You are on page 1of 2

ቀን 04/09/2015 ዓ.

 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

ወልደያ ድስትሪክት

ጉዳዩ ፡- የብድር መክፈያ ጊዜ እንዲራዘምልኝ ስለመጠየቅ፡-

ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት እኔ አመልካቹ ወ/ዮሐንስ አስፋዉ ኗሪነቴ በላሊይበላ ከተማ አስተዳደር

ደብረዘይት ቀበሌ አደባባይ አካባቢ ሲሆን በሆቴልና ሪሰቶራንት ኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርቼ እየሰራሁ መሆኑ

ይታወቃል ፡፡

በመሆኑም ለዚህ ለምሰራው ኢንቨስትመንት ማጠናቀቂያ እና የስራ ማስኬጃ የሚሆን ብድር የኢትዮጵያ

ንግድ ባንክ በመጀመሪያ በ 2013 ዓ.ም 3,200,000/ሶስት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሽህ ብር በሶስት አመት ተከፍሎ

የሚያልቅ እንዲሁም ተጨማሪ የስራ ማስኬጃ በ 2015 ዓ.ም 5,000,000 ብር በ 3 አመት ተከፍሎ የሚያልቅ

ብድር ተፈቅዶልኝ ወደ ስራ መግባቴ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም እነዚህ ሁለቱም የስራ ማስኬጃ ብድሮች

ከተፈቀደልኝ ጊዜ ጀምሮ ብድሩንም ለታለመለት አላማ በማዋልና የወሰድኩትንም ብድር በዉለታየ መሰረት

በመክፈል ግዴታየን እየተወጣሁ ቆይቻለሁ፡፡ በዚህም በዉሌ መሰረት ማለትም ከመጀመሪያዉ ብድር በየ ሶስት

ወሩ ማለትም 192,378.66 ሁለተኛዉ ብድር በየ ሶስት ወሩ 529,278.59 በድምሩ 721,657.25 ብር በየ ሶስት

ወሩ እየከፈልኩ ቆይቻለሁ፡፡

ነገር ግን አሁን ከተማችን ላይ ካለዉ የገባያ እንቅስቃሴ መዳከም አንፃር ማለትም ከተማችን የሚታወቅበትና

ትልቁ የገቢ ምንጩ ቱሪዝም ላይ የተመሰረተ ከመሆኑ አኳያ ይህን የቢዝነስ ምንጭ የሚያዳክሙ ተግዳሮቶች

በሀገራችን ብሎም በአለም አቀፍ በተሰራጨው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክኒያት ወደ ከተማችን የፈስ የነበረዉ

የቱሪዝም ፍሰት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ምንም አይነት ስራ ሳንሰራ በችግር ተወጥረን እስካሁን ድረሰ
መቆየታችን፣ይባስ በሎም ይህኛውን ችግር ሳንወጣ ክልላችን በዋናነት የሰሜን ወሎ ዞንና የላሊይበላ ከተማ

አስተዳደርን ከሀምሌ 2013 እስክ ታህሳስ 2015 ዓ.ም ድረስ በጦርነት በመቆየቱ ለተጨማሪ ችግር ያጋለጠን

በመሆኑ በአሁኑ ስዓት እንደ ላሊበላ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የሆነ ንግድ እንቅስቃሴ መዳከም ገጥሞናል፡፡

ቢሆንም ግን እነዚህ ተደራራቢ ችግሮች ቢኖሩም የራሴን ጥረት በመጨመር እስካሁን ድርስ ክፍያየን በዉሌ

መሰረት እየከፍልኩ ቆይቻለሁ፡፡

ስለሆነም በአሁኑ ስዓት ካለዉ የገባያ እንቅስቃሴ መዳከም አንፃርና በየሶስት ወሩ የምመልሰዉ የገንዘብ መጠን

721,657.25 ብር በመሆኑ እና ይህንም ካለዉ ወቅታዊ ተጨባጭ የስራ እንቅስቃሴ አንፃር በየሶስት ወሩ

ለመመለስ በእጅጉ ተቸግሪያለሁ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የጠየኩትን የስራ ማስኬጃ ብድር በመስጠት

ወደ ስራ እንደገባ ተገቢዉን ትብብር ባደረገልኝ ልክ አሁንም ከዚህ ካጋጠመኝ የመክፈል ችግር እንድወጣ

በመጀመሪያዉ ዙር ለተፈቀደልኝ የስራ ማስኬጃ ብድር ከነበረዉ 3 አመት ተጨማሪ 2 አመት እንዲሰጠኝ

እንዲሁም በሁለተኛዉ ዙር ለተፈቀደልኝ የስራ ማስኬጃ ብድር ከነበረዉ 3 አመት ላይ ተጨማሪ 3 አመት

ተጨምሮኝ በ ስድስት አመት እንዲያልቅ ቢደረግልኝ ክፍያየን ያለምንም ማቆራረጥ የምክፈል መሆኑን

እያሳወኩ ባንኩ ያቀረብኩትን የተጨማሪ የብድር መክፈያ ጊዜ አይቶ የተለመደ ትብብራችሁን እንድታደርጉልኝ

በማለት በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር

ወ/ዮሐንስ አስፋዉ ዘለቀ

You might also like