You are on page 1of 4

በለሚኩራ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የ6ኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ ሞዴል ግንቦት 2015 ዓ.

የተሰጠ ሰዓት 1፡00 አካባቢ ሳይንስ

I. የሚከተሉትን ጥያቄዎች ካነበባችሁ በኋላ ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል በመምረጥ በመልስ መሥጫ
ወረቀቱ ላይ መልስ የያዘውን ፊደል አጥቁሩ
1. ከሚከተሉት ውስጥ መሬትን በሰሜንና በደቡብ እኩል የሚከፍል የሀሳብ መስመር የትኛው ነው ?
ሀ. ግሪኒዊች ሜሪዲያን ሐ. ትልቁ ሜሪዲያን
ለ. አብይ ቋሚ መስመር መ. የምድር ወገብ
2. ምሥራቅ አፍሪካን የሚያዋስኑ ውሀማ አካላት የትኞቹ ናቸው ?
ሀ. የህንድ ውቅያኖስ ሐ. የኤደን ባህረ ሰላጤ
ለ. የቀይ ባህር መ. ሁሉም መልስ ናቸው
3. በምሥራቅ አፍሪካ በእሳተ ገሞራ ፍንዳታ ያልተፈጠረው ተራራ የትኛው ነው ?
ሀ. የኪሊማንጃሮ ተራራ ሐ. የራስ ደጀን ተራራ
ለ. የሩዋንዝሪ ተራራ መ . የኬንያ ተራራ
4. የታላቁ ምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መነሻ የሆነችው ሀገር የትኛዋ ናት ?
ሀ. ሶሪያ ሐ. ታንዛንያ
ለ. ኬንያ መ. ኢትዮጵያ
5. የአንድን ቦታ አቅጣጫ ፣ የገቢያ ትስስርና መልዕክትን ለማድረስ የሚጠቅመው መተግበሪያ የትኛው ነው ?
ሀ. ጂ.ፒ.ኤስ ሐ. ጎግል ካርታ
ለ. ጎግል ኸርዝ መ. መልስ የለም
6. ከሚከተሉት የደም ህዋሶች ውስጥ ኦክስጅንን ከሳንባ ተቀብለው በመሸከም ለመላው የሰውነታችን ህዋሶች
የሚያደርሱት የትኞቹ ናቸው ?
ሀ. ነጭ የደም ህዋሶች ሐ. ፕላትሌቶች
ለ . ቀይ የደም ህዋሶች መ. ሁሉም መልስ ናቸው
7. የልብ ትርታን የምናዳንጥበት መሳሪያ ምን በመባል ይታወቃል ?
ሀ. ማይክሮስኮፕ ሐ. ቴሌስኮፕ
ለ. ስቴቶስኮፕ መ. ለ እና ሐ መልስ ናቸው
8. በወንዶችና በሴቶች ላይ የሚከሰተው የጋራ የሆነው ስነ ህይወታዊ ለውጥ የቱ ነው ?
ሀ. በብብት ስር ፀጉር ማብቀል ሐ. በብልት አካባቢ ፀጉር ማብቀል
ለ. የዳሌ መስፋት መ. ሀ እና ሐ መልስ ናቸው
9. ናይትሮችንና ኦክስጅን ከአጠቃላይ ከባቢ አየር ምንዝሮች ስንት በመቶ ድርሻ አላቸው ?
ሀ. 99% ሐ. 78%
ለ. 98% መ. 89%
10. ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ፈሳሾችን በድብልቁ ውስጥ ባላቸው የነጥበ ፍሌት ልዩነት የምንለይበት የመለያ
ዘዴ የትኛው ነው ?
ሀ. ንጥረት ሐ. ቀረራ
ለ. ትነት መ. ጥሊያ
በለሚኩራ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የ6ኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ ሞዴል ግንቦት 2015 ዓ.ም

II. ቀጥሎ የተቀመጠውን ስዕል መሰረት በማድረግ ከተራቁጥር 11 እስከ ተራቁጥር 14 ላሉት ጥያቄዎች
ትክክለኛውን መልስ በመምረጥ በመልስ መስጫ ወረቀት ላይ አጥቁሩ ፡፡

11. ከዐብይ ትንቧ ወደ ሳንባ ለሚገባውና ለሚወጣው አየር መተላለፊያ የመተንፈሻ አካልን የሚያመለክተው
ቁጥር የትኛው ነው ?
ሀ. 1 ሐ. 4
ለ. 3 መ. 2
12. አየር የሚያሞቅ እንዲሁም ቆሻሻንና ጀርሞችን የሚያጣራውን የመተንፈሻ አካል የሚያመለክተው ቁጥር
የትኛው ነው?
ሀ. 2 ሐ. 4
ለ. 1 መ. 3
13. ወደ ባላ ትንቧ ለሚገባው እና ለሚወጣው አየር መተላፊያ በመሆን የመተንፈሻ አካልን የሚያመለክተው
ቁጥር የትኛው ነው?
ሀ. 4 ሐ. 2
ለ. 3 መ. 1
14. ወደ ታች ሲወርድና ወደቦታው ሲመለስ የአየር ግፊት እንዲጨምርና እንዲቀንስ የሚያደርገውን የመተንፈሻ
አካል የያዘው ቁጥር የትኛው ነው ?
ሀ. 3 ሐ. 4
በለሚኩራ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የ6ኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ ሞዴል ግንቦት 2015 ዓ.ም

ለ. 1 መ. 2
15. ክብደት ያላቸውን ነገሮች ለመጫንና ለማውረድ የሚጠቅመው የቀላል ማሽን አይነት የትኛው ነው ?
ሀ. ዘንባይ ወለል ሐ. መፈንቅል
ለ. ሽክርክሪት ዘንግ መ. ሽብልቅ
16. ሁልጊዜ ያለማቋረጥ በስራ ላይ የሚገኘው የሰውነታችን ክፍል የትኛው ነው ?
ሀ. አፍ ሐ. ዐይን
ለ. ልብ መ. ኩላሊት
17. ከሚከተሉት ውስጥ የአየር ንብረት ተቆጣጣሪ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የውቅያኖስ ሞገድ ሐ. የሙቀት መጠን
ለ. ከምድር ወገብ ያለው ርቀት መ. ከፍታ
18. በምሥራቅ አፍሪካ ማዕድናትን አውጥቶ ለመጠቀም ዓበይት ተግዳሮቶች ከሆኑት ውስጥ የሚመደበው
የትኛው ነው ?
ሀ. በቂ የመሰረተ ልማት አለመኖር ሐ. የቴክኖሎጂ እጥረት
ለ. የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት መ. ሁሉም
19. ደን ባልነበረበት ስፍራ ችግኞችን የመትከል ተግባር ምን ይባላል?
ሀ. ዳግም ድነና ሐ. ጣምራ የደን እርሻ
ለ . የእርከን ስራ መ. ድነና
20. ከሚከተሉት ውስጥ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ያልሆነው የትኛው ነው ?
ሀ. ካቦራ ባሳ ሐ. ቪክቶሪያ
ለ. ካሪባ መ. ቆቃ
21. ቅጠላቸውን አርጋፊ እጸዋቶች በበጋ ወራት ቅጠላቸውን የሚያራግፉበት ዋና ምክንያት ምንድነው ?
ሀ. ውሀ በትነት መልክ እንዲወጣ ሐ. ትንፈሳን ለማካሄድ
ለ. ውሀ በትነት መልክ እንዳይወጣ መ. ሁሉም
22. ከሚከተሉት ውስጥ የሞቃት በርሀ እፅዋት ያልሆነው የትኛው ነው ?
ሀ. ጥድ ሐ. ቁልቋል
ለ. ግራር መ. መልስ የለም
23. በአንድ መልክዓ ምድራዊ ክልል ውስጥ ያለውን የሰው አሀዛዊ ቁጥርን መጠን ማሳያ የሆነው የትኛው ነው ?
ሀ. የህዝብ ብዛት ሐ. የህዝብ ስርጭት
ለ. የህዝብ እድገት ምጣኔ መ. የፆታና የእድሜ ስብጥር
24. በምሥራቅ አፍሪካ ካሉ ሀገራት በህዝብ ብዛት አነስተኛዋ ሀገር ማናት ?
ሀ. ኢትዮጵያ ሐ. ሶማሊያ
ለ. ሲሸልስ መ. ኤርትራ
25. የኩሽ መንግስት የመጀመሪያ ዋና ከተማ ማን በመባል ይታወቅ ነበር?
ሀ. ሜሶፖታሚያ ሐ. ናፓታ
ለ. ሜሮይ መ. መልስ የለም
26. ለሜሮይ ስልጣኔ ማሽቆልቆል ዋናው ምክንያት ምን ነበር?
ሀ.የአክሱም መንግስት መዳከም ሐ.የሙስሊም አረቦች ተቃዋሚ ሀይል መነሳት
ለ.የኑቢያ ጥንታዊ ስልጣኔ መነሳት መ. የአክሱም መንግስት መነሳት
27. ከሚከተሉት ውስጥ መንፈሳዊ ቅርስ ያልሆነው የትኛው ነው?
ሀ. የባህል ጀግንነት ሐ. ሀይማኖታዊ ስርዓቶች
ለ. ትርኢቶች መ. ቅሪተ አፅሞች
28. የሀረር ጀጎል ግንብ የተገነባት ዋና ምክንያት ለምን ነበር ?
ሀ. ለመዝናኛነት ሐ. ከተማዋን ከጎርፍ ለመከላከል
ለ. ከተማዋን ከወራሪዎች ለመከላከል መ. ሁሉም
በለሚኩራ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የ6ኛ ክፍል አካባቢ ሳይንስ ሞዴል ግንቦት 2015 ዓ.ም

29. የአፍሪካ ትልቁ የቪክቶሪያ ፋፋቴ የተፈጠረው በየትኛው ወንዝ ነው ?


ሀ. በታና ወንዝ ሐ. በአባይ ወንዝ
ለ በዛምቤዚ ወንዝ መ. በሩቩማ ወንዝ
30. በስተምዕራባዊ አቅጣጫ ለብቻው የሚገኘው የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያን የቱ ነው ?
ሀ. ቤተ-መድኃንዓለም ሐ. ቤተ-ጊዮርጊስ
ለ .ቤተ-ማርያም መ. ቤተ- መርቆርዮስ
31. ጥሬ ሀብትን ዘመነዊ የማረቻ መሳሪያችን ለመጠቀም ለተጠቃሚዎች የሚሆን ምርት የሚያቀርብ ተቋም ምን
ይባላል ?
ሀ. ግብርና ሐ. ኢንዱስትሪ
ለ. ቱሪዝም መ. ንግድ
32. ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል በኢንዱስትሪ የምትታወቀው ሀገር የትኛዋ ናት ?
ሀ. ኬንያ ሐ. ኢትዮጵያ
ለ. ኤርትራ መ. ታንዛኒያ
33. አንድ ሀገር ከሌሎች ሀገሮች ጋር የሚያደርገው እቃዎችን የመሸጥና የመግዛት ሂደት ይባላል፡፡
ሀ. የውጪ ንግድ ሐ. የንግድ ልውውጥ
ለ. የውስጥ ንግድ መ. ሁሉም
34. የኢጋድ አባል ሀገራት መቀመጫ የት ነው ?
ሀ. ታንዛንያ ሐ. ኬንያ
ለ. ጅቡቲ መ. ሶማሊያ
35. ከሚከተሉት ውስጥ ለናይል ወንዝ ምንም አስተዋፅኦ የሌላት ሀገር የትኛዋ ናት ?
ሀ. ኤርትራ ሐ. ግብጽ
ለ. ጅቡቲ መ. ታንዛንያ
36. ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ የማይተላለፍባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው ?
ሀ. ስለታማ ነገሮችን በጋራ በመጠቀም ሐ. ያልተመረመረ የደም ልገሳ
ለ. ልቅ የሆነ የግብረስጋ ግንኙነት መ. በነፍሳት መነከስ
37. ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስን ለመከላከል ከህይወት ክህሎት ውስጥ የማይመደበው የትኛው ነው ?
ሀ. መተሳሰብ ሐ. ጭንቀትን አለመቋቋም
ለ. ራስን መግዛት መ. መተባበር
38. በትንባሆ ቅጠል ውስጥ የሚገኝ ኬሚካል ምን ይባላል ?
ሀ. ኢታኖል ሐ. ኒኮቲን
ለ. ካቴኒን መ. ሁሉም
39. አንድ ሴት ልጅ ካለፍላጎቷ በግዳጅ በማታውቀው( በምታውቀው) ወንድ ለጋብቻ መወሰድ ምን ይባላል ?
ሀ. ጠለፋ ሐ. የሴት ልጅ ግርዛት
ለ. ያለእድሜ ጋብቻ መ. አስገድዶ መድፈር
40. በዓለም የተመዘገቡ የተለያዩ የተፈጥሮ እጽዋት የሚገኙበት በየትኛው ቦታ ነው ?
ሀ. የሳር ምድር በኬንያ ሐ. ደንከል በረሀ
ለ. የተፈጥሮ ደን በዩጋንዳ መ. ማሳይማራ

You might also like