You are on page 1of 1

ለተከበራችሁ የህብር መረዳጃ ዕድር አባላት በሙሉ

በፀደቀው የእድራችን መተዳደሪያ ደንብ መሰረት የእድሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ ወደ ቀጣይ
ስራዎቻችን ለመግባት የሚያስችለንን የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ በአስቸኳይ መጀመር እንዳለብን ስምምነት ላይ
ተደርሷል፡፡

በዚሁም መሰረት፤

1. ከያዝነው ግንቦት ወር 2014 ዓ/ም ጀምሮ ወርሃዊው የእድር ክፍያ ብር 200.00


2. የመስራች አባልነት መዋጮ ብር 6000.00 (ስድስት ሺህ) በመተዳደሪያችን መሰረት ከያዝነው ከግንቦት
ወር 2014 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር 2015 ዓ/ም ድረስ ባሉት ስድስት ወራት ውስጥ ተከፍሎ
እንዲያልቅ፡፡ (አቅሙ ያለው አባል ክፍያውን በአንድ ጊዜም ይሁን በሁለት ጊዜ እንደሚያመቸው
መክፈል እንዲችል) በሚል ተወስኗል፡፡

በመሆኑ አባላትም ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ከዚህ በታች በተገለጸው የዕድራችን የባንክ አድራሻ ገቢ
እንድታደርጉልን እየጠየቅን

ለህብር መረዳጃ ዕድር

ሕብረት ባንክ

ሰሚት ሳፋሪ

የሂሳብ ቁጥር 4730412092810019

ገቢ ያደረጋችሁበትን መረጃ በመያዝ የስራ አመራር ኮሚቴው የጀመረውን እድሩን የማስመዝገብና የደረሰኝ
ህትመት ፈቃድ ሲጨርስ በሚያወጣው ማስታወቂያ መሰረት ገቢ ያደረጋችሁበትን የባንክ ሰነድ በመያዝ ደረሰኝና
የአባልነት ደብተር የምንሰጥ መሆኑን እየገለጽን አባላት ያለባችሁን መዋጮ በተባለው ጊዜ ውስጥ
እንድታጠናቅቁ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

ከዚህ በፊት ለእድር አባልነት በተለያየ ጊዜ በወረቀት ላይ ስማችሁን ያስመዘገባችሁን አባላት ነገር ግን በዚህኛው
ፎርም ላይ ያልፈረማችሁ በሙሉ ፎርሙ በግቢው ጽ/ቤት የሚገኝ በመሆኑ በዚህኛው ፎርም ላይ
እንድትፈርሙልን ስንል በማክበር እየጠየቅን ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

ከማክበር ሰላምታ ጋር

እድሩ

You might also like