You are on page 1of 1

ሁንያለዉ ካሴ ጠቅላላ ተቋራጭ

አድራሻ ጎንደር

ቀን 12/01/2015 ዓ/ም

ቁጥር__________________

ለቃብትያ ሁመራ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት ጽ/ቤት

ሁመራ

ጉዳዩ ፡- መልስ መስጠትን ይመለከታል

በመጀመሪያ ላደረጋችሁልን መልካም ትብብራችሁ እና ለመጪዉም ለምታደርጉልን ትብብራችሁ ላቅ ያለ ምስጋና


እያቀረብን ከምስጋናችን በመቀጠል በክረምት ምከንያት የተቋረጠዉን ስራ ለመጀመር ለተሰጠን ዴብዳቤ በቀን
10/01/2015 ዓ/ም ደብዳቤ ቁጥር ቃ/ሁ/ወ/15/ እንደተቋራጭ ደስተኛ መሆናችንን እየገለጽን በኛ በኩል ያለዉን ነባራዊ
የሆነና ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ በዴብዳቤዉ ላይ እንደተገለፀዉ የስራ ጀምር ገደበ ቀኖች እንዲትረዱልን ልናሳዉቅ
እንወዳለን፡፡ በአጠቃላይ በስራ ሁኔታና ባህሪ ቀደም ብለን በያዝነዉ ዉል መሰረት የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ልዩነቶች ብታዩም
የመንገዱ መሰራትና በአስቸኳይ ማለቅ ለማህበረሰቡ ወሳኝ ሚና ስላለዉ ተቋራጫችን ያለ ምንም ቅድሜ ሁኔታ
ለመስራትና ለማስረከብ ጽኑ ፍላጎታችን ነዉ፡፡ እንደ ቅድመ ችግር ለመግለጽ የምንፈልገዉ ወይም ባለፈዉ የስራ ህደቶች
ያጓተቱ ምክንያቶችና አሁን ስራዉን ለማሳለጥ ከእናንተ የምንፈልገዉ ድጋፎች እንደሚከተሉት ናቸዉ፡፡

1. ወቅቱ ክረምት በመሆኑና ደጋማ ቦታ ስለሆነ ለመስራት አስቸጋሪ በመሆኑ


2. መጀመሪያ መሀንዲሶቹ የተመረጠዉ ኳሬ ማቴሪያሎች ስላለቀ ሁለተኛዉን ለመምረጥ ስለተቸገርን ጊዜ
ስለወሰደብን
3. ክፍያ የፋይናንስ ህግን ያልተከተለ እየሆነ ያስቸገረ ስለሆነብን በተጨማሪ ካለፈዉ የስራ ጊዜያችን ለግዳጅ 25
ቀን የባከነ መሆኑ
4. በአጠቃላይ በዞኑ ዉስጥ እና ወረዳ የሚገኙ ማሽነሪዎች ባለዉ ገበያ ኪራያቸዉን እንከፍላለን ስራ እንዲሳለጥ
ትብር እንዲታደርጉልን እየጠየቅን ስራዉ የጋራችን እና የህዝባችን ተጠቃሚነት እሰካረጋገጠ ድረስ የተሰጠንን
ዴብዳቤ በአወንታዊ ተቀብለናል፡፡

ከላይ የገለፅናቸዉ ሁኔታዎች ግንዛቤ ዉስጥ ገብተዉ አሁን በተሰጠን የስራ ጀምሩ ጊዜ ላይ ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ
ማሽኖችን ይሁን መኪኖችን ማግኘት እንደልብ ስለሆነ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠን በትህትና እንጠይቃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር!

ሁንያለዉ ካሴ

ጠቅላላ ተቋራጭ

ስራአስኪያጅ

You might also like