You are on page 1of 88

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ

ትምህርት
የመምህር መምሪያ
6 ኛ ክፍል

አዘጋጆች
ተስፋሁን መብራቱ
ሁነኝ ገ/ክርስቶስ

አርታኢዎች
ቢኒያም ደጉ
አለምነው ደሳለኝ

ቡድን መሪ
ዶ/ር ተከተል አብርሃም

ዲዛይነር
አትርሳው ጥግይሁን

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ


ይህ መጽሐፍ የተዘጋጀው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በተመደበ በጀት በአብክመ ትምህርት
ቢሮና በምሁራን መማክርት ጉባዔ ትብብር ነው።

የመጽሐፉ ሕጋዊ የቅጂ ባለቤት © 2015 ዓ.ም. አብክመ ትምህርት ቢሮ ነው።

ምሁራን መማክርት ጉባዔ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ትምህርት ቢሮ


ማውጫ
ምዕራፍ 1

የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት

1.1. የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላማዎች.................................................5


1.2 የስፖርት
ምንነት...............................................................................
................6
1.3 የስፖርት ጉዳቶችን መከላከያ
መንገዶች................................................................7
1.4 የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማ፣አርማና መሪ
ቃል........................................................8
1.5 የኢትዮጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች በኢንቨስትመንት/በልማት፣ በፖለቲካዊ እና በማህበራዊ
ገጽታዎች ያላቸው
ተሳትፎ...............................................................................
.........9
ምዕራፍ 2

ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)

2.1. ራስን ማወቅና ራስን መምራት የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች........................13


2.2. ማህበራዊ ግንኙነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች.......................15
2.3. ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥ የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች.................16
2.4. በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች............................18
2.5. ማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች.........19
ምዕራፍ 3

ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)

3.1 የአካል ብቃት


ዓይነቶች..............................................................................
.......22
3.2 የልብና የአተነፋፈስ ስርዓት
ብርታት..................................................................23
3.3 የጡንቻ
ብርታት..............................................................................
.................28
3.4
መተጣጠፍ.............................................................................
.........................35
3.5
ቅልጥፍና..............................................................................
...........................36
3.6 የስፖርት አበረታች ቅመሞች /ዶፒንግ/
ጉዳት.....................................................37
ምዕራፍ 4

አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)

4.1
ሩጫ................................................................................
................................42
4.2
ውርወራ..............................................................................
............................44
4.3
ዝላይ................................................................................
...............................47
3 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል
የተማሪ መጽሐፍ
ምዕራፍ 5

ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)

5.1 የጅምናስቲክስ ምንነትና ጥቅም


........................................................................50
5.2 የጅምናስቲክስ
አይነቶች..............................................................................
.......51
5.3 ሪትሚክ ጅምናስቲክስ
...................................................................................
...59
ምዕራፍ 6

የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)

6.1 ኳስ ከታች ወደላይ መለጋትና ልግን በክንድ መቀበል...........................................64


6.2 ኳስ
መንዳት...............................................................................
.....................65
6.3 ኳስ
ማንጠር..............................................................................
......................68
6.4 የቡድን
ጨዋታዎች.............................................................................
.............71
ምዕራፍ 7

የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)

7.1 የባህላዊ ጭፈራ


ምንነት...............................................................................
.....75
7.2 በአማራ ክልል የሚገኙ ባህላዊ
ጭፈራዎች.........................................................77
7.3 የባህላዊ ጨዋታዎች
ምንነት.............................................................................81
7.4 በአማራ ክልል የሚገኙ ባህላዊ
ጨዋታዎች........................................................83

4 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል


የተማሪ መጽሐፍ
የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

ምዕራፍ

1 የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት

(7 ክ/ጊዜ)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላማዎችና ስፖርት ፅንሰ-ሀሳብ ይረዳሉ።
ƒƒ የስፖርት ጉዳት መከላከያ መንገዶችን ያውቃሉ።
ƒƒ የኢትዮጲያ ዝነኛ ስፖርተኞችን ተግባራት ያደንቃሉ።
ƒƒ የኦሎምፒክ አርማና መመሪያ ትርጓሜዎችን ይረዳሉ።
መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ ስር የተካተቱት አብይ ይዘቶች የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላዎች፣ የስርፖት ትርጓሜዎች፣ የስፖርት ጉዳት
መከላከያ መንገዶች፣ የኢትዮጲያ ዝነኛ ስፖርተኞች ተግባራት፣ የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማ እና መሪ ቃል ትርጓሜዎች ተካተዋል።

1.1. የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላማዎች (1 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡-
ªª ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የጤናና የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላማዎችን ይዘረዝራሉ።
ªª የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ለአካላዊ፣ ለአእምሮዊና ለክህሎታዊ እድገት ያለውን አስተዋጽኦ ይገልጻሉ።

የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ለተማሪዎች ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያበረክት አንዱ የትምህርት ዘርፍ ነው።
ተማሪዎች በእንቅስቃሴዎች አማካይነት ክህሎትና አካላዊ ብቃታቸውን የሚያዳብሩትን ያህል በትምህርት መስኩ መሰረታዊ ንድፈ
ሀሳቦች አማካይነት ደግሞ ግንዛቤያቸውን ያዳብራሉ፤ የአመለካከት ለውጥ ያመጣሉ፤ ለወደፊት ሕይወታቸውና አካላዊ እንቅስቃሴን
ሲሰሩ ውጤታማ የሚያደርጓቸውን መሠረታዊ መርሆዎች ይረዳሉ፤ እንዲሁም ያገኙትን ዕውቀትም በተግባር ይጠቀማሉ።
በተጨማሪም የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላማ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላሉ።

1. የተስተካከለ ብቁ አካላዊ እድገት


2. የክህሎት መዳበር
3. የአእምሮዊ እድገት
4. ማህበራዊና ስሜታው እድገት ናቸው

5 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕሎች፣ ፖስተሮች


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª ከአምስተኛ ክፍል በተማሩት መሰረት የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ትርጉምን እንዲናገሩ የቃል ጥያቄ መጠየቅ
ªª የዕለቱን ትምህርትና አላማ ማስተዋወቅ
ªª የክፍሉን ተማሪዎች አምስት አምስት በማድረግ በቡድን በመከፋፈል የመወያያ ጥያቄዎችን መስጠት ለምሳሌ
ƒƒ የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ት/ት አላማዎች
ƒƒ የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ት/ት አካላዊና አዕምሮዊ እድገት እንዴት ማምጣት ይቻላል
ƒƒ የክህሎት መዳበር ማለት ምን ማለት ነው ወዘተ
ªª በሚወያዩበት ጊዜ እየተዘዋወሩ በመመልከት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ªª የተወያዩበትን በቡድን ተወካይ አማካኝነት ለክፍሉ ተማሪ እንዲያቀርቡ እድል መስጠት
ªª ተማሪዎች የቃል ጥያቄ እንዲጠይቁ ማበረታታት፣ ለጥያቄዎች ምላሽ መስጠትና ዋና ዋና ሀሳቦችን በመድገም ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄ፣ የቡድን ፅብረቃ

ተግባር 1. መልስ
1. በምትኖሩበት አካባቢም ሆነ በሌላ ቦታ የተስተካከለ ጥሩ የአካል ቁመና ያላቸውን ሰዎች ተመልክታችኋል? ይህ
የተስተካከል የአካል ቁመና እንዴት ሊመጣ እንደሚችል በቡድን በመወያየት ለክፍል ጓደኞቻችሁ አስረዱ?
•• የተስተካከለ አካላዊ ቁመና ሊመጣ የሚችለው፡-
• የእንቅስቃሴ መርሆዎችን መከተልና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራት
• ወጥና ዘላቂ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ
• የተስተካከለ አመጋገብ ስርአትን በመከተል
• በቂ እረፍት ማድረግ ወዘተ
2. የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች የትምህርት አይነቶች በምን ይለያል፣ በቡድን እንዲወያ ማድረግ።
•• የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ከሌሎች የትምህርት አይነቶች የሚለይበት
• ትምህርቱ በአብዛኛው በተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ያተኮረ ሆኖ በተጨማሪም በፅንሰ ሀሳብ የተደገፈ መሆኑ።
በመሆኑም የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ያለ እንቅስቃሴ ትርጉም አልባ ማለት ነው።
• አላማው ሁሉንም የባህሪ ፈርጆች የያዘ በመሆኑ በተማሪዎች ላይ አካላዊ፣ አመለካከታዊና የክህሎት ለውጦችን
ለማምጣት ያስችላል
• በምዘና ስልቱ

1.2 የስፖርት ምንነት (1 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የስፖርትን ትርጉም ይገልጻሉ።
ªª የስፖርትና የሰውነት ማጎልመሻ ልዩነትን ይዘረዝራሉ።

6 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

ስፖርት ውድድራዊ ይዘት ያለው ጨዋታ ሲሆን ሀገር አቀፋዊ ወይም ዓለም አቀፋዊ ህግ ያለው ሆኖ አካላዊና አዕምሮዊ ፉክክር
የሚደረግበት ነው። እንቅስቃሴውንም ለመምራት የተቋቋመ የራሱ የሆነ አደረጃጀት ያለው ነው።

• በዋናነት ለውድድር ተግባር ተብሎ የሚደርግ እንቅስቃሴ ሲሆን አሸናፊና ተሸናፊ የሚለዩበት ነው።
• ህጎች ከተወዳዳሪዎች ውጭ በሆነ አካል የወጡና ቀደም ብሎ የተደነገጉ ናቸው። ለምሳሌ የኳስ ጨዋታዎች፣ አትሌቲክስና
ጅምናስቲክስ ሊጠቀሱ ይችላሉ።
የስፖርት ትርጉም ከላይ በተዘረዘረው መሰረት ሆኖ በስሩ የተገለጹት የውድድር ዓይነቶች በሙሉ በሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ይዘት
ውስጥ ተካተው የሚሰጡ ናቸው። ስፖርት በጥቅሉ ሲታይ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ውስጥ የሚገኝና ራሱን በውድድር መልክ
በማደራጀት የሚካሄድ ዘርፍ ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕሎች፣ፖስተር
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• ያለፈውን ትምህርት በጥያቄ መልክ መከለስ
• ስለ ስፖርት ትርጉም ከዚህ በፊት ከተማሩት ጋር በማገናኝት እንዲመልሱ የቃል ጥያቄ መጠየቅ።
• ከተማሪዎች መልስ በመነሳት ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት
• ስፖርት ከጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለውን አንድነትና ልዩነት ጥንድ ጥንድ ሆነው እንዲወያዩ እድል
መስጠት።
• በጥንድ የተወያዩበትን አራት አራት ሆነው በቡድን እንዲወያዩ ማድረግ
• በቡድን የተወያዩበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ
• ከተሰጡት ሀሳቦች ላይ ተጨማሪ ማብራሪያ በመስጠት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄ፣የቡድን ፅብረቃ፣ፈተና

1.3 የስፖርት ጉዳቶችን መከላከያ መንገዶች (1 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የስፖርት ጉዳት ምንነትን ይገልፃሉ።
ªª የስፖርት ጉዳትን ለመከላከል የሚረዱ መከላከያ መንገዶችን ይዘረዝራሉ።
በስፖርት እንቅስቃሴዎች አማካኝነት ሊከሰቱ የሚችሉት ጉዳቶች ብዙ ቢሆኑም ጥቂቶቹ ስብራት፣ውልቃት፣ወለምታ፣የጡንቻ
መሰንጠቅ የአጥንት ወደ ውስጥ መሰርጎድ እና ሌሎችም ይገኛሉ።እነዚህ ስፖርታዊ ጉዳቶች አብዛኛውን ጊዜ ሊከሰቱ የሚችሉት ለምሳሌ
ተገቢ የሆነ የሰውነት ማሟሟቂያ ባለማድረግ እድሜን፣ፆታንና የአካል ብቃትን መሰረት ያደረጉ እንቅስቃሴዎችን ባለማድረግ፣ትክክለኛ
የእንቅስቃሴ ቅደም ተከተል ጠብቆ ባለመስራት እና ሌሎችም ናቸው።
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት ስፖርታዊ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ
ሀ. አዲስና ውስብስብ እንቅስቃሴዎችን ያለ ረዳት አለመስራት
ለ. ድካምና የህመም ስሜት እየተሰማን አለመስረት
ሐ. ለእንቅስቃሴ ተስማሚ የሆ የስፖርት ትጥቅ መልበስ
መ. ከእንቅስቃሴ በፊት ተገቢ የሆነ ሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ መስራት

7 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

ሠ. የእንቅስቃሴ ቅደም ተከተል ጠብቆ መስራት


ረ. የስፖርት መስሪያ መሳሪዎችን በአግባቡ መጠቀም
ሰ. የስፖርት መስሪያ ሜዳዎች አካላዊ ጉዳት ከሚያስከትሉ ነገሮች ነፃ መሆናቸውን ማረጋገጥ።
ሸ. ጥንቃቄ የሚፈልጉ አካላዊ እንቅስቃሴዎች ያለ ባለሙያ ክትትልና ድጋፍ አለመስራት።
ቀ. በቡድን ጨዋታ ወቅት ግጭትን እና መጎዳትን ለመቀነስ የጨዋታ ህግን አክብሮ መጫወት፤
በ. ወጥ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት የአካል ብቃትን ማዳበር ወዘተ የአካል ብቃትን ማዳበር በእንቅስቃሴ
ወቅት በቀላሉ አካላዊ ጉዳት እንዳይከሰት ከመከላከሉም በላይ አካላዊ ጉዳት ቢከሰትም ቶሎ ለማገገም ይረዳል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስፖርታዊ ጉዳቶችን የሚያሳዩ ስዕሎች፣ፎቶግራፍ፣ፖስተር፣
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በአምስተኛ ክፍል የተማሩትን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጊዜ የሚደረጉ ጥንቃቄዎችን እንዲያስታውሱ ጥያቄ መጠየቅ።
ªª ተማሪዎች በቡድን እንዲወያዩ ማድረግና የደረሱበትን ሀሳቦች ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ።
ªª በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ አይነት አካላዊ ጉዳት እንዳይከሰት የምንጠቀምባቸውን የመከላከያ መንገዶች በመዘርዘር ማብራሪያ
መስጠት።
ªª ጥያቄ እንዲጠይቁ ማበረታታት
ªª ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ መስጠትና የቃል ጥያቄ በመጠየቅ ተጨማሪ ማብራሪያ በመስጠት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
ªª በእንቅስቃሴ ወቅት ስፖርታዊ ጉዳቶች እንዳይከሰቱ የሚወሰዱ መከላከያ መንገዶች መግለፃቸውን በቃልና በፅሑፍ ጥያቄ
በመጠየቅ ማረጋገጥ።

1.4 የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማ፣አርማና መሪ ቃል (2 ክ/ጊዜ)


ዝርዝርአላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የኦሎምፒክ ሰንደቅ ዓላማ፣አርማና መሪ ቃልን ይለያሉ።
ªª የኦሎምፒክ ስፖርት አላማን ያደንቃሉ።

1. የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማ ምንም ድንበር በሌለው በነጭ ቀለም መደብ ላይ ያረፈ ሲሆን በመሃሉ አምስት ቀለበቶች ከግራ ወደ
ቀኝ ሰማያዊ፣ ብጫ፣ ጥቁር፣ አርንጓዴና ቀይ ቀለሞችን በማጣመር ይይዛሉ።
2. የኦሎምፒክ አርማ አምስቱ የተለያየ ቀለም ያለቸው ቀለበቶች ሲሆኑ ቀለማቸውም ከላይ እንደተገለጸው የተለያየ ሲሆን
የሚወክሉትም የአምስቱን አህጉራት ሰንደቅ አላማ/ባንዲራዎች ነው። በተጨማሪም የእያንዳንዱ ሀገር የሰንደቅ አላማ ቀለም
ቢያንስ ከኦሎምፒክ አርማ ቀለማት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ቀለም ይወከላል ተብሎ ይታሰባል።
3. የኦሎምፒክ መሪ ቃል (ሞቶ) ማለት ሲቲየስ(ፈጣን)፣ አልቲየስ(ከፍያለ)፣ ፎርቲየስ (ጠንካራ) በኦሎምፒክ ጨዋታዎች የታወቀ
መሪ ቃል (ሞቶ) ሲሆን ትርጓሜውም በውድድሮች አትሌቶች በፍጥነት እንዲሮጡ፣ የበለጠ እንዲወረውሩ፣ ከፍ ብለው
እንዲዘልሉ እና ከተፎካካሪዎቻቸው የበለጠ እንዲዘሉ ስለሚፈለግ አትሌቲክስ የዚህ የኦሎምፒክ መፈክር ፍጹም መግለጫ
ነው። የሚገልጸው ከፍተኛውን የኦሎምፒክ እንቅስቃሴ ምኞትና ፍላጎት ነው። ይኽውም ወንድማማችነት፣ ህብረት፣ ብሎም
ለጋራ ጥቅም በአንድነት መቆም ነው።

8 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

4. የኦሎምፒክ አርማና ምልክቶች የተቀመጡት አምስቱ ቀለሞች ማለትም ሰማያዊ፣ ቢጫ፣ ጥቁር፣ አርንጓዴና ቀይ ሲሆኑ በቀለሞች
የሚወከሉት የአህጉራት ሰንደቅ አላማዎች ሲሆኑ አህጉራቶች ደግሞ አውስትራሊያ፣ ኤሲያ፣ አፍሪካ፣ አውሮፓና፣ አሜሪካ
ናቸው። የኦሎምፒክ መሰረታዊ መርሆዎች የሚባሉት ለስፖርት እንቅስቃሴ መሰረት የሆኑት አካላዊ ሞራላዊ ብቃቶችን
ማሳደግ፣ ወጣቱን ትውልድ በስፖርት ኮትኩቶና አሰልጥኖ ከሁሉም ጋር በመተሳሰብና በወንድማማችነት መንፈስ ተደጋግፎ
በመኖር የተሻለ ሰራማዊ አለምን ለመፍጠር እንዲችል ወዘተማድረግ ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ፖስተር፣ ስእል፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተሎች
ªª ከቀደምት እውቀታቸው በመነሳት ስለኦሎምፒክ ስፖርት ምንነትና አጀማመር እንዲናገሩ እድል መስጠት
ªª ስለ ኦሎምፒክ ባንዲራ፣አርማና መሪ ቃል (ሞቶ) በስዕል በማስደገፍ ገለጻ መስጠት
ªª የቃል ጥያቄዎችን በጠየቅና ተማሪዎችም እንዲጠይቁ እድል መስጠት
ªª ጥያቄዎችን በመመለስና ተጨማሪ ማብራሪያ በመስጠት ማጠቃለል
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄ፣ግብረ-መልስ

1.5 የኢትዮጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች በኢንቨስትመንት/በልማት፣ በፖለቲካዊ (- ክ/ጊዜ)


እና በማህበራዊ ገጽታዎች ያላቸው ተሳትፎ
ዝርዝርአላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የኢትዮጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች ተግባራቸውን ይዘረዝራሉ።
ªª የኢትዮጵያ ዝነኛ ስፖርተኞች ተግባራቸውን ያደንቃሉ።
በኢትዮጵያ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች በአለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ ውድድሮች በመሳተፍ የሀገራቸውን ሰንደቅ አላማ ከፍ ያደረጉና
ሀገራቸውን ለአለም ማህበረሰብ ያስተዋወቁ በርካታ ስፖርተኞችን አፍርታለች።
እነዚህ ስፖርተኞች በውድድር ተሳትፎ ውጤት ማምጣትና ሀገራቸውን በአለም አቀፍ ደረጃ ከማስተዋወቅ በተጨማሪ በሀገራቸው
በስራ ፈጠራ፣ በፖለቲካዊና ማህበራዊ ተሳትፎ የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ ነው። በኢንቨስትመንትና በስራ ፈጠራ የተለያዩ ሆቴሎችንና
የንግድ ተቋማትን በመገንባት፣ ስፖርት ማዘውተሪያና መዝናኛ ስፍራዎችና በማስፋፋት፣ ብዙ የስራ ዕድሎችን ፈጥረዋል። በፖለቲካው
ዘርፍ ደግሞ በተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች በመመደብ አስተዋፅዖ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በማህበራዊ ተሳትፎ በተመለከተ ማህበረሰቡን
በማንቃት የተለያ ቅራኔዎች በሚከሰቱበት ጊዜ በማስታረቅና በማግባባት ወዘተ የሚጫዎቱት ሚና ከፍተኛ ነው።
የኢትዮጲያ ዝነኛ ስፖርተኞች አጭር ታሪክ
1. ቀነኒሳ በቀለ እ.ኤ.አ ሰኔ 13/1982 ዓ.ም, አርሲ ዞን በቆጂ ከተማ ተወለደ።የረጅም ርቀት ሩጫ ተወዳዳሪ ሲሆን በርቀቱ
በአለም
የአትሌቲክስ ውድድር ስኬታማ ሯጭ ነው። በረጅም ርቀት ውድድር መጨረሻ ላይ በጣም በፍጥነት በመጨመር ችሎታው
ይታወቃል።በ 2008 ቤጅንግ ላይ በተካሄደው ኦሎምፒክ በአንድ ውድድር በ 5000 እና 10000 ሜትር ሁለት ሜዳሊያ
ባለቤት ነው። በ 2009 በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዎና በ 5000 ሜ እና በ 10000 ሜ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ
በማሸነፍ የመጀመሪያው ሯጭ ነው።እ.ኤ.አ እስከ 2020 ዓ.ም ድረስ በ 5000 ና 10000 ሜትር ሪከርድ ባለቤት ነው።
የፋጡማ
ሮባ፣የሀይሌ ገ/ስላሴና የደራርቱ ቱሉ አድናቂ ነው።ከስፖርቱ በተጨማሪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ማለትም በስፖርት
ማዘውተሪያ፣ በሆቴልና መዝናኛ ኢንዱስትሪ በስፋት ይሳተፋል።
2. ሰውነት ቢሻው በኢትዮጲያ እግር ኳስ ታሪክ በአሰልጣኝነት ይታወቃል። እ.ኤ.አ በ 1952 ዓ.ም በምዕራብ ጎጃም ቡሬ ከተማ
ተወለደ። በ 1997 ከኢትዮጲያ ብሔራዊ ቡድን ጋር የሴካፋ ዋንጫን አሸነፈ።በ 2004 ዓ.ም የኢትዮጲያን ብሔራዊ ቡድንን
በአሰልጣኝነት በመምራት ከ 31 አመታት በኋላ ለአፍሪካ ዋንጫ ውድድር እንዲያልፍ አደረገ። በአሁኑ ሰአት በግሉ ታዳጊዎችን

9 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

በማሰልጠን ለኢትዮጲያ እግር ኳስ ተተኪዎችን በማፍራት የራሱን ድርሻ በመወጣት ላይ ይገኛል።


3. አትሌት መሰረት ደፋር እ.ኤ.አ ህዳር 19/1983 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተወለደች መሰረት ደፋር በኢትዩጵያ ስኬታማ ሴት
አትሌቶች ውስጥ የምትጠቀስ ናት። ውጤታማ ከሆነችባቸው ውድድሮች ውስጥ በ 3000 ሜትር እና በ 5000 ሜትር
ውድድሮች በዋናነት የምትፎካከር ኢትዮጵያዊ የረዥም ርቀት ሯጭ ናት። በኦሎምፒክ፣ በዓለም ሻምፒዮና እና በአፍሪካ
ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በከፍተኛ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች። የዓለም የቤት
ውስጥ ሻምፒዮና ከ 2004 እስከ 2010 ድረስ በተከታታይ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ የ 3000 ሜትር የቤት ውስጥ
ውድድርን በበላይነት ተቆጣጥራለች። ከስፖርቱ በተጨማሪ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች በስፋት ትሳተፋለች።
መርጃ መሳሪያዎች፦ፖስተር፣ስእል፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የክፍሉን ተማሪዎች አምስት አምስት በማድረግ በቡድን መከፋፈል፣
ªª በአምስተኛ ክፍል የተማሯቸውን ስፖርተኞች በማስታዎስ በየትኛው የስፖርት አይነት ስኬታማ እንደሆኑ፣በተጨማሪ በስራ
ዕድል ፈጠራ፣ በፖለቲካና በማህበራዊ ተሳትፏቸው ያበረከቱትን አስተማፅዖ በቡድን ተወያይተው እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
ªª ለክፍል ደረጃው የተመረጡ ዝነኛ ስፖረተኞች በየትኛው የስፖርት አይነት ስኬታማ እንደሆኑ፣በተጨማሪ በስራ ዕድል
ፈጠራ፣በፖለቲካና በማህበራዊ ተሳትፏቸው ያበረከቱትን አስተማፅዖ በቡድን ተወያይተው እንዲያቀርቡ ማድረግ፣
ªª በቡድን ሲወያዩ ሁሉም ተማሪዎች መሳተፋቸውን ክትትልን ድጋፍ ማድረግ፣
ªª የተወያዩበትን በቡድን ተወካያቸው አማካኝነት ሪፖርት እንቅያቀርቡ ማድረግ፣
ªª የቃል ጥያቄ በመጠየቅና ተማሪዎችም እንዲጠይቁ እድል በመስጠት፣
ªª አጠቃላይ ማብራሪያና ማጠቃለያ በመስጠት ማጠቃል።
ክትትልና ግምገማ
ªª የፕሮጀክት ስራ፣ምልከታ፣ጥያቄና መልስ

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃዎች


መመሪያ አንድ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እውነት ወይም ሀሰት በማለት መልሱ
1. የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ በመስራት አካላዊ ጉዳትን መቀነስ ይቻላል።
2. ስፖርት ማለት በክፍል ውስጥ በእንቅስቃሴ የምንማረው የትምህርት አይነት ነው።
3. ድካም እየተሰማን አካላዊ እንቅስቃሴ መስራትና ከባድ እንቅስቃሴዎችን ያለማንም ርዳታ መስራት ለአካላዊ ጉዳት ይዳርጋል።
4. ከጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ት/ት ዓላማዎች ውስጥ አንዱ የሰዎችን የተስተካከለና ብቁ የሆነ የአካል እድገት ማስገኘት ነው።
መመሪያ ሁለት ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ
1. የአካል እንቅስቃሴ ከአዕምሮ እድገት ጋር ያለው ግንኙነት አብራሩ?
2. በእንቅስቃሴ ወቅት አካላዊ ጉዳት እንዳይከሰት መወሰድ ከሚገባቸው መከላከያ መንገዶች ውስጥ ቢያንስ አራት ጥቀሱ።
3. አምስቱን የኦሎምፒክ አርማ ቀለበት ቀለማቸውን ዘርዝሩ።

10 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርትና ስፖርት
ምዕራፍ 1

መልስ
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
1. እውነት 2. ሀሰት 3. እውነት 4.
እውነት
1. የአካል እንቅስቃሴ ከአዕምሮ እድገት ጋር ያለው ግንኙነት አብራሩ
የሰውነታችን አጠቃላይ ክፍል ትብብር የሚከናወነው በአእምሮአችንና እንዲሁም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ጡንቻዎችና
ነርቮች አማካኝነት ነው።
ለምሳሌ በማንኛውም የሰውነት ክፍላችን የህመም ስሜት ቢሰማን አዕምሯችን ስለሚረብሸው ሌሎች አካላዊም ሆነ አዕምሯዊ
ተግባር ለመፈጸም እንቸገራለን። ስለሆነም የደረሰው የህመም ስሜት አዕምሯችንንም ስለሚጎዳው ያልተስተካከለ የጤና አቋም
አዕምሯችንም ሆነ አካላችን ሊሰሯቸው የሚችሉትን ልዩ ልዩ ክህሎቶች ያደናቅፋል።
2. በእንቅስቃሴ ወቅት አካላዊ ጉዳት እንዳይከሰት መወሰድ ከሚገባቸው መከላከያ መንገዶች ውስጥ ቢያንስ አራት
ጥቀሱ።
ከተማሪው መማሪያ መፅሀፍ ከተገለፁት በተጨማሪ
ƒƒ ከእንቅስቃሴ በፊት የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ መስራት
ƒƒ ተገቢ የስፖርት ትጥቅ ማድረግ
ƒƒ ከእንቅስቃሰው ወይም ከውድድሩ በፊት በቂ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት ማድረግ
ƒƒ የስፖርት መገልገያ መሳሪያዎችን በአግባቡ መጠቀም
ƒƒ ስፖርት ከምንሰራበት ቦታ አደጋ ሊያደርሱ የሚችሉ ቁሳቁሶችን ማራቅ
3. የኦሎምፒክ አምስቱ ቀለበቶች ቀለማቸው ሰማያዊ፣ቢጫ፣ጥቁር፣አርንጓዴና ቀይ ነው

11 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

ምዕራፍ

2 ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ


ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
• የራስን ግንዛቤና አስተዳደርን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይገነዘባሉ።
• ማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ክህሎትን ያዳብራሉ።
• በሀላፊነት የዳበር ውሳኔ አሰጣጥን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይጫወታሉ።
• በጥልቀት ማሰብንና ማገናዘብን የሚያዳብሩ በልዩልዩ ጨዋታዎች ይሳተፋሉ።

መግቢያ
በዚህ ምዕራፍ ስር የተካተቱት አብይ ይዘቶች የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት አላዎች፣ የስርፖት ትርጓሜዎች፣ የስፖርት ጉዳት
መከላከያ መንገዶች፣ የኢትዮጲያ ዝነኛ ስፖርተኞች ተግባራት፣ የኦሎምፒክ ሰንደቅ አላማ እና መሪ ቃል ትርጓሜዎች ተካተዋል።

መግቢያ
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት በግል፣ በጥንድና፣ በቡድን/በህብረት ማከናወን ይቻላል።የቡድን/ህብረት ስራ የማህበራዊ
ግንኙነት አካልና የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴ አንዱና ዋናው ክፍል ነው።
ይህ እንቅስቃሴ በአንድነት ቡድናዊ ቅንጅታቸውን ጠብቀን የምንሰራቸው እንደ ጅምናስቲክስ፣እግር ኳስ፣ ቮሊቦል፣ቅርጫት ኳስና ልዩ
ልዩ ጨዋታዎች ወዘተ ይጠቀሳሉ። ለተሳታፊ ስፖረተኞችም፡-
ªª በጋር የመስራትንና የመፈቃቀድን
ªª ለጋራ አላማ በአንድ መቆምን
ªª ጤንነትንና ደህንነትን ለማስጠበቅ
ªª የጨዋታውን ህግና ደንብ ለማወቅ
ªª ማህበራዊ ኑሮን ለማዳበር
ªª ራስን ለመግዛትና የራስን ስሜት ለመምራት
ªª በጥልቀት የማሰብ ክህሎትን ለማዳበር
ªª በራስ መተማመንና ውሳኔ ሰጭነት ለማዳበር የሚያስችሉ ብቃቶችን ያሳድጋሉ።

12 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

2.1. ራስን ማወቅና ራስን መምራት የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች (3 ክ/ጊዜ)

ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-


ªª የራስን ግንዛቤና አስተዳደርን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ይዘረዝራሉ።
ªª የራስን ግንዛቤና አስተዳደርን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ይጫዎታሉ።
ªª የራስን ግንዛቤና አስተዳደርን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ለመጫዎት ተነሳሽነትን ያሣያሉ።

ራስን ማወቅ ማለት ጥንካሬያችን ፣ ድክመቶቻችን እና ገደቦቻችን፣ መረጃዎችን እንዴት እንደምንሰበስብ እና እንደምናከናውን፣ አሻሚ
እና አስቸጋሪሁኔታዎችን እንዴት እንደምናልፍ እና መፍትሔ እንደምንሰጥ ከሌሎች ጋር እንዴት እንደምንተባበርና እንደምንረዳዳ
ያካትታል።
ራስ መምራት ችሎታዎች ድርጊትን ፣ ስሜትንና እና ሀሳቦችን የመቆጣጠር ችሎታ ናቸው።ራስ ማስተዳደር መቻል አላማን ከግብ
ለማድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን የበለጠ ስኬታማ ለማድረግ ይረዳል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል፣ፖስተር
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በአምስተኛ ክፍል በተማሩት መሰረት ራስን ማወቅና ራስን መምራት የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች እንዲዘረዝሩ የቃል ጥያቄ
መጠየቅ።
ªª ተማሪዎች ከመለሱት መልስ በመነሳት ተጨማሪ ማብራሪያ መስጠት
ªª የእለቱን ትምህርት ከ 5 ኛ ክፍል ከተማሩት ጋር በማያያዝ ማብራሪያ መስጠት።
ªª በቡድን በማደራጀት የመወያያ ጥያቄ መስጠታና እንዲወያዩ ማድረግ
ªª የተወያዩበትን ከየቡድናቸው እንዲያቀርቡ ማድረግ
ªª በቀረበው ላይ ተማሪዎች ጥያቄ እንዲጠይቁ እድል መስጠትና ተጨማሪ ማብራሪያ በመስጠት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-የቃልጥያቄ

ተግባር
1. በ 5 ኛ ክፍል የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የተማሯቸው ራስን ማወቅና ራስን ማስተዳደር የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን
የሚባሉት ጭራ ነቀላ፣የአራት ቤት ምርኮና ውጭና ውስጥ ናቸው።
2. የቀለበት ማጥለቅ እሽቅድድም
የቀለበት ማጥለቅ እሽቅድድም ተማሪዎች ስለራሳቸው ያላቸውን ግንዛቤና ራስን መምራት ችሎታን ለማዳበር የሚያስችል እንቅስቃሴ
ሲሆን በተጨማሪም ለማጥለቅና ለማውለቅ በሚደረግው እንቅስቃሴ ሰውነትን እንደልብ የማዘዝ ችሎታን ከማስገኝቱም ሌላ
ፈጣንና ቀልጣፋ ለመሆን ያስችላል። ጨዋታውን ቡድን በውድድር መልክ ማከናወን ይቻላል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ክብ ጎማ፣ገመድ፣ሰፊ የእንጨት ቀለበት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ªª የክፍሉን ተማሪዎች እኩል በሆነ በሁለት ወይም በአራት ቡድን በረድፍ ማሰለፍ።

13 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

ªª የጨዋታው የአጨዋወት ቅደም ተከተል መንገር


ªª አሰራሩን በተግባር ሰርቶ ማሳየት
ªª ከፊት ለፊት ለቆሙት ለእያንዳንዱ ቡድን አንድ አንድ ቀለበት በመስጠት
ªª ጀምሩ ሲባል ቀለበቱን የያዘው ልጅ ቀለበቱን ከራሱ ጀምሮ ወደ ታች በማውረድ በእግሮቹ አሾልኮ ለተረኛው ልጅ እንዲሰጥ
ማድረግ።
ªª ተረኛው በዚሁ መልኩ በማጥለቅና በማውለቅ ለሚቀጥለው የቡድኑ አባል ይሰጣል ቀድሞ የጨረሰ ቡድን የጨዋታው አሸናፊ
ይሆናል።
ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልክታ
1. እጅ ከፍንጅ
እጅ ከፍንጅ ራስን መምራትና የራስ ግንዛቤን ለማዳበር ከተመረጡ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች አንዱ ነው። በተጨማሪ ጨዋታው ቅልጥፍናን፣
ጥንቃቄንና ማሰብ ችሎታን ለማዳበር ይረዳል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ትንንሽ ኳሶች
መማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ªª የጨዋታው የአጨዋወት ቅደም ተከተል መንገር
ªª ተማሪዎች ክብ ሰርተው እንዲቆሙ ማድረግ።
ªª ለመያዝ የሚመች ትንሽ ኳሽን ለአንዱ ተማሪ መስጠት
ªª ኳሷን እየተቀባበሉ ወደቀኝ ወይም ወደ ግራ ማዞር
ªª በቃ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ኳስ በእጁ ላይ የተገኘበት ልጅ እንደ ዳተኛ ተቆጥሮ እጅ ከፍንጅ ይባላል።
ªª በቃ የሚል ትዕዛዝ እንደተሰጠ ኳሷን ወደ መሬት በመጣል ከጨዋታ ውጭ አለመሆን ይቻላል።
ªª እስከ መጨረሻ ኳስ በእጁ ላይ ያልተገኘ አሸናፊ ይሆናል።
ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ
ªª በጨዋታው ምን ለማዳበር እንደሚጠቅም የቃል ጥያቄ መጠየቅ
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ፣ የቃል ጥያቄ
2. የደሮ ጥል
የደሮ ጥል ጨዋታ ራስን መምራትና ራስን ማስተዳደርን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚካተት ሲሆን በተጨማሪም የእግርና
የእጅ ጡንቻዎችን ለማዳበርና ሚዛንን ለመጠበቅ ይረዳል።

14 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

መርጃ መሳሪያዎች፦ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የበቡድን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª የጨዋታው የአጨዋወት ቅደም ተከተል መንገር
ªª በአካል ብቃት ተቀራራቢ የሆኑትን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው ፊት ለፊት ቁጢጥ/ከጉልበታቸው ሸብረክ በማለት
እንዲቀመጡ ማድረግ።
ªª ቁጢጥ/ከጉልበታቸው ሸብረክ በማለት ዝልል ዝልል በማለት ሚዛናቸውን በመጠበቅ እጃቸውን በደረታቸው በማስጠጋት
በእጅ መዳፍ መጋፋት።
ªª ሚዛን ያሳተ ተማሪ አንድ ነጥብ ያገኛል በዚህ መልኩ አስር ነጥብ ያገኝ ተማሪ አሸናፊ ይሆናል።
ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ
ªª የደሮ ጥል ጨዋታ የአካል ብቃትን ከማዳበር በተጨማሪ ያለውን ጠቀሜታ እንዲናገሩ እድል መስጠት
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ

2.2. ማህበራዊ ግንኙነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች (3 ክ/ጊዜ)


ማህበራዊ ግንኙነትንና ግንዛቤን ማዳበር ከሌሎች ጋር መረዳዳትንና ርህራሄን፣መቻቻልን የሌሎችን ስሜት መረዳትን ያጠቃልላል።
ማህበራዊ ግንኙነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች
ዝርዝርአላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª ማህበራዊ ግንኑነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይጫዎታሉ።
ªª ማህበራዊ ግንኑነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ለመጫዎት ተነሳሽነት ያሣያሉ።
ªª ማህበራዊ ግንኑነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ከጓደኞቻቸው ጋር ለመጫዎት ፈቃደኛ ይሆናሉ።
1. ኳስ እየተቀባበሉ መሮጥ
መርጃ መሳሪያዎች፦ኳስ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª ሰውነታቸውን በቡድን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
ªª የጨዋታውን አጨዋወትና ቅደም ተከተል መንገር
ªª የክፍሉን ተማሪዎች 10፡10 በማድረግ በቡድን መክፈል ጨዋታው በሁለት ቡድኖች መካከል የሚደረግ ሲሆን ጨዋታው ለ 10
ደቂቃ ይደረጋል።
ªª ከሜዳው መሀል ላይ ኳሷን ወደ ላይ በማሻማት ማስጀመር።
ªª ኳስ የደረሰው ቡድን በቡድኑ ላሉ ልጆች በአየር ላይ በመወርወር መቀባበል።
ªª ኳስ መሬት ላይ ካረፈች እንደገና ጨዋታው በመሻማት ይጀምራል።
ªª ብዙ ጊዜ ኳስ መሬት ላይ የወደቀችበት ቡድን ተሸናፊ ይሆናል

15 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ


ªª ኳስ ጨዋታ እንዴት ማህበራዊ ግንኙነትን ማዳበር እንደሚቻል የቃል ጥያቄ መጠየቅ
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፣በጨዋታው ህግ መሰረት መጫዎታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ
2. የቁጥር ትዕዛዝ
መርጃ መሳሪያዎች፦ትንንሽ ኳሶች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቅ ማድረግ
ªª የክፍሉን ተማሪዎች በሁለት እኩል ቡድን በመከፋፈል ከ 30-40 ሜትር ርቀት ፊት ለፊት እንዲቆሙ ማድረግ።
ªª የአጨዋወት ቅደም ተከተሉን መንገር
ªª ከመካከላቸው የ 30 ሳ.ሜ ስፋት ባለው ክብ ውስጥ ሁለት ኳሶች ማስቀመጥ
ªª ለእያንዳንዱ ቡድን አባልት ከአንድ ቁጥር ጀምሮ ቁጥር መስጠት መምህሩ ቁጥር ሲጠራ ከሁለቱ ቡድን ቁጥራቸው የተጠራው
ተማሪዎች በፍጥነት ወደ ኳሷ በመሮጥ ኳሷን በመያዝ በቀኝ በኩል በመዞር ተመልሰው ኳሷን በክቡ መሀል በማስቀመጥ ወደ
ጀመሩበት ቦታ እንዲመለሱ ማድረግ።
ªª በዚህ አኳኋን በየቡድኑ ቁጥሮችን በየተራ በመጥራት ጨዋታውን ማስቀጠል።
ªª ቀድሞ የጨረሰ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ
 ምልከታ

2.3. ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥ የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች (3 ክ/ጊዜ)


በሃላፊነት ተሞላ ውሳኔ ሰጭነት ማለት የስነ ምግባር መመዘኛዎች፣ማህበራዊ ደንቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት የግል ባህሪንና
ማህበራዊ ግንኙነትን በሚያዳብር መልኩ ውሳኔ የመስጠት ችሎታን ያሳያል።
ሃላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች
ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ ለመወሰን የሚረዱ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይዘረዝራሉ።
ªª ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ ለመወሰን የሚረዱ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይጫዎታሉ።
ªª ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ ለመወሰን የሚረዱ ልዩልዩ ጨዋታዎችን በመጫዎት ይደሰታሉ።

16 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

1. በትንንሽ ኳስ ከጉልበት በታች መምታት


በትንንሽ ኳስ ከጉልበት በታች የመምታት ጨዋታ በሚሳተፉበት ጊዜ ተማሪዎች ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ በጨዋታው ህግ መሰረት
ከጉልበት በታች ያለውን እግር ክፍል ብቻ ለመምታት የሚወዳደሩበት ሲሆን በዚህ ጨዋታ ሀላፊነት መወጣትን ከማዳበሩ በተጨማሪ
ወርዋሪዎች በሚወረውሩበት ጊዜ የእጅ ጡንቻ ጥንካሬንና ኢላማ የመምታትን፣ለሚወረወርባቸው ልጆች ደግሞ በኳሱ ላለመመታት
ሲዘሉ የእግር ጡንቻ ጥንካሬንና ቅልጥፍናን ያዳብራል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ትንንሽ ለስላሳ ኳሶች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በቡድን ሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª የክፍሉን ተማሪዎች ከሁለት ቡድን እኩል መክፈል የአጨዋወቱን ቅደም ተከተል መንገር።
ªª አንዱን ቡድን ለሁለት በመክፈል በ 30 ሜትር ርቀት ሁለት ትይዩ መስመሮችን በማስመር በረድፍ እንዲቆሙ ማድረግ።
ªª ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ከመስመሩ መሀል መቆም
ªª ጀምሩ ሲባል ኳስ የያዙት ልጆች ከሜዳው መካከል ያሉትን ተማሪዎች ከጉልበት በታች ለማስነካት ይወረውራሉ መሀል ላይ ያሉ
ልጆች ደግሞ በኳስ ላለመመታት ይዘላሉ።
ªª በኳስ የተመታ ተማሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
ªª ጨዋታው በዚህ ሁኔታ ይቀጥልና መጨረሻ የቀረው ልጅ የቡድኑ አሸናፊ ይሆናል።
ªª ወርዋሪ የነበረው ቡድን ይቀየርና ጨዋታው ይቀጥላል።
ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ
2. ከወገብ መያያዝ
ከወገብ መያያዝ ጨዋታ ላይ ከፊት የሚሰለፈው የቡድኑ መሪ የመጨረሻው የቡድኑ አባል እንዳይነካበት የመከላከል ሀላፊነትና ነጥብ
ለማስመዝገብ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የኋላ ተጫዋች ለመንካት ጥንቃቄና ሀላፊነት በተሞላበት መንገድ ይጫዎታል። የክፍሉ ተማሪዎች
አምስት አምስት በማድረግ በቡድን መከፋፈልና በቡድናቸው በመሰለፍ ከኋላ በሁለት እጅ ወገብ ላይ መያያዝ። አጨዋወቱ የራስን
ቡድን 5 ኛ ተማሪ ላለማስነካትና የተቃራኒን ቡድን ከኋላ ያለውን 5 ኛ ተማሪ ለመንካት መሞከር ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በቡድን ሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª የጨዋታውን የአሰራር ቅደም ተከተል መንገር
ªª የክፍሉን ተማሪዎች አምስት አምስት በማድረግ በቡድን በመክፍል በሰልፍ ከኋላ ወገባቸውን እንዲያያዙ ማደረግ
ªª ከፊት ያለው ተማሪ የቡድን መሪ በመሆን የኳለኛው/5 ኛው ተማሪ እንዳይነካበት እየተከላከለ የተቃራኒ ቡድንን ከኋላ ያለውን
ተማሪ ለመንካት ይጥራል
ªª ጨዋታው በዚህ ሁኔታ ይቀጥልና ቡዙ ግዜ የነካ ቡድኑ አሸናፊ ይሆናል።

17 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

ªª በጨዋታው ያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን በማሰራት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
ªª የጨዋታውን ህግ ጠብቀው መጫዎታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ

2.4. በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብ የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች (2 ክ/ጊዜ)


በጥልቅ ማሰብና ማገናዘብ ማለት ውስብስብ ተገባሮች በሚያጋጥሙን ጊዜ በንቃት እና በችሎታ መረዳትን፣ መተንተን፣ ማዋሃድ እና/
ወይም በመሰብሰብ፣ በማንፀባረቅ፣ በማመዛዘን ወይም በመግባባት የሚጠይቅ ሂደት ነው ።
በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች
ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይዘረዝራሉ።
ªª በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን ይጫዎታሉ።
ªª በጥልቀት ማሰብና ማገናዘብን የሚያዳብሩ ልዩልዩ ጨዋታዎችን በመጫወት ይደሰታሉ።
1. ኳስ በጠባብ ጎል ማሳለፍ
ይህ ጨዋታ ተማሪዎችን በቡድን በመክፈል ከ 10-15 ሜትር ርቀት ላይ አንድ ሜትር ስፋት ያለው ጎል መስራት። በግቦች መካከል
በውስጥ የጎን እግር እንዲመታ ይደረጋል። በትክክል ጎል ሲያስቆጥር በአንድ ጎል አንድ ነጥብ ለቡድኑ ይመዘገባል። የተሸለ ነጥብ
ያስመዘገበ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ትንንሽ ኳሶች፣ኮን
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በቡድን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª የክፍሉን ተማሪዎች ቁጥራቸው እኩል በሆነ በሁለት ወይም በአራት ቡድን መከፋፈልና የጨዋታውን ቅደም ተከተል
መንገር።
ªª በቡድናቸው በመስመር እንዲቆሙ በማድረግ ከ 10-15 ሜትር ርቀት የአንድ ሜትር ስፋት ጎል ማበጀት ለእያንዳንዱ ቡድን መሪ
ኳስ መስጠት።
ªª ጨዋታው በጠባብ ጎል በውስጥ የጎን እግር ጎል ማስገባት ሲሆን አንድ ተማሪ አንድ ጊዜ ብቻ መምታት ይኖርበታል።
ªª አንድ ጎል አንድ ነጥብ ያስገኛል ብዙ ጎል ያስገባ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
ªª የሁሉንም ተማሪዎች ጥረት በማድነቅ ለአሸናፊ ቡድን አድናቆት በመስጠትና ቀላል እንቅስቃሴዎችን በማሰራት የዕለቱን
ትምህርት ማጠናቀቅ።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ
2. በቁጥር መያያዝ
ይህ የጨዋታ አይነት ሁሉንም የክፍሉን ተማሪዎች የሚያሳትፍ ሲሆን በጨዋታው ቁጥር በሚጠራበት ጊዜ ተማሪዎች በንቃት በማሰብ
በተጠራው ቁጥር መሰረት ከየትኛው ልጅ ጋር መያያዝ እንዳለባቸው መወሰን እንዳለባቸውና በተጨማሪም የመስማት ችሎታን
የሚያዳብር የጨዋታ አይነት ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል

18 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል


ªª የሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
ªª የጨዋታውን የአጨዋወት ቅደም ተከተል መንገር
ªª የክፍሉን ተማሪዎች ክብ ሰርተው እንዲቆሙና ትዕዛዝ ሲሰጥ በክቡ መካከል መሮጥ።
ªª ቁጥር ሲጠራ በተጠራው ቁጥር ልክ መያያዝ ለምሳሌ 2 ቁጥር ከተጠራ ሁለት ሆነው መያያዝ፣3 ቁጥር ከተጠራ ሶስት ሆነው
መያያዝ…
ªª ባልደረባ ያላገኘ ልጅ ከጨዋታ ውጭ ይሆናል።
ªª በዚህ አኳኋን ጨዋታው ይቀጥልና መጨረሻ የቀሩ ሁለት ልጆች አሸናፊ ይሆናሉ።
ªª ከጨዎታው ምን ጥቅም እንዳገኙ የቃል ጥያቄ በመጠየቅና ተጨማሪ ማብራሪያ በመስጠት የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ
እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የቃል ጥያቄ

2.5. ማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ (3 ክ/ጊዜ)


ጨዋታዎች
ማህበራዊ ግንኙነትን ማዳበርና የትብብር ችሎታ ማለት ከቡድን አባል ጋር ወደ አንድ የጋራ ግብ በተሳካ ሁኔታ ለመድረስ የሚያስችል
ህብረት ነው። ስለሆነም በግልጽ መግባባት፣ ሌሎችን በንቃት ማዳመጥ፣ ለስህተቶች ሃላፊነትን መውሰድ እና ባልደረባንን ማክበርን
ያካትታሉ።
ማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች
ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª በማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይዘረዝራሉ።
ªª በማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን በቡድን ይጫዎታሉ።
ªª ማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታን የሚያዳብሩ ጨዋታዎችን የጨዋታ ህግና ደንብ አክብረው ይጫወታሉ።
1. በእጅ መጓተት
በ 30 ሜትር ርቀት ክልል ሶስት መስመሮችን ማስመር፣ የክፍሉን ተማሪዎች ለሁለት እኩል መክፈል፣በቁመትና በሰውነት ተመጣጣኝ
የሆኑት ከየቡድኑ ፊት ለፊት ትይዩ ሆነው መቆም፣አንድ እግርን ወደፊት በማድረግ እጅ ለእጅ መያያዝና ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ
ሁሉም በበኩሉ ወደራሱ ሜዳ በመጎተት የመጨረሻውን መስመር ለማሳለፍ መሞከር።
መርጃ መሳሪያ፡- ፊሽካ፣ ገመድ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የበቡድን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª የጨዋታው የአጨዋወት ቅደም ተከተል መንገር
ªª በ 30 ሜትር ርቀት ክልል ሶስት መስመሮችን ማስመር
ªª የክፍሉን ተማሪዎች ለሁለት እኩል መክፈል፣በቁመትና በሰውነት ተመጣጣኝ የሆኑት ከየቡድኑ ፊት ለፊት ትይዩ ሆነው
እንዲቆሙ ማድረግ።

19 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

ªª አንድ እግርን ወደፊት በማድረግ እጅ ለእጅ መያያዝና ጀምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ሁሉም በበኩሉ ወደራሱ ሜዳ በመጎተት
የመጨረሻውን መስመር ለማሳለፍ መሞከር።
ªª ጎትቶ ወደራሱ መስመር ያስገባ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
ªª ውድድሩ በተማሪዎች ላይ እጅ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ሆኖ ከታየን በእጅ መያያዙን ትተን የገመድ መጓተት ማድረግ ይቻላል
ªª በግል ወይም በቡድን የሰውነት ማቀዝቀዣ እንዲሰሩ ማድረግ
ªª ውድድሩ የአካል ብቃትን ከማዳበር በተጨማሪ ያለውን ጠቀሜታ እንዲናገሩ እድል መስጠት
ªª ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
ªª የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ
ªª በተቀመጠው ህግ መሰረት መጫዎታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣የቃል ጥያቄ
2. ዘንግ/ዱላ ቅብብል
የዘንግ/ዱላ ቅብብል ጨዋታ የሩጫ ውድድር ጨዋታ ሲሆን ውድድሩ በቡድን የሚከናወን ሲሆን ለቡድኑ አሸናፊነት ሁሉም የቡድኑ
አባላት አስተዋፅኦ ያደርጋል በዚህም የማህበራዊ ግንኙነትንና የትብብር ችሎታ ያዳብራሉ። በተጨማሪም ፍጥነትና ቅልጥፍናን፣የዱላ
የመቀባበል ክህሎትን ያዳብራሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦ አነስተኛ ዘንግ/ዱላ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª ማህበራዊ ግንኙነትን የትብብር ችሎታን እንዴት ማዳበር እንደሚቻል የቃል ጥያቄ መጠየቅ።
ªª የጨዋታውን ቅደም ተከተል መንገር
ªª ተማሪዎችን በአራት ቡድን በመከፈል ከ 30-50 ሜትር ሁለት ትይዩ መስመር ማስመር።በተሰመረው መስመር ኋላ ትይዩ ሆነው
በሰልፍ እንዲቆሙ ማድረግ።
ªª የመጀመሪያው ቡድን ሁለቱ ልጆች ዱላ ይይዛሉ፤፤
ªª ጅምሩ የሚል ትዕዛዝ ሲሰጥ ዱላ የያዙት ልጆች በመሮጥ ፊት ለፊት ላሉት ልጆች በማቀበል ከኋላ ይሰለፋሉ።
ªª በዚህ መሰረት ሁሉም የቡድኑ አባልት ይቀባበላሉ ቀድሞ የጨረሰ ብድን አሸናፊ ይሆናል።
ªª በጨዋታው ምን እንደተማሩ የቃል ጥያቄ መጠየቅ
ªª ማህበራዊ ግንኑነትንና የትብብር ችሎታን እንዴት ማዳበር እንዳለባቸው ማጠቃለያ መስጠት
ªª የሰውነት ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን በማሰራት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-የቃል ጥያቄ፣ምልከታ
3. ኳስ መቀባበል
ተማሪዎችን በቡድን እኩል በመከፋፈል ማሰለፍ፣ከፊት ለቆሙ ተማሪዎች ኳስ መስጠት፣30 ሜትር ርቀት ምልክት/ኮን ማስቀመጥ
ትዕዛዝ ሲሰጥ ኳስ የያዙ ተማሪዎች ኳሱን እንደያዙ በመሮጥ ምልክቱን ዙረው በመምጣት በተነሱበት ቦታ በመሆን ኳስን ወደኋላ ከራስ
በላይ ማቀበል።ሁሉም የቡድኑ አባላት ኳስን ከራስ በላይ ወደኋላ ካቀበሉ በኋላ የመጨረሻው ተማሪ ኳስን ይዞ በመሮጥ ምልክቱን ዙሮ

20 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ማህበራዊና ስሜታዊ እድገትን የሚያዳብሩ ልዩ ልዩ ጨዋታዎች(15 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 2

በመምጣት የመጀመሪያው ተማሪ የሰራውን ተመሳሳይ ይሰራሉ ሁሉም በዚህ መልኩ ከተዳረሰ በኋላ ቀድሞ የጨረሰ ቡድን አሸናፊ
ይሆናል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያዩ ኳሶች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በቡድን የሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት።
ªª የአጨዋወቱን ቅደም ተከተል መንገር
ªª የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን እኩል በመክፈል ማሰለፍ፣30 ሜትር ርቀት ምልክት/ኮን ማስቀመጥ
ªª ከፊት ለተሰለፉት ለሁሉም ቡድን ተማሪዎች ኳስ መስጠት ጅምሩ ሲባል ኳሱን በመያዝ 30 ሜ በመሮጥ ምልክቱን ዙረው
ከተነሱበት ሰልፍ በመቆም ኳስን ከራስ በላይ ወደኋላ መቀባበል
ªª ኳሱ የመጨረሻው ተማሪ ጋር ሲደርስ ልክ የመጀመሪያው ተማሪ እንደሰራው በፍጥነት በመሮጥ ተመልሶ ፊት መስመር ላይ
ይቆምና ኳስን ወደኋላ ይቀባበላሉ
ªª ሁሉም ተማሪዎች ተመሳሳይ ተግባራትን ይሰሩና ቀድሞ የጨረሰ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
ªª የሁሉንም ተማሪዎች ተሳትፎ በማድነቅ ቀላል የሰውነት ሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የቃል ጥያቄ

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃዎች


1. ራስን ማወቅና ራስን መምራት ማለት ምን ማለት ነው
2. ማህበራዊ ግንኙነትንና ግንዛቤን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ዘርዝሩ
3. ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥ ማለት ምን ማለት ነው።
4. በሰውነት ማጎልመሻ ት/ት ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥ እንዴት ማዳበር እንችላለን።

መልስ
1. የራስ ግንዛቤ/ራስን ማወቅ ማለት ጥንካሬያችን፣ ድክመቶቻችን እና ገደቦቻችን፣ መረጃዎችን እንዴት እንደምንሰበስብ
እና እንደምናከናውን፣ አሻሚ እና አስጨናቂ ሁኔታዎችን እንዴት እንደምናልፍ እና መፍትሔ እንደምንሰጥና ከሌሎች
ጋር እንዴት እንደምንተባበርና እንደምንረዳዳ ያካትታል።
2. ኳስ እየተቀባበሉ መሮጥ፣የቁጥር ትዕዛዝ..
3. በሃላፊነት ተሞላ ውሳኔ ሰጭነት ማለት የስነ ምግባር መመዘኛዎች፣ማህበራዊ ደንቦች ከግምት ውስጥ በማስገባት የግል
ባህሪንና ማህበራዊ ግንኙነትን በሚያዳብር መልኩ ውሳኔ የመስጠት ችሎታን ያሳያል።
4. በሰውነት ማጎልመሻ ት/ት ሀላፊነት ተሞላበት ውሳኔ አሰጣጥን ለማዳበር በተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴዎች፣ በቡድን
የኳስ ጨዋታዎች ጊዜ በሚፈጠረው የእርስ በርስ ግንኙነት ጊዜ ግጭቶች እንዳይከሰቱ ከተከሰቱም በሰላማዊ መንገድ
በውይይት መፍታት፣ በውድድር ጊዜ በተለያዩ ሀላፊነትን መሳተፍና ሀላፊነትን በአግባቡ ለመወጣት ይረዳል።

21 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

ምዕራፍ

3 ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/


ጊዜ)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ የአካል ብቃትን የሚያዳብሩ የእንቅስቃሴ አይነቶችንና የአካል ብቃት ዓይነቶችን ይገነዘባሉ።
ƒƒ ከዕድሜቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት የአካል ብቃታቸውን ያዳብራሉ።
ƒƒ በተለያዩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለመሳተፍ ተነሳሽነት ያሣያሉ።
ƒƒ አበረታች ቅመሞች(ዶፒንግ) በጤና ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ይገነዘባሉ።

መግቢያ
የጤናና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ተደጋግሞ እንደተገለጸው ጤናማ ሕይወትን ለመምራት ከሚያገለግሉት ትምህርቶች አንዱ ነው።
ጤናማ ሕይወት፣ የአካል ብቃትና ሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት የተሳሰሩ ፅንሰ ሃሳቦች ናቸው። በንድፈ ሃሳብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን
ተሳታፊዎች አካላዊ እንቅስቃሴ በሰሩት መጠን የጤናና የብቃት ደረጃቸውን እንደሚያሳድጉ በተግባር ተረጋግጧል።
በዚህ ምዕራፍ የውስጥ የተጠቃለሉት የአካል ብቃት ዓይነቶች፣ የልብና የአተነፋፈስ ሥርዓትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች፣ የጡንቻ
ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች፣ መተጣጠፍን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች፣ ቅልጥፍናን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ተካተዋል።
በዚህም መሰረት መምህራን የተጠቀሱትን ክፍለ ጊዜያት በአግባቡ በመጠቀም በሥራ እንዲተረጉሟቸው ተማሪዎቹ በመደበኛውም
ሆነ ከመደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ውጪ በመኖሪያ ቤታቸውና አካባቢም ጭምር በመሳተፍ የበለጠ ተጠቃሚ እንደሆኑ እናሳስባለን።

3.1 የአካል ብቃት ዓይነቶች (2 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª የአካል ብቃት ዓይነቶችን ይዘረዝራሉ።
ªª የተለያዩ አካል ብቃትን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።
ªª የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ተነሳሽነትን ያሣያሉ።

የአካል ብቃት ዓይነቶች የተለያዩ ሲሆኑ እነዚህን የአካል ብቃት ለመገንባትም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ወይም መለማመድ
ይጠይቃል። የአካል ብቃት ጤና ተኮርና ክህሎት ተኮር በመባል በሁለት የሚከፈል ሲሆን ጤና ተኮር የምንለው የሰውነታችንን የተለያዩ
ክፍሎች ተፈጥሮዊ አሰራር በተስተካከለ ሁኔታ እንዲካሄድ ለማድረግ የሚረዳ ሲሆን ክህሎት ተኮር የምንለው ደግሞ በአንድ የውድድር
አይነት ብቁ ተወዳዳሪ ለመሆን በሚያስችል መልኩ የምንሰራውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የሚይዝ ነው።

22 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

አብዛኛው የመሰኩ ባለሙያዎች በጋራ እንደሚሰማሙበት የአካል ብቃት ማለት አንድ ሰው የዕለት ተዕለት መደበኛ ስራውን ለማከናወን
በተለያዩ መዝናኛዎች ለማሣተፍ እና ድንገተኛ አጋጣሚዎችን ለመወጣት የሚያስችለውን የመስራት አቅም እና የመገንባት ሂደት
እንደሆነ ይስማማሉ።
አንድ ሰው የአካል ብቃት አለው የሚባለው የእንቅስቃሴ ፍጥነትና ቅልጥፍና የአካል ጥንካሬና ብርታት እንዲሁም የመሳሳብና
የመተጣጠፍ ችሎታን አሟልቶ ሲገኝ ነው። እነዚህ ችሎታዎችም የአካል ብቃት ዘረፎች ተብለው ይጠራሉ።
•• የአካል ብቃት ዓይነቶች በሁለት ይከፈላሉ እነሱም፡-
1. ጤና ተኮር የአካል ብቃት
2. ክህሎት ተኮር የአካል ብቃት ይባላሉ።
1. ጤና ተኮር የአካል ብቃት
•• ጤና ተኮር የአካል ብቃት ዘርፎች የሚባሉት የልብና የአተነፋፈስ ብርታት፣ የጡንቻ ብርታት ፣የጡንቻ ጥንካሬ፣
መተጣጠፍ፣ ሰውነት አደረጃጀት ይባላሉ።
2. ክህሎት ተኮር የአካል ብቃት
•• ክህሎት ተኮር የአካል ብቃት ዘርፎች የሚባሉት ፍጥነት፣ ቅልጥፍና፣ ሀይል፣ የአካል መስተጋብር፣ሚዛን
መጠበቅ ወዘተ ናቸው።
መርጃ መሳሪያዎች፡ -የተለያዩ የአካል ብቃት ዘርፎችን የሚያሳዩ ስዕል፣ፖስተር
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª በ 5 ኛ ክፍል በተማሩት መሰረት የአካል ብቃት ምንነትን እንዲያብራሩ እድል መስጠት።
ªª በተለያየ ቡድን እንዲደራጁ ማድረግ
ªª የየዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማ ማስተዋወቅና የመወያያ ነጥቦችን መግልፅ
ªª የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጤና ጋር ያለዉን ግንኙነት በቡድን እንዲወያዩ ማድረግ
ªª ተማሪዎች በቡድን ሲወያዩ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ªª በቡድን የተወያዩበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ
ªª በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ማድረግ
ªª ተጨማሪ ነጥቦችን በመጨመር ማጠቃለል
ክትትልና ግምገማ፦ በምልከታ፣ የቃል ጥያቄ መጠየቅ፣ የቡድን ፅብረቃ

3.2 የልብና የአተነፋፈስ ስርዓት ብርታት (8 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የልብና የአተነፋፈስ ስርዓት ብርታትን ለማሻሻል የሚረዱ የእንቅስቃሴ አይነቶችን ይዘረዝራሉ።
ªª የልብና የአተነፋፈስ ስርዓት ብርታትን ለማሻሻል የሚረዱ የእንቅስቃሴዎችን ለመስራት ተነሳሽነት ያሣያሉ።
የልብና የአተነፋፈስ ስርዓት ብርታት ስንል የልብና የሳንባ ክፍሎች ተግባራቸውን ለረጀም ጊዜ በትክክልና በተገቢው መንገድ የማከናወን
ብቃት ማለት ነው። ልብና ሣንባችን የተለያዩ ስራን እንደሚያከናውኑ ይታወቃል ስለሆነም የልብ ብርታት ስንል ልብ በተደጋጋሚና

23 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

ያለማቋረጥ ደም የመርጨት ተግባሩን በአግባቡ መወጣት ሲችል ነው የስርዓተ ትንፈሣ ብርታት ስንል ደግሞ ሣንባችን ኦክስጅንን
የማስገባትና ካርበንዳይ ኦክሣይድን በአግባቡ ማስወጣት ስራውን በብቃት ማከናወን ሲችል ነው።
የልብና የአተነፋፈስ ስርአት ብርታትን ለማዳበር የኤሮቢክስ/አየራዊ/ እንቅስቃሴን አዘውትረን በመስራት የልብ ጡንቻን እንዲጠነክርና
የበለጠ ብቁ እንዲሆን በማድረግ በእያንዳንዱ የልብ ምት በቂ ደም እንዲሰራጭ ያደርጋል ። በተጨማሪም የኤሮቢክስ እንቅስቃሴ ብቁና
ለረጅም ጊዜ የመስራት አቅም በመጨመር ሰውነት በፍጥነት እንዲያገግም /Recover/ ያደርጋል ።
የኤሮቢክስ እንቅስቃሴ የሚከናወነው የእንቅስቃሴውን ክብደት በመቀነስ ለረጅም ጊዜ /ጊዜውን በመጨመር / የሚከናወን ተግባር
ነው ። ተግባሮችም ርምጃ ፣ ረጅም ርቀት ሩጫ፣ ሶምሶማ ሩጫ፣ ኤሮቢክስ ዳንስ፣ ብስክሌት መጋለብ፣ ውሃ ዋና ከሚጠቀሱት ውስጥ
ጥቂቶች ናቸው እነዚህን እንቅስቃሴዎች ለመተግበር ኦክስጅን በሰፊው የሚያስልጋቸው በመሆኑ ተገቢ የሆነ የኦክስጅን አጠቃቀምን
ልምምድ ሥርዓትን መከተልን ይጠይቃል እነዚህን እንቅስቃሴዎች ስንሰራ ከፍተኛ የስራ ጫና የሚኖረው በልባችንና በመተንፈሻ አካላት
ላይ ነው።
የልብና የመተንፈሻ አካላቱ የዳበረ ሰው የዕለት ተዕለት ተግባራትን ያለድካም ማከናወን ይችላል፣የተስተካከለ ክብደት ይኖረዋል፣በሽታ
የመከላከል አቅም ያዳብራል፣የልብና የሳንባ ጡንቻው ተንካራና ጤነኛ ይሆናል ወዘተ.
በ 5 ኛ ክፍል ከተማሩት የልብና የመተንፈሻ ብርታትን ለማዳበር ከሚሰሩ እንቅስቃሴዎች መካከል እግር ጉዞና የሶምሶማ ሩጫ እንዲሁም
ገመድ ዝላይ የላቀ ውጤት ያስገኛሉ።በዚህ ክፍል ደረጃም ከላይ ከተጠቀሱት እንቅስቃሴዎች በተጨማሪም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት
እንቅስቃሴዎች የተማሪዎችን የአካል እድገትና የክፍል ደረጃ በሚመጥን መልኩ በማዘጋጀት ማቅረብ ከመምህሩ ይጠበቃል።
የማስተማሪያ መሳሪያ፡- ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስዕሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
ªª የልብና የስርአተ ትንፈሳ ብርታት ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን ጥያቄ ከዚህ በፊት ከተማሩትና ከሚያውቁት በመነሳት
እንዲናገሩ እድል መስጠት።
ªª አራት አራት በማድረግ በቡድን ማደራጀት።
ªª የልብና የስርአተ ትንፈሳ ብርታት ለማዳበር የሚያገለግሉ የእንቅስቃሴ አይነቶችን በቡድን እንዲዘረዝሩ ማድረግ።
ªª በቡድን የዘረዘሯቸውን እንቅስቃሴዎች በግድግዳ ላይ በመለጠፍ ሌሎች ቡድኖች የዘረዘሩትንም በመዘዋወር ማየት።
ªª የቡድን ስራቸውን በመዘዋወር ማየትና ድጋፍ ማድረግ።
ªª ተጨማሪ ሀሳቦችን በመጨመር ማጠቃለያ መስጠት።
ክትትልና ግምገማ፦ በሚወያዩበት ወቅት በምልከታ ማረጋገጥ፣ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ፣ በፈተና
የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች
ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
ªª የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ªª የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ከጓደኞቻቸው ጋር ይሰራሉ።
ªª የልብና የአተነፋፈስ ብርታትን የሚያዳብሩ የተመረጡ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
1. የሶምሶማና ሩጫን በማፈራረቅ መሮጥ
መርጃ መሳሪያዎች፦ስዕሎች፣ ፖስተሮች፣ፊሽካ

24 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል


• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና የመሳሳብ እንቅስቃሴዎች እንዲሰሩ ማድረግ።
• የእንቅስቃሴውን የአሰራር ቅደም ተከተል ማብራሪያ መስጠት
• እንቅስቃሴውን የእጅና የእግር ቅንጅትን አስተካክሎ መጀመር(ቀኝ እጅ ከግራ እግር ግራ እጅ ከቀኝ እግር ጋር
በማቀናጀት ማሰራት)
• ከወገብ ትንሽ ወደ ፊት በማዘንበል ከአንገት ቀና በማለት በሶምሶማ መሮጥ
• ከወገብ ትንሽ ወደ ፊት በማዘንበል ከአንገት ቀና በማለት በመካከለኛ ፍጥነት መሮጥ
• ከወገብ ትንሽ ወደ ፊት በማዘንበል ከአንገት ቀና በማለት በሶምሶማና በመካከለኛ ፍጥነት መሮጥ
• 100 ሜትርን በሶምሶማ 100 ሜትርን ደግሞ በመካከለኛ ፍጥነት በመሮጥ 800 ሜትሩን እንዲሸፍኑ ማድረግ።
• እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ፣ የቃል ጥያቄ
2. ገመድ ዝላይ
መርጃ መሳሪያዎች፦ ገመድ፣ስዕል፣ሰዓት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የመሳሳብ እንቅስቃሴዎች ማሰራት።
• የአስራር ቅደም ተከተሉን ማብራሪያ መስጠት
 የገመድ ዝላይ በሚከናወንበት መልክ ገመዱን እንዲይዙ ማድረግ
 ከዚያም በገመዱ ላይ ወደፊት ተራምደው እንዲያልፉ ማድረግ
 በመቀጠልም ገመዱን ከራስ በላይ አዙረው ወደፊት ማምጣት
 በመጀመሪያ በቦታ ከዚያም ዕርምጃ እያደረጉ ፍጥነትን ቀስ በቀስ በመጨመር የገመድ አዘላለል ስልት
ከተማሩ ከኋላ ቀጥሎ ያሉትን እንቅስቃሴዎች እንዲያከናውኑ ማድረግ
 በመካከለኛ ፍጥነት ገመድ እየዘለሉ ወደፊት እንዲሮጡ ማድረግ
• የተለያዩ የአዘላለል ዓይነቶችን ተጠቅመው ገመድ ዝላይን እንዲያከናውኑ ማድረግ።
• እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ፡
• በቡድን በቡድን በመሆን የገመድ ዝላይን በውድድር መልክ ማከናወን።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
• እንቅስቃሴው የተፈለገውን አጥጋቢ ውጤት እንዲያመጣ ተማሪዎች በሰፈራቸው እንዲለማመዱ መግለጽ።

25 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

ክትትልና ግምገማ
• እንቅስቃሴውን በትክክልና በተገቢው ሁኔታ መስራታቸውን በምልከታ ማረጋጥ
3. የፍጥነት እርምጃ
መርጃ መሳሪያዎች፦ስዕል፣ፖስተር
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የመሳሳብ እንቅስቃሴዎች ማሰራት።
• የፍጥነት እርምጃን ሲሰሩ ትክክለኛ የእጅና የእግር ቅንጅትን እንዴት እንደሆነ ማሳየት።
• ከዝቅተኛ ፍጥነት እርምጃን እንዲሰሩ ማድረግ።
• እርምጃን ፍጥነት እየጨመሩ እንዲሰሩ ማድረግና ዕርስ አርስ እየተጋገዙና እየተራረሙ እንዲሰሩ ማድረግ
• የፍጥነት ሩጫ በሚሰሩበት ሰአት የትኛው የሰውነት ክፍል ይበልጥ እንደሰራ መጠየቅ
• የፍጥነት ሩጫ በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የቃል ጥያቄ
4. በቦታ ላይ መሮጥ
•• ተግባር፡-3.3
1. ባለንበት ስንሮጥ ፍጥነት ስንጨምር አተነፋፈሣችን እየከበደና እየጨመረ ይመጣል ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው
ትላላችሁ።
መልስ፡- ሰውነት ንጥረ ሃይልን ለማግኘት ሲል በቂ ኦክስጅን የሚቀበል ከሆነ የስፖርት እንቅስቃሴ እስኪጠናቀቅ ድረስ የሚሰማ የድካም
ስሜት ዝቅተኛ ይሆናል። ፍጥነት እየጨመርን በምንሄድበት ጊዜ ግን ኦክስጅን አልባ ንጥረ ሃይል ከባለኦክስጅን ንጥረ ሃይል በልጦ
ይገኛል በአጭር ጊዜ የስፖርት እንቅስቃሴ ከፍተኛ የድካም ስሜት ይሰማል።
ስለዚህ በስፖርት እንቅስቃሴ ጊዜ ያለድካም መቆየት የሚያስችል አቅም የሚገኘው ሰውነት የባለኦክስጅን ንጥረ ሃይልን ስራ የማካሄድ
ብቃት ሲኖረው መሆኑ ግልጽ ነው።
ልብ፣ ሣንባና ጡንቻ ለሚያካሄዱት የስራ ብቃት ሰውነት የሚያመነጨው የባለኦክስጅን /ኦክስጅንን በመጠቀም/ ንጥረ ሃይል መጠን
ወሣኝነት አለው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የእግርና የእጅ ቅንጅትን የሚያሣይ ስዕል፣ሰዓት
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን ገመድ እየዘለሉ እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የመሳሳብ እንቅስቃሴዎች ማሰራት።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 በቆምንበት ቦታ እግርና እጅን በሩጫ እንቅስቃሴ ላይ ማዋል።
 እጅ ከክንድ ታጥፎ ወደላይና ወደታች ይንቀሳቀሳል።
 እግር በሩጫ መልክ አንዱ እግር ከቦታው ላይ ይነሳል አንዱ እግር መሬት እንደያዘ ይቆያል በተራና በመካከለኛ
ፍጥነት ተግባሩ ይከናወናል።
26 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

 እንቅስቃሴውን ደጋግሞ መስራት


• በቦታ ላይ ሩጫን ሲሰሩ ትክክለኛ የእጅና የእግር ቅንጅትን እንዴት እንደሆነ ማሳየት።
• ከዝቅተኛ ፍጥነት በቦታ ላይ ሩጫ እንዲሰሩ ማድረግ።
• በመካከለኛ ፍጥነት በቦታ ላይ ሩጫ እንዲሰሩ ማድረግ።
• በቦታ ላይ ሩጫ በሚሰሩበት ሰአት የትኛው የሰውነት ክፍል ይበልጥ እንደሰራ መጠየቅ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• በቦታ ላይ ሩጫ በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የቃል ጥያቄ
5. እጅና እግርን መክፈትና መመለስ (ጃምፒንግ ጃክ)
የማስተማሪያ መሳሪያዎች፡-
• እጅና እግርን መክፈትና መመለስ /ጃምፒንግ ጃክ ሲሰራ የእግርና የእጅ ቅንጅትን የሚያሣይ ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• ሰውነታቸውን በቦታ ላይ የሶምሶማ ሩጫ፣በገመድ ዝላይ እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የመሳሳብ እንቅስቃሴዎች ማሰራት።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 እግርን ገጥሞ ቀጥ ብሎ በመቆም መጀመር
 ሁለት እግር ወደ ጎን ሲከፈት ሁለቱ እጃችን ደግሞ ወደ ጎንና ወደ ላይ ይዘረጋል።
 የእጅና የእግርን ቅንጅት በመጠበቅ መስራት
• እጅና እግርን መክፈትና መመለስ/ጃምፒንግ ጃክን በመቆም እንዲያከናውኑ ማድረግ።
• እጅና እግርን መክፈትና መመለስ/ጃምፒንግ ጃክን ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በማቀናጀት ማሰራት
• እጅና እግርን መክፈትና መመለስ /ጃምፒንግ ጃክን በመንቀሳቀስ እንዲያከናውኑ ማድረግ።
• እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ፡
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
• እንቅስቃሴው የተፈለገውን አጥጋቢ ውጤት እንዲያመጣ ተማሪዎች በሰፈራቸው እንዲለማመዱ መግለጽ።
ክትትልና ግምገማ፡-በምልከታ፣በቃል ጥያቄ
6. የመካከለኛ ርቀት ሩጫ
መርጃ መሳሪያዎች፦ፖስተሮች፣ስዕሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።

27 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

• የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈል።


• የመካከለኛ ርቀት ሩጫን በቡድን በቡድን ሜዳውን በመዞር እንዲሮጡ ማድረግ። የመጀመሪያ ዙር በፍጥነት
ርምጃ
ሁለተኛውን ዙር በሶምሶማ ርምጃ እንዲሮጡ ማድረግ።
• በመካከል እረፍት እየሰጡ 50 ሜትሩን በሶምሶማ 30 ሜትሩን በፍጥነት ርምጃ እንዲተገብሩ ማድረግ። በዚህ
ሁኔታ
ቀስ በቀስ 800 ሜትሩን መሸፈንና ፍጥነታቸውን በመቆጣጠር ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-እንቅስቃሴውን በተግባር ሲሰሩ በምልከታ ማረጋገጥ።
ማስታዎሻ፡- ከላይ ከተዘረዘሩት የልብና የአተነፋፈስ ስርአትን ከሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ ብስክሌት መጋለብ፣ ውሃ
ዋና፣ደረጃ መውጣትና መውረድ ወዘተ እንቅስቃሴን የእንቅስቃሴውን ጫና በመቀነስ ለረጅም ጊዜ በሰፈራችን/በቤታችን/ አዘውትረን
በመስራት የልብና የአተነፋፈስ ብርታት ደረጃችንን ማሻሻል እንደምንችል ማስገንዘብ ያስፈልጋል።
ተግባር 3.4 ከላይ የተጠቀሱትን እንቅስቃሴዎች በምንሰራበት ጊዜ ከፍተኛ ስሜት/የስራ ጫና
የሚሰማን በየትኞቹ የሰውነት ክፍሎች ነው
መልስ፡- የልብና የአተነፋፈስ ስርአት ብርታትን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ስንሰራ ከፈተኛ የስራ ጫና ወይም ድካም የሚሰማን
በመተንፈሻ አካላት/በሳንባችን/፣ በልባችንና በደም ስሮቻችን ይሆናል።

3.3 የጡንቻ ብርታት (6 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
• የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።
• የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።

የጡንቻ ብርታት የምንለው አንዱ የአካል ብቃት ዘርፍ ሲሆን የሰውነት ጡንቻ ለረጅም ጊዜ ያለ ድካም የመስራት ችሎታ ወይም
በአንድ በተወሰነ ፍጥነት ድካምን በመቋቋም የመስራት ችሎታ ነው።
በተጨማሪም የጡንቻ ብርታት ማለት ጡንቻዎች በመኮማተርና በመዘርጋት ያለ ድካም ለረጅም ጊዜ የመስራት ብቃት ማለት
ነው።ለረጅም ጊዜ የመስራት ችሎታ ማለት ከ 5 ደቂቃ እስከ 2 ሰዓት የሚወስድ ሊሆን ይችላል።እንቅስቃሴዎች ሲመረጡ መጠነኛ
የሆነ ክብደትን በመጠቀም ለረጅም ጊዜ ደጋግሞ መስራት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያዩ ስዕሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በአምሰተኛ ክፍል በተማሩት መሰረት የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩ እድል መስጠት።
• በአምስተኛ ክፍል በሰሯቸው እንቅስቃሴዎች አማካኝነት አካላዊ ለውጥ ማምጣታቸውን መጠየቅ።
• በቡድን በቡድን በመከፋፈል 5 ኛ ክፍል ከተማሯቸው በተጨማሪ ሌሎች የጡንቻ ብርታትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን
እንዲዘረዝሩ ማድረግ።
• የተወያዩበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ እድል መስጠት።

28 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

• ማጠቃለያ መስጠትና የእለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ።


የጡንቻ ብርታት የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች
ሀ. ከወገብ በላይ ያሉ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች
1. ፑሽ አፕ
ዝርዝር አላማ፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
• ከወገብ በላይ የሚገኙ ጡንቻዎችን ለማዳበር የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ይሰራሉ።
• ከወገብ በላይ የሚገኙ ጡንቻዎችን ለማዳበር የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ፑሽ አፕን ለመስራት ተነሳሽነትን ያሣያሉ።
• ከወገብ በላይ የሚገኙ ጡንቻወችን ለማዳበር የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ፑል አፕን ይሰራሉ።
• ከወገብ በላይ የሚገኙ ጡንቻወችን ለማዳበር የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በእጅ መሄድን እየተጋገዙ ይሰራሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራሩን ቅደም ተከተል መንገር
 ለወንዶች በእጅ መዳፍ መሬት በመመርኮዝ እግርን ዘርግቶ በደረት መተኛት፣ ክንድን እያጠፉ በመዘርጋት
ወለሉን ተጠግቶ መነሳት።
 ለሴቶች እግርን ገጥሞ በመንበርከክ በእጅ መዳፍ መሬት መደገፍ።
 ወደ ጀመሩበት ሁኔታ መመለስ በመካከሉ እረፍት በመውሰድ እየደጋገሙ መስራት።
• የክፍሉን ተማሪዎች በመሀላቸው በቂ ክፍተት በመስጠት በአራት ማሰለፍ።
• ከዚህ በፊት ከሚያውቁት ተነስተው ፑሽ አፕ እንዲሰሩ ማድረግ
• የተማሪዎችን ሙከራ በማድነቅ በትክክል የሰሩትን ልጆች በመምረጥ ደግመው እንዲያሳዩ ማድረግ
• ትክክለኛውን የፑሽ አፕ አሰራር የወንዶችንም የሴቶችንም የፑሻ አፕ አሰራር ማሳየት።
• በትክክለኛው አሰራር እንዲሰሩ ማድረግ፣ እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• ፑሽ አፕ ራሱን ችሎ የአንድ ክፍለ ጊዜ ትምህርት ስለማይሆን በመካከሉ በእረፍት፣ ሶምሶማ ሩጫና ጃንፒንግ ጃክ ማሰራት
ከጓደኞቻቸው ጋር በመደጋገፍ እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ፣ቸክ ሊስት፣ የዕርስ በርስ ግምገማ
2. በእጅ መሄድ
የማስተማሪያ መሳሪያዎች፡- ስዕል፣ፎቶግራፍ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።

29 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።


• የአሰራር ቅደም ተከተል ማብራራት
 ከቆሙበት ከወገብ በመታጠፍ በእጅ መዳፎች መሬት በመደገፍ ሁለቱን እግር ከኋላ ጓደኛ በመያዝ ወደ
ፊት መሄድ።
 ከቆሙበት ከወገብ በመታጠፍ በእጅ መዳፎች መሬት በመደገፍ እግርን ወደላይ በመዘርጋት በእጅ መሄድ።
• የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማድረግ መከፋፈል።
• በእጅ መሄድን ራሳቸውን ችለው ከመስራታቸው በፊት አንደኛው ተማሪ እጁን ተደግፎ በደረቱ ሲተኛ አንደኛው ተማሪ
ደግሞ ሁለቱን እግሩን ከኋላ በማንሳት በእጁ እንዲሄድ ማድረግ
• እንቅስቃሴውን እየተቀያየሩና እየተረዳዱ እንዲሰሩ ማድረግ።
• በመካከሉ የተለያዩ ቀላል እንቅስቃሴዎችን በማሰራት እረፍት እንዲያገኙ ማድረግ
• በእጅ መሄድን ሚዛናቸውን በመጠበቅ ራሳቸውን ችለው እንዲሰሩ ማበረታታት
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የዕርስ በርስ ግምገማ
3. በነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ወደ ላይ መሣብ/ፑል አኘ /
መርጃ መሳሪያዎች፦ነጠላ አግዳሚ ዘንግ፣ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁና የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተሉን ማብራራት
 ነጠላ አግዳሚ ዘንግን በሁለት እጅ በመያዝ መንጠልጠል፡
 ሰውነትን ቀጥ አድርጎ መዘርጋት
 ክንዳችን በማጠፍ ወደ ላይ መሳብ
 እንቅስቃሴውን እረፍት እየወሰዱ በድግግሞሽ መስራት የበለጠ ውጤት ለማምጣት ይረዳል።
• የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማድረግ መከፋፈል።
• ሁለት ለሁለት ፊት ለፊት በመሆን የእጅ መዳፋቸውን በማገጣጠም እንዲገፋፉ ማድረግ
• ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ እየተቀያየሩና እየተደጋገፉ እንዲሰሩ ማድረግ።
• በመጀመሪያ ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ እየጠንላጠሉ እንዲወርዱ ማድረግ፣በመቀተል ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ክንዳቸውን
በማጠፍ ወደላይ እንዲሳቡ ማድረግ
• እንቅስቃሴውን ከሌሎች እንቅስቃሴዎች ጋር በማቀናጀት እንዲሰሩ ማድረግ
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።

30 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።


ክትትልና ግምገማ
• እንቅስቃሴውን በተገቢው ሁኔታ መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ።
ተግባር 3.5 መልስ በነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ወደላይ መሳብ እንቅስቃሴን ስንሰራ ከፍተኛ የእንቅስቃሴ ጫና የሚኖረው በእጃችን ላይ፣
በደረታችን ላይና በትከሻ ላይ በሚገኝ ጡንቻዎቻችን ላይ ነው።
ማስታዎሻ፡- ከላይ ከተጠቀሱት እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ የተለያዩ ክብደቶችን በመስራት ከወገብ በላይ የሚገኙ ጡንቻዎችን ማዳበር
ይቻላል። ነገር ግን ህፃናት ክብደት ያላቸውን ነገሮች በሚያነሱበት ጊዜ አካላዊ ጉዳት እንዳይከሰት የክብደቱን መጠንና ድግግሞሹን
ከእድሜቸው አንጻር መመጠን ያስፈልጋል።
ለ. የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች
ዝርዝር አላማ
• የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ይለያሉ።
• የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
• የሆድና የጀርባ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ የተመረጡ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ ድግግሞሽ ይሰራሉ።
1. ሲት -አኘ
መርጃ መሳሪያዎች፦ የእንቅስቃሴውን አሰራር የሚያሳዩ ስእሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተል
 እግርን ዘርግቶ በጀርባ መተኛት።
 እግርን ዘርግቶ እጅን በደረት አመሰቃቅሎ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ማንሳት(እግር ከመሬት
ሳይነሳ)
 እጅን ጭንቅላት ላያ በማድረግ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ማንሳት።
 ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል በማንሳት እግርን በማጠፍ ጉልበትን ማቀፍ።
• የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን በቡድን መከፋፈል።
• በተለያ የአሰራር ዘዴዎች እንቅስቃሴውን እየተረዳዱና እየተራረሙ እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
• እንቅስቃሴውን በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፡
2. በደረት ተኝቶ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ማንሳት
መርጃ መሳሪያዎች፦ የአሰራር ቅደም ተከተሉን የሚያሳዩ ስዕሎች

31 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል


• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 እጅና እግርን በመዘርጋት በደረት መተኛት።
 ከወገብ በታች ያለው ሰውነት ክፍል ሳይነሳ እጆች ከራስ በላይ እንደተዘረጉ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል
ቀና አድርጎ ከወለሉ ማንሳትና ለ 10 ሴኮንድ ያህል ማቆየት።
 ወደ ጀመሩበት አቅጣጫ መመለስ በመካከሉ እረፍት እየወሰዱ በመደጋገም መስራት።
• የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማድረግ መከፋፈል።
• እንቅስቃሴውን እየተራረሙና እየተረዳዱ እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
• እንቅስቃሴውን በትክክል መስራታቸውን በምልከታ ማረጋጥ
3. በጀርባ ተኝቶ እግርን ወደላይ ማንሳት
መርጃ መሳሪያዎች፦ ፍራሽ፣ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 በጀርባ ተኝቶ ክንድን በሰውነት ትይዩ መዘርጋትና መዳፍን ወለሉ ላይ ማድረግ።
 እግርን ከወለሉ በዝግታ በማንሳት ከ 20- 30 ሴኮንድ በአየር ላይ ማቆየት።
 ወደ ጀመሩበት አቅጣጫ መመለስና በመካከሉ እረፍት እየወሰዱ በመደጋገም መስራት።
• የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በማድረግ መከፋፈል።
• እንቅስቃሴውን እየተራረሙና እየተረዳዱ እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
• እንቅስቃሴውን መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣የቃል ጥያቄ

32 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

ሐ. ከወገብ በታች የሚገኙ ጡንቻዎችን ለማዳበር የሚሰሩእንቅስቃሴዎች


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
• ከወገብ በታች የሚገኙ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ይለያሉ።
• ከወገብ በታች የሚገኙ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
• ከወገብ በታች የሚገኙ ጡንቻዎችን የሚያዳብሩ የተመረጡ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ ድግግሞሽ ይሰራሉ።
1. በቦታ ላይ ዝላይ
መርጃ መሳሪያዎች፦ የእንቅስቃሴውን አሰራር የሚያሳይ ስዕሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 ጉልበትን በማጠፍ በቦታ ላይ ወደላይ መዝለል
 እግርን በመዘርጋት መሬት ላይ ማረፍ
 በመካከሉ እረፍት እየወሰዱ እንቅስቃሴውን ደጋግሞ መስራት
• የክፍሉን ተማሪዎች በመካከላቸው በቂ ክፍተት በመስጠት እንዲሰለፉ ማድረግ።
• በመካከሉ እረፍት እየወሰዱ ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
• እንቅስቃሴውን መስራታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣ የቃል ጥያቄ
2. የጥንቸል ዝላይ(ሸብረክ ብሎ ወደፊት መዝልለ)
መርጃ መሳሪያ፡- የእንቅስቃሴውን አሰራር የሚያሳይ ስዕል
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 ሁለት እግርን በመግጠም ከጉልበት ሸብረክ ማለት
 እጅን ወደፊት በመዘርጋት ወደፊት መዝለል
 በየመሃሉ እረፍት በመውሰድ እንቅስቃሴውን ደጋግሞ መስራት
• የክፍሉን ተማሪዎች በመካከላቸው በቂ ክፍተት በመስጠት በረድፍ እንዲሰለፉ ማድረግ።

33 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

• የመጀመሪያ ረድፍ ላይ ያሉ ተማሪዎች ከ 10-15 ሜትር ድረስ የጥንቸል ዝላይን እንዲሰሩ ማድረግ።
• በየመካከሉ እረፍት እየወሰዱ ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ።
• እንቅስቃሴውን በቡድን በውድድር መልክ ማከናወን
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ
3. ግድግዳ(የጓደኛ ጀርባን) ተደግፎ መቀመጥ
መርጃ መሳሪያዎች፦የእንቅስቃሴውን አሰራር የሚያሳዩ ስዕሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 በአካል ብቃት ተመጣጣኝ የሆኑትን ተማሪዎች በአንድ ላይ በማድረግ በጥንድ በጥንድ ሆነው በጀርባቸው
ተደጋግፈው እንዲቆሙ ማድረግ
 በጀርባ እየተደጋገፉ ጉልበትን በማጠፍ ቀስ በማለት እንዲቀመጡ ማድረግ
 ከ 5-10 ሴኮንድ ከተቀመጡ በኋላ ቀስ ብለው እንዲነሱ ማድረግ
• የክፍሉን ተማሪዎች ጥንድ ጥንድ በመሆን በጀርባቸው ተደጋግፈው እንዲቆሙ ማድረግ።
• በመካከሉ እረፍት እየወሰዱ ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ
4. ሳጥን ላይ መውጣትና መውረድ / የሳጥኑ ከፍታ ከ 20-30 ሣ.ሜ/
መርጃ መሳሪያዎች፦የእንቅስቃሴውን አሰራር የሚያሳዩ ስዕሎች፣ትንንሽ ሳጥኖች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የማሳሳብ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ።
• የአሰራር ቅደም ተከተልን ማብራራት
 እግር በትከሻ ስፋት ልክ ከፍቶ ከሳጥኑ ጎን መቆም
 አንዱን እግር ሳጥኑ ላይ በማሰቀል ሁለተኛውን እግር ማስከተል

34 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

 በመዝለል በሁለት እግር ሳጥኑ ላይ ማረፍ


• የክፍሉን ተማሪዎች ባለን የሳጥን ቅጥር ልክ በመስመር ተሰልፈው እንዲቆሙ ማድረግ።
• ቀኝ እግራቸው ሳጥን ላይ በማሳረፍ ግራ እግርን ማስከተል ይህን እንቅስቃሴ አምስት ጊዜ ከሰሩ በኋላ ለተረኛ ተማሪ በመልቀቅ
ከኋላ መሰለፍ
• በሁለት እግራቸው ዝል በማለት ሳጥኑ ላይ ማረፍና መመለስ ይህንንም እንቅስቃሴ አምስት ጊዜ ከሰሩ በኋላ ለተረኛ ተማሪ
በመልቀቅ ከኋላ መሰለፍ
• በመካከሉ እረፍት እየወሰዱ ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ።
• እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ።
• የሰውነታቸውን ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• እንቅስቃሴውን በመስራታቸው የሚያገኙትን ጠቀሜታ በመጠየቅ ማጠቃለል።
• ይህን እንቅስቅሴ ስትሰሩ ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማቸውና በትኛውን የሰውነት ክፍል ላይ የተለየ ጫና እንዳለ የቃል
ጥያቄ መጠየቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ

3.4 መተጣጠፍ (2 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ፡-ተማሪዎች ከዚህ ትምህርት በኋላ፡-
• የመተጣጠፍ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይዘረዝራሉ።
• የተለያዩ የመተጣጠፍ ችሎታን የሚዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ተነሳሽነትን ያሣያሉ።
• የመተጣጠፍ ችሎታን የሚያዳብሩ የተመረጡ እንቅስቃሴዎችን በተሻለ ድግግሞሽ ይሰራሉ።
መተጣጠፍ ማለት የጤና ተኮር የአካል ብቃት ዘርፍ ሲሆን የአጥቆች/መገጣጠሚያዎች ያለ ህመም(በመጠነኛ) ስሜት ሰፊና በተፈጥሮአዊ
የእንቅስቃሴ አቅጣጫቸውን ሳይለቁ የሚደረግ የእንቅስቃሴ ዓይነት ነው። የመተጣጠፍ ችሎታን ለማዳበር በሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
ጊዜ በይበልጥ የሚሳተፉት የአካል ክፍሎች፡-
• የጡንቻ መገጣጠሚያ አጥንቶች
• የአጥንት መገጣጠሚያ ጅማቶች
• ጡንቻዎች
የመተጣጠፍ ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
1. በማጐንበስ ክንድን ወደ ላይ ቀጥ አድርጐ መዘርጋት
2. እግርን ዘርግቶ በመቀመጥ የእግር ጣት መንካት
3. የተለያዩ የማሳሳብ እንቅስቃሴዎች
• ወደግራና ወደ ቀኝ መጠማዘዝ
• እግርን ከፍቶ በመቆም ወደ ግራና ቀኝ እያዘነበሉ በአንድ እግር ላይ መቀመጥ
• የትከሻ ማሳሳብ

35 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

4. ወደ ተለያየ አቅጣጫ ማዘንበል


5. እራስን ወደተለያዩ አቅጣጫ ማዘንበል
•• ተግባር 3.6
1. ሰውነታችን ከመጠን በላይ ሲሣሣብ ምን እንደሚያስከትል ተወያዩ
•• ሰውነታችን ከመጠን በላይ በምናሳስብበት ጊዜ የተለያዩ አካላዊ ጉዳቶች ይከሰታሉ ለምሳሌ ከፍተኛ የህመም ስሜት፣ የጡንቻ
መለጠጥ፣ የጡንቻ መበጠስ፣ የጅማቶች መበጠስ ወዘተ
መርጃ መሳሪያዎች፦አሰራሩን የሚያሳዩ የተለያዩ ስእሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የተለያዩ የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• ክፍሉን ተማሪዎች በመካከላቸው በቂ ቦታ በመስጠት በረድፍ በማሰለፍ።
• ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ወደተለያዩ አቅጣጫ ማዘንበል።
• ጭንቅላትን ወደ ተለያዩ አቅጣጫ ማዘንበል።
• በማጎንበስ ክንድን ወደ ላይ ቀጥ አድርጎ መዘርጋት።
• እግርን ዘርግቶ በመቀመጥ እግርን ጣት በእጅ መያዝ።
• እንቅስቃሴውን ደጋግሞ ማሰራት
• በሚሰሩበት ጊዜ ክትትልና ድጋፍ መስጠት።
• የሰውነት ማቀዝቀዝና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የቃል ጥያቄ

3.5 ቅልጥፍና (3 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ፡- ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ተማሪዎች፡-
• የቅልጥፍና ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይዘረዝራሉ።
• የቅልጥፍና ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
• በመሰናክሎች መካከል በቅልጥፍና መሮጥን ይሰራሉ።
• የቅልጥፍና ችሎታን ለማዳበር የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎችን ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
የቅልጥፍና ችሎታ ማለት በእንቅስቃሴ ጊዜ ሰውነትን በፍጥነትና በትክክለኛ ሁኔታ በተወሰነ ክፍተት/ቦታ/ ውስጥ አቅጣጫን
የመቀየር ችሎታ ነው። በተጨማሪም አካላዊና አእምሮዊ ቅንጅትን የሚጠይቅ የአካል ብቃት ዘርፍ ነው።
የቅልጥፍና ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
• በመሰናክሎች መካከል መሮጥ
• የተለያዩ የአነሳስ ዘዴዎችን በመጠቀም የፍጥነት ሩጫ
መርጃ መሳሪያዎች፦መሰናክል፣ኮን፣ፍራሽ፣ፊሽካ፣ሰአት

36 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

መማር ማስተማር ቅደም ተከተል


• በቡድን በቡድን ሆነው ሰውነታቸውን እንዲያሟሙቁ ማድረግ።
• የተለያዩ የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት።
• ክፍሉን ተማሪዎች በመካከላቸው በቂ ቦታ በመስጠት በቁመት ማሰለፍ።
• ከኋላ ያለው ተማሪ ከፊት ለፊት ባሉት ተማሪዎች በዚግዛግ በመሽሎክ ማለፍ፣በየ አንድ ሜትር ርቀት ምልክቶችን በማስቀመጥ
በፍጥነት እሮጡ በዚግዛግ እንዲሾልኩ ማድረግ
• የተለያዩ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ማሰራት(ወደፊትና ወደኋላ መንከባለል።
 ወደ ፊት መንከባለል
 ወደ ኋላ መንከባለል
 መገለባበጥ ከተለያዩ እንቅስቃሴዎች ጋር በማጣመር ማሰራት
• በተለያዩ አቀማመጥ በመጀመር የፍጥነት ሩጫ ማስሮጥ።
 በደረት ወለል ላይ በመተኛት ትዕዛዝ ሲሰጥ 30 ሜትር ርቀትን በፍጥነት መሮጥ
 በጀርባ ወለል ላይ በመተኛት ትዕዛዝ ሲሰጥ 30 ሜትር ርቀትን በፍጥነት መሮጥ
 በእግር ተረከዝ ላይ ቁጢጥ በማለት ትዕዛዝ ሲሰጥ 30 ሜትር ርቀትን በፍጥነት መሮጥ
• እንቅስቃሴውን ደጋግሞ ማሰራት
• በሚሰሩበት ጊዜ ክትትልና ድጋፍ መስጠት።
• በሶምሶማ ሩጫና በርምጃ ሰውነታቸውን እንዲያቀዘቅዙ ማድረግና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን በማሰራት ማጠናቀቅ።
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ

3.6 የስፖርት አበረታች ቅመሞች /ዶፒንግ/ ጉዳት (2 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ፡ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
• የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ምንነት ይገልጻሉ።
• የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) በስፖርተኞች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ይዘረዝራሉ።
የስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ማለት ስፖርተኞች በተፈጥሮ ወይም በልምምድ ካገኙት የአካል ብቃት ውጪ ልዩ ልዩ
መድሃኒቶችን በመጠቀም ተጨማሪ ኃይል በማግኘት በውድድሮች እንዲያሸንፋ የሚያስችል ኃይል ሰጪ ንጥረ ነገር ነው። እንደ
ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ህግ አብዛኞቹ የተከለከሉት ንጥረ ነገሮች የአበረታች መድሃኒት አካል ናቸው።
ኮሚቴው እነዚህነ ንጥረ ነገሮች በስድስት የከፍላቸዋል፡-
1. አነቃቂ (stimulants)
2. አደንዛዥ እጽ (Narcotics)
3. የሰውነት ገንቢ ሰው ሰራሽ ንጥረ ነገር (Anabolic Agents)
4. የሰውነት ውስጥ ያለው ፈሳሽ የሚያስወግድ(Diuretics)
5. ተፈጥሮ ኪሚካሎችን በሰው ሰራሽ መንገድ የሚተኩ ንጥረ ነገሮች (Peptidase Hormones)

37 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23
ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

6. ማሪዋና (Marijuana)
እነዚህን አበረታች መድሀኒቶች ወስደው የተገኙ ስፖርተኞች የስፖርት ስነ ምግባርን ያልጠበቁ በመሆናቸው ተመጣጣኝ የሆነ የስነ
ምግባር እርምጃ ይወሰድባቸዋል።
አበረታች መድሃኒቶች ለስፖርተኞች ለጊዜያዊ ውጤት ማስገኛ ወይም የአካል ብቃት ማሻሻያ ቢጠቀሙበትም በጤና ላይ ከፍተኛ
ጉዳት ያስከትላሉ። የአበረታች መድሃኒት የልብ ህመም፣የደም ግፊት፣የመገጣጠሚያ ህመም፣ የጡንቻ መዛል፣የደም ካንሰር፣የክብደት
መቀነስ፣የራስ ምታት ወዘተ ከሚያስከትሏቸው ጉዳቶች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ስዕሎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
• በቡድን እንዲደራጁ በማድረግ የመወያያ ጥያቄዎችን መስጠት
 በ 5 ክፍል በተማሩት መሰረት የአበረታች መድሀኒት ምንነትንና
 በአካባቢያቸው የሚገኙ አበረታች/አነቃቂ/ መድሀኒቶች በጤና ላይ ያላቸውን ጉዳት ዘርዝሩ
• በሚወያዩበት ጊዜ እየተዟዟሩ መመልከትና እገዛ ማድረግ
• የተወያዩበትን ነጥቦች በተወካያቸው አማካኝነት እንዲያቀርቡ ማድረግ
• በቀረቡት ሀሳቦች ላይ የክፍሉ ተማሪዎች አስተያየት እንዲሰጡበት ማድረግ
• ተጨማሪ ነጥቦችን በመጨመር ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
• ምልከታ፣የቡድን ተሳትፎ፣የቃል ጥያቄ

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃዎች


መመሪያ አንድ፡-ለሚከተሉት ጥያቄዎች ተስማሚውን መልስ በመምረጥ መልሱ።
1. በቦታ ላይ በመካከለኛ ፍጥነት ረዘም ላለ ጊዜ የመሮጥ ልምምድ የሚያዳብረው የትኛው የአካል ብቃት ነው
•• ሀ. ፍጥነት ለ. ቅልጥፍና
•• ሐ. ጥንካሬ መ. የልብና አተነፋፈስ ብርታት
2. ከሚከተሉት ውስጥ ቅልጥፍና ችሎታን ለማዳበር የሚጠቅመው የእንቅስቃሴ አይነት የቱ ነው።
•• ሀ. ፑሽ አፕ ለ. በመሰናክል መካከል መሮጥ
•• ሐ. የገመድ ዝላይ መ. ሶምሶማ ሩጫ
3. ከሚከተሉት ውስጥ የሆድ ጡንቻን ለማዳበር የሚጠቅመው የእንቅስቃሴ አይነት የቱ ነው
•• ሀ. ፑል አፕ ለ. ቆሞ ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች ማዘንበል
•• ሐ. ሲት አፕ መ. ፑሽ አፕ
4. ፑል አፕ እንቅስቃሴን ለመሥራት የሚያስፈልገው መሣሪያ--
•• ሀ. አግዳሚ ወንበር ለ. አግዳሚ ዘንግ
•• ለ. ክብደት መ ኳስ
38 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ
ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

5. በደረት ተኝቶ ከወገብ በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል ወደ ላይ እያነሱ መመለስ የሚያዳብረው የትኛውን የጡንቻ ክፍል ነው
•• ሀ. የእግር ጡንቻዎች ለ. የክንድ ጡንቻን
•• ሐ. የሆድና የጀርባ ጡንቻዎች መ. መልሱ አልተሰጠም
6. ደረጃ የመውጣትና የመውረድ እንቅስቃሴ የሚያዳብረው የትኛውን የጡንቻ ክፍል ነው
•• ሀ. እግርን ለ. እጅን
•• ሐ. ከወገብ በላይ ያውን ክፍል መ. የትከሻ ጡንቻን
7. ወደ ተለያዩ አቅጣጫዎች እያዘነበሉ የመመለስ ልምምድ የሚያሻሽለው
•• ሀ. ፍጥነትን ለ . ጥንካሬን ሐ. ቅልጥፍናን መ. መተጣጠፍን
መመሪያሁለት አጭር መልስ ስጥ/ጭ
1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጤና ጋር ያለዉን ግንኙነት ከጓደኞቻችሁ ጋር በመሆን ለመምህራችሁ አቅርቡ?
2. የልብና የመተንፈሻ አካላቱ የዳበረ ሰው ምን ምን ተግባራትን ማከናወን ይችላል?
3. የደም ዝውውር እና አተነፋፈስ ብርታት እድገት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ/ የሚያሳርፉ/ ነገሮች
በመለየት አብራሩ
4. በመተጣጠፍ ችሎታ ሴቶች ከወንዶች የተሻሉ ናቸው ለምን? በቡድን ተወያይታችሁ ለክፍሉ ተማሪውች አቅርቡ
5. የአበረታች መድሀኒት በስፖርተኞች ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ ዘርዝሩ

39 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጤናና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ(23
ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 3

መልስ

1.መ 2.ለ 3.ሐ


4.ሐ 5.ለ 6.ሀ 7.

1. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ከጤና ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አለው። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዋነኛ ጠቀሜታ የተሟላ
ጤንነት ለመጠበቅ፣ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ለመከላከል፣ በሽታዎችን በቀላሉ ለመቋቋም፣ ቋሚ የሆነ ጤና ይዞ
ለመቆየት ወዘተ
2. የልብና የአተነፋፈስ ስርዓቱ የዳበረ ሰው የእለት ተዕለት እንቅስቃሴውን ያለድካም ማከናወን ይችላል፣ የተለያዩ አየራዊ/
ኤሮቢክስ እንቅስቃሴዎችን ማከናወን ይችላል
•• 3.የደም ዝውውር እና አተነፋፈስ ብርታት እድገት ላይ ተጽእኖ የሚያሳድሩ/ የሚያሳርፉ/
ነገሮች በመለየት አብራሩ
• ሲጋራ ማጤን /smoking/
• የአካል እንቅስቃሴ ያለማድረግ / መቀነስ /
• የተመጣጠነ ምግብ ያለማግኘት /Diet/
• ጫት መጠቀም /Drug use/
• ከመጠን ያለፈ ውፍረት /Obesity/
• የሀሳብ ጫና / Stress /
• የእንቅልፍ ማጣት / sleeplessness
4. በመተጣጠፍ ችሎታ ሴቶች ከወንዶች የተሻሉ ናቸው ለምን? በቡድን ተወያይታችሁ ለክፍሉ ተማሪውች አቅርቡ
•• የመተጣጠፍ ችሎታ ስንመለከት ሴቶች ከወንዶች የተሻሉ እንደሆኑ የተለያዩ ምሁራን ያምናሉ። ይህ የሆነበት
ምክንያትም ሴቶች በመገጣጠሚያ አካላታቸው ዙሪያ የሚገኙ ለስላሣ ጅማቶች ስላላቸው እና ከወሊድ ሂደት ጋር
በተያያዘ የመጨረሻ አከርካሪ አጥንት /Vertabral bone/ ተንቀሣቃሽ ስለሆነና የሰውነታቸው ጡንቻዎች በተፈጥሮ
የመሣሣብ ባህሪ ስላላቸው ነው።
5. የአበረታች መድሃኒት የልብ ህመም፣ የደም ግፊት፣ የመገጣጠሚያ ህመም፣ የጡንቻ መዛል፣ የደም ካንሰር፣ የክብደት
መቀነስ፣ የራስ ምታት ወዘተ ከሚያስከትሏቸው ጉዳቶች ውስጥ የተወሰኑት ናቸው።

40 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

ምዕራፍ

4 አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ የአጭርና የመካከለኛ ርቀት ሩጫን በተግባር ይሰራሉ።
ƒƒ ውርወራ በሚያከናውኑበት ጊዜ የእጅና የላይኛው የሰውነት ክፍል እንቅስቃሴን ያሳያሉ።
ƒƒ በርዝመት ዝላይና በስሉስ ዝላይ መካከል ያለውን ልዩነት ይለያሉ።
ƒƒ ትክክለኛውን የአሰራር ስልቶችን ተጠቅመው የስሉስ ዝላይ ይሰራሉ።
ƒƒ ለርቀት ውርወራ በሚወረውሩ ጊዜ ያለውን ተግዳሮት ይለያሉ።
ƒƒ በቡድን የክህሎት ልምምድ በሚያከናውኑበት ጊዜ ከጓደኞቻቸው ጋር ይተባበራሉ።

መግቢያ
አትሌትክስ ተፈጥሯዊ የሆኑ ጥቅም ያላቸውን እንቅስቃሴዎች የያዘ የትምህርት ዘርፍ ነው። አትሌቲክሳዊ እንቅስቃሴዎች የሚባሉት
ሩጫ፣ ውርወራና ዝላይ ናቸው። እነዚህ አትሌቲክሳዊ እንቅስቃሴዎች ተፍጥሯዊ ፀባይ ያላቸው በመሆናቸው የተሳታፊዎችን አካላዊ
አሰራር ችሎታ ለመጨመር ፣ጤንነትን ለመገንባትና ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን የእንቅስቃሴ ችሎታና እውቀትን፣ አካላዊና ስነልቦናዊ
ብቃቶችን ለማዳበር ይረዳሉ።
ይህ ምዕራፍ በሥርዓተ ትምህርቱ በተመረጠው መሰረት የሩጫ ውርወራና ዝላይ ተግባራትን የሚያስተዋውቅና የሚያጠናክር ሲሆን
ርምጃ ምንም ጊዜም ቢሆን ከነዚህ ተግባራት ጋር በተለያየ መልኩ በሥራ ላይ የሚውል እንቅስቃሴ ነው። በዚህ ምዕራፍ አማካኝነት
ተማሪዎች የፍጥነትና የርቀት ሩጫ፣ የውርወራና የስሉስ ዝላይ የሚያጠናክሩበትና የሚተዋወቁበት ይሆናል።

41 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

4.1 ሩጫ (6 ክ/ጊዜ)

4.1.1 ለፍጥነት መሮጥ


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª የፍጥነት ሩጫ ችሎታን ለማዳበር የሚያገለግሉ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
ªª ጉልበትን ወደ ላይ በማጠፍ በቦታ ላይና ከ 20-30 ሜ የፍጥነት ሩጫ ይሮጣሉ።
ªª የፍጥነት ሩጫ ጥቅምን ይዘረዝራሉ።
ªª የአጭር ርቀት ሩጫ አነሳስ ዘዴን በመጠቀም ከ 30-50 ሜ ይሮጣሉ።

መርጃ መሳሪያዎች፣የሩጫ ሰዓት ፣የሩጫ ተግባራትን የሚያሳዩ ሥዕሎች ፎቶ ግራፎች


የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ትምህርቱ ስድስት ክ/ጊዜ ስላለው አንዱን ክ/ጊዜ በክፍል ውስጥ በጽንሰ ሀሳብ ማቅረብ፡-የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ
የእንቅስቃሴ አይነቶችን 5 ኛ ክፍል በተማሩት መሰረት እንዲዘረዝሩ ማድረግ
 በ 5 ኛ ክፍል የተማሯቸውን የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር የሚጠቅሙ የእንቅስቃሴ አይነቶች በቃል ጥያቄ እንዲያስታውሱ
ማድረግ።
 የሩጫ አይነቶችን፣ አጭር ርቀት የሩጫ አይነቶችን፣ አጭር ርቀት ሩጫ አነሳስና ትዕዛዞችን በመዘርዘር ማብራሪያ መስጠት።
 ቀሪውን ክፍለ ጊዜ ሜዳ ላይ በተግባር በሚከተለው መልኩ ማስተማር
 የክፍሉን ተማሪዎች ከአራት እስከ አምስት ቡድን መክፈል።
 ከ 3-5 ደቂቃ በሶምሶማና በሩጫ የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴና የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት፣
 ጉልበትን ወደ ላይ በማንሳት የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
 በቦታ ላይ እንዲሮጡ ማድረግ
 ከ 20-30 ሜትር እንዲሮጡ ማድረግ
 ጉልበትን በማጠፍ በእግር መቀመጫን በመምታት የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
 በመቆም ጉልበትን በማጠፍ በእግር መቀመጫን በመምታት መስራት።
 ከ 20-30 ሜትር በመንቀሳቀስ ጉልበትን በማጠፍ በእግር መቀመጫን በመምታት ማሰራት።
 የአጭር ርቀት ሩጫ የአነሳስ ዘዴዎችንና ትዕዛዞችን በመጠቀም የፍጥነት ሩጫ
 30 ሜትር ሩጫ
 50 ሜትር ሩጫ
 እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግና ደጋግሞ መስራት የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር ያለውን አስተዋጽዖ ማስገንዘብ፣
 እንቅስቃሴውን በውድድር መልክ ማዘጋጀ
 በሁለት እኩል ቡድን በመክፈል በ 100 ሜትር ርቀት ፊት ለፊት እንዲቆሙ ማድረግ
 የአጭር ርቀት አነሳስን በመጠቀም ዱላ/ቀለበት እንዲቀባበሉ ማድረግ።

42 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16
ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

 ሁሉም ተማሪዎች እስኪዳረስ ውድድሩን ማካሄድ።


 ቀድሞ የጨረሰ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
 በየዕለቱ ትምህርት መጨረሻ የሰውነት ማብረድና የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት

ማሳሰቢያ
አካላዊ ጉዳት ያለባቸውን ተማሪዎች ርቀቱን በመቀነስ እንዲሳተፉ ማድረግ፣ማየት የተሳናቸው ተማሪዎች በሌሎች ተማሪዎች
እገዛ እንዲሳተፉ ማድረግ።

ክትትልና ግምገማ፡-የቃል ጥያቄ፣ምልከታ፣

ተግባር 4.1. መልስ የአጭር ርቀት ሩጫ ውድድሮች የሚባሉት ከ 100-400 ሜትር ርቀት ድርስ ያሉት ናቸው።
ተግባረው 4.2
1. የፍጥነት ችሎታን ለማዳበር ከሰሩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ከተለያዩ የአነሳስ ዘዴዎች በመጠቀም በፍጥነት መሮጥ፣ከ 20-30 ሜ በፍጥነት
መሮጥ፣የአጭር ርቀት ሩጫ አነሳስን በመጠቀም 100 ሜ በፍጥነት መሮጥ ወዘተ ናቸው።
2. የአጭር ርቀት ሩጫ አነሳስ ዘዴን ሶስቱን ትዕዛዞች ማለትም በቦታህ/ሽ፣ተዘጋጅ/ጂ፣ሂድ/ጂ በተግባር እነዲያሳዩ ማድረግ።

4.1.2 ለርቀት መሮጥ

ዝርዝር አላማ ተማሪዎችይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-


 የረጅም ርቀት ሩጫ አይነቶችን ይዘረዝራሉ
 ለርቀት ሩጫ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ይሰራሉ።
 የርቀት የመሮጥ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎች ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
የረጅም ርቀት ሩጫን እንደ ፍጥነት ሩጫ በአንድ ትንፋሽና በሙሉ ፍጥነት የሚከናወን ሳይሆን ኦክስጅንን በመጠቀም ለረጅም
ጊዜ(ሰዓት) መስራትን የሚጠይቅ ነው። የመካከለኛ ርቀት ሩጫን ለማከናወን ፍጥነትም ብርታትም በእኩል ደረጃ ያስፈልጋሉ። ለረጅም
ርቀት ሩጫዎች ደግሞ ዝቅተኛ ፍጥነትና ከፍተኛ ብርታት ያስፈልጋል።
የርቀት ሩጫ በሚከናወንበት ጊዜ ዘና የማለትና እንቅስቃሴን ቆጥቦ የመሮጥ እንዲሁም የአተነፋፈስ ስርዓት ተመሣሣይነት መኖር
አስፈላጊ ነው። አተነፋፈስን ከሩጫ ፍጥነት ጋር ማስማማት ያስፈልጋል። የመካከለኛ ፍጥነት ሩጫ ብቃትን ለማዳበር በየመካከሉ

ዕረፍት እየወሰዱ ልምምድ ማካሄድ አስፈላጊ ነው።


መርጃ መሳሪያዎች፦የሩጫ ሰዓት፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ከ 3-5 ደቂቃ የሰውነት ማሟሟቂያና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት
 በመካከለኛ ፍጥነት ሶምሶማ ሩጫ መሰረታዊ የሆኑትን የእግርና እጅ እንቅስቃሴዎችን ትክክለኛ አሰራር በተግባር ማሣየት።
 በመካከለኛ ፍጥነት ሩጫ በ 500 ሜ በመከፋፈል 2000 ሜ እንዲሮጡ ማበረታታት።
 በቂ ጊዜ ሰጥቶ ትክክለኛውን አሰራር ተከትለው በተግባር እንዲለማመዱ ማድረግ።

43 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

 ከዚያም በገለጻ በሥዕሎች በመታገዝና የተሻለ የሚሰሩ ተማሪዎችን በመጠቀም የአሰራሩን ቅደም ተከተልና ትክክለኛውን
የአሰራር ሁኔታ እንዲለዩ ማድረግ።
 ትክክለኛውን አሰራር ተከትለው ደጋግመው እንዲለማመዱ ማድረግ።
 በእንቅስቃሴው መካከል ጥያቄ ማቅረብ ይኸውም በረጅም ርቀት ሩጫ ጊዜ የእግር አነሳስ የእጅ ውዝዋዜ ከወገብ በላይ ያለው
የሰውነት ክፍል እንዴት መሆን እንዳለበት መጠየቅ።
 የረጅም ርቀት ሩጫዎች የትኛውን የአካል ብቃት ዘርፍ እንደሚያዳብሩ መጠየቅና የአሯሯጥ ቴክኒኩን ከፍጥነት ሩጫ በምን
እንደሚለይ እንዲያስረዱ ማበረታታት።
 ሰውነታቸውን እንዲያበርዱና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ፣የቃልጥያቄ

4.2 ውርወራ (6 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎችይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
 ውርወራ ችሎታን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን ይሰራሉ።
 በመዞር ትንንሽ ቀለበትን ለርቀት ይወረውራሉ።
 ክብደት ያላቸውን ትንንሽ ኳሶች ይወረውራሉ።
 በፍጥነት በመንደርደር ርጅም ዘንግ ለርቀት ይወረውራሉ።
 ከጓደኞቻቸው ጋር በመተጋገዝ የውርወራ ተግባራትን ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
በጥንት ጊዜ የሰው ልጅ የዕለት ተዕለት ፍላጐቱን ለማሟላት ሲል ውርወራን እንደ አንድ አይነተኛ መሳሪያ ይጠቀምበት ነበር። ይህ
የጥንት ሂደት ለዛሬው ዘመናዊ ውርወራ መሠረት ሆኗል::
ውርወራን ከቦታ ማከናወን ይቻላል። ሆኖም ርቀትን ለመጨመር ከተፈለገ እንደ ቦታው ሁኔታ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማከል
መወርወር ውጤታማ ያደርጋል። ይሁንና መሮጥ ወይም መንሸራተት ወይም መሽከርከር ከተጨመረበት ውስብስብ ያደርገዋል።
ስለሆነም በመንሸራተት የሚከናወን ውርወራ በቦታ መወርወር ችሎታ በሚገባ ከደረጀ በኋላ መከናወን አለበት።
በዚህ ደረጃ ላሉ ተማሪዎች መደበኛ ዲስከስን ወይም አሎሎን ማስወርወር አይፈቅድም። በአቅማቸው ተስማሚ የሆኑ መጠነኛ ክብደት
ያላቸው ቀለበቶች፣ ኳሶችን በመጠቀም ማስተማር ውጤታማና አስደሳች ይሆናል።
ሀ. በመዞር ትንንሽ ቀለበቶችን ለርቀት መወርወር
መርጃ መሳሪያዎች፦ትንንሽ ቀለበቶች፣ጠፍጣፋ ጣውላ፣ጠንካራ ካርቶን
የመማር ማሰተማር ቅደም ተከተል
 በቡድን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
 በ 5 ኛ ክፍል የተማሩትን ለርቀት የመወርወር ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ
መከለስ
 የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ብዛታቸው በአራት ወይም በአምስት ቡድን መክፈል፣
 የተለያዩ የውርወራ መለማመጃ መሳሪያዎችን ማቅረብና ትንንሽ ቀለበት እንዴት መወርወር እንደሚቻል በሙከራ እንዲያሣዩ
ማድረግ።

44 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

 የውርወራ እንቅስቃሴዎች ቀደም ሲል ከተማሩትና ከራሳቸው ልምድ ተነስተው ትንንሽ ቀለበቶች፣ጠፍጣፋ ጣውላ
በመወርወር እንዲለማመዱ ጊዜ መስጠት።
 የተማሪዎችን ሙከራ በማድነቅና በማበረታታት የእያንዳንዱን ውርወራ አሰራር፣ አያያዝ፣ መግለጽና በተግባር ሰርቶ ማሣየት።
 የሚወረወረውን ትንንሽ ቀለበት ወይም ጠፍጣፋ ጣውላ ጣትን ዘርዘር በማድረግ በጣታችን ጫፍ መያዝ
 ወደ ሚወረውሩበት አቅጣጫ በመቆም ትንንሽ ቀለበቶችን ፊት ለፊት እንዲወረውሩ ማድረግን ደጋግመው እንዲለማመዱ
ማድረግ
 ወደ ጎን ፊትን ዞሮ በመቆም እጅን በማወዛወዝ ወደ ጎን መወርወር
 ዕርስ በርስ አስተያየት እየተሰጣጡ እንዲወረውሩ ማድረግ፣
 ውርወራውን እየደጋገሙ እንዲሰሩ እድል መስጠት፣
 የውርወራ ተግባራት የትኛውን የአካል ብቃት ዘርፍ እንደሚያዳብሩ መጠየቅ፣
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ
ለ. ክብደት ያላቸውን ትንንሽ ኳሶችን ወደ ጎን መወርወር
መርጃ መሳሪያዎች፦ክብደት ያላቸው ትንንሽ ኳሶች
የመማርማሰተማር ቅደም ተከተል
 በቡድን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
 በ 5 ኛ ክፍል የተማሩትን ለርቀት የመወርወር ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ
መከለስና ትንንሽ ቀለበቶችን ለርቀት ለመወርወር ምን ማድረግ እንዳለብን ጥያቄዎችን በመጠየቅ መከለስ
 የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ብዛታቸው በአራት ወይም በአምስት ቡድን መክፈል፣
 የተለያዩ የውርወራ መለማመጃ መሳሪያዎችን ማቅረብና ትንንሽ ቀለበት እንዴት መወርወር እንደሚቻል በሙከራ እንዲያሣዩ
ማድረግ።
 የውርወራ እንቅስቃሴዎች ቀደም ሲል ከተማሩትና ከራሳቸው ልምድ ተነስተው ትንንሽ ኳሶችን ለርቀት እንዲወረውሩ ጊዜ
መስጠት።
 የተማሪዎችን ሙከራ በማድነቅና በማበረታታት የእያንዳንዱን ውርወራ አሰራር፣አያያዝ፣ መግለጽና በተግባር ሰርቶ ማሣየት።
 የሚወረወረውን ትንንሽ ኳሶች ጣትን ዘርዘር በማድረግ በእጃችን መሀል በመያዝ ወደ ጀሮ ማስጠጋት
 ውርወራው የሚከናወነው በመግፋት መሆኑን መግለፅ
 ወደ ሚወረውሩበት አቅጣጫ በመቆም ትንንሽ ኳሶችን ፊት ለፊት በመግፋት እንዲወረውሩ ማድረግን ደጋግመው
እንዲለማመዱ ማድረግ
 እግርን በትከሻ ስፋት ልክ ከፍቶ ጀርባችን ወደ ምንወረውርበት አቅጣጫ በማዞር መቆም፣ አንድ እግርን ወደ ጎን በመንሸራተት
ለርቀት መወርወር
 እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲወረውሩ ማድረግ፣
 ውርወራውን እየደጋገሙ እንዲሰሩ እድል መስጠት፣

45 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

 የውርወራ ተግባራት የትኛውን የአካል ብቃት ዘርፍ እንደሚያዳብሩ መጠየቅ፣


 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልናግምገማ፡-ምልከታ
•• ሐ. በፍጥነት በመንደርደር ረጅም ዘንግ መወርወር
መርጃ መሳሪያዎች፦ረጃጅም ዘንግ፣ዱላ፣ሸንበቆ
የመማርማሰተማር ቅደም ተከተል
 በቡድን የሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
 ለርቀት የመወርወር ችሎታን ለማዳበር የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን እንዲዘረዝሩ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ መከለስና ትንንሽ ኳሶች
ለርቀት ለመወርወር ምን ማድረግ እንዳለብን ጥያቄዎችን በመጠየቅ መከለስ
 የክፍሉን ተማሪዎች እንደ ብዛታቸው በአራት ወይም በአምስት ቡድን መክፈል፣
 የተለያዩ የውርወራ መለማመጃ መሳሪያዎችን ማቅረብና ዘንግ እንዴት መወርወር እንደሚቻል በሙከራ እንዲያሣዩ ማድረግ።
 የውርወራ እንቅስቃሴዎች ቀደም ሲል በ 5 ኛ ክፍል ከተማሩትና ከራሳቸው ልምድ ተነስተው ዘንግ ለርቀት እንዲወረውሩ ጊዜ
መስጠት።
 የተማሪዎችን ሙከራ በማድነቅና በማበረታታት የዘንግ ውርወራ አሰራር፣አያያዝ፣ መግለጽና በተግባር ሰርቶ ማሣየት።
 የሚወረወረውን ዘንጎች በአውራ ጣትና በአራቱ ጣቶች መካከል ጨብጦ በመያዝ ወደ ጀሮ ማስጠጋት
 ውርወራው የሚከናወነው እጃችንን ወደኋላ በመዘርጋትና ወደፊት በማወናጨፍ መሆኑን መግለፅ
 ወደ ሚወረውሩበት አቅጣጫ በመቆም ከራስ በላይ ትንንሽ ኳሶችን እጅን በማወናጨፍ እንዲወረውሩ ማድረግን ደጋግመው
እንዲለማመዱ ማድረግ
 ዘንግን በጀሮ ትክክል በመያዝ ከዚህ በፊት በ 5 ኛ ክፍል በተማሩት መሰረት በመቆም እንዲወረውሩ ማድረግ
 ይህንኑ ውርወራ ከሁለትና ከሶስት ርምጃ በኋላ እንዲወረውሩ ማድረግ
 ከ 10-15 ሜትር በመንደርደር እጃቸውን ወደኋላ በማወናጨፍ ለርቀት እንዲወረውሩ ማድረግ
 እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲወረውሩ ማድረግ፣
 ውርወራውን እየደጋገሙ እንዲሰሩ እድል መስጠት፣
 የውርወራ ተግባራት የትኛውን የአካል ብቃት ዘርፍ እንደሚያዳብሩ መጠየቅ፣
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-ምልከታ
ማስታዎሻ፡- በሁሉም የውርወራ አይነቶች ተማሪዎችን ስናሰልፍ ትይዩ ሆነው መቆም የለባቸውም፣ውርወራውን እየተያዩና እየተጠባበቁ
በተራ እንዲሰሩ ማድረግ፣የአካል ጉዳተኞች በመምህሩ ቀጥተኛ ድጋፍና ክትትል መስራት ይችላሉ።
የተግባር 4.5. መልስ የውርወራ አይነቶች አራት ሲሆኑ እነሱም የጦር ውርወራ፣ የዲስከስ ውርወራ፣ የአለሎ ውርወራና መዶሻ
ውርወራ ናቸው።

4.3 ዝላይ (4 ክ/ጊዜ)

46 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

•• ሀ. የስሉስ(የእምርታ) ዝላይ
ዝርዝር አላማ ተማሪዎችይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
 የስሉስ ዝላይ ቅደም ተከተሎችን ይዘረዝራሉ።
 የስሉስ ዝላይ ወቅት ትክክለኛውን የእጅና የእግር አቀማመጥ ይገልጻሉ።
 ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጋገዙ የስሉስ ዝላይን ይዘላሉ።
ዝላይ ተፈጥሯዊ ከሆኑት ጥቅም ያላቸው እንቅስቃሴዎች ውስጥ አንዱ ነው። ዝላይ የሜዳ ተግባር ሲሆን በእያንዳንዱ የዝላይ ዓይነቶች
የመዝለያ ክልልና ህጐች ይኖሩታል ለዝላይ ወሳኝ የሆኑ ነገሮች። እድሜ፣ ቁመት፣ ፍጥነት፣ የጡንቻ ጥንካሬና መታዘዝ፣ የሩጫ ፍጥነት
አንድ ዓይነት እንቅስቃሴ፣ መስፈንጠር፣ መንሳፈፍና አስተራረፍ ችሎታዎች ናቸው።
የስሉስ(የእምርታ) ዝላይ የርዝመት ዝላይ ዓይነት ሲሆን ከርዝመት ዝላይ የሚለየው በአንድ የዝላይ ወቅት ሶስት የዝላይ ክንዉኖች
የሚካሄዱበት በመሆኑ ነዉ። እነሱም ሆፕ፣ ስቴፕ( እምርታ)፣ዝላይን የያዘ ነው።እንቅስቃሴው ሦስት ተከታታይ ዝላዮችን የያዘ ሲሆን
የመጀመሪያው ዝላይ ሆፕ የምንለው በአንድ እግር ተነስቶ በተነሱበት እግር ማረፍ ሲሆን ሁለተኛው ስቴፕ(እምርታ) ደግሞ በተቃራኒ
እግር በመስፈንጠር ማረፍ ነው ዝላይ የምንለው የመጨረሻው ተግባር ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ በሁለቱም እግሮች አንድ ላይ ማረፍን
ያጠቃልላል ።
መርጃ መሳሪያ፡- ገመድ፣ኮን፣
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ከ 3-5 ደቂቃ ሰውነት ማሟሟቂያ እንቅስቃሴና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
 ያለፈውን ትምህርት የተግባር ስራውን በመስራት መከለስ
 ተማሪዎችን በአራት ቡድን በመክፈል የራሳቸውን የአዘላለል ዘዴ ተጠቅመው በአንድ እግራቸው እንዲዘሉ ማድረግ
 የተማሪዎችን የአዘላለሉን ስልት አስተውሎ መመልከትና የተለያዩ የአዘላለል ዘዴዎችን የተጠቀሙትን በመምረጥ ልዩነታቸውን
እንዲለዩ ጥያቄዎችን ማቅረብ
 ከመቆም/በቦታላይ አንድ እግርን በማጠፍ በአንደኛው እግር ዘሎ በዘለሉበት እግር እንዲያርፉ ማድረግ
 ከ 10-15 ሜትር በመንደርደር በአንድ እግር ዘሎ በዘለሉበት እግር እንዲያርፉ ማድረግ
 ከመቆም/በቦታ ላይ አንድ እግርን በማጠፍ በአንደኛው እግር ዘሎ በዘለሉበት እግር እንዲያርፉ ማድረግና ቀጣዩን ዝላይ
በተቃራኒ እግር እንዲያርፉ ማድረግ
 ከ 10-15 ሜትር በመንደርደር ሆፕ፣ስቴፕና መዝለልና በተከታታይ እንዲዘሉ ማድረግ
 ትክክለኛውን የአዘላለል ዘዴ በተግባር ሰርቶ ማሳየት
 ዝላዩን ደጋግሞ መስራት የተሻለ ለመዝለል እንደሚረዳ ማስገንዘብ
 የዕለቱ ትምህርት ጠቀሜት እንዲናገሩ የቃል ጥያቄ መጠየቅ
 ይህ የዝላይ ተግባር በቀጣይ ትምህርት ደረጃዎች ለሚማሯቸው የዝላይ ትምህርቶች እገዛ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎች እንደሆኑ
ማስገንዘብ፣
 በሶምሶማ ሩጫና በርምጃና የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴዎችን በማሰራት የእለቱን ትምህርት ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ፣የቃል ጥያቄ

47 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

ልዩ ትኩረት
• በአስተራረፍ ጊዜ ሁለት እግር አንድ ላይ ማረፍ አለበት።
• ዘለው በሚያርፉበት ጊዜ አካላዊ ጉዳት እንዳይከሰት አሽዋ ወይም ለስላሳ አፈር ላይ እንዲያርፉ ማድረግ
• የሰውነት ሚዛን ወደፊት ማዘንበል አለበት።
• እጅ ወደፊትና ወደ መሬት ማመልከት አለበት።
• ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች ተጨማሪ እገዛ ማድረግና የእንቅስቃሴውን ጫና በመቀነስ ማሰራት።

48 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


አትሌቲክስ(16 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 4

የምዕራፉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች

መመሪያ አንድ፡-የሚከተሉትን ጥያቄዎች ትክክል ከሆነ “እውነት ስህተት ከሆነ ደግሞ “ሀሰት በማለት መልሱ
1. የስሉስ ዝላይ ጊዜ ስቴፕ(እምርታ) የምንለው በአንድ እግራችን ተነስተን በሁለት እግራችን የምናርፈውን ሂደት ነው።
2. መካከለኛ ርቀት ሩጫ የሚባሉት ርቀታቸውን በአንድ ትንፋሽና በሙሉ ፍጥነት የመጨረስ ክህሎትን የሚጠይቁት ናቸው።
3. ርምጃ ማለት ከሩጫ ፈጠን ያለ እንቅስቃሴ ነው።
4. የአጭር ርቀት ሩጫ ትዕዛዞች በሦስት ክፍሎች ይመደባሉ።
መመሪያ ሁለት ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ
5. የርዝመት ዝላይ ከስሉስ ዝላይ ጋር ያለውን አንድነትና ልዩነት አብራሩ
6. በዝላይ ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ ምክንያቶችን ዘርዝሩ
7. የውርወራ አይነቶችን ዘርዝሩ

መልስ
1. ሀሰት 2. ሀሰት 3. ሀሰት 4. እውነት
5. አንድነታቸው ሁለቱም የዝላይ አይነቶች ለርዝመት የሚዘለሉ ሲሆን በተጨማሪም ሁሎቱም የዝላይ ዓይነቶች
ፍጥነት፣ጥንካሬ፣መተጣጠፍ ችሎታን የሚጠይቁ ናቸው። ልዩነታቸው ፤-ርዝመት ዝላይ አንድ ወጥ አግድም ዝላይ
ሲሆን የሱሉስ ዝላይ ደግሞ ሶስት ዝላዮችን በተከታታይ መዝለልልን ይጠይቃል።
6. እድሜ፣ ቁመት፣ ፍጥነት፣ የጡንቻ ጥንካሬና መታዘዝ፣ የሩጫ ፍጥነት አንድ ዓይነት እንቅስቃሴ፣ መስፈንጠር፣መንሳፈፍና
አስተራረፍ ችሎታዎች
7. የውርወራ አይነቶች የሚባሉት የጦር ውርወራ፣የአለሎ ውርወራ፣የዲስከስ ውርወራና የመዶሻ ውርወራ ናቸው።

49 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-
16)
ምዕራፍ 5

ምዕራፍ

5 ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ የጅምናስቲክስ አይነቶችን ይረዳሉ።
ƒƒ በነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ወደ ላይ የመሳብን እንቅስቃሴ ያሳያሉ።
ƒƒ ቀላል የመሳሪያ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን ያከናውናሉ።
ƒƒ የመሳሪያ ጅምናስቲክስ የአሰራር ሂደቶችን ያደንቃሉ።
ƒƒ የጂምናስቲክስ እንቅስቀሴ ጥቅሞችን ዋጋ ይሰጣሉ።

መግቢያ፡-
ጅምናስቲክስ 5 ኛ ክፍል ላይ ለክፍሉ በሚመጥን መልኩ መስራታችሁ ይታወቃል በመሆኑም በዚህ የክፍል ደረጃ ደግሞ የአካል
ክፍሎችን በማስተባበር ለሰውነታችን የተሟላ የአካል እድገት፣ ጤንነት፣ ድፍረትን፣ የተስተካከለ የአካል ቁመናና ቅርፅ ለማስገኘት
የሚያግዝ እንቅስቃሴ በማካተት ይተገበራል።
ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የጅምናስቲክስ ጠቀሜታ፣ የጅምናስቲክስ ዓይነቶች (ነፃ ጅምናስቲክስ፣ የመሳሪያ ጅምናስቲክስ) እንዲሁም
ከውድድራዊ ጅምናስቲክስ ውስጥ የሪትሚክ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን አካቶ የያዘ በመሆኑ የአካል ክፍሎችን በማስተባበር
ለሰውነታችን የተሟላ የአካል እድገት፣ ጤንነት፣ ውሳኔ ሰጭነትን፣ የተስተካከለ የአካል ቁመናና ቅርፅ ለማስገኘት የሚያግዝ እንቅስቃሴ
በማካተት ይተገበራል።

5.1 የጅምናስቲክስ ምንነትና ጥቅም (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª የጅምናስቲክስን ምንነት ያብራራሉ።
ªª የጅምናስቲክስን ጥቅም ይገልፃሉ።

በዚህ ርዕስ ውስጥ ሰፊ የሆኑ ሀሳቦች ቢኖሩም በ 5 ኛ ክፍል የተወሰነ ግንዛቤ ያለ በመሆኑ ለዚህ ክፍል በሚመጥን ሁኔታ የጀምናስቲክን
አይነቶች ትርጉማቸውንና ጥቅማቸውን በይበልጥ የምናይበት ይሆናል።
መርጃ መሳሪያዎች፦መፅሐፍት፣ የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ ፖስተሮች

50 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል


• ያለፈውን ትምህርት በጥያቄና መልስ መልክ መከለስ
• የዕለቱን ትምህርት ይዘትና ዓላማዎችን ማስተዋወቅ፤
• በጥንድ ወይም በቡድን በመሆን የጅምናስቲክስ አይነቶችን ትርጉማቸውን እና የጅምናስቲክስ ጥቅሞቻቸውን (ተግባር-1)
በቡድን እንዲነጋገሩ ማድረግ
• ሀሳባቸውን ለክፍል ጓደኞቻቸው እንዲያቀርቡ ማድረግ
• ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ መግለጫ ወይም ማብራሪያ መስጠት
• ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን ጥያቄ እንዲጠይቁ እድል መስጠት
• የተጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ለሚቀጥለው ፔሬድ የተግባር እንቅስቃሴ ለመስራት የሚያስፈልጋቸውን አሟልተው
እንዲመጡ መንገርና መሰናበት
ክትትልና ግምገማ፦ በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ እና የቡድን ፅብረቃ እንዲያደርጉ በማድረግ
•• ተግባር 1 መልስ፡-
1. የጅምናስቲክስን አይነቶችን ምንነት አብራሩ? የጅምናስቲክስ አይነቶች ብዙ ቢሆኑም ባጠቃላይ በሁለት ዋና ተግባራት ውስጥ
ይካተታሉ። እነርሱም ነፃ ጅምናስቲክስና የመሣሪያ ጅምናስቲክስ ይባላሉ ነፃ ጅምናስቲክ ማለት የጅምናቲክ እንቅስቃሴውን
የሚሠራው ሰው ምንም አይነት ረዳት መሣሪያ ሳይጠቀም ተፈጥሮአዊ በሆኑት የሠውነት ክፍሎች ብቻ በመጠቀም በመሬት ላይ
የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚያጠቃልል ነው። ሁለተኛው ደግሞ የመሣሪያ ጅምናስቲክስሲሆን ይህ ከጅምናስቲክስ ዋና ዋና
ክፍሎች አንዱ ሲሆን የሚከናወነውም የተለያዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም የሚሰራ የጅምናሰቲክስ እንቅስቃሴ ነው።
2. የጅምናስቲክስን ጥቅሞች ከቡድን ጓደኞቻችሁ ጋር በመወያየት ለክፍሉ ተማሪዎች አቅርቡ? ከላይ በተጠቀሰው መሠረት
የጅምናስቲክስ እንቅሰቃሴ ለተሳታፊዎቹ ይሰጣል ተብሎ የሚታመነው ጥቅም፤

 የመተጣጠፍና በፍጥነት አቅጣጫን የመቀያየር ችሎታን (ቅልጥፍናን) ያዳብራል

 በተግባራዊ ተሳትፎ ጊዜ የመንከባለልና የመዞር፣ መስፈንጠር፣ መጠማዘዝ ችሎታን ያሳድጋሉ።

 ከዋና ዋና ውድድሮች በፊት ሰውነትን ለማሟሟቅ አጠቃላይ የሰውነት ቅርጽንና አሰራርን ጤነኛ ለማድረግ ይጠቅማሉ።

 አልፎ አልፎም የህመም ስሜት ለማስታገስ ያገለግላሉ።

 በከፍተኛ ሁኔታ የአካልና የአእምሮ መስተጋብራዊ እድገትን ያጎለብታሉ።

 የድፍረትንና የውሳኔ ሰጭነትን ችሎታ ያዳብራሉ።

 በአደጋ ጊዜ ትክክለኛ የሆነ የአወዳደቅ ስልትን ያስተምራሉ ወዘተ....

5.2 የጅምናስቲክስ አይነቶች (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ከዚህ ርዕስ በኋላ ተማሪዎች
 የጅምናስቲክስ አይነቶችን ከነትርጉማቸው ይለያሉ።
 የነፃ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በትክክል ይሰራሉ።

51 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

 የመሳሪያ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ቅደም ተከተላቸውን ጠብቀው ይሰራሉ።


5 ኛ ክፍል በተማራችሁት መሰረት ጅምናስቲክስ በሁለት የሚከፈል ሲሆን እነዚህም ነፃ ጅምናስቲክስና የመሳሪያ ጅምናስቲክስ
ይባላሉ እንቅስቃሴዎችም በውስጣቸው ሚዛንን፣ ጥንካሬን፣ ተጣጣፊነትን፣ ቅልጥፍናን፣ ቅንጅትን እና ድፍረትን የሚጠይቁ አካላዊ
እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት ስፖርት ነው። በጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች መሳተፍ የሚሰጠው ጥቅም ውስጥ እጆችን፣ እግሮችን፣
ትከሻዎችን፣ ጀርባቸውን፣ ደረታቸውን እና የሆድ ጡንቻ ክፍሎችን ለማዳበር አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

5.2.1 ነፃ ጅምናስቲክስ (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማ ተማሪዎች ከዚህ ርዕስ በኋላ፡-
 የነፃ ጅምናስቲክስ አይነቶችን ምንነታቸውን ይገልፃሉ።
 የተለያዩ የነፃ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ሠርተው ያሳያሉ።
 የሰሯቸው የነፃ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ያስገኙላቸውን ጠቀሜታ ይናገራሉ።
ነፃ ጅምናስቲክስ የምንለው ሰው ምንም አይነት መሳሪያ ሳይጠቀም ሊያከናውናቸው የሚችላቸውን እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት
ሲሆን የማሳሰብን፣ የመዝለልና የመፈናጠር፣ ጉልበት የማመንጨትን፣ የመገለባበጥን፣ ሚዘንን የመጠበቅንና መውጣት መውረድን
ሊያደብርልን የሚችል እንቅስቃሴ ነው።
ሀ. በትከሻ መቆም፡- በትከሻ መቆም እንቅስቃሴ በአሰራር ሂደቱ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ሲሆን ከወገብ በላይ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን
ለማሳብ፣ የመተጣጠፍ ችሎታን ለመጨመር እና ፅናትን ለማዳበር የሚሰራ እንቅስቃሴ ነው። በትከሻ መቆም እግሮችን ወደላይ በማድረግ
ከተፈጥሮ አቋቋም በተቃራኒ የሚከናወን በመሆኑ ጥቂት ጭንቀትን መፍጠሩ አይቀርም። በዚህም ሚዛንን በመጠበቅ የሰውነት ክብደት
ሙሉ ለሙሉ የሚውለው በትከሻ በላይኛው ክፍልና በእጆች ክርን ድጋፍ በመታገዝ ይሆናል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕሎች፣ፖስተሮች
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
• ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
• በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• ባለፈው የተማሩትን የቃል ጥያቄ በመጠየቅ እንዲያብራሩ ማድረግ
• በትከሻ የመቆም እንቅስቃሴ ሂደትን ቀደምት እውቀታቸውንና ሥራቸውን በማስታዎስ እያንዳንዱን የሚያወቁትን
እንዲያሳዩ መጠየቅ
• ስለ እንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በትከሻ መቆምን እንደፈለጉ እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• የመማሪያ መፅሐፉ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ በመመልከት መጀመሪያ በጀረባ በመተኛት ሁለቱንም እግር ወደ ላይ ማንሳት
• ሁለት እግር ከፍ ብሎ በሚመጣበት ወቅት በሁለቱም እጅ በመደገፍ ከዳሌ እና ከመቀመጫ ወደ ላይ አንዲነሳ ማገዝ
• ከወገብ ቀና በማለት እና እግርን ወደ ላይ ቀጥ በማድረግ በትከሻ መቆም መቻል
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ ሰውነታቸውን እንዲያዝናኑና እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ

52 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

 የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች ከጉዳታቸው አንፃር በማየት እንቅስቃሴውን አጋዥ በመመደብ አብረው እንዲሰሩ ማድረግ
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት የአሰራር ሰህተቶች ካሉ እርስ በርስ
እንዲተራረሙ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
 ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
 የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ በጥያቄና መልስ ማረጋገጥ እና የሰሩትን ተግባር በመመልከት
ለ. በግንባር መቆም፡- ከግንባር መቆም በኋላ ወደፊት መንከባለል፡- በግንባር መቆምና መንከባለል የመተጣጠፍና የመገለባበጥ
የጅምናስቲክስ አይነቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን የሰውነት ክብደትን በግንባርና በእጅ ላይ በማሳረፍ ቀጥ ብሎ ከቆሙ በኋላ ወደ ፊት
መንከባለል ማለት ነው። ይህም የእንቅስቃሴ አይነት የሰውነትን የመተጣጠፍ ችሎታ ከማሳደጉ በተጨማሪ ጥንካሬንና ብርታትን
ለማጎልበት ይጠቅመናል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ሰዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ይህን እንቅስቃሴ ለመስራት መጀመሪያ ሶስት ማዕዘን በእጅ ለክቶ መስራት፣
• ሁለቱን እጆች እና ግንባርን በሶስቱ ማዕዘን ውስጥ ማሳረፍ፣
• እግርን ቀስ እያደረጉ ተራ በተራ ወይም አንድ ላይ ማንሳትና ክርን ላይ በማሳረፍ፣ ወዲያው ቀስ እያደረጉ ተራ በተራ
ወይም አንድ ላይ ከክርን ማንሳት
• በመጨረሻም ሁለቱን እግሮች ቀጥ በማድረግ በግንባር መቆም።
• ሲወርድም ቀስ በማለት ወደ ፊት በመንከባለል እንዲቆሙ ማድረግ
• ሁለቱን ተግባራት በማቀኛጀት በመካከሉ እረፍት በመውሰድ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ።
• ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ በመንገር መሰናበት
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ሐ. በእጅ መቆም፡- በእጅ የመቆም እንቅስቃሴ ሌላኛው የመተጣጠፍንና የመገልበጥን ጅምናስቲክ አይነት ሲሆን የሰውነት ክብደት
በእጅ ላይ በማሳረፍ የእጅ ጥካሬንና ሚዛንን የመጠበቅ አቅምን ለማሳደግ የምንጠቀምበት ተግባር ነው። በእጅ የመቆም እንቅስቃሴ
ወቅት እጅና ከወገብ በላይ ያለው የሰውነት ክፍል ቀጥ ማለት አለበት።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ

53 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ


• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በእጅ የመቆም አሰራር እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• የመማሪያ መፅሐፉ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ከመቆም እጆችን በደረት አኳያ ወደፊት ቀጥ አድርጎ በመዘርጋት የግራ
እግርን
ወደ ፊት ማስቀደም
• ከወገብ ወደፊት ጎንበስ ብሎ እጅን በመሬት ላይ በሁለት እጅ ማስደገፍ
• ወደ ኋላ የቀረውን እግር መጀመሪያ ቀጥሎ ወደ ፊት የነበረውን እግር ቀጥሎ ማንሳት
• ክብደትን ሙለ በሙሉ በእጃችን ላይ በማዋልና አንገትን ወደፊት ትንሽ ወጣ በማድረግ መቆም
• እንቅስቃሴውን በጓደኛ ረዳትነት እንዲለማመዱ ማድረግ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
መ. ከእጅ መቆም በኋላ ወደፊት መንከባለል፡- ይህ እንቅስቃሴ ከላይ ከተሰራው ተግባር ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ልዩነቱ በእጅ በትክክል
ከቆምን በኋላ ወደ ፊት የምንከባለልበት ሂደት ነው። በመሆኑም ቅንጅታዊ ሥራዎችን የሚጠይቅ ስለሆነ የአሰራር ቅደም ተከተሉን
መከተል እስፈላጊ ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን ከእጅ መቆም በኋላ ወደፊት መንከባለል እንቅስቃሴን እንደፈለጉ እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• የመማሪያ መፅሐፉ ላይ ያለውን እንቅስቃሴ ከመቆም እጆችን በደረት አኳያ ወደፊት ቀጥ አድርጎ በመዘርጋት የግራ
እግርን
ወደ ፊት ማስቀደም
• ከወገብ ወደፊት ጎንበስ ብሎ እጅን በመሬት ላይ በሁለት እጅ ማስደገፍ
• ወደ ኋላ የቀረውን እግር መጀመሪያ ቀጥሎ ወደ ፊት የነበረውን እግር ቀጥሎ ማንሳት
• ክብደትን ሙለ በሙሉ በእጃችን ላይ በማዋልና አንገትን ወደፊት ትንሽ ወጣ በማድረግ መቆም
• ሰውነትን ወደፊት በመግፋትና እጅን በማጠፍ የሰውነት ክብደትን ጀርባ ላይ በማዋል ወደ ፊት መንከብልና መቆም
 በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ

54 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

ሠ. ወደፊት ዘሎ መንከባለል/ዳይቨ ሮል/፡- ይህ እንቅስቃሴ ከፍተኛ የሆነ እርዳታንና ጥንቃቄን የሚጠይቅ በመሆኑ የአሰራር ሂደቱን
ተከትሎ መስራት ቅድሚያ የሚሰጠው ይሆናል። ይህ ተግባር ሁሉንም የሰውነት ክፍሎች በማስተባበር ሊሰራ የሚችል ሲሆን የእጅን
ጥንካሬ፣ አጠቃላይ ከወገብ በላይ ያለው የሰውነት ክፍል የመተጣጠፍና የቅልጥፍና ባህሪ እንዲሁም የአዕምሮ ቅንጅት ትልቁን ቦታ
ይይዛሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በጥልቀት መንከባለል እንቅስቃሴን አሰራር እንደፈለጉ እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• መጀመሪያ በትክሻ ስፋት ልክ እግርን በመክፈት እጅን ወደፊት ማመልከት
• ትንሽ ሸብረክ እንደማለት በማለትና ከእግር ወደ ላይ የተወሰነ በመነሳት አየር ላይ የመንሳፈፍ ሂደት ማሳየት
• እግር በአየር ላይ ቀጥ እንዳለ እጅን ወደ መሬት በመላክ እንዲያርፍ ማድረግ
• ወዲያውኑ የሰውነትን ክብደት እጅ ላይ በማሳረፍ ወደፊት መንከባለልና መቆም
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ

5.2.2 የመሳሪያ ጅምናስቲክስ (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማተማሪዎች ከዚህ ርዕስ በኋላ፡-
 የመሳሪያ ጅምናስቲክስ አይነቶችን ጥቅማቸውን ይገልፃሉ።
 የመሳሪያ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ሠርተው ያሳያሉ።
 የመሳሪያ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች በመስራት ያስገኙትን ጠቀሜታ ይናገራሉ።
 ለመሳሪያ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴ ያላቸውን ተነሳሽነት ያሳያሉ።
የመሳሪያ ጅምናስቲክስ የምንለው የተለያዩ ለጅምናስቲክስ እንቅስቃሴ አጋዥ የሆኑ መሳሪያዎችን በመጠቀም የምንሰራው ተግባር
የመሳሪያ ጅምናስቲክስ ተብሎ ይጠራል። የመሳሪያ ጅምናስቲክስ በረዳት ወይም በዋና መሳሪያዎች በመጠቀም ማለትም ነጠላ አግዳሚ
ዘንግ፣ ጥንድ አግዳሚ ዘንግ፣ ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚ ዘንግን በመጠቀም የምንሰራቸውን እንቅስቃሴዎች የሚያካትት
ሲሆን ዋነኛ ዓለማውም ጥንካሬንና የመተጣጠፍን ችሎታ ለማሳደግ ነው።
ሀ. ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ በሁለት እጅ በመንጠላጠል እግርን ወደላይ ማንሳት፡- በነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎች
የተለያዩ ናቸው። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ በሁለት እጅ በመንጠላጠል እግርን ወደላይ ማንሳት ሲሆን ይህን
ተግባር ለማከናወን የእጅ ጥካሬንና ከወገብ በላይ ያሉ የሰውነት ክፍሎችን ትብብር የሚጠይቅ ሲሆን ለእጅ ጥንካሬንና የመተጣጠፍ
ችሎታን ለማሳደግ ሊጠቅመን የሚችል እንቅስቃሴ ነው።

55 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

መርጃ መሳሪያዎች፦ ነጠላ አግዳሚ ዘንግ፣ ፍራሽ


የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
• ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
• በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• ባለፈው የተማሩትን /የነፃ ጅምናስቲክስ ተግባር/ በመጠየቅ የተወሰነ እንዲያሳዩ ማድረግ
• በመሳሪያ የሚሰሩ የእንቅስቃሴ ሂደትን የ 5 ኛ ክፍል ሥራቸውን በማስታዎስ የሚያወቁትን በተግባር እንዲያሳዩ መጠየቅ
• ስለ እንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• መጀመሪያ ከነጠላ አግዳሚ ዘንጉ ፊት ለፊት በትክሻ ልክ እግርን በመክፈት መቆም፣
• እጅን ወደ ላይ በማንሳት ዘሎ ነጠላ ዘንጉን በመያዝ ምቾት እንዲሰማን ማድረግ
• እጅንና ሌላውን የሰውነት ክፍል በማስተባበር በስዕሉ መሰረት እግርን ወደ ላይ ማንሳት
• ቀስ በማለት አግዳሚው ዘንግ ድረስ መውሰድና መመለስ
• በመካከሉ እረፍት በመውሰድ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ።
 የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች ከጉዳታቸው አንፃር በማየት እንቅስቃሴውን አጋዥ በመመደብ አብረው እንዲሰሩ ማድረግ
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት የአሰራር ሰህተቶች ካሉ እርስ በርስ
እንዲተራረሙ ማድረግ
 ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ ተግባራትን ክብደቱን በመጨመር ማሰራት
 በቡድን ሆነው የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
 ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱማድረግ
 ለተጠየቁት ጥያቄዎች እያንዳንዱ ቡድን ማብራሪያ እንዲሰጥ ማድረግ
 የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ለ. ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ተንጠልጥሎ በሁለት እጅ ወደ ኋላ መገልበጥ፡- ይህ እንቅስቃሴ የሰውነትን የመተጣጠፍ፣ የቅልጥፍናን፣
በፍጥነት የማሰብን እንዲሁም ጥንካሬንና ብርታትን ሊያደብርልን የሚችል ተግባር ነው። በተጨማሪም ሚዛንን ለመጠበቅ የሚያስችል
ሲሆን እንቅስቃሴውን ስንተገብር ግን መጀመሪያ ሁለት ለሁለት በመተባበር ቢሆን ይመረጣል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ነጠላ አግዳሚ ዘንግ፣ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ተንጠልጥሎ በሁለት እጅ ወደ ኋላ መገልበጥ ከአሁን በፊት የሚያውቁትን የአሰራር ሂደት
እንደፈለጉ እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ

56 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

• ከነጠላ አግዳሚ ዘንጉ ፊት ለፊት በትክሻ ስፋት ልክ እግር በመክፈት መቆም


• እጅን ወደ ላይ በማንሳት ዘሎ ነጠላ ዘንጉን በሚያመች ሁኔታ መያዝ
• እግርን ከአግዳሚ ዘንጉ በላይ በመውሰድ ወደ ኋላ በመገልበጥ በስዕሉ መሰረት በመያዝ የተወሰነ ጠልጠል በማለት
መቆየት
• ወዲያውኑ የተወሰነ በመስራት ሳይደክም መሬት ላይ ማረፍ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ሐ. ነጠላ አግዳሚ ዘንግ ላይ ተንጠላጥሎ በሁለት እጅ መሀል ወደኋላ መሹለክ ፡- ይህ እንቅስቃሴ ትኩረት የሚያደርገው የእጅና የእግር
ጥንካሬን፣ ሚዛንን የመጠበቅንና ድፍረትን የበለጠ በማሳደግ ላይ ትኩረት ይሰጣል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ነጠላ አግዳሚ ዘንግ፣ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከነጠላ አግዳሚ ዘንጉ ፊት ለፊት በትክሻ ልክ እግር በመክፈት መቆም
• እጅን ወደ ላይ በማንሳት ዘሎ ነጠላ ዘንጉን በሚያመች ሁኔታ መያዝ
• እግርን በሁለቱ እጆች መሀል በማሾለክ በእጅ አግዳሚ ዘንጉን በስዕሉ መሰረት በመያዝ የተወሰነ ጠልጠል በማለት
መቆየት
• ወዲያውኑ የተወሰነ በመስራት ሳይደክም መሬት ላይ ማረፍ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
መ. ጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ በመወዛወዝ ወደ ፊት መውጣት፡- ይህ እንቅስቃሴ የአካል ብቃትን በማዳበር ረገድ ከፍተኛ የሆነ
አሰተዋፅዎ አለው። ከዚህ በተጨማሪ ሚዛንን በመጠበቅ፣ አጠቃላይ የሰውነት ቅንጅትን በማሳደግ፣ ድፍረትን፣ ተወዛውዞ ወደፊት
በመውጣት ውሳኔ ሰጭነትን ለማሳደግ፣ ጥንካሬንና ብርታትን ለማጎልበት ትልቅ የሆነ ዋጋ አለው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ጥንድ አግዳሚ ዘንግ፣ስዕል፣ቪድዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
• የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ በመወዛወዝ ወደ ፊት የመውጣት የአሰራር ሂደት እንዲሰሩ
እድል
መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ

57 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

• ከጥንድ አግዳሚ ዘንጉ ፊት ለፊት በትከሻ ልክ እግር በመክፈት መቆም


• እጅን ወደ ላይ በማንሳት ዘሎ ጥንድ አግዳሚ ዘንጉን በሚያመች ሁኔታ በሁለቱም እጆች መያዝና እንዲመች ማድረግ
• ሁለቱንም እግሮች በአንድ ላይ ሌላውን የሰውነት ክፍል በማስተባበር ወደፊትና ወደ ኋላ ሚዛንን በመጠበቅ በአግዳሚው
ዘንግ መሀል ማወዛወዝ
• የተወሰነ በመስራት ሳይደክም መሬት ላይ ማረፍ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ሠ. ጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ በመወዛወዝ ወደ ኃላ መውጣት፡- ይህ እንቅስቃሴ ከላይ በመ ተግባር ላይ ከተገለፅው ማብራሪያ ጋር
ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን መሰረታዊ ልዩነቱ ይህ ተግባር ውዝዋዜውን ካደረግንና ከጨረስን በኋላ ወደኋላ ዘለን የምንመጣበት መሆኑ
ብቻ ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ጥንድ አግዳሚ ዘንግ፣ስዕል፣ቪድዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
 የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በጥንድ አግዳሚ ዘንግ ላይ በመወዛወዝ ወደ ፊት የመውጣት የአሰራር ሂደት እንዲሰሩ
እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• ከጥንድ አግዳሚ ዘንጉ ፊት ለፊት በትክሻ ልክ እግር በመክፈት መቆም
• እጅን ወደ ላይ በማንሳት ዘሎ ጥንድ አግዳሚ ዘንጉን በሚያመች ሁኔታ በሁለቱም እጆች መያዝና እንዲመች ማድረግ
• ሁለቱንም እግሮች በአንድላይ ሌላውን የሰውነት ክፍል በማስተባበር ወደፊትና ወደ ኋላ ሚዛንን በመጠበቅ በአግዳሚው
ዘንግ መሀል ማወዛወዝ
• የተወሰነ በመስራት ሳይደክም መሬት ላይ ማረፍ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ረ. ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚ ዘንግ ላይ የጅመናስቲክ እንቅስቃሴ፡- ይህ እንቅስቃሴ በመሰረታዊነት የሚከናወነው በሁለት
ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚዎች ሲሆን ጥካሬን፣ የመተጣጠፍ ችሎታን፣ ቅልጥፍናንና ድፍረትን ለማሳደግ ከምንሰራቸው
ውስጥ ይካተታል። በዚህ ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚ ዘንግ የተለያዩ አንቅስቃሴዎችን ለመስራት የእያንዳንዳቸውን የአሰራር
ቅደም ተከተል ማወቅ ተገቢ ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚ ዘንግ፣ስዕል፣ቪድዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
58 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ
ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ


 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
 የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚ ዘንግ ላይ የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ የአሰራር ሂደት
እንዲያሳዩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• ትይዩ ያልሆነ(ያልተመጣጠነ) አግዳሚ ዘንግ ፊት ለፊት በትክሻ ልክ እግር በመክፈት መቆም
• እጅን ወደ ላይ በማንሳት ዘሎ ረጅሙን ዘንግ በሚያመች ሁኔታ መያዝ
• ሁለቱንም እግሮች በአንድ ላይ ሌላውን የሰውነት ክፍል በማስተባበር ወደፊትና ወደ ኋላ ሚዛንን በመጠበቅ ማወዛወዝ
• ከውዝዋዜ በኋላ እጅን ረጅሙን አግዳሚ ዘንግ እንዲለቅና አጭሩን በአየር ላይ እንዳለ(መሬት ሳይነካ) መያዝ
• የተወሰነ በመስራት ሳይደክም መሬት ላይ ማረፍ
• ሁለተኛውን አሰራር ማለትም ሁለቱንም እግሮች በአንድ ላይ ሌላውን የሰውነት ክፍል በማስተባበር ረጅሙ ዘንግ ላይ
ወደፊትና ወደ ኋላ መወዛወዝ
• ከውዝዋዜ በኋላ በረጅሙና በአጭሩ ዘንጎች መካከል ሁለቱንም እግሮች በማሾለክ ወደ መሬት መውረድ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ

5.3 ሪትሚክ ጅምናስቲክስ (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማ፡- ተማሪዎች ከዚህ ርዕስ በኋላ፡-
 የተለያዩ የሪትሚክ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎችን በተግባር ሠርተው ያሳያሉ።
 የሰሯቸው የሪትሚክ ጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ያስገኙላቸውን ጠቀሜታ ይናገራሉ።
 ለሪትሚክ ጅምናስቲክስ ያላቸውን ፍላጎት ያንፀባርቃሉ።
በሪትሚክ ጅምናስቲክስ ውስጥ የተለያዩ የመሳሪያ ዓይነቶችን በመጠቀም ማለትም ገመድ፣ ቀለበት፣ ኳስ፣ ሆፕን እና ሪባን በመያዝ
መዝለልን፣ መወርወርን፣ ማሽከርከርን እና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የምንሰራበት የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴ ነው። ሪትሚክ
ጂምናስቲክስ የተለያዩ የጂምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች እና የዳንስ ልምምዶች በሙዚቃ፣ በተለያዩ የጂምናስቲክስ መሣሪያዎች ወይም
ያለ እይታ ሊከናወኑ ይችላል።
ሀ. በገመድ የሚሰሩ ሪትሚክ ጅምናስቲክስ፡- ይህን ተግባር በተለያዩ አቀራረቦች እና ከክፍል ደረጃው አንፃር 5 ኛ ክፍል ላይ በሰፊው
ተምራችሁታል ነገር ግን የአሰራር ሂደቱንና ክብደቱን በመቀየር በግልና በቡድን በመስራት የአሰራር ጥበባችሁን እንድታሳድጉ በዚህ
ክፍል የቀረቡ በመሆናቸው ደጋግማችሁ መስራት ይጠበቅባችኋል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያየ መጠን ያላቸው ገመዶች
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ

59 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

• በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ


• ባለፈው የተማሩትን /የነፃ ጅምናስቲክስ ተግባር/ በመጠየቅ የተወሰነ እንዲያሳዩ ማድረግ
• በመሳሪያ የሚሰሩ የእንቅስቃሴ ሂደትን የ 4 ኛ ክፍል ሥራቸውን በማስታዎስ የሚያወቁትን እንዲያሳዩ መጠየቅ
• ስለ እንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ገመዱን ከወገብ ቀበቶ ላይ በመለካት የሚሆነንን መጠን መለየት
• በመፅሐፉ ላይ ያሉትን አሰራሮች መከተል ለምሳሌ ገመዱን በሁለት እጅ ይዞ በፊት፣ በግራና በቀኝ በኩል በሪትም
መዝለል
• በመቀጠል ከምት ጋር አቀናጅተው በውድድር መልክ በግል በሁለት እግር፣ በማፈራረቅ እና በአንድ እግር እንዲዘሉ
ማድረግ
• ተጨማሪ በገመድ ሪትሚካዊ እንቅስቃሴ ማሰራት
• በመካከሉ እረፍት በመውሰድ በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ።
 የአካል ጉዳት ያለባቸው ተማሪዎች ከጉዳታቸው አንፃር በማየት እንቅስቃሴውን አጋዥ በመመደብ አብረው እንዲሰሩ ማድረግ
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት የአሰራር ሰህተቶች ካሉ እርስ በርስ
እንዲተራረሙ ማድረግ
 ሌሎች ተመሳሳይ የሆኑ ተግባራትን ክብደቱን በመጨመር ማሰራት
 በቡድን ሆነው የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
 ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
 ለተጠየቁት ጥያቄዎች እያንዳንዱ ቡድን ማብራሪያ እንዲሰጥ ማድረግ
 የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ለ. በኳስ የሚሰሩ ሪትሚክ ጅምናስቲክስ፡- ይህ እንቅስቃሴ ትኩረትን፣ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ቅንጅትን፣ በጨዋታው አማካኝነት
መደሰትን እና በጋራ አብሮ የመስራትን ባህሪ ሊያሳድግ የሚችል እንቅስቃሴ ነው፤ ተግባሮችም ከ 5 ኛ ክፍል የቀጠሉ በመሆኑ የፈጠራ
ችሎታችንን በማከል እነዚህንና ሌሎችን ተግባሮች ከኳስ ጋር በማቀናጀት መስራት አለብን።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ኳስ፣ ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
 የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በኳስ የሚሰሩ ሪትሚክ ጅምናስቲክስ የአሰራር ሂደት እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• ኳሱን ከልጆቹ እድሜና አቅም ጋር ሊሄድ የሚችል እንዲሆን መለየት

60 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

• በመፅሐፉ ላይ ያሉትን አሰራሮች መከተል ለምሳሌ ኳሱን በሁለት እጅ ይዞ ከእግር ወይም ከሌላው የሰውነት ክፍል ጋር
በማቀናጀት በሪትም ማሽከርከር
• በመቀጠል ከምት ጋር አቀናጅተው በውድድር መልክ በግል ከተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ጋር በማቀኛጀት እንዲያነጥሩ
ማድረግ
• ተጨማሪ የራሳቸውን የፈጠራ ችሎታ ተጠቅመው ኳሱን እያነጠሩ ሪትሚካዊ እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
ሐ. በቀለበት የሚሰሩ ሪትሚክ ጅምናስቲክስ፡- እንቅስቃሴው በቀለበት የሚሰራ ሆኖ ከ 5 ኛ ክፍል ቀጣይ የሆኑ ተግባራትን የያዘ ነው።
ስለዚህ እንቅስቃሴው እንደሌሎች የሪትም እንቅስቃሴዎች ሁሉ ትኩረትን፣ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ቅንጅትን፣ በጨዋታው
አማካኝነት መደሰትን እና በጋራ አብሮ የመስራትን ባህሪ ሊያሳድግ የሚችል ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ሰፋፊ ቀለበት፣ ገመድ፣ ስዕል፣ፖስተር፣ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል
 ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 በቡድን ሆነው የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያ እንዲሰሩ ማድረግ
 የእንቅስቃሴው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ከአሁን በፊት የሚያውቁትን በቀለበት የሚሰሩ ሪትሚክ ጅምናስቲክስ የአሰራር ሂደት እንዲሰሩ እድል መስጠት
• ትክከለኛውን አሰራር ማሳየትና ቅደም ተከተሉን አንዲከተሉ ማድረግ
• ቀለበቱን ከልጆቹ እድሜና አቅም ጋር ሊሄድ የሚችል እንዲሆን መለየት
• በመፅሐፉ ላይ ያሉትን አሰራሮች መከተል ለምሳሌ ቀለበቱን ወገብ ላይ አድርጎ ውይም አንገት ላይ በማድረግ በሪትም
ማሽከርከር
• በመቀጠል ከምት ጋር አቀናጅተው በውድድር መልክ በግል ቀለበቱን በጭንቅላት በኩል ወደ ላይ ወደፊት በመወርወርና
ቀድሞ ወደፊት ተንከባሎ በመነሳት ቀለበቱን የመያዝን እንቅስቃሴ እንዲሰሩ ማድረግ
• በየመካከሉ ዕረፍት እየሰጡ እንቅስቃሴውን ደጋግመው እንዲሰሩማድረግ
• የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ፣ ምልከታ ማድረግ
መ. በቀለበት ሪትማዊ ጅምናስቲክስ ውድድር፡- ሁሉንም ተማሪ በመፅሐፉ ያሉትን እንቅስቃሴዎች ሲሰሩ የቅርብ ክትትልና እርምት
በማድረግ ስራቸውን ማሰራት ውድድሩንም በማስተባበር ውጤታማ እንዲሆኑ እርምት መስጠትና ማገዝ ይጠበቃል።
የተግባር 2 መልስ
ማሳሰቢያ፡ ይህ ተግባር ተማሪዎችን በቡድን በማድረግና በማደረጀት ሰፊ ጊዜ አስቀድሞ ተሰጥቶ ሊሰራ የሚችል ነው። ተማሪዎች
ይዘውት ከሚመጡት የቀለበት ሪትሚካዊ ተግባር ጋር በማገኛኘት ማየትና እርስ በርሳቸው አስተያየት እንዲሰጣጡ በማድረግ መተግበር
ይቻላል። ነገር ግን ለተማሪዎች መፅሐፍቶችን፣ ሙያተኞችን (የጅምናስቲክ) እና ሌሎች አማራጮችን ማመቻቸት ይገባል።

61 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

የምዕራፍ ማጠቃለያ ጥያቄ


የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካነበባችሁ በኋላ ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ሐሰት በማለት መልሱ
1. የጅመናስቲክስ እንቅስቃሴ የሚባለው መሳሪያ ላይ ብቻ መከናወን ሲችል ነው።
2. በትክሻ መቆም ከመሳሪያ ጅምናስቲክስ ይመደባል።
3. የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴን በተገቢው መንገድ መተግበር የአካል ብቃትን ከማሳደጉ በተጨማሪ ውሳኔ ሰጭነትን ማሳደግ
ይችላል።
4. ሪትሚክ ጅምናስቲክስ የሚከናወነው አንድ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ተማሪዎች ይከናወናል።
ለሚከተሉት ጥያቄዎች ትክከለኛውን መልስ ከተሰጡት አማራጮች ምረጡ
1. ከሚከተሉት የጅምናስቲክስ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሰውነት ክብደት በእጅና በግንባር የሚያርፈው በየትኛው ተግባር ነው?
ሀ. ወደፊት መንከባለል ለ. ወደኋላ መንከባለል ሐ. በእጅ መቆም መ. በግንባር መቆም
2. ከሚከተሉት ውስጥ በዋናና በረዳት መሳሪያ ሊተገበር የሚችለው እንቅስቃሴ ምን ይባላል?
•• ሀ. የወለል ጅምናስቲክስ ለ. የመሳሪያ ጅምናስቲክስ
•• ሐ. ነፃ ጅምናስቲክስ መ. መልስ የለውም
3. ከሚከተሉት ውስጥ ለሪትሚክ ጅምናስቲክስ መስሪያነት የማይካተተው የቱ ነው?
ሀ. ኳስ ለ. ቀለበት ሐ. ገመድ መ. ራይቦን ሠ. ሁሉም
4. ነጠላ አግዳሚ ዘንግ የበለጠ ሊጠቅም የሚችለው የትኛውን የሰውነት ክፍል ነወ?
ሀ. ወገብን ለ. እግርን ሐ. እጅን መ. ሁሉንም
ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ
1. የጅምናስቲክስ ጠቀሜታዎች ውስጥ አምስቱን ዘርዝሩ?
2. የጅምናስቲክስ አይነቶችን ከነትርጉማቸው አብራሩ?
3. የሪትሚክ ጅምናስቲክስ ማለት ምን ማለት ነው?

62 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


ጅምናስቲክስ (ክፍለ ጊዜ ብዛት፡-16)
ምዕራፍ 5

መልስ

የእውነት ወይም ሀሰት መልስ 1.ሀሰት 2.ሀሰት 3.እውነት 4. ሀሰት

የአጭር መልስ ስጥ መልስ


1. የጅምናስቲክስ ጠቀሜታዎች ውስጥ አምስቱን ዘርዝሩ?

 የመተጣጠፍና በፍጥነት አቅጣጫን የመቀያየር ችሎታን (ቅልጥፍናን) ያዳብራል

 በተግባራዊ ተሳትፎ ጊዜ የመንከባለልና የመዞር፣ መስፈንጠር፣ መጠማዘዝ ችሎታን ያሳድጋሉ።

 ከዋና ዋና ውድድሮች በፊት ሰውነትን ለማሟሟቅ አጠቃላይ የሰውነት ቅርጽንና አሰራርን ጤነኛ ለማድረግ
ይጠቅማሉ።

 አልፎ አልፎም የህመም ስሜት ለማስታገስ ያገለግላሉ።

 በከፍተኛ ሁኔታ የአካልና የአእምሮ መስተጋብራዊ እድገትን ያጎለብታሉ።

 የድፍረትንና የውሳኔ ሰጭነትን ችሎታ ያዳብራሉ።


2. የጅምናስቲክስ አይነቶችን ከነትርጉማቸው አብራሩ
•• የጅምናስቲክስ አይነቶች ነፃ ጅምናስቲክስና የመሳሪያ ጅምናስቲክስ በመባል በሁለት ይከፈላሉ።
 ነፃ ግምናስቲክስ
ነፃ ጅምናስቲክ የምንለው ሰው ምንም አይነት መሳሪያ ሳይጠቀም ሊያከናውናቸው የሚችላቸውን እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት
ሲሆን የማሳሰብን፣ የመዝለልና የመፈናጠር፣ ጉልበት የማመንጨትን፣ የመገለባበጥን፣ ሚዘንን የመጠበቅንና መውጣት
መውረድን ሊያደብርልን የሚችል እንቅስቃሴ ነው።
 የመሳሪያ ጅምናስቲክስ
የመሳሪያ ጅምናስቲክ የምንለው የተለያዩ ለጅምናስቲክ እንቅስቃሴ አጋዥ የሆኑ መሳሪያዎችን በመጠቀም የምንሰራው ተግባር
የመሳሪያ ጅምናስቲክ ተብሎ ይጠራል።
3. የሪትሚክ ጅምናስቲክስ ማለት ምን ማለት ነው?
በሪትሚክ ጅምናስቲክስ ማለት የተለያዩ የመሳሪያ ዓይነቶችን በመጠቀም ማለትም ገመድ፣ ቀለበት፣ ኳስ፣ እና ሪባን በመያዝ
መዝለሎችን፣ መወርወርን፣ ማሽከርከርን እና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን የምንሰራበት የጅምናስቲክ እንቅስቃሴ ነው።

መልስ

63 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

ምዕራፍ

6 የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21


ክ/ጊዜ)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡
ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-
ƒƒ ኳስ የመንዳትና የመለጋት መሰረታዊ ክህሎትን ይለያሉ።
ƒƒ አወንታዊ የዕርስ በርስ ግንኑነትን ያዳብራሉ።
ƒƒ ትክክለኛውን ኳስ የማንጠርና ከታች ወደላይ የመለጋት ክህሎትን ያሳያሉ።

መግቢያ
በኳሶች አማካኝነት የሚከናወኑ የተለያዩ ጨዋታዎች ልጆች ክህሎታቸውን ለማዳበር የሚገለገሉባቸው እንቅስቃሴዎች ከመሆናቸውም
በላይ በጣም የሚያስደስቱዋቸው ተግባራት ናቸው። እነዚህ እንቅስቃሴዎች ሀይላቸውን በሚገባ ለመጠቀም የሚያገለግሏቸው ናቸው።
ልጆች አብዛኛውን ጊዜ መጫወት ይወዳሉ። በዚህ ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎች የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እንደ ጨዋታ ጊዜ ብቻ
አድርገው ይቆጥሩታል። ሆኖም ስሜታቸው ሳይነካና ፍላጎታቸው ሳይገደብ ትምህርታዊ ማድረግ ይቻላል። ስለሆነም ደረቅ የሆነ
የክህሎት ትምህርት ከማድረግ ይልቅ ቀላል በሆነ ዘዴ ከጨዋታና ከመዝናናት ጋር አቀናጅቶ ማቅረብ ያስፈልጋል። በዚህ ሁኔታ ከቀረበ
ጤናማ ደስተኛ ሆነው ይቀጥላሉ።

6.1 ኳስ ከታች ወደላይ መለጋትና ልግን በክንድ መቀበል (5 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª ከታች ወደ ላይ የመለጋት ተግባርን ለመስራት ተነሳሽነት ያሣያሉ።
ªª ከቮሊቦል መለጋት አይነቶች ውስጥ ከታች ወደላይ መለጋትን በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።
ªª በ 3፣በ 6 ሜ ርቀት ከታች ወደላይ የልግ አይነቶችን በመጠቀም በትክክል ለጓደኛቸው ኳስ ያቀብላሉ።
ªª ከታች ወደላይ የልግ አይነትን በመጠቀም ከመረብ በላይ በትክክለ ያሳልፋሉ።
ªª ከታች ወደላይ የተለጋች ኳስን በትክክል በክንዳቸው ይቀበላሉ።

መርጃ መሳሪያዎች፦ኳስ፣መረብ፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ከ 3-5 ደቂቃ በቡድን የሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት፣

64 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 የክፍሉ ተማሪዎች በረድፍ እንደቆሙ የዕለቱን ትምህርት ማስተዋወቅና የትምህርቱን ዓላማ መግለጽ፤ከዚህ ቀደም ይህንን
እንቅስቃሴ ሰርተው ያውቁ እንደሆነና እንዴት እንደሚሠራ ጥያቄዎችን መጠየቅ፤
 ሁሉም ከመሞከራቸው አስቀድሞ መጀመሪያ መሥራትና ለሌሎች ማሣየት የሚፈልጉ ተማሪዎች ካሉ ቅድሚያ መሥጠትና
እንዲያሣዩ ማድረግ፤
 ሌሎችም በሚገባ እንዲመለከቱ ማድረግና አሰተያየታቸውን እንዲሰጡ እንዲሁም በተሻለ መልክ መስራት የሚፈልጉ ካሉ
እድሉን መሥጠት፤
 ከአስተያየታቸው በመነሳት ይህ እንቅስቃሴ እንዴት እንደሚሠራ ማስረዳት፤ ሠርቶም ማሳየት፤
 በቀረቡት ኳሶች ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን መክፈልና አጠገብ ለአጠገብ በረድፍ አሰልፎ ለአንድ ቡድን አንድ ኳስ
መስጠት መጀመሪያ ኳስ ወደ ላይ ወርውሮ መሬት ነጥራ ስትመለስ በትክክል ወደላይ መለጋትን እንዲለማመዱ ማድረግ፤
 ተመሣሣዩን እንቅስቃሴ ኳስ ወደላይ በመጠኑ ከወረወሩ በኋላ በአየር ላይ ከታች ወደላይ መለጋትን መለማመድ፣
 በጥንድ ወይም እንደ ኳሶች ብዛት በቡድን በመሆን ከ 3 ሜትር ርቀት በመጀመር ወደኋላ ርቀትን በመጨመር እስከ 6 ሜትር
ርቀት ኳሶችን ከላይ በተገለጸው መልክ የመለጋት እና ለጓደኛ በትክክል ማድረስ፣ የተለጋችውን ኳስ በክንድ መቀበል
 ተመሳሳዩን እንቅስቃሴ ከመረብ በላይ በማሳለፍ ለጓደኛ ማድረስን ደጋግመው እንዲለማመዱ ማድረግ፣
 በርምጃና በሶምሶማ ሩጫ ሰውነታቸውን እንዲያቀዘቅዙና የማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ትምህርቱን ማጠቃለል።
ክትትልና ግምገማ
 የተግባር ስራ ሲሰሩ ምልከታ ማድረግ፣ የቃል ጥያቄ

6.2 ኳስ መንዳት (6 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 በውስጥና በውጭ የጎን እግር ኳስ የመንዳት ጠቀሜታ ይዘረዝራሉ።
 በውስጥና በውጭ የጎን እግር ኳስ የመንዳት ክህሎትን ለማዳበር የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።
 በውስጥና በውጭ የጎን እግር ኳስ በሚመነዳት ጊዜ ያለውን የሰውነት እንቅስቃሴ በቡድን ይወያያሉ።
 በቀጥታ መስመርና በዚግዛግ በውስጥና በውጭ የጎን እግር ኳስ መንዳትን በተግባር ሰርተው ያሳያሉ።
 በውስጥና በውጭ የጎን እግር ኳስ መንዳት ጨዋታዎችን ይጫዎታሉ።

ኳስ ተቆጣጥሮ በትክክል በእግር መንዳት ከመሠረታዊ የኳስ ጨዋታ ክህሎቶች ውስጥ ዋነኛው ነው። ኳስን በውስጥ የጎን እግር፣
በውጭ የጎን እግር፣በፊት ለፊት እግር መንዳት ይቻላል።ተማሪዎች በዚህ የክፍል ደረጃ ላይ ኳስን በውስጥና በውጭ የጎን እግር
መንዳትን የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን በሚገባ ከተለማመዱ ኳስ በትክክል ለመንዳት የሚያስችል የእንቅስቃሴ ቅንጅት ይኖራቸዋል።

ስለዚህ ሁሉም ተማሪዎች በዚህ ርዕስ በአጥጋቢ የችሎታ ደረጃ ላይ የተጠቀሱትን ለውጦች እንዲያመጡና ኳስ የመንዳት
ችሎታቸው እንዲሻሻል የተሰጡትን መለማመጃ እንቅስቃሴዎች በሚገባ እንዲለማመዱ፤ ተግባራዊ ክንዋኔዎችንም በሚገባ መተግበር
ይጠበቅባቸዋል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ስዕል፣ፖስተር
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ያለፈውን ተምህርት የሪቲምካዊ ጅምናስቲክስ አሰራር ዘዴዎችን የቃል ጥያቄ በመጠየቅ መከለስ፤

65 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 የዕለቱን ትምህርት ርዕስና አላማ ማስተዋወቅ

 የክፍሉን ተማሪዎች አምስት አምስት በማድረግ በቡድን በመከፋፈል፡-

 ኳስ በውስጥና በውጭ እግር መግፋትን ጠቀሜታ

 ኳስ በፊት ለፊት እግር (በጫማ ማሰሪያ)መግፋት ጠቀሜታ

 ኳስ በተለያየ የእግር ክፍል መግፋትን የሚያዳብሩ እንቅስቃሴዎችን

 ኳስ በሚገፋበት ጊዜ ሰውነት እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል በቡድናቸው እንዲወያዩ እድል


መስጠት፣

 በውይይቱ ሁሉም ተማሪ እንዲሳተፍ ማበረታታትና ድጋፍ ማድረግ፣

 የተወያዩበትን ሀሳብ በተወካያቸው አማካኝነት ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ፣

 ተማሪዎች ካቀረቧቸው ተጨማሪ ሀሳቦችን በመጨመር ማጠቃለል።

ክትትልና ግምገማ

 የቡድን ውይይት በሚያደርጉበት ጊዜ ሁሉም ተማሪዎች በንቃት መሳተፋቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣

 የቃል ጥያቄ፣የቡድን ጽብረቃ

ሀ. በቀጥታ መስመር በውስጥ፣ በውጭ የጎን እግርና በፊት ለፊት


(በጫማ ማሰሪያ) እግር ኳስ መንዳት
መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያዩ ኳሶች፣ኮን
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 የክፍሉን ተማሪዎች ከ 4-5 ቡድን በመክፈል ከ 3-5 ደቂቃ የሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት

 ያለፈውን ትምህርት ርዕስ በጥያቁ በማስታዎስ የእለቱን ትምህርት ርዕስና አላማ በማስተዋወቅ አጭር ገለፃ መስጠት

 ኳስ ለመንዳት የምንጠቀምበት የእግር ክፍል የቱ እንደሆነ የቃል ጥያቄ መጠየቅ

 ባለን የኳስ ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን ፊት ለፊት በማሰለፍ በፈለጉት የእግር ክፍል ኳስ 20 ሜትር እየነዱ እንዲያቀብሉና
ከኋላ እንዲሰለፉ ማድረግ፣

 በውስጥና በውጭ የጎን እግረ ኳስ አነዳድን በተግባር ሰርቶ ማሳየት፣

 በውስጥና በውጭ የጎን እግረ ኳስ አነዳድን ከጓደኞቻቸው ጋር እየተራረሙ እንዲሰሩ ማድረግ፣

 በፊት ለፊት እግረ ኳስ አነዳድን በተግባር ሰርቶ ማሳየት፣

 በፊት ለፊት እግረ ኳስ አነዳድን ከጓደኞቻቸው ጋር እየተራረሙ እንዲሰሩ ማድረግ፣

 የተማሪዎችን ጥረት በማድነቅ በትክክል የሰሩትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያሳዩ እድል መስጠት፣

 በውስጥና በውጭ የጎን እግረ ኳስ መንዳት በእግር ኳስ ጨዋታ ጊዜ ያለውን ጠቀሜታ ማስገንዘብ፣

66 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 በፊት ለፊት እግር ኳስ መንዳትን በጨዋታ ጊዜ መቸ እንደምንጠቀምበት ማብራሪያ መስጠት።

 በርምጃና በሶምሶማ ሩጫ የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴ በማሰራት ትምህርቱን ማጠቃለል።

ክትትልና ግምገማ

 ተግባሩን በትክክልና በመተጋገዝ መስራታቸውን በምልክታ ማረጋገጥ፣ የቃልጥያቄ

ለ. በመሰናክል/በኮን መካከል ኳስን በውስጥና በውጭ የጎን እግር መንዳት


መርጃ መሳሪያዎች፦የተለያዩ ኳሶች፣ኮን፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 የክፍሉን ተማሪዎች ከ 4-5 ቡድን በመክፈል ከ 3-5 ደቂቃ የሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት

 የእለቱን ትምህርት ርዕስና አላማ ማስተዋወቅ

 ኳስ በውስጥና በውጭ የእግር ክፍል በሚነዳበት ጊዜ ትክክለኛውን የሰውነት እንቅስቃሴ እንዲያሳዩ መጠየቅ

 ባለን የኳስ ቁጥር የክፍሉን ተማሪዎች በቡድን በማሰለፍ ኳስን 20 ሜትር በውስጥና በውጭ የጎን እግረ እየነዱ እንዲመለሱ
ማድረግ፣
 ከተማሪዎች ፊት ለፊት ኮኖችን በ 1 ሜትር ርቀት መደርደር
 በተደረደሩት መሰናክሎች መካከል ያለ ኳስ በዚግዝግ እየሮጡ እንዲመሉሱ ማድረግ፣
 በመሰናክል/በኮን መካከል በውስጥና በውጭ ጎን እግረ ኳስ መንዳት የሚችል ተማሪ ካለ በመጠየቅ እድል መስጠት
 የተማሪዎችን ስራ በማድነቅ ትክክለኛውን ተግባር ሰርቶ ማሳየት፣
 በ 20 ሜትር ርቀት በተደረደሩ መሰናክሎች/በኮኖች መካከል ኳስን በውስጥና በጎን እግር በፍጥነት እየነዱ ደርሶ መልስ
እንዲሰሩ ማድረግ፣
 ተግባሩን ደጋግመው እንዲሰሩ እድል መስጠትና በቡድን በጨዋታ መልክ እንዲሰሩት ማድረግ
 ጨዋታው በቡድናቸው ሁሉም ተማሪዎች ተግባሩን እንደሰሩ በማድረግ ቀድሞ የጨረሰ ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ፣የቃልጥያቄ፣የቡድን ጨዋታ ተሳትፎ

ሐ. ትንንሽ ጨዋታዎች
 የክፍሉን ተማሪዎች ትንንሽ ቡድኖችን በመመስረት በአነስተኛ ሜዳ በውስጥ፣ በውጭና በፊት ለፊት እግር ኳስን የመንዳት
ክህሎትን ትኩረት በማድረግ በቡድን እንዲጫወቱ ማመቻቸት

67 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

የጨዋታው ህግ
የጨዋታው አላማ

ኳስን በሁለት ንክኪ ማቀበል 
በ 5 ኛና በ 6 ኛ ክፍል የተማሯቸውን የእግር ኳስ ክህሎቶች

በውስጥ፣ በውጭና በፊት ለፊት እግር መጫዎት ለማዳበር

ማህበራዊ ግንኙነትን ለማዳበር

6.3 ኳስ ማንጠር (6 ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 ኳስ የማንጠርን ጠቀሜታ ይገልጻሉ።
 የኳስ ማንጠር አይነቶችን ይዘረዝራሉ።
 ኳስ ማንጠርን በተግባር ለመስራት ተነሳሽነት ያሳያሉ።
ማንጠር ማለት ኳስን በማያቋርጥ ሁኔታ ከመሬት ጋር በእጅ እየገፉ በማጋጨት በቁጥጥር ሥር ማቆየት ማለት ነው። ማንጠር ተመሣሣይ
የሆነ የምት ድግግሞሽ መከተል ይፈልጋል። ሰውነትም ከወገብ በመጠኑ አጠፍ በማለት እግሮች ከፈት ብለው በተፈለገ ጊዜ ወደተፈለገው
አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ ሆነው የሚገኙበት ሁኔታ ነው። በዚህ ጊዜ ኳስ የሚያነጥረው እጅ ከባለጋራ የራቀ መሆን ሲኖርበት ኳስ
የማያነጥረውም እጅ ደግሞ ኳሱን ከባለጋራ እንቅስቃሴ መከላከል አለበት።
ከሜዳ ውስጥ አንድ ተጨዋች ኳስን ይዞ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል መሠረታዊ ዘዴ ሲሆን በመቆምና በመንቀሳቀስ እጅና አቅጣጫን
በመለዋወጥ በተለያየ ከፍታ ኳስ ከመሬት ጋር በማጋጨት የሚከናወን ተግባር ነው።
ኳስ ማንጠር በቅርጫት ኳስና በእጅ ኳስ ጨዋታ ላይ በጣም አስፈላጊና መሰረታዊ ከሚባሉ ክህሎቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን ተጨዋቾች
እርስ በርስ የሚተሳሰሩበትና ተቃራኒያቸውን በኳስ ቁጥጥር የበላይነትን ለማግኘትና ውጤት ለማስመዝገብ ይጠቀሙበታል።
ኳስን በተለያ ዘዴ ማንጠር ይቻላል እነሱም፡-
 በዝቅተኛ የማንጠር ዘዴ
•• ኳስ በዝቅታ ማንጠር ማለት ኳስን እስከ ጉልበት ከፍታ በታች የማንጠር ዘዴ ሲሆን አነጣጠሩም ወደ ጎን በኩል ሆኖ ኳስን
ከተቃራኒ በማራቅና መቆጣጠር ነው።
•• ኳስ በዝቅታ ማንጠር ኳስን ከተቃራኒ ቡድን ለመከላከል፣ከከበባ ለመውጣት፣ ጓደኛችን አመች ቦታ እስከሚይዝ ኳስን
በቁጥጥር ስር ለማቆት የሚያግዝ ነው።
 በከፍታ የማንጠር ዘዴ
•• በከፍታ የማንጠር ዘዴ በቅርጫት ኳስ ጨዋታና በእጅ ኳስ ጨዋታ ጊዜ ኳስን እስከ ወገብ ከፍታ የማንጠር ዘዴ ሲሆን
አነጣጠሩም
ፊት ለፊት በመሆኑ በላጋራ በሌለበት በፍጥነት በመንቀሳቀስ ከተፈለገው ቦታ ለመድረስ የሚያስችልየማንጠርዘዴነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦የማንጠርን ተግባራት የሚያሳዩ ሥዕሎች ፎቶግራፎች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ባለፈውን ክፍል ጊዜ የተማሩትን ኳስ በውስጥና በውጭ የጎን እግር መንዳትን በተመለከተ በጥያቄና መልስ መከለስ፣
 የእለቱን የትምህርት ርዕስና አላማ ማስተዋወቅ፣

68 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 ተማሪዎችን አምስት አምስት በማድረግ በቡድን በመክፈል የመወያያ ጥያቄ መስጠት


 ኳስ የማንጠር ጠቀሜታ
 ኳስ በማንጠር ወቅት ያለውን የሰውነት ሁኔታ/አቋቋም
 በየትኛው የእጃችን ክፍል ኳስ ማንጠር እንዳለብን ወዘተ እንዲወያዩ በማድረግ
 በውይይቱ ሁሉም ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታትና እገዛ ማድረግ፣
 የተወያዩበትን ለክፍሉ ተማሪዎች እንዲያቀርቡ ማመቻቸት፣
 ከተማሪዎች ጽብረቃ በመነሳት ተጨማሪ ማብራሪያ በመስጠት ማጠቃለል
ክትትልና ግምገማ
 በውይይቱ በንቃት መሳተፋቸውን በምልከታ ማረጋገጥ፣የቃል ጥያቄ መጠየቅናበጽሁፍ ጥያቄ ማረጋገጥ።

6.3.1 ኳስ በዝቅታና በከፍታ ማንጠር (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 ኳስ በዝቅታና በከፍታ ማንጠር ልዩነታቸውንና ጥቅማቸውን ይዘረዝራሉ።
 ኳስ የማንጠርን ተግባራትን ከጓደኞቻቸው ጋር ይተገብራሉ።
 የኳስ ማንጠርን ተግባራት ለመስራት ፍላጎት ያሳያሉ።
መርጃ መሳሪያዎች
 የማንጠርን ተግባራት የሚያሳዩ ሥዕሎች ፎቶግራፎች
 የተለያዩ መጠን ያላቸው የሚነጥሩ ኳሶች
 ፊሽካ
 ኮኖች ወይም ለምልክት የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 በቡድን በመክፈል የተለያዩ የሰውነት ማሟሟቂያና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት፣
 በዝቅታና በከፍታ ኳስ ማንጠር ጠቀሜታ፣ ልዩነት፣ኳስ ለማንጠር የምንጠቀምበት የእጅ ክፍል ወዘተ የቃል ጥያቄ በመጠየቅ
መከለስ፣
 ባለን የኳስ ቁጥር መሰረት ተማሪዎችን በቡድን መክፈል
 በቡድናቸው ክብ ሰርተው እንዲቆሙ በማድረግ ቀደምት ክህሎታቸውን ተጠቅመው ኳስ እንዲያነጥሩ መፍቀድ፣
 የሁሉንም ተማሪዎች የአነጣጠር ዘዴ በመመልከት ስለትክክለኛው የአነጣጠር ዘዴ ኳስን በእጃችን መግፍት እንጂ መምታት
እንደለለብን፣በዝቅታ ስናነጥር ኳስን በጎን በኩል አድረገን በማያነጥረው እጅ እየተከላከልን ማንጠር እንዳለብን፣ በከፍታ
ስናነጥር ደግሞ ወደፊት ለመንቀሳቀስ እንዲያመቸን ፊት ለፊት ማድረግ እንዳለብን፣ ወዘተ ማብራሪያ መስጠትና በተግባር
ሰርቶ ማሰየት፣
 በቡድናቸው በቦታ ላይ ኳስን በዝቅታ እጃቸውን እያቀያየሩ እንዲያነጥሩ ማድረግ፣
 እጅን እያቀያየሩ በእግር መካከል የስምንት ቁጥር ቅርጽን በመስራት ማንጠር

69 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 ተግባሩን ከጓደኞቻቸው ጋር እየተራረሙ ደጋግመው እንዲሰሩ ማድረግ


 የክፍሉን ተማሪዎች ባለን የኳስ ቁጥር በቡድን በመክፈል እንዲሰለፉ ማድረግ
 ከ 20-30 ሜትር ኳስ በከፍታ እያነጠሩ ደረሰው እንዲመለሱ ማድረግ(ሲሄዱ በቀኝ እጃቸው ሲመለሱ ደግሞ በግራ እጃቸው
እንዲያነጥሩ ማድረግ)
 ከ 20-30 ሜትር መሰናክሎችን/ኮኖችን ከ 1-2 ሜትር ርቀት በመደርደር ያለኳስ ዚግዛግ እየሮጡ እንዲመለሱ ማድረግ
 ኳስ በከፍታ እያነጠሩ ከ 20-30 ሜትር መሰናክሎችን/ኮኖችን መካከል ደረሰው እንዲመለሱ ማድረግ(ሲሄዱ በቀኝ እጃቸው
ሲመለሱ ደግሞ በግራ እጃቸው እንዲያነጥሩ ማድረግ)
ማሳሰቢያ አካል ጉዳተኞች ተማሪዎች እንደ አካል ጉዳታቸው ዓይነት እንቅስቃሴዎቹን እንዲሰሩ ተገቢውን
ድጋፍ መስጠት። የአካል ጉዳተኞች በእግር መንቀሳቀስ የማይችሉ ከሆነ ተቀምጠው ወይም ግድግዳ ላይ በማንጠር
የእጅ ጉዳት ከሆነ በእግር እየመቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ።

ተግባሩን በመደጋገም እንዲሰሩ ማድረግ፣በእንቅስቃሴው የተሰማቸውን ስሜት በመጠየቅ የሰውነት


ማቀዝቀዣና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን በማሰራት ማጠናቀቅ።

ክትትልና ግምገማ
 ኳስ የማንጠርን መሰረታዊ ቴክኒኮችን መለየታቸውን በቃልና ከቡድን ጓደኞቻቸው ጋር በመተጋገዝ መስራታቸውን
በምልከታ ማረጋገጥ።
 የግራና ቀኝ እጆቻቸውን በማፈራረቅ በተከታታይ ሳያቀርጡ ማንጠራቸውን መገምገም።

6.3.2 ኳስ የማንጠር ውድድራዊ ጨዋታዎች (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር አላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 የኳስ ማንጠር ክህሎቶችን በጨዋታ መልክ በትክክል ይተገብራሉ።
 በቡድን የመስራት ክህሎታቸውን ያሻሽላሉ።
 በቡድን ጨዋታ በመሳተፍ ይደሰታሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦ኳስ፣ፊሽካ፣ ኮን

•• ጨዋታ 1
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 በቡድን ከ 3-5 ደቂቃ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ኳስ እያነጠሩ ሰውነታቸውን ማሟሟቅና የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት፣
 የእለቱን ትምህርት አላማና ጥቅም ማስተዋወቅ
 ተማሪዎችን በኳሶቹ ቁጥር መጠን በእኩል ቡድን በመከፋፈል ማሰለፍ።
 ኳስን በቀኝና በግራ እጅ እያቀያየሩ የተለያዩ የፊደል ቅርፆችን ምሳሌበ‹v›፣በ‹ሀ›፣በ‹W›ቅርፅ ኳስን ወደጎን፣ወደፊትና ወደኋላ
በመንሸራተት እንዲያነጥሩ ማድረግ
 በትክክል በፊደላት ቅርፅ ኳስን ያነጠረ ተማሪ ተሸናፊ ይሆናል።

70 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 በጨዋታው የተሰማቸውን ስሜት በመጠየቅ የሰውነት ማቀዝቀዣና የማሳሳቢያ እንቅስቃሴዎችን በማሰራት ትምህርቱን
ማጠናቀቅ።
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ
ጨዋታ 2
መርጃ መሳሪያዎች፦ኳስ፣ፊሽካ፣ ኮን
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 በቡድን ከ 3-5 ደቂቃ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ ኳስ እያነጠሩ ሰውነታቸውን ማሟሟቅና የማሳሳብ እንቅስቃሴ ማሰራት፣
 የእለቱን ትምህርት አላማና ጥቅም ማስተዋወቅ
 ተማሪዎችን በኳሶቹ ቁጥር መጠን በእኩል ቡድን በመከፋፈል ማሰለፍ።
 ተማሪዎች በኳሶቹ ቁጥር መጠን ከተከፋፈሉ በኋላ እያንዳንዱ ቡድን እንደገና በሁለት በመከፋፈል በመካከላቸው 30 ሜትር
ርቀት ፊት ለፊት አንዲቆሙ ማድረግ።
 ከዚያም ኳስ ካለችበት ቡድን የመጀመሪያዎቹ ልጆች ኳስ እያነጠሩ ፊት ለፊት እስከ 25 ሜትር ከሮጡ በኋላ 5 ሜትር
ሲቀራቸው በደረት ትይዩ ለቡድን ጓደኛቸው ማቀበልና ከኋላ መሰለፍ።
 በዚህ መልኩ ጨዋታው ይቀጥልና ሁሉም ተማሪዎች ተዳርሰው ተሎ የጨረሰው ቡድን አሸናፊ ይሆናል።
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
የጨዋታው ህግ የጨዋታው አላማ

 25 ሜ በፍጥነት እያነጠሩ መሄድና  የኳስ የማንጠር ክህሎት ማዳበር


 5 ሜ ሲቀር በደረት ትይዩ ማቀበል  በ 5 ኛ ክፍል የተማሩትን ኳስ በደረት ትይዩ
 ሁሉም የቡድኑ አባላት መሳተፍ ማቀበልን ማዳበር
 ለአንድ አላማ በጋራ መስራት
 በጨዋታ ማሸነፍና መሸነፍን መቀበል

ክትትልና ግምገማ፦ በተቀመጠው የጨዋታ ህግ መሰረት መጫዎታቸውን በምልከታ ማረጋገጥ

6.4 የቡድን ጨዋታዎች (4 ክ/ጊዜ)

6.4.1 ጨዋታ አንድ የቮሊቮል ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


መርጃ መሳሪያ፡-ኳስ፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ተማሪዎችን በሁለት ቡድን በመክፍል የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
 የእለቱን ትምህርት አላማ ማስተዋወቅ
 የክፍሉን ተማሪወች እንደ ብዛታቸው 6፡6 በማድረግ መከፋፈል ከዚህ በፊት የተማሯቸውን የቮሊቮል ክህሎቶች
በመጠቀም እጣ የደረሳቸው ሁለቱ ቡድኖች ሲጫዎቱ ቀሪዎቹ የዳኝነትን ሚና ይወጣሉ። ጨዋታው በ 3 ንክኪ

71 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

ማሳለፍ ሲሆን ቀድሞ 10 ነጥብ ያመጣ ቡድን አሸናፊ ይሆናል። ተሸናፊው ቡድን ይወጣና ውጭ ከነበሩት ቡድኖች
አንደኛው በእጣ ይገባል።
 በጨዋታው ሁሉም ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተሰጠው ሰዐት እንዳለቀ አሸናፊውን ቡድን በማስወጣት ሌሎችን ቡድኖች በእጣ ማስገባት
 በጨዋታው፣በዳኝነትና ኳስ በማቀበል የነበራቸውን ተሳትፎ በማድነቅ የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴዎችን
በማሰራት የእለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ

6.4.2 ጨዋታ ሁለት የእግር ኳስ ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


መርጃ መሳሪያ፡-ኳስ፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ተማሪዎችን በሁለት ቡድን በመክፍል የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
 የእለቱን ትምህርት አላማ ማስተዋወቅ
 ከዚህ በፊት የተማሯቸውን የእግር ኳስ ክህሎቶች በመጠቀም የሚጫዎቱት ጨዋታ ሲሆን ሜዳውን ከሁለት
በመክፍል የክፍሉን ተማሪዎች በአምስት አምስት ቡድን መክፈልና ለየቡድኖቹ አገረኛ ስያሜ መስጠት ከሁለቱ
ሜዳ አራት ቡድኖችን በእጣ ማስገባት የሌሎች ቡድን አባለት የዳኝነትንና ኳስ የማቀበልን ሀላፊነት እንዲወጡ
ማድረግ።
 ጨዋታው ሁለት 5 ደቂቃን ይይዛል። ሰአት እንዳለቀ የተጫወቱት ቡድኖች ዳኛና ኳስ አቀባይ ሲሆኑ ውጭ የነበሩት
ተመሳሳይ ሰአት ይጫዎታሉ።
 በጨዋታው ሁሉም ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተሰጠው ሰዐት እንዳለቀ ብዙ ጎል የገባበትን ቡድን በማስወጣት ሌሎችን ቡድኖች በእጣ ማስገባት
 በጨዋታው፣በዳኝነትና ኳስ በማቀበል የነበራቸውን ተሳትፎ በማድነቅ ቀላል የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴዎችን
በማሰራት የእለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ

6.4.3 ጨዋታ ሶስት የቅርጫት ኳስ ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


መርጃ መሳሪያ፡-ኳስ፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ተማሪዎችን በሁለት ቡድን በመክፍል የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
 የእለቱን ትምህርት አላማ ማስተዋወቅ
 ከዚህ በፊት የተማሯቸውን የቅርጫት ኳስ ክህሎቶችን በማቀናጀት በጨዋታ አንድ ላይ በተጠቀምንበት ዘዴ
ውድድር ማድረግ።
 በጨዋታው ሁሉም ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተሰጠው ሰዐት እንዳለቀ አሸናፊውን ቡድን በማስወጣት ሌሎችን ቡድኖች በእጣ ማስገባት

72 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

 በጨዋታው፣በዳኝነትና ኳስ በማቀበል የነበራቸውን ተሳትፎ በማድነቅ የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴዎችን


በማሰራት የእለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ

6.4.4 ጨዋታ አራት የእጅ ኳስ ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


መርጃ መሳሪያ፡-ኳስ፣ፊሽካ
የመማር ማስተማር ቅደም ተከተል
 ተማሪዎችን በሁለት ቡድን በመክፍል የሰውነት ማሟሟቂያና ማሳሳቢያ እንቅስቃሴ ማሰራት
 የእለቱን ትምህርት አላማ ማስተዋወቅ
 ከዚህ በፊት የተማሯቸውን ኳስ የማንጠርና የማቀበል ዘዴዎች በመጠቀም የእጅ ኳስ ጨዋታ መጫወት።
 በጨዋታው ሁሉም ተማሪዎች በንቃት እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተሰጠው ሰዐት እንዳለቀ አሸናፊውን ቡድን በማስወጣት ሌሎችን ቡድኖች በእጣ ማስገባት
 በጨዋታው፣በዳኝነትና ኳስ በማቀበል የነበራቸውን ተሳትፎ በማድነቅ የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴዎችን
በማሰራት የእለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ ምልከታ
የጨዋታዎች ህግ የጨዋታዎች አላማ
 በትንንሽ ቡድን መጫዎት  የኳስ ጨዋታ ክህሎትን ማዳበር
 ለየጨዋታው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ  በቡድን መጫዎትን
መጫዎት
 ሀላፊነትን መወጣት
 መተባበር
 ሀላፊነት የተሞላበት ውሳኔ መስጠትን
 ሁሉም ቡድን የዳኝነትንና የኳስ ማቀበል
ሀላፊነትን መወጣት

የምዕራፉ የመልመጃ ጥያቄዎች


መመሪያ አንድ፡- ለሚከተሉት ጥያቄዎች ተስማሚውን መልስ ምረጥ/ጭ

1. ከሚከተሉት የልግ አይነቶች በጣም ቀላልና ብዙውን ጊዜ ጀማሪና ተለማማጅ ተጫዋቾች የሚያከናውኑት የቱ ነው?

ሀ. ከታች ወደላይ ለ. ከላይ ወደታች

ሐ. ሁሉም

2. ኳስ ወደፊት ሲነዳ የሰውነት አቋቋም እንዴት መሆን አለበት?

ሀ. ወደ ኋላ ያዘነብላል ለ. ወደጎን ያዘነብላል

73 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኳስ ጨዋታዎች መሰረታዊ ክህሎት(21 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 6

ሐ. ወደፊት ያዘነብላል መ. ወደመሬት ሸብረክ ይላል

3. ኳስ በፍጥነት ወደፊት በሚነዳበት ጊዜ ዓይኖች ማየት ያለባቸው

ሀ. ወደ መንቀሳቀሻ አቅጣጫ ለ. ወደኋላ

ሐ. ወደላይ መ. ኳስ ወደሚነዳው
እግር

4. ከሚከተሉት ውስጥ ኳስን በዝቅታ ማንጠር ጠቀሜታ ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ተቃራኒ ተጫዋችን ለማታለል ለ. ኳስን በቁጥጥር ስር ለማዋል


ሐ. በፍጥነት ለመንቀሳቀስ መ. ሁሉም
መመሪያ ሁለት - ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ በፅሁፍ ስጡ
1. ኳስ መንዳት ማለት ምን ማለት ነው?
2. ኳስ ለመንዳት አስፈላጊ የሆኑ የሰውነት ሁኔታዎች እነማን ናቸው?
3. ኳስ ማንጠር ለምን ያስፈልጋል?
4. ለኳስ ማንጠር መሰረታዊ ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው?

መልስ

1. ሀ 2. ሐ 3. ሀ 4. ሐ
1. ኳስ ይዞ ወደፊት በእግር የተለያዩ ክፍሎች እየገፉ ለመንቀሳቀስ የሚጠቅም ቴክኒክ ነው
2. ኳስ ለመንዳት ሰውነትን ኳስ ወደሚነዳበት አቅጣጫ ዘንበል ማድረግ፤ ከራስ ቀና ማለትና ወደ ሚነዳበት
አቅጣጫ መመልከት፤ ኳስ ርቃ እንዳትሄድ የተመጠነ ጉልበት መጠቀም፤
3. ኳስ ማንጠር የሚያስፈልግበት ምክንያት የሚፈለገው ርምጃ ለመውሰድ አመቺ ሁኔታ እስኪፈጠር ድረስ
ወይም ከኳስ ጋር ከቦታ ወደቦታ ተንቀሳቅሶ ተፈላጊውን ግብ ለመምታት እንዲቻል ለማመቻቸት ነው።
ለኳስ ማንጠር መሰረታዊ ሁኔታዎች የእጆችን መገጣጠሚያ (አንጓ) እንቅስቃሴ በሚገባ መጠቀም ሰውነት
በመጠኑ ከወገብ አጠፍ ብሎ ኳስን መቆጣጠር እይታን በኳሷና በተፈላጊ አቅጣጫ ላይ እየለዋወጡ
እንዲውሉ ማድረግ ይሆናል።
4. ሰውነትን ከወገብ በመጠኑ እጥፍ ማድረግና እግሮች በትከሻ ስፋት ልክ ከፈት ማድረግ፣የእጅ ጣትን ዘርዘር
ማድረግ፣ኳስን በእጅ መምታት ሳይሆን መግፋት፣ኳስ የሚያነጥረው እጅ ከባለጋራ የራቀ መሆን ሲኖርበት
ኳስ የማያነጥረውም እጅ ደግሞ ኳሱን ከባለጋራ እንቅስቃሴ መከላከል አለበት።

74 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

ምዕራፍ

7 የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ


ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)

አጠቃላይ ዓላማዎች፡

ተማሪዎች ይህንን ምዕራፍ ከተማሩ በኋላ፡-


ƒƒ የባህላዊ ጭፈራዎችንና ባህላዊ ጨዋታዎችን ምንነት ይረዳሉ።
ƒƒ በአማራ ክልል የሚተገበሩ የተወሰኑ የተመረጡ ባህላዊ ጭፈራዎችንናጨዋታዎችን ይጫወታሉ።
ƒƒ የክልሉን ባህላዊ ጭፈራዎችና ባህላዊ ጨዋታዎች ለአካላዊ እድገት ያላቸውን አስተዋፅዎ ይገነዘባሉ።

መግቢያ
ይህ ምዕራፍ በሀገራችን በተለይም በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች በውስጣቸው የያዟቸውን የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችንና ባህላዊ
ጨዋታዎችን ለማሳወቅና የበለጠ በክልሉ እንዲያድጉ ለማድረግ የምንማርበት ነው። በመሆኑም ምዕራፉ በውስጡ የሚያካትተው ዓብይ
ርዕሶች የባህላዊ ጭፈራዎችንና የባህላዊ ጨዋታዎችን ምንነት፣ በኢትዮጲያ በአማራ ክልል የሚተገበሩ ባህላዊ ጭፈራወችን በተግባር
እና በኢትዮጱያ በአማራ ክልል የሚተገበሩ ባህላዊ ጨዋታዎችን በእንቅስቃሴ የምናካትትበት ነው።በዚህም መሰረት ተማሪዎቹ
የሚቀረቡት ተግባራት የደረጃውን የትምህርት ዓላማዎች ግብ ለማስመታት ዓይነተኛ መሳሪያ መሆናቸውን ማስገንዘብ ይገባል።

7.1 የባህላዊ ጭፈራ ምንነት (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፡-
ªª የጭፈራን ምንነት ያብራራሉ።
ªª በክልሉ የሚገኙ የባህላዊ ጭፈራ አይነቶችን ይዘረዝራሉ።
ªª በክልሉ የሚገኙ የባህላዊ ጭፈራ አይነቶች ሊያካትታቸው የሚችሉ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ይለያሉ።

የባህል ጭፈራ በደስታና በስራ ቦታ የሚደረግ ተግባራዊ የእንቅስቃሴ ክፍል ነው። ብዙ የሀገራችን ብሔረሰብ ጨዋታዎች የመላ
ሰውነት እንቅስቃሴ የሚጠይቁ በመሆናቸው ተማሪዎች መንፈሳቸውን እያደሱና እየተደሰቱ እንቅስቃሴዎችን እንዲያደርጉ እጅግ
ጠቃሚ ነው። ባህላዊ ጭፈራዎች የሚባሉት የሀገራችንን ብሎም የክልላችንን ባህል፣ ወግና ልማድ ሊያንፀባርቁ የሚችሉና ህብረተሰቡ
በተለያየ መንገድ ሊተገብረው የሚችል አካላዊ፣ አዕምሯዊና ማህበራዊ እድገትን እንዲሁም ፍላጎትንና ዝንባሌን ሊያሰድጉ የሚችሉ
እንቅስቃሴዎች ናቸው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ባህላዊ ጭፈራን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ ፖስተሮች

75 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-


 በባህላዊ ጭፈራ የመጀመሪያ ክፍለ ጊዜ በመሆኑ የመተዋወቂያ ሂደቶችን በማስገንዘብ በተግባራዊ እንቅስቃሴ ወቅት ሊከናወኑ
የሚገባቸውን ነጥቦች በአጭሩ መግለፅ
 ከባህላዊ ጭፈራ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ባህላዊ ጭፈራ ምንነት ቀደምት እውቀታቸውን ለማወቅ ጥያቄ በመጠየቅ መልስ እንዲመልሱ ማድረገ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ተግባር-1 መስጠት የባህላዊ ጭፈራ ምንነት፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያላቸውን ግንኙነት
እና በአካባቢያቸው የሚገኙ ባህላዊ ጭፈራዎችን ዘርዝሩ የሚሉትን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
 ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ መስጠት
 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
 የተጠየቁትን ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ ተግባር አንድን በመስጠት መሰናበት
ክትትልና ግምገማ፡-የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ
የተግበር፡-7.1.መልስ
1. ባህላዊ ጭፈራ ማለት ምን ማለት ነው?
መልስ፡- አንድ ማህበረሰብ በራሱ አካባበያዊ ሙዚቃዎች ታጅቦ፣ የራሱን ባህላዊ አልባሳት ለብሶ፣የራሱን ባህል የሚያንፀባርቁ የተለያዩ
ቁሳቁሶችን በመያዝ የሚከውነው ጭፈራ ነው። ይህ ጭፈራ በአንድ በተወሰነ ማህበረሰብ ባህላዊና አካባቢያዊ ድንበር ውስጥ የታጠረና
የማህበረሰቡን ማንነት የሚያሳይ ነው። ጭፈራውም ማህበረሰቡ ባህሉን፣ አካባቢውን፣ ፍልስፍናውን፣ ታሪኩን፣ የኑሮ መሰረቱን፣
የዕለት ተዕለት ድርጊቱን ወዘተ መነሻ በማድረግ ባህላዊ የጭፈራ ቅንብር የፈጠረውና በውክልና ከትውልድ ወደ ትውልድ እያስተላለፈ
ያቆየው የጋራ ሀብት ነው።
2. ባህላዊ ጭፈራ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው አብራሩ?
መልስ፡- ባህላዊ ጭፈራ መሰረታዊ ዓላማዎቹን ስንመለከት ሁሉንም የሰውነት ክፍሎች በጭፈራው በማካተት መዝናናትን፣ መደሰትን
እና በሌላ መንገድ አካልን ማዳበር ነው። በመሆኑም የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እንደ ጭፈራው ሁል ከዓላማዎቹ ውስጥ
የሚጠቃለለው አካልን በማዳበር መዝናናትንና ደስታን መፍጠር ነው። ስለዚህ ባህላዊ ጭፈራዎችን በማከናወን የሰውነት ማጎልመሻ
ትምህርት ሊያመጣው የሚገባውን ዓለማ ልናሳከ እንችልለን ማለት ነው።
3. በአካባቢያችሁ የምታውቋቸውን ባህላዊ ጭፈራዎች ዘርዝሩ?
መልስ፡- በአካባቢያችሁ የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎች ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህም ጭፈራዎች የአጨፋፈር ሂደታቸውም እንደዚሁ
እንደየአካባቢው ሊለያይ ይችላል። ስለዚህ መመህሩ በአካባቢው ሊገኙ/ሊዘወተሩ/ የሚችሉ ባህላዊ ጭፈራዎችን ሊካትት ይገባዋል።
ነገር ግን እነዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የተወሰኑ እንደ ምሳሌ የቀረቡ ናቸው።
የጎንደር አካባቢ፡- መንጥቅ፣ ደስቅ፣ ስክስክ እና ሌሎች
ጎጃም አካባቢ፡- ግርድፍ እንቅጥቅጥ፣ ዝናብ ምት እና ሌሎችም
ወሎ አካባቢ፡- መንጥቅ የደረት፣ የአንገት ድስቃ፣ የትከሻ ድሰቃ እና ሌሎችም
ከሚሴ አካባቢ፡-ሀሚሳዉ በግር የሚሰራ፣ በሁለት ትክሻ የሚሰራ ጉሰማ/ደስቃ እና ሌሎችም
የአዊ አካባቢ፡- የወገብ/የዳሌ/ማሽከርከር/፣ ትክሻን በማሳለቅ/በማቀያየር/ እና ሌሎችም

76 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

የዋግ/የሰቆጣ/አካባቢ፡- ትክሻን ወደታች እና ትክሻ በመጠኑ በመርገጥ የሚሰራ ደስቅ ሌሎች


ሰሜን ሽዋ አካባቢ፡-እጅን በመዘርጋትና በማጠፍ ከትክሻ ጋር በመርገጥ እና ሌሎችም

7.2 በአማራ ክልል የሚገኙ ባህላዊ ጭፈራዎች (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን ባህላዊ ጭፈራዎች ይዘረዝራሉ።
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን ባህላዊ ጭፈራዎች በተግባር ያሳያሉ።
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ባህላዊ ጭፈራዎች ከሰውነት ማጎልመሻ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይገልፃሉ።
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን ባህላዊ ጭፈራዎች ያደንቃሉ።
የአማራ ክልል ባህልን፣ ወግንና ልማድን ሊያንፀባርቁ የሚችሉ ብዛት ያላቸው ጭፈራዎችንና ውዝዋዜዎችን የያዘ ከሚባሉ ክልሎች
ውስጥ አንዱ ነው። የአማራ ባህል በምሳሌዎች፣ በአፈ ታሪኮች እና በሃይማኖታዊ ምሳሌዎች እና ተረት ተረቶችን የያዘ ባህል አለው።
በተጨማሪም ሳይንሳዊ ገለፃዎች ብዙውን ጊዜ ባህላዊ ጭፈራዎችን ከባህል አጠቃቀም ውጭ ስለሚሆኑ ትክከለኛውን ትርጉምና አሰራር
ለመግለፅ ያመች ዘንድ የክልሉን ባህላዊ ጭፈራ ማወቅ ተገቢ ነው። ስለዚህ በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ ዞኖች የሚጠቀሙባቸው/
የሚተገብሯቸው/ የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችን ከተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ጋር በማቀናጀት ሁሉም የክልሉ ተማሪዎች እንዲያውቋቸው
በሚያስችል ሁኔታ ተካተዋል።
ሀ.የጎንደር ባህላዊ ጭፈራ፡- በጎንደር አካባቢ በሰሜንና በደቡብ ጎንደር የሚጨፈሩ አጨፋፈሮች በአብዛኛዉ ደረትን ወደ ላይ
በመመንጠቅ፣ ትክሻን በመደሰቅ፣ ትከሻን በማርገብገብ፣ አንገትን በመሰክሰክ እግርን በማንሳትና በማስቀመጥ በመዝለል እጅን
በማርገብገብ ወዘተ…. የሚጨፈሩ ናቸው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያዩ የጎንደርን አጨፋፈር የሚያሳይ ስዕል ወይም ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 የጎንደር የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ በመጠየቅ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ
 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች ክብ ሠርተው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የጎንደር ባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች እንዲያቀርቡ ማድረግ
 በቀረበው ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
o ይህ የጎንደር ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ
አስረዱ
 ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረግ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር

77 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል


ለ.የጎጃምባህላዊጭፈራ፡- ጎጃም አካባቢ በምዕራብና በምስራቅ ጎጃም የተለያዩ ጭፈራዎች ሲኖሩ አጨፋፈሮች በአብዛኛዉ ሙሉ
ሰዉነትን በማንቀጥቀጥ፣ ትክሻን በመርገጥ፣ /በመደሰቅ/ በመዝለል እግርን ወደ ፊትና ኋላ በማንሳትና በማስቀመጥ በሁለት እግር
በመርገጥ የሚጨፈሩ ናቸው።
የማስተማሪያ መሳሪያዎች፡- የተለያዩ የጎጃምን አጨፋፈር የሚያሳይ ፖስተር ወይም ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ውጭ ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 የጎጅም የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ በመጠየቅ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ
 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች በየቦታቸው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የጎጃም ባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች እንዲያቀርቡ ማድረግ
 በቀረበው ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
o ይህ የጎጃም ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ አስረዱ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል
ሐ. በአማራ ሰሜን ሽዋ ባህላዊ ጭፈራ፡-ሰሜን ሸዋ አካባቢ አጨፋፈር አብዛኛዉ ከእርሻ ስራ ጋር የተያዘ ሲሆን በትከሻ ወደታች
በመርገጥ በአንገት አብዛኛዉ በእግር አስተራረስን የእህል አወቃቅን አስተጫጨድን ወዘተ በሚያሳ ይሁኔታ ይጨፈራሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦የተለያዩ የሰሜንሽዋን አጨፋፈር የሚያሳይ ፖስተር/ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ውጭ ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 የሰሜን ሽዋ የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ
 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች በየቦታቸው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የሰሜንሽዋባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች እንዲያቀርቡ ማድረግ
 በቀረበው ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ

78 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

o ይህ የሰሜን ሽዋ ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ
አስረዱ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ በመመለስ ለሚቀጥለው ፔሬድ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል
ተግባር 5፡- የፕሮጀክት ሥራ መልስ
በአካባቢያችሁ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎች ውስጥ አንዱን በመምረጥ በቡድን ተለማምዳችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ በተግባር
አቅርቡ?
መልስ፡- ይህ ተግባር በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎችና ዞኖች ባህላዊ አጨፋፈር ላይ ያተኮረ በመሆኑ ተግባሩ ትምህርት ቤቱ
ባለበት አካባቢ ብቻ የተወሰነ ስለሚሆን መምህሩ የፕሮጀክቱን ሥራ አካባቢውን መሰረት እንዲያደርጉና እንዲወስኑት በመንገር
ማሰራት ይኖርበታል።
መ. የወሎ ባህላዊ ጭፈራ፡- ወሎ አካባቢ ማለትም በሰሜንና በደቡቡ ወሎ አካባቢ የተለያዩ ጭፈራዎች ሲኖሩ በትከሻ የሚሰሩ በአንገት
የሚሰሩ፣ በእጅ የሚሰሩ፣ በመቀመጥና በመነሳት እንዲሁም በመዝለል ሁለት እግር በማንሳት አንድ እግር በማንሳት እና በማስቀመጥ
የሚጨፈሩ ብዛት ያላቸው ጭፈራዎች ይገኛሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦የተለያዩ የወሎ ባህላዊን አጨፋፈር የሚያሳይ ፖስተር/ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ውጭ ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 የወሎ ባህላዊ የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ
 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች በየቦታቸው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የወሎ ባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች እንዲያቀርቡ ማድረግ
 በቀረበው ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
o ይህ የወሎ ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ አስረዱ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል
ሠ. የአዊ ባህላዊ ጭፈራ፡- የአዊ አካባቢ የተለያዩ ጭፈራዎች ሲኖሩ በአብዛኛዉ የዳሌ ከወገብ በታች የሚሰሩስራዎች በትክሻ የሚሰሩ
እግርን በማንሳት በመንቀሳቀስ ይጨፈራሉ፡
መርጃ መሳሪያዎች፦የተለያዩ የአዊን አጨፋፈር የሚያሳይ ፖስተር ወይም ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ

79 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

 የአዊን የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ


 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች በየቦታቸው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የአዊ ባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች ከሰውነት ማጎልመሻ ጋር አቀናጅተው እንዲያቀርቡ ማድረግ
 በቀረበው ባህላዊ ጭፈራ ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
o ይህ የአዊ ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ አስረዱ
 ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረግ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል
ረ. የዋግ ህምራ ባህላዊ ጭፈራ፡- የዋግ ህምራ አካባቢ አጨፋፈር አብዛኛዉ የትከሻ ስራ ሲሆን ትከሻን
በሪትሙ ልክ ወደታች በመርገጥ በአንገት የደረት መደስቅ እጅን ወደላይና ታች በማድረግ ይጨፈራሉ።

መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያዩ የዋግ ህምራ አጨፋፈር የሚያሳይ ፖስተር/ ቪዲዮ


የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 የዋግህምራ የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ
 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች በየቦታቸው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የዋግህ ህምራ ባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች ማሳየት
 በቀረበው ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
o ይህ የዋግ ህምራ ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ
አስረዱ
 ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረግ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
 የሰውነት ማቀዝቀዣ እንቅስቃሴና የሰውነት ማሳሳብ እንቅስቃሴ በማሰራት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል

80 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

ሰ. በአማራ ክልል የከሚሴ ባህላዊ ጭፈራ፡- በአብዛኛዉ ከሚሴና አካባቢዉ የሚጨፈሩ ጭፈራዎች በሴትም በወንድም ሲሆኑ የፍቅር
ጨዋታዎች ላይ የሚሰሩ ሲሆኑ እጅን በመዘርጋት እግርን በማቀያየር በማንሳትና በማስቀመጥ እደ ማንከስ አይነት በመቀመጥና
በመነሳት በመዝለል ይጨፈራሉ።
መርጃ መሳሪያዎች፦የተለያዩ የኬሚሴን አጨፋፈር የሚያሳይ ፖስተር ወይም ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
 የኬሚሴ የአጨፋፈር ሂደትን የሚያወቁ ካሉ እንዲናገሩ/እንዲያሳዩ ማድረግ
 ስለ አጨፋፈሩ ሂደት ከሚዲያው ማሳየትና አጭር ማብራሪያ መስጠት
 የክፍሉን ልጆች በቡድን ከፍሎ ቡድኖች በየቦታቸው እንዲቆሙ ማድረግ
 በቡድናቸው መሰረት ያዳመጡትንና ከሚዲያው ያዩትን እርስ በርስ እየተጋገዙ እንዲለማመዱ ማድረግ።
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ሁሉም እንዲሳተፉ ማበረታታት
 የተለማመዱትን የኬሚሴ ባህላዊ ጭፈራ ለሌሎች ቡድኖች እንዲያቀርቡ ማድረግ
 በቀረበው ባህላዊ ጭፈራ ላይ ከሌሎች ቡድኖች እርምት እንዲሰጥ ማድረግ
 ተጨማሪ የክፍለ ጊዜው ማጠቃለያ ጥያቄዎችን መጠየቅ
o ይህ የኬሚሴ ባህላዊ ጭፈራ ጠቀሜታው ምንድን ነው፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነትስ
አስረዱ
 ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ማድረግ
 የተጠየቁትን ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል
ተግባር 10፡- የፕሮጀክት ሥራ መልስ
በተግባር አራት ላይ የሰራችኋቸውን በአካባቢያችሁ የሚዘወተሩ ባህላዊ ጭፈራዎችን ሁሉንም የክፍሉን ተማሪዎች በማሳተፍ ልምምድ
አድርጋችሁ ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አቅርቡ?
መልስ፡- ይህ ተግባር በተግባር አምስት የሰሩትን ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ የሚያቀርቡት በመሆኑ በክፍል ውስጥ ያሳዩትን ጊዜ
በመስጠት የበለጠ በየ ቡድኑ እንዲዘጋጁበት በማድረግ የባህል ቀን በሚል ስያሜ ማሰራትይኖርበታል።

7.3 የባህላዊ ጨዋታዎች ምንነት (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማዎች፡- ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን ባህላዊ ጨዋታዎች ይዘረዝራሉ።
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን ባህላዊ ጨዋታዎች በተግባር ያሳያሉ።
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች ባህላዊ ጭፈራዎች ከሰውነት ማጎልመሻ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይገልፃሉ።
 በአማራ ክልል የሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎችን ባህላዊ ጨዋታዎች ያደንቃሉ።

81 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

የባህል ስፖርት ሰዎች በሚያደርጓቸው ቤተሰባዊ፤ ጉረቤታዊ፤ መንደራዊ፣ ወረዳዊ፣ሀገራዊ፤ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ግንኙነት
አማካኝነት አካላዊ፣ መንፈሳዊ፣ አዕምሮአዊና ስነ-ልቦናዊ እርካታ ለማግኘት የሚያደርጉት ፉክክርና ጨዋታ ነው። በአሁኑ ወቅት
በሀገራችን በገጠር የሚኖረው አርሶ አደርና አርብቶ አደሩ አካላዊ ብቃቱን ከሚያዳብርባቸውና መንፈሳዊ እርካታ ከሚጎናፀፍባቸው
እንዲሁም ባህሉን ልምዱን ወጉና ማዕረጉን ከሚገልፅባቸው ውስጥ አንዱ የባህል ስፖርት ጨዋታ ነው። በዚህም ክፍል በአካባቢያችሁ
ያሉና የሚታወቁትን ባህላዊ ጨዋታዎች አጨዋወታቸውን የምናውቅበት ይሆናል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ ባህላዊ ጨዋታን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ ፖስተሮች፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከባህላዊ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ባህላዊ ጨዋታ ምንነት ቀደምት እውቀታቸውን ለማወቅ ጥያቄ በመጠየቅ መልስ እንዲመልሱ ማድረገ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ተግባር-10 መስጠት ባህላዊ ጨዋታ ምንነት፣ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያላቸውን
ግንኙነት እና በአካባቢያቸው የሚገኙ ባህላዊ ጨዋታዎችን ዘርዝሩ የሚሉትን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
 ለሁሉም ለተጠየቁ ጥያቄዎች አጠር ያለ ማብራሪያ መስጠት
 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
 የተጠየቁትን ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ ተግባር አንድን በመስጠት የዕለቱን ትምህርት
ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ
የተግበር 11.መልስ
1. ባህላዊ ጨዋታ ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፡- ባህላዊ ጨዋታ የአንድ ህብረተሰብ ልዩ ልዩ ማህበራዊ መተዳደሪያ ስርዓቶችን የሀዘንና የደስታ ስሜት መግለጫ የሆኑ ልዩ ልዩ
ስነ ቃሎችን፣ ማንነትን፣ አካባቢንና አልባሳትን ያካተተ ሲሆን ሲጠቃለል ባህላዊ ጨዋታ የህዝቦች ማህበራዊ ህይወት ማሳያና የማንነት
መገለጫ ነው።

2. ባህላዊ ጨዋታ ከሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ጋር ያለው ግንኙነት ምንድን ነው አብራሩ?


መልስ፡- መልስ፡- ባህላዊ ጨዋታ መሰረታዊ ዓላማዎቹን ስንመለከት ሁሉንም የሰውነት ክፍሎች በጨዋታው በማካተት መዝናናትን፣
መደሰትን፣ አካልን፣ አዕምሮን እና ማህበራዊ ግንኙነትን ማዳበር ነው። በመሆኑም የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እንደ ጨዋታው
ሁሉሁሉንም ዓላማዎች የሚያጠቃልል ነው። ስለዚህ ባህላዊ ጨዋታዎችን በማከናወን የሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት ሊያመጣው
የሚገባውን ዓላማ ልናሳከ እንችላለን ማለት ነው። በሌላ መንገድ ባህላዊ ጨዋታዎች ለሰውነት ማጎልመሻ ትምህርት እንደመነሻነትም
ያገለግላሉ።
3. በአካባቢያችሁ የምታውቋቸውን ባህላዊ ጨዋታዎች ዘርዝሩ?

መልስ፡- ይህ ጥያቄ እንደየ አካባቢው የተለያየ መልስ ሊሰጥ የሚችል በመሆኑ መምህሩ በአካባቢው የተለመዱትን ጨዋታዎች
በመሰብሰብ ሊገልፅላቸው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪ እንደ ባህልዊ ጭፈራዎች በጥናት መልክ የተቀመጠ ነገር ስለሌለው በአካባቢው
በመወሰን ማስረዳት/ማቅረብ ይቻላል።

82 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

7.4 በአማራ ክልል የሚገኙ ባህላዊ ጨዋታዎች (- ክ/ጊዜ)


ዝርዝር ዓላማ ተማሪዎች ይህን ትምህርት ከተማሩ በኋላ፡-
 በአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች ይዘረዝራሉ።
 በአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች በተግባር ያሳያሉ።
 በአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎችን ከሰውነት ማጎልመሻ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ይገልፃሉ።
 በአካባቢያቸው የሚገኙ የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎች ያደንቃሉ።
የባህል ጨዋታ ሰዎች በሚያደርጓቸው ቤተሰባዊ፤ ጉረቤታዊ፤ መንደራዊ፣ ወረዳዊ፣ ሀገራዊ፤ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ ግንኙነት
አማካኝነት አካላዊ፣ መንፈሳዊ፣ አዕምሮአዊና ስነልቦናዊ እርካታ ለማግኘት የሚያደርጉት ፉክክርና ጨዋታ ነው። በአሁኑ ወቅት
በሀገራችን በገጠር የሚኖረው አርሶ አደርና አርብቶ አደሩ አካላዊ ብቃቱን ከሚያዳብርባቸውና መንፈሳዊ እርካታ ከሚጎናፀፍባቸው
እንዲሁም ባህሉን ልምዱን ወጉና ማዕረጉን ከሚገልፅባቸው ውስጥ አንዱ የባህል ስፖርት ጨዋታ ነው። በዚህም ክፍል በአካባቢያችሁ
ያሉና የሚታወቁትን ባህላዊ ጨዋታዎች አጨዋወታቸውን የምናውቅበት ይሆናል።

7.4.1 የገበጣ ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


የገበጣ ጨዋታ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ 6 ኛውና በ 7 ኛው ክፍለ ዘመን በሀገራችን ይዘወተር እንደነበር ታሪክ ያስረዳል። ከዚህ በፊት
በአፄ ቴወድሮስ ዘመነ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ ከገቡት እንግሊዛውያን መካከል የአፄ ቴወድሮስ የቅርብ ጓደኛ የነበረው እንደገለፀው
በበጌምድር በራስ አሉላ ካምፕ ውስጥ የነበሩት ወጣቶች በከፍተኛ ስሜት የገበጣ ጨዋታ ይጫወቱ እንደነበር ያስረዳል።
ሀ. የገበጣ ላሜ ወለደች ጨዋታ፡- የላሜ ወለደች ጨዋታ በሀገራችን ከሚተገበሩ ባህላዊ ጨዋታዎች አንዱ ሲሆን የአጨዋወቱም
ህግ እንደየ አካባቢው የተለያየ ነው። በመሆኑም በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተቀመጠው የገበጣ ጨዋታ በብዙ መልኩ የተለየ ስለሆነ እንደ
አካባቢያችን ሁኔታ ልንጫወተው እንችላለን።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የተለያዩ የጉድብ ዝላይን የሚያሳይ ፓምፕሌት፣ ስዕል ወይም ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከክፍል ውሰጥ ወይም ከክፍል ወጥተው ወደ ሜዳ እንዲሄዱ ማድረግ
• የላሜ ወለደች አሰራርን በአካባቢያቸው የሚያወቁትን እንዲያሳዩ መጠየቅ
 ስለ ጨዋታው የአሰራር ሂደት አጭር ማብራሪያ መስጠት
• ሁለት ለሁለት ሆነው እንዲቀመጡ ማድረግ
• ጠጠሮችን በባለ 12 ጉድጓድ ውስጥ አራት አራት አድርገው በእያንዳንዱ ማስቀመጥ
• በእጣ በወጣላቸው መሰረት ከራሳቸው ቤት ጀምረው ከአንዱ ጉድጓግ ጠጠር አንስተው እንዲደረድሩ ማድረግ
• ባዶ ቦታ ላይ የመጨረሻው ጠጠር ካረፈ ለተረኛው መልቀቅ ነገርግን ሶስት ጠጠር በተቃራኒ ጉድጓድ ኖሮ አራተኛ
በመጨረሻው ጠጠር ካስቀመጥን አፍሶ ለራስ ማድረግና በዚያው ጨዋተውን መቀጠል
• በዚህ መልኩ ቀጥለው መጨረሻ ላይ ብዙ ጠጠር ያለው አሸናፊ ይሆናል
 የተግባር እንቅስቃሴውን በሚተገብሩበት ወቅት ማበረታታት የአሰራር ሰህተቶች ካሉ እርስ በርስ እንዲተራረሙ ማድረግ
 ከሰሩት ተግባር አንፃር ተጨማሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እንዲመልሱ ማድረግ
 የተጠየቁትን በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ተዘጋጅተው እንዲመጡ መንገር

83 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ ተግባሩን እንዲያሳዩ በማድረግ መከታተል


ለ. የባለ 12 ጉድጓድ ቅንጭቦሽ ባህላዊ ጨዋታ ምንነት፡- የቅንጭቦሽ ገበጣ ጨዋታ ውድድር በሁለት ተወዳዳሪወች መካከል የመጫወቻ
ገበጣውን በመሀከላቸው በማስቀመጥ የጨዋታ ህግ በሚፈቅደው መሰረት በየተራ በየጉድጓዳቸው ውስጥ ያሉትን ጠጠሮች አፍሶ
በመነሳት በየጉድጓዶቹ ላይ አንዳንድ ጠጠር በመዘርዘር በተጋጣሚ ቤት ውስጥ ውግ በመውጋት በመጫወቻ ጉድጓዶቹ ውስጥ ያሉትን
ጠጠሮች በውግ ላይ በማከማቸት የቤትና የጠጠር ብልጫ እንዲኖር በማድረግ አሸናፊ ለመሆን የሚደረግ ባህላዊ ጨዋታ ነው።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የባለ 12 ጉድጓድ ገበጣ ባህላዊ ጨዋታን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ፖስተሮች፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከባህላዊ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ገበጣ ባለ 12 ጉድጓድ ባህላዊ ጨዋታቀደምት እውቀታቸውን በመጠየቅ ማወቅ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ስለ አጨዋወቱ አጠር ያለ ማብራሪያ መስጠት
 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
 የተጠየቁትን ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ክፍለ ጊዜ ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ ተግባር አንድን በመስጠት የዕለቱን ትምህርት
ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ

7.4.2 ገና ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


ገና በትክክል በሀገራችን መቼ እንደተጀመረ በፅሁፍ የተደገፈ መረጃ ባይገኝለትም ከክርስቶስ ልደት በፊት ይዘወተር እንደነበር በአፈታሪክ
ይነገርለታል። ገና በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ይዘወተር እንደነበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ባህላዊ
በሆነ ሁኔታ እየተተገበረ ያለ ጨዋታ ነው።
•• ሀ. የገና አካባቢያዊ ባህላዊ ጨዋታ
መርጃ መሳሪያዎች፦ የገና ባህላዊ ጨዋታን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ ፖስተሮች፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከገና ባህላዊ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ገና ባህላዊ ጨዋታ ምንነት ቀደምት እውቀታቸውን በመጠየቅ ማወቅ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ስለ ገና በታህሳስ የገና በዓል ጊዜ የሚከናወነውን አጨዋወቱን አጠር ያለ ማብራሪያ መስጠት
 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
 ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ በመስጠት የዕለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ
ለ. ዘመናዊ የገና ጨዋታ
መርጃ መሳሪያዎች፦የገና ባህላዊ ጨዋታን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ፖስተሮች፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-

84 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

 ከገና ባህላዊጨዋታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ገና ዘመናዊ ጨዋታ ምንነት ቀደምት እውቀታቸውን በመጠየቅ ማወቅ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ስለ ገና በዘመናዊ መልክ በውድድር መልክ የሚከናወነውን አጨዋወቱን አጠር ያለ ማብራሪያ
መስጠት
 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
 ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ በመስጠት የዕለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ።
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ

7.4.3 የትግል ባህላዊ ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


ትግል /ግብግብ/ በሀገራችን በጣም ተስፋፍቶ ይገኝ የነበረው በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት መሆኑ ይነገራል። ለዚህም ማስረጃው
በአፄ ቴዎድሮስ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የነበሩትን የእንግሊዝ ተወላጆች የኢትዮጵያውያንን የአካል ጥንካሬና ጀግንነት ማወቅና ማየት
አለባቸው በማለት በራሳቸው ዳኝነት እንግሊዛውያንን ከኢትዮጵያውያን ጋር ያታግሏቸው እንደነበርና ለአሸናፊ ኢትዮጵያውያንም
ሰጋር በቅሎ ከነሙሉ እቃው ፤ ጎራዴና ጋሻ ፤ ሙክትና ሌሎችንም ሽልማቶችን በወቅቱ ይሸልሙና ይሰጡ እንደነበር ይነገራል።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የትግል ባህላዊ ጨዋታን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ ፖስተሮች፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከትግል ባህላዊ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ትግል ባህላዊ ጨዋታ ምንነት ቀደምት እውቀታቸውን በመጠየቅ ማወቅ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ስለ ትግል አጨዋወቱን አጠር ያለ ማብራሪያ መስጠት
 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት
 ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ በመስጠት የዕለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፡-የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ

7.4.4 የፈረስ ሽርጥ ጨዋታ (- ክ/ጊዜ)


የፈረስ ሽርጥ እንደ አሁኑ ስልክም ሆነ ሬዲዮ ባልነበረበትና ባልተስፋፋበት ጊዜ ፈረስ ጭኖ በግልቢያ መልዕክት ለማድረስ ወይም
ከጠላት ለመጠንቀቅ ይረዱ የነበሩት ከዘመኑ ፈጣን መላላኪያ አንዱ በፈረስ ጋልቦ በመድረስ ነበር።
መርጃ መሳሪያዎች፦ የፈረስ ሸርጥ ባህላዊ ጨዋታን የሚያንፀባርቁ ስዕሎች፣ፖስተሮች፣ ቪዲዮ
የመማር ማስተማር ቅድም ተከተል፡-
 ከፈረስ ሸርጥ ባህላዊ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ሁኔታ በሰፈራቸው ከሰሯቸው ስራዎች ውሰጥ የተወሰኑ ተማሪዎች እንዲናገሩ ማድረግ
 ስለ ፈረስ ሸርጥ ባህላዊ ጨዋታ ምንነት ቀደምት እውቀታቸውን በመጠየቅ ማወቅ
 በሚመልሱበት ወቅት ሁሉም ተማሪዎች እንዲሳተፉ ማበረታታት
 ከሚመልሱት መልስ በመነሳት ስለ ትግል አጨዋወቱን አጠር ያለ ማብራሪያ መስጠት

85 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ


የኢትዮጵያ ባህላዊ ጭፈራና ባህላዊ ጨዋታዎች(20 ክ/ጊዜ)
ምዕራፍ 7

 ከተሰጠው ማብራሪያ በመነሳት ያልገቧቸውን እንዲጠይቁ ተጨማሪ እድል መስጠት


 ጥያቄ በመመለስ ለሚቀጥለው ሰርተውት የሚመጡትን ጥያቄ በመስጠት የዕለቱን ትምህርት ማጠናቀቅ
ክትትልና ግምገማ፦ የቃል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ማረጋገጥ

የምዕራፉ ማጠቃለያ መልመጃ


መመሪያ አንድ፡- የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካነበባችሁ በኋላ ትክክል የሆነውን እውነት ትክክል ያልሆነውን ሐሰት በማለት መልስ ስጡ
1. ጭፈራ በአንድ በተወሰነ ማህበረሰብ ባህላዊና አካባቢያዊ ድንበር ውስጥ የታጠረና የማህበረሰቡን ማንነት የሚያሳይ ነው።
2. ባህል በራሱ የአንድ ሀገር ህዝብ ማንነት መገለጫ ሊሆን አይችልለም።
3. ባህላዊ ጭፈራዎች ሁሉ ቋሚ ህግና ደንብ የሌላቸው በመሆኑ በተወዳዳሪዎች ላይ ቅራኔ ያስከትላሉ።
መመሪያ ሁለት፡- ለሚከተሉት ጨዋታዎች አጭር መልስ ስጡ
1. ባህላዊ ጨዋታ ዓላማው ምንድን ነው አስረዱ?
2. ከተማራችሁት ውጭ ሌሎችን በክልላችሁ ያሉትን ባህላዊ ጭፈራዎችና ጨዋታዎችን ለይታችሁ ለክፍል ጓደኞቻችሁ አቅርቡ?
3. የላሜ ወለደች ጨዋታ መሰረታዊ ጠቀሜታው ምንድን ነው አብራሩ?
4. የገና ባህላዊ ጨዋታና የገና ባህላዊ ስፖርት ልዩነቱ አስረዱ?

መልስ

መመሪያ አንድ መልሰ

1. እውነት 2. ሐሰት 3. እውነት


መመሪያ ሁለት መልሰ

1. የባህላዊ ጨዋታ ዋነኛ ዓላማው በሚጫወቱት መካከል የባህል የወግ እና የአካባቢውን ልማድ በማስተዋወቅ እና
የአንድ ሀገር ወይም ህዝብ መገለጫ እንደመሆኑ መጠን ህብረተሰቡ በዕለት ተዕለት የሚከዉነዉን እንቅስቃሴ
የሚተገብርበት የሚያሳይበት ኩነት ማለት ነዉ፡፡ በጨዋታውምመተሳሰብን፣ መረዳዳትን፣ ለሌላው ማሰብን፣ እና
ሌሎችንም ለማሳደግ ይጠቅማል፡፡
2. የዚህ ጥያቄ መልስ እንደልጆች የመረጃ አሰባሰብ ሁኔታ ሊለያይ ስለሚችል በተቻለ መጠን መምህሩ የተለያዩ ባህልላዊ
ጭፈራዎችንና ጨዋታዎችን በማሰባሰብ ሊያስተገብር ይችላል፡፡
3. የላሜ ወለደች ጨዋታ መሰረታዊ ጠቀሜታው የመጀመሪያው የአካባቢውን ባህላዊ ጨዋታ የአጨዋወት ስልት
መለየት ሲሆን ሁለተኛው አገር አቀፍ የሆነውን የገበጣ ጨዋታን ለማወቅና ለመጫዎት እንደመነሻነት እንዲያግዝ
የተዘጋጀ መሆኑ ነው፡፡
4. የገና ባህላዊ ጨዋታ የምንለው ከህዳር እስከ ታህሳስ ድረስ ባህላዊ በሆነ ሁኔታ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ
የሚተገበርና የራሱ የሆነ ቋሚ ህግ፣ የሜዳ ክልል፣
የአጨዋወት ስርዓት የሌለው ሲሆን የገና ባህላዊ ስፖርት ግን አገር አቀፍ በሆነ ሁኔታ የራሱ የሆነ ቋሚ ህግ፣ የሜዳ ክልለ እና
የአጨዋወት ስርዓት ያለው መሆኑ እንዲሁም የመጫወቻ የጊዜ ገደብ የሌለው ነው፡፡

86 ጤናና ሰውነት ማጎልመሻ 6 ኛ ክፍል የተማሪ መጽሐፍ

You might also like