You are on page 1of 5

ቀን 25/10/2011 ዓ.


ስዓት 2፡00
ቦታ ዋብር ት/ቤት
ተሰብሳቢ አባላት
1 ኛ. ታደገ መንግስቴ--------------------ሰብሳቢ

3 ኛ. ወ/ሪት ትነበብ ጥጋቡ--------------------ሂሳብ ኦፊሰር

4 ኛ. ወ/ሪት መልካም ተመስገን----------------ገ/ያዥ

5 ኛ. አቶ አለሙ ወለንካው ር/መ/ር ሆነን በስብሰባው አለንበት፡፡

የስብሰባው ዋና አጀንዳ፡- በት/ቤታችን ውስጥ የኤሌክትሪክ መብራት ትርንስፎርመር ክፍያ


የሚያገለግል ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጭ እንዲሆን ለመወያየት እና ለመወሰን ነው፡፡
በትምህርት ቤታችን ውስጥ የኤሌክትሪክ መብራት ትራንስፎርመር ማስገባት አስፈላጊ ስለሆነና ይህን
ትራንስፎርመር ለት/ቤቱ ማስገባት እንዳለብን በት/ቤቱ ወመህ ኮሚቴ ስለታመነበት እና አስፈላጊ ሆኖ
ስለተገኘ ለዚህ ክፍያ የሚሆን ገንዘብ 322,000 (ሦስት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ ብር) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
መውጣቱ አስፈላጊ እንደሆነ በኮሚቴዎች ታምኖበታል፡፡

 ስለሆነም ለዚህ የኤሌክትሪክ መብራት ትራንስፎርመር ማስገቢያ የሚሆን ገንዘብ ከኢትዮጵያ


ንግድ ባንክ ካለው የት/ቤቱ አካውንት መውጣቱ አስፈላጊ ስለሆነ የገንዘብ መጠኑ ከኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ መዉጣት እንዳለበት 322,000 (ሦስት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ ብር) የሁሉም ሰው
የስምምነት ሃሳብ ነው፡፡

የኮሚቴው ውሳኔ
በትምህርት ቤታችን ውስጥ የኤሌክትሪክ መብራት ትራንስፎርመር ማስገባት አስፈላጊ ስለሆነና ይህን
ትራንስፎርመር ማስገባቱ በት/ቤቱ ወመህ ኮሚቴ ስለታመነበት ለዚህ ማሰሪያ ለክፍያ የሚሆን ገንዘብ
ጠቅላላ 322,000 (ሦስት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ ብር) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጭ እንዲሆን ልዩነት
በሌለው ድምፅ ወስነናል፡፡
1.

2.

3.

4.

5.

ቁጥር ዋብ- 232/14-02


ቀን 25/10/20011 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢቡኝ ቅርንጫፍ

ድጎ-ፅዮን

ጉዳዩ፡- ገንዘብ ወጭ ሆኖ እንዲሰጠን ስለመጠየቅ

ከላይ በጉዳዩ ለመግለፅ እንደተሞከረው በት/ቤታችን ውስጥ የኤሌክትሪክ መብራት ትራንስፎርመር ማስገባት
አስፈላጊ ስለሆነና እና ይህም በከሚቴ ስለተወሰነ በት/ቤታችን ገ/ያዥ በሆኑት ወ/ሪት መልካም ተመስገን እና
በት/ቤታችን ር/መ/ር በሆነት በአቶ አለሙ ወለንካው ገላው ስም ለዚህ ማሰሪያ ለክፍያ የሚሆን ገንዘብ ጠቅላላ
322,000 (ሦስት መቶ ሃያ ሁለት ሽህ ብር) ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጭ እንዲሆን በከሚቴ ስለተወሰነ ከላይ
የተጠቀሰው ገንዘብ ወጭ ሆኖ እንዲሰጠን በአክብሮት እየጠየቅን የኮሚቴውን ውሳኔ 1 ገጽ አባሪ አድርገን
የላክን መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

“ከሰላምታ ጋር”

ግልባጭ//

 ለዋብር አጠ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የቀትስቦ ኮሚቴ


 ለት/ቤቱ ወመህ
ዋብር

ቀን 25/10/2011 ዓ.ም
ስዓት 2፡00
ቦታ ዋብር ት/ቤት
ተሰብሳቢ አባላት
1 ኛ. ታደገ መንግስቴ--------------------ሰብሳቢ

3 ኛ. ወ/ሪት ትነበብ ጥጋቡ--------------------ሂሳብ ኦፊሰር

4 ኛ. ወ/ሪት መልካም ተመስገን----------------ገ/ያዥ

5 ኛ. አቶ አለሙ ወለንካው ር/መ/ር ሆነን በስብሰባው አለንበት፡፡

የስብሰባው ዋና አጀንዳ፡- በት/ቤታችን ውስጥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገንዘብ አንቀሳቃሽ ኮሚቴ
ለመቀየር ለመወያየት እና ለመወሰን ነው፡፡
በትምህርት ቤታችን ውስጥ በኢትዮጵ ንግድ ባንክ በት/ቤቱ ስም ተከፍቶ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ገንዘብ
በርዕሰ መምህርነት ተመድበው አብረው በኮሚቴነት ሲያንቀሳቅሱ የነበሩት ግለሰብ ማለትም አቶ መብት
ጫኔ ብርሃኔ ት/ቤቱን በዝውውር ምክንያት ለቀው የሄዱ ስለሆነ በምትካቸው አሁን የት/ቤቱ ርዕሰ
መምህር ሆነው የተመደቡት ግለሰብ ማለትም አቶ አለሙ ወለንካው ገላው ስለሆኑ ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ
የት/ቤቱ የገንዘብ እንቅስቃሴ በዚህ ግለሰብ ተተኪነት የሚንቀሳቀስ መሆኑን በሰፊው የተወያየን ሲሆን
በውይይታችን መሰረት የሚከተለውን ውሳኔ ወስነናል፡፡
የኮሚቴው ውሳኔ
በትምህርት ቤታችን ውስጥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀመጠውን የት/ቤቱን ገንዘብ በርዕሰ መምህርነት
ተመድበው ሲያንቀሳቅሱ የነበሩት ግለሰብ ማለትም አቶ መብት ጫኔ ብርሃኔ በዝውውር ምክንያት
ት/ቤቱን የለቀቁ ስለሆነም በምትካቸው አሁን ርዕሰ መምህር ሆነው የተመደቡት ግለሰብ ማለትም አቶ
አለሙ ወለንካው ገላው የሚያንቀሳቅሱት መሆኑን ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስነናል፡፡
1.

2.

3.

4.

5.

ቁጥር ዋብ-233/14-02

ቀን 25/10/2011 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢቡኝ ቅርንጫፍ

ድጎ-ፅዮን

ጉዳዩ፡- ኮሚቴ የቀየርን መሆኑን ስለማሳወቅ


ከላይ በጉዳዩ ለመግለፅ እንደተሞከረው በትምህርት ቤታችን ውስጥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተቀመጠውን
የት/ቤቱን ገንዘብ በርዕሰ መምህርነት ተመድበው ሲያንቀሳቅሱ የነበሩት ግለሰብ ማለትም አቶ መብት ጫኔ
ብርሃኔ በዝውውር ምክንያት ት/ቤቱን የለቀቁ ስለሆነም በምትካቸው አሁን ርዕሰ መምህር ሆነው የተመደቡት
ግለሰብ ማለትም አቶ አለሙ ወለንካው ገላው የሚያንቀሳቅሱት መሆኑን እያሳወቅን የኮሚቴውን ውሳኔ 1 ገጽ
አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

“ከሰላምታ ጋር”

ግልባጭ//

 ለዋብር አጠ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የቀትስቦ ኮሚቴ


 ለት/ቤቱ ወመህ
ዋብር

You might also like