You are on page 1of 1

MT BUILDING CONSTRUCTION Plc.

ኤም.ቲ የህንፃ ኮንስራትራክሽን ሥራ ተቋራጭ ኃ/የተ/የግ/ማ

ቁጥር: M T / _ _ _ / 2 0 1 6
Ref. No.:

ቀን:_ _ _ / 0 4 / 2 0 1 6
Date:

በአ/ቃ/ክ/ከተማ

ለወረዳ 13 ዋና ስራ አስፈጻሚ

አዲስ አበባ

ጉዳዩ: ለሠራንው ስራ ክፍያ በአስቸኳይ እንዲፈጸምልን ስለመጠየቅ

ድርጅታችን፡ ኤም.ቲየህ/ኮን/ስ/ተ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአ/ቃ/ክ/ከ፣ በወረዳ 13፣ ቱሉ ዲምቱ ማህበር ቤት፣ ቁጥር-2፣ ብሎክ-1
የዝናብ ውሃ ተፋሰስ የዲች እና የከልቨርት ስራ መሰረታችን እና ከስድስት ወር በፊት ጨርሰን ማስረከባችን ይታወቃል። ሆኖም
እስካሁን ድረስ ክፍያ ሊፈፀምልን አልቻለም። እኛም ለብዙ ጊዜ የወረዳውን ህ /ተ/በ/ፈ/ማ/ጽ/ቤት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ በደብዳቤ
እንዲሁም በአካል ቀርበን ብንጠይቅም ተገቢውን ምላሽ ልናገኝ አልቻልንም። ታዲያ እኛም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የብሎኩ
ኮሚቴዎች ጋር በአካል ተገናኝተን ክፍያ ስለሚፈፀምበት ሁኔታ ተወያይተናል፤ እንዲሁም ኮሚቴው ያልተሰበሰበ ሀብት አለኝ ብሎ
ባቀረበው ማስረጃ መሠረት በቀጥታ ተሳታፊ ሆነን ገንዘቡን ያሰባሰብን ቢሆንም ከቀረው ክፍያ አንፃር የተሰበሰበው ገንዘብ በጣም
ትንሽ መሆኑን ተመልክተናል፤ ይህንንም ለወረዳውም ሆነ ለኮሚቴው አባላት አቅርበን አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጥ እና ክፍያችን
እንዲፈፀምልን ብንጠይቅም፣ ምክንያት እየደረደሩ ጊዜ መግዛት እና ማጉላላት ነው የተያዘው። እኛም የችግራችንን መጠን
በአካልም ሆነ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ሁሉ ብናሳውቅም እየተሰጠን ያለውምላሽ ግን ችግራችንን የሚያባብስ ሆኖ
አግኝተንዋል። ስለዚህም በአንድ ሳምንንት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ አርብ ታህሣሥ 26/2016 ዓ.ም ድረስ ክፍው የማይፈፀምልን
ከሆነ፣ ለስራው የተጠቀምንባቸውን ማቴርያሎች፡ ማለትም ሰሌክት፣ ብሎኬት፣ የማንሆል ከቨር እና የኮንክሪት ትቦ ከቦታው የምናነሳ
መሆኑን እናሳውቃለን። ምላሻችሁንም በፅሁፍ እንድታሳውቁን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

ከሠላምታ ጋር!

ብርሃኑ ገ/ሚካኤል
ዋ/ሥ አስኪያጅ

ግልባጭ

 በአ/ቃ/ክ/ከ/ ዋና ስራ አስፈጻሚ

 በአ/ቃ/ክ/ከ/ህ/ተ/በ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት

 በአ/ቃ/ክ/ከ/ ፓርቲ ጽ/ቤት

 በአ/ቃ/ክ/ከ/ ወረዳ 13 ህ/ተ/በ/ፍ/ማ/ጽ/ቤት


 ለኢትዮ ኤክሰለንስ ት/ቤት ባለንብረቶች

Mobil: +251966558408 ETHIOPIA


ADDIS ABABA

You might also like