You are on page 1of 20

የጠሃራ ህግጋቶች

አንደኛ ትምህርት 1

1
የጠሃራ ህግጋቶች 1

ጠሃራ {ንፅህና} በኢስላም


ሶላት ከኢስላም ማዕዘናት ሁለተኛው ነው፡፡
እናም ሶላት ያለ ንፅህና ዋጋ የለውም፡፡
ንፅህና በውሃ ወይም በአፈር እንጂ በሌላ ነገር አይሆንም፡፡

2
የጠሃራ ህግጋቶች 1

የውሃ አይነቶች
የውሃ አይነቶች ሁለት ናቸው፡፡ እነሱም
1) ንፁህ ውሃ የሚባለው ሲሆን፡- እርሱም ለራሱ ንፁህ ሆኖ ሌላውንም ነገር ማፅዳት
የሚችል ውሃ ነው፡፡ ከራሱ ንፅህና አልፎ ሌላን ማፅዳት የሚችል ውሃ ማለት ደግሞ
የተፈጥሮ ባህሪውን ያልለቀቀ የውቅያኖስ፤ የጉድጓድ፤ የምንጭና የጅረት ውሃዎች ማለት
ነው፡፡ ይህ አይነቱ ውሃም ሀደስን ያነሳል፡፡ ቆሻሻን ያስወግዳል፡፡

2) የተነጀሰ ውሃ ሲሆን ፡- እሱም ጥቂት ዉሃ ከሆነ ነጃሳ ነገር የተደባለቀበት ሲሆን: ብዙ


ከሆነ ግን ጣዕሙ ወይም መልኩ ወይም ሽታው በነጃሳው የተለወጠ ውሃ ነው፡፡

3
የጠሃራ ህግጋቶች 1

• ማሳሰቢያ፡
ብዙ ውሃ የሚነጀሰው ነጃሳው ከሶስቱ ባህሪያቶቹ መካከል አንዱን ማለትም: መልኩ
ወይም ጣዕሙ ወይም ሽታው ሲቀየር ነው የሚነጀሰዉ፡፡
ጥቂት ውሃ ደግሞ ነጃሳው ከሱ ጋር በመደባለቁ ብቻ ይነጀሳል ማለት ነዉ፡፡
ውሃ ብዙ የሚባለው ከሁለት ቁልለት (ከሁለት መቶ አስር ሊትር)
የበለጠ ከሆነ ነው፡፡

4
የጠሃራ ህግጋቶች 1

• ዕቃዎች
ከወርቅና ከብር ሌላ በሆኑ ንፁህ ዕቃዎች ሁሉ መጠቀም ይፈቀዳል፡፡
ከሁለቱም በተሰሩ እቃዎች መጸዳዳቱ ወንጀል ቢኖረውም ይቻላል፡፡
መነጀሳቸው ያልተረጋገጡ፡ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች እቃቻቸውንና
ልብሶቻቸውንም መጠቀም ይፈቀዳል፡፡

5
የጠሃራ ህግጋቶች 1

የበክት ቆዳ
• የበክት ቆዳ ሁሉም ነጃሳ ነው፡፡
በከት ለሁለት ይከፈላል፦
1. በምንም መልኩ (ቢታረድም ባህታረድም) ስጋው የማይበላ፡፡
2. ስጋው የሚበላም ሆኖ ሳይታረድ የሞተ ነዉ፡፡
ስጋው የሚበላ ሆኖ የበከተ ቆደው ከተነከረ ለፈሳሽ
ሳይሆን ለደረቅ ነገር ብቻ በሱ መጠቀም ይፈቀዳል፡፡

6
የጠሃራ ህግጋቶች 1

ኢስቲንጃዕ
ኢስቲንጃዕ ማለት በሁለቱ መፀዳጃዎች በኩል የሚወጡ ነገሮችን ማስወገድ ነው፡፡
ይህም ተግባር በውሃ ከሆነ ኢስቲንጃእ ሲባል በድንጋይ ወይም በሶፍት ከሆነ ደግሞ ኢስቲጅማር ይባላል፡፡
ኢስቲጅማር ለማድረግ ከዚህ የሚከተሉት ሁኔታዎች ሊሟሉ ይገባል፡፡
እስቲጅማር የሚደረግበት ነገር ንፁህ፤
የተፈቀደ፤
የሚያፀዳ (ነጃሣን ማስወገድ የሚችል) መሆንና ለምግብነት የማይገለገሉበት መሆን ይኖርበታል፡፡
ኢስቲጅማር በሶስትና ከዚያም በላይ በሆኑ ድንጋዮች ይሆናል፡፡
ከሁለቱ መጸዳጃ መንገዶች በአንዱ መንገድ የወጣን ሁሉ በኢስቲንጃ ወይም በኢስቲጅማር ማስወገድ ግዴታ ነው፡፡
7
የጠሃራ ህግጋቶች 1

በመጻዳዳት ጋራ የተያያዙ ክልክል ነገሮች፡


1. የሚፀዳዳ ሰው በመፀዳጃ ቦታ ላይ ከአስፈላጊ ሰዓት በላይ መዘግየት፤
2. በውሃ መውረጃ ላይ
3. ሰዎች የሚተላለፉበት መንገድ ላይ መጻዳዳት፤
4. ለሰዎች አገልግሎት በሚሰጥ ጥላ ስር መጻዳዳት ፤
5. የሚበላ ፍሬ ከምታፈራ ዛፍ ስር መፀዳዳትና
6. በሜዳ ላይ ሲፀዳዳ ወደ ካዕባ መዞሩ ክልክል ነው፡፡
8
የጠሃራ ህግጋቶች 1

በመጸዳዳት ጋር ተያይዞ የሚጠሉ ነገሮች፡


1. ለሚፀዳዳ ሰው የአላህ ስም ያለበትን ነገር ይዞ ወደ መፀዳጃ ቤት መግባት፤
2. እየተፀዳዳ ባለበት ቦታ ላይ መነጋገር፣
3. በቦይና መሰል ነገሮች ላይ መሽናት
4. የመፀዳጃ አካሉን በቀኝ እጁ መንካት፤
5. በቤተ መፀዳጃ ውስጥ እንኳ ቢሆን ወደ ቂብላ መዞር ይጠላል፡፡
ለችግር ጊዜ ከሆነ ግን ይህ ሁሉ ይፈቀዳል፡፡
በመጸዳዳት ጋር ተያይዞ የሚወደዱ ነገሮች፡
1. የሚፀዳዳ ሰው በትጥበትም ሆነ በማበስ ጊዜ በነጠላ ቁጥር ማድረጉ ይወደዳል፡፡
2. በድንጋይ ካበሱ ቡሃላ በውሃ ማጠብ ነዉ፡፡
9
የጠሃራ ህግጋቶች 1

• ሲዋክ (ጥርስን መፋቅ)


እንደ አራክ ዛፍ ባለ ለስላሳ እንጨት ጥርስን መፋቅ ሱና ነው፡፡
በተለይም ወደ ሶላት ለመግባት ባሰቡ ጊዜ፤ ቁርአንን ሊቀሩ ሲያስቡ፤ በውዱእ ጊዜ አፍን
ከመጉመጥመጥ በፊት፤ ከዕንቅልፍ ሲነሱ፤ ወደ መስጂድና ወደ ቤት ሲገቡ፤ የአፍ ጠረን (ሽታ)
ሲለወጥና በመሳሰሉት ጊዜ ሲዋክ መጠቀም የበለጠ ይወደዳል፡፡
በሲዋክም ጊዜ ሆነ በንፅህና ጊዜ በቀኝ በኩል ባለ አካል መጀመርና የማይወደዱ ነገሮችን
ለማስወገድ ደግሞ በግራ እጅ መጠቀም ሱና ነው፡፡

10
የጠሃራ ህግጋቶች

ሁለተኛ ትምህርት 2

1
የጠሃራ ህግጋቶች 2

• ውዱእ
• የዉዱእ ግዴታዎች ፡-
• 1ኛው፡- ፊትን መታጠብ ሲሆን፤ መጉመጥመጥና በአፍንጫ
ውሃን መውሰድ በዚሁ ግዴታ ውስጥ ይጠቃለላል፡፡
• 2ኛው፡- እጆችን ከጣት ጫፍ አንስቶ እስከ ክርን ድረስ ማጠብ፤
• 3ኛው፡- ሙሉ እራስን ከጆሮዎች ጋር አንድ ጊዜ ማበስ፡፡
• 4ኛው፡- እግርን ከቁርጭምጭሚት ጋር ማጠብ
• 5ኛው፡- ቅደም ተከተሉን (ተራውን) መጠበቅ
• 6ኛው፡- የውዱእ አካላትን ትጥበት ማጠጋጋት

2
የጠሃራ ህግጋቶች 2

• የውዱእ ዋጂቦች፡-
የዉዱእ ዋጂቦች
1. መጀመሪያ ላይ ቢስሚላህ ማለት፤
2. ከሌሊት ዕንቅልፍ የነቃ ሰው በውሃ ውስጥ እጁን ከማስገባቱ
በፊት መዳፎቹን ሶስት ጊዜ ማጠብ ናቸው፡፡

3
የጠሃራ ህግጋቶች 2

• የዉዱእ ሱናዎች፡-
1. ሲዋክ ወይም ጥርስን መፋቅ፤
2. መጀመሪያ ላይ መዳፎችን መታጠብ፤
3. ፊትን ከመታጠብ በፊት መጉመጥመጥና አፍንጫን ውሃ ማስቀደም፤
4. በመጉመጥመጥና አፍንጫን በሚታጠቡበት ጊዜ ፆመኛ ላልሆነ ሰው በደንብ ማዳረስ፤
5. ብዛት ያለውን የፂም ፀጉር መፈልፈል፤
6. ጣቶችን መፈልፈል፤
7. በቀኝ በቀኝ መጀመር፤
8. የውዱእ አካሎችን ሁለትና ሶስት ጊዜ ማጠብ፤
9. አፍንጫን በቀኝ እጅ መማግና በግራ ማስወጣት፤
10. የውዱእ አካሎችን መፈግፈግ፤
11. ውድእን ማሳመር፤
12. በስተመጨረሻ ከነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በተነገረው ዱዓ ማሳረግ፡፡
4
የጠሃራ ህግጋቶች 2

በውዱእ ጊዜ የሚጠሉ፡
• በሙቅ ውሃም ሆነ በጣም በቀዘቀዘ ውሃ ውዱዕ ማድረግ፤
• ለሚታጠቡ አካሎች ከሶስት በላይ መጨመር፤
• ከውዱዕ በኋላ ውሃን ከአካሉ ማራገፍ፤
• ውስጥ አይንን ማጠብ ሲሆን በፎጣ ማዳረቅ ግን ችግር የለውም፡፡

5
የጠሃራ ህግጋቶች 2

• ማሳሰቢያ፡-
• በመጉመጥመጥ ጊዜ ውሃን በአፍ ውስጥ ማንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡
• በአፍንጫ ውሃን መሣብ፡ ውሃን በእጁ ብቻ ሳይሆን በትንፋሽ ወደ ውስጥ ማስገባትና መሳቡ
አስፈላጊ ነው፡፡
• እንደዚሁም በመናፈጥ ውሃውን ከአፍንጫ ማስወጣት ይገባል፡፡
• መጉመጥመጥም ሆነ በአፍንጫ ውሃን ማስገባት በዚህ መልኩ ካልሆነ
በስተቀር አይሆንም፡፡

6
የጠሃራ ህግጋቶች 2

የውዱእ ስርኣት ቅድመ ተከተል፡-


የውዱእ አደራረግ በልብ በማሰብና የአላህን ስም በማውሳት ውዱዕ ይጀመራል፤
አስቀድሞ መዳፎችን ማጠብ ውዱእ በሚደረግበት ጊዜ ሁሉ ይወደዳል፡፡
በጣም የሚወደደው ግን በተለይ ከእንቅልፉ ለተነሳ ሰው ነው፡፡

7
የጠሃራ ህግጋቶች 2

ማሳሰቢያ፡-
በውዱእ ጊዜ የሚታጠቡ አካሎችን ከሶስት ከሶስት ጊዜ በላይ ማጠብ ይጠላል፡፡
አንድ ጊዜ መጉመጥመጥ ግዴታ ሲሆን ከዚያ በላይ መጨመሩ ግን የበለጠ ነው፡፡
አንድ ጊዜ አፍንጫን ማጠብ ግዴታ ሲሆን ሶስት ጊዜ ማድረጉ ግን ተመራጭ ነው፡፡
የፊት ክልሉ (ገደቡ): ፊት በርዝመቱ በተለምዶ የፀጉር መብቀያ ተብሎ ከሚጠራው ቦታ አንስቶ
እስከ መንጋጭላ ድረስ ሲሆን በወርዱ ደግሞ ከአንድ ጆሮ አንስቶ እስከዚያኛው ጆሮ ድረስ ነው፡፡
አንድ ጊዜ እስከ ክርኖቹ ድረስ እጆቹን ማጠብ ግዴታ ነው፡፡ ሶስት ጊዜ ማድረጉ ግን ይበልጣል፡፡
8
የጠሃራ ህግጋቶች 2

በመቀጠል የራሱን ፀጉር ይበስ፡፡


አመልካች ጣቶቹን በጆሮዎቹ ክፍተት ውስጥ ያስገባ፡፡
በአውራ ጣቶቹ ደግሞ የጆሮቹን ጀርባ ይበስ፡፡ ይህ ሁሉ አንድ ጊዜ ብቻ ነው፡፡
ልዩ ልዩ ማሳሰቢያዎች፡-
1) በመጉመጥመጥ ጊዜ ውሃን አስገብቶ ማውጣቱ ብቻ በቂ አይደለም በውስጡ ማንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው፡፡
2) በውዱእ ውስጥ ሲዋክን መጠቀም ይወደዳል፡፡
3) ፂሙ ስስ ከሆነ መብቀያ ቆዳውን ማጠብ ግዴታ ነው፡፡
ጥቅጥቅ ያለና ብዙ ከሆነ ግን የፀጉሩን ላይ ላዩን ብቻ ማጠብ ይበቃል፡፡

9
የጠሃራ ህግጋቶች 2

4) ቀኝ እጁን ከግራው በፊት ማጠብ ይወደዳል፡፡


ከዚያም እግሮቹን ከቁርጭምጭሚቶቹ ጋር ይጠብ፡፡
አንድ ጊዜ ማጠቡ ግዴታ ሲሆን ሶስት ጊዜ ማጠቡ ግን ይበልጣል፡፡
5) ከራስ ማበስ የሚወደደው ከፊቱ መጀመሪያ አንስቶ ወደ ኋላው ነው፡፡
6) ከጆሮ በላይ ያለው ባዶ ቦታ ከራስ አካል ጋር የሚቆጠር ይሆናል፡፡
7) ከውዱዕ ቡኋላ አሽሀዱ አንላ ኢላሀ ኢለሏህ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ
ወ አሽሀዱ አነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉሁ ማለት ያስፈልጋል፡፡

10

You might also like