You are on page 1of 3

ሐዋርያዊ መልሶች - Apostolic Answers

ተከታታይ መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት መስጫ አጭር አጋዥ ጽሑፍ - 1

መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ስል ዶግማ የሆነውን ትምህርታችንን ወይም ሃይማኖታችንን ማለቴ ሲሆን ይህም የራሱ የእግዚአብሔር
መገለጥ ወይም ራሱ የሰጠን እንጂ በሰዎች የተጀመረ አይደለም። ይሁዳ በመልእቱ እንደሚለው፡ “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ የተሰጠ
ሃይማኖት”(ይሁዳ 3) ፤ እንዲሁ ጳውሎስም “በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችሁዋለሁ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ
ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም”(ገላ 1 ፡ 11-12) እንዳለው። ታድያ ግን የሚቀድመው ይህንን
ትምህርት(እምነት ወይም ሃይማኖት) የሰጠን ይህ አምላክ ማን ነው..?? የምርስ ፈጣሪ አለን..?? የሚለው ነውና ከዚህ በመነሳት
ትምህርታችንን የምንጀምር ሲሆን ጠቅለል ያለው ትምህርታችን በአጭሩ ከታች የዘረዘርኳቸውን ያጠቃልላል፡
- የፈጣሪ መኖር
- ያ ፈጣሪ የክርስቲያኖች አምላክ ቅድስት ሥላሴ መሆኑ
- መሠረታዊ የክርስትና ትምህርትን ለምን እንማራለን
- የክርስትና ትምህርት ምንጭ(ቅዱስ ትውፊት)
- መጽሐፍ ቅዱስ
- መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ..??
- ምስጢረ ሥላሴ
- ነገረ ክርስቶስ
- ነገረ ድኅነት
- ነገረ ቤተ ክርስቲያን
- ነገረ ፍጻሜ(ትንሳኤ ሙታን)
እነርዚህ አርእስት አንዳንዶቹን አጠር ያለ ነገር የምናስቀምጥባቸው ሲሆን አንዳዶቹ ግን ሌሎች ሰፋፊ ንኡስ አረስትን የያዙ ሊሆኑ ይችላሉ..
አሁን ቀጥታ ወደ ፈጣሪ መኖር(ኃልዎተ እግዚአብሔር) ትምህርት እንለፍ

ኃልዎተ እግዚአብሔር
ከአምላክ መኖር አለመኖር ጋር በተያያዘ የተለያዩ እሳቤዎች የሚሰጡ ሲሆን ከእርዚህም ዋናዎቹን እንመልከት፡

Theism(ቲዝም): ይህ በአምላክ መኖር የሚታመን እሳቤ ነው። ያ አምላክ አንድ ነው ወይስ ብዙ ከሚለው ጋር ተያይዞ ወይም ደግሞ
ከፍጥረቱ ጋር ካለው ግንኙነት አንጻር ቲዝም ውስጥ ራሱ የተለያዩ ክፍሎች ሊኖሩ ይችላሉ.. ለምሳሌ እንደ ክርስቲያኖች፣ አይሁዳውያን
እና ሙስሊሞች ያሉት በአንድ አምላክ መኖር የሚያምኑ ሲሆኑ monotheist(ሞኖቲስት) ይባላሉ። ሌሎች ደግሞ እንዲሁ በብዙ
አማልክት የሚያምኑ አሉ እነርሱም polytheist(ፖሊቲስት) ይባላሉ። ሌሎች ደግሞ በአምላክ መኖር ያምኑና ግን ደግሞ ያ አምላክ
ፍጥረትን ፈጠረና ከዚያም ራሱን ከፍጥረቱ ለየ ወይም አራቀ.. አሁን ፍጥረትን እያስቀጠለ ያለው እርሱ አይደለም ይላሉ.. ልክ እንደ ሰዓት
ሰራተኛው.. ሰዓትን የሚሰራ ሰው አንዴ ሰዓቱን ካበጃጀው በኋላ ሰዓቱ በራሱ እንደሚሽከረከር እንዲሁ ፈጣሪም አንዴ ዓለምን ካበጃጀ
በኋላ ዓለም በራሷ ትቀጥላለች አምላክ አያስፈልጋትም የሚሉ ናቸው.. እነዚህም deist(ዲስት) ይባላሉ። እነዚህ ሁሉም በአምላክ መኖር
የሚያምኑ በቲዝም ስር ያሉ የተለያዩ እምነቶች ናቸው። ስለዚህም በtheism(ቲዝም) ሥር እስካሁን 3 እምነቶችን አይተናል፡
- Monotheism(ሞኖቲዝም) ፦ የአንድ አምላክ መኖር እምነት - አማኞቹ Monotheist(ሞኖቲስት) ይባላሉ።
- Polytheism(ፖሊቲዝም) ፦ የብዙ አማልክት መኖር እምነት - አማኞቹ Polytheist(ፖሊቲስት) ይባሉ።
- Deism(ዲዝም) ፦ ፈጥሮ ዞር ያለ አምላክ መኖር እምነት - አማኞቹ Deist(ዲስት) ይባላሉ።
እነርዚህ ሦስቱ ከዓለማት(universe) ከፍ ያለ አምላክ ወይም አማልክት እንዳለ ሲያምኑ pantheist(ፓንቲስት) የሚባሉ ደግሞ አሉ..
እነርዚህም አምላክ ከዓለም(ዩኒቨርስ) ጋር አንድ ነው.. ዓለም ራሱ ነው አምላክ የሚሉ ናቸው.. ይህም ማለት ዓለም ራሱን በራሱ ፈጠረ
አይነት ነገር። ለምሳሌ እህታለም አንቺ ራስሽን ጸነስሽ እንደ ማለት ነው። ምንም ነገር ካለመኖር ወደ መኖር ራሱን ፈጥሮ ብቅ ሊል ግን
እንደማይችል እሙን ነው። እምነቱ pantheism(ፓንቲዝም) ይባላል።
Atheism(ኤቲዝም)፡ ይህ ደግሞ አምላክ የለም የሚል እሳቤ ነው። ምናልባት ሁለት አይነት ኤቲዝም ሊኖር ይችላል.. አምላክ
በፍጹም የለም የሚል(strong atheism) እና ለአምላክ መኖር በቂ ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም የሚል(weak atheism)። ኤቲስቶች
አምላክ ላለመኖሩ ምንም ዓይነት ማስረጃ አያቀርቡም ብሎ ለመናገር ያስደፍራል.. አምላክ አለመኖሩን የሚያሳዩት “አምላክ ለመኖሩ
ምንም ማስረጃ የለም” በሚል እንጂ እነርሱ ራሳቸው አምላክ አለመኖሩን ተመራምረው ደርሰውበት አይደለም። አምላክ ለመኖሩ ማስረጃ
ባይኖር ራሱ ማስረጃ ስላልቀረበ በቃ አምላክ የለም ማለት ነው ብሎ መደምደም argument from ignorance የተሰኘ ተፋልሶ(fallacy)
ነው። ለምሳሌ አንድ የሆነ ሰው ተገደለ እንበልና ይህንን የምታነበው ወዳጄ አንተን “ይህንን ሰው እንዳልገደልከው ማስረጃ ስላላቀረብክ
ገዳዩ አንተ ነህ” ብትባል ማለት ነው። እንዳልገደልክ ማስረጃ ማቅረብ ባትችል ራሱ በቃ ገድለሃል ማለት አይደለም። በዚኛው በኩልም
ደግሞ ኤቲስቶች አምላክ እንደሌለ ማሳየት ስለማይችሉ አምላክ አለ ማለትም አይደለም.. ይህም ተመሳሳይ ተፋልሶ ነው። ስለዛ በሁለቱም
በኩል ማስረጃዎቻቸውን ሊያቀርቡ ይገባል።
ከዚ ውጪ ግን ከቀድሞውም ዘመን ጀምሮ ለአምላክ አለመኖር ማስረጃ ተብሎ የሚሰጠው ዓለም ላይ የሚታዩ ክፋቶች ናቸው። ዓለም
ላይ ክፋቶችን የምናየው አምላክ ስለሌለ ነው.. አምላክ ቢኖር ክፋቶችን ያስቆም ነበር ለምሳሌ ረሃብ፣ ጥማት፣ ግድያ፣ መደፈር እና ወዘተ..
ይህ በፍልስፍናው እና በቴዮሎጂው ዓለም the problem of evil ተብሎ ይጠራል። እውን ክፋቶችን ማየታችን ግን አምላክ እንደሌለ
ያሳያል..?? ወይም ደግሞ ለኤቲስቶች ማስረጃ ይሆናል..?? በፍጹም.. ለምሳሌ ያህል እስቲ ይህ አሳብ አምላክ ላለመኖሩ እንደ ማስረጃ
ሊሰጥ የማይችልባቸውን የተወሰኑ ነጥቦችን ላስቀምጥላችሁ፡
- አምላክ ኖሮ ግን ደግሞ ክፋቶችን ማስቆም ባይፈልግስ..?? ለምን..?? ከተባለ ለምንም ምክንያት ይሁን ወላ ስለ ክርስቲያኖች
አምላክ እንደምንለው ፍቅር ሳይሆን ቀርቶም ይሁን ግን ደግሞ ክፋቶችን ማስቆም ሳይፈልግ ቀርቶ ቢሆንስ..?? ስለዛ የክፋቶች
መኖር ጭራሹኑ አምላክ የለም አያስብለውም። (እንዲህ ያለ የሙግት አሳብ የምናነሳው ኤቲስቶች ዋናው እሳቤያቸው ፍቅር
የሆነ አምላክ የለም የሚል ሳይሆን ጭራሹኑ አምላክ የለም የሚል ስለሆነ ነው። ታድያ ግን የክርስቲያኖች አምላክ ፍቅር ነው
ስለዚህም ከታች የተወሰነ ነገር እላችኋለው)

- አምላክ ኖሮ ግን ደግሞ ክፋቶች እንዳሉ እንኳን የማያውቅ ቢሆንስ..?? ስለዚህም ሁሉን አዋቂ ያልሆነ አምላክ ቢሆንስ
ያለው..??(ከላይ እንዳልኩት ይህን የሙግት አሳብ የምናቀርበው ኤቲስቶች ዋናው እሳቤያቸው ሁሉን አዋቂ አምላክ የለም
የሚል ሳይሆን ጭራሹኑ ምንም ዓይነት አምላክ የለም የሚል ስለሆነ ነው)

- ሌላው ደግሞ ክፋት ማየታችን አምላክ የለም የሚያስብል ከሆነ ለምሳሌ የተለያየ በሳይንስ ምርምር የማይደረስባቸው
ተአምራቶችስ ለአምላክ መኖር ማስረጃ አይሆኑም ወይ..?? ለምሳሌ በሕክምና አልድን ያለ በሽታ በጸሎት ሊድን ይችላል። ይሄ
ተአምር ነው።

እዚህ ላይ አንድ ነገር ልናስተውል ይገባል.. የክፋቶች መንስኤ ብዙውን ጊዜ ነጻ ፈቃድም ሊሆን ይችላል.. ለምሳሌ ሰው ነጻ ፈቃዱን
ተጠቅሞ የሚያደርጋቸው ነገሮች ወደ ጥፋት የሚያመሩት ይሆናሉ.. ስለዚህ ክፋቶች የእኛው ከእግዚአብሔር አሳብ የመራቅ ውጤት
ሊሆኑ ይችላሉ። አልያም ደግሞ አምላክ ከባድ ክፋት እንዳይፈጠር ቀላል ክፋትን ሊፈቅድ ይችላል። ለምሳሌ መብራት ሲጠፋ ይከፋናል
መቼስ.. እና እንደውም መብራት ኃይል ሰራተኞችን እንራገምም ይሆናል(ያው ባይገባም ትላለህ ሎል).. እና የመብራትን መጥፋት እንደ
ክፋት ያዙትና.. ግን ደግሞ መብራት ያጠፉብን ዋናው ምክንያታቸው መብራቱን ባያጠፉትና እንዲሁ ቢተዉት ሙሉ ከተማዋ ወይም
የእናንተ ሰፈር በኤሌክትሪክ ምክንያት የምትነድ ስለሆነ ቢሆንስ..?? ስለዛ ሙሉ ከተማው እንዳይጠፋ ሲባል ከብርሃን ተከልክለህ ጨለማ
ውስጥ እንድታልፍ ልትደረግ ትችላለህ.. አምላክም ከባድ ክፋቶች እንዳይፈጠሩ በአንጻሩ ቀላል የሆኑ ክፋቶችን ሊፈቅድ ይችላል። አዳም
በበደለ ሰዓት ከገነት ተባረረ.. ገነት የኃጢአተኞች መንደር ከምትሆን ጌታ ሰውን እስኪያድሰው ድረስ ከገነት ውጭ አድርጎ ያስጠብቀዋል፣
ወይም ደግሞ በኖኅ ዘመን የነበረው ነውር ቀጥሎ ሙሉ በሙሉ ምንም ዓይነት የፈጣሪን ስም የሚጠራ ሰው እንኳን እስኪጠፋ ድረስ
ምድር በኃጢአት እንዳትሸፈን ጥቂት ነፍሳትን አስቀርቶ ሌላውን በማጥፋት ያድሰዋል ስለዚህም በኋላ የሚመጣው ትውልድ ውስጥ
ጥቂት እንኳን የእግዚአብሔር ሰዎች ይገኙ ዘንድ። በእስራኤል ማኅበር ውስጥ በኃጢአት የጨቀየ በተለይ ጣዖትን እየሰራ የሚያመልክ
ሲገኝ እርሱ ተለይቶ እንዲገደል ይፈቅድ ይሆናል በዛ ሰው መለየት ማኅበሩ ከጣዖት አምላኪነት ሊተርፍ ይችላልና።
በትልቁ ልታሰምሩበት የሚገባው ነገር ግን እኛ ይህንን የምንለው እንደው መሆን የሚችሉ ነገሮችን ለማቅረብ ያህል እንጂ የእግዚአብሔር
አሳብ ጥልቅ ነው.. ትልቅ ክፋት ብናይ የእግዚአብሔርን አሳብ እንዲሁ በእኛ ትንሽ አእምሮ ተመራምረን ልንደርስበት አንችል ይሆናል..
እርሱ ግን ለፍጥረቱ የሚራራ አምላክ ፍቅር የሆነ አባት እንደሆነ እናምናለን። ነገሮችን ሁሉ በአመክንዮ እናውቃለን ማለት አንችልም..
ስለዚህ ጉዳይ ከታች ጥቂት ነገሮችን እላችሁዋለሁ።
Agnosticism(አግኖስቲሲዝም)፡ ይህ ደግሞ በአጭሩ አምላክ ይኑር አይኑር አይታወቅም የሚል ነው። ይህም ሁለት ዓይነት
ይኖረዋል አንዱ ማንም ሰው የፈጣሪን መኖር አለመኖር በፍጹም ሊያውቅ አይችልም የሚል ነው(strong agnosticism) ሌላው ደግሞ
ነገሩን ግላዊ ያደርገውና እኔ ይኑር አይኑር አላውቅም አያስጨንቀኝምም ሌላ ሰው ግን ምናልባት ሊያውቅ ይችላል የሚል ነው(weak
agnosticism)።

እውን ግን አግኖስቲኮቹ እንደሚሉት የአምላክ መኖር ሊታወቅ አይችልምን..?? ኤቲስቶቹስ እንደሚሉት ጭራሹኑ አምላክ የለምን..??
የምርም አምላክ ከሌለ ሕይወት ራሷ ተስፋ የሌለባት ባዶ ነው የምትሆነው። ሰዎች ከሌላው ምድር ላይ ከሚኖሩ ፍጥረት ተለይተን
“ለምን..??” ብለን እንጠይቃለን። “ማን ነን” “ለምን እና እንዴት ተፈጠርን..??” እኚህ ጥያቄዎች የሁላችንም ሲሆኑ አንዳንዶች በሚያሳዝን
ሁኔታ አምላክ የለም ሲሉ የእኛም አመጣጥ እንደው ድንገተኛ እንደሆነና ከዚያም እንደማንኛውም የምድር ነፍሳት ጠፍተን እንደምንቀር
ያስባሉ። ሰው ግን ተስፋ አለው.. የተፈጠረውም በአምላክ ነው አላማም አለው ለዘላለምም ይኖራል እንጂ ሞቶ አይቀርም። ከታች
ለአምላክ መኖር የተወሰኑ የሙግት አሳቦችን የምናቀርብ ይሆናል።

You might also like