You are on page 1of 2

የማርና ሎሚ - ዘርፈ ብዙ ጥቅም

ማር እና ሎሚን በመጠቀም የምናገኛቸው ዘርፈ ብዙ የጤና ጠቀሜታዎች አሉ፡፡ ለዛሬ ከነአሰራራቸው


ይዘንላችሁ መጥተናል፤ አሁኑኑ ሼር አድርገው ይተግብሯቸው፡፡

ማር እና ሎሚ በተፈጥሮ የያዙት አንቲ ኦክሲደንት የሰውነታችንን በሽታ የመካለከል አቅም


እንዲጨምር የማድረግ ሃይል እንዳላቸው በተለያዩ ጊዜያቶች የተካሄዱ ጥናቶች ያመለክታሉ።

በተጨማሪም ማር እና ሎሚ ውፍረትን ለመቀነስ እንዲሁም ለውበት መጠበቂያነት


እንደሚያገለግሉም ተጠቅሷል።

ለብ ባለ አንድ ብርጭቆ ዉሃ ውስጥ ሎሚ እና ማር ጨምሮ ሁሌም ጠዋት መጠጣት ብዙ


ጠቀሜታዎች አሉት።

✔ቦርጭን ለማጥፋት እና ሰዉነታችንን ክብደት ለመቆጣጠር ይረዳናል፦ ለብ ባለ 1 ብርጭቆ ውሃ


ውስጥ ግማሽ ሎሚ እና አንድ የሻይ ማንኪያ ማር በማድረግ መጠጣት።

ይህም ሎሚ በውስጡ ባለው አንቲኢክሲደንት አማካኝነት የስብ ሴሎች እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡


እንዲሁም ማር በተፈጥሮ ሃይል ሰጪ በመሆኑ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ስለሚረዳን ማር እና
ሎሚን መጠቀም ይመከራል።

✔የተስተካከለ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖረን ያድርጋል፦ ለብ ባለ 1 ብርጭቆ ውሃ ውስጥ አንድ የሻይ


ማንኪያ ማር እና ሁለት የሻይ ማንኪያ ሎሚ ጨምሮ ጠዋት ጠዋት መጠጣት የመተንፈሻ አካላችን
እንዲፀዳ በማድረግ የተስተካከለ የአተነፋፈስ ስርዓት እንዲኖረን ያግዛል።

✔የጠራ ቆዳ እንዲኖረን ይረዳናል፦ እኩል መጠን ሎሚ እና ማር በመደባለቅ ቆዳችን ላይ ጠቆር ያለ


ምልክት ባለበት ቦታ ላይ ከቀባን በኃላ ከ 20 እስከ 30 ደቂቃ አቆይተን በቀዝቃዛ ውሃ በመታጠብ የጠራ
ቆዳ እንዲኖረን ማድረግ እንችላለን።

በተጨማሪም ማር እና ሎሚን መጠቀም ቆዳችንን ከድርቀት እና ከኢንፌክሽን ይከላከላል።

✔ጉንፋን ሲይዘን ፍቱን መድሃኒት ነው፦ ማር እና ሎሚ በውስጣቸው ቪታሚን ሲ ስላላቸው ጉንፋን


አምጪ ባክቴሪያዎችን የመከላከል አቅም አላቸው። ግማሽ ሊትር ውሃ፣ ሶስት የሻይ ማንኪያ ማር እና
ሶስት የሻይ ማንኪያ ሎሚ እንዲሁም ዝንጅብል በመጨመር አንድ ላይ በማፍላት መጠጣት ጉንፋንን
ለመከላከል ይመከራል።
✔ብጉርን ያጠፋል፦ ሎሚ እና ማር አንድ ላይ ደባልቆ መቀባት ቆዳችን ላይ ያለ ብጉር ደርቆ እንዲረግፍ
በማደርግ ከብጉር የፀዳ ቆዳ እንዲኖረን ያስችላል።

✔ አሁኑኑ ሼር አድርገው ይተግብሯቸው፡፡

የዝንጅብል ሻይ 10 የጤና በረከቶች

1. በመኪና ሲጓዙ ለሚያስመልሳቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

2. ከማይግሬን የራስ ህመም ይገላግልዎታል፡፡

3.በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ቁርጠትን ይቀንሳል፡፡

4. የትልቅ አንጀት ካንሰርን ይከላከላል፡፡

5. በስኳር በሽታ ምክንያት የሚመጣን የኩላሊት ህመም/ጉዳትን ይከላከላል፡፡

6. በቃር ለሚሰቃዩ ፍቱን ነው፡፡

7. ህመምና ኢንፍላሜሽን (የሰውነት መቆጣትን) እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

8. ጠዋት ጠዋት ለሚከሰቱ ህመሞች ፍቱን ነው፡፡

9. ለጉንፋን እና ፍሉ ህመሞች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

10. የእንቁላል ከረጢት ካንሰርን ይከላከላል፡፡

አሁኑኑ ለሚወዱት ሼር ያድርጉት፣ እርስዎም ይሞክሩት፡፡

You might also like