You are on page 1of 1

ግንቦት 28 ቀን 2012

ዓ/ም ለፈድራል መንግስት ቤቶች ኮርፖሬሽን


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡ያለሁበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ስለመግለጽ እና ቤት ኪራይ አእንዲሰጠኝ


ስለመማጸን

አመልካች ስሜ በስተመጨረሻው ላይ የተጠቀሰው እና በአርት (በተዋናይነት) ሙያ ላይ


በመሰማራት ራሴንና ቤተሰቤን ሳስተዳድር የቆየሁ ነኝ፡፡
ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው በሙያዬ በርከቱ ያሉ ስራዎችን የሰራሁ እና ከተለያዩ የግብረ
ሰናይ ድርጅቶች ጋር በመሆን በበጎ ፈቃድ ሙያዬን እና ዝናዬን በመጠቀም ለድርጅቶቹ በርካታ
የገቢ ማሰባሰቢያዎችን የሰራሁ ሲሆን በተያያዘም በተለያዩ ሀገራዊ ስራዎችን በፈቃደኝነት
ያለምንም ክፍያ የራሴን አስተዋጻኦ አበርክቻለሁ ፡፡ ሆኖም ግን በሙያዬ ላይ በመተማመን
ትዳር መስርቼ ሁለት ልጆችን ያፈራሁ ሲሆን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከልጆቸ አባት ጋር
ተለያይተን የእግዚያብሄር ስጦታ የሆኑትን እነዚህን ልጆቼን በብቸኝነት እያሳደግሁ እገኛለሁ፡፡
ኑሮዬን ስገፋም የግለሰብ ቤትን ተከራይቼ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ኝ ፈጽሞ ልቋቋመው
ያልቻልሁት ደረጃ ላይ በመድረሴ በዚህ ማመልከቻዬ አማካኝነት መ/ቤታችሁን ለመማጸን
ተገድጃለሁ፡፡
በግልጽ እንደሚታወቀው በጽቅሉ ከሚኖር የህይወት ጫና በተጨማሪ በኮሮና መከሰት ሳቢያ
በወቅቱ በተፈጠረው ሁኔታ የተነሳ የአርት ስራ ዘርፍ ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ
የተቋረጠ በመሆኑ እኔም ከነቤተሰቤ የጥቃቱ ሰለባ ሁኜ ልጆቼም ለችግር ተጋልጠውብኛል ፡፡
በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ይቅርና በመደበኛው የህይወት ጎዳና ሂደትም የግለሰብን ቤት
ተከራይቶ መኖር ምንም ያህል አዳጋች እንደሆነ ማንኛውም ሰው ይገነዘባልብዬ አምናለሁ፡፡
በመሆኑም ድርጅታችሁ ማንኛውንም አይነት ቤት በየትኛውም አካባቢ በኪራይ እንድሰጠኝ
በትህትና እየተማጸንሁ የችግሬን መጠንና ጥልቀት በአካልክ ቀርቤ በዝርዝር ለማስረዳት ዝግጁ
መሆኔን እገልጻለሁ፡፡

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
አርቲስት ኤደን ሽመልስ

You might also like