You are on page 1of 2

አቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ

Abune Gorgorious SchoolsLebu Branch


2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ወሰነ ትምህርት የሥነ - ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት መለማመጃ ሁለት ለ 6 ኛ
ክፍል
ስም ክፍል ቁጥር

ሀ. የሚከተሉትን ጥያቄዎች በጥሞና ካነበባችሁ በኋላ ትክክል ከሆነ “እውነት” ትክክል ካልሆነ ደግሞ “ሐሰት” በማለት መልስ መስጫ
ቦታው ላይ ፃፉ፡፡

1. ቁጠባ ማለት ጊዜን ፣ ጉልበትን እና እውቀትን ተጠቅሞ ከተገኘ ገቢ አሉታዊ


ፍጆታዎችን ሳያሟሉ ገንዘብ ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡

2. ባንክ እና እቁብ ባህላዊ የገንዘብ መቆጠቢያ ተቋማት ናቸው፡፡


3. በኮንትሮባንድ ንግድ ከባህላችን ጋር ተፃራሪ የሆኑ እና ከማህበራዊ ህይወት ውስ
ችግር የሚያስከትሉ ፓስተሮች እና ፊልሞች ወደ ሀገር ውስጥ ይገባሉ፡፡

4.የአስተሳሰብ ድህነት ከገንዘብ ድህነት እጅግ አስከፊ ነው፡፡


5. የትምህርት እድል ማጣት፣ ረሀብ እና መጠለያ ማጣት ድህነት እንለዋለን፡፡

ለ. በ “ሀ” ረድፍ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች በ “ለ” ረድፍ ከተሰጡት ተስማሚያቸው ጋር በመምረጥ አዛምዱ፡፡

“ሀ” “ለ”
1. በራስ መተማመን ሀ. በራስ መተማመንን ያዳብራል

2. ጥገኝነት ለ. ስለራስ ትክክለኛ ግንዛቤ መኖር

3. ራስን የመቻል ጠቀሜታ ሐ. ገንዘብና ንብረትን ያለእቅድ ማውጣት እና መጠቀም

4. ጥገኝነትን መፀየፍ መ. ሌሎች በደከሙበት ውጤት ለመኖር አለመፈለግ

5. ብኩንነት ሠ. በሌሎች ሠዎች እውቀት እና ገንዘብ መኖር

ሐ. ከሚከተሉት ጥያቄዎች ከተሰጡት አማራጮች መካከል ትክክለኛ መልስ የያዘውን ፊደል በመምረጥ በተሰጠው ከፍት ቦታ ላይ ፃፉ፡፡

1.ከተሰጡት አማራጮች መካከልየኮንትሮባንድ ንግድና ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ


ጫና ያልሆነው የትኛው ነው?

ሀ. ህጋዊ ነጋዴውን ከገበያ ውጭ ያደርጋል

ለ. በአነስተኛ የንግድ ምርት ሥራ ውስጥ የተሰማሩትን ዜጎች ያበረታታል

ሐ. ህብረተሰቡን የሚጎዱ ጥራታቸው ያልተጠበቀ እቃዎች እንዲገቡ ያደርጋል

2. በራስ የመተማመን ባህሪ መገለጫ መንገድ የሆነው የትኛው ነው?


ሀ. የሌሎችን ፍላጎችት እና አስተሳሰብ ማክበር

ለ. የራስን ብቃት እና ችሎታ አሳንሶ መመልክት

ሐ. ስህተትን አምኖ አለመቀበል

መ. ራስን አለማወቅ
3. ከሚከተሉት ውስጥ የቁጠባ አስፈላጊነትን የሚገልፀው ሀሳብ የትኛው ነው?
ሀ. ራስን እና ቤተሰብን በትምህርት ለማሳደግ ለ. ከጥገኝነት ለመላቀቅ

ሐ. ራስን ለመቻል መ. ሁሉም

4. የቁጠባ ባህልን የሚፃረር ተግባር ያልሆነው የቱ ነው?


ሀ.ከአቅም በላይ ድግስ ሐ. ሠዎች ተሳስበው እቁብ መግባት

ለ. ኋላ ቀር አመለካት መ. የቅንጦች እቃ መግዛት

5. ለትርፍ ያልተቋቋመ እና በአንድ አካባቢ የሚተዋወቁ ሠዎች በችግር እና


በሀዘን ጊዜ የሚረዳዱበት ማህበር ምን ይባላል?

ሀ. ባንክ ለ. እድር ሐ. እቁብ መ. ሁሉም

6. ለአንድ ሀገር መሠረት የሆነው የቱ ነው?


ሀ. ጥገኝነት ለ. በራስ መተማን ሐ. ልመና መ. ጠንካራ የሥራ ባህል

7. እቃዎችን በህገ ወጥ መንገድወደ ሀገር የማስገባት እና ከሀገር ውጪ የመላክ


ሂደት ይባላል?

ሀ. ራስን መቻል ለ. ጥገኝነት ሐ. ኮንትሮባንድ መ. በራስ መተማመን

8. የድህነት አስከፊነት የሚገልፀው ሃሳብ የቱ ነው?


ሀ. ክብርን ያጎናፅፋል ሐ. ስብዕናን ያሳጣል

ለ. ረሀብን ያስከትላል መ. የሚወዱትን ያሳጣል

መ. ለሚከተሉት ጥያቄዎች አጭር መልስ ስጡ፡፡

1. ኋላቀር አመለካከት ሲባል ምን ማለት ነው

2. የእቁብ እና የእድር አንድነትና ልዩነት አብራሩ፡፡

You might also like