Professional Documents
Culture Documents
ለሉቄ መረደጃ ዕድር (3)
ለሉቄ መረደጃ ዕድር (3)
የሉቄ አካባቢ ነዋሪዎች መረዳጃ ዕድር አመታዊ ሪፖርት የተከበራችሁ የዕድሩ አባላት
የአሁኑ ሥራ አመራር ኮሚቴ ሥራውን ከተረከበ ከየካቲት 2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 2011 ዓ.ም ድረስ
ያከናወናቸው ሥራዎችን ከዚህ ቀጥለን እናቀርባለን፡፡
የተከናወኑ ሥራዎች
1. የዕድሩ ሕግና ደንብ ከተረቀቀና ሥራ ላይ መዋል ከጀመረ ቆይቷል፡፡ በመሆኑም አጠቃላይ ግመገማ
ለማድረግ አንድ ኮሚቴ ተቋቁሞ እንዲጠና ቢደረግና የሚሻሻለው እንዲሻሻል የሚለመጠውም
እንዲለወጥ ተደርጎ ወቅቱን የሚመጥን ተደርጎ ቢዘጋጅ
2. የቀደመው የሥራ አመራር ኮሚቴ በአንዳንድ ሕጎችና ዳንቦች ላይ ማሻሻያ በማድረግ ሥራ ላይ
አውሎአል እኛም ይህንኑ ስንተግብር ቆይተናል ግን አሁን ለጠቅላላው ጉባኤ ቀርቦ መፅደቅ
ስለሚኖርበት ከዚህ ቀጥሎ አቆርበንዋል፡፡
ረ/ ዕንግዳ ደራሽ /ሠራተኛ ሞቶ አስክሬን ከቤት ሲወጥ ብር 1,000 እንዲሁም የዕድሩ የዕድሩ አባል መሆን
ለሚፈልግ አዲስ ገቢ ብር 10,000 ናቸው፡፡
ልማትን በተመለከተ
ብዙ የሚሰራ ሥራ እንዳለ የታወቀ ቢሆንም እንኳ አቅም በፈቀደ መጠን የሚከተሉትን ሥራዎች መስራት
አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
1. በወንዙ በኩል ለሚገኘው ቤት መሰረቱ በውሃ እየተሸረሸረ ስለሆነ ጥገና ያስፈልገዋል እንዲሁም
በዚያው በኩል ላለው የብሎኬት ግድግዳ በውጭ በኩል የግርፍ ሥራ ይሰራለት፡፡
2. በፊት ለፊት በኩል ያለው የቆርቆሮ አጥር እየፈረሰ ስለሆነ ከስር ያለውን የድንጋይ ግን በቢም አስሮ
በብሎኬት ቢገነባ በቋሚነት አካልግሎት ይሰጣል
3. ለግቢው በር ስፊ የብረት መዝጊያ ከተሸካሚ ብረቶች ጋር ተሰርቶ/ ተገዝቶ ይገጠምለት፡፡ በማለት
ሃሳብ ቀርቧል፡፡