Professional Documents
Culture Documents
FILES
FILES
ዲላ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ፤ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን ዋና አጥቢያ በዲላ ከተማ
ከፌዴራል አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር በአዋጅ 916/2008 መሠረት ህጋዊ ፍቃድ 001083 ከጳጉሜ 04/2010 ጀምሮ
በመቀበል፤ በዲላ ከተማ መንፈሳዊ አገልግሎት እያካሄደች ትገኛለች፡፡
ይሁንና ቤተ-ክርስቲያኒቱ በእነኚህ ዓመታት ለማምለኪያ ቦታ የለላትና መንስትንም በተደጋጋሚ የጠየቅን ቢሆንም ምላሽ
ያልተገኘ በመሆኑ በየጊዜ እየጨመረና እየናረ የመጣዉን የቦታ ኪራይ መሸከም ባለመቻሉ በአሁን ወቅት ወደ ግሏ የአምልኮ
አደራሽ ለመግባት በሚደረግ ጥረት ዙሪያ አደራሽና ቢሮዎችን ማሰሪያ ገንዘብ ስላጠረን፤ ከዚህ በታች በተዘረዘረ ሁኔታ መሠረት
ብድር እንድሰጠን በታላቅ አክብሮትና ትህትና እንጠይቃለን፡፡
1. የብድሩ ዓላማ፡- የቤተ-ክርስቲያኒቱ ማምለኪያ አደራሽ G+UPSTAIR; የልዩ ልዩ መንፈሳዊ ቢሮ BASEMENTwith full
concrete፤ የደቀመዝሙርነትና የመንፈሳዊ ልህቀት ፅንሰ-ሃሳብ ኮሌጅ B+G+3 የቢሮ ብዛት 12 ፤ለበለጠ መረጃ ፕላን ኮፒ
ተያይዞ ቀርቧል፡፡
2. የብድሩ መጠን፡- 5,000,000.00 በፊደል/ አምስት ሚሊዮን ብር ብቻ/፡፡
3. የክፍያ ዓመትና ሁኔታ፡- የባንኩ የእፎይታ ጊዜ ካለቀ በኋላ በየ 3 ወሩ እየተከፈለ በ 10 ዓመት የሚጠናቀቅ፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!!!
ግልባጭ
ለፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን
ለመንፈሳዊ ዘርፍ ጽ/ቤት
ዲላ
ከአስራት በወር ቢያንስ ከ 15,000- 25,000 በፊደል ከብር አስራ አምስት ሺ እስከ ሃያ አምስት ሲ ድረስ
ትሰበስባለች፡፡
ሌሎች ወጪዎች ተቀንሶ ከመባ በወር እስከ 10,000 በፊደል እስከ አስር ሺ ድረስ ትሰበስባለች፡፡
ከፍቅር ስጦታ በወር እስከ ብር 15,000 በፊደል እስከ ብር አስራ አምስት ሺ ድረስ ታገኛለች፡፡
ሌሎችም አማራጮች በመጠቀም ብድሩን ለመመለስ በቂ ገቢ ይኖራታል፡፡
ከሁሉ በላይ ደግሞ ቤተ-ክርስቲያኒቱ በባለራዕይ የሚትመራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ባለራይ ተገቢ ጥንቃቄ
በማድረግ በግሉ ያገኛቸዉ መልካም አጋጣሚዎችን ጭምር በመሰብሰብ ለብድሩ ከተፈቀደዉ ጊዜ ቀደም
ብሎ መክፈል የሚቻል መሆኑን እናረጋግጣለን፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ቤተ-ክርስቲያኒቱ በአሁን ወቅት በብርሃን ባንክ ከግማሽ ሚሊዮንብር በላይ ቁጠባ
ያላት ሲሆን፤ይህንንም ማስረጃ ከእናንተዉ ዘንድ ያለዉን አካዉንት በማየት የሚታረጋግጡ ይሆናል፡፡
በስተመጨረሻም በቤተ-ክርስቲያኒቱ ገቢ ፍሰትና ደረሰኝ ኮፒዎችን ከዚህ ማረጋገጫ ደብዳቤ ጋር
አያይዘናል፡፡
ከላይ የተሰጡ መረጃዎች ትክክል መሆኑን እያረጋገጥኩኝ እኔ ባለራዕይና መስራች የሆንኩ አገልጋይ ታምራት ታደሰ
ማንኛዉም ተጨማሪ ግዴታ ለመግባት እና ብድሩን በግል ንብረቴ ጭምር ለመክፈል መስማማቴን በፍርማዬ
አረጋግጣለሁ፡፡
አ.አ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ፤ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን በ 2014 ዓ.ም
በመንፈሳዊና በሌሎች በማህበራዊ ዘርፎች ያከናወናቸዉን ስራዎችን ዝርዝር ሪፖርት እና ፋይናንሻል ሪፖርት ------ገፅ ከዚህ ሸኚ
ደብዳቤ ጋር አያይዘን ያቀረብን መመሆኑን በትህትና እናሳዉቃለን፡፡
ዲላ
በመቀጠልም፤ ምንም እንኳን የኃይማኖት ተቋማት የስራ ግብር እንዲከፍል የሚያስገድድ አዋጅ ባይኖርም፤ በአንዳንድ
ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ቤተ-ክርስቲያኒቱ ተሳትፎ ስታደርግ በህጋዊ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እንድሆን ይመከራል፡፡
በተጨማሪም በተለያዩ ግብይቶች እንደማንኛዉም ድርጅት የሚንሳተፍ በመሆኑና የባንክ እንቅስቃሴና የብድር
ሁኔታ፤እንዲሁም ዓመታዊ የስራና የፋይናንስ ሪፖርት በሚቀርብበት ጊዜ TIN NO. አስፈላጊ በመሆኑ፤ በድርጅታችን
ስም ማለትም፡- ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን-ዲላ /ዋና ጽ/ቤት/ በሚለዉ TIN NO.
እንድሰጠን በታላቅ ትህትናና አክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ግልባጭ
ዲላ
ባሉበት
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ፤እርስዎ በዲላ ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን
በቆዩበት ጊዜ በተለያዩ ምክንያቶች የቤተ-ክርስቲያኒቱን የዕድገት መንገድ የሚጎዱ ተግባራትን በመፈፀምዎ ከአንድም
ሁለት ፤ሶስት ጊዜ ከቤተ-ክርስቲያኒቱ ዋና መጋቢና ከተመረጡ አገልጋዮች ጋር በመሆን ለመምከር ተሞክረዋል፡፡
ከተነሱ ነገሮች መካከል ጥቂቱን ለመጥቀስ ያህል፡-
1 ኛ. ቤተ-ክርስቲያንን የምመሩ አገልጋዮችን ምክር ሰምተዉ በቸልተኝነት ማለፍ፡፡
2 ኛ. የተሰጥዎትን የቤተ-ክርስቲያኒቱን አምልኮ አገልግሎት ያለ ማንም ፍቃድ ከአምልኮ መሪ ወንድም
ከፍያለዉ ጋር በመሆን በአድማ አንድ ላይ መደበኛ ፕሮግራሞችን ዘግተዉ መቅረት
3 ኛ.ለቤተ-ክርስቲያን በማያመች አኳሃን ከአምልኮ ቡድን መሪ ጋር እና ከሙዝቃ ተጫዋቾች ጋር በመሆን
የዓመፅ ቡድን መፍጠር ናቸዉ፡፡
በእነዚህ ጉዳዮች የቤተ-ክርስቲያኒቱ ባለራዕይና አገልጋዮች ግንቦት /2013 ዓ.ም ተነጋግረዉ ጉዳዩ ጥፋት እንደሆነ
በማመን ራስን የማያ የ 1 ወር ጊዜ ቢሰጥም ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠትዎን ተመልሶ እንዲያገለግሉ በተሰጥዎት ጊዜ
ለማጣራትና ለመረዳት መቻላችንን በቀን 16/01/2014 ዓ.ም በተደረገዉ በቤተ-ክርስቲያኒቱ አባላት አጠቃላይ ስብሰባ
ላይ አንስተናል፡፡
ስለሆነም ጉዳዩ በዉስጠ ደንባችንም ሆነ በራዕዩ አቅጣጫ አደገኛና አንድን ራዕይ ለማደናቀፍ ከሚደረገዉ እንቅስቃሴ ተርታ
የሚሰለፍ አመለካከት በመሆኑ ለከባድ የዲስፕልን ቅጣት የሚዳርግ ነዉ፡፡ በዚሁ መሠረት ቤተ-ክርስቲያናችን እርስዎን ላላልተወሰነ
ጊዜ ከማናቸዉም መንፈሳዊ አገልግሎት ተቆጥቦ እንዲቆዩ ከማሳወቅ በተጨማሪ በቆይታዎ ወቅት የሚያሳዩት መንፈሳዊ ፍሬ
ተመልሶ እንደቤተ-ክርስቲያናችን አባልም አገልጋይም ሆኖ ለመቀጠል ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ተገቢ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ
ጭምር በጥብቅ አሳዉቃለሁ፡፡
ግልባጭ
ዲላ
የንብረት ገቢና ወጪ ቅፅ
ስም--------------------------
ፍርማ---------------
10
12
13
14
15
ቀን------------------------------------- ቀን------------------------------------
CHRIST OUR PASSOVER FOR ALL
ቀን---------------------------------
ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ
NATION INTERNATIONAL CHURCH-
ቤተ-ክርስቲያን- ዲለ
DILLA
2. እግዚአብሔር በሰጠን ራዕይ ልክ ትዉልድን እንድናገለግል በተለያየ የፀጋ ሥጦታ የተቀቡ አገልጋዮችን እንዲበዙ፡፡
3. በአከባቢያችን ብሎም በሀገሪቱ መርገም እንድሰበር በተለያየ አዳዲስ መገለጥ እንድንቆም ጌታ እንድረዳን፡፡
4. አሁን ያለንበት አዳራሽ በኪራይ በመሆኑ እግዚአብሔር የተሻለ የማመለኪያ ሥፍራ እንድሰጠን፡፡
ተባረኩልን!!!
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/19/2013
ባሉበት
ግልባጭ
በመቀጠል በቀን 12/11/2012 ዓ.ም ባመለከቱት ደብዳቤያቸዉ፤እርስዎ ከቤተ-ክርስቲያ 2 ኒቱ ስላለኝ ጉዳይ ይቅርታ ይደረግ ባሉን
መሠረት፤ቤተ-ክርስቲያኒቱም በጉዳዩ ዙሪያ ባለራዕይና የተወሰኑ አገልጋዮች ተነጋግረን የሚከተለዉን ዉሳኔ አስተላልፈናል፡፡
1 ኛ. እርስዎ ከዚህ ቀደም የአምልኮ ቡድን እንድያስተባብር የተሰጠዎት ብሆንም፤ቤተ-ክርስቲያኒቱ አምና የሰጠችዉን
አደራ ፍፁም ጥንቃቄ በጎደለ እና ለራዕዩ ካለማሰብ የተነሳ በትነዉ፤ ለአንድ ዓመት ያህል፤መሄዱን እንደ ትልቅ ጥፋት
ታይቷል፡፡
2 ኛ.የቤተ-ክርስቲያኒቱን እድገት ከሚገቱ ነገሮች አንዱና ዋነኛ የቅድስና ጉድለት ነዉ፡፡ በመሆኑም እርስዎ የቅድስና
ጉድለት ያሳዩ መሆኑና ለትዳርዎም፤ለአገልግሎትዎም እንዲሁም ለእግዚአብሔርም ያልታመኑና ያሳዘኑን
በመሆኑ፤ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ይቅር ባይነትና መሐሪነት የምናምን ቢሆንም፤ነገር ግን እንዲህ አይነቱ ስህተት
ለራዕይ እድገት ቀይ መስመር በመሆኑ፤በቀላሉ በቃ ይቅር ብለናል በማለት ብቻ የማይታለፍ አለመሆኑን በሚገባ
ተነጋግረናል፤በዉስጠ ደንባችንም እንደ ከባድ ጥፋት ከሚታዩ ነገሮች አንዱ ነዉ፡፡
በስተመጨረሻ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ነገሮችን ከግምት በማስገባት ከዚህ በኋላ እርሶ በኑሮም ሆነ ለንስሃ የሚገባ ፍሬ
እንድያደርጉ እንዲሁም በቂ የንስሃና የጥሞና ጊዜ ወስደዉ እንድያስቡ ስትል ቤተ -ክርስቲያናችን ለአንድ ዓመት ከማንኛዉም
መንፈሳዊ አገልግሎት ተቆጥቦ፤ነገር ግን በማንኛዉም በቤተ-ክርስቲያኒቱ ፕሮግራሞች ከነቤተ-ሰብዎ ባለመቅረት እንድሳተፉ
የተወሰነ ሲሆን፤ነገር ግን በዚህ ቆይታ ወቅት እርስዎ በሕይወት የሚያሳዩት ትጋት፤ቤተ -ክርስቲያን መገኘት፤ከዚህ ቀደም ይቅርታ
ግልባጭ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/20/2013
ዲላ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ቤተ-ክርስቲያናችን የህብረቱ ተባባሪ አባል ለመሆን ከዚህ በፊት ጥያቄ ያቀረብን
ቢሆንም የጽ/ቤቱን ዉሳኔና ምላሽ ስንጠባበቅ አንድ ዓመት ሆኗል፡፡
ነገር ግን ህብረቱ ጉዳዩን በተመለከተ በተገቢ አይቶና መርምሮ ዉሳኔ እንድሰጥ በሚል እነዚያ ጊዜያቶችን
በትዕግስት ለመጠበቅ ችለናል፡፡ ዛሬም ቤተ-ክርስቲያኒቱ ጥያቄዋን ካቀረበችበት ዕለት አንስቶ በትዕግስትና በጉጉት
የህብረቱን ጽ/ቤት ምላሽ እየተጠባበቀች ያለ በመሆኗ በድጋሚ የህብረቱ ጽ/ቤት ይህንኑ ጥያቄያችን ተቀብሎ ምላሽ
እንድሰጠን ስንል በታላቅ ትህትና እናመለክታለን፡፡
ግልባጭ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/29/2014
አ/ አ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ በዲላ ከተማ የሚትገኘዉ ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-
ክርስቲያን የቤተ-ክርስቲያናችሁ አገልጋይ የሆኑትን ነብይ ሰለሞን ከተማን እግዚአብሔር በሰጣቸዉ ፀጋ
እንዲያገለግሉን ቤተ-ክርስቲያኒቱ ከየካቲት 11 እስከ የካቲት 13/2014 ዓ.ም ድረስ ባዘጋጀችሁ ኮንፈራንስ ተገኝተዉ
የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንዲያገለግል እንድፈቀድልን በታላቅ ትህትናና አክብሮት እየጠየቅን ስለሚደረግልን ቀና
ትብብርም ከወዲሁ በጌታ ስም ልንባርካችሁ እንወዳለን ፡፡
ግልባጭ
ቁጥር --ዲ/ፋ/ክ/01/015
ዲላ
በጣምራ ያለገደብ እንድያንቀሳቅሱና ለዚሁም የሚረዳ የቼክ ደብተር እንድዘጋጅ ጭምር እንዲደረግልን እየጠየቅን
ስለሚደረግልን ቀና ትብብርም ከወዲሁ እናመሰግናለን፡፡
ግልባጭ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/29/2013
ዲላ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ህብረቱ ከመንግስት በተሰጠዉ ህጋዊ እዉቅና አኳያ ቤተ-ክርስቲያናችን
ከሐምሌ 20/ 2012 ዓ.ም ጀምሮ የማምለኪያ ቦታ ችግር እንደገጠመንና በዚሁ ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ
ከመጣዉ የቦታና የቤት ኪራይ የተነሳ በኪራይ መቀጠሉ ከአቅማችን በላይ ስለሆነብን፤የዲላ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ
ይህንኑ ችግራችንን አይተዉ ምላሽ እንድሰጠን የጠየቅን ቢሆንም ጉዳዩ ወደ ማዘጋጃ ቤት ከተመራ ከ 7 ወር በላይ የፈጀ
በመሆኑ፤ አብያተክርስቲያናት ህብረት ጽ/ቡቱ የጉዳዩን አንገብጋቢነት በተሰጠዉ ህጋዊ እዉቅና መሠረት ለከተማ
አስተዳደሩ እንዲያሳስብልን እየጠየቅን ከዚህ ቀደም የቀረበዉ ጥያቄ ኮፒና ተያያዥ ፕሮፖዛል ከዚህ ደብዳቤ ጋር
አያይዘን ያቀረብን መሆኑንም በትህትና እንገልፃለን፤ስለሚደረግልን ቀና ትብብርም እግዚአብሔር ይባርካችሁ ልንል
እንወዳለን፡፡
ግልባጭ
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ቤተ-ክርስቲያናችን የህብረቱ ተባባሪ አባል ለመሆን ባቀረበዉ ጥያቄ መሠረት
የአብያተ ክርስቲያናት ህብረት ጽ/ቤት በቀን 20/02/2013 ዓ.ም የይሁንታ ምላሽ መስጠቱ ይታወቃል፡፡
ግልባጭ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/30/2013
ዲላ
ከላይ በአርዕስቱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ በዲላ ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-
ክርስቲያን ከመጋቢት 17 እስከ መጋቢት 19/2013 ዓ.ም ድረስ ኮንፈራንስ ስተዘጋጄ በኮንፈራንሱ የኃይል መቆራረጥ
እንዳያስቸግረን ለጀኔሬተር ፍጆታ የሚሆን 30 ሊትር ነዳጅ በጽ/ቤታችሁ በኩል ትብብር እንዲደረግልን በጌታ
ፍቅርና ትህትና እንጠይቃለን፡፡
ግልባጭ
ዲላ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/31/2013
ለ ወንድም/እህት----------------------------------
ዲላ
ከላይ በአርዕስቱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ከቀን 27/09/2013 ዕለተ ዓርብ ማለዳ 2፡00 ጀምሮ እስከ ዕለተ
እሁድ 29/09/2013 ዓ.ም 9፡00 ሰዓት ድረስ በሚቆየዉ ልዩ የፆምና የፀሎት ፕሮግራም ላይ እርስዎ ካለዎት ተግባር
ሁሉ አስቀድሞ መጥተዉ የፀሎቱ ተካፋይ እንድሆኑ ቤተ-ክርስቲያኒቱ የከበረ ጥሪዋን እያስተላለፈች የፕሮግራሙን
ሁኔታ በተመለከተ እንደሚከተለዉ የሚፈፀም ይሆናል፡-
ግልባጭ
ዲላ
አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/35/2013
ከላይ በተጠቀሱ አጀንዳዎች ላይ በመፀለይ ጠቃሚ ምክረ-ሃሳብ ይዘዉልን እንዲመጡና እንድገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
ግልባጭ
አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/35/2013
ከላይ በተጠቀሱ አጀንዳዎች ላይ በመፀለይ ጠቃሚ ምክረ-ሃሳብ ይዘዉልን እንዲመጡና እንድገኙ በአክብሮት ተጋብዘዋል፡፡
ግልባጭ
ዲላ
ለ --------------------------------------------------------
ባሉበት
ዕለታዊና ሳምንታዊ የግብዓት ወጪዎችን ለመሸፈን ካለን ምዕመን ብዛትና ከገቢ ምንጫችን አንፃር አስቸጋሪ
ስለሆነብን እርስዎ የቤተ-ክርስቲያናችን አባል እንደመሆንዎ መባ፤አስራት እና የፍቅር ስጦታ ከመስጠት ባሻገር ለ 2014
በጀት ዓመት ከቤተ-ሰብዎ ጋር በመማከር --------------------ብር በተቻለ መጠን እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም እንድደግፉ
ቤተ-ክርስቲያን መንፈሳዊ ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡
እግዚአብሔር ይባርክዎት!!!
ግልባጭ
ክርስቶስ ለ/ሁ/ዓ/አ/ቤተ-ክርስቲያን
ዲላ
ማሳሰቢያ ፡- ድጋፍዎን በቤተ-ክርስቲያኒቱ አካዉንት ቁጥር 16011660035440 ብርሃን ባንክ ዲላቅርንጫፍ አስገብተዉ
ቁጥር--ዲ/ፋ/ክ/34/2013
ዲላ
ከላይ በአርዕስቱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ወንድም በረከት መንገሻ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት በዲላ ከተማ
ቃለ ሕይወት ለመማር ስለፈለጉ የድጋፍ ደብዳቤ ይፃፍልኝ ብለዉ በቀን 12/12/2013 ዓ፣ም አመልክተዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ወንድም በረከት መንገሻ የቤተ-ክርስቲያናችን አባል መሆኑን እያረጋገጥን የመጽሐፍ ቅዱስ
ትምህርቱን ለመከታተል ይረዳ ዘንድ ከእናንተ በኩል አስፈላጊዉን ትብብር እንድታደርጉለት በትህትና
እንጠይቃለን፡፡
እግዚአብሔር ይባርክዎት!!!
ግልባጭ
ዲላ
ዲላ
እኛ ግን የተሰቀለዉን ክርስቶስን እንሰብካለን 1 ኛ ቆሮንቶስ 1፡23
ጉዳዩ፡- የቤተ-ክርስቲያኒቱ ተወካይ ስለማሳወቅ ይሆናል፤
ከላይ በርዕሱ ለመግለፅ እንደተሞከረዉ ፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን የዲላ ወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት
ህብረት አባል መሆኗ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን የቤተ-ክርስቲያኒቱ ዋና መጋቢ ከቤተ-ክርስቲያን አገልግሎት ዉጪም ከፍተኛ የመንግስት ተቋም አመራር በመሆኑ ምክንያት
በተለይም ወራዊ ስብሰባዎችና ሌሎችም አስቸኳይ ስብሰባዎች ላይ በንቃት ለመሳተፍ እንዳልቻልን እናስተዉላለን፡፡
ስለሆነም ቤተ-ክርስቲያኒቱ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በህብረቱ ጉዳይ ቋሚ ተወካይ መሰየም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ወንድም አብንያም ታመነ ሾካ ከዛሬ ይህ ደብዳቤ ከተፃፈበት ቀን አንስተዉ በዲላ ወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያን ህብረት
የፋሲካችን ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ዓለም አቀፍ ቤተ-ክርስቲያን ተወካይ ሆኖ እንድያገለግሉ በዋና መጋቢ ተሰይመዋል፡፡
የዲላ ወንጌላዊያን አብያተ-ክርስቲያናት ህብረትም ቤተ-ክርስቲያኒቱን በተመለከተ በማናቸዉም ጉዳይ የዋና መጋቢ መገኘት ግዴታ ሆኖ ከታየ
በስተቀር ተወካዩን እንድያገኙ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ወንድም አብንያም ታመነ ሾካም ከቤተ-ክርስቲያኒቱ ዋና መጋቢ የተሰጥዎትን መንፈሳዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንድወጡና ህብረቱ በሚፈልግዎት
ጊዜ ሁሉ በመገኘት እንድያገለግሉ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ፡፡
ግልባጭ