን ትንሽ ወረድ እንዲሉ ማድረግ፣
ƒƒ ከታች የተጣመረዉን እጅ ወደ ጎን በመዘርጋት እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ እንደገና እጅን ማጣመር፣
ƒƒ በተከታታይ ሁለት ጊዜ፣ ሶስት ጊዜ እና አራት ጊዜ በመካከል እረፍት በመስጠት ማሰራት፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—6ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ስለእንቅስቃሴው የሚያውቁትን በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ረ. እጅን አጣምሮ መቆምና ወደ ጎን በየተራ ማሽከርከር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ እጅ በማጣመር ቀጥ ብሎ መቆም፣
ƒƒ ከዚያ በኋላ የተጣመረውን እጅ በየተራ ማሽከርከር፣
ƒƒ ይህንኑተግባር በየዙሩ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ3—6 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ሰ. በመቀመጥ በሁለት እግር መካከል ኳስ በአየር ላይ መያዝ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ኳስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እጅን መሬት ላይ ቁጭ ብሎ በመደገፍ በሁለት እግር መካከል ኳስ በማስቀመጥ መዘጋጀት፣
ƒƒ በሁለት እግር መካከል የተያዘን ኳስ ወደ ላይ እንዲያነሱ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—5ጊዜ በመደጋገም ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በመቀመጥ በሁለት እግር መካከል ኳስ በመያዝ በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 41
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ተግባር፦ ሸ.በመቀመጥ በሁለት እጅ በቀኝና በግራ አቅጣጫ በመጠማዘዝ መሬት መንካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመቀመጫ እግርን ዘርግቶ መሬት በማስቀመጥ ማዘጋጀት፣
ƒƒ በተወሰነ መልኩከጉልበት ማጠፍና ሁለት እጅን ወደ አንድ አቅጣጫ በማዞር መሬት በመንካት ማሰራት፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ባልሰራው አቅጣጫ በተመሳሳይ ሁኔታ እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ ለ1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—5ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በቃል ጥያቄ፣ በተግባር ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታውተስማሚ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

4.3. መሳሳብና መተጣጠፍን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች (4 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªበመሳሳብና በመተጣጠፍ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ይገልጻሉ።
ªªመሳሳብና በመተጣጠፍ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን በተግባር በመስራት የመተጣጠፍ ችሎታቸዉን ያሻሽላሉ።
ªªበመሳሳብና በመተጣጠፍ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

ተግባር፦ ሀ. አንገት ማዘንበል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ አንገትን ቀስ ብለው ወደ ግራ አቅጣጫ ማዘንበልና ወደ ነበረበት ቦታ መመለስ፣
ƒƒ አንገትን ወደ ቀኝ አቅጣጫ ማዘንበልና ወደ ነበረበት ቦታ መመለስ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ አንገታቸውን ወደ ቀኝና ወደ ግራ አቅጣጫ በትክክል ሲያዘነብሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 42


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ተግባር፦ ለ. በመቆም ወደ ግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ማሳሳብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ አንድ እጅ ወደ ላይ በማንሳትና በአንድ እጅ ወገብ በመያዝ ወይም እጅን ወደ ታች በመዘርጋት እግር ከፍቶ እንዲቆሙ
ማድረግ፣
ƒƒ አንድ እጅ ወገብ እንደያዘና አንድ እጅ ወደ ላይ እንደተነሳ ወደ ግራ በመታጠፍ እስከ 12 ሴኮንድ እንዲቆዩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ወደ አልተሰራበት አቅጣጫ በተመሳሳይ ሁኔታ ማሰራት፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን በየዙሩ 10 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ4—7 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ሲሰሩ በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. ሁለት እጅ ወደ ላይ ማሳሳብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ከፍቶ እጅን ወደ ላይ በማድረግ ጣቶችን በማስተሳሰር በማሳሳብ መልኩ ማዘጋጀት፣
ƒƒ በእግር ጣት በመቆም እጅን ወደ ላይ በመወጠር እስከ 20 ሴኮንድ ወደላይ መንጠራራት /መሳብ/፣
ƒƒ ሁለት ጊዜ፣ ሶስት ጊዜ እና አራት ጊዜ በመካከሉ ትንሽ እረፍት በመስጠት ወደ ላይ እየተሳቡ መመለስ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ2—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ ሁለት እጅ ወደ ላይ በትክክል ሲያሳስቡ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. ሸብረክ በማለት ወደ ፊት መሳብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን በደንብ በመክፈት ፊትና ኋላ አድርጎ ማቆም፣
ƒƒ እግርን ትንሽ ሸብረክ በማድረግና ሁለት እጅን ጉልበት ላይ በማድረግ የላይኛዉን የሰዉነት ክፍል ወደ ፊት በማምጣ ማሳሳብ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 43
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ƒƒ ያልሰራዉን እግር በመቀየር እንቅስቃሴውን እንዲሰሩት ማድረግ፣


ƒƒ ሁለት ጊዜ፣ ሶስት ጊዜ እና አራት ጊዜ በመካከሉ እረፍት በመስጠት እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሠ. ወደ ፊት እና ወደ ኋላ ማዘንበል
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር ከፈት አድርጎ እጅ ወደ ታች በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ የላኛዉን የሰዉነት ክፍል ወደ ፊት አጥፎ በእጅ መሬት በመንካትና ወደ ነበረበት ቦታ እንዲመለሱ ማድረግ፣
ƒƒ እንደገና በእጅ ወገብን በመያዝ ወደ ኋላ መውሰድና ወደ ነበረበት ቦታ እንዲመለሱ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር ጉልበት ሳይታጠፍ በእንቅስቃሴው መካከል እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደ ፊት እና ወደ ኋላ መታጠፍ ሲሰሩ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. ወገብን ወደ ቀኝና ግራ አቅጣጫ መጠምዘዝ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በግል ወይም በጋራ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን በትክሻ ስፋት ከፈት አድርጎ እጅን ወደ ታች መዘርጋት፣
ƒƒ የቀኝ እጅን ወደ ግራ፣ የግራ እጅን በጀርባ ወደ ቀኝ በኩል በማድረግ ወደ ቀኝ አቅጣጫ መጠማዘዝና መመለስ፣
ƒƒ የግራ እጅን ወደ ቀኝ የቀኝ እጅን በጀርባ ወደ ግራ በኩል በማድረግ ወደ ግራ አቅጣጫ መጠማዘዝና መመለስ፣
ƒƒ ሁለት ጊዜ፣ ሶስት ጊዜ፣ አራት ጊዜ በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ2—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወገብን ወደ ቀኝና ግራ አቅጣጫ በትክክል ሲያጠማዝዙ በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 44


ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ተግባር፦ ሰ. አንድ እግር አጥፎ ሌላኛውን ዘርግቶ በመቀመጥ ወደ ፊት በመሳብ የእግር ጣት


መንካት
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ዘርግቶ በመቀመጫ መሬት መቀመጥ፣
ƒƒ አንድ እግርን በማጠፍ ሌላኛውን እግር ዘርግቶ ወደ ፊት በመሳብ በእጅ የእግር ጣት መንካት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ባልሰራው የአካል ክፍል እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 20 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በመቀመጥ ወደ ፊት በመሳብ አንድ ወይም ሁለት እግራቸውን በትክክል ለመንካት ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሸ. በመቀመጥ የውስጥ እግርን ማነካካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ መሬት ላይ በማስቀመጥ ለእንቅስቃሴው እንዲዘጋጁ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ትእዛዝ ሲሰጥ ሁለት እግርን በማጠፍና የዉስጥ እግሮችን ማነካካት፣
ƒƒ የተነካኩት የሁለት ዉስጥ እግር እንዳይለያዩ በእጅ በመግፋት እስከ -1 ደቂቃ ደረትን ቀና በማድረግ ማቆየት፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በመካከሉ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ በቃል ጥያቄ፣

ተግባር፦ ቀ. ከወገብ በላይ ማሳሳብ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግርን ወደ ኋላ ዘርግቶ በሆድ መተኛት፣
ƒƒ እጅን በደረት አካባቢ በማድረግ በመዳፍ መሬትን እንዲደገፉ ማድረግ፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 45
ምዕራፍ 4 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ

ƒƒ በእጅ መሬትን በመግፋት የላኛዉን የሰዉነት ክፍል ወደ ላይ ሊታይ በሚችል መልኩ ማንሳትና መመለስ፣
ƒƒ ይህንኑ ተግባር በየዙሩ እስከ 30 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ከ2—5ጊዜ በመደጋገም ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ እንቅስቃሴው ምን ያክል እንዳስደሰታቸው የቃል ጥያቄ እና በምልከታ ማረጋገጥ

የመልመጃ መልስ ተግባር፡-1


ƒƒ ለ. ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ሰውነታችንን እንደፈለግን ወደተለያዩ አቅጣጫ ለማንቀሳቀስ፣ ሰውነታችንን በቀላሉ
ለማዘዝ እና የመሳሰሉት ጥቅሞች ይኖሩታል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 46


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ምዕራፍ

5 ጅምናስቲክስ

የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 21

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ የነጻ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ያዉቃሉ።
ƒƒ የነጻ ጅምናስቲክስ የእንቅስቃሴ አይነቶችን በተግባር ይሰራሉ።
ƒƒ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ለመስራት ይነሳሳሉ።

መግለጫ፡-
የተለያዩ መሰረታዊ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች በመስራት የአካላችን እና የአእምሮአችን ጤንነት መጠበቅ ይቻላል። በተጨማሪም
እርስበርስ ያለንን ግንኙነት ለማሻሻል ይጠቅማል።

5.1. መሰረታዊ የጅምናስቲክስ እቅስቃሴዎች (11 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªመሰረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች የሚባሉትን ይዘረዝራሉ።
ªªመሰረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªመሰረታዊ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በመስራት ይደሰታሉ።

ተግባር፦ ሀ. መቆም፣ መቀመጥ፣ በሆድና በጀርባ መተኛት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ፣ ፍራሽ፣

የክፍል አደረጃጀት፦ በግልወይም በጋራ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ መምህሩ አንድ ቁጥር ብሎ ትዕዛዝ ሲሰጥ መቆም፣ ሁለት ቁጥር ሲል መቀመጥ፣ ሶስት ሲል ደግሞ በሆድ መተኛት በመጨረሻም
አራት ሲል በጀርባ መተኛት መሆኑን ማስረዳት፣
ƒƒ ይህንንእንቅስቃሴ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 47


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ መቆም፣ መቀመጥ፣ በሆድና በጀርባ መተኛት እንቅስቃሴ ሲሰሩ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. በጎን መንከባለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ፣ ፍራሽ፣

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—8 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ በጀርባቸው እንዲተኙ ማድረግ፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ከመምህሩ ትዕዛዝ ሲሰጥ ወደ አንድ አቅጣጫ በጎን መንከባለል፣
ƒƒ ባልሰሩበት ጎን እንዲሰሩ በማድረግ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በጎን በትክክል ሲንከባለሉ በምልከታ ማረጋገጥና ማስተካከያ መስጠት፣

ተግባር፦ ሐ. እግር በማቀፍ ወደ ግራ ወይም ወደ ቀኝ አቅጣጫ መንከባለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ፣ ፍራሽ፣

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በቡድን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በቅድሚያ ሁለት እግራቸውን ከጉልበት በማጠፍ እጅ መሬት በመንካት ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ከመምህሩ ሲሰጥ እግርን በማቀፍ ወደ ቀኝ ጎን እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ በመቀጠልም በግራ ጎን ማሰራት፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ማስራትያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እግራቸውን አቅፈው ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ሲንከባለሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. በጀርባ መሬት እየነኩ ወደ ፊትና ወደ ኋላ መመላለስ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፍራሽ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ6—9 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ እግራቸውንአጥፈውቁጭ እንዲሉ ማድረግ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 48


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲያሰማ ተማሪው/ዋበጀርባ መሬት እየነኩ ወደ ፊትና ወደ ኋላ በመመላለስ እንቅስቃሴዎችን
እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ እንቅስቃሴው ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደ ፊትና ወደ ኋላ መመላለስ እንቅስቃሴ ሲሰሩ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፡

ተግባር፦ ሠ. ወደቀኝና ወደግራ ጎን አቅጣጫ መወዛወዝ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም ከ5—8 ተማሪዎች በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ እግራቸውን በመያዝ እንዲቀመጡ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝሲሰጥ ወደቀኝ እና ወደግራ ጎን አቅጣጫ እያዘንበሉ ወደ ነበሩበት ቦታ እየተመለሱ እንዲለማመዱ
ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በየዙሩ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ጎን አቅጣጫ እያዘነበሉ ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. ጉልበትን ወደላይ ማንሳት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ፣

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በቡድን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በአንድ እግር በመቆም ሌላኛውን እግር ወደላይ ማንሳት፣
ƒƒ ባልሰራው እግር እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ እረፍት በመስጠት ከ6—9 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ጉልበትን ወደ ላይ በትክክል ሲያነሱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሰ. የእግር ተረከዝ ወደላይ ማንሳትና መመለስ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 49


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በሁለት እግር በመቆም ተረከዝን ወደላይ ማንሳትና ወደነበረበት መመለስ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ8—12 ጊዜ በመደጋገም እረፍት በመስጠት ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ የእግር ተረከዝ ወደላይ ማንሳት እንቅስቃሴ ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሸ. ከትንሽ ከፍታ ላይ መንሸራተት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ የመንሸራተቻ ቁሳቁስ፣ ገላጭ ስዕል፣ ፈሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍል ተማሪዎች ሰልፋቸውን በመጠበቅ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ መጀመሪያ ተማሪዎችን ተራ በተራ ከመንሸራተቻ ቦታ ላይ በማስቀመጥ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ትዕዛዝ ድምፅ ሲሰሙ ተራቸውን ጠብቀው መንሸራተት፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ሁሉንም ተማሪዎች ከ5—8 ጊዜ በመደጋገም እረፍት በመስጠት በየተራ እንዲሰሩት ማድረግ

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ከትንሽ ከፍታ ላይ ሲንሸራተቱ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ቀ. ቁጢጥ ከማለት ወደ ላይ መዝለል


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ5—7ተማሪዎች በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ተማሪዎች ቁጢጥእንዲሉ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ከዚያ እንዲዘሉ ማድረግ፣
ƒƒ በመጨረሻም ቁጢጥ ብለው እንዲጨርሱ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እረፍት በመስጠት እንዲሰሩት ማድረግ፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ቁጢጥ ከማለት ወደ ላይ በትክክል ሲዘሉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 50


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

5.2. ሚዛን መጠበቅ (4 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴ መስራት የሚሰጠውን ጠቀሜታ ይዘረዝራሉ። ፡
ªªሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ይሰራሉ።
ªªሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴ መስራት የሚሰጠውን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

ተግባር፦ ሀ. እንደ ዳክዬ አስመስሎ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሰዉነታቸውን በማሟሟቅና በማሳሳብ ራሳቸውን ማዘጋጀት፣
ƒƒ እንቅስቃሴ የሚሰሩበትን ርቀት እስከ ከ5—7 ሜትር በመለካት ምልክት ማስቀመጥ፣
ƒƒ ጀምር ሲባል እንደ ዳክዬ አስመስለው ይራመዳሉ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ እንቅስቃሴውን ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም በቂ እረፍት በመስጠት እንዲተገብሩ ማድረግ፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንደ ዳክዬ አስመስለው በትክክል ሲራመዱ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. እንደ ቀጭኔ አስመስሎ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሰዉነታቸውን በማሟሟቅና በማሳሳብ ራሳቸውን ማዘጋጀት፣
ƒƒ እንቅስቃሴ የሚሰሩበትን ርቀት እስከ 10 ሜትር በመለካት ምልክት ማስቀመጥ፣
ƒƒ ጀምር ሲባል እንደ ቀጭኔ አስመስለው ይራመዳሉ፣
ƒƒ በዚህ ሁኔታ እንቅስቃሴውን ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም በቂ እረፍት በመስጠት እንደ ቀጭኔ አስመስለው እንዲራመዱ ማድረግ
ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንደ ቀጭኔ አስመስለው በትክክል ሲራመዱ ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 51


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ተግባር፦ ሐ. እንደ ድብ አስመስሎ መራመድ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ መጀመሪያ ተስተካክለው እንዲቆሙ ማድረግ፣
ƒƒ በሁለት እጅ መሬትን በመደገፍ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ጀምር ሲል ተማሪዎች እንደ ድብ አስመስለው መራመድ ይጀምራሉ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ4—6 ጊዜ በመደጋገም በቂ እረፍት እየሰጡ እንዲሰሩ ማድረግ።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ እንደ ድብ አስመስሎ የመራመድ እንቅስቃሴ በትክክል ሲሰሩ የትኛውን የሰውነት ክፍል በይበልጥ እንደተሰማቸው በቃል
መጠየቅ፣

ተግባር፦ መ. መጋለብ
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ 1.5 ሜትር ርዝመት ያለው ዱላ / ልምጭ /፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ6—10 ተማሪዎችን በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ሰውነታቸውን ማሟሟቅና ማሳሳብ እንዲሰሩ በማድረግ ለእንቅስቃሴው ዝግጁ ማድረግ፣
ƒƒ ዱላ/ ልምጭ /በእግራቸው መካከል በማስገባት በእጃቸው እንዲይዙት ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን የሚሰሩበት ርቀት ከ10--15 ሜትር ላይምልክት በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ቃል መምህሩ/ሯሲሰጥ / ስትሰጥ / ተማሪዎች የፈረስ የመጋለብ አይነት እንዲለማመዱ ማድረግ፣
ƒƒ መጋለብ የሚለውን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ እረፍት በመስጠት በተደጋጋሚ እንዲሰሩ ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ የመጋለብ እንቅስቃሴበተግባር ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሠ. አንድ እግር ወደፊት በመዘርጋት ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ሰውነታቸውን በሚገባ ማሟሟቅና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 52
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ በሁለት እግር በመቆም ለመጀመር ቦታ መያዝ፣


ƒƒ መምህሩ ጀምሩየሚል የቃል ትዕዛዝ ሲሰጥ አቅማቸው በሚፈቅደው መሰረት አንድ እግራቸውን ወደፊት እንዲዘረጉት
ማደረግ፣
ƒƒ መመለስ ሲል ወደፊት የተዘረጋውን እግርወደነበረበት ቦታ እንዲመልሱት ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ባልሰራው እግር ማሰራት፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ እስከ 40ሴኮንድ እረፍት በመስጠት እንዲሰሩ ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ አንድ አግር ወደፊት በመዘርጋት ሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴን ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. አንድ እግር ወደኋላ በመዘርጋት ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በሁለት እግር በመቆም ለእንቅስቃሴው መዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል የቃል ድምጽ ሲሰጥ በቻሉት መጠን አንድ እግራቸውን ወደኋላ መዘርጋት፣
ƒƒ ሰውነትን ወደፊት ማዘንበል፣
ƒƒ መመለስ ሲል ወደነበሩበት ቦታ ወደኋላ የተዘረጋውን እግራቸውን መመለስ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ባልሰራው እግር እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ እረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ከ5—8 ጊዜ በተደጋጋሚ እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ:-
ƒƒ አንድ እግር ወደኋላ በመዘርጋት ሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴን ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውንእንዲሰሩ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ሰ. በጥንድ በአንድ እግር በመቆም ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ጥንድ በመሆን ጎን ለጎን እጅ ከትከሻ በማድረግ ማቆም፣
ƒƒ ከትከሻ ላይ ያልሆነው እጅ ወደጎን እንዲዘረጋ ማድረግ፣
ƒƒ መምህሩጀምሩ የሚል የቃል ድምጽ ሲሰጥ በቻሉት መጠን በጥንዶች መካከል የአካል ንክኪ በሌለበት በኩል አንድ እግራቸውን
ወደጎን መዘርጋት፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 53
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ መመለስ ሲል የተዘረጋውን እግር ወደነበረበት ቦታ መመለስ፣


ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ባልሰራው እግር እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ እረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ከ5—7 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በጥንድ በአንድ አግር ሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴ በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሸ. በጥንድ ፊት ለፊት በመቆም በአንድ እግር ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ፊት ለፊት በመቆም እጅ ለእጅ እንዲያያዙ ማድረግ፣
ƒƒ ቀኝ እና ግራ እግራቸውን ከጉልበት በማጠፍ ወደፊት በመውሰድ ሚዛናቸውን እንዲጠብቁ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ባልሰራው እግር እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ በቂ እረፍት በመስጠት እንቅስቃሴውን ከ5—8 ጊዜ በመደጋገም ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በጥንድ ፊት ለፊት በአንድ አግር ሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴ በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣
ƒƒ በጥንድ ፊት ለፊት በአንድ አግር ሚዛን መጠበቅ እንቅስቃሴ ሲሰሩ ፍላጎት ማሳየታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው ተስማሚ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

ተግባር፦ቀ. እጅን ዘርግቶ በአንድ እግር ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በቡድን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በአንድ እግር በመቆም ሌላኛውን እግር ወደ ጎን እንዲዘረጉ በማድረግ እስከ 1 ደቂቃ በማቆየት ማሰራት፣
ƒƒ ባልሰራው እግር እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ እረፍት በመስጠት ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩት ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅን ዘርግቶ በአንድ እግር ሚዛን መጠበቅ በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 54


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ተግባር፦ በ. እጅን ከወገብ ላይ በማድረግ በአንድ እግር ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በአንድ አግር በመቆም እና እጅ በወገብ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ሌላኛውን እግር ከጉልበት በማጠፍ የእግር ጣት ከቆመው እግር ጉልበት ላይ በማድረግ አስከ 30 ሴኮንድ ድረስ ማቆየት፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ ባልሰራው እግር ከ3—5 ጊዜ በመደጋገም እረፍት በመስጠት ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ
ƒƒ እጅን ከወገብ ላይ በማድረግ በአንድ እግር ሚዛን መጠበቅ የሚሰጠውን ጠቀሜታ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ተ. በመቀመጥ ሁለት እግር ማንሳት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በቡድን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ በመቀመጥ እጃቸውን ከመቀመጫቸው ትንሽወደ ኋላ በማድረግ መሬት ላይ እንዲያስቀምጡ በማድረግ
ማዘጋጀት፣
ƒƒ ሁለት እግርን በመግጠም ከጉልበት በማጠፍ ከመሬት ማንሳት፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ20—30 ሴኮንድ በማቆየት እንዲሰሩት ማድረግ፣
ƒƒ በእንቅስቃሴው መካከል እስከ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠትከ4—5 ጊዜ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንቅስቃሴውን ሲሰሩ በይበልጥ የተሰማቸውን የሰውነት ክፍል እንዲገልጹ በቃል መጠየቅ፣

ተግባር፦ ቸ. ጥንድ በመሆን በእንጨት / በብረት / ላይ ሚዛን መጠበቅ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ከእንጨት ወይም ከብረት የተሰራ ሚዛን መጠበቂያ መሳሪያ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ጥንድ ጥንድ በማድረግ ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በጥንድ በመሆን በተቃራኒ አቅጣጫ ከብረቱ ወይም ከእንጨቱ በማስቀመጥ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምርየሚል ቃል ሲሰጥ አንደኛው ተማሪ የተቀመጠበትን ዝቅ ሲያደርግ ሌላኛው ከፍ እያለ ይተገብሩታል፣
ƒƒ ከፍ ብሎ የነበረው ተማሪ ዝቅ በማለት ዝቅ ብሎ የነበረው ተማሪ ደግሞ ከፍ በማለት እንቅስቃሴውን ይሰሩታል፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 55
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ በእንቅስቃሴው መካከል በቂ እረፍት እየሰጡ ከ5—7 ጊዜ በመደጋገም ይሰሩታል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ጥንድ በመሆን እንቅስቃሴውን በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ማስታዎሻ፡- ልዩ ፍላጎት ለሚሹ ተማሪዎች እንደሁኔታው ተስማሚ ተግባራትን በማዘጋጀት ማስተማር ያስፈልጋል።

5.3. ከወገብ በላይ የሚሰሩ የካለስተነቲክስ የጅምናስቲክስ


(6 ክ/ጊዜ)
እንቅስቃሴዎች

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªከወገብ በላይ የሚሰሩ የካለስተነቲክስ ጅምናስቲክስ እንቅስቀሴዎችን ይገልጻሉ።
ªªከወገብ በላይ የሚሰሩ የካለስተነቲክስ ጅምናስቲክስ በትክክል ይሰራሉ።
ªªከወገብ በላይ የሚሰሩ የካለስተነቲክስ ጅምናስቲክስ በመስራታቸው ይደሰታሉ።

ተግባር፦ ሀ. እጅ ትከሻ ላይ በማድረግ ወደጎን መዘርጋትና ማጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በቡድን


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ በመጀመሪያ ሁለት እጅ ከትከሻ ላይ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ወደጎን እንዲዘረጉ ማድረግ፣
ƒƒ መመለስሲል ሁለት እጃቸው ወደ ትከሻቸው እንዲመልሱ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ እረፍት በመስጠት ከ5—7 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ትከሻ ላይ በማድረግ ወደጎን መዘርጋትና ማጠፍ እንቅስቃሴ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. እጅ ትከሻ ላይ በማድረግ ወደላይ መዘርጋትና ማጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት እጃቸውን ከትከሻቸው ላይ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ትዕዛዝ ሲሰጥእጅ ወደላይ መዘርጋት፣
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 56
ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ƒƒ መመለስሲል ወደነበረበት ቦታ እንዲመልሱ ማድረግ፣


ƒƒ እንቅስቃሴውን ከ5—8 ጊዜ በተደጋጋሚ በማሰራት 40 ሴኮንድ እረፍት መስጠት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ትከሻ ላይ በማድረግ ወደላይ መዘርጋትና ማጠፍ ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሐ. እጅ ትከሻ ላይ በማድረግ ወደፊት መዘርጋትና ማጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት እጃቸውን ከትከሻቸው በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምር የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ እጅ ወደፊት መዘርጋት፣
ƒƒ መመለስ ሲል ወደነበረበት ቦታ እንዲመልሱ ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚ እስከ 40 ሴኮንድ እረፍት በመስጠት ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ትከሻ ላይ በማድረግ ወደፊት መዘርጋትና ማጠፍ በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ መ. እጅ ወደጎን መዘርጋትና ወደታች ማጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች /ማቴሪያሎች/፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት እጃቸውን ከትከሻቸው በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥእጅ ወደጎን መዘርጋት፣
ƒƒ ወደታች ማጠፍሲል እጃቸውን ወደጭን እንዲወስዱ ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን እረፍት በመስጠት ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እጅ ወደጎን መዘርጋትና ወደታች ማጠፍ እንቅስቃሴ በትክክል ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ሠ. አንድ እጅ ወደፊት በመዘርጋት ሌላኛውን እጅ ማሽከርከር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 57


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ ወይም በቡድን በማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት ወይም በመግጠም እንድ እጃቸውን ወደ ፊት እንዲዘረጉ በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩአንድ እጅን ማሽከርከር ሲል እጃቸውን ያሽከረክራሉ፣
ƒƒ ያልሰራውን እጅ ማሽከርከር ሲል ያልሰራውን እጅእንዲሽከረከር ማድረግ፣
ƒƒ እንቅስቃሴውን እረፍት በመስጠት ከ2—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ አንድ እጅ ወደፊት በመዘርጋት ሌላኛውን እጅ በሚያሽከረክሩበት ወቅት እጃቸውን በትክክል መሽከርከሩን በምልከታ
ማረጋገጥ፣
ƒƒ አንድ እጅ ወደፊት በመዘርጋት ሌላኛውን እጅ ማሽከርከር በመስራታቸው መደሰታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ረ. ሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደፊት ማሽከርከር


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ፣ ገላጭ ስዕል

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ ወይም በመግጠም እጃቸውን ከትከሻቸው በማድረግ ማዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደፊት ማሽከርከር ሲል ወደፊት ዘርግተው እንዲያሽከረክሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በቂ እረፍት በመስጠት እንቅስቃሴውን ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደፊት ማሽከርከር በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፡-ሰ. ሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደኋላ ማሽከርከር

አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-


ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ እጃቸውን ከትከሻቸው በማድረግ መዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ትዛዝ ሲሰጥ ወደኋላ እንዲያሽከረክሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህን እንቅስቃሴ በቂ እረፍት በመስጠት እንቅስቃሴውን ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደኋላ ሲያሽከርክሩ በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 58


ምዕራፍ 5 ጅምናስቲክስ

ተግባር፦ ሸ. ሁለት እጅ ወደፊት ዘርግቶ በማፈራረቅ ጭን ማስነካት


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ በመክፈት እጃቸውን ከጭናቸው በማድረግ መዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩ ጀምሩ ሲል ሁለት እጅ ወደፊት ዘርግቶ በማፈራረቅ ጭን እንዲነኩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ በቂ እረፍት በመስጠት እንቅስቃሴውን ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ የሚሰሩትን እንቅስቃሴ በምልከታ እና በቃል በመጠየቅ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ተግባር፦ ቀ. ሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደጭን ማጠፍ


አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እግር በትከሻ ስፋት ልክ እጃቸውን ከጭናቸው በማድረግ መዘጋጀት፣
ƒƒ መምህሩጀምሩ ሲል ሁለት እጅ ወደፊት ዘርግቶ በአንድ ጊዜ ጭን እንዲነኩማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ በቂ እረፍት በመስጠት እንቅስቃሴውን ከ3—6 ጊዜ በተደጋጋሚ ማሰራት፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ ሁለት እጅ ወደፊት በመዘርጋት ወደጭን በትክክል ሲያጥፉ በምልከታ ማረጋገጥ፣

የመልመጃ መልስ ተግባር፡-1

የተለያዩ የአካል ክፍሎች ቅንጅት እንዲዳብር ይጠቅማል፣ ውሳኔን ሰጭነትን ለማዳበር ይረዳል፣ የጅምናስቲክስ ክህሎት እንዲጨምር
ያደርጋል እና ሌሎችን ጠቀሜታ መጥቀስ ይቻላል።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 59


ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች

ምዕራፍ

6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና


ጨዋታዎች
የክፍለ ጊዜ ብዛት፡ 20

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ በምንኖሩበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች ያዉቃሉ።
ƒƒ በምንኖሩበት አካባቢ የሚዘወተሩ የባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች በተግባር ይጫወታሉ።
ƒƒ በምንኖሩበት አካባቢ የሚዘወተሩ የባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች ለጤናቸዉ የሚሰጠዉን ጠቀሜታ ያደንቃሉ።

መግለጫ፡-

ተተማሪዎች በየአካባቢያቸዉ የሚጫወቷቸዉ በርካታ ባህላዊ ጭፈራዎችና ጨዋታዎች አሉ።

6.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎች (10 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªበምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎችን ይዘረዝራሉ።
ªªበምንኖርበት አካባቢየሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎችን ይጫወታሉ።
ªªበምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎችን ለመስራት ፍላጎት ያሳያሉ።

6.1.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶች ባህላዊ ጭፈራዎች


የመልመጃ ተግባር፡-1

ማስታዎሻ፡- ሴት ተማሪዎች በሠፈራቸዉ እና በአካባቢያቸዉ አዘውትረው የሚጫወቷቸው ባህላዊ ጭፈራዎችን በማምጣት


እንደጭፈራዎች ባህሪያት አንጻርከተለያዩ የአካል ክፍሎች እና ጡንቻዎች ጋር አቀናጅተዉ በእንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
ያስፈልጋል።

6.1.2. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የወንዶች ባህላዊ ጭፈራዎች

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 60


ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች

የመልመጃ ተግባር፡-1

ማስታዎሻ፡- ተማሪዎች በየሠፈራቸዉና በየአካባቢያቸዉ ወንዶች አዘውትረው የሚጫወቷቸው ባህላዊ ጭፈራዎች


በማምጣት በጋራ በመሆን እንደጭፈራዎች ባህሪያት አኳያ ከተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ጋር በማቀናጀት በእንቅስቃሴ
እንዲሰሩ ማድረግ አስፈላጊ ነው።

6.1.3. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶችና የወንዶች ባህላዊ ጭፈራዎች


የመልመጃ ተግባር፡-1

ማስታዎሻ፡- ተማሪዎቹ በየሰፈራቸውና በየአካባቢያቸው ተዘዉትረዉሴቶች እና ወንዶች በጋራ የሚተገብሯቸውን


ባህላዊ ጭፈራዎችን እንዲያመጡ በማድረግ የጭፈራ እንቅስቃሴዎችን ከእጅና ከእግር ጋር በማቀናጀት እንዲሰሩ ማድረግ
ያስፈልጋል።

6.2. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታዎች (10 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ንዑስ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች፡-


ªªበምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ እስከ አምስት ባህላዊ ጨዋታዎችንይዘረዝራሉ።
ªªበምንኖርበት አካባቢየሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታዎችን በመጫወት ክህሎታቸዉን ያሻሽላሉ።
ªªበምንኖርበት አካባቢየሚዘወተሩ ባህላዊ ጨዋታዎችን ለመጫወት ተነሳሽነት ያሳያሉ።

6.2.1. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶች ባህላዊ ጨዋታዎች


የመልመጃ ተግባር፡-1

ማስታወሻ፡-ተማሪዎቹ በየሰፈራቸውና በየአካባቢያቸዉ ሴቶች አዘውትረው የሚጫወቷቸዉን ባህላዊ ጨዋታዎች


እዲያመጡ በማድረግ ከእጅና ከእግር ጋር እንቅስቃሴዎችንጋርአቀናጅቶ ማሰራት አስፈላጊ ነው።

አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-


ƒƒ እንደየ ባህሉ ጨዋታ የሚሆኑ ግባቶችን ማሟላት

የክፍል አደረጃጀት፦ በግልና በቡድን ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ የትምህርቱን ርዕስና አላማዎችን ማስተዋወቅ፣
ƒƒ ሰውነትን በተገቢው ማሟሟቅና ማሳሳብ፣
ƒƒ እንደጨዋታው አይነት በግልና በቡድን በማደራጀት ማሰራት፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 61


ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች

6.2.2. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የወንዶች ባህላዊ ጨዋታዎች


የመልመጃ ተግባር፡-1

ማስታወሻ፡- ተማሪዎቹ በየሰፈራቸውና በየአካባቢያቸው ወንዶች አዘውትረው የሚጫወቷቸዉን ባህላዊ ጨዋታዎች


እዲያመጡበማድረግ ከእጅና ከእግር ጋር እንቅስቃሴዎችንአቀናጅቶ ማሰራት አስፈላጊ ነው።

6.2.3. በምንኖርበት አካባቢ የሚዘወተሩ የሴቶችና የወንዶች ባህላዊ ጨዋታዎች

ተግባር፦ ሀ. እንጫወት ልጆች


ዘፈን፡-ሰኞ——ማክሰኞ - እንጫወት ልጆች
እንሩጥ እንጨፍር - እንጫወት ልጆች
ሩጫ ሽሽጎሽ - እንጫወት ልጆች
ጠጠር ለቀማ ገመድ ዝላይ - እንጫወት ልጆች
አኩኩሉ አየሁሽ - እንጫወት ልጆች እያሉ በቡድን እንዲጫዎቷቸው ማድረግ ያስፈልጋል።
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገመድ፣ ጠጠር፣ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ ከ4—5 ተማሪዎች በየቡድኑ ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎቹን በአነስተኛ ቡድኖች በመከፋፈል እንጫወት ልጆች የሚለዉን ዘፈን ማዘፈን፣
ƒƒ ሰኞ——ማክሰኞን፣ ሩጫ፣ ጠጠር ለቀማ፣ ገመድ ዝላይን የተወሰኑት እንዲዘምሩና የተቀሩት ደግሞ እንቅስቃሴዎቹን እዲሰሩ
ማድረግ፣
ƒƒ ዘማሪዎቹ እንቅስቃሴዎቹን እንዲሰሩ እንቅስቃሴዉን የሚሰሩ ዜማዉን እንዲሉ ማድረግና ማሰራት፣

ƒƒ በዚህ ሁኔታ ጨዋታዉንከ4—6 ጊዜ በመደጋገም ይጫወቷቸዋል፣

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ በእንቅስቃሴው መደሰታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

ተግባር፦ ለ. እንደበቅ ከወንበሩ ስር


ዘፈን፦ ሀሀሀ…….
ሁሁሁ….
እናጨብጭብ በአንድነት።
ሀሀሀ…….
ሁሁሁ….
እንዝለል በአንድነት።
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 62
ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች

ሀሀሀ…….
ሁሁሁ….
እንሩጥ በአንድነት።
ሀሀሀ…….
ሁሁሁ….
እንደበቅ ከወንበሩ ስር------ እያሉ በመዘመር ይጫወቱታል።
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ፣ ወንበር

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎች ካላቸው ቁጥር አንጻር በትንንሽ ቡድኖች ከ5—6 አባላት የያዘ ቡድን ማዘጋጀት፣
ƒƒ ዘፈኑን እየዘፈኑ ወደግራና ወደ ቀኝ አቅጣጫ እጅና አንገታቸውን እያዘነበሉእንዲያጨበጭቡ ማድረግ፣
ƒƒ ዘፈኑን እየዘፈኑ ወደ ግራና ቀኝ አቅጣጫ እጅና አንገታቸውን እያዘነበሉ እንዲዘሉ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ እስከ 1 ደቂቃ እረፍት እየሰጡ ማሰራት።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንደበቅ ከወንበሩ ስር እንቅስቃሴ ሲሰሩ በይበል የተሳተፈው የአካል ክፍል የትኛው እንደሆነ በቃልበመጠየቅ ማረጋገጥ።

ተግባር፦ ሐ. ልቤ ልቤ በርታ
ዘፈን፡- ልቤ ልቤ —— ልቤ በርታ፣
እንዳትረታ (2×)
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ በጥንድ ማደራጀት


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ ተማሪዎችን በሰልፍ ማሰለፍ፣
ƒƒ ተማሪዎችን በሰልፍ በማሰለፍ ልቤ ልቤ —— ልቤ በርታ፣
ƒƒ እንዳትረታ (2×) የሚለውን ዘፈን እያዘፈኑ ከእግርና ከእጅ ጋር በማቀናጀት እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ዘፈኑን እንደጨረሱ ከ10—15 ሜትር እርቀት እጃቸውን ወደጎን እና ወደፊት ዘርግተው የሶምሶማ ሩጫ እንዲሰሩ ማድረግ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ2—4 ጊዜ በተደጋጋሚ እረፍት እየሰጡ ማሰራት ነው።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እንስቃሴውን ለመስራት ያላቸውን ተነሳሽነት በምልከታ ማረጋገጥ፣

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 63


ምዕራፍ 6 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራ እና ጨዋታዎች

ተግባር፦ መ. እርስበርስ ተያይዘን


ዘፈን፡- እጅ ለእጅ ተያይዘን፣
ወደላይ በጋራ ዘለን (2×)
እጅ ለእጅ ተያይዘን፣
ሰላማታ ተለዋውጠን (4×)
እጅ ለእጅ ተያይዘን፣
በጋራ አጨብጭበን (2×)
አስፈላጊ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች፡-
ƒƒ ገላጭ ስዕል፣ ምልክት ማድረጊያ ቁሳቁስ፣ ፊሽካ

የክፍል አደረጃጀት፦ የክፍሉ ተማሪዎች በሙሉ


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል፡-
ƒƒ እጅ ለእጅ ተያይዘው በመቆም መዘጋጀት፣
ƒƒ ወደላይ በጋራ ዘለን የሚለውን ዘፈን ካሉ በኋላ እንደተያያዙ መዝለል፣
ƒƒ መያያዛቸውን ጨርሰው እጅ ከፍ አድርጎ ወደቀኝና ወደግራ ማወዛወዝ፣
ƒƒ በጋራ አጨብጭበን ካሉ በኋላ አራት ጊዜ ማጨብጨብ፣
ƒƒ ይህንን እንቅስቃሴ ከ3—5 ጊዜ በተደጋጋሚ እረፍት እየሰጡ ማሰራት ያስፈልጋል።

ክትትልና ግምገማ፡-
ƒƒ እርስበርስ ጨዋታ ሲጫወቱ እንቅስቃሴውን ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት በምልከታ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

ወንድሜ ያዕቆብ፣ ድንቢለድንቢ፣ ተነሱእንጫወት፣ ዉርዬዉርዬ፣ ጨረቃድንቡልቃ፣ ሁለት ለሁለት ተያይዘን፣ እቴእሜቴ፣
ድንቡሸገላ እና ሌሎች በየሰፈራቸውና በየአካባቢያቸው አዘውትረው የሚጫወቷቸውን ባህላዊ ጨዋታዎችን እንዲያመጡ
በማድረግ ከእጅና ከእግር እንቅስቃሴዎች ጋር በማቀናጅት በተግባር እንዲጫወቷቸው ማድረግ ተገቢ ነው።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ~ 1ኛ ክፍል ~ የመምህር መምሪያ ~ 64

You might also like