You are on page 1of 2

አንድ ሰው ጌታን ሲቀበል ምን አዲስ ነገር ያገኛል

የመንፈሳዊ አስተማሪዬ እንዲህ ብለው ተናገሩ፤ አንድ ሰው ሀጢአቱን በመናዘዝ ጌታን ሲቀበል 38 ነገሮች
ይከናወናሉ፡፡ አርሰሱግን የሚገነዘባቸው የሃጢአት ስርየትን ሰላምንና ደስታን ብቻ ነው፡፡

፻.ከእግዚአብሔር አባት ጋር በተመለከተ

1. ወደ እግዚአብሄር ጸጋ ይቀርባል ኤፌሶን 2፡18 በመጀመሪያ ለመዳን ቀጥሎም ለፀሎት እንቀርባለን ዔፌሶን 3፤ 12

2. እንደልጅ ወደ እግዚአብሄር ቤተሰብ ይገባል ገላ 4፤15 ኤፌሶ 1፣5

3. የእግዚአብሂር እርስት ወራሽ መሆን ሐ/ስራ 26፤18

4. በእግዚአብሄር መመረጥ 1 ጴጥ 1፤2 ኤፌ 1፤4 ዮሐ 15፤16

5. የእግዚአብሄር ልጅ መሆን ዮሐ 1፤12 1 ዮሐ 3፡1

6. ሰማያዊ ዜግነት ፊሊጲ 3፤20

7. የእግዚአብሄር ርስት ወራሽ ይሆናል ሮሜ 8፤17 ገላ 3፤29

8. አዲስ ፍጥረት መሆን 2 ቆሮ 5፤17

9. የእ/ር አገልጋይ መሆን ፡፡ ሮሜ 6፤22 ሮሜ 1፤1

10. የእ/ር ሊቀካህን መሆን ፡፡ 1 ጴጥሮስ 2፤9

11. ከእ/ር ጋር መታረቅን አግኝቷል ፡፡ ሮሜ 5፤10

12. ቅድስና አግኝቷል 1 ቆሮ 6፡11 ፡፡ ሐሥ 26፣18

ከእ/ር ወልድ ጋር በሆነ ነገር

13. በተወደደው በክርስቶስ በኩል በእግዚአብሄር ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ፡፡ ኤፌ 1፤6

14. በክርስቶስ ውስጥ መጠመቅ ፡፡ 1 ቀሮ 12፤13 ገላ 3፣21

15. ከክርስቶስ ጋር መቀበር ፡፡ ሮሜ 6፤4 ቆላ 3፤3

16.ከአባት የፍቅር ስጦታ ሆኖ ለወልድ መሰጠት ፡፡ ዮሐ 17፤9

17. በክርስቶስ መዳን ፡፡ ሐሥ 4፤12

18. በክርስቶስ ውስጥ መኖር ፡፡ ዮሐ ራዕ 3፤20 ዮሐ 14፡23

19. በክርስቶስ የዘላለምን ህይወት ማግኘት ፡፡ ዮሐ 10፣28 1 ዮሐ 5፤13

20. ሰላም ያገኛል፡፡ ዮሐ 14 ፤27 ፊል 4፤7

21.የእግዚአብሔር ወዳጅ መሆን፡፡ ዮሐ 15፤15

22. በሰማይ ስሙ ይፃፋል፡፡ ሉቃስ 10፤20 ፊሊጲ 4፤3

23. በሰማይ ሰማያት ከክርስቶስ ጋር ይቀመጣል፡፡ ኤፌ 2፤6


አንድ ሰው ጌታን ሲቀበል ምን አዲስ ነገር ያገኛል

24.ከስላሴዎች ጋር ህብረት ይኖረዋል፡፡ 1 ዮሐ 1፤3 ህብረታችን ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው

25.የተባረከ ተስፋ ማግኘት ፡፡ ቲቶ 2፤13

26. የክብር መኖሪያ ባለቤት መሆን ፡፡ ዮሐ 14፤2

እግዚአብሄር መንፈስቅዱስን በተመለከተ

27. እንደገና መወለድ ዮሐ 3፤3፤7

28. በመንፈስቅዱስ ቅብአት መቀባት 1 ዮሐ 2፤27 ዮሐ 14፤26፣16፤13

29.የመንፈስቅዱስ ማደሪያ ይሆናል 1 ቆሮ 6፤12

You might also like