You are on page 1of 29

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦

www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
ማኅበረ ቅዱሳን

አምስቱ አዕማደ ምሥጢር


መ/ር ምሥጢረሥላሴ ማናዬ
አምስቱ አዕማደ ምሥጢር
❑ የአዕማደ ምሥጢር ምንነት
❑ ምሥጢረ ሥላሴ
❑ ምሥጢረ ሥጋዌ
❑ ምሥጢረ ጥምቀት
❑ ምሥጢረ ቁርባን
❑ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ምዕራፍ ስድስት
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
❑ የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትርጉም
❑ የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት
❑ ሞት እና የሞት ሞት
❑ የሰዎች ትንሣኤ
❑ ትንሣኤ ሙታን በመጽሐፍ ቅዱስ
❑ ዳግም ምጽዓትና የዓለም ፍጻሜ
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.1 የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትርጉም
❖ ትንሣኤ ለሚለው ቃል መነሻ ግሡ ተንሥአ የሚለው የግዕዝ ቃል ነው፡፡
➢ የግዕዙ “ተንሥአ” ወደ አማርኛ ሲተረጎም፦ ተነሣ ማለት ሲሆን መነሣት፣
አነሣስ፣ አዲስ ሕይወት ማለት ነው፡፡

❖ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ስለ ሙታን መነሳት፣ ከሥጋ ሞት በኋላ


ስላለው የዘለዓለማዊ ሕይወት ተስፋ የምንማርበትና የምናጠናበት
የመጨረሻው ምስጢር ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.1 የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትርጉም ...
❖ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን፣ ክርስቶስ ሦስት
ቀንና ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር ቆይቶ ሞትን ድል አድርጎ
እንደተነሣ ሁሉ፣ በክርስቶስ ያመኑትም እንዲሁ ይነሣሉ፤ የአዲስ
ዘላለማዊ ሕይወት ባለቤት ይሆናሉ ብላ ታስተምራለች።
➢ “...ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን፣ ወሕይወተ ዘይመጽዕ = የሙታንንም
መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት...”
ጸሎተ ሃይማኖት

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.1 የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትርጉም ...
❖ ትንሣኤ ሙታን ምሥጢር መባሉ ከሥጋ ሞት በኋላ ያለውን ትንሣኤ
እና ዘላለማዊ ሕይወት በእምነት የምንቀበለው እና በተስፋ የምንጠብቀው
እንጂ በሥጋዊ አዕምሮ ተመራምረን የምንደርስበት ጉዳይ ስላልሆነ ነው።

❖ በምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን፣ ተስፋ ከምናደርገው ዘለዓለማዊ አዲስ


ሕይወት በተጨማሪ የክርስቶስን ዳግም ምጽአት፣ የዓለምን ፍጻሜ፣
ዘለዓለማዊ ሞት... ወዘተ እና ተያያዥ ጉዳዮችን እናነሳለን።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ምዕራፍ ስድስት
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
❑ የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትርጉም
❑ የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት
❑ ሞት እና የሞት ሞት
❑ የሰዎች ትንሣኤ
❑ ትንሣኤ ሙታን በመጽሐፍ ቅዱስ
❑ ዳግም ምጽዓትና የዓለም ፍጻሜ
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት
❖ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነው፣ መከራ መስቀልን
የተቀበለው፣ በኋላም የሞተው አዳምና ልጆቹን ለማዳን እንደሆነ ይታወቃል።
➢ አዳም ላይ የተፈረደውን የሞት ፍርድ በሞቱ ለመሻር፣ ስለ አዳም በደል ቤዛ፣ ካሳ
ለመሆን ሞተ፤ በሶስተኛውም ቀን ሞትን አሸንፎ፣ ለሙታን ሁሉ በኩር ሆኖ ተነሳ።
✓ “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷአል፤ ሞት በሰው በኩል
ስለመጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኗልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ፣ እንዲሁ ሁሉ
በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና። ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ ክርስቶስ
እንደ በኩራት ነው። ...” 1ኛ ቆሮ.15፥20-23

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
❖ ጌታችን በዘመነ ሥጋዌው ለሐዋርያትና አብረውት ለነበሩት፣ ስለ ነገረ
ትንሣኤው በቃል አስተምሯቸዋል፤ በኋላም በገቢር ፈጽሞ
አሳይቷቸዋል።
➢ “አሁን ወደ ኢየሩሳሌም እንወጣለን የሰውን ልጅ ይይዙታል ይሰቅሉታል
ይገድሉታልም በሦስተኛውም ዕለት ይነሣል።” ማቴ.20፥18-19

➢ “... እንዲህ አሏቸው፦ ሕያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ?


ተነሥቷል እንጂ በዚህ የለም።” ሉቃ.24፥5

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
❖ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ በመስቀል ላይ ሆኖ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት
ሥጋው ከቀኑ 9 ሰዓት ከለየ በኋላ መለኮት ከሥጋውና ከነፍሱ ሳይለይ
በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ ለዘመናት በዚያ ተግዘው ይኖሩ ለነበሩ ነፍሳት
ነፃነትን አውጆላቸዋል።
➢ “... በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ። በእርሱም ደግሞ ሔዶ በወኀኒ
ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው።” 1ኛ ጴጥ.3፥18-19

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
❖ በአካለ ሥጋ ደግሞ ለሦስት ዕለታት ያሕል በመቃብር ቆይቷል።
➢ “ዮናስ በዓሳ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደነበር እንዲሁ የሰው
ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።” ማቴ.12፥40

➢ “ኢየሱስም መልሶ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ


አላቸው።” ዮሐ.2፥19

➢ “መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ...” 1ኛቆሮ.15÷4

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
❖ ነገር ግን፣ ክርስቶስ በሥጋ ከሞተበት እስከ ተነሳበት ያለው ጊዜ
እንዴት ሦስት ቀን ሊሆን ይችላል የሚለው ብዙ ጊዜ ሲያወዛግብ
ይታያል።

❖ ይህን በተመለከተ ሁለት አይነት አቆጣጠሮች አሉ።


1. መደበኛው የዕለታት አቆጣጠር

2. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አቆጣጠር

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
1. መደበኛው የዕለታት አቆጣጠር
➢ በዕብራውያን አቆጣጠር አንድ ዕለት የሚባለው 24 ሰዓት ነው።
✓ 12 ሰዓት መዓልት (ቀን፣ ብርሃን)
✓ 12 ሰዓት ለሊት (ማታ፣ ጨለማ)

➢ ለሊቱ መዓልቱን ይቀድማል። ማለትም፦


✓ አንድ ዕለት የሚጀምረው እኛ በተለምዶ ከምሽቱ 12፡00 ከምንለው ጊዜ ነው።
✓ ለምሳሌ፦ ሰኞ የሚጀምረው፣ እሁድ ሰርክ 12፡00 ሰዓት
ላይ ንው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
➢ አንድ ዕለት ሳያልቅ የተከናወነ ነገር (በደቂቃዎች ልዩነት እንኳን ቢሆን)
በዚያ ዕለት እንደተከናወነ ይቆጠራል።
✓ ለምሳሌ፦ ቅዳሜ ከሰዓት 11፡30 የተከናወነ ነገር በዕለተ ቅዳሜ ተከናወነ
ሲባል 12፡30 ላይ ቢሆን ግን በዕለተ ዕሁድ እንደተከናወነ ይቆጠራል።
✓ በዚህ መሠረት ሌሊቱ መዓልቱን፣ መዓልቱም ሌሊቱን ይስባል።

➢ በነገራችን ላይ፣ ቤተክርስቲያናችን ለሥርዓተ አምልኮዋ (Liturgy)


የምትጠቀመው ይህንኑ አቆጣጠር ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
1. መደበኛው የዕለታት አቆጣጠር ...
➢ በዚህ መሠረት፣ የመጀመርያው ዕለት፦
✓ ጌታችን ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የለየው አርብ 9፡00 ሲሆን ወደ
መቃብር የወረደው ደግሞ 11፡00 ሰዓት ላይ ነው።
✓ ይህ ጊዜ 12፡00 በፊት ስለሆነ በዕለተ አርብ የተከናወነ ነው።
✓ ስለዚህ አርብን አንድ ዕለት ብለን እንቆጥራለን (1 ዕለት = 1 ቀን + 1
ለሊት)።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
1. መደበኛው የዕለታት አቆጣጠር ...
➢ ሁለተኛው ዕለት፦
✓ ቅዳሜ ለሊቱንም ቀኑንም በመቃብር ነበር። ሁለተኛው ዕለት ሆነ።

➢ ሦስተኛው ዕለት፦
✓ ጌታችን የተነሳው ቅዳሜ ለእሁድ አጥቢያ በእኩለ ለሊት ነው፤ ይህ ጊዜ ደሞ
የዕለተ እሁድ ነው።
✓ ስለዚህ እሁድን እንደ ሦስተኛው ዕለት እንቆጥረዋለን። (1 ቀን + 1 ለሊት)
➢ ጌታችን ለሦስት ዕለታት (3 ቀንና 3 ለሊት) በመቃብር
ቆየ የምንለው በዚህ አቆጣጠር መሠረት ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
2. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አቆጣጠር
➢ የቤተክርስቲያናችን ሊቃውንት፣ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን
በተሰቀለ ጊዜ በተዓምር ፀሃይ መጨለሟን መሠረት አድርገው
የሚቆጥሩበት ሌላ አቆጣጠር አላቸው።
✓ ጌታ በተሰቀለ ጊዜ ከቀኑ 6፡00 እስከ 9፡00 ጨለማ ሆኗል።

➢ በኢትዮጵያውያን ልማድ አንድ ዕለት የሚጀምረው ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት


ላይ ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
2. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አቆጣጠር ...
➢ በዚሁ መሠረት፣ የመጀመሪያው ዕለት፦
✓ አርብ ከጠዋቱ 12፡00 እስከ 6፡00 ብርሃን ነበር = 1 ቀን።
✓ ከ 6፡00 እስከ 9፡00 ጨለማ ነበር = 1 ለሊት።
✓ አንድላይ 1 ዕለት ይሆናል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
2. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አቆጣጠር ...
➢ ሁለተኛው ዕለት፦
✓ አርብ 9፡00 እስከ 12፡00 ብርሃን ነበር = 1 ቀን።
✓ ከ 12፡00 እስከ ቅዳሜ ንጋት 12፡00 ጨለማ = 1 ለሊት።
✓ አንድ ላይ ሁለተኛው ዕለት ተፈፀመ።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
2. የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት አቆጣጠር ...
➢ ሦስተኛው እለት፦
✓ ቅዳሜ ጠዋት 12፡00 እስከ ምሽቱ 12፡00 = 1ቀን
✓ ቅዳሜ ከምሽቱ 12፡00 እስከ ለሊቱ 6፡00 = 1 ለሊት
✓ አንድ ላይ አንድ ዕለት ይሆናሉ፤ ሦስተኛው ዕለት ተፈፀመ!

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.2 የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት …
❖ በዚህ መሠረት ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ፣ በአርባኛው ቀን ወደ
ሰማይ አርጓል።
➢ “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው፣ ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት እየነገራቸው፣ በብዙ ማስረጃ
ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው፡፡” ሐዋ.1፥3

➢ “...ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፡፡
እርሱም ሲሔድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች
በአጠገባቸው ቆሙ፤ ... ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ
ሰማይ ሲሔድ እንዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል አሏቸው” ሐዋ.1÷9-11
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ምዕራፍ ስድስት
ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
❑ የምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትርጉም
❑ የክርስቶስ ትንሣኤ እና እርገት
❑ ሞት እና የሞት ሞት
❑ የሰዎች ትንሣኤ
❑ ትንሣኤ ሙታን በመጽሐፍ ቅዱስ
❑ ዳግም ምጽዓትና የዓለም ፍጻሜ
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.3 ሞት እና የሞት ሞት
❖ ስለ ሰዎች ትንሣኤ በጥልቀት ከማንሳታችን በፊት ስለሞት ማወቅ
አለብን፤ ሳይሞቱ ትንሣኤ የለምና፡፡

❖ እንደ ቤተክርስቲያናችን አስተምህሮ ሁለት አይነት ሞት አለ፦


1. የሥጋ ሞት (በተለምዶ ሞት ብለን የምንጠራው)

2. የነፍስ ሞት (በተለምዶ የሞት ሞት ይባላል)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.3 ሞት እና የሞት ሞት ...
1. የሥጋ ሞት፦
➢ የሥጋ ሞት ማለት የነፍስ ከሥጋ መለየት፣ እረፍት፣ እንቅልፍ፣ ከዚህኛው የሚያልፍ ዓለም
ወደዚያኛው የማያልፍ ዓለም መሔጃ፣ መሸጋገሪያ መንገድ ማለት ነው፡፡
✓ “...ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፤ ነገር ግን ከእንቅልፉ ላስነሳው እሔዳለሁ አላቸው።... ኢየሱስ
ስለሞቱ ተናግሮ ነበርና እነርሱ ግን ስለ እንቅልፍ መተኛት እንደተናገረ መሰላቸው።”
ዮሐ.11፥11-13

✓ “ ከዚህም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች ባንድ ጊዜ ታየ፤ ከነርሱም

የሚበዙቱ እስከ አሁን አሉ፤ አንዳንዶች ግን


አንቀላፍተዋል...” 1ቆሮ.15፥6

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.3 ሞት እና የሞት ሞት ...
2. የሞት ሞት (የነፍስ ሞት)፦
➢ የሞት ሞት ወይም የነፍስ ሞት የምንለው በሥጋ ሞት የተለየች ነፍስ የምትቀበለውን
ፍርድ ነው።

➢ የሞት ሞት የተባለበትም ምክንያት የሥጋ ሞትን ተከትሎ የሚመጣ በመሆኑ ነው።


➢ ይህ ሞት በመጽሐፍ ቅዱስ ሁለተኛው ሞት ተብሎ ተጠርቷል።
✓ “ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት

ነው። በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ


ተጣለ።” ራዕ.20፥14-15

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.3 ሞት እና የሞት ሞት ...
2. የሞት ሞት (የነፍስ ሞት)፦ ...
➢ ሰዎች ይህንን ሁለተኛ ሞት የሚሞቱት እንደ ሥጋ ሞት በማረፍ
አይደለም፡፡

➢ ሞቱ ማብቂያ የሌለው ዘላለማዊ የነፍስ ቅጣት ነው፡፡


✓ ከሥጋ ሞት በኋላ ያለው ሕይወትም ሆነ ሞት ዘላለማዊ የሆነው፣ የሰው

ነፍስ በባሕሪዋ ሕያውነት(ዘላለማዊነት) ስላላት ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
6.3 ሞት እና የሞት ሞት ...
2. የሞት ሞት (የነፍስ ሞት)፦ ...
➢ ስለዚህኛው ሞት፣ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስረዳን እንዲህ
ብሎናል፦
✓ “ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም
ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።” ማቴ.10፥28

➢ ይህ የሞት ሞት በዳግም ትንሣኤ ጊዜ ከግራ ቁመት በኋላ ይፈጸማል።


✓ “በዚያን ጊዜ፣ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፣ እናንተ ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክቱ
ወደተዘጋጀ ወደዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ። ... ” ማቴ.25፥41-46

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ይቆየን !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org

You might also like