You are on page 1of 25

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦

www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
ሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
ማኅበረ ቅዱሳን

አምስቱ አዕማደ ምሥጢር

መ/ር ምሥጢረሥላሴ ማናዬ


አምስቱ አዕማደ ምሥጢር
❑ የአዕማደ ምሥጢር ምንነት
❑ ምሥጢረ ሥላሴ
❑ ምሥጢረ ሥጋዌ
❑ ምሥጢረ ጥምቀት
❑ ምሥጢረ ቁርባን
❑ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ምዕራፍ ሁለት
ምሥጢረ ሥላሴ
❑ የምሥጢረ ሥላሴ ምንነት

❑ ምሥጢረ ሥላሴን የሚያስረዱ ተፈጥሮአዊ ምሳሌዎች

❑ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የቅዱሳት መጻሕፍት ማስረጃዎች

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
2.1 የምሥጢረ ሥላሴ ምንነት
❖ ይህ የመጀመሪያ ምሥጢር የእግዚአብሔርን አኗኗር የምናጠናበት እንደመሆኑ ቀላል
አይደለም:: ግን ደግሞ ከባድ ነው ተብሎ አይተውም።
➢ ልክ እንደ እሳት መሞቅ ነው፤ እሳትን ተጠግተው እንሙቅህ ቢሉት ያቃጥላል፤ ርቀን እንሙቅህ
ቢሉትም ልምላሜ ሙቀቱን ማግኘት አይቻልም፤ ሳይርቁትና ሳይጠጉት የሞቁት ጊዜ ግን
ተፈላጊውን የእሳት ጥቅም ማግኘት ይቻላል፡፡

➢ ልክ እንደዚሁ ካባድ ነው ብለን ሳንተወው፣ቀላል ነው ብለንም ሳንዳፈረው በዕውቀታችን አቅም


ይህንን ምሥጢር ልንማርና ልናጠና ይገባል።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
2.1 የምሥጢረ ሥላሴ ምንነት
❖ ምሥጢረ ሥላሴ አምላካችን እግዚአብሔር አንድም ሦስትም መሆኑን፤
የአንድነቱንና የሦስትነቱን ነገር የምንማርበት፣ ከአምስቱ አዕማደ ምሥጢራት
የመጀመሪያው ነው።

❖ ቅድስት ሥላሴ ስንል የተለየች ሦስትነት ማለታችን ነው፡፡ ማለትም፣ አምላካችንን


በተለየች ሦስትነቱ ስንጠራው ቅድስት ሥላሴ እንላለን።

❖ በአንድነቱ ስንጠራው ደግሞ እግዚአብሔር እንላለን።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
2.1 የምሥጢረ ሥላሴ ምንነት ...
❖ አምላካችንን አንድም ሦስትም ነው ብለን ስናምን ሦስት አማልክት ማለታችን
አይደለም፡፡ አንዱን አምላክ ወይም አንዱን እግዚአብሔር በአካል፣ በስም፣ በግብር
ሦስት ብለን ማመናችን እንጂ፡፡
➢ "…በአንድ አምላክ አምናለሁ አንድነት በሦስትነት፣ ሦስትነት በአንድነት እንዳለ
አውቃለሁ…" እንዲል (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ ምዕ.90ቁ.5)
❖ በመቀጠል፣ አምላካችን በአካል፣ በስም፣ በግብር ሦስት
ስለመሆኑ፣ የሦስትነቱን ነገር በዝርዝር እንመለከታለን።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት
ሀ. የአካል ሦስትነት

❖ ሥላሴ በአካል ሦስት ናቸው ስንል፦


➢ ለአብ ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል አለው፤

➢ ለወልድም ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል አለው፤


➢ ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም ገጽ፣ ፍፁም መልክ፣ ፍፁም አካል አለው፤

ማለታችን ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ...
ለ. የስም ሦስትነት

❖ ሥላሴ በስም ሦስት ናቸው ስንል፦


➢ አብ በራሱ ስም አብ ይባላል እንጂ ወልድ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፣
➢ ወልድም በራሱ ስም ወልድ ቢባል እንጂ አብ ወይም መንፈስ ቅዱስ አይባልም፣
➢ መንፈሰ ቅዱስም በራሱ ስም መንፈስ ቅዱስ ቢባል እንጂ አብ ወይም ወልድ
አይባለም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ...
ለ. የስም ሦስትነት ...
❖ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስቅዱስ የሚለው የሥላሴ ስም ጥንት፣ ቅድመ ዓለም
ከመለኮታዊ ባህርይ እና ግብራቸው የመነጨ እንጂ እንደ ተጸውዖ (መጠሪያ) ስም
ከጊዜ በኋላ የወጣ ስም አይደለም።
➢ "እንግዲህ ሒዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፣
ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው"
(ማቴ 28፡19)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ...
ሐ. የግብር ሦስትነት
❖ ግብር ትርጉሙ ሥራ፣ ተግባር ማለት ነው። የግብር ሦስትነት ስንልም፣ አብ ወልድና
መንፈስቅዱስ በተለየ አካላቸው ያላቸውን አካላዊ ግብር ማለታችን ነው።
❖ ሥላሴ በግብር ሦስት ናቸው ስንል፦
➢ የአብ ግብሩ መውለድና ማስረጽ ነው።
✓ ወልድን ይወልዳል፣ መንፈስ ቅዱስን ያሰርጻል (ያወጣል)።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ...
ሐ፣ የግብር ሦስትነት ...
➢ የወልድ ግብሩ መወለድ ነው።
✓ ከአብ ይወለዳል።

➢ የመንፈስቅዱስ ግብሩ መስረጽ ነው፡፡


✓ ከአብ ይሰርጻል (ይወጣል)።

✓ "… እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል" እንዲል...

(ዮሐ. 15፡26)

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ...
ሐ. የግብር ሦስትነት ...
❖ አብን ወላዲ አስራጺ፣ ወልድን ተወላዲ፣ መንፈስቅዱስን ሰራጺ ስንል በመካከላቸው በእድሜ
መቀዳደም እና መበላለጥ አይኖርምን? የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል።
➢ ነገር ግን፣ በሥላሴ ዘንድ በእድሜ መቀዳደምም ሆነ መበላለጥ የለም። ሦስቱም እኩል ናቸው።
➢ በሰው ሥርዓት አባት ልጁን በእድሜ እንደሚበልጥ፣ ልጅም እንደሚያንሰው... በሥላሴ ዘንድ እንደዚህ
አይደለም።

➢ ሥላሴ፣ ፍጥረታት ሳይፈጠሩ፣ ጊዜም ሳይፈጠር ጀምሮ በእኩልነት ነበሩ።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ ሦስትነት ...
ሐ. የግብር ሦስትነት ...

❖ የሥላሴ አካላዊ ግብራት ቅድመ ዓለም ፍጥረታት ሳይፈጠሩ ጊዜም ሳይፈጠር


(መቆጠር ሳይጀምር) የተከናወኑ ናቸው። በመሆኑም እንዲሁ ዕጹብ ድንቅ ብለን
እናደንቃለን እንጂ መርምረን አንደርስበትም።
➢ “...ከአብ የወልድ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ መስረጽ በዕፁብ ይወሰናል እንጂ እንዲህ ነው
ተብሎ አይነገርም ከህሊናት ሁሉ በላይ ነው አይመረመርም…”
እንዲል (ሃይማኖተ አበው ዘዲዮናስዮስ ምዕ.10፣ ቁ.12)
ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦
www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ አንድነት
❖ ቅድስት ሥላሴ በአካል፣ በስም፣ በግብር ሦስት ቢሆኑም፤ በመለኮት፣ በአገዛዝ፣
በባሕርይ እና በመሳሰሉት አንድ ናቸው፡፡

❖ የሥላሴ አንድነት ሦስትነታቸውን አይጠቀልለውም፣ ሦስትነታቸውም


አንድነታቸውን አይከፋፍለውም፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ...
❖ መለኮት በአካል ልዩ ሳይሆን በቅድስት ሥላሴ አንድ መለኮት በሦስት አካላት ህልው ነው፡፡
"በዕውቀት ማነስ የተሳሳቱ ሰዎች (እነ ዮሐንስ ተዓቃቢ) ልዩ በሆነች ሦስትነት (ቅድስት ሥላሴ)
የመለኮትን ልዩነት የአካላትን አንድነት አግብተው ይናገሩ ዘንድ አይድፈሩ ለአንድ አምላክ
እንስግዳለን እንጂ ለሦስት አማልክት አንሰግድምና አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ ብለን በሦሰት ስም
እንጠራቸዋለን እኒህም ሦስቱ አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በአንድ መለኮትና /ሕይወት/ በአንድ
ህልውና አንድነት የተገናዘቡ ሦስት ሲሆኑ አንድ ባሕርይና ኃይል ናቸው" ሃ.አበው 4፡22

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ...
❖ በአጠቃላይ ቅድስት ሥላሴ፡-
✓ በፈቃድ፣

✓ በምክር፣

✓ በመፍጠር፣

✓ በእግዚአብሔርነት፣

✓ በአምላክነት፣

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ...
✓ በመንግሥት፣

✓ በሥልጣን ፣

✓ በአገዛዝ፣

✓ ቀድሞ ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ በመፍጠር፣

✓ ኋላም ይህን ዓለም ከመኖር ወደ አለመኖር በማሳለፍ፣

✓ መዓልትና ሌሊቱን በማመላለስ፣

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ...
✓ ክረምትና በጋውን በማፈራረቅ፣

✓ ኃያሉን ድኩም ድኩሙን ኃያል፣

✓ ባለጤናውን ድውይ ድውዩን ባለጤና፣

✓ ድኃውን ባለጸጋ ባለጸጋውን ድኃ በማድረግ

✓ ... ወዘተ አንድ ናቸው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
የቅድስት ሥላሴ አንድነት ...
❖ “...አሐቲ ልቡና፣ አሐቲ ቃል፣ አሐቲ እስትንፋስ፣ አሐቲ መንግሥት፣ አሐቲ
ሥልጣን፣ አሐቲ ክብር፣ ወአሐቲ ምኲናን...” እንዳለ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም

❖ ትርጉሙም፦ “...አንድ ልብ፣ አንድ ቃል፣ አንድ ሕይወት፣ አንድ አገዛዝ፣ አንድ
ስልጣን፣ አንድ ክብር፣ አንድ አገዛዝ...” ማለት ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሦስቱ ኩነታት
❖ በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት በአንድ መለኮት ሦስት ኩነታት(መሆኖች) አሉ።
እነዚህም፦
➢ ከዊነ ልብ (ልብ መሆን)፣
➢ ከዊነ ቃል (ቃል መሆን)፣
➢ ከዊነ እስትንፋስ (እስትንፋስ ወይም ሕይወት መሆን) ናቸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሦስቱ ኩነታት ...
❖ በምሥጢረ ሥላሴ፣ የአካል ሦስትነት እና ሦስቱ መለኮታዊ ኩነታት የተለያዩ ነገሮች
ናቸው።
➢ ሦስቱ አካላት መጠቅለልና መቀላቀል ሳይኖርባቸው በተከፍሎ፣ በተፈልጦ፣
በፍፁም ገጽ፣ በፍፁም መልክዕ፣ በየራሳቸው የቆሙ ናቸው፡፡
➢ ሦስቱ ኩነታት ግን መከፈልና መለየት ሳይገባቸው በተዋሕዶ፣ በአንድነት
አካላትን በህልውናና በአኗናር እያገናዘቡ በአንድ መለኮት የነበሩ ያሉና የሚኖሩ
ናቸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሦስቱ ኩነታት ...
❖ በሦስቱ ኩነታት፦
➢ አብ ለራሱ ልብ ሆኖ ለወልድና ለመንፈስ ቅዱስ ልባቸው ነው።
✓ በአብ ልብነት ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሕልዋን ናቸው ስለዚህም በአብ ልብነት ያስባሉ።

➢ ወልድም ለራሱ ቃል ሆኖ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ነው።


✓ በወልድ ቃልነት አብ መንፈስ ቅዱስ ሕልዋን ናቸው ስለዚህ በወልድ ቃልነት ይናገራሉ።

➢ መንፈስቅዱስም ለራሱ እስትንፋስ (ሕይወት) ሆኖ ለአብና ለወልድ እስትንፋሳቸው ነው፡፡


✓ በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት አብ ወልድ ሕልዋን ናቸው ስለዚህ
በመንፈስ ቅዱስ ሕይወትነት ሕያዋን ሆነው ይኖራሉ።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ሦስቱ ኩነታት ...
ከዊነ ልብ (ልብ መሆን) በአብ መሠረትነት ለራሱ ለባዊ(አሳቢ) ሆኖ ለወልድና
ለመንፈስ ቅዱስ ዕውቀት ማወቂያ መሆን ነው።

ከዊነ ቃል (ቃል መሆን) በወልድ መሠረትነት ለራሱ ነባቢ(ተናጋሪ) ሆኖ ለአብና


ለመንፈስ ቅዱስ ንባብ (መናገሪያ) መሆን ነው።

በመንፈስ ቅዱስ መሠረትነት ለራሱ ሕያው ሆኖ ለአብና


ከዊነ እስትንፋስ (እስትንፋስ መሆን) ለወልድ ሕይወት መሆን ነው።

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org
ይቆየን !

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ማኅበረ ቅዱሳን ዋና መካነድር፦ የርቀት ትምህርት ድረገጽ፦


www.eotcmk.org elearning.eotcmk.org

You might also like