You are on page 1of 4

አቤኔዘር ትምህርት ቤት

(ከአፀደ ሕፃናት እስከ ኮሌጅ መሰናዶ )

ቢሾፍቱ

2012 ዓ.ም የ2ኛ መንፈቀ ዓመት ሕብረተሰብ የክለሳ ጥያቄዎች ለ7ኛ ክፍል የተዘጋጀ

ስም ክፍል ቁጥር ሰዓት፡- 1፡00

አስተውላችሁ አንብቡ:-

እንደሚታወቀው ይህ ወቅት መልካም የሚባል አይደለም:: ነገር ግን አስተውሎ በመራመድ ይህን ክፉ ነገር ማለፍ
ይቻላል:: እናንተም ይህ ጊዜ እንደሚያልፍ ሙሉ በሙሉ በመተማመን ትምህርታችሁን ባላችሁ መፅሀፍ እና
ደብተር በመጠቀም መከታተል እንዳታቆሙ::

በድጋሚ ላስታውሳችሁ የምፈልገው ነገር ቢኖር

 ፀሎት ማድረግ ሁልጊዜ እንዳትዘነጉ


 ቤተሰብ የሚላችሁን ነገር ብቻ አድርጉ
 በትርፍ ጊዜያችሁ ፊልሞች የሀገር ውስጥም ሆነ የውጪ ሀገር ከጥቅማቸው ጉዳታቸው ስለሚያመዝን
በታማኝነት አትመልከቱ… የምትመለከቱትን ፕሮግራም ከቤተሰብ ጋር ሆናችሁ ምረጡ
 ከቤት አትውጡ… በየቀኑ የሰራችሁትን ስራ መዝግቡ… ጊዜያችሁን ያለአግባብ አታጥፉ… ጊዜን
ያለአግባብ መግደል COVID 19 ከሚያስከትለው ጉዳት አይተናነስም እና ጊዜያችሁን በአግባቡ
ተጠቀሙ

የባለፈውን ጥያቄዎች ሰርታችኋል ብዬ በመተማመን ከዚህ በታች ከመፅሀፋችሁ ምዕራፍ 4ን በማንበብ


የተሰጡትን 40 ጥያቄዎች በደብተራችሁ ላይ ስሩ….…. መልካም ጊዜ

በ 4ኛው ምዕራፍ የሚገኘው ዋነኛ ሀሳብ የሕዝብ አጀንዳ ወይም ጉዳይ ሲሆን በዋናነት የተካተቱት ሀሳቦች

 HIV/AIDS በማህበረሰብ ላይ ያደረሰው ተፅዕኖ


 የሕዝብ በከፍተኛ ፍጥነት መጨመር እና የሚያስከትለው ተፅዕኖ
 ስለ መብት በተለይም የሕፃናት መብት ፣ ሰላም እና በሰላም እጦት ምክኒያት ስለሚከሰት እርስበርስ
ጦርነት
 ስለ መልካም አስተዳደር
 በአፍሪካ ውስጥ ስላሉ የትብብር ተቋማት በስፋት ተካቷል

በመጽሀፋችሁ ላይ በስፋት የተካተተ ሀሳብ ስለሆነ መፅሀፋችሁን በደንብ አንብቡ እና ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች
ስሩ

1. HIV/AIDS ምንነቱን ተንትናችሁ ፃፉ?


ገፅ 1
2. HIV/AIDS በአጭር ጊዜ ውስጥ በተለያዩ አህጉራት ውስጥ እንዴት ሊስፋፋ ቻለ?
3. HIV/AIDS እና COVID-19 ቫይረስ ለአለም ሕዝብ ካላቸው ስጋትነት አንጻር የሚያመሳስላቸው ነገር
አለ ብላችሁ ታስባላችሁ?
4. HIV/AIDS በዋናነት አብዛኛውን ጊዜ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከ16-24 እድሜ ክልል ውስጥ
ያሉትን ወጣቶች ያጠቃል:: ይህ እድሜ ደግሞ የተማሪነት እድሜ ነው:: ለሀገርም ይህ ከፍተኛ አምራች
የሆነን ሀይል ማጣት ነው:: ለዚህ ዋነኛ ምክኒያቱ ምንድ ነው አብራርታችሁ ፃፉ?
5. HIV/AIDS ከሌሎች አህጉራት በበለጠ በአፍሪካ አህጉር ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል ለዚህ ምክኒያቱ ምን
ይመስላችኋል?
6. HIV/AIDS ን ለመከላከል በዋናነት ምን ምን ተግባሮችን ማከናወን አለብን? ከሚመጣበት ምክኒያቶች
ጋር አብራርታችሁ ፃፉ?
7. ለሕዝብ ቁጥር በፍጥነት መጨመር ዋነኛ ምክኒያት የሚባሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?
8. በአፍሪካ ለሕዝብ ቁጥር መጨመር ምክኒያቶች የሚባሉት ዋነኞቹ ምን ምን ናቸው? እንዴት እንዲጨምር
እንደሚያደርጉ ግለፁ?
9. የሕዝብ ቁጥር በከፍተኛ ቁጥር መጨመር በቤተሰብ ደህንነት ላይ፣ በእርሻ መሬት ላይ፣ በማህበራዊ
አገልግሎት ላይ፣ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለውን ተጽዕኖ አብራርታችሁ ግለፁ?
10. ፈጣን የሆነ የሕዝብ እድገት መጠንን ለመቀነስ በዋናነት ምን ምን ማድረግ አለብን?
11. መብት እና ሰላም ትርጉማቸውን፣ አንድነታቸውን እና ጥቅማቸውን ግለፁ?
12. በሕፃናት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ምን ምን ናቸው? ዘርዝራችሁ ፃፉ?
13. በአለም አቀፍ ደረጃ የሕፃናት መብቶች ስምምነትን አሜሪካ እና ሶማሊያ አልፈረሙም ለምን?
14. በተባበሩት መንግስታት በ1989 የተፈረመው የሕፃናት መብቶች ስምምነት በምን ምን መርሆች ላይ
የተመሰረተ ነው?
15. ሕፃናት ከሚደርስባቸው አደጋዎች ወይም የተለያዩ ጥቃቶች እንዴት ማምለጥ ይችላሉ?
16. መልካም አስተዳደር ማለት ምን ማለት ነው?
17. የመልካም አስተዳደር 8 ዋና ዋና መገለጫዎችን ዘርዝራችሁ በመፃፍ አብራሩዋቸው?
18. ሙስና ማለት ምን ማለት ነው?
19. የሙስና አይነቶች፣ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ እና እንዴት ከሕዝብ መካከል መቀነስ እንደሚቻል ግለጹ?
20. ኮንትራባንድ ምንድነው? አብራርታችሁ ግለፁ?
21. የእርስበርስ ጦርነት እንዴት ይከሰታል? ዋነኛ የእርስ በርስ መነሻ ምክኒያቶችን ዘርዝራችሁ አብራሩዋቸው?
22. በአፍሪካ የእርስ በርስ ጦርነት በብዛት የሚካሄድባቸው እና ተካሂዶባቸው የሚያውቁ ሀገራትን ፃፉ?
23. የእርስ በርስ ጦርነትን እንዴት መከላከል እና ማጥፋት ይቻላል?

ገፅ 2
የትብብር ተቋማትን በተመለከተ በምርጫ መልክ ትሰራላችሁ
24. የምዕራብ አፍሪካ የገንዘብ ዞን በስንት ሀገራት ተመሰረተ?

ሀ. 21 ለ. 5 ሐ. 8 መ. 15

25. የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የልማት ኮሚቴ መቀመጫ የት ሀገር ይገኛል?

ሀ. ቦትስዋና ለ. ዛምቢያ ሐ. ናይጄርያ መ. ጂቡቲ

26. በስፓኒሽ ሰሀራ ባለቤትነት ላይ ከህብረቱ ጋር በተፈጠረ የሀሳብ ልዩነት የአፍሪካ ህብረት እንደተመሰረተ

ከአባልነት የወጣች ሀገር የቷ ነች?

ሀ. ሞሮኮ ለ. ጊኒ ሐ. ማዳጋስካር መ. ኒጀር

27. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ተጠባባቂ ዋና ፀሀፊ የነበረው ሰው የቱ ነው?

ሀ. ኢዴ ኦማሩ ለ. ሳሊም አህመድ ሳሊም ሐ. ፒተር ኦኑ መ. ድያሎ ቴሊ

28. የምዕራብ አፍሪካ የሆነው ትብብር ተቋም የቱ ነው?

ሀ. SADC ለ. ECOWAS ሐ. COMESA መ. NEPAD

29. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የት እና በስንት ዓ.ም ተቋቋመ?

ሀ. ሎሜ፣ 2000ዓ.ም ለ. ሰርጤ፣ 1999ዓ.ም

ሐ. ፊንፊኔ፣ 1963ዓ.ም መ. ደርባን፣ 2002ዓ.ም

30. የምዕራብ አፍሪካ የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ህብረት አባል ሀገር ያልሆነው የቱ ነው?

ሀ. ቶጎ ለ. ማሊ ሐ. ጊኒ ቢሳው መ. ማላዊ

31. የ COMESA መቀመጫ የት ሀገር ይገኛል?

ሀ. ዛምቢያ፣ ሉሳካ ለ. ናይጄርያ፣ አቡጃ

ሐ. ቦትስዋና፣ ጋቦሮኒ መ. ፊንፊኔ፣ ኢትዮጵያ

32. የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ስንት አባል ሀገራት አሉት?

ሀ. 15 ለ. 21 ሐ. 8 መ. 12

33. ECOWAS በስንት ሀገራት እና የት ተመሰረተ?

ሀ. አቡጃ፣ በ15 ለ. ሌጎስ፣ በ21 ሐ. ሴኔጋል፣ በ8 መ. ሌጎስ፣ በ15

34. ከሚከተሉት የትብብር ተቋማት አንዱ አህጉር አቀፍ ነው?

ሀ. ECA ለ. PTA ሐ. IGAD መ. ECOWAS

35. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ወደ አፍሪካ ህብረት የተቀየረው የት ሀገር ነበር?

ሀ. ደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ለ. ቶጎ ሐ. ሊብያ መ. ናይጄርያ


ገፅ 3
36. ከምእራብ አፍሪካ የገንዘብና ኢኮኖሚ ህብረት አባል ሀገራት የፖርቹጋል ቅኝ ግዛት የነበረችው የቷ
ነች?

ሀ. ኮትዲቯር ለ. ጊኒ ሐ. ቤኒን መ. ጊኒ ቢሳው

37. የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ ዋና ፅህፈት ቤት የት ይገኛል?

ሀ. ጋቦሮኒ ለ. ፊንፊኔ ሐ. አቡጃ መ. ሉሳካ

38. ከሚከተሉት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሀፊዎች አንዱ ታንዛኒያዊ ነበሩ?

ሀ. ኤዴም ኮጆ ለ. ድያሎ ቴሊ ሐ. ሳሊም አህመድ ሳሊም መ. ኢዴ ኦማሩ

39. የአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቼ እና እና የት ተመሰረተ?

ሀ. ፊንፊኔ፣ ግንቦት 23, 1964 ለ. ጆሀንስበርግ፣ ግንቦት 23, 1963

ሐ. ሎሜ፣ ሐምሌ 9, 2002 መ. ፊንፊኔ፣ ግንቦት 23, 1963

40. ኔልሰን ሮሊሃላሃላ ማንዴላ ብለን ደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ካልን ሮበርት ሙጋቤ ብለን?

ሀ. ዛምቢያ ለ. ዙምባብዌ ሐ. ግብፅ መ. ሴኔጋል

እንዳትረሱ የዛሬ ስራችሁ ለነገ ማንነታችሁ ወሳኝ ነውና በማስተዋል ተንቀሳቀሱ

ገፅ 4

You might also like